Download as docx, pdf, or txt
Download as docx, pdf, or txt
You are on page 1of 34

የእግዚአብሔር መንግስት መምጫው መቼ ነው?

ከ 2031 G.C እስከ 2033 G.C ምን ይከሰታል ?


ከዚህ በኋላ በምድራዊ መንግስት ሰላም እና መረጋጋት
ሊመጣ ይችላል ?

በፋንታሁን አናጋው

መስከረም 2016

ጥያቄ ወይም አስተያየት ቢኖርዎ፡-

+251913771034

fantahun04@gmail.com

I
ማውጫ

መግቢያ -----------------------------------------------------------------------------------------------------III

ፍጻሜ ዘመንን የመመርመር አስፈላጊነት --------------------------------------------------------------1

የመጨረሻዎቹ ሰባት (7) ዓመታት ---------------------------------------------------------------------2

ከመጨረሻዎቹ ሰባት (7) ዓመታት በኋላ --------------------------------------------------------------4

ጌታ ኢየሱስ እንደ ግ.አ. ከ 2031-2033 ዓ.ም. ከቅዱሳኑ ጋር ዳግም ይመጣል -------------------5

ሌሎች ነብያትስ ምን ይላሉ ------------------------------------------------------------------------------8

የበለሷ ምሳሌ -----------------------------------------------------------------------------------------------8

እግዚአብሔር በምድር ላይ ለሰው ልጅ የያዘው የ 7000 ዓመታት አጀንዳ -------------------------10

ከአዳም እስከ ክርስቶስ እርገት --------------------------------------------------------------------------12

የሄኖክስ ትንቢት ምን ይላል ----------------------------------------------------------------------------20

ስለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤ/ክ እግዚአብሔር ይባረክ --------------------------------------20

በምሳሌ የተነገሩ ሌሎች ትንቢቶች ---------------------------------------------------------------------28

የኢዮቤልዩ ምሳሌ -----------------------------------------------------------------------------------------30

እና ምን እናድርግ? ---------------------------------------------------------------------------------------34

II
መግቢያ
ይህ ጽሑፍ (Article) የየትኛውንም ሐይማኖት ተቋም አስተምሕሮ የሚከተል፣ የሚቃወም፣ ወይም
የሚደግፍ (የሚያንጸባርቅ) አይደለም፡፡ የማንኛውም ሐይማኖት ተቋም እምነት ተከታይ የሆነ ግለሰብ ሁሉ
ይህ ጽሑፍ ይመለከተዋል፡፡ ማለትም ሰይጣን የሚዘውረው የዚህ ዓለም (የባቢሎን) ስርዓት የታከተው ሁሉ
ይህን ጽሑፍ ሊያነብ ግድ ይለዋል፤ እውነተኛ መንፈሳዊና ስጋዊ ነጻነትን እና ፍትሕን ለሚናፍቅ ሁሉ ይህች
አጭር ጽሑፍ ተስፋ አለ ትለዋለች፡፡ ክርስትና ሐይማኖት አይደለም፡፡ ክርስትና የመንግስት ጉዳይ ነው፡፡
ክርስትና የሰማይ ፖለቲካ (Heavenly Politics) ነው፡፡ ጌታ ኢየሱስ በማቴ. 6፡33 እንዳስተማረን “33 በመጀመሪያ
የእግዚአብሔርን ጽድቅና መንግስት ፈልጉ ሌላው እንዲሁ ይጨመርላችኋል” ነው ያለን፡፡ በሌላም ቦታ በማቴ. 24፡14 “14
ለአሕዛብም ሁሉ ምስክር እንዲሆን ይህ የመንግስት ወንጌል በዓለም ሁሉ ይሰበካል፤ በዚያም ጊዜ መጨረሻው ይመጣል፡፡” ይለናል፡፡
ሌሎች ብዙ ጥቅሶችን ከመጽሐፉ በመጥቀስ ጌታ ኢየሱስ ዳግመኛ በታላቅ ክብር በአካል (በስጋ) የሚመጣበት
ዋንኛ ምክኒያት ሰይጣን የሚዘውራትን የዚህችን ክፉ አለም (ባቢሎን) ስርዐት በመደምሰስ በዙፋኑ ሆኖ
የሰማይን መንግስት በምድር ላይ ለ 1000 ዓመታት ገልጦ ከገዛ በኋላ መንግስታትንና ስልጣናትን ሁሉ ሁሉን
ላስገዛለት ለእርሱ ለእግዚአብሔር አብ በማስረከብ በመጨረሻም እርሱ ራሱ ሁሉን ላስገዛለት ለእርሱ ለአብ
ሊገዛ ዘንድ እንደሆነ ማሳየት ይቻላል፡፡ ስለዚህ ወደጄ፣ ጌታ ኢየሱስ ዳግመኛ የሚመጣው የፕሮቴስታንትን
(የጴንጤን)፣ የኦርቶዶክስን፣ የአይሁድን፣ የሙስሊምን፣ የቡዲዝምን፣ ወዘተ… ሐይማኖት ስርዐት
ለመመስረት አይደለም፡፡ በመሆኑም የማንኛውም ሐይማኖት እምነት ተከታይ የሆነ ሰው ሁሉ ይህ ጽሑፍ
(Article) ይመለከተዋል፡፡

III
ፍጻሜ ዘመንን የመመርመር አስፈላጊነት
ውድ አንባቢ ይህን ያልተለመደ ፅሁፍ ርዕሱን በሚያዩበት ቅፅበት ወደ አዕምሮዎ የሚመጣው ሃሳብ ማቴ. 24፡36
“ስለዛች ቀንና ስለዛች ሰዓት ግን ከአባት ብቻ በቀር የሰማይ መላዕክትም ቢሆኑ ልጅም ቢሆን የሚያውቅ የለም” የሚለው ቃል
እንደሚሆን መገመት እችላለሁ፡፡ ይሁንና ውድ አንባቢዬ ርዕሱን አይተው ይህን ፅሁፍ ለማንበብ ከመቆጠብዎ
በፊት በመጀመሪያ እንዲያስተውሉልኝ የምፈልገው ነገር ቢኖር በግሪጎሪያን አቆጣጠር ከ 2031 እስከ 2033
ዓ.ም ይመጣል በማለት ሊመጣ የሚችልበትን ዓመታት ማመልከቴን እንጂ ምንም አይነት ቀንና ሰዓት
አለማመልከቴን ነው፡፡ ሌላው እነዲያስተውሉልኝ የምፈልገው ነገር ጌታ ቀንና ሰዓቱ አይታወቅም አለ እንጂ
ዘመናቱ ወይም ዓመታቱ አይታወቁም አለማለቱን ነው፡፡ እንዳውም ዘመናቱን ወይም ዓመታቱን
እንድናስተውል በርከት ያሉ ምልክቶችን ጠቁሞናል፡፡ አኒህም ምልክቶች ጌታ ካረገበት ጊዜ ጀምሮ እየተፈጸሙ
እንደሚገኙ እናስተውላለን፡፡ ይሁንና አብዛኛው ኢትዮጵያዊ ክርስቲያኖች በማቴ. 24፡36 (ቀንና ሰዓቱ
አይታወቅም) ተብሎ የተጻፈውን እና ጌታ የሰጠንን ካረገበት ጀምሮ እየተፈፀሙ ያሉትን ምልክቶች በማሰብ
እየተዘናጉ ይገኛሉ፡፡

ውድ አንባቢዬ ጌታ በዚህ ጊዜ ይመጣል ብዬ ይህን እብደት የሚመስል ፅሁፍ ለመጻፍ የተነሳሁት ከራሴ ሀሳብ
እና ከራሴ ራዕይ ወይም ቅዠት በመነሳት አይደለም ነገር ግን እያንዳንዱ ፅሁፌ ላይ የማቀርበው ማስረጃ
በሁለት በኩል የተሳለ ሰይፍ የሆነውን እና የማይዋሸውን የእግዚያብሔር ቃል በጥቅስ በማስደገፍ ስለሆነ
በጥሞና እና በትዕግስት እስከ መጨረሻው ገፅ ድረስ እንዲያነቡት እና አስተያየቶን በፅኁፌ መጀመሪያ ገጽ ላይ
ባስቀመጥኩት የኢሜል አድራሻ ላይ እንዲለግሱኝ ስል በእግዚአብሔር ፍቅር እጠይቆታለሁ፡፡

የእግዚያብሔር ቃል በዳን.12፡4 “ዳንኤል ሆይ አንተ ግን እስከፍጻሜ ዘመን ድረስ ቃሉን ዝጋ መጽሀፉንም አትም ብዙ ሰዎች
ይመረምራሉ እውቀትም ይበዛል” እንደሚል በመጽሃፍ ቅዱስ ውስጥ በተለያየ ቦታ ላይ ጌታ ተመልሶ የሚመጣበትን
ዘመን ወይም አመት (ፍጻሜ ዘመን) የሚያመለክት ቃል ሁሉ ጊዜውን ጠብቆ እንዲገለጥ ለዘመናት ሚስጥር
ሆኖ እንዲቆይ በመንፈስ ቅዱስ ሃይል ታትሞ ወይም ተዘግቶ እንደቆየ እናስተውላለን፡፡ ይሁንና በአሁኑ ዘመን
በምድራችን በተለይም በምዕራቡ አለም ታላላቅ የእግዚያብሄር ቃል ሙላት ያላቸው አገልጋዮች (Bible
Scholars) ተመራምረው እና በመንፈስ ቅዱስ ሀይል ተመርተው የተዘጋውን የዳንኤል መጽሃፍ እና ሌሎች
ፍጻሜ ዘመንን የሚያመለክቱ መጻህፍቶችን አውቀው ማሳወቅ ችለዋል፡፡ በመሆኑም ውድ አንባቢዬ ቀንና
ሰዐቱ አይታወቅም ብለው ሳይዘናጉ ይህን ፅኁፍ በትዕግስት እንዲያነቡት በጌታ ፍቅር እማጸኖታለሁ፡፡

ምናልባትም ጌታን ካወቅኩት እና እንደፈቃዱ መኖር ከቻልኩ በቂዬ ስለሆነ የሚመጣበትን ጊዜ ማወቅ
አይጠበቅብኝም ብለው ያስቡ ይሆናል፡፡ መጽሐፉ በ 1 ተሰ 5፡4 “እናንተ ግን ወንድሞች ሆይ ቀኑ እንደሌባ ይደርስባችሁ
ዘንድ በጨለማ አይደላችሁም” እንደሚል በጨለማ አለመሆናችንን የምናውቀው በመገለጥም ይሁን የትንቢት
ቃልን በማጥናትና በመመርመር አሁን ያለንበትን ዘመን መረዳት ስንችል ነው፡፡ አለበለዚያ ቀኑ እንደ ሌባ
ይደርስብናል ማለት ነው፡፡ በሉቃ.12፡36 “እናንተም ጌታቸው መጥቶ ደጁን ሲያንኳኳ ወዲያው እንዲከፍቱለት ከሰርግ
እስኪመለስ ድረስ የሚጠብቁ ሰዎችን ምሰሉ” እንደሚል ዳግመኛ መገለጡን በናፍቆት እንድንጠባበቅ ያዘናል፡፡ ልክ
በመጀመሪያ በመጣ ጊዜ የመሲሑን መገለጥ በናፍቆት ለሚጠባበቁ ብቻ ራሱን እንደገለጠ ዳግምኛም ሲመጣ
በናፍቆት ለሚጠባበቁት ብቻ ራሱን እንደሚገልጥ መጽሐፉ ብዙ ቦታ ላይ ያስረዳናል፡፡ ለዚህም ማሳያ በዮሐ. 4
“መሲሑ ሲመጣ ሁሉን ይነግረናል” ብላ በናፍቆት ትጠባበቅ የነበረችውን ሳምራዊቷን ሴት ለማግኘት መንፈስ
ጌታን መሄድ በማይገባው መንገድ እንዲሄድ እንዴት እንዳስገደደውና መሲሑ መሆኑን ከሌሎች እየደበቀ ለርሷ
ግን መሲሑ እርሱ ራሱ መሆኑን ሲገልጥላት እንመለከታለን፡፡ እንዲሁም በዕብ. 9፡28 “28 እንዲሁ ክርስቶስ ደግሞ
የብዙዎችን ሀኃጢአት ሊሸከም አንድ ጊዜ ከተሰዋ በኋላ፣ ያድናቸው ዘንድ በናፍቆት ለሚጠባበቁት ሁለተኛ ጊዜ ያለኃጢአት
ይታይላቸዋል፡፡” በማለት ቃሉ የጌታን ዳግም መምጣት በናፍቆት መጠባበቅ እንዳለብን ያዘናል፡፡ በአንድ ቦታ ላይ

1
ደግሞ ፈሪሳዊያንና ሰዱቃዊያን ከሰማይ ምልክት እንዲያሳያቸው ጌታን በጠየቁት ጊዜ፡- በማቴ. 16፡2-3 “2 እርሱ
ግን መልሶ እንዲህ አላቸው “በመሸ ጊዜ ሰማዩ ቀልቷልና ብራ ይሆናል ትላላችሁ፤ 3 ማለዳም ሰማዩ ደምኖ ቀልቷልና ዛሬ ይዘንባል
ብሎ ሲወቅሳቸው እንመለከታለን፡፡
ትላላችሁ፡፡ የሰማዩን ፊትማ መለየት ትችላላችሁ የዘመኑንስ ምልክት አትችሉምን?“
ስለዚህ ዘመናትን እንድናስተውል ከኛ ይጠበቃል ማለት ነው፡፡ በአሁኑ ሰዐት ብዙዎች ክርስቶስ በምድር ላይ
ስላስገኘላቸው እና ስለሚያስገኝላቸው ብልጽግና እና ስኬት ላይ ብቻ በማተኮራቸው ፈጽሞ ስለ ዳግም
መምጫው ጊዜ ማሰብም፣ መስማትም፣ መናገርም አይፈልጉም፡፡ እንደውም ብዙ አገልጋዮች የጌታን መምጫ
ጊዜ ማሰብ፣ መስማት፣ እና መናገር እንደሚያስፈራቸው በግልጽ ሲናገሩ ሰምቻለው፡፡ ውድ አንባቢዬ ምናልባት
እርሶ በዚህም ምክንያት ሆነ በሌላ ጌታ ይዘገያል ብለው የሚያስቡ ከሆነ ወይም ደግሞ በጽሁፌ ርዕስ ላይ
ያመለከትኩትን የዳግም መምጫውን ዓመታት ፈፅሞ የማያውቁ ወይም የማያምኑ ከሆነ ይህን ጽሁፍ
እንዲያነቡ በጌታ ፍቅር እጋብዞታለሁ፡፡

ፍጻሜ ዘመንን የማወቅ አስፈላጊነት ምክንያቶች ብዙ ነገሮችን ከቃሉ መዘርዘር እንችላለን፡፡ ይሁንና ፍጻሜ
ዘመንን የማወቅ አስፈላጊነት ላይ ጊዜዎትን እንዳላባክን ወደዋናው ሃሳቤ መሄድን መርጫለሁ፡፡

የመጨረሻዎቹ ሰባት (7) ዓመታት


እንግዲህ ወደ ዋናው አጀንዳ ከመሄዴ በፊት አንባቢዎች የጽሑፉ ሙሉ መረዳት እንዲኖራቸው የመጨረሻዎቹ
ሰባት (7) ዓመታት ምን ይመስላሉ የሚለውን ጠቅለል ባለ መልኩ ላቀርበው ሞክሪያለሁ፡፡ እነዚህ ዓመታት
ምንድናቸው ስንል በየኋንስ ራእይ መጽሐፍ በራእ. 13 ከባሕር የወጣው አውሬ የአለምን ሕዝቦች ሁሉ በቀኝ
እጃቸው ወይም በግንባራቸው በማታለልና በማስገደድ የራሱን ምልክት እንዲወስዱ በማድረግ ዓለምን
የሚገዛበት ዓመታት ናቸው፡፡ እነዚህ ዓመታት ከእስራኤል ሕዝብና ከተቀደሰችው ከተማ (ኢየሩሳሌም) ጋር
ያላቸውን ግንኙነት ማወቅ ግድ ስለሆነ ትንቢተ-ዳንኤል ምዕራፍ 9 ን መቃኘት ይጠበቅብናል፡፡

ዳን.9፡24-26 “2 ዐመፃን ለማስቆም፤ ኃጢአትን ለማስወገድ፤ በደልን ለማስተሰረይ፤ ዘላለማዊ ጽድቅን ለማምጣት፤ ራእይንና
ትንቢትን ለማተምና፤ እጅግ ቅዱስ የሆነውን ለመቀባት ስለ ሕዝብህና ስለተቀደሰችው ከተማህ ሰባ ሱባዔ ታውጇል፡፡ 25 ይህንን
ዕወቅ አስተውለውም፤ ኢየሩሳሌምን ለማደስና ለመጠገን ዐዋጁ ከወጣበት ጊዜ ድረስ፣ ገዥው መሲሕ እስከሚመጣበት ጊዜ ድረስ፣
ሰባት ሱባዔና ሥልሳ ሁለት ሱባዔ ይሆናል፡፡… 26 ከሥልሳ ሁለቱ ሱባዔ በኋላ መሲሑ ይገደላል፡ ምንም አይቀረውም፡፡ የሚመጣው
አለቃ ሰዎችም፤ ኢየሩሳሌምንና ቤተ-መቅደሱን ይደመስሳል፡፡ ፍጻሜውም እንደጎርፍ ይመጣል፤ ጦርነት እስከመጨረሻው ይቀጥላል
ጥፋትም ታውጇል፡፡”

ነብዩ ዳንኤል ይህን ራእይ የተቀበለው የእስራኤል ሕዝብ በባቢሎን በግዞት በነበሩበት ጊዜ ነው፡፡ ሰባው ሱባዔም
መቁጠር የጀመረው በወቅቱ የተነሳው የባቢሎን ንጉስ ኢየሩሳሌምን እንዲያድሱና እንዲጠግኑ አዋጅ ካወጣበት
ጊዜ ጀምሮ ነው፡፡ ከዛን ጊዜ በኋላ ሁለተኛውን ቤተ-መቅደስ ለመገንባት አርባ ስድስት (46) ዓመታት
እንደፈጀባቸው ከመጽሐፉ እንረዳለን፡፡ ታረክም እንደሚያስረዳው የኢየሩሳሌም ዋና አጀንዳ መቅደሱ ስለሆነ፣
በመጀመሪያዎቹ ሰባት ሱባዔዎች (49 ዓመታት) ውስጥ ኢየሩሳሌምን እንደጠገኑና እንዳደሱ እንገነዘባለን፡፡
በመሆኑም ኢየሩሳሌም ከታደሰችበት ጊዜ ጀምሮ ልክ በስልሳ ሁለት ሱባዔው (434 ዓመታት) መሲሑ መጣ
(ተገለጠ)፡፡ ከታሪክና ከዳንኤል መጽሐፍ ሰዋሰዋዊ አገባብ (Gramatical Context) በመነሳት በዳንኤል
መጽሐፍ አንድ ሱባዔ ሰባት (7) ዓመታት መሆናቸውን እንረዳለን፡፡ ስለዚህ በአጠቃላይ ከዐዋጁ ጀምሮ በስልሳ
ዘጠነኛው ሱባዔ (በ 483 ዓመታት) መጨረሻ ላይ መሲሑ መጥቶ (ተገልጦ) ከዛ በኋላ ተገደለ፡፡
እስራኤላውያንም መሲሑን ባለመቀበላቸው የእግዚአብሔር መንፈስ እስከአሁንም ድረስ ስለተዋቸው
የሚመጣውም አለቃ (በራእ.13 ከባሕር የሚወጣው አውሬ) ሰዎች ማለትም የሮም ወታደሮች ቤተ-መቅደሱን
ደመመሰሱ፤ እስራኤላውያንም ወደ አሕዛብ ሁሉ ተሰደዱ፡፡ ታዲያ ይህ ሁሉ የሆነው ዐዋጁ ከወጣበት ጊዜ
ጀምሮ ከስልሳ ዘጠኝ ሱባዔ በኋላ ከሆነ 70 ኛዋ ሱባዔ (የመጨረሻዋ 7 ዓመታት) ወዴት ሄደች?

2
እንደሚል፣ ይህ
ዮሐ 5፡43 “43 እኔ በአባቴ ስም መጥቼ አልተቀበላችሁኝም፤ ሌላው በራሱ ስም ቢመጣ ግን ትቀበሉታላችሁ”
ቃል ይፈጸም ዘንድ እውነተኛውን መሲሕ ሳይቀበሉ እስከአሁን ድረስ በአሕዛብ መካከል ተበትነው ያሉት
እስራኤላውያንና አሁን በኢየሩሳሌም የሚኖሩት እስራኤላዊ ተብዬ አይሁዶች እውነተኛውን መሲሕ
ባለመቀበላቸው በሐሰተኛው መሲሕ ይፈተኑ ዘንድ የመጨረሻዋ ሱባዔ (የመጨረሻዋ 7 ዓመታት)
ቀርታላቸዋለች፡፡

ዳን.9፡27 “27 አለቃው ከብዙዎች ጋር ለአንድ ሱባዔ ቃል ኪዳኑን ያጸናል፤ በሱባዔውም እኩሌታ መስዋዕትና ቁርባን ማቅረብን
ያስቀራል፡፡ የታወጀው ፍርድ በእርሱ ላይ እስኪፈስ ድረስ፤ ጥፋትን የሚያመጣ የጥፋት ርኩሰት በቤተ-መቅደሱ ውስጥ ያቆማል፡፡”

እንግዲህ ከላይ በዳን.9፡27 እንዳየነው 70 ኛዋ ሱባዔ (የመጨረሻዋ 7 ዓመታት) አለቃው (አውሬው) ከብዙ
ሀገራት ጋር ለሰባት ዓመታት ኪዳኑን አጽንቶ አለምን ሚገዛባትና በእኩሌታዋም (ከ 3.5 ዓመታት በኋላ)
የእምነት ተቋማትን ሁሉ አዘግቶ ምስሉን አሁን በቅርብ ጊዜ በኢየሩሳሌም በሚገነባው በ 3 ኛው ቤተ-መቅደስ
እና በሌሎች የእምነት ተቋማት በተቀደሰ ስፋራ ሁሉ በማቆም ለምስሉ ስገዱ እያለ የአለምን ሕዝብ ሁሉ
የሚያስጨንቅባት እና የማይሰግዱትን በሰይፍ የሚገድልባት ጊዜ ናት ማለት ነው፡፡ ታዲያ ከእኩሌታዋ ጀምሮ
እስከምን ያህል ጊዜ ነው የአለም ሕዝቦችን የሚያሰቃየው?

