Download as docx, pdf, or txt
Download as docx, pdf, or txt
You are on page 1of 31

መታየት -

በከተሞች
ውስጥ
ከተማን
መቤዠት
-
ወጣቶች በፓስተር ዩሪ ፌርራ

ከተሞቻ
ቸውን
ሲለውጡ
የካቲት 30-መጋቢት 7 / 2016

ስለ ጸሐፊው

1
ፓስተር ዩሪ ፌሬራ የሰባተኛ ቀን አድቬንቲስት ቤተክርስቲያን ፓስተር ናቸው፡፡ ከአንድሪውስ ዩኒቨርሲቲ በአመራር፣
ስነመለኮት እና መጽሐፍ ቅዱሳዊ ስብከት ማስተርስ ዲግሪ ያላቸው ሲሆን በተጨማሪም በስብከት ዶክትሬት ዲግሪ
አላቸው፡፡ ፓስተርና ወንጌላዊ ሆነው የሰሩ ሲሆን በአሁኑ ጊዜ በሰባተኛ ቀን አድቬንቲስት ቤተክርስቲያን በታላቁ
ኒውዮርክ ኮንፍራንስ ውስጥ የሂስፓኒክ ሚኒስትሪ ሃላፊ በመሆን እያገለገሉ ይገኛሉ፡፡

“ያለፍርሃት መኖር”፣ “የ 2021 የሚሲዮንያውያን መጽሐፍ ለሰሜን አሜሪካ” እና “ቃሉን ስበክ” የመሳሰሉ መጻሕፍት
ደራሲ ናቸው፡፡ ከባለቤታቸው ከማሪኤል ፌራሪ ጋር ተጋብተው በደስታ የሚኖሩ ሲሆን ሁለት ለጆችን ማለትመ
እረኔስቶ እና ኤልዛቤትነ አፍረተዋል፡

የትምህርቱ አሰጣጥ

በመጀመሪያ አጠር አድርጎ የመጋቢነት የማነቃቂያ ትምህርቱን አንድ ሰው ያቀርባል፡፡ ከዚያም ወጣቶች ጥሩ መጋቢዎች
ሆነው እንዲገኙ አንድ ሰው ለወጣቶች ይጸልያል፡፡ ከዚያም የጸሎት ሳምንቱን ስብከት የሚያቀርበው ሰው ይቀጥላል፡፡
ስለዚህ 2 ሰዎች እንዲዘጋጁ ይደረጋል ማለት ነው፡፡

2
1 ኛ ቀን
የመጋቢነት ትምህርት

በልግስና ማምለክ
በዌንያ ፑንዱ
ትርጉም በፓስተር ተስፋዬ ሽብሩ
የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅስ
“እጅህን በምትጥልበት ሁሉ አምላክህ እግዚአብሔር ስለዚህ በሥራህ ሁሉ ይባርክሃልና ፈጽመህ ስጠው፥ በሰጠኸውም ጊዜ
በልብህ አትጸጸት።”
የዛሬው ትምህርት በዘዳግም 15፡3-11 ላይ ያተኩራል፡፡ የዘዳግም መጽሐፍን በአንድ ቃል ለመግለጽ ብትፈልጉ “ቃልኪዳን” ብላችሁ
ልትገልጹት ትችላላችሁ፡፡ ይህ መጽሐፍ እግዚአብሔርን እና እስራኤልን ያጣመረውን ቃልኪዳን ወይም ተስፋ ያሳያል፡፡ በዚህ የዘዳግም
መጽሀፍ ክፍል የመጀመሪያ ሶስት ቁጥሮች ስለሰባቱ አመት መጨረሻ የእዳ ምህረት ይናገራል፡፡
በዚህ ጊዜ በእስራኤል ውስጥ፣ በሰባተኛው ዓመት፣ የእዳ ምህረት፣ የጌታ መፈታት እንደሚኖር በመረዳት ገንዘብን መበደር ምንጊዜም
ያለ ነው፡፡ ይህ ማንም ሥር የሰደደ ድህነትን ውስጥ እንዳይገባ እግዚአብሔር ያቋቋመው የኢኮኖሚ ሥርዓት መንገድ ነበር። አንዳንዶች
በመጥፎ ጊዜ ውስጥ ሊያልፉ ይችላሉ, ነገር ግን እንደገና ለማገገም እድሉ ይኖራቸዋል፡፡
አሁን ዘዳ 15፡3-11 ን በድጋሚ አንብቡ፡፡
እነዚህን ጥቅሶች ሳነብ ሶስት ዋና ሐሳቦችን አገኛለሁ፡፡
የመጀመሪያዎቹ ሁለቱ - መታዘዝና በረከት ቁ. 4
በራስ ወዳድነት፣ በእጦትና በድህነት በተሞላ አለም ውስጥ “በህዝቡ መካከል ድሃ አይኖርም” የሚለው የእግዚአብሔር ተስፋ ጸንቶ
ይኖራል፡፡
የርስታችን ምድር አካላዊ ብቻ አይደለም; መንፈሳዊ እና የጋራ ነው። እንደ ወጣት ጎልማሶች፣ የእግዚአብሔር በረከቶች ለመካፈል
የታሰቡ መሆናቸውን መገንዘብ አለብን። የእርሱን ልግስና ስንቀበል፣ የፍቅሩ መጠቀሚያዎች እንሆናለን፣ ይህም ሌሎችን ለመድረስ የእሱ
ብዙ በረከት በእኛ በኩል እንደሚፈስ በማረጋገጥ ነው። እግዚአብሔርም እንደሚባርከን ቃል ገብቷል።
ሶስተኛው , የልባችሁ አቋም ቁ.7
ጥቅሱ በምንም አይነት ሁኔታዎች ውስጥ ቢሆኑም በዙሪያችን ላሉ ርህራሄን እና ፍቅርን በማሳየት ለጋሽ ልብን እንድናዳብር
ይገዳደረናል፡፡ በራስ ብቃት ላይ በሚያተኩር አለም ውስጥ ጌታ እንደሌሎችን እንዳናስብና የተለየን እንድንሆን ይጠራናል፡፡ እንደወጣት
ጎልማሳዎች የሌሎችን የህይወት ትግል የሚያይና ምላሽ የሚሰጥ የርህራሄን መንፈስ የማዳበር እድል አለን፡፡ ከጭካኔ ይልቅ የርህራሄ
ምላሽ ይኑረን፡፡
የመጨረሻው - እንዴት እንደምንሰጥ ቁጥር 9-11
እነዚህ ጥቅሶች ከስጦታችን ጀርባ ያለው አነሳሽ ምንነት ላይ ያተኩራሉ፡፡ እግዚአብሔር በፈቃደኝነት ደስ እያለው የሚሰጠውን ሰው
ይደሰትበታል፡፡ ደስተኛ ከሆነ ልብ ስንሰጥ ተግባራችን የእግዚአብሄርን ባህሪይ ያንጸባርቃል፡፡ በተጨማሪም ካለን መስጠት እንዳለብን
ያሳስበናል፡፡ ትዕዛዝ ስለሆነ ሳናደርገው ከቀረን ሃጢአት ነው፡፡ ጊያችንን ይሁን ሐብታችንን ወይም መክሊታችንን ስንሰጥ በደስታ
እንድንሰጥ ያደፋፍረናል፡፡ ይህ አመለካከት ተቀባዩን መጥቀም ብቻ ሳይሆን ባጠቃላይ ወደ ህይወቱ በረከትን ማምጣት ነው፡፡
ጸሎት፤
ጌታ ሆይ፣ እኛን ስለባረክበት በረከት ሁሉ እናመሰግንሃለን፡፡ ያለስስት መስጠት እንድንችል እርርን፡፡ ያለንን ንብረት ብቻ ሳይሆን
ጊዜያችንን፣ መክሊታችንን እና ርህራሄያችንንም እንድንሰጥ እርዳን፡፡ በደስታ፣ ኪሳራን ሳንቆጥር፣ ልባችንን እንደመምታይ በማሰብ
እንድንሰጥ እርዳን፡፡ አንተ ልንገምት በማንችለው መንገድ እንደምትባርከን ተስፋ ሰጥተኸናል፡፡ላይህ አለም ሁሌም ፍላጎት አለው፡፡
እነዚህን ፍላጎቶች ለማሟላት እጆቻችን የተከፈቱ እንዲሆኑ ጠርተኸናል፡፡ አቤቱ የፍቅርህ መሳሪያዎች በመሆን በረከትህን በዙሪያችን
ላሉ እንድናጋራ እርዳን፡፡
አሜን፡፡

3
1 ኛ ቀን ስብከት
እግዚአብሔር ከተማችሁን ይወዳልን?

በፓስተር ዩሪ ፌሬራ

ትርጉም - በፓስተር ተስፋዬ ሽብሩ

እግዚአብሔር ከተማህን ይወዳል ne? ዛሬ ይህንን ጥያቄ ለመመለስ እንሞክራለን:: ያንን ከማድረጋችን በፊት
ግን ስለ ከተሞች አንዳንድ አስደሳች ነገሮችን እንመልከት። አንዳንድ ጥናቶች እንደሚያመለክቱት ከተማ
ከፍተኛ ህዝብ የሚኖርበት እና በከፍተኛ ደረጃ የተደራጀ ቦታ ነው፡፡ የገንዘብ፣ የባህል፣ የፖለቲካ እና
ሌሎችም ነገር ሁሉ ማዕከል ሆኖ የሚያገለግል ነው፡፡ ከተሞች ሰማይ ጠቀስ ፎቆች፣ መንገዶች፣ የምድር
ውስጥ ባቡር እና በሌሎች በርካታ አገልግሎቶች ተሞልተዋል። በተጨማሪም፣ በከተሞች ውስጥ ከሁሉም
ቦታዎች እና ባህሎች የመጡ ሰዎች አሉ፤ እናም እንደ ፈጠራ፣ ትምህርት እና ስራ ያሉ ብዙ አስደሳች
ነገሮች የሚገኙባቸው ቦታዎች ናቸው።
እስኪ ደግሞ በአለማችን ስላሉት ታላላቅ ከተሞች እናውራ፡፡

• በጃፓን የምትገኘው የቶኪዮ ከተማ በምድራችን ላይ ካሉት ከፍተና የህዝብ ብዛት ካላቸው ከተሞች አንዷ
ናት። በጣም በቴክኖሎጂ የበለጸገች እና እጅግ በጣም ጥሩ ዘመናዊ ባህል ያላት በመሆኑ ታዋቂ ናት።
• በዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ የምትገኘው ኒውዮርክ ከተማ ብዙ ገንዘብ፣ ንግድ እና ሌሎችም ያሉባት
የሁሉም ነገር ማዕከል ናት።
• የእንግሊዝ ዋና ከተማ የሆነችው ለንደን አሁንም በአለም ኢኮኖሚ እና ፖለቲካ ውስጥ ጉልህ ሚና
የምትጫወት ታሪካዊ ከተማ ነች።
• ቤጂንግ የቻይና ዋና ከተማ ስትሆን ለፖለቲካ እና ለባህል ትልቅ ቦታ ያላት ነች።
• በደቡብ አሜሪካ ሁሉም ነገር የሚከሰትባት የብራዚልዋ ከተማ ሳኦፓሎ ስትሆን፣ ብዙ የንግድ ልውውጥ
እና አስደሳች ባህል ያለባት ከተማ ናት፡፡
• የህንዷ ከተማ ሙምባይ፣ እያደገች ያለች ከተማ ስትሆን ለንግድ ስራ በጣም አስፈላጊ ከተማ ነች።
• በናይጄሪያ የሚገኘው ሌጎስ የአፍሪካ የባህል፣ የፋይናንስ እና የመዝናኛ መዲና ተብሎ የተገለፀ ትልቅ
የአፍሪካ የፋይናንስ ማዕከል ነው።

አሁን ደግሞ በከተሞች ውስጥ የሚኖሩ ሰዎች ስሜታዊ ጉዳዮችስ ምን ይመስላሉ የሚለውን እናንሳ?
በከተማ ውስጥ መኖር ሁል ጊዜ በፊልሞች ላይ እንደሚታየው አይደለም። ሁሉም ነገር በፍጥነት
ስለሚንቀሳቀስ እና የትራፊክ ፍሰቱ ግራ የሚያጋባ በመሆኑ በከተማው ውስጥ ያሉ ሰዎች ጭንቀት
ሊሰማቸው ይችላል፡፡ በብዙ ሰዎች የተከበቡ ቢሆኑም፣ አንዳንዶች ከሌሎች ጋር ጥልቅ ግንኙነት
ስለሌላቸው የብቸኝነት ስሜት ሊሰማቸው ይችላል። ፉክክር እና የስኬት ጫና ከፍተኛ ሊሆን ስለሚችል
ጭንቀትም ችግር ሊሆን ይችላል። ህይወት ከባድ ስለሚሆን አንዳንድ ጊዜ የመንፈስ ጭንቀት በከተሞች
ውስጥ በጣም የተለመደ ሊሆን ይችላል፡፡
4
ሆኖም ግን ይህ የምስራች አለ፡፡ እግዚአብሔር ከተሞችን ይወዳል! እናም ያ ማለት በችግራቸው እና
በተጨነቀ ስሜታቸው ውስጥ የሚኖሩትን ሰዎች ይወዳል ማለት ነው። እግዚአብሔር ሰፊ ልብ አለው እናም
ሰዎችን በአስቸጋሪ ጊዜያት ውስጥ ሲያልፉ አይቶ ያስብላቸዋል። ታዲያ እግዚአብሔር ለከተሞች ያለውን
ፍቅር እንዴት ያሳያል? ፍቅሩን በተግባር የሚያሳዩ ሦስት ነገሮችን እንመልከት።

የስብከት ዋና ክፍል
1. እግዚአብሔር ወደ ከተሞች መልእክተኞችን ይልካል።
በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ከተማ የሚለው ቃል ለመጀመሪያ ጊዜ የተጠቀሰው ቃየል የገነባትና በልጁ ሄኖክ
የሰየመው ከተማ እንደሆነ ታውቃላችሁ (ዘፍ 4፡17፣ NIV)? ሄኖክ የከባድ ጉዳዮች ታሪክ ካለው ቤተሰብ
እንደመጣ ያሳውቃል። የርሱ ዝርያዎች ብዙ ሴቶችን እንደማግባት፣ ግድያ እና የመሳሰሉ አንዳንድ አስከፊ ነገሮች
የተከሰቱባቸውን ከተሞች መስርተዋል፡፡ ነገር ግን በሙዚቃ እና በኪነጥበብ ፈጠራዎችም የታወቁ ነበሩ።
ከውሃ ጥፋት በኋላም ቢሆን ነገሮች አልተሻሻሉም። የኖህ የልጅ ልጆች በተለይም የካም ልጆች አንዳንድ ክፉ
ከተሞችን መገንባት ጀመሩ (ዘፍጥረት 10፡6-12 አ.መ.ት)፣ መጨረሻው ደግሞ ታዋቂ ለመሆን በሚል ሃሳብ
የባቢሎንን ግንብ እየገነቡ ነበር (ዘፍጥረት 11፡4፣ NIV) .
በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ፣ በርካታ ከተሞች አሉ፣ ከእነዚህም ውስጥ በጣም ታዋቂዎቹ ባቢሎን፣
የከለዳውያን ዑር፣ ሰዶም፣ ገሞራ፣ ነነዌ እና ኢየሩሳሌም ናቸው። አብዛኛዎቹ እነዚህ ከተሞች የክፋት እና
የኃጢአት ማዕከል ነበሩ። ነገር ግን የሚገርመው ነገር ምንም አይነት ጥፋት/ችግር ቢኖርባቸውም
እግዚአብሔር ተስፋ አልቆረጠባቸውም፡፡ በመሆኑም መልእክተኞችን የርህራሄ መልእክት እና የመለወጥ
እድልን አስይዞ ልኮላቸዋል። ለዚህ ምሳሌ የሚሆነንን የዮናስን ታሪክ እናነባለን። (የዮናስን መጽሐፍ
አንብብ።)

