Download as docx, pdf, or txt
Download as docx, pdf, or txt
You are on page 1of 20

ለአመራሩ የቀረቡ ጥያቄዎች

ዓላማ
የዚህ ግልጽ ፈተና ዓላማ አመራሩ የብልጽግና ፓርቲ ሰነዶችን፣ ሥልጠናዎችንና ውይይቶችን

እንዲያነብ፣ እንዲያስታውስና በሚያውቀው ነገር ላይ ተመሥርቶ ተልዕኮውን እንዲያሳካ

ለማድረግ ነው፡፡

ዝግጅት
እነዚህ ጥያቄዎች ከብልጽግና ሰነዶች፣ ከተሰጡ ሥልጠናዎችና ካደረግናቸው ውይይቶች

የተወሰዱ ናቸው፡፡

አሠራር
መጀመሪያ ምንም ዓይነት ሰነድና ማስታወሻ ሳንመለከት ጥያቄዎቹን ብንሠራቸው ይመከራል፡፡

በዚህም ምን ያህል መርሖቻችንን፣ ዕሴቶቻችንን፣ ዕሳቤዎቻችንንና አስተምህሮዎቻችንን

እንደምናስታውስ ራሳችንን ለመፈተሽ ይጠቅመናል፡፡

በዚህ ሙሉ በሙሉ መሥራት ካልቻልን፣ በመቀጠል ጥያቄዎቹን አስቀምጠን፣ የብልጽግናን

ሰነዶች ከመነሻ እስከ አሁን በመመልከት፤ ማስታዎሻዎቻችንን በማገላበጥ የተወሰነ ጊዜ

እናሳልፍ፡፡ ከዚያም ሰነዶቹን ትተን በምናስታውሰው ብቻ ለሁለተኛ ጊዜ ጥያቄዎቹን እንሥራ፡፡

ይሄም ለሁለተኛ ጊዜ ራስን ለመለካት ያገለግላል፡፡

ይሄ ሁሉ ሆኖ ካልተሳካ በመጨረሻ ሰነዶቹንና ማስታዎሻዎቹን ጎን ለጎን ይዞ ጥያቄዎችን መሥራት

ነው፡፡

መልስ የሚዘጋጀው ራሱን በቻለ ወረቀት፣ የጥያቄ ቁጥሮቹን ቀድሞ በመጻፍ ነው፡፡

የተሰጠው ጊዜ
አመራሩ እነዚህ ጥያቄዎች በመመለስ በአራት ሳምንት ጊዜ ውስጥ አጠናቆ ማስረከብ

ይኖርበታል።

Page 1 of 20
ክፍል አንድ

1. የሰው ልጆች ተደማሪ ፍላጎቶች ምንድን ናቸው? የእነዚህ ፍላጎቶች መጓደል የፈጠረው ሀገራዊ ጫና

ምንድነው? ዴሞክራሲ እነዚህን ፍላጎቶች ከመመለስ አንጻር የሚኖረውን ሚና ከአስፈላጊነቱ ጋር በማያያዝ

አአብራሩ?
መልስ
 የሰው ልጆች ፍላጎት በርካታ ናቸው፡፡ የሰው ልጆች ፍላጎቶች ቀጥተኛ የህልውና ፍላጎትና ተዘዋዋሪ

ፍላጎት ተብሎ ሊጠቀስ ይችላል፡፡

 ቀጥተኛ የህልውና ፍላጎት ሲባል የሰው ልጅን በቀጥታ ከሚፈታተናቸው ግድያ፣ ጦርነት ፣ ወይም ሌላ

ማንኛውም የመጠቃት ስጋት ራሳቸውን የመታደግና በህይወት የመቆየት ፍላጎት ነው፡፡ ተዘዋዋሪ

የህልውና ፍላጎት ሲባል ስጋዊ ፍላጎት፣ የስም/ክብር ፍላጎት እና የነጻነት ፍላጎት የሚሉ ጽንጸ ሀሳቦችን

የያዘ ነው፡፡

 በመደመር እይታ የሰው ልጆች ፍላጎት ተደማሪ ባህሪይ አላቸው፡ ፍላጎቶቹ እርስ በእርስ የተሳሰሩና

ተደማሪ ፍላጎቶች ሲሆኑ በሌላ በኩል ደግሞ በመካከላቸው ተቃርኖ አላቸው ስለሆነም ሰዎች

ፍላጎቶቹን በተናጠል ሳይሆን በመደመር ሊያሳኳቸው ይችላሉ፡፡

 የእነዚህ ፍላጎቶች መጓደል በሀገራችን ከለውጡ በፊት በርካታ ችግሮች በመንግስት ላይ ጫና

መፍጠሩን ማስታወስ ይቻላል፡፡ በኢሀኣዴግ ዘመን እንደ ሀገር የታየው የኢኮኖሚ እድገት በመኖሩና

የዜጎች ስጋዊ ፍላጎት በተወሰነ ደረጃ ማሟላት በመቻሉ የዜጎችን ሌሎች ፍላጎቶችን ያለማድመጥና

ያለማክበር ሁኔታ ሲሰተዋል ታይቷል፡፡ በዚህ ምክንያት ዜጎች ወደ ትግል እንዲገቡና ሀገራዊ ለውጡ

እንዲፈጠር ማድረግ ችሏል፡፡

 ዴሞክራሲ እነዚህን ፍላጎቶች ከመመለስ አንጻር ያለው ፋይዳ ሲታይ ከፍተኛ ነው፡፡ ዴሞክራሲ

በባህሪው የዜጎች መንግስት መመሰረትና የዜጎችን ጥያቄዎች መመለስ በመሆኑ፤ የዜጎች ተደማሪ

ፍላጎት ለመመለስ ከዜጎች ጋር መወያየትና መግባባት ያስፈልጋል፡፡ እንደ መንግስት በዚህ ደረጃ ለህዝብ

ቅርብ ሆኖ ለመስራት እራስን ዴሞክራሲያዊ ማድረግ የግድ ይላል፡፡ ስለዚህ ዴሞክራሲ የዜጎችን

ተደማሪ ፍላጎት ከመመለስ አንጻር አስፈላጊነቱ የጎላ ይሆናል፡፡

2. የብቸኝነት ጉድለት ምን ማለት ነው? የብቸኝነት ጉድለትን ከመሠረታዊ ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ

ስብራቶቻችን አንጻር ምን ማለት እንደሆነ አስረዱ?


መልስ
 በመደመር መነፅር ምንም ነገር በራሱ ምሉዕ አይደለም፡፡ ነገሮች ሁሌም በለውጥ ሂደት ውስጥ

የሚያልፉ ናቸው፡፡ ምሉዕነት ለማምጣት የሚደረግ ውጣ ውረድ አላቸው፡፡ ምሉዕነት ለማምጣት


Page 2 of 20
የሚደረግ የው ልጅ ማህበራዊ ግንኙተንር ይኖራል፡፡ በምሉዕነት ጉዞ ውሰጥ አስፈላጊውን ግንኙነት

ማድረግ ካልተቻለ የብቸኝነት ጉድለት ይከሠታል፡፡ የሰው ልጆች ማህበራዊ ህይወት ውስጥ

የብጨኝነት ጉድለት ትልቕ ሥፍራ አለው፡፡

 የብቸኝነት ጉድለት በተለያዩ ምክንያቶች ሊከሰት ይችላል፡፡ በማህበራዊ ግንኙነት ውስጥ በፉክክርና

በትብብር መካከል የየሚከሰት የሚዛን መዛባት ለብቸኝነት ጉድለት መፈጠር ዋነኛ ምንጭ ነው ተብሎ

ይወሰዳል፡፡

 ከመሰረታዊ የፖለቲካና ኢኮኖሚያዊ ስብራቶች ውስጥ አንዱ የትብብርና የፉክክር ሚዛን ተብቆ መጓዝ

ችግር ነው፡፡ የብቸኝነት ጉድለትን ለመሞላት ሰዎች ወደ ትብብር ወይም/እና ወደ ፉክክር ሊገቡ

ይችላሉ፡፡ ከልክ ያለፈ ትብብር የሰውን ልጅ ወደ ስንፍና እና የተሻለ ፈጠራ ውስጥ እንዳይገባና በፈጣን

እድገት ላይ ባለቸው አለም ውስጥ ወደ ሃላ የመቅረት ችግር ሊፈጥር ይችላል፡፡ ከልክ ያለፈ ፉክክርም

የራሱ ሆነ እጥረት አለው፡፡ እነዚህ ችግሮች የሰው ልጅን ወደ ተሻለ ለውጥ እንዳይገቡና ባሉበት

ቦታ/ደረጃ ረክቶ ወይም ተስፋቆርጠው እንዲቀመጡ ያደርጋል፡፡ እንዲህ አይነት ትውልድ ደግሞ

በፍጠነት ማደግ ለሚትፈልግ ሀገር ችግር ይሆናል፡፡

 ስለሆነም ትብብሩና ፉክክሩን ሚዛናቸውን አስጠብቆ በአግባቡ በመጠቀም የሀገራችንን ፖለቲካያዊና

ኢኮኖሚያዊ ስብራትን ማከም ላይ የራሱ ድርሻ አለው፡፡

3. በመደመር መነጽር መሠረታዊ የፖለቲካ ስብራታችንን አስረዱ? እነዚህን ችግሮች እያባባሱ ያሉት ነባራዊ

ፈተናዎች ምንድናቸው? ነባራዊ ሁኔታ በእነዚህ ሥር በሰደዱ ወይም መሠረታዊ ሀገራዊ የፖለቲካ ችግሮቻችን

እና ችግሮቹን ለመፍተት በሚደረገው ጥረት ላይ የፈጠረው ጫና ምንድነው?


