Download as pdf or txt
Download as pdf or txt
You are on page 1of 8

‫إعداد‪:‬‬

‫الشيخ عبدالرزاق بن عبدالمحسن البدر‬

‫‪ትርጉም፡ ዩሱፍ አሕመድ‬‬


ምስጋና ለአላህ ይገባው ፡፡ በእርሱ እመካለሁ ፣ ወደርሱ ተጸጽቸ እመለሳለሁ ፡፡ ከአላህ
በቀር በእውነት የሚመለክ አምላክ የሌለ መሆኑን ፣ ሙሐመድ ‫ ﷺ‬የአላህ
አገልጋይና መልክተኛ መሆናቸውን ፣ እስከ እለተ ሞታቸው ድረስ ህዝብን በትክክል
የመከሩና የተሰጣቸውን አደራ በአግባቡ የተወጡ መሆናቸውን ፤ መልካም ነገር ኖሮ
የተውት ፣ መጥፎ ነገር ኖሮ ያላስጠነቀቁት አንድም ነገር የለም ብየ በእርግጠኝነት
እመሰክራለሁ፡፡ በእርሳቸው ፣ በቤተሰቦቻቸውና በባልደረቦቻቸው ላይ የአላህ ሶላትና
ሰላምታ ይስፈን፡፡
ከዚህ በመቀጠል፡
‫ أن رسول هللا صلى‬، ‫روى اإلمام أحمد في "مسنده" من حديث عبد هللا بن عمرو‬
، ‫ حفظ أمانة‬، ‫ "أربع إذا كن فيك فال عليك ما فاتك من الدنيا‬:‫هللا عليه وسلم قال‬
"‫ وعفة في طعمة‬، ‫ وحسن خليقة‬، ‫وصدق حديث‬
“ሙስነድ” በተባለው የኢማም አህመድ ኪታብ ዓብደሏህ ብን ዓምር 4
የሚከተለውን ሐዲስ አስተላልፈዋል፡-
“አራት ነገሮች ካንተ ዘንድ ካሉ ባመለጠህ (የዱንያ ትርፍ) ምንም ዓይነት ችግር በአንተ
ላይ የለብህም ፤ አደራን መጠበቅ ፣ እውነት መናገር ፣ መልካም ስነ-ምግባር ፣
(ሐራም የሆኑ) ምግቦችን አለመዳፈር ናቸው፡፡” አህመድ፡ ሐዲሱን አላባኒ ሶሂህ ብለውታል ሶሂህ
አል ጃሚዕ፡

ይህ ሐዲስ ሁሉም ነጋዴ ወደተግባር ሊቀይረውና የአይኑ ማረፊያ ሊያደርገው


የሚገባ ሐዲስ ነው፡፡ በዚህ ሐዲስ ውስጥ ገንዘብ ይዞ ወደ ንግድ ሙያ ለመሰማራት
የፈለገ ማንኛውም አካል በንግድ ሂደቱ ላይ ለሚፈጠሩ አደገኛ ሁኔታዎች መከላከያ
የሚሆኑ ጥበብ የተሞላባቸው መፍትሄዎች ተካተውበታል፡፡ ነጋዴዎች የፈለገውን ያክል
ትርፍ ቢያተርፉ በዚህ ሐዲስ ውስጥ የተወሱ አራት ጽኑ የሆኑ አንኳር መርሆዎችን
እስካልጠበቁ ድረስ የሚነግዱት ንግድ በፍጹም ሰላም ሊሆን አይችልም፡፡ እንዴውም
እነዚህን መርሆዎች ለእያንዳንዷ የንግድ እንቅስቃሴው ለሰከንድ ያክል እንኳ
የማትጠፋ ጽኑ መሰረት ሊያደርጋቸው ይገባል፡፡ የረሡልን ‫ ﷺ‬ምክሮች በአግባቡ
ተግባራዊ አድርጎ ከፊት ለፊቱ ተስፋ የሚያደርገው ትርፍ ቢያመልጠው እንኳ
አመለጠኝ ብሎ ጸጸት ውስጥ ሊገባ አይገባም፡፡
1/6
የአላህ መልክተኛ ‫ﷺ‬ የሚከተለውን ተናግረዋል፡-
"‫"فال عليك ما فاتك من الدنيا‬
“ከዱንያ ባመለጠህ (ትርፍ) ምንም ዓይነት ችግር በአንተ ላይ አይኖርም፡፡” አህመድ፡
ሐዲሱን አላባኒ ሶሂህ ብለውታል ሶሂህ አል ጃሚዕ፡

