Download as docx, pdf, or txt
Download as docx, pdf, or txt
You are on page 1of 19

ቁጥር

ቀን

ለወላይታ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት

ሶዶ፣

ከሳሽ፡- የወላይታ ዞን ከፍተኛ ዐ/ህግ

ተከሳሾች፡-

1. ታፈሴ ሎሃ ዕድሜ 35 ሥራ አርሶ አደር አድራሻ ዳሞት ፑላሳ ወረዳ አልቶ ቀበሌ

2. መላኩ ዋና ጋላሦ ዕድሜ 25 ሥራ ተማሪ አድራሻ ዳሞት ፑላሳ ወረዳ ዴምባ ጋሌ ቀበሌ

3. ሚናሴ ዋና ጋላሦ ዕድሜ 20 ሥራ አርሶ አደር አድራሻ ዳሞት ፑላሳ ወረዳ ዴምባ ጋሌ ቀበሌ

4. ዘላለም/ጃሊያው/ዘለቀ ጥሩነህ ዕድሜ 30 ሥራ ነጋዴ አድራሻ ዳሞት ፑላሳ ወረዳ ዴምባ ጋሌ ቀበሌ

5. ተስፋዬ ሎሃ ሎራቶ ዕድሜ 28 ሥራ አህያ ጋሪ ነጅ አድራሻ ዳሞት ፑላሳ ወረዳ አቦታ ኡልቶ ቀበሌ

6. ገዛሀኝ ታፈሰሎሃ ዕድሜ 17 ሥራ ተማሪ አድራሻ ዳሞት ፑላሳ ወረዳ አቦታ ኡልቶ ቀበሌ

7. በረከት ሾሞሴ ኩንታ ዕድሜ 18 ሥራ የባጃጅ ሾፌር አድራሻ ዳሞት ፑላሳ ወረዳ አቦታ ኡልቶ ቀበሌ

8. ቾንቤ ሙላቱ ጨቱ ዕድሜ 26 ሥራ ነጋዴ አድራሻ ዳሞት ፑላሳ ወረዳ አቦታ ኡልቶ ቀበሌ

9. ባልቻ አንገና አዴማ ዕድሜ 20 ሥራ ነጋዴ አድራሻ ዳሞት ፑላሳ ወረዳ አቦታ ኡልቶ ቀበሌ

10. አጥናፉ አንግኖ አዴማ ዕድሜ 18 ሥራ ሞተር አከራይ አድራሻ ዳሞት ፑላሳ ወረዳ አቦታ ኡልቶ ቀበሌ

11. መስፍን ጌታ ግዴቦ ዕድሜ 25 ሥራ ተማሪ አድራሻ ዳሞት ፑላሳ ወረዳ አቦታ ኡልቶ ቀበሌ

12. ቴዎድሮስ ፈለቀ ጉቴ ዕድሜ 18 ሥራ ሞቴር አከራይ አድራሻ ዳሞት ፑላሳ ወረዳ አቦታ ኡልቶ ቀበሌ

13. ሚካኤል ጉቴ ሄጋኖ ዕድሜ 22 ሥራ አርሶ አደር አድራሻ ዳሞት ፑላሳ ወረዳ አቦታ ኡልቶ ቀበሌ

14. አቢቲ ታፋኖ ኮሬ ዕድሜ 19 ሥራ ተማሪ አድራሻ ዳሞት ፑላሳ ወረዳ አቦታ ኡልቶ ቀበሌ

15. ጵጵ/ጵል/ጶስ/ደበበ ጆርጌ ዕድሜ 18 ሥራ ተማሪ አድራሻ ዳሞታ ፑላሳ ወረዳ አቦ ኡልቶ ቀበሌ

16. አመነት/ወንድሙ/በቀለ ባልጣ ዕድሜ 19 ሥራ ተማሪ አድራሻ ዳሞት ፑላሳ ወረዳ ቡሻ ቀበሌ

17. በራና ባፋ ኤጹም---- ዕድሜ 35 ሥራ አርሶ አደር አድራሻ ዳሞት ፑላሳ ወረዳ ዴምባ ጋሌ

18. አየለ አንጁሎ ደሌቦ ዕድሜ 40 ሥራ ዳሞት ፑላሳ ወረዳ ዴንባ ጋሌ ቀበሌ

19. ተዋበች ታፈሴ ሌሃ ዕድሜ 21 ሥራ የቤት እመቤት አድራሻ ዳሞት ላሳ ወረዳ አቦታ ኡልቶ ቀበሌ

20. ጣላኔ ሱፋረ ያንጋጋ ዕድሜ 60 ሥራ የቤት እመቤት አድራሻ ዳሞት ፑላሳ ወረዳ አቦታ ኡልቶ ቀበሌ

21. መሠረት አብራሃም ዋንኬ ዕድሜ 35 ሥራ የቤት እመቤት አድራሻ ዳሞት ፑላሳ ወረዳ አቦታ ኡልቶ ቀበሌ

ወንጀሉ
የኢፈድሪ ወንጀል ህግ አንቀጽ 32 (1) (ሀ) (ለ) እና 539 (1)(ሀ) ላይ የተመለከተውን ድንጋጌ በመተላለፍ

የወንጀሉ ዝርዝር

ተከሳሾች አስቀድሞ ሰው ለመግደል በማሰበ በህብረት በመደራጀት ለጊዜው ካልተያዙ ተጠርጣሪዎ በረከት

