C 0 Efb 4 Ae 38 Bad 923

You might also like

Download as pdf or txt
Download as pdf or txt
You are on page 1of 8

የአዕምሮ ህጒች

በህይወት የምናከናዉናቸዉ ተግባራት ሁሉ ፈቅደን ወደ እኛ የጋበዝናቸዉ እዉነታዎች ናቸዉ። ያልፈለግነዉን ተግባር ከተመለከትን
የማንፈልገዉን ነገሮች ወደ ህይወታችን እየጋበዝን ነዉ። ሁሉን የሚወጥነዉ እና የሚቀምረዉ አዕምሮ ሲሆን ፤ አዕምሮን
መቆጣጠር እና መግራት ካልቻልን የዘፈቀደ እዉነታን እንመለከታለን።

አዕምሮ ስንል የማይታይ የማይዳሰስ የሰዉ ልህቀ ህሊና ነዉ። አዕምሮን ስናስብ አንጐል የማይዘነጋ ነዉ። አንጐል በራሱ የአዕምሮ
ስጋዊ መገለጥ ሲሆን ፤ የማይታየዉን የሰዉ የላቀ ቀመር በአካል ተመስሎ የተቀመጠ ስጋዊ አቀናባሪ ነዉ።

ማስተዋል
ማሰብ መቻል በራሱ ማስተዋልን ይመራል። የብዙ ሰዉ ጠላቱ ያለፈ ህይወቱ ነዉ። ይህ ያለፈ ክንዉን በሀሳብ መልክ ስጋዊ
አዕምሮ(አንጐል) ላይ ሲብሰለሰል ይዉላል። ያለፈን እየተመለከቱ ወደፊት የለም። ያለፈዉን እየኖርን ከሆነ አሁንንም ካለፈ በሁአላ
ለመኖር እንጥራለን።
ብታስብ መሆን ትችላለህ ፤ የመጣህበትን እና ያሳለፍከዉን እያየህ የማትችል ስሜት ዉስጥ እራስህን አትክተት። በማስተዋል
ነገሮችን መመርመር (ማሰብ) የራሱ የሆነ የሚከፍታቸዉ ደጃፋት አሉ።

መጀመሪያ የራስን ማንነት መቀየር ፤ እኔ የምደርስበት ቦታ አለ ብሎ ማሰብ መቻል ወደ አሰብነዉ ግብ ያደርሰናል። ሰዉ እንዳሰበዉ
እንደዛዉ ነዉ ፤ ለራሱ የሰጠዉ ምስል በምድር ተንፀባርቆ ይመለከተዋል።

ግምት
የገመትከዉን ነህ።

ይህ ይገባኛል ካልክ ሆኖ ታየዋለህ።


ይህ አይገባኝም ካልክ እሱንም ሆኖ ታየዋለህ።

ሀሳብ የግምቶች ዉቅር ነዉ። የሀሳብ መገለጫዉ ማሰብ እና ማስተዋል ነው። እዉቀትም አንዱ ሀሳብ ነዉ። እንዳወቅነዉ እና
እንደተረዳነዉ ነዉ የምንቀሳቀሰዉ። አንድን ነገር ካላወቅን አናስበዉም።

እዉቀት ብርሀን ነዉ። ባወቅነዉ ልክ ህይወታችንን እንመራለን። እዉቀታችን ነዉ ክፋ የሚያደርገዉ ፤ እዉቀታችንም ነዉ


መልካምን የሚያደርገዉ። እዉቀት በራሱ አንዱ የሀሳብ ጥርቅም ነዉ። ይህ ፅሁፍ እያነበባቹ የተለያዩ ሀሳቦች ወደ አዕምሮአቹ
ይመጡ ይሆናል ፤ ቀጣይ ክንዉን ፣ የቤታቹ ጓዳ ፣ ያለፋት ቀናት ጥርቅም ሀሳቦች ወ.ዘ.ተ። ሀሳብን ገርቶ ግምትን ማስተካከል
የተመቸ መንገድ ለህይወት መዘርጋት ነዉ።

የህይወት እጣ ፋንታ
ሁሉም ቀርቦልናል የቱን እንመርጣለን?