ራእ.13፡5 “5 አውሬው የትዕቢት ቃል የሚናገርበትና የሚሳደብበት አፍ ተሰጠው፤ አርባ ሁለት ወር በስልጣን እንዲሠራም
ተፈቀደለት፡፡”

ስለዚህ አውሬው በምድር ላይ የሚኖሩ ሕዝቦችን ሁሉ ስገዱልኝ እያለ የሚያሰቃይበት በዛን ጊዜ በምድር ላይ
የሚኖሩ ሕዝቦች የሚፈተኑበት ከዚህ በፊት በአለም ታይቶ የማይታውቅ የታላቁ መከራ ጊዜ (Time of the
Great Tribulation) አርባ ሁለት ወራት (3.5 ዓመታት) ይሆናል ማለት ነው፡፡ ማለትም አውሬው ከብዙ
ሀገራት ጋር የ 7 ዓመታት ኪዳን ከፈጸመበት ጊዜ ውስጥ የ 7 ዓመታቱ የሁለተኛው እኩሌታ (The 2nd half of
the 7 Years) በምድር ላይ ለሚኖሩ ሕዝቦች ሁሉ (በተለይም በእስራኤል ለሚኖሩ ሕዝቦች) የታላቁ መከራ
ዘመን ይሆናል ማለት ነው፡፡ ከዚህ በኋላ (ከመጨረሻዎቹ የ 3.5 ዓመታት የታላቁ መከራ ጊዜ በኋላ) ጌታ ኢየሱስ
በታላቅ ክብር ከቅዱሳኑ ጋር በሰማይ ይገለጣል፡፡

ከመጨረሻዎቹ ሰባት (7) ዓመታት በኋላ


በመቀጠል በራእ. 20፡1-6 እንደተጻፈው ዘንዶው (ሰይጣን) ታስሮ ለ 1000 ዓመታት ወደ ጥልቁ ይጣላል
እንደዚሁም በታላቁ መከራ ጊዜ የአውሬውን ምልክት ባለመቀበላቸውና ለአውሬው ባለመስገዳቸው
የተገደሉት ሁሉ ከሙታን ይነሱና ለ 1000 ዓመታት (The Brand New Mellennium) ከጌታ ጋር ይነግሳሉ፡፡

ከአንድ ሺው ዓመታት በኋላ በራእ. 20፡7-15 እንደተጻፈው ሰይጣን ለጥቂት ጊዜ ይለቀቅና የዓለምን መንግስታት
በማሳት የቅዱሳንን ከተማ እንዲወሩ ያደርጋል እሳትም ከሰማይ ወርዶ ይበላቸዋል፤ ሰይጣንም ለአንዴና
ለመጨረሻ ጊዜ ወደተዘጋጀለት የእሳት ባሕር የጣላል፡፡ ከዚህ በኋላ ታላቁ ነጭ ዙፋን ይዘረጋል፤ አሮጌው
ሰማይና አሮጌዋ ምድር ያልፋሉ፤ ሙታን ሁሉ ይነሱና ለፍርድ ይቀርባሉ፤ በሕይወት መዝገብ ላይ ስማቸው
ያልተገኘ ሁሉ ለሰይጣንና ለመላእክቱ በተዘጋጀው የእሳት ባሕር ውስጥ ይጣላሉ፡፡ በመጨረሻም በራእ. 21
እንደተጻፈው አዲስ ሰማይና አዲስ ምድር ይገለጣሉ፤ ድል የሚነሳ ሁሉ ይህን ይወርሳል፤ ለዘላለም ሞትን
አያይም (ዘላለማዊነት ውስጥ ይገባል)፤ ነገር ግን ፈሪዎች፣ የማያምኑ፣ እርኩሳንም፣ ነፍሰ-ገዳዮችም፣
ሴሰኛዎችም፣ አስማተኞችም፣ ጣኦትንም የሚያመልኩ፣ ሐሰተኛዎችም፣ እንዲሁም የአውሬውን ምልክት
የወሰዱ ሁሉ እጣ ፈንታቸው ወደ እሳቱ ባሕር መጣል ነው፡፡ በበጉ የሕይወት መዝገብ ላይ ስማቸው ተጽፎ
የተገኘ ሁሉ ግን ከሰማይ የምትወርደዋን አዲሲቷን ኢየሩሳሌም ይወርሳሉ፡፡

3
ታዲያ ይህ ሁሉ መቼ ይሆናል? መልሱን ከዚህ በኋላ የሚቀጥሉትን የጽኁፉን ክፍሎች ሙሉውን በማንበብ
ያገኙታል፡፡ መልካም ንባብ!

ጌታ ኢየሱስ እንደ ግሪጎሪያን አቆጣጠር ከ 2031 እስከ 2033 ዓ.ም. ከቅዱሳኑ ጋር


ዳግም ይመጣል
ውድ አንባቢ ጌታ ከላይ በተጠቀሰው ጌዜ እንደሚመጣ አስረግጦ የሚያስረዳውን ዋነኛ ጥቅስ ከማመልከቴ
በፊት የግሪጎሪያን ካሌንደር መነሻው የክርስቶስ ልደት ቀን መሆኑን ታሪክ እንደሚያስረዳ ከወዲሁ መግለጽ
እፈልጋለሁ፡፡ ይሁንና አንዳንድ የታሪክ ጠበብቶች አሁን የምንጠቀምበት የግሪጎሪያን ካሌንደር ከክርስቶስ ልደት
በኋላ ሁለት ዓመት ዘግይቶ ነው የጀመረው ሲሉ ሌሎች ደግሞ አራት ዓመት ዘግይቶ ነው የጀመረው ብለው
ይሞግታሉ፡፡ ስለዚህ ከላይ ያስቀመጥኩት ከ 2031-2033 ዓ.ም ይህን ውዝግብ ታሳቢ ያደረገ መሆኑን ከወዲሁ
እንዲረዱልኝ አሳስባለሁ፡፡ ማለትም አሁን ዓለም የሚጠቀምበት ካሌንደር ትክክል ከሆነ ጌታ በ 2033 ይመጣል
ነገር ግን እነደመጀመሪያው ሞጋች ይህ ካሌንደር ሁለት ዓመት ዘግይቶ ከሆነ የጀመረዉ ጌታ በ 2031 ይመጣል
ወይም ደግሞ እንደሁለተኛው ሞጋች አራት ዓመት ከሆነ የዘገየው በ 2029 ይሆናል ነገር ግን ዛሬ ኦክቶበር
2023 ላይ ሆነን እስከ 2029 ብንቆጥር ስድስት ዓመታት ብቻ ናቸው ያሉት ይሁን እንጂ የሚመጣው አለቃ
(አውሬው) እስከ አሁን በሚስጥር እንጂ በግልፅ አልተገለጠም፤ ለመጨረሻው ሰባት (7) ዓመታት ሲቀሩ
ይገለጣል ማለታችንን ያስታውሱ፡፡ በመሆኑም አቆጣጠሩ አራት ዓመት ከሆነ የዘገየው በ 2030 ይመጣል ብለን
ማሰብ እንችል ነበር፤ ነገር ግን ጌታ ከ 2031 ዓ.ም. በፊት እንደማይመጣ አስረግጦ የሚናገር በእግዚአብሔር
ቃል የተነገረ ትንቢት ስላለ ነው ከ 2031-2033 ዓ.ም ያልኩት፡፡ ከግሪጎርያን አቆጣጠር አንጻር ጌታ
የተወለደበትን ትክክለኛ ዕለት ማንም ማወቅ እንዳልተፈቀደለት ወይም አውቃለሁ የሚል የታሪክ ጠበብት ካለ
እየዋሸ መሆኑን ከማቴ. 24፡36 መረዳት እንችላለን፡፡ ምክንያቱም ጌታ የተወለደበት ትክክለኛው ዕለት ቢታወቅ
ኖሮ ጌታ ዳግመኛ የሚመጣበትን ዕለት (ቀን) ማወቅ (መገመት) ይቻል ነበር፤ ይሁንና ይህን እለት (ቀን) ከአብ
በቀር ማንም እንዲያውቅ አልተፈቀደለትም፡፡ በመሆኑም አሁን ዓለም የሚጠቀምበት ግሪጎሪያን ካሌንደር
ትክክል ከሆነ ይህን ጽሁፍ እየጻፍኩ ባለሁበት በአሁኑ ጊዜ ማለትም በ 2023 ዓ.ም. ግ.አ. የጌታ ኢየሱስ እድሜ
በምድር አቆጣጠር 2023 ኛ ዓመቱ በዲሴምበር 25 ግ.አ. (ይህ ዕለት ተቀባይነት ባይኖረውም ዓመተምህረቱን
ግን ትክክል ሊሆን ይችላል ብለን መገመት እንችላለን) በፈረንጆቹ ገና በዐል እንደሚከበር ሁላችንም
የምናውቀው ነው፡፡

4
ይህን ያክል ስለግሪጎሪያን ካሌንደር ካወራሁ በቂ ነው ብዬ በማሰብ ጌታ በተጠቀሰው ጊዜ እንደሚመጣ
የሚያሳየውን ዋነኛ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች ቃል በመጠቆም እጀምርና በተከታታይ ክፍሎች ውስጥ ይህን
ቃል የሚደግፉ ሌሎች ጥቅሶችን በማቅረብ ሀሳቤን አብራራለሁ፡፡

ሆሴ. 5፡14-15 አ.መ.እ. “14 እኔ ለኤፍሬም እንደ አንበሳ ለይሁዳም እንደ ደቦል አንበሳ እሆናለውና፡ ሰባብሬና አድቅቄያቸው
እሄዳለው ነጥቄ እወስዳቸዋለሁ ማንም ሊያድናቸው አይችልም፡፡ 15 በደላቸውን እስኪያውቁ ድረስ ወደስፍራዬ እመለሳለሁ ፊቴን
ይሻሉ በመከራቸውም አጥብቀው ይፈልጉኛል”

ይህ ቃል እግዚአብሔር በመንፈሱ በኩል በእስራኤላውያን ላይ ስለሚያመጣባቸው መከራ ለነብዩ ሆሴዕ


የተናገረው ትንቢት እንደሆነ በግልጽ ማስተዋል እንችላለን፡፡ እንግዲህ ጠቅለል ባለ መልኩ ይህ ትንቢት
ስለየትኛው መከራቸው ወይም ስለየትኛው ጊዜ እንደሚያወራ ለማወቅ ሆሴ. 3፡4-5 ን ማየት በቂ ይመስለኛል
ምክንያቱም ይህ ጥቅስ እስራኤላውያን ለብዙ ዘመን ያለንጉስና ያለአለቃ ይኖሩና በመጨረሻም ዘመን
እግዚአብሔርን እና ንጉሳቸውን ዳዊትን እንደሚፈልጉ (እንደሚሹ) ያሳያል፡፡ ስለዚህ ይህ ትንቢት (ሆሴ. 5፡14-
15) እስራኤላውያን ያለንጉስ እና ያለ አለቃ በሚኖሩበት ጊዜ እና እግዚያብሔርን አጥብቀው በሚፈልጉበት
በመጨረሻው ዘመን የሚፈጸም መሆኑን ከዚህ ቃል መረዳት እንችላለን፡፡ በመሆኑም ሆሴ. 5፡14-15 ላይ
የተነገረባቸውን ትንቢት ስናይ የተፈጸመ እና ገና የሚፈጸም ትንቢት እንደሆነ ማየት እንችላለን፡፡ የትኛው
ተፈጸመ መቼስ ተፈጸመ ለሚለው፡-

ማቴ. 23፡37-39 “37 ኢየሩሳሌም ኢየሩሳሌም ሆይ ነብያትን የምትገድል ወደ እርሷ የተላኩትንም የምትወግር ዶሮ ጫጩቶችዋን
ከክንፎችዋ በታች እንደምትሰበስብ ልጆችሽን እሰበስብ ዘንድ ስንት ጊዜ ወደድሁ! አልወደዳችሁምም፡፡ 38 እነሆ ቤታችሁ የተፈታ
ሆኖ ይቀርላችኋል፡፡ 39 እላችኋለሁና በጌታ ስም የሚመጣ የተባረከ ነው እስክትሉ ድረስ ከእንግዲህ ወዲህ አታዩኝም፡፡” እንዲሁም
በማቴ. 24፡1 “1 ኢየሱስም ከመቅደስ ወጥቶ ሄደ…‘

ይህን ቃል ስንመለከት፡- በጌታ ስም የሚመጣ የተባረከ ነው እስክትሉ ድረስ ከእንግዲህ አታዩኝም ብሎ


ከቤተመቅደስ ወጥቶ ሄደ፡፡ ከዚያ ጊዜ ጀምሮ ወደ ቤተመቅደስ አልተመለሰም በቀናት ጊዜ ውስጥ ተሰቅሎ ሞተ
በሶስተኛው ቀን ከሞት ተነሳ እና ለተከታዮቹ ብቻ በተለያየ ጊዜ ታያቸው እና ለተቃዋሚዎቹ ላንዳቸውም
ሳይታይ አረገ፡፡

እርሱ ካረገ በኋላ በ 70 A.D እንደ ግ.አ. (ጌታ ከተወለደ ከ 70 ዓመታት በኋላ) የሮማ ወታደሮች መጥተው
ቤተመቅደሱን እንዳቃጠሉና እስራኤላውያን እንደተበተኑ ታሪክ ያስረዳናል፡፡ እንግዲህ እዚህጋ እግዚያብሔር
በስጋ ውስጥ (በክርስቶስ) ሆኖ እስራኤላውያንን ጎብኝቶ ስላላወቁት ሰባብሮና አድቅቋቸው ወደ ስፍራው
እንደተመለሰ እናስተውላለን፡፡ ስለዚህ ሆሴ. 5፡14-15 አ.መ.እ. “14 እኔ ለኤፍሬም እንደ አንበሳ ለይሁዳም እንደ ደቦል አንበሳ
እሆናለሁና፡ ሰባብሬና አድቅቄያቸው እሄዳለሁ ነጥቄ እወስዳቸዋለሁ ማንም ሊያድናቸው አይችልም፡፡ 15 በደላቸውን እስኪያውቁ
የሚለው ቃል እዚህጋ ማለትም “እነሆ ቤታችሁ የተፈታ ሆኖ ይቀርላችኋል” ብሎ ከአፉ
ድረስ ወደስፍራዬ እመለሳለሁ”
በወጣው ቃል በመንፈስ ከሰባበራቸውና ካደቀቃቸው በኋላ በማቴ.24፡1 ላይ ከመቅደሱ ከወጣ በኋላ ሞቶ ተነስቶ
በማረግ ወደስፍራው በተመለሰ ጊዜ መፈጸሙን እናስተውላለን፡፡ ስለዚህ ገና ያልተፈጸመው እና ወደፊት በ 3.5
ዓመታቱ (በአርባ ሁለት ወራቱ) በታለቁ መከራ የሚፈጸመው ትንቢት ሆሴ. 5፡15 “15 ፊቴን ይሻሉ በመከራቸውም
አጥብቀው ይፈልጉኛል” የሚለው መሆኑን እንረዳለን፡፡

እንግዲህ ጌታ በነብዩ ሆሴዕ በኩል በሆሴ. 5፡14-15 አ.መ.እ. የተናገረው ትንቢት ማለትም ሰባብሬና አድቅቄያቸው
በደላቸውን እስኪያውቁ ድረስ ወደስፍራዬ እመለሳለሁ ብሎ የተናገረው ቃል በማቴ. 23፡37-39 እና በማቴ. 24፡1
ላይ ከዛሬ 2023 ዓመታት በፊት (2023 ዓ.ም. ግ.አ ላይ ሆነን ስናስበው) በስጋ ተወልዶ ከ 33 ዓመታት በኋላ
እነሆ ቤታችሁ የተፈታ ሆኖ ይቀርላችኋል ብሎ ሰባብሮ ካደቀቃቸው በኋላ ከዛሬ 1,990 ዓመታት በፊት (2023

5
ዓ.ም. እንደ ግ.አ ላይ ሆነን ስናስበው) ከመቅደስ ወጥቶ ከሄደ ከጥቂት ቀናት በኋላ በማረግ ወደስፍራው
በተመለሰ ጊዜ መፈጸሙን ማንም ሊክደው የማይችል ሀቅ መሆኑን እንረዳለን፡፡

ስለዚህ ጌታ እስራኤላውያንን ሰባብሮና አድቅቋቸው ወደ ስፍራው የተመለሰው መቼ ነው? ለሚለው ጥያቄ


መልሳችን ከዛሬ 1,990 ዓመታት በፊት (2023 ዓ.ም. እንደ ግ.አ ላይ ሆነን ስናስበው) ብለን ለመመለስ ምንም
ነገር አያግደንም፡፡

ታዲያ መቼ ተመልሶ ይመጣል?

ለዚህ ጥያቄ ጌታ በዚሁ ነብይ ሆሴዕ በኩል በቀጣዩ ምዕራፍ ላይ መልስ ሰጥቷል፡፡

ሆሴ.6፡1-3 አ.መ.ት “1 ኑ ወደ እግዘያብሔር እንመለስ እርሱ ሰባብሮናል እርሱም ይጠግነናል እርሱ አቁስሎናል እርሱም ይፈውሰናል፡፡
2 ከሁለት ቀን በኋላ ያነቃናል በእርሱም ፊት እንድንኖር በሶስተኛው ቀን ያስነሳናል፡፡ 3 እግዚያብሔርን እንወቀው የበለጠ
እናውቀውም ዘንድ እንትጋ እንደንጋት ብርሃን በርግጥ ይገለጣል ምድርን እነደሚያረሰርስ የበልግ ዝናብ እንደክረምት ዝናብ ወደእኛ
ይመጣል፡፡”

እንግዲህ ጌታ እስራኤላውያንን የሰባበራቸው እና ያቆሰላቸው ማለትም ያደቀቃቸው መቼ ነው? ከዛሬ 1,990


ዓመታት በፊት (2023 ዓ.ም. እንደ ግ.አ ላይ ሆነን ስናስበው) አይደለም? “ከሁለት ቀን በኋላ ያነቃናል በእርሱም ፊት
እንድንኖር በሶስተኛው ቀን ያስነሳናል” እና “እንደንጋት ብርሃን በርግጥ ይገለጣል ምድርን እነደሚያረሰርስ የበልግ ዝናብ
እንደክረምት ዝናብ ወደእኛ ይመጣል” ማለት ምን ማለት ነው? ሰባብሮና ካደቀቃቸው ከሁለት ቀን በኋላ ይመጣል
ማለት አይደለም? ታዲያ ሰባብሮና አድቅቋቸው ወደስፍራው የተመለሰው ከዛሬ 1,990 አመታት በፊት (2023
ዓ.ም. እንደ ግ.አ ላይ ሆነን ስናስበው) ነው ካልን፣ ሰባብሮና ካደቀቃቸው ከሁለት ቀን በኋላ እስካሁን ድረስ
እስራኤላውያን ወደ እግዚያብሔር (ወደ ክርስቶስ ኢየሱስ) አልተመለሱም እርሱም አልመጣም፡፡ ታዲያ ጌታ
እየዋሸ ነው ማለት ነው? በፍጹም! ጌታ ይዋሽ ዘንድ ሰው አይደለም፡፡ ጌታ ከአፉ የወጣውን ቃል ይፈጽም ዘንድ
ይተጋልና፡፡ ታዲያ ጌታ ካደቀቃቸው ከሁለት ቀን በኋላ ይመጣል ማለት ምን ማለት ነው? አሁንም ጌታ ለዚህ
ጥያቄ መልስ አለው፡-

2 ጴጥ. 3፡8 አ.መ.ት “8 ወዳጆች ሆይ በጌታ ዘንድ አንድ ቀን እንደ ሺህ ዓመት፣ ሺህ ዓመትም እንደ አንድ ቀን መሆኑን ይህን አንድ
ነገር አትርሱ፡፡”

2 ኛ ጴጥሮስ ምዕራፍ 3 ን ሙሉ ምዕራፉን ስናነበው ስለጌታ መምጫ ጊዜ ነው ሚያወራው፡፡ ስለዚህ በጌታ


ዘንድ አንድ ቀን ለኛ ሺህ ዓመት ከሆነ፣ በጌታ ዘንድ ሁለት ቀን ማለት ለኛ ስንት ዓመት ማለት ነው? ሁለት
ሺህ ዓመት ማለት አይደለም? በትክክል ሁለት ሺህ ዓመት ማለት ነው፡፡ ስለዚህ ጌታ ሰባብሮና ካደቀቃቸው
ከሁለት ቀን በኋላ ይመጣል ማለት ሰባብሮና ካደቀቃቸው ከሁለት ሺህ ዓመት በኋላ ይመጣል ማለት ካልሆነ
ምን ማለት ነው? ጌታ ከአፉ የወጣውን ቃል ይፈጽመው ዘንድ ይተጋልና በእርግጠኝነት በማቴ. 24፡1 ጌታ ኢየሱስ
ከመቅደሱ ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ ወይም ደግሞ ካረገበት (ወደስፍራው ከተመለሰበት) ጊዜ ጀምሮ ከሁለት ሺህ
ዓመታት በኋላ ይመጣል፡፡

እንግዲህ ጌታ በማቴ. 24፡1 ከመቅደሱ ወጥቶ የሄደው (ያረገው) ከዛሬ 1,990 አመታት በፊት (2023 ዓ.ም.
እንደ ግ.አ ላይ ሆነን ስናስበው) ነው ካልን ሁለት ሺህ ዓመት የሚሆነው መቼ ነው? ከ 10 ዓመታት በኋላ
አይደለም? ምክኒያቱም 2000-1990=10 በመሆኑ፡፡ ስሊዚህ ጌታ ከዛሬ (2023 ዓ.ም) 10 ዓመት በኋላ ይመጣል
ካልን በ 2033 ዓ.ም እንደ ግ.አ ይመጣል ማለት ካልሆነ ምን ማለት ነው? እንግዲህ ጌታ ከ 2033 ዓ.ም እንደ ግ.አ
ቀድሞ ወይም ዘግይቶ ከመጣ የእግዚያብሔር ቃል ይዋሻል ማለት ነው? በፍጹም አይደለም፡፡ ቀድሞ ወይም
ዘግይቶ ይመጣል የሚለውን የሚወስነው የግሪጎሪያን አቆጣጠር ከክርስቶስ ልደት ዘግይቶ ወይም ቀድሞ ነው

6
የጀመረው የሚለው ነው፡፡ ነገር ግን አሁን በምድራችን ላይ እየሆነ ካለው ነገር አንጻር ጌታ እስከ 2033 ዓ.ም
እንደ ግ.አ. ድረስ እንደሚመጣ በእርግጠኝነት መናገር እችላለው፡፡

ሌሎች ነብያትስ ምን ይላሉ?


