Tsega, Haxiyat, Dinet

You might also like

Download as docx, pdf, or txt
Download as docx, pdf, or txt
You are on page 1of 11

መዉጫ

ሪዕስ ገፅ

1. መግብያ………………………………………………………………………………………

………………………. 2

2. ሕግ………………………………………………………………………….……… 3

1.1. የህግ ትርጉም…………………………………………………………………… 3

1.2. የሐዋርያውን ጳውሎስ የሙሴ ህግ እይታ ………………………..……………..3

1.3. ሕግ በአዲስ ክዳን አሰተምሮ……………………………………………………. 4

1.4. ሰለ ህግ የዘመኑ ቤተክርሰትያን ዕሳቤ…………………………………….….… 5

2. ፀጋ…………………………………………………………………………………..……..5

2.1. የፀጋ ትርጉም ……………………………………………………..………………5

2.2. ስነ-መለኮታዊ ጠቃመታ…………………………………………………..………6

2.3. ሰለ ፀጋ በአዲሰ ክዳን አሰተምሮ……………………………………………….. 6

2.4. የዘመኑ ቤተክርሰትያን ዕሳቤ ……………………………………….……………7

3. ድነት/ደህንነት………………………………………………………………….………….7

3.1. ድነት/ደህንነት ትርጉም…………………………………………………………..7

3.2. ስነ-መለኮታዊ ጠቃመታ…………………………………………….…………….8

3.3. ሰለ ድነት በአዲሰ ክዳን አሰተምሮ …………………………………………… 8

3.4. የዘመኑ ቤተክርሰትያን ዕሳቤ……………….….………………………………..10


4. ኃጢአት ……………………………………………………………………………….. 10
4.1. የኃጥያት ትርጉም …………………………………………………………….. 10
4.2. ስነ-መለኮታዊ ጠቃመታ ……………………………………………………… 11

