Professional Documents
Culture Documents
By Dr. Eyob Mamo
By Dr. Eyob Mamo
የዚህ ስልጠና ዋና ዓላማ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ የሚገኙ ወጣትና ተተኪ መሪዎች ራእይን በማወቅ ውስጥ
ያለውን ራስን መርቶ ሌላውን የመምራት ሂደት እንዲገነዘቡ ማስቻል ነው፡፡
መግቢያ - የመንፈሳዊ አመራር ትርጓሜ
ክፍል አንድ - የመንፈሳዊ አመራር ሁለንተናዊ ገጽታ
ክፍል ሁለት - መልካም ተጽእኖን የሚያመጣ ራእይ
ክፍል ሶስት - ለራእያችን የሚመጥን ዲሲፕሊን
ክፍል አራት - ለራእያችን የሚመጥን ባህሪይ
ክፍል አምስት - ለራእያችን የሚመጥን ክህሎት
መግቢያ
የመንፈሳዊ አመራር ትርጓሜ
“13ከእናንተ መካከል ጥበበኛና አስተዋይ የሆነ ሰው ማን ነው? ሥራውን ከጥበብ በሆነ በመልካም አኗኗር ያሳይ። 14ነገር ግን መራራ ቅናትና ራስ
ወዳድነት በልባችሁ ቢኖር ኵራት አይሰማችሁ፤ እውነትንም አትካዱ። 15እንዲህ ያለችዋ ጥበብ ከላይ አይደለችም፤ ነገር ግን ከምድር፣ ከሥጋና
ከአጋንንት ናት። 16ቅናትና ራስ ወዳድነት ባሉበት ስፍራ በዚያ ሁከትና ክፉ ሥራ ሁሉ ይገኛሉ። 17ከሰማይ የሆነችው ጥበብ ግን በመጀመሪያ
ንጽሕት ናት፤ በኋላም ሰላም ወዳድ፣ ታጋሽ፣ እሺ ባይ፣ ምሕረትና መልካም ፍሬ የሞላባት፣ አድልዎና ግብዝነት የሌለባት ናት። 18የጽድቅም ፍሬ
ሰላምን ለሚያደርጉ በሰላም ይዘራል” - ያዕ. 3፡13-18
• “መምራት” (በእንግሊዝኛው “to lead”) የሚለው ቃል “ሌድን” (“leden”) ወይም “ሎዳን” (“loadan”) ከሚለው ጥንታዊ የእንግሊዝኛ ቃል
የመጣ እንደሆነ ይታመናል፡፡
• ትርጓሜውም፣ “ወደ ፊት ማስኬድ”፣ “ምሪት መስጠት”፣ “መንገዱን ማሳየት” ነው፡፡
• በአመራር ሂደት ውስጥ እኛ ያልሆንነውን ነገር ሰዎች ወደመሆን እንዲመጡ ማድረግ አንችልም፡፡
• በአመራር አለም ውስጥ እኛ በውስጠ-ሕሊናችንና በተግባር ወዳልሄድንበት
አቅጣጫ ሰዎችን መምራት አንችልም፡፡
• አመራር ማለት ራሳችንን፣ ሰዎችን፣ አገልግሎትን ወይም የስራ ሂደትን
የምንመራበት የስነ-ጥበብ ዘርፍ ነው፡፡
• አመራር “ሳይንስ” አይደለም፣ ምክንያቱም በተለያዩ ሁኔታዎች ውስጥ ለተከሰተ
ተመሳሳይ ክስተት የምንሰጠው ምላሽ ሊለያይ ስለሚችል ማለት ነው፡፡
• አመራር ማለት በራሳችን ላይ፣ በሰዎች ላይና በአንድ የአሰራር ሂደት ላይ
መልካም ተጽእኖ ማምጣት ማለት ነው፡፡
• ይህ የመልካም ተጽእኖ እውነታ መንፈሳዊ ጥበብን የሚጠይቅ ጉዳይ ነው፡፡
