Download as doc, pdf, or txt
Download as doc, pdf, or txt
You are on page 1of 21

Waldaa Manneen Barnoota Dhuunfaa Oromiya Finfiine

ተ.ቁ. ይዘት ገፅ
1 መግቢያ 2
2 አንቀፅ 1፡ መቋቋም 3
3 አንቀፅ 2፡ ስያሜ 3
4 አንቀፅ 3፡ ትርጓሜ 3-4
5 አንቀፅ 4፡ አድራሻ 5
6 አንቀፅ 5፡ አርማና ማህተም 5
7 አንቀፅ 6፡ የማህበሩ አላማ 5-8
8 አንቀፅ 7፡ አባልነት 8
8 አንቀፅ 8፡ የአባላት መብት 8
10 አንቀፅ 9 ፡የማህበሩ አባላት ግዴታ 9
11 አንቀፅ 10 ፡ አባላነት የሚቋረጥበት ሁኔታ 9
12 አንቀፅ 11፡ የማህበሩ መዋቅር 10
13 አንቀፅ 12 ፡ ጠቅላላ ጉባኤ 11
14 አንቀፅ 13፡ የጠቅላላ ጉባኤ ሥልጣንና ኃላፊነት 11-12
15 አንቀፅ 14፡ የማህበሩ የሥራ አመራር ቦርድ 12
16 አንቀፅ 15፡ የማህበሩ የሥራ አመራር ቦርድ የሥልጣን ዘመን 12
17 አንቀፅ 16፡ የማህበሩ ሥራ አመራር ቦርድ ሥልጣንና ተግባር 12-15
18 አንቀፅ 17፡ የሥራ አመራር ቦርድ አባላት ስራ ድርሻና ኃላፊነት 15
19 አንቀፅ 18፡ የሥራ አመራር ቦርድ ሊ/መንበር የሥራ ድርሻና ስልጣን 15-16
20 አንቀፅ 19፡ የምክትል ሰብሳቢ ሥልጣንና ተግባር 16
21 አንቀፅ 20፡የፀሀፊ ሥልጣንና ተግባር 16-17
22 አንቀፅ 21 ፡የውስጥ ኦዲተርና ሥልጣንና ተግባር 17-18
23 አንቀፅ 22፡ የህግ አማካሪና ጠበቃ ሥልጣንና ተግባር 18
24 አንቀፅ 23 ፡ የማህበሩ ቅጥር የፅ/ቤት ሠራተኞች 19
25 አንቀፅ 24፡ የፅ/ቤት ሥራ አሥኪያጅ ሥልጣንና ኃላፊነት 19-20
26 አንቀፅ 25፡ የሒሳብ ሠራተኛ ሥልጣንና ኃላፊነት 20-21
27 አንቀፅ 26 ፡ የገንዘብ ያዥ ሥልጣንና ተግባር 21
28 አንቀፅ 27፡ የግዢ እና ንብረት አስተዳደር ኃላፊነትና ተግባር 21-22
29 አንቀፅ 28፡ የዕቃ ግምጃ ቤት ኃላፊነትና ተግባር 22
30 አንቀፅ 29፡ የአይሲቲ ባለሙያ ሀላፊነትና ተግባር 22-23
31 አንቀፅ 30፡ የጥበቃ ሠራተኛ ኃላፊነትና ተግባር 23
32 አንቀፅ 31፡ የፅዳት ሠራተኛ ኃለፊነትና ተግባር 24
33 አንቀፅ 32 ፡ የቅርንጫፍ ማስተባበሪያ ማዕከላት ኃላፊነትና ተግባር 24
34 አንቀፅ 33፡የጠቅላላ ጉባኤ የስብሰባና የምርጫ እና የውሳኔ አሰጣጥ ሥነ ሥርዓት 25
35 አንቀፅ 34 ፡ የሥራ አመራር ቦርድ የስብሰባ ምልዐተ ጉባኤ እና ውሳኔ አሰጣጥ 25-26
36 አንቀፅ 35 ፡ የማህበሩ የገቢ ምንጭ 26
37 አንቀፅ 36፡ የበጀት አመት 26
38 አንቀፅ 37 ፡ የማህበሩን መተዳደሪያ ደንብ ስለማሻሻል 26
39 አንቀፅ 38፡ ስለ ማህበሩ መፍረስ 26

የኦሮሚያ የግል ት/ቤቶች ማህበር የተሻሻለ መተዳደሪያ ደንብ

ኦሮሚያ የግል ት/ቤቶች ማህበር -ፊንፊኔ


1
Waldaa Manneen Barnoota Dhuunfaa Oromiya Finfiine

መግቢያ

በ 2003 ዓ.ም ተቀርጾ በስራ ላይ ያለውን የኦሮሚያ የግል ት/ቤቶች ማህበር መተዳደሪያ ደንብ ከ 12 ዓመታት

በላይ ስራ ላይ የቆየ ሆኖ የአባላት ት/ቤቶች ብዛትም ሲመሰረት ከነበረው ከእጥፍ በላይ ያደገ እና ማህበሩም

ከተቋቋመለት ዓላማና ሀገሪቷ ካደረገችው የትምህርት ፖሊሲ ማሻሻያ አንጻር ማህበሩ በሱ ስር ባሉት አባል

ት/ቤቶች አስፈላጊውን ድጋፍ ለመስጠትም ሆነ በመንግስት እና በት/ቤቶች መካከል እንደ ድልድይ ሆኖ

ለማገልገል እና በመንግስት፣ በግል ት/ቤቶች እና በት/ቤቱ ማህበረሰብ መካከል በየጊዜው የሚታዩትን ችግሮች

በመቅረፍ የመማር ማስተማር ሂደት የተሳለጠ ለማድረግ የራሱን ድርሻ ለማበርከት በስራ ላይ ያለው

የመተዳደሪያ ደንብ ውስንነት ስለሚታይበት ማህበሩ ይህንን የመተዳደሪያ ደንብ እንዲያሻሻል አድርጓል፡፡

አንቀጽ አንድ

መቋቋም

የኦሮሚያ የግል ት/ቤቶች ማህበር አባላቱን ያለ ልዩነት ለማገልገል ትርፍ አልባ እና አገልግሎት ሰጪ ሆኖ
በ 1952 ዓ.ም በወጣው የኢትዮጵያ የፍ/ብ/ሕ/ቁ 404 እና በሲቪክ ማህበር ደንብ ቁጥር -------- አንቀጽ -------
መሰረት እንዲሁም በተሻሻለው በኢትዮጵያ ንግድ አዋጅ ቁጥር 1243/2013 አንቀጽ 24 መሰረት የተቋቋመ
ትርፍ አልባ እና አገልግሎት ሰጪ ማህበር ነው፡፡

አንቀጽ ሁለት

ስያሜ

ኦሮሚያ የግል ት/ቤቶች ማህበር -ፊንፊኔ


2
Waldaa Manneen Barnoota Dhuunfaa Oromiya Finfiine

ይህ መተዳደሪያ ደንብ በ 2003 ዓ.ም የወጣውን ደንብ ለማሻሻል የወጣ የኦሮሚያ የግል ት/ቤቶች ማህበር
የተሻሻለ መተዳደሪያ ደንብ ቁጥር 01/2016 ተብሎ ሊጠቀስ ይቻላል፡፡

አንቀጽ ሶስት

ትርጓሜ

በዚህ ደንብ ውስጥ የቃሉ አግባብ ሌላ ትርጉም የሚያሰጠው ካልሆነ በስተቀር፡-

‹ደንብ›› ማለት ፡- የኦሮሚያ የግል ት/ቤቶች የተሻሻለ ደንብ ማለት ነው፡፡


‹ማህበር›› ማለት፡- የኦሮሚያ የግል ት/ቤቶች ማህበር ማለት ነው፡፡
‹የግል ት/ቤቶች›› ማለት፡- በኦሮሚያ ክልል በፌደራሉ የትምህርት ሚኒስተር ወይም በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት የትምህርት
ቢሮ ወይም ስልጣን በተሰጠው አካል ፈቃድ ተሰጥቷቸው በትምህርት ስራ ላይ ተሰማርተው እየሰሩ ያሉ በግል ባለሀብቶች፣
በሀይማኖት ተቋማት፣ መንግስታዊ ባልሆኑ ድርጅቶች፣ እንዲሁም በህብረተሰቡ የተቋቋሙ ት/ቤቶች ማለት ነው፡፡
‹‹ት/ቤቶች›› ማለት፡- በኦሮሚያ ክልል በትምህርት ስራ ላይ ተሰማርተው ህብረተሰቡን እያገለገሉ ያሉ ከአፀደ ህፃናት/ቅድመ
መደበኛ/ ጀምሮ እስከ 2 ኛ ደረጃ ት/ቤቶች ያሉትን መንግስታዊ ያልሆኑ ት/ቤቶችን ያካትታል፡፡
‹‹አባል ት/ቤቶች›› ማለት፡- ከ 2003 ዓ.ም ጀምሮ በኦሮሚያ የግል ት/ቤቶች ማህበር በአባልነት ተመዝገበው የሚገኙ እና
ለወደፊቱም በመተዳደሪያ ደንቡ ውስጥ የተቀመጡትን መብት እና ግዴታ በማክበር በአባልነት የሚመዘገቡትን መንግስታዊ
ያልሆኑ ት/ቤቶች ያካትታል፡፡
‹የኦሮሚያ የግል ት/ቤቶች ማህበር›› ማለት፡- ከ 2003 ዓ.ም ጀምሮ በኦሮሚያ የግል ት/ቤቶች ማህበር በአባልነት
ተመዝግበው ያሉትን ት/ቤቶች እና ለወደፊቱም ለማህበሩ ደንብ እና መመሪያ ተገዢ ሆነው አዲስ አባላት
መንግስታዊ ያልሆኑ ት/ቤቶችን በማደራጀት እና በመምራት በመማር ማስተማሩ ጥራት እና ስኬት
ውጤታማነት የግል ት/ቤቶቹ የሚጠበቅባቸውን ድርሻ እንዲወጡ ለማስተባበር እና ለት/ቤቶቹ መንግስታዊ
እና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች አስፈላጊውን ድጋፍ እንዲያደርጉላቸው እና የሚያጋጥማቸውንም ችግር
በጋራ እንዲወጡ ለማስቻል የተቋቋመ ትርፍ አልባ ማህበር ማለት ነው፡፡
‹የአባልነት ምዝገባ›› ማለት፡- በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ህጋዊ እውቅና በትምህርት ስራ ላይ የተሰማሩ
መንግስታዊ ያልሆኑ የግል ት/ቤቶች በክልሉ ውስጥ በሚገኙበት ዞን፣ ከተማ መስተዳደር፣ በንኡስ ከተማ
አስተዳደር፣ በወረዳ እና በቀበሌ ተለይተው በየት/ቤቱ ደረጃ እና ሀብትነታቸው የማን እንደሆነ ተለይቶ
በአባልነት ተመዝግበው ያሉ ት/ቤቶችን እና ለወደፊቱም በአዲስ አባልነት የሚመዘገቡትን ት/ቤቶች ምዝገባን
ያካትታል፡፡
‹የአባልነት መዋጮ›› ማለት፡- በስራ አመራር ቦርድ ት/ቤት በአመት ለማህበሩ መክፈል የሚገባው በኢትዮጵያ
ህጋዊ ገንዘብ ተወስኖ የሚከፈል መዋጮ ማለት ነው፡፡
‹የማህበሩ የስራ አመራር ቦርድ››ማለት፡- በጠቅላላ ጉባኤ ስብሰባ የሚመረጡ ሆነው የኦሮሚያ የግል ት/ቤቶች
ማህበርን የሚያስተዳድሩ 7 /ሰባት/አባላት ያሉት ስብስብ ማለት ነው፡፡