እግዚአብሔር ዮናስን ማስጠንቀቂያ ለመስጠት ወደ ነነዌ ከተማ እንዲሄድ ነገረው። ነነዌ በክፋት የተሞላች
እጅግ ጨካኝ ስፍራ ነበረች (ናሆም 3፡1)። ጥንታዊ ታሪክ የዚህች የነነዌ ከተማ የከፉ ነገሥታት
ጠላቶቻቸውን ይዘው ቆዳቸውን ከገፈፉ በኋላ ያቃጥሏቸው እንደነበር ይናገራል፡፡ አስገራሚ እብደት ነበር!
ነገር ግን ሁሉም ዓመጸኛና ክፉ ቢሆኑም፣ እግዚአብሔር የመለወጥ እድል ሳይሰጣቸው ተስፋ ሊያሰጣቸው
አልፈለገም። ነቢዩ ዮናስን ላከላቸው። እና ምን እንደሆነ ታውቃላችሁ? የነነዌ ከተማ በንስሐ ምላሽ ሰጠች
(ዮናስ 3፡5-10፣ NIV)።
እግዚአብሔር ዛሬም ለውጦችን እና ንስሐን በከተሞች ማየት እንደሚፈልግ ታውቃላችሁ? ለዚህም ነው
መልክተኞችን የላከው! እግዚአብሔር ከመልእክተኛው በአንዱ በኩል የተናገረውን እናንብብ፡- “እኔ ሕያው
ነኝና፤ ኃጢአተኛው ከመንገዱ ተመልሶ በሕይወት ይኖር ዘነድ እንጂ ኃጢአተኛው ይሞት ዘንድ አልፈቅድም፤ ይላል
ጌታ እግዚአብሔር፣ የእስራኤል ቤት ሆይ ተመለሱ፥ ከክፉ መንገዳችሁ ተመለሱ። ስለ ምንስ ትሞታላችሁ?
በላቸው፡፡ ( ሕዝቅኤል 33:11)
ይህ የሆነው በጥንት ጊዜ ብቻ አይደለም! እግዚአብሔር ዛሬም በከተሞቻችን ለውጦችን ማየት ይፈልጋል።
“እኔ በከተሞቻችሁ ያሉ መልካም ነገሮች እንዳያመልጣችሁ አልፈልግም፤ ንስሃ እንድትገቡ እና ወደ
መልካም ነገር እንድትቀይሩ እፈልጋለሁ” እያለ ይመስላል።
5
ስለ ከተማችሁ አስቡ፡፡ በመልካም ነገሮች የተሞላ ሊሆን ይችላል ነገር ግን የራሱ ጉዳዮች፣ ችግሮች፣
ወንጀሎች ወዘተ ሊኖሩት ይችላል። ያም ቢሆን አሁንም እግዚአብሔር ፍቅርን እንዲያሳዩ የራሱን ሰዎች
ወደ ከተማችሁ እየላከ "ሄይ እኔ እዚህ ነኝ! ይህንን በጋራ ሆነን እንለወጥ"

ስለዚህ፣ እግዚአብሔር ስለ ከተማችን ያስባል ወይ ብለህ ብትጠይቁ፣ መልሱ አዎን፣ እሱ ያስባል! የሚል
ነው፡፡ እግዚአብሔር እያንዳንዷ ከተማ ሰዎች በሰላም፣ በብልጽግና እና በስምምነት የሚኖሩባት እንድትሆን
ይፈልጋል። ያንን ለማድረግ እንደ እናንተ ያሉ ሰዎችን ለመጠቀም ፈቃደኛ ነው። ስለዚህ ደስ እያላችሁ
በከተማችሁ ውስጥ የለውጡ አካል ሁኑ!
ወጣቶች፣ እግዚአብሔር በጣም አመጸኛ እና እብድ የሆኑትን ከተሞች እንኳን የመለወጥ ሥራ ላይ ነው።
ፍቅር በተግባር ማለት ያ ነው!

2. እግዚአብሔር ለከተሞች ርኅራኄን ያሳያል

እግዚአብሔር መልእክተኞችን መላክ ብቻ ሳይሆን በእነዚያ ከተሞች ውስጥ ለሚኖሩ ሰዎች በተለይም በአስቸጋሪ
ጊዜያት ውስጥ ለሚኖሩ ሰዎች ታላቅ ርኅራኄን ያሳያል። ይህንን ለመረዳት የማቴዎስ ወንጌል 9፡35-36 ተመልከቱ ።

"ኢየሱስም በምኩራቦቻቸው እያስተማረ፥ የመንግሥትንም ወንጌል እየሰበከ፥ በህዝብም ያለውን ደዌና ህመም ሁሉ
እየፈወሰ በከተማዎችና በመንደሮች ሁሉ ይዞር ነበር።"

ርህራሄ ማለት ምን ማለት ነው? ባጭሩ እራስህን በሌላ ሰው ጫማ ውስጥ ማስገባት እና ችግሮቻቸውን እና ህመሞችን
መረዳት ማለት ነው። አዎን፣ አምላክ በተለይ በአስቸጋሪ ጊዜያት በከተሞች ውስጥ ላሉ ሰዎች በጥልቅ ያስባል!

ይህንን አስቡት፡ ከተማችሁ ሁከት የተሞላበት ቦታ ሊሆን ይችላል፣ አንዳንድ ጊዜ ሁሉም ሰው ግራ መጋባት ውስጥ የገባ
ይመስላል። ሰዎች ብቸኝነት፣ ጭንቀት፣ ሕመም ወይም ሌሎች ጉዳዮችን እያስተናገዱ ሊሆን ይችላል። እግዚአብሔር
ግን አለ! ኢየሱስ ራሱ ሰዎችን እያስተማረ እና እየፈወሰ በከተሞች ውስጥ ተዘዋወረ። ሕዝቡን ባየ ጊዜ ልቡ ተነካ። እሱ
"ወገኖች, እኔ ለእናንተ እዚህ ነኝ, በዚህ ውስጥ ብቻችሁን አይደላችሁም" ለማለት የፈለገ ይመስላል፡፡

በሚቀጥለው ጊዜ በከተማችሁ ውስጥ በሚሆነው ነገር ሁሉ ስትታክቱ ሳለ፣ እግዚአብሔር እንደሚረዳችሁ


አስታውሱ። እሱ ለእናንተም ሆነ ለሌሎች ሰዎች ሁሉ ይራራል። ዓለም የቱንም ያህል የተመሰቃቀለ ቢሆንም፣
እግዚአብሔር እዚያ ተገኝቶ ሊንከባከበን ፈቃደኛ ነው። ንጹህ ፍቅር በተግባር ማለት ያ ነው!

3. እግዚአብሔር ከተሞችን ይለውጣል


እስካሁን፣ እግዚአብሔር ወደ ከተማዎች መልእክተኞችን እንዴት እንደሚልክ እና በዚያ ለሚኖሩ ሰዎች እንዴት
እንደሚራራላቸው ተነጋግረናል። ግን ያ ብቻ አይደለም! እግዚአብሔር ከተሞችን ቅልጥፍና በመስጠት ረገድም አዋቂ
ነው። የጠርሴሱ ሳውል ታሪክ ታስታውሳለህ?

6
አንድ ቀን፣ ሳውል ክርስቲያኖችን ለማሳደድ ተልእኮው ላይ ነበር እና ነገሩን ለማድረግ ወደ ደማስቆ አቀና። ቆይ ግን
አስደናቂው ክፍል ይህ ነው፡ ኢየሱስ ራሱ በመንገድ ላይ ተገለጠለት እና ህይወቱን ሙሉ በሙሉ ለውጦታል! ታሪኩ
በሐዋርያት ሥራ 9፡1-6 ላይ ነው። የክርስቲያኖች ቀንደኛ ጠላት የነበረው ሳውል በዘመኑ ከነበሩት ዋና ዋና ሐዋርያት
አንዱ ወደሆነው ጳውሎስ ተለወጠ።

እስቲ ይህንን አስቡ፤ የክርስቲያኖች አሳዳጅ የነበረው ሳውል በየቦታው አብያተ ክርስቲያናትን በመትከል ታላቅ የወንጌል
አስተማሪ የሆነ ሰው ነበር። እግዚአብሔር ሳውልን ወደ ሌላ ሰው ለወጠው።

ይህ ምን ያስተምረናል? አምላክ ግለሰቦችን ብቻ ሳይሆን ከተማዎችንም የመለወጥ ታላቅ ኃይል እንዳለው ይነግረናል።
ጸጋው በሥራ ላይ ሲሆን፣ ሁሉም ነገር ሊለወጥ ይችላል፡፡ ከተማችሁ ለውጥ ያስፈልገዋል ብላችሁ የምታስቡ ከሆነ፣
እግዚአብሔር ሰዎችን እና ነገሮችን የመለወጥ ባለቤት መሆኑን አስታውሱ። እሱ በተግባር ላይ ያለ አርቲስት ነው፡፡
ሁሉንም ነገር የተሻለ ያደርገዋል!

ማጠቃለያ

እግዚአብሔር ለከተሞች ልዩ ፍቅር አለው። በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ፣ ፍቅሩን በሚያስደንቅ ሁኔታ እንዴት
እንደሚያሳይ አይተናል፡ መልእክት ሲልክ፣ እጅግ በጣም አስተዋይ ነው፡፡ እንዲያውም እጅግ የከፉ ኃጢአተኛ
ከተሞችንም ይለውጣል። የእግዚአብሔር ወጣቶች እንደመሆናችን መጠን ከተሞቻችንን መውደድ እና በውስጣቸው
ያለውን የእግዚአብሔርን መንግሥት ማስፋፋት የእኛ ግዴታ ነው። ሁልጊዜም እግዚአብሔር በከተሞቻችን ውስጥ
በጣም ንቁ እንደሆነ አስታውሱ፣ ስለሆነም እኛ የፍቅሩ እና የርህራሄው መሳሪያዎች ልንሆን እንችላለን። የእግዚአብሄር
ፍቅር በከተሞቻችን እየፈሰሰ እንዲቀጥል እንፀልይ።

2 ኛ ቀን የመጋቢነት ትምህርት
የተለየ እይታ
7
በ: ማሪያ ማንደርሰን
ትርጉም በፓስተር እሱባለው ምህረት
የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅስ፡ ኤር፡ 29:11
“ለእናንተ የማስባትን አሳብ እኔ አውቃለሁ፤ ፍጻሜና ተስፋ እሰጣችሁ ዘንድ የሰላም አሳብ ነው እንጂ የክፉ ነገር አይደለም።”
እንደ www.wickipedia.org ዘገባ፣ እስልምና በዓለም ላይ በፍጥነት በማደግ ላይ ያለ ሀይማኖት ነው፣ እናም ከቁጥር አንጻር ኢ-
ሃይማኖታዊነት ወይም በአጠቃላይ አለማዊነት እየጨመረ የመጣ ይመስላል ። የአሜሪካ የሃይማኖት ዳሰሳ መንፈሳዊነት ከ 1990 እስከ
2001 ባለው ጊዜ ውስጥ በአማካይ የ 143 በመቶ እድገት ማሳየቱን ይናገራል።
ታዲያ ክርስቲያን ወጣቱ ምን እያደረገ ነው? ከእነዚህ እና ከሌሎች ቡድኖች ጋር ወንጌልን እንዴት እያየ ነው? በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ
ከሌሎች የእምነት ቡድኖች ጋር የተገናኙትን ሦስት ሁኔታዎችን እንመልከት።
ሆን ብሎ ፡
እግዚአብሔር አብርሃምን ጠራው።
በብሉይም ሆነ በአዲስ ኪዳን፣ እግዚአብሔር ሰዎችን እና ደቀመዝሙርቱን ሰዎችን እንዲደርሱ ሆን ብሎ ሲጠራ እናያለን። በዘፍጥረት
12፡1 እግዚአብሔር አብርሃምን (በወቅቱ አብራም ተብሎ የሚጠራው) ሲጠራው አገሩን፣ ቤተሰቡንና የወላጆቹን ቤት እንዲለቅ
ነገረው። የሚያውቀው ነገር ሁሉ መተው ነበረበት፤ ይህም ሃይማኖቱን ይጨምራል። በእውነትም እንዲህ ይላል፡— እርሱም።
የያዕቆብን ነገዶች እንድታስነሣ ከእስራኤልም የዳኑትን እንድትመስል ባሪያዬ ትሆን ዘንድ እጅግ ቀላል ነገር ነውና እስከ ምድር ዳር
ድረስ መድኃኒት ትሆን ዘንድ ለአሕዛብ ብርሃን አድርጌ ሰጥቼሃለሁ ይላል። (ኢሳ 49:6) ጣዖት አምላኪ የሆነው አብራም የአምላክ
ወዳጅ አብርሃም መሆን እንዴት ያለ ለውጥ ነው ኢያሱ 24:2 እና ኢሳ 41:8 ን አንብብ። አብርሃምም አብርሃም ባደረገው ነገር ላይ
የተመሠረተ አልነበረም፤ ይልቁንም እግዚአብሔር ከአብርሃም ጋር በገባው የዘላለም ቃል ኪዳን እና አብርሃም በመቀበል ላይ ባለው
እምነት ላይ የተመሠረተ ነው።
ኢየሱስ እና ሳምራዊቷ ሴት
በጕድጓዱ አጠገብ ከሳምራዊት ሴት ጋር በተገናኘ ወቅት ኢየሱስ ወደ ሴቲቱ ለመድረስና ምሥራቹን ለመስበክ ሆን ብሎ ሲጓዝ
እንመለከታለን። ደቀ መዛሙርቱ ምግብ ሊገዙ በሄዱ ጊዜ ኢየሱስ በአጋጣሚው ሴቲቱን አነጋገረ። ( ዮሐንስ 4:8 ) እሷም የሚቀጥለውን
ጥሩ ነገር ትፈልግ ነበር። በሌላ ሰው (ወይም ነገር) የማይገኝ የተሟላ ሕይወት ተመኘች። ኢየሱስ ጊዜ ወስዶ በእርጋታ በማናገር ከእርሷ
ጋር አሳለፈ። እኛም ሌሎችን ለመድረስ ሆን ብለን ማድረግ አለብን። የሱስ ይችን ሴት አላሳፈራትም፤ ይልቁንም ኢየሱስ
ኃጢአትዋን በእርጋታ ጠቁሟታል፣ ይህ ደግሞ ዓይኖቿ ስለ ማንነቱ እውነት እንዲገለጡ አድርጓቸዋል። ዮሐንስ 4:18-26 ን አንብብ።
ኃጢአቷ ኢየሱስን አላስደነገጠውም። ኃጢአታችን ኢየሱስን አያስደነግጠውም። ከኃጢአታችን መዳን የምንችለው በኢየሱስ ብቻ ነው።
እግዚአብሔር ፍቅሩን እና ይቅርታውን ለሁሉም አሕዛብ እና ለምድር ሰዎች ስለማድረስ ሁልጊዜ ያሳስበው ነበር። እና ኤርምያስ 29፡11
እንደሚለው፣ ለእናንተ የማስባትን አሳብ እኔ አውቃለሁ፤ ፍጻሜና ተስፋ እሰጣችሁ ዘንድ የሰላም አሳብ ነው እንጂ የክፉ ነገር
አይደለም። ሁላችንም ማለት ነው። ሁሉም ሰው!