ዳካ፣ ዘርሁን ዳካ፣ በቀለ ባልጣ፣ ይትባረክ ስሞኦን፣ ሀብታሙ ሉቃስ፣ ጋጋ ጦና እና ዓለሙ ቡሹሮ ጋር

በመሆን በቀን 12/02/2016 ዓ/ም ዕለተ ሰኞ ከምሽቱ 3፡00 ሰዓት በሚሆንበት ጊዜ በዳሞት ፑላሳ ወረዳ

ዴምባ ጋሌ ቀበሌ ውስጥ ልዩ ስፍራ 02 ወራንቾ ተብሎ በሚጠራበት አከባቢ ሁሉም ተከሳሾችና ያልተያዙ

ተጠርጣሪዎች በአንድነት ከእኛ ጋር ያለው ከሁሉም ይበልጣል እያሉ እየጨፈሩ ከመጡ በኃላ 1 ኛ ሟች

ታደሰ ዳና የተባለውን መኖሪያ ቤቱን በር በእርግጫ ስሰበሩ እስከ 7 ኛ ተራ ቁጥር ድረስ የተዘረዘሩ

ተከሳሾች እና ያልተያዙ በረከት ዳካ፣ ዘርሁን ዳካ እና በቀለ ባልጣ ጋር በመሆን ሟች ታደሰ ዳናን ጐትተው

ወደ ውጭ ስያወጡ 2 ኛ ተከሳሽ በራሱ ሁለት እጅ የሟች ግራ እጅ ስይዝ 3 ኛ ተከሳሽ በራሱ ሁለት እጅ

የሟች ቀኝ እጅ ስይዝ 4 ኛ ተከሳሽ አንገቱን ከለበሰው ልብስ ጋር እንቆ ስያዝ 1 ኛ ተከሳሽ እና ያልተያዙ

2 ኛ እና 3 ኛ ተጠርጣሪዎች በቀኝ እጃቸው በያዙት ቆንጮራ ሟች ታደሰ ዳናን ጭንቅላቱን ደጋሞ

በመቆረጥ ሟች ደክሞ መሬት ላይ ወድቆ ያለውን ያልተያዘው በቀለ ባልጣ እና 5 ኛ፣ 6 ኛ እና 7 ኛ

ተከሳሾች ጋር በመሆን ሟች በወደቀበት በያዙት ፌሮ ብረት ጭንቅላቱን ደጋግሞ በመምታት ጉዳት

ሲያደርሱ የሟች ጨኸት ስምተው ለማትረፍ የመጣውን 2 ኛ ሟች መስፍን ተካ የተባለውን

1 ኛ፣2 ኛ፣3 ኛ፣4 ኛ፣5 ኛ፣6 ኛ፣7 ኛ፣8 ኛ፣9 ኛ፣10 ኛ 11 ኛ ተከሳሾ ካልተያዙ በረከት ዳካ፣ ዘርሁን ዳካ፣

በቀለ ባልጣ እና ይትባረክ ስሞኦን ጋር በመሆን በግራ እጃቸው ፌሮ ብረት ይዞ 2 ኛ ሟች መስፍን ተካን

ጭንቅላቱን ደጋግሞ በመምታት ጉዳት ስያደርሱ ሟች መሬት ላይ ወድቆ እያለ 1 ኛ ተከሳሽን ያልተያዙ

በረከት ዳካ እና ዘርሁን ዳካ በቀኝ እጃቸው በያዙት ቆንጮራ ደጋግሞ ጭንቅላቱን በመቁረጥ ጉዳት

አድርሶ የሟች ህይወት እንድያልፍ ስያደረጉ ከ 12 ኛ ተራ ቁጥር እስከ 22 ኛ ተራ ቁጥር የተጠቀሱ

ተከሳሾች ለጊዜው ካልተያዙ ጋጋ ጦና እና አለሙ ቡሽሮ ከተባሉት ጋር በመሆን በእጃቸው ፌሮ ብረት እን

ቆንጮራ በመያዝ የሟቾችን ህይወት ለማትረፍ የደረሱ ሰዎን ለማከረር እንዲሁም ከመታቸው

እንዳይወጡ በራፋቸው ላይ በመቆም ከልክሎ እያሉ

1 ኛ፣2 ኛ፣3 ኛ፣4 ኛ፣5 ኛ፣6 ኛ፣7 ኛ፣8 ኛ፣9 ኛ፣10 ኛ፣11 ኛ እና ያልተያዙ በረከት ዳካ፣ ዘርሁን ዳካ፣ በቀለ

ባልጣ እና ይትባረክ ስሞኦን ጋር በመሆን ከ 1 ኛ ሟች ታደሰ ዳና ቤት ሁለት በሬቃችን----- መልካቸው

ቀይ የሆኑትን የሁለቱ ዋጋ 100,000 (አንድ መቶ ሺህ) ብር የሚያወጡትንና ጥሬ ብር 100,000 (አንድ

መቶ ሺህ) ብር ሣጥን ሰብሮ ስወስዱ ከ 1 ኛ ተራ ቁጥር እስከ 17 ኛ ተራ ቁጥር የተጠቀሱ ተከሳሾች

ካልተያዙ በረከት ዳካ፣ ዘርሁን ዳካ፣ በቀለ ባልጣ፣ ይትባረክ ስሞኦን፣ ሀብታሙ ሉቃስ፣ጋጋ ጦና እና አሉሙ
ቡሹሮ ጋር በመሆን ከ 2 ኛ ሟች መስፍን ተካ መኖሪያ ቤት አንድት መልኳ ቀይ የሆነችውን የወተት ላ