መልስ
 በመደመር እይታ መሰረታዊ የፖለቲካ ስብራቶች የሚባሉት የሀገረ መንግስትን ህልውና የተፈታተነው

ጭቆና (ሰው ወለድና መዋቅር ወለድ ጭቆና)፣ ትክክለኛ ዲሞክራሲ መገንባት አለመቻል፣ የሀገረ

መንግስት ቅቡልነት የማረጋገጥ ፈተና፣ ነጻ ገለለተኛና ብቁ ተቋማት ግንባታ ችግር፣ የፖለቲካ አመራር

የመሪነት ሚና መጫወት አለመቻል እና ዘመናዊ የፖለቲካ ባህል መገንባት አለመቻል የሚሉ ናቸው፡፡

 አገራችን በማያቋርጥ የለውጥ ጉዞ እየገሰገሰች ትገኛለች፡፡ አሁን በኢትዮጵያ እየተካሄደ ያለው ለውጥ

መሠረት የሚያደርገው በሀገሪቱ ለረጅም ጊዜ የህዝብ ጥያቄ ሆነው የቆዩ ጉዳዮችን ደረጃ በደረጃ

መመለስ ላይ ነው፡፡ እነዚህ ጥያቄዎች የእኩልነትና ፍትሐዊ ተጠቃሚነት፣ ዴሞክራሲን የመትከልና

የማፅናት ጥያቄዎች ናቸው፡፡ የለውጡ መነሻና መሰረታዊ አጀንዳዎችም ነበሩ፡፡ ስለሆነም የብልጽግና

ፓርቲ ዓላማ የለውጡ አቅጣጫ መሠረታውያን ተብሎ የተለዩ እነዚህን አጀንዳዎች እውነተኛ ህብረ-

Page 3 of 20
ብሔራዊ ፌደራሊዝም ሥርዓት በማረጋገጥ፣ የዜጐች ነፃነትና ክብርን ከፍ በማድረግ፣

የኢትዮጵያውያን ወንድማማችነት/እህትማማችነት በማጐልበት፣ ሁለተናዊ ብልጽግናን ዕውን

በማድረግ የህዝብን የለውጥ ፍላጎት ማርካት ነው፡፡ ይህንን የህዝብን የለውጥ ፍላጎት ማሳካት

የሚቻለው ብቁ የሆነ፣ የአላማና የተግባር አንድነት ያለው የአመራር ሥርዓት መፍጠር ሲቻል ነው፡፡

 በአገራችን ከ 2010 ዓ.ም በኋላ ጥልቀትና ሰፋት ያለው የሪፎርም ሥራዎች እይተከናወኑ የሚገኝ

ቢሆንም በለዉጡ አጀንዳዎች ላይ ሁሉም በየደረጃዉ የሚገኘዉ አመራራችንና ፈፃሚ ኃይል የጋራ

መግባባት እና የዓላማ አንድነት በተሟላ ሁኔታ የተፈጠረ ነዉ ብሎ መዉሰድ ያዳግታል፡፡ በብልጽግና

እሳበና መንገድ የጠራ አመለካከትና አቋም የያዘ፣ በፓርቲው አደረጃጀትና አሰራር በቂ ክህሎት

የጨበጠ፣ በአግባቡ የተደራጀና የስራ አፈፃፀም አመራር ብቃት ያለውና የሕዝብ አገልጋይ የሆነ

የአመራር ኃይል መፍጠር ላይ ገና የሚቀሩን ስራዎች መኖሩ አንዱ ችግር ነው፡፡

4. በለውጡ አንዱና ትልቁ ፈተና ባልተጠናቀቀ ሀገረ መንግሥት ውስጥ ዴሞክራሲን የመትከልና የማጽናት ጉዳይ

ነው። ‹ያልተጠናቀቀ ሀገረ መንግሥት› ስንል ምን ማለታችን ነው? ‹የተጠናቀቀ› እና ‹ያልተጠናቀቀ› ሀገረ

መንግሥት ልዩነቶቻቸው ምንድን ናቸው፡፡ ባልተጠናቀቀ ሀገረ መንግሥት ውስጥ ዴሞክራሲን መትከልና

ማጽናት እንዴት ፈተና ሊሆን ይችላል?


መልስ
 በሀገር መንግስት ግንባታ ሂደት ውስጥ አንዱ ምሶሶ ጉዳይ ነፃና ገለልተኛ ተቋማት መገንባትና ሀገራዊ

መግባባትን መፍጠር ነው፡፡

 የዲሞክራሲ ሥረዓት ግንባታ ደግሞ በአግባቡ ተግባራዊ ማድረግ የሚቻልው ለዲሞክራሲ ስርዓት

ግንባታ ውስጥ የተቋማት ግንባታ ማሳካት ሲቻል ነው፡፡

 በሀገረ መንግስት ውስጥ የተቋማት ግንባታ ባልተጠናቀቀበት ሁኔታ ዲሞክራሲ ማፅናት ሂደትን

አስቸጋሪ የሚያደርግ ይሆናል፡፡

 ያልተጠናቀቀ ሀገረ ም›መንግስት ግንባታ የነፃና ገለልተኛ ተቋማት ግንባታ ጋር የተቆራኘ ነው፡፡

5. የብልጽግናን ምንነት እና ሁለንተናዊነት አስረዱ?


መልስ
 ብልጽግና ስባል አንድም የፓርቲያችን ስያሜ ሲሆን በሌላ በኩል ደግሞ ፓርቲያችን ሊያሳካው

የሚፈልግው ግብ ነው፡፡ ፓርቲያችን ስያሜው በመተዳደሪያ ደንቡ ላይ እንደተቀመጠው “ብልጽግና

ፓርቲ” ወይም “ብልጽግና” ተብሎ እንደሚጠረ ተቀምጧል፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ ፓርቲያችን ሊያሳካው

የሚፈልገው የኢትጲያን ብልጽግና ነው፡፡ ከዚህ አንጻር ብልጽግና የፓርቲያችን መዳራሻም መሆኑ

ይታወቃል፡፡
Page 4 of 20
 ሁለንተናዊ ብልጽግና ሲባል ደግሞ እንደ ፓርቲ ለማሳካት የሚንፈልገው ኢኮኖሚያዊ ብልጽግና ብቻ

ሳይሆን በፖለቲካም፣ በማሀበራዊ እና በውጭ ጉንኝነትም ብልጽግናን ለማረጋገጥ ግብ ተጥሎ

እየተሰራ ይገኛል፡፡ ይሄንን ሁለንተናዊ ብልጽግና እንላለን፡፡ በፓርቲያችን ፐሮግራም ላይ

እንደተቀመጠው የብልጽግና ፓርቲ አላማዎች ጠንካራ፣ ዴሞክራሲያዊ፣ ቅቡልነት ያለው ዘላቂ

ሀገረመንግስትና ህብረብሄራዊ አንድነት መገንባት፣ ልማትና ፍትሀዊ ተጠቃሚነትን የሚያረጋግጥ

አካታች የኢኮኖሚ ስርአት መገንባት፣ሁለንተናዊ ብልጽግናን የሚያሰፍን ማህበራዊ ልማትን ማረጋገጥ

እና ሀገራዊ ክብርንና ጥቅምን ማዕከል ያደረገ የውጭ ግንኙነት ማካሄድ ናቸው፡፡ ይሄን አላማ በአጭሩ

ሁለንተናዊ ብልጽግና ተብሎ ይጠራል፡፡

6. ብልጽግና ፓርቲ ስለ ማኅበራዊ ፍትሕ ያለውን አመለካከት በዝርዝር አስረዱ? በሀገራችን ለማኅበራዊ ፍትሕ

አስፈላጊነት ዋነኛው ምክንያት ምንድነው?


መልስ
 ብልጽግና ፓርቲ በማህበራዊ ዘርፍ ሁለንተናዊ ማህበራዊ ብልጽግና የማረጋገጥ ኢላማ ይዞ እየሰራ

ይገኛል፡፡ በዚህም የማኅበራዊ ልማት ሥራዎቻችን የዕድገትና ፍትሐዊ ተጠቃሚነት መንትያ ግቦች

የማሳካት ጉዳይ ይሆናል፡፡ ለሀገራዊ ኢኮኖሚያዊ እድገት ማበረከት የሚችል እና ከተጠቃሚነትም

አንጻርም ፍተሀዊ ተጣቃሚነት ማረጋጥ ላይ ይህ ግብ አስተዋጽኦው ከፍተኛ ነው፡፡

 የማኅበራዊ ፕሮግራማችን ዜጎችን የሚያስተሣሥር፣ ከችግርና ከመከራ የሚታደጋቸው፣ የሀገርን

አለኝታነት የሚያሠርጽ እና በሀገራችን አወንታዊ ሰላምን የሚያረጋግጥ ይሆናል፡፡ የማኅበራዊ ልማት

ፕሮግማራችን ኅብረ ሀገራዊ ማንነት መሠረት ያደረገ ሀገራዊ አንድትን የሚያጎለብት እንዲሆን ዒላማ

አድርጎ መንቀሳቀስ የፓቲያችን ማኅበራዊ ፕሮግራም ዓላማ መገለጫ ናቸው፡፡ በዚህ ስር ዘርዘር

ተደርጎ ስታይ፡-

o ከትምህርት አንጻር ፍትሐዊነት፣ ጥራት፣ አካታችነት እና አግባብነት ያለው የትምሀርት


ሥርዓት ማረጋገጥ፣
o ከጤና አንጻር መከላከልና አክሞ የሚያድን የጤና ስርዓት መዘርጋት፣

o ከማህበራዊ ጥበቃ አንጻር ዐቅም ያናዘበ ከዳረጎት ወደ መብት የዞረ ማህበራዊ ጥበቃ ስረዓት
መዘርጋት፣
o ከወጣቶች አንጻር የወደፊት ሀገር ተረካቢ ብቻ ሳይሆን የዛሬ ሀገር ባለቤት ወጣቶች ማፍራት፣

o ከሴቶች አንጻር የሴቶችና ወጣቶች ፍትሃዊ የፖለቲካ ውክልናና ተሳትፎ እንዲኖር ማድረግ፣

Page 5 of 20
o ኅብረ ሀገራዊ ከመፍጠር አንጻር ብዝኃነታችነን ማዕከል ያደረገ የባህልና ቅርስ ልማት

(ብዘሃ ልሳን የስራ ቋንቋ ከማድረግ፣ ለባህልን ቅርስ ተገቢውን ትኩረት በመስጠትና በማልማት

አና እስፖትን የህዝቡ የማድረግ) የሚሉ ግቦችን የያዘ ነው፡፡

7. በኢትዮጵያ ዴሞክራሲን ለመትከልና ለማጽናት ተግዳሮቶችን በዝርዝር አስረዱ? በኢትዮጵያ ነባራዊ ሁኔታ

ፓርቲያችን ተመራጭ የሚያደርገውን ዴሞክራሲ እና መለያ ባህሪያቱን አስረዱ? በመደመር ዕሳቤ የምንገነባው

ዴሞክራሲ ምንን ማዕከል ያደረገ ነው?


