Agreement of Casing Sales

You might also like

Download as docx, pdf, or txt
Download as docx, pdf, or txt
You are on page 1of 3

የፒቪሲ ኬዚንግ (PVC Casing) ሽያጭ/ ግዥ ውል

ይህ ውል በውል ሰጪ በአጃይ ፓይፕስ ኃ/የተ/የግል ኩባንያ አድራሻ አዲስ አበባ ቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 03 የቤት ቁጥር አዲስ
ስልክ ቁጥር 0911 52 25 98 ሻጭ ድርጅት ተብሎ በሚጠራው፤-
እና
በጢስ እሳት ውሃ ስራዎች ኃ/የተ/የግል ኩባንያ አድራሻ ባህር ዳር ክፍለ ከተማ ወረዳ የቤት ቁጥር
ስልክ ቁጥር ገዥ ድርጅት ተብሎ በሚጠራው መካከል ዛሬ የካቲት
ቀን 2013 ዓ.ም ውል ተፈርሟል፡፡

አንቀጽ አንድ
የውል ዓላማ
1.1 የዚህ ውል መሰረታዊ ዓላማ ገዥ ለሚሰራቸው የውሃ ጉድጓዶች የሚሆኑ የፒቪሲ ኬዚንግ ቱቦዎችን ገዥው
ባቀረበው ዝርዘር መሰረት ለመግዛት በመፈለጉ እና በዚህ ውል ሻጭ ተብሎ የተጠቀሰው ድርጅት ይህንኑ ደረጃውን
የጠበቀ ኬዚንግ ለመሸጥ ያቀረበው ዋጋ በገዥ ተቀባይነት በማግኘቱና ገዥም የቀረበውን ዋጋ ከፍሎ በራሱ
ትራንስፖርት ለማጓጓዝና ሳይቱ ላይ ለማድረስ በመስማማቱ ከዚህ ቀጥሎ በተመለከተው አኳኋን የውል ስምምነት
ተፈጽሟል፡፡

አንቀጽ ሁለት
የፒቪሲ ኬዚንግ ቱቦ መስፈረትና ጥራት
2.1 ሻጭ የሚሸጠው ፒቪሲ ኬዚንግ ቱቦ ገዥ ባቀረበው ዝርዝር መመሪያ መሰረት የጥራት ደረጃ DIN Standard
4925 የሚያሟላ መሆን አለበት፡፡

አንቀጽ ሶስት
የብረት ዝርዝርና፤ ዋጋና የክፍያ የሁኔታ
3.1 ገዥ ከዚህ በታች በተዘረዘረው መስረት ይገዛል ሻጭም ይሸጣል፡፡
ተራ የብረት አይነት መለኪያ ብዛት የአንዱ ዋጋ ጠቅላላ ዋጋ
ቁጥር (መጠን) ከቫት በፊት ከቫት በፊት
1 PVC Casing Shoulder type, 5” Blind 5m, ቁጥር 200 1,981.00 396,200.00
6.5mm wall thickness
2 PVC Casing Shoulder type, 5” Screen 5m, ቁጥር 100 2,111.00 211,100.00
6.5mm wall thickness
ድምር 607,300.00
ተጨማሪ እሴት ታክስ 91,095.00
ጠቅላላ ድምር 698,395.00

3.2 ገዥ ከዚህ በላይ በአንቀጽ 3. ተራ ቁጥር 3.1 በተዘረዘረው መሰረት የሚገዙትን ቱቦዎች የዋጋውን 50% ብር
346,697.50 ( ሶስት መቶ አርባ ስድስት ሺህ ስድስት መቶ ዘጠና ሰባት ብር ከ 50 ሳንቲም) ቫትን ጨምሮ
ለሻጭ በቅድሚያ ክፍያ በመክፈል ምርቱን ያስመርታል፡፡ ምርቱንም አጠናቆ በተረከበ በ 5 ቀናት ውስጥ ቀሪውን
50% ይከፍላል ሻጭም ደረሰኝ ያቀርባል፡፡
3.3 ገዥ ከዚህ በላይ በአንቀጽ 3. ተራ ቁጥር 3.2 በቀረበው መሰረት ቀሪውን 50% ብር 346,697.50 (ሶስት መቶ
አርባ ስድስት ሺህ ስድስት መቶ ዘጠና ሰባት ብር ከ 50 ሳንቲም) ቫትን ጨምሮ ምርቱን በተረከበ በ 5 ቀናት
ውስጥ ለሻጭ ባይከፍል ለዘገየበት ለእያንዳንዱ ቀን በባንክ ወለድ መሰረት ቅጣት ለመክፈል ተስማምቷል፡፡
3.4 ሻጭ ቱቦዎቹን ገዥ ባዘጋጀው የማጓጓዣ መኪና ለመጫን ተስማምቷል ፡፡