ጸሎት፡ አምላኬ ሆይ፣ እኛን ሆን ብለህ ስለደረስኸን በጣም እናመሰግናለን። ሁላችንም ካንተ ጋር ለዘላለም እንድንኖር ስለ ወደድኸን
በጣም እናመሰግናለን። እባክህ ምንም አይነት ሁኔታ ቢፈጠር ሁሉንም ሰው ማዳን እንደምትችል አስታውሰን፡አስታውሰኝ፣
ኃጢአታችንን በራሳችን ማሸነፍ እንችልም ፣ አንተን እንፈልጋለን። እባክህ ዓይኖቼን ክፈትና ፍቅርህን ለሌሎች እንድካፍል
የምትፈልግበትን መንገዶች አሳየኝ፣ በተለይም አንተ አዳኝ መሆንህን ለማይቀበሉ እና እንደገና እንድንኖር ለእኛ መሞትህን ለማያምኑ።
በምናገረው እና በምኖረው ኑሮ ለማገኛቸው ሰዎች ሁሉ ቃልህን እንዳካፍል ደፋር እንድሆን እርዳኝ። አሜን።
2 ኛ ቀን ስብከት
ከተሞችን በመለወጥ፡ የኢየሱስን ምሳሌ መከተል
በ፡Pr. S. Yeury Ferreira
ትርጉም በፓስተር እሱባለው ምህረት
( ማቴዎስ 9:35፣ NIV )
መግቢያ
ዛሬ፣ በከተሞች ውስጥ ውጤታማ የሚስዮናዊነት ሥራ እንዴት ማከናወን እንደምንችል በመመርመር በኢየሱስ ተመስጦ መንፈሳዊ ጉዞ
እያደረግን ነው። ኢየሱስ በዘመኑ ካጋጠመው ነገር ጋር የሚመሳሰል ፈታኝ የሆነችውን ከተማ እናስብ። ወደዚህ አስደሳች ርዕስ
ከመግባታችን በፊት ግን አንድ አጭር ታሪክ ላካፍላችሁ።
ከጥቂት አመታት በፊት፣ በታላቅ ከተማ መሃል ዳዊት የሚባል ወጣት ይኖር ነበር። በከተማው የማያቋርጥ ግርግር እና ሁከት ውስጥ፣
ዳዊት በዙሪያው ባሉ ብዙ ሰዎች ህይወት ላይ ባየው የተስፋ ማጣት እና የዓላማ እጦት ተጨነቀ። ይሁን እንጂ አንድ ቀን ዳዊት
የሕይወቱን ጎዳና ለዘላለም የሚቀይር ነገር አጋጠመው። ኢየሱስ በከተሞች ስላከናወነው አገልግሎት ከሚናገረው አረጋዊ ሰው ኤልያስ
ጋር መንገድ ተገናኙ። አዛውንቱም መጽሐፍ ቅዱሳቸውን ወስደው የማቴዎስ ወንጌል 9፡35 አነበቡ።

8
" ኢየሱስም በምኩራቦቻቸው እያስተማረ የመንግሥትንም ወንጌል እየሰበከ በሕዝብም ያለውን ደዌና ሕማም ሁሉ እየፈወሰ
በከተማዎችና በመንደሮች ሁሉ ይዞር ነበር።"
ኤልያስ ይህ ጥቅስ ኢየሱስ ለከተሞች ጥቅም ሲል ያከናወናቸውን ሦስት ዋና ዋና ተግባራት ጎላ አድርጎ ሲገልጽ ዳዊት ትኩረት ሰጥቶ
ያዳምጥ ነበር።
ልማት
1. የመጀመሪያ ግሥ፡ አስተምር
በመጀመሪያው ወሳኝ ግስ እንጀምር፡ “ማስተማር”። ኢየሱስ ጥበቡን በከተሞች ውስጥ ለነበሩት ሰዎች በማካፈል ጊዜ አሳልፏል።
በማቴዎስ 9፡35 ላይ፡- “ኢየሱስም በምኩራቦቻቸው እያስተማረ በየመንደሩና በየሰፈሩ ዞረ” ይላል። ሆኖም፣ ትምህርቱ በቃላት ብቻ
የተገደበ አልነበረም። በሕይወቱ ውስጥ በኖረበት መንገድም ተንጸባርቋል። በህይወቱ የፍቅር፣ የርህራሄ፣ የፍትህ እና የእምነት
ትምህርቶችን አስተላልፏል።
አሁን፣ የዳዊትን ታሪክ እንቀጥል። ዳዊት ከኤልያስ ጋር ከተገናኘና የኢየሱስን ፈለግ ለመከተል ካስገደደው አዲስ የጋለ ፍቅር ስሜት
በኋላ አንድ ትልቅ ትርጉም ያለው ነገር ለማድረግ ተገደደ። በከተማው የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴ እና በሚታይ ጥፋት ከመወሰድ ይልቅ
እርምጃ ለመውሰድ ወሰነ። አንድ ቀን ከሰአት በኋላ፣ ዳዊት በከተማው መናፈሻ ውስጥ ሲዘዋወር፣ ስለ መንፈሳዊነት እና ስለ ሃይማኖት
የሚወያዩ ወጣቶችን አገኘ። በጣም ጓጉቶ ቀረበና ያዳምጥ ጀመር። እነዚህ ወጣቶች ስለ አምላክና ስለ መጽሐፍ ቅዱስ የበለጠ ለማወቅ
ጓጉተው ነበር። ዳዊት ሃይማኖታቸውን በጥልቅ ለመማር ያላቸው ልባዊ ፍላጎት አይቶ ተደንቆ ነበር።
ዳዊት ከእነዚህ ወጣቶች የመማር ፍላጎት በመነሳሳት አማካሪያቸው ለመሆን ፈቃደኛ ሆነ። የተማረውን በማካፈል የከተማውን ህይወት
ተግዳሮቶች ከመንፈሳዊ እይታ አንጻር እንዲያዩ ረድቷቸዋል። በተጨማሪም፣ መንፈሳዊ ርእሶችን በኦንላይን በማጋራት የራሱን
መንፈሳዊ ግንዛቤ ያበለፀጉ መጽሃፎችን እና ፖድካስቶችን እንዲያጠኑ ይመክራቸው ነበር።
ወጣት የከተማ ሚስዮናውያን፣ ኢየሱስ ካደረገው እና ከዳዊት ተሞክሮ ተነሳሱ። እርምጃ ለመውሰድ እና በከተማዎ ውስጥ ለውጥ
ለማምጣት ጊዜው አሁን ነው! አንዳንድ ጠቃሚ ምክሮች እነሆ፡-
• የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ቡድኖችን ማደራጀት፡- ጓደኞችህን ወይም የማታውቃቸውን ሰዎች ሰብስብ እና የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት
ቡድኖችን እንደ ካፌዎች ወይም መናፈሻ ቦታዎች ላይ አደራጅ። መጽሐፍ ቅዱስን ማንበብ ብቻ ሳይሆን የዕለት ተዕለት ሕይወት ምን
ማለት እንደሆነ መመርመር ።
• መካሪዎች ሁኑ፡ መንፈሳዊ መመሪያ ለሚያስፈልጋቸው ሌሎች ወጣቶች መካሪ ይሁኑ። የህይወት ውጣ ውረዶችን እንዲያስሱ፣
ልምዶቻችሁን እንዲያካፍሉ እና በእምነት አብረው እንዲያድጉ እርዷቸው።
• መርጃዎችን ያካፍሉ፡ በአንተ ላይ ተጽእኖ ያደረጉ እና ስለ እግዚአብሔር እና ስለ ድነት የሚናገሩትን መጽሃፎችን፣ ፖድካስቶችን እና
የኦላይን ቁሳቁሶችን ለወጣቶች ተገቢ እና አሳታፊ በሆነ መንገድ ያካፍሉ። የሚፈልጉትን ያስቡ እና በጋለ ስሜት ያካፍሉት።
አስታውስ ማስተማር መረጃን ማስተላለፍ ብቻ አይደለም; ለሌሎች አርአያ መሆን ነው! በዕለት ተዕለት ሕይወትዎ ውስጥ ፍቅርን፣
ርህራሄን እና እምነትን ያሳዩ፣ እና ብርሃንዎ በከተማ ውስጥ እንዴት እንደሚበራ ያያሉ። በእርስዎ ማህበረሰብ ውስጥ ምልክት ለማድረግ
ዝግጁ ነዎት? ጊዜው አሁን፤ ለወጣት አዋቂዎች ነው!
2. ሁለተኛ ግሥ፡ መስበክ
አሁን፣ ወደ ሁለተኛው ቁልፍ ግስ እንሂድ፡ “ስብከት”። ኢየሱስን ተመልከት; እሱ በእውነት በዚህ ላይ አዋቂ ነበር። ጥበቡን ማካፈል
ብቻ ሳይሆን በታሪክ ውስጥ እጅግ አስደሳች የሆነውን ለሁሉም ሰው በጉጉት ተናግሯል፡- የእግዚአብሔር መንግሥት እዚህ አለች፣
በተስፋ፣ በይቅርታ እና በዕርቅ!
በአንድ ወቅት በከተማ ውስጥ ጥፋተኝነት ተሰምቶት የሕይወትን ዓላማ ሲፈልግ የነበረውን ወዳጃችንን ዳዊትን ታስታውሳለህ? ዳዊት
ከኤልያስ ጋር ከተገናኘና የኢየሱስን ፈለግ ለመከተል ካደረገው አዲስ ፍቅር ውሳኔ በኋላ አንድ አስፈላጊ ነገር ለማድረግ ተገደደ።
አንድ ቀን፣ ዳዊት በትምህርት ቤቱ እያለ፣ “ስብከት” የሚለውን ግስ ተግባራዊ ለማድረግ ፍጹም እድል አገኘ። አምላክ የለም ብሎ
የሚያምነው መምህሩ ዳዊትን ለምን በእግዚአብሔር እንደሚያምን ጠየቀው። ዳዊት በአምላክ ላይ እምነት ስላሳደረባቸው ምክንያቶች
በክፍሉ ጓደኞቹ ፊት በድፍረትና በእርግጠኝነት ተናገረ። የፍጥረትን አስደናቂነት እና መጽሐፍ ቅዱስ በሕይወቱ ላይ ምን ለውጥ
እንዳመጣ አብራራ። ተማሪዎቹ ዳዊት የተናገራቸውን ቃላት ሁሉ በትኩረት ያዳምጡ ነበር፣ እና መምህሩ በእምነታቸው ጽናት
ተደንቀዋል!
ለአስር ደቂቃ ያህል ከተናገረ በኋላ፣ ዳዊት በረጅሙ ተነፈሰ እና አስደናቂውን የኢየሱስን ታሪክ አካፍለ።
በእርሱ ላይ ያለው እምነት የራሱን ሕይወት እንዴት እንደለወጠው። በእግዚአብሔር ላይ ስላለው ተስፋ እና ይቅርታ፣ እርቅ ሁሉንም
ነገር እንዴት እንደሚለውጥ ተናገረ።
በጀግንነት ግን በትህትና እና በፍቅርም አቀረበ። እምነቱን ለመጫን አልሞከረም ነገር ግን በእውነተኛ እና በአክብሮት እውነትን
አካፍሏል። የዳዊት እውነተኛ ፍቅር በቃላቱ ውስጥ በራ።
የዳዊት ስብከት ለሚያዳምጡት ወጣቶች ተስፋ አስገኝቷል። ልክ እንደ ኢየሱስ፣ ዳዊትም በድፍረት እና በፍቅር ምሥራቹን ሰበከ፣ እናም
በዚያ ቅጽበት፣ በከተማው ትምህርት ቤት ለውጥ አሳይተል።

9
ስለዚህ ወንድሞች እህቶች “መስበክ” ከመድረክ ላይ ሆኖ መናገር ብቻ ሳይሆን በዙሪያችን ካሉ ሰዎች ጋር የእግዚአብሔርን ፍቅር
ለመካፈል የዕለት ተዕለት እድሎችን መፈለግ ነው። የኢየሱስንና የዳዊትን ምሳሌ በመከተል ምሥራቹ በከተማችን እንዲበራ እናድርግ።
እርስዎም በዕለት ተዕለት ሕይወት ውስጥ ተስፋ እና ለውጥ ተሸካሚ ሊሆኑ ይችላሉ!
3. ሦስተኛው ግሥ፡ ፈውስ
በመንፈሳዊ ጉዟችን ላይ ሦስተኛው ወሳኝ ግስ “ፈውስ” ነው። ኢየሱስ ማስተማርና መስበክ ብቻ አልነበረም; የታመሙትን ፈውሷል
የተጎዱትን አጽናንቷል! በማቴዎስ ወንጌል 9፡35 ላይ "በሰዎች ላይ ያለውን ደዌና ህመም ፈውሷል" ይለናል። ነገር ግን ያስታውሱ፣
አካላዊ ህመሞችን ማዳን ብቻ አይደለም; እሱም መንፈሳዊ እና ስሜታዊ ቁስሎችን መፈወስን ያመለክታል፡፡ ይህ በከተማ ውስጥ ያለን
ተልእኮ አስፈላጊ አካል ነው።
የዳዊትን ተሞክሮ እናስታውስ ። ወጣቶቹን ካዳመጠ በኋላ የመፈወስን አስፈላጊነት ተረዳ አንድ ቀን፣ መጽሐፍ ቅዱስን በጥልቀት
ከመረመረ በኋላ፣ ዳዊት ለማስተማርና ለመስበክ ብቻ ሳይሆን የበለጠ እንዲያገለግልም እንደጠራው በልቡ ተሰማው።
ተጨባጭ መንገድ.
ዳዊት በከተማው ውስጥ ምግብና ልብስ የሚያስፈልጋቸው ብዙ ቤት የሌላቸው ሰዎች መኖራቸውን እና ብዙም እንግዳ የማይቀበሉ
አረጋውያን እንዳሉ ተመልክቷል። ከቤተክርስቲያኑ ፓስተር ጋር ለመነጋገር እና በአገልግሎት ቡድን ውስጥ ለመሳተፍ ያለውን ፍላጎት
ለመግለፅ ወሰነ። ፓስተሩ ቤት ለሌላቸው ምግብ የማቅረብ አገልግሎት ስላላቸው ስለ አንድ የቤተ ክርስቲያን አባላት ቡድን ነገረው።
ዳዊት ለአፍታም አላመነታም ወደዚህ ቡድን ተቀላቅሏል። በየሳምንቱ ቅዳሜ ከቤተክርስቲያን አገልግሎት በኋላ ከባልንጀሮቹ ጋር
በመሆን ወደ ሁለት መቶ የሚጠጉ ምግቦችን በማዘጋጀት በከተማው ጎዳናዎች ላይ ለማደል ይወጣ ነበር። ይህ ሥራ የዳዊትን ልብ
በደስታ ሞላው እና “ፈውስ” የሚለውን ግስ ከምንፈጽምባቸው መንገዶች አንዱን የተረዳው በዚህ ነው።
ፈውስ ማለት የታመሙትን ማከም ብቻ አይደለም; የተቸገሩትን መንከባከብ ማለት ነው። ምግብ፣ አልባሳትና ድጋፍ ማድረግ፣
በሆስፒታል ውስጥ የታመሙትን መጠየቅ፣ በከተማው ውስጥ ካሉ አረጋውያን ጋር በአረጋውያን መጦሪያ ቤት ማሳለፍ፣ ባልቴቶችን
መጠየቅ፣ ወላጅ አልባ ሕፃናትን ማሳደግ፣ ለተገለሉ ወገኖች የምትችለውን ማድረግ ነው።
ልክ እንደ ኢየሱስ፣ ዳዊት ፈውስ ከሥጋዊው በላይ እንደሆነ ተረድቶ ነበር። ልብን መንካት እና የተጎዱትን ሸክሞች ማቃለል ነው።
እናም፣ ዳዊት በከተማው ውስጥ ያለውን "ፈውስ" የሚለውን ግስ ለመፈጸም ኃይለኛ መንገድ አገኘ።
ስለዚህ፣ ወጣት የከተማ ሚስዮናውያን፣ የኢየሱስንና የዳዊትን ምሳሌ እንከተል። ችግረኞችን ለማገልገል እድሎችን እንፈልግ። በፍቅር
እና በርህራሄ በተሞላ ድርጊት በከተማው ውስጥ ለውጥ ማምጣት ይችላሉ!
ማጠቃለያ
በታሪካችን ውስጥ ያለው ወጣት ዳዊት በከተማው የነበረውን የኢየሱስን ምሳሌ ተከትሏል። ማስተማርን፣ መስበክን እና መፈወስን
ተማረ፣ እና የሚስዮናዊነት ስራው የብዙ ሰዎችን ህይወት ቀይሯል። ዛሬ፣ በከተሞች ውስጥ የምንኖር ወጣት ሚስዮናውያን፣ የለውጥ
ወኪሎች የመሆን ተመሳሳይ ዕድል አለን። የኢየሱስን ምሳሌ መከተል በጥበብ ማስተማርን፣ በፍቅር መስበክንና በርኅራኄ መፈወስን
እንደሚጨምር አስታውስ። ይህን በማድረግ፣ በከተሞቻችን የለውጥ መሳሪያ መሆን እንችላለን፣ ይህም በጣም ለሚፈልጉ ሰዎች ተስፋን
እና የእግዚአብሔርን ፍቅር ማምጣት እንችላለን። ይህ ተልዕኮ የእኛ ፍላጎት እና ቁርጠኝነት ይሁን። አሜን።

