Download as docx, pdf, or txt
Download as docx, pdf, or txt
You are on page 1of 2

የአይሲቲ ማናጀር የሁለት ወራት እቅድ

አፈፃፀም ሪፖርት
የተሰሩ ስራዎች

 የተቋሙን የአይቲ እቃዎች ዝርዝር መመዝገቢያ ዶክመንቴሽን ስርአት ተለምቶ ተዘጋጅቷል።

 የተቋሙን ድረ-ገጥ ለማልማት አስፈላጊው ስራ ተሰርቶ የተጠናቀቀ ሲሆን ባለው የሰርቨር እጥረት ምክንያት
እንዲዘገይ ተደርጓል።
 የመልቲ-ሞዳል ስርአት ልማት ላይ በመሳተፍ አስፈላጊውን ድጋፍ እና ክትትል ለማድረግ ተሞክሯል።

 የመልቲ-ሞዳል ስርአት ልማት እና ትግበራ ላይ የሚኖረውን የጊዜ እጥረት ከግምት በማስገባት የስርአቱን
መተግበሪያ በመጫን እና ኮንፊገር በማድረግ ለመለማመጃ የሚሆን ስርአት ተዘጋጅቶ የተቋሙ አይሲቲ
ባለሙያዎች እየተገለገሉበት ይገኛል።
 ተቋሙ ስርአቱን ለማስተግበር እንደ አማራጭ ወስዶት የነበረውን የንጋት ኮርፖሬት ዳታ ማእከል ብቃት
ከስርአቱ ፍላጎት ጋር በማገናዘብ የደሰሳ ጥናት በማከናወን የሪፖርት ሰነድ ተዘጋጅቶ ቀርቧል።
 ለተቋሙ ቀጣይ የስርአት ትግበራ የሚየስፈልገውን የኔትዎርክ እና የክላውድ አገልግሎት ልየታ ስራ እና የበጀት
መጠን ትመና ስራ ተከናውኗል።
 የተቋሙን የአይሲቲ ፖሊሲ ሰነድ አሁን ተቋሙ ያለበትን ሁኔታ ከግንዛቤ በማስገባት ተሰርቶ የተጠናቀቀ
ቢሆንም ተቋሙ እያደረገ ባለው የለውጥ እንቅስቃሴ ምክንያት የቀጣዩን የተቋሙን አዲስ አደረጃጀት ጋር
ሊያስኬድ የሚችል መሆኑን ማረጋገጥ በማስፈለጉ ማስፀደቅ ስራ ሳይሰራበት እንዲዘገይ ተደርጓል።

ታቅደው ያልተከናወኑ ስራዎች

 የተቋሙን የአይሲቲ እቃዎች ምዝገባ መስራት እና የዶክመንቴሽን ስርአት ማኖር

 ስርአቱ ተለምቶ መተግበሪያ ሰርቨር ባለመኖሩ የዘገየ


 የተቋሙን የድረ-ገጥ ማልማት እና ተግባራዊ ማድረግ
 ተቋሙ ባለበት የመሰረተ-ልማት እና ሰርቨሮች አለመኖር ምክንያት የዘገየ
 የተቋሙን የውሰጥ አሰራር የሚያዘምኑ ስርአቶችን ለመተግበር ጥናቶችን ማከናወን
 ለስርአት ትግበራ በዋናነት ታሳቢ የተደረገው የንጋት ኮርፖሬት ዳታ ማእከል በሙሉ አቅም መስራት
ባለመቻሉ እና የመውደቅ ችግር ያጋጠመው በመሆኑ የዘገየ

ያጋጠሙ ችግሮች
 በመልቲ ሞዳል ስርአት ልማቱ ምክንያት የታቀዱ ስራዎችን በሚፈለገው ደረጃ ለማከናወን አልተቻለም።

 ባለፉት ሁለት ወራት መሰረታዊ የሚባሉ እና ለተቋሙ አስፈላጊ የሆኑ ስርአቶችን አልምቶ ለመተግበር የታቀደ
ቢሆንም ተቋሙ ባለበት የሰርቨር እጥረት እና የመሰረተ-ልማት ዝግጁነት ማነስ ምክንያት ስርአቶቹ ተለምተው
የተዘጋጁ ሲሆን የመተግበሪያ ሰርቨር እስኪገኝ እንዲዘገዩ ተደርገዋል።
 የበላይ አመራር አካላት ካሉበት የስራ ቦታ ርቀት ምክንያት የሚያጋጥሙ የአስተዳደር ችግሮችን በቅርበት
ተወያይቶ እንዲፈቱ ለማድረግ የማያመች ሁኔታ ስለፈጠረባቸው የሚፈጠሩት ክፍተቶች በስራ ላይ ጫና
አሳድረዋል።
 በመልቲ-ሞዳል ስርአት ልማት ላይ ሃላፊነት ከወሰዱት ከንጋት ኮርፖሬት ባለሙያዎች ጋር ተቀራርቦ ለመስራት
እና እንደ ባለቤት የስራውን ዝርዝር ማወቅ ይገባኛል ስሜት ይዞ በጋራ በመተጋገዝ ለማከናወን የተደረገው
ሙከራ ባለመሳካቱ ችግሩ ስራውን በሚመሩት አመራር አካላት እንዲፈታ ቀርቧል።

You might also like