ከፍታ
ዝቅታ

በአዕምሮአችን የመረጥነዉን እንሆናለን። በድጋሜ “ሰዉ በልቡ እንዳሰበ እንደዛዉ ነዉ”። ሰዉ ያሰበዉን ነዉ ፤ ሰዉ የሚወስደዉም
እንምጃ ነዉ። ሰምተን አዉቀን ወደ ተግባር ካልገባን ጥቅም አልባ ነዉ። ያወቅነዉን በእቅስቃሴ እና በአኗኗሯችን መግለጥ መቻል
አለብን።

ዉስጥህ ምን ይልሀል? ዉስጥህንም መቆጣጠር መቻል ያለብህ አንተዉ ነህ። እጣፋንታ አዕምሮአችን ላይ ነዉ። አዕምሮአችንን
ጥለን የምንጓዘዉ ጉዙ የተሳሳተ ነዉ። ባህሪህን ቀይር ፤ ደጋግመህ የምታከናዉነዉም ተግባር ይቀየራል ፤ እሱም እጣፋንታህን
ይወስነዋል። አዕምሮን ብርቱ ሀይል እንዲሆን ካስተማርነዉ ይሆናል።

ድግምት (ድግምግሞሽ)
አንድን ተግባር ደጋግሞ ማከናወን ዉጤታማ ያደርጋል። የዓለም ስርአት የጀመርከዉን እየረሳህ አዲስ ተግባር ዉስጥ ያለማቋረጥ
እንድትዋትን ነዉ የሚገፋፋዉ። አንድን ተግባር ከደጋገምነዉ አሸናፊ እንደምንሆን በዛተግባር ላይ ይታወቃል። ሰማዐያዊን እንኳን
ተመልከት ደጋግሞ በሚያደርጋቸዉ ተግባራት የተነሳ በዘርፋ ከሚገኙ ሙሁራን ተርታ እየተሰለፈ ነዉ ፤ አንተም አንቺም አንድን
ተግባር ደጋግሞ በማድረግ በህይወታቹ ለዉጥን ማየት ትሻላቹ።

በማይሆኑ እና መንገድን ከሚያስረሱ ብሎም ከሚያስቱ ጥሩ መሳይ የዓለም ማታለያዎች እራስን መግዛት የምንፈልገዉን ተግባር
ላይ ደጋግመን እያከናወንን ዉጤት እንድንመለከት ይረዳናል። ሰይጣኑም መልአኩም አዕምሮህ ነዉ የመረጥከዉም መንገድ ከማን
ጋር እየተዛመድክ እንደሆነ ማሳያ ነዉ።

ያለማመድከዉ የደጋገምከዉ ባህሪህ ሆኖ ይወጣል። እስቲ ተመልከቱ ወደ እራሳቹ አንድ ነገር ትጀምሩ እና ከሆነ ግዜ በሁአላ ወደ ሌላ
ተግባር ተዉጣቹ እራሳችሁን ታገኙታላቹ ፤ ለምን? ከዚህ የህይወት ድግምግሞሽ አልፋቹ ወደ ምትፈልጉት እዉነታ አትመጡም።
አንድ ተግባር ላይ ብቻ በማተኮር ለዉጡንም ምስክር መሆን ትጀምራላቹ። አንድ ነገር እወቁ የደጋገምነዉ ተግባር አንተን ወይም
አንቺን በዛ ዘርፍ የላቀ ዉጤት ዉስጥ እንድንገባ ያደርገናል።

ወደ መናፍስት ዓለማት እራሱ እንመልከት ፤ መድገም መደጋገም ነዉ ያንንተግባር እንዲሆን የሚያደርገዉ። አንድ ደጋሚ አካል
በጥሩም በመጥፎም እንዲሆን የሚሻዉን ዉጤት እየደጋገመ ይሁን ሲል ያም ሆኖ በስጋዊ ልምምድ ላይ ይታያል። ይሄ ሁሉ
መደጋገም እና አንድ ተግባር ላይ ማተኮር የምናየዉን እዉነታ ምን ያህል እንደሚቀይረዉ ማሳያ ነዉ።
መስጠት
በምድር ላይ ሰጠ ካልን ካለዉ አጐደለ ይሆናል ፤ በማይታየዉ መንፈሳዊ ዓለም ላይ ሰጠ ካልን አተረፈ ፣ አባዛ ፣ እንዲጨመርለት በር
ከፈተ ነዉ።

ምን እንስጥ? የተሰጠንበትን መስጠት መልሱ ይሆናል። ገንዘብ ፣ እዉቀት ፣ ሀይል ፣ ጉልበት ፣ ፍቅር ፣ ሀሳብ የተለያዩ እኛ በምድር
የተሰጠንባቸዉን ፀጋዎች ለሌሎችም ማካፈል መስጠት ነዉ። አሁን ሰማዐያዊ አዕምሮአችንን በተለየ መልኩ እንዲሰፋ የሚያቀዉን
በማካፈል እየሰጠ ነዉ። እናንተስ ለምድር እና በሷ ዉስጥ ለሚኖሩ አካላት ምን እየሰጣቹ ነዉ? መልሱን ለእናንተዉ እተዋለዉ።

