Download as doc, pdf, or txt
Download as doc, pdf, or txt
You are on page 1of 63

ሳሙኤል ተመስገን ዘመሰረተ ተዋህዶ ሰ/ት/ቤት:

+++ሥራህን ሥራ+++
ሥራህን ሥራ፦ ጌታ ለእያንዳንዱ ሰው ሥራ ሰጥቶታል፤ ያንን መሥራት የእርሱ ፈንታ ነው። ቢቻለው እሱን ማገድ
የዲያብሎስ ሥራ ነው። በርግጥ ሥራውን እግዚአብሔር እንደሰጠህ ያህል ሰይጣን ሊያግድህ ይጥራል። ሌላ ነገር
በበለጠ ደስ የሚያሰኝ ሊያቀርብልህ ይጥራል፤ በዓለማዊ ተስፋዎች ያባብልሃል። የሐሜት ጎርፍ ያስወርድብሃል።
ደራሲያን እንዲጠይቁህ፣ እጅግ ስመጥር ሰዎችም በክፉ እንዲናገሩብህ ይጠቀምባቸዋል።
ጲላጦስ፣ ሔሮድስ፣ ሐናና ቀያፋ ሁሉም በአንተ ላይ ያድማሉ። ይሁዳም በአጠገብህ ቆሞ በሠላሳ ብር ሊሸጥህ
ይከጅላል። ይሄ ሁሉ የደረሰብህ ሰይጣን በዚህ ከሥራህ ሊስብህና እግዚአብሔርን ከመታዘዝ ሊያሰናክልህ መሆኑን
ልትገነዝብ አትችልምን?
ሥራህን ሥራ፦ ዓላማህ እንደ ኮከብ የጸና ይሁን። ተወው ዓለም እንደፈለገው ይነታረክ ይጨቃጨቅ፡፡ አንበሳው
ሲያጓራ ፍንክች አትበል። የሰይጣን ውሻዎችን ለመውገር አትቁም፡፡ ጥንቸሎቹን በማባረር ጊዜህን አታጥፋ።
ሥራህን ሥራ፦ ዋሾች ይዋሹ፣ ጠበኞች ይጣሉ፣ ማኅበሮችም ይወስኑ፣ ደራሲዎችም ይድረሱ፣ ሰይጣንም የፈለገውን
ያድርግ። አንተ ግን ምንም ነገር እግዚአብሔር የሰጠህን ሥራ ከመፈፀም እንዳያግድህ ተጠንቀቅ።
ሥራህን ሥራ፦ ገንዘብ እንድታተርፍ አልተላክህም፣ እንድትበለጽግም አልታዘዝክም፣ ለክብርህ ተከላከል ብሎ
አልተነገረህም፤ ሰይጣን አገልጋዮቹ የሚነዙትን የሐሰት ወሬ እንድታስተባብል አልተጠየቅህም። እነኚህን ሁሉ ነገሮች
ብታደርግ ሌላ ሥራ ልትሠራ አትችልም። ይህም ብቻ ሳይሆን ለራስህ እንጂ ለጌታ አልሠራህም።
ሥራህን ሥራ፦ ዓላማህ እንደ ዐለት የፀና ይሁን፣ ጥቃት ይደርስብህ፣ ትበደል፣ ትሰደብ፣ ትታማ፤ ትቆስልና ትናቅ
ይሆናል። አንተ ግን በጸና ውሳኔ በማያወላውል ቅናት እስከ መጨረሻ ጸንተህ “የሰጠኸኝን ሥራ ፈፀምኩ
ሃይማኖትንም ጠበቅሁ” ለማለት እስክትችል ድረስ የሕይወትህን ዓላማና የተፈጠርክበትን ግብ ተከተል።
ሥራህን ሥራ!!!
############
ነፍስ ሔር ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ
"የክርስቶስን አካል ልታከብሩት ትወዳላችሁን? መልሳችሁ አዎ ከሆነ ራቁቱን ሆኖ እያያችሁት አትለፉት፣ በየመንገዱ
ራቁቱን ሆኖ በብርድ እየተሰቃየ አለና፤ ራቁቱን ሆኖ በብርድ እየተሰቃየ አልፋችሁት መጥታችሁ እዚህ ከቤተ መቅደስ
በብርና በወርቅ ላስጊጥህ አትበሉት፡፡ "ይህ ሥጋዬ ነው" ብሎ የተናገረው ክርስቶስ ራሱ "ተርቤ አይታችሁኝ
አላበላችሁኝም" ያለው እንዲሁም "ከእነዚህ ከታናናሾች ወንድሞቼ ለአንዱ ያደረጋችት ለእኔ አደረጋችሁት"
ያለውም ያው እርሱ ራሱ ነውና፡፡ ወንድምህ በረሃብ እየተሰቃየና እየሞተ ቅዱስ ደሙ የሚቀዳበት ጽዋ በወርቅ
ቢለበጥና ቢንቆጠቆጥ ጥቅሙ ምን ላይ ነው? አስቀድመህ የወንድምህን ረሃብ በማጥገብና ጥሙን በማርካት ጀመር፤
ከዚያ በኋላ በተረፈህ ገንዘብ ቤተ መቅደሱንና ንዋያተ ቅድሳትን እንዲህ ማስጌጥ ትችላለህ፡፡"
#######
#ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ
"ሰው ሆይ! የሚጎዳህ ሀብትህ አይደለም፣ ድኽነትህም አይደለም። ሰው የሚጎዳው ክፉ ልብ ነው። ክፉ ልብ ደግሞ
በሀብትም ሀብት በማጣትም የሚመጣ አይደለም።
ክፉ ልብ ሌሎች ክፉ ልቦች ይወልዳል። እሳት እሳትን እየወለደ ብዙ ዕንጨቶችን እንደሚበላ ኹሉ ክፉ ልብም እንደዚህ
ነው።
አንተ ሰው! ይህን ማወቅ ትወዳለህን? ክፉ ምግባር ወይም በጎ ምግባር በተፈጥሮ የሚገኙ አይደሉም። እነዚህ ኹለቱ
ከክፉ ልብ ወይም ከመልካም ልብ የሚገኙ ናቸው።"
(#ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ - አምስቱ የንስሐ መንገዶች)
"ከቤተ ክርስቲያን የሚበልጥ ብርቱ (ጠንካራ) ምንም የለም። ይህችውም ከሰማይ ከፍ ያለች ከምድርም ይልቅ
የሰፋች ናት። አታረጅም ነገር ግን ዘወትር ታበራለች።"…
"ቤተ ክርስቲያን በዘመናት ሁሉ ትሰፋለች። መታሰቢያዋም የሚጠፋ (የሚሞት) አይደለም።"…
"ቤተ ክርስቲያን በስንቶች ውጊያ ተደርጎባት ነበር? አልተሸነፈችም እንጂ። የተዋጓት አላውያን፣ የጦር መሪዎች፣
ነገሥታቱስ ምን ያህል ናቸው? የተማሩና ኃይልን የተሞሉ ጎበዞች ሐዲሲቷን ቤተ ክርስቲያን በብዙ ጎዳናዎች
ተዋግተዋት ነበር። ሊነቅሏት ግን አልቻሉም። ነገር ግን እርሷን የተዋጉ ጥቂቶች ለዝምታና ቶሎም ለመረሳት
ተላልፈው ተሰጥተዋል። የወጓት ቤተ ክርስቲያን ግን ከሰማይ በላይ ከፍ ከፍ ብላለች። ቤተ ክርስቲያንን ድል
ከማድረግስ ፀሐይን ማጥፋት (ማጨለም) ይቀላል። ሰው ሆይ! ከቤተ ክርስቲያን የሚበልጥ ኃያል ምንም የለም።
ከሰው ብትጣላ ወይ ታሸንፋለህ አልያም ትሸነፋለህ። ቤተ ክርቲያንን ግን ብትጣላ፣ ታሸነፍ ዘንድ የሚቻልህ
አይደለም። እግዚአብሔር ከሁሉ ይልቅ ኃያል ነውና። እግዚአብሔር መስርቷታል፣ እንግዲህ ማን ሊነቀንቃት ይችላል?
"
#############
#ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ
(በዲያቆን አቤል ካሳሁን የተተረጎመ)
ሰይጣን ምንም አይነት የመስቀል ምልክት የለውም የተዘቀዘቀ መስቀል እንኳን ስትመለከቱ ሰይጣንን ሳይሆን ቅዱስ
ጴጥሮስን አስቡት
###########
ምክረ አበው
ከሰይጣን በቀር ምንም ጠላት አይኑርህ፡፡ የሰዎችን ስህተት አትመራመር፤ የባልንጀራህን ኃጢአት አትግለጥ፡፡
የባልጀራህን ውድቀት ደጋግመህ አታውራ፡፡ በራስህ ኃጢአት ላይ ፍረድ እንጂ በሌሎች ላይ አትፍረድ ገዢያቸው
አይደለህምና፡፡ ኃጢአትን በፈጸመ ሰው ላይ ወቀሳ አታብዛ አንተም ትበድላለህና፡፡ ነገር ግን ከኃጢአቱ ይመለስ ዘንድ
ረዳትና መካሪ ሁነው፡፡ ከወደቀበትም የስህተት ሥራ እንዲወጣ አበርታው፡፡ ተስፋውን በእግዚአብሔር ላይ ቢያደርግ
ኃጢአቱ ልክ በእሳት ፊት እንደወደቀ ገለባ ፈጥኖ እንደሚወገድለት ንገረው፡፡ቅዱስ፣ ጥንቁቅ፣ ግልጽና ብልህ ሁን፡፡
እርጋታን የተላበሰ ሰብእና ይኑርህ፡፡ደስተኛ ሁን፤ ሰላምታህ በፈገግታ የታጀበ ንጹህ ይሁን፡፡ንግግርህ የታረመ አጭርና
በጨው እንደተቀመመ ጣፋጭ ይሁን፡፡ ቃላቶችህ የተመጠኑ እና ጤናሞች ሁሉም የሚረዳቸው ይሁኑ፡፡ የጓደኛህን
ምስጢር አትግለጥ፤ለሚወዱህ ሁሉ የታመንክ ሁን፡፡ ወደ ጭቅጭቅ እና
ንትርክ ከመግባት ራስህን ጠብቅ፡፡ የሚሰሙህ ሁሉ እንዳይጠሉህ ወደ ጠብ አትግባ፡፡
ከቅዱስ ኤፍሬም
ለወዳጅዎ ሼር ያርጉላቸው
https://t.me/tsidq
###############
“#ማግባት_ለሚሹ”
የቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ምክር
ከምንም በፊት የጋብቻ ዓላማን ማወቅ አለባችሁ፡፡ በሕይወታችን ለምን ጋብቻ እንደሚያስፈልገን መረዳት
አለባችሁ፡፡ ከዚህ ውጪ ሌላ ነገርን አትጠይቁ፡፡ እናስ የጋብቻ ዓላማው ምንድነው? ለምንድነው እግዚአብሔር
ጋብቻን የሰጠን? ብጹዕ ጳውሎስን እናድምጠው፤ እንዲህ ያለውን፦ "ስለ ዝሙት ጠንቅ ለእያንዳንዱ ለራሱ ሚስት
ትኑሮው፤ ለእያንዳንዲቱ ደግሞ ለራሷ ባል ይኑራት" (1 ኛ ቆሮ.7፥2)። "ከድህነት ይወጣ (ትወጣ) ዘንድ" ነው
የሚለውን? ወይስ "ሀብት ለማግኘት ሲባል" ነው የሚለውን? አይደለም፡፡ ታዲያ ምንድነው የሚለው? ከዝሙት
እንጠበቅ ዘንድ፤ ራሳችንን መቆጣጠር እንችል ዘንድ፤ ንጽህናን ገንዘብ እናደርግ ዘንድ፤ በትዳር አጋራችን ደስ ተሰኝተን
እግዚአብሔርን እናመሰግን ዘንድ፡፡ አያችሁ ይኼ ነው የጋብቻ ስጦታው ይኼ ነው የጋብቻ ፍሬው፤ ይኼ ነው የጋብቻ
ጥቅሙ፡፡
ስለዚህ #ልጆቼ! እማልዳችኋለሁ ትልቁን ጥቅም ዘንግታችሁት ዓይናችሁን በትንሹ ላይ አታሳርፉ፡፡ የትዳር አጋርን
ስትመርጡ የሀብት ጉዳይ የእናንተ ትልቅ አጀንዳ ሊኾን አይገባም፡፡ ስለ ሀብት ብሎ የትዳር አጋርን መምረጥ ድንቁርና
ነው፤ ሀብት ነገ ሊጠፋ ይችላልና፡፡ ስለዚህ ለትዳር የምትመርጡት ሰው ከምንም በላይ መንፈሳዊ ሀብቱን ተመልከቱ፡፡
በዚህም ዓለም በወዲያኛውም ዓለም ይበልጥ የሚጠቅማችሁ ይኼ ነውና፡፡
#አባቶች_ሆይ! አብርሃምን ምሰሉት፡፡ አብርሃም ለልጁ ለይስሐቅ ሚስትን ሲፈልግለት፦ ሀብትን አላየም፤
የንጉሣውያን ቤተሰብን አልተመለከተም፤ አፍአዊ ውበትን መመዘኛ አላደረገም፤ ወይም ይህን የመሰለ ሌላ
መስፈርትን አልደረደረም፡፡ የነፍስ ንጽህናን እንጂ፡፡
#እናቶች_ሆይ! ሴት ልጆቻችሁን እንደ ርብቃ አሳድግዋቸው፡፡
እናንተ ማግባትን የምትሹ #ወጣቶች_ሆይ! ይስሐቅን ምሰሉት፦ ዘፈንን፣ ዳንኪራን፣ ሳቅና ስላቅን፣ የከበሮንና
የዋሽንት ጫጫታን፣ ሌላውንም የዲያብሎስ ትርኢት በሰርጋችሁ ቀን አታስቡ፡፡ ከዚህ ይልቅ በምታደርጉት ኹሉም
ላይ እግዚአብሔር እንዲቀድማችሁ ለምኑት፡፡ ይህን ያደረጋችሁ እንደኾነ ትዳራችሁ ፍቺ፣ ዝሙት፣ ቅናት፣
ጭቅጭቅ፣ ንትርክ የሌለበት ኾኖ ይፀናላችኋል፡፡ ይህን ያደረጋችሁ እንደኾነ፥ ሌላው በረከትም ተትረፍርፎ
ይመጣላችኋል፡፡ የአውሎ ነፋስ ዓይነት በዙሪያችሁ ቢነፍስም፥ አትነዋወፁም፡፡
#እናንተ_ልጃገረዶች_ሆይ! ርብቃን ምሰሏት፡፡ የትዳር አጋራችሁን ፍጹም ለማፍቀር የተዘጋጃችሁ ኹኑ፡፡ ይህን
ያደረጋችሁ እንደኾነ ቤታችሁ ፍጹም ሰላማዊ ባሎቻችሁ የምትልዋቸውን የሚያደርጉና በፍቅራችሁ የሚንበረከኩ
ይኾናሉ፡፡ ትዳር እንዲህ ኾኖ ሲጀመር፥ እግዚአብሔርንና ወላጆቹን ደስ የሚያሰኝ ልጅ ይገኝበታል፡፡
የቤት ዕቃዎችን መግዛት ስንፈልግ፥ በጣም እንጠነቀቃለን፡፡ የሻጮቹን ማንነት አይተን፣ የዕቃዉንም ጥንካሬ
አገላብጠን ተመልክተን ነው የምንሸምተው፡፡ ሚስት ስናገባም ከዚህ የበለጠ ልንጠነቀቅ ይገባናል፡፡ የገዛነው ዕቃ ችግር
ቢኖርበት ለሸጠልን ሰው መመለስ እንችላለን፡፡ ሚስት ስናገባ ግን ወደ ቤተሰቦቿ መመለስ አንችልም፤ እስከ
ዕድሜአችን ፍጻሜ ድረስ ከእኛ ጋር ነው የምትኾነው፡፡ ክፉ ናት ብለን ብንመልሳት፥ በሕገ እግዚአብሔር መሠረት
አመንዝራ እንኾናለን፡፡ ስለዚህ፥ ሚስት ስትመርጡ የሀገራችሁን ሕገ መንግሥትን ብቻ አታንብቡ፤ ከኹሉም በፊት
ሕገ ቤተ ክርስቲያንን አንብቡ እንጂ፡፡
###############
+ አቤቱ ቅጣኝ ነገር ግን እንዳታዋርደኝ! +