4.3. ሰለ የኃጥያት በአዲሰ ክዳን አሰተምሮ ……………………………………… 11

4.4. የዘመኑ ቤተክርሰትያን ዕሳቤ …………………………………………………. 11

ሕግ፤ ፀጋ፤ ኃጥያት እና ድህነት 1


መግብያ

የሮሜ እና ገላትያ መልዕክት መሪ ሃሳብ ወይም ጭብጥ ወንጌል፤እምነት፤ ሕግ፤ ጽድቅ፤ ኃጥያት፤ የተሰፋ ቃል፤

አይሁድ፤ አህዛብ እና ወዘተ የሚሉ ጭብጦች በሁለቱም መልዕክቶች ዉስጥ ተጠቅሰዉ ይገኛሉ፡፡ይህንኑ

ሰቀድሞ ያሰተዋዉቃል፡፡ ራሱን እንደ ጻሐፊ ከገለጠ ቦሓላ በሞለኮታዊ ጥሪ ወንጌልን ለመስበክ እንደተላከ

ይናገራል፡፡ ጳውሎስን በግል ለማያውቁት እንዲያውም ይህ ምን A ልባት ስለ እርሱ መጥፎ ነገር ሰምተው

ለሚያውቁ ሰዎች እራሱን እና ስነመለኮቱን ለማስተዋወቅ ያደረገው ሙከራ ነው። ሐዋርያ ጳዉሎስ እና

የተሃድሶ አራማጂ አባቶች በገላትያና ሮሜ መልዕክቶች ዉሥጥ የተበራሩትን ጭብጦች በመጠቀም

በየዠመናቸዉ የተነሱትን የስሃተት ትምህርቶች ለመቐቐም ብዙ ዋጋ ከፍለዋል፡፡ መልዕክቶቹ እግዚአብሔር

የሰዉ ልጅ በእርሱና የእርሱም በሆነ እዉነት ላይ ያለዉን አመለካከት ሁሉ እንደት እንዴት እንደሚናገኝ

ያሳያል፡፡

በአጠቃላይ እነዚህ መልዕክቶች ሰዎችን የወሰደዉ የሰህተት ትምህርቶችን ጎርፎ እኛንም በፍጥነት ሆነ ቀስ

በቀስ በግልም ሆነ በጋራ እንዳይወሰደን ነዉ፡፡

ሕግ፤ ፀጋ፤ ኃጥያት እና ድህነት 2


1. ሕግ

1.1. የህግ ትርጉም፡-

ፅድቅን በስራ ለማገኘት የሚደርግ ጥረት ነዉ፡፡ ሮሜ፤ 3፤27 እና ገላ. 3፤10 – 12 ሕግ ማለት ለማድሪግ

የሚያዚዝ፡ ከማድርግ የሚያስከልክል ዉሳኔና ስሪዓት ነዉ፡፡ሥራዎችን በስርዓት ለመስራት ህጎችና

መመሪያዎች የግድ ያሰፈልጋሉ፡፡የሙሴ ህግ የተበለዉ የህጎች ሁሉ መሰረት የሆኑትን በእግዚአብሔር ጣት

የተጻፉትን አሥርቱ ትዕዛዛትን የሚያመለክት ነዉ፡፡ ህግ በራሱ ቅዱስ ነዉ፡፡ መንፈሳዊም ነዉ፡፡ ይከለክላል፤

ደግሞም ይፈቅደል፡፡ ሮሜ. 7፤ 12 - 14

1.2. ስነ-መለኮታዊ ጠቃመታ

እምነትም ሳይመጣ ሊገለጥ ላለው እምነት ተዘግተን ከሕግ በታች እንጠበቅ ነበር። እንደዚህ በእምነት

እንጸድቅ ዘንድ ሕግ ወደ ክርስቶስ የሚያመጣ ሞግዚታችን ሆኖአል፤ እምነት ግን መጥቶአልና ከእንግዲህ ወዲህ

ከሞግዚት በታች አይደለንም። ገላ. 3፡23-25  ሮሜ 7፡6 አሁን ግን ለእርሱ ለታሰርንበት ስለ ሞትን፥ ከሕግ

ተፈትተናል፥ ስለዚህም በአዲሱ በመንፈስ ኑሮ እንገዛለን እንጂ በአሮጌው በፊደል ኑሮ አይደለም። ገላ. 5፡1-4

በነጻነት ልንኖር ክርስቶስ ነጻነት አወጣን፤ እንግዲህ ጸንታችሁ ቁሙ እንደ ገናም በባርነት ቀንበር አትያዙ።

እነሆ፥ እኔ ጳውሎስ እላችኋለሁ። ብትገረዙ ክርስቶስ ምንም አይጠቅማችሁም። ሕግንም ሁሉ እንዲፈጽም

ግድ አለበት ብዬ ለሚገረዙት ሁሉ ለእያንዳንዶች ደግሜ እመሰክራለሁ። በሕግ ልትጸድቁ የምትፈልጉ

ከክርስቶስ ተለይታችሁ ከጸጋው ወድቃችኋል። ገላ. 5፥6 በክርስቶስ ኢየሱስ ሆኖ፥ በፍቅር የሚሠራ እምነት