አላፊዎች የማያልፍ ነገሮችን አሳለፋልን


በሀሳብ ፣ በእዉቀት አልፈዉ ነገሮችን የገመቱ ፣ ያሰቡ ፣ የቀመሩ ሰዎች ለእኛ የተላለፈ ለትዉልድ የሚተርፍ ነገራትን ፈጠሩ።

መብረር አይቻልም ላለዉ ተንቀሳቃሽ የአየር መጓጓዣ ተፈጠረ። ከሩቅ ለሩቅ ለማዉራት ያዳገረዉን በስልክ ችግሩ ሲፈታ የተለያዩ
የላቁ እና የቀደሙ ሀሳቦች አካል ለብሰዉ ስራቸዉ እየተጠቀምን እነሱ ቢያልፋም የማያልፋ ክንዉኖችን አበረከቱልን።ታዲያ
እናንተም አላፊ ሁኑ እና የማይቻል የሚመስለዉን እንዲቻል አድጉ።

ብዙ ነገሮችን ያጣነዉ ፤ እዉቀትን ያላገኘነዉ አዕምሮአችንን ስለገደብነዉ ነዉ። አዕምሮህን አትገድበዉ ከማይታየዉ ዓለም
የሚላኩትን ሀሳቦች ለመቀበል ዝግጁ ሁኑ። ዉስጣችሁን አዳምጡ ከስጋ በላይ የላቀ ቀመር ናችሁ እና።

ፈጣሪ ያቃል
ተዉ ተዉ ፈጣር አዉቆ በአምሳያዉ ፈጥሮናል ፤ እሱ ያቃል እያሉ ለትንሽ ለትልቁ የተሰጠንን ነፃ የመፍጠር ፈቃድ መተዉ ተገቢ
አይደለም። አሁንም እንዳላደግን እና ጥገኝነታችን እንዳላበቃ ማሳየት የለብንም።

የምድራዊ ቤተሠቦችህ እድገትህን ጨርሰህ ከጥገኝነት ተላቀህ ሰዉ እንድትሆን ነዉ ዓመታትን ዋጋ የሚከፍሉት ፤ ፈጣሪህም
በምድራዊ ቆይታ የላቀ አስተሳሰብ እና መረዳት ደረጃላይ ደርሰን የተፈጠርንበትን ልምምድ ጨርሰን ወደ ቀጣይ የህይወት ምዕራፍ
መሻገርን ነዉ ለእኛ የሰጠዉ።

ምድር ላይ ያለዉ ሁሉ በአንተ ቁጥጥር ስር ነዉ ፤ ምክንያቱም የአባትህ የሆነዉ ሁሉ የአንተም ስለሆነ። አባትህ የአፅናፈ ዓለም
ፈጣሪ ፤ የሁሉ ገዢ ነዉ። አንተ የሱ አምሳያ ፈጣሪ ነህ ምድር ላይ መፍጠር እና ማየት የምትሻዉን ሁሉ ከዚህ ሀይል ጋር በመገናኘት
መፍጠር ጀምር። ለአባትህም የሚኮራበት ፍጡር ሁን እንድታደርግ እና እንድታከናዉን በሰጠህ እድል ላይ ልቀህ የዚህን ሀይል ዋና
ተቋዳሽ ሁኑ። ስለዚህ የስንፍና ኑሮህን ተዉ እና እርምጃ ዉሰድ። አዎ ጥሩ ነዉ ለዚህ ትልቅ ሀይል መሪዉን መስጠት ፤ ነገር ግን
መንገድህን ምረጥ የሱ ባህሪ በአንተ እንዲታይ ፍቀድ። የአባትህ የማያልቅ ሀይል በዉስጥህ አለ ፤ ከአንተ የሚጠበቀዉ ማዳመጥ እና
ልጅነትህን ማወጅ ብቻ ነዉ። እሱ ፈቅዶ ምድርን ግዛ አለህ ታዲያ ለምንድነዉ እሱ ያዉቃል እያልን የሰጠንን ሀይል የምናራክሰዉ።
ይህ ያንተ ነዉ ተብሎ የተሰጠንን እቃ መልሰን የእኔ ነዉእን? እያል የሰጠንን አካል በጥያቄ እንደማናደርቀዉ ሁሉ ፤ ፈጣሪም
የሰጠንን ሀይል መጠቀም አሁን መጀመር አለብን።