ኦሮሚያ የግል ት/ቤቶች ማህበር -ፊንፊኔ


3
Waldaa Manneen Barnoota Dhuunfaa Oromiya Finfiine

‹የጠቅላላ ጉባኤ›› ማለት፡- በኦሮሚያ የግል ት/ቤቶች ማህበር ውስጥ በአባልነት ተመዝግበው ወይም የት/ቤቶች
ባለሀብቶች የሆኑ ወይም በባለሀብቱ ስም ተወክሎ በጠቅላላ ጉባኤ እንዲሳተፉ ህጋዊ ስልጣን የተሰጣቸው
ወይም በድርጅትነት በህዝብ ወይም በመንግስታዊ ባልሆኑ ት/ቤቶች የጠቅላላ ጉባኤ አባል እንዲሆኑ ህጋዊ
የውክልና ስልጣን የተሰጣቸው ተወካዮች የተካተቱበት ጠቅላላ የማህበሩ አባላት ወይም ከግማሽ በላይ
የማህበሩ አባላት የተገኙበት ጉባኤ ማለት ነው፡፡
‹ጽ/ቤት›› ማለት፡- የኦሮሚያ የግል ት/ቤቶች ማህበር ዋና መስሪያ ቤቱ ስራውን የሚያከናውንበት እና
እንደአስፈላጊነቱ የሚቋቋሙ የዞን፣ የከተማ አስተዳደር እና የወረዳ ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶችን ያካትታል፡፡

በወንድ ጾታ የተገለጸው ለሁለቱም ጾታዎች እንደተገለጸ ይቆጠራል፡፡

አንቀጽ አራት

አድራሻ

የማህበሩ ዋና ጽ/ቤት አዲስ አበባ ከተማ ቂርቆስ ክ/ከተማ ወረዳ 04 የቤ/ቁ አዲስ የፖስታ ሳጥን ቁጥር
--------------- የስልክ ቁጥር 09 0505 0887 የፋክስ ቁጥር ----------------------------ሲሆን እንደ አስፈላጊነቱ
በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በሚገኙ የዞን ከተሞች የከተማ አስተዳደሮች እና ወረዳዎች ሁሉ
ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች በተዋረድ ይኖሩታል፡፡

አንቀጽ አምስት

አርማ እና ማህተም

ማህበሩ አላማውን እና ተግባሩን የሚያመለክት አርማ እና ማህተም ይኖሩታል፡፡

አንቀጽ ስድስት

የማህበሩ አላማ

በሀገሪቷም ሆነ በክልሉ የመማር ማስተማር ሂደት የሚታዩትን ችግሮች መፍትሄ ለመስጠት፤ የሚሰጠው
ትምህርት ደረጃውን የጠበቀ፣ በሳይንስ እና ምርምር ተደግፎ ሕብረተሰቡን ለእድገት ሊያዘጋጅ በሚችል
መልኩ የተሳለጠ ትምህርት የሚሰጥበትን ሁኔታ ከሌሎች አጋር መንግስታዊ እና መንግስታዊ ካልሆኑ አካላት
ጋር በትብብር በመስራት ማህበሩ የተቋቋመለትን ዓላማ ከግቡ ለማድረስ የሚከተሉትን ዝርዝር ዓላማዎች
መርህ አድርጓ ይሰራል፡፡

ኦሮሚያ የግል ት/ቤቶች ማህበር -ፊንፊኔ


4
Waldaa Manneen Barnoota Dhuunfaa Oromiya Finfiine

1. በሀገሪቷ የተቀረጸው አዲሱ የትምህርት ፖሊሲ ላይ በመመርኮዝ የመማር ማስተማሩ ሂደት የማህበሩ አባል
ት/ቤቶች ማህበረሰብ አቀፍ ለማድረግ የሚሰጠው ትምህርት ደረጃውን የጠበቀ እና የተሳለጠ ማድረግ፣
ትምህርቱን በሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ተደግፎ የማህበረሰቡን ችግር ፈቺ ሆኖ ሀገሪቷን በመካከለኛ እድገት ካሉት
ሀገሮች ተርታ እንድትሰለፍ ለማብቃት የማህበሩን አባላት በማስተባበር የበኩሉን አስተዋፅኦ ያበረክታል፡፡
2. የመማሪያ እና የማስተማሪያ መፅሀፍትንና ቁሳቁሶችን ከአባል ት/ቤቶቹ በሚሰበሰቡ ገንዘብ እና ማህበሩ ካለው
ካፒታል በማቀናጀት የህትመት ስራን ማከናወን፣ እንዲታተሙ ማድረግና በገበያ ላይ ታትመው የሚገኙትን
በመግዛትና ከውጭ አገር በማስመጣትበተመጣጣኝ ዋጋ እና በፍትሀዊነት ለአባል ት/ቤቶች በሽያጭ
ማከፋፈል፤
3. ማህበሩ ለስራ ምቹ የሆነ ጽ/ቤት የሚሰራበት ቦታ ከኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት፣ ከኦሮሚያ ትምህርት ቢሮ፣
ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር እና ከሸገር ከተማ አስተዳደር ጋር አስፈላጊ የስራ ቅንጅት እና ትብብር
በመፍጠር ከአዲስ አበባ ከተማ እና ከሸገር ከተማ አስተዳደር የህንጻ መስሪያ ቦታ ከሊዝ ክፍያ ነጻ እንዲሰጠው
በመጠየቅ ለተግባራዊነቱም ያላሰለሰ ጥረት በማድረግ በሚፈቀድለት ቦታ ላይ ማህበሩ የተለያዩ ግንባታዎችን
የማህበሩ አባላት እና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶችን በማስተባበር የራሱን ህንጻ በመገንባት የማህበሩን
ጽ/ቤት ለአባላቱ ተደራሽ ለማድረግ ሰንቆ መስራት፣
4. በክልሉ የሚገኙ መንግስታዊ ያልሆኑ ከአፀደ ህፃናት/ቅድመ መደበኛ/ እስከ 2 ኛ ደረጃ ት/ቤቶች ድረስ ያሉትን
አባል ያልሆኑ ት/ቤቶችን አባል እንዲሆኑ ጠንክሮ መስራት የክልሉ ትምህርት ቢሮ በየአመቱ የት/ቤቶችን የስራ
ፈቃድ በሚያድስበት ወቅት በማህበሩ አባል መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ማረጋገጫ (ክሊራንስ) እንዲያቀርቡ
እንደ አንድ መስፈርት እንዲወሰድለት በማድረግ የአባል ት/ቤቶችን ቁጥር በማብዛት ጠንካራ ማህበር እና
ተጽእኖ ፈጣሪ ለመሆን ይጥራል፡፡
5. አባል ት/ቤቶችን በመወከል በሀገር አቀፍ እና በክልሉ ትምህርት ቢሮ መሪ ጉባኤዎች ላይ በመሳተፍ በግል
ት/ቤቶች ተለይተው የወጡትን ችግሮች መፍትሄ እንዲያገኙ ምክረ ሀሳቦችን ማቅረብ እስከመጨረሻው
የሚታዩትን ችግሮች ለመቅረፍ ተግቶ ይሰራል፡፡
6. ከመንግስታዊ ት/ቤቶት፣ ከሙያ ማህበራት እና ከሲቪክ ማህበራት ጋር በትብብር መስራት፡፡
7. መንግስት የግል ት/ቤትን በተመለከተ በሚያወጣው ደንብ እና መመሪያ ላይ በመገኘት የሀሳብ አመንጪነት እና
የተሳታፊነት እድል እንዲሰጠው በማድረግ በቅንጅት መስራት፡፡
8. ት/ቤቶች ተቀራርበው በጋራ በመስራት የልምድ ልውውጥ በማድረግ እንዲማማሩ ማስቻል እና በቦርዱ ጽ/ቤት
በኩል ከማዕከሉ የተመረጡና አዳዲስ ትምህርት ሰጪ እና አጋዥ ቴክኖሎጂዎችን ለግል ት/ቤቶች
የማስተዋወቅ እና የማስተላለፍ ስራን መስራት፡፡
9. የትምህርትን ጥራት ፓኬጅን ለማስጠበቅ ማህበሩ የተቋቋመበትን አላማ መሰረት በማድረግ መንግስታዊ እና
መንግስታዊ ባልሆኑ የግል ት/ቤቶች መካከል ጠንካራ ትስስር መፍጠር እና ጥሩ አብሮ የመስራት ባህል ማዳበር፡፡