እንጂ መገረዝ ቢሆን ወይም አለመገረዝ አይጠቅምምና።…በራሱ ርኩስ የሆነ ነገር እንደሌለ በጌታ በኢየሱስ

ሆኜ አውቄአለው… ሮሜ. 14፡14

1.2. የሐዋርያውን ጳውሎስ የሙሴ ህግ እይታ

ሀ. ከእግ/ር ነው ሮሜ 7፡!2-16

ለ. ሕግ በመጠበቅ ሰው አይፀድቅም ገላ. 3

ሐ. ሕግ ለክርስቲያኖች የእግ/ር ፈቃድ ነው

ሕግ፤ ፀጋ፤ ኃጥያት እና ድህነት 3


መ. አማኞች በብሉይ ኪዳን መፅሐፋት እንዲጠቀሙ መፅሐፋ ቅዱስ ያዛል ሮሜ 4፡23- 24, 15፡4, 1 ቆሮ 10፡6,

11, ሐዋ 15 ሮሜ 4

ሠ. በአዲስ ኪዳንም ሕጉ ይሰራል፤

 ከሃጢያት ነፃ መሆን ገላ 3፡15-29

 በሕብረተሰቡ መሃከል መመሪያ ይሆናል

 ክርስቲያኖች የታነፃ ኑሮ እንዲኖር ያደርጋል፡፡ ሐዋርያው ጳውሎስ ሕግ ቅዱስ ነው

ይላል ሮሜ 7፡12, 22 በሌላው A ቅጣጫ ክርስቶስ እርግማን ዋጅቶናል ይላል ገላ 3፡

13፡፡

1.3. ሕግ በአዲስ ክዳን አሰተምሮ

 ሕግን ሥራ በመሥራት ሥጋ የለበሰ ሁሉ በእርሱ ፊት ስለማይጸድቅ ነው፤ ኃጢአት በሕግ

ይታወቃልና። ሮሜ. 3፡20

 ሰው በኢየሱስ ክርስቶስ በማመን እንዲጸድቅ እንጂ በሕግ ሥራ እንዳይሆን አውቀን፥ ሥጋን የለበሰ

ሁሉ በሕግ ሥራ ስለማይጸድቅ፥ እኛ ራሳችን በሕግ ሥራ ሳይሆን በክርስቶስ እምነት እንጸድቅ ዘንድ

በክርስቶስ ኢየሱስ አምነናል። የእግዚአብሔርን ጸጋ አልጥልም፤ ጽድቅስ በሕግ በኩል ከሆነ እንኪያስ

ክርስቶስ በከንቱ ሞተ። ገላ. 2፡21

 ጻድቅ በእምነት ይኖራል ተብሎአልና ማንም በእግዚአብሔር ፊት በሕግ እንዳይጸድቅ ግልጥ ነው።

ገላ. 3፡11

 ከሥጋ የተነሣ ስለ ደከመ ለሕግ ያልተቻለውን፥ እግዚአብሔር የገዛ ልጁን በኃጢአተኛ ሥጋ ምሳሌ

በኃጢአትም ምክንያት ልኮ አድርጎአልና፤ እንደ መንፈስ ፈቃድ እንጂ እንደ ሥጋ ፈቃድ በባንመላለስ

በእኛ የሕግ ትእዛዝ ይፈጸም ዘንድ ኃጢአትን በሥጋ ኰነነ። ሮሜ 8፡3

 እንግዲህ ወንድሞች ሆይ፥ በእርሱ በኩል የኃጢአት ስርየት እንዲነገርላችሁ፥ በሙሴም ሕግ

ትጸድቁበት ዘንድ ከማይቻላችሁ ሁሉ ያመነ ሁሉ በእርሱ እንዲጸድቅ በእናንተ ዘንድ የታወቀ ይሁን።

ሐዋ. 13፡39  እንግዲህ ወንድሞች ሆይ፣ የሃጢአት ይቅርታ የሚገኘው በኢየሱስ በኩል መሆኑ እንደ

ተሰበከላችሁ እወቁ፤ በእርሱ የሚያምን ሁሉ በሙሴ ሕግ በኩል ማግኘት ያልተቻለውን ጽድቅ

ያገኛል።

ሕግ፤ ፀጋ፤ ኃጥያት እና ድህነት 4


1.4. ሰለ ህግ የዘመኑ ቤተክርሰትያን ዕሳቤ

 አማኞች በሕግ ሳይሆን በእየሱስ ፀገ ማዳናችዉን ታሰተምራለች፡፡

 ስዉ ከዳነ በኃላ ህግን የምጠብቀዉ ለመፅደቅ ሳይሆን ሰለ ተለወጠ መሆኑን ታሰተምራለች፡፡

 ፀጋ እንድበዛ በኃጥያት ፀንተን መኖር ሳይሆን በአዲስ ህይዎት መኖር እንደለብን ዘንድ

ታሰተምራለች፡፡
2. ፀጋ
2.1. የፀጋ ትርጉም
ያለምንም የሰዉ ክፍያ በእግ/ር ለሰዉ ሌጆች የተሰጠ ነፃ ስጦታ ነዉ፡፡ ሮሜ. 3፤24 በጸጋ መጽደቅ የሚገኘዉ