አጉል ምስኪን መምሰል ወራሽ አያደርግም ፤ የልጅነት ባህሪ ከአባት የወረስነዉን መተግበር እንጂ በቃላት እራስን ስላሽሞነሞንን
አይደለም ምድርን የምንገዛዉ። የፈጣሪህ ባህሪ በአንተ / በአንቺ ይታያል? መልሱን ለራሳችሁ መልሱ። መታየቱን እየተጠራጠርክ
ከሆነ ለዚህ ነዉ ከተጠያቂነት ስሜት ለመሸሽ እያልክ እሱ ያቃል ስትል የከረምከዉ።

አንፃር (የህይወት ሚዛን)


የህይወት አንፃር በሰዉ ዘንድ ያለዉን ልዩነት አመልካች ነዉ። አንፃርን ስናስብ የህይወትን ሚዛን መንካት ለተብራራ እና ለጠለቀ
መረዳት ግብአት ይሆነናል። ዓለም ከምናየዉ ስርአት ዉጪ የራሷ መመሪያ ህጐች አሏት። የአንዱ ከፍታ የሌላዉን ዝቅታ መፍጠር
ግዴታ ነዉ።

አንድ ሰዉ ሙሁር ወይም አዋቂ እንዲባል በተቃራኒዉ የማያዉቅ ደነዝ የሚባል ሊኖር ይገባል።
ሀብታም ባለጠጋ እንዲባል ደሀ የሌለዉ ሊኖር ይገባል።

ሁሉም በመረጠዉ ስርአት ሲኖር እኛ የቱን ነዉ የመረጥነዉ? የመረጥነዉስ ካልወደድነዉ መቀየርም ነዉ።

“የድሀ ጥፋቱ ድህነቱ ነዉ” ድሀ ነኝ ስላለ እና የተሰጠዉን ግብአት ብሎም አዕምሮዉን ስላልተጠቀመ ድሀ ሆነ። እሺ ታዲያ አሁን
ገብቶናል ካልን ይህንን እንዴት ወደራሳችን ጥቅም እናምጣዉ? መልሱ የምናዉቀዉን ከትንሽ ተግባራት ማከናወን መጀመር እና
ዉስጥ ምሪትን መከተል ነዉ።

ድሀ ጥፋቱ ድህነቱ ነዉ
የህይወት አንፃር እንደሚለያይ ከተገነዘብን ፤ አሁን ሁሉ ጥፋት የሚባል በራሱ ዘንዳ ይዞ ይንቀሳቀሳል። በመጀመሪያ ደሀ የሚለዉን
ቃል አመለካከታችን እንዴት እንደሆነ ለእራሳችን ግንዛቤ መስጠት አለብን።

ድሀ ወይም ድህነት የገንዘብ ብቻ አይደለም።

የአዕምሮ ድህነት
የሀሳብ ድህነት
የአኗኗር ዘይቤ ድህነት
የእዉቀት ማጣት ድህነት
አላማን ያለማወቅ ድህነቶች ከብዙ በጥቂቹ ናቸዉ።

ድህነት የምንፈልገዉን የሚገባንን አለማግኘት ፤ ድርጊት መዉሰድ ሲገባን ለዛ ድርጊት ሙሉ ሀይል እንዳንጠቀም መቆጠብ ድህነት
ነዉ።

አንድ ሰዉ የዓለም መገበያያ ሀይል ገንዘብን ማግኘት ፈልጐ ነገር ግን ያለዉን አቅም ፣ ሀሳብ ፣ ግምት ፣ ማስተዋል እና አዕምሮ
ለሚፈልገዉ ተግባር ከማዋል ይልቅ ማህበረሰቡ ባሳየዉ የዉሸት ዓለም ሀሳብ በመሞላት ተወጥሮ መድረስ ከነበረበት ደረጃ በሰዉ
ምስል ተመስሎ ደሀ ሆኖ የሚቀረዉ።

ማህበረሰቡ ተጉዞ የደረሰበትን እያወከዉ ለምን አንድ አይነት መንገድ መርጠህ የተለየ ዉጤት ትጠብቃለህ። የራስህን ዓለም
ፈጣሪዉ አንተ ነህ ስለዚህ ሰዉ በፈጠረልህ ሳይሆን መፍጠር በፈለከዉ ዓለም ዉስጥ ኑር።

የእኛ ሀብታሞች ሚስጢር ይህ ነዉ :- ያለንን እንዴት አሳምረን ማቅረብ እንደምንችል እናዉቅበታለን። ፈጣሪ የሰጠን ሀሳብ ላይ
አንተኛም ወዲያዉ ወደ ተግባር እንቀይረዋለን። ዉሳጣዊ ምክር ብሎም እኛነታችንን ለመገንዘብ አንታክትም ቀን ማታ እራስን
ለማሻሻል ሂደት ላይ ነን ፤ ብሎም ያለንን ስለምንሰጥ እና ስለምናካፍል ምድር ለእኛ አብዝታ ታደላለች።

