Download as pdf or txt
Download as pdf or txt
You are on page 1of 10

፯ቱ ደጃፋት በሰዎች ላይ (Chakras)

ይህ ‘chakra’ የምንለዉ የማይታይ ፤ ሰዉነታችን ላይ ተሽከርካሪ የሀይል እና ጉልበት መንኮራኩር ነዉ።


በማይታየዉ ዓለም ላይም የሚገኘዉን ሀይል እና ጉልበት በዚህ በአካል ላይ ቀጥተኛም ተዘዋዋሪም ግንኙነት አለዉ።
ይህ ሀይል በከባቢያችን ላይ የሚገኘዉን የንዝረት እና ስበት ሀይል (Aura/Bio field) የሚያንቀሳቅስ ደጃፍም ነዉ።

እያንዳንዱ ደጃፍ በአካላዊዉም ፤ በማይታየዉም መንፈሳዊ ዓለም ላይ ቀጥተኛ ተፅዕኖም አለዉ።


እያንዳንዱን ደጃፍ እየከፈትን ከስር ወደ እላይም እንወጣለን ፤ አንዱን በር ሳንከፍት ሌላኛዉ ጋር
መድረስ ስለማንችል ፤ አንድ በ አንድ በመክፈት ከነብስ ፣ ከእኛ የላቀዉ እኛነት ጋር የምንገናኝም
ይሆናል።
● ከታቺኛዉ ደጃፍ ወደ እላይኛዉ ደጃፍ ጉዞ በዚህ ፅሁፍ ቀርቦሎታል።
● ይህን ፅሁፍ አዘጋጅቶ ያቀረበዉ ሰማዐያዊ ነዉ።
● ይህን ፅሁፍ ለመማሪያ እና ሰዎችን የተሻለ እነሱነታቸዉንም እንዲያገኙ የቀረበ ሲሆን ፤ በሚገባ እና በተብራራ መልኩ ቀርቧል።

ሰማዐያዊ (semaayawi) በሁሉም መገናኛ ድህረ ገፅ ላይ ማግኘት ይችላሉ።

7 chakras are the 7 attributes of God and the 7 planets.

– መገናኛ ፤ መተላለፊያ ዋሻ/መንገድ ወደ እግዝሐብኤራዊ ባህሪ።


– ወደ ትክክለኛ እኛነት መቅረቢያ ብሎም መድረሻ በሮች ናቸዉ።
ይህ ሂደት (matter) ወይም አካላዊ የሚታየዉን ባህሪ ወደ (spirit) መንፈስ እና የተራቀቀዉ እኛነትን ማግኛ መንገድ ነዉ።
ከመንፈስ ወደ ስጋ እንደወረድነዉ ፤ መልሰን ከስጋ ወደ መንፈስ ማደግም ይሆናል።

Saturn
● Saturn is ‘satan’ that’s why we symbolize the devil with red.
● በዚህ ንዝረት ሀይል ላይ ስንሆን ስጋዊ ፤ እንስሳዊ ባህሪ ላይ እየተመራን ነዉ።
● እዚህ ላይ የምንገኝ ከሆነ ወደ መንፈሳዊ እኛነት መመለስ ይኖርብናል።
፭ተኛ ባህሪያተ ስጋ (መንፈስ)
– መንፈሳዊ አካላችን ጋር ለመገናኘት ብዙ መንገድ ይጠበቅብናል በአንድ ጀንበር አልፈን የምንገናኘዉ አይደለም ፤ ድግምግሞሽ ስራ እና እራስ ላይ
መስራት ያስፈልጋል።
– ቀጣይነት ያለዉ የራስ ስራም አስፈላጊ ነዉ።

ይህን ሂደት ማምጣት እንችላለን መንገዱን በስርአት መጓዝ ከቻልን ፤ አባቶች (Christ Consciousness) የሚሉትም ይህን ነዉ ፤ የላቀ መንፈሳዊ
አስተሳሰብ እና ማንነት።
እዚ ደረጃ ላይ መድረስ የአስተሳሰብ ደረጃም ይሆናል።
አሁን አዕምሮን መቆጣጠር መቻል ነዉ ፤ ለስጋዊ ማንነት አለመገዛት። (የአዕምሮ በአካል ላይ መሰልጠን)