ኦሮሚያ የግል ት/ቤቶች ማህበር -ፊንፊኔ


5
Waldaa Manneen Barnoota Dhuunfaa Oromiya Finfiine

10. ከአባላት ፤ ከመንግስታዊ እና መንግስታዊ ካልሆኑ ተቋማት በተለያዩ መንገድ የሚገኙትን ድጋፍ በማሰባሰብ
ለማህበሩ ስራ ማዋል፡፡
11. በወቅታዊ የትምህርት ጉዳዮች ዙሪያ አባላት በቂ ግንዛቤ እና መረጃ በየጊዜው እንዲያገኙ መስራት፡፡
12. አመታዊ ጉባዔ ልዩ ልዩ ስብሰባዎችን እና አውደ ጥናቶችን፣ የውይይት መድረኮችን ማዘጋጀት እና ለትምህርት
ሥራ ድጋፍ ሊሰጡ በሚችሉ ጉዳዮች ላይ መሳተፍ፡፡
13. ማህበሩ ትርፍ አልባ እና ለአገልግሎት ሰጪ የተቋቋመ ቢሆንም በተሻሻለው የኢትዮጵያ ንግድ አዋጅ ቁጥር 1243/2013 እና
በተሻሻለው የሲቪክ ደንብ በማይጻረር መልኩ በማህበሩ ስም ትርፍ የሚያስገኙ ድርጅቶችን በማቋቋም የማህበሩን ገቢ
በማሳደግ ጠንካራ ማህበር መፍጠር፡፡
14. ጥራት ያለውን ትምህርት ለዜጎች ለማዳረስ ማህበራዊ ሀላፊነትን መወጣት፡፡
15. በአባል ት/ቤቴች መካከል ጤናማ ያልሆነ ፉክክር እና የገበያ ውድድር እንዳይኖር ተግቶ መስራት፡፡
16. በመንግስት በኩል የሚወጡ ደንቦች እና መመሪያዎች በአባል ት/ቤቶች ተፈጻሚ እንዲሆኑ ማድረግ፣ ችግር የሚፈጥሩ ከሆነም
ከሚመለከተው ጋር በመመካከር እና በመወያየት ለችግሩ እልባት መስጠት፡፡
17. ት/ቤቶች እርስ በራሳቸው እንዲሁም በት/ቤቶች እና በመንግስት አካላት መካከል መልካም ግንኙነት እና ቅርበት
እንዲኖራቸው ማድረግ፡፡
18. የአባልነት መዋጮ፣ ከመንግስታዊና መንግስታዊ ካልሆኑአካላት በገንዘብ እና በአይነት የሚገኙ ድጋፎች በአግባቡ ተይዞ ስራ
ላይ መዋላቸውን ማረጋገጥ፡፡
19. የኢንተርኔት መረብን በመጠቀም የት/ቤቶችን የህዝብ ግንኙነት ስራዎች ለአባላቶች ተደራሽ ማድረግ፡፡
20. የትምህርትን ጥራት የሚያሳልጡ ተግባሮችን ስራ ላይ ለማዋል አስፈላጊ በሆኑ ጉዳዮች ላይ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር
በትብብር መስራት፡፡
21. ሀገራችን ትምህርትን በስፋት እና በጥራት ለህብረተሰቡ ለማዳረስ በምታደርገው ፈርጀ ብዙ ስራዎች የበኩሉን ድርሻ
መወጣት፡፡
22. የግል ት/ቤቶች ለመምህራኖቻቸው እና ለሰራተኞቻቸው የብቃት ማረጋገጫ እና የአቅም ግንባታ ስልጠና ስራዎችን
በማንኛውም ጊዜ ለመስራት የሚያስችል የኦሮሚያ የግል ት/ቤቶች የመምህራን ማሰልጠኛ ተቋም ወይም ኮሌጅ ለመክፈት
ጠንክሮ መስራት፡፡
23. የመጸሀፍት አቅርቦትን በበቂና በጊዜ በማቅረብ፣ በተጨማሪም የተለያዩ ማኑዋሎችንና መማሪያዎችን በወቅቱ ለአባል ት/ቤቴች
ተደራሽ ለማድረግ የት/ቤቶችን የብቃት ደረጃን ለማሻሻል ጥረት ማድረግ፡፡
24. ማህበሩማህበራዊ ኃላፊነቱን ከመወጣት አኳያ ለሀገራዊ ጥሪ ምላሽ ለመስጠት እና እንዲሁም በኢኮኖሚያዊ እና በማህበራዊ
ቁሶች የተነሳ የመማር እድል ለተነፈጉ ህጻናትን አባል ት/ቤቶችን በማስተባበር ዘላቂ እና ቀጣይነት ባለው የበጎ ስራዎች ላይ
ማስተባበር እና የራሱንም ድርሻ መወጣት፡፡
25. ለትምህርት ጥራት መሻሻል የሚረዱ የተለያዩ ጥናቶችን እና ምርምሮችን በማድረግ ለሚመለከተው አካል ያቀርባል፡፡
እንዲሁም የትምህርት ኤግዚቢሽኖችን በማዘጋጀት ለዕይታ እንዲቀርቡ ያደርጋል፡፡

ኦሮሚያ የግል ት/ቤቶች ማህበር -ፊንፊኔ


6
Waldaa Manneen Barnoota Dhuunfaa Oromiya Finfiine

26. የግል ት/ቤቶች በትምህርት ሥራው ላይ ከሚያበረክቱት ከፍተኛ አስተዋፅኦ አኳያ በየ ደረጃው ባሉ የመንግስት የስራ
ኃላፊዎችም ሆነ ፖሊሲ አውጪዎች ውስጥ ተገቢውን ውክልና ኖሯቸው ገንቢ ተፅዕኖ እንዲፈጥሩ እንዲደረግ ማህበሩ አበክሮ
ይሰራል፡፡
27. ከዚህ በላይ የተዘረዘሩት ስራዎች ጋር ተዛማዥነት ያላቸውን ማንኛውንም ስራዎች መስራት፡፡

አንቀጽ ሰባት

አባልነት

1. ማንኛውም መንግስታዊ ያልሆኑ ት/ቤቶች የማህበሩን መተዳደሪያ ደንብ አክብረው የሚፈለግባቸውን ግዴታ
በመወጣት በሚሰጠው መብትም ለመገልገል ዝግጁ ሆነው እና ለማህበሩ አላማ ግብ መምታት የበኩሉን
አስተዋጾ የሚያደርጉ
2. የማህበሩ አባል መስፈርት
ሀ/ በትምህርት ስራ ላይ የተሰማራና የተመዘገበ እንዲሁም የትምህርት ቤት ስራ ፈቃድ ያለው በስራው ላይ
የተሰማራ መሆን አለበት፡፡
ለ/ የመመዝገቢያ እና የማህበሩን መዋጮ ለመክፈል ፈቃደኛ የሆነ
ሐ/ ለማህበሩ የገንዘብም ይሁን የሙያ አገልግሎት ለመስጠት ፈቃደኛ የሆነ
መ/ የትምህርት ሚኒስተር እና የክልሉ ትምህርት ቢሮ ለሚያወጣቸው መመሪያዎች ተገዢ የሆነ
ሠ/ ከማህበሩ ጠቅላላ ጉባኤ የተቀመጡ ሌሎች መሳፍርቶችን የሚያሟላ እና ለማህበሩ ህገ ደንብ ተገዢ የሆነ

አንቀጽ ስምንት
የአባላት መብት
1. ሁሉም አባል እኩል መብት አላቸው፡፡
2. የማህበሩ አባልነት በህግ የተሰጠው አባልነትና የድርጅቱ የባለቤትነት መብት የተከበረ ይሆናል፡፡
3. ማንኛውም የማህበሩ አባል፡-
ሀ/ የመምረጥ፣ የመመረጥ፣ ስለ ማህበሩ እንቅስቃሴ ማንኛውንም መረጃ ጠይቆ የማግኘት፤
ለ/ በጠቅላላ ጉባኤ ስብሰባ የመገኘት፣ ሀሳብን የማቅረብ፣ የመጠየቅ፣ የቀረበውን ሀሳብ የማሻሻል፣ የመደገፍና
የመቃወም መብት አለው፡፡
ሐ/ ማህበሩ የሚያገኘውን ማንናውንም ጥቅሞችና አገልግሎቶች የድርሻውን የማግኘት መብት አለው፡፡

አንቀጽ ዘጠኝ

የማህበሩ አባላት ግዴታ

1. ማንኛውም የማህበሩ አባል የአባልነት መዋጮ በወቅቱ መክፈል አለበት፡፡


1.1. ማንኛውም የማህበሩ አባል የአባልነት መዋጮ በየአመቱ ከሀምሌ 1 እስከ ነሐሴ 30 ለማህበሩ ገቢ
የማድረግ ግዴታ አለበት፡
1.2. ከመስከረም ወር በኋላ በየወሩ በቅጣት ብር 100 (አንድ መቶ ብር) እየጨመረ ገቢ የማድረግ ግዴታ
አለበት፡፡
ኦሮሚያ የግል ት/ቤቶች ማህበር -ፊንፊኔ
7
Waldaa Manneen Barnoota Dhuunfaa Oromiya Finfiine

2. አንድ አባል ከማህበሩ ሲወጣ ያለበትን እዳ አጠቃሎ በመክፈል ክሊራንስ የመውሰድ ግዴታ አለበት፡፡
3. ማንኛውም አባል የማህበሩን አላማዎች፣ ደንቦች እና መመሪያዎች በማክበር እና በማስከበር የሚጠበቅበትን
አገልግሎት የመስጠት ግዴታ አለበት፡፡
4. ማንኛውም አባል ከማህበሩ ደንብ እና መመሪያዎች ከሚጻረሩ ድርጊቶች የመቆጠብ ግዴታ አለበት፡፡
5. ማንኛውም አባል ሌሎች የአባል ት/ቤቶችን የሚጎዱ ስራዎች ከመስራት መታቀብ አለበት፡፡
6. ማንኛውም አባል በማህበሩ ብቻ በሚስጥርነት ሊጠበቁ የሚገቡ የማህበሩን ሚስጥራዊ መረጃዎች ለ 3 ኛ
ወገን አሳልፎ ከመስጠት የመቆጠብ ግዴታ አለበት፡፡

አንቀጽ አስር

አባልነት የሚቋረጥበት ሁኔታ

1. የሚጠበቅበትን ግዴታ ባለመወጣት እና መተዳደሪያ ደንቡን ባለማክበሩ የተነሳ የስራ አመራር ቦርዱ አባልነቱ
እንዲቋረጥ ከወሰነ በኋላ ለጠቅላላ ጉባኤው ቀርቦ ከጸደቀ ጊዜ አንስቶ አንድ አባል ከአባልነቱ እንዲቋረጥ
ይደረጋል፡፡
2. ስልጣን ባለው አካል የስራ ፈቃዱ ሲሰረዝ ከአባልነቱ ይሰናበታል፡፡
3. ስልጣን ባለው ፍ/ቤት ወይም በህግ ፍቃዱ ሲሰረዝ

አንቀጽ አስራ አንድ - የማህበሩ መዋቅር

ጠቅላላ ጉባኤ

የውጪ ኦዲተር

የስራ አመራር ቦርድ

የህግ አማካሪ የውስጥ ኦዲተር

የዋናው ጽ/ቤት ስራ አስኪያጅ


ኦሮሚያ የግል ት/ቤቶች ማህበር -ፊንፊኔ
8
የጽ/ቤት ሰራተኞች
የዕቃሌሎች
የአይሲቲ
የጥበቃ
የሂሳብ
የጽዳት
ሰራተኞች
ሹም
ሰራተኞች
ሰራተኛ
ባለሙያ የቅርንጫፍ ማስተባበሪያ ማዕከላት
የግዢግምጃገንዘብ
እና ቤት
ያዥ
ንብረት
Waldaa Manneen Barnoota Dhuunfaa Oromiya Finfiine

