Download as docx, pdf, or txt
Download as docx, pdf, or txt
You are on page 1of 5

የስራ ላይ ደህንነት እና ጤንነትን ለማጎልበት ይረዳ ዘንድ የወጣ መመሪያ

መግቢያ

ፊቤላ ተመስርቶ ወደ ስራ ከገባ ገና ሦሥተኛ አመቱን ይዟል። ፋብሪካው የተመሰረተበት አካባቢ


ኢንዱስትሪ ያልተስፋፋበት በመሆኑ በፋብሪካ ውስጥ ተቀጥረው በመስራት ላይ የሚገኙት ሰራተኞች
አብዛኛዎቹ የፋብሪካ የስራ ልምድ የሌላቸው ከመሆናቸውም በላይ በግልም ተቋምም ሆነ በመንግስት
መ/ቤት ተቀጥረው የቢሮ አሰራር ልምድ የሌላቸው ናቸው።

በዚህ ምክንያት

 የስራ ሰዓት ማክበር የሚገባ መሆኑን በአግባቡ አለመገንዘብ


 ሙሉ ስምንት ሰዓት በስራ ማሳለፍና የሚለካ ውጤት ያለው ስራ ሰርቶ መገኘት ግድ መሆኑን
አለመረዳት
 ከሰራተኛና ከስራ መሪዎች ጋር መኖር የሚገባ መልካም ግንኙኘነት የላላ መሆን
 በስራ ላይ እሰካሉ ድረስ የራስ፣ የፋብሪካውና የአካባቢ ደኅንነት አስፈላጊ መሆንን አለመገንዘብ
መብትን ብቻ እንጂ ግዴታዎቹን ለመፈጸም ዝግጁ አለመሆን
 የድርጅቱ ኅልውና የሰራተኛውም በስራ ላይ የመገኘት ዋስታና ነው ብሎ አለመገንዘብ፣ ወዘተ
በስፋት እየታዩ ነው።

ለዚህ እንደ ዋነኛ ምክንያት የሚወሰደው ደግሞ የሰራተኞች የግንዛቤ ችግር ፤ የድጋፍና የክትትል/ቁጥጥር/

ማነስ እና አስተማሪ የሆነ እርምጃ ያለመውሰድ ናቸው

እነዚህን ችግሮች ደረጃ በደረጃ ለማስወገድ ከሰራተኛ አስተዳደር መመሪያ በተጨማሪ ይህ የኢንዱስትሪ
ባህል ማጎልበቻ መመሪያ እንዲወጣ ተደርጓል።

በዚህ መሰረት የሠራተኞች ግንዛቤ እንዲሻሻል፣ ድጋፍና ክትትል እንዲጠነከር እና ጠንከር ያለ አስተማሪ

እርምጃ እንዲወሰድ ለማስቻል የሴፍቲ ቲሙ ጤናማ ያልሆኑ ተግባራትን በመለየት በማኔጅመንቱ


ተገምግሞና ዳብሮ ተግባራዊ ይሆን ዘንድ ቀርቧል።

1. የመመሪያው አላማ
ከላይ የተመለከቱትን ችግሮች በማስወገድ በኢንዱስትሪው ውስጥ የሰራተኞችን የስራ ባህል
ማሻሻል ነው፡፡
2. ተፈጻሚነት፡ በኢንዱስትሪው ውስጥ በስራ ወቅት ከታች የተዘረዘሩትን ተገቢ ያልሆኑ ተግባራት
በሚፈጽም ማነኛውም ሰራተኛ፤ ክፍል ሀላፊዎች፤ ስራ አስኪያጆች እና ስራ አስፈጻዎች ላይ
ተፈጻሚ ይሆናል
3. አስፈላጊነት

በኢንዱስትሪው ውስጥ ተገቢ ያልሆኑ ተግባራትን እና እንቅስቃሴዎችን በመለየት፤በማሳወቅና እና


በመቆጣጠር አደጋን እና በንክኪ የሚመጣን ችግር ከመቆጣርም በተጨማሪ በሰራተኞች ዘንድ ደምብ
በማክበር ጤናማ እንቅስቃሴ እና የተሻለ የስራ ባህል እንዲዳብር ይረዳ ዘንድ ይህን አጭር ደምብ ማዘጋጀት
አስፈላጊ ሁኗል፡፡