• “13ከእናንተ መካከል” ጥበበኛና አስተዋይ የሆነ ሰው ማን ነው? ሥራውን ከጥበብ በሆነ በመልካም አኗኗር ያሳይ . . . 17ከሰማይ
የሆነችው ጥበብ ግን በመጀመሪያ ንጽሕት ናት፤ በኋላም ሰላም ወዳድ፣ ታጋሽ፣ እሺ ባይ፣ ምሕረትና መልካም ፍሬ የሞላባት፣ አድልዎና
ግብዝነት የሌለባት ናት። 18የጽድቅም ፍሬ ሰላምን ለሚያደርጉ በሰላም ይዘራል” ያዕ. 3፡13-18
• ሰማያዊው የአመራር ጥበብ የክርስቶስን ማንነት ከተላበሰ ማንነትና ከመልካም ባህሪይ የሚመነጭ ነው፡፡
• “14ነገር ግን መራራ ቅናትና ራስ ወዳድነት በልባችሁ ቢኖር ኵራት አይሰማችሁ፤ እውነትንም አትካዱ። 15እንዲህ ያለችዋ ጥበብ ከላይ
አይደለችም፤ ነገር ግን ከምድር፣ ከሥጋና ከአጋንንት ናት። 16ቅናትና ራስ ወዳድነት ባሉበት ስፍራ በዚያ ሁከትና ክፉ ሥራ ሁሉ ይገኛሉ”
ያዕ. 3፡13-18
• የዚህች ዓለም የአመራር ጥበብ ምንጩ ምድራዊ፣ ስጋዊና አጋንንታዊ ነው፡፡
የውይይት ሃሳቦች
• ባለንበት ዘመን የዚህች ዓለም (የምድር፣ የስጋ እና የአጋንንት) ጥበብ ወደ አማኞች ሕይወት የሚገባው በምን መንገድ ይመስላችኋል?
• ከዚህች ዓለም ጥበብ ይልቅ ወደ ሰማያዊው ጥበብ ለማድረላት ምን አይነት ልምምድ ያስፈልገናል ብላችሁ ታስባላችሁ?
ክፍል አንድ
የመንፈሳዊ አመራር ሁለንተናዊ ገጽታ
“ይህን ሕዝብ የምትመራው አንተ ነህና በርታ” - ኢያ. 1፡6
“መሪያቸው ከራሳቸው ወገን ይሆናል፤ ገዣቸውም ከመካከላቸው ይነሣል፤ ወደ እኔ አቀርበዋለሁ፤ እርሱም ይቀርበኛል” - ኤር. 30፡21
• ልጅ ሆኖ የማያውቅ አባት መሆን አይችልም፤ ተማሪ ሆኖ የማያውቅም አስተማሪ መሆን ያስቸግረዋል፤ አገልጋይ ሆኖ የማያውቅ ተገልጋይ
መሆን ያዳግተዋል፡፡
• በተመሳሳይ ሁኔታ ተመሪ እና ተከታይ ሆኖ የማያውቅ መሪ መሆን አይችልም፡፡
• መንፈሳዊውን የአመራር ጥበብ ለመከተልና ስኬታ ለመሆን በቅድሚያ እኛ የምሪትን ሕይወት መለማመድ አስፈላጊ ነው፡፡
• ከዚህ በታች የሚገኙትን ከአመራር፣ ከመሪነትና ከተመሪነት ጋር የሚዛመዱ እይታዎች በሙላት ስንለማመድ ሌሎችን በመልካም ተጽእኖ
የመምራትን ብቃት ይሰጠናል፡፡
• ሌሎችን ለመምራት የሚያበቃ የምሪት ሕይወትና ልምምድ አራት ጽታዎችን ያቀፈ ነው፡፡
1. በቃሉ መመራት
3. ራስን መምራት
የውይይት ሃሳቦች
• አንድ አማኝ ቃሉን አውቃለሁና የመንፈስ ቅዱስ ምሪት አለኝ እያለ ራሱን የማይመራ ከሆን ለምን አይነት ሁኔታ ሊጋለጥ ይችላል?
• አንድ አማኝ ራሱን በራሱ እንደሚመራ እያሰበና እየተናገረ ለቤተ ክርስቲያን አመራር ራሱን ካላስገዛ ለምን አይነት ሁኔታ ሊጋለጥ ይችላል?