አሁን ደጃፎቹን እንመልከት

Root Chakra | ስር ደጃፍ


ቀለም : ቀይ
የሚገኘዉ : የጀርባ አጥንት መጨረሻ (ወደ መቀመጫ ጫፍ)
የሚወክለዉ : አካላዊነት (ስጋዊ ባህሪ)

ሳይመጣጠን (ሲገደብ) ሲቀር የሚታይ ባህሪ


● ፍርሀት ፤ ጭንቀት ፤ አለመረጋጋት
● የወረደ በራስ መተማመን
● ያልተመጣጠነ የሰዉነት ቅርፅ
● የደም መዉረድ (ማነስ)
● የደም መዉረድ (ማነስ)
● እፍረት ስሜት መሰማት
ለማመጣጠን (ለመክፈት) ማድረግ ያለብን ተግባር
● መሆን ፤ መገኘት ፤ መረጋጋት
● ጥበቃ
● እምነት (በራስ መተማመን)
በስጋ መጠመድ ፣ የምናየዉ ሁሉ በእኛ ላይ ሀይል አለዉ ብሉም ማመን ፤ መሽቆጥቆጥ ፤ እራስን አለማወቅ ፤ ከራስ ይልቅ ዉጫዊዉ ዓለም ምን አለኝ
ብሎ ፤ እራስን በአብዛኛዉ ግዜያት ተጠቂ እና ተበዳይ እንደሆነ ማመን በዚ የመጀመሪያ ደጃፍ ላይ እንዳለን እና ከዚ ማለፍ እንዳለብን መጠቆሚያ
ነዉ።
ይህን በር ከፍተን የምናልፈዉም ከላይ እንደጠቀስኩት (በመገኘት ፣ በመሆን እራስን ፣ በማረጋጋት ቆም ብሎ እራስን ለመገንዘብ በመጣር ፣ ጥበቃ እና
ከለላ የሚሰጠንን ተግባር ወይም ሁኔታ ዉስጥ በመክተት በራስ መተማመንን ለመገንባት በመወሰን ከማይታየዉ ከባቢ አየር ላይ የሚገኘዉን ሀይል እና
ጉልበት ለመጠቀም መወሰን ይህን በር ከፍተን ወደ ሁለተኛዉ ደጃፍ እንድንቀርብ ያደርገናል።

Sacral Chakra | ሴክራል ደጃፍ


ቀለም : ብርቱካናማ
የሚገኘዉ : ከእምብርት ወረደ ብሎ
የሚወክለዉ : መፍጠር ፤ ስሜት (ወሲባዊነት)

ሳይመጣጠን (ሲገደብ) ሲቀር የሚታይ ባህሪ


● ያልተገባ የወሲብ ስሜት
● ሁሉን ተግባር ከስሜት ጋር ማቆራኘት
ለማመጣጠን (ለመክፈት) ማድረግ ያለብን ተግባር
● መፍጠር
● እራስን ማክበር
● ተፈጥሮአዊ ግንኙነት ማከናወን
● በራስ መተማመን
ሁለተኛዉ ደጃፍ ላይ ስንደስር የምንፈተነዉ ይህን የወሲብ ስሜት መቆጣጠር እንድንችል እና ስጋዊ ስሜትን በመቆጣጠር ለቀጣይ ደጃፍ እራስን
ማዘጋጀት ነዉ።
ይህ ኬላ ወይም ደጃፍ ማለፍ በመንገዳችን እንደቆረጥን እና ወደቀጣዮቹ ደጃፋት ስንቅ እየቋጠርን ማመልከቻ ነዉ።
በወሲብ ፤ በዝሙት ፤ በሴጋ (እራስን በወሲብ ማርካት) የተጠመደ ሰዉ ወደ እሱነቱ / እሷነቷ መመለስ አዳጋች ነዉ የሚሆነዉ።
ከነዚህ ተግባራት ብሎም ወደነዚህ ተግባራት ከሚገፉ ክንዉኖች መቆጠብ ይህን በር ለመክፈት ያስችለናል።
Solar Plexus Chakra | ብርሀን ወንጣቂ ደጃፍ
ቀለም : ቢጫ
የሚገኘዉ : ከእንብርት ከፍ ብሎ ሆድ እቃ ላይ
የሚወክለዉ : ሀይል ፣ መፍጨት ስርአት ፣ ደስታ ፣ እራስን መግለጥ