መልስ
 በኢትዮጲያ ዴሚክራሲን ለመትከልና ለማጽናት ተግዳሮቶች ውስጥ አንዱ የልህቃኖች ጽንፈኝነት

ነው፡፡ ለምሳሌ ፍጹም አንድነትና ፍጹም ልዩነት የሚያቀነቅኑ ሀይሎች ተቀራርበው የጋራ ሀገር

ለመገንባት ሲቸገሩ ከርሟል፡፡ ስለዚህ ህብረብሄራዊነትን ያቀፈ ዴሞክራሲ ለመገንባት አልተቻለም፡፡

 ብልጽግና ዴሞክራሲን በሚረዳበትና በሚተገብርበት መንገድም ከታሪካችን ፈጽሞ ይለያል። እናም

በዴሞክራሲ ላይ ያለን አዲስ አረዳድ የፓርቲያችን ሁለተኛው የሃሳብ እድገት ማሳያ ነው ማለት

እንችላለን። ፓርቲያችን በፕሮግራሙ አማካኝነት ይፋ እንዳደረገው የመግባባት ዴሞክራሲን

ይከተላል። እንደሚታወቀው ዴሞክራሲ የፉክክርና የአብላጫ ስርዓት ነው። በዴሞክራሲ መርህ

መሰረት ብዙሃን ይገዛሉ ውህዳን መብታቸው ይከበራል። ዴሞክራሲው በፉክክርና በትብብር መካከል

ሚዛን የመጠበቅ መርህ ሲመራና ሲገራ ግን ውህዳን መብታቸውን ከማስከበር ያለፈ ጥቅም ያገኛሉ።

በቅድሚያ በየደረጃውና በየዘርፉ ተመጣጣኝ ውክልና የማግኘት ዕድል ይኖራቸዋል። አለፍ ሲል ደግሞ

የብዙሃንን ተጽዕኖ መቋቋም ብቻ ሳይሆን አስፈላጊ በሆነ ጊዜ መቀልበስ የሚችሉበት የህግ ከለላና

ፖለቲካዊ ጉልበት ይጎናጸፋሉ።

 በዴሞክራሲ መርህ አብላጫ ድምጽ ሁሌም ተፈጻሚ ይሆናል። ዴሞክራሲ ለፉክክር ብቻ ሳይሆን

ለትብብርም ቦታ ሲሰጥ ግን በአብላጫ ድምጽ የሚሸነፉ ትክክለኛ ሃሳቦች ተቀባይነትና ተፈጻሚነት

የማግኘት እድል ያገኛሉ። ከውህዳን የሚወጡ ጠንካራ ሰዎችም በሃሳባቸው ትክክለኛነት ከፊት

የመሆን በር ይከፈትላቸዋል። ስለዚህ ዴሞክራሲያችን በፉክክርና ትብብር መካከል ሚዛን ጠብቆ

ፍትሓዊነትን በሚያረጋግጥ መልኩ መሬት ለማስነካት የሚሰራ የመግባባት ዴሞክራሲ በመሆኑ

የፓርቲያችንን የአካታችነት መርህ ሁሌም በተግባር ለመደገፍ ያግዛል። በውጤቱም የባይተዋርነትና

የመገፋት ስሜትን ለመቀነስና ለማስወገድ በሚያስችለን ትክክለኛ ሃዲድ ላይ እንድንራመድ

ያስችለናል።

8. መደመርን እና የመደመርን ትውልድ በማስተሣሠር አብራሩ?

Page 6 of 20
መልስ
 መደመር መንገዳችን ነው፡፡ መደመር ሲባል ሰፊ ጽንሰ ሀሳብና ሀገረኛ አስተሳሰብ ነው፡፡ ጽንጸ ሀሳቡ

የተለያዩ የአለም ተሞክሮዎችንም ከግምት በማስገባት ሀገር በቀል እውቀቶችና እሴቶችን ጨምሮ

የተቀመረ የቀጣይ ሀገራዊ የብልጽግና መዳረሻ ጉዞ ላይ እንደ መንገድ የሚንጠቀምበት ነው፡፡ መደመር

ቁስሎች እንዲጠጉ፤ ህመሞች እንዲድኑ፤ ችግሮች እንዲፈቱ፤ ፈተናዎች እንዲታለፉ፤ ያለፈውን

ጉዟችንን መመልከቻና የቀጣይ ጉዟችን ጠቋሚ፤ አዲስ የእሳቤ ማዕቀፍ ነው፡፡

 መደመር የዛሬን ትውልድ ዐቅም በማሰባሰብ፤ ካለፈው ትውልድ የወረስናቸውን ጥንካሬዎች

በማሳደግ፤ እንዲሁም ክፍተቶችን በማረም፤ የቀጣዩን (የመደመር) ትውልድ የምንመከትበት የሃሳብ

መነጽርና የመግባቢያ ሰነዳችን ነው፡፡ ይህ የትውልድ ግንበታ እውን እንዲሆን፤ በተገዳዳሪ አፍራሽ

እይታዎች (ፓራዳይሞች) ውስጥ የመደመር ዕይታንና እሴትን ያለማሰለስ በትጋት ማሥረጽና

ማጠናከርን ይጠይቃል፡፡

 የመደመር ትውልድ በሚል የተዘጋጀዊ ሶስተኛው የክቡር ጠቅላይ ሚንስተራችን የመደመር መጸሀፍ

ትውልድን ከትውልድ ለመደመር የተቀየሰ መንገድ ነው፡፡ ካለፈው ትውልድ የተማረ የዛሬው ትውልድ፤

ነገ ሀገርን ተረክቦ ለሚመራው አዲስ ትውልድ የሚያሰማው ታላቅ የአደራ ደወል ነው፡፡ ከትውልድ

ለትውልድ ስለ ትውልድ የቀረበ ሀገራዊ ጥሪ፡፡

 የመደመር ትውልድ ስባል ቀጣይ በመደመር መንገድ ላይ የሚንገነባው ትውልድ ወይም የወደፊት

ኢትዮጲያን የሚናይበት ነው፡፡

9. በሀገረ መንግሥት ግንባታ ሂደት የኅብረ ብሔራዊ ፌደራል ሥርዓት፣ የሀገረ መንግሥቱን ቁልፍ መሠረታዊ

ክፍተቶች በመመለስ ረገድ ምን አስተዋጽ አለው?


መልስ
 እንደ ኢትዮጵያ ያሉ ብዙ ብሄርና ማንነቶች የሚታይበት ሀገር ውስጥ ህብረ ብሔራዊ ፌዴራል

ሥርዓት መግንባት ወሳኝ እና አማራጭ የሌለው ጉዳይ መሆኑ ግልፅ ነው፡፡

 በሌላ በኩል ይህንን ህብረ ብሔራዊ የፌዴራል ሥረዓት ለሀገረ መንግስት ግንባታ ወሳኝ የሆነ ሚና

የሚጫወት ሂደት ነው፡፡

 የሀገረ መንግስት ግንባታ ሂደት ዘርፈ ብዙ ሥራዎችን ማካናወን የሚጠይቅ ብቻ ሳይሆን ረጅም ጊዜን

የሚጠይቅ ነው፡፡

 የሀገረ መንግስት ግንባታ ሂደት ውስጥ የሚንከተለው ስርዓት ፌዴራል ስርዓት መሆኑ ከዚሀ ቀደም

የነበረውን የሀገረ መንግስት ግንባታ ሂደት ስብራቶችን ለማከምና ክፍተቶችን ለመምላት ይግዛል

ማለት ይቻላል፡፡
Page 7 of 20
10. የከረረ ልዩነት እና አለመግባባት በዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ላይ የሚፈጥረው አደጋ ምንድነው? ብሔራዊ

መግባባት - ዴሞክራሲያዊ ሥርዓትን ለመገንባት የሚኖረው አስተዋጽዖ ምንድነው?


መልስ
 የዲሞክራሲ ስረዓት ግንባታ በሚገነባው ስርዓት ዙሪያ መግባባትን መፍጠር ይፈለጋል፡፡

 እንደ ኢትዮጵያ ብዙ ልዩነት የሚታይበት ሀገር ውስጥ ልዩነቶች ላይ መነጋገርና በሰከነ ሁኔታ

በመወያየት መግባባትን መፍጠር ያስፈለጋል፡፡

 ልዩነት ላይ ያቶከረ አላስፈላጊ ክርክር ማድረግ ወደ ከረረ ልዩነት እና አለመግባባትን የሚወስደን ሲሆን

በዲሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ሂደት ውስጥ ከፍተኛ ችግሮችን ይፈጥራል፡፡

 የተካረረ ልዩነት ሁል ጊዜ ወደ መግባባት ሊያመጣ አይችልም፡፡ ልዩነት እየሰፋ በሚሄድበት ወቅት

ለውይይት እድሎች አይኖርም፡፡

 ብሔራዊ መግባባት በመሰረቱ ከነፃ ተቋማት ግንባታ ጋር በእጅጉ የተቆራኘ ነው፡፡ የትኛው ይቀድማል

የሚል ሀሳብ ላይ ከፍተኛ ክርክርከ ይታያል፡፡ ነገር ግን ሁለቱ ጉዳዮች የሚጻረሩ ብቻ ሳይሆኑ

የሚመጋገቡ መሆነቸውን መዘንጋት የለብንም፡፡

 በዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ሂደት ውስጥ ነፃ ተቋማት መገንባት ወሳኝ ጉዳ ሲሆን በኢተዮጵያ ሁኔታ

ግን ፡፡ ነፃ ተቋማት ተገንብተው በነፃ መከራከር፣ መወያየት እና መደራደር ከተቻለ ብሔራዊ መግባባት

ለማምጣት ምቹ ኔታን ይፈጥራል፡፡ ምክንያቱም በጭቆና ስርዓት ውስጥ የቆየ ህዝብ በነፃነት ተነጋግሮ

ለመግባባት የሚችልበት እድል መፍጠር አስፈላጊ ጉዳ ስለሆነ ነፃ ተቋመት መኖር ወሳብ ጉዳይ ነው፡፡

 ብሔራዊ መግባባት በዜጎች እምነት ላይ የተመሰረተ ጉዳይ በመሆኑ ዜጎች በተቋመቱ ላይ እምነት

ማሳደር ሲጀምሩ ወደ ብሔራዊ መግባባት ያመራናል፡፡

 በአጠቃላይ በአንድ ሀገር ውስጥ ብሔራዊ መግባባት መፈጠር ከተቻለ ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት

ለመገንባት ትልቅ አስተዋፅኦ አላቸው፡፡

11. ክሡትነትን ሀገራዊ ምሳሌዎችን በመጥቀስ አስረዱ? ኢትዮጵያን በክሡትነት መነጽር ግለጿት? አብሮነትን

ከክሡትነት ጋር በማያያዝ አስረዱ?