4. ዝርዝር ጤናማ ያልሆኑ ተግባራትና የሚወሰዱ እርምጃወች

ተ.ቁ ጤናማ ያልሆኑ ድርጊቶች ሲተላለፉ የሚወሰድ እርምጃ/ቅጣት

1 የደህንነት መጠበቂያ መሣሪያዎችን ሳይጠቀሙ ከስራ ውጭ ይሆናል ያልሠራበት የ 1 ቀን ቀሪ ሆኖ


መስራት ከደሞዙ ይቀጣል

2 የተበላሹ መሆናቸው የታወቁና የተለዩ መሣሪያዎችን ከስራ ውጭ ይሆናል ያልሠራበት የ 1 ቀን ቀሪ ሆኖ

ለስራ መጠቀም ከደሞዙ ይቀጣል

3 በኢንዱስትሪ ውስጥ ተገቢ ያልሆነ ጩኸትና ፉጨት ከስራ ውጭ ይሆናል ያልሠራበት የ 1 ቀን ቀሪ ሆኖ

ማሰማት፤መታገል/ መጨፈር/ያለ ምክንያት መሮጥና ከደሞዙ ይቀጣል

መሯሯጥ
4 ለስራ ከተፈቀደላቸው ሰራተኞች ውጭ ወደ የመጀመሪያ የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ ይሰጠዋልማህደሩ

አልተፈቀደ/ክልክል/ ቦታ መሄድ (ቦይለር፤ ጀኔሬተር፤ ጋር ይያያዛል

ታንከር)
6 የእግረኛ መንገድ አለመጠቀም 50 ብር በደረሰኝ ይከፍላል

7 በሚሰሩበት ጊዜ ስልክ በማዉራቱ ምክንያት የማሽን ከስራ ውጭ ይሆናል እንዳልሰራ ተቆጥሮ ቀሪ ሆኖ

ወይም የምርት ብልሽት ወይም የሚባክን ጊዜ ለፈጠር የአንድ ቀን ደሞዝ ይቀጣል

ከቻለ
8 ኢንዱስትሪው ቅጥር ግቢ ውስጥ ከተፈቀደው 200 ብር በደረሰኝ ይከፍላል

የፍጥነት ወሰን በላይ ማሽከርከር


9 በእግረኛ መንገድ አና ዜብራ ላይ መኪና ማቆም 100 ብር በደረሰኝ ይከፍላል

10 ፎርክሊፍት ላይ ሰው ጭኖ ማሽከርከር 100 ብር በደረሰኝ ይከፍላል

11 ለስራው አስፈላጊ የሆኑ እንደ ጓንት፤ የጸጉር መሸፈኛ፤ ከስራ ውጭ ይሆናል ያልሠራበት የ 1 ቀን ቀሪ ሆኖ

ማስክ፤ሳይጠቀሙ መስራት ከደሞዙ ይቀጣል

12 ከመመገቢያ አዳራሽ ውጭ መመገብና መጠጣት የመጀመሪያ የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ ይሰጠዋል ማህደሩ


(ከውሃ ውጪ) ጋርይያያዛል

13 የአትክልት ቅቤ፤የዘይት ሙሊት፤ፕላስቲክ ፋብሪካ እና ከስራ ውጭ ይሆናል ያልሠራበት የ 1 ቀን ቀሪ ሆኖ

ሰሊጥ ማቀነባበሪያ እና ላቦራቶሪ ሰራተኞች ደምብ ከደሞዙ ይቀጣል

ልብስ ለብሶ ሽንት ቤት መገኘት


14 የደምብ ልብስ ሳይለብሱ ስራ ላይ መገኘት ከስራ ውጭ ይሆናል ያልሠራበት 1 ቀን ቀሪ ሆኖ
ከደሞዙ ይቀጣል

15 በኢንዱስትሪው ውስጥ ልብስ፤ ጫማና ካልስ ማጠብ የመጀመሪያ የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ ይሰጠዋል ማህደሩ
ጋርይያያዛል