ሳይመጣጠን (ሲገደብ) ሲቀር የሚታይ ባህሪ


● በራስ አለመተማመን
● ያሰብነዉን ያለማሳካት
● የወረደ የንዝረት ሀይል
● ሀይል ማጣት ፤ ያለንን ሀይል እና አቅም መጠቀም አለመቻል
ለማመጣጠን (ለመክፈት) ማድረግ ያለብን ተግባር
● አብዝቶ አለመመገብ
● ደስታ
● እችላለዉ ስሜትን ማንፀባረቅ
ይህ ሶስተኛ ደጃፍ ሲሆን እዚ መድረስ ወደምንፈልገዉ እዉነታ ለመድረስ ማለፍ ያለብን ሌላ ደጃፍ ነዉ።
አብዝተን የምንመገብ ከሆነ ፤ የምንመገበዉን ነገሮች የማንከታተል ከሆነም ይህን ደጃፍ እንዳናልፍ እና እዳንከፍት የሚያዳግረን ይሆናል። አሁን
ባለንበት የምድር ስርዐት (መመገብ ፣ መጠጣት ፣ መዘሞት የሚበረታታ እና እንደ ዘመናዊ ባህል ተደርጐ የሚታየዉ ይህ የማይታይ የሰዉን ሀይል (ንዝረት
ሀይል) በማዉረድ በእስሳዊ አስተሳሰብ እንዲጠመድ እና ካለበት እዉነታ ሌላ እዉነታ እንዳይገነዘብ መቆጣጠሪያ መንገድም ነዉ።
ሰዎች ማከናወን የሚሹት እና የሚኖሩት እዉነታ የተለያየ የሆነባቸዉ በእነዚህ ተግባራት ዉስጥ ስለሚመላለሱም ነዉ። አብዝቶ የዚህን ደጃፍ ሀይል
መጠቀም መልሶ ወደ ሁለት እና አንደኛዉ ደጃፍ ሊመልሰን ስለሚችን የዚህን ደጃፍ ሀይል በስርአት መጠቀም ወደ ቀጣዮ በር ያቀርበናል።
Heart Chakra | ልብ ደጃፍ
ቀለም : አረንጓዴ
የሚገኘዉ : ልብ ጋር
የሚወክለዉ : ፍቅር ፤ መረዳት

ሳይመጣጠን (ሲገደብ) ሲቀር የሚታይ ባህሪ


● ፍቅር ማነስ
● የበዛ ፍቅር
● እራስን አለመቀበል ፤ ፍቅር አለመስጠት
● ብቸኝነት ስሜት
● ከተፈጥሮ ጋር አለመስማማት
ለማመጣጠን (ለመክፈት) ማድረግ ያለብን ተግባር
● ፍቅር መስጠት
● ነገሮችን በሰዉ ጫማ ዉስጥ ሆኖ ለመረዳት መጣር
ህይ ደጃፋ ወሳኝ እና አስፈላጊ በር ነዉ።
የህይወት ዛፍ በሰዉነታችን ይህ ደጃፍ ነዉ። መሀል ላይ ስለሚገኝ አመጣጣኝ እና አመዛዛኝ ባህሪንም የምናገኘዉ ከዚህ ነዉ።
ከታቹ 3 ደጃፋት ከበላዩ 3 ደጃፋት በመሆን መተላለፊያ ኬላም ነዉ። ከዚ ደጃፍ በታች ከወረድን ገሀንም ካለፍን ገነትም ነዉ።
ከዚህ ደጃፍ በታች የሚገኙት 3 ደጃፋት ገሀንም የተባሉት ስጋዊ ባህሪን ስለሚወክሉ ነዉ።
ከበላዩ ገነት የሆነዉ ከዚህ ደጃፍ በላይ መጓዝ ስንችል ስጋን አልፈን ወደ መንፈሳዊ ባህሪያችን ስለምንዋሀድ ነዉ።
ይህ ልብ ከአዕምሮ በ 5000 እጥፍ የስበት ሀይል አለዉ ፤ ይህን ደጃፍ አስከፍተን ከልባችን መኖር ስንችል የስበት ሀይላችንም ጠንካራ ይሆናል።