‹‹በእየሱስ ክርስቶስ ቤዛነት ነዉ፡፡›› ይህም እግዚአብሔር ሰዉን የሚያድንበት ምክንያት ነዉ፡፡ ፀጋ ማለት

ሀጢያተኛው እና ሙታን የሆነው እንዲሁም በደለኛ የሆነው ሰው ንፁህ ነውር ከሌለበት ህይው ከሆነው

ከእግዚአብሔር ጋር የሚገናኝበት መንገድ ነው፡፡ ሮሜ 11፤5 - 6 በኢየሱስ ክርስቶስም በሆነው ቤዛነት በኩል

እንዲያው በጸጋው ይጸድቃሉ። ፀጋ የሰጪውን ትልቅነት አፍቃሪነት ሙሉ ማንነት እንጂ የተቀባዩን ማንነት

የማያሳይ ነው፡፡ የኃጢአት ደመወዝ ሞት ነውና፤ የእግዚአብሔር የጸጋ ስጦታ ግን በክርስቶስ ኢየሱስ በጌታችን

የዘላለም ሕይወት ነው። በደንብ ማወቅ ያለብን ነገሮች፡-

1. ስጦታ ማለት በሁለት አካላት መካከል ባለ መስማማት መዋደድ የሚሰጥ ነው፡፡ አግዚአብሔር ለእኛ

ይህን አልሰጠንም ምክንያቱም ምንም መስማማት ህብረትም የለንም ነበርና፡፡

2. ደሞዝ ማለት አንድ ሰው ለሰራው ስራ ላወጣለት ጉልበት እውቀት ግዜ የሚከፈለው ነው፡፡ ዋናው

የእኛ ስራ ምንድነው? ሀጢያት ነው፡፡ ስለዚህ ደሞዛችንን ሞት ነው፡፡ ስለዚህ አግዚአብሔር የሰጠን

ደሞዛችንን አይደለም፡፡ የኃጢአት ደመወዝ ሞት ነውና፡፡

3. ፀጋ ይሄ ደግሞ ያለ ምንም ስራ ያለምንም ህብረት የተቀባዩን ማንነት ሳይመለከት የሰጪውን

ትልቅነት የሚያሳይ ነው፡፡ይሄ ነው ለእኛ የተሰጠው፡፡ ጌታ ይመስገን፡፡

" የኃጢአት ደመወዝ ሞት ነውና፤ የእግዚአብሔር የጸጋ ስጦታ ግን በክርስቶስ ኢየሱስ በጌታችን

የዘላለም ሕይወት ነው። ሮሜ 6:23 ሰዎችን ሁሉ የሚያድን ፀጋ ተገልጧል፡፡ ሰዎቸን ሁሉ ያለበት

ምክንያት ሁሉ ሀጢያትን ሰርቷል፡፡ ስለዚህ ሁሉ ከሰራ ሁሉን የሚያድን ነገር ያስፈልጋል፡፡ እርሱም ፀጋ

ነው፡፡ ፀጋው አሁን ተገልጧል እንጂ አልተፈጠረም፡፡ አለም ሳይፈጠር የተዘጋጀ ነበር፡፡ ነገር ግን ከሰው

ተሰውሮ ነበር አሁን ግን የእግኢአብሔር ፀጋ ተገለጠ ፡፡

ሕግ፤ ፀጋ፤ ኃጥያት እና ድህነት 5


2.2. ስነ-መለኮታዊ ጠቃመታ
ዋናኛዉ ከኃጥያት የምንድንበትና የእግ/ር ዕቅርታ የምንቀበለበት ነዉ፡፡
ራሳችን ዕንድንገዛና መልካም ተግባር ዕንድናደርግ በመከራም እንድን ፀና እና ፈተናን ድል እንድናደርግ
በዉሰጣችን ኃይልን ይሰጠናል፡፡
የምንድነዉ በመልካም ስራችን ሳይሆን እነድሁ በፀጋ እንደሆነ እነድናዉቅ ይረዳናል፡፡ ሮሜ. 11፤6
እየሱስ ዕራሱ ታላቅ የእግ/ር ፀጋ መገለጫ ሰለሆነ በርሱ ለመኑት ሁሉ እግ/ር ይቅርታ በነፃ
ይሠጠቸዋል፡፡ ሮሜ. 4፤5፣ 3፤24
2.3. ሰለ ፀጋ በአዲሰ ክዳን አሰተምሮ

ጸጋ፥ ኃጢአተኝነትንና ዓለማዊን ምኞት ክደን፥ የተባረከውን ተስፋችንን እርሱም የታላቁን የአምላካችንንና

የመድኃኒታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን ክብር መገለጥ እየጠበቅን፥ ራሳችንን በመግዛትና በጽድቅ

እግዚአብሔርንም በመምሰል በአሁኑ ዘመን እንድንኖርያስተምረናል፡፡

ከኮነኔ የዳነዉ በፀጋ መሆኑን ያሰተምራል፡፡ ከፀጋ በታች እንጂ ከህግ በታች ሰላልሆንን ኃጥያት አይገዛንም

ይላል፡፡

ሀጢያትን የሚያስክድ የፀጋ ስራ ነው፡፡ ፀጋው እንዳዳነን ፀጋው እራሱ ሀጢያትን አለማዊ ምኞትን ያስክደናል፡፡

ፀጋው እግዚአብሔርን የማያስከብር፡ የማይመስል ነገር ሁሉ በማስወገድ ወደ እግዚአብሔርን እሱን ወደ

ሚመስል ማንነት ይለውጠናል፡፡

ጌታ እየሱስን እንድነጠብቅ የሚረዳን ፀጋው ነው፡፡ የጌታችንን የኢየሱስን መምጣት

መጠበቅ ሲባል ሲከፋን እና ከሰው ጋር በሰላም መኖር ሲያቅተን በር ዘግቶ የምፅአት መዝሙር መዘመር

አይደለም፡፡ መጠበቅ በከፍታም በዝቅታ በማግኘት ይሁን በማጣት በማንኛውም ሁኔታ ውስጥ የማያቋርጥ

የህይወት ባህሪ መሆኑን ያሰተምራል፡፡

ብዙ ክርስቲያን የሚያደንቁት ከአጋንት እስራት ነፃ መውጣቸውን ብቻ ነው፡፡ በዚህም ምክንያት ቀጣዩን

የእግዚአብሔር እቅድ አያውቁም፡፡የእግዚአብሔር ፀጋ ሰውን ከዲያብሎስ እጅ የማስለቀቅ አለማ ብቻ

ቢኖረው ደህንነት አጅግ አሳዛኝ ይሆን ነበር፡፡

ምሳሌ አስራኤላዊያንን እግዚአብሔር ከግብፅ በርነት በክብር የማስለቀቅ ቀይ ባህርን የማሻገር ሀሳብ ብቻ

ቢኖረው የተሻገረው ህዝብ ምድረ በዳ ላይ ተቅበዝብዞ የሚጠፋ ህዝብ በሆነ ነበር፡፡ ነገር ግን አምላክ

እግዚአብሔር ከዚያ የሚበልጥ የከበረ አለማ ነበርው፡፡ የተሻገረውን ህዝብ ወደ ማርና ወተት የምታፈሰው

ምድር ማስገባት፡፡

ሕግ፤ ፀጋ፤ ኃጥያት እና ድህነት 6


ልክ እንዲሁ በክርስቶስ የተገለጠው ፀጋ ከሰይጣን ከሀጠያትና ከአለም ተፀኖ በማውጣት)