አንቀፅ አራት
ስለ ርክክብ

4.1 ሻጭ የሚያቀርበውን ፒቪሲ ኬዚንግ ቱቦ በውሉ ላይ በተቀመጠው የጥራት ደረጃ መሰረት ለገዥ ይህ ውል
በተፈረመና ክፍያ በተፈጸመ በ 7 የስራ ቀናት ውስጥ ያስረክባል፡፡ የቱቦ ማጓጓዣ በገዢ የሚሸፈን ይሆናል፡፡
ሆኖም ሻጭ በዚህ አግባብ ክፍያ በተፈጸመለት በ 7 ቀናት ውስጥ ቱቦዎችን ማቅረብ ካልቻለ ባልተፈፀመው
መጠን በየቀኑ 0.1 በመቶ ቅጣት ለመክፈል ተስማምቷል፡፡
4.2 ገዥ በራሱ በኩል የቀረበው ቱቦ በዚህ ውል በአንቀጽ 2 በተራ ቁጥር 1 መሰረት ስለመሆኑ በአከል በሻጭ
መጋዘን በመገኘት የማረጋገጥ መብት አለው በረክክብም ወቅት ይህንኑ ያደርጋል፤

4.3 የቱቦ ርክከቡ የሚፈጸመው በሻጭ መጋዘን ሆኖ የገዢ ተወካዮች በሚገኙበት ይሆናል፡፡ የገዥ ተረካቢም
የሚያጓጉዝበትን ትራንስፖርት ያቀርባል፡፡

አንቀፅ አምስት
ከአቅም በላይ ሰለሆኑ ሁኔታዎች
5.1 በፍትሐ ብሄር ሕግ ቁጥር 1792 እንደ ተደነገገው ከአቅም በላይ በሆኑ ምክንያቶች ውሉን ለመፈፀም
ካልተቻለ በውሉ አለመፈፀም ምክንያት ለሚደርስ ጉዳት ሁለቱም ተዋዋይ ወገኖች ተጠያቂ አይሆኑም፡፡ ይሁን
እንጂ ከአቅም በላይ የሆነ ምክንያት ሳይኖር እንደውሉ ባለመፈጸሙ ለሚደርስ ጉዳት ግራ ቀኝ ተዋዋዮች ሃላፊነት
አለባቸው፡፡
5.2 ይህ ሥምምነት እንደ ውሉ ለመፈፀም የማያስችል ከአቅም በላይ የሆነ ሁኔታ አለ የሚባለው በፍትሐ ብሄር
ህግ 1793 ላይ ከተጠቀሱት ሁኔታዎች አንዱ ሲረጋገጥ ነው፡፡

አንቀፅ ስድስት
ከአቅም በላይ ሰለሆኑ ሁኔታዎች
6.1 በማንኛውም ሁኔታ በዚህ ውል ተፈፃሚነት ላይ አለመግባባት ቢፈጠር፣ ሁለቱ ተዋዋይ ወገኖች ተገናኝተው
ችግሩ በሰላማዊ መንገድ እንዲፈታ አስፈላጊውን ጥረት ያደርጋሉ፣
6.2 በሁለቱ ተዋዋይ ወገኖች ውይይት አለመግባባቱ በሰላማዊ መንገድ ሊፈታ ካልቻለ በጉዳዩ ላይ አግባብ ያለው
ፍ/ቤት የሚሰጠው ውሳኔ ተፈፃሚ ይሆናል፡፡

አንቀፅ ሰባት
ውሉ የሚቋረጥበት ሁኔታ
7.1 ሁቱለም ወገኖች በስምምነት ውሉን ሊያቋርጡ ይችላሉ፣
7.2 ውሉን ማቋረጥ የፈለገ ወገን ከ 5 ቀን በፊት ማሳወቅ ይኖርበታል፡፡ ይህ ካልሆነ እንደጸና ተደገርጎ ይወሰዳል፡፡
7.3 ይህ ውል ሁለታችንም ተዋዋዮች አንብበን የውሉ ቃል የሁለታችንንም ፈቃድና ፍላጎት ያሟላ መሆኑን እንደ
ውሉ ለመፈፀም እማኞች በተገኙበት ዛሬ የካቲት ቀን 2013 ዓ.ም. ተፈራርመናል፡፡

አንቀጽ ስምንት

8.1 በዚህ ውል ውስጥ ገዥ እና ሻጭ እየተባልን የምንጠራው ባደረግነው የውል ድርድር ከጋራ ስምምነት ደርሰን ፣
በፍታብሄር ህግ ቁጥር 1675፣1719፣1731 እና 2266 መሰረት ይህን ውል እንደ ህግ አድርገን ተቀብለነዋል፡፡
ገዥ ሻጭ
ስም ፊርማ ስም ፊርማ

----------------------------------

------------------------------------

እማኞች

ስም ፊርማ

1.

2.

3.

You might also like