መልስ
 ክሱትነት የሚባለው ስርዓቶች ያለባቸውን ጉድለት በመሞላት ወደ ምሉእነት የሚያደረጉት ጉዞ ነው፡፡

ከአካባያቸው ጋር ያላቸውን ጉንኝነት ቀጣይነት ባለው መልኩ ከትንንሽ ነገሮች ጉንኝነት ወደ ትልልቅ

ነገሮች የመፈጠራቸውን ሂደት ክሱትነት እንሉዋለን፡፡ ለምሳሌ የሀገር ኢኮኖሚ ለማሳደግ አንዱ ዘርፍ

ለአብነት ግብርና ብቻውን የሚፈልገውን ሙሉ ሀገራዊ ኢኮኖሚያው እድገት ማምጣት አይችልም፡፡

ለብቻው የራሱን ድርሻ ሊወጣ ይችላል፡፡ ነገርግን ሁሉም ዘርፎች የግላቸውን ድርሻ በአግባቡ
Page 8 of 20
መወጣጥት ከቻሉ እና እርስበእርስ መደጋገፍ ባለባቸው ልክ መደጋገፍ ከቻሉ የሚታሰበውን ሀገራዊ

እድገት ማሳካት ይቻላል፡፡

 በሌላ ምሳሌ አንዱ ክልል በተወሰነ ዘርፎች ላይ የጎላ ተሳትፎ በማድረግ ሌላ አካባቢ ደግሞ በሌሎች

ዘርፎች ላይ በማተኮር ያመረቱትን ምርት የጋራ በማድረግ አንዱ ዘንደ ያጠረውን ሌላው ዘንድ

በማግኘት ፍላጎታቸውን መሟላት ይችላሉ፡፡ ይሄ ማለት አርቦት አደር አካባቢ ወተትና ስጋ ላይ

ትኩረት በማድረግ ማምረት ቢቻልና አርብቶ አደሩ ደግሞ ሰብልና ፍራፍሬን በአግባቡ ማምረት

በማረት ከተሞች አካባቢ ደግሞ በማኑፋክቸረንግና በአግልግሎት የሚከሰተውን ጉድለት በመሸፈን

በጥቅል ውጤቶች እንደ ሀገር ያለውን ፍላጎት በሙሉ ማሳካት ይቻላል፡፡ ይሄን አይነት ሂደትን ክሱትነት

ማለት ይቻላል፡፡

 ኢትዮጲያን በክሱትነት መነጽር ሲንመለከት አንድት ሀገር አንድነቷ የተጠበቀና አንድነቷ ደግሞ

በህዝቦቿ ህብረብሄራዊ ወንድማማችነት ድምር የመጣ መሆኑን ሲናይ ይሄን ክሱትነት ማለት ይቻላል፡፡

የተለያየ ክልሎች፣ የተለያዩ ብሄርብሄረሰቦች፣ የተለያዩ ተፈጠራዊ ስጦታዎቻን እና በርካታ አኩሪ

ድሎቻችን ተደምረው አንድ ላይ በክሱትነት ኢትዮጲያ የሚትባል ሀገር መፍጠር ተችሏል፡፡

የህዝቦቻችንም የተለያዩ ማነንቶች ብኖራቸውም አንድ ላይ በአብሮነት አንድ ማህበረሰብ መፍጠር

መቻላቸውን እንደ አንድ ክሱትነት ማየት ይቻላል፡፡

12. ቀጣናዊ ትሥሥር አንዱና ዋነኛው የውጭ ጉዳይ ግባችን እንደሆነ ይታወቃል። ይህንን የቀጣናዊ ትሥሥር

ጉዳይ አስፈላጊነቱን ከክሡትነት አንጻር አስረዱ?


መልስ
 በመደመር መነፅር የውጭ ጉዳይ ዋና ትኩረታችን፡-
 በቀጠናው ካሉ ሀገሮች ጋር የጋራ ጥቅሞቻችንን መሠረት ያደረገ አካባቢያዊ የልማት፣የኢኮኖሚ
እና የሰላም ትሥሥር እንዲፈጠር በትብብር መስራት እና ቀስ በቀስ እያደገ የሚሄድ ቀጣናዊ
የኢኮኖሚ ትሥሥር እንዲሆን አስፋለጊውን ጥረት ማድረግ፡፡
 ይህንንም ለማድረግ በቀጣናችን ያሉ ነባር አካባቢያዊ ድርጅቶች እንዲጠናከሩ ለማድረግ
እንዲሁም ድርጅቶቹ ለቀጣናዊ ትሥሥር መፈጠር መሠረት እንዲጥሉ በትኩረት ይሠራል፡፡
 በተጨማሪም እነዚህ አካባቢያዊ ድርጅቶች የቀጣናው የተበታተኑ ድምፆች ወደ አንድ
መሰባሰቢያ በማድረግ የቀጣናው ሀገራት የመደራደሪያ ዐቅም እንዲሆኑ ጥረት ያደርጋል፡
 ከጎረቤቶቻችን ጋር በሚያገናኙን የተፈጥሮ ሀብቶች ላይ በጋራና ፍትሐቂ ተጠቃሚነት መርሕ
የሀገራችንን ጥቅም ለማስከበር ፓርቲያችን ይሠራል፡፡ ድንበር ተሸጋሪ ወንዞቻችንን የመጠቀም
መብታችንን ባከበረ፣ ዓለም አቀፍ የድንበር ተሸፋሪ ወንዞች መርሖችን በተንተራሰ መልኩ
ለጥቅም እንዲውሉ ማድረግ አስፈላጊ ነው፡፡

Page 9 of 20
 በአጠቃቀም ምክንያት የሚመጡ አለመግባባቶችም በዓለም አቀፍ መርሖችና በዲፕሎማሲያዊ
መንገዶች እንዲከፈቱ በዘላቂነትም በወንዞቹ ላይ ሁሉን አቀፍ የሆነ ስምምነት እንዲደረስ
ያደርጋል፡፡
 በተመሳሳይ ሀገራችን በአካባቢያችን ካሉ ባለ ወደብ ሀገሮች የተሸለ የወደብ ተጠቃሚነት መብት
በሚያረጋግጥ መልኩ አካባቢያዊ ትብብሮች ላይ ትኩት በመስጠት ለመስራት እንደ አንድ ግብ
ተቀምጧል፡፡
13. በመደመር ዕሳቤ ቁልፍ የፖለቲካ ስብራታችንን በመጠገን ረገድ የብሔራዊነት ትርክት ፋይዳን አስረዱ?
መልስ
 የብሄራዊነት ትርክት የሀገራችን ፖለቲካ ስብራቶችን ከመጠገን አንጻር ከፍተኛ ፋይዳ አለው፡፡

ብሄራዊነት ማለት ህብረብሄራዊ አንድነት ማለት ነው፡፡ ይህ ደግሞ ህገመንግስታዊ ጭምር ነው፡፡

በህገመንግስቱ መግቢያ ላይ እንደተቀመተው ኢትዮጲያውያን በገዛ ፍቃዳቸው አንድ የፖለቲካና

ኢኮኖሚ ማህበረሰብ መገንባት እንደሚፈልጉ ያትታል፡፡ ህብረብሄራዊ አንድነት ማለት ደግሞ

የኢትጲያውያንን የብሄር፣ የቋንቋ፣ የሀይማኖት፣ የጾታ፣ የአስተሳሰብ፣ የታርክ ብዝሃነት እንደ ጌጥ

ወይም እንደ ጸጋ ሚቀበል ነው፡፡ እነዚህን ማንነቶች አስተሳስሮ፣ አስተባብሮ የያዘ ሀገራዊ አንዲነት አለ

ብሎ የሚያምን ነው፡፡ ብዝሃነቱ አንድነቱን ሳይከፋፍለው፣ አንዲነቱም ብዝሃነቱን ሳይጠቀልለው

ብዝሃነትን እንደ ጸጋ አንድነቱም እንደ ኃይል ብርታት የሚቀበል ነው፡፡

 በሀገራችን ካሉ ቁልፍ የፖለቲካ ስብራቶች ውስጥ አንዱ ሌላውን በጠላት የመፈራረጅና ተቀራርቦ

መስራት ባህል አለመዳበር ነው፡፡ ከዚህ አንጻር ብሄራዊነት ሁሉንም የሚያግባባ እና የሚያሰባስብ

በመሆኑ ለስብራቱ ፈዋሽ ይሆናል፡፡

14. የሀገረ መንግሥት ቅቡልነት ችግር በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ ከዕዳ ወደ ምንዳ ሽግግር እንዳይፈጠር

የፈጠረውን ፈተና አስረዱ?