የቆመ ብቻ ሳይሆን ከዘላለም በፊት የተወሰልንን የእግዚአብሔርን ህይወት ያወርሰናል፡፡እግዚአብሔር

በመጽሐፍ ቅዱስ እንደተናገረው ሰው ያለሕግ እና ያለመልካም ስራ በነጻ በክርስቶስ የቤዛነት ስራ

በማመን በጸጋ ብቻ መጽደቅ እንደ ምቻል ያሰተምራል።

2.4. የዘመኑ ቤተክርሰትያን ዕሳቤ

ሐጥያተኛ ሰው የሚጸድቀው ጸጋውን በእምነት በመቀበልና በክርስቶስ የጸጋ ወንጌል ብቻ መሆኑን


ታሰተምራለች፡፡

ከጸጋ ወንጌል ውጭ የሚሰብክ ማንኛውም ፍጥረት በመለኮታዊ እርግማን ስር ነው፡፡

በጸጋ ከዳንን የሕግ ሰባኪዎች አርነታችንን (ነጻነታችንን) እንዲሰልሉ ልንፈቅድላቸው ፈጽሞ አይገባም፡፡

የወንጌል እውነት ጸንቶ እንዲኖር ታላላቅ የእግዚአብሔር ሰዎች እንኳን ወደ ሕግ ፈቀቅ ቢሉ ሊወቀሱ

ይገባቸዋል፡፡ ሰው በኢየሱስ ክርስቶስ በማመን እንጂ ሕግን በመፈጸም ከቶ ሊጸድቅ አይችልም፡፡ ነገርግን ሰው

በኢየሱስ ክርስቶስ በማመን እንዲጸድቅ እንጂ በሕግ ስራ እንዳይሆን አውቀን ስጋን የለበሰ ሁሉ በህግ ስራ

ስለማይጸድቅ እኛ ራሳችን በህግ ስራ ሳይሆን በክርስቶስ እምነት እንጸድቅ ዘንድ በክርስቶስ ኢየሱስ አምነናል፡፡

የእግዚአብሔርን ጸጋ መጣል አይገባም፡፡ ጽድቅ የሚገኘው ሕግን በመፈጸም ከሆነ ክርስቶስ መሞት

አያስፈልገውም ነበር ብላ ታሰተምራለች፡፡ ፀጋ በነፃ ሰለ ተሰጠን ሪካሸ እነዳል ሆነ አጥብቃ ታሰተምራለች፡፡

3. ድነት/ደህንነት

3.1. ድነት/ደህንነት ትርጉም

ድነት ማለት በመድሃታችን በኢየሱስ ክርስቶስ በማመንና ንስሃ በመግባት ብቻ ከሀጢያትና ፍርድ በማምለጥ

የሚገኝ ዘላለማዊ ህይወት ነው፡፡ የድነት መንገድ ሰው ከሀጢያትና ከዘላለማዊ ሞት ድኖ ህይወት እንዲያገኝ

የሚያስችለውን ስራ መስራት ስለማይችል እግዚአብሔር አንድያ ልጁን ኢየሱስ ክርስቶስን በማመን ነዉ፡፡

ሮሜ 6፡23

ድነት በክርሰቶስ የመሰቀል ስራ የምገኝ ነዉ፡፡ ሮሜ 3፤25 የዘላለም ህዎት ዋሰትና ማግኝት ነዉ፡፡ ሮሜ 5፤1-2

3.2. ስነ-መለኮታዊ ጠቃመታ

ሕግ፤ ፀጋ፤ ኃጥያት እና ድህነት 7


ድነት/ደህንነት (Salvation) በውስጡ ሦስት ነገሮችን ያካትታል፤ ቃሉ የግዕዝ ቃል ሲሆን ‹መዳን› የሚለውን

ሐሳብ ያመለክታል፡፡ መዳን በመጀመሪያ ችግሩን (ሰውን ያሰመጠ ውኃ)፣ በሁለተኛ የሚድነውን (በውኃ

ውስጥ የሰመጠ ሰው)፣ በሦስተኛ አዳኙን (ሰውን ከውኃ መስመጥ የሚያድን ዋናተኛ) ያካትታል፡፡ ውኃ

ውስጥ የገባ ሰው ቢኖር፣ ከውኃ ውስጥ የሚያወጣው ሌላ ሰው ያስፈልገዋል፤ የታመመ ካለ የሚያድን ሰው