ወደ ንግድ አንድ ብሎ የገባ ሰው ሰፊ የሆነ ትርፍ ለማግበስበስ ሲባል ከንግድ


መርሆዎች ወጥቶ ማጭበርበርን ልክ እንደህጋዊ የንግድ መርሆ አድርጎ የሚጠቀምበት
አጋጣሚ አለ፡፡ በዚህ አጋጣሚ አጭበርብሬ ትርፍ ላግኝ ወይስ ረሡል ‫ﷺ‬
የተናገሯቸውን አራቱን የንግድ መሰረታዊ መርሆዎች ልጠብቅ? በሚል ከነፍሳቸው
ጋር ግብ ግብ የሚገጥሙ በኢማናቸው ደካማ የሆኑ ሙስሊሞች ይኖራሉ፡፡ ግልጽ ኪሳራ
ውስጥ ቢገቡም ወይም በርካታ የሆነ ትርፍ ቢያመልጣቸውም የረሡልን ‫ ﷺ‬ምክር
መስማትና ተግባራዊ ማድረግ ይኖርባቸዋል፡፡ ባመለጣቸው ትርፍ አላሁ ‫ ﷻ‬የተሻለውን
ይቀይራቸዋል፡፡ ምክንያቱም የሲሳይ ምንጩ አላህ እንጅ ሌላ ማንም አይደለም፡፡
“ባመለጠህ (ትርፍ) ምንም ዓይነት ችግር በአንተ ላይ አይኖርም፡፡” የሚለው የረሡል
‫ﷺ‬ ንግግር ለነጋዴዎች ትልቅ ዋስትና ነው፡፡ ይህ ማለት የምታገኘው ትርፍ ትልቅ እንኳ
ቢሆን አንተ በመልካም ሁኔታ ላይ ነው ያለኸው ፤ የዱንያን ትርፍ ብታጣ ከአኼራ
ትርፍ አታጣም ፤ በዱንያም ላይ ቢሆን አላህ የተሻለ ነገር ይቀይርሃል፡፡ በዚህ ምክንያት
ማንኛውም ነጋዴ ለእነዚህ አራት መሰረታዊ መርሆዎች ትኩረት ሊሰጥና በጽናት
ሊጠብቃቸው ይገባል፡፡
አደራን መጠበቅ
የመጀመሪያው የረሡል ‫ ﷺ‬ምክር ስትሸጥ ስትለውጥ አለመዋሸት ፣
አለማጭበርበርና ቃል ኪዳን መጠበቅ ፤ ገንዘብ በአደራ መልክ የተቀበልካቸው አካላት
ካሉ በአግባቡ መመለስ እንደሚገባህ የሚያስገነዝብ ነው፡፡ ሰዎች በአብዛኛው ወደ
ንግዱ አለም ሲገቡ የተሰጣቸውን አደራ ከመጠበቅ ላይ መንሸራተት ይስተዋልባቸዋል፡፡
አብዛኛው ሰው በዚህ ፈተና ውስጥ የወደቀ ነው፡፡ ለዚህች አላፊ የዱንያ ጥቅም ብሎ
አደራውን ያጠፋል ፤ አንዳንዱ እንደአየሩ ሁኔታ ባህሪው ይገለባበጣል ፤ ሰዎች ቃል
ኪዳን ከጠበቁ እርሱም ይጠብቃል ፤ ካጭበረበሩ ደግሞ እርሱም ያጭበረብራል፡፡ “ይህን
ከሰራኝ እኔም ይህን እሰራዋለሁ” የሚል እልህ የተሞላበት መመሪያ ይዞ ይንቀሳቀሳል፡፡
ይህ ደግሞ በፍጹም የሙእሚን ባህሪ ሊሆን አይገባም፡፡
2/6
‫ففي المسند وغيره بإسناد صحيح من حديث أنس بن مالك رضي هللا عنه أن النبي‬
"‫ "أد األمانة إلى من ائتمنك وال تخن من خانك‬:‫صلى هللا عليه وسلم قال‬
“ሙስነድ” በተባለው የኢማም አህመድ ኪታብ በተዘገበ ሐዲስ አነስ ብን ማሊክ 4
የሚከተለውን አስተላልፈዋል፡-
“ላመነህ ሰው አደራህን በአግባቡ ተወጣ ፤ የሸወደህን አትሸውድ፡፡” አህመድ፡ አቡዳውድ፡
ቲርሚዚይ፡ ሐዲሱን አላባኒ ሶሂህ ብለውታል ሶሂህ አል ጃሚዕ፡