መልስ
 በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ በተለያዩ ምግስታዊ ስርዓቶች ውስጥ ያልፈታናቸው የፖለቲካ የኢኮኖሚ እና

የማህበራዊ ችግሮች በመብዛታቸው የነሣ በለውጥ ሂደታችን ውስጥ ከእዳ ወደ ምንዳ የሚናደርገው

ሽግግር ውስጥ ከፍተኛ ችግር መሆኑ ግልፅ ነው፡፡

 ነገር በዚህ ሽግግር ውስጥ ትልቁ ፈተና የትርክት ግንባታ ላይ የተፈጠረ አለመግባባት ነው፡፡ የጋራ

መግባባት ለመፍጠር የሚደረገው ጥረት የገራ ታላቅ ትርክት መፍጠር፡፡

15. የመደመር ሳንካዎችን በዝርዝር አስቀምጡ? የፍጹም አንድነት እና የፍጹም ልዩነት ትርክት ክፍተት ከመደመር

ሳንካዎች ጋር በማያያዝ አስረዱ?

Page 10 of 20
መልስ
 የመደመር ሳንካዎች በጥቅሉ በሁለት ይቀመጣሉ፤ የአስተሳሰብና የግብር፡፡ የአስተሳሰብ ሳንካዎች

የሚባሉት፡- ዋልታ ረገጥነት፣ ጊዜ-ታካኪነት፣ አቅላይነት፣ ሙያን መናቅ እና ሞገደኝነት- ፌዘኝነትና

አድር-ባይነት ናቸው፡፡ የግብር ሳንካዎች የሚባሉት ፡- ሂሊና ቢሲነት፣ ልግመኝነት ናቸው፡፡

 ፍጹም አንድነት የሚባለው ጽንሰ ሀሳብ በራስ አምሳያነት ሁሉንም ለመሳል መሞከር፣ ወይም ሀገር

በሙሉ እኔን መምሰል አለበት በሚል የሚታይ እሳቤ ነው፡፡ ይህ አስተሳሰብ ብዘሃነትን በመልካም ማየት

የሚቸገርና ብዝሃነት ወደ ልዩነትና ግጭት ያመራል የሚል እምነት የሚይዝ ነው፡፡ በተቃራናዊ ደግሞ

ፍጹም ልዩነት በፍጹም አንድነት አስተሳሰብ በመገፋት ምክንያት የሚፈጠርና በተገፋ ልክ በደ ጫፍ

በመሄድ ልዩነትን የሚያጎላ እና አኛና እናነት የሚል ልዩነቶችን የሚፈጥር አስተሳሰብ ነው፡፡ እነዚህ

አስተሳሰቦች ከመደመር ሳንካዎች አንጻር ሲታይ በአስተሳሰብም በግብርም ሚገለጹ ናቸው፡፡ ለምሳሌ

ከዋልታረገጥነት አንጻር ሲታይ ሁለቱ አስተሳሰቦች ጫፍና ጫፍ ያሉና አንዱ ሌላውን በጠላት የሚያይ

ለመደመር የሚቸገር ነው፡፡ ከግብር አንጻርም አንዱ በራሱ በያዘው ሀሳብ ላይ ግትር በማለት

ልግመኝነት የሚያንጻባርቅ ሁኔታ ይስተዋላል፡፡

 የመደመር ሳንካዎችን መፍታት በራሱ የሀገራችን ፖለቲካ ስብራቶች ውስጥ ሚታዩ የፍጹም አንድነት

እና የፍጹም ልዩነት ትርክትን ማስታረቅ የሚችል መሆኑን መገንዘብ ይቻላል፡፡

16. የመደመር ዓምዶች የሚባሉት እነ ማን ናችው? የብሔራዊነት ትርክትን ከመደመር ዓምዶች ጋር በማያያዝ

አስረዱ?

17. ዴሞክራሲ በኢትዮጵያ ሀገረ መንግሥት ግንባታ ውስጥ ቁልፍ አስፈላጊነቶቹ ምንድን ናቸው? የሀገረ

መንግሥት ስብራቶቹን በመመለስ ረገድ ምን አስተዋጽዖ አለው?

መልስ
 በሀገር መንግስት ግንባታ ሂደት ውስጥ አንዱ ምሶሶ ጉዳይ ነፃና ገለልተኛ ተቋማት መገንባትና ሀገራዊ

መግባባትን መፍጠር ነው፡፡

 የዲሞክራሲ ሥረዓት ግንባታ ደግሞ በአግባቡ ተግባራዊ ማድረግ የሚቻልው ለዲሞክራሲ ስርዓት

ግንባታ ውስጥ የተቋማት ግንባታ ማሳካት ሲቻል ነው፡፡

 በሀገረ መንግስት ውስጥ የተቋማት ግንባታ ባልተጠናቀቀበት ሁኔታ ዲሞክራሲ ማፅናት ሂደትን

አስቸጋሪ የሚያደርግ ይሆናል፡፡

 ያልተጠናቀቀ ሀገረ ም›መንግስት ግንባታ የነፃና ገለልተኛ ተቋማት ግንባታ ጋር የተቆራኘ ነው፡፡

Page 11 of 20
18. በኢትዮጵያ ለተቋማት ድቀት ሥር የሰደደ ምክንያቱን አስረዱ? ይህንንም የተቋማት ድቀት ለፖለቲካ ገበያ

የሚፈጥረው ምቹ ሁኔታ እና የፖለቲካ ገበያ መልሶ በተቋማት ግንባታ ሂደት ላይ የሚኖረውን አደጋ አስረዱ?

የተቋማት ግንባታ አስፈላጊነትን በዝርዝር አስረዱ?

19. የሀገረ መንግመንግሥት ግንባታን ምንነትን በማብራራት የድኅረ እውነት ፖለቲካ በሀገረ መንግሥት ግንባታ

ሂደት ላይ የሚደቅነውን ፈተና በዝርዝር ግለጹ?

20. በመደመር ዕይታ መመሥረት በሀገራችን የተስተዋሉ የመሪነት ፈተናዎች ምን ምን ናቸውበዝርዝር አስረዱ?

እነዚህን የመሪነት ፈተናዎች ፍጥነትን ከሚያንቀረፍፉ ፈተናዎች ጋር በማያያዝ አስረዱ?

21. ነጠላ ትርክቶችን ከብቸኝነት ጉድለት ጋር በማዛመድ የሚፈጥሩትን ፈተና አስረዱ?

22. መደመር ጭቆናን አሽቀንጥሮ ለመጣል የፖለቲካ ባህልን ቁልፍ የሚያደርገው ለምንድነው? የፖለቲካ ባህል

ክፍተት እና ነጻነትን የማስተዳደር ችግሮች ምን እንደሆኑና የሚያስከትሏቸውን ችግሮች አያይዛችሁ በዝርዝር

አአብራሩ?

23. በፕሮግረሲቭ ካፒታሊዝም እና በኢንተርፕርነራል መንግሥት መካከል ያለውን አንድነት አስረዱ?

 እንደ ኢንተርፕሬነር መንግስት በሀብት ፈጠራ ላይ ትኩረት ማድረግና የተፈጠረውን ሀብት በጥቅቶች

እንዳይመዘበር በመከላከል ፍትኃዊና ፈጣና እድገት በማምጣት የኑሮ ውድነትና ስራ አጥነት ችግር

ፈጥነን መቅረፍ ይኖርብናል፡፡

 በየግዜው የሚገጥሙን ችግሮች በመጋፈጥ ወደ እድል በመለወጥ የጀመረነውን የብልጽግና ጉዞ

ሳይደናቀፍ ማስቀጠል የሚችል

24. የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ የባለፉት ዓመታት የዕድገት ጥራት ፈተናዎች መገለጫዎች ምንድን ናቸው? ለለዕድገት

ጥራት ችግሩ መነሻ እና ማሳያ የሆኑ ጉዳዮች እና መዛባቶቹ ምን ነበሩ? ብልጽግና ይህንን ለማስተካከል

የወሰዳቸው እና እየወሰዳቸው ያላሉ መፍትሔዎች ምንድን ናቸው?

25. የሰው ልጅ ተደማሪ ፍላጎቶች እና ከሥነ ምግባር አስተውሎት ጋር ያላቸው ግንኙነት ምንድነው? የሰው ልጆች

ፍላጎትን በማሟላት ረገድ ሥነ ምግባር የሚኖረው ቁልፍ አስተዋጽዖ ምንድነው?

Page 12 of 20

26. የፖለቲካ ገበያ መሣሪያዎች የሚባሉት ምን ምንድን ናቸው? በዝርዝር አስረዱ?

27. የሰው ሠራሽ አስተውሎትን መልካም ጎኖች እና አደጋዎችን አስረዱ? መልካም ጎኖቹ ብልጽግናን በማረጋገጥ

የሚኖራቸውን አስተዋጽዖ እንዲሁም አደጋዎቹ በሀገረ መንግሥት ቅቡልነት እና በፖለቲካ መረጋጋት ላይ

ያላቸውን አሉታዊ ተጽዕኖዎች አስረዱ?

