Download as docx, pdf, or txt
Download as docx, pdf, or txt
You are on page 1of 2

1. የድንግል ማርያምን ስም መዝገበ ቃላዊ ፍቺ አብራሩ?

 ማርያም የሚለው ቃል በከሳቴ ብርሃን ተሰማ መዝገበ ቃላት ሲፈታ “ከባህር የተገኘች እንቁ” ብሎ ነው ይህም ማለት በመጽሐፍ
ቅዱስ ባህር የዚች አለም ምሳሌ ሲሆን እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ደግሞ ከዚህ አለም የተገኘች ብትሆንም እንኳን
አምላክን ለመውለድ የተገባ ቅድስና የተገኝባት እንቋችን ናት ስለሆነም “ከባህር የተገኘች እንቁ” ይላታል።
2. ዝምታ በመጽሐፍ ቅዱስና በድንግል ሕይወት እንዴት ይታያል?
 በመጽሐፍ ቅዱስ እይታ ዝምታ ፍጥረት ካለመኖር ወደ መኖር የመጣበት ማለትም እግዚአብሄር ሃያሁለቱን ሥነ-ፍጥረታት እና
ሃያውን አለማት ሲፈጥር ሰባቱን ፍጥረታት በዝምታ ወይም በሃሊዪ ነው የፈጠራቸው።
 በዓለመ መላዕክት እግዚአብሔር በዝምታ ይመሰገንበታል። ራእ. 8፥1
 በድንግል ማርያም ህይወት ደግሞ ልናገር ብትል ብዙ መናገር የምትችለው ነገር እያለ በዝምታ እና በአርምሞ የኖረች እናት ነች።
“ማርያም ግን ይህን ሁሉ ትጠብቀው፤ በልብዋም ታኖረው ነበር”። ሉቃ. 2፥19
3. ስደቷ ስለ ፅድቅ ነው ስንል ምን ማለታችን ነው?
 “ስለ ጽድቅ የሚሰደዱ ብጹዓን ናቸው፤ መንግስተ ሰማያት የእነርሱ ናትና”። ማቴ. 5፥10
 ጽድቅ (ጸደቀ) ማለት እውነት ማለት ሲሆን እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ልጅዋን ወዳጇን እየሱስ ክርስቶስን
እራሱ ጽድቅን ይዛ ስለተሰደደች ስለ ጽድቅ ተሰደደች እንላለን።
 አንድም ስድቅ የምንለው የነብያትን ትንቢት ሲሆን ትንቢቱ የፈጸም እና እውነት ይሆን ዘንድ ተሰደደች ስለዚህ ስደቷ ስለ ጽድቅ ነው
እንላለን።
4. ከድንግል ማርያም የብሉይ ኪዳን ምሳሌዎች አንዱን መርጣችሁ አብራሩ።
 ያዕቆብ ከወንድሙ ዔሳው ጋር ተጣልቶ ወደ እናቱ ወንድም ላባ ዘንድ ሶርያ ሲሸሽ ሎዛ በምትባል ሥፍራ ላይ ህልምን አለመ:: ኦ/ዘ.
28 ፥ 12 መሰላል ከምድር እስከ ሰማይ ተዘርግታ በመሰላሉም ላይ መልአክት ሲወጡባትና ሲወርዱባት በላይዋ ላይ ደግሞ
እግዚአብሔር ቆሞ ተመለከተ ይህች መሰላል የእመቤታችን ምሳሌ ናት” ያዕቆብ በሎዛ ያያት ሰዋሰው (መሰላል) አንቺ ነሽ” እንዳላት
ቅዱስ ኤፍሬም ዘሶርያ:: በማክሰኞ ውዳሴ ማርያም "አንቀጽ 2 " ላይ ፥ መሰላሉ የወርቅ ነው ! ይህም ለእመቤታችን የንጽሕናዋና
የድንግልናዋ ምሳሌ ነው መሰላሉ ከምድር እስከ ሰማይ የተዘረጋው እርከኑ ( ደረጃው ) ብዙ ነው ይህም ለእመቤታችን የተሰጣት
ስጦታና ክብር ተቆጥሮ የማያልቅ ብዙ መሆኑን የሚያሳይ ነው::ያዕቆብ በመሰላሉ ላይ መልአክት ሲወጡና ሲወርዱ እንዲሁም
የመልአክት አለማቸው እግዚአብሔርን ደግሞ ከመሰላሏ ላይ ቆሞ ማየቱ ፥ እመቤታችን የመልአክት አለማቸውን ክርስቶስን በማኅፀንዋ
በጸነሰች ጊዜ ፥ መልአክት በማኅፀንዋ አለምነት የተጸነሰውን አምላካቸውን ፥ ቅዱስ ፥ ቅዱስ ፥ ቅዱስ ፥ እያሉ የማመስገናቸው የዛ ምሳሌ