እናንተም የእኛን ህይወት ፣ አስተሳሰብ ካሻቹ ሚስጢሩ እሩቅ አይደለም ሁሉ እራሳቹ ጋር ነዉ። የተኛህበትን ሀሳቦች አሁን ወደ
ተግባር ቀይራቸዉ።

እይታ
የህይወት እይታ እና የአዕምሮ ቀመሮች ተመሳሳይ የአኗኗር ዘይቤ ነገር ግን የተለየ ምልከታን ይፈጥራሉ።

አንዱ ይህ በህይወቴ የገጠመኝ ለዚህ ነዉ እናም አዝኛለዉ ሲል ፤ ተመሳሳይ ገጠመኝ ያጋጠመዉ ሌላ ሰዉ ይህ በህይወቴ የገጠመኝ
ለዚህ ነዉ እናም ተምሬበታለዉ እራሴንም እንዳሻሽል እረድቶኛል ይላል።

አተያየታችን እንዴት ነዉ ፤ ህይወትንስ እንዴት ነዉ የምንመለከታት? እዉነት እያጋጠመህ / እያጋጠመሽ ያለዉ ሁሉ እናንተን
ለመጉዳት ነዉ? እራሳችሁን ጠይቁት። ስንት ግዜያት ይህ ተበላሸ ብላቹ ወዳላያችሁት ጥሩ ዉጤት ሲቀየርስ ተመልክታችሁአል?
አዎ በህይወት የሚፈጠረዉ ሁሉ እኛን ሊጠቅም እንጂ ሊጐዳ አይደለም።

የአዕምሮ ትኩረት የሚሄድበት ሁሉ ለዛ ተግባር ሀይል ይመግባል። የምናስበዉን ነን። አጋጣሚዎችን የምንመለከትበት እይታ
በህይወታችን የምንመለከተዉን ወጤትም ይወስናል።

እብድ
ከማህበረሰቡ ነጥሮ የወጣ አስተሳሰብ ካላቹ እብድ ለመባል ተዘጋጁ። ሰዉ የማያየዉን ማየት ከቻልክ እብድ ትባላለህ ያ እብድ
ያስባለህ ሀሳብ ሰርቶልህ ሲመለከቱ አሁን በተራቸዉ እብድ መባልን ይፈልጋሉ አልፎም ያ-እማ ሊቅ ነዉ እያሉ ያወሩልሀል።

አድናቆትንም ዘለፋንም ከቆዳህ ስር እንዲቀመጥ አትፍቀድ።

በዘለፋ ቀናት አንገትህን አትድፋ እንደዉም ይህ አለማመናቸዉ እና መዝለፋቸዉ የሀይልህ ግብአት ይሁንህ ፤ በስራህ ላይ
እምነት እና ፅናትን አጠንክረህ ለዉጤትህ ተጓዝ።
ባሞገሱ ቀናት አትጥነን መሬት ያዝ አድርግ። ጥሩ አሁን ስራህ አስሞግሶሀል ፤ ጉዞ ተጀመረ እንጂ አላበቃብ ስለዚህ በክብር ላይ
ክብር ፤ በዘዉድ ላይ ዘዉድ እየጨመርክ ወደፊት ብቻ። በሁለቱም ቀናት ወደ አላማህ እንጂ ከሰዎች ስለሚወጣዉ ያማሩ እና
የሚያስጠሉ ቃላት ትኩረትህ አይሁን።

መንፈሳዊ ንቃት እራስን መሆን ነዉ። አዕምሮ የፈጠረዉን በአካላዊዉ አንጐል ግብ እንዲመታ ማድረግ።

እራስን ማግኘት
የነቃ ሁሉ እንደነቃ ላይቀጥል ይችላል በደከመዉ ግዜ ስለሚያርፍ። የአስተራረፍ ስርአቱን መምረጥ ግን ተገቢዉ ተግባር ነዉ። ነቅቼ
ስለቆየዉ አሁን እራሴን በዚ ጐጂ ተግባራት ላስታግስ ማለት እንደ “ግመል ሽንት” ወደ ሁአላ መመለስ ነዉ።

እራስን ለማግኘት የብቻ ግዜ ወሳኝ ነዉ። ስሜትን ወዲያዉ ከሚያወጡ እና ከሚያወርዱ ተግባራት መቆጠብ እራስን ፈልጐ
ለማግኘት የመጀመሪያዉ እርምጃ ነዉ።