ክፍል ሁለት
መልካም ተጽእኖን የሚያመጣ ራእይ
“ባሪያውን ዳዊትን መረጠ፤ ከበጎች ጕረኖ ውስጥ ወሰደው፤ ለሕዝቡ ለያዕቆብ፣ ለርስቱም ለእስራኤል እረኛ ይሆን ዘንድ፣ የሚያጠቡ በጎችን
ከመከተል አመጣው። እርሱም በቅን ልቡ ጠበቃቸው፤ ብልኀት በተሞላ እጁም መራቸው” - መዝ. 78፡70-72
• የመልካም ተጽእኖ መሪዎች ለመሆን አራት ልምምዶች ያስፈልጉናል፡- 1) ራእይ፣ 2) ዲሲፕሊን፣ 3) መልካም ባህሪይ፣ እና 4) ክህሎት፡፡
• “እንደ ልቤ የሆነና እኔ የምሻውን ሁሉ የሚያደርግ የእሴይን ልጅ ዳዊትን አገኘሁ” (የሐዋ. 13፡22) ከተባለለት ከዳዊት ሕይወት
እንመለከታለን፡፡
የራእይ እውነታዎች
አምስቱ የራእይ የመነሻ ሃሳብ፡-
1. ጌታን የማክበርና የማስከበር ፍላጎት የመነሻ ሃሳብና የሁሉ ነገር መጨረሻ እንጂ ራእይ አይደለም፡፡
2. አንድን ተግባር የማድረግ ፍላጎት ለራእይ መዋጮ የሚያደርግ ተግባር እንጂ ራእይ አይደለም፡፡
3. የመንፈስ ቅዱስ ስጦታ ራእይን ለማስፈጸም የሚሰጠን ጸጋ ነው እንጂ ራእይ አይደለም፡፡
4. በተፈጥሮ ያገኘነው ወይም በስልጠና ያዳበርነው የሞያ ክህሎት ራእይን በተሻለ መንገድ ለመፈጸም ያግዛል አንጂ ራእይ አይደለም፡፡
5. የትንቢትና የመገለጥ መልእክት ራእይን ለማረጋገጥ ሊመጣ ይችላለ እንጂ ራእይ አይደለም፡፡
• የራእይ ምንጩም ሆነ የአሰራሩ ሂደት መለኮታዊ ስለሆነ ሁል ጊዜ ከሰውኛው ምልከታ ጋር እንደተጋጨ ይኖራል፡፡
• መለኮታዊ ምንጭና መንፈሳዊ ባህሪይ ያለውን ራእይን ለመገንዘብና አብሮ ለመፍሰስ መንፈሳዊ ግንዛቤን ይጠይቀናል፡፡
• ራእይን አስመልክቶ በእኛና በጌታ መካከል ያለውን የምልከታ ክፍተት ለመሰተካከል ትርጉሙንና አሰራሩን መገንዘብ የግድ ነው፡፡
3. ራእይ ጊዜ ይፈልጋል
• “ራእዩ የተወሰነለትን ጊዜ ይጠብቃልና” ቁ. 3
• ራእይ “ሂደታዊ” እንጂ “ቅጽፈታዊ” አይደለም፤ ስለዚህ ማድረግ
የሚገባንን በማድረግ ሂደቱን ልንጠብቅለት ይገባል፡፡
የውይይት ሃሳቦች
• አብዛኛው አማኝ የራእይን ትክክለኛ ትርጉም የተገነዘበና የግል ራእዩን ለይቶ የሚያውቅ ይመስላችኋል? መልሳችሁ “አይመስለኝም” ከሆነ
ምክንያቱ ምን ይመስላችኋል?
• “አምስቱ ራእይ ያልሆኑ ነገሮች” በሚለው ርእስ ስር ከጠቀስናቸው አምስት ነጥቦች መካከል ራእይ እንደሆነ አስባችሁት የምታውቁት ነጥብ
የትኛው ነው? አሁን ከትምህርቱ የተነሳ ምን ማስተካከያ የምታደርጉ ይመስላችኋል?
