Download as doc, pdf, or txt
Download as doc, pdf, or txt
You are on page 1of 5

የካህሊል ጂብራን መሳጭ ንግግሮች

📖📖📖
📜 በህይወቴ መናገር ያቃተኝ አንድ ጊዜ ብቻ ነው ። ይኸውም አንድ ሰው "አንተ
ማነህ?" ብሎ የጠየቀኝ ጊዜ ።

📜 ጭንቅላቱ የሰው ፣ ሰውነቱ የአንበሳ የሆነው የግብፅ ሐውልት (ስፊንከስ) አንድ
ጊዜ ብቻ ተናግሯል ። እንዲህም አለ ፦ " ደቃቅ አሸዋ በረሀ ነው ፣ በረሀም ደቃቅ
አሸዋ ነው ። አሁን ሁላችንም እንደገና ዝም እንበል ። "
፨ ስፊንከስ የተናገረውን ሰምቻለሁ ፣ ግን አልገባኝም

📜 እግዚአብሔር እኔን እንደጠጠር ወደዚህ አስገራሚ ሀይቅ ሲወረውረኝ የረጋውን
የላይኛውን ክፍሉን በበርካታ የክብ ሞገዶች አደፈረስኩት ። ነገር ግን በጥልቁ ቦታ
ስደርስ ያለምንም እንቅስቃሴ ተቀመጥኩ ።

📜 ዳግም የምወለደው ነፍሴ እና አካሌ እርስ በእርስ ሲፋቀሩ እና ሲጋቡ ነው ።

📜 ትዝታ(ተዘክሮ) የመገናኘት ያህል ነው ። መርሳት ደግሞ የነፃነት ያህል ነው ።

📜 እኛ ሰዓት የምንቆጥረው በፀሐይ እንቅስቃሴ(አቅጣጫ) ነው ። እነሱ ሰዓት
የሚቆጥሩት ኪ ሳቸው ውስጥ በሚያስቀምጡት አነስተኛ መሳሪያ(ማሽን) ነው ።
፨ እስኪ ንግሩኝ፣ እንዴት ብለን ነው በአንድ ቦታ በተመሳሳይ ሰዓት ልንገናኝ
የምንችለው?

📜 ፨ ቤቴ " ያለፈው ህይወትህ እዚህ ሥላለ ትተህኝ አትሂድ " አለችኝ ።
፨ ጎዳናውም " እኔ የወደፊት ሕይወትህ ስለሆንኩ ተከተለኝ " አለኝ ።
፨ እኔ ደግሞ ለቤቴ እና ለጎዳናው " እኔ ያለፈም ሆነ የወደፊት ህይወት የለኝም ።
እዚህ ከቆየሁኝ በመቆየቴ ውስጥ መሄዴ አለ ፣ ከሄድኩኝም በመሄዴ ውስጥ እዚህ
መቆየቴ አለ ። ሁሉንም ነገሮች መለወጥ የሚችሉት ፍቅር እና ሞት ብቻ ናቸው "
አልኳቸው

📜 ነብሴን ለሰባት ጊዜያት ጠላኋት


፨ በመጀመርያ ከፍታ ላይ እደርሳለሁ ብላ ቅን የሆነች ጊዜ ፣
፨ ሁለተኛ አካለ ስንኩል ፊት ያነከሰች ጊዜ ፣
፨ ሶስተኛ ከከባድ እና ከቀላል እንድትመርጥ ስትጠየቅ ቀላልን የመረጠች ጊዜ ፣
፨ አራተኛ ስህተት ፈፅማ ሌሎችም ስህተት ይፈፅማሉ ብላ ራሷን ያፅናናች ጊዜ ፣
፨ አምስተኛ ለድክመት እጇን የሰጠች እና ትዕግስቷን ለጥንካሬ የሰጠች ጊዜ ፣
፨ ስድስተኛ የፊትን(የመልክን) አስቀያሚነት ስትጠየፍ እና ከራሷ ጭምብሎች
አንዱ መሆኑን ያላወቀች ጊዜ ፣
፨ ሰባተኛ የምስጋና መዝሙር የዘመረች እና እንደመልካም ነገር የወሰደችው ጊዜ ፣
📖📖📖
ምንጭ የጥበብ መንገድ ፪ ገጽ 109-113 📖
ደራሲ ✍ ካህሊል ጂብራን
ትርጉም ✍ ደመላሽ ጥላሁን
📖 ማንበብ የተሻለ ሰው ያደርጋል 📖
✍ ንባብ ለሕይወት
@books4all32