እንግዲህ ጌታ ካረገበት ጊዜ ከ 2000 ዓመታት በኋላ እንደሚመለስ የነብዩ ሆሴዕ ትንቢት ካስረዳን በጌታ ኢየሱስ
በኩልና በሌሎች ነብያት በኩል ስለጌታ ዳግም መምጫ ጊዜ የተነገሩ ትንቢቶች በነብዩ ሆሴዕ በኩል የተነገረውን
የ 2000 ዓመታት ጊዜ እንዴት እንደሚደግፉ በቀጣዮቹ ክፍሎች እንመለከታለን፡፡

የበለሷ ምሳሌ
በጌታ ኢየሱስ በማቴ. 24፡32-34 የተነገረውን የበለሷን ዛፍ ምሳሌ እንመልከት፡-

ማቴ. 24፡32-34 “32 ምሳሌውንም ከበለስ ተማሩ ጫፏ ሲለሰልስ ቅጠሏም ሲያቆጠቁጥ ያን ጊዜ በጋ እንደቀረበ ታውቃላችሁ፤ 33
እንዲሁ እናንተ ደግሞ ይህን ሁሉ ስታዩ በደጅ እንደቀረበ እወቁ፡፡ 34 እውነት እላችኋለሁ ይህ ሁሉ እስኪሆን ድረስ ይህ ትውልድ
አያልፍም፡፡”

መጽሐፍ ቅዱስ በተለያየ ቦታ ላይ የእስራኤልን ምድር ወይም ሕዝብ በበለስ ዛፍ እንደሚመስላቸው በጥቂቱ
ሆሴ. 9፡10፣ ኤር. 8፡13፣ እና ኤር. 24 መመልከት እንችላለን፡፡ እንግዲህ በማቴ. 24፡32 ላይ የተመለከተው ቃል “የበለስ
ዛፍ ጫፏ ሲለሰልስ ቅጠሏም ሲያቆጠቁጥ ያን ጊዜ በጋ እንደቀረበ ታውቃላችሁ” ሲል ስለእስራኤል ምድር እያወራ እንደሆነ
መረዳት አያዳግትም፡፡ ከዚህ በፊት ለመጥቀስ እንደሞከርኩት ጌታ ኢየሱስ የእስራኤልን ሕዝብ በመንፈስ
አድቅቋቸው ካረገ በኋላ እንደ ግሪጎሪያን አቆጣጠር በ 70 A.D. የሮማ ወታደሮች መጥተው ቤተ-መቅደሱን
እንዳቃጠሉ እና የእስራኤል ሕዝብ ወደ አለም ሁሉ እንደተበተኑ ታሪክ ያስረዳናል፡፡ ከዛ ጊዜ ወዲህ እስራኤልን
(ኢየሩሳሌምን) “ቤትሽ የተፈታ (ባድማ) ይሆናል” ብሎ ጌታ እንደረገማት እስራኤል እንደ ግ.አ. እስከ 1948 ዓ.ም.
ድረስ ምድረ በዳ ሆና እንደቆየችና እንደ ግ.አ. በ 1948 ዓ.ም. የተባበሩት መንግስታት (United Nations)
የእስራኤል ሕዝብ ናቸው ያላቸውን ከየሀገራቱ ሰብስቦ የእስራኤልን መንግስት እንዲመሰርቱ እንዳደረገ ከታሪክ
እንረዳለን፡፡ ስለዚህ የበለስ ዛፍ (እስራኤል) እንደ ግ.አ. ከ 1948 ዓ.ም ጀምሮ ጫፏ መለስለስ እና ቅጠሏ
ማቆጥቆጥ እንደጀመረና በጋም እደቀረበ አውቀናል ማለት ነው፡፡ ስለዚህ ይህን ባየንበት ጊዜ ማለትም እነደ
ግ.አ. ከ 1948 ዓ.ም ጀምሮ በማቴ. 24፡33 ላይ እንደተጠቀሰው ጌታ በደጅ እንደቀረበ እናውቃለን፡፡

ይሁንና በቁ. 34 ላይ “እውነት እላችኋለሁ ይህ ሁሉ እስኪሆን ድረስ ይህ ትውልድ አያልፍም” ሲል “ይህ ሁሉ እስኪሆን ድረስ”
የሚለው ሀረግ ከቁ.2 ጀምሮ እስከ ቁ.31 ድረስ ያሉትን ኩነቶች እንደሚያመለክት መረዳት አያዳግተንም፡፡ ነገር
ግን “ይህ ትውልድ አያልፍም” የሚለው ዐረፍተ-ነገር የትኛውን ትውልድ ነው ሚያመለክተው? ጌታ በምድር ላይ
በነበረ ጊዜ የነበረውን ትውልድ ነው? በፍጹም አይደለም፡፡ ያ ትውልድማ ከ 1,990 ዓመታት (እንደ
ግ.አ 2023 ዓ.ም. ላይ) በፊት እንዳለፈ ግልጽ ነው፡፡ ስለዚህ ይህ ትውልድ አያልፍም ሲል በለሷ (እስራኤል)
ጫፏ በለሰለሰበትና ቅጠሏ ባቆጠቆጠበት ማለትም እስራኤል እንደገና መንግስት በመሰረተችበት ጊዜ እነደ
ግ.አ. ከ 1948 ዓ.ም ጀምሮ የተወለዱ እና ከዛ ጊዜ ጥቂት ቀደም ብለው ተወልደው ከ 1948 ዓ.ም በኋላ በትንሹ
ለቀጣይ 83.5 ዓመታት በህይወት መኖር የሚችሉ ትውልድን የሚያመለክት እንደሆነ ከቀጣዩ ጥቅስ
እንረዳለን፡፡ እንግዲህ የእግዚያብሔር ቃል ለጥያቄ ሁሉ መልስ አለውና የአንድ ትውልድ ጊዜ (period) ምን
ያህል ዓመታት ናቸው? የሚለውን ጥያቄ በመዝ. 90፡10 መልሶታል፡፡

መዝ. 90፡10 “የዘመኖቻችንም እድሜ ሰባ ዓመት ቢበረታም ሰማኒያ ዓመት ነው፤ ቢበዛ ግን ድካምና መከራ ነው፤ ከእኛ ቶሎ
ያልፋልና፤ እኛም እንገሰጻለንና፡፡”

7
በአጠቃላይ መዝሙር 90 ን ከቁ.1 ጀምረን ስናነበው ስለ አንድ ትውልድ ጊዜ (period) እንደሚያመለክት
መረዳት አያዳግተንም፡፡ ስለዚህ የእግዚያብሔር ቃል የአንድ ትውልድ ጊዜ (period) ቢበረታ 80 አመታት
ናቸው ካለን እንደ ግ.አ. በ 1948 ዓ.ም ላይ አንድ ትውልድ ማለትም 80 ዓመታትን ስንደምር እነደ ግ.አ. 2028
ዓ.ም እንደሚሆን እንረዳለን ከዛ በኋላ ጌታ እስኪመጣ ያለው ጊዜ ግን ቃሉ በመዝ. 90፡10 “ቢበዛ ግን ድካምና መከራ
ነው፤ ከእኛ ቶሎ ያልፋልና፤ እኛም እንገሰጻለንና” እንደሚል እንደ ግ.አ. ከ 2028 ዓ.ም. በኋላ እውነተኛውን መሲሕ
ክርስቶስ ኢየሱስን ያልተቀበሉ ዐመፀኞች ሁሉ ከእግዚአብሔር ቁጣ የተነሳ ድካምና መከራ ውስጥ
የሚገቡበትና የሚገሰጹበት (የሚጠፉበት) ጊዜ ይሆናል ማለት ነው፡፡ ይህም ማለት በዓለም (በምድር)
በተለይም በእስራኤል የሚኖር ሕዝብ ሁሉ በታላቁ መከራ (The Great Tribulation) ውስጥ የሚያልፍበት
ቢበዛ 3.5 ዓመታት (42 ወራት) ብቻ እንደሚሆን ከነብዩ ዳንኤል እና ከዮኀንስ ራዕይ መጽሐፍት መረዳት
እንችላለን፡፡ በመሆኑም በግ.አ. 2028 ዓ.ም. ላይ 3.5 ዓመታትን ስንደምር፣ 2028 + 3.5 = 2031.5 ሲሆን እንደ
ግ.አ 2031 ዓ.ም. መጨረሻዎቹ ወራት ላይ ማለት ነው፡፡

ስለዚህ ከበለሷ ምሳሌ ከማቴ. 24፡32-34 እና ከመዝ. 90፡10 ያገኘነው መረጃ ጌታ እነደ ግ.አ. በ 2031 ዓ.ም
እንደሚመጣ ያስረዳናል፡፡ የነብዩ ሆሴዕ እና የማቴዎስ ወንጌል መጻሕፍት ደግሞ እንደ ግ.አ. ጌታ ከ 2031 ዓ.ም
እስከ 2033 ዓ.ም እንደሚመጣ ያስረዱናል፡፡ ስለዚህ በአጠቃላይ ከእግዚአብሔር ቃል በማቴ. 24 ከበለሷ ምሳሌ
ጌታ እንደ ግ.አ. እስከ 2031 ዓ.ም ድረስ እንደሚመጣ ስንረዳ ከሆሴ. 6 ደግሞ እንደ ግ.አ. እስከ 2033 ዓ.ም.
ድረስ እንደሚመጣ እንረዳለን፡፡ ይሁንና በሁለቱ ትንቢቶች መሀል የሁለት ዓመት ልዩነት ብቻ እናስተውላለን፡፡
ይህ ልዩነት ከየት መጣ? ሁለቱ ትንቢቶች ስለተጣረሱ ነው? በፍጹም አይደለም፡፡ መጀመሪያ ለመጥቀስ
እንደሞከርኩት ይህ ልዩነት የመጣው ከግሪጎሪያን ካሌንደር (አቆጣጠር) አጀማመር ስህተት እንደሆነ
እንገነዘባለን፡፡ ስለዚህ ጌታ እነደ ግ.አ. በ 2031 ዓ.ም ከመጣ የግሪጎሪያን አቆጣጠር ከጌታ ልደት ሁለት ዓመት
ዘግይቶ እንደጀመረ እንገነዘባለን ማለት ነው፡፡ ስለዚህ በአጠቃላይ የማቴ.24 የበለሷ ምሳሌ ከሆሴ. 6 የ “ሁለት
ቀን (የ 2000 ዓመታት)” ትንቢት ጋር ይስማማል ብለን በድፍረት መናገር እንችላለን ማለት ነው፡፡ ምክንያቱም
የበለሷ ምሳሌ ትንቢት ውጤት 2031 ዓ.ም በሆሴዕ ትንቢት ውጤት ማለትም ከ 2031 ዓ.ም እስከ 2033 ዓ.ም
ውስጥ ስለሚያርፍ ነው፡፡

እግዚአብሔር በምድር ላይ ለሰው ልጅ የያዘው የ 7000 ዓመታት አጀንዳ


ዕብ. 3፡7-19፣ ዕብ. 4፡1-11፣ እና ዘፍ. 2፡1-3

ሌላው የሆሴን ሁለት ቀን (2000 ዓመት) ትንቢት የሚደግፉት ጥቅሶች ዕብ. 3፡7-19፣ ዕብ. 4፡1-11 እና ዘፍ. 2፡1-3
ናቸው፡-

ውድ አንባቢ በዕብ. 3፡7-19 እና ዕብ. 4፡1-11 የተጠቀሰውን ቃል ሙሉ ለሙሉ በዚህ ላይ ማስፈር ብክነት ስለሚሆን
ከውስጡ ጥቂቱን ብቻ መርጬ በመውሰድ ሃሳቤን ለመግለጽ እሞክራለሁ፡፡ ነገር ግን እርሶ በቂ መረጃ
እንዲያገኙ ሙሉ ለሙሉ እንዲያነቡት እጋብዞታለው፡፡ ስለዚህ ከምዕራፍ 3 ዕብ. 3፡7-11 እና 16-17 ያለውን
እንደሚከተለው አቀርበዋለሁ፡-

ዕብ. 3፡7-11 “7 ስለዚህ መንፈስ ቅዱስ እንደሚል፡፡ 8-9 ዛሬ ድምጹን ብትሰሙት አባቶቻችሁ እኔን የፈተኑበት የመረመሩበትም
አርባ አመትም ስራዬን ያዩበት በምድረበዳ በፈተና ቀን በማስመረር እንደሆነ ልባችሁን እልከኛ አታድርጉ፡፡ 10 ስለዚህ ያን ትውልድ
ተቆጥቼ ዘወትር በልባቸው ይስታሉ መንገዴን ግን አላወቁም አልሁ፤ 11 እንዲሁ ወደ እረፍቴ አይገቡም ብዬ በቁጣዬ ማልሁ፡፡”

ዕብ. 3፡16-17 “16 ሰምተው ያስመረሩት እነማን ነበሩ? በሙሴ ተመርተው ከግብፅ የወጡ ሁሉ አይደሉምን? 17 አርባ አመትም
የተቆጣባቸው ዕነማን ነበሩ? ሬሳቸው በምድረበዳ የወደቁ ሀጢያትን ያደረጉት እነርሱ አይደሉምን?”

8
እንግዲህ ከላይ የተጠቀሰው ቃል እግዚያብሔር እስራኤላውያንን በሙሴ መሪነት ከግብፅ ምድር ካወጣቸው
በኋላ ከባርነት ያወጣቸውን እግዚያብሔርን ባለማመናቸው ምክንያት ወደ ተስፋይቱ ምድር እንዳይገቡ
የማለባቸውን እና ወደምድሪቱ ሳይገቡ በምድረበዳ ሞተው የቀሩትን ትውልድ እንደሚያመለክት እንረዳለን፡፡
እንዲሁም የተስፋዪቱን ምድር (ማርና ወተት የምታፈልቀውን የከናናውያንን ምድር) በዕረፍቱ ሲመስላት
እንመለከታለን፡፡ ይሁንና በዕረፍቱ መሰላት እንጂ የእግዚያብሔር ዕረፍት አይደለችም፡፡ ታዲያ የእግዚያብሔር
ዕረፍት ማናት? ወይስ ምንድናት? መልሱን ከዕብ.4 እንመልከት፡-

ዕብ.4፡1 “1 እንግዲህ ወደ ዕረፍቱ ለመግባት ተስፋ ገና ቀርቶልን ከሆነ ምንአልባት ከእናንተ ማንም የማይበቃ መስሎ እንዳይታይ
እንፍራ፡፡”

ዕብ.4፡3-4 “3 ሥራው አለም ከተፈጠረ ጀምሮ ምንም እንኳ ቢፈጸም እንዲህ ወደ ዕረፍቴ አይገቡም ብዬ በቁጣዬ ማልሁ እንዳለ
እኛስ ያመንን ወደ ዕረፍቱ እንገባለን፡፡ 4 ስለ ሰባተኛው ቀን በአንድ ስፍራ እግዚአብሔርም በሰባተኛው ቀን ከስራው ሁሉ ዐረፈ
ብሏልና፡፡”

ዕብ. 4፡7-11 “7 ዛሬ ድምፁን ብትሰሙት ልባችሁን እልከኛ አታድርጉ በፊት እንደተባለ፣ ይህን ከሚያህል ዘመን በኋላ በዳዊት ሲናገር
ዛሬ ብሎ አንድ ቀን እንደገና ይቀጥራል፡፡ 8 ኢያሱ አሳርፏቸው ኖሮ ቢሆንስ ከዚያ በኋላ ስለሌላ ቀን ባልተናገረ ነበር፡፡ 9 እንግዲያስ
የሰንበት ዕረፍት ለእግዚያብሔር ሕዝብ ቀርቶላቸዋል፡፡ 10 ወደ ዕረፍቱ የገባ እግዚያብሔር ከስራው እንዳረፈ እርሱ ደግሞ ከስራው
ዐርፏልና፡፡ 11 እንግዲህ እንደዚያ እንደአለመታዘዝ ምሳሌ ማንም እንዳይወድቅ ወደዚያ ዕረፍት ለመግባት እንትጋ፡፡”

እንግዲህ ቃሉን ከላይ በዝርዝር እንደምንመለከተው በዕብ. 4፡1 ላይ ሌላ የእግዚያብሔር ዕረፍት ተስፋ
እንደቀረልን እናስተውላለን፡፡ በዕብ. 4፡3-4 ላይ ደግሞ ይህች የቀረችልን ዕረፍት በዘፍ. 2፡1-3 እግዚአብሔር
ከስራው ሁሉ ያረፈባትን የሰባተኛይቱን ቀን እንደምትመስል እናስተውላለን፡፡ በዕብ. 4፡7 ደግሞ የቀረችልን
ዕረፍት የአንድ ቀን ዕረፍት እንደሆነች እንገነዘባለን፡፡ ከዕብ. 4፡8 ደግሞ ጌታ በኢያሱ በኩል ያወረሳቸው
የተስፋዪቱ ምድር የጌታ ዕረፍት እንዳልሆነች እንረዳለን፡፡ ዕብ. 4፡9 ይህች የቀረችልን ዕረፍት የሰንበት ዕረፍት
(የሰባተኛ ቀን ዕረፍት) እንደሆነች ያስረዳናል፡፡ ዕብ.4፡10 ደግሞ ይህችው የቀረችልን የምንገባባት ዕረፍት
በእግዚያብሔር የሰባተኛይቱ ቀን ዕረፍት እንደምትመሰል እንረዳለን፡፡

እንግዲህ ይህች የቀረችልን ዕረፍት ከላይ ከተጠቀሰው ምሳሌ ወጥተን በግልጽ ስናያት ማናት? ወይስ
ምንድናት? መቼ እንገባባታለን? ለሚሉት ጥያቄዎች በዘፍ. 2፡1-3 እና 2 ጴጥ. 3፡8 የተሰጠንን ቃል መመርመር
ይጠበቅብናል፡-

ዘፍ. 2፡1-3 “1 ሰማይና ምድር ሰራዊታቸውም ሁሉ ተፈጸሙ፡፡ 2 እግዚያብሔር የሰራውን ስራ በሰባተኛው ቀን ፈጸመ፤ በሰባተኛው
ቀን ከሰራው ስራ ሁሉ ዐረፈ፡፡ 3 እግዚያብሔርም ሰባተኛውን ቀን ባረከው ቀደሰውም፤ እግዚያብሔር ሊያደርገው ከፈጠረው ስራ
ሁሉ በእርሱ ዐርፏልና፡፡”

ጠቅለል ባለ መልኩ ይህች የቀረችልን ገና ወደፊት የምንገባባት ዕረፍት በእግዚያብሔር ዕረፍት ከተመሰለች፣
እግዚያብሔር ስድስት ቀን ሰርቶ በሰባተኛይቱ ቀን እንዳረፈ እኛም አዳም ከተፈጠረባት ቀን ጀምሮ ስድስት
ቀን ሰርተን በሰባተኛይቱ ቀን የምናርፍባት የአንድ ቀን የሰንበት ዕረፍት እንደሆነች እንገነዘባለን፡፡ ነገር ግን
አዳም ከተፈጠረ ጀምሮ እስከዛሬ ድረስ ያረፍናቸው በሺዎች የሚቆጠሩ የቅዳሜ ወይም የዕሁድ ዕረፍቶች
ቢሆኑ ኖሮ፣ በዕብ. 4፡7 “7 ዛሬ ድምፁን ብትሰሙት ልባችሁን እልከኛ አታድርጉ በፊት እንደተባለ፣ ይህን ከሚያህል ዘመን በኋላ
በዳዊት ሲናገር ዛሬ ብሎ አንድ ቀን እንደገና ይቀጥራል፡፡” ተብሎ እንደተጻፈው ገና ወደፊት እንደምትመጣ በነጠላ ቁጥር
የአንድ ቀን ዕረፍት ተስፋ አድርጎ አያቀርባቸውም ነበር፡፡ ስለዚህ ይህች የአንድ ቀን የሰንበት ዕረፍት በ 2 ጴጥ. 3፡8
እንደተጻፈው በእግዚአብሔር ዘንድ አንድ ቀን እንደ 1000 ዓመት ነው በሚለው ቀመር የምትሰላ የ 1000
ዓመታት ዕረፍት እንደሆነችና የ 7 ኛይቱ ቀን ዕረፍት እንደመሆኗ ከአዳም ጀምሮ ከ 6000 ዓመታት በኋላ
የምንገባባት ሰባተኛዋ 1000 ዓመታት እንደሆነች እንረዳለን፡፡

9
ታዲያ ከአዳም ጀምሮ ከ 6000 ዓመታት በኋላ ከሆነ የምንገባባት እኚህ 6000 ዓመታት መቼ ነው
የሚጠናቀቁት? ከአዳም ጀምሮ እስከ አሁን (ማለትም እንደ ግ.አ. እስከ 2023 ዓ.ም.) ድረስ ምን ያህል
ዓመታትን አስቆጥረናል? ምን ያህል ዓመታትስ ይቀሩናል? ማለትም በእግዚአብሔር ካሌንደር (ቀን አቆጣጠር)
አሁን የት ነው ያለነው? ለዚህም ጥያቄ የእግዚአብሔር ቃል (መጽሐፍ ቅዱስ) መልስ አለው፡፡ ከአዳም ጀምሮ
እስከአሁን ድረስ ያሉትን ዘመናት ለማወቅ ከአዳም ጀምሮ እስከ ክርስቶስ ልደት ድረስ ያሉትን ዘመናት ማወቅ
በቂ ነው፡፡ በሚከተሉት ሰንጠረዦች ልተነትናቸው ሞክሪያለሁና በጥሞና ይመልከቷቸው፡፡

ከአዳም እስከ ክርስቶስ እርገት

የክስተት ጊዜ በክስተት መሐል ያለ የኋለኛው ክስተት ቀን ማጣቀሻ


(Period of Events) የአመታት ብዛት ከአዳም ጀምሮ (References)
(Duration b/n Events) (Date of Later event
from Adam)
ከአዳም እስከ ኖኅ ጥፋት 1656 1656 ዘፍ. 5 & ዘፍ. 7:6
ውሃ
ከኖኅ ጥፋት ውሃ እስከ 452 2108 ዘፍ. 11, ዘፍ.12:4
ያዕቆብና ኤሳው ልደት ዘፍ.16:3-6, ዘፍ.17:24,
ዘፍ.:25-26
ከያዕቆብና ኤሳው ልደት 430 (የያዕቆብን 130 2538 ገላ. 3:17, ዘጸ.12:41,
እስከ ዘጸአት ዓመታት ጉዞ ያካትታል) ዘፍ.47:9
ከዘጸአት እስከ የሰለሞን 480 3018 1 ነገ. 6:1
መቅደስ መሰረት መጣል
ከሰለሞን መቅደስ 428.5 3447 2 ዜና
መሰረት መጣል እስከ
ባቢሎን ግዞት
ከባቢሎን ግዞት እስከ 70 3516.5 ኤር.25:11,
ነጻነት 2 ዜና.36:11-23, ዘካ.
11:12
ከነጻነት እስከ ክርስቶስ 483-30=453 3969.5 ሉቃ. 3:23
ልደት
ከነጻነት እስከ ክርስቶስ 483 3999.5 ዳን.9:1-2, ዳን.9:25,
መምጣት/መገለጥ 2 ዜና.36:22, እዝቅ.1:1,
(ጥምቀቱ) ዮሐ. 1:27-30
ከክርስቶስ 3.5 4003 ሉቃ. 3:23, የሐ. 2:23,
መምጣት/መገለጥ 6:4, 19-14
(ከጥምቀቱ) እስከ ሞቱ፣
ትንሳኤው፣ እና እርገቱ
ሠንጠረዥ-1 ከአዳም እስከ ክርስቶስ ሞት፣ ትንሳኤ፣ እና እርገት (Overview)