ያስፈልገዋል፡፡ ወድቆ የተሰበር ካለ ጠግኖ የሚያድነው ይፈልጋል፡፡ ኃጢአት ካለ ኃጢአተኛ ይኖራል፣

ኃጢአተኛ ካለ ከኃጢአት የሚያድን አዳኝ መኖር አለበት፡፡ አዳምና ሔዋን ኃጢአት በመሥራታቸው

ምክንያት ኃጢአተኛ እንደሆኑ መጽሐፍ ቅዱስ ያስተምረናል፡፡ አዳምና ሔዋን ኃጢአት በሠሩ ጊዜ

እግዚአብሔር የወሰደው የፍርድ እርምጃ ሞት ነበረ፡፡

ከአግ/ር ዘንድ ለሰዉ የተሰጠ የመዳን መንገድ በዕመነት በመቀበል እና የኃጥያጥ ዕቅርታ በማግኝት መሆኑን
ያተምራል፡፡ ድነት የፀጋ ስጦታ ዕንጂ የመልካም ስራ ዋጋ አለመሆኑን እንድናዉቅ ይረዳናል፡፡

3.3. ሰለ ድነት በአዲሰ ክዳን አሰተምሮ

ሐዋርያው ጳውሎስ በሮሜ መልእክቱ ሰው ኃጢአተኛ ነው እንደሚል ከኃጢአቱም ሊድን የሚችልበትን

መድኃኒት እንዲህ በማለት ያስቀምጣል፡፡ ‹‹በኢየሱስ ክርስቶስም በሆነው ቤዛነት በኩል እንዲው በጸጋው

ይጸድቃሉ›› (ሮሜ 3፡24) ፣ ‹‹የእግዚአብሔር የጸጋ ስጦታ ግን በክርስቶስ ኢየሱስ በጌታችን የዘላለም

ሕይወት ነው›› (ሮሜ 6፡23) ፡፡ ድነት ስንል ኃጢአትን፣ ኃጢአተኛንና አዳኝን ሦስቱንም ሐሳቦች

እንደሚያጠቃልል አይተናል፡፡ ድነት ኃጢአት ከሚያመጣው ሞት ድኖ በሕይወት መኖርን ያሰተምራል፡፡

ሰው ድነት ቢያስፈልገውም ራሱን ማዳን በፍጹም አይችልም፤ ምክንያቱም የኃጢአት ዋጋ ሞት ስለሆነ

ሰው ያንን ዋጋ ሊከፍል በፍጹም አይችልም፡፡ ሰው ኃጢአት ካመጣው ፍርድና ሞት ለመዳን ሕግን

ቢጠብቅም፣ የሥነ ምግባር ሕይወትን ለመኖር ቢሞክርም፣ እንዲሁም የተለያዩ ሃይማኖቶችን መሥርቶ

ቢከተልም ራሱን ማዳን በፍጹም አልቻለም፡፡ የሰው ልጅ ከወደቀበት ውድቀት ለመነሳትና ከተፈረደበት

ፍርድ ነፃ ለመሆን በራሱ ሞክሮ አቅቶታል፤ ለዚህ ነው አዳኝ ያስፈለገው፡፡

ኢየሱስ ክርስቶስ እኛን ከእግዚአብሔር ጋር ለማስታረቅ እኛ መፈጸም የሚገባንን ሕግ እርሱ ፈጸመ፤

መክፈል የነበረብንን ዕዳ እርሱ ስለ እኛ በሞቱ ከፈለው፡፡ ስለዚህ ድነት የተፈጸመው በክርስቶስ የመስቀሉ

ሥራ ብቻ ነው፤ ‹‹የሚያምኑ ሁሉ ይጸድቁ ዘንድ…›› (ሮሜ. 10፡4) ፣ ‹‹…ክርስቶስ ስለ እኛ እርግማን ሆኖ

ሕግ፤ ፀጋ፤ ኃጥያት እና ድህነት 8


ከሕግ እርግማን ዋጀን›› (ገላ. 3፡13)፡፡ ስለዚህ ከኃጢአት መዳን የምንችለው ጌታ በመስቀሉ ላይ

በፈጸመው የድነት ሥራ በማመን ብቻ ነው፡፡

እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን እስኪሰጥ ድረስ ዓለሙን እንዲሁ ወዶአልና››

