Professional Documents
Culture Documents
ማንዋል
ማንዋል
መግቢያ
የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና ተቋም ሥራ አጥነትን ከማስወገድ አንጻር ያለዉ ሚና እጅግ ጉልህ ከመሆኑ በተጨማሪ
የጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞችን ድጋፍ የሚሰጠውም ሆነ ለመካከለኛና ከፍተኛ ተቋሞች የሚያስፈልገው ብቃት ያለው
የሰለጠነ የሰው ኃይል የሚመነጨውም ከዚሁ ከቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና ሥርዓቱ እንደሆነ የተቀረጹ የልማት
ስትራተጂዎቻችን ያስቀምጣሉ። የስትራቴጂው ግቦችም በሃገሪቷ ብቁ የሰለጠነ የሰው ሀይል በማፍራት እና በኢንዱስትሪ
ኤክስቴንሽን አገልግሎት የጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞችን ተወዳዳሪነት በማሳደግ ድህነትን ከሀገራችን ማስወገድና
ለማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እድገት አስተዋጽኦ ማድረግ ናቸው። ከዚህ ጋር በተያያዘ በከተማም ሆነ በገጠር ለሚገኙ ሥራ አጥ
ዜጎች የሥራ ገበያ ፍላጎትን መሰረት ያደረገ አጫጭር ሥልጠና በመስጠት ሰፊ የሥራ ዕድል መፍጠር ከሚተኮርባቸው ዋነኛ
ግቦች አንዱ ነው።
የትኛዉም የቴክኒክና ሙያ ትምህርት ማሠልጠኛ ተቋማት ከተወዳዳሪዎቹ ልቆ እንዲገኝ ከሚያደርጉት ነገሮች ዋነኞቹ በቂ
ቴክኒካል ክህሎትና የኢንተርፕሪነርሽፕ ባህሪይ የተላበሰ የሰው ሐይል እንዲሁም ምርጥ ቴክኖሎጂና የጥራትና ምርታማነት
ማሻሻያ አሰራር ሲኖር ነው፡፡ ይህ አሰራር ከሌለ በስተቀር ማንኛውም አይነት ግብአት፣ መሰረተ ልማትና ዘመናዊ አደረጃጀት
ቢኖርም ለትርፋማነትና ለተወዳዳሪነት ሊያበቁ እንደማይችሉ የተለያዩ የጥናት ውጤቶች ያመለክታሉ።
በጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ልማት ስትራቴጂ ላይ በግልጽ እንደሚታየው ጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞችን
ለማልማት ከተቀመጡት የድጋፍ ማእቀፎች ውስጥ አንዱ ለኢንተርፕራይዞቹ ብቃት ያለው የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን
አገልግሎት መስጠት ነው። ይህ አገልግሎት የጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞችን ችግር በፍላጎት ላይ ተመስርቶ ክፍተትን
የለየና የተሟላ መረጃ የማደራጀትና ስልጠናና ምክር፣ የቴክኖሎጂ ልማት፣ ምርጥ ተሞክሮ ቅመራና ማስተላለፍን የሚያካትት
ድጋፍ ነው፡፡
በኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን ትግበራው ሂደት የተገኙ ምርጥ ተሞክሮዎችን ቀምሮ በማስፋት የአገልግሎቱን