10
ከላይ ከተመለከተው ሰንጠረዥ-1 እንደምናስተውለው አዳም ከተፈጠረበት ቀን ጀምሮ እስከ ክርስቶስ ሞት፣
ትንሳኤ፣ እና እርገት ድረስ ያለው ጊዜ 4,003 ዓመታት ናቸው፡፡ ምናልባትም ይህን ሰንጠረዥ በዝርዝር
መረዳት የሚፈልጉ አንባቢ ከሆኑ፤ ማለትም ‘በክስተቶች መሐል ያሉት የአመታት ብዛት (Duration b/n
Events)’ ወይም ‘የኋለኛው ክስተት ቀን ከአዳም ጀምሮ (Date of Later event from Adam)’ ስሌት እንዴት
እንደመጣ ማወቅ የሚፈልጉ አንባቢ ከሆኑ የስድስቱን ክስተቶች ማለትም ‘ከያዕቆብና ኤሳው ልደት እስከ
ዘጸአት’፣ ‘ከዘጸአት እስከ የሰለሞን መቅደስ መሰረት መጣል’፣ ‘ከባቢሎን ግዞት እስከ ነጻነት’፣ ‘ከነጻነት እስከ
ክርስቶስ ልደት’፣ ‘ከነጻነት እስከ ክርስቶስ መምጣት/መገለጥ (ጥምቀቱ)’፣ እና ‘ከክርስቶስ መምጣት/መገለጥ
(ከጥምቀቱ) እስከ ሞቱ፣ ትንሳኤው፣ እና እርገቱ’ በቀላሉ በማጣቀሻው (References) ኮለም ላይ
የተጠቀሱትን ጥቅሶች ከመጽሐፍ ቅዱስ ላይ በማየት መረዳት ይችላሉ፡፡ ነገር ግን የተቀሩት ሶስቱ ዘመናት
ማለትም ‘ከአዳም እስከ ኖኅ ጥፋት ውሃ’፣ ‘ከኖኅ ጥፋት ውሃ እስከ ያዕቆብና ኤሳው ልደት’፣ እንዲሁም
‘ከሰለሞን መቅደስ መሰረት መጣል እስከ ባቢሎን ግዞት’ ጥቂት ዘርዘር ያለ ትንተና (Analysis) ሊፈልጉ
ስለሚችሉ በሚከተሉት ሰንጠረዦች ልተነትናቸው ሞክረሪያለሁና በጥሞና ሊመለከቷቸው ይችላሉ፡፡

ከአዳም እስከ ኖኅ ጥፋት ውሃ (ዘፍ.5 እና ዘፍ.7:6)

የወላጅ/የአባት አባት ልጁን በወለደ ጊዜ የተወለደ ልጅ የተወለደበት/ክስተት የተከሰተበት ቀን


ስም የነበረው አድሜ ልጅ/የተከሰተ ክስተት (የአመታት ብዛት) ከአዳም ጀምሮ
(Name of (Age of father when (Son born/Event (No. of yrs after Adam when a son is
parent/father) he begot his son) happened) born for a man/when event
happened (Date from Adam)
አዳም 130 ሴት 130
ሴት 105 ሄኖስ 130+105=235
ሄኖስ 90 ቃይናን 325
ቃይናን 70 መላልኤል 395
መላልኤል 65 ያሬድ 460
ያሬድ 162 ሄኖክ 622
ሄኖክ 65 ማቱሳላ 687
ማቱሳላ 187 ላሜሕ 874
ላሜሕ 182 ኖኅ 1056
ኖኅ 600 የጥፋት ውሃ 1656
ሠንጠረዥ-1.1 ከአዳም አስከ ኖኅ ጥፋት ውሃ (ዘፍ.5 እና ዘፍ.7:6)

ከላይ ሰንጠረዥ-1.2 እንደሚያመለክተን ከአዳም ጀምሮ የኖህ ጎርፍ በ 1656 እንደመጣ ከዘፍጥረት ምዕራፍ 5
(ሙሉ ምዕራፉን ያንብቡት) እና ከዘፍጥረት ምዕራፍ 7 ቁጥር 6 እንረዳለን፡፡ ማለትም አዳም በ 130 አመቱ
ሴትን ወለደ፣ ሴት በ 105 አመቱ ሄኖስን ወለደ፣ ሄኖስ በ 90 አመቱ ቃይናንን ወለደ፣ ቃይናን በ 70 አመቱ
መላልኤልን ወለደ፣ መላልኤል በ 65 አመቱ ያሬድን ወለደ፣ ያሬድ በ 162 አመቱ ሄኖክን ወለደ፣ ሄኖክ በ 65
አመቱ ማቱሳላን ወለደ፣ ማቱሳላ በ 187 ዓመቱ ላሜሕን ወለደ፣ ላሜሕ በ 182 አመቱ ኖኅን ወለደ፡፡
በመጨረሻም የጥፋት ውሀ በምድር ላይ በመጣ ጊዜ ኖኅ የ 600 አመት ሰው ነበር፡፡ ስለዚህ ከአዳም ጀምሮ እስከ
ላሜሕ ድረስ ያሉት ሰዎች እያንዳንዳቸው ልጅ በወለዱ ጊዜ የነበራቸውን እድሜ በመደማመር እና
በመጨረሻም የጥፋት ውሃ በመጣ ጊዜ ኖኅ የነበረውን እድሜ በመደመር አዳም ከተፈጠረበት ቀን ጀምሮ እስከ
የጥፋት ውሃ የመጣበት ቀን ድረስ ያሉትን የዓመታት ብዛት (ከአዳም ጀምሮ የጥፈፋት ውሃ የመጣበትን ቀን)
ማወቅ እንችላለን ማለት ነው፡፡ ማለትም 130+105+90+70+65+162+65+187+182+600=1,656
ዓመታት.

11
ከአዳም እስከ ያዕቆብና ኤሳው

የወላጅ (የአባት) አባት ልጁን የክስተት/የተወለደ ልጅ ልጅ የተወለደበት/ክስተት


ስም/የክስተት ጊዜ በወለደ/በክስተት ጊዜ ስም የተከሰተበት ቀን (የአመታት ብዛት)
(Name of የነበረው አድሜ (Name of Event/Son ከአዳም ጀምሮ
parent/Period (Age of father born ) (No. of yrs after Adam when a
of Event) when he begot his son is born for a father/when
son/when event event happened (Date from
happened) Adam)
ከአዳም እስከ ኖኅ 600 የኖኅ ጥፋት ውሃ 1656
ጥፋት ውሃ
ኖኅ 502 ሴም 1558
ሴም 100 አርፋክስድ 1658
አርፋክስድ 35 ሳላ 1693
ሳላ 30 ዔቦር 1723
ዔቦር 34 ፋሌቅ 1757
ፋሌቅ 30 ራግው 1787
ራግው 32 ሴሮህ 1819
ሴሮህ 30 ናኮር 1849
ናኮር 29 ታራ 1878
ታራ 70 አብራም 1948
ከአዳም እስከ ያዕቆብና ኤሳው (ዘፍ. 12:4, 16:3-6, 17:24)
አብራም 75 ካራንን ለቀቀ 2023
አብራም 85 አጋር ኢስማኤልን ፀነሰች ሶራ 2033
አጋርን ከትዕቢቷና ከንቀቷ
የተነሳ ስላሰቃየቻት አጋር
ኮበለለች
አብራም 86 ኢስማኤል 2034
አብራሃመ 100 ይስሐቅ 2048
ይስሐቅ 60 ያዕቆብና ኤሳው 2108
ሠንጠረዥ-1.2 ከሴም እስከ አብራም እና ከአብራም እስከ ያዕቆብና ኤሳው

ሰንጠረዥ-1.2 እንደሚጠቁመን ከአዳም እስከ ያቆብና ኤሳው ውልደት ድረስ ያለው ጊዜ 2,108 ዓመታት
እንደሆኑ ወይም ያቆብና ኤሳው ከአዳም ጀምሮ በ 2108 እንደተወለዱ ከዘፍጥረት 11 እና ዘፍ. 12:4፣ 16:3-6፣
እና 17:24 እንረዳለን፡፡ ዘፍ. 11፡10 ‘ሁለት ዓመት ከጥፋት ውሃ በኋላ ሴም በ 100 ዓመቱ አርፋክድን ወለደ፡፡‘ እንግዲህ ሁለት
ዓመት ከጥፋት ውሃ በኋላ ሴም የ 100 ዓመት ሰው ሲሆን ኖኅ ደግሞ የ 602 ዓመት ሰው እንደሆነ እንረዳለን
ምክኒያቱም የጥፋት ውሃ በመጣ ጊዜ ኖኅ የ 600 ዓመት ሰው ስለሆነ፡፡ ስለዚህ ኖኅ ሴምን በወለደ ጊዜ 602-
100 = የ 502 ዓመት ሰው ነበር ማለት ነው፡፡ ስለዚህ ሴም የጥፋት ውሃ ከመምጣቱ 600-502 = 98 ዓመት
በፊት ተወለደ ማለት ነው፡፡ በመሆኑም ሴም ከአዳም ጀምሮ 1656-98 = በ 1558 ተወለደ ማለት እንችላለን፡፡

ሴም በ 100 ዓመቱ አርፋክስድን ወለደ፣ አርፋክስድ በ 35 ዓመቱ ሳላን ወለደ፣ ሳላ በ 30 ዓመቱ


ዘፍ.11፡10-32
ዔቦርን ወለደ፣ ዔቦር በ 34 ዓመቱ ፋሌቅን ወለደ፣ ፋሌቅ በ 30 ዓመቱ ራግውን ወለደ፣ ራግው በ 32 ዓመቱ
ሴሮህን ወለደ፣ ሴሮሕ በ 30 ዓመቱ ናኮርን ወለደ፣ ናኮር በ 29 ዓመቱ ታራን ወለደ፣ ታራ በ 70 ዓመቱ አብራምን
ወለደ፡፡ ስለዚህ አብራም ከአዳም ጀምሮ 1558+100+35+30+34+30+32+30+29+70 = በ 1948 ተወለደ
ማለት ነው፡፡ በመቀጠል ከዘፍ. 12:4, 16:3-6, እና 17:24 አብርሀም በ 100 ዓመቱ ይስሀቅን ወለደ፣ ይስሀቅ በ 60

12
ዓመቱ ያዕቆብና ኤሳውን ወለደ፡፡ ስለዚህ ከአዳም ጀምሮ የያዕቆብና የኤሳው የልደት ቀን 1948+100+60 =
2108 ይሆናል ማለት ነው፡፡

በብሉይ (በአሮጌው) ኪዳን የሚገኝ ክስተት ወይም ትንቢት ሁሉ በአዲሱ ኪዳን ሊመጣ ላለው ጥላ (ምሳሌ)
እንደሆነ ከእግዚያብሔር ቃል እንረዳለን፡፡ በሰንጠረዥ-1.2 ውስጥ በአሮጌው ኪዳን የተከሰቱ ሶስት ትኩረቴን
የሳቡ ክስተቶች አሉ፡፡ ትኩረቴን የሳቡት ክስተቶቹ ብቻ ሳይሆኑ ከአዳም ጀምሮ የተከሰቱበት ጊዜም ጭምር
ነው፡፡ ከሶስቱ አንዱ የመጀመሪያው ክስተት በአዲሱ ኪዳን ወቅት በተመሳሳይ ጊዜ በድጋሚ የተፈጸመ ሲሆን
ቀሪዎቹ ሁለቱ ወደፊት ይፈጸማሉ ብዬ እምገምታቸው ናቸው፡፡ እነዚህ ሶስት ክስተቶች፡- የአብራም ልደት
ቀን (ከአዳም ጀምሮ 1948)፣ አብራም ከካራን የወጣበት ቀን (ከአዳም ጀምሮ 2023)፣ እና አጋር ኢስማኤልን
በፀነሰች ጊዜ ሶራ አጋርን ከትዕቢቷና ከንቀቷ የተነሳ ስላሰቃየቻት አጋር የኮበለለችበት ቀን (ከአዳም ጀምሮ
2033) ናቸው፡፡

የመጀመሪያውን ክስተት ከሰንጠረዡ እነደምንመለከተው አብራም ከአዳም ጀምሮ በ 1948 እንደተወለደ


እናስተውላለን፡፡ የእስራኤል ሕዝብ ከአብራም ዘር ስለመጣ አብራም በተወለደ ጊዜ የእስራኤል ሕዝብ
(መንግስት) እንደተወለደ እንገነዘባለን፡፡ ስለዚህ በአሮጌው ኪዳን የእስረራኤል ሕዝብ (መንግስት) ከአዳም
ጀምሮ በ 1948 ተወለደ፡፡ ይሄንን ክስተት በአዲሱ ኪዳን ወቅትም የእስራኤል ሕዝብ እንደ ግ.አ. ከሁለተኛው
አዳም ከክርስቶስ ልደት ጀምሮ በ 1948 ዓ.ም መንግስት ሲመሰርቱ በድጋሚ ሲፈፀም እናስተውላለን፡፡ ታዲያ
ይህ ክስተት የተፈጸመበት ጊዜ በአጋጣሚ የሆነ ይመስሎታል? በፍፁም በአጋጣሚ አልሆነም፡፡ በእግዚያብሔር
ዘንድ አጋጣሚ ብሎ ነገር አለ ብዬ አላስብም፡፡ እንዲያውም እንደዚህ አይነት ክስተቶች በተደጋጋሚ በመጽሀፉ
ውስጥ እናስተውላለን፡፡ እግዚአብሔር ይህን የሚያደርግበት ምክኒያት የዘመናትን ምስጢር እንድናስተውል
ነው ብዬ አስባለሁ፡፡

ሁለተኛው ክስተት አብራም ከካራን የወጣበት ቀን (ከአዳም ጀምሮ 2023) ነው፡፡ እንግዲህ በዚህ ጊዜ
እግዚአብሔር አብራምን ከካራን እኔ ወደማሳይህ ምድር ሁሉ ውጣ ሲለው እንመለከታለን፡፡ ይሄንን ጊዜ
በአዲሱ ኪዳን ላይ ሆነን ስናስበው እንደ ግ.አ. ከክርስቶስ (ከሁለተኛው አዳም) ጀምሮ ይህን ጽሁፍ እየጻፍኩ
ካለሁበት ጊዜ ማለትም ከ 2023 ዓ.ም ጋር ይመሳሰላል፡፡ በመሆኑም ከአዳም ጀምሮ በ 2023 እግዚአብሔር
አብራምን ከሚኖርበት ምድር እኔ ወደማሳይህ ምድር ውጣ ብሎ እንዳዘዘው አሁን በያዝነው ዓመት እንደ ግ.አ.
በ 2023 ዓ.ም. እግዚአብሔር ለህዝቡ (ለክርስቲያን) ህዝብ ተመሳሳይ ክስተትን የሚያደርግ ይመስለኛል
(ምናልባትም ከምቾት ስፍራችን/confort zone እንድንወጣ ቢፈልግስ?)፡፡

ሶስተኛው ክስተት ከላይ እንደጠቀስኩት አጋር የኮበለለችበት ቀን (ከአዳም ጀምሮ 2033) ነው፡፡ ይህን ጊዜ
በአዲሱ ኪዳን ላይ ሆነን ስናየው እንደ ግ.አ. ከክርስቶስ (ከሁለተኛው አዳም) ጀምሮ ከ 2033 ዓ.ም ጋር
ይመሳሰላል፡፡ እንደ ግ.አ. በ 2033 ዓ.ም. የሚከሰተውን ተመሳሳይ ክስተት ግን የጽሁፌ ዋና አጀንዳ ስለሆነ
ለመገመት አልፈራም፡፡ ይህም ልክ አጋርን ከትዕቢቷና ከንቀቷ የተነሳ ሶራ እንዳሰቃየቻት እና አጋር
እንደኮበለለች ሁሉ፣ አሁን በእስራኤል ምድር የሚኖሩ እስራኤላዊ ተብዬ አይሁዶች ክርስቶስን ካለማመናቸው
የተነሳ እርሱ ዳግመኛ በክብር በሚመጣበት ጊዜ ከሚደርስባቸው ታላቅ መከራ (The Great Tribulation)
የተነሳ የሚያጋጥማቸውን ስደት (መኮብለል) የሚያመለክት ይመስለኛል፡፡

13
ከመጀመሪያው መቅደስ ምስረታ እስከ ባቢሎን ግዞት (2 ዜና መዋዕል)

የንጉስ ስም ንጉሱ የነገሰባቸው ልዩ ክስተት ከመቅደሱ ምስረታ ጀምሮ ማጣቀሻ


(Name of King) ዓመታት ብዛት (Special event) ንጉሱ በስልጣን የቆየባቸው (Reference)
(No. of yrs. ዓመታት ብዛት
The King (No. Of years the King
reigned for) stayed in power after
Temple foundation)
ሰለሞን ከነገሰ አራት ዓመታት 0 2 ዜና.3:2
በኋላ የመቅደሱ መሰረት
መጣል ተጀመረ
ሰለሞን 40 40-4=36 2 ዜና.9:30
ሮብዓም 17 36+17=53 2 ዜና.12:13
አብያ ኢዮርብአም በነገሰ 2 ዜና.13:1
በ 18 ኛ ዓመቱ ነገሰ

14
አብያ 3 በዚህ ጊዜ በአብያና 53+3=56 2 ዜና.13:1-2
በኢዮርብአም መሃል
ጦርነት ነበር
አብያ 10 በዚህ ጊዜ በሰላም ነገሰ 66 2 ዜና.14:1
አሳ 41 107 2 ዜና.16:13
ኢዮሳፍጥ 25 132 2 ዜና.20:31
ዒዮሆራም 8 140 2 ዜና.21:20
አካዝያስ 1 141 2 ዜና.22:2
ጎቶልያ 6 147 2 ዜና.22:12
ኢዮአስ 40 187 2 ዜና.24:1
አሜስያስ 29 216 2 ዜና.26:1
ኦዝያን 52 268 2 ዜና.26:3
ኢዮአታም 16 284 2 ዜና.27:8
አካዝ 16 300 2 ዜና.28:1
ሕዝቅያስ 29 329 2 ዜና.29:1
ምናሴ 55 384 2 ዜና.33:1
አሞን 2 386 2 ዜና.33:21
ኢዮስያስ 31 417 2 ዜና.34:1
ኢዮአሃዝ 3 ወራት 417.25 2 ዜና.36:2
ኢዮአቄም 11 428.25 2 ዜና.36:5
ዮአኪን 3 ወራት 428.50 2 ዜና.36:9
ዮአኪን ዮአኪን በናቡከደነጾር 428.50 2 ዜና.36:10
ተማረከ እስራኤልም
በባቢሎን ግዞት ስር ዋለች
ሠንጠረዥ-1.3 ከሰለሞን መቅደስ ምስረታ እስከ ባቢሎን ግዞት (2 ዜና መዋዕል)

ሰንጠረዥ 1.3 የሰለሞን መቅደስ ከተመሰረተበት ጊዜ ጀምሮ እስራኤላውያን በባቢሎን ንጉስ ተማርከው
እስከተወሰዱበት ድረስ ያለው ጊዜ 428.5 ዓመታት (428 ዓመት ከ 6 ወር) መሆኑን በትንታኔ ያሳያል፡፡
መረጃውን በማጣቀሻው (Reference) ኮለም ላይ ለመዘርዘር እንደሞከርኩት ከ 2 ዜና መዋዕል መጽሐፍ ላይ
ያገኙታል፡፡ ስሌቱን የሰራሁበትን ቀመር እንደሚከተለው ላቀርበው ሞክሪያለው፡፡

ከ 2 ዜና. 3፡2 ሰለሞን በነገሰ በ 4 ኛው ዓመት መቅደሱን መስራት እንደጀመረ እንገነዘባለን፡፡ ከ 2 ዜና. 9፡30-31 ደግሞ
ሰለሞን 40 ዓመት ነግሶ እንደሞተ እና ልጁ ሮብዓም በእሱ ምትክ እንደነገሰ እንረዳለን፡፡ ስለዚህ መቅደሱ
መሰራት ከተጀመረበት ጊዜ ጀምሮ ሰለሞን እስከሞተበት (ሮብዓም እስከነገሰበት) ጊዜ ድረስ ያለው ጊዜ ብዛት
40-4 = 36 ዓመታት እንደሆኑ እንረዳለን፡፡ ስለዚህ ከመቅደሱ ምስረታ ጀምሮ በባቢሎን ንጉስ እስከተማረኩበት
ጊዜ ድረስ ያለውን ጊዜ ብዛት ለማግኘት ከሰለሞን በኋላ ማለትም ከሮብዓም ጀምሮ እስከተማረኩበት ጊዜ
ድረስ የነገሱትን ነገስታት እያንዳንዳቸው የነገሱበትን ጊዜ በ 36 ላይ ደማምረን የምናገኘው ይሆናል ማለት
ነው፡፡

በመሆኑም ሮብዓም 17 ዓመት ነግሶ ሲሞት አብያ በምትኩ ነገሰ፡፡ አብያም 3 ዓመት በጦርነት 10 ዓመት ደግሞ
በሰላም ነግሶ ሲሞት አሳ በምትኩ ነገሰ፡፡ አሳ 41 ዓመት ነገሶ ሲሞት ኢዮሳፍጥ በምትኩ ነገሰ፡፡ ኢዮሰፍጥ 25
ዓመት ነግሶ ሲሞት ኢዮሆራም በምትኩ ነገሰ፡፡ ኢዮሆራም 8 ዓመት ነግሶ ሲሞት አካዝያስ በምትኩ ነገሰ፡፡
አካዝያስ 1 ዓመት ነግሶ ሲሞት ጎቶልያ በምትኩ ነገሰች፡፡ ጎቶልያ 6 ዓመት ከነገሰች በኋላ በምትኳ ኢዮአስ
ነገሰ፡፡ ኢዮአስ 40 ዓመት ገዝቶ ሲሞት በምትኩ አሜስያስ ነገሰ፡፡ አሜስያስ 29 ዓመት ነግሶ ሲሞተት በምትኩ
ኦዝያን ነገሰ፡፡ ኦዝያን 52 ዓመት ነግሶ ሲሞት በምትኩ ኢዮአታም ነገሰ፡፡ ኢዮአታም 16 ዓመት ነግሶ ሲሞት
በምትኩ አካዝ ነገሰ፡፡ አካዝ 16 ዓመት ነግሶ ሲሞት በምትኩ ሕዝቅያስ ነገሰ፡፡ ሕዝቅያስ 29 ዓመት ነግሶ ሲሞት

15
በምትኩ ምናሴ ነገሰ፡፡ ምናሴ 55 ዓመት ነግሶ ሲሞት በምትኩ አሞን ነገሰ፡፡ አሞን 2 ዓመት ነግሶ ሲሞት
በምትኩ ኢዮስያስ ነገሰ፡፡ ኢዮስያስ 31 ዓመት ነግሶ ሲሞት በምትኩ ኢዮአሐዝ ነገሰ፡፡ ኢዮአሐዝ 3 ወር (0.25
ዓመት) ከነገሰ በኋላ በምትኩ ኢዮአቄም ነገሰ፡፡ ኢዮአቄም 11 ዓመት ከነገሰ በኋላ በምትኩ ዮአኪን ነገሰ፡፡
ዮአኪን 3 ወር (0.25 ዓመት) ከነገሰ በኋላ በባቢሎን ንጉስ በናቡከደነጾር ተማርኮ ተወሰደ፡፡ ከዚህ ጊዜ በኋላ
የእስራኤል ምድር በባቢሎን ግዞት ስር ሆነች፡፡ ስለዚህ የቤተመቅደሱ ስራ ከተጀመረበት ጊዜ ጀምሮ እስራኤል
በባቢሎን ግዞት ስር አስከዋለችበት ጊዜ ድረስ ያለው ዘመን ብዛት 428.5
(36+17+3+10+41+25+8+1+6+40+29+52+16+16+29+55+2+31+0.25+11+0.25=428.5) ዓመታት
ይሆናል ማለት ነው፡፡

እንግዲህ ውድ አንባቢ በዚህ ስሌት መሰረት የመጀመሪያው አዳም ከተፈጠረበት ቀን አንስቶ ሁለተኛው አዳም
(ኢየሱስ ክርስቶስ) እስከተወለደበት ቀን ድረስ ያሉት የዘመናት ብዛት 3969.5 ዓመታት እንደሆኑ እንረዳለን፡፡
ከሉቃ. 3፡23 ጌታ በ 30 ዓመቱ አገልግሎቱን እነደጀመረ ስንረዳ አገልግሎት ከጀመረበት ጊዜ እስከ እርገቱ ድረስ
ያለው ጊዜ መጠን ትክክለኛው ባይታወቅም ከተለያዩ ጥቅሶች 3.5 ዓመታት (3 ዓመት ከ 6 ወር) እነደሚሆን
ይገመታል፡፡ ከዚህ በመነሳት ጌታ በምድር ላይ 33.5 ዓመታት ኖሯል ተብሎ ይታሰባል፡፡ ስለዚህ ከአዳም ጀምሮ
እስከ ጌታ እርገት ድረስ ያሉት ዘመናት ብዛት 3969.5+33.5 = 4003 ዓመታት ናቸው ማለት ነው፡፡

ስለዚህ ውድ አንባቢዬ አንድ ላረጋግጥሎ የምፈልገው ነገር ቢኖር በዚህ ጽሁፍ ላይ ካካተትኳቸው ዘመናት
ውስጥ ጌታ በምድር ላይ ከ 30 ዓመቱ ጀምሮ እስከ እርገቱ ድረስ ካገለገለባቸው ዘመናት ብዛት በቀር ሌሎቹ
በሙሉ ማለትም ከአዳም ጀምሮ ጌታ አገልግሎቱን እስከ ጀመረበት ድረስ ያሉት ዘመናት በግልጽ (100%
Degree of Accuracy) በመጽሐፉ ተቀምጠውልናል፡፡ ነገር ግን ጌታ በምድር ላይ ያገለገለባቸው ዘመናት
መጠን ለምን በመጽሐፉ ውስጥ እንዳልተቀመጠልን ያውቃሉ? ለዚህ ጥያቄ መልሱ ግልጽ ነው፤ ምክኒያቱም
ማቴ. 24፡36 (ስለዛች ቀንና ስለዛች ሰዓት ግን ከአባት ብቻ በቀር የሰማይ መላዕክትም ቢሆኑ ልጅም ቢሆን የሚያውቅ የለም)
ተብሎ የተጻፈው ቃል ይፈጸም ዘንድ ነው፡፡ ይህ ባይሆን ኖሮ ጌታ ካረገ ከ 2000 ዓመታት በኋላ ዳግመኛ
እንደሚመጣ በመጽሐፉ ስለተቀመጠልን ዳግመኛ የመምጫውን ቀንና ሰዓት ማወቅ (መገመት) እንችል ነበር፡፡
በመሆኑም እግዚአብሔር አብ መሲሁ በክብር ዳግመኛ የሚመጣበትን ዘመናት (ዓመታት) እንድናውቅ
በመጽሐፉ ግልጽ አድርጎ አስቀምጦልን ቀንና ሰዐቱን እንድናውቅ (እንድንገምት) ፈቃዱ ስላልሆነ ሁለት
ነገሮችን ብቻ እንዳናውቅ ሚስጥር አደረጋቸው እነዚህም ነገሮች ጌታ የተወለደበት እለት (ቀን) እና
ከተጠመቀበት ቀን ጀምሮ በምድር ላይ ያገለገለባቸው ዓመታት ብዛት ናቸው፡፡ እግዚአብሔር አዋቂ ነው፡፡

ታዲያ እግዚአብሔር በምድር ላይ ወደያዘልን ወደሰባተኛዋ 1000 ዓመት የዕረፍቱ ቀን መቼ እንገባለን ማለት
ነው?