እግዚአብሔር ፍቅር ነው ፣ መሐሪ ነው ፣ ይቅር ባይ ነው፡፡ ፍቅር ይቆጣል ወይ? ይቅር ባይስ ይቀጣል ወይ?
ብዙዎቻችን ስለ ክርስቶስ ሲነገረን መሐሪነቱና ፍቅሩ ብቻ ቢነገረን አንጠላም፡፡ ጨርሶ የማንፈራው እግዚአብሔር
እንፈልጋለን፡፡ እንዲህ አታድርግ! የሚለን ሲመጣ ‘አትፍረድ’ እንላለን ፤ ቆይተን ግን የሰማዩን ዳኝም አትፍረድ
ማለት ይቃጣናል፡፡ ቅጣት የሌለበት ክርስትና እንሻለን፡፡
ይህ ዓይነቱን ክርስትና ‘ጣፋጭ ክርስትና’ {የስኳር ክርስትና ይሉታል} ምንም ምሬት የሌለበት ሁሌም ማር ማር
የሚል ሕይወት አድርገው ክርስትናን የሚሰብኩም ብዙ ናቸው፡፡ ‘አይዞህ ብትታመም ትፈወሳለህ ፣ ቤትህ ይሞላል ፣
ቀዳዳህ ይደፈናል ፣ ብትበድልም አትቀጣም’ ብቻ የሚሉ ስብከቶች የስኳር ክርስትና ስብከቶች ናቸው፡፡ ይህንን ብቻ
የሚያጮሁ ሰዎች ክርስቶስ ‘የምድር ጨው ናችሁ’ ያለውን ትተው የምድር ስኳር ለመሆንና ዓለምን ለማስደሰት
የሚፈልጉ ናቸው፡፡
በእርግጥ እግዚአብሔር ይቆጣል ወይ? አዎን ይቆጣል! እንዲህ ይላል መጽሐፉ
‘እግዚአብሔር ቀናተኛና ተበቃይ አምላክ ነው እግዚአብሔር ተበቃይና መዓትን የተሞላ ነው እግዚአብሔር
ተቃዋሚዎቹን ይበቀላል፥ ለጠላቶቹም ቍጣውን ይጠብቃል። በቍጣው ፊት የሚቆም ማን ነው ? የቍጣውንም
ትኵሳት ማን ይታገሣል? መዓቱ እንደ እሳት ይፈስሳል፥ ከእርሱም የተነሣ ዓለቶች ተሰነጠቁ’ ናሆ 1፡1፣6
‘‘ከቍጣው የተነሣ ምድር ትንቀጠቀጣለች አሕዛብም መዓቱን አይችሉም’’ ኤር 10፡10
‘‘እኛ በቍጣህ አልቀናልና፥ በመዓትህም ደንግጠናልና’’ መዝ. 90፡7
እግዚአብሔር በተቆጣ ጊዜ የሚመልሰው የለም፡፡ ቅዱሳን የቁጣውን መጠን ስለሚያውቁ በትሕትና ይለምኑታል፡፡
ይሁንና መጽሐፍ ቅዱስ ስለ እግዚአብሔር ቁጣ ደጋግሞ ቢነግረንም አንድ ሌላ ደስ የሚያሰኝ ነገርም ነግሮናል፡፡
የእግዚአብሔር ቁጣው ለዘላለም አይደለም፡፡ "ምሕረቱ ለዘላለም ነውና" ይላል እንጂ"ቁጣው
ለዘላለም ነውና" አይልም:: የእግዚአብሔር ቁጣ ጊዜያዊ ነው፡፡
‘መሐሪ ነኝና ለዘላለም አልቆጣም’ ኤር 3፡12
‘ቁጣው ለጥቂት ጊዜ ሞገሱ ግን ለሕይወት ዘመን ነው’ መዝ 29፡5
‘ጌታ ለዘላለም አይጥልም ቢያሳዝንም እንደ ምሕረቱ ብዛት ይራራል ፤ የሰው ልጆችን ከልቡ አያስጨንቅም
አያሳዝንምም’ ሰ.ኤር 3፡31
የፈጣሪን የነነደ የቁጣ እሳት ማጥፋት የሚቻለን በዕንባ ነው፡፡ በደላችንን አምነን ቅጣት ይገባናል ነገር ግን መሐሪ ነህና
ማረን ማለት ይገባል፡፡ ንጉሥ ዳዊት ‘አቤቱ በቁጣህ አትቅሠፈኝ በመዓትህም አትገሥፀኝ’ ብሎ የፈጣሪን ቁጣ
አበረደ፡፡ /መዝ 38፡1/ ነቢዩ ኤርያስም ‘አቤቱ ቅጣኝ ነገር ግን እንዳታዋርደኝ በመጠን ይሁን እንጂ በቁጣ አይሁን’
ብሎ ተለማመጠ፡፡ ኤር 10፡24
አንድ ሠዓሊ በጣም ብዙ ደክሞ የተጠበበትን ሥዕሉን የፈለገ ቢበሳጭ ለረዥም ጊዜ ያንን ሥዕል ለመሳል የተጠበበትን
ጥበብ አስቦ ሥዕሉን ወደ እሳት አይጨምረውም፡፡ አባ ጊዮርጊስ እንዲህ ሲል ይለምናል ‘ሠዓሊ ሥዕሉን ያጠፋል
ወይ? [ጌታ ሆይ እኔን ስትፈጥር የተጠበብክበትን] የቀደመ ጥበብህን አስብ እንጂ! አስበህም ማረኝ! [ያጠፋዖኑ
ለሥዕሉ ሠዓሊ ፤ ኪነተከ ዘትካት ኀሊ]
ይቅርታውን በንስሓ ለሚለምኑ ሁሉ ምሕረቱ ቅርብ ነው፡፡ በቀኝና በግራው ወንበዴዎች በተሰቀሉበት በዕለተ አርብ
የግራው ወንበዴ ሲሰድበው ጌታ መልስ አልሠጠም፡፡ የቀኙ ወንበዴ ማረኝ ሲለው ግን ከአፉ ተቀብሎ በገነት ትሆናለህ
አለው፡፡ ቁጣው የራቀ ምሕረቱ የበዛ እርሱ የራበው ሰው ለምግብ የሚቸኩለውን ያህል ይቅር ለማለት ይቸኩላል፡፡
‘ምሕረትን ይወድዳልና ቁጣውንም ለዘላለም አይጠብቅም ተመልሶ ይምረናል ፤ ክፋታችንንም ይጠቀጥቃል ፤
ኃጢአታችንንንም በባሕሩ ጥልቅ ይጥለዋል’ ሚክ 7፡18
ልጆች ሳለን ጥፋት ስናጠፋ ከወላጆቻችን እንደበቃለን፡፡በተደበቅንበት ሰዓት ውስጣችን በፍርሃት ይርዳል፡፡ ‘ዛሬ
ገደለኝ’ ‘ዛሬ መሞቴ ነው’ ብለን እንጨነቃለን፡፡ የሚደርስብንን ቅጣት እጅግ አጋንነን ከመፍራታችን የተነሣ
መሬት ተሰንጥቃ ብትውጠን አንጠላም፡፡ በዚያ ሁሉ ጭንቀት ውስጥ ግን ወላጆቻችንም እስኪያገኙን ይጨንነቃሉ፡፡
እግዚአብሔርም እንዲህ ነው፡፡ አጥፍቶ በገነት ዛፎች መካከል የተሸሸገ አዳምን ወዴት ነህ ብሎ የፈለገ እርሱ እኛንም
ይፈልገናል፡፡ አዳም ከገነት ሳይባረር ገነት ውስጥ እንደጠፋ ፈጣሪ ሳያባርረን ራሳችንን በኃጢአት ተሸማቅቀን ያባረርን
እኛን ይፈልገናል፡፡ እርሱ ስለመጥፋትህ ይጨነቃል አንተ ‘ዛሬስ አይምረኝም’ ትላለህ፡፡
የሚገርመው በጥፋታችን ከተደበቅንበት ወላጆቻችን ካገኙን በኋላ ሁለተኛው ዙር ጭንቀታችን ‘ምን አጥፍተህ
ነው የተደበቅከው’ መባል ነው፡፡ ጥፋታችንን ሲያውጣጡን እንንቀጠቀጣለን፡፡ ያጠፋነውን ስለምናውቀው ስንት
እንደሚያስገርፈንም እናውቀዋለን፡፡ ‘ብትናገር ይሻላል? ግዴለህም!’ ብለው አግባብተውም አስፈራርተውም
ወላጆቻችን ጥፋታችንን ያውጣጡናል፡፡ እየፈራን ያጠፋነውን ጥፋት ስንናዘዝ ግን ወላጆቻችን በጥፋታችን ቅጥል
ብለው ‘አልመታህም ተናገር’ ያሉንን ረስተው የዱላ ዝናም ያዘንቡብናል፡፡ እግዚአብሔር ግን ጥፋትህን
ስትነግረው ቁጣው የሚገነፍል አባት አይደለም፡፡
’’ኃጢአታችንን ብንናዘዝ ኃጢአታችንን ይቅር ሊለን ከዓመፃም ሁሉ ሊያነፃን የታመነና ጻድቅ ነው’ 1 ዮሐ 1፡9
###########
አንተ ሰው እስኪ ንገረኝ!
አንድን የሥጋ ቁስል ለመፈወስ ለእያንዳንዱ ሰው ከባድ ነው፤ የነፍስን ቁስል መፈወስ ግን ለኹሉም ቀላል ነው፡፡ የሥጋ
ቁስል ለመፈወስ መድኃኒት ብሎም ገንዘብ ያስፈልጋል፤ ነፍስን ለመፈወስ ግን ቀላል ብሎም ወጪን የማይጠይቅ
ነው፡፡ ሥጋን ከዚያ ከሚያሰቃይ ቁስሉ ለመፈወስ አድካሚ ነው፡፡ ምክንያቱም በቀዶ ጥገና ምላጭ መቀደድ አለበት፤
መራራ መድኃኒቶችም ሊጨመሩበት ይገባል፡፡ ነፍስን ለመፈወስ ግን እንዲህ ዓይነት ነገር አያስፈልግም፡፡ ፈቃደኛ
መኾን ብቻ በቂ ነው፤ ፍላጎቱ ካለ ኹሉንም ነገር ለማድረግ ቀላል ነው፡፡ የእግዚአብሔር መግቦቱም እስከ አሁን ድረስ
ይህ ነው፡፡ ሥጋ ቢቆስል ያን ያህል ከባድ ጉዳትን አያመጣብንም፤ ምክንያቱም ምንም ባንታመምም እንኳን ሞት
መጥቶ ይህን ሥጋችን ያፈርሰዋል፤ ያበሰብሰዋልምና፡፡ ነፍሳችን ብትታመም ግን ጉዳቱ ብዙ ነው፡፡ እግዚአብሔር
የነፍስን ሕመም ለመፈወስ መድኃኒቱ ቀላል፣ ምንም ወጪና ስቃይ የሌለበት ያደረገውም ስለዚሁ ነው፡፡ ታዲያ
ምንም እንኳን በሕመሙ ምክንያት የሚያገኘን ጉዳት ያን ያህል ብዙ ባይኾንም የገንዘብ ወጪን የሚጠይቀው፣
ሐኪም የሚያስፈልገው፣ ብዙ ስቃይ ያለበት ሥጋችን ሲታመም እርሱን ለማከም እጅግ የምንደክም ኾነን ሳለ፥ እጅግ
ብዙ ጉዳት የሚያመጣውን፣ እርሱን ለመፈወስ ወጪ የማይጠይቀውን፣ ለማስታመም ሌሎች ሰዎች
የማያስቸግረውን፣ እንደ ምላጩና እንደ መራራ መድኃኒቱ ስቃይ የሌለበትን ይልቁንም ከእነዚህ አንዱስ እንኳን
ሳይፈልግ በእኛ ኃይል ባሉ ምርጫና ፈቃድ ብቻ መዳን የሚችለውን፣ ይህን ማድረግ ሳንችል ስንቀርም ከባድ ፍርድና
ቅጣት ስቃይም እንደሚያገኘን በእርግጥ እያወቅን የነፍሳችንን ቁስል ችላ የምንል ከኾነ ሊደረግልን የሚችል ምሕረት
እንደ ምን ያለ ምሕረት ነው? እኮ የምናገኘው ይቅርታ እንደ ምን ያለ ይቅርታ ነው?
ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ - ትምህርት በእንተ ሐውልታት መጽሐፍ #በገብረ_እግዚአብሔር_ኪደ የተተረጎመ
#########
+ በእግዚአብሔር መንግሥት አንድ ቀን +
ጸአተ ነፍስ (The departure of Soul) ከተሰኘው የኦርቶዶክስ ቴዎሎጂ ምሁራን የጋራ ሥራ የሆነ ዳጎስ ያለ ድንቅ
መጽሐፍ መግቢያ ላይ አንድ አባት ስለ አንድ ሰው ታሪክ የጻፉት ነገር በጣም አስገራሚ ነበር :: እጅግ መጥፎ የነበረ
አንድ ሰው ድንገት በጠና ይታመምና በአልጋ ላይ ይውላል:: ሕመሙ እጅግ የጠና ቢሆንም የማይገድለው ሆነና ለሠላሳ
ዓመታት ተሠቃየ:: በክፉ አመል ላይ ክፉ ሕመም ተጨምሮ ለሌሎችም ችግር ሆነ:: በአልጋው ላይ ሆኖም ደጋግሞ
ሰውንም ፈጣሪውንም ይሳደብ ነበር::
ከሠላሳ ዓመታት ሥቃይ በኁዋላ ግን ይህ ሰው ነፍሱ ከሥጋው ተለየች:: የመንደሩ ሰው ተሰበሰበና ማልቀስ ጀመረ::
"ውይ ተገላገለ" "ይኼ ክፉ አረፈ? ያረፍነውስ እኛም ነን!" እያለ በልቡ እያሸሞረ ቁጭ አለ:: አጅሬው ግን ሞተ
ከተባለ ሦስት ሰዓታት ቆይታ በኁዋላ ድንገት እንደ እንቅልፍ ነቃ:: ሰዉ ድንጋጤም ደስታም ተቀላቅሎበት
ተቀበለው::
ከዚያች ዕለት ጀምሮ ሞገደኛው ሰው እንደቀደመው መናከሱን ትቶ ትሑት ለሰው አዛኝ ሆኖ አረፈው :: የጠሉት ሁሉ
ይቅርታ እስኪያደርጉለት ድረስ እጅግ መልካም ሰው ሆነ:: አንድ አባት በሰውዬው መለወጥ ተደንቆ ሞቶ በነበረበት
ጊዜ ምን እንደገጠመው ጠየቀው:: እርሱም
እንዲህ አለ :-
"ከሞትሁ በኁዋላ ለሦስት ሰዓታት ያህል በሲኦል ሥቃይ ውስጥ ቆይቼ ነበር:: በሲኦል ካሳለፍሁት የሦስት ሰዓታት
ሥቃይ የምድር ላይ የሠላሳ ዓመት ሥቃይ እጅግ ይሻለኛል :: በሲኦል ሦስት ሰዓት ከመቆየት በምድር ላይ የዕድሜ ልክ
ሥቃይ ይሻላል"
በእርግጥ የሲኦል የአንድ ሰዓት ሥቃይ ከዚህ ዓለም የዐሥር ዓመት ሥቃይ ከበለጠ ከዚህ ዓለም የዕድሜ ልክ ደስታም
የመንግሥተ ሰማያት የአንዲት ቀን ደስታ ይበልጣል::
ንጉሥ ዳዊት "ከአእላፍ ይልቅ በአደባባዮችህ አንዲት ቀን ትሻላለች" እንዳለ በመንግሥተ ሰማያት አንዲት ቀን
መቆየት ደግሞ በዚህ ምድር ላይ ሺህ ዓመት ከመደሰት ይበልጣል::
“በዚህ ዓለም ብዙ ዘመን ከመኖር በገነት አንዲት ቀን ደስ መሰኘት ይሻላል :: ከብዙ ዘመኖችም አቤቱ ይቅርታህን
ማግኘት ይሻላል" 2 መቃ. 13:4
ለተጨነቀች ነፍስ ዕረፍት የሆነው የእግዚአብሔር ቃል ለሁሉ ይዳረስ ዘንድ ጸልዩ! ሌሎች እንዲያነቡትም
######
አንኳኩቼ አላገኘሁም አትበል፡፡ ብቻ የለመንከው፣ ደጅ የጠናኸው አንተ የምትወደው ሳይሆን እግዚአብሔር
የሚወድልህ ይሁን፡፡ ወደ እግዚአብሔር የተዘረጋ እጅ ፈጽሞ ባዶውን አይመለስም፡፡ ስለዚህ ራስህን፣ ልመናህን ምን
ዓይነት እንደሆነ ፈትሽ እንጂ አንኳኩቼ አላገኘሁም አትበል፡፡ እንኳንስ ንጹሐ ባሕርይ የሆነው እግዚአብሔር ክፋት
የሚስማማው ምድራዊ አባትም ለልጁ ጀሮውን አይደፍንም፡፡

አስቀድሞ ሕያዊት ነፍስን “እፍ” ብሎ እንዲሁ የሰጠን ጌታ፣ ኋላም ተቀዳሚ ተከታይ የሌለው አንድ ልጁን ሳይራራ
ከሰጠን እንደምን በዚህ ይታማል? እንደምንስ አይሰጠንም እንላለን? /ሮሜ.8፥32/፡፡ ልጁን የሰጠው እኮ ጭራሽ
“ስጠን” ብለው ላልለመኑ አሕዛብም ጭምር ነው፡፡ ታድያ እንዲህ የምንለምን እኛማ እንዴት አብልጦ
አይሰጠንም? የሚበልጠውን ሰጥቶን ሳለስ እንደምን ትንሹን አይሰጠንም እንላለን? ስለዚህ ከእኛ የሚጠበቀውን
ሳናደርግ “እግዚአብሔር ጸሎቴን አይሰማም” የሚል የሰነፎች አባባል የምንናገር አንሁን፡፡ ጆሮን የፈጠረ
ይሰማል!”

ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ
##########
በትሕትና ማደግ
ስለብዙ ነገር መጻፍ ይቻላል፤ ስለትሕትና ግን ለመናገር እና ለመጻፍ በኛ ደረጃ ላለ ድፍረት (ጥቂት ትዕቢት)
ይፈልጋል። ትሑት ልትሆን ትችላለህ ግን ትሑት እንደሆንክ ባሰብክ ሰዓት ትህትናህን አጥተኸዋል። ትህትናን ከባድ
የሚያደርገው ያ ነው። ትሁት እንደሆንክ እያሰብክ ትሁት መሆን አትችልም። ትህትና በመሆን ብቻ የሚገለጽ
መንፈሳዊ ፍሬ ነው።
ዴቪድ በድቢል እንዲህ ይላል “ታዋቂ መሆን እፈልጋለሁ ምክንያቱም ስለታዋቂነቴ ትሁት መሆን እሻለሁ። ግን
ምንድነው የኔ ትህትና በዚህ ወጥመድ ውስጥ ተቀርቅሬ?” ለዚህ ነው ትህትናን እንዳገኘናት መቼም እርግጠኛ
የማንሆነው። ትሁት ለመሆን እንፈልጋለን ከዛ ያን ትህትና በማሳየት እንታበያለን። በስክሩቴፕ ደብዳቤው ሉዊሲ
እንዲህ ይላል ወርምውድ የተባለው ሰይጣን አዲሱ ክርስቲያን ትሁት እየሆነ መምጣቱን ለታላቁ ሰይጣን ሲነግረው፣
ታላቅየው ሰይጣን ለወርሙድ ያለው ይሄን ነበር፤ “ወርምውድ እውነት ነው ታማሚህ (አዲሱ ክርስቲያንን ነው)
መቼም ትሁት እንዲሆን ልትፈቅድለት አይገባም፤ ትሁት ሆነ ማለት እቅዳችንን ሁሉ ማሳካት አንችልም ማለት
ነው። ስለዚህ ሂድ ትህትናውን አሳየው፣ ትሁት እንደሆነ ግለጥለት፤ ስለትህትናው ይወቅ ፥ መኖሩ የታወቀ ትህትና
ትህትና መሆኑ ያበቃለታል።”
አንድሪው መሬ እንዳለው ከትዕቢቶች ሁሉ በላይ የከፋው በቅድስናችን መታበይ ነው። ብዙዎቻችን ያለምንም
ምክንያት ትሁት እንደሆን እናስባለን ምክንያቱም ትሁት የሚመስሉ ቃላቶችን ስለተጠቀምን ወይም አንገታችንን
ስላቀረቀርን ወይም ትዕቢትን ስለተጠየፍን፤ እውነታው ግን ትዕቢተኞች በሆንን መጠን በሌሎች ላይ የሚታይን
ጥቂቷን ትዕቢት ራሱ መታገስ አንችልም። ዊሊያም ሎ እንዳለው ትህትናን መለማመድ ከፈለግህ ትዕቢተኛ
እንደሆንህ ማወቅ እና ማመን ያስፈልጋል፤ በሕይወትህ ሁሉ በዚህ በሽታ የተጠቃህ ነህና።
በትህትና ማደግ
አሁን ውይይታችንን እንጀምር ፥ ትዕቢተኛው በዚህ ለሚመስሉት የጻፈው በሚል መነሻ። መጀመሪያ ግን ለምን
በትህትና እንደግ ፥ መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል? ትዕቢት እንዴት የከፋ ነገር ነው ፥ ትህትናስ በፈጣሪያችን ዓይን
እንደምን ያማረ ነው?
• 2 ኛ ሳሙ 22፥28 “አንተ የተጠቃውን ሕዝብ ታድናለህና፤ የትዕቢተኞችን ዓይን ግን ታዋርዳለህ።”
• ኢሳ 66፥2 “ እነዚህን ሁሉ እጄ ሠርታለችና እነዚህ ሁሉ የእኔ ናቸው ይላል እግዚአብሔር፤ ነገር ግን ወደዚህ ወደ
ትሑት፥ መንፈሱም ወደ ተሰበረ፥ በቃሌም ወደሚንቀጠቀጥ ሰው እመለከታለሁ።”
• መዝ 107፥6 “እግዚአብሔር ትሑታንን ያነሣል፥ ኃጢአተኞችን ግን እስከ ምድር ድረስ ያዋርዳል።
• ምሳ 3፥34 “በፌዘኞች እርሱ ያፌዛል፥ ለትሑታን ግን ሞገስን ይሰጣል።”
• ትን.ሚክ 6፥8 “ሰው ሆይ፥ መልካሙን ነግሮሃል፤ እግዚአብሔርም ከአንተ ዘንድ የሚሻው ምንድር ነው? ፍርድን
ታደርግ ዘንድ፥ ምሕረትንም ትወጅ ዘንድ፥ ከአምላክህም ጋር በትሕትና ትሄድ ዘንድ አይደለምን?”
• ማቴ 18፥4 “እንግዲህ እንደዚህ ሕፃን ራሱን የሚያዋርድ ሁሉ፥ በመንግሥተ ሰማያት የሚበልጥ እርሱ ነው።”
• ሉቃ 14፥11 “ራሱን ከፍ የሚያደርግ ሁሉ ይዋረዳልና፥ ራሱንም የሚያዋርድ ከፍ ይላል።”
• ኤፌ 4፥2 “በትሕትና ሁሉና በየዋህነት በትዕግሥትም፤ እርስ በርሳችሁ በፍቅር ታገሡ፤”
• ያዕ 4፥10 “በጌታ ፊት ራሳችሁን አዋርዱ ከፍ ከፍም ያደርጋችኋል።”
• 1 ጴጥ 5፥5 “እንዲሁም፥ ጐበዞች ሆይ፥ ለሽማግሌዎች ተገዙ፤ ሁላችሁም እርስ በርሳችሁ እየተዋረዳችሁ
ትሕትናን እንደ ልብስ ታጠቁ፥ እግዚአብሔር ትዕቢተኞችን ይቃወማልና፥ ለትሑታን ግን ጸጋን ይሰጣል።”
የቤተክርስቲያን አባቶችም በተግባራቸው እንደገለጡት ከመካከላቸው ታላቅ ሆኖ የሚወጣው ሁልጊዜ ለራሱ ዝቅተኛ
ቦታ ያለው ነው። ራሱን ከልቡ ያነሰ እንደሆነ የሚያስብ አባት በእግዚአብሔር ከሌሎች ሁሉ አበው ተለይቶ ሲከብር
ተጽፎ አንብበናል። አውግስጢኖስ እንዳለው “አንድ ታዋቂ የንግግር ጥበብ አዋቂ በንግግር ትምህርት ውስጥ ትልቁ
ሕግ ምንድነው ተብሎ ሲጠየቅ ፥ መናገር አለ። ሁለተኛው ትልቁ ሕግስ ቢባል መናገር አለ አሁንም። ሦስተኛውስ
ተብሎ ሲጠየቅ ፥ ሦስተኛውም መናገር ነው አለ። እኔንም በክርስትና ትልቁ ሕግ ምንድነው ብትሉኝ፣ ሁለተኛውም
ሦስተኛውም ሁልጊዜ ትህትና ነው የምላችሁ” ይላል።
ዊልያም ሎ እንዳለው ሃይማኖትን ከትህትና ውጪ መኖር ማለት ከዓይን ውጪ ማየት እችላለሁ እንደማለት ነው
ወይም ሳይተነፍሱ በሕይወት እቆያለው ብሎ እንደማሰብ ነው ይላል። በጥልቀት ካሰባችሁበት ሰው ያለትህትና
እግዚአብሔርን ማወቅ አይችልም። ከፍ ያለውን ለማየት ዝቅ ማለት ያስፈልጋል። አባታችን ሆይ የሚለው የጸሎቶች
ሁሉ አውራ ሲጀምር በሰማያት ያለኸው አባታችን ብሎ ነው የሚጣራው። መቼስ እግዚአብሔርን ከደመናት በላይ
አስቀምጠነው ፥ ቦታን (space) ከሱ በላይ በሚያደርግ ሀሳብ እየጸለይን እንዳልሆነ ይገባናል። እርሱ ከየትኛውም
ስፍራ በላይ ግዙፍ ነው ፥ ሰማያት ይጠቡታል። በርግጥ ደግሞ እርሱ ረቂቅ ነው በዚህም ልባችንን ዙፋኑ ማድረግ
ይቻለዋል። በሰማይ እንዳለው ሁሉ በጥልቁ ሲዖልም እሱ በዛ አለ። ያለእርሱ ምንም ነገር ሕልውና የለውምና። ነገር
ግን “በሰማያት ያለው” የምንለው የኛን በዝቅተኛው ምድር ማለትም በውድቀት እና ውርደት ስፍራ ላይ ሆነን
የሱን የፍቅር ከፍታ አንጋጠን እያየን ስለሆነ ነው ፥ ያን ሰማያዊ አባት ነው ዝቅ ብለን የምንጠራው። እሱ ሁልጊዜ
ከላይ ነው፤ ከፍቅር ዝቅ ብሎ፣ ከፍትሕ ወርዶ፣ ከምሕረት ጎድሎ፣ ከኃይል ተቀንሶ፣ ከምልዓት አንሶ አያውቅም። እኛ
ግን ከምድር ነው ይሄን ጥሪ የምናቀርበው። የኢዮብ ምሬት ከኢዮብ ወዳጆች መልካም ቃላት በላይ የተወደደው እኮ
ለዚህ ነው፤ ኢዮብ ከቆመበት ሥፍራ ሆኖ እግዚአብሔርን ጠራው፤ ከሕመሙ፣ ሕመሙ ካስከተለበት ቁጣ፣ እጦቱ
ካመጣበት የስሜት ጉስቁልና ሆኖ እግዚአብሔርን ጠራው ፥ ከምድር ሆኖ። አላስመሰለም፣ ልቡ ተከፍቶ አንደበቱ
አልመረቀም፣ ምሬት ውጦት አድናቆት አፉን አልሞላም። ካለበት ሆኖ እግዚአብሔርን ጠራው። ወዳጆቹ ግን ይሄ
ታላቅ ምስጢር ተሰውሮባቸው ሳለ ፥ እንደሚያውቁ አስመሰሉ፣ ኢዮብን እግዚአብሔር እንደሚናገረው ከታላቅ
ዙፋን ተናገሩት፣ ፈርተው ሳለ ከፍርድ ወንበር ከማስመሰል ከፍታ ተናገሩ። ምድር ላይ ከሆንን ከምድር እንጥራው፣
ተናደን ሳለ ከእርጋታ ከፍታ፣ ጥላቻ ወርሶን ሳለ ከፍቅር ከፍታ፣ በቀል አንዶን ሳለ ከሀሰት የምህረት ፋፋቴ አንጥራው ፥
ከአለንበት እንጀምር።
ትዕቢት ግን ከከፍታ ለማየት ስለሚሞክር ፥ ጌታችን ከገለጠልን ሰማያዊ አባት ጋር መገናኘት ይሳነዋል። ራሱን በከፍታ
አስቀምጦ ስለሚናገር የእግዚአብሔርን ከፍታ ማየት እና ማግኘት አይችልም። ለዚህ ነው ነቢዩ ኢሳይያስ (57፥15)
እንዲህ ያለው “ለዘላለም የሚኖር ስሙም ቅዱስ የሆነ፥ ከፍ ያለው ልዑል እንዲህ ይላል። የተዋረዱትን ሰዎች
መንፈስ ሕያው አደርግ ዘንድ፥ የተቀጠቀጠውንም ልብ ሕያው አደርግ ዘንድ፥ የተቀጠቀጠና የተዋረደ መንፈስ ካለው
ጋር በከፍታና በተቀደሰ ስፍራ እቀመጣለሁ።” ጌታችንም በተራራው ላይ ስብከቱ ከዚህ ዝቅታ የሚጸልዩ ብቻ ወደ
ከፍታው መንግስቱ እንደሚገቡ ነግሮናል “በመንፈስ ድሆች የሆኑ ብፁዓን ናቸው፥ መንግሥተ ሰማያት የእነርሱ
ናትና።” (ማቴ 5፥3)። ውርደትን ትዕቢት እንደምትቀድማት ሁሉ ትህትናን ከፍታ ይከተለዋል። (ምሳ 11፥2)።
የትዕቢት መሠረት ራሳን ከሌላው ጋር ማነጻጸር እንደሆነ ሁሉ፤ ትዕቢት ሌሎችን የመብለጥ ጥማት ነው። ከባልንጀራህ
በላይ ሀብታም የመሆን ጥማት፣ ከባልንጀራህ በላይ ጎበዝ የመሆን ጥማት፣ ከባልንጀራህ በላይ ታዋቂ የመሆን ጥማት፣
ከባልንጀራህ በላይ ትሁት የመሆን ጥማት፣ ከባልንጀራህ በላይ ጻድቅ የመሆን ጥማት፣ ከባልንጀራህ በላይ ታዋቂ
የመሆን ጥማት እንደሆነ ሁሉ ፥ ትህትናም ራስን የማነጻጸር ውጤት ነው። ከማን ጋር ? በልቡ የዋህ እና ትሁት ከሆነው
ከጌታችን ጋር። በርሱ ፊት እንዴት ደቃቅ እንደሆንን የማወቅ ውጤት ነው፣ የኛ የሆነ እና ከርሱ ያልተቀበልነው ምንም
ምን እንደሌለ የማወቅ ውጤት ነው። ማንነታችንን ገልጦ በሚያያው በሱ ፊት ከፍቅሩ ውጪ ምንም የምንመካበት
ነገር እንደሌለን ራሳችንን ከሱ ጋር በማነጻጸር የምናውቅበት ውጤት ነው። ሁሉን ከእሱ እንደተቀበልን ካመንን
ስለየትኛው ነገር ነው የምንታበየው? ሁሉ ከኛ ሊወሰድ እንደሚችል ካመንን እንዴት በራሳችን ሁሉን እንዳልተቀበልን
እንመካለን?
ይሄን ስናስተውል የዛኔ እሱን እንፈራለን ፥ ያለእርሱ ፈቃድ በኛ ላይ ምንም ማድረግ የማይችሉትን ደግሞ ከመፍራት
እንቆጠባለን። ምክንያቱም ትዕቢት ማለት አንድም ያለአግባብ የዋለ ፍርሃት ማለት ነው። ፍርሃት ቦታውን ሲስት
ትዕቢትን ይወልዳል። ኃያሉን እግዚአብሔር መፍራት አቁመን ደካማውን ሰው ስንፈራ ትዕቢት ይወለዳል። በሰዎች
ፊት ጎድሎ የመታየት ፍርሃት ነው ትዕቢትን የሚወልደው። ሰዎች እውነተኛ ማንነታችንን ቢያውቁ ወይም
እንደማንም መሆናችንን ቢረዱ ይንቁናል ወይም ከኛ ይርቃሉ ወይም የምንፈልገውን ነገር አይሰጡንም የሚለው
ፍርሃት ነው አንደኛው የትዕቢት ምንጭ።
ነገር ግን በጸጋው ብዛት ፥ በምህረቱም ጥልቀት ልጆች እንድንሆን የጠራን እግዚአብሔርን ስንመለከት፤ እኛ
ስለራሳችን ከምናውቀው ደካማነት በላይ፣ ትላንት እና ዛሬ የበደልነውን ብቻ አይደለም ወደፊትም እንደምንበድለው
እና እንደምንክደው እያወቀ የሚወደን አምላክ እንዳለን ሲገባን የዛኔ ከዚህ አግባብ ያልሆነ ፍርሃት እንላቀቃለን።
ለዚህ ነው ትህትና ማለት ከፍርሃት መላቀቅ ማለት የሚሆነው። በሰዎች ፊት አንሶ ያለመታየት እና የመናቅ እና
የመጠላት ፍርሃት ሲለቀን ነው ትህትናን ገንዘብ የምናደርገው። ይሄ ግን በእርሱ የምህረቱ ብዛት በጸጋው የሚቻል
እንጂ በኛ ጥረት ብቻ አይደለም። ጸጋው ወደ ትህትና እንደሚመራን ሁሉ የክርስቶስን ጸጋ ለመቀበል ደግሞ ትህትና
ያስፈልጋል። ማለት ትህትና ነው ጸጋው እንዲሰራ የሚያደርገው። ጸጋው ነው ትሑት እንድንሆን የሚያደርገን።
ትህትና ነው ጸጋውን እንድንቀበል የሚያስችለን።
በአዲስ ኪዳን ላይ ስለእምነታቸው በጌታችን የተደነቁ ሰዎች ፥ ትሕትና ነበር ለእምነታቸው መደነቅ ምክንያት
የሆነው። ወደ ቤቴ ልትገባ አይገባህም ያለው መቶ አለቃ ፥ ጌታ ያደነቀለት እምነቱን ነበር ፥ መቶ አለቃው ግን ራስን
የማዋረድ ተምሳሌት ነው፤ ራሷን ከውሾች ጋር አንድ በማድረግ የወዳደቀ ምግቦች ለውሾች እንደሚሰጠው ለርሷም
የርሱ የምህርት እጅ ሊዘረጋ እንደሚገባ የለመነችው ያቺ ከነናዊት ሴትም ፥ እምነትሽ ታላቅ ነው የተባለችው።
ይሄም የሰው ልጅ በማመን ብቻ ትህትናን እንደሚለብስ ሲነግረን ነው ፥ ግን ደግሞ በትህትና ብቻ ነው ወደ ፍጹም
እምነትም የምንደርሰው።
የሚወዱትን አምላክ ሳይሆን እውነተኛውን አምላክ ለማየት የፈቀዱ ሰዎች ነበሩ እነዚህ የአዲስ ኪዳን አማኞች።
የምንፈልገውን አምላክ ሳይሆን እውነተኛውን አምላክ ለማየት ስንፈቅድ እና በእርሱ ላይ ምንም ምን መብት
እንደሌለን ስናውቅ ነው ያ ትሕትና መስራት የሚጀምረው። ጸሎታችን እሱን ለመቀየር ሳይሆን እኛን ለመለወጥ
ሲሆን እናየዋለን። እሱ በሰማያት ነው ያለው እኛ ነን ከጥልቁ መውጣት የሚያሻን። ከእኔነት ጥልቀት፣ ከወረድንበት
ውርደት ወደ ማይቀየረው እንዲቀይረን ስንማጸን ነው እሱን የምናውቀው። የዛኔ ጌታችን እንዴት ያለ ትሁት
እንደሆነ ይገባናል። ለትህትናዋ በፍጥረት መኃል ወደር የሌላትን የድንግል ማርያም ማሕጸን ውስጥ ለማደር ፍቃዷን
ጠየቀ፤ ከኃጢአት ጠብቆ ለራሱ ማደሪያነት ያቆየውን ሰውነት ለመግባት ፍቃድ ጠየቀ። ራሱ ያበጃጀውን ሰውነት
እንደ እንግዳ እና እንደ ባዕድ ልግባበት ብሎ መልዕክተኛ ላከ። ይሄ እንዴት ያለ ትሕትና ነው ? እንዴት ያለ ሰውን
ማክበር ነው ፥ እርሱ የሆነውን ጥቂቱን ብንናገር አከበርነው እንናለን እኛን ግን ከሚገባን በላይ ሰጠን። ከሚመጥነን
በላይ ወደደን። ይሄ ለሸክላ የሚገባው ክብር አልነበረም። ድንግል ማርያምም ይሄ የፈጣሪ ትህትና ቢደንቃት ፥ እንዲህ
ያለ ክብር ለባሪያው ምንድነው ብላ አደነቀች። “ትዕቢተኞችን በልባቸው አሳብ በተነ ፥ ትሑታንን ግን ከፍ
አድርጓል” አለችን ፍጥረት መድረስ የሚችለው የመጨረሻ ከፍታ ላይ የወጣችው ድንግል ማርያም።
ቅዱስ ጳውሎስ ለፊልጵስዩስ ሰዎች በጻፈው መልዕክቱ ይሄን ከላይ ጀምሮ የተገለጸውን እንዴት በሚገርም ውበት
እንዳስተማረን እንይ “ለወገኔ ይጠቅማል በማለት ወይም በከንቱ ውዳሴ ምክንያት አንድስ እንኳ አታድርጉ፥ ነገር ግን
እያንዳንዱ ባልንጀራው ከራሱ ይልቅ እንዲሻል በትሕትና ይቁጠር፤ እያንዳንዱ ለራሱ የሚጠቅመውን አይመልከት፥
ለባልንጀራው ደግሞ እንጂ። በክርስቶስ ኢየሱስ የነበረ ይህ አሳብ በእናንተ ዘንድ ደግሞ ይሁን። እርሱ በእግዚአብሔር
መልክ ሲኖር ሳለ ከእግዚአብሔር ጋር መተካከልን መቀማት እንደሚገባ ነገር አልቈጠረውም፥ ነገር ግን የባሪያን መልክ
ይዞ በሰውም ምሳሌ ሆኖ ራሱን ባዶ አደረገ፥ በምስሉም እንደ ሰው ተገኝቶ ራሱን አዋረደ፥ ለሞትም ይኸውም
የመስቀል ሞት እንኳ የታዘዘ ሆነ። በዚህ ምክንያት ደግሞ እግዚአብሔር ያለ ልክ ከፍ ከፍ አደረገው፥ ከስምም ሁሉ
በላይ ያለውን ስም ሰጠው፤” (ፊል 2፥3፡11)። በሰዓቱ እንዲያከብረን ፥ ራሳችንን እንደጌታችን እናዋርድ። መዋረድን
እንደመቀማት ላለመቁጥር እንጸልይ። በጊዜው ከፍ እንዲያደርገን ፥ በጊዜዬአችን ፈልገን እንዋረድ። መርጠን ዝቅ
እንበል።
በመጨረሻ ለዚህ ጽሑፍ ትልቅ ግብአት የሆነኝ መምህር ትህትናን ለመለማመድ እንድንችል ማድረግ ስላለብን
ደረጃዎች የዘረዘረውን ልጥቀስና ላብቃ፤

1) ለሌሎች ትችት እንዴት እንደምንመልስ እናስተውል፤

ብዙ ጊዜ “የማንረባ እና ደካሞች፣ ከንቱዎች እንደሆን” እንናገራለን፤ ግን ማንም እንደዚያ እንደሆንን ቢያምን እና


ያን መልሶ ቢነግረን ይከፋናል። እንናደዳለን። ትሑት ሰው ግን ግሳፄ እና ትችት የሚገቡት እንደሆነ ያውቃል፤ ራሱ
የተናገረው እውነት ስለሆነ ሌሎች ሲነግሩትም አይከፋውም።

ሰዎች ሲተቹን እና ሲገስጹን የመጀመሪያው መልሳችን መሆን ያለበት “አመሰግናለሁ። አስብበታለሁ። ልክ ልትሆኑ
ትችላላችሁ።” ይሁን መልሳችን። ራስን ነጻ እና ንጹህ ከማድረግ ሱስ እንላቀቅ። ትችትን በደስታ እንቀበል።
አንሽሸው።

2) ለሰዎች ትዕቢት የምንመልስበትን መንገድ እናስተውል፤

ዊልያም ሎ እንዳለው በትዕቢት የተሞላ ሰው የሌሎችን የሰናፍጭ ቅንጣት የምታህል ትዕቢት መታገስ አይቻለውም።
የሌሎች ትዕቢት ሲመረን ያ ሰው ለኛ ቦታ ስለሌለው ይሆናል። ይሄም በዛ ሰው ፊት መዋረዳችን ነው ያመመን።
ለዚህም ይሆናል ትዕቢተኛን በቀላሉ ማወቅ የምንችለው ፥ ለኛ ትዕቢት ቦታ ስለማይኖረው። እንዲህ ያለው ሰው
ሲገጥመን የትህትና መማርያ እናድርገው::

3) ለመከራ እና ለመናቅ የምናሳየውን ባህሪ እናስተውል፤

ትሑት ሰው ባሪያ ሆኖ ሳለ ከጌታው የተሻለ ክብርን አይሻም፤ የትኛውም ባሪያ ከጌታው የበለጠ ሊከበር ሊወደድ
አይገባውና። ጌታችን ከተሰቃየ፣ መከራንም ከተቀበለ፣ በሰዎች ፊት፣ በአለቆች ፊት ከተናቀ ለኛ እሱ ከተቀበለው
በላይ ክብር መፈለግ ትዕቢት ነው። ጆርጅ ማክዶናልድ እንዳለው “የሰው ልጅ (ጌታችን) እስከሞት ድረስ የተሰቃየው
፥ እኛ ሰዎች እንዳንሰቃይ ሳይሆን የኛ ስቃይ እንደእርሱ እንዲሆን ነው።” ከሱ ስቃይ ጋር ስቃያችን እንዲቆጠር
ነው። ስለዚህ በዚህ ምድር ክብርን መፈለግ ከጌታችን በላይ ለመሆን መመኘት ነው።

4) ከማን ጋር እንደምንገጥም እናስተውል፤

ቅዱስ ጳውሎስ ለሮሜ ክርስቲያኖች ትዕቢተኞች አትሁኑ ፥ ከእናንተም ከሚያንሱ ጋር ለመወዳጀት ፍቀዱ
እንዳለው፤ ይሄንንም ቅዱስ ጳውሎስ ራሱ ባሪያ ከሆነው ከአናሲሞስ ጋር ጥብቅ ወዳጅነት መስርቶ እንዳሳየን ፥ ከኛ
በሁሉ ነገር ዝቅ ካሉ ሰዎች ጋር ለመወዳጀት እንጣር። ከተከበሩ፣ ከታወቁ፣ ከአዋቂ ሰዎች ጋር ለመታየት፣ ፎቶ
ለመነሳት ከመጣር ያላነሰ ከኛ ከሚያንሱ፣ ማህበረሰብ ቦታ ከማይሰጣቸው ሰዎች ጋር ለመሆን እንፍቀድ።

5) ከጌታችን ትምህርት ወስደን ፥ ከኛ ክብር በታች የሆኑ ተግባሮችን ለመስራት እንፍቀድ፤

ሌሎች መስራት የማይፈልጉትን እንስራ። ሰዎች የሚሸሹትን አገልግሎት እናገልግል። ቆሻሻ መጥረግን፣
ማስተናገድን፣ ለታናናሾች የተተውትን አገልግሎት ሆን ብለን እንምረጥ። ይሄን ነው ዝቅ ብሎ እግር ያጠበው ጌታችን
ያስተማረን። ይሄን ደግሞ ለታይታ አናድርግ፤ ይሄን የማያደርጉትንም እኔ እንደነሱ አይደለሁም በሚል ትዕቢት
ላለመመልከት እንጣር።

6) በሌሎች ውድቀት እና ኃጢአት ፃድቅነታችሁን ስትለኩ ራሳችሁን ከያዛችሁት፤ የራሳችሁን ደካማነት እና ኃጢአት
የበለጠ አስቡ።

7) በጌታችን እና በቅዱሳን ስም በድብቅ በጎ ነገርን ለሰዎች አድርጉ፤ ከዛም ለማንም አትናገሩ፤ በድብቅ ይጽና
ለዘላለም። ያን ማድረግ ምን ያህል ከባድ እንደሆነ በፍጥነት ትደርሱበታላችሁ።

😍 ለሰዎች ስንል የውሸት ገጽታ ግንባታን ከማድረግ እንቆጠበ።

ባዚል ፓስካል እንዳለው ባለን ሕይወት እና በራሳችን አንረካም፤ ስለዚህ በሰው አዕምሮ ውስጥ ሀሳብ ወለድ
(imaginary) የሆነ ሕይወትን መኖር እንሻለን። በዚህም ምክንያት መብለጥ፣ ማንጸባረቅ እንፈልጋለን። ይሄን ሀሳብ
ወለድ (imaginary) ማንነት ለመጠበቅ እንደክማለን በዚህም ለእውነተኛው ማንነታችን ቦታ የለንም። ርጋታ፣
ደግነት፣ እውነተኝነት ባህሪያችን ከሆነ ያን ማንነታችንን ለሰው ለማሳወቅ እና ከሀሳብ ወለዱ ማንነታችን ጋር
ለማጣበቅ እንተጋለን። እነዚህን መልካም ባህሪያችንን ከራሳችን ለይተን ከሀሳብ ወለዱ ማንነታችን ጋር
እናስተሳስረዋለን። ጀግና ለመባል ፈሪዎች መሆንን እንመርጣለን። የከንቱ ማንነታችን መገለጫው አንዱ በአንዱ ብቻ
መርካት አለመቻላችን ነው። ስለዚህ እውነተኛ ማንነታንችንን እንክደዋለን። ለክብራችን ለመሞት እንወዳለን።

9) ምክር እና ሀሳብ ከመስጠት እንቆጠብ፤

ዘሎ የመምከር እና ሰውን የማቃናት ፍላጎታችንን እንግታ። ከዛ ይልቅ አጠገባችን ባለው እና በሚያወራን ሰው ላይ


እናተኩር። አጠገባችን ያለው ሰው ሕይወት ያለውን ውበት እናድንቅ። በተለይ ሰዎች ችግራቸውን ሲነግሩን የኛ ሀሳብ
ልዩ ስለሆነ አድርገን አናስብ። መደመጥ ፈልገው እንደሆነና፣ ብንችል በጸሎታችን እንድናስባቸው ይሁን እንጂ
ለመምከር አንፍጠን።

10) የምስጋና ሕይወትን እንምራ። አመስጋኝነት ትሕትና የሚበቅልበት ለም አፈር ነው።

11) መታዘዝን እንማር ፥ ራስን መስጠት እንለማመድ። መታዘዝ የሚፈልጉትን ማድረግ አይደለም። እሱማ
ሕጻናትም የሚወዱትን እንዲያደርጉ ሲነገራቸው ያደርጋሉ። የማንወደውን እና የማንፈልገውን ማድረግ እንጂ።

12) ሰዎችን እናክብር ፥ ለእውቀታቸው እና ለስብዕናቸው እውቅና እንስጥ፤

ሰዎችን በመተቸት እና በማዋረድ የእኛን ክብር በድብቅ ከፍ ከማድረግ ይልቅ ለሰዎች እውቀት፣ ስብዕና፣ አገልግሎት
እውቅና እንስጥ። እንዴት የእነሱ ማንነት እና ትምህርት እኛን እንደለወጠን በይፋ እንግለጽ። በሌሎች ስኬት
የመቅናትን ቅርምት እንዋጋ።

13) ትሕትናን አንፍራው፤


ትሕትና የጸጋ በር ነው፣ ትሕትና የክብር ዙፋን ነው፣ ትህትና የከፍታ መቅድም ነው፣ ትህትና የዓለማት ጌታን ወደእኛ
የሚያቀርብ ሠረገላ ነው፤ ስለዚህ እንዲህ እያልን እንጸልይ “ጌታ ሆይ ምንም ቢወስድ ፥ ምንም ቢፈጅ ትሑት
አድርገኝ።”

ሴምና ያፌት

| ጃንደረባው ሚድያ | ጥር 2016 ዓ.ም.|

✍🏽
ሊቀ ሊቃውንት ስምዐ ኮነ መልአክ

ምድር ከጥፋት ውኃ መድረቅ በኋላ በኖኅ መርከብ ውስጥ ከነበሩ እንስሳትና አራዊት በቀር ሌላ አንዳች ፍጥረት
አልነበረባትም። በምድር ላይ የሚርመሰመሰውን ሥጋ ለባሽ ፍጥረት ሁሉ ለጥፋት የዘነበው ውኃ ሙልጭ አድርጎ
ደምስሶታል። ኖኅ ከመርከብ ሲወጣ ምድርን በዝሙታቸው ያበላሿት የቃኤል ልጆች በከተሞቻቸው አልነበሩም።
ቅዱስ መጽሐፍ “በምድር ላይ ስማቸው የታወቀ ኃያላን ሆኑ” ዘፍ 6፥4 ብሎ የሚጠራቸው ኔፊሊሞች አሁን
የሉም። የደብር ቅዱስ ባህታውያንን በውበታቸው ያሳቱ የቃኤል ቆነጃጅትም እንደ ቀድሞው በከተሞች መካከል
ሲመላለሱ አይታዩም።

እግዚአብሔር ከተቆጣ ጉልበት አያድንም፤ ውበትም ልብ አያራራም፤ ደም ግባትም አያኖርም፤ ሀብትና ዝናም
መሸሸጊያ ሊሆን አይችልም። የእግዚአብሔር ትዕግሥት ምድርን ከዝሙቷ ካልመለሳት በቀር ከቁጣው የሚያስጥላት
ምንም ነገር የለም።
ምድርን ሁሉ ባዳረሰው በዚያ ጥፋት መካከል ራሱንና ቤተሰቡን ማትረፍ የተፈቀደለት ኖኅ ብቻ ነበረ፤ በእግዚአብሔር
ፊት ብቻውን ጻድቅ ሆኖ ተገኝቷልና። ከገነት ያስወጣችን ኃጢአት በዚህ ምድርም ከመኖር ከለከለችን። በገነት ሳለን
እርግማንን አመጣችብን፤ በዚህ ምድርም ላይ የጥፋት ዝናምን አዘነመችብን። ወዮ ! ከኃጢአት የተነሣ በሰው ላይ
የደረሰው መከራ ብዛቱን ማን ቆጥሮ መጨረስ ይችላል?