ተደራሽነት በማረጋገጥ ኢንተርፕራይዞቹን ወደሚቀጥለው የዕድገት ደረጃ ለማሸጋገር እንዲቻል
በመሆኑም የጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ተወዳዳሪነታቸውንና ምርታማነታቸውን አሁን ካለበት ደረጃ በተሻለ ሁኔታ
ለማሳደግ እንዲቻል ይህ የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽንና ቴክኖሎጂ ሽግግር አገልግሎት ድጋፍ ማስተግበሪያ ማንዋል
ተዘጋጅቷል፡፡
አገራችን እየተከተለች ያለችው ከግብርና መር የኢኮኖሚ ስርአት ወደ ኢንዱስትሪው ክፍለ ኢኮኖሚ ለሚደረገው ሽግግር
የመሪነቱን ሚና እንደሚይዝ ታሳቢ ተደርጎ እንቅስቃሴ በመደረግ ላይ ይገኛል፡፡
3. የቴክኖሎጂ ድጋፍና
3. የቴክኖሎጂ ድጋፍ፡- ይህ ድጋፍ የሚደረገው ደግሞ ለአገራችን ነባራዊ ሁኔታ የሚስማማውንና ተመርጦ
መቶ ፐርሰንት የተቀዳውን ቴክኖሎጂ በመውሰድ ውጤታማ የቴክኖሎጂ አብዢዎች እንዲሆኑና በቴክኖሎጂ
ሽግግር ስራ ብቁ ተዋናኝ እንዲሆኑ ለማስቻል ነው፡፡
የጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ዘመናዊ የሂሳብ አያያዝ ስርዓትን እንዲተገብሩ በማድረግ ትርፋማነታቸውን
እንዲጨምሩ ማስቻል፣
ጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች የገበያ ልማት እውቀትና ክህሎት እንዲያዳብሩ በማገዝ በገበያ ላይ በምርት
ጥራት፣ ዋጋና አቅርቦት ተወዳዳሪ እንዲሆኑ ማስቻል፣
2. የቴክኖሎጂ አቅምን መገንባት ለኢኮኖሚ እድገት ቁልፍ መሳሪያ መሆኑን አምኖ መተግበር፤
“ የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን አገልግሎት ድጋፍ ማለት የጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞችን ችግር በፍላጎት ላይ ተመስርቶ
የለየና የተሟላ መረጃ የማደራጀትና የመስጠት፣ ስልጠናና ምክር፣ የቴክኖሎጂ ልማት፣ ግብይት፣ ምርጥ ተሞክሮ ቅመራና
ማስተላለፍን የሚያካትት ድጋፍ ነው፡፡”
የካይዘን (KAIZEN) አስተሳሰብ የተጀመረውም ሆነ በስፋት ስራ ላይ የዋለው በጃፓን ሲሆን የተገነባውም ከሁለት የጃፓን
ቃላት ነው፡፡ እነርሱም ካይ (KAI) እና ዘን (ZEN) ናቸው፡፡ ካይ ማለት ለውጥ ማለት ሲሆን ዘን ማለት ደግሞ መልካም
(ጥሩ) ማለት ነው፡፡ አጠቃላይ የቃሉ ፍቺም የማያቋርጥ መልካም ለውጥ በሚለው የአማርኛው ቃል ሊመነዘር ይችላል፡፡ ይህ
የማያቋርጥ መልካም ለውጥ በአንድ ድርጅት/ተቋም ውስጥ በሚከናወነው የእለት ተእለት የስራ እንቅስቃሴ በምርቱና
በአገልግሎቱ የሚታይ ይሆናል፡፡
የጥራትና ምርታማነት ማሻሻያ ድጋፍ አገልግሎት መነሻ የሚያደርገው በአገሪቱ የሙያ ደረጃዎች ላይ
በተቀመጡት የካይዘን /የጥራትና ምርታማነት ማሻሻያ/ የብቃት አሀዶችና በነዚህ ስር ባሉ ዝርዝር ስራዎች ላይ