3 ኛ ቀን
አጭር የማነቃቂያ መልዕክት
በእዮኔ ኦማና
ትርጉም
10
በልዩነት አንድ በመሆን የትዉልድን ክፍተት ማጥበብ፤ በገሃዱ አለም በከተማችን የተለያዩ ማህበረሰብ ከልዩ ልዩ
ፍላጎቶች ጋር አብረን እንኖራለን። የመጣልን ጥሪ እንደ አገልጋይነታችን ባለንበት ከተማ ይህን በማስተዋል ተጽእኖ
ፈጣሪ እንድንሆን ነዉ።
1 ኛ ጢሞ 4 12 ይህን እዘዝና አስተምር/ይነበብ/
በእግ/ር ቃል ዉስጥ የሁለንትናዊ ልዩነትን ዉበት በማስተዋል የሱስ የተጠቀመበትን ዘዴ በመጠቀም ወደ ሌሎች
እንድንደርስ ይጋብዘናል።
1 በወጣትነት ሀይል ማገልገል፤ የቅርብ ጊዜ ጥናት እንደሚያሳየን ወጣቶች በከተማዎቻችን ከፍተኛ መነቃቃትንና
ለዉጥን እያመጡ ይገኛሉ። ለከተማዉም ህዝብ ግንባር ቀደምና ጠበቃ እስከመሆን ድረስ ለፍትህና ለእኩልነት ሲሞግቱ
ይስተዋላሉ። ጳዉሎስ ጢሞቴዎስን እንዳበረታታዉ ወጣቶቻችን ዛሬም ሊበረታቱ፣ ሊደፋፈሩና ምሳሌ ሊሆኑ
ይገባቸዋል።
2 ለጥበብና ልምድ ዋጋ በመስጠት ማገልገል፤ እንደነኒቆድሞስና ስምኦን ካሉ ጥሩ ልምድና መንፈሳዊ ተሞክሮ
በመውሰድ ለሌሎች ጥንቃቄ ማድረግ ይጠበቅብናል።
3 በትዉልድ ቅብብሎሽ የአንድነትን ሀይል መተግበር፤ የርስ በርስ ህብረት ፋይዳዉ ብዙ ሲሆን ለአእምሮ ሰላም፣ለአካል
ጤናና ለመንፈሳዊ አገልግሎታችንም ከፍተኛ ጠቀሜታ አለዉ። የርስ በርስ ቅንጅት የእግዚአብሔር መንግስትን ወንጌል
በጋራ ለማስፋፋት ትልቅ አቅም ይሆነናል። ሉቃስ 2 36_38
4 የየሱስን ዘዴ መከተል፤የሱስ በአገልግሎት ዘመኑ፤
ሀ ሁሉን አቃፊና ዘመን ተሻጋሪ አገልግሎት አገለገለ።
ለ አለም አቀፋዊ መልእክት አስተላለፈ።
ሐ የተምሳሌትነቱም ሀይል የፍቅር፣የማመዛዘንና ሰዉን በቅርበት የማስተዋል ስለሆነ አሸናፊ ሆነ። ስለዚህ
የዘመናችንን የትዉልድ ብዘሀነትን እንደ ተግዳሮት ሳይሆን እንደእድል በመጠቀምና በማድነቅ የየሱስን ፍቅር በማሳየት
በእምነት ጎዳና መጓዝ አለብን።
ጸሎት፤ በልዩ ልዩ ማህበረሰብ ዉስጥ ስንመላለስ የአንተን መርነት እንሻለንና በጊዜዉም ያለጊዜዉ በፍቅር፣ በእምነትና
በንጽህና ምሳሌዎች እንድንሆን እርዳን። ታላላቆቻችንን እንድናከብራቸዉና እንድናስተዉላቸዉ እርዳን። በአንድነት
ተሳስረን ያለ ልዩነት እንድናገለግልህ እርዳን። አሜን።
3 ኛ ቀን ስብከት ፤
ብቸኝነትን መጋፈጥ
በፓ/ር ኤስ ዮሪ ፌሪራ
ትርጉም በፓስተር ተስፋዬ ሽብሩ
ዮሐ 16 32 “እነሆ፥ እያንዳንዳችሁ ወደ ቤት የምትበታተኑበት እኔንም ለብቻዬ የምትተዉበት ሰዓት ይመጣል”
መግቢያ፤ ብቸኝነት በአለም አቀፍ ደረጃ እያደገ መጥቷል። በግል፣ በቤተሰብና ማህበራዊ ችግሮች ብዙዎች ብቸኝነትን
ይጋፈጣሉ። በተለይ ከቅርብ አስርት አመታት ወዲህ ብቸኝነት እጅግ እየጨመረ መጥቷል፡፡ እአአ በ 2020 ይፋ በወጣዉ
መረጃ መሰረት ከአለም ህዝብ 55% በከተማ ይኖራል። አሀዙም እየጨመረ መጥቷል።እንደ አሜሪካ ቀይ መስቀል

11
ማህበር ጥናት ደግሞ ከአሜሪካ ብቻ 20% የሚሆኑ አዋቂዎች በብቸኝነት ይንከራተታሉ።ይህም የብዙ ሰዎች ስጋት
እየሆነ የመጣ ጦስ ሲሆን ለዚህም ከምክንያቶቹ ጥቂቶቹ፤
ሀ አማራጭ መፈለግ
ለ. ስራ አጥነት
ሐ. የቤተሰብ መፈረካከስ - ተፈጥሯዊና ሰዉ ሰራሽ ችግሮች ሲሆኑ ራስን በራስ ማግለልን፣ጭንቀትን፣ድብርትንና ራስን
መናቅን የሚያስከትል ነዉ፣
ብቸኝነት የሚያስከትለዉ ችግር፤ብቸኝነት ማለት በአንድም ሆነ በሌላ ሱሰኛ በመሆን፣ ደጋፊ በማጣትና በልዩ ልዩ
ችግሮች የሚከሰት ነዉ። ብቸኝነት ማለት ለብቻ ከመሆን ይለያል። አንዳንድ ጊዜ እንደ የሱስ ለብቻ መሆን
መልካም ነዉ። ማቴ 14 13 ብቸኝነት በሆነ ነገር ስሜታዊ በመሆን ከብዙ ነገር መገለል፣ በትርጉም የለሽ
ህይወት ትርጉም ያለዉን ህብረት ማጣትና በሁኔታዎች ተጽእኖ ስር መሸነፍ ማለት ነዉ። ብቸኝነት በሌላ
መንገድ ወደ ክፋት ይመራል።መጥፎ ክስተት ያስከትላል።እንደ ሀዘን፣ደጋፊ ማጣት፣የአእምሮ ህመም፣ የህሊና
ክስና ራስን እስከማጥፋት የሚያስከትል ሲሆን በከተማችን ያሉ የእነዚህ አይነት ሰዎች የእኛን ድጋፍ ልያገኙ
ይገባል።
የብቸኝነት መድሃኒት/መፍትሄ/ - በመጽሐፍ ቅዱስ ስለብችኝነት 118 ጊዜ የተጠቀሰ ሲሆን ይህም ለብቻ ስለመሆን
እንጂ ስለብቸኝነት አይዶለም። እግ/ር በቃሉ ሰዉ ብቻዉን ይሆን ዘንድ መልካም አይደለም አለ። ዘፍ 2 18
እግ/ር በሰዉ ብቸኝነት አይደሰትም። አንዱ ለሌላዉ ረዳት እንዲሆንለት ይፈልጋል። እንሥሣትና ወፎችም
ጥንድ ጥንድ ሆነዉ ተፈጠሩ። ወደ ኖህ መርከብ የገቡትም ሁለት ለሁለት በመሆን ነበር። የብቸኝነትን አሉታዊ
ጎን የሚያዉቅ ዘላለማዊ እግ/ር ረዳትና የሚትስማማ እንፍጠርለት አለ።
ብቸኝነት ለሰብአዊ ዘር ቀዳሚ የእግ/ር እቅድ አልነበረም። እኛ ከእግዚአብሔርና ከሌሎች ጋር ለማበር የተፈጠርን
ማህበራዊ ፍጡራን ነን። ማህበራዊ አንድነትንም እርስ በርስ ለመለዋወጥ የምንፈላለግ ሆነን የተፈጠርን ነን።
ከሀጥአታችንም የተነሳ ከእግ/ርና ከሰብአዊ ዘር በመለየት በብቸኝነት መኖር ሆነብን።ብቸኝነት በሁለት ዋናዋና
መንገዶች ይጎዳናል።
አንድኛዉ፤መንፈሳዊ ብቸኝነት ሲሆን ይህም ከእግዚአብሔር መለየት ማለት ነዉ። ዮሴፍ፣ጳዉሎስ፣ዮሀንስ፣ የሱስ
ራሱና ሌሎችም ሰማእታት ከቃሉ እዉነት የተነሳ እስከ ሞት ድረስ ብቻቸዉን ሆኑ። ይህ ብቸኝነት
አይደለም።መንፈሳዊ ብቸኝነት ከእግዚአብሔር ጋር ያለንን ግኝኙነት ማቋረጥ ማለት ነዉ። ሁለተኛዉ፤ከሰዉ መለየት
ማለት ነዉ። ይህም የርስ በርስ ህብረትን ያቋርጣል። አዳም ከተፈጠረ በኋላ ከእግ/ር ጋር ፍጹም ግንኙነት ቢኖረዉም
በብቸኝነት አልተተወም። እግ/ር ሰዉ ብቻዉን መኖር እንደማይችል ጠንቅቆ ያዉቃል። ረሀብ የምግብ ማስጠንቀቂያ
እንደሆነ ሁሉ ብቸኝነትም ሰዉ ብቻዉን መሆን እንደሌለበት ማስጠንቀቂያ ነዉ። ስለዚህ ብቸኝነት ሲሰማን ወደ
እግ/ርና ወደ ሰዉ እንቅረብ።የብቸኝነት ፍቱን መድሃኒቱ የርስ በርስ ግኝኙነት ሲሆን ዋናዉ ግን በእግ/ር ቤት የሚኖረው
ግንኙነት ነዉ። ለዚህም ቤ/ክ ምቹ ሊትሆን ይገባል። 1 ኛጴጥ 2፡9-10 ቤ/ክ ክርስቲያናዊ ማህበረሰብ አንዱ ለሌላዉ
የሚጠነቀቅ፣ የሚያፈቅር፣ የሚያስጠጋ፣ የሚያገለግል፣ የሚያስተምር፣ ይቅር የሚል የሚደጋገፍና አንዱ ሌላዉን
‘’ሰዉን ሁሉ ወደሚያድነዉ የእግ/ር ጸጋ” እንኳን ደህና መጣህ/ሽ የሚልበት ተቋም ነዉ።

12
ማጠቃለያ፤ዉድ ወጣቶች ብዙ ሰዎች በከተማችን ከብቸኝነት ጋር ይታገላሉ። በድብርትና በጭንቀት ከሞት ጋር ፊት
ለፊት ይፋጠጣሉ። ወሳኝ ለሆነዉ የህይወት ለዉጥ ጓደኛ ያስፈልጋቸዋል።ጥያቄዉ፤ እነዚህን ሰዎች የሚፈልጉ
እግሮች፣ የሚያግዙ እጆች፣ የየሱስን ፍቅር የሚያበስሩ አንደበቶች የማን ይሆኑ? በከተማችን ያሉትን
ብቸኝነት፣ ጭንቀትን፣ ድብርትንና ሞትን በመቀነስ ልዩነት እንድናሳይ እግ/ር ይርዳን። አሜን እግ/ር ይርዳን።

4 ኛ ቀን የጤና ትምህርት
ፈውስ እና ተስፋ ማግኘት

በኢቮን ኦማና

ትርጉም በፓስተር ተስፋዬ ሽብሩ

"ጻድቃን ጮኹ እግዚአብሔርም ሰማቸው፤ ከመከራቸውም ሁሉ አዳናቸው፡፡ እግዚአብሔር ልባቸው ለተሰበረ

ቅርብ ነው መንፈሳቸው የተሰበረውንም ያድናቸዋል" (መዝሙረ ዳዊት 34:17-18)

በተጨናነቀው የዓለም ከተሞች፣ በጩኸት እና ትርምስ መካከል፣ የማይታይ ትግል ያሉባቸው ልቦች አሉ፡፡

የአዕምሮ ጤና ተግዳሮቶች ብዙ ጊዜ ይስተዋላል። በከተማ ጥድፊያ ወቅት፣ ከአእምሮ ጤና ተግዳሮቶች

ጋር በሚታገሉት ሰዎች ህይወት ውስጥ የእግዚአብሔር መገኘት ደምቆ ይታያል። መጽሐፍ ቅዱስ

ለእግዚአብሔር ታማኝ የነበሩት እንኳን የተስፋ መቁረጥ፣ የጭንቀት እና የአስጨናቂ ሁኔታዎች

እንዳጋጠሟቸው ይገልጻል።

ኤልያስ፡ መገለልን እና ተስፋ መቁረጥን ማሸነፍ

የአምላክ ኃያል ነቢይ የነበረው ኤልያስ ከባድ የመፈራረስና የሐዘን ጊዜ አጋጥሞታል። በ 1 ኛ ነገ 19 ላይ፣

በዛቻ ምክንያት ሲሸሽ እና ከሸክሙ በታች ሲወድቅ እናገኘዋለን። ነገር ግን፣ በዚህ ተጋድሎው መካከል፣

እግዚአብሔር ብቻውን እንዳልሆነ አረጋግጦ በለዘብታ ሹክሹክታ አገኘው። እግዚአብሔር ለኤልያስ ህይወትን፣

ማጽናኛን እና ዓላማን እንደሰጠው ሁሉ፣ መጽናናትን እና መመሪያን በማምጣት በጨለማችን ጊዜ ከእኛ


ጋር ይሆናል፡፡

ዳዊት: በተጋላጭነት ውስጥ ጥንካሬን ማግኘት

እግዚአብሔር እንደልቤ ያለው ንጉሥ ዳዊት ስሜቱን እና ድክመቱን በመዝሙረ ዳዊት ውስጥ ገልፆአል።

በመዝሙረ ዳዊት 42 ላይ፣ ዳዊት በውስጣዊ ትግሉ ውስጥ ለእግዚአብሔር ያለውን ናፍቆት ገልጿል። ታድያ

13
ሐቀኝነቱ እንደገና የመተማመን መንፈስ እንዲያገኝ መንገድ ጠርጓል። እኛም እርሱ ጩኸታችንን

እንደሚሰማ እና ለመፅናት ብርታትን እንደሚሰጠን በመተማመን ልባችንን በጌታ ፊት ማፍሰስ እንችላለን።

ጳውሎስ፡ በጸጋ ተለወጠ

በማያወላውል እምነቱ የታወቀው ሐዋርያው ጳውሎስ ስለ ሥጋው መውጊያ ይናገራል፡፡ ታላቅ ጭንቀት

አስከትሎበት ነበር። በ 2 ኛ ቆሮንቶስ 12 ላይ፣ ጳውሎስ የክርስቶስን በድካም ውስጥ ያለውን የጥንካሬ ኃይል

በማስተማር የእግዚአብሔር ጸጋ እንዴት እንደደገፈው ተናግሯል። የእግዚአብሔር ጸጋ ጳውሎስን

እንደለወጠው ሁሉ፣ በውስጣችን መስራቱን ቀጥሏል፣ ይህም የአእምሮ ጤና ተግዳሮቶቻችንን በመዳሰስ

መጽናኛ እና ጥንካሬን ይሰጣል።

በተስፋ መጽናት እንችላለን።

ትግሎቻችን አይገልጹንም፡፡ የጉዟችን አካል ናቸው። ጎህ በጣም ጨለማ የሆነውን ምሽት ተከትሎ ጎህ

እንደሚመጣ ሁሉ፣ እንዲሁ በችግሮቻችን ውስጥ ተስፋ ይበራል። መጽሐፍ ቅዱስ በተሃድሶ፣ እና በፈውስ

ተስፋዎች የተሞላ ነው። ኤርምያስ 29፡11 እግዚአብሔር ለወደፊት ህይወታችን እቅድ እንዳለው፣ እቅዱም

በተስፋ የተሞላ እንደሆነ ያስታውሰናል። የአእምሮ ጤና ፈተናዎችን ስንጋፈጥ ጊዜ እነዚህን ተስፋዎች

እንጠማጠም።

በአለም ከተሞች የአእምሮ ጤና ተግዳሮቶች የገጠማቸውን ስናገለግል፣ መጽሐፍ ቅዱስ የእግዚአብሔርን

ርኅራኄ እና ማስተዋል የሚያሳይ መሆኑን እናስታውስ። በኤልያስ፣ በዳዊት፣ በጳውሎስ እና በሌሎች ስፍር

ቁጥር በሌላቸው ታሪኮች፣ በድካማችን ጊዜ የእግዚአብሔር ብርሃን እንዴት እንደሚበራ እንመሰክራለን።

ከአእምሮ ጤና ችግሮች ጋር ለሚታገሉት የርህራሄ እጆቻችንን በመዘርጋት ማረጋገጫ መስጠት የምንችለው

እንዴት ነው ብለን ራሳችንን እንጠይቅ? ብቻቸውን እንዳልሆኑ እንዴት ልናሳያቸው እንችላለን?