እሳት ከሰማይ ቢዘንብብን፣ ንፍር ውኃ ቢያቃጥለን፣ ምድር ተከፍቶ ቢውጠን፣ ረሀብና ቸነፈር ቢያጠቃን፣ ድርቅ
ምድራችንን እንዳታበቅል ቢያደርግብን፣ እርስ በእርሳችን መስማማት ቢያቅተን ይህ ሁሉ የሆነው በሌላ አይደለም፥
በኃጢአት ምክንያት ነው። ወደን በሠራነው ኃጢአት የማንወደው መቅሰፍት እየመታን እንኖራለን። ጣፍጦን
የፈጸምነው ኃጢአት መራራ ሞትን እያስፈረደብን ወደ ሲዖል ያወርደናል። እኛ ኃጢአትን መሥራታችንን፣
ኃጢአትም እኛን ማስጠፋቷን ቀጥላለች።

ከአባታቸው ጻድቅነት የተነሣ ከሞት የተረፉት የኖኅ ልጆች ከመርከብ ከወጡ በኋላ በሌላ መንገድ ኃጢአት በራቸውን
ስታንኳኳ ተመልክተናል። ለካ ያ ሁሉ ምድርን ለመቶ ሃምሳ ቀናት የሸፈናት ውኃ ኃጥአንን እንጅ ኃጢአትን ከምድር
ላይ አላጠባትም ኖሯልና ኃጢአት አሁንም በሰዎች ልብ ውስጥ ሥር መስደድ ጀመረች። ሰይጣን አዲስ አዲስ
የኃጢአት አሠራሮችን ማምጣት ልማዱ ነው። ከመርከብ የወጣው ትውልድ እንዳያመልጠው የቀደመውን ኃጢአት
ይዞ አልቀረበም፤ አዲስ የኃጢአት አሠራር ይዞ ብቅ አለ እንጅ። እስካሁን የአባቱን ዕርቃን አይቶ በገዛ አባቱ የሚሳለቅ
ትውልድ አልነበረም ዛሬ ግን ከሦስቱ የኖኅ ልጆች መካከል አንዱ የሆነው ካም የአባቱን ዕርቃን አይቶ ተሳለቀ፤
ብቻውንም አይቶ ሊቀር ስላልፈለገ ለወንድሞቹ ሁሉ የአባታቸውን ሀፍረት እንዲያዩ ቅስቀሳ አደረገ። “የከነዓን
አባት ካምም የአባቱን ዕራቁትነት አየ ወደ ውጭም ወጥቶ ለሁለቱ ወንድሞቹ ነገራቸው” ዘፍ 9፥22 እንዲል።

ሰይጣን ዘመናዊ ነው፤ አሠራሩም ለትውልድ እንዲስማማ አድርጎ ማቅረብም ልዩ ችሎታው ነው። የአንድ ዘመን
ትውልድ የተቀጣበትን ኃጢአት ለሌላ ትውልድ በማቅረብ ተከታይ ማጣት አይፈልግም። ስለዚህ ምን ያደርጋል
መሰላችሁ፥ የፅንሰ ሀሳብ ልዩነት ባይኖረውም የንድፈ ሀሳብ ልዩነት አድርጎበት በሌላ መንገድ ያቀርበዋል። ያን ጊዜ
ተከታዮችን ማግኘት ይችላል ማለት ነው። በዓለም ላይ ታላላቅ ጥፋቶችን ያስከተሉ ታላላቅ ኃጢአቶች ከአዳም
ኃጢአት {አምላክነትን መሻት} ጀምሮ እስከ ሞተ ወልደ እግዚአብሔር ድረስ ሰባት ናቸው። እነዚህን ለአዲሱ
ትውልድ በሌላ መንገድ ያቀርባቸዋል እንጅ ሌላ አዲስ ኃጢአት አያቀርብም።

ዮሐንስ በራእዩ የተመለከታቸው ሰባቱ የአውሬው ራሶች የተባሉትም እነዚሁ እንደሆኑ የሐዲስ ኪዳን መምህራን
ያስተምራሉ ራዕ 13፥1 ከመርከብ በወጣው ትውልድ መካከል የገባችው ይህች የዛሬዋ በደል ኖኅ ወደ መርከቡ
ከመግባቱ በፊት የነበረው ትውልድ የማያውቃት ሌላ በደል ናት − እሷም የአባትን ዕራቁትነት ማየት ናት። አዳም
ዕራቁቱን በነበረ ጊዜ በገነት ዕፀዋት መካከል መሸሸጉ ዕራቁትነት አሳፋሪ ነገር በመሆኑ ነው። እግዚአብሔርም ዕርቃኑን
ያሳይበት ዘንድ የገነትን ዕፀዋት በቅጠላቸው እንዳይሠውሩት አላደረጋቸውም። ዕርቃንን መግለጥ የማይገባ ስለሆነ
ነው።

ሴምና ያፌት እንደ እግዚአብሔር ሆነዋል፤ የኖኅን ዕርቃን አላዩምና። ይህንን ነገር በሰሙ ጊዜ በማስተዋል ያደረጉትን
ነገር መጽሐፍ ቅዱስ ይናገርላቸዋል። “ሴምና ያፌትም ሸማ ወስደው በጫንቃቸው ላይ አደረጉ የኋሊትም ሂደው
የአባታቸውን ዕራቁትነት አለበሱ ፊታቸውም ወደ ኋላ ነበረ የአባታቸውንም ዕራቁትነት አላዩም” ዘፍ 9፥23
ተባለላቸው።

አስተዋይ ትውልድ እርቃንን በማየት አይደሰትም። እርግማን ከምድራችን ላይ እንዲወገድ የሚያደርግ እንዲህ ያለ
ትውልድ ያስፈልገናል! ወደ ኋላ ሂዶ የታሪክ ዕርቃንን የሚሸፍን። እንዲህ ያለ ዘመን እንዲመጣልን እንጸልያለን፤
የአባቱን ሀፍረት ላለማየት በትክሻው ላይ ልብስ የሚያኖር ትውልድ እንዲሰጠን። ሴምና ያፌት በዚህ ዘመን ሊኖሩን
ያስፈልገናል።

የሆነ ዘመን ላይ ከጭንቅ ያወጡን፣ ክፉውን ዘመን ያሻገሩን ሰዎች ጥቂት ኅፀፅ ስናገኝባቸው በሰዎች ፊት መሳቂያና
መሳለቂያ የምናደርጋቸው ከሆነ ሰውነታቸውን ረስተናል ማለት ነው። ያኔ የታላቁ ቀላይ ምንጮች ተነድለው
የሰማይም መስኮቶች ተከፍተው ከላይና ከታች የጥፋት ዝናም በዘነመ ጊዜ በጥበባቸው የምንሳፈርበትን መርከብ
የሠሩልንን ሰዎች መሆናቸውን መዘንጋት አይገባንም።

ወደ ኋላ ተመልሶ በአባቶቹ የሚሳለቅ ትውልድ መፍጠር ምን ያደርጋል። ምንም ይሁን ምን ከጥፋት ውኃ ያተረፈን
አባቶቻችን የሠሩት ሥራ ነው። ያንን ሞት ያለፍነው አባቶቻችን በእግዚአብሔር ፊት ሞገስ ስለነበራቸው ነው። ወደ
ኋላ ከተመለስንም የምንሻገርበት መርከብ፤ የምንጠጋበት ወደብ የሠሩልን መሆናቸውን ማሰብ ይገባናል እንጅ
ዕርቃናቸውን እያነሣን ብናሳይ ከመረገም በቀር ምንም ጥቅም የለውም።

ከእኛ በፊት የነበሩ አባቶቻችን የሠሩትን ታሪክ ቀድሞ ያጠና ካለ ለሚሰሙት ሁሉ መናገር ያለበት ኖኅ ደክሞ
መተኛቱን እንጅ ዕርቃኑን መሆኑን አይደለም። ይህ ዛሬ ዕርቃኑን ያየነው ኖኅ ነው ዛሬ በሕይወት እንድንኖር ያደረገን።
በቤተ መንግሥት፣ በቤተ ክህነት፣ በማኅበራት፣ በግለ ሰቦች፣ በመኳንንት፣ በካህናት የደረሱ ጥፋቶች የተነገሩ የማይገቡ
ቃላት ሊኖሩ ይችላሉ። ዛሬ ላለው ትውልድ በየቀኑ ብናዘክረው እግዚአብሔር በመርከብ ጭኖ ከሞት ቢያሻግረው ሌላ
ሞት እንዲገጥመው ማድረግ ካልሆነ ሌላ ጥቅም የለውም። ይህንን ቀን እንድናይ መጽሐፍ ጽፈው፣ ጉባኤ ዘርግተው፣
አገር ለአገር ዞረው አስተምረው ክፉውን አመል በመልካም አመል እንድንለውጥ አድርገው የደከሙልን ብዙ አባቶች
አሉ።

የፖለቲካ፣ የጎሣ፣ የሃይማኖት መሪ የነበሩ ሊሆኑ ይችላሉ። ምናልባት የማይጠቅም ታሪክ ሠርተው እንኳን
ብናገኛቸው ለሚመጣው ትውልድ የማይነበብ የሚል ከላዩ ላይ ጽፈንበት እንጅ እንዲሁ ማስተላለፍ አይገባም።
ሴምን ያፌትን መሆን ይገባናል። “የሴም አምላክ እግዚአብሔር ይባረክ፤ እግዚአብሔር ያፌትን ያስፋ በሴምም
ድንኳን ይደር ከነዓንም ለእነርሱ ባሪያ ይሁን” ዘፍ 9፥26 ብሎ የሚመርቀን አባት የምናገኘው ሴምና ያፌትን በመሰለ
ሥራ ብንገኝ ነው። የሌሎችን ኃጢአት በትዕግሥት የራሳችንን ኃጢአት በንስሐ ማለፍ ከቻልን ከጻድቁ ኖኅ አፍ
የወጣው የሴምና የያፌት በረከት ዛሬም በኛ ላይ ነው። ከእኛ መካከል የሌላውን ነውር

መሆን እና መኖር

| ጃንደረባው ሚድያ | ጥር 2016 ዓ.ም.|

✍🏽 ቀሲስ ታምራት ውቤ እንደጻፉት

ቅዱስ ጴጥሮስ በደብረ ታቦር ተራራ የጌታችን መልኩ ተለውጦ ሲያበራ፤ ልብሱም በምድር አጣቢ ሊያነፃው
ከሚችለው በላይ ነጭ ሲሆን፤ ሙሴና ኤልያስም መጥተው ከጌታ ጋር ሲነጋገሩ አይቶ የመጣለትን ሀሳብ የገለጠበት
ቃል ነው " በዚህ መሆን ለእኛ መልካም ነው"።

አባቶች ቢርበንና ቢጠማን ሙሴ መና እያወረደ ውሃ እያፈለቀ፤ ጠላት ቢነሣብን ኤልያስ እሳት አውርዶ እያጠፋ፤
አንተ ደግሞ ብንታመም እየፈወስኸን ብንሞት እያነሳኸን በዚህ መሆን መልካም ነው ማለቱ እንደ ሆነ ይተረጉማሉ።

ቅዱስ ጴጥሮስ በዚህ ንግግሩ በዚያ ሥፍራ ብንገኝ ልናስበውና ልንመኘው የምንችለውን ሁላችንን ወክሎ
ስሜታችንን ነው የተናገረው። ለሥጋችንና ለስሜታችን ምቾትና ደስታ የሚሰጥ ቦታ መሆን የሁላችን ምኞት ነው::
ቢሆንልን መሆን የምንፈልግ የት ይሆን? አሁን ያለንበት ቦታና ሁኔታ ውስጥ ያለነውስ ተመችቶን ወይም ያን ሆነን
መኖርን አምነንበት ነው?

በእውነታው አንድ ነገር መሆንና (ሆኖ መገኘትና) የሆነውን መኖር እጅግ በጣም የተለያዩ ነገሮች ናቸው። ከትንሹ
ብንጀምር በተሰማራንበት ሙያ ባለሙያ መሆንና ሙያውን መኖር ይለያያል። አንድ ሰው ፖሊስ ቢሆን ዩኒፎርም
ለብሶ በሚንቀሳቀስበት የሥራ ሰዓቱ ወንጀል እየተከላከለ ከሥራ ውጭ ነኝ ብሎ ባሰበበት ሰዓት ወንጀል ሲፈፀም
አይቶ በግዴለሽነት ካለፈ ፖሊስ ሆነ እንጂ ሙያውን አይኖረውም፡፡ የሕክምና ባለሙያስ ሙያውን መኖር ያለበት የት
ይሆን? ብዙዎቻችንን የምንደስተው በ "መሆን" አችን እንጂ የሆነውን ስለ "መኖር" ተጨንቀን አናውቅም። መሆን
ውስጥ ያለው ደስታና ምቾት ሲሆን መኖር ውስጥ ግን የሚጠብቀን ተግባርና ኃላፊነት ነው። ብዙዎቻችን ጌታ
እግዚአብሔርን የምንለምነው የለመነውን ነገር እንድንሆን እንጂ የሆነውን እንድንኖረው አይደለም።

ትዳር የምንለምን ባል/ሚስት ስለ መሆን አብዝተን እንለምናለን የለመነውም ይሰጠናል። ትልቁ ችግር መሆን
የለመነውን ለመኖር ፍላጎቱ፣ ዝግጁነቱና ቁርጠኝነቱ ስለሌለን በ "መሆን" ገነት የመሰለን ሕይወት በ "መኖር" ደረጃ
ሲዖል ይሆንብናል። ስለዚህ ብዙዎቻችን ባል/ሚስት መሆን ችለናል ፤ ያልቻልነው ነገር ቢኖር ባል/ሚስት ሆነን መኖር
ነው። ባል/ሚስት መሆን ምቾት አለው። ከቤተሰብ ጭቅጭቅ፣ ከጓደኞች የነገር ጉንተላ፣ ከማኅበረሰብ ሐሜት፣
ከዕድሜ ጋር የጎሪጥ ከመተያየት፣ ሰው ሁሉ በፈሰሰበት ቦይ መፍሰስ አለመቻል ከሚፈጥረው ጭንቀት፣ ወዘተ . . .
ያሳርፋል። ባልነት/ሚስትነት የሚጠይቀውን መኖር ግን ያደክማል፤ ያታክታል። በመሆኑም ሚስትህን ባልሽ ነኝ
ከማለትህ በፊት ባልነትን መኖርህን ጠይቅ፤ ባልሽን ሚስትህ ነኝ እኮ ከማለትሽ በፊት ሚስትነትን መኖርሽን ጠይቂ፤
ሁለቱ ለየቅል ነው:: መሆን ከብዶ አያውቅም የሆነውን መኖር እንጂ !!!
አባት/እናት መሆንም እንዲሁ ደስታና የኅሊና ምቾት አለው፤ ከምላስ ያድናል። ወላጅነትን መኖር ግን ስንቶቻችንን
አታክቶን ልጆቻችን እንደ ምድረ በዳ አበቦች በክረምቱ ዝናምና በፀሐይ ብርሃን ብቻ አድገው እንዲፈኩ
አስመኝቶናል። የመሆንና የመኖር ልዩነቱ አይጣል!!!

ከፍ ወዳለ ሀሳብ ሰንሄድ ሰው መሆንና እንደ ሰው መኖር የተለያዩ ነገሮች ናቸው። ሰው ለመሆን የፃፍነው ማመልከቻ፣
ያወጣነው ወጪ ወይም የደከምነው ድካም የለም። እኔ ስለ ራሴ እስከማስታውሰው ድረስ ሰው ያልነበርኩበት ጊዜን
አላስታውስም። ስፀነስም ስወለድም ሰው ተብዬ እውቅና ተሰጥቶኛል፡፡ ሁላችንም እንዲሁ ነን። የሁላችንም ችግር
ደግሞ ሰው መሆንን መኖር አለመቻላችን ነው:: ዳዊት ሰው የሆነውን ልጁን ሰሎሞንን "ልጄ ሆይ ሰው ሁን!" ያለዉ
ሰውነትን ኑረው ሲለው ነው። ፈረስን ፈረስ ሁን፤ አንበሳን አንበሳ ሁን፤ እባብን እባብ ሁን ልንለው አንችልም።
ምክንያቱም የሆኑትን ይኖሩታልና። ሰው ግን በመጀመሪያ የሆነውን የማወቅ ጸጋ ስለተሰጠው ማለት ፈረስ ፈረስ፣
አንበሳ አንበሳ፣ እባብም እባብ ምን መሆኑን አያውቁም፤ ሰው ግን ሰው መሆኑን ስለሚያውቅ። ሁለተኛ ሰው የሆነውን
የመኖርም ሆነ ያለመኖር አቅም ስላለው ሌሎቹ ግን ስለሌላቸው የሆነውን በተግባርና በኃላፊነት እንዲገልጥ
(እንዲኖር) ይጠየቃል፤ ይነገረዋል። የሆነውን በመኖር ካልገለጠው ግን የሆነውንም ያጠፋዋል።

የበለጠ ከፍ ወዳለው ስናልፍ ደግሞ እኛ ክርስቲያን ሆነናል። ክርስቲያን የመባል ቀጥተኛ ፍቺ የእግዚአብሔር ልጅ
መሆን ማለት ነው። በመሆንና በመኖር ግን ትርጒሙ ይለያያል። የእግዚአብሔር ልጆች መሆናችንን ማንም ሊነጥቀን
አይችልም። ሲፈርድብን እንኳ እንደ ልጅ ነው:: ለፍርድ የሚያበቃን ግን የሆነውን አለመኖራችን ነው።

እንደ እውነቱ ይህን ጽሑፍ ከምናነበው ውስጥ ክርስቲያን በመሆኑ የሚከፋና "ምን አቅብጦኝ ነው ክርስቲያን
የሆንኩት" የሚል ወይም በአቅፋቸው ወስደው ያስጠመቁትን የሚረግም እንደሌለ እተማመናለው። ክርስትና ግን
ክርስቲያን ከመሆን ባለፈ መኖርን ባትጠይቀን ምንኛ መልካም ነበር?! የምንልም ቁጥራችን ቀላል አይሆንም። እንደው
በመሆን ብቻ ያቺ መንግሥት ብትወረስ ምን ነበረበት?! ግን የሆንከውን "መኖር" የሚል ግዴታ ተከተለው።

አሁንም እናስተውል አብዛኞቻችን ክርስቲያን ለመሆን ምንም አልደከምንም:: ማስታወስ ከምንችልበት ጊዜ አንስቶ
ክርስቲያን ያልነበርንበት ጊዜ ትዝ አይለንም። የሚገርመው ክርስትናን መኖር የቻልንበት ጊዜንም እንዲሁ
አናስታውስም። ክርስቲያን መሆንንም በመታወቂያ ደረጃ ያልተውነው በዚህ መሆን ለእኛ መልካም መስሎ ስለታየን
እንጂ መኖር ለሚጠበቅብን ቁርጠኛ ስለሆንን አይደለም። በክርስትና አስተምህሮ የሰማነው አምላክና እርሱን ከበው
በሚኖሩ ቅዱሳን ዙሪያ ስለ መሆን የሰማነው ትርክት የሰጠን ምቾት ስላለ በዚህ መሆን መልካም ነው ብለን
እናስባለን። ከገናናው ክብር ግን የሆነውን መኖር እንዳለብን የሚያስገነዝበው "እርሱን ስሙት" የሚለው ቃል ሲመጣ
ለ "መኖር" ወድቀን እንደ ሞተ ሰው እንሆናለን፤ ሁሉን ወደ መኖር ያመጣው እጅ እስኪዳስሰን ድረስ።