1. ማህበራዊ ድህረ ገፅ
2. የተቀነባበሩ ምግቦች
3. ሰዉነትን የሚያነቁ ወይም የሚያደነዝዙ እፆች

ለእራስ ከላይ ከተጠቀሱት እና ተዛማጅ ተግባራት እረፍት ማድረግ እኛነትን እንድናዳምጥ የሚረዳን ይሆናል።

የጥሞና ግዜ ተፈጥሮአዊ ቦታዎች ላይ ማሳለፍ ፤ አርምሞ ፤ ፀሎት እና ከእራስ ጋር ዉይይት ማድረግ።


እራስን የሚገልፅ እለት ተዕለት መከታተያ መፅሐፊያ ደብተር ላይ ለዉጥን መመዝገብ።
ሀሳብ ሲፈልቅ እና ትዉስታዎች ሲመጡ ጠቃሚ የሚመስለንን ሀሳቦች በመፃፍ ማስቀመጥ።
እራስን ፤ ተንቀሳቃሽ አካልን ከተለያዩ ተግባራት መግታት። መፆም።

ይህ ተግባራት ሁሉ አዕምሮ ፣ ነብስ ፣ ስጋን ለማቀናጀት እና በአንድ እንዲሰሩ ይረዳል።

የመኖር አላማ
የምንኖረዉ ለምድን ነዉ? ምንድን ማድረግን እንወዳለን? አከናዉነን ማለፍስ የምንፈልገዉ ተግባራት? በእለት እንቅስቃሴ ለምን
ተግባራትን እያከናወንን እንደሆነ ቆም ብሉ ምልከታን ማስተካከል። ደጋግመን በእለት የምናከናዉናቸዉ ተግባራት ወደ አላማች
የሚወስዱ መሆናቸዉን መመርመር። የምንፈልገዉ የአባታችን ባህሪ በእኛ እየታየ መሆኑን መፈተሽ ካልሆነ መስተካከል አለበት
የምንላቸዉን ቦታዎች ማስተካከል።

ቤተሰብ ፤ ጓደኛ እና በአካባቢያችን የሚገኙ አካላች ስለኛ ሲያስቡ እና ሲመለከቱ ወደ አላማችን የምንጓዘዉን ወይስ ለግዜያዊ ደስታ
የሚኖረዉን እኛነት ነዉ የሚያዉቁት ይህን ሁሉ እየመለሳቹ ለራሳቹ ማለፍም አለባቹ። እኛ እራሳችንንስ እንዴትስ ነዉ
የምንገልጠዉ? ልኖርለት ይገባኛል የምንለዉ የቱስ ነዉ? የምትኖርለት አላማ ያለዉ ያ አንተነት አሁን የምታከናዉናቸዉን ተግባራት
ይፈፅማል ብለህ ታስባለህን? የምትኖሩለትን አላማ አግቼዋለዉ ካልንስ ህይወትን እንዴት እየመራናት ነዉ ፤ አላማችን ላይ
ተኝተናል ወይስ እደሚገባዉ እየኖርነዉ ነዉ። ጥረታችን እና አካሄዳችን ለዚዉ ግብ የሚመራም መሆን አለበት።

አላማ በራሱ እኛዉ ነን። በምድር መገኘታችን በራሱ አላማ ነዉ። መኖርን መለማመድ እራሱ አላማ ነዉ። ምድርን መገንዘብ በራሱ
አላማ ነዉ። እራስን መገንዘብ ደግሞ ከምንም በላይ ትልቁ አላማ ነዉ።

ህይወት ምንድን ነዉ
ህይወት ለእናንተ ምንድን ነዉ? እይታን አንብባቹ እዚህ ጋር ከመጣቹ ተከታኙን ሀሳብ ለመረዳት ያግዛችሁአል። ላንተ ወይም ላንቺ
ህይወት እንደ እይታቹ ነዉ የሚወሰነዉ። እኛ እንደምንመለከተዉ ህይወትም እንደዛ ሆኖ ይታየናል።

እይታ -) ሀሳብ -) የአዕምሮ ዉቅሮች በጠቅላላ ህይወት ምንድነዉ የሚለዉን ይመልሱልናል።

ህይወት ልምምድም ነዉ። መንፈስ በስጋ ዉስጥ ይህ የምናየዉን አካል ለብሶ ልምምድ እያደረግን ነዉ። ህይወት ሰዋዊ ልምምድ
የሚለዉ ጥሩ ከላጭ ነዉ። ዉጣ ዉረድ ፣ የህይወት ፈተና ፣ የሰዋዊ ስሜቶች(ሀዘን ፣ ደስታ) ምን እንደሚመስሉ ይህ የማይታይ
መንፈስ በስጋ ያያል።