አደራን መወጣት በማንኛውም ሁኔታና ወቅት ተፈላጊና የሚወደስ ተግባር ነው፡፡


መሸወድ ደግሞ በማንኛውም ወቅትና ሁኔታ አስቀያሚ ተግባር ነው፡፡ ለዚህ ነው ረሡል
‫“ ﷺ‬የሸወደህን አትሸውድ” በማለት አጥብቀው የመከሩት፡፡ ንብረትህን በመዋሸት
ሳይሆን ሐቅ በመናገር ለማግኘት ጥረት አድርግ፡፡
እውነት መናገር
አንድ ነጋዴ ሰዎችን ሲያወራ፣ ሲሸጥ ሲገዛ ውሸትን በመራቅ ሁልጊዜ እውነተኛ
ሊሆን ይገባል፡፡ እቃ ሲሸጥ “ይህ እቃ አዲስ ነው” ወይም “ይህ እቃ ኦርጅናል ነው” ፤
“ይህ የዛሬ እንጅ የትናንት ምርት አይደለም” ብሎ ሲናገር እውነትን መሰረት ማድረግ
ይኖርበታል፡፡ እውነት ሳይናገር “ካንዱ ሰው አንድ ብር ከሌላው ሰው ሁለት ብር
በመለቃቀም በአንዴ ለመክበር ምኞት ቢኖረው እንኳ እውነት ካልተናገረ የሚፈይደው
ምንድን ነው?!”
"‫ وإن الفجور يهدي إلى النار‬، ‫"إياكم والكذب فإن الكذب يهدي إلى الفجور‬
“ሐሰትን አደራ ተጠንቀቁ ፤ ሐሰት ወደጥመት ይመራል ፤ ጥመት ደግሞ ወደእሳት
ይመራል፡፡” ቡኻሪ፡ ሙስሊም፡