የእነዚህን ደጃፋት መክፈት እና ከልብ መኖር ወደምድር የመጣንበት አላማ ነዉ። ምድር ላይ ጥሩም መጥፎም የሚካሄድበት መድረክ ነዉና ፤ ሰዉም
ከልቡ በመኖር ከስጋ ሳይወርድ ወደ መንፈሳዊ ባህሪዉ ተጠግቶ በፍቅር ነዉ መኖር ያለበት።
በምድር የተነገሩን ታሪኮችም ይህን ነዉ የሚያሳዩን። (ክርስቶስ ፣ ቡዳህ ፣ ሞሐመድ) ሌሎችም ለተከታዮቻቸዉ ማስተማርን የፈለጉት ከልብ በፍቅር
በመኖር ማመዛዘን እንድንችል ነዉ።
Throat Chakra | ጉሮሮ ደጃፍ
ቀለም : ዉሃ ሰማያዊ
የሚገኘዉ : ጐሮሮ ላይ
የሚወክለዉ : መግባቢያ

ሳይመጣጠን (ሲገደብ) ሲቀር የሚታይ ባህሪ


● እራስን መግለፅ አለመቻል
● የማይዛመዱ ክንዉኖችን እያዛመዱ መቀባጠር
● የዉስጥ ሀሳብ ሰካክቶ መናገሮ አለመቻል
ለማመጣጠን (ለመክፈት) ማድረግ ያለብን ተግባር
● እራስን በተደጋጋሚ መግለፅ
● የዉስጥ ስሜት አዉጥቶ መናገር
● ከራስ ጋር ማዉራት
● ዉይይት እና ንግግር አብዝቶ መተግበር
እራስን መግለፅ ፤ ስሜት በቃላት ለማስረዳት መተግበር ፤ ከስጋዊ ባህሪ ሳይሆን ልብ አመዛዝኖ የሚልከዉን ከአዕምሮ ጋር በማቀናጀት በቃላት ማዉጣት
ጠቃሚ እና የዚህን ደጃፍ በር የሚከፍተዉ ቁልፍም ይሆናል።
ለታይታ የማናዉቀዉን እንደምናቅ የምናወራ ከሆነ የዚህን ደጃፍ ሀይል ላለአግባብ እያዋልነዉም ስለሆነ ወደ ትክክለኛ ባህሪ መመለስ ነዉ።
በምድር ላይ ተፅዕኖ ፈጣሪ እና አንደበተ-እርቱ ናቸዉ የምንላቸዉ መሪዎች ፣ አስተማሪዎች ፣ አስተዳዳሪዎች የዚህን ደጃፍ ሀይል መጠቀም ስለቻሉ
ነዉ የደረሱበት እዉነታላ ያየናቸዉ።
3rd eye Chakra | ፫ተኛ ዓይን ደጃፍ
ቀለም : ሰማያዊ
የሚገኘዉ : ግንባርላይ
የሚወክለዉ : እይታ (መንፈሳዊ ምልከታ)