በምድር የምናየዉንም የማናየዉንም በስጋ ዉስጥ ማየት እና መለማመድ ህይወት ነዉ።

የሆነዉን እንጂ የፈለግነዉን አንሆንም


የምንፈልገዉን ሳይሆን የሆነዉን ነዉ ወደ ህይወታችን የምናቀርበዉ ፤ የምናየዉ ፤ የምኖረዉ።

አንድ ሰዉ ዘፋኝ መሆን ስለፈለገ ሳይሆን ዘፋኝነትን አምኖ ሲኖር ነዉ ዘፋኝ የሚሆነዉ።

ፍላጐት :- መነሻዉ ነዉ። አንድ ነገር ለማግኘት መፈለግ መነሻዉ እና ዋናዉ ነዉ ነገር ግር መዳረሻ ጠቋሚ እንጂ በራሱ
መዳረሻ አይደለም።
መሆን :- ከፍላጐት ቀጥሎ የሚመጣዉ የአዕምሮ ዉቅረ ሀሳብ ይህ ነዉ። ከፍላጐታችን በመነሳት መሆንን እና መገኘትን
ማለማመድ ፍላጐት ግብ እንዲመታ ያደርገዋል። ለዚህም ነዉ የምንፈልገዉን ሳይሆን የሆነዉን የምንሆነዉ።

አንድ ሰዉ ሠላም እና ደግነት በዉስጡ ሆኖ የሆነዉ እና ተግባሩ ክፋት እና ጥላቻ ከሆነ በፈለገዉ ሳይሆን በሆነዉ ተግባር ነዉ ያንን
ሰዉ ምንገልጠዉ።

በህይወት የምናያቸዉ ሰዎችም እኛ የሆነዉን አይነት እንጂ የፈለግነዉን አይደሉም። ጓደኞቻችን የእኛዉ ግልባጭ ናቸዉ በሆነዉ
ባህሪ እንጂ በፈለግነዉ ባህሪ አይደለም ጓደኛ ያደረጉን። የሆነዉ ባህሪ ከእነሱ ባህሪ ጋር ስለተዛመደ ጓደኛ ሆንን። ዉስጥህ ፍላጐትህ
ሌላ ሆኖ የሆንከዉ ሌላ ከሆነ የሆንከዉን እንጂ የፈለከዉን አትሆንም።

አንድ ጐረምሳ ቆንጆ ኮረዳ ስለፈለገ ብቻ አያገኝም ፤ እራሱ በተለያዩ የህይወት ዘርፎች ቆንጆ መሆን አለበት። ያቺ ኮረዳ
የምትሻዉን ወንድ ሆኖ መገኘት አለበት ፍላጉት ብቻዉን ልዕልትን ከቤተ መንግስት ወደ ጉድጓድ አይስብም ፤ ለሱአ
የሚመጣጠነዉን ቤተ መንግስት መገንባት እና የቤቱ ንጉስ እንደሆነ ሲሆን ነዉ ልዕልቷ ቤቱን የምታሞቀዉ።

የተሻለዉን እኛነትን መሆን ስንችል የተሻለዉ እኛነት የሚገባዉን ሁሉ እናገኛለን።

ጠማማ ሀሳብ እና ስሜት


ሰዉ ስሜቱን መግዛት ካልቻለ ሰዉ ሳይሆን እንስሳ ነዉ። ስሜታችን ዉሳኔዎቻችን ላይ ዋነኛ አስተዋፅዎ አለዉ። ስሜቱንም
መቆጣጠር ያልቻለ ማህበረሰብ ነዉ ለትዉልድ ጠር የሚሆነዉ።

አዕምሮ የሚልከዉን ሀሳብ ተቆጣጥሮ ወዴት እየሄደ እንደሆነ መወሰን የእኛዉ ስራ ነዉ። የመጣ ሀሳብ ሁሉ አይስተናገድም በጠራ
ምልከታ መመርመር አለበት። የጥላቻ የክፋት መነሻዉ ጠማማ ምልከታ እና ሀሳብ ነዉ።

አዕምሮአችሁን ለምንድን ጥቅም እያዋላችሁት ነዉ። ስሜትህን መቆጣጠር ካልቻልክ መቆጣጠሪያዉ የተበጠሰ የህይወት ጋሪ ላይ
እንዳለህ አስታዉስ ፤ መቆጣጠሪያዉን በፍጥነት መጠገን ህይወትህን በቁጥጥር ስር እንዲሆን ይረዳዋል።