ዋናው ቁምነገሩ አንድ ብር ወይም ሁለት ብር ለማግኘት እውነትን መሸራረፍ


አይደለም፡፡ ሲሳይ በአላህ እጅ መሆኑን በቅድሚያ መገንዘብ ያስፈልጋል፡፡ እውነት
የማይደራደሩበት የጸና መሰረትና ሊያጠፉት የማይገባ ትልቅና ቋሚ ንብረታችን ሊሆን
ይገባል፡፡ አንዳንድ ሰው ለዱንያ ካለው ጉጉቱ የተነሳ ከሐቀኛነት ባህሪው ሾልኮ ይወጣል
፤ መልካም ስነምግባሩ ወደአውሬነት ይቀየራል ፤ በተወሰነ ቃል ኪዳን ፈተና ላይ
ይወድቃል ፤ ነፍሱ ወደሐሰት ሸለቆ ታወርደዋለች ፤ ሳያስበው ባልሆነ ጉዳይ ከባድ
መሐላን ይምላል፡፡
‫ "ثالث ال يكلمهم هللا يوم القيامة وال ينظر إليهم وال‬: ‫وقد قال عليه الصالة والسالم‬
"‫يزكهم ولهم عذاب أليم‬
3/6
የአላህ መልክተኛ ‫ﷺ‬ የሚከተለውን ሐዲስ ተናግረዋል፡-
“ሶስት ሰዎች አላህ የትንሳኤ ቀን አያናግራቸውም ፤ ወደነርሱም አይመለከታቸውም ፤
አላህም (ከሐጢያት) አያጠራቸውም ፤ ለእነርሱ አሳማሚ ቅጣት አላቸው፡፡ ከእነዚህ
ሶስት ሰዎች መካከል አንዱ “በውሸት ማሃላ እቃውን የሚያስወደድ ነው፡፡” ሙስሊም፡
ተወጋጅ ለሆነችው ዱንያ እውነትን በካልቾ ብሎ ሐሰትን አንጡራ ሐብቱ ያደርጋል፡፡
መልካም ስነ-ምግባር
ከሰዎች ጋር ሲሰራ በመልካምና በተከበረ ስነ-ምግባር መስራት ነው፤ በንግድ ስራ
ላይ የተሰማራ ሰው ከሰዎች መልካምም ይሁን መጥፎ የተለያየ አይነት ስነ-ምግባሮችን
ያስተውላል ፤ በመሆኑም ከዚህ በፊት በሐዲሱ ላይ የተጠቀሱትን አራት መሰረታዊ
መርሆዎች አጥብቆ ካልያዘ ከሰዎች ጋር በሚያደረገው ውሎ ስነ-ምግባሩ በቀላሉ
ይቀያየራል፡፡ ሰውየው ወደንግድ ከተሰማራ “መልካም ስነምግባርን” ለማስገኘት
ከነፍሱ ጋር ከፍተኛ ትግል ይገጥማል፡፡ ከሰዎች ጋር በመቀላቀሉ የነበረውን መልካም
ስነምግባር ያጣል፡፡ አንዳንድ ሰው ከሰዎች ጋር ባለው የዘወተረ ግንኙነት አራቱን
መሰረታዊ መርሆዎች ዘንግቶ ልክ እንደሰዎች ተራጋሚ፣ ተሳዳቢና ሐይለኛ ባህሪን
ይወርሳል፡፡
ነፍሱን መካሪ የሆነ ነጋዴ ከሰዎች ጋር ባለው ግንኙነት የነበረውን መልካም ስነ-
ምግባር በቀላሉ ለመጣል ምክንያት አይሆነውም፡፡ የሰው ልጅ ስነ-ምግባሩ ከተበላሸ
ምንድን ነው የሚያተርፈው? ስነ-ምግባሩ ጠፍቶ ከዚህ በኋላ የገንዘቡ መበራከት
ምንድን ነው የሚፈይድለት?
ከሐራም ምግቦች ቁጥብ መሆን
አንድ ነጋዴ ከሀራም ወይም አሻሚ ከሆኑ ምግቦች ርቆ በሐላል ምግቦች ብቻ
መወሰን ይኖርበታል፡፡
‫ "إن الحالل بين وإن الحرام بين وبينهما مشتبهات‬: ‫وقد قال عليه الصالة والسالم‬
‫ ومن وقع‬، ‫ فمن اتقى الشبهات استبرأ لدينه وعرضه‬، ‫ال يعلمهن كثير من الناس‬
‫ أال وإن لكل‬، ‫في الشبهات وقع في الحرام كالراعي حول الحمى يوشك أن يرتع فيه‬
"‫ملك حمى أال وإن حمى هللا محارمه‬
“የተፈቀደው ግልጽ ነው ፤ የተከለከለውም ግልጽ ነው ፤ በሁለቱ መካከል አሻሚ ነገሮች
አሉ ፤ ከሰዎች ብዙዎቹ አያውቋቸውም ፤…
4/6
አሻሚ የሆኑ ነገሮችን የተጠነቀቀ ዲኑንና ክብሩን በርግጥ ጠበቀ ፤ በአሻሚው ነገር ላይ
የወደቀ በተከለከለው ነገር ላይ መውደቁ አይቀርም ፤ ልክ ከተከለከለ አካባቢ ከብቶቹን
አሰማርቶ ሊያግጥ እንደሚቀርብ ዘላን ነው፡፡ ንቁ! ለንጉሱ ሁሉ የሚያስከብረው ክልክል
አለው ፤ ንቁ! የአላህ ክልክል ደግሞ እርም ያደረጋቸው ናቸው፡፡” ሙስሊም፡
መልካም ነጋዴ ምግቡ ከሀራም የጸዳ አላህ ከፈቀደው ዓይነት እንዲሆን ከፍተኛ
ጥረት ያደርጋል፡፡ ሲሸጥ ሲለውጥ ከአራጣ (ከወለድ) ፣ ከማጭበርበር እና
በአጠቃላይ በሸሪዓ ከተከለከሉ የንግድ አይነቶች ይርቃል፡፡ ከእርሱ ዘንድ መሰረታዊና
ከማይቀየሩ የንግድ መመሪያዎቹ መካከል አንዱ ከሀራም ፍጹም መጽዳት ነው፡፡ ትርፍ
ለማግኘት ሲሞክርም ይህን ህግ የማያፈርስ መሆኑን ማረጋገጥ ተቀዳሚ ተግባሩ ነው፡፡
አንዳንድ ሰዎች ወደንግድ ሙያ ሲሰማሩ ሀላል ሀራም የሚለውን ሕግ ጠብቀው
አይጓዙም፡፡ በሚበሉት በሚጠጡት በሚሰሩት ከአላህ መመሪያ የራቁ ግድ የለሽ ሆነው
ታገኛቸዋለህ፡፡ እንዴውም መመሪያቸው የሚከተለው ሆኖ ታገኘዋለህ፡-
"‫ والحرام ما حرمت منه‬، ‫"الحالل ما حل بيدك‬
“ሀላል ማለት እጅህ የተቆጣጠረው ነው ፤ ሀራም ማለት ደግሞ አንተ ከእርሱ እርም
ያደረከው ነው፡፡” መጅሙዕ አል ፈታዋ ሊብን ተይሚያህ፡
، ‫ "كل لحم نبت من سحت فالنار أولى به‬: ‫وقد قال عليه الصالة والسالم‬
የአላህ መልክተኛ ‫ ﷺ‬የሚከተለውን ተናግረዋል፡-
“በሐራም ተኮትኩቶ ያደገ ማንኛውም ስጋ (የሰውነት አካል) እሳት ለእርሱ ተገቢው
ነው፡፡” ቲርሚዚይ፡ ሐዲሱን አልባኒ ሶሂህ ብለውታል አስ ሲልሲቱ አስ ሶሂህ፡