ይህን ጥያቄ ከመመለሴ በፊት ሰባተኛዋን 1000 ዓመታት ከሌሎቹ 6000 ዓመታት የተለየች የሚያደርጋትን
አንድ ነገር ብቻ መጥቀስ እፈልጋለው፡፡ ይህች የመጨረሻዋ አንድ ቀን (1000 ዓመታት) በራዕ. 20 እንደተገለጸው
ሰይጣን ታስሮ ወደ ጥልቁ ተጥሎ የሚቆይባትና የታረደው በግ (ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ) በአካል ማለትም በስጋ
በታላቅ ክብር በዙፋኑ ላይ ሆኖ በምድር ሁሉ ላይ ነግሶ ዓለምን የሚገዛበትና በስጋ ከሰዎች ጋር (ኢማኑኤል፤
ትርጓሜውም እግዚአብሔር ከሰዎች/ከእኛ ጋር) የሚሆንበት ነው፡፡ ወደጥያቄው መልስ ሳመራ ክርስቶስ
በተወለደ ቀን ከአዳም ጀምሮ የሰው ልጅ በምድር ላይ 3969.5 ዓመታትን አስቆጥሯል፡፡ ክርስቶስ ከተወለደበት
ቀን ጀምሮ እስከ አሁን (ግ.አ. ኦገስት 2023 ዓ.ም.) ድረስ ደግሞ የሰው ልጅ በምድር ላይ 2022.5 ዓመቱን
አስቆጥሯል፡፡ ስለዚህ በአጠቃላይ እስከአሁን (ግ.አ. ኦገስት 2023 ዓ.ም.) ድረስ የሰው ልጅ በምድር ላይ 3969.5
+ 2022.5 = 5992 ዓመታትን አስቆጥሯል ማለት ነው፡፡ በመሆኑም ከአዳም ጀምሮ 6000 ዓመታቱ ሊጠናቀቁ
6000 - 5992 = 8 ዓመታት ይቀሩናል ማለት ነው፡፡ ስለዚህ ዛሬ እንደ ግ.አ. ኦገስት 2023 ዓ.ም. ላይ ሆነን

16
ስናሰላው 2023 + 8 = ኦገስት 2031 ሲሆን እንደ ግ.አ 2031 ዓ.ም. አጋማሽ ላይ ይጠናቀቃሉ ማለት ነው፡፡
ከዚህ ስሌት ጌታ እንደ ግ.አ. በ 2031 ዓ.ም. አጋማሽ በኋላ እንደሚመጣ እንረዳለን፡፡ ይህም ማለት ግ.አ.
በ 2031 ዓ.ም. አጋማሽ በሆሴዕ ትንቢት ውጤት ከ 2031 እስከ 2033 ዓ.ም ውስጥ በማረፉ ከሆሴዕ ትንቢትና
ከበለሷ ምሳሌ ትንቢት ጋር ይስማማል ማለት ነው፡፡ አንዳንድ ጠበብቶች የመጨረሻዎቹ ሰባት የመከራ
ዓመታት የሚጀምሩት የሆሴ 2000/የዕብራዊያን 6000 ዓመታት ከተጠናቀቁ በኋላ ነው ብለው ያስባሉ፡፡ ነገር
ግን አሁን በዓለማችን እየሆነ ካለው ነገር አንጻር ሐሳባቸው አያስኬድም፡፡

የሄኖክስ ትንቢት ምን ይላል? (ይሁዳ 1፡14-15)


በመቀጠል ከአዳም ጀምሮ ሰባተኛ የሆነ ሄኖክ ስለጌታ መምጫ ጊዜ የተናገረውን ትንቢት እንቃኛለን፡፡ በቀጥታ
ወደ ትንቢቱ ዝርዝር ከመግባቴ በፊት ስለመጽሐፈ-ሄኖክ ጥቂት ማለት ግድ ይለኛል፡፡ እንደሚታወቀው
መጽሐፈ-ሄኖክ ከመጽሐፍ ቅዱስ ቀኖና ውጪ ነው ተብሎ ስለታሰበ ከመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ እንዲወጣ
ተደርጓል፡፡ በአሁኑ ሰዐት ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ-ክርስቲያን ሰማኒያ አሐዱ (80 አሐዱ) መጽሐፍ
ቅዱስ ውጪ በአለም ላይ በምንም አይነት ቤተ-ክርስቲያን መጽሐፍ ውስጥ የለም፡፡ ነገር ግን ይህ መጽሐፍ ጌታ
ኢየሱስ በምድር ላይ አገልግሎቱን ጨርሶ እስካረገበት ጊዜ ድረስ እና በጌታ መንፈስ ተመርተው አዲስ ኪዳንን
የጻፉልን የጌታ ሐዋርያት በምድር ላይ በስጋ እስከነበሩበት ጊዜ ድረስ መጽሐፈ-ሄኖክ በአይሁድ መጽሐፍ ቅዱስ
ቀኖና ውስጥ እንደነበር እና በእግዚአብሔር መንፈስ ምሪት እንደተጻፈ መጽሐፈ-ሄኖክን ባገለለው በአሁኑ ጊዜ
ፕሮቴስታንትን ጨምሮ ዓለም በሚጠቀምበት በ 66 ቱ (በ 66 አሐዱ) የመጽሐፍ ቅዱስ ቀኖና ውስጥ ያለው
የእግዚያብሔር ቃል ራሱ ይመሰክርልናል፡፡

መቼ ከመጽሐፍ ቅዱስ ቀኖና እንዲወጣ ተደረገ?

የወጣበት እውነተኛ ምክኒያት ምንድነው?

የእግዚያብሔር ቃል አሁን ባለው የ 66 ቱ መጽሐፍ ውስጥ ስለመጽሐፈ-ሄኖክ ምን ብሎ ይመሰክራል?

በዚህ የመጨረሻ ዘመን ጊዜ በአለም ላይ ታዋቂ የመጽሐፍ ቅዱስ ጠበብቶች (Bible Scholars) እና የዘመነ-
ፍጻሜ ጥናት ጠበብቶች (Eschatologists) መጽሐፈ-ሄኖክ ከሐዋርያው ዮሐንስ በቀር ሌሎቹ አዲስ ኪዳንን
የጻፉልን ሐዋርያት በምድር ላይ በስጋ እስከነበሩበት ጊዜ ድረስ በአይሁድ መጽሐፍ ቅዱስ ቀኖና ውስጥ
እንደነበር እና ከዛ ጊዜ በኋላ ከአይሁድ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ እንደወጣ አስረግጠው ይናገራሉ፡፡ እኒሁ
ጠበብቶች የወጣበትን እውነተኛ ምክኒያት ሲገልፁ አብዛኛው የመጽሐፈ-ሄኖክ ይዘት ስለጌታ ኢየሱስ
በተለይም ስለዳግም ምጻቱ እንዲሁም አይሁዳውያን የካዱትን ከሞት መነሳቱን እና ማረጉን በመመስከር
የሚተነብይ በመሆኑ ነው ይላሉ፡፡ በመሆኑም በክርስትና ዘመን የክርስቲያን መጽሐፍ ቅዱስ በሚቀናጅበት
ወቅት የክርስቲያን መጽሐፍ ቅዱስ ብሉይ ኪዳን ክፍል ሙሉ ለሙሉ በወቅቱ ከነበረው (መጽሐፈ-ሄኖክን
ካስወገደው) ከአይሁድ መጽሐፍ ቅዱስ በመወሰዱ በወቅቱ የነበረው የአይሁድ መጽሐፍ ደግሞ መጽሐፈ-
ሄኖክን ስለማያካትት ነው ይላሉ፡፡ በተጨማሪም እኒህ ጠበብቶች የመጽሐፈ-ሄኖክ ከመጽሐፍ ቅዱስ ቀኖና
ውስጥ እንዲወጣ ሀሳቡ የመነጨው ከክርስቶስ ተቃዋሚ መንፈስ እንደሆነ ግምታቸውን ያስቀምጣሉ፡፡

ስለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤ/ክርስቲያን እግዚአብሔር ይባረክ

17
በአሁኑ ሰዐት የመጽሐፈ-ሄኖክን ሙሉ ይዘት በክብር ይዛ ያቆየችው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ-
ክርስቲያን እንደሆነችና ሙሉ-ለሙሉ የመጽሐፉ ይዘት አሁን ካለው የ 66 ቱ መጽሐፍ ጋር የሚጣጣም እንጂ
በአንዲት ቦታ እንኳን አንደማይፃረር እኚሁ ጠበብቶች ይገልጻሉ፡፡ ከዚህም በተጨማሪ እንደ ግ.አ. በ 1947
እና በ 1956 ዓ.ም. መካከል በሰሜን-ምዕራብ ሙት ባህር ዳርቻ (Dead Sea Shore) ኪርበት ኩምራን
(Khirbet Qumran) በሚባል አካባቢ በሚገኙ አስራሀንድ (11) ዋሻዎች ውስጥ በተገኙ በዕብራኢስጥ እና
በአራማይክ ቋንቋ የተጻፉ የሙት ባህር ጥቅሎች (Dead Sea Scrolls) ውስጥ መጽሐፈ-ሄኖክ እንዳለበት
ተረጋግጧል፡፡ በዚህ ጥቅል ውስጥ ያለው የሄኖክ መጽሐፍ ምንም እንኳን ጥቂት ክፍሉ በስብሶ በመበላሸቱ
ጥቂት ፅሁፉ የማይታይ ቢሆንም የሚታየው ክፍል ወደ እንግሊዝኛ ቋንቋ ተተርጉሞ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ
ተዋህዶ ቤተ-ክርስቲያን ከሚገኘው የሄኖክ መጽሐፍ ጋር ተነጻጽሮ ሙሉ ለሙሉ የሚጣጣም እንጂ የማይጻረር
ሆኖ ተገኝቷል፡፡ በመሆኑም በአሁኑ ጊዜ በዓለም ላይ አሉ የተባሉ ታዋቂ የመጽሐፍ ቅዱስ ጠበብቶች (Bible
Scholars) ከመጽሐፉ ሲያስተምሩ እየተስተዋሉ ነው፡፡

በመጨረሻም እኔ ራሴ በግሌ እግዚአብሔር በረዳኝ መጠን መጽሐፈ-ሄኖክን በተደጋጋሚ አጥንቼ የ 66 ቱ


መጽሐፍን የሚጻረር ነገር አላገኘሁበትም፡፡ ይልቁንም የ 66 ቱ መጽሐፍ ቅዱስ በብዙ ቦታ ላይ የመጽሐፈ-
ሄኖክን ትክክለኛነት ሲመሰክር አግኝቼዋለሁ፡፡ የመጽሐፈ-ሄኖክን ትክክለኛነት ከሚመሰክሩ በ 66 ቱ መጽሐፍት
ውስጥ ከሚገኙ ብዙ ጥቅሶች ውስጥ ሁለቱን ማለትም ይሁ. 1፡14-15 እና ማቴ. 22፡29-30 ማቅረብ በቂ ነው ብዬ
አስባለሁ፡፡

ይሁ. 1፡14-15 አ.መ.ት. “14 ከአዳም ጀምሮ ሰባተኛ የሆነው ሄኖክ ስለ እነዚህ ሰዎች እንዲህ ሲል ተንብዮአል፤ “እነሆ ጌታ ከእልፍ
አእላፋት ቅዱሳኑ ጋር ይመጣል፡፡ 15 ይህም በሰው ሁሉ ላይ ለመፍረድ እንዲሁም ዐመፀኞችን ሁሉ በክፋት መንገድ በሰሩት የዐመፅ
ስራና በክፋት በእርሱ ላይ ስለተናገሩት የስድብ ቃል ሁሉ አጥፊነታቸውን ይፋ ለማድረግ ነው“፡፡”

ታዲያ ሄኖክ በ 66 ቱ መጽሐፍት ውስጥ የት ጋር ነው ይህን ትንቢት የተናገረው? ይህን ጥቅስ የጻፈልን ይሁዳ
ከየት አምጥቶ ጻፈው?

የ 66 ቱን መጽሐፍ ከዘ-ፍጥረት እስከ ዮሐንስ ራዕይ ድረስ ያጠና ምንም አይነት ሰው ቢኖር ይህን ቃል በዚህ
መጽሐፍ ውስጥ አይቻለሁ የሚል የለም አይኖርምም፡፡ ስለዚህ በ 66 ቱ መጽሐፍ ላይ የምናገኛቸው ነብያት
ሁሉ የተነበዩዋቸውን ትንቢቶች ሁሉ በራሳቸው መጽሐፍ እንደጻፉልን ሁሉ ሄኖክም ይህን ትንቢት የጻፈበት
የራሱ መጽሐፍ አለ ማለት ነው፡፡ ስለሆነም የዚህን ትንቢት ቃል የምናገኝበት መጽሐፍ ቢኖር መጽሐፈ-ሄኖክ
ብቻ ነው፡፡ እንደሚከተለው አቅርቤዋለሁ፡-

ሄኖ. 1፡9 “9 ፍርድን ያደርግላቸው ዘንድ እነሆ ከብዙ ቅዱሳን ጋር ይመጣል፤ ዝንጉዎችንም ያጠፋቸዋል፤ ኃጥኣንና ዝንጉዎች
ፈጽመው በእርሱ ላይ ስላደረጉት ሁሉ ስጋዊውን ሁሉ ይወቅሳል፡፡“

ሌላው በመጽሐፈ-ሄኖክ ብቻ የሚገኘው ቃል በማቴዎስ 22 በሙታን ትንሳኤ የማያምኑት ሰዱቀዊያን


ስለሙታን ትንሳኤ ጌታን በጠየቁት ጊዜ ጌታ በማቴ. 22፡29-30 የሰጠው መልስ ነው፡፡

ማቴ. 22፡29-30 አ.መ.ት. “29 ኢየሱስም አንዲህ ብሎ መለሰ፤ “ቅዱሳት መጻሕፍትንና የእግዚአብሔርን ኀይል ስለማታውቁ
ትስታላችሁ፤ 30 ከትንሣኤ በኋላ ሰዎች እንደ ሰማይ መላእክት ይሆናሉ እንጂ አያገቡም፤ አይጋቡም“፡፡“

“ከትንሣኤ በኋላ ሰዎች እንደ ሰማይ መላእክት ይሆናሉ” የሚለው ቃል በእንግሊዘኛው NIV ትርጉም “At the
resurrection people will be like the angeles in heaven“ ተብሎ ነው የተጻፈው፡፡ ስለዚህ የአማርኛው ትርጉም
“ከትንሣኤ በኋላ ሰዎች በሰማይ እንደ መላእክት ይሆናሉ” ተብሎ መስተካከል አለበት ማለት ነው፡፡ እንግዲህ ጌታ
“ቅዱሳት መጻሕፍትን ስለማታውቁ ትስታላችሁ” ብሎ ባለ ጊዜ ከዚህ ዐረፍተ-ነገር በኋላ የተናገረው ቃል ማለትም

18
“ከትንሣኤ በኋላ ሰዎች በሰማይ እንደ መላእክት ይሆናሉ” የሚለው ቃል በግልጽ (Literally) በመጻሕፍት የተጻፈ
መሆኑን እንረዳለን፡፡ በቁ. 32 ላይ እግዚአብሔር የአብርሀም፣ የይስሐቅ፣ እና የያዕቆብ አምላክ ነኝ ብሎ
በማለቱ እግዚአብሔር የሕያዋን እንጂ የሙታን አምላክ አለመሆኑን የሚያመለክት ቃል መሆኑን ገለፀላቸው
እንጂ “ከትንሣኤ በኋላ ሰዎች በሰማይ እንደ መላእክት ይሆናሉ” የሚለውን ቃል እንደሚያመለክት አልገለጸላቸውም፡፡
ስለዚህ “ቅዱሳት መጻሕፍትን ስለማታውቁ ትስታላችሁ፤ ከትንሣኤ በኋላ ሰዎች በሰማይ እንደ መላእክት ይሆናሉ” በማለቱ
ከትንሣኤ በኋላ ሰዎች በሰማይ እንደ መላዕክት እንደሚሆኑ የሚናገር ቢያንስ አንድ መጽሐፍ እንዳለ
እንገነዘባለን፡፡ ነገር ግን በ 66 ቱ መጻሕፍት ውስጥ ከዘ-ፍጥረት እስከ ራዕይ ድረስ በአንድም ስፍራ “ከትንሣኤ በኋላ
ሰዎች በሰማይ እንደ መላእክት ይሆናሉ” ተብሎ የተጻፈ ቃል አናገኝም፡፡ ይሁንና ይህን ቃል በመጽሐፈ-ሄኖክ
ውስጥሄኖ.13፡29-33 ላይ በግልፅ ተጽፎ እናገኘዋለን፡፡

ሄኖ.13፡29-33 “29 በእነዚያም ወራቶች ምድር አደራዋን ትመልሳለች፤ መቃብርም የተቀበለችውን አደራ ትመልሳለች፡፡ 30 ሞትም
የሚከፍለውን ይመልሳል፤ እነርሱም ይድኑ ዘንድ ቀንዋ ቀርባለችና ጻድቃንንና ቅዱሳንን ከእነርሱ ይመርጣል፡፡ 31 አስታራቂውም
በእነዚያ ወራቶች በዙፋኑ ይቀመጣል፤ የጥበብንም ምስጢር ሁሉ ከአንደበቱ ያወጣል የመናፍስት ጌታ ሰጥቶ አክብሮታልና፡፡ 32
በእነዚያ ወራቶች ተራሮች እንደጊደሮች ይዘፍናሉ፤ ኮረብቶችም ወተት እንደጠገቡ ጠቦቶች ይዘላሉ፡፡ 33 በእነዚያም ወራቶች
አስታራቂው ተነሥቷልና ሁሉም በሰማይ እንደ መላእክት ይሆናሉ፡፡“

እንግዲህ ውድ አንባቢ ጌታ ኢየሱስ እራሱ በትንሹ በዚህ መልኩ ስለ መጽሐፈ-ሄኖክ ትክክለኛነት ሲመሰክር
እናስተውላለን፡፡ ስለ ሄኖክ መጽሐፍ ትክክለኛነት በዚህ መልኩ በሰፊው ለማብራራት የሞከርኩት ያለምክንያት
አይደለም፡፡ ስለዘመን ፍጻሜ (Eschatology) በሌሎች መጽሐፍት (በ 66 ቱ መጽሐፍት) ከተጻፈው ይልቅ
በሄኖክ መጽሐፍ በግልፅ እና በሰፊው ስለተጻፈልን ነው፡፡ በመሆኑም ዘመናትን የመረዳት ጥልቅ ፍላጎት ካለዎት
ይህን መጽሐፍ ከ 66 ቱ መጻሕፍት ጋር በማጣቀስ ደጋግመው እንዲያጠኑት እጋብዞታለሁ፡፡

የሄኖክን መጽሐፍ እንዳነሳ ያስገደደኝ ዋንኛ ነጥብ ምንድነው?