በማለት የእግዚአብሔርን ፍቅር በግልጽ ያሳየናል፡፡ የአብ ጸጋ የተገለጠው በፍቅሩ ነው፣ ፍቅሩ ደግሞ

የተገለጠው ልጁን በመስጠቱ ነው፡፡ጳውሎስ በሮሜ. 5፡8 ላይ ‹‹ነገር ግን ገና ኃጢአተኞች ሳለን ክርስቶስ ስለ

እኛ ሞቶአልና እግዚአብሔር ለእኛ ያለውን የራሱን ፍቅር ያስረዳል›› በማለት እግዚአብሔር ሰውን ሁሉ

እንደ ወደደ ያሳያል፡፡ እርሱም ክርስቶስ›› (ገላ. 3፡16) በማለት የዓለም አዳኝ የሆነው ክርስቶስ፣ ከአብርሃም

ዘር መምጣቱን ያመለክተናል፡፡ ስለዚህ የአብርሃም መመረጥ ለድነት ሳይሆን ለአገልግሎት ነው፡፡

ለአገልግሎት መመረጥና ለድነት (ደህንነት) መመረጥ ልዩነት እንዳላቸው አስቀድመን መረዳት ይኖርብናል፤

ጳውሎስም ‹‹ዓለም ሳይፈጠር በፊቱ ቅዱሳንና ነውር የሌለን በፍቅር እንሆን ዘንድ በክርስቶስ መረጠን››

ሲል፤ ክርስቲያኖችም በዚህ የምርጫ መደብ ውስጥ በኤፌሶን 1፡4 መሠረት መግባታችንን ያመለክታል፡፡

ይህን ጥቅስ የበለጠ ለመረዳት ወደ ወደ ሮሜ 8፡28-30 ላይ ያለውን አዛምደን በመመልከት ግልጽ ለማድረግ

ያስፈልጋል፤ ‹‹…እግዚአብሔር አብ አስቀድሞ እንዳወቃቸው በመንፈስም እንደሚቀደሱ፣ ይታዘዙና

በኢየሱስ ክርስቶስ ደም ይረጩ ዘንድ ለተመረጡት…›› ‹‹እግዚአብሔርንም ለሚወዱት እንደ አሳቡም

ለተጠሩት ነገር ሁሉ ለበጎ እንዲደረግ እናውቃለን፡፡ እግዚአብሔር ላለማዳን በማንም ላይ ፈርዶ አያውቅም፡፡

ነገር ግን ለመዳን የተሰጣቸውን ዕድል ሳይጠቀሙበት ጸጋውን ቸል በማለታቸው ሊጠፉ ያሉትን አስቀድሞ

አወቃቸው በማለት ያሰተምራል፡፡

3.4. የዘመኑ ቤተክርሰትያን ዕሳቤ

 ድነት ከእግ/ር ዘንድ ለሰዉ የተሰጠ የመዳን መንገድ በዕምነት መቀበል መሆኑን ታሰተምራለች፡፡
 ድነት የኃጥያት ይቅርታ በማገኝት የሚከናወን ብሆንም በትጋት የምፈፅም መሆኑን ታሰተምራለች፡፡

4. ኃጢአት
4.1. የኃጥያት ትርጉም

ከአግ/ር ክብር መጉደል ነዉ፡፡ ሮሜ 3፤23

ሕግ፤ ፀጋ፤ ኃጥያት እና ድህነት 9


ኃጥያት የእግዚአብሔርን ህግ መተላለፍ ነዉ፡፡የእግዚአብሔርን ፍቃድ መቃወም፤ በየእግዚአብሔር ላይ

ማመጽና መነሳት ነዉ፡፡ ኃጢአት የእግዚአብሔርን ሥልጣን፤ ፍቅርና ጥበብ አለመቀበል ነዉ፡፡ ኃጢአት

የእግዚአብሔርንና እርሱ የተናገረዉን መጠራጠር፤ እርሱ በተናገረዉ ላይ እምነት ማጣት ነዉ፡፡ ኃጢአት

ከእግዚአብሔር አመራር እና ሥርዓት ዉጪ መኖር ወይም ለመኖር መፈለግ ነዉ፡፡ ዓመፃ ሁሉ ኃጥያት ነዉ፡፡

ኃጠአት በመጽሐፍ ቅዱስ የተገለጸው የእግዚአብሔርን ሕግ እንደመተላለፍ ነው፡፡ ኃጢአት የጀመረው

በሉሲፈር ነው፣ እኛም የአዳም ዝርያዎች ከእርሱ ኃጢአትን ወረስን። ሮሜ 5፡12 የሚነግረን በአዳም

ምክንያት ኃጢአት ወደ ምድር መግባቱን ነው፣ ሞትም ወደ ሰዎች ሁሉ ተላለፈ፣ “የኃጢአት ዋጋው ሞት”