ጸሎት፡-

ጌታ ሆይ ፣ በርህራሄ እና በትዕግስት መንገድ እንድትመራን እፀልያለሁ። ከግል ፈተናዎቻቸው ጋር እየታገሉ

ያሉትን ለመድረስ እና የፍቅር እና የተስፋ ስሜት እንድናስገኝላቸው እርዳን። እግዚአብሔር ሆይ

የተሰበረውን እና የደከመውን በጸጋ እና በተስፋ እንዳገኘኸው እኛም የፍቅርህ ዕቃ እንድንሆን እና፣ ፈውስህ

በጣም ለሚያስፈልጋቸው ልቦች ተሀድሶን እንድናመጣ እርዳን። የሚፈልጉትን ለመርዳት በሄድንበት ቦታ ሁሉ

የአንተ መኖር እና መመሪያ እንዲሰማን እርዳን። በኢየሱስ ክርስቶስ ስም አሜን፡፡

14
4 ኛ ቀን ስብከት

በከተማችሁ ውስጥ የመንፈስ ጭንቀትን መጋፈጥ

በፓስተር ኤስ ዩሪ ፌሬራ
ትርጉም በፓስተር ተስፋዬ ሽብሩ
መዝሙረ ዳዊት 40:2 “ከጥፋት ጕድጓድ ከረግረግም ጭቃ አወጣኝ፥ እግሮቼንም በድንጋይ ላይ አቆማቸው፥

አረማመዴንም አጸና።”
መግቢያ

ዘመኗን ሙሉ በከተማዋ ያሳለፈችውን አና የተባለች ወጣት እናንሳ። የከተማ ህይወት የሚያቀርባቸውን እንደ ባህል፣

ምግብ እና የስራ እድሎችን አስደሳች የሆኑ ነገሮች ሁሉ ትወዳለች። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ግን የሆነ ነገር ትክክል

አይደለም። እሷን ያስደስቷት የነበሩት እንቅስቃሴዎች እና እርካታ ያለላቸው ማህበራዊ ግንኙነቶች አሁን የዛሉ እና

ትርጉም የሌላቸው ይመስላሉ፡፡

አና ከአመት በፊት የማይጠፋ ጥልቅ ሀዘን ይሰማት ጀመሯል። ሌሊቱን ሙሉ ተኝታ ብታድርም ጧት በድካም

ትነቃለች። ሥራ መቋቋም የማትችለው ሸክም ሆነባት፣ እናም በምትደሰትባቸው ሥራዎች ላይ ለማተኮር ትታገል

ነበር። ጓደኞቿ ራሷን ራሷን እያገለለችና እና ከአሁን በኋላ የመውጣት ወይም የመግባባት ፍላጎት እንደሌላት

አስተውለዋል። ከጓደኞቿ ጋር ለመገናኘት የከተማ ውስጥ የመኪና ጭንቅንቁን መጋፈጥ ማሰቡ በጭንቀት ሞልቷታል።

በተጨማሪም አና የምግብ ፍላጎቷ ላይ ለውጦችን አስተውላለች። አንዳንድ ጊዜ ስሜታዊ ክፍተቷን

ለመሙላት በመሞከር ከመጠን በላይ ትበላ ነበር፡፡ በሌላ ጊዜ ደግሞ ትንሽ የምግብ ፍላጎት ይኖራትና እና

ክብደቷ እየቀነሰ ይሄድ ነበር፡፡ እንቅልፍ ማጣቷ እና አሉታዊ ሀሳቦች ደግሞ እኩለ ሌሊት ላይ ሲያነቋት በዚህ

ሁኔታ እንቅልፍ የማያቋርጥ ውጊያ ሆነ።

ይህን ሸክም በጸጥታ ከተሸከመች በኋላ በመጨረሻ እርዳታ ለመጠየቅ ወሰነች። ወደ ቴራፒስት ሄዳ ስለ

ሀዘን፣ ጭንቀት እና የተስፋ መቁረጥ ስሜቷን ማውራት ጀመረች። ቴራፒስት የመንፈስ ጭንቀት እንዳለባት

መርምሮ ከለየ በኋላ የሕክምና ዕቅድ ጠቶማት፡፡

የመንፈስ ጭንቀት ችግር

የመንፈስ ጭንቀት በቀላሉ የማይለቅ እና እንደ አንተ እና እኔ ያሉ ወጣቶችን የሚያጠቃ ጥቁር ደመና

ነው። ሐዘን እንዲሰማህ፣ እና በምትደሰትባቸው ነገሮች ላይ ፍላጎት እንዳይኖረህ ሊያደርግህ ይችላል፡፡

15
የጥፋተኝነት ስሜት እንዲሰማህ ወይም ዋጋ እንደሌለህ እንድታስብ ሊያደርግ ይችላል። እንዲሁም

በእንቅልፍህ እና በምግብ ፍላጎትህ ላይ ተጽእኖ ሊያሳድር ይችላል፡፡ ይሄ ደግሞ ጉልበት አልባ ያደርግሃል፡፡

የተለያዩ የመንፈስ ጭንቀት ዓይነቶች አሉ ለምሳሌ፡-

ሁኔታዊ ድብርት፡- ይህ የሚከሰተው እንደ የሚወዱትን ሰው በሞት በማጣት ወይም በገንዘብ ነክ ችግሮች

ባሉ አስጨናቂ ሁኔታዎች ምክንያት ነው። ሁኔታው ከተሻሻለ በኋላ ሊጠፋ ይችላል.

ወቅታዊ የመንፈስ ጭንቀት፡- አንዳንድ ሰዎች በዓመቱ ውስጥ በተወሰኑ ጊዜያት ሀዘን ይሰማቸዋል፣ ለምሳሌ

በክረምት ወራት የፀሐይ ብርሃን በማይኖርበት ጊዜ።

ከሐዘንና ከተስፋ መቁረጥ የሚመጣ ከፍተኛ ድብርት - እነዚህ ምልክቶች በጣም ከባድ ናቸው፡፡ በሁሉም

እንቅስቃሴዎች ላይ ፍላጎት እንዳይሆርህ ያደርጉሃል፡፡ ብዙ ክብደት ታጣለህ፣ ንዴት ወይም በጣም ቀርፋፋ

መሆን እንዲሁም የጥፋተኝነት ስሜት ሊሰማህ ይችላል።

ሳይኮቲክ ዲፕሬሽን፡ ይህ ይበልጥ የተወሳሰበ ነው፣ በቅዠት (የሌሉ ነገሮችን ማየት ወይም መስማት) ወይም

በመታለል ውሸት እምነት። ይህ ለበሽታው ተጨማሪ ውስብስብነትን ይጨምራል፡፡

ከፍተኛ የመንፈስ ጭንቀት - ይህ በጣም የተለመደ ዓይነት ሲሆን ጥልቅ ሀዘን፣ የነገሮች ፍላጎት ማጣት፣

የምግብ ፍላጎት እና እንቅልፍ ማጣት እና ሌሎች ምልክቶች የዕለት ተዕለት ህይወት ላይ ተጽዕኖ

ያሳድራሉ ።

እንደ ትላንትናው ርዕስ ፣ ብቸኝነት ሁሉ ከተማዎች ከውጥረት ፣ ከተፈጥሮ ጋር አለመግባባት ፣ ከብክለት

እና ሌሎች ምክንያቶች የተነሳ ለድብርት መፍለቂያ ቦታ ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ እነዚህ ምክንያቶች በከተማ

አካባቢ ያሉ ብዙ ሰዎችን ሊነኩ ይችላሉ፣ በመሆኑም በአእምሯዊ ጤንነታችን እንዴት እንደሚነኩ ማወቅ

በጣም አስፈላጊ ነው።

የመንፈስ ጭንቀት ወጣቶችንም ሆነ ጎልማሶችን ይጎዳል፡፡ አኃዛዊ ዘገባዎች እንደሚያሳዩት ከሆነ በዓለም

ዙሪያ ከ 20% በላይ የሚሆኑት በአሥራዎቹ ዕድሜ ውስጥ የሚገኙ ወጣቶች በአእምሮ ሕመም ይሰቃያሉ፡፡1

የመንፈስ ጭንቀት በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ

የመንፈስ ጭንቀትን ብዙ ጊዜ ከዘመናዊው የሕክምና ሳይንስ ጋር ብናይዘውም፣ መሰረቱ የሚገኘው ስለ ጥንት ዘመን

ከተነገሩ በመጽሐፍ ቅዱሳዊ ዘገባዎች ውስጥም ጭምር ነው። መጽሐፍ ቅዱስ ጥልቅ ሀዘንና የተስፋ መቁረጥ ስሜት

ያጋጠማቸው የተከበሩ ሰዎች ታሪክ አለው። በእነዚህ ታሪኮች፣ እምነት፣ ተስፋ እና ከመለኮታዊው ጋር ያለው ግንኙነት

ድብርትን ለመጋፈጥ እንዴት ግብዓቶች እንደሆኑ ማሰስ እንችላለን። አንዳንድ ምሳሌዎችን እንመልከት፡-

16
1. ዳዊት፡- እግዚአብሔር እንደልቤ ያለው ሰው

“እንደልቤ” በመባል የሚታወቀው ዳዊት ጥልቅ የሆነ የሃዘንና የጭንቀት ጊዜያትን አሳልፏል። መዝሙሮቹ

ለስሜታዊ ትግሎቹ ልብ የሚነኩ ምስክሮች ናቸው። በመዝሙር 42 ላይ ዳዊት እንዲህ ሲል ጽፏል:- "ነፍሴ

ሆይ፥ ለምን ታዝኛለሽ? ለምንስ ታውኪኛለሽ? የፊቴን መድኃኒት አምላኬን አመሰግነው ዘንድ በእግዚአብሔር

ታመኚ።" (መዝሙረ ዳዊት 42፡11)። .

በዚህ ምንባብ፣ ዳዊት ጭንቀቱን አምኗል፣ ነገር ግን ተስፋን እና መለኮታዊ እርዳታን ለመሻት በእምነቱ

ጥንካሬን አግኝቷል። ይህ የሚያስተምረን በተስፋ መቁረጥ ውስጥም ቢሆን እምነት ከድብርት ጋር

ለሚታገሉ ሰዎች መሪ ብርሃን ሊሆን ይችላል።

2. ኤርምያስ፡- አልቃሻው ነቢይ

ኤርምያስ፣ “አልቃሻው ነቢይ” በመባል የሚታወቀው፣ ጥልቅ ሀዘን የደረሰበት ሌላው መጽሐፍ ቅዱሳዊ

ምሳሌ ነው። የሰቆቃው ኤርምያስ መጽሃፍ ነቢዩ ባያቸው መከራዎች ስቃይ እና ሀዘን የተሞላ ነው።

ኤርምያስ በመከራው መካከል እንዲህ ሲል ጽፏል፡ “ይህችን በልቤ አኖራለሁ፥ ስለዚህ እታገሣለሁ፡፡”

ጥፋት ኤርሚያስን ቢከበውም የማሰላሰል እና በልቡ ውስጥ ያለውን ተስፋ የማግኘት ችሎታው በጣም

ጨለማ በሆነ ጊዜ ውስጥ እንኳን ራስን መመርመር እና ተስፋ ወደ መንፈሳዊ ማገገም እንደሚመሩት

ያስታውሰዋል።
3. ኤልያስ፡ የተዳከመው ነቢይ
የመንፈስ ጭንቀት ያጋጠመው ሌላው የመጽሐፍ ቅዱስ ገጸ ባሕርይ ነቢዩ ኤልያስ ነው። በበኣል ነቢያት ላይ ታላቅ ድል
ካገኘ በኋላ፣ ኤልያስ በድካም እና በፍርሃት በመዋጥ ሞትን ተመኘ። ነገር ግን፣ በተስፋ መቁረጥ ውስጥ ሆኖ ሳለ፣
በየዋህነት እና በሹክሹክታ ከእግዚአብሔር ጋር ልዩ ግንኙነት ፈጠረ፡፡ (1 ነገ. 19፡12)።
የኤልያስ ታሪክ እንደሚያስተምረን በጣም ዝቅተኛ በሆነ የመንፈስ ጭንቀት ውስጥ እንኳን መለኮታዊ መገኘት የጥንካሬ
እና የመንፈሳዊ መታደስ ምንጭ ሊሆን ይሆናል፡፡
የመንፈስ ጭንቀትን የማሸነፊያ መንገድ
ውድ ወጣቶች፣ በከተማችሁ ውስጥ የምታውቁት ሰው ወይም ራሳችሁ ከመንፈስ ጭንቀት ጋር እየታገላችሁ ሊሆን ይችላል።
በዚህ ሁኔታ ውስጥ ሊረዱ የሚችሉ አንዳንድ ምክሮች የሚከተሉት ናቸው፡፡
ጸሎት እና የእግዚአብሔርን መገኘት መፈለግ፡- ጸሎት በመንፈስ ጭንቀት ወቅት መጽናናትን፣ ተስፋን እና ጥንካሬን
የምናገኝበት መንገድ ሊሆን ይችላል።
የክርስቲያን ማህበረሰብ እና መንፈሳዊ ድጋፍ፡ ከሌሎች አማኞች ጋር ያለው ግንኙነት እና የክርስቲያን ማህበረሰብ ድጋፍ
ወሳኝ ሊሆን ይችላል። በጉባኤ፣ የድጋፍ ቡድን ወይም የእምነት ማህበረሰብ ውስጥ መሳተፍ የአባልነት ስሜትን እና
ስሜታዊ ድጋፍን ሊሰጥ ይችላል።

17
ቅዱሳት መጻህፍትን ማንበብ እና ማሰላሰል፡- መጽሐፍ ቅዱስን ማንበብ እና ተስፋን፣ ጥንካሬን እና ተግዳሮቶችን
ስለማሸነፍ በሚናገሩ ጥቅሶች ላይ ማሰላሰል ጠቃሚ ሊሆን ይችላል።
ክርስቲያናዊ ምክር መፈለግ፡- በምክር የሰለጠነ ክርስቲያን አማካሪ ወይም ፓስተር ከመጽሐፍ ቅዱሳዊ እይታ አንጻር
ለመንፈስ ጭንቀት የተለየ መንፈሳዊ እና ስሜታዊ መመሪያና ምክር ሊሰጥ ይችላል።
ይቅርታን እና ምስጋናን መለማመድ፡- ሌሎችን እና ራስን ይቅር ማለትን መማር ነጻ የሚያወጣ ሂደት ሊሆን ይችላል።
ራስን ማግለልን ማስወገድ፡- በእምነት ውስጥ ከጓደኞችና ከምትወዳቸው ሰዎች ጋር መቀራረብ ጠቃሚ ሊሆን ይችላል።
አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ የባለሙያ እርዳታ መፈለግ፡ ድብርት እውነተኛ በሽታ ነው፣ እና በብዙ አጋጣሚዎች እንደ ቴራፒ
ወይም መድሃኒት ያሉ ሙያዊ ህክምና ማግኘት ያስፈልጋል።
የእግዚአብሔርን ጸጋ እና ፍቅር መቀበል፡- የእግዚአብሔርን ፍቅር እና ጸጋ ማስታወስ ከጭንቀት ጋር የተያያዘውን
ጥፋተኝነት ወይም እፍረትን ለማቃለል ይረዳል።
ማጠቃለያ
በከተማችሁ ውስጥ ከድብርት ጋር የሚታገሉ በሺዎች የሚቆጠሩ ወጣቶች እና ጎልማሶች አሉ። ለእነሱ ተስፋ ለመስጠት
ጊዜው አሁን ነው። እግዚአብሔር ከተስፋ መቁረጥ ጉድጓድ የሚያወጣቸው ኃይል እንዳለው የምንነግራቸው ጊዜ አሁን
ነው። ውድ ወጣቶች፣ እናንተም ሆናችሁ የምታውቁት ሰው ከመንፈስ ጭንቀት ጋር እየታገለ ከሆነ፣ በመንፈሳዊም ሆነ
በሕክምናው መስክ እርዳታ መፈለግ ችግሩን ለመፍታት ከሁሉ የተሻለው መንገድ ሊሆን ይችላል። እናንተን ለመርዳት
ዝግጁ የሆኑ እና የአእምሮ ጤና ስፔሻሊስት እንድታገኙ ግብዓቶችን ለመስጠት ዝግጁ የሆኑ ሽማግሌዎች እና ዲያቆናት
አሉ። ዲያብሎስ ነፍስህን ከመግደል፣ ከመስረቅና ከማጥፋት ሌላ ምንም አይፈልግም፤ ነገር ግን እግዚአብሔር የተትረፈረፈ
ሕይወት እንዲኖርህ መጣ። እግዚአብሔር ሕይወት እንዲኖርህ ይፈልጋል፣ እኛም ሕይወት እንዲኖርህ እንፈልጋለን።
ስለዚህ እርዳታ ጠይቅ!
አይዟችሁ፣ አብረን፣ በከተማችሁ ውስጥ ያለውን የመንፈስ ጭንቀት ጉዳይ እንጋፈጥ።
5 ኛ ቀን የመጋቢነት ትምህርት
ሐብታሞችን መድረስ
በኢቮኒ ኦማፍያ
ትርጉም በፓስተር ተስፋዬ ሽብሩ

የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅስ፡- “ደቀ መዛሙርቱ ይህን በሰሙ ጊዜ እጅግ ተገረሙና፡— እንኪያስ ማን ሊድን

ይችላል? አሉ፡፡ ኢየሱስም እነርሱን ተመልክቶ፡- “ይህ በሰው ዘንድ አይቻልም በእግዚአብሔር ዘንድ ግን ሁሉ

ይቻላል። አላቸው” ማቴዎስ 19:25-26

ወንጌልን ለሌሎች ለማካፈል ስንመጣ፣ በአብዛኞቻችን ውስጥ ፍርሃትና ጥርጣሬን የሚያመጣ የተወሰነ

የሰዎች ስብስብ አለ፣ እነዚያ ሀብታም እና ባለ ጠጎች ናቸው። ለዚህ የሰዎች ቡድን ያለው አመለካከት

እንደ እድል ሆኖ ኢየሱስ ከደቀ መዛሙርቱ ጋር በይሁዳ መንገዶች ሲሄዱ ከነበረበት ጊዜ ጀምሮ ነበር።

18
ሰዎች የመዳንን ዜና ለሀብታሞች ስለመካፈል ያላቸውን አመለካከት ለመግለጽ ከሁሉ የተሻለው ምሳሌ

በማቴዎስ 19፡16-26 ውስጥ በባለጠጋው ወጣት ታሪክ ተገልጿል:: ይህ ገዥ ሀብታም ነበር፣ እና መጽሐፍ

ቅዱስ ኢየሱስ ምድራዊ ንብረቱን ሁሉ ትቶ እንዲከተለው እንደጠየቀው ይናገራል፣ ወጣቱ ገዥ በጣም

ሀብታም ነበርና እያዘነ ሄደ። ማቴ 19፡22

ከሁሉ የሚገርመው እና ወንጌልን ከሀብታሞች ጋር ስለመካፈል የዘመናችን ግንዛቤ ነጸብራቅ የሆነው ወጣቱ

ገዥ ከሄደ እና የአዳኙን ግብዣ ውድቅ ካደረገ በኋላ ደቀ መዛሙርቱ የሰጡት ምላሽ ነው። ኢየሱስን

“አንድ ሰው እንዴት መዳን ይችላል?” ብለው ጠየቁት። ቁ.25 ኢየሱስም ለእንዲህ ዓይነቱ እምነት የለሽ

ጥያቄ ፍጹም የሆነ ምላሽ ሰጥቷል፡- “ለሰው የማይቻል ለእግዚአብሔር ይቻላል” ቁ.26 ይህም ወንጌልን

ለሀብታሞች ለመካፈል የታሰበ ማንኛውም የወንጌል ስርጭት ማዕከል ነው። በተለይም በዚህ ዘመናዊ

ማህበረሰብ ውስጥ.

እንደ የማይቻል ነገር የምናየው፣ እናም እኛ ሰዎች የማይቻል ነው ብለን ያወቅነውን በስኬት ለማሳካት እግዚአብሔር

የሚሳነው ነገር የለም፡፡ እግዚአብሔር የመጀመሪያውን እርምጃ እንድንወስድ እና ይህን ቡድን መዳን የሚችሉ ሰዎች

ቡድን አድርገን እንድንቆጥረው እየጠበቀን ነው። በጣም የተሳካላቸው እና ሀብታም ጥንዶች ከነበሩት ታሪክ ውስጥ

አንድ ክሊፕ በቅርቡ አይቻለሁ። በትጋትና በብልሃት ብዙ ሚሊዮን ዶላር የሚያወጣ የአሻንጉሊት ኩባንያ ገነቡ።

ሊትገምቱት የምትችሉት ነገር ሁሉ ያለው በርካታ መኖሪያ ቤት ነበሯቸው። ቆንጆ ቤተሰብ ነበራቸው፤ እና ከውጭ

ሆናችሁ ስትመለከቱ ምንም የሚጎልባቸው እንደሌለ ታስባላችሁ፡፡ ከዚያም ጥንዶቹ ስለ ድርጅታቸው ስኬት ሊወያዩ

ተቀምጠው ሳለ ጋዜጠኛው ስለ ህይወት እና ስኬት ያለውን ስሜት ሴትየዋን ጠየቃት፡፡ ገና ከ 5 ዓመቷ ጀምሮ በነፍሷ

ውስጥ ከሌላው ሰውና ከባለቤቷም ጭምር ከ 40 አመታት በላይ የደበቀችው ባዶነት እንዳለ ተናግራለች። ህይወት

ምንም ትርጉም እንደሌለው ተሰማት፡፡ ምንም ግድ አልነበራትም፤ ህይወቷ በነፍሷ ውስጥ ያለውን ክፍተት ለመሙላት

በምትፈልገው በቁሳዊ ነገሮች የተከበበ ነው። እንዲህ አይነቱ ቡድን አዳኝ እንደሚያስፈልገው መገንዘብ አለብን።

ሐዋርያው ጳውሎስ በአግሪጳ የፍርድ አደባባይ በባለስልጣናት ፊት ወንጌልን የማጋራት እድል በማግኘቱ ተደስቶ ነበር፡፡

ዳንኤልና ሶስቱ የአይሁድ ጓደኞቹ በናቡከደነጾር መንግስት ውስጥ የእምነትና ለእግዚአብሔር የመታመን ምሳሌዎች

ነበሩ፡፡ ዮሴፍም በጥንታዊቷ ግብጽ ውስጥ ፈርኦንን ሲያገለግል ተመሳሳይ ነገር አደረገ፡፡ በንዕማን ቤት ከነበረችው ደፋር

ብላቴና የተነሳ ንዕማን ሊድንና የእስራኤልን አምላክ ሊወድ ችሏል፡፡ በዚህ ዘመናዊ ማህበረሰብ መካከል ወንጌልን

ለሐብታሞች ለማጋራት እድሎችን መፈለግ አለብን፡፡ ለሰው የማይቻል ለእግዚአብሔር በእርግጥ ይቻላል፡፡ አዳኝ

ለሚያስፈልጋቸው ለነዚህ ሰዎች በተከፈተ ልብ እግዚአብሔርን እንጠይቅ፡፡

19
ጸሎት

ውድ አምላክ ሆይ፣ በማቴዎስ 19፡25-26 ባለው ትምህርት እየተመራን ከልብ እንጸልያለን። ለሀብታሞች

ወንጌልን ማካፈል ፈታኝ ሊሆን እንደሚችል እናውቃለን፣ ነገር ግን ከእናንተ ጋር ሁሉም ነገር የሚቻል

መሆኑን እናስታውሳለን። “ማን ሊድን ይችላል””ብለው እንዳሰቡት ደቀ መዛሙርት ሁሉ እኛም ባለጠጎችን

መድረስ አይቻልም ብለን ልንጠራጠር እንችላለን። ሆኖም ታሪኩ የሚያሳየን የማይደረስ የሚመስሉትን እንኳን

ህይወት መንካት እንደምንችል ነው፡፡ ልክ ጳውሎስ፣ ዳንኤል፣ ዮሴፍ ሌሎች ያንተ ሰዎች መልእክትህን

ለኃያላን መሪዎች እንዳደረሱት፣ ዛሬ በዓለማችን ላሉ ባለጠጎች ፍቅርህን ለመካፈል እድሎችን እንድናገኝ

እርዳን። አዳኝ እንደሚያስፈልጋቸው ግለሰቦች እንያቸው። ለእኛ ከባድ መስሎ የሚታየው ለአንተ የሚቻል

መሆኑን አውቀን ቃልህን ወደ እነርሱ ለማቅረብ ድፍረትን፣ ጥበብን እና ደግነትን ስጠን። በኢየሱስ ስም

እንጸልያለን። ኣሜን።
5 ኛ ቀን ስብከት
በከተማችሁ ያለውን በሽታ መጋፈጥ
በፓስተር ኤስ ዩሪ ፌሬራ
ትርጉም በፓስተር ተስፋዬ ሽብሩ
3 ዮሐ 2
መግቢያ

በተጨናነቀች ታዋቂ ከተማ መሃል የከተማ ኑሮ ፈጽሞ አልቆመም። መንገዶቹ ሁል ጊዜ በተጣደፉ ሰዎች

ተሞልተዋል፣ ሰማይ ጠቀስ ፎቆች እንደ ምኞት ማማ ሰማይን የነኩ ይመስላሉ ። ነገር ግን በዚያ ሁሉ ዘመናዊ ቅንጦት

እና ገጽታ ስር የማይታዩ አደጋዎች ተሰውረዋል፡፡

አንድ የቀዝቃዛ ክረምት ማለዳ ላይ ማንም ያልተረዳው በሽታን በተመለከተ ወሬዎች መሰራጨት ጀመሩ። ሰዎች ገዳይ

ጉንፋን፣ ከፍተኛ ትኩሳት፣ የመተንፈስ ችግር እና የማያቋርጥ ሳል ይሰማቸዋል። መጀመሪያ ላይ ማንም ሰው ብዙ

ትኩረት የሰጠው አልነበረም ምክንያቱም ጉንፋን እንደዚህ ባሉ ሰዎች በሚበዛባት ከተማ ውስጥ የተለመደ ስለነበር

ነው፡፡

ይሁን እንጂ በሽታው በሚያስደነግጥ ሁኔታ መስፋፋት ጀመረ፡፡ ሆስፒታሎች በአጭር ጊዜ በህመምተኞች ተሞልተዋል፣

ዶክተሮች በጣም ስራ በዝቶባቸው ነበር። የጤና ዘርፍ ባለስልጣናት ማስጠንቀቂያ ካወጡ በኋላ ምን እየተፈጠረ እንዳለ

መመርመር ጀመሩ። የህብረተሰብ ጤና ባለሙያዎች እንዴት እየተስፋፋ እንዳለ ተንትነው በሽታው በመሀል ከተማ

20
ውስጥ በተወሰነ ደረጃ “ከተለመደ” የምግብ ገበያ ጋር የተያያዘ መሆኑን ደረሱበት፡፡ በዚያ ገበያ ያልተለመዱ እንስሳትን

ይሸጡ ነበር።

በሽታው ከእንስሳት ወደ ሰው በሚተላለፍ አዲስ ቫይረስ የሚመጣ መሆኑ ሲታወቅ ከተማዋ በፍርሃት ተሞላች፡፡

ኋላም እንቅስቃሴ አደረጉ እና የኳራንቲን አዋጅ አወጁ፣ ከተማዋን በሙሉ እንቅስቃሴ እንዳይኖራት አደረጉ!

እንግዳውንም ገበያ በቅጽበት ዘግተውታል፤ ነገርግን በሽታውን ሙሉ በሙሉ ለማስቆም ጊዜው አልፏል።

በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች በቫይረሱ የተያዙ ሲሆን የሟቾች ቁጥርም ጨምሯል።

ከተማዋ በአጠቃላይ ትርምስ ውስጥ ገባች። በአንድ ወቅት የተጨናነቁ ጎዳናዎች ከድህረ-ምጽዓት በኋላ

የተሰኘውን ፊልም ሁኔታ እስኪመስሉ ድረስ ተለውጠዋል። ሰዎች በፍርሃት ቤታቸው ውስጥ ቆዩ፣ የንግድ

ድርጅቶች በራቸውን ዘግተዋል፣ እና ኢኮኖሚው በ 180 ዲግሪ ዞረ። ሆስፒታሎች በመውደቅ አፋፍ ላይ

ነበሩ፤ ዶክተሮች የታመሙትን ለመንከባከብ ነገ እንደሌለ አድርገው ይሰሩ ነበር.

ምንም እንኳን ይህ ዘገባ ንጹህ ልብወለድ ቢመስልም እውነት መሆኑን እናውቃለን። በከተማ ውስጥ ያለው

ህይወት ከሚታየው የበለጠ ደካማ ሊሆን ይችላል፡፡ በዘመናዊ ከተሞች ውስጥ በሽታዎች ሲገጥሙን ዝግጁ

መሆን እና መተባበር ወሳኝ ነው፡፡


የስብከት ዋና ሐሳብ
1 ኛ. በሽታ በከተሞች ውስጥ

በከተሞች ውስጥ ያሉ በሽታዎች ከከተማ ህይወት እና ከሰዎች ጤና ጋር የተቆራኙ ውስብስብ ጉዳዮች

ናቸው. የዚህ ችግር ዋና መንስኤዎችን እንመልከት፡-

• የአየር ብክለት፡- በተለያዩ ከተሞች የሚተነፈሰው አየር ከመኪናዎች፣ ፋብሪካዎች እና ሌሎች የብክለት

ምንጮች ብዛት የተነሳ ከፍተኛ ችግር ነው። ይህ ብክለት እንደ አስም እና የሳባ ምች ያሉ የመተንፈሻ
አካላት ችግር ከማስከተሉም አልጆ የልብ ችግር ሊያመጣ ይችላል፡፡
• የውሃ ብክለት፡- ውሃ በከተሞች ውስጥ ወሳኝ ነገር ነው፣ነገር ግን በአግባቡ ካልተያዘ ወደ መጥፎ ውጤት

ሊመራ ይችላል። ቧንቧዎቹ እና የጽዳት ስርዓቱ በጥሩ ሁኔታ ላይ ካልሆኑ እንደ ኮሌራ ያሉ የውሃ ወለድ

በሽታዎች ሊሰራጩ ይችላሉ፡፡

• የህዝብ ብዛት፡- በከተሞች ውስጥ ሰዎች ልክ በጣሳ ውስጥ እንዳለ እንደ ሰርዲን ታጭቀዋል፡፡ ይህም

ተላላፊ በሽታዎችን በቀላሉ እንዲባዙ ያግዛል። ኢንፍሉዌንዛ፣ ኮቪድ-19 እና ሌሎች ህመሞች ሰዎች በብዛት

በሚኖሩባቸው አካባቢዎች በቀላሉ ሊሰራጩ ይችላሉ።

21
• የጤና አጠባበቅ አገልግሎት ውስንነት፡ ከተማዎች ሆስፒታሎች እና ክሊኒኮች በሁሉም ቦታ ቢኖራቸውም፣ ለሁሉም

ሰው ማግኘት እና እንክብካቤ ማግኘት ሁልጊዜ ቀላል አይደለም። አንዳንድ ሰዎች የኢኮኖሚ አቅም የሌላቸው ወይም

ከህክምና ተቋማት ርቀው የሚኖሩ ናቸው, ይህም በሽታዎችን ለመፍታት አስቸጋሪ ያደርገዋል.