ስለዚህ መጽሐፍ ትክክለኛነት የሚመሰክሩ በጣም ብዙ እጅግ ብዙ ጥቅሶችን ከ 66 ቱ መጻሕፍት ውስጥ


አውጣጥቶ መናገር ቢቻልም ከጊዜ አንጻር ለጊዜው ይህ በቂ ነው ብዬ ስላሰብኩ ወደ ዋንኛው ነጥብ መሄድን
መርጫለሁ፡፡ የሄኖክን መጽሐፍ እንዳነሳ ያስገደደኝ ዋንኛ ነጥብ እግዚአብሔር በምድር ላይ ለሰው ልጅ የያዘው
የ 7000 ዓመታት አጀንዳ (ዕብ. 3፡7-19 እና ዕብ. 4፡1-11) በሄኖክ መጽሐፍ ውስጥ በግልጽና ቃል በቃል (Literally)
የተጻፈልን ስለሆነ ነው፡፡

ይህም ቃል የሚገኘው በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን (80 አሐዱ) መጽሐፍ ቅዱስ መሰረት
በመጽሐፈ ሄኖክ ምዕራፍ 35 ውስጥ ሲሆን በሙሉው ምዕራፍ ማለትም ሄኖ. 35፡1-36 ውስጥ ነው፡፡
ዘመናቱንም የገለጸበት መንገድ 700 ዓመታትን እንደ አንድ ሱባዔ በመውሰድ ከአዳም ጀምሮ በእያንዳንዱ
ሱባዔ የሚከሰቱትን መጽሐፍ ቅዱሳዊ ክስተቶች በመተንበይና በአስረኛዪቱ (በ 10 ኛዪቱ) ሱባዔ በሰባተኛዪቱ
ክፍል አሮጌው ሰማይ እና አሮጌዋ ምድር አልፈው አዲስ ሰማይና አዲስ ምድር እንደሚገለጡ በመግለጽ ነው፡፡
ማለትም በሄኖ.35፡21-36 ውስጥ ሄኖክ ከተወለደባት የመጀመሪያዪቱ ሱባዔ (የመጀመሪያዪቱ 700 ዓመታት)
ጀምሮ እስከ ሰባተኛዪቱ ሱባዔ (ከአዳም ጀምሮ እስከ 4900 ዓመታት) ድረስ በእያንዳንዷ ሱባዔ (በእያንዳንዷ
700 ዓመታት) ውስጥ የሚከሰቱትን መጽሐፍ ቅዱሳዊና አለም አቀፋዊ ክስተቶችን በመተንበይ ሲሆን በሄኖ.35፡
1-20 ባለው ክፍል ደግሞ ከስምንተኛዪቱ ሱባዔ ጀምሮ እስከ ዓስረኛዪቱ ሱባዔ (ከአዳም ጀምሮ ከ 4901 ኛዋ
ዓመት እስከ 7000 ኛዋ ዓመት) ድረስ በእያነዳንዷ ሱባዔ ውስጥ የሚከሰቱትን መጽሐፍ ቅዱሳዊ እና አለም
አቀፋዊ ክስተቶችን በመተንበይ ነው የሚያጠናቅቀው፡፡ ስለዚህ ውድ አንባቢ በዚህ መጽሐፍ በዚህ ምዕራፍ
ውስጥ የተጻፈውን ቃል እውነተኛነት ከዚህ በፊት በሰንጠረዦች ውስጥ በትንታኔ ያስቀመጥኳቸውን ዘመናት
በመጠቀም ከአዳም ጀምሮ እስከ አሁኗ ጊዜ (ከአዳም እስከ ግ.አ. 2023 ዓ.ም.) ድረስ በእያንዳንዷ ሱባዔ

19
(በእያንዳንዷ 700 ዓመታት) ውስጥ ሄኖክ የተነበያቸውን ትንቢቶች በ 66 ቱ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ከተጻፉ
(ከተፈጸሙ) ትንቢቶችና ክስተቶች እንዲሁም በዓለም አቀፍ ደረጃ ከጌታ እርገት ጀምሮ እስከአሁን (ግ.አ.
2023 ዓ.ም.) ድረስ በታሪክ ከተጻፉ ክስተቶች ጋር በማነጻጸር ማረጋገጥ ይቻላል፡፡ ከጊዜ አንጻር በዓስሩም ሱባዔ
ውስጥ የተከሰቱትን የሄኖክ ትንቢቶች ማብራራት ስለሚከብድ በዘፈቀደ በመረጥኳቸው ናሙናዎች (Random
Samples) በ 3 ኛ፣ በ 4 ኛ፣ እና በ 6 ኛ ሱባዔዎች ውስጥ ያሉትን የሄኖክ ትንቢቶች በ 66 ቱ መጽሐፍ ቅዱስ
ውስጥ ከተፈጸሙ ትንቢቶች ጋር በማነጻጸር ለማብራራት እሞክራለሁ፡፡ በመጀመሪያ ግን በሄኖክ መጽሐፍ
አንድ ሱባዔ 700 ዓመታት መሆናቸውን ለማሳየት እሞክራለሁ፡፡

ሄኖ. 35፡21 “21 ሄኖክም ከመጻሕፍት ይናገር ጀመረ፤ እኔ ሰባተኛው ትውልድ በመጀመሪያቱ ሱባዔ ተወለድሁ፡፡”

ከላይ ከጥቅሱ እነደምንመለከተው ሄኖክ ሰባተኛው ትውልድ እንደሆነ እና በመጀመሪያዋ ሱባዔ እንደተወለደ
እንገነዘባለን፡፡ በሄኖክ መጽሐፍ ውስጥ አንድ ሱባዔ ምን ያህል ዓመታት ናቸው የሚለውን ለማወቅ በመጽሐፍ
ቅዱስ ውስጥ “ሱባዔ” ምን ማለት እንደሆነ እና ከአዳም ጀምሮ ሄኖክ የተወለደባትን ዓመት ማወቅ
ይጠበቅብናል፡፡ ከመጽሐፍ ቅዱስ በተለያየ ቦታ ላይ “ሱባዔ” ማለት ሰባት (7) የጊዜ መለኪያን (7 units of
time) ማለት መሆኑን እንረዳለን፡፡ ማለትም “አንድ ሱባዔ” እንደ አገባቡ (contextually) 7 ሰዓትን፣ 7
ቀናትን፣ 7 ዓመታትን፣ 70 ዓመታትን፣ 700 ዓመታትን፣ 7000 ዓመታትን ወዘተ… እንደሚያመለክት
አንረዳለን፡፡ ለምሳሌ በትንቢተ-ዳንኤል ሰዋሰዋዊ አገባብ (Grammatical context) መሰረት “አንድ ሱባዔ”
ሰባት ዓመታት እንደሆኑ እናውቃለን፡፡ በሄኖክ መጽሐፍ ሰዋሰዋዊ አገባብ (Grammatical context) መሰረት
“አንድ ሱበዔ” ስንት ዓመታት እንደሆኑ ለማወቅ ከአዳም ጀምሮ ሄኖክ መቼ እንደተወለደ ማወቅ
ይጠበቅብናል፡፡ ከዚህ በፊት ባስቀመጥኳቸው የዘመናት ትንታኔ ሠንጠረዦች (ሠንጠረዥ-1.1) ውስጥ ሄኖክ
ከአዳም ጀምሮ 622 ኛዋ ዓመት ላይ እንደተወለደ እንረዳለን፡፡ በሄኖ. 35፡21 ደግሞ ሄኖክ በመጀመሪያዪቱ ሱባዔ
እንደተወለደ ያስረዳናል፡፡ በመሆኑም እንደሄኖክ መጽሐፍ ከአዳም ጀምሮ 622 ኛዋ ዓመት የመጀመሪያዪቱ
ሱባዔ ውስጥ እንደሆነች እንገነዘባለን ማለት ነው፡፡ ከላይ ከዘረዘርኳቸው የሱባዔ ትርጉሞች (7 ሰዓት፣ 7
ቀናት፣ 7 ዓመታት፣ 70 ዓመታት፣ 700 ዓመታት፣ 7000 ዓመታት) ውስጥ ለ 622 ዓመታት የሚቀርበው (The
nearest to 622 years) 700 ዓመታት መሆኑ ግልፅ ነው፡፡ ስለዚህ በሄኖክ መጽሐፍ ሰዋሰዋዊ አገባብ
የመጀመሪያዋ ሱባዔ የመጀመሪያዋ 700 ዓመታት እንደሆነች መረዳት አያዳግትም፡፡ ማለትም በሄኖክ መጽሐፍ
ሰዋሰዋዊ አገባብ (Grammatical context) “አንድ ሱበዔ” 700 ዓመታት ናቸው ማለት ነው፡፡

እንግዲህ በሄኖክ መጽሐፍ ሰዋሰዋዊ አገባብ መሰረት አንድ ሱባዔ 700 ዓመታት እንደሆኑ ከተረዳን ከላይ
ለመጥቀስ እንደሞከርኩት ሶስት ሱባዔዎችን ማለትም 3 ኛ፣ 4 ኛ፣ እና 6 ኛ ሱባዔዎች እንደናሙና በመውሰድ
በነዚህ ሱባዔዎች ውስጥ ሄኖክ የተነበያቸውን ትንቢቶች መፈጸምና አለመፈጸማቸውን ከ 66 ቱ መጽሐፍ
ቅዱስ ጋር በማነጻጸር እናጣራለን፡፡

አዳም 700 1400 2100 2800 3500 4200

700 700 700 700 700 700

1 ኛ ሱባዔ 2 ኛ ሱባዔ 3 ኛ ሱባዔ 4 ኛ ሱባዔ 5 ኛ ሱባዔ 6 ኛ ሱባዔ

20
ከላይ ከዲያግራሙ እንደምንመለከተው 3 ኛው ሱባዔ ከአዳም ጀምሮ በ 1401 ኛ እና በ 2100 ኛው ዓመታት
ውስጥ ያርፋል፡፡ 4 ኛው ሱባዔ ደግሞ በ 2101 ኛው እና በ 2800 ኛው ዓመታት ውስጥ ያርፋል፡፡ 6 ኛው ሱባዔ
ደግሞ በ 3501 ኛው እና በ 4200 ኛው ዓመታት ውስጥ ያርፋል፡፡ እንግዲህ ሄኖክ በ 3 ኛው፣ በ 4 ኛው፣ እና
በ 6 ኛው ሱባዔ ይፈጸማሉ ብሎ የተነበያቸው ትንቢቶች በሙሉ ከአዳም ጀምሮ ሱባዔዎቹ በሚያርፉበት
ዓመታት ውስጥ መፈጸም አለባቸው ማለት ነው፡፡ በ 3 ቱ ሱባዔዎች እንደሚፈጸሙ ሄኖክ የተነበያቸው
ትንቢቶች እያንደንዳቸው በየዘመናቸው በ 66 ቱ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ መፈጸማቸውን እናጣራ፡፡

ሦስተኛዪቱ ሱባዔ (ከ 1401-2100)

ሄኖ. 35፡25 “25 ከዚህም በኋላ በሦስተኛዪቱ ሱባዔ በመጨረሻዋ ሰው ለእወነተኛ ፍርድ ተክል ይመረጣል፤ ከእርሱም በኋላ የዘላለም
ጽድቅና ርትዕ ተክል ይወጣል፡፡”

ሦስተኛይቱ ሱባዔ ከአዳም ጀምሮ በ 1401 ኛ እና በ 2100 ኛው ዓመታት ውስጥ እንደምታርፍ አስተውለናል፡፡
ከዘመናት ትንታኔ ሰንጠረዦች ውስጥ በነዚህ ዓመታት ውስጥ የተከሰቱ ከሄኖክ ትንቢት ጋር የሚሄዱ ክስተቶች
ካሉ እንመልከት፡፡ በሠንጠረዥ-1.2 ውስጥ ከአዳም ጀምሮ በ 1948 አብራም ተወለደ በተወለደ በ 75 ዓመቱ
ማለትም ከአዳም ጀምሮ በ 2023 እግዚአብሔር አብራምን እኔ ወደማሳይህ ምድር ውጣ በማለት “ለእውነተኛ
ፍርድ ተክል” ሲመርጠው እንመለከታለን፡፡ ከአብርሃምም በኋላ ጌታ ኢየሱስን የሚያስገኝ ዘር የሆነው ይስሃቅ
“የዘላለም ጽድቅና ርትዕ ተክል” ሆኖ ከአዳም ጀምሮ “ከእርሱም በኋላ የዘላለም ጽድቅና ርትዕ ተክል ይወጣል፡፡” እንደሚል
በ 2048 ሲወለድ እናስተውላለን፡፡ እንግዲህ ከአዳም ጀምሮ አብራም የተመረጠበትን 2023 እና ይስሃቅ
የተወለደበትን 2048 ስንመለከት በ 3 ኛዪቱ ሱባዔ ማለትም ከአዳም ጀምሮ በ 1401 ኛ እና በ 2100 ኛው
ዓመታት ውስጥ በመጨረሻዋ በ 2000 ኛው እና 2100 ኛው ዓመታት ውስጥ (2000<2023<2048<2100)
ሲፈጸሙ እናስተውላለን፡፡

አራተኛዪቱ ሱባዔ (ከ 2101-2800)

ሄኖ. 35፡26 “26 ከዚህም በኋላ በአራተኛዪቱ ሱባዔ በመጨረሻዋ የቅዱሳንና የጻድቃን ራእያት ይገለጣሉ፡፡ ሥርዐትና ቅጥርም ለልጅ
ልጅ ዘመን ይሰራላቸዋል፡፡”

በአራተኛዪቱ ሱባዔ (ከአዳም ጀምሮ ከ 2101 እስከ 2800) “የቅዱሳንና የጻድቃን ራእያት ይገለጣሉ፡፡ ሥርዐትና ቅጥርም
ለልጅ ልጅ ዘመን ይሰራላቸዋል፡፡” ይለናል የሄኖክ መጽሐፍ፡፡ እኚህ ሥርዐትና ቅጥር ለልጅ ልጅ ዘመን የተሰራላቸው
የቅዱሳንና የጻድቃን ራእያት እነማን ናቸው? መልሱ ግልጽ ነው፤ የእውነተኛ ፍርድ ተክል ከሆነው ከአብርሀም
ዘር ከወጣው ከዘላለሙ ጽድቅና ርትዕ ተክል (ከይስሀቅ) የወጡት አስራሁለቱ የያዕቆብ ነገዶች እስራኤላውያን
ናቸው፡፡ እንዴት ተገለጡ? መቼስ ተገለጡ? እግዚአብሔር ለሙሴ በሀያሉ ክንዴ ሕዝቤን ከግብጽ ምድር
አውጥቼ ለአባቶቻቸው ለልጆቻችሁ አወርሳቸዋለሁ ብዬ የማልኩላቸውን የተስፋይቱን ምድር በማውረስ
ስሜን ለአለም አሳውቃልው ባለው መሰረት እስራኤላውያን ግብጻውያንን፣ አማሌቃውያንን፣ ኢያቡሳዊያንን፣
ከናናዊያንን፣ እና የመሳሰሉትን በእግዚአብሔር ሀያል ክንድ ድል አድርገው የተስፋይቱን ምድር በወረሱ ጊዜ
በዓለም መንግስታት ዘንድ ታወቁ (ተገለጡ)፤ እግዚአብሔርም ሀያል ስሙን ለዓለም አሳወቀ፡፡ መቼ ተገለጡ
ለሚለው ጥያቄ የዘመናት ትንታኔ ሠንጠረዥ-1 ይመልከቱ፡፡ ሠንጠረዡ እንደሚያመለክተን ያዕቆብና ዔሳው
በተወለዱ ከ 430 ዓመታት በኋላ ማለትም ከአዳም ጀምሮ በ 2538 ምድሪቱን እንደወረሱ እንገነዘባለን፡፡ በሄኖክ
መጽሐፍ አራተኛዪቱ ሱባዔ ከአዳም ጀምሮ ከ 2101 እስከ 2800 ዓመታት ውስጥ ናት ካልን ከአዳም ጀምሮ
2538 በአራተኛዪቱ ሱባዔ ውስጥ (2101<2538<2800) መሆኗን መረዳት አያዳግትም፡፡

ስድስተኛዪቱ ሱባዔ (ከ 3501-4200)

21
ሄኖ.35፡28-29 “28 ከዚህም በኋላ በስድስተኛዪቱ ሱባዔ በእርሷ የሚኖሩ ሰዎች ሁሉ ደንቆሮዎች ናቸው፤ የሁሉም ልቡናቸው
ከጥበብ ይለያል፤ በእርሷም ሰው ያርጋል፡፡ 29 በመጨረሻዋም ቤተ-መንግስቱ በእሳት ይቃጠላል፤ የተመረጠው የመንግስት ወገን
ሁሉም በእርሷ ይበተናሉ፡፡”

በስድስተኛዪቱ ሱባዔ (ከአዳም ጀምሮ ከ 3501 እስከ 4200) “በእርሷ የሚኖሩ ሰዎች ሁሉ ደንቆሮዎች ናቸው፤
በእርሷም ሰው ያርጋል፡፡ በመጨረሻዋም ቤተ-መንግስቱ በእሳት ይቃጠላል፤ የተመረጠው የመንግስት ወገን ሁሉም በእርሷ
በማለት ሄኖክ በመጽሐፉ ትንቢትን ይናገራል፡፡ ይህን ትንቢት የተፈጸመበትን ጊዜ ከ 66 ቱ መጽሐፍ
ይበተናሉ፡፡”
ቅዱስ ለይቶ ለማውጣት ከሠንጠረዥ-1 ጌታ ኢየሱስ ያረገበትን ጊዜ እና በ 70 AD የሮም ወታደሮች ቤተ-
መቅደሱን ሲያቃጥሉ እስራኤላውያን የተበተኑበትን ጊዜ ማስላት በቂ ነው፡፡ ሠንጠረዥ-1 እንደሚያሳየን ጌታ
ኢየሱስ ከአዳም ጀምሮ በ 4003 እንዳረገ እንረዳለን፡፡ ታሪክ (World History) እንዳስረዳን ደግሞ ሁለተኛው
ቤተ-መቅደስ ከክርስቶስ ጀምሮ በ 70 AD ተቃጠለ ካልን ከአዳም ጀምሮ ደግሞ በ 4003 + (70-33) = በ 4040
ተቃጠለ ማለት እንችላለን፡፡ እንግዲህ ጌታ (ሰው) ያረገበት ቀን ከአዳም ጀምሮ 4003 እና ቤተ-መቅደሱ (ቤተ-
መንግስቱ) የተቃጠለበት ቀን 4040 ከአዳም ጀምሮ በ 3500 አና በ 4200 ውስጥ (3500<4003<4040<4200)
ስለሆኑ የሄኖክ ትንቢት በስድስተኛዪቱ ሱባዔ ውስጥ እንደተፈጸመ እንረዳለን፡፡

እንግዲህ ውድ አንባቢ ይህን ያህል ሦስት የሄኖክ ሱባዔዎች በዘፈቀደ ናሙና (Random Samples) ወስጄ
ትንቢቶቹ በ 66 ቱ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ መፈጸማቸውን ካሳየሁ እርሶ ደግሞ የናሙናው መጠን (Sample
Size) በቂ አይደለም ብለው ካሰቡ ከሰባተኛው ሱባዔ ጀምረው እስከ አሁን (እነደ ግ.አ. 2023 ዓ.ም) ድረስ
በአለም ታሪክ ከተፈጸሙ ትንቢቶች (ክስተቶች) ጋር በማነጻጸር የትንቢቱን እውነተኛነት ማረጋገጥ ይችላሉ፡፡
በእኔ በኩል በግሌ ከአንደኛ አስከ ስምንተኛው ሱባዔ ድረስ ከ 66 ቱ መጽሐፍ ቅዱስና ከአለም ታሪክ (World
History) ጋር አመሳክሬ በማጥናት የትንቢቱን እውነተኛነት በሙሉ ልብ ስለተረዳሁ እግዚያብሔር ለሰው ልጅ
ከአዳም ጀምሮ በምድር ላይ የያዘው ጊዜ 7000 ዓመታት ብቻ ናቸው ብዬ በ 100% ልበ-ሙሉነት (100%
Degree of Accuracy) አረጋግጫለሁ፡፡ ስለዚህ አሮጌው ሰማይና አሮጌው ምድር አልፈው አዲሱ ሰማይና
አዲሲቱ ምድር ሊገለጡ እና ነጩ ዙፋን ሊዘረጋ ቢበዛ 1010 ዓመታት ይቀሩናል ማለት ነው (እንደ ግ.አ 2023
ዓ.ም ላይ ሆነን ስናሰላው)፡፡ ከነኚህ 1010 ዓመታት ውስጥ 1000 ዓመታቱ አሁን በምድር ላይ እየገዛ ያለው
የሰይጣን መንግስት (ስርዐት) ተደምስሶ የጌታ ኢየሱስ መንግስት በአካል ተገልጦ የሚነግስበት እንደሆነ
እናውቃለን፡፡ ስለዚህ ጌታ የሚመጣበትን ቀንና ሰዓት አላውቅም ነገር ግን አሁን ያለው የግሪጎሪያን አቆጣጠር
እና ጌታ ኢየሱስ በምድር ላይ ያገለገለበት 3.5 ዓመታት ትክክለኛነት (Degree of Accuracy) ላይ ተሞርክዤ
ጌታ እንደ ግ.አ. ከ 2031 እስከ 2033 ዓ.ም. ድረስ በታላቅ ክብር ይመጣል ብዬ በድፍረት እናገራለሁ፡፡

እንደዚህ በድፍረት ቀንና ሰዐቱን ሳይሆን ዘመናቱን አስልቼ እንድናገር ያደረገኝ ምንድነው? መልሱ ግልጽና
ግለጽ ነው፡፡ የፍጥረታቱን ሁሉ መጨረሻ ከመጀመሪያው ማሳወቅ ልማዱ የሆነው የአብርሀም፣ የይስሀቅ፣ እና
የያዕቆብ አምላክ የሆነው እግዚያብሔር ዓለምንና በውስጡ ያሉትን ሁሉ በፈጠረ ጊዜ መጨረሻቸውን
ከመጀመሪያው በማይሻረው ቃሉ ግልጽ አድርጎ አስቀምጦታል፡፡ በተጨማሪም፣ በዚህ ድምዳሜ ላይ
እንድደርስ ያደረገኝ አንድን ትንቢት (ቃል) ብቻ ወስጄ እንዳልሆነ አንባቢ ሁሉ እንደሚረዳ እርግጠኛ ነኝ፡፡
ምክኒያቱም ጽሁፌን ከመጀመሪያው ጀምሮ እስከእዚህ ቦታ ድረስ ያነበበ አንባቢ ከአንድም ሶስት ከሶስትም
አራት በተለያየ ጊዜ ማለትም በብሉይ ኪዳን፣ በአዲስ ኪዳን፣ እና ገና ኦሪት ዘፍጥረት በብሉይ ኪዳን ከመጻፉ
በፊት እና የእውነተኛ ፍርድ ተክል የሆነው አብርሀም በአካል በእግዚአብሔር ከመመረጡ በፊት ጌታ ኢየሱስን
ጨምሮ በአራት ነብያት ማለትም ነብይ ሆሴዕ፣ ጌታ ኢየሱስ፣ ሐዋርያው ጳውሎስ፣ እና ከአዳም ጀምሮ
ሰባተኛ የሆነው ነብይ ሄኖክ የተናገሩትን (የጻፉትን) ትንቢት ጠቅሼ ነው፡፡ ጌታን ጨምሮ የእነዚህን አራት
ነብያት ትንቢት ስንመለከት የአራቱም ነብያት አራት ትንቢት በሦስት አይነት መንገድ ነው የተገለጸው፡፡ ይህም
ማለት፡-

22
1. የመጀመሪያው ትንቢት የተገለጸበት መንገድ በነብይ ሆሴዕ ትንቢት ጌታ በደላቸውን እስኪያውቁ ድረስ
ወደስፍራዬ እመለሳለሁ ብሎ በሆሴ. 5፡14-15 እንደተናገረው ወደስፍራው ከተመለሰበት (ካረገበት) ጊዜ
ጀምሮ ነብይ ሆሴዕ በሆሴ. 6፡1-3 ከሁለት ቀን (ከ 2000 ዓመታት) በኋላ ጌታ በክብር እንደሚመጣ
የተነበየበት ሲሆን የ 2000 ዓመታት ትንቢት እንደሆነ እንረዳለን፡፡
2. ሁለተኛው ትንቢት የተገለጸበት መንገድ ደግሞ ጌታ ኢየሱስ በማቴ. 24፡32-34 በበለሷ ምሳሌ የእስራኤል
ምድር መንግስት ከምትመሰርትበት ጊዜ ጀምሮ የአንድ ትውልድ ጊዜ ሳያልፍ በክብር እንደሚመጣ
የተነበየበት ሲሆን በመዝ. 90፡10 እንደተገለጸው ወደ 83.5 ዓመታት የሚደርስ ትንቢት እንደሆነ
እንረዳለን፡፡
3. ሦስተኛው ትንቢት የተገለጸበት መንገድ ደግሞ ሐዋርያው ጳውሎስ (ዕብራዊን የጻፈው ሐዋርያው
ጳውሎስ ነው በሚል ሕሳቤ) በዕብ. 3፡7-19 እና በዕብ. 4፡1-11 እንደዚሁም ነብይ ሄኖክ በሄኖ. 35፡1-36 አዳም
ከተፈጠረበት ጊዜ ጀምሮ እግዚአብሔር ለሰው ልጅ በምድር ላይ የያዘውን የ 7000 ዓመታት አጀንዳ
የተነበዩበት ትንቢት እንደሆነ እንረዳለን፡፡

