Download as pdf or txt
Download as pdf or txt
You are on page 1of 1

ለ ህያው አምላክ የኤርትራውያን ወንጌላዊት ቤተክርስቲያን

ግዳዩ :- ስለ መጋቢ እዝራ ሐዋርያ ተብሎ ስለመጠራት

በቶሮንቶ የምንገኝ አብያተክርስቲያናት ህብረት በጋራ የጀመርነውን እንቅስቃሴ ለማሰቀጠል


እንዲሁም የእርስ በእርስ መደጋገፍና መበረታታት የሚያስችል በጋራ ራእይ የተመሰረተ እና
እንዲሁም ይህን ህብረት ለመጠበቅ በጋራ መጸሐፍ ቅዱሳዊ ደነብ ቀርጾ የሚንቀሳቀስ ነው
በዚህም ምክንያት ከላይ የተገለጸው ጉዳይ ዘመን አመጣሽ አዲስ ልምምድ ስለሆነ
በመተዳደሪያ ደንባችን በመተዳደሪያ ደንባችን በቀጥታ ባይቀመጥም ነገር ግን የአጥቢያ
ቤተከርስቲያኒቱን ጤናማ መጸሐፍ ቅዱሳዊ አካሄድ ይከታተላል በሚለው መሰረት ባለፈው
Feb.4 2024 በነበረው የመሪዎች አመታዊ ስብሰባ ላይ ጉዳዩ በአጀንዳ ቀርቦ በመነጋገር
የህብረቱ አባል የሆነችው ቤተከርስቲያኒቱ ይህን ምላሽ እንድትሰጥ ወስነናል

1. በቅድሚያ ወደ ህብረቱ አቅርቦ ምክንያቱን ማሰረዳት ሲገባ መጠሪያዬ ተቀይሮ


ብታዩት ግር እንዳይላችሁ በማለት ማሳወቅ አካሄዱ ያልጠበቀ እነደሆነ ግንዛቤ
ህብረቱ ስላለው
2. ሐዋርያዊ ተልእኮ እንዳገለግል እግዚአብሔር ተናግሮኛል የሚለው አገላለጽ ይህን
ተልእኮ መጋቢ በመባል ማገልገል እንደሚቻል ህብረቱ ግንዛቤ ስላለው
3. ሐዋርያነት ከአንድ አጥቢያ ዘለል በተለያየ ከተማ ውስጥ ቤተክርስትያኖችን
መትከልና ማነጽ ሲሆን ይህም ሰጦታ በግል እግዚአብሔር ተናገረኝ በሚል ብቻ
ሳይሆን በሌሎች ቤተክርስቲያኖች ምስክርነት የታነጸ መሆን አለበት ሆኖም የህያው
አምላክ ቤተክርስቲያን እንደ ቤተክርስቲያን ጸንታ ለመቆም በብዙ ተግዳሮት ያለፈች
መሆኖንና ለዚህ ጥሪ ምስክር የሚሆን ነገር እንደሌላት በመረዳት እንደ ዘመኑ ሰዎች
ራሳቸውን በመሰየም የሚሄዱበት ሩጫ እንደሆነ በህብረቱ ይህ ግንዛቤ ስላለ

ቤተክርስቲያኒቱ ይህን በማጤን ለህብረቱ በቂ ምላሽ በመስጠት አልያም የአካሄድ እርምት


በመውሰድ ከላይ የተገለጹ ሃሳቦችን መሰረት አድርጎ ህብረቱ በድጋሚ ለውይይት እና ለውሳኔ
እንዲረዳው ምላሻችሁን በደብዳቤ እንድታሳውቁን በትህትና እንገልጻለን

የህብረቱ አሰተባበሪዎች

You might also like