• የአእምሮ ጤና ጉዳዮች፡ ጭንቀት እና ድብርት በከተሞች ውስጥ አሳሳቢ ጉዳዮች ናቸው። የከተማ ኑሮ በስራ

ውድድር፣ በትራፊክ፣ በማህበራዊ መገለል እና በሌሎች ምክንያቶች የተነሳ ለአእምሮ ጤና ችግርና አስጨናቂ ሊሆን

ይችላል።

• የሚረብሹ ነፍሳት እና አይጦች፡ በአንዳንድ ከተሞች እንደ ትንኞች እና አይጥ ያሉ ነፍሳት በአግባቡ ካልተያዙ

በሽታዎችን ሊያስተላልፉ ይችላሉ። ለምሳሌ ዴንጊ እና ሌሎች በሽታዎች በንክሻ ወይም ከነዚህ ተባዮች ጋር

በመገናኘት ሊተላለፉ ይችላሉ።

• መቀመጥ የበዛበት የአኗኗር ዘይቤ፡- ብዙ የከተማ ነዋሪዎች በቢሮ ስራዎች እና የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ቦታዎች

እጦት ሳቢያ ጤናማ ያልሆነ ህይወት ይመራሉ። ይህ ደግሞ እንደ ውፍረት እና ከልብ ጋር የተያያዙ በሽታዎችን

በማስከተል ወደ ጤና ችግሮች ሊያመራ ይችላል፡፡

• የድምፅ ብክለት፡- በከተማው ውስጥ የማያቋርጥ ጫጫታ ከፍተኛ ጭንቀትን ሊያስከትል እና እንቅልፍን ሊያስተጓጉል

ይችላል። ይህ የደም ግፊትን ሊያስከትል እና እረፍትን ሊጎዳ ይችላል፡፡ ውጤቱ ደግሞ ወደ ጤና ችግሮች ማምራት

ሊሆን ይችላል፡፡
2 ኛ. እግዚአብሔርና ጤንነት

የመጽሐፍ ቅዱስ አምላክ የጤና አምላክ ነው። በ 3 ኛ የዮሐንስ መልእክት 1፡2 ላይ፡ “ወዳጆች ሆይ፥ ነፍስህ

እንደሚከናወን በነገር ሁሉ እንዲከናወንልህና ጤና እንዲኖርህ እጸልያለሁ” የሚል ኃይለኛ መልእክት እናገኛለን።

እግዚአብሔር ለሰው ልጆች ባዘጋጀው የመጀመሪያ እቅድ ውስጥ በሽታ አልነበረም። የመጀመሪያዎቹ ወላጆቻችን

እንዲህ ባለው ጤናማ የአኗኗር ዘይቤ ውስጥ እንዳሉ መገመት ትችላለህ? ምንም አይነት ብክለት አልነበረም፡፡ ያለ

እንግዳ ኬሚካሎች ጤናማ በሆነ አካባቢ፣ ለውዝ፣ እህል እና የተፈጥሮ ፍራፍሬዎችን መብላት ነበር። ስለ ጤና ብዙ

የጻፈችው ኤለን ጂ ዋይት የመጀመሪያዎቹ ወላጆቻችን ፍጹም ጤናማ ሆነው ይኖሩ እንደነበር ተናግራለች።

የፎቶግራፍ ምስል በማይደርሳቸው መልኩ ረጅምና ቆንጆዎች ነበሩ። አዳም ዛሬ ካሉ ሰዎች በጣም የሚበልጥ ነበር፣

እና ሔዋን በመጠኑ አጠር ያለች ነገር ግን በጣም ቆንጆ እና የተዋበች ነበረች። Patriarchs and Prophets p. 45.3

አዳምና ሔዋን ፍጹም ጤንነት ነበራቸው። አካላዊ፣ አእምሮአዊ እና ማህበራዊ ጤና ነበራቸው። ከሁሉ የሚበልጠው

ግን ከአምላክ ጋር በጣም የተቆራኙ ነበሩ፣ ይህም የሚያስቀና መንፈሳዊ ጤንነት ሰጥቷቸዋል። ይሁን እንጂ ይህ ፍጹም

22
ጤና ተስተጓጎለ፡፡ አዳምና ሔዋን በእግዚአብሔር አለመታመንን መርጠው ከገነት በተባረሩ ጊዜ ሁሉም ነገር ተለወጠ

እና በሁሉም አካባቢዎች በሽታዎች ተከሰቱ።

ዘፍጥረት 3 የመጀመሪያዎቹ ጥንዶች የእግዚአብሔር ጠላት በሆኑት እንዴት እንደተሸነፉ እና ለፈጣሪያቸው

ጀርባቸውን እንደሰጡ ይናገራል። ሆኖም የመጀመሪያዎቹ ወላጆቻችን ቢያምፁም አምላክ አሁንም

ለጤንነታችን በጥልቅ ያስባል።

ወሰን በሌለው ፍቅሩ፣ ጤናማ ህይወት ለመኖር እድል የሚሰጥን ቃል ኪዳን ትቶልናል። በመጀመሪያ

እግዚአብሔር ለእስራኤላውያን በምድረ በዳ ሲጓዙ ይህን የተስፋ ቃል ሰጥቷቸዋል፤ ይህን ተስፋ እኛም

ልንቀበለው እንችላለን፤ ሮሜ 15፡4 እንዲህ ይላል፡- “በመጽናትና መጻሕፍት በሚሰጡት መጽናናት ተስፋ ይሆንልን

ዘንድ አስቀድሞ የተጻፈው ሁሉ ለትምህርታችን ተጽፎአልና።"

በዘጸአት 15፡26 ላይ እግዚአብሔር ለእስራኤል በሙሴ በኩል የሰጠውን ተስፋ ተመልከቱ፡- እርሱም፦ `አንተ

የአምላክህን የእግዚአብሔርን ቃል አጥብቀህ ብትሰማ፥ በፊቱም የሚበጀውን ብታደርግ፥ ትእዛዙንም

ብታደምጥ፥ ሥርዓቱንም ሁሉ ብትጠብቅ፥ በግብፃውያን ላይ ያመጣሁትን በሽታ አላደርስብህም፤ እኔ

ፈዋሽህ እግዚአብሔር ነኝና አለ።”


በጥንት ዘመን የእስራኤል ሕዝብ የላቀ የጤና መርሆች ነበራቸው። በሙሴ ዘመን በ 1500 ዓ.ዓ አካባቢ

በግብፃውያን የተጻፈ “ኤበር ፓፒረስ” የተባለ ጥንታዊ መጽሐፍ በአርኪዮሎጂስቶች ተገኝቷል። ምንም

እንኳን አንዳንድ ሀሳቦቻቸው በጣም እንግዳ ቢሆኑም ይህ መጽሐፍ ለግብፅ ጤና መመሪያ ሆኖ አገልግሏል።

በዚህ ጥቅል ውስጥ የሚገኙትን አንዳንድ የሕክምና ምክሮች እንመልከታቸው፡፡ ነገር ግን በቁም ነገር ይህንን

በቤት ውስጥ አትሞክሩት!

ለምሳሌ፣ ሽበትን ለመከላከል፣ በዘይት የተቀቀለውን የጥቁር ድመት ደም ወይም የእባብ ስብን ፀጉርን

መቀባትን ይመክራሉ። ራሰ በረሃነትን ካልፈለጋችሁ ስድስት ዓይነት ስብ ማለትም ፈረስ፣ ጉማሬ፣ አዞ፣

ድመት፣ እባብ እና ፍየል መጠቀም እንደሚገባ ይመክራሉ። ፀጉርህን ለማጠናከር ማርን ከአህያ ጥርስ ዱቄት

ጋር መቀላቀል ይላሉ።

በሰውነታቸው ላይ ስንጣቂ ካዩ፣ የህክምና ማዘዣው "የትል ደም እና የአህያ ፋንድያ" መጠቀምን ያካትታል። ሌሎች

እንግዳ ምክሮች "የእንሽላሊት ደም ፣ የአሳማ ጥርስ ፣ የበሰበሰ ሥጋ ፣ የአሳማ ጆሮ እርጥበት እና የሰው ፣ የእንስሳት እና

የዝንብ እዳሪ" ጭምር ነበር። ዛሬ ዶክተራችሁ እነዚህን ምክሮች ቢለግሳችሁ ምን እንደምትሉ መገመት አያዳግትም፡፡

እንዴት ያለ እብደት ነው! እነዚህ በሙሴ ዘመን የነበሩ “ሊቃውንት” ነበሩ።

23
በእርግጠኝነት፣ ሙሴ እነዚህን የ”ኤበርስ ፓፒረስ” ጽሑፎች ጠንቅቆ ሊያውቅ ይገባል፤ ምክንያቱም በቅዱሳን

ጽሑፎች መሠረት የግብፃውያንን እውቀት ሁሉ ተምሯል። ነገር ግን የሚያስደንቀው ነገር ከእነዚህ እንግዳ ምክሮች

ውስጥ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ምንም ማግኘት አትችሉም። ለምን? አስቀድመን እንደገለጽነው፣ እግዚአብሔር

ለሕዝቡ የሰጣቸው የጤና ሕጎች በጊዜያቸው እጅግ የላቁ ነበሩ።

ለምሳሌ በመካከለኛው ዘመን አውሮፓ በ"ጥቁር ሞት" ተጨነቀች። ወረርሽኙ ከአራት ሰዎች አንዱን ገደለ፣ ማንም

እንዴት እንደሚያቆመው አያውቅም ነበር ምክንያቱም እንደ ዛሬው ጌዜ ማይክሮባዮሎጂ እንኳን መረዳት

አለመቻላቸው ነበር። ምን እንዳዳናቸው ታውቃለላችሁ፤ መጽሐፍ ቅዱስ ነው፡፡ በመጨረሻ ወደ ቅዱሳት መጻሕፍት

በተለይም ዘሌዋውያን 13፡46 ላይ ደዌው ባለበት ዘመን ሁሉ ርኩስ ይሆናል፤ እርሱ ርኩስ ነው፤ ብቻውን ይቀመጣል፤

መኖሪያውም ከሰፈር በውጭ ይሆናል።" የታመሙትን ከካምፑ ገለል ማድረግ አስፈላጊ መሆኑን ከመጽሐፍ ቅዱስ

ተምረዋል።
ጤናችንን እንዴት መጠበቅ እንዳለብን መጽሀፍ ቅዱስ ግልጽ መመሪያ ይሰጣል፡፡ የእግዚአብሔር መድሃኒት ከፈውስ
ይልቅ መከላከል ላይ እንደሚያተኩር ታውቃላችሁ? መጽሐፍ ቅዱስ አካላዊ ጤንነት ላይ ብቻ ሳይሆን ስሜታዊ፣
ማህበራዊና በተለይም መንፈሳዊ ጤንነታችንን እንዴት መንከባከብ እንዳለብን ግልጽ መመሪያ ይሰጣል፡፡
ምን ይመስላችኋል!

Conclusion

ማጠቃለያ

ውድ ወጣቶች፣ እግዚአብሔር ጤናማ እንድትሆኑ እና ያንን የጤንነት መንገድ በከተማችሁ እንድታጋሩ ይፈልጋል።

የእግዚአብሔር መድሀኒት ከመፈወስ ይልቅ መከላከል እንደሆነ እወቁ፡፡ ጠንካራና እና ሚዛናዊ ህይወት እንድትኖሩ

የሚያግዙ ስምንት ተፈጥሯዊ ምክሮችን ትቶልናል። ምን እንደሆኑ ማወቅ ትፈልጋላችሁ? ወደፊት (FORWARD)

ከሚለው ምህፃረ ቃል ጋር የተያያዙ ናቸው!

• Fresh ንፁህ አየር፡ ሰውነትን በንጹህ አየር ማጥለቅለቅ፣ በቀን ውስጥ ጥልቅ የሆነ ትንፋሽ መውሰድ

ወይም አየርን በሚገባ ማስገባት። በምትተነፍሰው ንጹህ አየር፣ የበለጠ ጉልበት ይኖርሃል።

• One’s Control ራስን መቆጣጠር፡ ሰዎች ራሳቸውን መቆጣጠር ባለመፈለጋቸው ትምባሆ፣ አልኮል፣ ካፌይን

እና ሱስ የሚያስይዙ ንጥረ ነገሮችን መለማመድ ይጀምራሉ። መሻትን መግዛት ከብዙ ነገሮች ለመከልከል

ያግዛል፡፡ ሁሉን በልክ ማድረግና ሚዛናዊነት መልካምና ጠቃሚ ነው።


24
• Rest እረፍት፡ በቂ እንቅልፍ መተኛት አስፈላጊ ነው፡፡ ማለትም ከሰባት እስከ ስምንት ሰአታት ጥሩ አየር

ባለው ክፍል ውስጥ መተኛት ማለት ነው። ሕይወታችሁ በስራ እና በእረፍት መካከል ሚዛን እንዲጠብቅ

አድርጉ።

• Water and Workout ውሃ እና የአካል ብቃት እንቅስቃሴ - ውሃ፣ ውሃ እና ተጨማሪ ውሃ መረሳት

የሌለበት ነገር ነው። በጤንነት ለመቆየት በጣም ጥሩው መጠጥ ውሃ ነው። በቀን ከስድስት እስከ ስምንት

ብርጭቆዎች እንዲጠጣ ይመከራል፡፡ እንዲሁም. በየእለቱ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ በማድረግ ሰውነታችሁን

ማጠንከር አለባችሁ፡፡ ከተቻለ እንቅስቃሴው ከቤት ውጭ ቢሆን ይመከራል። ግማሽ ሰዓት ያህል ትንሽ

የእግር ጉዞ ማድረግ ጥሩ ጅምር ነው። ወገኖቼ ተንቀሳቀሱ!

• Accepting God’s Will የእግዚአብሔርን ፈቃድ መቀበል፡- መንፈሳዊ ህይወታችሁን አትርሱ። በእግዚአብሄር

ማመን እና መታመን ጤናችሁን ያበለጽጋል፤ ደስታንም ያመጣል፡፡ በተጨማሪም ፍቅርን እና ተስፋን በማዳበር

ከቤተሰቦቻችሁ ጋር ጊዜ ስታሳልፉ የእግዚአብሔር ፈቃድ ስለምትፈጽሙ በጤንነታችሁ ላይ አዎንታዊ ተጽዕኖ

ይኖረዋል።

• Right Nutrition ትክክለኛ አመጋገብ፡ ጤናማ ምግቦችን መመገብ አስፈላጊ ነው፡፡ ከሁሉም አስፈላጊ ንጥረ

ነገሮች እና ፋይበር/አሰርን ያካተቱ ምግቦችን ተመገቡ። ይሄ አካላችሁን በጥሩ ሁኔታ ለመጠበቅ ቁልፍ ነገር

ነው።

• Daylight የጸሐይ ብርሃን፡- ትንሽ የፀሀይ ብርሀን ስሜትን ከፍ በማድረግ እና ጥንካሬን ይጨምራል። ግን

በመጠኑ መሆን አለበት፣ ከመጠን በላይ የፀሐይ መጋለጥ ጎጂ ሊሆን ስለሚችል ነው፡፡ የጸሐይ ብርሃንን

ለማግኘት ጠዋት ላይ ቢሆን ይመረጣል።


ስለዚህ ወገኖች በነዚህ የጤና ምክሮች እየተደገፍን ወደፊት እንራመድ፡፡ አካላችሁን በጤንነት ጠብቁ፡፡

25
6 ኛ. ቀን
ጥርጣሬ እንዲያታልላችሁ አትፍቀዱ
የማነቃቂያ ንግግር
በማሪያ ማንደርሶን
ትርጉም በፓስተር ተስፋዬ ሽብሩ

የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅስ - ያዕቆብ 1፡5-6

የትንሣኤ ምሽት ነበር። አስሩ የኢየሱስ የቅርብ ወዳጆች በአንድ ክፍል ውስጥ በፍርሃት ተሰባስበው ነበር...

ይሁዳ አስቀድሞ ራሱን አጥፍቷል፡፡ ዲዲሞስ በመባል የሚታወቀው ቶማስም በዚያ አልነበረም። መጽሐፍ

ቅዱስ ቶማስ ለምን እንደጠፋ አይናገርም ነገር ግን አሥሩ ብቻ እንደሆኑ እናውቃለን። ኢየሱስን ከገደሉት

ሰዎች መካከል አንዳንዶቹ እነርሱንም ለመግደል ሊመጡ እንደሚችሉ በሩን ዘግተው ነበር። ብቸኝነት

ተሰምቷቸው፣ ግራ ተጋብተው፣ ተጨንቀው .... እና ጥርጣሬ ወደ ልባቸው ዘልቆ መግባት ጀምሮ ነበር።

ተሳስተው ቢሆንስ? ኢየሱስ ሐሰተኛ ቢሆንስ? በድንገት ኢየሱስ በመካከላቸው ተገለጠ። የተዘጋው በር

ኢየሱስን ከውጪ ሊያስቀረው አቅም አልነበረውም፡፡ ከዚያም በፊታቸው ቆመ። ከተወሰነ ጊዜ በኋላ ደቀ

መዛሙርቱ የሆነውን ነገር ለቶማስ ነገሩት፣ ተጠራጣሪው ቶማስ ግን የማምነው በኢየሱስ የእጆቹን ቁስል

አይቶና እጆቹን በጎኑ ቁስሉ ውስጥ ካስገባ ብቻ እንደሆነ ተናገረ። ከተወሰነ ጊዜ በኋላ ሁሉም እንደገና

አብረው በነበሩት ኢየሱስ ተገለጠላቸው። በዚህ ጊዜ ግን ኢየሱስ ትኩረቱን በቶማስ ላይ አደረገ። ኢየሱስ

በእርጋታ እንዲህ አለው፡- “ጣትህን አምጣና እጆቼን እይ፤ እጅህንም አምጣና በጎኔ አግባው። ያመንህ እንጂ

ያላመንህ አትሁን።” አለው፡፡ ዮሐ 20፡27 ወገኔ አንተስ ቶማስ ነህን? ማስረጃውን ማየት አለብህ?

ተጠራጣሪዎች ብዙ ጊዜ እንዳይታለሉ ይፈራሉ እና ከዚህም የተነሳ አብዛኛውን ጊዜ ሐቀኛ ያልሆኑ


ሰዎችን ያውቃሉ፡፡ ስለዚህም እንዲህ አይነት ሰዎች ክርስቲያኖችን ይጠራጠራሉ። መጽሐፍ ቅዱስን
ለማያምኑ ሰዎች ስናካፍል ሐቀኛ መሆን በጣም አስፈላጊ ነው። ከላይ ባለው ክስተት ቶማስ ስለ ስሜቱ
በጣም ታማኝ እንደነበረ እናያለን።

በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ያለውን ሌላ ምሳሌ እንመልከት፣


ዮሐንስ 6:42 “አባቱንና እናቱን የምናውቃቸው ይህ የዮሴፍ ልጅ ኢየሱስ አይደለምን? እንግዲህ ‘ከሰማይ
ወርጃለሁ’ እንዴት ይላል?”