እንግዲህ ማንም ምክኒያታዊ አእምሮ (Critical Mind) ያለው አንባቢ ሊቃወመው በማይችለው መልኩ
የጌታን ዳግም መምጫ ዘመናት ግልጽ በሆነ ትንታኔ በመንፈሳዊም ይበሉት በሳይንሳዊ መንገድ አስልቼ
አቅርቤዋለሁ ብዬ አምናለሁ፡፡ ምክኒያቱም ጌታን ጨምሮ በተለያየ ጊዜ የተነሱ አራት ነብያት በሦስት መንገድ
የጌታን መምጫ ጊዜ ገለጹት፡፡ የመጀመሪያው ካረገበት ጊዜ ጀምሮ ጌታ ከ 2000 ዓመታት በኋላ አንደሚመጣ
ሲተነብይ፤ ሁለተኛው ደግሞ የእስራኤል ምድር መንግስት ከመሰረተችበት ጊዜ ጀምሮ ከ 83.5 ዓመታት በኋላ
ጌታ ዳግም እንደሚመጣ ሲተነብይ፤ ሦስተኛው ደግሞ አዳም ከተፈጠረበት ጊዜ ጀምሮ ጌታ ከ 6000 ዓመታት
በኋላ ዳግም እንደሚመጣ ይተነብያል፡፡ ሦስቱንም ትንቢቶች እንደየመረጃቸው ስናሰላቸው ወደ አንድ ዘመን
ነው ያነጣጠሩት፤ እንደ ግ.አ. ከ 2031 እስከ 2033 ዓ.ም ያነጣጥራሉ፡፡ በመጨረሻም እኚህን ሦስት ትንቢቶች
በሚከተለው ዲያግራም ላጠቃልላቸው ሞክሪያለሁ፡፡

0 1000 2000 3000 4000 5000 6000 7000


ከአዳም (የእግዚአብሔር ካላንደር)
3969.5 4003 6001 6003

የሆሴ ትንቢት (2000 ዓመታት)

0 33 1948 2033
ከክርስቶስ (ግ.አ.)
2031

የበለሷ ምሳሌ
(83.5 ዓመታት)

የሄኖክና ዕብራዊያን 3 አና 4 ትንቢት (6000 ዓመታት)

23
በምሳሌ የተነገሩ ሌሎች ትንቢቶች
የእግዚአብሔር ቃል በኢሳ. 46፡10 አ.መ.ት፡-

“10 የመጨረሻውን ከመጀመሪያው፣ ገና የሚመጣውንም ከጥንቱ ተናግሪያለሁ፣ ‘ዐላማዬ የጸና ነው፡ ደስ የሚያሰኘኝንም ሁሉ
አደርጋለሁ’ እላለሁ፡፡”

ይህ ቃል የሚያስረዳን እግዚአብሔር አሁን በምንኖርበት በአሮጌው ሰማይና በአሮጌው ምድር ለፈጠራቸው


ፍጥረታት ሁሉ መጨረሻቸውን ከመጀመሪያው ማለትም ገና ሲፈጥራቸው መናገሩን ነው፡፡ በግልጽ አማርኛ
እግዚያብሔር የዘመናትን መጨረሻ ገና ከመጀመሪያው ገልጾታል ማለት ነው፡፡ በሌላ ግልጽ አማርኛ ደግሞ
አሁን የምንኖርበት አሮጌው ሰማይና አሮጌው ምድር እንዲሁም በውስጣቸው ያሉ ፍጥረታት ሁሉ መቼ
እንደተፈጠሩና መቼ እንደሚፈጸሙ (እንደሚያልፉ) ገና በመጀመሪያው በፈጠራቸው ጊዜ መጨረሻቸው መቼ
እንደሆነ ተናግሬያለሁ እያለን ነው፡፡ ስለዚህ ከመጀመሪያው መጨረሻውን የተናገረበት መጀመሪያ መቼ ነው
ስንል ፍጥረታትን የፈጠረበት ጊዜ ዘፍጥረት 1 እንደሆነ አውቀናል ማለት ነው፡፡ በመሆኑም እግዚአብሔር
ከመጀመሪያው መጨረሻውን የተናገረበትን ዘፍጥረት 1 ምን እንደተናገረን ለማወቅ ጠቅለል ባለ መልኩ
እንቃኘው፡፡

እንግዲህ እግዚአብሔር በዘፍጥረት 1 ከመጀመሪያው (1 ኛው) ቀን ጀምሮ እስከ ስድስተኛው (6 ኛው) ቀን


ድረስ ፍጥረታቱን ሁሉ ፈጥሮ ጨርሶ ሰማይና ምድርን ሰራዊታቸውንም ሁሉ ፈጽሞ በሰባተኛው (በ 7 ኛው)
ቀን ባረፈ ጊዜ መጨረሻውን ከመጀመሪያው እንደተናገረ ገልጾልናል፡፡ ነገር ግን ከመጀመሪያው ከዘፍጥረት 1
በምሳሌ እግዚአብሔር የተናገረውን መጨረሻውን ለመረዳት በ 2 ጴጥ. 3፡8 “8 …በእግዚአብሔር ዘነድ አንድ ቀን እንደ
1000 ዓመታት ነው…” በሚለው ቀመር ከዚህ በፊት ያስቀመጥኳቸውን የዘመናት ትንታኔ ሠንጠረዦች
በመጠቀም በዘመናት ከአዳም ጀምሮ እስከአሁን ድረስ የተከሰቱ ክስተቶችን ከዘፍጥረት 1 አንጻር መመርመር
ይጠበቅብናል፡፡

ይኸውም በዘፍ.1 በመጀመሪያው ቀን (በቀን 1) “እግዚአብሔር ብርሃንን ከጨለማ ለየ፡፡” እንዲሁም ከአዳም ጀምሮ
በመጀመሪያዎቹ 1000 ዓመታት (በ 1 ኛው ቀን) እግዚአብሔር ሰዎችን (አዳም እና ሔዋንን) በለሷን በበላችሁ
ቀን ትሞታላችሁ ባላቸው ጊዜና ባለመታዘዛቸው ከገነት ባባረራቸው ጊዜ ጽድቅን ከኃጢአት በመለየት
ብርሃንን ከጨለማ ለየ፡፡ በሁለተኛው ቀን (በቀን 2) “ከሰማይ በላይ ያለውን ውሃ ከሰማይ በታች ካለው ውሃ ለየ፡፡”
እንዲሁም ከአዳም ጀምሮ በ 1656 ማለትም በ 2000 ኛው ዓመት (በ 2 ኛው ቀን) በኖሕ የጥፋት ውሃ በዘፍ. 7፡
11-12 እንደተጠቀሰው የታላቁን ጥልቅ ምንጮች እና የሰማይን መስኮቶች በመክፈት ምድርን ካጥለቀለቀ በኋላ
የከፈታቸውን የሰማይ መስኮቶችና የጥልቁን ምንጮች በዘጋ ጊዜ ከሰማይ በላይ ያለውን ውሃ ከሰማይ በታች
ካለው ውሃ ለየ፡፡ በሶስተኛው ቀን (በቀን 3) ደግሞ “እግዚአብሔር ምድር ዘር የሚሰጡ ተክሎችንና በምድር ላይ ዘር ያዘሉ
ፍሬ የሚያፈሩ ዛፎችን እንደየወገናቸው ታብቅል” እንዳለ ከአዳም ጀምሮ በ 2023፣ በ 2048፣ እና በ 2538 ማለትም
በ 3000 ኛው ዓመት (በ 3 ኛው ቀን) እንደቅደምተከተላቸው እግዚአብሔር አብርሀምን “ለእውነተኛ ፍርድ ተክል”
መርጦ ይስሐቅ ደግሞ “የዘላለም ጽድቅና ርትዕ ተክል” ሆኖ ከአብርሀም ከወጣ በኋላ እግዚአብሐር ከይስሐቅ
የወጣውን የያዕቆብን አስራ ሁለት ነገዶች “የቅዱሳንና የጻድቃን ራእያት” አድርጎ ባወረሳቸው ምድር ስርዐትና
ቅጥር በሰራላቸው ጊዜ እንደየወገናቸው (እነደየነገዳቸው) ምድር ያበቀለቻቸው ዘር የሚሰጡ ተክሎችና
በምድር ላይ ዘር ያዘሉ ማለትም ጌታ ኢየሱስን ያዘሉ (ያረገዙ) ፍሬ የሚያፈሩ ዛፎች አድርጎ ለያቸው፡፡

24
በአራተኛው ቀን (በቀን 4) “እግዚአብሔር ለምድር ብርሃንን ይሰጡ ዘንድ ሁለት ታላላቅ ብርሃናትን አደረገ ታላቁ ብርሃን በቀን
እንዲሰለጥን ታናሹ ብርሃን በሌሊት እንዲሰለጥን አደረገ፡፡” ከአዳም ጀምሮ በ 3018 እና በ 3999.5 ማለትም
በ 4000 ኛው ዓመት (በ 4 ኛው ቀን) እንደቅደምተከተላቸው ከአዳም ጀምሮ በ 3018 በእስራኤል
የመጀመሪያው መቅደስ ግንባታ ተጀምሮ ባለቀ ጊዜ እግዚአብሔር ለንጉስ ሶሎሞን ጥበብን በሰጠው ጊዜና
የአለም ነገስታት ጥበብን ፍለጋ ስጦታን እየያዙ ወደሱ በመጡ ጊዜ እግዚአብሔር ጠቢቡ ሶሎሞንን በሌሊት
የሚሰለጥን ታናሹ ብርሃን አደረገው፡፡ እንደዚሁም ከአዳም ጀምሮ በ 3999.5 ጌታ ኢየሱስ በተገለጠ ጊዜ ጌታ
ኢየሱስ እራሱ ‘እኔ የአለም ብርሃን ነኝ’ ‘ከሶሎሞን የሚበልጥ በዚህ አለ’ እንዳለው በቀን የሚሰለጥን ታላቁ ብርሃን ሆኖ
መጣ፡፡ በአምስተኛው ቀን (በቀን 5) “እግዚአብሔር የባህር ውሆች ሕይወት ባላቸው በሕያዋን ፍጡራን ይሞሉ ብዙ ተባዙ
የባህርንም ውሃ ሙሏት ወፎችም ከምድር በላይ በሰማይ ጠፈር ይብረሩ በምድር ላይ ይብዙ ብሎ ባረካቸው፡፡” እንዲሁም ጌታ
ኢየሱስ ሲጠመቅ መንፈስ ቅዱስ በእርግብ አምሳል በእርሱ ላይ ከወረደበት ጊዜ በኋላ በቀጣዮቹ የ 3.5
ዓመታት አገልግሎት ዘመኑ ማለትም ከአዳም ጀምሮ በ 5000 ኛው ዓመት (በ 5 ኛው ቀን) ቃሌ ሕይወት
(መንፈስ) ነው ብሎ እንዳለው ሁሉ እስከአሁን እስከ ወደፊትም በዮሐንስ ራዕይ በባሕር ውሆች የተመሰሉት
የዓለም ሕዝቦች ሁሉ የጌታን ቃል (ወንጌልን) ሰምተው ሲቀበሉ ሕይወትን ያገኛሉ (ሕያዋን ፍጡራን
ይሆናሉ)፤ በሰማይ ወፍ (እርግብ) የተመሰለው መንፈስ ቅዱስም በእነርሱ ያድራል፡፡ እነዚህም የባሕር ውሆች
በተመሰሉት በዓለም ሕዝቦች ውስጥ እየበዙና እየተባዙ ናቸው፡፡

በስድስተኛው ቀን (በቀን 6) “እግዚአብሔር ሰውን በእግዚአብሔር መልክ ፈጠረው፤ ወንድና ሴት አድርጎ ፈጠራቸው፡፡ ብዙ
ተባዙ ምድርንም ሙሏት ብሎ ባረካቸው፡፡” እንዲሁም እንደ ግ.አ. በ 2001 ዓ.ም. ማለትም ከአዳም ጀምሮ
በ 6000 ኛው ዓመት (በ 6 ኛው ቀን) በተጠና ጥናት የአለም ሕዝብ ቁጥር እድገት ግራፍ (Curve) እንዳሳየው
እንደ ግ.አ. ከ 1000 ዓ.ም. ጀምሮ በቀጥታ መስመር (Linearly) አድጎ በ 800 ዓመታት ውስጥ በ 1800 ዓ.ም.
1,000,000,000 ሲደርስ ከ 1801 ዓ.ም. እስከ 2000 ዓ.ም. በ 200 ዓመታት ውስጥ ግን በቀጥታ መስመር
ሳይሆን ኤክስፖኔንሻሊ (Exponentially) አድጎ 7,000,000,000 እንደደረሰ ያሳያል፡፡ ይህ እንደሚያሳየው
ከአዳም ጀምሮ በ 6000 ኛው ዓመት (በ 6 ኛው ቀን) በእግዚአብሔር አምሳል የተፈጠሩት የሰው ልጆች
እንደበዙና እንደተባዙ ምድርንም እንደሞሏት ነው፡፡ በሰባተኛው ቀን (በቀን 7) “ሰማይና ምድር ሰራዊታቸውም ሁሉ
ተፈጸሙ፡፡ እግዚአብሔር ይሰራ የነበረውን ስራ በሰባተኛው ቀን ላይ ፈጽሞ ነበር፤ ስለዚህ ከሰራው ስራ ሁሉ በሰባተኛው ቀን ዐረፈ፡፡
እግዚአብሔር ሰባተኛውን ቀን ባረከው፤ ቀደሰውም፤ ካከናወነው የመፍጠር ስራው ሁሉ ያረፈው በሰባተኛው ቀን ነውና፡፡”
እንግዲህ ከአዳም ጀምሮ 7000 ኛውን ዓመት (7 ኛውን ቀን) ገና ባንገባበትም በዘፍጥረት ከቀን 1 እስከ 6 ጌታ
በፈጠራቸውና ከአዳም ጀምሮ እስካሁን ድረስ ከተከሰቱ ክስተቶች ጋር ካላቸው ተመሳሳይነት (Analogy)
በመነሳት ወደፊት ምን እንደሚሆን መገመት ሳይሆን ማወቅ አያዳግትም፡፡ ይህች 7000 ኛዋ ዓመት (7 ኛዋ
ቀን) እግዚአብሔር ካከናወነው የመፍጠር ስራው ሁሉ ስላረፈባት የባረካትና የቀደሳት፤ ሰይጣን ታስሮ ወደ
ትልቁ የሚወርድባት ጌታችንና መድሐኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በአካል (በስጋ) በምድር ላይ ተገልጦ
የሚነግስባት በናፍቆት የምንጠባበቃት የመጨረሻዋ 1000 ዓመታት ነች፡፡ እንግዲህ አንባቢ ወዳጄ፣
እግዚአብሔር “የመጨረሻውን ከመጀመሪያው ተናግሪያለሁ” እንዳለው በዘፍጥረት 1 በምሳሌ ተናግሮታል “ገና
የሚመጣውንም ከጥንቱ ተናግሪያለሁ” እንዳለው ደግሞ ጥንት ገና ዘፍጥረት በሙሴ ሳይጻፍ አዳም ከተፈጠረ
በመጀመሪያዎቹ 800 ዓመታት አካባቢ በግልጽ ቋንቋ (Literally) ምንም አይነት ምሳሌ ሳይጠቀም
በመጽሐፈ-ሄኖክ በሄኖ 35፡1-36 ተናግሮታል፡፡ ነገር ግን መጽሐፈ-ሄኖክ አሁንም ይህን ጽሑፍ ካነበብክ በኋላም
ያልተዋጠልህ አክራሪ ሐይማኖተኛ ጴንጤ ከሆንክ ከላይ ያስቀመጥኳቸው የዘፍጥረት 1 ምሳሌዎች በቂ መረጃ
ይሆኑሀል ብዬ አስባለሁ፡፡ እኔ ግን እግዚአብሔር መጨረሻውን ከመጀመሪያው እና ከጥንቱ ከአንድም ሁለት ጊዜ
የተናገረውን ደጋግሜ ብዙ ጊዜ ሰማሁት (አሰላሰልኩት)፤ የሰማሁትን እርሱ የተናገረውን ደግሞ ደጋግሜ
እናገረዋለሁ፡- ጌታ እንደ ግ.አ. ከ 2031 እስከ 2033 ዓ.ም በታላቅ ክብር ዳግም በአካል (በስጋ) ይመጣል፡፡
ማራናታ፣ አሜን! ጌታ ሆይ ቶሎ ና!

የኢዮቤልዩ ምሳሌ
እግዚአብሔር እስራኤላውያንን በዘሌ. 25፡11-12፡-

25
“11 ያ አምሳኛው ዓመት ለእናንተ ኢዮቤልዩ ይሆናል፤ በእርሱም አትዝሩ፣ የገቦውንም አትጨዱ፣ የወይኑንም ፍሬ አታከማቹ፡፡ 12
ኢዮቤልዩ ነውና የተቀደሰ ይሁንላችሁ፣ በሜዳ ላይ የበቀለውን ብሉ፡፡” ብሎ ያዛቸዋል፡፡

ስለዚህ አንድ ኢዮቤልዩ አምሳ ዓመታት ናቸው ማለት ነው፡፡ በሌላ ቦታም እግዚአብሔር ሁል ጊዜ የከፋውን
የሰውን ልብ ስላየ፡-

በዘፍ. 6፡3 “6 እግዚአብሔርም መንፈሴ እያዘነ በሰው ላይ ለዘላለም አይኖርም፤ እርሱ ስጋ ነውና ዘመኖቹም መቶ ሀያ ዓመት
ይሆናሉ አለ፡፡” በማለት ህግን ደነገገ፡፡

አንዳንድ ሰዎች ይሄን ህግ ይዘው የሰው እድሜ 120 ዓመት ነው ይላሉ፡፡ ነገር ግን በመጽሐፍ ቅዱስ ታሪክ
ከአብርሀም፣ ከይስሐቅ፣ እና ከያዕቆብ በኋላ ሙሴ ብቻ ነው ይህን ያህል ጊዜ የኖረው፡፡ በአሁኑ ጊዜም
ምንአልባት በዓለም ላይ ይህን ያህል ጊዜ የኖረ ሰው ቢኖር በጣት የሚቆጠር ነው፡፡ ስለዚህ በዘፍ. 6፡3 የተደነገገው
የሰው ልጅ ዘመን ምሳሌያዊ (Symbolic) ነው ማለት ነው፡፡ ምሳሌውም ከኢዮቤልዩ ጋር የተያያዘ ነው፡፡ በዘፍ.
3፡8 “…አዳምና ሚስቱ ጌታ በገነት ሲመላለስ ድምጹን ሰምተው በገነት ዛፎች መካከል ተሸሸጉ” እንደሚል ኃጢአትን
ከመስራታቸው በፊት አግዚአብሔር በአካል ከእነርሱ ጋር እንደነበር እንረዳለን፡፡ በኃጢአታቸው ምክንያት
እግዚአብሔር ከተለያቸው በኋላ እስከ አሁን ድረስ ከሙሴ በቀርና ጌታ ኢየሱስ በስጋ በምድር ላይ ከኖረበት 33
ዓመታት በቀር እግዚአብሔር ለሰዎች በመንፈሱ እንጂ ለማንም በአካል አልተገለጠም፡፡ ስለዚህ ከአዳምና
ሔዋን ከገነት መባረር ጊዜ ጀምሮ እስከ ጌታ ዳግም ምጻት ድረስ እግዚአብሔር አለምን እየገዛ ያለው
በመንፈሱ ነው ማለት ነው፡፡ በ 7 ኛዋ ቀን (በ 7000 ኛዋ ዓመታት) ወይም በመጨረሻዋ 1000 ዓመታት ጊዜ ግን
እግዚአብሔር ከኛ ጋር (አማኑኤል) እንደሚል ቃሉ፣ በአካል አለምን እንደሚያስተዳድር እናውቃለን፡፡ ስለዚህ
በምሳሌ መንፈሴ እያዘነ ከሰው ልጅ ጋር ዘላለም አይኖርም ዘመኑም 120 ይሆናል ሲል መንፈሴ ሰዎችን
የሚያስተዳድረው ለ 120 የኢዮቤልዩ ዓመታት ነው እያለን ነው፡፡ ምክኒያቱም 120 የኢዮቤልዩ ዓመታት=120
x 50 = 6,000 ዓመታት ስለሆነ ነው፡፡

ሌሎች የኢዮቤልዩ ምሳሌዎች፡- ሙሴ መሲሑን (ጌታ ኢየሱስን) ተመስሎ እስራኤላውያንን ነጻ ለማውጣት


ተቀብቶ የተገለጠው በ 80 ዓመቱ ሲሆን ጌታ ኢየሱስም የተገለጠው ከአዳም ጀምሮ በ 80 ኢዮቤልዩ ዓመታት
= 80 x 50 = 4,000 ዓመታት ነው፡፡ እንደዚሁም እስራኤላውያን ከግብጽ ወጥተው የተስፋዪቱን ምድር
ሳይወርሱ በምድረ-በዳ (በበረሀ) 40 ዓመታት እንደቆዩ እናውቃለን፤ በመቀጠልም በራዕ. 12 በምሳሌ
የተነጠቀውን ወንድ ልጅ ያስገኘችው ሴቲቱ (ድንግሊቷ እስራኤል) ለ 42 ወራት እንክብካቤ ይደረግላት ዘንድ
ወደበረሀ (ወደምድረ-በዳ) ሸሸች እንደሚል ጌታ ካረገበት ጊዜ ጀምሮ በመንፈስ እግዚአብሔር የተዋቸው
ቢሆንም ጌታ በማቴ. 24፡31 እንደተናገረው በመጨረሻ መላዕክቱን ልኮ ከአራቱም ነፋሳት እስኪሰበስባቸው
ድረስ በ 70 A.D. በአካል ወደ አሕዛብ (ምድረ-በዳ) ሁሉ እንደተበተኑ እናውቃለን፡፡ አሁንም እውነተኛዎቹ
እስራኤላውያን (ድንግሊቷ እስራል) በአራቱም ነፋሳት በአሕዛብ መካከል (በምድረ-በዳ) እንደተበተኑ
እነደሚኖሩ መጽሐፍ ቅዱስ በተለያየ ቦታ ላይ ያስረዳናል፡፡ ስለዚህ እሰከመቼ ነው ድንግሊቷ እስራኤል
በአሕዛብ መካከል (በምድረ-በዳ) ተሰዳ የምትኖረው? መልሱ ግልጽ ነው፡፡ በራዕ. 12 እንደተተነበየው
ለመጨረሻዎቹ 3.5 ዓመታት (42 ወራት) በእስራኤል ምድር የሚገለጠው አለም ከተፈጠረ ጊዜ ጀምሮ ታይቶ
የማይታወቀዉ ታላቁ መከራ (The Great Tribulation) እስኪያልፍ ድረስ ነው፡፡ ስለዚህ ልክ ከግብጽ ወጥተው
40 ዓመታት በምድረ-በዳ (በበረሐ) እንደቆዩ በሆሴ.6:2 ቃሉ እንዳመለከተን በአጠቃላይ ጌታን ያልተቀበለችው
ድንግሊቷ እስራኤል በጌታ ስም የሚመጣ የተባረከ ነው ብላ እስክትቀበለው ድረስ ጌታ ካረገበት ጊዜ ጀምሮ
በአሕዛብ መካከል (በምድረ-በዳ/ከመንፈስ ቅዱስ ተለይተው) ለ 40 ኢዮቤልዩ ዓመታት = 40 x 50 = ለ 2,000
ዓመታት ይቆያሉ ማለት ነው፡፡ ሌሎች ብዙ ምሳሌዎችን ማሳየት ቢቻልም በዚህ ማብቃትን መርጫለሁ፡፡

