Report Final

You might also like

Download as docx, pdf, or txt
Download as docx, pdf, or txt
You are on page 1of 3

የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተክርስቲያን መካነ ኢየሱስ ለማዕከላዊ ደቡብ ኢትዮጵያ ሲኖዶስ ለወጣቶች አገልግሎት

/
መምሪያ የተላከ የሻሎም ማ ምዕመናን የወጣቶች አገልግሎት ዘርፍ የ 2016 . ዓ ም የወጣቶች በዓል ርፖርት

ሚያዚያ 2016 ዓ.ም

መግቢያ

የዳዬ ሻሎም ማ/ም ወጣቶች አገልግሎት ዘርፍ ላለፉት ሁለትና ሶስት ዓመታት በተፈጠረው አለመግባባት ምክንያት የዘርፉ
አገልግሎት ቆሞ የቆየ ሲሆን ከ 2016 ዓ.ም መግቢያ ጀምሮ ግን ለማህበረ ምዕመናችን እግዚአብሔር አድስ መሪዎችን
ስሰጥና ዘርፉን የሚመሩ ከተሰየሙ በኋላ ለወጣቶች አገልግሎት የሚሆን ዕቅድ ታቅዶና በማ/ምዕመናችን መሪዎች ጸድቆ ወደ ሥራ
ተገብቶ ልዩ ልዩ ሥራዎች የተሰሩ ቢሆንም ይህ አጭር ርፖርት በማህበረ ምዕመናችን የወጣቶችን በዓል አከባበር በተመለከተ
በተለይም የበዓሉ ተሳታፍዎችን፣በበዓሉ የተሰሩ መንፈሳዊ ስራዎችን፣ የወጣቶች በዓል ዕለታዊ ገቢ በተመለከተ ጠቅለል አድርጎ
የያዘ ለማ/ምዕመናችን መሪዎች ቀርቦ ይሁንታ ከአገኘ በኋላ ለኢ/ወ/ቤ/ክ/መ/ኢ ማ/ደ/ኢ/ሲ ወጣቶች አገልግሎት መምሪያ የተላከ
ርፖርት ነው፡፡ ዓላመውም ለቤተክርስትያኒቱ የተሰሩ ስራዎችን ማሳወቅና ግልጸኝነት በመፍጠር አንድነትን ማጠናከር ነው፡፡
በዓሉን ምክንያት በማረግ የተሰሩ ስራዎችን በተመለከተ

በመጋቢት 29/2016 ዓ.ም “ሁለንተናዊ እድገት ለሁለንተናዊ ስኬት“ በሚል መሪ ቃል በዳዬ ሻሎም ማ/ም ወጣቶች
አገልግሎት የተከበረውን በዓል ምክንያት በማድረግ ልዩ ልዩ ስራዎች የተሰሩ ሲሆን፣ከእነዚህም ውስጥ ጥቂቶች
እንደሚከተለው ተጠቅሰዋል፡፡

 የከተማ ጽዳት ሥራ

ከቤተክርስቲያኒቱ አከባቢ ጅምሮ የከተማ ጽዳት ሥራ ከከተማው አስተዳደርና ከማዛጋጃ ጽ/ቤት ጋር በመቀናጀት
ተሰርቷል፡፡ በዚህም ሥራ አከባቢውን ማጽዳት ከመቻሉም በላይ ለከተማውና አከባቢው ነዋሪዎች ስለአከባቢ ጽዳት
ግንዛቤና መነሳሳት እንድፈጠር አድርጎአል፡፡

 ስለ አከባቢው ጽዳትና የወጣቶችን ሚና አጉልቶ በሚያሳይ መልኩ ልዩ ልዩ ጽሁፎችን ይዞ ከተማ በመውጣት


ማህበረሰቡን ማስተማር ተችሏል፡፡
 የጽዳት ሥራ እየተሰራ የወንጌል መልዕክት በጽሁፍ፣በዝማሬ፣የኢየሱስን አዳኝነት በድምጽ በማወጅና በመፎከር
የድነት መንገድና የወንጌል እውነት ለከተማው ነዋሪዎች ተሰብኳል፡፡
 ከጽዳት ዘመቻ በኋላ በተደረገው የአደባባይ የወንጌል ጄማ ስብከት እና አንድ ለአንድ የወንጌል ምስክርነት ከ 25
ሰዎች በላይ ንስሀ ስገቡ አስር ሰዎች ተስፋ ሰጥተዋል፡፡
 ከጽዳት ዘመቻና ከወንጌል ስርጭት በኋላ ለምድርቱ፣ለከተማው ነዋሪዎች፣ እንድሁም ለሀገር ጉዳይ