አንቀጽ አስራ ሁለት

ጠቅላላ ጉባኤ

ማህበሩ ሁሉም አባል ት/ቤቶች ያሉበት አንድ ጠቅላላ ጉባኤ ይኖረዋል፡፡

አንቀጽ አስራ ሶስት

የጠቅላላ ጉባኤ ስልጣን እና ሀላፊነት

ጠቅላላ ጉባኤው በዚህ መተዳደሪያ ደንብ የተጠቀሱትን አባላት የሚያካትት ሆኖ የሚከተሉት ስልጣን እና ተግባር
ይኖሩታል፡-
1. ጠቅላላ ጉባኤው የማህበሩ የበላይ ጠባቂ እና ኃላፊ ነው፡፡ የስራ አመራር አባላትን፣ ኦዲተርን፣ የስራ አስፈጻሚ አባላትን
በየደረጃው ይመርጣል ይሽራል፡፡
2. በቦርዱ የሚቀርቡለት አጀንዳ ላይ በመወያየት ውሳኔ ይሰጣል፡፡
3. አመታዊ የስራ ፕሮግራምን በመመርመር የማህበሩን እቅድ እና በጀት ያጸድቃል፡፡
4. አመታዊ የስራ ኦዲት እና ሪፖርት መርምሮ ያጸድቃል፡፡
5. የስራ አመራር ቦርዱም በበላይነት ይቆጣጠራል፡፡
6. ከስራ አመራር የሚቀርቡትን ጉዳዮች በመገምገም እና በመመርመር መመሪያ እና ውሳኔ ይሰጣል፡፡
7. የማህበሩን መተዳደሪያ ደንብ ያሻሽላል ተግባራዊነቱንም ይቆጣጠራል፡፡
8. የማህበሩን ጽ/ቤት በተዋረድም ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶችን የሚከፈትበትን አቅጣጫ ያስቀምጣል፡፡ አስፈላጊ ከሆነ ቦታውንም
ይወስናል፡፡
9. በጠቅላላ ጉባኤ በአመት አንድ ጊዜ መደበኛ ስብሰባ እና እንደአስፈላጊነቱ አስቸኳይ ስብሰባዎችን ያደርጋል፡፡
10. ግዴታቸውን በትክክል ያልተወጡትን የስራ አመራር ይሽራል፡፡ በተሸሩ ምትክም ሌላ አባል ያስመርጣል፡፡
11. የስነ ምግባር ችግር ባለባቸው የስራ አመራር እና አባል ት/ቤቶች ላይ አስተዳደራዊ እና የእርምት እርምጃ እንዲወሰንባቸው
ያደርጋል፣ ከገንዘብ ቅጣት እስከ አባልነት መሰረዝ ውሳኔ ይሰጣል፡፡
12. ከስራ አመራር ቦርዱ የሚቀርቡለትን ረቂቅ የገቢ ማስገኛ ፕሮጀክት ፕሮፖዛሎችን እና ሌሎች የገንዘብ አስተዋፅኦ መጠንን
መርምሮ በአባል ት/ቤቶች ላይ ይወስናል፡፡
13. ለማህበሩ የስራ አመራር ቦርድ ያልተሰጡትን የሀላፊነት ስልጣን ጉዳዮች መርምሮ ይወስናል፡፡

አንቀጽ አስራ አራት

የማህበሩ የስራ አመራር ቦርድ

ኦሮሚያ የግል ት/ቤቶች ማህበር -ፊንፊኔ


9
Waldaa Manneen Barnoota Dhuunfaa Oromiya Finfiine

ማህበሩን በበላይነት የሚያስተዳድሩ እና ተጠሪነቱም ለጠቅላላ ጉባኤ ሆኖ በጠቅላላ ጉባኤ የሚመረጡ 7 አባላት ያሉት አንድ
የስራ አመራር ኮሚቴ (ቦርድ) ይኖረዋል፡፡

አንቀጽ አስራ አምስት

የማህበሩ የስራ አመራር ቦርድ የስልጣን ዘመን

1. የማህበሩ የስራ አመራር ኮሚቴ የስራ ዘመን 3 አመት ይሆናል፡፡


2. አንድ የስራ አመራር ኮሚቴ አባል በተከታታይ ከ 2 (two term) ጊዜ በላይ ሊመረጥ አይችልም፡፡

አንቀጽ አስራ ስድስት

የማህበሩ የስራ አመራር ቦርድ ስልጣን እና ተግባር

1. የስራ አመራር ኮሚቴ በየወሩ መደበኛ ስብሰባ እና እንደ አስፈላጊነቱ አስቸኳይ ስብሰባዎችን በማድረግ የማህበሩን ስራዎች
ይመራል ፤ ይቆጣጠራል፡፡
2. በመተዳደሪያ ደንቡ የተቀመጡትን አላማዎች ለማሳካት ማህበሩ የትምህርት ባለሙያዎችን ለማሰባሰብ የጋራ ጥቅማቸውን
የሚያስከብሩበት፣ በችግሮቻቸውም ላይ በጋራ ተወያይተው የመፍትሄ ሀሳብ የሚያቀርቡበትን እንዲሁም በትምህርት ዘርፍ
ዙሪያ ውይይት የሚያደርጉበት መድረክ መፍጠር፣ ግንኙነቱም የሰመረ እንዲሆን ጥረት ማድረግ፣ የሚያጋጥሙትን
መሰናክሎች በማጥናት የመፍትሄ ሀሳቦችን ለመንግስት ማቅረብ እና ውሳኔ እንዲሰጥባቸው አስፈላጊውን ክትትል በማድረግ
በአባላት መካከል ሊፈጠር የሚችለውን አሉታዊ የውድድር መንፈስ በማስቀረት የአባላትን የትብብር መንፈስ ማጠናከር፣
ትክክለኛ እና ሀቀኛ የትምህርት ስነ ምግባር እንዲኖር ማድረግ ፤በማህበሩ አባላት መካከል መልካም ተሞክሮ ያለው
የትምህርት ልምድ እንዲመሰረት በሂደት በአጠቃላይ ሰላማዊ ግንኙነት እንዲሰፍን ያልተቋረጠ እና ተከታታይነት ያለው ጥረት
ማድረግ፤
3. የትምህርት ስራ በስፋት እና በጥራት የሚጠናከርበትን ሁኔታ ማመቻቸት፡፡
4. ከሚመለከታቸው መንግስታዊ እና መንግስታዊ ካልሆኑ መስሪያ ቤቶች ጋር ቅንጀት በመፍጠር ትምህርትን ለማስፋፋት
የሚረዱ ከተማ አቀፍ ጉባዮችን፣ ሴሚናሮችን፣ ኤግዚቢሽኖችን በማዘጋጀት ሌሎች ት/ቤቶች በሚያዘጋጃቸውም ላይ
በመሳተፍ የመማር ማስተማር ሂደት ማህበረሰብ አቀፍ ማድረግ እና ማጎልበት በትምህርት ስራ ላይ የሚያጋጥሙ የቴክኒካዊ
ችግሮች ላይ የምክር አገልግሎት በመስጠት አባላት የሚያደርጉትን አስተዋጽኦ ማስተባበር እና የሚከፍሉትን መዋጮ
በመወሰን ማሰባሰብ፤
5. የግዢ ውል (የስራ ግንባታ የህትመት እና የአገልግሎት) የሰራተኛ ቅጥር ውል መዋዋል፣ መሰረዝ፣ ማሻሻል፣ ንብረቶችን እና
ገንዘብን በስጦታ መስጠት፣ መቀበል እንዲሁም በማህበሩ ስም ማህበሩን በሚጎዱ ጉዳዮች ክስ መመስረት፤ ክስ ማንሳት
ስራዎችን በህግ ባለሙያ በመረዳት ማከናወን እና የማህበሩን አላማ ከግብ ለማድረስ የሚያስችሉ ተግባራትን ማከናወን፡፡
6. የማህበሩ መዋቅር በክልል፣ በከተማ፣ በክ/ከተማ እና በዞን በልዩ ከተሞች እና ወረዳዎች የመዘርጋት መዋቅር መስራት
7. የማህበሩ የመተዳደሪያ ደንብ በማሻሻል ማዘጋጀት በጠቅላላ ጉባኤ በማጸደቅ ተግባራዊነቱንም የማረጋገጥ ስራ መስራት፡፡