‫ "الرجل يطيل السفر أشعث أغبر يمد يديه إلى السماء‬: ‫وذكر عليه الصالة والسالم‬
‫ ومطعمه حرام ومشربه حرام وملبسه حرام وغذي بالحرام فأنى‬، ‫يا رب يا رب‬
"‫يستجاب لذلك‬
የአላህ መልክተኛ ‫ ﷺ‬የሚከተለውን ተናግረዋል፡-
“ግለሰቡ ጸጉሩ የተንጨፈረረ ፤ አካለ ቡላ ሆኖ ጉዞን ያበዛል ፤ ጌታየ ሆይ! ጌታየ ሆይ!
በማለት እጆቹን ወደሰማይ ዘርግቶ ጌታውን ይማጸናል ፤ ምግቡ ሀራም መጠጡ ሀራም
ልብሱ ሀራም በአጠቃላይ በሀራም ነው የተገነባው እንዴት ይህን ሰው ዱዓውን ሊቀበለው
ይችላል?!” ሙስሊም፡
እንደዚህ አይነት ባህሪ ያለውን ሰው አላህ እንዴት መልስ ሊሰጠው ይችላል?!
በዚህ ምክንያት ከቀደምቶች አንዱ የሚከተለውን ተናግሯል፡-
5/6
"‫ فليطب طعمته‬، ‫"من سره أن يستجيب هللا دعوته‬
“ዱዓውን አላህ እንዲቀበለው የፈለገ ሰው አላህ የፈቀደውን ይመገብ፡፡” ጃሚዕ አል ዑሉም
ወል ሂከም፡