28. ከተለያዩ ሥልጠናዎቻችን በመነሣት የምናብ እና የሐሳብን ኃይልና ዐቅም አስረዱ? መሪነትን ከዚህ አንጻር

አስረዱ?
መልስ
 ምናብ ሲባል እየተከሠተ ካለውና ከተከሠተው ነገር በሐሳባዊ ዓለም ርቆ በመሄድ፣ ለሁኔታዎችና እና

ለነገሮች አእምሯዊ ሞዴል የመፍጠር፣ የመቅረጽና የመጠቀም ሂደት ነው። ይህም በየግዜው

ለሚፈጠሩ ችግሮች አዳዲስ ዕድሎችን በመፍጠር አዲስ የዕድገት መንገድ ለማግኘት ያስችላል።

 በሀገራችን በቅርብ ዓመታት የለውጡ አመራር ኢኮኖሚያዊ ጫናዎች ሲፈጠሩ ለመመለስ

የተሞከረው በዚህ ምናባዊ መንገድ ነው። በችግሮች ውስጥ ተጠምዶ ለችግሮቹ ምላሽ በመስጠት፣

ከመጠመድ ይልቅ ችግሮችን ወደ ዕድል የሚለውጥ መንገድን ተከትሏል። በተፈጥሮና ሰው ሠራሽ

ችግሮች ምክንያት የደረሱ ኢኮኖሚያዊ ጫናዎችን ለመከላከል የሚያስችሉ ርምጃዎችን ብቻ

ከመውሰድ ይልቅ ከችግሩ ከፍ ብሎ ዕድሎችን መጠቀም ወደሚያስችሉ ጥረቶች ተደርጓል። በአቅርቦት

የዕሴት ሠንሰለት መበጠስ ምክንያት የምርት መቀዛቀዝ ሲፈጠር፣ ኢኮኖሚያዊ ጫናዎች ሲደረጉብን፣

ጫናዎችን ለማርገብ ወደ አልተፈለገ ድርድር መግባትን ምላሽ አልተደረገም። ይልቁንም ለጫናዎች

ያጋለጠንን ስንዴ ከውጭ አናስገባም የሚል ምላሽ ሰጥተናል።

 ምናባዊ ኢኮኖሚ ማለት፣ ከነበረው ስለ ምግብ ብቻ የማሰብ አካሄድ ወጣ ብሎ አዲስ አእምሯዊ ፍኖት

መፍጠር ነው። አረንጓዴ ዐሻራ የሚል ፍኖት። ስንዴ አናስገባም የሚል ፍኖት። ከነበረው ብዙ የራቀ፤

በዚህም የተነሣ የማይሆን የሚመስል፣ ነገር ግን ሆኖ መሬት ላይ ወርዶ ታሪክ እየቀየረ ያለ አካሄድ

ነው። የተፈጠሩ ችግሮችን በዕለታዊ ምላሽ ለማለፍ ከመጣር ይልቅ፣ ዘላቂ የሆነ የምግብ እጥረት

ጥያቄዎችን ለመመለስ እንደ ዕድል ተጠቅመናቸዋል።

29. ብልጽግና ፓርቲ በኢትዮጵያ የፖለቲካ ታሪክ ውስጥ ከተቋቋሙት ፓርቲዎች የሚለዩት ዋና ዋና ነገሮች

ምንድን ናቸው?

Page 13 of 20
መልስ
 የብልጽግና ፓርቲ ከማህበራዊ መሰረት አኳያ የሚከተለው ፖሊሲ ሁሉ አቀፍ አሳታፊነትን (big tent

or catch all approach) ማረጋገጥ ነው፡፡ ለዜጎች ግልጽ እና ተደራሽ የሆነ፣ ምንም አይነት አድሎ

የማያደርግ ሁሉንም ዜጋ በእኩል የሚያስተናግድ ህበረ ብሄራዊ ፓርቲ ነው፡፡

 ብልጽግና የመሀል ፖለቲካ አራማጅ ፓርቲ ነው። በዚህ ባህሪውም ከታሪካችንም ከኢህአዴግም የተለየ

ነው

30. ኢንተርፕርነራል መንግሥትን ከኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ሁኔታ አንጻር ተመራጭ የሚያደርገው ምንድነው?
መልስ
 የሀገራችን የኢኮኖሚ ሁኔታ ሲንመለከት ገና ያላደገ እና ብዙ የኢኮኖሚ ተግዳሮቶች የሚታይበት

ሲሆን ከእነዚህ ትግዳሮቶች ውስጥ ብዙ ወጣት ህብረትሰብ ክፍል በሥራ አጥነት ፈተና ውስጥ

የሚገኝበት፤ የመኒፋክቸሪንግ ዘረፍ ብዙም ያለደገበት መሆን፣ የኑሮ ውድነት እና የዋጋ ግሽበት

በከፍተኛ ሁኔታ ይታያል፡፡

 የኢኮኖሚውን ተግዳሮቶች ለመቀለበስ ከመንግስት ከሚጠበቀው ሁኔታ አንፃር በተለይም ለሥራ አጥ

ዜጎች የሥራ እድል ፈጠራ ጉዳይ የቅድሚያ ትኩረት የሚሰጠው ነው፡፡ ለዚህም ደግሞ መንግስት

የሀገሪቱ ሀብት ፈጠራ ላይ ትኩረት ማድረግ ያስፈልጋል፡፡

 እንደ ኢንተርፕሬነር መንግስት በሀብት ፈጠራ ላይ ትኩረት ማድረግና የተፈጠረውን ሀብት በጥቅቶች

እንዳይመዘበር በመከላከል ፍትኃዊና ፈጣና እድገት በማምጣት የኑሮ ውድነትና ስራ አጥነት ችግር

ፈጥነን መቅረፍ ይኖርብናል፡፡

31. የሠርጎ ገብ ፖለቲካ ምንነት፣ መነሻ እና ፈርጆችን አስረዱ? ከፖለቲካ ገበያ ጋር ያለው ተዛማጅነት ምንድን

ነው። የየሠርጎ ገብ ፖለቲካ በፓርቲያችን እና በለውጥ ሂደቱ ላይ የሚፈጥረው ጫና ምንድነው?


መልስ
 የሰርጎ ገብንት ፖለቲካ ሚባለው አንድን ፓርቲ ወይም መንግስትን በመጥለፍ የራስን ግብ ለማስፈፀም

ወይም ፓርቲውንና መንግስትን ለማዳከም የሚደረግ ጥረት ነው፡፡ ለምሳሌ በፓርቲ ውስጥ በአቋራጭ

ስልጣን እና ገንዘብ እናገኛለን ብለው የሚንቀሳቀሱ ኃይላት ፓርቲን በመጥለፍ እና በማዳከም

ስልጣንና ሀብት ለመቆናጠጥ ይንቀሳቀሳሉ፡፡

 ሰርጎ ገቦች የፓርቲያችንን ርዕይ ለመንጠቅ እና እይታውን ለመስረቅ የሚሞክሩበት 3 ጉዳዮችን

ማንሳት ይቻላል፡-

1. ከርዕያችን እና ከዘላቂ ግባችን ይልቅ በጊዜያዊ ክስተቶች እና አጀንዳዎች እንድንጠመድ እና

እንድንከፋፈል ማድረግ፣
Page 14 of 20
2. ክስተቶቹና አጀንዳዎችን ተጠቅመው የተጠለፉና የተወሰዱ አመራሮችን በመጠቀም ወደ

ፓርቲያችን ሰርገው መግባትና መዋቅሮችን መቆጣጠር፣

3. በክስተቶችና በአጀንዳዎች ያልተወሰዱትን እና ያልተጠለፉትን ወይም ፀንተው የቆዩትን

አመራሮች ማሸማቀቅና መግደል ነው፡፡

 ሰርጎ ገብነትን ከላይ በገለጸነው ትርጉም ሲናየው ከፖለቲካ ገባያ ጋር እንደሚመሳል መረዳት ይቻላል፡፡

በፖለቲካ ገበያ ውስጥ ፖለቲካን እንደ ሸቀጥ ለራስ ጥቅም ሲባል መሸቀጥን የሚመለከተ ሲሆን

በተመሳሳይ ሰርጎገቢነትም ለግል ጥቅም ሲባል አንድን ተቋም ከኢላማው ውጭ እንዲንቀሳቀስ

ማድረግ ነው፡፡

 ሰርጎገብነት በፓርቲያችን ላይ ያለው ተጽእኖ ሲታይም ፈተኛ ነው፡፡ አንድም የለውጥ ሂደቱን

ያልጨረሰና በየግዜው በተለዋወጭ ወቅታዊ ሁኔታ እየተፈተነ ያለው ፖለቲካችን ሰርጎ ገብነት ትልቅ

ፈተና ነው የሚሆነው፡፡ አንድም የሚፈጠረውን ጥቅት ሀብት በመዝበርና ለግል ጥቅም ለማዋል

በሚደረግ ጥረትና በሌላ በኩል ደግሞ በበርካታ አጀንዳዎች ላይ የልህቃን ስምምነት መፍጠር

ባለመቻሉ በነዚህ ጉዳዮች ላይ ብዥታን በመፍጠርና የፓርቲን ህልውና ሊፈታተኑ ይችላሉ፡፡

 ለዘህ መፍትሄው በአንድ በኩል የዴሞክራሲ ልምምዳችን ሳይደናቀፍ በማስቀጠል፣ በሌላ በኩልኢ-

ዴሞክራሲያዊ በሆነ መንገድ ስልጣን ለመቆናጠጥ የሚደረጉ ጥረቶችን መከላከል ያስፈልጋል።

32. በኢትዮጵያ ሕዝብ ትግል ውስጥ የተነሡ ቁልፍ ጥያቄዎች ምንድን ናቸው? ከእነዚህ ቁልፍ ጥያቄዎች በሁለቱ

አብዮቶች ሁለቱን ለመመለስ ጥረቶች ተደርገዋል፡፡ ጥያቄዎቹ ግን በምልዐት አልተመለሱም፡፡ ላለመመለሳቸው

ዋነኛው ምክንያት ምንድነው? ብልጽግና ጥያቄዎችን ለመመለስ ያደረገው ጥረት ምንድነው?