• እጃችሁ ላይ ባለው ወረቀት በአጭሩ ራእያችሁ ምን እንደሆነ ለመጻፍ ሞክሩ፡፡
ክፍል ሶስት
ለራእያችን የሚመጥን ዲሲፕሊን
“ለውድድር የሚዘጋጅ ማንኛውም ሰው በሁሉም ነገር ራሱን ይገዛል” – 1ቆሮ. 9፡25
• ዲሲፕሊን ማለት ዓላማችንን በሚመጥንና ሁለ-ገብ በሆነ መልኩ ራስን መግዛት ወይም መቆጣጠር ማለት ነው፡፡
• ዲሲፕሊን ለራእዩ ሲባል ማድረግ የማይፈልጉትን ማድረግ ወይም ማድረግ የሚፈልጉትን አለማድረግንም ይነካል፡፡
• “በሁሉም ነገር ራሱን ይገዛል” (ቁ. 25) የሚለው ሃሳብ ዲሲፐልን ሁለ-ገብ ወይም ሁለንተናዊ እንደሆነ ጠቋሚ ነው፡፡
1. ራስን በማስለመድና በማስገደድ - “ለእውነተኛ መንፈሳዊ ሕይወት ራስህን አሠልጥን” – 1ጢሞ. 4፡7
2. በትምህርትና በስልጠና - “ቅዱሳት መጻሕፍት ሁሉ የእግዚአብሔር መንፈስ ያለባቸው ናቸው፤ ለማስተማር፣ ለመገሠጽ፣ ለማቅናት በጽድቅም
መንገድ ለመምከር ይጠቅማሉ” – 2ጢሞ. 3፡16
3. በቅጣትና በቁጥጥር - “ቅጣት ሁሉ በወቅቱ የሚያሳዝን እንጂ ደስ የሚያሰኝ አይመስልም፤ በኋላ ግን ለለመዱት ሰዎች የጽድቅና የሰላም ፍሬ
ያስገኝላቸዋል” - ዕብ. 12፡11
ዲሲፕሊን ጊዜያዊ ነው
ለእውነተኛ መንፈሳዊ ሕይወት ራስህን አሠልጥን። 8የአካል ብቃት ልምምድ ለጥቂት ነገር ይጠቅማልና፤
ለእውነተኛ መንፈሳዊ ሕይወት ራስን ማሠልጠን ግን ለአሁኑም ሆነ ለሚመጣው ሕይወት ተስፋ ስላለው
ለሁለቱም ይጠቅማል” - 1ጢሞ. 4:7-8
• በዲሲፕሊን መኖር ማለት ሁል ጊዜ ራስን በማስገደድ፣ በቅጣትና በቁጥጥር መኖር ማለት ሲሆን
መጨረሻው ግን እሱ አይደለም፡፡
• በዲሲፕሊን፣ ማለትም ራስን በማስለመድና በማስገደድ፣ በትምህርትና በስልጠና፣ እንዲሁም
በቅጣትና በቁጥጥር ማድረግ የጀመርነውን ነገር ወደ ልማድ ደረጃ እስከሚደርስ ድረስ
ልንደጋግመው ይገባል፡፡
• ስለዚህም የዲሲፕሊን ዋነኛ ዓላማ አንድ ተግባር ከመደጋገሙ የተነሳ ልማድ ወደመሆን እንዲመጣ
ማድረግ ነው፡፡
ስለዲሲፕሊን ከተማርነው ሃሳብ በመነሳት ከላይ ከተጠቀሱት ዘርፎች መካከል ዲሲፕሊን የሚጠይቁት የትኞቹ እንደሆኑ ተወያዩ፡፡ ዲሲፕሊን
የሚጠይቁት ዘርፎች ምን ምን አይነት ዲሲፕሊን እንደሚጠይቁ በመወያየት ከዚህ በታች አስፍሩ፡፡
1. መንፈሳዊ ገጽታ፡-
2. የስሜት ገጽታ፡-
3. አካላዊ ገጽታ፡-
4. ማሕበራዊ ገጽታ፡-
5. የአእምሮ ገጽታ፡-
7. የገንዘብ ገጽታ፡-
ክፍል አራት
ለራእያችን የሚመጥን ባህሪይ
“እንግዲህ በጌታ እስረኛ የሆንሁ እኔ፣ ለተቀበላችሁት ጥሪ የሚገባ ኑሮ ትኖሩ ዘንድ እለምናችኋለሁ። ፍጹም ትሑታንና ገሮች ሁኑ፤ እርስ