ይህ ክፍል ከሙስሊም ነጋዴዎች ዘንድ መሰረታዊ ነገር ነው፡፡ ይህን ጉዳይ መገንዘብና
ማወቅ ላይ ትኩረት ሊሰጥ ይገባል፡፡ ሳይገነዘብ ወይም አላህ የፈቀደው መሆኑን ሳያውቅ
ወደምግብና መጠጥ ዘሎ መግባት የለበትም፡፡ ሀራም ወይም ብዥታ የሚፈጥር ከሆነ
ደግሞ ከፍተኛ ጥንቃቄ ሊያደርግና ፈጥኖ ሊርቅ ይገባል፡፡ አላህ የፈቀደውን ምግብ
መብላት የሚደራደሩበት ጉዳይ አይደለም፡፡ ምክንያቱም ረሡል ‫ ﷺ‬ለነጋዴዎች
ከጠቀሷቸው መሰረታዊ ነገሮች አንዱ እርሱ ነውና፡፡ ይልቁንም ከእርሱ ዘንድ ጥልቅ
እና የተረጋገጠ ጉዳይ ሊሆን ይገባል፡፡
አንተ ነጋዴ የሆንክ ሙስሊም ወንድሜ ሆይ! እነዚህን አራት መሰረታዊ መርሆዎች
በደንብ ጠብቀህ ያዛቸው፤ አታጥፋቸው፤ ከመጥፎ አዛዥ፣ ከነፍስያ ተንኮልና ከሰይጣን
በአላህ ተጠበቅ ፡፡ በገቢያ ውስጥ አብዛኛው ሰው በሐሰት የሚነግድ በመሆኑ
“እውነትን ይዥ እንዴት ያዋጣኛል ፤ ሰዎች ሁሉ በውሸት እየማሉ ነው የሚነግዱት ፤
በዚህ ምክንያት ኪሳራ ውስጥ መግባቴ አይቀርም” አትበል ፤ አንተ ብቻ በሐቅ ላይ
ሁን ፤ በሐቅ ላይ ከሆንክ አላህ በጥበቃውና በድጋፉ ከአንተ ጋር ነው፡፡
የተንጣለለው ሰፊ የንግድ ሜዳ የሰው ልጅ ስነምግባር የሚለካበት መድረክ ነው፡፡
ከዱንያ የሚያመልጥህ ትርፍ ቢኖርም እንኳ ነብዩ ‫ ﷺ‬የመከሩህን አራት መሰረታዊ
መርሆዎች የህይዎትህ መመሪያ አድርጋቸው ፤ በሱና ላይ ትዕግስት ካደረክ የነብዩን
‫ ﷺ‬አደራ ከጠበክ በዱንያም በአኼራም ያማረ ፍጻሜ ለአንተ ነው የሚሆነው፡፡
ስለዚህ በዚህ ላይ ተስፋ ልትቆርጥ አይገባም፡፡
የተከበርክ ወንድሜ ሆይ! ከመጥፎ ስነምግባር አላህ ይጠብቅህ! ሀላል የሆነ ገንዘብና
መልካም የሆነ ኑሮ አላህ ይለግስህ ! እነሆ እርሱ ሰሚና ዱዓን ተቀባይ የሆነ ጌታ
ነውና፡፡

‫وصىل هللا عىل نبينا محمد وعىل آهل وحصبه وسمل‬

6/6
:‫إعداد‬
‫الشيخ عبدالرزاق بن عبدالمحسن البدر‬
ትርጉም፡ ዩሱፍ አሕመድ

ባህር ዳር በሚገኙ የአህለሱና


መሻይኾች የተቀሩ ጠቃሚ ኪታቦች፣
ከሀገር ውስጥና ከውጭ በሚመጡ
መሻይኾች የተሰጡ ኮርሶች፣
ሙሓዶራዎች፣ የጁመዓ ኹጥባ፣
በትክክለኛ ማስረጃ የተደገፉ የተለያዩ
ኢስላማዊ መጣጥፎችን የሚከተለውን
የቴሌግራም ሊንክ ጆይን በማድረግ
መከታተል ይችላሉ

You might also like