Download as doc, pdf, or txt
Download as doc, pdf, or txt
You are on page 1of 2

CRUISE SCHOOL 2012 E.C.

የ 6 ኛ ክፍል የህብረተሰብ ትምህርት የመልመጃ ጥያቄዎች


I. ለሚከተሉት ጥያቄዎች በአጠያየቃቸው መሰረት ተገቢውን መልስ ስጡ፡፡

1. የአፈር ሀብትን ከምንጠቀምበት ወይም ከምንከባከብበት ዘዴዎች ውስጥ አራቱን ዘርዝሩ?

2. ለህዝብ እንቅስቃሴ (ፍልሰት) ዋንኛ ምክንያት የሚሆኑ ሶስት ነገሮች ፃፉ?


ሀ.
ለ.
ሐ.
3. ከአለቶች ስብርባሪ፣ ከእፅዋት ብስባሽ እና ከእንስሳት ቅሪት የሚገኙ የተፈጥሮ ሀብቶች ምን በመባል ይታወቃሉ?

4. የደን ስርጭትን ሊወስኑ ከሚችሉ ተፈጥሮአዊ ምክንያቶች ውስጥ ሁለቱን ዘርዝሩ?


ሀ.
ለ.
5. በምስራቅ አፍሪካ ለአደጋ ከተጋለጡ የዱር እንስሳት ውስጥ ሶስቱን ፃፉ?

6. ዳግም ድነናና ድነና ማለት ምን ማለት ነው?


7. አራት የዘር ማፈራረቅ ጥቅሞችን ፃፉ?

8. ጣምራ የደን እርሻ (Agro-forestry) ማለት ምን ማለት ነው?


9. የእርከን ስራን በከፍተኛ ስፍራ ላይ አግድሞ ማረስ አራት ጠቀሜታዎቹን ዘርዝሩ?
10. የእንስሳት መጠበቂያና መከለያ ስፍራ ማለት ምን ማለት ነው?
11. የባቢሌ የእንስሳት መጠበቂያ ስፍራ የተቋቋሙበት ዓላማ ምን ነበር?
12. በሰንቀሌ የእንስሳት መጠበቂያ ስፍራ ከሚገኙ የዱር እንስሳት ውስጥ አራቱን ፃፉ?

2012 ዓ. ም. . ክሩዝ ት/ቤት አ.አ. የህብረተሰብ ትምህርት 6 ኛክፍል ገፅ 1


CRUISE SCHOOL 2012 E.C.

13. ብሄራዊ ፓርክ ለአንድ አካባቢ ከሚሰጠው ጠቀሜታ ውስጥ ሁለቱን ፃፉ?

14. ኩሬዎችና ምንጮችን እንዴት በንፅህና ይያዛሉ?


15. በኢትዮጲያ ከሚገኙ ብሄራዊ ፓርኮች ውስጥ አምስቱን ዘርዝሩ?

16. ኤች አይቪ/ኤድስ በማህበረሰብ ላይ ምን ምጣኔ ሀብታዊና ማህበራዊ ችግሮች ያስከትላል ?


17. ፈጣን የህዝብ ቁጥር ዕድገት በውሃ ሀብትና በዕፅዋት ላይ ምን ተፅእኖ ያሳድራል?

18. በተባበሩ መንግስታት ድርጅት ከውጪ የህፃናት መብት ስምምነቶች ውስጥ ሁለቱን ፃፉ?

19. በአከባቢያችሁ ለህፃናት መብት ጥሰት መንስኤ ከሆኑ ጉዳዮች ውስጥ ሶስቱን ዘርዝሩ?

20. የአየር ፀባይና የአየር ንብረት ልዩነት ግለጹ?

2012 ዓ. ም. . ክሩዝ ት/ቤት አ.አ. የህብረተሰብ ትምህርት 6 ኛክፍል ገፅ 2

You might also like