ኦሮሚያ የግል ት/ቤቶች ማህበር -ፊንፊኔ


10
Waldaa Manneen Barnoota Dhuunfaa Oromiya Finfiine

8. የማህበሩ ጽ/ቤት የአስተዳደር ሰራተኞችን ይቀጥራል፣ ያስተዳድራል፣ ያሰናብታል፣ ደመወዝ ይከፍላል፡፡


9. ከባድ ጥፋት ሰርተው የተገኙትን የጽ/ቤቱ ሰራተኞችን ማስጠንቀቂያ ከመስጠት አልፎ በሀገሪቱ ህጎች በመታገዝ የዲሲፒሊን
እርምጃ ይወስዳል፡፡ጥፋቱ ከባድ ሆኖም በተገኘ ጊዜ ከስራ ያሰናብታል፡፡ በሌሎች የሀገሪቷ ህጎች መጠየቅ የሚገባቸውም
ላይም ክስ እንዲመሰረትባቸው ያደርጋል፡፡ ተግራዊነቱንም ይከታተላል፡፡
10. የስራ አመራሩ የስራ አካሄድ ይመራል፡፡ የማህበሩ አባላት በወል እና በተናጥል የተሰጣቸውን ስራዎች በትክክል
ማከናወናቸውን ይከታተላል፡፡ የስራ ክፍተት እና ግድፈት መፈጸማቸውን በደረሰባቸው አባላት ላይ በስራ አመራሩ የስነ
ምግባር ደንብ መሰረት አስተዳደራዊ እርምጃ ይወስዳል፡፡ ከፍተኛ ሆኖ ከተገኘም ለጠቅላላ ጉባኤው በማቅረብ ያስወስናል፡፡
11. የጽ/ቤቱ ሰራተኞች የስራ መርሀ ግብር በመዘርጋት አፈጻጸማቸውን በበላይነት ይቆጣጠራል፡፡
12. የማህበሩ አባላት የመጸሀፍ ህትመት ጨረታዎችን በማውጣት እና በህግ አግባብ የጨረታ ማስታወቂያዎቹም መውጣታቸውን
ይከታተላል፡፡ አሸናፊ ተጫራቾቸን በመለየት የውል ስራዎችን ያስፈጽማል፡፡ መጽሀፍቶችን ይረከባል፡፡ ክፍያዎችን
ይፈጽማል፡፡ የታተሙና የተገዙ መፅሀፍቶችን የዕቃ ግምጃ በቱ እንዲረከብ ያደርጋል፡፡መጽሀፍቶችም በጥያቄያቸው እና
በአባላት ክፍያ ላይ በመመርኮዝ እንዲሰራጩ ያደርጋል፡፡
13. በአባላት መካከል ሊፈጠር የሚችለውን አሉታዊ የውድድር መንፈስ በማስቀረት የአባላትን የትብብር መንፈስ ማጠናከር፣
ትክክለኛ እና ሀቀኛ የትምህርት ሥነ ምግባር እንዲኖር ማድረግ፣ በማህበሩ መካከል መልካም ተሞክሮ ያለው የትምህርት
ልምድ እንዲመሰረት በማድረግ በአጠቃላይ ሰላማዊ ግንኙነት እንዲሰፍን ያልተቋረጠ እና ተከታታይነት ያለው ጥረት
ማድረግ፡፡
14. የትምህርት ስራ በስፋት የሚደራጅበት እና ይበልጥ የሚጠናከርበትን ሁኔታ ማመቻቸት፡፡ ከሚመለከታቸው መንግስታዊ
መስሪያ ቤቶች ጋር በመመካከር እና በመተባበር ትምህርትን ለማስፋፋት የሚረዱ ከተማ አቀፍ ጉባኤዎች፣ ሴሚናሮችን፣
ኤግዚቢሽኖችን በማዘጋጀት ሌሎች ተቋማት በሚያዘጋጇቸው ላይም በመሳተፍ በሌሎች አካል እንዲዘጋጁ በማበረታታት
ት/ቤቶችን የማጠናከር ስራ ይሰራል፡፡
15. የማህበሩ አባላት እውቀታቸውን ህብታቸውን እና ጉልበታቸውን በማስተባበር በትምህርት ስራ እንቅስቃሴዎች ውስጥ
እንዲሳተፉ ማበረታታት፡፡
16. በትምህርት ስራ ላይ የሚያጋጥሙ የቴክኒክ ችግሮችን በመቅረፍ የምክር አገልግሎት በመስጠት አባላት የሚበለፅጉበትን
አስተዋጾ ማበርከት፡፡
17. ከተለያዩ መንግስታዊ እና መንግስታዊ ካልሆኑ ድርጅቶች ጋር የስራ ግንኙነትን በመፍጠር ቁሳዊና ትምህርታዊ ድጋፎች
የሚገኙበትን ሁኔታዎች በማመቻቸት ከሀገር አቀፍ መሰል ተቋማት ጋር አጋርነትን ፈጥሮ ተቀናጅቶ መስራት፣
18. የባንክ ሂሳብ መክፈት፣ ማንቀሳቀስ ፤የሚንቀሳቀስ እና የማይንቀሳቀስ ንብረት ማፍራት እና ለማህበሩ አላማ እንዲውል
ማድረግ፡፡
19. ከኦሮሚያ ትምህርት ቢሮ እና ከፌደራል ትምህርት ሚኒስቴር ጋር በመሆን ለማህበሩም ሆነ ለማህበሩ አባል ት/ቤቶች
የሚያስፈልጉት የትምህርት ግብአቶች የሚገኙበትን መንገድ ማመቻቸት እና ከውጪ ሀገር ከቀረጥ ነጻ የትምህርት ግብአቶች
እንዲገቡ መስራት፡፡

ኦሮሚያ የግል ት/ቤቶች ማህበር -ፊንፊኔ


11
Waldaa Manneen Barnoota Dhuunfaa Oromiya Finfiine

20. በግል ት/ቤቶች ውስጥ የሚገኙ መምህራን እና ሰራተኞች ወቅታዊ የሙያ ስልጠና የሚያገኙበት ሁኔታ ላይ ከመንግስት እና
ከሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር ተባብሮ እና ተቀናጅቶ መስራት፡፡
21. በግል ት/ቤቶች ውስጥ በማገልገል ላይ የሚገኙ መምህራን፣ ሰራተኞች እና ተማሪዎች የትምህርት እድል የሚያገኙበትን ሁኔታ
ማመቻቸት፡፡
22. የማህበሩን አባላት የስነ ምግባር ደንብ (code of conduct) ማውጣት እና ተግባራዊነቱንም መከታተል እና ማረጋገጥ፡፡
ሌሎች የማህበሩ አላማዎች የሚያስከብሩ ደንቦች፣ መመሪያዎች እና ሌሎችንም ማሻሻያዎች አድርጎ መስራት፡፡
23. ሌሎች የማህበሩን አላማዎች ለማሳካት ተጣማጅነት ያላቸውን ማንኛውንም ስራዎች ማከናወን፡፡
24. ሁሉም በክልሉ የሚገኙ የግል ት/ቤቶች የማህበሩ አባል እንዲሆኑ የተለያዩ መንገዶችን በመጠቀም የአባላቱን ቁጥር
ማሳደግ፡፡
25. ተጨማሪ ሌሎች በማህበሩ አላማ ስር ተዘረዝረው በዚህ ስር ያልተካተቱትን ስራዎች ይሰራል፣ ያስተባብራል፣
ተግባራዊነታቸውንም ይከታተላል፡፡

አንቀጽ አስራ ሰባት

የስራ አመራር ቦርድ አባላት የሥራ ድርሻ እና ሀላፊነት

የስራ አመራር ቦርዱ አንድ ሊቀመንበር፣ ምክትል ሊቀመንበር፣ ፀሀፊ፣ እና አራት አባላት ቢያንስ 7/ሰባት/ የአመራር አባላት
ይኖሩታል፡፡

አንቀጽ አስራ ስምንት

የስራ አመራር ቦርድ ሊቀመንበር የስራ ድርሻ እና ስልጣን

1. ማህበሩን በየትኛውም ቦታ ይወክላል፡፡ ተጠሪነቱ ለስራ አመራር ቦርዱ እና ለጠቅላላው ጉባኤ ይሆናል፡፡
2. የስራ አመራር ቦርድ አባላት የተሰጣቸውን የስራ ድርሻ በተገቢው መንገድ ማከናወናቸውን ይቆጣጠራል፣ ያስተባብራል፡፡
3. በማህበሩ መተዳደሪያ ደንብ መሰረት ከምክትል ሰብሳቢ እና ከጸሀፊው ጋር በመሆን የባንክ ሂሳብ ደብተር፣ ያንቀሳቅሳል፣
ገንዘብ ለማውጣት ከሶስቱ ቢያንስ በሁለቱ ፊርማ ገንዘቡ እንዲወጣ ያደርጋል፡፡ ተግባራዊነቱንም ይቆጣጠራል፡፡
4. ለማንኛውም የስራ ማስኬጃ የሚውለውን ገንዘብ የስራ አመራር ቦርድ ሲያፀድቀው ገንዘብ ወጪ እንዲሆን ያዛል፡፡
5. ተ/ቁ 4 ላይ ያለው እንደተጠበቀ ሆኖ በማህበሩ ስም ከመንግስት እና ከግል ድርጅቶች ጋር ለሚደረጉ ስምምነቶች በቅድሚያ
ጉዳዩን ለአመራር ቦርድ አቅርቦ ውሳኔ እንዲሰጥበት ካደረገ በኋላ በማህበሩ ስም ይፈርማል፣ ይፈጽማል፡፡
6. የማህበሩ ቋሚ እና ተንቀሳቃሽ ንብረቶች በአግባቡ እና በጥንቃቄ መጠበቃቸውን ይቆጣጠራል፡፡
7. የማህበሩን ገንዘብ በማህበሩ ስም ባንክ መግባቱን ይቆጣጠራል ያረጋግጣል፡፡
8. የመተዳደሪያ ደንቡ ስራ ላይ መዋሉን ይቆጣጠራል፡፡
9. ለአመራር ቦርዱ እንዲወያዩበት በጽሁፍ የሚቀርቡለትን ሀሳቦች ተቀብሎ ለውይይት እንዲቀርብ ያደርጋል፡፡ በአጀንዳ
ለጠቅላላ ጉባኤም እንዲቀርብ ያደርጋል፡፡

ኦሮሚያ የግል ት/ቤቶች ማህበር -ፊንፊኔ


12
Waldaa Manneen Barnoota Dhuunfaa Oromiya Finfiine

10. በመተዳደሪያ ደንቡ ግዴታውን ያልተወጣ አባል ጉዳዩ ለስራ አመራር ቦርድ ቀርቦ ውሳኔ እንዲሰጥበት ያደርጋል፡፡
11. ማህበሩ በሚከሰስበት ጉዳዮች ላይ በማህበሩ ስም ጠበቃ ይወክላል፡፡ ውክልናውንም ያነሳል፡፡ በስራ አመራር ቦርድ ሲወሰን
ማህበሩን በመወከል በውል ሰጪነት እና በውል ተቀባይነት ውል ያደርጋል ውል ያፈርሳል ተግባራዊነቱንም ይከታተላል፡፡
12. በስራ አመራር ቦርድ ተወስኖ ሲገኝም በፍ/ቤት የቀረበውን ጉዳይ ክስ ያነሳል፡፡

አንቀጽ አስራ ዘጠኝ

የምክትል ሰብሳቢው ስልጣን እና ተግባር

1. ተጠሪነቱም ለስራ አመራር ቦርዱ ይሆናል፡፡


2. የስራ አመራር ቦርድ ሰብሳቢ በሀገር ውስጥ ከሌለ ወይም ሰብሳቢው በፅሁፍ ሲወክለው ስብሰባዎችን ይመራል፣ በሊቀ
መንበሩ የሚከናወኑ ስራዎችን ሁሉ ያከናውናል፡፡
3. የመተዳደሪያ ደንቡ ስራ ላይ መዋሉን ይከታተላል ተፈጻሚነቱንም ይገመግማል፡፡
4. አመታዊ የስራ ፕሮግራም፣ እቅድ እና በጀት ከጽ/ቤቱ ስራ አስኪያጅ ጋር ሆኖ በማዘጋጀት ለሥራ አመራር ቦርድ ውሳኔ
ያቀርባል፡፡
5. የማህበሩን ገንዘብ ከባንክ ወጪ በሚሆንበት ጊዜ ከሰብሳቢ ወይም እና ምክትል ሰብሳቢ ጋር ሆኖ ይፈርማል፡፡
6. ሌሎች መሰል ስራዎችና የስራ አስፈጻሚ የሚሰጡትን ስራዎች ይሰራል፡፡