50,000 (ሃምሳ ሺህ) ብር የሚታወጣውንና ጥሬ ብር 50,000 (ሃምሳ ሺኅ) ብር የልብስ ሳጥን ሰብሮ ይዞ

የሄዱ ስለሆነ ተከሳሾች በዋና ወንጀል ተከፋይነት በፈጸሙት ከባድ የሰው መግደል ወንጀል ተከሷል፡፡

የሰው ማስረጃ

1. ወንድሙ ታደሰ ዳና ዕድሜ 30 ሥራ ሞተር አከራይ አድራሻ ዳሞት ፑላሳ ወረዳ ደምባ ጋ ቀበሌ

2. ተስፋየየ ተካ ሙኩሎ ዕድሜ 28 ሥራ አርሶ አደር አድራሻ ዳት ፑላሳ ወረዳ ዴምባ ጋሌ ቀበሌ

3. ታፈሴ ቶራ ሙኩሎ ዕድሜ 33 ሥራ አርሶ አደር አድራሻ ዳሞት ፑላሳ ወረዳ ቡሻ ቀበሌ

4. ፍሬው ታደሰ ዳና ዕድሜ 28 ሥራ ሞተረኛ አድራሻ ዳሞት ፑላሳ ወረዳ ደምባ ጋሌ ቀበሌ

5. ተገኝ ታፈራ ሙኩሎ ዕድሜ 28 ሥራ ሞተረኛ አድራሻ ዳሞት ፑላሳ ወረዳ ደምባ ጋሌ ቀበሌ

6. ትዕዛዙ ጃልዳ----- ጀርሳ ዕድሜ 25 ሥራ አርሶ አደር አድራሻ ዳሞት ፑላሳ ወረዳ ደምባ ጋሌ ቀበሌ

የሰነድ ማስረጃ

1. በቁጥር 4/298/30/7/14 በቀን 29/02/2016 ዓ/ም ከወላይታ ሶዶ ሆስፒታል የተሰጠ የ 1 ኛ ሟች

ታደሰ ዳና የህክምና ማስረጃ 01 ገጽ

2. በቁጥር 4/297/30/7/14 በቀን 29/02/2016 ዓ/ም ከወላይታ ሶዶ ሆስፒታ የተሰጠ የ 2 ኛ ሟች

መስፍን ተካ የህክምና ማስረጃ 01 ገጽ

3. ሁለቱ ሟቾችን የሚሳይ ባለ ቀለም ፎቶ ግራፍ ብዛት 2 ከመዝገቡ ጋር ተያይዟል


ማሳሰቢያ
ተከሳሾችን ሶዶ ማረሚያ ተቋም ያቀረባቿል፡፡
ቁጥር
ቀን
ለወላይታ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት
ሶዶ፣
ከሳሽ፡- የወላይታ ዞን ከፍተኛ ዐ/ህግ
ተከሳሾች ፡- 1. ታደለች ወ/ማሪያም ፆታ ሴት ዕድሜ 28 ስራ የቤት እመበት አድራሻ ቦ/ሶሬ ወረዳ አቹራ
ማዘጋዛ
2. ሀብታሙ አብርሃም ጨምሶ ፆታ ወንድ ዕድሜ 20 ሥራ አ/አድር አድራሻ ቦ/ሶሬ ወረዳ አቹራ ማዘጋዛ
3. አፈወርቅ አብርሃም ጨምሶ ፆታ ወንድ ዕድሜ 18 ሥራ ተማሪ አድራሻ ቦ/ሶሬ ወረዳ አቹራ ማዘጋጃ
4. አለሚቱ አብርሃም ጨምሶ ፆታ ሴት ዕድሜ 27 ሥራ የቤት እመበት አድራሻ ቦ/ሶሬ ወረዳ አቹራ
ማዘጋጃ
5. ሣራ አብርሃም ፆታ ሴት ዕድሜ 19 ሥራ ተማሪ አድራሻ ቦ/ሶሬ ወረዳ አቹራ ማዘጋጃ
6. አረጋሽ አብርሃም ጨምሶ ፆታ ሴት ዕድሜ 122 ሥራ የቤት እመበት አድራሻ ቦ/ሶሬ ወረዳ አቹራ
ማዘጋጃ
7. በረከት አብርሃም ጨምሶ ፆታ ወንድ ዕድሜ 19 ሥራ አ/አደር አድራሻ ቦ/ሶሬ ወረዳ አቹራ ማዘጋጃ
ወንጀሉ
የኢ/ወ/ህ/አ 32-1-ሀ እና 671 -1-ሀ- የተመለከተውን በመተላለፍ
የወንጀሉ ዝርዝር
ተከሳሾ በቀን 26/04/2016 ዓ/ም አርብ እለት ከጧቱ 2፡00 ሰዓት በሚሆንበት ጊዜ በቦሎሶ ሶሬ ወረዳ አቹራ
ማዘጋጃ ልዩ ቦታው ለጊዜው ካልተያዘችው አይናለም አብርሃም ጨምሶ ጋር በመሆን የአንድ በተሰብ አካል
የሆኑት በአንድነት በእጃቸው ዱላና ፔሮ በመያዝ የግል ተበዳይ አቶ ማቴዎስ ጆርጌ ሄበና መኖሪያ ቤቱ ድረስ
በመሄድ የመኖሪያውን በር በርግደው በመግባት 1 ኛ ተከሳሽ በቁጥር ሶስት እንስራ ስትሰብር 3 ኛ ተከሳሽ ጓዳ
በምግባት ቡና ሽጣ ያስቀመጠውን 30,000 (ሰላሳ ሺህ) ብር ከሳጥን ውስጥ በመውሰድ ይህ ብቻ አይደለም
አንተን በዚህ ቤት አናኖርም በማለት በከፍተኛ ሁኔታ የዛቱ ስለሆነ የማይገባ ብልፅግና ለማግኘት በማሰብ
በፈፀሙት ወንብድና ወንጀል ተከሷል፡፡

የሰው ማሳረጃዎች
1. አቶ ማቴዎስ ጆርጌ ሄባና ፆታ ው ዕድሜ 40 ሥራ ------ አድራሻ ቦ/ሶሬ ወረዳ አቹራ ማዘጋጃ
2. ወ/ሮ ብዙነሽ ከበደ ጨምሶ ፆታ ሴ ዕድሜ 35 ሥራ ነጋዴ አድራሻ ቦ/ሶሬ ወረዳ አቹራ ማዘጋጃ
3. ወ/ሮ ርብቃን ከበደ ጨምሶ ፆታ ሴ ዕድሜ 26 ሥራ ነጋዴ አድራሻ ቦ/ሶሬ ወረዳ አቹራ ማዘጋጃ
4. ወ/ሮ ሙሉነሽ ከበደ ጨምሶ ፆታ ሴ ዕድሜ 30 ሥራ የቤት እመበት አድራሻ ቦ/ሶሬ ወረዳ አቹራ ማዘጋጃ
የሰነድ ማስረጃ
- ከቁጥር 336/4/2016/8/09/16 በቀን 26/04/2016 ዓ/ም በግል ተበዳይ ላይ ወንጀል ስለመፈፀሙ ከአቹራ
ማዘጋጃ የተፃፈ የድጋፍ ደብዳቤ 01 ገጽ
- በግል ተበዳይ ንብረት/በር/ላይ ጉዳት ስለመድረስ የሚገልፅ ባለ ቀለም ፎቶ ግራፍ 02 ገጽ

ቁጥር
ቀን
ለወላይታ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት
ሶዶ፣
ከሣሽ፡- የወላይታ ዞን ከፍተኛ ዐቃቤ ሕግ
ተከሣሾች፡-
1. ታምሬ ታንቴቦ ዕድሜ 40 ሥራ አ/አደር አድራሻ ዳሞት ፑላሣ ወረዳ ኡልቴ ቀበሌ
2. ወንድሙ ደጀኔ ዳና ዕድሜ 20 ሥራ አ/አደር አድራሻ ዳሞት ፑላሣ ወረዳ ህ/ቆርኬ ቀበሌ
3. ማርቆስ ላቆ ላቢሶ ዕድሜ 30 ሥራ አ/አደር አድራሻ ዳሞት ፑላሣ ወረዳ ህ/ቆርኬ ቀበሌ
4. ፈቃዱ ዳና ዳድሶ ዕድሜ ሥራ አ/አደር አድራሻ ዳሞት ፑላሣ ወረዳ ህ/ቆርኬ ቀበሌ
ወንጀሉ
የኢፌዴሪ ወንጀል ህግ አንቀድ 32(1)(ሀ)፣ 59-1- እና 543-1- ላይ የተመለከተውን መተላለፍ
የወንጀሉ ዝርዝር
ተከሣሾች በቀን 15/11/2015 ዓ.ም ከቀኑ 6፡30 በሚሆንበት ጊዜ በዳሞት ፑላሣ ወረዳ በቡሻ ቀበሌና በህሊና ቆርኬ ቀበሌ
ድንበር አካባቢ ሟች ዳዊት እርሾ የተባለውን 1 ኛ ተከሣሽ ቤት መብራት ተበላሽቷል በማለት ጠርተውት አምጥተው
መብራት እንድሠራ ካደረገ በኋላ ቆጣሪ ሳይዘጉ ተዘግቷል በማለት ከ 2 ኛ እስከ 4 ኛ ያሉት ተከሣሾች ያልተዘጋውን ቆጣሪ
ዘግተናል በማለት ሟች በመብራት አደጋ እንድሞት ያደረጉ ስለሆነ ሆን ብለው በፈፀሙት በቸልተኝነት የሰውን ህይወት
በማጥፋት ወንጀል ተከሰዋል፡፡
የሰው ማስረጃ
1. ወ/ሮ አማረች ኤሊያስ ኪይራ ዕድሜ 27 ሥራ ነጋዴ አድራሻ ዳሞት ፑላሣ ወረዳ ደንባ ጋሌ ቀበሌ
2. ወ/ሮ ባሊጌ እራሻ እልታሞ ዕድሜ 20 ሥራ ነጋዴ አድራሻ ዳሞት ፑላሣ ወረዳ ደንባ ጋሌ ቀበሌ
3. ወ/ሮ ብዙነሽ እራሻ ኤጨሮ ዕድሜ 25 ሥራ የቤት እምቤት አድራሻ ዳሞት ፑላሣ ወረዳ ለማረዳ
ቀበሌ
4. እልፍነሽ እራሻ ኤጨሮ ዕድሜ 30 ሥራ የቤት እምቤት አድራሻ አባላ አባያ ወረዳ ፋራቾ ቀበሌ