መልስ
 በኢትዮጵያ ሕዝብ ትግል ውስጥ ለረጅም ጊዜ የህዝብ ጥያቄ ሆነው የቆዩ ጉዳዮች የእኩልነት፣

ዴሞክራሲ እያረጋገጡ መሄድ እና የልማት ጥያቄዎች ናቸው፡፡

 ኢትዮጵያ ውስጥ የተለያዩ የለውጥ ሙከራዎች ተደርገዋል፡፡ በእነዚህ የለውጥ ሙከራዎች አጠቃላይ

ሂደት ውስጥ የኢትዮጵያውያን ልሂቃን ተሳትፎ የአንበሳውን ድርሻ የሚይዝ ነበር፡፡ የመጀመርያው

አብዮት በመሰረቱ ዘውዳዊ ስርአቱን በመገርሰስና ወሳኝ የሚባለውን የመሬት ጥያቄ አንጻራዊ በሆነ

መልኩ መልሶ ከማለፍ አንጻር የተሳካ አብዮት ይሁን እንጂ ኢትዮጵያን በማሻገር ግብ ከተለካ የተሳካ

አብዮት ተደርጎ የሚወሰድ አይደለም፡፡ ሁለተኛው አብዮትም በመሰረቱ የብሄርንና ራስን በራስ

የማስተዳደር ውጥን የዜጎችን መብት ከመመለስ ያለፈ ውጤት አሳክቷል ተብሎ አይወሰድም፡፡ ይህም

የዜጎች መሰረታዊ ጥያቄ ሆኖ የቆየውን የብዝሀነት ጥያቄ በአንፃራዊነት የመለሰ ቢሆንም የዜጎችን

Page 15 of 20
የዴሞክራሲ እና የዕኩልነት መብትና የፍትሀዊ ተጠቃሚነት መብት በማሳካት በኩል እንደ

መጀመርያው አብዮት ሁሉ የተሳካ አብዮት ተደርጎ የሚወሰድ አይደለም፡፡

 ፓርቲያችን እያካሄደ ያለው ለውጥ መሠረት የሚያደርገው በሀገሪቱ ለረጅም ጊዜ የህዝብ ጥያቄ

ሆነው የቆዩ ጉዳዮችን ደረጃ በደረጃ መመለስ ላይ ነው፡፡ የእኩልነት፣ ዴሞክራሲ እያረጋገጡ መሄድ እና

የልማት ጥያቄዎች ናቸው፡፡ በሀገራችን የእኩልነት፣ የዴሞክራሲ እና የልማት ጥያቄዎች ደግሞ እርስ

በዕርስ የሚተሳሰሩ ናቸው፡፡ ዴሞክራሲ ሳይኖር የብሔሮችን ጥያቄ መፍታት እንደማይቻል ሁሉ፣

ኢኮኖሚያችን ሳያድግ ደግሞ ለዴሞክራሲ የተመቸ ህብረተሰብና ባህል መገንባት አይቻልም፡፡

ኢኮኖሚያችን ካላንሰራራ የተማረ ህበረተሰብ፣ ብቁና ለመላው ህዝብ ተደራሽ የሆነ ሚዲያ፣ የጐለበተ

የሲቪል ማህበረሰብ ተቋማት፣ ሐሳብ ማውጠንጠን የሚችል ልሂቅ፣ ፖሊሲዎችን መፈተሽ የሚችል

ወጣት፣ ትላልቅና ውስብስብ አጀንዳዎችን የሚረዱና የሚያስረዱ ምሁራን መፍጠር አይቻልም፡፡ ዘላቂ

ሠላም ለማስፈን፣ የተረጋጋ ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ለመገንባት፣ የዳበረና የበለፀገ የኢኮኖሚ ሥርዓት

እንዲኖረን እርስ በርሳቸው የሚተሳሰሩ ወሳኝ የህዝብ ጥያቄዎችን በተደራጀ መንገድ የመመለስ

አቅጣጫ መከተል ወሳኝ ነው፡፡

 አገራዊ ለውጡ ጅምርና በሂደት ላይ የሚገኝ እንደመሆኑ መጠን ዛሬም ሆነ ነገ መማርን፣ በተሞክሮ

ማደግን፣ በአዳዲስ ነገሮች መበልጸግን መነሻ አድርጎ ይወስዳል፡፡ አገራዊ ለውጡ ከመጀመርያው

አብዮት የመሬት ጥያቄ የተፈታበትን አግባብ በጥንካሬ ወስዶ፣ ከሁለተኛው አብዮት ብሄርን ጨምሮ

የብዝሀነት ጥያቄ መልስ እንዲያገኝ የተደረገውን ጥረት በመገምገም በሁለቱም አብዮቶች መሳካት

ያልቻለውንና ለመሬትና ለብሔር ጥያቄ የተሟላ ምላሽ አለማግኘት እንደምክንያት የሚወሰደውን

የዴሞክራሲ ጥያቄ አለም ከደረሰበት ነባራዊ ሁኔታና ከዜጎች የዘመናት ፍላጎት ጋር እያጣጣመ እና

ሚዛኑን እየጠበቀ መልስ መስጠትን ግቡ ያደረገ የለውጥ ሂደት ነው፡፡

33. ሥር የሰደዱ የሀገራችን የፖለቲካ ችግሮች እና ነባራዊ ሁኔታው የሚፈጥራቸው ፈተናዎች ተደምረው

በሀገራዊ አንድነት እና በፖለቲካ መረጋጋት ላይ የሚፈጥሩትን አደጋ አስረዱ?


መልስ
 ኢትዮጵያ ታሪኳን በሙሉ ያሳለፈችው በአንድ ጫፍ ብዝሃነትን በማይቀበል በሌላ ጠርዝ ደግሞ

መነጣጠልን ሳይሰለች በሚሰብክ ሁለት ፍጹም ተቃራኒ ሃገራዊ ትርክቶች ተወጥራ ነው። እነዚህ

ተቃራኒ ትርክቶች በሃገራችንና በህዝቦቿ ላይ የፈጠሯቸው ህመሞች በአይነትም በመጠንም ብዙ

ናቸው።

Page 16 of 20
 እነዚህ ትርክቶች የሃገራችንን የፖለቲካ ምህዳር ተቆጣጥረው በኖሩባቸው ዘመናት ሁሉ የመገፋትና

የባይተዋርነት ስሜት ነግሶ ቆይቷል። ብሄርተኝነት፣ ዘረኝነትና ጥላቻ ሁለመናችንን ተቆጣጥሮን

ኖሯል። የፖለቲካ ሴረኝነት፣ የአመራርና የአሰራር ብልሽትና ሌብነት ፈቃድ የተሰጣቸው የተከታታይ

ትውልዶች መታወቂያ ሆነው ቆይቷል።

 ወደድንም ጠላንም ከታሪካችን እጅግ በተለየ መንገድ የፈጠርነውን ለውጥና እየገነባን ያለነውን

ዓለማዊ ስርዓት እነዚህ ተሻጋሪ ህመሞች እየፈተኑት ነው። በኛ ዘመን በተሻጋሪ ህመሞች እየተጠቃን

ያለነውም አዲሱ ሃገራዊ አስታራቂ ትርክታችን ገዢ ቦታ እንዲይዝ ማድረግ ባለመቻላችን ነው።

ብሄርተኝነት፣ ዘረኝነትና ጥላቻ እጅግ ስር በመስደዳቸው እኛ በእጃችን በሰራነው የይቅርታ፣ የዕርቅና

የፍቅር ዘመን እርስ በራሳችን መፈራራቱ፣መጠራጠሩና መገፋፋቱ ቀላል አይደለም። የፖለቲካ

ጽንፈኝነት ተከትሎን በመዝለቁ እርስ በራስ መተማመን ተስኖን ዛሬም ወንድማማቾችና

እህትማማቾች በመግለጫ እንወራወራለን። ከሞራል ዝቅጠትና ከሃገር፣ ከህዝብና ከአላማ ፍቅር

ጉድለት የሚመነጨው ሌብነት ለልማት የሚውል ሃብታችንን፣ ብቃትና ንቃት ያላቸውን ወንድምና

እህቶቻችንን፣ የአገልጋይነት መንፈሳችንን፣ ዴሞክራሲያዊነትና ውጤታማነታችንን፣ ተቋማዊ

አሰራርና ሰላማችንን እየበላ ዛሬም ይከተለናል።

 በጥቅሉ ሲታይ ሁለቱ ጽንፈኛ ትርክቶች የወለዷቸውን ተሻጋሪ ህመሞች ከኛ ዘመን ትውልድ ህሊናና

ልብ ማራቅ የሚቻለው እኩልነትና ህብረ ብሄራዊ ወንድማማችነትና እህትማማችነትን

የሚያቀነቅነው አዲሱ ሃገራዊ አስታራቂ የትስስር ትርክት የበላይነት እንዲይዝ በማድረግ ብቻ ነው።

34. የባሕር በር ጉዳይን አስፈላጊ የሚያደረጉ ሀገራዊና ቀጣናዊ ጉዳዮች ምንድን ናቸው? የባሕር በር ጥያቄያችን

መሠረቱ ምንድነው? ጥያቄው ምላሽ እንዲያገኝ የምንከተላቸው አማራጮች የትኞቹ ናቸውናቸው?


መልስ
 ኢትዮጵያ ሀገራችን በውሃ የተከበበች፣ ሙሉ ዙሪያዋ ውሃ የሆነች ደሴት ነች ነገር ግን ሁል ጊዜ ውሃ

የሚጠማ ሀገር ነች፡፡ በሀገራችን በዋናነት የቀይ ባህርና የአባይ ጉዳይ ዋና አጀንዳ አድርገን መነጋገር

ይኖርብናል ምክንያቱም ሁለቱም ኢትዮጵያን የሚበይኑ ከኢትዮጵያ ጋር የተቆራኙ ለኢትዮጰያ

ጥፋትና እድገት መሰረት ናቸው፡፡ በዓለም ደረጃ በአሁኑ ጊዜ የውሃ ፖለቲካ ከፍተኛ ድርሻ ይኖራዋል፡፡

 የባህር በር ጉዳይ ኢትዮጵያ በታሪክ፣ በጂኦግራፊ በኢኮኖሚ ምክንያቶች አሳማኝ ጥያቄ አላት የሙል

ስምምነት በተባባሩት መንግስታት ቻርተር ላይ አለ፡፡

 ስለሆነም የሀገራችን የባህር በር ጥያቄ ዋና መሰረቱ የህዝብ ብዛት፣ የጂኦግራፊ አከባቢያዊ ቅርበት

ምክንያት የአኮኖሚ ጉዳይ ናቸው፡፡

Page 17 of 20
35. ለኢትዮጵያና መሰል አዳጊ ሀገራት መፍጠርና መፍጠን ካደጉት ሀገራት በይበልጥ ለምን አስፈለገን? መፍጠርና