አንቀጽ ሀያ

የጸሀፊው ስልጣን እና ተግባር

1. ተጠሪነቱም ለስራ አመራር ቦርዱ ይሆናል፡፡


2. የጠቅላላ ጉባኤና የስራ አመራር ቦርድ ሰብሳቢ እና ምክትል ሰብሳቢ በሀገር ውስጥ ከሌሉ ወይም በእነሱ ሲወከል ስብሰባዎችን
ይመራል፣ በእርሱ የሚከናወኑ ስራዎችን ሁሉ ያከናውናል፡፡
3. የስብሰባ ቃለ ጉባኤ ይይዛል፡፡ አስፈርሞ ፋይል ያደርጋል፡፡
4. የስብሰባ ውሳኔዎችን ለሚመለከተው አካላት ያስተላልፋል፡፡
5. የማህበሩ ሰነዶች በአግባቡ ተሰንደው እንዲቀመጡ ያደርጋል፡፡
6. የማህበሩን ገንዘብ ከባንክ ወጪ በሚሆንበት ጊዜ ከሰብሳቢ ወይም እና ምክትል ሰብሳቢ ጋር ሆኖ ይፈርማል፡፡
7. ከሰብሳቢው ጋር በመሆን የስራ አመራር ኮሚቴው የመወያያ አጀንዳዎችን ያዘጋጃል አፈጻጸማቸውንም ይከታተላል፡፡
8. ዓመታዊ የሥራ እንቅስቃሴ በማዘጋጀት ለቦርድ ውሳኔ ያቀርባል፡፡

አንቀጽ ሀያ አንድ

የውስጥ ኦዲተር ስልጣን እና ተግባር

1. ተጠሪነቱ ለሥራ አመራር ቦርድ ይሆናል፡፡

ኦሮሚያ የግል ት/ቤቶች ማህበር -ፊንፊኔ


13
Waldaa Manneen Barnoota Dhuunfaa Oromiya Finfiine

2. የማህበሩን የገንዘብ እና የንብረት አስተዳደር ትክክለኝነት ይቆጣጠራል፡፡


3. ማንኛውንም የገንዘብ ወጪ እና የማህበሩን የስራ እንቅስቃሴ በዚህ መተዳደሪያ ደንብ መሰረት የተከናወነ መሆኑን
ያረጋግጣል፡፡
4. የገንዘብ ወጪዎችን በማህበሩ ሰብሳቢ እና ስልጣን በተሰጣቸው የአመራሩ አባላት ወጪያቸው በትክክል መታዘዙን
ይቆጣጠራል ያረጋግጣል፡፡
5. የገንዘብ መቀበያ እና የክፍያ ደረሰኞችን ተራ ቁጥራቸው ሳይዛነፍ በትክክል መታተማቸው እና መመዝገባቸውንም እንዲሁም
ቅደም ተከተላቸው ተጠብቆ በስራ ላይ መዋላቸውን ይቆጣጠራል፡፡
6. ለማህበሩ የሂሳብ ሰራተኛ ሙያዊ ድጋፍ ማድረግ እና በትብብር መስራት
7. የማህበሩን ገንዘብ እና ንብረት አስፈላጊውን ቆጠራ መደረጋቸውን በየ ስድስት ወሩ ለሥራ አመራር ቦርድ ያቀርባል፡፡
8. የውስጥ ኦዲተር ስራ በመስራት ለውጪ ኦዲተር ማቅረብ እና የሚስተካከሉ ጉዳዮች ሲያጋጥም ለሥራ አመራር ቦርዱ
በማቅረብ ያስወስናልአስፈላጊውን አስተዳደራዊ እርምጃ እንዲወሰድ ያደርጋል፡፡
9. የፅ/ቤቱ ሥራዎች በመመሪያው መሰረት ስራቸውን በህግ አግባብ መወጣታቸውን ይከታተላል ለሥራ አመራ ቦርዱ ሪፖርት
ያቀርባል፡፡
10. ለማህበሩ የቦርድ አመራር የማማከር ስራዎችን ያከናውናል፡፡

አንቀጽ ሀያ ሁለት

የህግ አማካሪ እና ጠበቃ ስልጣን እና ተግባር

1. ተጠሪነቱ ለሥራ አመራር ቦርድ ይሆናል፡፡


2. ማህበሩ በሀገሪቷ እና በክልሉ ህገ መንግስት፣ ህጎች እንዲሁም ማህበሩ በደነገጋቸው ደንቦች እና መንግስት በሚያወጣቸው
ሌሎች ደንቦች እና መመሪያዎች መሰረት ስራቸውን ማከናወናቸውን ፣ ይቆጣጠራል፣ ይከታተላል፡፡
3. የማህበሩን መብት እና ግዴታ በተመለከተ ለጠቅላላ ጉባኤ እና ለስራ አመራሩ ቦርድ የህግ አስተያየት ይሰጣል፡፡
4. የማህበሩ የመተዳደሪያ ደንብ እና የስነ ምግባር ደንብ በመመርመር መሻሻል በሚገባቸው ላይ ማሻሻያ እንዲደረግበት የህግ
አስተያየት ይሰጣል እንዲሻሻሉም ያደርጋል፡፡
5. ማህበሩ በሚያወጣቸው የግዢ እና የጨረታ ማስታወቂያዎች ህጉን ተከትለው መፈጸማቸውን እና መተግበራቸውን
ይቆጣጠራል ይከታተላል የህግ አስተያየት ይሰጣል፡፡
6. ማህበሩ ከ 3 ኛ ወገኖች ጋር የሚያደርጋቸውን የተለያዩ ውሎች ላይ የህግ አስተያየት ይሰጣል መሻሻል የሚገባቸውንም
እንዲሻሻሉ ያደርጋል፡፡
7. ማህበሩ የሚያደርጋቸው ውሎች እንዲሁም የሚያከናውናቸው ስራዎች ለህግ እና ለሞራል ተቃራኒ ያለመሆናቸውን
ይቆጣጠራል ያረጋግጣል የህግ አስተያየት ይሰጣል፡፡

ኦሮሚያ የግል ት/ቤቶች ማህበር -ፊንፊኔ


14
Waldaa Manneen Barnoota Dhuunfaa Oromiya Finfiine

8. የማህበሩን መብቶች ጥሰት ባጋጠመ ወቅትም ህጋዊ መደራደሪያዎችን ያመቻቻል አስተያየት ይሰጣል፡፡ በድርድር የማይፈቱ
ጉዳዮችንም ስልጣን ባለው አካል ወይም ፍ/ቤት ጉዳዩ እንዲቀርብ እና ውሳኔ እንዲሰጥበት ለማህበሩ የስራ አመራር የህግ
አስተያየት ይሰጣል ተግባራዊነቱንም ይከታተላል፡፡
9. በማንኛውም ፍርድ ቤት ማህበሩ በሚከሰስበትም ሆነ በሚከስበት ጊዜ ማህበሩን በመወከል ይከራከራል፡፡

አንቀጽ ሀያ ሶስት

የማህበሩ ቅጥር የጽ/ቤት ሰራተኞች

1. ማህበሩ የተቋቋመለትን አላማ ከግብ ለማድረስ የተለያዩ ስራዎችን የሚያከናውኑ የማህበሩ ስራ አመራር ቦርድ ስር
የሚተዳደሩ፡-
1.1. የዋናው ጽ/ቤት ስራ አስኪያጅ 1
1.2. የሂሳብ ሰራተኛ 1
1.3. ገንዘብ ያዥ 1
1.4. የግዢ እና የንብረት አስተዳደር ሰራተኛ 1
1.5. የእቃ ግምጃ ቤት ሰራተኛ 1
1.6. የአይሲቲ ባለሙያ 1
1.7. የጥበቃ ሰራተኛ 2
1.8. የጽዳት ሰራተኛ 1
በድምሩ 9 ሰራተኞች ሊኖሩት የሚችል ሲሆን ሌሎች ተጨማሪ ሰራተኞችም እንደአስፈላጊነቱ የስራው ስፋት እና ብዛት
ታይቶ ይኖሩታል፡፡

አንቀጽ ሀያ አራት

የጽ/ቤት ስራ አስኪያጅ ስልጣን እና ሀላፊነት

1. ተጠሪነቱ ለስራ አመራር ቦርድ ሰብሳቢ ይሆናል፡፡


2. የማህበሩን የቅጥር የአስተዳደር ሰራተኞችን ይቆጣጠራል ያስተዳድራል፡፡
3. የማህበሩ ማንኛውም የጽህፈት ስራዎች ያከናውናል፡፡
4. የማህበሩን ሰነዶች በአግባቡ ሰንዶ ይይዛል፡፡
5. ማንኛውም ስራ ማስኬጃ ለምን ተግባር እንደዋለ የመቆጣጠር ስራ ይሰራል፡፡

ኦሮሚያ የግል ት/ቤቶች ማህበር -ፊንፊኔ


15
Waldaa Manneen Barnoota Dhuunfaa Oromiya Finfiine

6. በማህበሩ ጠቅላላ ጉባኤ ስብሰባ ላይ የተገኙትን እና ያልተገኙትን አባላት ለይቶ የመመዝገብ ስራ፣ ያልተገኙትን አባላት ለይቶ
ያቀረቡት ምክንያት ካለ ከነ ምክንያታቸው በመለየት ለስራ አመራር ቦርድ የማቅረብ ስራ ይሰራል፡፡
7. የማህበሩን አመታዊ የስራ እቅድ ከስራ አመራር ቦርድ በሚያገኘው ግብአት ላይ ተመስርቶ ያዘጋጃል፣ ክንዋኔያቸውንም በወር፣
በ 3 ወር፣ በ 6 ወር እና በአመት በመለየት አፈጻጸማቸውን ለስራ አመራር ቦርድ በየወቅቱ ሪፖርት የመቅረብ ስራ
ያከናውናል፡፡
8. አባል ት/ቤቶች በየጊዜው የሚያቀርቡትን አመታዊ የመጽሀፍት ህትመት የፍላጎት እቅድ እና ቅድመ ክፍያ እንዲሁም አጠቃላይ
የመጽሀፍት ዋጋ ክፍያ ለይቶ የመመዝገብ ስራ እና ለስራ አመራር ቦርዱ በየጊዜው በዝርዝርና በጥቅል የማቅረብ ስራን
ያከናውናል፡፡
9. የመጸሀፍ ስርጭት ስራ በቅደም ተከተል እና በከፈሉት የክፍያ መጠን የመደልደል እና የማሰራጨት ስራ በትክክል መከናወኑ
የመመዝገብ፣ የመከታተል እና የመቆጣጠር ስራዎችን ያከናውናል፡፡
10. መጽሀፍቶች ከማተሚያ ቤት ለማህበሩ ሲቀርቡ በየትምህርት አይነታቸው እና ለህትመት ውል በገቡት መጠን ገቢ
ስለመደረጋቸው የመመዝገብ እና የመቆጣጠር ስራ እንዲሁም የህትመቶቹ ጥራት ስራ በተሰጠው ስፔስፍኬሽን መከናወኑን
ይቆጣጠራል፡፡ ከማተሚያ ቤቶች ጋር በተደረገው ውል መሰረት ከህትመት ደረጃ በታች ሆነው ጉድለት የሚታይባቸውን
ህትመቶች በመለየት ከስርጭት በፊት ለስራ አመራር ቦርድ ለውሳኔ ሪፖርት ያደርጋል፡፡
11. ከማህበሩ የስራ አመራር ቦርድ ሊቀመንበር ሲታዘዝ በማህበሩ ስም ለማህበሩ አባላት፣ ለመንግስታዊ እና መንግስታዊ ላልሆኑ
ድርጅቶች እና ግለሰቦች በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ይፃፃፋል፡፡ በማህበሩ አድራሻም የተጻፉትን ደብዳቤዎች ከተለያዩ አካላት
ተቀብሎ ለሚመለከተው የስራ አመራር ቦርድ ያቀርባል፡፡ ከታዩም በኋላ ሰነዱን በተገቢ መልኩ ሰንዶ ያቀምጣል፡፡
12. አመታዊ የአባላት መዋጮ የከፈሉትን እና ያልከፈሉትን አባላት ለይቶ የመመዝገብ ስራ ፤ያልከፈሉትን አባላት ለይቶ ለስራ
አመራሩ በጊዜው በሚያቀርባቸው ሪፖርት ውስጥ በማካተት የማቅረብ ስራ ማከናወን፡፡
13. ሌሎች የማህበሩ የስራ አመራር የሚሰጡ ተጨማሪ ስራዎች ማከናወን፡፡