የሰነድ ማስረጃ
- በቁጥር 4/1065/71/14 በቀን 09/12/2015 ዓ.ም ከወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ጤና ሳይንስና ማስተማሪያ
የተፃፈ የአስክሬን ምርመራ ውጤት 01 ገጽ
- ሟች ስለመሞቱ የሚገልፅ ባለቀለም ፎቶ ግራፍ ማስረጃ 07 ገጽ

ማሳሰቢያ፡- ተከሣሾችን የማረሚያ ፖሊስ ያቀርባል፡፡


ቁጥር
ቀን
ለወላይታ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት
ሶዶ፣
ከሣሽ፡- የወላይታ ዞን ከፍተኛ ዐቃቤ ሕግ
ተከሣሾች፡-
5. ተዘራ ተሾመ ቦርኩ ዕድሜ 27 ሥራ የግል አድራሻ ቦዲቲ ከተማ አስ/ር ሸዋ በር ቀበሌ
6. ምህረቱ /ታምራት/ ተሾመ ቦርኩ ዕድሜ 23 ሥራ አጥ አድራሻ ቦዲቲ ከተማ አስ/ር ሸዋ በር ቀበሌ
7. ታከለ /ኩሉ/ ተሾመ ቦርኩ ዕድሜ 24 ሥራ የግል አድራሻ ቦዲቲ ከተማ አስ/ር ሸዋ በር ቀበሌ
ክስ አንድ ሁለንም ተከሣሾችን ይመለከታል
ወንጀሉ
የኢፌዴሪ ወንጀል ህግ አንቀድ 32(1)(ሀ) እና 555 (ለ) ላይ የተመለከተውን በመተላለፍ
የወንጀሉ ዝርዝር
ተከሣሾች በቀን 30/08/2015 ዓ.ም ዕለተ ሰኞ ከምሽቱ 1፡30 ሰዓት በሚሆንበት ጊዜ በቦዲቲ ከተማ አስ/ር ሸዋ በር ቀበሌ
ልዩ መጠሪያ ቦዲቲ ዶጌ ቀጠና አባይነህ ኩኬ መኖሪያ ቤት አካባቢ የግል ተበዳይ ኢያሱ ገላን የተባለው በዕለቱ በተከሣሾች
ቤት በዲኤስቲቪ ኳስ ጫዋታ ተከታትሎ ወደ ቤቱ እየተመለሰ ያለውን 1 ኛ ተከሣሽ በእጁ ዱላ በመያዝ በኋላ በኩል
በመምጣት የግል ተበዳይ ጉንጭ ላይ አንድ ጊዜ ስመታው የለኛው የኋላ ትልቁ ጥርስ በቁጥር 3(ሶስት) ሰሸራረፍ የግል
ተበዳይ መሬት ላይ ስወድቅ 2 ኛ ተከሣሽ በያዘው ዱላ በወደቀበት ቀኝ በኩል ጉንጭ ላይ አንድ ጊዜ በመታት በ 1 ኛ
ተከሣሽ ተመተው የተጎዱ ሶስት ጥርሶች እንደገና እንድጎዱ ስያደረግ 3 ኛ ተከሣሽ በያዘው ዱላ ቀኝ በኩል ጐን ላይ አንድ
ጊዜ ለመታት ጉዳት ያደረሱ ስለሆነ ተከሣሾች አስቦ በሌላ ሰው አካል ላይ ከባድ ጉዳት ማድረግ ወንጀል ተከሷል፡፡
ክስ ሁለት በሁለንም ተከሣሾችን ላይ
ወንጀሉ
የኢፌዴሪ ወንጀል ህግ አንቀድ 32(1)(ሀ) እና 670 ላይ የተመለከተውን በመተላለፍ
የወንጀሉ ዝርዝር
ተከሣሾች ተገቢ ያልሆነ ብልጽግና ለራሳቸው ለማግኘት በማሰብ በክስ 1 ላይ በተጠቀሰው ቀን፣ ወር፣ ዓ.ም ቦታ እና
ሁኔታ የግል ተበዳይ ኢያሱ ገላን የተባለውን 1 ኛ ተከሣሽ ሳሚንስግ ሞባይል መልኩ ሰማያዊ 12,000 ብር የሚያወጣውን
ከፊት ሱሪ ክስ ስወስድ 2 ኛ ተከሣሽም የውጤቱ ተከፋይ በመሆን በዱላ የቀኝ ጉንጩን አንድ ጊዜ ስመታው የግል ተበዳይ
ስወድቅ 3 ኛ ተከሣሽ ከቀኝ በኩል ከፊት ለፊት ሱሪ ክስ ውስጥ 6000 /ስድስት ሺህ/ ባለሁለት መቶ ኖት የወሰደ በመሆኑ
ተከሣሾች በህብረት በፈፀሙት ወንብድና ወንጀል ተከሷል፡፡

የሰው ማስረጃ
5. ኢያሱ ገላን ጋናሞ ዕድሜ 22 ሥራ ሾፌር አድራሻ ቦዲቲ ከተማ ሸዋ በር ቀበሌ
6. አድሱ ጋንታ ዕድሜ 26 ሥራ የታክስ ሾፌር አድራሻ ቦዲቲ ከተማ ሸዋ በር ቀበሌ
7. ብሩክ ፋንታ ዕድሜ 25 ሥራ የታክስ ሾፌር አድራሻ ቦዲቲ ከተማ ሸዋ በር ቀበሌ
8. ፈለቀ ፋንታ ዕድሜ 32 ሥራ የቀን ሠራተኛ አድራሻ ቦዲቲ ከተማ ሸዋ በር ቀበሌ