ነው፡፡
ደረጃ 1 (Level I): የአምስቱን “ማ” ዎችን የአሰራር ስርአቶች መተግበር (Apply 5s
Procedures)
ቀጣይነት ያለው የእሴት ማሻሻያ ሂደቶችን ለማጎልበት መልካም አጋጣሚዎችን ማሰስ (Explore
opportunities for further development of value stream improvement processes)
ከማሻሻያ ስትራቴጂ ጋር የሚጣጣሙ የአሰራር ስርአቶችን መገምገም (Review systems for
compatibility with improvement strategy)
የጥራትና ምርታማነት ማሻሻያ/ ድጋፍ ተግባራዊ ስናደርግ መከተል ያለብን የአተገባበር ሂደት፡-
ውጤታማ የሆነ የጥራትና ምርታማነት ማሻሻያ ስርዓትን በኢንተርፕራይዞች ስንተገብር ከዚህ በታች
የተዘረዘሩትን የአተገባበር ሂደቶችን መከተል አለብን፡፡
ካይዘን ከመተግበሩ በፊት የኢንተርፕራይዙን ነባራዊ ሁኔታ የሚገልፁ መረጃዎችን በፅሁፍ፣ በቁጥር፣
በፎቶ፣በቪዲዮና ነባራዊ የስራ ፍሰትን የሚገልፅ ንድፍ በሚገባ ማዘጋጀትና መያዝ
ከመረጃው በመነሳት ዋና ዋና ችግሮችን ከላይ ከተገለፁት ነጥቦች አንጻር መለየትና የችግሩን መንስኤ
መተንተንና ማደራጀት፣
የተለዩትን ችግሮች በምን ያህል አሁን ካለው በጥራትና ምርታማነት ፍልስፍናና መሳሪያዎች
በመጠቀም ማሻሻል እንደሚቻል ግብ ማስቀመጥ፣
ለተለዩት ችግሮች መፍቻ/መፍትሄ ሊሆኑ የሚችሉትን መሳሪያዎችና አሰራሮች መምረጥና ለድርጅቱ
በሚሆን መልኩ ማዘጋጀት፣
የተዘጋጁትን የመፍትሄ እርምጃዎች/መሳሪያዎች ተግባራዊ ለማድረግ ዝርዝር የትግበራ እቅድ
ማዘጋጀት
የተመረጠውን የመፍትሄ እርምጃ መተግበር፣
የትግበራውን አፈጻጸም ከተቀመጠው ግብ አንጻር ማወዳደር፤ ይህ ማለት ምን ያህል ሰዓት እንደ
ተሻሻለ፣ በቀን የሚመረተውን ምርት ከበፊቱ ምን ያህል እንደጨመረ፣ ምን ያህል የማምረቻ ወጪን
እንደቀነሰ፣ በምርት ጥራት የጨመረ የደንበኛ ብዛት፣ የተገኘን የቦታ ስፋትና አጠቃቀም፣ጠፍቶ የተገኘ
ንብረት፣ የጨመረ የሽያጭና የገቢ መጠን ከበፊቱ አፈጻጸም አንጻር፣ ሰራተኞቹ ምን ያህሉን ሰዓት
እሴት በሚጨምር ስራ ላይ እንደሚያሳልፉ፣ የስራ ቦታ ደህንነት በመጠበቁ የቀነሰ ወጪና ወዘተ…
ከላይ ከተገለጹት ነጥቦች በመነሳት የተገኘውን ለውጥ/ልዩነት ከበፊቱ አንጻር በማስላት ወደ ገንዘብ
መለወጥ፣
ዝርዝር ስራዎች 1 2 3 4 5
ሰራተኛው ስም
የቴክኒካል ክህሎት አቅም ግንባታ ማለት ጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች በገበያ ላይ ተወዳዳሪ እንዳይሆኑ
የሚያደርጓቸውን የክህሎት ክፍተቶችን ነቅሶ በመለየት እነዚህን ክፍተቶች ሊያስወግድላቸው የሚያስችል የአቅም
ግንባታ ስራ ነው። የተለየ የቴክኒክ ክህሎት ክፍተት ሳይኖር የክህሎት አቅም ግንባታ ፕሮግራሞችን ማቀድና
