01

You might also like

Download as pdf or txt
Download as pdf or txt
You are on page 1of 12

ማኅበረ ቅዱሳን ዋና መካነድር፦ የርቀት ትምህርት ድረገጽ፦

www.eotcmk.org elearning.eotcmk.org
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን
ሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደራጃ መምሪያ
ማኅበረ ቅዱሳን

ክርስቲያናዊ ተጋድሎ
የመምህሩ ስም: መጋቤ ሃይማኖት ምትኩ አበራ
ማስተባበርያ፡ ትምህርትና ሐዋርያዊ አገልግሎት

ማኅበረ ቅዱሳን ዋና መካነድር፦ የርቀት ትምህርት ድረገጽ፦


www.eotcmk.org elearning.eotcmk.org
ክርስቲያናዊ ተጋድሎ
 መግቢያ
 ጾም
 ጸሎት
 ስግደት
 መባእ እና ምጽዋት

ማኅበረ ቅዱሳን ዋና መካነድር፦ የርቀት ትምህርት ድረገጽ፦


www.eotcmk.org elearning.eotcmk.org
መግቢያ

 ክርስቲያናዊ ተጋድሎ ማለት መንፈሳዊውን ሕይወት ከስጋዊው ሕይወት


አጣጥሞ ለመጓዝ የሚደረግ ጥረትና ትግል ማለት ነው፡፡

 አንድ ክርስቲያን ሁለት ልደታት አሉት፤


 የመጀመሪያው ከእናትና አባት የሚወለደው ሥጋዊ ልደት ሲሆን
 ሁለተኛው ከውኃና ከመንፈስ ቅዱስ

የሚወለደው ረቂቅ የመንፈስ ልደት ነው፡፡


ማኅበረ ቅዱሳን ዋና መካነድር፦ የርቀት ትምህርት ድረገጽ፦
www.eotcmk.org elearning.eotcmk.org
መግቢያ
 ጌታችን በቅዱስ ወንጌል “እውነት እውነት እልሃለሁ፥ ሰው ዳግመኛ ካልተወለደ
በቀር የእግዚአብሔርን መንግሥት ሊያይ አይችልም አለው … ከሥጋ የተወለደ
ሥጋ ነው፥ ከመንፈስም የተወለደ መንፈስ ነው” (ዮሐ. ፫፥፭) በማለት
ኒቆዲሞስን እንዳስተማረው በሥጋ ልደታችን የሥጋ ሕይወት እንዳለን ሁሉ
በመንፈሳዊው ልደታችን ደግሞ መንፈሳዊ ሕይወት አለን፡፡

 እነዚህ ሁለት ልደታት የየራሳቸው ጠባይ አላቸው፡፡


ማኅበረ ቅዱሳን ዋና መካነድር፦ የርቀት ትምህርት ድረገጽ፦
www.eotcmk.org elearning.eotcmk.org
መግቢያ…
 አንዱ ለሌላው ድጋፍ የሚሆኑበት ወቅት አለ፡፡ በሌላ ጊዜ ደግሞ አንዱ ከሌላው
ጋር የሚጣሉበት ጊዜ አለ፡፡

 ሥጋ በመንፈስ ላይ መንፈስም በሥጋ ላይ ይመኛልና፥ እነዚህም እርስ በርሳቸው


ይቀዋወማሉ፤ ስለዚህም የምትወዱትን ልታደርጉ አትችሉም” (ገላ ፭፥፲፰)