በማ/ምዕመናችን ቄሶችና መሪዎች ጸሎት ተደርጓል

 በቅዳሜ ምሽትና በበዓሉ ቀን በዓሉን ምክንያት በማድረግ በተዘጋጀው ትምህርታዊ ኮንፍራንስ በሁለት ክ/ጊዜ
በተጋባዥ አገልጋይ ወጣቶች ልኖሩበት ስለሚገባ ህይወትና ሁለንተናዊ ዕድገት ለሁለንተናዊ ስኬት ማስተማር
ተችሏል፡፡
 በሁለቱም ቀናት ፒሮግራም በልዩ የዝማረ አምልኮ በአምልኮ መሪዎች ቡድን እግዚአብሔርን
አምልከናል፣በመዘምራን የዝማረ አገልግሎት፣በድራማና ሥነ ጽሁፍ ሥራ ወጣቶችን ማስተማር ተችሏል፡፡
 ይህንን በዓል ምክንያት በማድረግ እስከ ዋና ጸ/ቤት ያለውን የወጣቶችን አገልግሎት ለመደገፍ ገቢ የማሰባሰብ
ሥራ ተሰርቷል፡፡
 በአጠቃላይ በማ/ምዕመናችን እንድሁም በከተማችን ወጣቶች መካከል ከፍተኛ አንድነትና መነሳሳት መፍጠር የቻለ
ደማቅ የወጣቶችን በዓል ማክበር ተችሏል፡፡
 ከላይ የተጠቀሱ ስራዎችን በፎቶና በቪዲዮ ለማስደገፍ ተሞክሯል፡፡

የበዓሉ ገቢ እና አከፋፈል በተመለከተ

 የአስር ብር ፖሊሲን ለመሰብሰብ የማ/ምዕመናችንን ሁሉንም ወጣቶች ለማሳተፈ የተሞከረ ሲሆን ገቢን

ለመሰብሰብ በተዘጋጀው ጊዜያዊ ደረሰኝ/ፎርም መሰረት 345/ሶስት መቶ አርባ አምስት ወጣቶች ተሳትፈዋል፡፡

በዚህም 3450 ብር መሰብሰብ ተችሏል፡፡

 በእለቱም ለወጣቶች አገልግሎት እንድውል መባ የተሰበሰበ ሲሆን

ከሁለቱም ገቢ ምንጪ የተሰበሰበው ብር ማ/ምዕመናችን በሰበካ ደረጃ የሚታሰብ መሆኑን ግንዛቤ ውስጥ

በማስገባት 50 ፐርሰንት ለማ/ምዕመናችን ወጣቶች አገልግሎት ስውል ቀሪው 50 ፐርሰንት ወደ ማ/ደ/ኢ/ሲ

ወጣቶች አገልግሎት መምሪያ ገቢ ሆኗል፡፡ በዚህም ለሲኖዶሱ ወጣቶች አገልግሎት መምሪያ 4100 (አራት ሺ

አንድ መቶ ብር ገቢ ማድረግ ተችሏል)

 በአጠቃላይ የ 2016 ዓ.ም የወጣቶች በዓል ደማቅ፣ብዙ ትምህርትና ልምድ መቅሰም የተቻለበት፣ ለወጣቶች
ሁለንተናዊ ዕድገት ምክንያት መሆን የቻለ ስኬታማ በዓል ሆኖ በሰላም መጠናቀቁን በዚህ ርፖርት እናሳውቃለን፡፡
ክብሩን ሁሉ እግዚብሔር ይውሰድ፡፡
የዳዬ ሻሎም ማ/ምዕመናን የወ/አገ/ዘ

You might also like