26
በመጨረሻም አንድ በኪነ-ጥበቡ ዓለም ታዋቂ የሆነ የእግዚአብሔር ቃል ሙላት ያለው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ
ተዋሕዶ እምነት ተከታይ የሆነ ወዳጄ የዳግም ምጽዐቱን ወቅቶች (Seasons) እንደ እኔ ነጭ ነጯን ገልጾ
የማስላት ዝንባሌ ባይኖረውም ከእግዚአብሔር ቃል ወቅቶቹን በመረዳቱ “ሦሥተኛው ኪዳን” በተሰኘ
መጽሐፉ የምጽዐቱን ወቅቶች በጣም በረቀቀና በምሳሌያዊ ዘይቤ መጽሐፍ ቅዱስን ያጠኑ ሰዎች ብቻ
በሚረዱበት መንገድ ገልጾታል፡፡ በመሆኑም እኔ በግልጽ ያቀረብኩትን እግዚአብሔር ለምድር የያዘውን የ 7000
ዓመታት አጀንዳ እርሱም በመጽሐፉ በአንድ ቦታ ላይ ከእግዚአብሐር ቃል ወስዶ በምሳሌ አቅርቦታልና
እንደሚከተለው አቅርቤዋለሁ ይመልከቱት፡-

“አሮጌው ሰማይና ምድር ካለፉ አዲሶቹ ያስፈልጋሉ፡፡ … የመጀመሪያዎቹ ሰማይና ምድር እሁድ ቀን ተፈጠሩ፡፡ በእሁድነት
ይጠራሉ፡፡ ከእሁድ በኋላ ያሉት ስድስት ቀናት የእሁድ መሰረትነት አላቸው፡፡ እሳት፣ ነፋስ፣ ውሃና አፈር ከምንላቸው የሚታየው
ዓለም መጣ፡፡ በስድስተኛው ቀን መድሐኒቱ “ተፈፀመ” ብሎ ፈፀመን:: በሰባተኛው ቀን ሞትንና ሲኦልን በዝብዞ ነፍሳችንን
አገለገላት፡፡ ሰባተኛው ቀን ሲያልቅ በስምንተኛው ቀን በስጋና በነፍስ የበዘበዘውን ይዞት ተነሳ፡፡ ለእኛም ተሰጠ፡፡ ስምንተኛው ቀን
እሁድ መሆኑን አስብ! በሌላ አገላለፅ የመጀመሪያው ሳምንት (7 ቀን) አልፎ ሌላ ሳምንት ተጀምሯል፡፡ ለመግደላዊት ማርያም
ከሳምንቱ በመጀመርያው ቀን ነበር የታያት፡፡ በሥነ ፍጥረት እሁድ ከተጠራ ሰማይና ምድር ማለታችን ነው፡፡ የመጀመሪያው እሁድ
ሰማይና ምድር ካለው ሁለተኛውም ይኖረዋል፡፡ በመሆኑም በሁለተኛው እሁድ አዲስ ሰማይና ምድር አለ፡፡“

“ሦሥተኛው ኪዳን” አምስተኛ ዕትም የካቲት 2015 ዓ.ም. በደመወዝ ጎሽሜ

በመጀመሪያ እግዚአብሔር አምላኬን ስለ ደመወዝ ጎሽሜ እያመሰገንኩ ከላይ ያስቀመጥኩትን የመጽሐፉን


አጭር ክፍል እጅግ በጣም የረቀቀ መልዕክት እኔ በተረዳሁት መንገድ ከኔ ፅሁፍ ጋር ያለው ግንኙነት
እግዚአብሔር ከመጀመሪያው መጨረሻውን በዘፍጥረት ምዕራፍ አንድ እንደተናገረው ለሰዎች ልጆች
በአሮጌው ምድርና ሰማይ የያዘውን የ 7000 ዓመታት እቅድና በራእ. 21 የተጻፈውን በ 8 ኛው ሺህ ዓመት
የሚገለጡትን አዲስ ሰማይና አዲስ ምድር የገለፀበት መንገድ ነው ብዬ አስባለሁ፡፡ በመጨረሻም የፅሑፌን
ማጠቃለያውን ከሚከተለው ዲያግራም ይመልከቱ፡፡

27
120 ኢዮቤልዩ / 6 ቀናት
6000 ዓመታት 1 ቀን ዘላለማዊነት
የጌታ ቀን (Eternity)
80 ኢዮቤልዩ / 4 ቀናት 40 ኢዮቤልዩ / 2 ቀናት

4000 ዓመታት 2000 ዓመታት 1000 ዓመታት


∞ ዓመታት
(አዲስ ሰማይና አዲሰ
ምድር)

ምድር ዘር በቀን የባሕር ውሆች ሰውን በአምሳሉ እግዚአብሔር


ብርሃንን የሰማይ በላይ
ያዘሉና ፍሬን የሚሰለጥነውን በሕያዋን ፍጡራን ፈጠረ ብዙ ተባዙ ይሠራ ከነበረው
ከጨለማ ለየ ውሃን ከሰማይ
የሚያፈሩ ታላቁን ብርሀንና እንዲሞሉና ምድርንም ሙሏት ከመፍጠር ሥራ
በታች ውሃ ለየ
ዛፎችን በሌሊት ወፎችም በሰማይ ብሎ ባረካቸው አረፈ 7 ኛውንም
ታብቅል አለ የሚሰለጥነውን ጠፈር እንዲበዙ ቀን ባረከው
ታናሹን ብርሃን ባረካቸው ቀደሰውም
አደረገ

ቀን-1 ቀን-2 ቀን-3 ቀን-4 ቀን-5 ቀን-6 ቀን-7 ቀን-∞

6001-7000

የጌታ ቀን
(የእግዚአብሔር
ዕረፍት)

28
እና ምን እናድርግ?
ጌታ በተናገረው ጊዜ ዳግም ይመጣል፡፡ እና ምን እናድርግ? ለዚህ ጥያቄ ምርጫው ሁለት ነው፡፡ አንዱን
መምረጥ ግን የአንባቢው ግዴታ ይሆናል፡፡ አንደኛውና የሚመከረው ትክክለኛው ምርጫ ጊዜው አጭር እንደሆነ
በመረዳት ነፍስንም ስጋንም ሊገድልና ሊያድን የሚችለው፣ በመስቀል ተሰቅሎ የሞተው፣ በሦሥኛው ቀን
ከሙታን የተነሳው፣ ያረገው፣ እና ዳግም የሚመጣው ጌታችንና መድሐኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እርሱ
እውነተኛው መሲሕ እንደሆነ በማመን የእግዚአብሔር ልጅ እና ጌታ እንደሆነ በልብ አምኖ በአንደበትም
እየመሰከሩ ቃሉንም እለት እለት እያጠኑ እንደቃሉ በመኖር ዳግም ምጻቱን በናፍቆት መጠባበቅ ሲሆን
ሁለተኛው አደገኛና ጠማማው ምርጫ ግን እውነት የሆነውን እርሱን ክዶ ልክ እንደአይሁድ ሌላ መሲሕ
በመጠባበቅ አደገኛ ፈተና ውስጥ መውደቅ ወይም ደግሞ ባለማመን እግዚአብሔር የለሽ ሕይወት በመኖር
ከአመፀኞች ጋር በመተባበር የእግዚአብሔር ቁጣ በሚገለጥባት አሁን በቅርቡ በምትመጣው በመጨረሻዋ 3.5
ዓመታት ወደጥልቁ መጣል ነው፡፡ እኔ ግን አንደኛውን ምርጫ መርጫለሁ፡፡

የመጀመሪያውን ምርጫ የመረጡት በመጨረሻዎቹ ሰባት ዓመታት የሚገለጠው አውሬ


በተገለጠ ጊዜ
1-1000 1001-2000 2001-3000 3001-4000 4001-5000 5001-6000
በ 1 ተሰሎንቄ 4፡14-17
ጽድቅን በኖኅ ጊዜ የሰማይ እስራኤላውያንን ጌታ ኢየሱስ በቀን ወንጌልንና በርግብ የሕዝብ ቁጥር የተጻፈው
ከኃጢአት መስኮቶችንና ምድር የሚሰለጥነው (በወፍ) ባለፉት 200
በመለየት የጥልቁን ምንጮች ያበቀለቻቸው ዘር ታላቁ ብርሃን ሆኖ የተመሰለውን ዓመታት ውስጥ ይሆንላቸዋል፡፡
ብርሃንን በመዝጋት የሰማይ ያዘሉ (ክርስቶስን ሲገለጥ ጠቢቡ መንፈስ ቅዱስን ኤክሰፖኔንሻሊ
ከጨለማ ለየ በላይ ውሃን ያረገዙ) ፍሬ ሶሎሞንን ደግሞ ተቀብለው ሕያዋን 1 ተሰ. 4፡14-17 “14
(Exponentially)
ከሰማይ በታች የሚያፈሩ ዛፎች በሌሊት የሚሆኑ ሰዎች አደገ
ኢየሱስ እንደሞተና
ውሃ ለየ አድርጎ ለያቸው የሚሰለጥነው መብዛት ጀመሩ
እንደተነሳ ካመንን፣
ታናሹ ብርሃን
አደረገው በኢየሱስ ሆነው
ያንቀላፉትን እግዚአብሔር
ከእርሱ ጋር እንደዚሁ ያመጣቸዋል፡፡ 15 በጌታ ቃል
የምንላችሁ ይህን ነው፤ እኛ በሕይወት ያለንና ጌታ እስኪመጣ ድረስ የምንቀር ያንቀላፉትን
አንቀድምም፤ 16 ጌታ ራሱ በታላቅ ትዕዛዝ፣ በመላዕክት አለቃ ድምፅና በእግዚአብሔር የመለከት ድምፅ
ከሰማይ ይወርዳልና፡፡ በክርስቶስ የሞቱትም አስቀድመው ይነሳሉ፡፡ 17 ከዚያም በኋላ እኛ የቀረነው፣ በሕይወትም የምንኖረው ጌታን
በአየር ላይ ለመቀበል ከእነርሱ ጋር በደመና እንነጠቃለን፤ በዚህም መሰረት ለዘላለም ከጌታ ጋር እንሆናለን፡፡”

እንግዲህ ወዳጄ ሆይ የመጀመሪያውን ምርጫ ከመረጡት ውስጥ ከሆንክ እንደክርስቲያን ሊመጣ ያለውን
ታላቅ መከራ ለማምለጥ ይህን ቃል ማመን ግድ ይልሀል፡፡ ብዙ ክርስቲያኖች ይህን ቃል ለማመን ይቸገራሉ፡፡

29
ለመነጠቅ ገዳም መግባት የሚጠበቅባቸውም የሚመስላቸው አሉ፡፡ አንተ ግን ይህን ቃል አስብ “ሄኖክም
የተነጠቀው በማመኑ ነው”፡፡

ዕብ.11፡5-6 “5 ሄኖክ ሞትን እንዳያይ ከዚህ ዓለም በእምነት ተወሰደ፤ እግዚአብሔርም ስለወሰደወው አልተገኘም፤ ከመወሰዱም
በፊት አግዚአብሔርን ደስ እንዳሰኘ ተመስክሮለታልና፡፡ 6 ደግሞም ያለእምነት እግዚአብሔርን ደስ ማሰኘት አይቻልም…”

ስለዚህ ወገኔ ብታምን ነው የሚሻልህ፡፡ ገዳም ካልገባሁ ጻድቅ መሆን አልችልም ብለህ የምታስብ ከሆንክ ዘፍ.15፡
6 “አብራም እግዚአብሔርን አመነ ጽድቅም አድርጎ ቆጠረለት፡፡” ተብሎ የተጻፈውን አስብ፡፡ ማመን አቃተኝ ልቤ
ከበደብኝ የምትል ከሆነ በሮሜ.10፡17 “እምነት ከመስማት ነው መስመትም በክርስቶስ ቃል ነው፡፡” እንደሚል የክርስቶስን
ቃል አጥና ያጠናኸውን ደጋግመህ ስማው (አሰላስለው)፡፡ በተረፈ ፁም ፀልይ፣ ከክርስቲያኖች ጋር ሕብረት
ይኖርህ፤ እምነትም በመንፈስ ቅዱስ ኃይል ይሰጥሃል፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ ስለንጥቀት በተለያየ ቦታ ላይ ይናገራል
አንድ ሁለቱን እንደሚከተለው አቅርቢያቸዋለሁ፡-

ኢሳ.26፡20 “20 ሕዝቤ ሆይ፣ ና ወደ ቤትህም ግባ፤ ደጅህን በኋላህ ዝጋ፤ ቁጣው እስኪያልፍ ድረስ ጥቂት ጊዜ ተሸሸግ፡፡”

Isa. 26:20 “20 Come, my people, enter thou into thy chambers, and shut thy doors about thee;
hide thy self as it were for a little moment until the indignation be overpast.”

ከዚህ ቃል የምንማረው የእግዚአብሔር ቁጣ እስኪያልፍ ድረስ “ሕዝቤ ሆይ፣ ና…” ብሎ እግዚአብሔር የእርሱ
(የክርስቶስ) የሆኑትን ደህንነቱ ወደ ተጠበቀ ስፍራ ወደ እራሱ (ወደ ሰማይ) እንደሚሰበስባቸው ነው፡፡ ታዲያ
የእግዚአብሔር ቁጣ የሚጀምረውና የሚያልፈው መቼ ነው? ከዚህ በፊት እንዳየነው በመጨረሻዋ ሰባት
ዓመታት ውስጥ በሁለተኛው አጋማሽ መጀመሪያ ላይ ይጀምርና ለመጨረሻዋ ሦሥት ዓመት ተኩል ቆይቶ
ጌታ ከመላእክቱ ጋርና ከተነጠቁት ቅዱሳን ጋር በሰማይ ሲገለጥ ባለማመናቸው በምድር ላይ የቀሩትና ከቁጣው
የተረፉት ጌታን ከሰራዊቱ ጋር በታላቅ ክብር ከሰማይ ሲመጣ ሲያዩ ዋይ ዋይ ብለው በጮሁ ጊዜ (የምድር
ወገኖች ሁሉ ዋይ ዋይ ብለው ይጮሀሉ እንደሚል ቃሉ) የጌታ ቁጣ ያልፋል፡፡ በሌላም ቦታዎች ስለንጥቀት
እነደሚከተለው ተጽፏል፡-

ሄኖ.36፡19-20 “19 ጻድቃን ይህን ተስፋ አድርጉ፣ ኃጥአን ከፊታችሁ ፈጥነው ይጠፋሉና፤ እንደወደዳችሁም ስልጣን በእነርሱ ላይ
ይሆንላችኋልና፡፡ 20 ኃጥአንም መከራ በሚቀበሉበት ቀን የእናንተ ልጆች እንደ አሞሮች ከፍ ከፍ ይላሉ፤ ይነሳሉ፡፡”

ኃጥአን መከራ በሚቀበሉበት ጊዜ ማለትም በመጨረሻዋ ሦሥት ዓመት ተኩል “ጻድቃን እንደ አሞሮች ከፍ ከፍ
ይላሉ፤ ይነሳሉ” ሲለን ይነጠቃሉ ማለቱ እንደሆነ የተሰወረ አይደለም፡፡

ሄኖ.40፡28-29 “28 አሁንም ጻድቃን፣ ኃጥአንን በፈቃዳቸው ጸንተውና ተዘጋጅተው በምታዩአቸው ጊዜ አትፍሩ፡፡ 29 ከሰማይ
ሠራዊት ጋር አንድ ትሆኑ ዘንድ አላችሁና፤ ከእነርሱ ግፍ ራቁ እንጂ ከእነርሱ ጋር አትተባበሩ፡፡”

ይህም ቃል “ከሰማይ ሠራዊት ጋር አንድ ትሆኑ ዘንድ አላችሁና” ሲለን ወደ ሰማይ ከፍ ከፍ ትላላችሁ፣ ትነሳላችሁ፤
ትነጠቃላችሁ ማለቱ እንደሆነ መረዳት አያዳግትም፡፡ ስለዚህ አንባቢዬ የዚህ ቃል ተካፋይ ለመሆን መስፈርቱ
አንድ ነው፤ ሄኖክ በእምነት ተወሰደ እንደሚል፣ ቃሉን እያጠናህ በቃሉ እየኖርክ እንደሞኝ ብቻ ሳይሆን
አእምሮውን እንዳጣ እብድ ይህን ቃል በእምነት ጠብቀው፤ እግዚአብሔር ለቃሉ የታመነ ነውና ይህ ሁሉ
በስራችን ሳይሆን በጸጋው ሆኖልናልና፡፡

በአሁኑ ጊዜ የክርስቶስ ተቃዋሚ መንፈስ እየሰራ ያለው በምስጢር ነው፤ ነገር ግን የተቀጠረለት ጊዜ ሲደርስ
በግልጽ መስራት ይጀምራል፤ በጊዜው መንፈሱ የሚሰራበትም ግለሰብ ይገለጣል፡፡ በአሁኑ ጊዜ መንፈሱ
በምስጢር የሚሰራባቸው ግለሰቦች (ከጥንት ጀምሮ ዓለምን የሚዘውሯት የዓለማችን ታላላቅ ባለሐብቶች)

30
ታውቀዋል፡፡ ዘንዶው (ሰይጣን) የተያዘችለት አርባ ሁለት ወራት አጭር እንደሆነች ስለሚያውቅ በኚሁ
አገልጋዮቹ በኩል ከተያዘለት ጊዜ ቀድሞ ስራውን ለመጀመር ብዙ የማታለል ስራዎቹን እየሰራ ቢሆንም
የሚከለክለው ኃይል በምድር ላይ ስላለ እስካሁን ሳይሳካለት ቀርቷል (ከነኚህ አታላይ ስራዎቹ ውስጥ አንደኛው
በላብራቶሪ የፈጠረው የኮቪድ-19 በሽታና ክትባቱ ነው) ፡፡

2 ተሰ. 2፡6-8 “6 በራሱ ጊዜ ይገለጥ ዘንድ አሁን ምን እንደሚከለክለው ታውቃላችሁ፡፡ 7 የዐመፅ ምስጢር አሁን እንኳ እየሰራ ነውና፤
ነገር ግን ይህ የሚሆነው የሚከለክለው ከመንገድ እስኪወገድ ድረስ ብቻ ነው፡፡ 8 ከዚያም በኋላ ጌታ ኢየሱስ በአፉ እስትንፋስ
የሚያስወግደውና በምፅአቱም ክብር ፈጽሞ የሚያጠፋው ዐመፀኛ ይገለጣል፡፡”

ታዲያ በግልፅ እንዳይሰራ የሚከለክለው በኋላም ከመንገድ የሚወገደው ምንድነው ወይስ ማነው?

በዮሐ.10፡10 “10 ሌባው ሊሰርቅ፣ ሊገድልና ሊያጠፋ ብቻ ይመጣል…” እንደሚል ቃሉ፣ በመጨረሻዎቹ አርባ ሁለት
ወራት የሚገለጠው አውሬ የሚመጣው ሊሰርቅ፣ ሊገድልና ሊያጠፋ እንደሆነ እናውቃለን፡፡ “በኢዮ.24፡16 “16
አመንዝሮች (ሌቦች) በጨለማ ቤት ሰርስረው ይገባሉ፤ በቀን ግን ይሸሸጋሉ፤ ብርሃንንም አይፈልጉም፡፡” እንደሚል አውሬውና
አገልጋዮቹ ስራቸውን እንዲጀምሩ ሰዎች ሁሉ የሚተኙበት ጨለማ ያስፈልጋቸዋል ማለት ነው፡፡ ጨለማ
ደግሞ ብርሃን ባለበት ኃይል የለውም፡፡ ጨለማው ይሰራ ዘንድ ብርሃን መወገድ አለበት፡፡ ስለዚህ ይህ አውሬ
በሙሉ ኃይሉ ይሰራ ዘንድ ከመንገድ መወገድ ያለበት ብርሃን ነው ማለት ነው፡፡ ታዲያ ይህ ብርሃን ምንድነው?
መቼስ ይወገዳል? በማቴ. 5፡14 “14 እናንተ የዓለም ብርሃን ናችሁ፡፡” እንደሚል፣ ይህ ብርሃን ቤተ-ክርስቲያን
(እውነተኛ ክርስቲያኖች) እንደሆነች እንረዳለን፡፡ ስለዚህ ቤተ-ክርስቲያን (እውነተኛ ክርስቲያኖች) ከዓለም
(ከምድር) ስትወገድ ማለትም ስትነጠቅ ዓለም (ምድር) በጨለማ ትዋጣለች ማለት ነው፡፡ አውሬውም
ስራውን በግልጽ መስራት ይችላል ማለት ነው፡፡ ምክኒያቱም ጨለማው (ሰው ሁሉ በመንፈስ የሚተኛበት ጊዜ)
ስለሆነ ማንም አያየውም (አያስተውለውም)፡፡ ቤተ-ክርስቲያን (ክርስቲያኖች) ግን አሁን እንኳ አውሬው
በምስጢር በሚሰራበት ጊዜ ብዙዎቹን የአውሬውን አገልጋዮች ለይታቸዋለች፡፡ በኤፌ.5፡11 “11 ፍሬም ከሌለው
ከጨለማ ስራ ጋር አትተባበሩ፤ ይልቁንም ግለጡት እንጂ፡፡” እንደሚል፣ ለአንባቢ መረጃ እንዲሆን እኔ የማውቃቸው
በፒራሚዱ አናት ሆነው ዓለምን የሚዘውሩትን ቀንደኛ የአውሬውን አገልጋዮች እንደሚከተለው
ገልጫቸዋለሁ፡- Bill Gates, Elon Musk, Dr. Anthony Fauci, Klause Schwab (የዓለም ኢኮኖሚክ
ፎረም መሪ), Yuval Noah Harari, እንዲሁም ከጀርባ ሆነው የሚመሩት የእንግሊዝ (Wales’) ንጉሳውያን
ቤተሰቦች/King Charles (ያለምክንያት አላሰመርኩበትም፤ የዚህን ሰው ጉዳይ አሁን ለመናገር ጊዜው
አይደለም) እና የመሳሰሉት ናቸው፡፡ ስለዚህ አንተ የተኛህ ንቃ፤ ከሙታን ተነሳ፤ ክርስቶስም ያበራልሃል፡፡

31

You might also like