ማስታወሻ :- ቀሲስ ታምራት ውቤ የቴዎሎጂ ዲግሪና የሳይኮሎጂ ሁለተኛ ዲግሪ አላቸው:: ከክህነት አገልግሎታቸው
በተጨማሪም ደራሲና የሥነ ልቡና ባለሙያ (Clinical Psycologist) ናቸው:: ኤጲፋንያ በተሰኘ ቻናልም በቪድዮ
ያስተምራሉ:: https://youtube.com/@EpiphaniaTube?si=PNTkqiTwsXLytMYL
ቀሲስ ታምራት የጃንደረባው ሚድያ ዐምደኛ ሲሆኑ ጽሑፎቻቸው ዘወትር ረቡዕ የሚነበቡ ይሆናል:

ሙሴ ከሲና ተራራ ወርዶ ከሕዝቡ ጋር ሲገናኝ የፊቱን ማንጸባረቅ አይተው "ተሸፈንልን" ያሉት ሕዝቡ ናቸው።
እርሱ "ከእግዚአብሔር ጋር ስነጋገር ቆይቼ እኮ አሁን መውረዴ ነው ? ምነው የፊቴ ብርሃን አስቸገራችሁ?
ልሸፈንላችሁ እንዴ?" አላለም። እንዲያውም ቅዱስ መጽሐፍ "ሙሴም ከተራራው በወረደ ጊዜ እግዚአብሔር
ከእርሱ ጋር ስለ ተነጋገረ የፊቱ ቁርበት እንዳንጸባረቀ አላወቀም ነበር " ነው የሚለው።(ዘጸ 34፥29) ለቅዱሳን
እግዚአብሔር በፊታቸው የሚሥለው የክብር ብርሃን እነርሱን ለሚመለከታቸው እንጂ ለራሳቸው አይታወቃቸውም።
እውነተኞቹ ቅዱሳን "ተሸፈኑልን" የሚባሉ እንጂ "ልሸፈንላችሁ" የሚሉ አይደሉም።
ጥቂት በጎ ሥራ ሠርተህ ጻድቅነትህን በግድ ለማሳየት አትሞክር። ሌሎች ተሸፈንልን ይበሉህ እንጂ፣ አንተ ራስህ
"ልሸፈንላችሁ" እያልህ የዋሃንን አታስጨንቅ።

በአገራችን የሚታወቅ ተረት አለ። አንድ ጊዜ ትንኝ በሬ ቀንድ ላይ ቆመችና "ከብጄህ እንደ ሆነ ንገረኝና ልነሣልህ"
አለችው። በሬውም "እንኳን ልትከብጅኝ መኖርሽንም አላወቅሁም" አላት።

"ጻድቃን እንደ ሆኑ በራሳቸው ለሚታመኑና ሌሎቹን ሁሉ በጣም ለሚንቁ ይህን ምሳሌ ነገራቸው" ሉቃስ 18፥9

ዲያቆን አቤል ካሳሁን

+++ ልብስህን ማን ወሰደው? +++


❖❖❖❖
በአንድ ወቅት አባ ሰራብዮን ወደ እስክንድርያ በሄደ ጊዜ በገበያም ስፍራ አንድ ከልብስ የተራቆተ ነዳይ አገኘ፡፡ ለራሱም
"ይህ ደሃ ሰው ታርዞ መነኩሴ የተባልኩ እኔ እንዴት ለብሼ እታያለሁ ? በእውነት ይህ 'ታርዤ አልብሳችሁኛልና' ብሎ
የተናገረው ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ አይደለምን? በዚህ ብርድ እየተሰቃየ እንዴት አልፌው እሄዳለኹ?" ብሎ ፈጥኖ
ልብሱን በማውለቅ ይለብሰው ዘንድ ለዚያ ደሃ ሰጠው፡፡ ከዚያም በእጁ ያለውን መጽሐፍ ቅዱስ እንደ ያዘ እርቃኑን
በጎዳናው ዳር ተቀመጠ፡፡ እርሱን የሚያውቀው አንድ የከተማው ባለጠጋ ሰው አባ ሰራብዮን ባለበት ሥፍራ ሲያልፍ
ተመልክቶት ወደ እርሱ ቀረበና ‹አባ ሰራብዮን ሆይ ልብስህን ማን ወሰደው?› ሲል ጠየቀው፡፡ ቅዱሱም በእጁ ወደ
ያዘው መጽሐፍ ቅዱስ እየጠቆመ ‹ልብሴን የወሰደው ይህ ነው!› አለው፡፡ ያም ባለጠጋ አዲስ ልብስ ገዝቶ አለበሰው።

ከዚህም በኋላ አባ ሰራብዮን ከእርሱ እንደ ተለየ በመንገድ ሲሄድ ዕዳውን መክፈል ባለመቻሉ እያንገላቱ ወደ ወኅኒ ቤት
የሚወስዱትን አንድ ምስኪን ሰው ተመለከተ፡፡ እርሱም የያዘውን መጽሐፍ ቅዱስ ፈጥኖ በመሸጥ የዚያን ሰው ዕዳ
ከፍሎ ነጻ አደረገው፡፡ ይህንንም አድርጎ ጉዞውን ሲጀምር እንደ ገና ሌላ የታረዘ ነዳይ ሲለምን ተመለከተ። አባ
ሰራብዮንም እንደ ቀድሞው የለበሰውን ልብስ አውልቆ ለነዳዩ በመስጠት እርሱ እርቃኑን ወደ በአቱ ተመለሰ፡፡ ደቀ
መዛሙርቱም መምህራቸውን እርቃኑን ባዩት ጊዜ ደንግጠው ‹መምህር! ልብስህ ወዴት አለ?› ብለው ጠየቁት፡፡
እርሱም ‹መጸወትኩት› አላቸው፡፡ ደቀ መዛሙርቱም መልሰው ‹እኛን የምታጽናናበት መጽሐፍ ቅዱስህስ
አባታችን?› ሲሉ ደግመው ጠየቁት፡፡ አባ ሰራብዮንም ‹በእጄ የነበረው መጽሐፍ ቅዱስ ሁል ጊዜ ‹ሂድ ያለህን ሽጠህ
ለድሆች ስጥ› ይለኛል፤ ስለዚህ ያለኝ እርሱ ነበር እርሱንም ሸጥኩት› አላቸው፡፡

ኢትዮጵያዊው ቄርሎስ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ እንደሚናገረው ምጽዋት የፊት መብራት ናት፡፡ አንድ ሰው በጨለማ
ሲጓዝ ከኋላው መብራት ቢያበሩለትም እንኳ ከፊቱ የሚቀድመው የገዛ የአካሉ ጥላ እንቅፋት እየሆነበት ይጥለዋል፡፡
ወደ ፊት ያለውን መንገድ አጥርቶ እያየ ያለ ስጋት ለመሄድ እንዲችል የግድ የፊት መብራት ያስፈልገዋል፡፡ ጾም
፣ጸሎት እና ሌሎች መንፈሳዊ ትሩፋት እንደ ኋላ መብራት ናቸው፡፡ የፊት መብራት የተሰኘች ምጽዋት
ካልታከለችባቸው እነዚህ ብቻቸውን ዋጋን አያሰጡንም፡፡ የምጽዋትን ታላቅነት ልንረዳ ይገባል፡፡ ዓለም ሁሉ
ከወደቀበት የሕግ እርግማን የዳነው ቸር እረኛ በሆነው በመድኃኔ ዓለም በአካሉ ምጽዋትነት (በሥጋው በደሙ
መሰጠት) ነውና!!!

ለሌሎች ሼር በማድረግ እንድታደርሱ በፍቅር እጠይቃለሁ!

+ እኔ ግን እኔ አይደለሁም +

አውግስጢኖስ ፈጣሪ የለም ባይ እና በዝሙት የተበላሸ ሕይወት ይኖር የነበረ ሰው ነው :: በቅዱስ አምብሮስ ስብከት
ከተመለሰ በኁዋላ ግን ይህ ሰው ፍጹም በንስሓ ተለውጦ በምንኩስና መንገድ ሔዶ እስከ ጵጵስና ደረሰ :: ይህንን
የንስሓ ሕይወት መኖር ከጀመረ በኁዋላ ቀድሞ በአመንዝራነት ሕይወት ሲኖር ወዳጁ የነበረች አንዲት ሴት መንገድ
ላይ ከሩቅ አይታ ተከትላ ጠራችው::
ወደ ቀድሞ ትዝታውና ኃጢአቱ መመለስ ያልፈለገው ይህ አባትም ጥሪዋን እንዳልሰማ ሆኖ በፍጥነት መሔድ ጀመረ::
ይህች ሴትም እየሳቀች :-
አውግስጢኖስ እኔ እኮ ነኝ! ብላ ጮኸች

እርሱም ወደ እርስዋ ዞሮ :- "እኔ ግን እኔ አይደለሁም" አላት::

ክርስትና የወደቀ የሚነሣበት የረከሰው የሚነጻበት ሕይወት ነው:: በዚህ መስመር ያለፉ ሁሉ ትናንትን እየተዉ ሌላ
ማንነትን ይለብሳሉ:: ትልቁ ፈተና ሰዎች ተነሥተህ እያዩህም እንኩዋን መውደቅህን አለመርሳታቸው ነው :: ፈጣሪ
"ከእንግዲህ አትበድል" ብሎ ይቅር ቢልህም ሰዎች ግን ይቅር አይሉህም :: "ድመት መንኩሳ ዓመልዋን አትረሳ" እያሉ
እየተረቱ ወደ ነበርክበት እንድትመለስ ይገፉሃል እንጂ እንድትለወጥ አይፈቅዱልህም::

ሳውል አሳዳጅ ነበረ ዛሬ ግን ሐዋርያ ነው:: ብዙ ክርስቲያኖች ግን እርሱን ለማመን ተቸግረው ነበር:: ከመመረጡ
ጀምሮ "ኸረ እርሱ አይሆንም" ብለው ለፈጣሪ ምክር የሠጡም ነበሩ:: ከተመረጠ በኁዋላም ለመቀበል ተቸግረው
ከሐዋርያት አሳንሰው ያዩት አልጠፉም:: እርሱም በትሕትና "ሐዋርያ ተብዬ ልጠራ የማይገባኝ" ቢልም : "ጭንጋፍ"
ብሎ ራሱን ያለ ጊዜው ከሚወለድ ጽንስ ጋር አነጻጽሮ ዘግይቶ የተጠራ መሆኑን ቢናገርም ከሐዋርያት በምንም
የማያንስ ሐዋርያ ነበረ:: እነርሱ በትናንት ማንነቱ ሊያዩት ቢሹም እርሱ ግን "እርሱ አልነበረም" እርሱ መኖር አቁሞ
በእርሱ ይኖር የነበረው ክርስቶስ ነበረ::

አንዳንድ ሰዎች የማያምኑህ ከክፋት ተመልሰህ መልካም ስትሆን ብቻ አይደለም:: በጣም መልካም ስትሆንላቸውም
አያምኑህም:: ስታከብራቸው ምን አስቦ ነው? ብለው ይጠራጠራሉ:: መልካም ስታደርግላቸው "ምነው ደግነት
አበዛሽ? ተንኮል አሰብሽ እንዴ? "ይህቺ ጠጋ ጠጋ ዕቃ ለማንሳት ነው" "there is no free lunch” ብለው ሊሰጉ
ይችላሉ:: መልካም የሚያደርግላቸውን ሁሉ ሊያርድ የሚያሰባቸው የሚመስላቸው ሰዎች አሉ :: ፍቅር የትግል ስልት
የሚመስላቸው ጨብጠውህ ጣታቸው እንዳልጎደለ የሚቆጥሩ ዓይነት ተጠራጣሪ ሰዎች አሉ::

ዮሴፍ የገጠመው ይህ ነበር:: በሃያ ብር ሸጠው ግብፅ ያወረዱት ወንድሞቹን ይቅር ብሎ በፍቅር ተቀበላቸው ::
አባታቸውን ያዕቆብን አስመጥቶ በክብር በግብፅ እንዲኖሩ አደረጋቸው:: ከዓመታት በኁዋላ አረጋዊው ያዕቆብ ሞተ::
ይሄን ጊዜ የዮሴፍ ወንድሞች ድንገት ስብሰባ አደረጉ: "አባታችን ከሞተ በኁዋላ ቢበቀለንስ?!" ብለው ስጋታቸውን
ተመካከሩ::
ስለዚህ ዶልተው መጡና እንዲህ አሉት :-
አባታችን ከመሞቱ በፊት እንዲህ ሲል ተናዝዞ ነበር:: እባክህን የወንድሞችህን በደል ይቅር በል:: (ዘፍ 50:15-21)
ዮሴፍ ይኼን ሲሰማ አለቀሰ:: ይቅርታን አድርጎም አለመታመኑ አመመው::

እርሱ ለእነርሱ ድሮም ክፉ አልነበረም:: አሁን ደግሞ ላደረሱበት በደል እንኩዋን ፈጣሪውን የሚያመሰግን ሆኖአል::
"እናንተ ክፉ ነገርን አሰባችሁብኝ፤ እግዚአብሔር ግን ዛሬ እንደ ሆነው ብዙ ሕዝብ እንዲድን ለማድረግ ለመልካም
አሰበው" ነበር ያለው:: ምንም በደል ቢደርስበት እነርሱ አልተለወጡ ይሆናል እንጂ እርሱ ግን ትናንት የሚያውቁት
ዮሴፍ አይደለም:: "እኔ ግን እኔ አይደለሁም" አላቸው::

ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ


ታኅሣሥ 30 2012 ዓ ም
አዲስ አበባ

https://t.me/tsidq
+ አቤቱ ቅጣኝ ነገር ግን እንዳታዋርደኝ! +

እግዚአብሔር ፍቅር ነው ፣ መሐሪ ነው ፣ ይቅር ባይ ነው፡፡ ፍቅር ይቆጣል ወይ? ይቅር ባይስ ይቀጣል ወይ?
ብዙዎቻችን ስለ ክርስቶስ ሲነገረን መሐሪነቱና ፍቅሩ ብቻ ቢነገረን አንጠላም፡፡ ጨርሶ የማንፈራው እግዚአብሔር
እንፈልጋለን፡፡ እንዲህ አታድርግ! የሚለን ሲመጣ ‘አትፍረድ’ እንላለን ፤ ቆይተን ግን የሰማዩን ዳኝም አትፍረድ
ማለት ይቃጣናል፡፡ ቅጣት የሌለበት ክርስትና እንሻለን፡፡

ይህ ዓይነቱን ክርስትና ‘ጣፋጭ ክርስትና’ {የስኳር ክርስትና ይሉታል} ምንም ምሬት የሌለበት ሁሌም ማር ማር
የሚል ሕይወት አድርገው ክርስትናን የሚሰብኩም ብዙ ናቸው፡፡ ‘አይዞህ ብትታመም ትፈወሳለህ ፣ ቤትህ ይሞላል ፣
ቀዳዳህ ይደፈናል ፣ ብትበድልም አትቀጣም’ ብቻ የሚሉ ስብከቶች የስኳር ክርስትና ስብከቶች ናቸው፡፡ ይህንን ብቻ
የሚያጮሁ ሰዎች ክርስቶስ ‘የምድር ጨው ናችሁ’ ያለውን ትተው የምድር ስኳር ለመሆንና ዓለምን ለማስደሰት
የሚፈልጉ ናቸው፡፡
በእርግጥ እግዚአብሔር ይቆጣል ወይ? አዎን ይቆጣል! እንዲህ ይላል መጽሐፉ

‘እግዚአብሔር ቀናተኛና ተበቃይ አምላክ ነው እግዚአብሔር ተበቃይና መዓትን የተሞላ ነው እግዚአብሔር


ተቃዋሚዎቹን ይበቀላል፥ ለጠላቶቹም ቍጣውን ይጠብቃል። በቍጣው ፊት የሚቆም ማን ነው ? የቍጣውንም
ትኵሳት ማን ይታገሣል? መዓቱ እንደ እሳት ይፈስሳል፥ ከእርሱም የተነሣ ዓለቶች ተሰነጠቁ’ ናሆ 1፡1፣6
‘‘ከቍጣው የተነሣ ምድር ትንቀጠቀጣለች አሕዛብም መዓቱን አይችሉም’’ ኤር 10፡10
‘‘እኛ በቍጣህ አልቀናልና፥ በመዓትህም ደንግጠናልና’’ መዝ. 90፡7

እግዚአብሔር በተቆጣ ጊዜ የሚመልሰው የለም፡፡ ቅዱሳን የቁጣውን መጠን ስለሚያውቁ በትሕትና ይለምኑታል፡፡

ይሁንና መጽሐፍ ቅዱስ ስለ እግዚአብሔር ቁጣ ደጋግሞ ቢነግረንም አንድ ሌላ ደስ የሚያሰኝ ነገርም ነግሮናል፡፡
የእግዚአብሔር ቁጣው ለዘላለም አይደለም፡፡ "ምሕረቱ ለዘላለም ነውና" ይላል እንጂ "ቁጣው ለዘላለም ነውና"
አይልም:: የእግዚአብሔር ቁጣ ጊዜያዊ ነው፡፡

‘መሐሪ ነኝና ለዘላለም አልቆጣም’ ኤር 3፡12


‘ቁጣው ለጥቂት ጊዜ ሞገሱ ግን ለሕይወት ዘመን ነው’ መዝ 29፡5
‘ጌታ ለዘላለም አይጥልም ቢያሳዝንም እንደ ምሕረቱ ብዛት ይራራል ፤ የሰው ልጆችን ከልቡ አያስጨንቅም
አያሳዝንምም’ ሰ.ኤር 3፡31

የፈጣሪን የነነደ የቁጣ እሳት ማጥፋት የሚቻለን በዕንባ ነው፡፡ በደላችንን አምነን ቅጣት ይገባናል ነገር ግን መሐሪ ነህና
ማረን ማለት ይገባል፡፡ ንጉሥ ዳዊት ‘አቤቱ በቁጣህ አትቅሠፈኝ በመዓትህም አትገሥፀኝ’ ብሎ የፈጣሪን ቁጣ
አበረደ፡፡ /መዝ 38፡1/ ነቢዩ ኤርያስም ‘አቤቱ ቅጣኝ ነገር ግን እንዳታዋርደኝ በመጠን ይሁን እንጂ በቁጣ አይሁን’
ብሎ ተለማመጠ፡፡ ኤር 10፡24

አንድ ሠዓሊ በጣም ብዙ ደክሞ የተጠበበትን ሥዕሉን የፈለገ ቢበሳጭ ለረዥም ጊዜ ያንን ሥዕል ለመሳል የተጠበበትን
ጥበብ አስቦ ሥዕሉን ወደ እሳት አይጨምረውም፡፡ አባ ጊዮርጊስ እንዲህ ሲል ይለምናል ‘ሠዓሊ ሥዕሉን ያጠፋል
ወይ? [ጌታ ሆይ እኔን ስትፈጥር የተጠበብክበትን] የቀደመ ጥበብህን አስብ እንጂ! አስበህም ማረኝ! [ያጠፋዖኑ
ለሥዕሉ ሠዓሊ ፤ ኪነተከ ዘትካት ኀሊ]

ይቅርታውን በንስሓ ለሚለምኑ ሁሉ ምሕረቱ ቅርብ ነው፡፡ በቀኝና በግራው ወንበዴዎች በተሰቀሉበት በዕለተ አርብ
የግራው ወንበዴ ሲሰድበው ጌታ መልስ አልሠጠም፡፡ የቀኙ ወንበዴ ማረኝ ሲለው ግን ከአፉ ተቀብሎ በገነት ትሆናለህ
አለው፡፡ ቁጣው የራቀ ምሕረቱ የበዛ እርሱ የራበው ሰው ለምግብ የሚቸኩለውን ያህል ይቅር ለማለት ይቸኩላል፡፡
‘ምሕረትን ይወድዳልና ቁጣውንም ለዘላለም አይጠብቅም ተመልሶ ይምረናል ፤ ክፋታችንንም ይጠቀጥቃል ፤
ኃጢአታችንንንም በባሕሩ ጥልቅ ይጥለዋል’ ሚክ 7፡18

ልጆች ሳለን ጥፋት ስናጠፋ ከወላጆቻችን እንደበቃለን፡፡በተደበቅንበት ሰዓት ውስጣችን በፍርሃት ይርዳል፡፡ ‘ዛሬ
ገደለኝ’ ‘ዛሬ መሞቴ ነው’ ብለን እንጨነቃለን፡፡ የሚደርስብንን ቅጣት እጅግ አጋንነን ከመፍራታችን የተነሣ
መሬት ተሰንጥቃ ብትውጠን አንጠላም፡፡ በዚያ ሁሉ ጭንቀት ውስጥ ግን ወላጆቻችንም እስኪያገኙን ይጨንነቃሉ፡፡
እግዚአብሔርም እንዲህ ነው፡፡ አጥፍቶ በገነት ዛፎች መካከል የተሸሸገ አዳምን ወዴት ነህ ብሎ የፈለገ እርሱ እኛንም
ይፈልገናል፡፡ አዳም ከገነት ሳይባረር ገነት ውስጥ እንደጠፋ ፈጣሪ ሳያባርረን ራሳችንን በኃጢአት ተሸማቅቀን ያባረርን
እኛን ይፈልገናል፡፡ እርሱ ስለመጥፋትህ ይጨነቃል አንተ ‘ዛሬስ አይምረኝም’ ትላለህ፡፡

የሚገርመው በጥፋታችን ከተደበቅንበት ወላጆቻችን ካገኙን በኋላ ሁለተኛው ዙር ጭንቀታችን ‘ምን አጥፍተህ
ነው የተደበቅከው’ መባል ነው፡፡ ጥፋታችንን ሲያውጣጡን እንንቀጠቀጣለን፡፡ ያጠፋነውን ስለምናውቀው ስንት
እንደሚያስገርፈንም እናውቀዋለን፡፡ ‘ብትናገር ይሻላል? ግዴለህም!’ ብለው አግባብተውም አስፈራርተውም
ወላጆቻችን ጥፋታችንን ያውጣጡናል፡፡ እየፈራን ያጠፋነውን ጥፋት ስንናዘዝ ግን ወላጆቻችን በጥፋታችን ቅጥል
ብለው ‘አልመታህም ተናገር’ ያሉንን ረስተው የዱላ ዝናም ያዘንቡብናል፡፡ እግዚአብሔር ግን ጥፋትህን
ስትነግረው ቁጣው የሚገነፍል አባት አይደለም፡፡
’’ኃጢአታችንን ብንናዘዝ ኃጢአታችንን ይቅር ሊለን ከዓመፃም ሁሉ ሊያነፃን የታመነና ጻድቅ ነው’ 1 ዮሐ 1፡9

ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ


የቴሌግራም ቻናሌን መቀላቀል ለምትሹ
https://t.me/tsidq

ቤትህ ውስጥ ከፍተህ የረሳኸው ባንቧ ቢኖርና ድንገት ሌሊት ከእንቅልፍህ ስትነቃ መሬቱ እንዳለ በውኃ ተጥለቅልቆ
ብታገኝ በቅድሚያ ምን ታደርጋለህ? የፈሰሰውን ውኃ ለመጥረግ ወይስ የሚፈሰውን ቧንቧ ለመዝጋት ነው
የምትቸኩለው?