ሳይመጣጠን (ሲገደብ) ሲቀር የሚታይ ባህሪ


● ተስፋ ማጣት (የተገደበ እይታ)
● የነቃ አስተሳሰብ ማጣት
● ትልቁን ምስል አርቆ አለማየት
● በተገደበ እይታ ነገሮችን መመርመር
ለማመጣጠን (ለመክፈት) ማድረግ ያለብን ተግባር
● እይታ ማስፋት
● ዉስጥ ያለን ድምፅ ማመን
● የጥሞና ግዜ ከራስ ጋር ማሳለፍ (አርምሞ)
ይህ ሶስተኛ ዓይን የምንለዉ መንፈሳዊ ዓይን ነዉ። ሁለቱ የስጋ ዓይኖች ከሚያዩት አልፎ መገንዘብ እና መመልከት የሚችል ነዉ። ከስር ይዘነዉ
የመጣነዉን ሀይል እዚህ ግንባራችን መሀል ላይ ወደሚገኘዉ እጢ (ዽንኤል) ማቅረብ ስንችን የምንከፍተዉ ደጃፍ ነዉ።
ሁሉም መንፈሳዊ ናቸዉ ብለን የምናስባቸዉ አስተማሪዎች በዚህ ደጃፍ እርዳታ የማይታየዉን በማየት በስጋ ተአምርም ሲሰሩ ቆይተዋል። እኛም
አካሄዳችን የተስተካከለ እና የስሮቹን ደጃፋት ከፍተን እዚህ ጋር መድረስ የምንችል ከሆነ ፤ ከስጋ አልፈን መንፈሳዊ አለማትን መጐብኘት የምንችልም
ይሆናል።
Crown chakra | አክሊል ደጃፍ
ቀለም : ወይን ጠጅ
የሚገኘዉ : ከአናት ጫፍ በላይ
የሚወክለዉ : የአፅናፈ አለም እዉነታ

ሳይመጣጠን (ሲገደብ) ሲቀር የሚታይ ባህሪ


● እኛ ሰዉነታችንን ነን ብለን ማሰብ
● በ4ቱ ባህሪያተ ስጋ መገደብ (በመሬት ፤ በዉሃ ፤ በንፋስ ፤ በእሳት)
ለማመጣጠን (ለመክፈት) ማድረግ ያለብን ተግባር
● እራስን ማወቅ
● ዉሳጣዊ ምክር መስማት
● ተፈጥሮን መገንዘብ
ይህ ደጃፍ ከአፅናፈ ዓለም እዉነታ ጋር የሚያገናኝ የሀይል በር ነዉ። ከስር እየከፈትን የመጣነዉ ሀይል አሁን አፅናፈ ዓለም ጋር አንድ እንደሆንን
የምንገነዘብበት እና በመገኘታችን ብቻ መንፈሳዊዉንም ስጋዊዉንም ዓለም የመገንዘብ ጥግ ነዉ።
የፈጣሪ ድምፅ ከራስ ድምፅ ጋር መዛመድ እና መዋሀድ ፤ አፅናፈ ዓለም ጋር መቆራኘት በዚህ ደጃፍ ሀይል የሚገኙ ናቸዉ።

አሁን ደጃፋቱን ካስከፈትን ቀጣይነት ያላቸዉ ቅዱስ ተግባራት በማከናወን የበለጠ ሀይላችን ለጥቅም ማዋል እንችላለን።

አርምሞ/ማሰላሰል (Meditation)
– በዚህ ግዜ አሁን ላይ መኖር ፤ ዉስጥን ማዳመጥ ፤ ትንፋሽ ላይ በማተኮርም አየር ወደ ዉስጥ እና ወደ ዉጪ በቀስታ ማስገባት ማስወጣት።
– የተዛባ እና ያልተስተካከለ ደጃፍ በእኛ ላይ እንዳለ ከተሰማን እዛዉ ደጃፋ ላይ በማተኮር ሲከፈት እና ሀይሎ ሲለቀቅ መሳል።
– የተዛባ እና ያልተስተካከለ ደጃፍ በእኛ ላይ እንዳለ ከተሰማን እዛዉ ደጃፋ ላይ በማተኮር ሲከፈት እና ሀይሎ ሲለቀቅ መሳል።
– ሌላ ተግባር ቃሎችን እየጠራን በላያችን ላይ ሀይል እንዲሰለጥን ማድረግ።

ይህ ፅሑፍ እንደጠቀማችሁ እና እራሳችሁን ለመለወጥ እንዳበረታታችሁ አምናለዉ።


በምስል የተብራራ መረጃ ከፈለጋችሁ በዚሁ ሀሳብ ላይ የዩት-ዮብ ገፅ ላይ ሰባቱን ደጃፋት ሲብራሩ መመልከት ትችላላችሁ።
(www.youtube.com/semaayawi) ላይ የተብራራዉን ምስል ያገኛሉ።

ጠቃሚ ሆኖ ካገኙት ለቤተሠብ እና ለጓደኛ በማጋራት በአካባቢዎ የሚገኙ ሰዎችን ይጥቀሙ።

ሰማዐያዊ

You might also like