16 በስራ ቦታ መተኛት የመጀመሪያ የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ ይሰጠዋል ማህደሩ


ጋርይያያዛል

17 ባልተፈቀደ ቦታ ሲጋራ ማጨስ የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ ይሰጠዋል ማህደሩ ጋር ይያያዛል

18 ያለፍቃድ ከስራ ቦታ ውጭ መገኘት የመጀመሪያ የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ ይሰጠዋል


ማህደሩጋር ይያያዛል

19 በኢንዱስትሪው ውስጥ የሌላ ድርጅት የደምብ ልብስ ከስራ ውጭ ይሆናል እንዳልሰራ ተቆጥሮ ቀሪ ሆኖ
ለብሶ መገኘት የአንድ ቀን ደሞዝ ይቀጣል

20 በማሽን ላይ፤ምርት ትራንስፖርት በሚያደርግ ማሽን የመጀመሪያ የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ ይሰጠዋል


ላይ፤ በሞተር ላይ፤በጀሪካን ላይ፤ በጠረጰዛ ላይ ማህደሩጋር ይያያዛል
መቀመጥ ወይም መቆም
21 ጋቢ፤ ፎጣ ወይም ነጠላ ለብሶ መሰራት ከስራ ውጭ ይሆናል እንዳልሰራ ተቆጥሮ ቀሪ ሆኖ
የአንድ ቀን ደሞዝ ይቀጣል

22 ከመጸዳጃ ቤት ውጭ መጸዳዳት ሁለተኛ ደረጃ የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ ይሰጠዋል


ማህደሩጋር ይያያዛል
23 ቆሻሻ/ ወረቀት፤ጓንት፤ያገለገለ ማስክ፤ወዘተ ከቆሻሻ ከስራ ውጭ ይሆናል እንዳልሰራ ተቆጥሮ ቀሪ ሆኖ የአንድ
ማስቀመጫ ውጭ መጣል ቀን ደሞዝ ይቀጣል