በርሳችሁም በፍቅር እየተቻቻላችሁ ትዕግሥተኞች ሁኑ። በሰላም ማሰሪያ የመንፈስን አንድነት ለመጠበቅ ትጉ” - ኤፌ. 4፡1-3
• ጌታ ለሰጠን ራእይ ስኬታማነት ወሳኝ ከሆኑ አንጋፋ ነገሮች መካከል ባህሪያችን አንዱ ነው፡፡
• የአዲስ ኪዳን መልእክቶች ስለ ደህንነታችን ከመናገር ባሻገር የሚያወሩት የወንጌል ጥሪያችን ስለሚፈልግብን ባህሪይ ነው፡፡
• ይህ እውነታ የጌታን ስራ ከመስራታችን በፊት እኛ የመሰረታችንን ጉዳይ አስፈላጊነት ያጎላዋል፡፡
• ለተቀበልነው ጥሪና ራእይ የሚገባ ባህሪይና የኑሮ ዘይቤ የሚከተሉትን ያጠቃልላል፡፡
3. ሰላምና አንድነት፡- “ለተቀበላችሁት ጥሪ የሚገባ ኑሮ ትኖሩ ዘንድ . . . በሰላም ማሰሪያ የመንፈስን አንድነት ለመጠበቅ ትጉ” - ኤፌ. 4፡1-3
• አንድ ልብ (እምነት)፡- “ያመኑትም ሁሉ በአንድ ልብና . . . ተስማምተው ነበር” - የሐዋ. 4፡32
• አንድ ሃሳብ (ስሜትና ፈቃድ)፡- “ያመኑትም ሁሉ በአንድ . . . ሐሳብ ተስማምተው ነበር” - የሐዋ. 4፡32
• አንድ አቅርቦት (ሀብት)፡- “ያመኑትም ሁሉ . . . ያላቸውም ሁሉ የጋራ ነበር እንጂ የራሱ የሆነውን ሀብት እንኳ እንደ ግሉ የሚቈጥር
ማንም አልነበረም” - የሐዋ. 4፡32
ማጠቃለያ፡- ራእያችንን ስኬታማ በመሆኑ ሂደት ላይ የባህሪይ ጉዳይ ወሳኝና አስፈላጊ ስለሆነ ሐዋርያው በብዙ መልኩ ይገልጸዋል፡፡
1. ያበረታታል
• “ወደ መንግሥቱና ወደ ክብሩ ለጠራችሁ ለእግዚአብሔር እንደሚገባ ትኖሩ ዘንድ አበረታታናችሁ” – 1ተሰ. 2፡12
• አንዳንድ ጊዜ ለራእያችን ከሚመጥን ባህሪይ ወጣ የምንለው በአንዳንድ የሕይወት ሂደቶች ተስፋ ስንቆርጥ ነው፡፡
2. ያጽናናል
• “ወደ መንግሥቱና ወደ ክብሩ ለጠራችሁ ለእግዚአብሔር እንደሚገባ ትኖሩ ዘንድ … አጽናናችሁ”– 1ተሰ. 2፡12
• አንዳንድ ጊዜ ለራእያችን ከሚመጥን ባህሪይ ወጣ የምንለው በኃዘን ውስጥ ስንሆን ነው፡፡
3. ይለምናል
• “ወደ መንግሥቱና ወደ ክብሩ ለጠራችሁ ለእግዚአብሔር እንደሚገባ ትኖሩ ዘንድ … አጥብቀንም ለመንናችሁ” – 1ተሰ. 2፡12
• አንዳንድ ጊዜ ለራእያችን ከሚመጥን ባህሪይ ወጣ የምንለው በፍላጎት ማጣትና በግድ-የለሽነት ነው፡፡
የውይይት ሃሳቦች
ባለፈው ስልጠና ከጠቀስናቸው ሰባት የራእይ መሰረቶች መካከል የመልካም ባሪይ ጉዳይ በከፍተኛ ደረጃ የሚመለከታቸው የትኞቹ እንደሆኑ፣ ምን
አይነት መልካም ባህሪይን እንደሚጠይቁ እና የእነዚህ ባህሪያት መጉደል ምን መዘዝ ሊኖረው እንደሚችል ተወያየዩ፡፡