ቧንቧውን ሳትዘጋ መሬት ላይ ያለውን ውኃ ለማፈስ ብትሞክር ትርፉ ድካም ነው። ቀኑን ሙሉ ስትዝቅ ብትውል
ቤትህ የሞላውን ውኃ አታጎድልም። እናስ? ቧንቧውን ዝጋዋ!

በኃጢአት በወደቅህ ጊዜ መፍትሔ በማታገኝበት ነገር ላይ ጊዜህን አታባክን። ለዚህ የሚዳርገኝ መነሻው ምክንያት
ምንድን ነው? ብለህ ራስህን ጠይቅ። አእምሮህ ውስጥ የሞሉትን ክፋቶች ከመቁጠር በላይ እነዚያ ክፋቶች የገቡበትን
አንድ ቀዳዳ ወይም ሽንቁር ለማወቅ ጣር። እርሱን ያወቅኸው ቀን ለችግርህ ትልቁን መፍትሔ አብረህ ታገኛለህ። ያን
ቀዳዳ ከዘጋህ ወይም ምንጩን ካደረቅኸው የቀረው ቀስ እያለ ተኖ መጥፋቱ አይቀርም። ከመውደቅህ በላይ
የውድቀትህ ምክንያት ያስጨንቅህ።

ዲያቆን አቤል ካሳሁን


https://t.me/tsidq

"ኹሌም በሄድኩበት የምናገረው አንድ ነገር አለኝ"!

ቤተክርስቲያንን የሚያስቀጥሉ ሦስት ሰንሰለቶች አሉ እነርሱም


ትዳር፣
ምልኩስና
፣ክህነት ናቸው።
እነዚህ እክል ስለገጠማቸው ነው ቤተክርስቲያን እየተቸገረች ያለቸው።
ሌሎች ሰዎች ወይም አህዛብ ክፉ ስለሆኑ አይደለም።እነሱ ደግ የሚሆኑበት ዘመን ነገም እኔ አልጠብቅም ሰይጣን
ባለበት መልካም ነገር አይመጣም።

እኛ ግን የጎደለን ይህ ነው፣ በተከበረ ትዳር ፣በተከበረ ምንኩስና፣በተከበረ ክህነት ቤተክርስቲያን ትቀጥላለች።

ምሳሌ እንዴት ካልን፦


የተከበረ ትዳር" የተከበረ መነኩሴ ይወልዳል።
የተከበረ መነኩሴ የተከበረን ጵጵስናን ያመጣል።
የተከበረ ጳጳስ የተከበረን ክህነትን ይሾምና
የተከበረው ክህነት: የተከበረ ትዳርን ባርኮ ያጋባል። የተከበረው ትዳር መለሶ እንደገና የተከበረ ካህንን ይወልዳል
።በዚህ ኡደት ነው ቤተክርስቲያን ተጠብቃ የምትኖረው። አኹን ግን ምንጩ ደፍርሷል። ለዚህም ኹላችንም
መስተካከል አለብን" አሁን እኔ ኹሉም ሥርዓት እየፈረሰ እንደሆነ ነው የሚሰማኝ!ተምረን ማግባትና፣ተምረን
መመንኮስም ሆነ ክህነት መያዝ ማስቀጠል አለብን።

ር/ ሊቃውንት አባ ገብረ ኪዳን


የቴሌግራም ቻናሌ መቀላቀል ለምትሹ
https://t.me/tsidq

“በምድር ላይ የምንቆየው የዕድሜ ልክ ቆይታ በዘላለማዊው ሕይወት ካለው የዓይን ጥቅሻ አፍታ ጋር እንክዋን እኩል
አይሆንም:: የዚህ ምድር ቆይታ እንግዲህ ለዚያኛው የሚያበቃን ነው" አቡነ ሺኖዳ ሣልሳዊ

"እመቤቴ ሆይ በአንቺ ጸሎት በልጅሽ ቸርነት ከታመንሁ ሰማይ ወፍጮ ምድር መጅ ቢሆኑ ሁለቱም ሊያጠፉኝ
ቢፈልጉ አንዳች ሊያደርጉኝ አይችሉም" ቅዱስ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ

"ሰዎች የተራሮችን ከፍታ የባሕርን ሞገድ የወንዞችን ረዥም ፍሰት : ለማድነቅ ወደ ብዙ ሀገራት ይጉዋዛሉ :
የከዋክብትን ውበትም ያደንቃሉ:: አንድን አስደናቂ ፍጥረት ግን ቸል ብለው ያልፉታል : ይህ ድንቅ ፍጥረት የሰው ልጅ
ነው::" ቅዱስ አውግስጢኖስ

አንድን አባት ሰዎች መጡና "ዘወትር ጸሎት በማድረግህ በሕይወትህ ላይ የጨመረልህን ነገር ንገረን ?" አሉት:: እርሱ
ግን "ጸሎት በማድረጌ ከጨመርሁት ይልቅ የቀነስሁት ይበዛልና እርሱን ልንገራችሁ :: ጸሎት በማድረጌ ከሕይወቴ
ውስጥ ጭንቀት ፍርሃት ተስፋ መቁረጥና ቁጡነትን ቀንሻለሁ አላቸው::

የትንሣኤ ሰሞን ክርስቶስ ከሙታን ተነሣ ብሎ ሰላምታ መለዋወጥ በኦርቶዶክሱ ዓለም እጅግ የተለመደ ነው:: ቅዱስ
ኤፍሬም ሶርያዊ ግን ይህንን ዓመታዊ ሰላምታ የዘወትር አድርጎ ወደ እርሱ የመጣን ሰው ሁሉ በፈገግታ"ክርስቶስ
ተነሣ" ብሎ ያበሥር ነበር::

ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ


https://t.me/tsidq

+ እኔንም አስበኝ +

ዮሴፍ በበደል ላይ በደል የበዛበት ሰው ነው:: ሆድ ብሶታል:: ከሀገሩ የወጣው ፈልጎ ሳይሆን የገዛ ወንድሞቹ ሸጠውት
ነበር:: ከመሸጡ በላይ በሥጋ ወንድሞቹ መጠላቱ ልቡን አቁስሎታል:: ዐሥር ወንድሞቹ ጨክነው ተስማምተው
መሸጣቸውን ማሰብ ደግሞ በጣም ከባድ ነበር::

ባይተዋሩ ዮሴፍ እንደተከፋ ወደ ግብፅ ሲወርድ እግዚአብሔር ከዮሴፍ ጋር አብሮ ተሸጠ እንጂ ብቻውን
አልተወውም:: በመከፋቱ አብሮት ተከፋ:: ስለኀዘኑም አብሮት አዘነ::

ዮሴፍ ጲጥፋራ በተባለ ሰው ቤት ባሪያ ሆነ:: በአባቱ ተወዳጅ ሆኖ ላደገው ቅምጥሉ ዮሴፍ በሰው ቤት ባሪያ መሆን
እጅግ ከባድ ነበር::
ሆኖም በሰው ቤት ባሪያ በሆነ ጊዜ ግን የጌቶች ጌታ የሆነው እግዚአብሔር አብሮት ነበረ :: በጌታው ፊት ሞገስ
ሠጥቶት ስለነበር የቤቱ አዛዥ ናዛዥ ሆኖ ተሾመ::

እግዚአብሔር ከአንተ ጋር ከሆነ ባሪያ ሆነህ ብትሸጥም ባለ ሥልጣን ትሆናለህ::

እረፍት አልባው ዮሴፍ በተሾመበት ቤት ብዙም ሳይቆይ ግን የጌታው ሚስት ለዝሙት አስቸገረችው:: እግዚአብሔር
ን ፈርቶ አሻፈረኝ ሲላት ራስዋ ገርፋ ራስዋ ጮኻ እስር ቤት ጣለችው::

መከረኛው ዮሴፍ እስር ቤት ወረደ:: የታሰሩ ሁሉ ወንጀለኞች አይደሉም:: የአንዳንዶችን ኃጢአት ለመሸፈን
የሚታሰሩ ንጹሐን ብዙ ናቸው::

ዮሴፍ ያለ በደሉ ሲታሰርም ብቻውን አልሆነም::


እግዚአብሔር ከዮሴፍ ጋር አብሮ ታሰረ:: በበደል ላይ በደል ደርሶበት በገባበት ወኅኒ ቤት "እግዚአብሔር ከዮሴፍ ጋር
ነበረ ምሕረትንም አበዛለት፥ በግዞት ቤቱም አለቃ ፊት ሞገስን ሠጠው" ዘፍ. 39:21

እግዚአብሔር ከአንተ ጋር ከሆነ እስር ቤት ውስጥም ትሾማለህ:: ዮሴፍ የወኅኒው ባለ ሥልጣን ሆነ::

ከዚህ በኋላ ዮሴፍ በወኅኒው ለሁለት ሰዎች ሕልም ይፈታላቸው ጀመር:: የአንዱ ሕልም ፍቺ "ተሰቅለህ ትሞታለህ"
የሚል ሲሆን የሌላኛው ሕልም ፍቺ ደግሞ "በፈርኦን ፊት ዳግመኛ ትሾማለህ" የሚል ነበር::

ወደ ፈርኦን ቤተ መንግሥት ተሹሞ የሚሔደውን ሰው ዮሴፍ እንዲህ አለው :-

"ነገር ግን በጎ ነገር በተደረገልህ ጊዜ እኔን አስበኝ ምሕረትንም አድርግልኝ የእኔንም ነገር ለፈርዖን ነግረህ ከዚህ ቤት
አውጣኝ:: እኔን ከዕብራውያን አገር ሰርቀው አምጥተውኛልና፤ ከዚህም ደግሞ በግዞት ያኖሩኝ ዘንድ ምንም
አላደረግሁም።" ዘፍ. 40:14

ዮሴፍ "እኔንም አስበኝ ምሕረት አድርግልኝ" ብሎ የተማጸነው የፈርኦን ጠጅ አሳላፊ ግን "ዮሴፍን አላሰበውም፥
ረሳው እንጂ" ዘፍ. 40:23

ከዚህ በኋላ ዮሴፍ ለሁለት ዓመታት በእስር ቆየ እንጂ ምንም የተፈጠረ ነገር የለም::

ባሪያ ሆኖ ሲሸጥ አብሮት የተሸጠው እግዚአብሔር


እስር ቤት ሲገባ አብሮት የታሰረው እግዚአብሔር
አሁን ግን ዮሴፍን ዝም አለው::

ለምን?
ዮሴፍ "እኔንም አስበኝ ምሕረት አድርግልኝ" ብሎ የለመነው የጠጅ አሳላፊውን ነበር:: በግፍ ከሀገሩ እንደወጣ ያለ
በደሉ እንደታሰረ ያስረዳው ለፈርኦን ቤት ሹመኛ ነበር:: ስለዚህ እግዚአብሔር "ዮሴፍ ሆይ ጠጅ አሳላፊውን አስበኝ
አልክን? በል እሱ ያስብህ" ብሎ ተወው::

በሕይወትህ ሰውን አደራ ያልክ ቀን እግዚአብሔር ይተውሃል:: "አውጣኝ" ያልከው ሰውን ከሆነ ፈጣሪ የሰውን ነገር
እንድታይ ዝም ይልሃል::

ሁላችንም አደራ አስበኝ ብለን የተማመንንባቸው ጠጅ አሳላፊዎች አይጠፉም:: እንደ ዮሴፍ ቤተ መንግሥት ውስጥ
ሰው አለኝ ብለን ተስፋ የጣልንባቸው ፣ ዘመድ አለኝ ብለን የሙጥኝ ያልናቸው ሰዎች አይጠፉም :: "በአንድ ስልክ
ልጨርሰው እችላለሁ እኮ" ብለን የተመካንባቸው ሰዎች አናጣም::

ወዳጄ እመነኝ ሰው አደራ በላ መሆኑ አይቀርም:: ቃል የገባልህ ሰው ወደ ሹመቱ ሲገባ አያስታውስህም::


ሥጋ ለባሹን አደራ ብለህ ከፈጣሪህ አትጣላ::

ሰውን በቤተ መንግሥት አስበኝ ከማለት ፈጣሪን በመንግሥትህ አስበኝ ማለት ይሻላል::

"በሰው ከመታመን ይልቅ በእግዚአብሔር መታመን ይሻላል። በገዦች ተስፋ ከማድረግ ይልቅ በእግዚአብሔር ተስፋ
ማድረግ ይሻላል" መዝ. 118:8

ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ


ጥቅምት 6 2015 ዓ.ም.
ዲላ ኢትዮጵያ

ለተጨነቀች ነፍስ ዕረፍት የሆነው የእግዚአብሔር ቃል ለሁሉ ይዳረስ ዘንድ :: እኔም ለእናንተ ከሰበክሁ በኁዋላ
የተጣልሁ እንዳልሆን አጥብቃችሁ ስለ እኔ ጸልዩልኝ!
በኮሜንት መስጫው ሥር "ለሚሰሙት ጸጋን ይሰጥ ዘንድ፥ እንደሚያስፈልግ ለማነጽ የሚጠቅም ማናቸውም በጎ
ቃል እንጂ [ዋጋን በምድር የሚያስቀር ውዳሴም ሆነ ሌላ] ክፉ ቃል ከአፋችሁ ከቶ አይውጣ" (ኤፌ 4:29)

ሌሎች እንዲያነቡትም Share ያድርጉ :-


https://t.me/tsidq

ሰበር መረጃ
++++++++++++++++++++++++++++++++++
በምሥራቅ ሸዋ ሀገረ ስብከት በሚገኘው ጥታዊው የዝቋላ ደብረ ከዋክብት አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ገዳም እራሱን
ኦነግ ሸኔ ብሎ በሚጠራው ቡድን የገዳሙን መጋቢ ጨምሮ አራት አባቶችን መግደሉን ገዳሙ አስታውቋል፡፡
ሰኞ የካቲት 11 ቀን 2016 ዓመተ ምሕረት ታጣቂዎቹ ሦስት አባቶችን አግተው ወደ በረሃ ከወሰዱ በኋላ የታገቱትን
ለማስለቀቅ ገዳሙ ጥረት በሚያርግበት ወቅት የካቲት 13 ቀን 2016 ዓ.ም ተጨማሪ አባቶችን በመያዝ
1. የገዳሙ መጋቢ አባተክለማርያም ዐሥራት
2. የገዳሙ ጸሐፊ አባ ኪዳነ ማርያም ጥላሁን
3. የገዳሙ የመጽሐፍ መምህርና ቀዳሽ አባ ገ/ማርያም አበበ
4. በአመክሮ የሚኖሩ መናኝ ኃይለማርያ የተባሉት የገዳሙ የሥራ ኃላፊዎች እንደተገደሉና አብረው ከነበሩት አንድ
አባት ብቻ ማምለጥ መቻላቸውን የገዳሙ ኃላፊዎች ለኢኦተቤ ቴቪ
(EOTC TV) ገልጸዋል፡፡
የገዳሙ የሥራ ኃላፊዎች ቡድኑ ከዚህ ቀደም ገዳሙን በመዝረፍ ለከፋ ችግር አጋልጦት መቆየቱን አስታውሰው ገዳሜ
ጸጥታውን የሚያስከብረበት መሣሪያች በመወረሳቸው ለከፋ የጸጥታ ችግር መጋለጡን ገልጸዋል፡፡
በአሁኑ ወቅት ገዳማውያ በስጋት ላይ መሆናቸውንና የመንግሥት የጸጥታ አካላትን እገዛ እንደሚሹ አስታውቀው
መረጃውንም በየደረጃው ለሚገኙ የሀገረ ስብከቱና የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች ማሳወቃቸውን ገልጸዋል፡፡
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያና የመገናኛ ብዙኃን ሥርጭት አገልግሎት ድርጅት EOTC TV
በክሰተቱ ሕይወታቸው ላጡ ሰማዕታት አባቶች የተሰማውን ኃዘን ይገልጻል፡፡ ጉዳዩ አስመልክቶ ዝርዝር መረጃ
እየተከታተለ የሚያቀርብ መሆኑን ያስታውቃል፡፡
EOTC TV
+++++++++++++++++++++++++++++++++++++
=

ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን


የተላለፈ ወቅታዊ መልዕክት።

ጥንታዊት፣ ታሪካዊት፣ ብሔራዊትና ዓለም አቀፋዊት በሆነችው በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ሥር
ከሚገኙት ጥንታዊያን ገዳማት መካከል ዝቋላ ደብረ ከዋክብት አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ገዳም አንዱና ዋነኛው
መሆኑ ይታወቃል።

ይህ ጥንታዊና ታሪካዊ ገዳም በርካታ ቅርሶችና መናንያን የሚገኙበት ገዳም ሲሆን በተለያዩ ጊዜያት በተከሰተበት
ዘረፋና ቃጠሎ ከባድ ጉዳቶችን ያስተናገደ መሆኑም ይታወሳል።

በዛሬው ዕለት ከሀገረ ስብከቱ በደረሰን መረጃ መሰረትም፦


1. የገዳሙ መጋቢ አባተክለማርያም ዐሥራት
2. የገዳሙ ጸሐፊ አባ ኪዳነ ማርያም ጥላሁን
3. የገዳሙ የመጽሐፍ መምህርና ቀዳሽ አባ ገ/ማርያም አበበ
4. በአመክሮ የሚኖሩ መናኝ ኃይለማርያም ወልደሰንበት
የካቲት 12 ቀን "ኦነግ ሸኔ" በተባለው ታጣቂ ቡድን ከተወሰዱ በኋላ አራቱም በትላንትናው አለት የተገደሉ ሲሆን አባ
ኪዳነማርያም ገ/ሰንበት የተባሉት አባት ቆስለው በገዳሙ እንደሚገኙ ታውቋል።

በአሁኑ ሰዓትም ታጣቂዎቹ ወደ ገዳሙ ለመግባት እንቅስቃሴ የሚያደርጉበት መንገድ እንዳይኖርና መናንያኑና የገዳሙ
ቅርስ አደጋ ላይ እንዳይወድቁ የፌዴራልና የክልሉ የጸጥታ አካላት ገዳማዊያኑንና ገዳሙን የመታደግ ሥራ እንዲሠሩ
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ከአደራ ጭምር መልዕክቷን ታስተላልፋለች።

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን


መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽሕፈት ቤት
የካቲት ፲፬ቀኝ ፳፻ ፲ወ፮ ዓ.ም
አዲስአበባ -ኢትዮጵያ

ምንኩስና የተጀመረው እንዴት ነበር? ከመጽሐፍ ቅዱሳዊ መነሻዎቹ ባሻገር የምንኩስናን ታሪክ ስናጠና በ 4 ኛው ክፍለ
ዘመን እንደተጀመረ ይታወቃል:: ለሦስት መቶ ዓመታት በአሰቃቂው ዘመነ ሰማዕታት ቅድስት ቤተ ክርስቲያን መከራ
ስትቀበል ክርስቲያኖችም በየቀኑ ሲገደሉ የነበረበት ዘመን ድንገት አበቃ:: በደማቸው ለመጠመቅና በሞታቸው ክብር
ለመቀዳጀት የተዘጋጁ ምእመናንን ድንገት "በቃ ከእንግዲህ አትሞቱም" የሚል አዋጅ ታወጀባቸው::

ዕረፍት አገኘን ብለው የተደሰቱ እንደነበሩ ሁሉ ለሰማዕትነት ቆርጠው ለክብር አክሊል ተዘጋጅተው የነበሩ ብዙዎች
ግን ድንገት ሰማዕትነት ሲቆም አዘኑ:: ከሰማዕትነት ክብር ወርደው እንደማንኛውም ሰው መኖር ከበዳቸው::
ስለዚህም በሰይፍ ባይሞቱም በፈቃዳቸው ሞተው ለክርስቶስ ሕያው ሆነው ሊኖሩ ወደ ገዳማዊ ሕይወት ወደ
ምንኩስና ጎረፉ:: ይህም ክስተት ለምንኩስናና ለገዳማዊ ሕይወት ምክንያት ሆነ::

ዝቋላን በመሳሰሉ ገዳማት የሚገኙ መነኮሳት በሥጋ የሚሞቱበት ቀን ሳይደርስ በክርስቶስ ፍቅር በፈቃዳቸው የሞቱ
ሐዋርያው እንዳለው "ሥጋን ከክፉ ምኞቱና መሻቱ ጋር የሰቀሉት" ናቸው:: ሰማዕትነትም ቀድመው የተመኙት ክብር
ነበር:: በእነርሱ መገደል የሞትነው በእነርሱ ጸሎት ብርሃንነት የምንኖር ፣ ስንጨነቅ ከእግራቸው ሥር የምናለቅስ ፣
በዓለም ማዕበል ስንላተም በመስቀላቸው መልሕቅ ወደ ጸጥታ ወደብ የምንደርስ እኛው ነን::

ባለቆቡ ሰማዕት አባቴ ሆይ እርስዎን የገደሉ የገደሉት የእኔን ተስፋ ነው:: ሰማዕቱ መነኩሴ ሆይ በእርስዎ ሞት
የተቀደደው የዕንባዬ መሐረብ ነው:: አንጀታችን በኀዘን እርር የሚለው ለእናንተ ሳይሆን ለራሳችን ነው:: ከእናንተ
ጸሎት በቀር ምርኩዝ የሌለን እኛ ይለቀስልን እንጂ ለእናንተ አናለቅስም :: ቀድማችሁ የጠላችኋት ዓለም
ብትጠላችሁ አይገርምም:: በፍቅርዋ ለተሸነፍን ለእኛ ግን ዕንባ ያስፈልገናል:: እውነተኛዋ ቤተ ክርስቲያን የትኛዋ
እንደሆነች ፣ ዘመነ ሰማዕታትን የምትደግመዋ የክርስቶስ ቤተ ክርስቲያን ማን እንደሆነች በደማችሁ ያሳያችሁ
ምስክሮች ሆይ ለእኛ እንጂ ለእናንተ አናለቅስም:: የእኛን እግር ከማጠብ ፣ የእኛን ብሶት ከመስማት ፣ የእኛን
የክርስትና ስም ዘወትር በጸሎት ከመጥራት ፣ እኛን ተቀብሎ ከማስተናገድ አረፍ ብላችሁ ከመነኮሳችሁለት አምላክ
ዕቅፍ ስለገባችሁ አናዝንም:: የምናዝነው በተራራ ላይ ያለ መብራታችን ለጠፋብን ለእኛ ነው:: የእኛ ደብረ ታቦር
ዝቋላ ሥሉስ ቅዱስ በደመና ይጋርድሽ እንጂ ምን እንላለን?