እዚህ ላይ ጥያቄውን የሚጠይቁት ሰዎች ለመጠራጠር በቂ ምክንያቶች እንደነበሯቸው እናያለን፡፡ ነገር ግን


እንደ ብዙዎቹ ተጠራጣሪዎች ሁሉ የራሳቸውን ጥያቄ ይመልሳሉ፡፡ ከእንደዚህ አይነት ሰዎች ጋር በምትገናኝበት
ጊዜ ትክክለኛ መልስ ልትሰጣቸው ይገባል፤ ምክንያቱም በእግዚአብሔር እና በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ በጣም
ጠንካራ አስተያየት እና እምነት አላቸው። እውነቱን እንደሚያውቁ ያምናሉ። ይህን አስተሳሰብ አንዳንድ
ጊዜ ለመድረስ በጣም አስቸጋሪ ነው፡፡

26
እንዲያውም የኢየሱስ ደቀ መዛሙርትና የቅርብ ወዳጆቹ አንዳንድ ጥርጣሬዎች አጋጥሟቸዋል። ክርስቶስ

ከሞት ከተነሳና ደቀ መዛሙርቱን በገሊላ ካገኛቸው በኋላም “አንዳንዶች ተጠራጥረው” እንደነበረ

እናነባለን። እነዚህን ሰዎች በወንጌል ለመድረስ እንዴት እና ምን እንደምትሏቸው እግዚአብሔር በትክክል

እንዲያሳያችሁ መጸለይ ያስፈልጋችኋል። ማስረጃውን ማየት አለባቸው።

ጸሎት፡-

ውድ የሰማይ አባት፣ ስለ ምሕረትና ርህራሄህ እናመሰግንሃለን። አሁንም ቢሆን እምነት ስላለን

እናመሰግንሃለን፡፡ ነገር ግን ይበልጥ በአንተ እንድናምን እና በአንተም እንድንታመን እርዳን። በምንጠራጠርበት

ነገር አቤቱ አለማናችንን እርዳው።

" ለሚጠራጠሩት እዘንላቸው።" —ይሁዳ 1:22

6 ኛ. ቀን ስብከት

በከተማችሁ ተስፋ መቁረጥን መጋፈጥ

በፓስተር ኤስ ዩሪ ፌሬራ

ቆላ 1፡27

መግቢያ

በአንድ ትልቅ ከተማ ውስጥ ያደገውን ጆን የተባለ ወጣት በዓይነ ሕሊናህ እንድትመለከቱ ልጋብዛችሁ።

ከልጅነቱ ጀምሮ ከከተማ ሕይወት ጋር የሚመጡትን ተግዳሮቶች አጣጥሟል። ወላጆቹ ኑሯቸውን

ለማሟላት ሲሉ ብዙ ሰአታት ይሰሩ ነበር፡፡ ነገር ግን ፍላጎታቸውን ለማሟላት ብዙ መስራት የግድ ስለነበር፣

ሁልጊዜ በርሱ ሕይወት ውስጥ ሊኖሩ ወይም ስፍራ ሊሰጡት አልቻሉም።

ጊዜ እያለፈ ሲሄድ ዮሐንስ ወደ ጎረመሰ እና ጭካኔ የተሞላበት የከተማው ጫና ይሰማው ጀመር።

በሚማርበት ትምህርት ቤት የክፍልል ውድድሩ በጣም ከፍተኛ ነበር፡፡ በውጤት በልጦ ለመገኘት የነበረው ትግል

በጣም ከፍተኛ ነበር፡፡ ለማጥናት ጥረት ቢያደርግም አንዳንድ ጊዜ ግን ከሥራው ጫና እና ወላጆቹ

በሚጠብቁት ነገር የተነሳ ይጨነቅ ነበር። በዚያች ከተማ ውስጥ በእርግጥ ለእሱ የወደፊት ዕድል ይኖር

እንደሆነ አሰበ።

27
በእሱ ማህበረሰብ ውስጥ፣ የደህንነት ጉዳዮች የዕለት ተዕለት ክስተቶች ነበሩ፡፡ መዝረፍ እና ማጭበርበር

የተለመዱ ነበሩ፣ እናም ጆን ከትምህርት ቤት ሲመለስ በጨለማ እና በማይመቹ መንገዶችን ማለፍ

ነበረበት። ደህንነት አልተሰማውም፡፡ ይህም የበለጠ ብቸኝነት እና ተስፋ መቁረጥን አስከትሎበታል፡፡

ጆን እያደገ ሲሄድ ጓደኞቹና አብረውት የሚማሩት ልጆችም ተመሳሳይ ችግሮች እያጋጠሟቸው እንደሆነ

ተገነዘበ። ብዙዎቹ በትምህርት ቤት ውጥረት በኢኮኖሚያዊ ችግሮች እና በከተማው ውስጥ ግልጽ የሆነ

እቅድ አለመኖሩ ትግል ውስጥ ከቷቸዋል፡፡ ከጭንቀት አዙሪት መላቀቅና ብሩህ የሕይወት ገጽታ ሊያገኙ

እንደሚችሉ ይፈልጋሉ።

የትምህርቱ ዋና ሐሳብ

በከተሞች ውስጥ ያለው ተስፋ ማጣት በዓለም ዙሪያ ያሉ ሰዎችን ይነካል፡፡ በመሰረቱ ነገሮች ለመሻሻል

ምንም እድሎች እንደሌሉ እንዲሰማቸው እያደረገ ነው፡፡ ይሄ ደግሞ ከበርካታ ምክንያቶች ጋር ሊዛመድ

ይችላል።

• የኢኮኖሚ አለመመጣጠን፡- በከተሞች ውስጥ ላለው ተስፋ ማጣት በጣም ጠንካራ አስተዋፅዖ ካደረጉት

አንዱ የኢኮኖሚ አለመመጣጠን ነው። በከተማው ውስጥ ባሉ የተለያዩ ቡድኖች ሀብት እና የኑሮ ሁኔታ

መካከል ሰፊ ልዩነት ያለ መሆኑ አነስተኛ ገቢ ያላቸው የመሻሻል እድሎች እንደሌላቸው ይሰማቸዋል።

• የስራ እጦት፡- ከተማዎች የወደፊት ተስፋን የሚፈልጉ ሰዎችን ለስራ ፍለጋ ሰዎችን ይስባሉ፣ ነገር ግን በቂ

ስራ በማይኖርበት ጊዜ በርካቶች በኢኮኖሚ ችግር ውስጥ ይወድቃሉ፡፡ ይህም የተስፋ እጦትን ይጨምራል።

• የቤት እጦት፡ የመኖሪያ ቤት ኪራይ ውድነት ወይም ጥሩ መኖሪያ ቤት ውስጥ መኖር አለመቻል ለተስፋ

ማጣት ትልቅ ምክንያት ሊሆን ይችላል። አስተማማኝ እና ቋሚ የሆነ የመኖሪያ ቦታ ከሌለ ሰዎች ምንም
ዋጋ እንደሌላቸው ራሳቸውን ይቆጥራሉ፡፡
• የጸጥታ እጦት እና ወንጀል፡- በከፍተኛ የወንጀል ደረጃ ወይም በከተማው ውስጥ ከሚታየው ለጥቃት

መጋለጥ የተነሳ የመረጋጋት ስሜት ማጣት ለተስፋ መቁረጥ አስተዋጽኦ ያደርጋል። አንዳንድ ጊዜ፣

የእስረኝነት ስሜት ይሰማችኋል፡፡ በመሆኑም አዳዲስ እድሎችን ለመሞከር ትፈራላችሁ።

በከተማ ውስጥ ያለውን ተስፋ ማጣት ማሸነፍ ይቻላል? ተስፋስ ከየት ማግኘት እንችላለን? “ተስፋ” የሚለው ቃል

በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ብዙ ጊዜ የተጠቀሰ ሲሆን በእምነት ውስጥ ያለውን ጠቀሜታና ከአምላክ ጋር ያለንን

ግንኙነት የሚያጎላ ተደጋጋሚ ጭብጥ ነው።

28
ሮሜ 15:13 "የተስፋ አምላክ በመንፈስ ቅዱስም ኃይል በተስፋ እንድትበዙ በማመናችሁ ደስታንና ሰላምን ሁሉ

ይሙላባችሁ።" ዕብራውያን 11:1 ፡- “እምነትም ተስፋ ስለምናደርገው ነገር የሚያስረግጥ፣ የማናየውንም ነገር
የሚያስረዳ ነው፡፡”
መዝ 42:11 "ነፍሴ ሆይ ለምን ታዝኛለሽ? ለምንስ ታውኪኛለሽ? የፊቴን መድሃኒት አምላኬን አመሰግነው ዘንድ

በእግዚአብሔር ታመኚ፡፡”

ኤርምያስ 29:11፣ “ለእናንተ የማስባትን ሐሳብ አውቃለሁና፤ ፍጻሜና ተስፋ እሰጣችሁ ዘንድ…”

1 ኛ የጴጥሮስ መልእክት 1:3 " ኢየሱስ ክርስቶስ ከሙታን በመነሣቱ ለሕያው ተስፋና ለማይጠፋ፥ እድፈትም

ለሌለበት፥ ለማያልፍም ርስት እንደ ምሕረቱ ብዛት ሁለተኛ የወለደን የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አምላክና አባት

ይባረክ"

እነዚህ ጥቅሶች ተስፋን በተሻለ ሁኔታ እንድንረዳ ይረዱናል። ተስፋ በማዕበል መካከል ጸንተን እንድንኖር የሚረዳን

እንደ መልሕቅ ያለ አጽንቶ መያዣ ነው። አንድ መርከብ ከመንገድ ለመራቅ መልህቅ እንደሚያስፈልገው ሁሉ እኛም

ተስፋን ለመጠበቅ የሚከተሉትን ሦስት እውነቶች እንፈልጋለን።


Truth #1: The Bible - The Book of Hope:

1 ኛ. እውነት - መጽሐፍ ቅዱስ - የተስፋ መጽሐፍ፡-

ሮሜ 15፡4 “በመጽናትና መጽሐፍት በሚሰጡት መጽናናት ተስፋ ይሆንልን ዘንድ አስቀድሞ የተጻፈው ሁሉ

ለትምህርታችን ተጽፎአልና፡፡ ይለናል። መጽሐፍ ቅዱስ የተስፋ ውድ ሀብት ነው። መጽሐፍ ቅዱስ

ተግዳሮቶችን እና መሰናክሎችን በገጠሟቸው ነገር ገን ተስፋን ባደረጉና መለኮታዊ እርዳታ በበዛላቸው

ሰዎች ታሪኮች የተሞላ ነው፡፡ እግዚአብሔር በአስቸጋሪ ጊዜያት ውስጥ በተስፋ የሚሞላን ሲሆን ተስፋዎችን

እና የማበረታቻ ቃላትን በመስጠት በመጽሐፍ ቅዱስ በኩል ተናገረን።

በእግዚአብሔር ቃል ውስጥ ተስፋ፣ መመሪያ እና መጽናኛ ለማግኘት ጥናታችሁ ወጥነት ያለው መሆን

አለባችሁ። ባለቻችሁ ትርፍ ጊዜ ብቻ ብቻ እያነበባችሁ ሌላ ጊዜ የምትተዊት መሆን የለባችሁም፡፡ በየቀኑ

ቃሉን በጸሎት ማንበብ እና ማጥናት ይገባል። የዕለት ተዕለት ልማድ መሆን አለበት፡፡ በተጨማሪም፣

በአስቸጋሪ ጊዜያት ውስጥ እያለፉ ያሉትን ለማነቃቃት እና ለማበረታታት የመጽሐፍ ቅዱስን የተስፋ

ታሪኮች ለሌሎች ማካፈል ይገባል።

2 ኛ. እውነት - ኢየሱስ የክብር ተስፋ፡

ቆላስይስ 1፡27 “ለእነርሱ እግዚአብሔር በአሕዛብ ዘንድ ያለውን የዚህ ምስጢር ክብር ባለ ጠግነት ምን
እንደሆነ ሊያስታውቅ ወደደ፤ ምስጢሩም የክብር ተስፋ ያለው ክርስቶስ በእናንተ ዘንድ መሆኑ ነው፡፡”

ኢየሱስ የመጨረሻው የተስፋ ምንጭ ነው እናም መለኮታዊ ክብርን ይወክላል። የእርሱ ህይወት፣ ሞት እና
29
ትንሳኤ ከእግዚአብሔር ጋር የመታረቅን እና የዘላለም ህይወት ተስፋን ይሰጠናል። በኢየሱስ ማመን

ህይወታችንን ይለውጣል፡፡ ከዚያም በእርሱ ዘላለማዊ ክብር የማግኘት ተስፋ ይሞላናል።

ይህን ተስፋ ለመጠበቅ፣ በጸሎት እና በማሰላሰል፣ በህይወታችን ውስጥ የእርሱን ተስፋ እና የመለወጥ ሐይል

በመለማመድ ከኢየሱስ ጋር ግላዊ ግንኙነትን ማዳበር በጣም አስፈላጊ ነው።

3 ኛ. እውነት - የክርስቶስ ዳግም ምጽአት - የተባረከ ተስፋችን፡-

ቲቶ 2፡13 “የተባረከውን ተስፋ—የታላቁን የአምላካችንንና የመድኃኒታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን ክብር

መገለጥ ስንጠባበቅ” ይላል። ኢየሱስ ተመልሶ ይመጣል የሚለው ተስፋ ለአማኞች የተስፋ ምንጭ ነው።

ኢየሱስ ዘላለማዊ መንግስቱን ለመመስረት ተመልሶ እንደሚመጣ ማወቃችን በጉጉት ይሞላናል፡፡ ከዚያም

በቅድስና እና በመዘጋጀት እንድንኖር ያነሳሳናል። ይህ ተስፋ አሁን ያሉ ችግሮችን እንድንጋፈጥ ብርታት

ይሰጠናል፣ ወደፊትም በእርግጠኝነት እንድንኖር ያስችለናል።

በአስቸጋሪ ጊዜያት፣ መጽናናትን እና ጥንካሬን ለማግኘት የክርስቶስን ዳግም ምጽአት ቃል ኪዳን ሁልጊዜ

አስታውሱ።

ማጠቃለያ

መጽሐፍ ቅዱስ ማለቂያ የሌለው የተስፋ ምንጭ ይሰጠናል። ኢየሱስ የክብር ተስፋ ምሳሌ ነው፣ የክርስቶስ

ዳግም ምጽአት ደግሞ የተባረከ ተስፋችን ነው። እነዚህን እውነቶች በመቀበል እና በእለት ተእለት

ህይወታችን ውስጥ ተግባራዊ በማድረግ፣ ከሁኔታዎች በላይ የሆነ እና ከእግዚአብሔር ጋር ወደ ዘላለማዊ

ህይወት የሚመራን ተስፋ ማግኘት እንችላለን።

ዮሐንስን ታስታውሳለህ? አንድ ቀን፣ በከተማው በሚደረገው የስብከተ ወንጌል ጉባኤ ላይ የመሳተፍ እድል

አገኘ። ሰባኪው ጠንካራ ስለ መሆን፣ እድሎችን ስለ መፈለግ፣ የድጋፍ ትስስርን ስለማጠናከር እና ከኢየሱስ

ክርስቶስ ጋር ጥልቅ ግንኙነት ስለመፍጠር አስፈላጊነት ተናግሮ ነበር። የተናጋሪው ንግግሮች ሁኔታውን

የሚያሻሽልበትን መንገድ መፈለግ የጀመረውን ዮሐንስ በጥልቅ ነኩት።

ምንም እንኳን ከተማዋ አሁንም ፈተናዎች ቢኖሯትም ዮሐንስ ስለወደፊቱ ጊዜ የተስፋ ጭላንጭል ማየት

ጀመረ። በጥረት እና በትክክለኛ ድጋፍ እንቅፋቶችን ማለፍና ለተሻለ ህይወት መንገድ መጥረግ እንደሚቻል

ተገነዘበ። የዮሐንስ ታሪክ የሚያስገነዝበን በጣም አስቸጋሪ በሆኑት ከተሞች ውስጥ እንኳን፣ ተስፋ እና የግል

እድገት ማግኘት የሚቻለው ከጌታ ድጋፍን በማግኘት እና የክብር ተስፋ ለሆነው ለኢየሱስ ልባችሁን

ስትከፍቱ እንደሆነ ነው።

30
31

You might also like