አንቀጽ ሀያ አምስት

የሂሳብ ሰራተኛ ስልጣን እና ሀላፊነት

1. ተጠሪነቱ ለጽ/ቤቱ ስራ አስኪያጅ ይሆናል፡፡


2. የማህበሩን ገንዘብ ገቢ እና ወጪ ሰነዶችን በትክክል ያዘጋጃል ይቆጣጠራል፡፡
3. የወጪ ማዘዛዎች እና ደረሰኞች ትክክል ለመሆናቸው በፊርማ ያረጋግጣል፡፡
4. የገቢ እና የወጪ ሂሳቦችን በየወሩ አዘጋጅቶ ለፅ/ቤት ሥራ አስኪያጅ ሪፖርት የማቅረብ ሥራን ያከናውናል፡፡
5. የማህበሩ ኦዲተር ሂሳቡን ለመመርመር ሲፈልግ የሚጠይቀውን አስፈላጊ ሰነዶች አቅርቦ ያስመረምራል፡፡
6. ለሂሳብ ስራ መቃናት አስፈላጊ የሆነ ውስጣዊ መመሪያዎችን ለስራ አመራር ቦርድ አቅርቦ ከተፈቀደ በኋላ በስራ ላይ
ያውላል፡፡

ኦሮሚያ የግል ት/ቤቶች ማህበር -ፊንፊኔ


16
Waldaa Manneen Barnoota Dhuunfaa Oromiya Finfiine

7. የማህበሩን አባላት ስም እና ወርሀዊ ክፍያ ልዩ መዋጮ በጠቅላላ የተለያዩ ገቢዎችን እና ወጪዎችን ይመዘግባል፡፡ ከማህበሩ
መተዳደሪያ ደንብ እና መመሪያ ውጪ በአመራር ኮሚቴ ስብሰባ ያልጸደቁትን ወጪዎች ያግዳል፡፡
8. ሌሎች የስራ አመራር ቦርዱ እና የቅርብ ኃላፊ የሚሰጣቸውን ስራዎች ያከናውናል፡፡

አንቀጽ ሀያ ስድስት

የገንዘብ ያዥ ስልጣን እና ተግባር

1. ተጠሪነቱ ለፅ/ቤት ሥራ አስኪያጅ ይሆናል፡፡


2. የማህበሩን ጊዚያዊ ጥቃቅን ወጪዎች /petty cash/ገንዘብ እና የባንክ ደብተር ይይዛል፡፡
3. ማህበሩ ከአባላቱ የሚሰበስበውን ወርሀዊ መዋጮ እና ከተለያዩ የገቢ አርስት የሚገኘውን ገንዘብ በባንክ ገቢ የሆነውን ገንዘብ
ደረሰን በመውሰድ በገቢ ደረሰኝ ይረከባል፡፡
4. ከሂሳብ ሹም ጋር የወጪ እና የገቢ ሂሳብ በየወሩ ያመሳክራል፡፡
5. በማህበሩ ወጪ ማዘዣ እና በገቢነት የተመዘገቡ ሰነዶችን በመዝገብ ላይ ያሰፍራል፡፡
6. ኦዲተር በጠየቀው ጊዜ አስፈላጊ የሆኑትን የገቢ እና የወጪ ማዘዣዎችን (ቫውቸሮችን) ሰነዶች በማቅርብ ያስመረምራል፡፡
7. የተሰበሰበን የማህበር ገንዘብ ውስጠ ደንቡ በሚያዘው መመሪያ መሰረት በወቅቱ ባንክ ያስገባል፡፡
8. ሌሎች በስራ አስፈጻሚ ቦርድ እና የቅርብ ኃላፊ የሚሰጡትን ተጨማሪ ስራዎችን ያከናውናል፡፡

አንቀጽ ሀያ ሰባት

የግዢ እና ንብረት አስተዳደር ሀላፊነት እና ተግባር

1. ተጠሪነቱ ለፅ/ቤት ሥራ አስኪያጅ ይሆናል፡፡


2. የማህበሩን ቋሚ እና ተንቀሳቃሽ ንብረቶችን በቋሚ መዝገብ እና በዲጂታል መንገድ ተመዝግበው ተሰንደው እንዲቀመጡ
ያደርጋል፡፡
3. የማህበሩን ንብረቶች በአግባቡ ያስተዳድራል፡፡
4. የማህበሩን ግዢዎች በግዢ ደንብ መሠረት መፈፀማቸውን ይከታተላል፡፡
5. የማህበሩን ንብረቶች ገቢ እና ወጪ ስልጣን በተሰጠው የማህበሩ ቦርድ ወይም በቅርብ ኃላፊ ትዕዛዝ መሰረት መፈጸማቸውን
የማስተዳደር እና የመከታተል ስራዎችን ያከናውናል፡፡
6. ገቢ እና ወጪ ንብረቶችን በአግባቡ ተመዝግቦ መኖራቸውን የመከታተል ስራዎችን ያከናውናል፡፡
7. ወቅቱን የጠበቀ የንብረት ቆጠራ በማድረግ ለፅ/ቤቱ ሥራ አስኪያጅ እና ለማህበሩ ቦርድ ያቀርባል፡፡
8. ከማህበሩ ፅ/ቤት ሥራ አስኪያጅ እና ከማህበሩ የስራ አመራር ቦርድ የሚሰጡትን ሌሎች ስራዎች ማከናወን

አንቀጽ ሀያ ስምንት

የእቃ ግምጃ ቤት ሀላፊነት እና ተግባር

ኦሮሚያ የግል ት/ቤቶች ማህበር -ፊንፊኔ


17
Waldaa Manneen Barnoota Dhuunfaa Oromiya Finfiine

1. ተጠሪነቱ ለፅ/ቤት ሥራ አስኪያጅ ይሆናል፡፡


2. የማህበሩ ቋሚ እና ተንቀሳቃሽ ንብረቶች በቋሚ መዝገብ እና በዲጂታል መንገድ መዝግቦ ይይዛል፡፡
3. የማህበሩን ንብረቶች ከብክነት ነጻ በሆነ መንገድ በትክክል ለማህበሩ ስራ መዋላቸውን መከታተል፡፡
4. የንብረት ገቢ እና ወጪ በማህበሩ ደንብ እና ህግን በተከተለ መሰረት ስራ ላይ እንዲውሉ ማድረግ፤
5. የንብረት ገቢ እና ወጪዎች በዚሁ በተዘጋጁ ሰነዶች ላይ በመመዝገብ ስልጣን በተሰጠው አካል ሲታዘዝ ገቢ እና ወጪ
ማድረግ ፤
6. ከሌሎች ከማህበሩ ስልጣን ከሰጣቸው አካልት የሚሰጡትን ሌሎች ስራዎችን መስራት፤

አንቃጽ ሀያ ዘጠኝ

የአይሲቲ ባለሙያ ሀላፊነት እና ተግባር

1. ተጠሪነቱ ለማህበሩ ጽ/ቤት ስራ አስኪያጅ ይሆናል፡፡


2. ለማህበሩ ከአንድ አይሲቲ ባለሙያ የሚጠየበቀውን ግልጋሎት መስጠት
3. ማህበሩ የሚያከናውናቸውን ዋና ዋና ስራዎች፣ የስራ ሪፖርቶች በሶፍት እና በሀርድ ኮፒ ለስራ አመራሩ ቦርድ አባላት አስፈላጊ
ሲሆኑ ለአባል ት/ቤቶች እና ለሚመለከታቸው አካላት በማስተላለፍ ተደራሽነቱን ማረጋገጥ
4. የኢንተርኔት መረብን በመጠቀም የት/ቤቶችን የህዝብ ግንኙነት ስራዎችን ለአባላቶች ተደራሽ ማድረግ
5. ከስራ አመራሩ በሚሰጡት አቅጣጫ ላይ በመመርኮዝ የትምህርት ስራን ወቅታዊ ሁኔታን በሚመለከት በጉዳዩ ላይ
የሚመለከታቸው አካላት ቴክኖሎጂን በመጠቀም መረጃን ተደራሽ ማድረግ
6. የማህበሩን ቋሚ እና ተንቀሳቃሽ ንብረቶች በሶፍት ኮፒ እና በሀርድ ኮፒ ተመዝግበው እንዲቀመጡ የራሱን ድርሻ መወጣት
7. የማህበሩን ኮምፒውተሮች የኢንተርኔት መስመረ ፋክስ፣ ፕሪንተር፣ የፎቶ ኮፒ ማሽን ወ.ዘ.ተ… አጠቃቀም እና አያያዝ ላይ
ሙያዊ ድጋፍ ለጽ/ቤቱ ሰራተኞች ማድረግ
8. ከማህበሩ ስራ አመራር ቦርድ እና ከጽ/ቤቱ ስራ አስኪያጅ በተጨማሪነት የሚሰጡትን ሌሎች ስራዎችን መስራት፡፡