ገዳምንና ገዳማውያንን መንካት የንቡን ቀፎ ማፍረስ ነው:: ቤተ ክርስቲያን ከቅዱስ ሲኖዶስ እስከ ዐቃቢት ያሉት
ሁሉ በገዳም ቀፎነት የተሠሩ የማር እንጀራዎች ናቸው:: ማሩን የሚጋግሩት ንቦች ያሉት ከቀፎው ገዳም ውስጥ
ነው:: የአቡየ ገብረ መንፈስ ቅዱስ የቆብ ልጆች በአስኬማ ላይ የሰማዕትነት አክሊል የደረባችሁ ቅዱሳን መነኮሳት
ጸልዩልን በዙፋኑ ፊት ቆማችሁ "ቅዱስና እውነተኛ ጌታ ሆይ፥ እስከ መቼ ድረስ አትፈርድም ደማችንንስ በምድር
በሚኖሩት ላይ እስከ መቼ አትበቀልም?" ብላችሁ ስለ እኛ አማልዱ:: (ራእ. 6:10)

ወበጽባህ አሌሊ ገይሰ ኀበ ቤተ ክርስቲያን


❤በጥዋት ተነስተህ ወደቤተ ክርስቲያን ሂድ

ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን የምታገኘው በቤተ መቅደስ ውስጥ ነውና በጧት ከመኝታህ ተነስተህ ወደቤተ ክርስቲያን
ገስግስ

✍የ 300 ዓመት እድሜ ባለጸገው ስምዖን ጌታችንን አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመቅደሱ ውስጥ አግኝቶ
አቅፎታል

✍የ 106 ዓመት እድሜ ባለጸጋዋ ሀና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመቅደሱ አግኝተዋለች

✍እመቤታችንና ሽማግሌው ዮሴፍ ጌታችን ሲፈልጉት መቅደሱ ውስጥ ከሊቃውንቱ ጋር አግኝተውታል

✍መካኒቱ ሀና በመቅደሱ ፊት ቁማ ጸልያ ጸሎቷ ተሰምቶ ሰሙኤልን ያህል ልጅ ወልዳለች

✍ካህኑ ዘካርያስ ያረጀችው ሚስቱ ኤልሳቤጥ ጸንሳ እንደምትዎልድ መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል የነገረው በቤተ መቅደሱ
ውስጥ ነው

✍እመቤታችን ድንግል ማርያም ሰማያዊ ምግብ እና ሰማያዊ መጠጥ መልአኩ ያመጣላት በቤተ መቅደሱ ስትኖር ነው
✍ወላዲተ አምላክ ድንግል ማርያም ሐርና ወርቁን እያስማመች በቤተ መቅደሱ ስትፈትል አምላኳን እንድትዎልድ
መልአኩ አብስሯታል

✍እግሩ ሽባ ሁኖበት በቤተ መቅደሱ በር ወድቆ ሲለምን የነበረው ሰው ጴጥሮስና ዮሐንስ ለጸሎት ወደመቅደሱ
ሲሔዱ አግኝተው ፈውሰውታል

*ፈውስ ለማግኘት
*አዲስ ብስራት ለመስማት
*ሰማያዊ ምግብ ለማግኘት
*የጸለይከውን ጸሎት ለመሰማት
*ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ለማግኘት
በጧት ተነስተህ ወደቤተ ክርስቲያን ሂድ
ወደ እግዚአብሔር ቤት እንሂድ ባሉኝ ጊዜ ደስ አለኝ እንዳለው ደዊት ወደቤተ ክርስቲያን በመሄድህ ደስ ይበልህ
መጋቤ ሐዲስ ሄኖክ ፈንቴ

+ በራስህ ክፉ ነገር አታድርግ +

ይድረስ ለተከፋኸው ወንድሜ


መኖር ለደከመህ ፣ ሕይወት ለታከተህ ፣ የሚሰማህ ላጣኸው ፣ የሚረዳህ ሰው ላላገኘኸው መከረኛው ወዳጄ!

ከሞት ውጪ ሌላ መፍትሔ አልታይ ካለህ የአንተ ቢጤ መከረኞቹ ጳውሎስና ሲላስ እስር ቤት ውስጥ ሆነው እንዲህ
ይሉሃል::

"በራስህ ክፉ ነገር አታድርግ" ሐዋ. 16:28

አውቃለሁ ዙሪያው ገደል ሆኖብሃል:: ምነው ባልተፈጠርሁ እስክትል ድረስ ተጨንቀሃል::


ግን ይህ ስሜት በአንተ አልተጀመረም:: ሰው ሆኖ ተፈጥሮ ኑሮ ያልመረረው ማን አለ? መሞት ያልተመኘስ ማን አለ?

ሞት ያማረህ አንተን ብቻ መሰለህ?

" ስለ ምን ከማኅፀን አወጣኸኝ? ዓይን ሳያየኝ ምነው በሞትሁ" ያለውን ጻድቅ ኢዮብ አልሰማህም? (ኢዮ. 10:18)

"ከአባቶቼ አልበልጥምና ነፍሴን ውሰድ" ብሎ እንዲሞት የለመነውን ኤልያስን አላየኸውም? 1 ነገሥ. 19:4

ዮናስንስ "አሁንም፥ አቤቱ፥ ከሕይወት ሞት ይሻለኛልና እባክህ፥ ነፍሴን ከእኔ ውሰድ፡ አለው" ሲል አልሰማኸውም?
(ዮናስ 4:3)

ወንድሜ እመነኝ ምክንያቱ ምንም ይሁን ምን መኖር ያላስጠላው ሰው በታሪክ ፈልገህ አታገኝም::

ሞት ሞት የሸተተው ልቡ የተሰበረ ብዙ ነው:: አንተ ላይ ብቻ የደረሰ ልዩ ፈተና የለም:: "ለሰው ሁሉ ከሚሆነው


በቀር ምንም ፈተና አልደረሰባችሁም፤ ነገር ግን ከሚቻላችሁ መጠን ይልቅ ትፈተኑ ዘንድ የማይፈቅድ እግዚአብሔር
የታመነ ነው፥ ትታገሡም ዘንድ እንድትችሉ ከፈተናው ጋር መውጫውን ደግሞ ያደርግላችኋል" ይላል መጽሐፍ::
1 ኛ ቆሮ. 10:13
ምናልባት የልብህን መሰበር የኀዘንህን ጥልቀት አይቶ ምቹ ጊዜ አገኘሁ ብሎ ራስህን እንድትጎዳ ሰይጣን ሊገፋፋህ
ይችላል:: እንዴት እንዲህ ዓይነት ሃሳብ በልቤ ሊመጣ ቻለ ብለህ አትረበሽ:: ሰይጣን ይህንን ክፉ ሃሳብ ላንተ ብቻ
ሳይሆን ለክርስቶስም አቅርቦለታል::

"የእግዚአብሔር ልጅስ ከሆንህ፥ ወደ ታች ራስህን ወርውር" ብሎ ክርስቶስን እንኳን [ማንነቱን ሳያውቅ] ራሱን
እንዲወረውር ሊገፋፋው የሞከረ ደፋር ነው:: የእግዚአብሔር ልጅ የሆነ ሰው ግን ራሱን አይጎዳም:: "ጌታ አምላክህን
አትፈታተነው" "ሒድ አንተ ሰይጣን" ብለህ ሰይጣንን ገሠፀው::

ሰይጣን ክርስቶስን "ከሕንፃ ጫፍ በመወርወር የእግዚአብሔር ልጅ መሆንህን አሳይ" ሲለው ክርስቶስ ሰይጣንን
ሒድልኝ ብሎ በመገሠጹ በክብር ወደ ሰማይ ዐርጎ በእግዚአብሔር ቀኝ ተቀመጠ::
ወንድሜ ሆይ አንተም ሰይጣንን አትስማው ሃሳቡ ራስህን ጎድተህ ከፈጣሪህ እንድትጣላ ሊያደርግህ ነው :: ሰይጣንን
ከገሠጽከው በእግዚአብሔር ቀኝ ከበጎቹ ጋር ትቆማለህ::

አሁን ያለህበት ችግር ያልፋል:: የሚሰማህ ክፉ ስሜት መቼም የማይለወጥ አይምሰልህ:: ኀዘኑም ፣ ብቸኝነቱም ፣
ተስፋ ቢስነቱም ያልፋል:: ጨለማው ይነጋል:: የተዘጋው በር ይከፈታል:: ችግሩ ሲፈታ አንተ ከሌለህ ግን ትርጉም
የለውም::

ስለዚህ ለሚፈታ ችግር የማይቀለበስ ውሳኔ አትወስን:: ራስን ማጥፋት ከጊዜያዊ ችግር ለመሸሽ ሲሉ ዘላቂ ችግር
ውስጥ መግባት ነው:: ጊዜያዊ ሕመምን ለማስታገስ የዘላለም ሕመምን ለምን ትመርጣለህ? "የሞተ ተገላገለ" ሲሉ
ሰምተህ እንዳትታለል ሞት ዕረፍት የሚሆነው ራሱ እግዚአብሔር ሲጠራህ ብቻ ነው::
"እናንተ ደካሞች ሸክማችሁ የከበደ ወደ እኔ ኑ እኔም አሳርፋችኋለሁ " ያለው ጌታ ሳይጠራህ ራስን ማጥፋት የዘላለም
ስቃይ ያመጣል::

ወዳጄ "በራስህ አንዳች ክፉ አታድርግ"

የሕይወትህን ዋጋ ታውቅ ይሆን? አንተ እኮ የእግዚአብሔር ልጅ ለአንተ ሲል የሞተልህ ነህ:: ሊፈውስህ የቆሰለ ፣
ሊያከብርህ የተዋረደ ፣ ሊያረካህ የተጠማ ፣ ሊያለብስህ የተራቆተ ለአንተ እኮ ነው::
ክርስቶስ ስለ አንተ ሞቶአል:: አንተን ግን የጠየቀህ እንድትሞትለት ሳይሆን እንድትኖርለት ነው::
ለሞተልህ አምላክ እንዴት መኖር ያቅትሃል?

ወዳጄ ሆይ ሰውነትህ በአምላክ ደም የተገዛ ክቡር ሰውነት ነው:: አካልህ "አንተ" እንጂ "ያንተ" አይደለም:: "በዋጋ
ተገዝታችኋልና ለራሳችሁ አይደላችሁም፤ ስለዚህ በሥጋችሁ እግዚአብሔርን አክብሩ" ይላል

ስለዚህ በከበረ የእግዚአብሔር ልጅ ደም የተገዛ ሰውነትህን ለሰይጣን በርካሽ አትሽጠው:: አትግደል የሚለው ሕግ
ራስህንም ይጨምራል:: ቤተ መቅደስ የሆነ ሰውነትህን ለማፍረስ አታስብ::
"ማንም የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስ ቢያፈርስ እግዚአብሔር እርሱን ያፈርሰዋል፤ የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ
ቅዱስ ነውና፥ ያውም እናንተ ናችሁ" 1 ኛ ቆሮ. 3:17

ሰዎች አስቀይመውህ ይሆን?

"አሳያቸዋለሁ ፤ ስሞት የእኔን ነገር ይገባቸዋል" ብለህ በሰዎች ተቀይመህ ራስህን አትጉዳ:: እመነኝ ብትሞት ሰዎች
ከሳምንት በላይ አያስታውሱህም:: ለሕይወትህ ዋጋ ያልሠጡ ሰዎች ለሞትህ ዋጋ አይሠጡም :: ፈጥነውም
ይረሱሃል:: ለሚረሱህ ሰዎች ብለህ የማይረሳህን አምላክ አታሳዝን:: ሰው ስለ አንተ ግድ የለውም እግዚአብሔር ግን
የራስህን ጸጉር ሳይቀር በቁጥር ያውቀዋል :: እንኳንስ ራስህን ልትጎዳ አንዲት ጸጉር እንኳን ከአንተ እንድትወድቅ
አይፈልግም::

እግዚአብሔርን በኃጢአት ብታሳዝነው እንኳን ኖረህ ንስሓ እንድትገባ እንጂ እንድትሞት አይፈልግም:: አባትህ ነውና
ከእርሱ ጋር ባትሆንም እንድትኖር ይፈልጋል:: በምሳሌ ልንገርህ :-

ሁለት ሴቶች አንድን ሕፃን "የኔ ልጄ ነው" ብለው እየተከራከሩ ጠቢቡ ሰሎሞን ፊት ቀረቡ:: ጠቢቡ ሰሎሞን ሰይፍ
አመጣና "ልጁን ቆርጬ ለሁለት ላካፍላችሁ" አላቸው:: አንደኛዋ ሴት "እሺ እንካፈል" ስትል እውነተኛዋ እናት ግን
"ልጄ ከሚሞት እርስዋ ትውሰደው" አለች:: እናት መሆንዋም በዚህ ታወቀ::

ወዳጄ ያንተም ኑሮህ ከእግዚአብሔር ጋር ላይሆን ይችላል:: ዓለም የራስዋ አድርጋህም ይሆናል:: በሱስ ውስጥ
ትዘፍቀህ ፣ እንደ ሶምሶን በደሊላ እቅፍ ፣ እንደ ዴማስ በተሰሎንቄ ውበት ተማርከህ ይሆናል :: እግዚአብሔር ግን
አባትህ ነውና ሞትህን አይፈልግም::

"ልጄ ከሚሞት እርስዋ ትውሰደው" እንዳለችው እናት ፈጣሪህ ከነኃጢአትህም ቢሆን እንድትሞት አይፈልግም::
ከእርሱ ጋር ባትኖርም መኖርህን ይፈልጋል:: "የሟቹን ሞት አልፈቅድምና፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር፤ ስለዚህ
ተመለሱና በሕይወት ኑሩ" ሕዝ. 18:32

የይሁዳ ኃጢአቱ ጌታውን መሸጡ አልነበረም:: ራሱን መግደሉ ነው:: እግዚአብሔር የሚያዝነው ከበደልህ በላይ
በእርሱ ተስፋ ቆርጠህ ራስህን ስትጎዳ ነው::

ወዳጄ የአንተን መኖር የሚፈልጉ ብዙ ናቸው:: ፈጣሪ ወደዚህች ዓለም ያለ ምክንያት አላመጣህም:: በአንተ
አለመኖርም የሚጎድል ነገር አለ:: አንተን የሚመስል ሌላ ሰው አልፈጠረምና ለዚህ ዓለም አንተን የሚተካ የለም ::
በክብር ወደዚህ ዓለም ያመጣህ አምላክ በክብር ወደራሱ እስኪወስድህ ድረስ "በራስህ ላይ ክፉ ነገር አታድርግ"

"የወኅኒውም ጠባቂ ከእንቅልፉ ነቅቶ የወኅኒው ደጆች ተከፍተው ባየ ጊዜ፥ እስረኞቹ ያመለጡ መስሎት ራሱን
ይገድል ዘንድ አስቦ ሰይፉን መዘዘ።
ጳውሎስ ግን በታላቅ ድምፅ፦ ሁላችን ከዚህ አለንና በራስህ ክፉ ነገር አታድርግ፡ ብሎ ጮኸ" ሐዋ. 16:27-28

ይህ ሰው እስረኛ ያመለጠ መስሎት ራሱን ሊያጠፋ ሲል ጳውሎስ "ሁላችን ከዚህ አለንና በራስህ ክፉ ነገር አታድርግ "
አለው::

ወዳጄ አንተስ ተስፋ የቆረጥኸው ምን ያመለጠ መስሎህ ነው?

የትምህርት ዕድል ያመለጠህ መስሎህ ነው? ገና ሺህ የትምህርት ዕድሎች አሉህ:: ዕድሜህ ያመለጠህ መስሎህ ነው?
ነገ የሚጠብቁህ ብሩሕ ዘመናት እኮ ቁጭ ብለው አሉ? የሚረዳኝ ሰው የሚያስብልኝ ሰው አጥቼያለሁ? ብለህ
ከሆነም ካልሰሙህ ጥቂቶች በላይ ልንሰማህ የምንሻ "ሁላችን ከዚህ አለንና በራስህ ክፉ ነገር አታድርግ"

መከራ ጸናብኝ ኑሮ ጨለመብኝ የሀገሪቱ ሁኔታ ተስፋ አሳጣኝ ብለህ ይሆን? እኛስ አብረንህ አይደልንም? አብረን
ከገባንበት ችግር አብረን ብንወጣ አይሻልም? ከአንተ በባሰ ሁኔታ የታሰርንና የተገረፍን ጳውሎሶችና ሲላሶች "ሁላችን
በዚህ አለንና በራስህ ክፉ አታድርግ" ስንልህ ስማን::

ይልቅ አንተም እንደ ወኅኒው ጠባቂ "እድን ዘንድ ምን ላድርግ ብለህ?"ነፍስህን የምታድንበትን መንገድ ወደ መቅደሱ
ቀርበህ ጠይቅ::
ወዳጄ ይህንን ጽሑፍ ያነበብኸውም በሕይወት ስላለህ ነው:: የአንተን ዓይን የሚጠብቁ ብዙ ጽሑፎች ፣ የአንተን ጆሮ
የሚፈልጉ ብዙ ድምፆች ፣ የአንተን መሐረብ የሚፈልጉ ብዙ ዕንባዎች ፣ የአንተን ሳቅ የሚፈልጉ ብዙ ቀልዶች ... ገና
ብዙ ብዙ አሉ::

ስለዚህ ሰይጣንን አሳፍረው:: እንዲህ በለው :-

"ጠላቴ ሆይ፥ ብወድቅ እነሣለሁና፥ በጨለማም ብቀመጥ እግዚአብሔር ብርሃን ይሆንልኛልና በእኔ ላይ ደስ አይበልሽ "
ሚክ. 7:8

ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ


ጥቅምት 2016 ዓ.ም.
ሜልበርን አውስትራሊያ

ለተጨነቀች ነፍስ ዕረፍት የሆነው የእግዚአብሔር ቃል ለሁሉ ይዳረስ ዘንድ :: እኔም ለእናንተ ከሰበክሁ በኁዋላ
የተጣልሁ እንዳልሆን አጥብቃችሁ ስለ እኔ ጸልዩልኝ!
በኮሜንት መስጫው ሥር "ለሚሰሙት ጸጋን ይሰጥ ዘንድ፥ እንደሚያስፈልግ ለማነጽ የሚጠቅም ማናቸውም በጎ
ቃል እንጂ ክፉ ቃል ከአፋችሁ ከቶ አይውጣ" (ኤፌ 4:29)

እኔ በለኛና በኋጢያት የረከስኩ ሰው ነኝ በንስሐ አባቴ ፊት ስቀመጥ ጎስቋላነቴ ይሰማኛል ስለ ኋጢያቴ ብዛት ሳስብ
ወራዳነቴ ይታወቀኛል ለጸሎት በምቆምበት ሰዓት ዓይኖቼን ወደ አረያም አቀና ዘንድ የማይገባኝ እንደ ሆንኩ
እቆጥራለሁ ታዲያ ለምንድነው ሰዎች የሚያወድሱኝ ምናልባት በሰዎች ፊት እውነተኛው ማንነቴን ሸሽጌ የምቆም
ፈሪሳዊ ወይም ሁለት ባሕርይ ያለኝ ሰው ስለሆንኩ ይሆን ወይስ ተዋናይ እሆን ምናልባት እሆን ይሆናል
የነፍስ አርነት ገጽ 3