መፍጠንን ለመተግበርና ውጤት ለማየት ከአመራሩና ከተቋማት ምን ይጠበቃል እጥረትና ዐቅሞችን ለይተው

ያብራሩ?
መልስ
 ከወል እውነት ፈጠራና ፍጥነት አንጻር፡- መሰረታዊ የብልጽግናን ታሪካዊ ተልዕኮ ማወቅ ተገቢ ነው ፡፡

ከብልጽግና በፊት የነበሩት መንግስታት በሀገራችን የነጠላና የቡድን እውነት ገንብተው እንደነበር

ይታወቃል ፡፡ በመሆኑም ሀገራችን የሀገረ መንግስት ግንበታን አጠናቃ ያልጨረሰች ሀገራችን በወል

እውነት የተመሰረተ የሀገረ መንግስትና የህብረ መንግስት ግንባታን ማጠናቀቅ የብልጽግና ታሪካዊ

ኃላፊነት ነው፡፡ በዚህ አቅጣጫ የወል እውነት ተጨባጭ ለማድረግ የወንድማማችነት አስተሳሰብን

በመከተል በተግባር ከህብረ ብሄራዊ እሳቤ ጋር በማጣመር መሰራት ይገባል ፡፡ የሀገራዊ ምክክርና የእርቅ

ኮሚሽን ይህን ዓላማ ለማሳካት የተቋቋመ ተቋም መሆኑን መገንዘብ ይገባል፡፡ በዚህ ሂደት

ያልተግባባንባቸው ጉዳዮች ላይ ስምምነት በመፍጠር የነጠላ እውነቶች በማስታረቅ ወደ ወል

አውነቶች የማምጣት ስራ ይከናወናል ፡፡ በሀገራችን በየአካባቢው ከራሳቸው ነባራዊ ሁኔታ የተለያየ

ነጠላ እውነቶች ያሉ ሲሆን እነዚህ ነጠላ እውነት በራሳቸው ስህተት ነው ማለት አይደለም፡፡ ነገር ግን

በመነጋገርና በመደማመጥ የተናጥል እውነታችንን ወደ ወል እውነት ማሳደግ ይገባል፡፡

36. ከከዴሞክራሲ ባሕል ግንባታ ጋር ተያይዞ ማኅበረሰብ በዕሴትነት ሊላበሳቸው የሚገቡ ባሕሪያትን በመዘርዘር

ያብራሩ?
መልስ
 የዴሞክራሲ ባህል ግንባታ ሥራን ለማሳካት የህዝቡን የጋራ የሆኑ ብሔራዊ ጠባይ፣ ስነ ልቦናዊ መገለጫ

እና ኅብረተሰባዊ ልማድ ያገናዘበ መሆነ አለበት፡፡


 ጥናቶች ከዲሞክራሲያዊ ባህል ጋር የተያያዙ ዐሥር መሠረታዊና ዓለም አቀፍ የሆኑ የሕዝብ ዕሴቶችን ለይተዋል።
1. ራስን መምሪት፡- ራስን ችሎ ለማሰብና ራስን በራስ ለመምራት መቻል፣ ለመምረጥ፣ ለመፍጠር፣ ነጻ

ለመሆን፣ ግብ ለማስቀሙየ መጣጣር

2. መነቃቃት፡- የተነቃቃ ሥነ ልቦና፣ የበራለት፣ የሕይወትን ፈተና የማሸነፍ ሞራል

3. ዓለም አቀፋዊነት፦ ከሥጋዊ ወይም _ ከአካባቢያዊ ዝምድናና _ ወዳጅነት በዘለለ ስለሰው ልጆች መጨነቅ

4. ቅንነት፡- አብሯቸው የሚኖሩትን ሰዎች ለመርዳትና ከፍ ለማድረግ መጣር፣ የአጋዥነት፣ የይቅር ባይነት፣

ሐላፊነትን የመሸከም፣ መልካም ወዳጅነትን የመመሥረት ጠባይ

5. ደስታ አሳሽነት፡- ደስታን ማሰስና የሚያዝናኑ ነገሮችን ማሰስ

Page 18 of 20
6. እሽ ባይነት- ለሌሎች ሐሳብና ፍላጎት ተገዢ መሆን፣ በራስ ከማሰብና ከመወሰን ይልቅ የሌሎችን ሐሳብና

ፍላጎት መቀበልና የዚያ ተገዢ መሆን

7. ደኅንነት፡- ስለደኅንነት ወይም ከአደጋና ከጥቃት ስለመጠበቅ መጨነቅ

8. ጨዋነት፡- ለሌሎች ሰዎች መልካም መሆን፣ ችግራቸውን መረዳትና ለማገዝ መፈለግ፣ የወዳጅነት ስሜት

9. ስኬት፡- ስኬታማ ለመሆን መትጋት፣ኑሮን ለማሟላት መጣር

10. ስልጣን፡- የበላይ ለመሆንና ስልጣን ለማግኘት መጣር፣ ለሥልጣንና ለመላይነት መፎካከር

 ዲሞክራሲና የኢኮኖሚ ልሣት ዝቅተኛ የሆነባቸው ሀገራት ለኋለኞቹ አምስት ዕሴቶች (እሸ ባይነት፣ ደኅንነት፣

ጨዋነት፣ ስኬትና ሥልጣን) ትልቅ ዋጋ ይሰጣሉ። ይህም ማለት ዜጎች በኅብረተሰቡ ልማድ የሚደፈቁበትና
አዲስ ሐሳብ ለማመንጨት የሚፈሩበት፣ ፍርሐትና ጥርጣሬ የነገሠበት፣ ለግለሰባዊ ስኬትና ሥልጣን
እሽቅድድም የሚደረግበት ሀገራዊ ሁኔታ ይኖራል ማለት ነው። በዚህም ምክንያት ጠልፎ መጣል፣ የሥልጣን
ግጭትና አድር ባይነት የሰፈነበት ኅብረተሰብ ይኖራል ማለት ነው። ሀገራችን ኢትዮጵያ በኢኮኖሚ ልማቷ ገና
በማደግ ላይ ስላለች፣ ዲሞከራሲም ገና በጅምር ላይ የሚገኝ በመሆኑ የእነዚህ ኋላ ቀር ዕሴቶች የበላይነት
ይስተዋልባታል።
 ከእነዚህ ዕሴቶች መካከል የስኬት ዕሴት በተለየ ሁኔታ በሀገራችን ዝቅተኛ እንደሆነ በደምሳሳው ማስተዋል
ይቻላል። ጉዳዩ ከጠበኝነት ጠባያችን ጋር የሚገናኝ ነው። ነገሮችን በጉልበት ለማስፈጸም የምንሮጥና በትጋት

ስኬት ላይ ከመድረስ ይልቅ ሰዎችን _ በጉልበትና በሤራ ለማሸነፍ ትልቅ ዋጋ የምንሰጥ ይመስላል። በዚህም
የተነሣ ሠርቶ ለመለወጥና የሕይወትን ግብ ለማሳካት ያደጉ ሀገራትን የጠቀማቸው የስኬት ዕሴት በእኛ ሀገር
ግን ዝቅተኛ ቦታ ሳይሰጠው አልቀረም፡፡
 ከዕሴቶቹ መካከል በሀገራችን ጎልቶ የሚታየው አንዱ ዕሴት እሽ ባይነት ነው።

ክፍል ሁለት

ከዚህ የሚከተሉትን ሐሳቦች በመደመር ዕይታ ግለጡ

i. ማኅበረሰባዊ ብሔርተኝነት

ብሄር፣ ጎሳን ወይም ነገድን ማእከል ያደረገ የእኛነት ስሜት

ii. ሲቪክ ብሔርተኝነት

ዜግነት ወይም አገርን ማእከል ያደረገ የእኛነት ስሜት

iii. ቁስ ተሻጋሪ ዕሴቶች

ከቁሳዊ ጥቅም ለዘለሉ ጉዳዮች የሚሰጥ ግመት ወይም ዋጋ

iv. ኅብር

ህብር የሚለው ጽንጽሀሳብ የሚያሳያው ብዝሃነትና አብሮነት በጋራ የያዘ ነው፡፡ ያለንን ብዝሃነትን እንደ

Page 19 of 20
ጸጋ በመጠቀም ህብረብሄራዊ ወንድማማችነትና እህትትማማችነትን በማጎልበት ሀገራዊ አንድነትን

መገንባት፡፡

v. አማካዩ መንገድ

አመካይ መንገድ ሲባል የሚታዩ ዋልታ ረገጥ ሀሰቦችን ለማስተራቅ እና የተሸለ አማራጭ የሚንቀይስብት

ስልት ነው፡፡ የፓርቲያችን አንዱ መገለጫም አመካይ መንገድ የሚመረጥ ፓርቲ ነው፡፡

vi. አካታች ምኅዳር

አካታች ምህዳር ሲባል ፖለቲካ ምህዳሩ ሁሉንም የሚያቅፍ የሆነ እና የሚገለል አካል እንዳይኖር

የሚያደርግ ነው፡፡

vii. የመስፈንጠር ስልትስልት/ የዝላይ ስልት

ተፈጥሯዊ የኢኮኖሚ ሂደቶችን ሳይከተል፣ በሂደቱ የሚጠበቁ ደረጃዎችን ዘልለን ከግባችን እንዲንደርስ

የሚያደርገ አቋራጭ ስልት ነው፡፡

viii. ነ ቢር ነበብነት

ከነባራዊ ሁኔታ የሚነሳ፣ እውነታውን እያዩና እያገናዘቡ የሚሄድ አስተሳሰብ ወይም ፍልስፍና

ix. ገር ኃይል

ከወታደራዊና ኢኮኖሚያዊ ሃይል ውጭ ያለ ቀጥተኛ ያልሆነ የተጽዕኖ አቅም

x. ጠጣር ኃይል

በወታደራዊና ኢኮኖሚያዊ ይዞታ ላይ የተመሰረተ የተጽዕኖ አቅም

Page 20 of 20

You might also like