አንቀጽ ሰላሳ

የጥበቃ ሰራተኛ ሀላፊነት እና ተግባር

1. ተጠሪነቱ ለማህበሩ ጽ/ቤት ስራ አስኪያጅ ይሆናል፡፡


2. የማህበሩን ጽ/ቤት እና የእቃ ግምጃ ቤት ጥበቃ ስራ ማከናወን
3. የማህበሩ ጽ/ቤቶች እና የግምጃ ቤቶች በስራ ሰዓት መግቢያ እና መውጫ መቆለፋቸውን እና በመግቢያ ሰዓትም የደህንነት
ስራዎችን የማረጋገጥ ስራዎችን ማከናወን
4. በተለያየ ምክንያት ሳይዘጉ የቀሩ ጽ/ቤቶች እና የእቃ ግምጃ ቤት ከተገኘ ወዲያውኑ ለጽ/ቤቱ ስራ አስኪያጅ ወይም ለቦርዱ
አባላት ሪፖርት በማድረግ የእርምት ስራዎች እንዲወሰዱ ማድረግ
5. በማህበሩ ንብረት ላይ ጉዳት እንዳይደርስ የሙሉ ሰዓት /ሀያ አራት ሠዓት/የእለት ተእለት ስራ ማከናወን

ኦሮሚያ የግል ት/ቤቶች ማህበር -ፊንፊኔ


18
Waldaa Manneen Barnoota Dhuunfaa Oromiya Finfiine

6. አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ የማህበሩን ንብረት ለመጠበቅም ሆነ በማህበሩ ሰራተኞች ላይ ሊደርስ የሚችለውን ለመከላከል በህጉ
መሰረት የአካል ፍተሸ ስራዎችን ማድረግ
7. ከፅ/ቤቱ ስራ አስኪያጅ እና ከበላይ አካል የሚሰጡትን ሌሎች ተጨማሪ ስራዎችን ማከለናወን

አንቀጽ ሰላሳ አንድ

የጽዳት ሰራተኛ ሀላፊነት እና ተግባር

1. ተጠሪነቱ ለማህበሩ ፅ/ቤት ስራ አስኪያጅ ይሆናል፡፡


2. የማህበሩ አገልግሎት የሚሠጡ ሁሉንም ክፍሎች እና አካባቢያቸውን ማፅዳት
3. የማህበሩ ሰራተኞች የሚገለገሉበትን መቀመጫዎች መፃፊያዎች እና ለእቃ ማስቀመጫነት የሚያገለግሉትን ንብረቶች የጽዳት
አገልግሎት መስጠት
4. ከፅ/ቤቱ ስራ አስኪያጅ እና ከሌሎች በላይ አካላት የሚሰጡትን ተጨማሪ ስራዎች መስራት ፤

አንቀጽ ሰላሳ ሁለት

የቅርንጫፍ ማስተባበሪያ ማዕከላት

ማህበሩ አባላትን ለማስተናገድና ጥያቄዎቻቸውን ለማቅረብ ብዙ ት/ቤቶች ባሉበት ከተሞች ማዕከል ባደረገ አስተባባሪ
ማዕከሎችን በተመረጡ ት/ቤቶች ላይ አድርጎ ከዋና ማህበሩ ጋር በማስተባበርና በመናበብ ተቀናጅተው ይሰራሉ፡፡
የቅርንጫፍ ማስተባበሪያ ማዕከላት የሚከተሉት የሥራ ተግባርና ኃላፊነት ይኖሩታል፡፡

1. ተጠሪነቱ ለዋናው ቦርድ ሆኖ በቦርዱ የሚሠጡትን ተጨማሪ ተግባራት በኃላፊነት ይሰራል፡፡

2. ለአባላት ወቅታዊ መረጃን ይሰጣል፡፡

3. በባንክ የተከፈሉ የአባልነት ክፍያ ስሊፖችን በወቅቱ ለዋና ማህበሩ ያስተላልፋሉ፡፡

4. በየወቅቱ የሚቀርቡትን የአባል ት/ቤቶችን የፍላጎት አቅርቦትን ቅፅ ሞልተው ለዋና ማህበር ፅ/ቤት ይልካሉ፡፡

5. ከዋና ማህበር ፅ/ቤት እና ከኦሮሚያ ት/ቢሮ የሚተላለፉ ወቅታዊ መመሪያዎችን በተዋረድ ለአባላት ተደራሽ
ያርጋሉ፡፡

6. እንደየአካባቢያቸው ሁኔታ በትምህርት ሥራ ላይ የሚያጋጥሟቸውን ችግሮች ከዋናው ፅ/ቤት ጋር በመነጋገር


ከሚመለከታቸው አካላት ጋር መፍትሔ የሚሠጥበትን ሁኔታ ያመቻቻሉ፡፡

7. የመፅሀፍት ስርጭት ከዋናው ፅ/ቤት ጋር በመነጋገር በየአካባቢያቸው ተደራሽ እንዲሆን በተናጥል ከመምጣት በጋራ
የሚጓጓዝበትን ሁኔታ የማመቻቸት ስራን ይሰራሉ፡፡

ኦሮሚያ የግል ት/ቤቶች ማህበር -ፊንፊኔ


19
Waldaa Manneen Barnoota Dhuunfaa Oromiya Finfiine

አንቀጽ ሰላሳ ሶስት

የጠቅላላ ጉባኤው የስብሰባ፣ የምርጫ እና የውሳኔ አሰጣጥ ስነ ስርአት

1. የጠቅላላ ጉባኤ መደበኛ ስብሰባ በአመት አንድ ጊዜ የሚካሄድ ሆኖ አስቸኳይ ጉዳዮች ሲያጋጥሙ አስቸኳይ ስብሰባ ሊጠራ
ይችላል፡፡
2. ከማህበሩ አባላት ከ 25% እና በላይ የሆኑ አባላት ጥያቄ ሲያቀርቡ ወይም የስራ አመራር ቦርዱ አስቸኳይ ጉባኤ እንዲካሄድ
አምኖበት ሲወስን አስቸኳይ ስብሰባ ሊጠራ ይችላል፡፡
3. ጉባኤው ምርጫ ሲያደርግ ምእላተ ጉባኤው እንደተሟላ 3 የአስመራጭ ኮሚቴ አባላት ተመርጠው የስራ አመራር አባላት
ምርጫ ይደረጋል፡፡
4. አስመራጭ ኮሚቴው ከሁሉ አስቀድሞ የምርጫ መመዘኛዎች በጉባኤው እንዲወሰኑ አድርጎ ምርጫውን ያስፈጽማል፡፡
5. የማህበሩ መደበኛ አባላት 51% ሲገኙ ምእላተ ጉባኤ ይሆናል፡፡
6. ይህ ሳይሟላ ቀርቶ 2 ኛ ጥሪ አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ እና ለአባላት መድረሱ ሲረጋገጥ በተገኙት አባላት በጥሪው ላይ በተገለጸው
አጀንዳ ላይ ብቻ ስብሰባ ተደርጎ ውሳኔ ሊሰጥ ይችላል፡፡ በዕለቱ የተሠጠው ውሳኔ በሁሉም የማህበሩ አባላት ላይ ተፈፃሚ
ይሆናል፡፡
7. የአባላቱ ቁጥር ከመብዛታቸው የተነሳ የማህበሩ አባላት ሙሉ በሙሉ መሰብሰብ ካልቻሉ በውክልና መሰብሰብ ይቻላል፡፡
አወሳሰኑም ማህበሩ በሚያወጣው ደንብ የሚወሰን ይሆናል፡፡
8. ይግባኝ ውሳኔዎች የሚተላለፉት በስብሰባው በተገኙት አባላት የድምጽ ብልጫ ሆኖ እኩል ድምጽ ሲኖር ሰብሳቢው የደገፈው
ሀሳብ ተፈጻሚ ይሆናል፡፡

አንቀጽ ሰላሳ አራት

የስራ አመራር ቦርድ የስብሰባ ምእላተ ጉባኤ እና የውሳኔ አሰጣጥ ስነ ስርአት

1. የስራ አመራር ኮሚቴው በየወሩ መደበኛ ስብሰባ ያደርጋል፡፡


2. በተ/ቁ 1 የተጠቀሰው እንዳለ ሆኖ የስራ አመራሩ ሊቀመንበር ወይም የአመራሩ አባላት አስቸኳይ ስብሰባ እንዲደረግ ሲጠይቁ
እና ሲታመንበት አስቸኳይ ስብሰባዎች ይደረጋሉ፡፡
3. የስብሰባው ምእላተ ጉባኤ ከኮሚቴው አባላት ውስጥ ከግማሽ በላይ ከተገኙ የስብሰባው ምእላተ ጉባኤ እንደተሟላ
ይቆጠራል፡፡
4. የኮሚቴ ውሳኔዎች የሚተላለፉት በስብሰባው ከተገኙት አብላጫ ድምጽ ሆኖ በእኩል ድምጽ ሲሆን የአመራሩ ሰብሳቢ
የደገፈው ሀሳብ ተፈጻሚ ይሆናል፡፡
5. የሥራ አመራር ቦርዱ የራሱ የሆነ የሥነ ምግባር ደንብ እና መመሪያ አውጥቶ ተግባራዊ ማድረግ ይችላል፡፡

አንቀጽ ሰላሳ አምስት

ኦሮሚያ የግል ት/ቤቶች ማህበር -ፊንፊኔ


20
Waldaa Manneen Barnoota Dhuunfaa Oromiya Finfiine
የማህበሩ ገቢ ምንጭ

1. የማህበሩ አባላት የመመዝገቢያ እና አመታዊ መዋጮ


2. ከእርዳታ ሰጪዎች የሚገኝ ገንዘብ ወይም ንብረት
3. ከመጸሀፍ ሽያጭ ከሚገኝ አነስተኛ ገቢ፣ ከኢግዚቢሽኖች፣ ከተለያዩ ጽሁፎች እንዲሁም ከሌሎች ማህበሩ ለገቢ ምንጭነት
ከሚያቋቁማቸው ድርጅቶች የሚገኙ ገቢዎች ይሆናሉ፡፡

አንቀጽ ሰላሳ ስድስት

የበጀት አመት

የማህበሩ የበጀት አመት በየአመቱ ከሀምሌ 1 ቀን --------- ዓ.ም እስከ ሰኔ 30 ቀን ------------ ዓ.ም ይሆናል፡፡

አንቀጽ ሰላሳ ሰባት

የማህበሩ መተዳደሪያ ደንብ ስለማሻሻል

መተዳደሪያ ደንቡ በጠቅላላ ጉባኤው 3/4 ኛ ድምጽ እንዲሻሻል ሲወሰን የሚሻሻል ይሆናል፡፡

አንቀጽ ሰላሳ ስምንት

ስለ ማህበሩ መፍረስ

የጠቅላላ ጉባኤው አባላት ማህበሩ እንዲፈርስ ¾ ኛው እንዲፈርስ ሲወስኑ የሚፈርስ ይሆናል፡፡

ኦሮሚያ የግል ት/ቤቶች ማህበር -ፊንፊኔ


21

You might also like