Download as pdf or txt
Download as pdf or txt
You are on page 1of 3

FastMereja.

com - በአዲስ አበባ ቦሌ ቡልቡላ አቅራቢያ 300ሺህ


ነዋሪ የሚይዝ ዘመናዊ አዲስ...

facebook.com/fastmereja/posts/pfbid034EXjBaXy2Hc2TWj328LvLteehDxUwzHX7fa6V3trzR1hNS7Wus1wFqebV7MY
8Fn6l

በአዲስ አበባ ቦሌ ቡልቡላ አቅራቢያ 300ሺህ ነዋሪ የሚይዝ ዘመናዊ አዲስ ከተማ ግንባታ ተጀመረ።

#FastMereja
ኦቪድ ግሩፕ «ኦቪድ ገላን ጉራ» የተሰኘ ከተማ በአዲስ አበባ ቦሌ ቡልቡላ አቅራቢያ እየገነባ እንደሆነ የኦቪድ ሪል
እስቴት ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ፍሬው በየነ ለሚዲያ አካላት በአድዋ ሙዚየም በሰጡት መግለጫ አስታወቁ።

የኦቪድ ገላን ጉራ ከተማ ከቦሌ አየር መንገድ በስምንት ኪሜ ርቀት ላይ ከቦሌ ቡልቡላ ጀርባ 560 ሄክታር መሬት
ላይ የሚያርፍ ሲሆን ከ300ሺህ በላይ ነዋሪዎችን ተጠቃሚ የሚያደርጉ 60 ሺህ ቤቶችን የሚኖሩት ሲሆን በቂና
ዘመናዊ መሰረተ ልማቶችና የተለያዩ መገልገያዎች የተሟሉለት

አለም አቀፍ ስታንዳርድን የሚያሟላ ማራኪ የመኖሪያ የንግድና የመዝናኛ ከተማ ይሆናል ሲሉ አቶ ፍሬው
ተናግሯል።

መጋቢት 24 በከንቲባ አዳነች አበቤ በይፋ የመሰረተ ድንጋይ የተቀመጠለት 60 ሺህ ቤቶችን የያዘው የኢትዮጲያ
አዲሱ ከተማ ግራውንድ ፍሎሩ ለሰው ልጅ የሚያስፈልጉ መሰረታዊ ነገሮች ሁሉ የተሟሉለት ጂ ፕላስ 30
የሆኑ ህንጻዎች ያሉበት ሲሆን ሆስፒታሎች፣ የአምልኮ ቦታዎች፣ ስቴዲየም፣ የውሃ ፋውንቴኖችና በርካታ
የመዝናኛ አማራጮች በስፋትና በጥራት ይገኙበታል ተብሏል።

G+12 የሆኑ 600 ብሎክ ያላቸው 27 ሺህ ቤቶች ስታንዳርድ በሚለው ምድብ ውስጥ ተካተዋል። G+8 የሆኑ
በ600 ብሎኮች ውስጥ 24 ሺህ ቤቶችን የያዙትን ደግሞ ዴሉክስ የሚባሉ ሲሆን፣ ፕሪሚየም በሚል ደርጃ ስር
በ90 ብሎክ 9ሺህ ቤቶችን ይይዛል። ታውን ሃውስ የሚል ስያሜ የተሰጣቸው G+1 አና G+2 ቤቶችም
በከተማው የሚገነቡ እንደሆኑ ተነግሯል።

ኦቪድ ሪል ስቴት ሀላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር በራሱ መሬት ላይ ከሚያለማቸው ቤቶች በተጨማሪ የኦቪድ
ገላን ጉራ ፕሮጀክትን ጨምሮ ባጠቃላይ 65 ሺህ ቤቶችን ለማልማት በመስራት ላይ ያለ ሲሆን ከኢፌዲሪ
ጠቅላይ ሚኒስተር ፅህፈት ቤት ጋር የጥምረት ቤትና የጫካ ፕሮጀክትን ጨምሮ በአሁኑ ወቅት 18.5 ቢሊየን
ዶላር በላይ የሚያወጡ ፕሮጀክቶችን እያስተዳደረ ይገኛል።

ከነዚህም በተጨማሪ የ60 ሺህ ቤቶች ግንባታ የሚከናወንበት የአዲሱ ኦቪድ ገላን ጉራ ከተማ ፕሮጀክቶችን
ጨምሮ ከ4 ሺህ በላይ የቤት ልማት ፕሮጀክቶች ላይ ተሰማርቶ ይገኛል።

በተመጣጣኝ ዋጋ ቤት ለመግዛት ፍላጎት ያላቸው ግለሰቦችና ተቋማት በሽያጩ ላይ መሳትፍ ይችላሉ የተባለ
ሲሆን ከሚያዝያ 16 እስከ ሚያዝያ 20/2016 ዓ.ም ለ5 ቀን በሚቆየው መርሃ ግብር 6124 ቤቶች ምዝገባ
በአድዋ ሙዚየም ለሽያጭ መቅረባቸው ተነግሯል።

FastMereja / ጥላሁን ደሳለኝ

All reactions:

471 471

1/3
44

Like

Comment

Share

Most relevant


Write a comment…

ህልሜነህ ምዕራፍ
ኤረ ፋስት መረጃዎች እናንተ እንኳን ለከተማዋ አርሶ አደር ድምጽ መሆን ያቅታች. . .!!

አዎን ኦቪድ በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረዳ 10 ክልል ገላን ጉራ አካባቢ በ488 ሔክታር ላይ የሚያርፍ
በ70/30 የቤቶች ፕሮግራም 60ሺህ ቤቶች ለመገንባት በከተማ አስተዳደሩ ጋር ከቀናት በፊት የመሠረት
ድንጋይ ተቀምጦለታል።…
See more

4h
Like

Reply

Tam Bel
የኮንዶሚኒየም ቤት የተመዘገብነው ቀረ ማለት ነው ሁሌም አዳዲስ ፕሮጀክት ነው የምንሰማው እንጂ
ስለተመዘገበው ህዝብ የሚናገር የሚያስታውስ የለም

4h
Like

Reply

2/3
ሜስ የቅዱስጊዮርጊስ ·
Follow

ለገሀርም እንደዚ ብለው ነበር ህዝቡን ሿሿ የሰሩት አይ ብል*ግና

3h
Like

Reply

Most relevant is selected, so some comments may have been filtered out.

3/3

You might also like