📜 የካህሊል ጂብራንን ንግግርና ፍልስፍናዎች በርከት አርጋችሁ ብታስነብቡን


ብላችሁን ነበር በጥያቄአችሁ መሰረት እነሆ ተጋበዙልን
📜📜📖📜📜
📖 " እምነት ማለት ልብ ውስጥ የሚገኝ ውሀ ያለበት የበረሀ ቦታ ሆኖ በፍጹም ጉዞ
ሊደረስበት የማይቻል ነው ። "
💫💫💫
📖 " ስለ መንገዶች ከጥንቸሎች በላይ ኤሊዎች ያውቃሉ ። "
💫💫💫
📖 " በልባችን ያሉትን ሚስጥራት ማየት የሚችሉት ፣ በልባቸው ሚስጥሮችን
የያዙ ብቻ ናቸው ። "
💫💫💫
📖 " ደግነት መስጠት ከምትችለው በላይ መስጠት ሲሆን ፣ ኩራት ደግሞ
ከምትፈልገው ያነሰ መውሰድ ነው ። "
💫💫💫
📖 " ግነት ፣ ስሜቱን ያጣ እውነት ነው ። "
💫💫💫
📖 " አሳፋሪ ሽንፈት ከሚመጻደቁበት ስኬት የተሻለ ነው ። "
💫💫💫
📖 " በጥልቀት የማሰብ ችሎታ የሌለው ሳይንቲስት ፣ የደነዘ ቢላዋ እና የተበላሸ
ሚዛን እንዳለው ስጋ ነጋዴ ነው ። "
💫💫💫
📖 " ለራበው ሰው ብታዜምለት የሚሰማህ በሆዱ ነው ። "
💫💫💫
📖 " ህልምና ምኞት በሌላቸው ሰዎች መሃል ታላቅ ከመሆን ይልቅ ፣ ህልም እና
ምኞት ባላቸው ሰዎች መሃል ደካማ መሆንን እመርጣለሁ ። "
💫💫💫
📖 " ሁላችንም እስረኞች ብንሆንም ልዩነታችን አንዳንዶቻችን የታሰርንባቸው
ክፍሎች ፣ መስኮቶች ሲኖራቸው የአንዳንዶቻችን ግን የላቸውም ። "
💫💫💫

📖 " የሌላ ሰውን ድክመቶች ከማወቅ የበለጠ ምንም አይነት ድክመት የለም ። "
💫💫💫
📖 " ፈጣን የምትሆነው የሚያሯሩጥህ ሲኖር ብቻ ነው ። "
💫💫💫
📖 " ዓይኖቹ ውስጥ ያለውን ጥላቻ በከንፈሮቹ ፈገግታ ለመሸፈን የሚሞክር ሰው
የማይረባ ነው ። "
💫💫💫
📖 " <<አልተገነዘብኩህም>> ማለትህ ለኔ ከሚገባኝ በላይ ሙገሳ ሲሆን ለአንተ
ደግሞ የማይገባህ ስድብ ነው ። "
💫💫💫
📖 " ህይወት ልክ እንደ ሰልፍ ናት ። ቀስ እያለ ለሚራመደው ሰልፉ ስለሚፈጥንበት
ከሰልፉ ይወጣል ፤ ለፈጣኑ ደግሞ በጣም ስለሚዘገይበት እሱም ከሰልፉ ይወጣል ።
"🗒🗒🗒

ምንጭ የጥበብ መንገድ ፪ 📖


✍ ካህሊል ጂብራን

ከፍልስፍና ዓለም እንዲሁም ንባብ ለሕይወት ቴሌግራም ቻናሎች ዝግጅት ክፍል


@filsfina
@books4all32

You might also like