ማከናወን እንደ ብክነት ሊቆጠር ይገባል። ሰራተኛው ከፕሮግራሙ ባገኘው ክህሎት የሚያስመዘግበው
ምርታማነት ለአቅም ግንባታው ከዋለው ሀብትና በክህሎት አቅም ግንባታ ፕሮግራሞች ላይ ለመሳተፍ ከስራ
ሀ. የቴክኒካል ክህሎት አቅም ግንባታ ድጋፍ ከብቃት አሀዶችና ዝርዝር የስራ ተግባራት
ጋር የማስተሳሰር ሂደት
የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን የቴክኒካል ክህሎት ድጋፍ አሰጣጥ በአገልግሎት ተቀባዩ ምርጫ መሰረት
በአገልግሎት ሰጪ ክፍተቶቹ ከተለዩ በኋላ ከደረጃ አንድ እስከ ደረጃ አምስት በተለያዩ ሙያዎች ካሉት የሙያ
ደረጃ የብቃት አሀዶች እና ዝርዝር ስራዎች ጋር በማዛመድ ክፍተቶቹ የሚሞሉና ብቃታቸው በምዘና
የሚረጋገጥ ሲሆን ዝርዝር አተገባበሩ በሚከተለው ቅደም ተከተል ይሆናል፡
ያለንን ሀብት በአግባቡ ስራ ላይ ለማዋልና የአቅም ውስንነትን ትኩረት ውስጥ በማስገባት የክህሎት አቅም
ግንባታ ድጋፎችን በምናካሄድበት ወቅት በአካባቢያችን የትኩረት ኢንዱስትሪዎች መሰረትና
በኢንተርፕራይዞች ውስጥ ባሉ ለተወዳዳሪነት ወሳኝ በሆኑ የስራ ሂደቶች ላይ በሚያጋጥሙ የክህሎት
ክፍተቶች ላይ ማተኮር ይኖርብናል።በተጨማሪም በጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች የእድገት ደረጃ
መሰረት ትኩረት በማድረግ የአቅም ግንባታውን ማካሄድ ስልታዊ ጠቀሜታ እንዳለው ይታመናል።
የቴክኒካል ክህሎት አቅም ግንባታን ቅድሚያ አሰጣጥ ከኢንተርፕራይዞች ፍላጎትና ካለው የክህሎት ደረጃና
ከትኩረት ዘርፉ ወሳኝነትና አስፈላጊነት አንጻር ለመገምገም ይቻል ዘንድ እያንዳንዱን ስራ ከአስቸጋሪነት
/difficulty፣ ከአስፈላጊነት /importance፣ ከድግግሞሽ /frequency (DIF) አንጻር መተንተንና ቅድሚያ
የሚሰጣቸውን መወሰን ያስፈልጋል። ይህም ውስን ሀብትን በማያስፈልጉ የስልጠና ፕሮግሮሞች ላይ
እንዳናባክንና በተወሰኑ ችግሮች ላይ ብቻ በማተኮር ውጤታማ እንድንሆን ይረዳናል።
የቴክኖሎጂ አቅም ግንባታ ጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ከቴክኖሎጂ ለውጥ ጋር ተስማምተው እንዲሄዱ
የሚያስችል የማያሻማና የተቀናጀ ችሎታ/አቅም እንዲፈጥሩና እንዲያጎለብቱ የሚያድረግ የአቅም ግንባታ
ሂደት ነው፡፡ በዚህ መሰረት የኢንተርፕራይዞችን ተወዳዳሪነት ለማረጋገጥ ተፈላጊውን ቴክኖሎጂ በመለየት፣
በማግኘትና በመኮረጅ በማመሳሰልና አቅምን አዳብሮ ለማሻሻል አዋጪ የሆነ የአሰራር ስርዓት ሂደት ሞዴል
መከተል ያስፈልጋል፡፡
የእሴት ሰንሰለት ማለት የአንድን ለገበያ የሚቀርብ ምርት ከግብዓቱ ጀምሮ እስከ ፍጆታ (ጥቅም ላይ
እስክዋለበት ጊዜ) ድረስ ያሉና ለምርት አስተዋጽኦ የሚያደርጉ ነገሮች የሚቀነባበሩበት ዓላማ መር ቅደም
ተከተል ነው፡፡ የእያንዳንዱን ኢንዱስትሪ ሥራ ከግብዓት እስከ ውጤት ድረስ መዘርዘር የሚያስፈልግበት ዓላማ