የሰነድ ማስረጃ
- ከቦዲቲ ከተማ መጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል በቁጥር በመደሆ 8047/12/2015 በቀን 08/09/2015 ዓ.ም
የተፃፌ 01 ገጽ የሕክምና ማስረጃ
ቁጥር
ቀን
ለወላይታ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት
ሶዶ፣
ከሣሽ፡- የወላይታ ዞን ከፍተኛ ዐቃቤ ሕግ
ተከሣሾች፡-
1. ሞገስ ወንጃሎ ዳና ዕድሜ 40 ሥራ አርሶ አደር አድራሻ ቦሎሶ ሶሬ ወረዳ ባሣ ጐፋራ ቀበሌ
2. ፋንታሁን ፋንጨ ዴቢሣ ዕድሜ 25 ሥራ ነጋዴ አድራሻ ቦሎሶ ሶሬ ወረዳ ባሣ ጐፋራ ቀበሌ
3. ማትዎስ ጐዳቶ ጐዳና ዕድሜ 26 ሥራ ነጋዴ አድራሻ ቦሎሶ ሶሬ ወረዳ ባሣ ጐፋራ ቀበሌ
4. በረከት መሸሸ ወንጀሎ ዕድሜ 26 ሥራ ተማሪ አድራሻ ቦሎሶ ሶሬ ወረዳ ባሣ ጐፋራ ቀበሌ
ወንጀሉ
የኢፌዴሪ ወንጀል ህግ አንቀድ 32(1)(ሀ) እና 670 ላይ የተመለከተውን በመተላለፍ
የወንጀሉ ዝርዝር
ተከሣሾች ተገቢ ያልሆነ ብልጽግና ለራሳቸው ለማግኘት ወይም ለሌላ ሰው ለማስገኘት በማሰብ በቀን
07/10/2015 ዓ.ም ዕለተ ረብዕ ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ለሚሆንበት ጊዜ በቦሎሶ ሶሬ ወረዳ ባሣ ጐፋራ ቀበሌ ልዩ መጠሪያ
ነዋሴ ተብሎ በሚጠራበት አካባቢ የግል ተበዳይ አሸናፊ አስራት የተባለው የወላጅ እናቱ ላሞች በሌባ ተወስዶ እናቱ
ባሰማችሁ ጩኸት መነሻ ሮጦ የደረሰውን 1 ኛ ተከሣሽ በቀኝ እጅ የግል ተበዳይ ዓይን አካባቢ ጉንጭ ላይ ሁለት ጊዜ
በቦክስ በመምታት ጉዳት ስያደርስ 2 ኛ ተከሣሽ በያዘው ዱላ አንድ ጊዜ ቀኝ በኩል ትኬሻ ላይ ጉዳት ስያደርስ 3 ኛ
ተከሣሽ በያዘው ዱላ አንድ ጊዜ ግራ በኩል ጃርባ ላይ ከመታ በኋላ ጀርባው ላይ በእርግጫ አንድ ጊዜ በመምታት ጉዳት
ስያደረስ የግል ተበዳይ ስወድቅ 4 ኛ ተከሣሽ በየግል ተበዳይ በወደቀበት ግራ በኩል ጐድን ላይ በእርግጫ በመምታት ጉዳት
ካደረሰ በኋላ ከሱሪ ኪስ ውስጥ መልኩ ሰማያዊ እንፍንክስ ታች ስክሪን ሞባይል ስልክ ዋጋው 9,000 /ዘጠኝ ሺህ ብር/
የሚያወጣውን ይዞ ያመለጠ በመሆኑ ተከሣሾች በዋና ወንጀል ተከፋይነት በህብረት በፈፀሙት ውንብድና ወንጀል
ተከሷል፡፡

የሰው ማስረጃ
1. አሸናፊ አስራት ኩሼ ዕድሜ 24 ሥራ ተማሪ አድራሻ ቦሎሶ ሶሬ ወረዳ ጦቅሳ ጐዳ ቀበሌ
2. አማረች አያኖ ባዳቾ ዕድሜ 30 ሥራ የቤት እመቤት አድራሻ ቦሎሶ ሶሬ ወረዳ ጦቅሳ ጐዳ ቀበሌ
3. ኤልሳዬ ዳንኤል ኦርሣጐ ዕድሜ 20 ሥራ ነጋዴ አድራሻ ቦሎሶ ሶሬ ወረዳ ጦቅሳ ጐዳ ቀበሌ

የሰነድ ማስረጃ
- ከአረካ ከተማ ጤና አጠባበቅ ጣቢያ በቀጥር 12348/15 በቀን 15/10/15 ዓ.ም የተፃፌ 01 ገጽ የህክምና
ማስረጃ፡፡

ማሳሰቢያ፡- ተከሣሾችን የቦሎሶ ሶሬ ወረዳ ፖሊስ ያቀርባል፡፡


ቁጥር
ቀን
ለወላይታ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት
ሶዶ፣
ከሣሽ፡- የወላይታ ዞን ከፍተኛ ዐቃቤ ሕግ
ተከሣሾች፡-
1. ታምራት ጅንጋ ጋጌቦ ዕድሜ 35 ሥራ አርሶ አደር አድራሻ ዳሞት ጋሌ ወረዳ አካ ቢሎ ቀበሌ
2. ታጁራ ጅንጋ ጋጌቦ ዕድሜ 27 ሥራ አርሶ አደር አድራሻ ዳሞት ጋሌ ወረዳ ጃጌ ከተማ
3. ሞጐስ ጅንጋ ጋጌቦ ዕድሜ 48 ሥራ ሥራ አጥ አድራሻ ዳሞት ጋሌ ወረዳ አካ ቢሎ ቀበሌ
ወንጀሉ
የኢፌዴሪ ወንጀል ህግ አንቀድ 27(1) እና 539(1)(ሀ) ላይ የተመለከተውን በመተላለፍ
የወንጀሉ ዝርዝር
ተከሣሾች ለጊዜው ካልተያዙ ምትኩ ጅንጋ እና አማኖ ጅንጋ ከተባሉት ጋር በመሆን በቀን 30/04/2015 ዓ.ም ዕለተ እሁድ
ከምሽቱ 2፡00 ሰዓት በሚሆንበት ጊዜ በዳሞት ጋሌ ወረዳ ጃጌ ከተማ ልዩ መጠሪያ ዳሞታ በር ተብሎ በሚጠራበት
አካባቢ የግል ተበዳይ ----- የተባለው ከጃጌ ከተማ ገቢያ እየተመለሰ መኖሪያ ቤቱ በራፍ ስድርስ ያለምንም በቂ ምክንያት
1 ኛ ተከሣሽ በያዘው ቆንጮራ ግራ በኩል ጭንቅላቱ አናቱ ላይ አንድ ጊዜ በመቁረጥ ከፍተኛ ደም እንድፈሰስ በማድረግ
ጉዳት ስያደርስ 2 ኛ ተከሣሽ በያዘው ጦር በግል ተበዳይ ላይ ወርውረው ስያመልጥ 3 ኛ ተከሣሽ 1 ኛ፣ 2 ኛ እና ያልተያዙ
ሁለት ተከሣሾችን --- ወደ ቤት ገብታችሁ አትልቀቁ በማለት የድርጊቱ ቀጥታ ተካፋይ በመሆን ሂደቱን የመራ ስለሆነ
ተከሣሾች በህብረት በፈፀሙት መግደል ሙከራ ወንጀል ተከሷል፡፡