ክርስቲያናዊ ተጋድሎ ማለት እነዚህን ሁለት ሕይወቶች

አጣጥሞ ለመጓዝ የሚደረግ ጥረትና ትግል ለማለት ነው፡፡


ማኅበረ ቅዱሳን ዋና መካነድር፦ የርቀት ትምህርት ድረገጽ፦
www.eotcmk.org elearning.eotcmk.org
መግቢያ…
የኃጢአት ምንነትና ውጤቱ
 ኃጢአት ማለት ልዑል እግዚአብሔር አታድርግ ያለውን ማድረግ አድርግ
ያለውንም አለማድረግ ነው፡፡
 ለዚህ ነው ቅዱስ ጳውሎስ “ኃጢአት በሕግ ይታወቃል” (ሮሜ 3፡20)
ያለው፡፡ በሌላ አነጋገር ኃጢአት ማለት
ዓመጽ ነው ማለትም በእግዚአብሔር ላይ
 የሚደረግ ዓመጽ ነው፡፡
ማኅበረ ቅዱሳን ዋና መካነድር፦ የርቀት ትምህርት ድረገጽ፦
www.eotcmk.org elearning.eotcmk.org
መግቢያ…
 ለዚህ ነው ቅዱስ ዮሐንስ በመልዕክቱ “ኃጢአትን የሚያደርግ ዓመጽን ሁሉ
ያደርጋል፡፡ ኃጢአትም አመጽ ነው” (፩ኛ ዮሐ. ፫፥፬) ያለው፡፡

 ስለዚህም ኃጢአት ንጹሕ በሆነው የሰው ልጅ ተፈጥሮ ላይ የመጣ እድፈት ወይም


ቆሻሻ ወይም ባዕድ ነገር ነው፡፡

 ኃጢአት በሀሳብ በንግግር ወይም በድርጊት ሊሠራ ይችላል፡፡

ማኅበረ ቅዱሳን ዋና መካነድር፦ የርቀት ትምህርት ድረገጽ፦


www.eotcmk.org elearning.eotcmk.org
መግቢያ…

 በሀሳብ ማለት ሰው በልዑል እግዚአብሔር አታድርግ የተባለውን ለማድረግ አድርግ


የተባለውን ላለማድረግ በልብ ውስጥ ባለ አመጽ ኃጢአትን ሲሠራ ነው፡፡

 ከዚህ ኃጢአት ፈጽሞ መራቅ ከፍ ያለና የመጨረሻው የቅድስና ደረጃ ነው፡፡

 ሆኖም ግን በሀሳብ ያለ ኃጢአት እንዳያድግ መከላከል ተገቢ ነው::


 ምክንያቱም በሀሳብ ያለ ኃጢአት በቃለ እግዚአብሔር
ካልተገሰጸና ካልተገደበ ወደ ንግግር ኃጢአት ያድጋል፡፡
ማኅበረ ቅዱሳን ዋና መካነድር፦ የርቀት ትምህርት ድረገጽ፦
www.eotcmk.org elearning.eotcmk.org
መግቢያ…
 የንግግር ኃጢአት ቍጣ፣ ስድብ፣ የዝሙትና የመግደል ክፉ ምኞት፣ ሐሰትና
የመሳሰለው ሁሉ ነው
 ይህም በንግግር ባለበት ደረጃ ንስሓ ካልተገባበትና ለመተው ጥረት ካልተደረገ
በሥራ ወደሚገለጥ ኃጢአት ያድጋል፡፡ ሰው ኃጢአትን ከመሥራት መራቅ
ይገባዋል፡፡  ኃጢአትን አለማሰብ ቢያቅተው እንኩዋን
በሀሳብ እያለ ማቆም መልካም ነው
ማኅበረ ቅዱሳን ዋና መካነድር፦ የርቀት ትምህርት ድረገጽ፦
www.eotcmk.org elearning.eotcmk.org
መግቢያ…

 መንፈሳዊ ተጋድሎ የምንለው መንፈሳዊ ሕይወትን መኖር እንደሚገባንና


እንደምንፈልገው እንዳንኖር የሚቃወመን ኃይል ጋር የምናደርገው ትግል ነው፡፡

 ተጋድሎ የሚኖረው ተቃዋሚ ሲኖር ነውና፡፡

 ሰው ክርስቲያናዊ ሕይወትን እንዳይኖር የሚያደርጉ ሁለት መሠረታዊ ነገሮች አሉ፡፡

 እነዚህም የሥጋ ፈቃድና ሰይጣን ናቸው፡፡

ማኅበረ ቅዱሳን ዋና መካነድር፦ የርቀት ትምህርት ድረገጽ፦


www.eotcmk.org elearning.eotcmk.org
ክርስቲያናዊ ተጋድሎ

የመግቢያውን ክፍል በዚህ ፈጸምን!

በቀጣዩ የትምህርት ክፍል “ጾምን” በተመለከተ እንማማራለን...

ይቆየን!

ማኅበረ ቅዱሳን ዋና መካነድር፦ የርቀት ትምህርት ድረገጽ፦


www.eotcmk.org elearning.eotcmk.org

You might also like