በመጨረሻ ላይ የምርቱን ጥራት የሚወስኑ ነገሮች ከግብዓቱ ወይም ከአሰራሩ ወይም ሌላ ከምን እንደሆነ
ለመወሰን እንዲቻል ነው፡፡
ከላይ የቴክኖሎጂን ትርጓሜና ክፍሎቹ ላይ በመንተራስ የእሴት ሰንሰለቱ ሲተነተን የቴክኖሎጂ ክፍተቶችን
(ቁሳዊ፣ ዕውቀታዊ፣ ሰነዳዊ፣ ድርጊታዊ) ብሎ በመለየት በምርት ጥራት ላይ ችግር/ ክፍተት ያመጣውንና
ቢሻሻል ሊያመጣ ይችል የነበረውን ክፍተት መለየት አንድ ትልቁ ሥራ ነው፣ ምክንያቱም ችግርን ማወቅ
የመፍትሄው ግማሽ አካል ነውና፡፡
ለገበያ በሚቀርቡ ምርቶች ከግብዓት ጀምሮ ምርቱ ጥቅም ላይ እስከሚውልበት ድረስ ያለውን ሰንሰለት
በማጥናትና በምርት ጥራት ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ ሊያመጡ ያስቻሉትን ችግሮች/ክፍተቶች ከተለዩ ቦኋላ
የሚወሰዱ የቴክኖሎጂ አማራጮችን በዝርዝር ማየት ነው፡፡
በመሆኑም የተለያዩ አማራጮችን በመዘርዘር (ለእያንዳንዱ ዝርዝር አሰራር በመፃፍ) የመጨረሻና አማራጭ
የሆነውን ምርጥ ቴክኖሎጂ በግልጽ ማስቀመጥና የተመረጠበትን የአሠራር ዝርዝር ከሌሎቹ ጋር በአዋጭነት
መስፈርት መሰረት ማነፃፀር ያስፈልጋል፡፡
iv. አዋጭነት
የቴክኖሎጂ ክፍተቶች ያለበትን አንድ የምርት ሰንሰለት ክፍተት ከላይ በተጠቀሰው መሠረት ክፍተቱን
የሚሞሉ አማራጭ ቴክኖሎጂዎች ከተመረጡለት በኋላ የሚቀጥለው ሥራ ለተመረጠት የቴክኖሎጂ
አዋጭነት ግምገማ ማካሄድ ነው፡፡ አዋጭነት ከብዙ መንገድ የሚታይ ሲሆን ዋና ዋናዎቹ ምርታማነት፣ ጥራት፣
ጉልበትን በስፋት መጠቀምና ዋጋ ናቸው፡፡
የአንድን ምርት የዕሴት ሰንሰለት በማየትና ያለበትን ክፍተት ለመሙላት ሊጠቅሙ የሚችሉ ቴክኖሎጂዎች
ከተዘረዘሩ በኋላ የሚቀጥለው ሥራ የእያንዳንዱን አዋጭነት በመተንተን አንድ ቴክኖሎጂ መምረጥ ነው፡፡
ምርጡን ቴክኖሎጂ በመምረጥ ሂደት ውስጥ ከአዋጭነት በተጨማሪ ሌሎች መታየት ያለባቸው ነገሮት
የአሠራር ደህንነትንና የጤና ጉዳዮች ናቸው፡፡
በኢኮኖሚ ቀጠና ውስጥ ያለ የትኩረት ኢንዱስትሪን የዕሴት ሰንሰለት ትንተና ያገናዘበ ምርጥ ቴክኖሎጂን
ለማስተላለፍና ሌሎች ደረጃውን ጠብቀው እንዲሰሩት ለማድረግ ቴክኖሎጂውን ማቀብ (ማከማቸት)
ያስፈልጋል፡፡
ቴክኖሎጂ በማቀብ ሂደት ውስጥ የተመረጠውን ቴክኖሎጂ ንድፍ (Blue Print) ማዘጋጀትና ናሙና ሰርቶ
ተከታታይ ፍተሻ ማካሄድ ዋና ዋና ሥራዎቹ ናቸው፡፡ የቴክኖሎጂ ተቋማት ቴክኖሎጂ ማቀብ ዋና ስራቸው
በመሆኑ በሳይንሳዊ ትንተናና መረጃ ተመስርተው የቴክኖሎጂ ንድፍ ማዘጋጀት ይጠበቅባቸዋል፡፡ በተዘጋጀው
ንድፍ መሠረት ብቃት ያለው ናሙና ማዘጋጀት፣ የተዘጋጀውን ናሙና በተገቢው ቦታና የሥራ ምህዳር
ደረጃውን ጠብቆ ለመሠራቱ ተከታታይ የፍተሻ ሥራ ማካሄድ፣ በፍተሻ በተገኙ መረጃዎች ላይ በመመርኮዝ
ማስተካከያ/ማሻሻያ አድርጎ ማጠናቀቅ ይጠበቅባቸዋል፡፡