5. አፈፃፅም
1. ይህ ደምብ ከጸደቀ በኋላ ለሁሉም ሰራተኞች ግንዛቤ ይፈጠራል፡፡ ይህን ለማድረግ ሲፍቲ ቲሙ
ከክፍሉ ሀላፊዎች ጋር በመሆን በየፋብሪካው በመገኘት ግንዛቤ ይፈጥራሉ
2. ደምቡ ለሁሉም ሰራተኞች ተደራሽ በሚሆን መልኩ በየስራ ክፍሉ ይለጠፋል
3. የስራ ዘርፍ ሀላፊዎች ፤የሙያ ደህንነት እና ሴፍ ቲሙ ተገቢውን ክትትል ያደርጋል
4. የተቀመጠውን ተገቢ ያልሆኑ ተግባራትን ተላልፈው ሲገኙ
4.1 የክፍል ሀላፊው/ስራ አስኪያጁ/ በኩል ሴፍቲ ቲም ሰብሳቢ እንዲያውቀው ይደረግና
ሴፍቲ ቲሙ ሰብሳቢው በኩል ተረጋግጦ ለሰው ሀይል ያሳውቃል፡
4.2 ወይም ሴፍቲ ቲሙ በክትትል ወቅት ካረጋገጠ የሴፍቲ ቲም ሰብሳቢ በቀጥታ ድርጊቱ
መፈጸሙን በቀጥታ ለሰው ሀይል ያሳውቃል፡፡
4.3 ሰው ሀይል የማስጠንቀቂያ ደብዳቤ ለሰራተኛው ይሰጠዋል ወይም የገንዘብ ቅጣት
ከሆነ ለፋይናንስ ቅጣቱ ተግባራዊ እንዲሆን በደብዳቤ ያሣውቃል፤ በዚህ መሰረት
ፋይናንስ ከደምወዝ ይቆርጣል
5. አሽከርካሪዎች ፍጥነት ወሰን በመተላለፍ በፍጥነት ማሽከርከራቸውን የትራፊክ ፖሊስ
ሲያረጋግጥ ተሸከርካሪው እንዲቆም በማድረግ የሹፌሩን ስም ለገንዘብ ሰብሳቢ መዝግቦ
ያስተላልፍና ሹፊሩ ገንዘብ ከፍሎ ሲመጣ ወደ ስራው እንዲሰማራ ያደርጋል
6. በኢንዱስትሪው ውስጥ በስራ ስዓት በየትኛውም ቦታ ቢጫ አረንጓዴ የማይለብሱ የማኔጅመንት
አባላት ሲገኙ ሲፍቲ ቲም ሰብሳቢው ለገንዘብ ያዝ ያሳውቅና 200 ብር እንዲከፍል ይደረጋል
7. ጤናማ ተግባራትን በመረጃ አስደግፈው ለሴፍቲ ቲሙ በማሳወቅ በተሻለ ሪፖርት ለሚደርጉ
ወይም ለሚጋልጡ ሰራተኞች ወይም ሀላፊዎች በአመቱ መጨረሻ ማበረታቻ ይሰጣቸዋል
8. አንድ ሰራተኛ በሚሰራበት ክፍል በስራ ወቅት መጠቀም ያለበትን ቁስ ተጠቅሞ ባለመስራቱ
ከተረጋገጠ ሱፐርቫይዘሩ እና ፈረቃ መሪው የስራ ዘርፍን ሰራተኛ ባለመቆጣጠሩና ኃላፊነቱን
ባለመወጣቱ የአንድ ቀን ደምወዝ እንዲቀጣ ስሙ ለገንዘብ ያዥ ይተላለፋል፡፡ ሆኖም ከላይ
የተጠቀሱትን ነገሮች የማይጠቀም ሰራተኛ ካለ እና ምክንያታዊ እና አሳማኝ ከሆነ ሊያሰራው
ይችላል ለሴፍ ቲሙም ማስረዳት ይኖርበታል
9. አንድ ሰራተኛ ተመሳሳይ ጥፋት ቢያጠፋ፡
9.1 ቅጣቱ የገንዘብ ከሆና እና ለሁለተኛ ጊዜ ካጠፋ ላጠፋው ጥፋት የተቀመጠው ቅጣት
ሁለት እጥፍ ይከፍላል፤ለሶስተኛ ጊዜ ከደገመ ከመጀመሪያ የጹሁፍ ማስጠንቀቂያ
ጀምሮ በአስተዳደር መመሪያው መሰረት ተፈጻሚ ይሆናል፡፡
9.2 ቅጣቱ የመጀመሪያ የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ ከሆነ ቀጥሎ ያሉት ቅጣቶች በአስተዳደር
መመሪያው መሰረት ተፈጻሚ ይሆናል
10. በቅጣት የሚሰበሰበው ገንዘብ ለሰራተኛ ማህበሩ ገቢ የሚሆን ይሆናል
11. አንድ ሰራተኛ ደምቡን መተላለፍ ሲረጋገጥ ለሪፖርት በተዘጋጀው ቅጽ እንዲፈርም ይደረጋል፡፡
ሆኖም በቸልተኝነት፤ በእቢተኝነት ወይም በማናለብኝነት አልፈርምም ካል ተቆጣጣሪው ለጥበቃ
ሪፖርት በማድረግ እንዲወጣ ይደረጋል፤ ቅጣቱ በገንዘብ ከሆነ እጥፍ ይሆናል፤ የመጀመሪያ
ማስጠንቀቂያ ከሆነ ሁለተኛ ደረጃ ማስጠንቀቂያ ይሰጠዋል፤ ሁለተኛ ደረጃ ማስጠንቀቂያ ከሆነ
ከሶስተኛ ደረጃ ማስጠንቀቂያ እስከ መባረር ተፈጻሚ ይሆናል፡፡
12. በወር መጨረሻ በሴፍቲ ክፍል ሀላፊ በኩል ለማኔጅምንት እንዲቀርብ በማድረግ አጠቃላይ
አፈጻጸሙ እንዲገመገም ይደረጋል ።

You might also like