የሰው ማስረጃ
1. ኡሩቶ ዋልአ ዋለና ዕድሜ 45 ሥራ አርሶ አደር አድራሻ ዳሞት ጋሌ ወረዳ ጃጌ ከተማ
2. አለምቱ አይዛ ጐዳቶ ዕድሜ 28 ሥራ ነጋዴ አድራሻ ዳሞት ጋሌ ወረዳ ጃጌ ከተማ
3. ሄለን ኡሩቶ ዋልአ ዕድሜ 18 ሥራ ነጋዴ አድራሻ ዳሞት ጋሌ ወረዳ ጃጌ ከተማ

የሰነድ ማስረጃ
- ከዳሞት ጋሌ ወረዳ አዴ ጃጌ ጤና አጠባበቅ ጣቢያ በቁጥር አድጤ/2517/15 በቀን 22/07/2015 ዓ.መረ
የተሰጠ 01 ገጽ የህክምና ማስረጃ ፡፡

ማሳሰቢያ፡- ተከሣሾችን የዳሞት ጋሌ ወረዳ ፖሊስ ያቀርባል፡፡


ቁጥር
ቀን
ለወላይታ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት
ሶዶ፣
ከሣሽ፡- የወላይታ ዞን ከፍተኛ ዐቃቤ ሕግ
ተከሣሽ፡- ታምራት ኢያሱ አይዛ ዕድ 25 ሥራ የቀን ሠራተኛ አድራሻ ሶዶ ከተማ ኪዳኔ ምህረት ቀበሌ
ወንጀሉ
የኢፌዴሪ ወንጀል ህግ አንቀድ 670 ላይ የተመለከተውን በመተላለፍ
የወንጀሉ ዝርዝር
ተከሣሽ የማይገባ ብልጽግና ለራሱ ለማግኘት ወይም ለሌላ ሰው ለማስገኘት በማሰብ በቀን 14/10/2015 ዓ.ም ዕለተ
ረብዕ አመሻሽ 12፡30 ሰዓት በሚሆንበት ጊዜ ቦዲቲ ከተማ አስ/ር መሐል ቀበሌ ዶጌ ቀጠና ልዩ መጠሪያ መኪና መናኸሪያ
ፊት ለፊት የግል ተበዳይ ሀይሉ ኡሽላ የተባለው ሹቅ ዕቃ ሽጦ ወደ ቤቱ እየሄደ ያለውን ተከሣሽ ሌሎች ያልተያዙና
ማንነታቸው የማይታወቁ ሰዎች ጋር በመሆን የግል ተበዳይን ሎቶሪ አንተን ደርሷል በማለት አደናግሮት ማንነታቸው
የማይታወቁና ያልተያዙ ሰዎች አንቀው ስይዙ ከለበሰው ሸሚዝ ከፊት ለፊት ደረጃ ኪስ ባለሁት መቶ ኖት 30 እና
ባለአንድ መቶ 10 ኖት ተቀላቅሎ ያለውን 70,000 /ሰባ ሺህ/ ብር ወስዶ ያልተያዙ ተጠርጣሪዎች ገፍትሮ መሬት ላይ
ስጥሉ ከኪሱ የኢት/ያ ንግድ ባንክ ኤቲኤም እና የቀበሌ መታወቂያ ከጥቁር ቦርሣ ከኋላ ክስ ወስዶ ላልተያዙ
ተጠርጣሪዎች ስሰጥ ብሩን የኤቲኤም እና የባንክ ደብቴር ይዞ ሮጦ ስያመልጡ ተከሣሽን የመንገድ ትራፊክ ፖሊስ ይዘው
ለፖሊስ ያስረከበ ስለሆነ በፈፀመው ውንብድና ወንጀል ተከሷል፡፡

የሰው ማስረጃ
1. ሀይሉ ኡሻለ ኡርዳ ዕድሜ 24 ሥራ ነጋዴ አድራሻ ቦዲቲ ከተማ አስ/ር ሸዋ በር ቀበሌ
2. ቡዙአየሁ ጃታ ዕድሜ 28 ሥራ የመንግስት አድራሻ ቦዲቲ ከተማ አስ/ር ሸዋ በር ቀበሌ
3. አሚና ኢባቴ ዕድሜ 30 ሥራ የመንግስት አድራሻ ቦዲቲ ከተማ አስ/ር ሸዋ በር ቀበሌ

የእግዝብት ማስረጃ
- ተከሣሽ የወንብድና ወንጀል ለመፈፀም አስቦ ያልደረሰውን ፈጣን ሎቶሪ ደርሷል በማለት ለወንጀሉ
የተጠቀመበት ፈጣን ሎቶሪ እስከ 75,000 ብር የሚደርስ የጎን ቁጥር 001-2007 እና 028624-30
የሆነውን አንድ ፍሬ ከተከሣሽ እጅ የተያዘ ከመዝገቡ ጋር ተያይዟል ፡፡

ማሳሰቢያ፡- ተከሣሹን ቦዲቲ ከተማ ፖሊስ ያቀርባል፡፡


ቁጥር
ቀን
ለወላይታ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት
ሶዶ፣
ከሣሽ፡- የወላይታ ዞን ከፍተኛ ዐቃቤ ሕግ
ተከሣሽ፡- አስፋው ጫሬ አዳማ ዕድሜ 21 ሥራ ሞተረኛ አድራሻ ጠበላ ከተማ አስ/ር አምባና ቀበሌ
ወንጀሉ
የኢፌዴሪ ወንጀል ህግ አንቀድ 670 ላይ የተመለከተውን በመተላለፍ
የወንጀሉ ዝርዝር
ተከሣሽ ለጊዜው ካልተያዙ 1 ኛ መንግሥቱ መስቀሌ 2 ኛ ዝናቡ አባተ ጋር በመሆን በቀን 29/08/2015 ዓ.ም ዕለተ ቅዳሜ
ከምሽቱ 1፡30 ሰዓት በሚሆንበት በጠበላ ከተማ አስ/ር አምባና ቀበሌ ልዩ መጠሪያ መንደር 03 ቅቤ ተራ ተብሎ
በሚጠራበት አካባቢ የግል ተበዳይ ታራፎ ፈለቀ የተባለውን ያልተያዘው መንግስቱ መስቀሌ የተባለው ድንጋይ አንስተው
ደረት ላይ በመወገር ገደ--- በወደቀበት ከቀኝ በኩል ሱሪ ክስ ውስጥ 5,000 /አምስት ሺህ/ ብር ስወስድ ዝናቡ አባቴ
የተባለው ለጊዜው ያልተያዘ ግራ በኩል አገጭ በቀኝ እጁ በቦክስ በመምታት ጉዳት ስያደርስ ያሁኑ ተከሣሽ ድንጋይ
ከመሬት በቀኝ እጁ በማንሳት የግል ተበዳይ የቀኝ እግር ከጉልበት በታች አጥንት ላይ በመወገር ጉዳት ካደረሰ በኋላ ቴክኖ
ሞባይል ታች ስክሬን 6500 /ስድስት ሺህ አምስት መቶ ብር የሚያወጣውን ይዞ ያመለጠ ስለሆነ በፈፀመው ውንብድና
ወንጀል ተከሷል፡፡