በመሆኑ ምክንያት (ሮሜ 6፡23)።

ሌለኛው የኃጢአት ዓይነት የፍቃድ (የግል) ኃጢአት በመባል ይታወቃል። በሁለቱም፣ በገንዘብና በሕጋዊ

መቼቶች ጥቅም ላይ ሲውል፣ የግሪኩ ቃል ሲተረጎም “የግል” ማለት “የአንዱ የሆነውን ነገር መውሰድና

በሌለኛው ሒሳብ ማስቀመጥ ነው።” የሙሴ ሕግ ከመሰጠቱ በፊት ኃጢአት በሰው ላይ አልተቆጠረም ነበር፣

ምንም እንኳ ሰዎች በውርስ ኃጢአት ምክንያት ኃጢአተኞች የነበሩ ቢሆኑም። ሕግ ከተሰጠ በኋላ፣ ሕግን

በመጣስ ምክንያት ኃጢአት መታሰብ (መቆጠር) ጀመረ፣ በእነርሱ ላይ (ሮሜ 5፡13)። ከሕግ መተላለፍ በፊት

እንኳ ቢሆን፣ በሰው ላይ ተቆጠረ፣ የመጨረሻው የኃጢአት ቅጣት (ሞት) መግዛቱን ቀጠለ (ሮሜ 5፡14)።

ሰዎች ሁሉ፣ ከአዳም እስከ ሙሴ፣ በሞት ሥር ነበሩ፣ የሙሴን ሕግ በኃጢአታዊ ድርጊታቸው በመቃወም

ሳይሆን፣ (እነርሱም ያልነበራቸውን)፣ ነገር ግን በወረሱት በገዛ ራሳቸው የኃጢአት ተፈጥሮ ምክንያት። ከሙሴ

በኋላ፣ ሰዎች ለሞት ተገዢ ሆኑ፣ በሁለቱም፣ ከአዳም በወረሱት ኃጢአት እና ፈቅደው የእግዚአብሔርን

ሕግጋት በመጣሳቸው ምክንያት።

የግል ኃጢአትን ላለመሥራት፣ ምክንያቱም በእኛ ላይ በሚያድረው በመንፈስ ቅዱስ ኃጢአትን ለመቋቋም

ኃይልን ስለምናገኝ፣ እኛን በመቀደስና ኃጢአተኝነታችንን በማሳሰብ፣ በምንተላለፍበት ጊዜ (ሮሜ 8፡9-11) ።

እኛ ሁላችንም ሦስት ጊዜ ተኮንነናል፣ በውርስ ኃጢአት፣ በፍቃድ ኃጢአት፣ እና በግል ኃጢአት ምክንያት።

ለዚህ ኃጢአት ብቸኛው ትክክለኛ ቅጣት ሞት ነው (ሮሜ 6፡23) ፣ ክርስቲያኖች ኃጢአትን ማስወገድ

አለባቸው ምክንያቱም ኃጢአት ከአብ ፣ ከወልድ እና ከመንፈስ ቅዱስ ጋር ካለው የሕብረት ስምምነት

የሚያርቀን ከእግዚአብሔር ጋር ባለን ግንኙነት መቋረጥ ነው ፡፡

4.2. ስነ-መለኮታዊ ጠቃመታ

 ኃጥያት ከእግ/ር የሚለየንና ከክብሩም የምያጎለን እንደሆነ እንድናዉቅ ዘንድ ይረዳናል፡፡


ሕግ፤ ፀጋ፤ ኃጥያት እና ድህነት 10
 ስዉ ሁሉ ኃጥያተኛ መሆኑን አዉቆ ንስሐ በመግባት (በጌታ በማመን) ከኃጥያት የሰዉ ልጆች ሁሉ
እንድድኑ አበክራ ተሰተምራለች፡፡
 የኃጥያት ይቅርታ በክርሰቶስ በማመን እንደምገኝ ያሰተምረናል፡፡
4.3. ሰለ የኃጥያት በአዲሰ ክዳን አሰተምሮ

ኃጥያት ከእግ/ር ክብር የሚያጎል ጠላታችን መሆኑን በደንብ ያሰረዳናል፡፡

 ስዉ ልጆች ሁሉ የአዳም ልጆች በመሆናችዉ ኃጥያተኞች መሆናችዉን ያሰተምራል፡፡ ሮሜ 5፤12

 ሰዎች ዕራሳችዉን በሰሩት ኃጥያት ሚክንያት ኃጥያተኛ መሆናችዉን ያሰተምረናል፡፡ ሮሜ 3፤23

 ሐጥያት ገዳይ በሽታ መሆኑንና መዲሃንቱ የእየሱስ እየሱስ ክርስቶስ ደም መሆኑን ያሰተምረናል፡፡

 ሐጥያት ከእግ/ር መንግሰት (ከዘላለም ህዎት) ሊያሳጣ የሚችል ጠላት መሆኑን ያሰረዳል፡፡

4.4. የዘመኑ ቤተክርሰትያን ዕሳቤ

 ሰዉ ሁሉ ኃጥያተኛ መሆኑን ታምናለች፡፡ የኃጥያት መዳንት ሆኖ የቀረበዉን እየሱስን በማመንና

በደሙ በመታጠብ ከኃጥያት መዳን እንደምንችልተሰተምራለች፡፡ የኃጥያት ደሞዝ ሞት እንደ ነዉና፡፡

ሕግ፤ ፀጋ፤ ኃጥያት እና ድህነት 11

You might also like