አንድ ቴክኖሎጂ ከተለየ፣ ንድፍ ተዘጋጅቶለት የናሙና ስራ ከተከናወነ እንዲሁም በተሠራው ናሙና ላይ የፍተሻ
ስራ ተካሄዶበት ፍተሻውን ካለፈ በኋላ ወደ ማሸጋገር ስራ ይገባል፡ ከናሙናነት አንስቶ አባዝቶ ወደ ገበያ
ለማሸጋገር በመጀመሪያ አብዢዎችን የመለየትና እነሱን የማብቃት ስራ ሊሠራና ከዛም አልፎ ቴክኖሎጂውን
ከገበያ ጋር ማስተሳሰር ይገባል፡፡
አንድ ቴክኖሎጂ የፍተሻ ስራ ከተሠራበትና ፍተሻው ካለፈ በኋላ የማብዛት ስራ ይሰራል፡፡ ቴክኖሎጂውን
ለማብዛት መጀመሪያ አብዢን መለየት ያስፈልጋል፡፡ አብዢዎችን ስንለይ ልንመለከታቸው ከሚገቡን ነገሮች
መካከል ዋንኛው የአብዢዎቹን አቅም ማወቅ ነው፡፡ የአብዢዎችን አቅም ስንል የሰው ሀይል፣ የማምረቻ
ቴክኖሎጂ፣ የገንዘብ አቅምን ከግምት ያካተተ ነው፡፡ በኢትዮጵያ ቴክኖሎጂ ሽግግር ሂደት ውስጥ የማብዛቱን
ስራ ሊሠሩ የሚችሉት የጥቃቅንና አነስተኛ ተቋማት ናቸው፡፡ ከጥቃቅንና አነስተኛ ተቋማት መካከል
የተፈተሸውን ቴክኖሎጂ ለማብዛት አቅሙ ያላቸውን መርጦ የማባዛት ስራው እንዲሰራ ማድረግ ይገባል፡፡
2. ሥራ ፈጠራ (ኢንተርፕሪነርሽኘ)
ኢንተርፕሪነር(ሥራ ፈጣሪ) ብቃትን ለመመዘን የሚያስችሉ የብቃት መመዘኛ ባህርያት አሉ፡፡ እነዚህ ባህርያት ሥራን
የማከናወን ብቃትዎን፣ የማቀድ ብቃትዎን እንዲሁም በራስ መተማመንና ሰዎችን የማግባባት ብቃትዎን በሚፈትሹ አጠቃላይ
ባህርያት ሥር ተሰባስበዋል፡፡
ሥራ ፈጣሪው ማለትም አንተርፕሪነሩ ለስራ ከመነሳቱ በፊት ማድረግ ያለበት መረጃ ማሰባሰብና ማጠናቀር ነው፡፡ መረጃ የሚገኘው
ተፈጥሮ ካደለችን የስሜት ህዋሳት ማለትም በማየት፣ በመስማት፣ በማሽተት፣ በመቅመስና በመዳሰስ በመጠቀም ነው፡፡
ግብ መጠኑ ሰፋ ያለ ጊዜን መሰረት ያደረገ እንቅስቃሴን የሚያመለክት ፅንስ-ሀሳብ ሲሆን መሪ ዕቅድ የሚለው ቃል በትክክል ይገልፀዋል፡፡
ግብና ዓላማ ትርጉማቸው እንዳይምታታና አንዱ ያንዱን ቦታ እንዳይወሰድ መጠንቀቅ ያስፈልጋል፡፡ ግብ ከፍ ላለ የጊዜ መጠን
የሚቀመጥ ሲሆን ዓላማ በጊዜ መጠኑ አነስ ይላል፡፡ ሁለቱም በ 3 ንዑሳን ክፍሎች ይከፈላሉ፡፡
የሚለካ Measurable
ግ ግብ ተጨባጭ Achievable
ምክንያታዊ Reasonable
ከዕቅድ ጓደኞች ውስጥ ሦስተኛው የማቀድና የመቆጣጠር ዘዴ የተባለው ነው፡፡ በውስጡ ደግሞ ማቀድ /Planning/እና መቆጣጠር
/Monitoring/አሉት፡፡
i. ማቀድ/ Planning/
ማቀድ/ Planning / እጅግ ቁልፍ የሆኑ ስድስት ጥያቄዎችን በማቅረብ ፕሮጀክታችን ማለትም ልንሰራው ያሰብነው ምርት ወይም
አገልግሎት በመጀመሪያ ሊመልሳቸው የሚገባቸውን መልሶች በስርዓትና በተደራጀ መልክ የምንመልስበት መሳሪያ ነው፡፡ እነርሱም፡-
የተግባር ጉድኝት ስሙ እንደሚመለከተውና በምዕራፍ አንድ እንደተጠቀሰው ያቀድነው ቢዝነስ እንዴት ወደ ገበያ እንደምናቀርበው