ነው ፥ ፥ ይህም ደግሞ እመቤታችን የሐዲስ ኪዳን አማናዊ ታቦት መሆኗን በትክክል የሚያሳይ ነው ! እንዴት ቢሉ ታቦት ማለት
ማደርያ ማለት ነውና ፥ ፥ የማን ማደርያ ቢሉ ? የአምላክ ማደርያ ! በእመቤታች ማኅፀን የተጸነሰው ደግሞ አምላክ ነው ! ስለዚህ
መልአክት በእመቤታችን ማኅፀን ውስጥ ፥ ቅዱስ ፥ ቅዱስ ፥ ቅዱስ ፥ እያሉ ለአምላካቸው ሥርዓተ ቅዳሴን እያደረጉ መሆናቸው
የሚያሳይ ነው ፥ ፥ ስለዚህም ነው ሊቁ በሃይማኖተ አበው ስለ እመቤታችን ሲናገር ፥ ዦሮዋን ዘንበል አድርጋ የልጇን ምስጋና በሆዷ
ታደምጥ ነበር ያላት ፥፥ ይህም ከሰው ልጆች ዘንድ የመጀመሪያውን ሥርዓተ ቅዳሴ ተሳታፊ ፥ እመቤታችን መሆኗን የሚያሳይ ነው ፥ ፥
ታቦት እመቤታችን ናት ፥ በእርሷ ያደረው ደግሞ የሚመሰገን አምላክ ኢየሱስ ክርስቶስ ፥ ቀዳሾቹ ደግሞ ቅዱሳን መልአክት ናቸው ፥ ፥
እንዴት ያለ መታደልና ልዩ ሥጦታ ነው ? ደግሞም ያዕቆብ በመሰላሉ ጫፍ እግዚአብሔርን ቆሞ አየ ፥ እመቤታችን በሥጋዋ መለኮትን
ስትሸከመው ፥ እንዲሁም እርሱም በመለኮቱ እርሷን መሸከሙን የሚያሳይ ነው ፥ ፥ ይህም እግዚአብሔር በመሰላሉ ላይ መቆሙ ፥
በመሰላሉ ከተመሰለችው እመቤታችን ፥ በተዐቅቦ ፍጹም ተዋሕዶ ከእመቤታችን ቅዱስ ሥጋንዋን መንሳቱንና ሰው መሆኑን የሚያሳይ
5. ከድንግል ማርያም የሐዲስ ኪዳን ምሳሌዎች አንዱን መርታችሁ አብራሩ።
6. ድንግል ማርያም ለዮሴፍ የታጨችበትን ታሪክ በአጭሩ ተርኩ።
 እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም እድሜዋ በደረሰ ጊዜ እና ዘካርያስም ጫና በበዛበት ጊዜ ካህኑ ዘካርያስ ወደ
እግዚአብሔር አመለከተ እግዚአብሔርም ሚስቶቻቸው ከሞቱባቸው ከእስራኤል ሽማግሌዎች በትር ሰብስቦ ማታ
አንድ ሰዓት ወደ ቤተ-መቅደስም አስገብቶ ጠዋት አንድ ሰዓት ላይ እንዲያወጣው እና እንዲመለከት እናም በበትሯ ላይ
የተለየ ምልክት ያለበት የዛ በትር ባለቤት በእግዚአብሔር የተወደደችዋ እና የታላቋ ድንቅ ሴት ይጠብቅ ዘንድ አዘዘ
እርሱም እንደታዘዘው በትሮችን ሰበሰበ የበትሮቹም ቁጥር 1985 ነበር ከዛም ቤተ-መቅደስ አስቀመጠው እናም ጠዋት
አንድ ሰዓት ህዝብ ሁሉ በተሰበሰበበት በሩ ተከፈተ ከእነዚያም በትሮች መካከል አንዲት በትር ሶስት የተለያዩ
ምልክቶችን ይዛ ተገኘች አነርሱም
 1. የለመለመ የለውዝ ቅጠልና የለውዝ ፍሬ አፍርታ ታየች።
 2.”ኦ ዮሴፍ እቀባ ለማርያም ፍህርትከ” ትርጉሙም ዮሴፍ ሆይ እጮኛህ ማርያምን ጠብቃት የሚል ጽሁፍ
ተቀርጾ ተገኘ።
 3.ነጭ እርግብ ህዝብ ሁሉ እያየ አረፈበት።
 በእነዚህ ሶስት ምክንያቶች ዮሴፍ እጮኛው ማርያምን ይዞ ወደ ቤቱ ገባ።
 እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ለዮሴፍ የታጨችበት ዋናው አላማ እንደ አባት ሊጠብቃት እንደ አሽከር ሊያገለግላት ነው።
አንድም የእግዚአብሔርን ቤተ-መቅደስ ድንግል ማርያምን እንዲጠብቅ እንዲያገለግል ከብዙ አረጋውያን መካከል የተመረጠ ታማኝ
አገልጋይ ነው።

You might also like