የሰው ማስረጃ
1. ታራፎ ፈለቀ ጃታ ዕድሜ ..... ሥራ የእንጨት ሥራ አድራሻ ጠበላ ከተማ አስ/ር አምባና ቀበሌ
2. ማርቆስ ማቴዎስ ዕድሜ .... ሥራ ተማሪ አድራሻ ሁምቦ ወረዳ ሶሬ ጠውራታ ቀበሌ
3. ክፍሌ ወጋሶ ዕድሜ... ሥራ ሥራ አጥ አድራሻ ሁምቦ ወረዳ ሶሬ ጠውራታ ቀበሌ
4. ምህረት ካለብ ዕድሜ የቀን ሠራተኛ አድራሻ ሁምቦ ወረዳ ሶሬ ጠውራታ ቀበሌ

የሰነድ ማስረጃ
- ከጠበላ መጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል በቁጥር ጠ/መ/ደ/ሆ/08/3296 በቀን 21/09/2015 ዓ.ም የተሰጠ 01
ገጽ የህክምና ማስረጃ፡፡

ማሳሰቢያ፡- ተከሣሹን ጠበላ ከተማ ፖሊስ ያቀርባል፡፡


ቁጥር
ቀን
ለወላይታ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት
ሶዶ፣
ከሣሽ፡- ወላይታ ዞን ከፍተኛ ዐ/ሕግ
ተከሣሽ፡-እታለም ኤፌሶን ጫሎፎ ዕድሜ 20 ሥራ የግል አድራሻ ዳሞት ሶሬ ወረዳ ሱንቃሌ
ገጠር ቀበሌ
ወንጀሉ
በሰው መነገድ እና ሰውን በሕገ-ወጥ መንገድ ድንበር የማሻገር ወንጀልን ለመከላከልና
ለመቆጣጠር የወጣ አዋጅ ቁጥር 1178/2012 አንቀጽ 3(2) (3) ሥር የተደነገገውን በመተላለፍ
የተፈፀመ
የወንጀሉ ዝርዝር
ተከሳሿ በቀን 04/08/2015 ዓ.ም፣ ከቀኑ 11፡30 በሚሆንበት ሰዓት በዳሞት ሶሬ ወረዳ አንጩቾ 01 ቀበሌ ልዩ
ስሙ መሬ ሙስጣፋ ቡና መፈልፈያ ተብሎ በሚጠራበት አካባቢ የግል ተበዳይ ሕፃን ትንሣኤ ፀጋዬ
የተባለችውን የ 8 ዓመት ልጅ ከቤት ሰፈር ተልካ እየሄደች ያለችውን እኔ አድስ ልብስና ጫማ እገዛልሻለሁ ከእኔ
ጋር ከተማ ሄደሽ ከዚህ የተሻለ ኑሮ ትኖሪያለሽ በማለት አታልላ ይዛ ስትሄድ በአካባቢ ህብረተሰብ ጥቆማ
የተያዘች ስለሆነ በፈፀመችው በሰው መነገድ ወንጀል ተከሳለች፡፡

የሰው ማስረጃ
1. ሕፃን ትንሳኤ ፀጋዬ ዕድሜ 8 ሥራ ተማሪ አድራሻ አንጩቾ 01 ቀበሌ
2. ወ/ሮ እታለም ሶርሳ ዕድሜ 27 ሥራ የመንግስት ሠራተኛ አድራሻ አንጩቾ 01 ቀበሌ
3. ወ/ሮ አስራት ኡጉዬ ዕድሜ 40 ሥራ የቤት እመቤት አድራሻ ሱንቃለ ቀበሌ
4. መ/ር ፀጋዬ አስፋው ዕድሜ 38 ሥራ የመንግስት ሠራተኛ አድራሻ አንጩቾ 01 ቀበሌ
5. አቶ አየለ አስፋው ዕድሜ 38 ሥራ የመንግስት ሠራተኛ አድራሻ አንጩቾ 01 ቀበሌ

ማሳሰቢያ፡- ተከሣሿን የዳሞት ሶሬ ወረዳ ፖሊስ ያቀርባል፡፡

ቁጥር
ቀን
ለወላይታ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት
ሶዶ፣
ከሣሽ፡- ወላይታ ዞን ከፍተኛ ዐ/ሕግ
ተከሣሾች፡-
1. ስንታየሁ ታንጋ ዕድሜ 25 ሥራ ተማሪ አድራሻ ገሱባ ከተማ አስተዳደር 02 ቀበሌ
2. አድሱ ታንጋ ዕድሜ 18 ሥራ ቀን ሥራ አድራሻ ገሱባ ከተማ አስተዳደር 02 ቀበሌ
ወንጀሉ
የኢፌዴሪ የወንጀል ሕግ አንቀጽ 32/1/(ሀ) 27/1/ እና 539(1)(ሀ) ላይ የተመለከተውን
በመተላለፊ
የወንጀሉ ዝርዝር
ተከሣሾች ካልተያዘው ፈቃዱ ጵልጵስ ጋር በመሆን ሰውን ለመግደል አስቦ በቀን 15/07/2015 ዓ.ም ከምሽቱ 2፡
30 በሚሆንበት ጊዜ ገሱባ ከተማ 01 ቀበሌ ልዩ ቦታ ፋሲካ ሆቴል ግል ተበዳይ መላኩ ዋንዛ የተባለው እራት
ለመብላት እጅ መታጠቢያ ቦታ ስደርስ አሁን ያልተያዘ ከኋላ በኩል አንቆ ስይዝ የአሁኑ 1 ኛ ተከሣሽ ቀኝ በኩል
እጁን ጠምዝዞ ስይዝ 2 ኛ ተከሣሽ ግራ እጁን ጠምዝዞ ይዞ እንዳይንቅሳቀስ አመቻችቶ ይዞ እያሉ ያልተያዘ
ፈቃዱ ጵልጵስ ከወገብ ስለታም ሣንጃ አውጥቶ በሆዱ (4) አራት ቦታ በቀኝ አንገቱ 2 (ሁለት) ቦታ፣ በግራ
ደረቱ 3 (ሶስት) ቦታ አከታትሎ በመውጋት ከፍተኛ ጉዳት አድርሶ ተጐጅው ሶዶ ክርስቲያን አጠቃላይ
ሆስፒታል ህክምና ክትትል ላይ የሚገኝ ስለሆነ በፈፀሙት በዋና ወንጀል አድራጊነት የሰው መግደል ሙካራ
ወንጀል ተከሷል፡፡
የሰው ማስረጃዎች
1. መላኩ ዋንዛ ዕድሜ 23 ሥራ ነጋዴ አድራሻ ገሱባ ከተማ አስተዳደሪ 02 ቀበሌ
2. ወሰን ተስፋዬ ታክሶ ዕድሜ 30 ሥራ ሥራ አጥ አድራሻ ገሱባ ከተማ አስተዳደሪ 02 ቀበሌ
3. ፋትርስ ፋራንጀ ዕድሜ 24 ሥራ ሥራ አጥ አድራሻ ገሱባ ከተማ አስተዳደሪ 02 ቀበሌ
የሰነድ ማስረጃ
1. ሶዶ ክርስቲያን ሆስፒታል በቁጥር SCH-24/376/15 በቀን 19/08/2015 ዓ.ም ስለመላኩ ዋንዛ ጉዳት
መጠን የሚገልጽ 01 (አንድ) ገጽ
የገላጭ ማስረጃ
- በተጐጂው መላኩ ዋንዛ ላይ የደረውን ጉዳት በገላጭነት የሚያሳይ ፎቶ ግራፍ 04 (አራት) ገጽ ኮፒ
ማሳሰቢያ፡- ተከሳሾችን ገሱባ ከተማ ፖሊስ ጣቢያ በጊዜ ቀጠሮ ታስሮ ይገኛሉ፡፡