የምንማርበት ዘዴ ነው፡፡ በተግባር ጉድኝት (Power Cluster) ውስጥ ሁለት ጓደኛሞችን እናገኛለን፡፡ እነርሱም፡-
1 ኛ. የጀመርነውን የቢዝነስ /የንግድ ዓላማ ውጤታማ ለማድረግ ቁልፍ ሰዎችን እና የድርጅት ወኪሎችን በግንባር በማነጋገር በጓደኝነት
መንፈስ ቀርበን ልናሳምናቸው ይገባል፡፡
2 ኛ. ተከታታይነትና ዘላቂነት ያለው ታክቲክና ስትራቴጂ በመቀየስ የምርታችንን እና አገልግሎታችንን ጠቃሚነት ልንገልፅላቸው
ይገባል፡፡
3 ኛ. የንግዳችን ጤንነትና ጭድገት የተጠበቀ እንዲሆን ተደጋጋሚ ጥረት ያስፈልጋል፡፡በተለይ ንግግርን ለማድረግ ተፈጥሮ ለሁላችንም
ሁለት ነገሮችን አድላናለች፡፡እነርሱም አይናችንና እጃችንን ነዉ፡፡ ሌላው ልንጠነቀቅ የምንገባው ጤንነታችን ፣ ንፅህናችን እና አለባበሳችን
ሰዎችን የሚማርክ መሆን አለበት፡፡
የዋጋ አወጣጥ ሥልቶች፡- የተለያዩ ዓይነቶች የዋጋ አወጣጥ ሥልቶች አሉ፡፡ እነዚህም፡-
1. ወጪ ላይ ተመስርቶ ዋጋ መወሰን
ቅድመ ጥናት በማድረግ ለወደፊት ሊገዙ የሚችሉ ወይም የምርታችን ተጠቃሚ ሊሆኑ ይችላሉ የምንላቸዉን ደንበኞች መለየት አስፈላጊ
ነዉ፡፡በተጨማሪም፡
ሽያጭ መፈፀም
ደንበኛ ማለት ማንኛዉም ግለሰብ ድርጅት ወይም ተቋም የሌላዉን ምርት ወይም አገልግሎት የሚፈልግ / የሚገዛ
ማለት ነዉ፡፡
ደንበኛ ንጉስ/ንግስት መሆኑ/ን ÷ደንበኛ ከሌለ እኛም የለንም÷ምርት የመግዛት ወይም ያለመግዛት ዉሳኔ በደንበኛ እጅ
ነዉና አምራች/አከፋፋይ ድርጅት በደንበኛዉ ላይ ጥገኛ ናቸዉ የሚሉትን አባባሎች ታሳቢ ማድረግ ያስፈልጋል፡፡
ለ. የደንበኛ ባህሪያት
በቃል መገኘት
ቁርጠኝንት(Commitment)
የንድ ዕቅድ (Business Plan) ማለት አንድ ድርጅት በየጊዜዉ ምን እንደሚሠራ የት እንደሚሰራ እንዴት እንደሚሰራ
ለምን እንደሚሰራ እና ምን ዓይነት ሥልቶች ወደ ግብ እንደሚያደርሱ የሚያመለክት በወረቀት ላይ የተጻፈ መንገድ
ወይም ካርታ ነዉ፡፡
1. ገንዘብ ለማግኘት
2. ግቦችን አስቀምጦ ለመንቀሳቀስ ቢዝነስ ፕላን እንደ ካርታ ሆኖ ያገለግላል
3. የየዕለቱን ተግባራት ለመተግበር እንደ መመሪያ ሆኖ ያገለግላል
4. ችግሮችን ቀድሞ ለማየትና የፕሮጀክቱን አዋጪነት ለመገምገም በዚህም ጊዜንና ገንዘብን ይቆጥባል
5. ስለ ደንበኞችና ስለገበያው የጠለቀ ዕውቀት እንዲኖረን ያስችላል
6. ቢዝነሱን እንዴት መልቀቅ እንደሚገባን የሚያሳይ ስትራቴጂም ሊያካትት ይችላል
4.3 የንድ ዕቅድ (Business Plan) ዝግጅት
ማንኛዉም ኢንተርፕራይዝ ወይም ኢንዱስትሪ የቢዝነስ ዕቅድ ማዘጋጀቱ በይበልጥ ሥራዉን ዉጤታማ ያደርግለታል፡፡
የንግድ ዕቅድ በዉስጡ የሚይዛቸዉ ነገሮች፡-
ይህ ሥም አመሠራረት የባለቤት/ቶች ስም አድራሻ የባለቤቱ/የመሥራቹ የግል መረጃ ዕድሜ የት/ት ደረጃ ልምድ
የመነሻ ካፒታል እና አሁን ያለዉ ካፒታል የሚያመርታቸዉ የምርት ዓይነቶች የኢንተርፕራይዙ ዓይት አምራች/አከፋፋይ
የሚሉትን ያካትታል፡፡