ማንነታችን ማንነት የሚኖርበትን ዓለም ፈጠረ


ዓለማችንን እኛ ፈጠርነዉ። አፅናፈ ዓለም እና ህዋ በሀይል ፣ በድግምግሞሽ እና በንዝረት ሀይል ይንቀሳቀሳል። ያሰብነዉን ነን።
ሳንነቃ በሰመመን የምናከናዉነዉን ተግባር በነቃ እይታ ማየት።

ሰዎች በህይወታቸዉ የመጣባቸዉን እንጂ የሆነላቸዉን አያዉቁም ፤ ይሄም አዕምሮአቸዉ ላይ የሌላቸዉን እንጂ ያላቸዉን
አይገነዘቡም። ይህም ዓለማቸዉ ሆኖ ያዩታል።

ሰዉ ወደ ዉድቀት የሚሄደዉ ዕራይ ስለሌለዉ ነዉ


ሰዋዊ ልምምድ ስናከናዉን የሚመራን የዉስጥ ድምፅ አለ። ይህ ድምፅ ሁሉም ማህበረሰብ የተለያየ ስም ይሰጠዋል (የተሻለ እኛ ፣
መንፈሳዊ እኛነት (፭ተኛ ባህሪያተ ስጋ) ፣ መንፈስ ቅዱስ ሌላም ሌላም የተለያዩ የራስ የሆነ መጠሪያ ልናሰፍር እንችላለን። ይህ
ድምፅ የሌለዉ ሰዉ በድን ነዉ ፤ ሰዉ አይደለም።

ዕራይ ከዉስጥ ካለ ድምፅ ይነሳል። በእኛ እና በትልቁ ሀይልም ይፈፀማል።

ዉድቀት :- ዉድ እዉቀትን ለእኛ ይዞ ይመጣል። ወደኩኝ ከማለት ዉድ እዉቀት አገኘዉ ማለት እራስን ለቀጣይ ጉዞ ስንቅ
ማዘጋጀት ነዉ።

ዕራይ :- የዉስጥ ድምፅ የሚልክልን ምስል ነዉ።

በዉስጣችን ያለዉ ድምፅ (መንፈስ) የሚልካቸዉ ሶስት ነገሮች አሉት።

1. ዕራይ ማየት :- የዉስጥ ድምፅ።


2. ህልም ማለም :- ድምፅ ወደ ምስል ሲቀየር።
3. ትንቢት መናገር :- ያየዉን ምስል ሲያብራራ።

ዉስጥ ያለን ድምፅ እና ሀይል መከተል ከዉድቀት አስነስቶ ወደ ዉድ እዉቀት ይከታል። ዕራይህ / ዕራይሽ ምን እንደሆነ እስቲ ቆም
እያላቹ አስቡት።

አዕምሮን እንደ አዲስ መገንባት


እስካሁኑ የህይወት ልምምዳችን ፈቅደንም ሳንፈልግም የተገነባብን የአዕምሮ ዉቅር ሀሳቦች አሉ። እንዴት መኖር እንዳለብን ፤
ክንዉኖቻችን ሁሉ በተነገሩን እና በተሰራብን የአዕምሮ ሙሌት እየመነዘርን መተናል።

ይህ እንዲህ ነዉ ስለተባልን ያንን ሀሳብ ይዘን እስካሁኑአ ሰዓት ድረስ ህይወታችን እናቀዋለን ብለን በምናስበዉ ስንመራ ቆይተናል።

ምሳሌ :- መሬት ክብ ነዉ ፣ የሰዉ ልጅ ጨረቃ ላይ በዚህ ዘመናት ወጥቷል ፣ ስለሀይማኖት ፣ የሰዉ ልጅ መነሻ ብዙ ብዙ
እዉነታ በሚመስሉ ሙሌቶች አወቅን ብለን ህይወትን እንመራለን።

እዉነታ ዉጪ ሳይሆን እዚሁ እኛዉ እራሳችን ጋር ነዉ። ከማያልቅ ሀይል በአምሳሉ የተፈጠርን ፍጡራን ወደ ዉስጥ መመልከት
ብንችል ሁሉ እየተመለሰልን ይሄዳል።

በልጅነት አዕምሮ አይተን የማንችል የማንደርስባቸዉ ተደርገዉ የተቀመጡብንን ሀሳቦች አሉ ፤ እነዚህን ሙሌቶች ቧጦ እና ነቃቅሎ
ማስወገድ ለቀጣዩ የአዕምሮ ልዕቀ ሀሳብ ቦታ መክፈት እና ማደላደል ነዉ።

ስራዉ ከእኛ ይጀምራል በእኛም ያልቃል።

©️April 2024 / ሚያዚያ 2016

You might also like