ቀን
ለወላይታ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት
ሶዶ፣
ከሣሽ፡- ወላይታ ዞን የሙስና ወንጀል ጉዳዮች ከፍተኛ ዐ/ሕግ
ተከሣሾች፡-
4. ታረቀኝ መሶሬ ሚሎሬ ዕድሜ 35 ሥራ ቴሌ ሠራተኛ አድራሻ ካምባታ ጣምባሮ ሺሽቾ ቀበሌ
5. አስራት ደሌቦ ጋጃቦ ዕድሜ 26 ሥራ መ/ሠራተኛ አድራሻ ፤ቦ/ቦምቤ ወረዳ ሄሬጂ ቀበሌ
ክስ - አንድ በ 1 ኛ ተከሳሽ ላይ ብቻ
ወንጀሉ
የሙስና ወንጀሎችን ለመደንገግ የወጣ አዋጅ ቁጥር 881 /2007 አንቀጽ 13(1) ላይ
የተመለከተውን በመተላለፍ የተፈጸመ
የወንጀሉ ዝርዝር
1 ኛ ተከሣሽ የኢትዮ ቴሌኮም ሠራተኛ ሆኖ እየሠራ የተጣለበትን ኃላፊነትና እምነት ወደ ጐን በመተው
ያልተገባ ጥቅም ለማግኘት ሲል በቀን 23-01-2015 ዓ.ም ሰኞ ዕለት ከቀኑ 10፡00 ሰዓት አከባብ ግልተበዳይ
መኮንን መንቼ የተባለ በውክልና ይዘው እየተገለገለ ያለው ሲም/ስልክ ቁጥር 0913757355 የሆነውን
ግልተበዳይ ቀርቦ ሳይመልክት ሲሙን ዘግቶ ለጊዜው ላልተያዘ አክሊሉ መርክን ምትክ ሲም ከፍቶ በመስጠት
ግል ተበዳይ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሂሣብ ቁጥር 1000317773858 ያጠረቀመው 190,000 (አንድ መቶ ዘጠና
ሺህ) ብር በሞባይል ባንክንግ እንዲዘርፍ በማድረጉ ተከሣሽ በፈፀመው የድርጅትን ሥራ በማይመች አኳሃን
መምራት የሙስና ወንጀል ተከሰዋል፡፡
ክስ - ሁለት በ 2 ኛ ተከሣሽ ላይ
ወንጀሉ
የኢፌድሪ ወንጀል ሕግ አንቀጽ 32(1) ሀ፣33 እና የሙስና ወንጀሎችን ለመደንገግ የወጣ አዋጅ
ቁጥር 881 /2007 አንቀጽ 32(1) ላይ የተመለከተውን በመተላለፍ የተፈጸመ
የወንጀሉ ዝርዝር
2 ኛ ተከሳሽ በክስ አንድ ላይ በተጠቀሰው ጊዜ እና ቦታ ለጊዜው ካልተያዘ አክሊሉ መርክን ከተባለ ጋር አብሮ
በመሆን ግል ተበዳይ መኮንን መንቼ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሂሣብ ቁጥር 1000317773858 ላይ ካጠራቀመው
ገንዘብ ላይ ሞባይል ባንክንግ ተጠቅሞ 70,000 (ሰባ ሺህ ብር) በመውሰዱ ተከሣሽ በፈፀመው ከባድ አታላይነት
ወንጀል ተከሰዋል፡፡

የሰው ማስረጃ
1. አቶ መኮንን መንቼ ዕድሜ 33 ሥራ ንግድ አድራሻ ሶዶ ከተማ ጐላ ቀበሌ
የሰነድ ማስረጃ
2. ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ወላይታ ሶዶ ቅርንጫፍ በቁጥር WSB/ወታ/10117/22 በቀን 01/02/2015 ዓ.ም
የተሰጠ የባንክ ዝውውር፣ የተከሣሽ ህሳብ ቁጥር እና ማንነትን የሚገልጽ 12 ገጽ
3. በቀን 01/03/2015 የገንዘብ ዝውውር የተደረገበት ስልክ ቁጥር እና የዝውውር መረጃ 03 ገጽ
4. ግል ተበዳይ አቶ መኮንን መንቼ ከአቶ ጉማይዴ ጉርዜ የሲም/የስልክ ቁጥር ውክልና የወሰዱበት 01 ገጽ
5. ትክክለኛ አቶ ጉማይዴ ጉርዜ ማንነት የሚገልጽ የቀበሌ መታወቂያ በቁጥር 640291 ከአዲስ አበባ
አስተዳደር የተሰጠ 01 ገጽ
6. ሀሰተኛ ጉማይዴ ጉርዜ የአክሊሉ መርክን ፎቶ የተለጠፈበት መታወቂያ ቁጥር 642 የሚል 01 ገጽ
7. በቁጥር SSWR/RDC/002/2015 በቀን 30/01/2015 ዓ.ም ከደቡብ ደቡብ ምዕራብ ረጅን ቴሌኮም
የተሰጠ መግለጫ 01 ገጽ እና ያልተያዘ ተከሣሽ ማንነት የሚገልጽ 01 ገጽ
በድምሩ ገጽ የሰነድ ማስረጃ ከክሱ ጋር ተያይዟል፡፡

ማሳሰቢያ፡- ተከሳሾቹን የሶዶ ከተማ ፖሊስ ያቀርባቸዋል፡፡

You might also like