እግዚአብሔር ሆይ አፈርና ትንቢያ ትንቢያ ሆኜ ሳለ ጻዲቅ አድርገው ከሚቆጥሩኝ ሰዎች አድነኝ አባ እንጦንስ
https://t.me/tsidq

ምክረ አበው
ከሰይጣን በቀር ምንም ጠላት አይኑርህ፡፡ የሰዎችን ስህተት አትመራመር፤ የባልንጀራህን ኃጢአት አትግለጥ፡፡
የባልጀራህን ውድቀት ደጋግመህ አታውራ፡፡ በራስህ ኃጢአት ላይ ፍረድ እንጂ በሌሎች ላይ አትፍረድ ገዢያቸው
አይደለህምና፡፡ ኃጢአትን በፈጸመ ሰው ላይ ወቀሳ አታብዛ አንተም ትበድላለህና፡፡ ነገር ግን ከኃጢአቱ ይመለስ ዘንድ
ረዳትና መካሪ ሁነው፡፡ ከወደቀበትም የስህተት ሥራ እንዲወጣ አበርታው፡፡ ተስፋውን በእግዚአብሔር ላይ ቢያደርግ
ኃጢአቱ ልክ በእሳት ፊት እንደወደቀ ገለባ ፈጥኖ እንደሚወገድለት ንገረው፡፡ቅዱስ፣ ጥንቁቅ፣ ግልጽና ብልህ ሁን፡፡
እርጋታን የተላበሰ ሰብእና ይኑርህ፡፡ደስተኛ ሁን፤ ሰላምታህ በፈገግታ የታጀበ ንጹህ ይሁን፡፡ንግግርህ የታረመ አጭርና
በጨው እንደተቀመመ ጣፋጭ ይሁን፡፡ ቃላቶችህ የተመጠኑ እና ጤናሞች ሁሉም የሚረዳቸው ይሁኑ፡፡ የጓደኛህን
ምስጢር አትግለጥ፤ለሚወዱህ ሁሉ የታመንክ ሁን፡፡ ወደ ጭቅጭቅ እና
ንትርክ ከመግባት ራስህን ጠብቅ፡፡ የሚሰሙህ ሁሉ እንዳይጠሉህ ወደ ጠብ አትግባ፡፡
ከቅዱስ ኤፍሬም
ለወዳጅዎ ሼር ያርጉላቸው

ዓለም ሲሳሳት ከመገሠጽ ይልቅ አብሮ ማጨብጨብ ተለማምደናል

#Ethiopia | «እኛ የሃይማኖት አባቶች አልጫ የሆነውን የዘመናችንን ትውልድ በትጋት አስተምረን በቈራጥነት
ገሥጸንና መክረን ወደ እግዚአብሔር ካልመለስነው ከቁጣው አንድንም፡፡ ቅዱስ መጽሐፍ እንዳስተማረን አስተምረነው
የማይመለስ ከሆነ ደሙ በራሱ ላይ ይሆናል፤ እኛ ባለማስተማራችን የሚጎዳ ትውልድ ካለ ግን እኛ የደሙ ተጠያቂዎች
መሆናችንን በማያሻማ ሁኔታ ተገልጾአልና ነው፤ የኛ ኃላፊነት እስከዚህ ድረስ ከባድ መሆኑን ባንዘነጋውም እንደዓለሙ
በልዩ ልዩ ደካማ አስተሳሰቦችና ተግባራት እየተሰናከልን መሆናችን የአደባባይ ምሥጢር ከሆነ ውሉ አድሮአል፡፡

ዓለም ሲሳሳት ከመገሠጽ ይልቅ አብሮ ማጨብጨብ ተለማምደናል፤ ባናጨበጭብም ዝምታን መርጠናል፤ ነገር ግን
ኃላፊነቱን የተረከብነው ጥፋት ሲፈጸም ዝም ብሎ ለማየት አልነበረም፤ ከዓለሙ ጋር አብሮ ለማጨብጨብ ወይም
አድማቂ ለመሆንም አልነበረም፡፡ ከቅዱስ ወንጌሉ መሠረተ ሐሳብ ፍንክች ሳንል የእውነት፣ የፍትሕ፣ የሰላም፣ የፍቅር፣
የዕርቅ፣ የይቅርታ፣ የአንድነትና የስምምነት ጠበቃ መሆናችንን ማሳየት ነበረብን፡፡

ሰውን ሁሉ በእኩልነት በመቀበልና የሁሉም እኩል አባቶች መሆናችንን በተግባር ማስመስከር ይገባን ነበር፤ የተዛባውን
በማረም ትውልዱን ለማዳን ያደረግነው ጥረት የሚያረካ እንዳልሆነ ታዛቢው ሁሉ አይቶብናል፡፡ያም በመሆኑ ሁኔታው
እኛንም ቤተ ክርስቲያንንም ለፈተና ለመዳረግ እየዳዳ ነው፤ በመሆኑም በዚህ ክሥተት የእግዚብሔር ቁጣ የለበትም
ለማለት አንደፍርም፤ በዓለሙ ብልሹ አሰራርም ተሳታፊ ከመሆን አላመለጥንም፡፡ክሱ፣ አቤቱታው፣ ሰውን ከሥራ
እያፈናቀሉ ፍትሕ ማዛባቱ፣ በደምብ ተለማምደነዋል፤ ደመወዛችሁ ይብቃችሁ የሚለውን አምላካዊ መርሕ ዘንግተን
የዚህ ዓለም ንዋይ እያሸነፈን ነው፤ ግን ዓለምን ልናሸንፍ እንጂ በዓለም ልንሸነፍ አልተጠራንም።»

የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወእጨጌ
ዘመንበረ ተክለሃይማኖት 11 ኛ ዓመት በዓለ ሢመተ ላይ ቅዱስነታቸው ያስተላለፉት ቃለ ምእዳንና ቡራኬ የተወሰደ።

ተወዳጅ ሆይ! ክርስቶስ ኢየሱስ እንዲህ ይልሃል፦

✟ አንተ ግን ለድኾች ምጽዋትን ትሰጣለህ፤ እኔም እጄን ዘርግቼ ካንተ እቀበላለሁ፡፡


✟ የታረዙትን በምታለብሳቸው ጊዜ እኔን ታለብሰኛለህ፡፡
✟ የታሰሩትን በምታረጋጋቸው ጊዜ በመካከላቸው ኾኜ በዚያ ታገኘኛለህ፡፡
✟ በሽተኛውንም በምትጎበኘው ጊዜ ከእርሱ ጋር በአልጋው ላይ ኾኜ ዳግመኛ ታገኘኛለህ፡፡
✟ በቦታው ኹሉ የራቅሁ አይደለሁም፡፡ ትእዛዜን በምትፈጽምበት ዘንድ እኔ ከአንተ ጋር እኖራለሁና ችግረኞችን
የምረዳቸው እኔ ነኝና፤ ለድኾች የምታደርገው ኹሉ ለእኔ ማድረግህ ነው፡፡ እኔም በእርሱ ፈንታ በጎ ዋጋ
እከፍልሃለሁና፡፡
✟ በቤትህ ውስጥ እንግዳ በአሳደርክ ጊዜ እነሆ ከእንግዳው ጋር በማደሪያህ አስገባኸኝ፡፡
✟ እንደዚህ ለሚያደርግ ቁጣዬ ከእርሱ ይርቃል፤ ወደ ሕይወት ወደብም አደርሰዋለሁ፡፡ ከክፉ ነገር ኹሉ
እጠብቀዋለሁ፡፡ እባርከዋለሁ፡፡ ዘሩንም አበዛለሁ፡፡ ዋጋውንም በሰማይ ባለው በአባቴ ዘንድ ከፍ ከፍ አደርገዋለሁ፡፡
ዘለዓለማዊ ዕረፍትንም እሰጠዋለሁ፡፡"

(ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ በገብረ እግዚአብሔር ኪደ)

"በጎ ነገር አግኝተህ እንደ ሆነ እግዚአብሔርን አመስግን፤ ያም በጎ ነገር ከአንተ ጋር ጸንቶ ይኖራል፡፡ በጎ ያልሆነ ነገር
ደርሶብህ እንደሆነም እግዚአብሔርን አመስግን፤ ያም በጎ ያልሆነ ነገር ወደ በጎ ነገር ይቀየራል፡፡"

ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ

+ ወደ ኖኅ መርከብ ለመጨረሻ ጊዜ የገባችው እንስሳ +

የኖኅ መርከብ ጉዳይ በጣም አስገራሚ ከሚሆኑብኝ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች አንዱ ነው:: በዓለማችን አሁን ያሉ
እንስሳት ሁሉ "ከነ ባለቤትዎ" እንዲገኙልን እንደሚባልበት ሰርግ ጥንድ ጥንድ ሆነው የገቡባት ትልቅ መርከብ ታሪክ :
ዳግም ለሰው ልጆች ወላጆች ለመሆን የተመረጡ አራት ወንዶችና አራት ሴቶች ብቻ የተሳፈሩባት ትልቅ መርከብ
ሁኔታ ትኩር ብሎ ላየው አስገራሚ እውነቶችን ያዘለ ነው::

ከሁሉም በላይ ግን መርከቢቱ የቤተ ክርስቲያን ምሳሌ መሆንዋ ብዙ ነገር እንድናስብ ያግዘናል:: ቅዱስ ዮሐንስ
አፈወርቅ "ወደ ኖኅ መርከብ ተኩላ ገብቶ ሲወጣም ተኩላ ሆኖ ይወጣል:: ወደ ቤተክርስቲያን ግን ተኩላ ሆነው
ገብተው በግ ሆነው የወጡ ብዙዎች ናቸው" ብሎአል::

እውነትም ቤተ ክርስቲያን ወደ እርስዋ የገቡትን መለወጥ የምትችል መርከብ ናት :: ወደ ቤተ ክርስቲያን እንደ ጅብ


ሆዳም ሆነው ገብተው ጾመኞች ሆነው የወጡ አሉ :: እንደ የሌሊት ወፍ በቀን መኖር አቅቶአቸው ሌሊቱን የልባቸው
ዓይን ታውሮ በኃጢአት ጨለማ ሲደናበሩ የኖሩ ሰዎች ወደ መርከቢቱ ገብተው እንደ ንስር አርቀው አጥርተው ቀኑን
የሚያዩ ሆነዋል:: ቤተ ክርስቲያን ወደ እርስዋ የገቡትን የምትለውጥ መርከብ ናት:: ውኃ ወደ እርስዋ ሲገባ ጠበል
ይሆናል:: አፈር ወደ እርስዋ ሲገባ እምነት (እመት) ይሆናል:: ዘይት ወደ እርስዋ ሲገባ ቅዱስ ቅባት ይሆናል:: ኅብስትና
ወይን ወደ እርስዋ ሲገባ ወደ ቅዱስ ቁርባን ይለወጣል::

ወደ ቤተ ክርስቲያን ገብቶ ያልተለወጠ ሰው ግን ሲገባም ጅብ ሲወጣም ጅብ ሆኖአል:: ኖኅ ከመርከብ መልእክት ልኮት


የቀረው የቁራ ነገርስ? ከቤተ ክርስቲያን ወጥተው ስንቶች በዚያው ቀርተዋል? ለዓለም ጨው እንዲሆኑ ተልከው
በዚያው ሟሙተው የቀሩ ስንት አሉ:: ርግብ ግን ማረፊያ ስታጣ ተመልሳ ነበር:: ከመርከቢቱ የራቅን ሁላችን "ልባችን
በእግዚአብሔር እስካላረፈ ድረስ ዕረፍት የለውም" እንዳለ ሊቁ ወደ መርከቢቱ ፈጥነን መመለስ አለብን::

ሰሞኑን ደግሞ አንድ ጥያቄ በአእምሮዬ ተመላለሰብኝ:: "ወደ ኖኅ መርከብ ለመጨረሻ ጊዜ የገባው እንስሳ ማን ሊሆን
ይችላል?" የሚል:: ይህን ጥያቄ በግልም በጉባኤ ላይም ሰዎችን ጠይቄ ነበር:: መቼም ለዚህ ጥቅስ አያስፈልገውም::
ኖኅ ቆሞ እንስሳቱ እስኪገቡ ድረስ እንደጠበቀና ማንንም እንስሳ ጥሎ እንዳልገባ የታወቀ ነው::
በዚህ ምክንያት እንስሳቱ ወደ መርከቢቱ የሚገቡት እንደደረሱበት ቅደም ተከተል ነው:: ክንፍ ያላቸው በርረው
ቀድመው ይገባሉ:: እንደ ጥንቸል እንደ ካንጋሮ እንደ ሚዳቁዋ ያሉትም እየዘለሉ ፈጥነው ይገባሉ::

ወደ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ነፍሳቸውን ለማዳን ፈጥነው በርረው የገቡ እንደ ሚዳቋ ዘልለው የደረሱ ብርቱዎች
አሉ:: እንደ ፒኮክ ያሉ ባለ ውብ ክንፎች : እንደ ቀጭኔ ያሉ ባለ ረዥም አንገቶች እንደ ጃርት ያሉ ሌላው ላይ
የሚሰኩት እሾኽ የለበሱ እንስሳት ወደ መርከብዋ ገብተዋል :: በቤተክርስቲያን እንደ ፒኮክ አምሮ መታየት መዘባነን
የሚወዱ ለታይታ የሚገዙ ብዙዎች ገብተዋል:: እንደ ቀጭኔ አንገታቸውን ከፍ አድርገው ሰውን ቁልቁል
የሚመለከቱና "አንገታቸውን እንደሚያገዝፉ የዕብራውያን ሴቶች" ዓይነት ሕይወት ያላቸውም ገብተዋል:: እንደ
ጃርት በክፉ ንግግር የሰው ልብ ላይ የሚሰኩት ጥላቻ የተላበሱ ሰዎችም ገብተዋል:: የኖኅ መርከብ ያልያዘችው እንስሳ
እንደሌለ ቤተ ክርስቲያንም ያልተሸከመችው ዓይነት ሰው የለም::

ወደ ጥያቄው ስመለስ በእኔ ግምት ወደ መርከቡ በጣም ዘግይታ የገባችው ኤሊ ነበረች :: በላይዋ ድንጋይ የተጫናት
እጅግ ቀርፋፋዋ ኤሊን የማይቀድም እንስሳ መቼም አይኖርም:: ምንም ብትዘገይም ኖኅ እስከመጨረሻው ጠብቆ
አስገብቶ ለዘር አትርፎአታል:: የኤሊ ዘሮችም "ኖኅ ዘርን ባያስቀርልን ኖሮ እንደ ዳይኖሰር በጠፋን ነበር" ብለው ኖኅን
ማመስገናቸው አይቀርም:: እግዚአብሔር ምንም ብትዘገይ ኤሊ ሳትገባ መርከቡን አልዘጋውም::

የኤሊ በመርከቡ መትረፍ በቤተ ክርስቲያን ልንተርፍ ተስፋ ለምናደርግ ለእኛ ትልቅ መጽናኛችን ነው::

ወዳጄ ወደ ቤተ ክርስቲያን ለመምጣት እንደ ወፍ ትበርራለህ? እንደ ሚዳቋ ትዘልላለህ? ወይንስ እንደ ኤሊ
ትጎተታለህ? እግሮችህ ለመንፈሳዊ ነገር ሲሆን አቅም እያጡ አልተቸገርህም?
ልብህ ቢፈልግም እንደ ኤሊዋ የተጫነህ የኃጢአት ድንጋይ አላንቀሳቅስ ብሎህ አልዘገየህም?
እንዲህ ከሆነ አትጨነቅ መርከብዋ ቤተ ክርስቲያን አንተን ሳትይዝ ጥላህ ወዴትም አትሔድም :: ጉዞህን እስካላቆምህ
ድረስ ትጠብቅሃለች:: እየተጎተትህም እየተሳብህም ቢሆን አንተ ብቻ ወደ ደጁ ገስግስ::
አንተ ብቻ መንገድ ጀምር እንጂ ፈጣሪ በሩን የሚዘጋው አንተ እስክትገባ ጠብቆ ነው::

ከቅዱስ ኤፍሬም ጋር እንዲህ ብለህ ለምነው :-


"ብበድልህም እንኳን አሁንም በርህን እያንኳኳሁ ነው:: እየተጎተትሁም ቢሆን አሁንም የምጉዋዘው ወደ አንተ
ለመምጣት ነው"

ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ


ሚያዝያ 5 2013 ዓ ም

ለተጨነቀች ነፍስ ዕረፍት የሆነው የእግዚአብሔር ቃል ለሁሉ ይዳረስ ዘንድ :: እኔም ለእናንተ ከሰበክሁ በኁዋላ
የተጣልሁ እንዳልሆን ስለ እኔ ጸልዩ! በኮሜንት መስጫው ሥር "ለሚሰሙት ጸጋን ይሰጥ ዘንድ፥ እንደሚያስፈልግ
ለማነጽ የሚጠቅም ማናቸውም በጎ ቃል እንጂ ክፉ ቃል ከአፋችሁ ከቶ አይውጣ" (ኤፌ 4:29)

ሌሎች እንዲያነቡት Share ያድርጉ

+ የሐሰት መገለጦች ፣ ራእዮችና ሕልሞች +

በተሳሳተ አስተሳሰብህ እንድትቀጥል ለማድረግ አንዳንድ ጊዜ ዲያቢሎስ ነገሮችን ከመሆናቸው በፊት


እንድታውቃቸው ሊያደርግህ ይችላል፡፡ ወይም የሌሎች ሰዎችን ሐሳብ እንድታውቅ ሊያደርግህ ይችላል፡፡

ዲያቢሎስ እንዴት ይህን ማድረግ ይችላል? በጣም ቀላል ነው! ለምሳሌ ሀገር ቤት ያሉ አያትህ በጠና እንደታመሙ
ያውቃል ፤ ስለዚህ ይህንን ሐሳብ በአንተ ኅሊና እንዲታሰብ ያደርጋል፡፡አንተም ደንገግጠህ ስልክ ትደውላለህ ፤ በዚህ
ጊዜ አያትህ በጣም እንደታመሙ ይነገርሃል፡፡ ይህንን ስታምን ሌሎች ነገሮችንም እየነገረህ እግዚአብሔር የገለጠልኝ
ነው ብለህ እንድታስብ ያሳምንሃል፡፡

በትእቢትና ራስን እንደ ጻድቅ በማየት ኃጢአትም


እንድትሞላ ያደርግሃል፡፡ ዮሐንስ ዘሰዋስው ደግሞ እንዲህ ሲል ገልጾታል፡፡ ዲያቢሎስ ሐሳቦችን በአንድ ሰው ኅሊና ላይ
ከተከለ በኋላ ይህንኑ ሐሳብ ለሌላ ሰው በመንገር ራሱን የሰውን አእምሮ የሚያነብ እንደሆነ እንዲሰማው ያደርገዋል፡፡
ጠንቋዮች የሚያውቁትን ነገር ከየት የሚያገኙት ይመስላኋል? ከዲያቢሎስ እኮ ነው! በእርግጥም አብዛኞቹ ጠንቋዮች
በትክክል በአጋንንት የተያዙ ናቸው፡፡

ሦስት መነኮሳት አንድ ነገር ተገልጦላቸው የተገለጠው ነገር ከእግዚአብሔር ነው ወይንስ ከዲያቢሎስ እያሉ ይከራከሩ
ነበር፡፡ በመጨረሻም ወደ ቅዱስ እንጦንስ ሔደው ሊጠይቁት ወሰኑ፡፡ ወደ ቅዱስ እንጦንስ ሲሔዱ በመንገድ ላይ
ይዘውት ሲሔዱ የነበረ አህያ ሞተባቸው፡፡

መንገዳቸውን ቀጥለው ወደ ቅዱስ እንጦንስ ሲደርሱ


‹‹አህያችሁ መሞቱ በጣም ያሳዝናል!›› አላቸው፡፡
እነርሱም ‹‹ስለ አህያው እንዴት ልታውቅ ቻልህ?›› ሲሉ ጠየቁት፡፡ እርሱም ‹‹ሰይጣን ነገረኝ!›› አላቸው፡፡
እነርሱም ‹‹ሳንጠይቅህ ጥያቄያችንን መለስህልን!›› አሉት፡፡

አንዳንድ ሰዎች መላክትንና ቅዱሳንን በራእይ ያያሉ፡፡ ነገር ግን እንዲህ ያሉትን ራእዮች ከመቀበል በፊት ከፍተኛ
ጥንቃቄ ያስፈልጋል ፤ ምክንያቱም ዲያቢሎስ መንፈሳዊ ሕይወታችንን ለማፈራረስ ሲል ሊያስመስል ይችላል፡፡ የበረሃ
አባቶች ታሪክ ራእይና ሕልምን ከእግዚአብሔር መሆኑንና ከሰይጣን መሆኑን ሳይለዩ ስለተቀበሉ ሰዎች በሚናገሩ
አስፈሪ ታሪኮች የተሞላ ነው፡፡

ከእነዚህ ታሪኮች አንዱ የሄሮን ታሪክ ነው፡፡ ይህ መነኩሴ ለሃምሳ ዓመታት በብሕትውና የኖረ ሲሆን ለረዥም ጊዜ
ይገለጥለት በነበረ የሐሰት መልአክ እየወደቀ የመጣ ነው፡፡ መልአክ ስለተገለጠለት ወደ ቤተ ክርስቲያን መሔድ አቆመ ፣
ለአበምኔቱ እንዲነግራቸው ሌሎች መነኮሳት የመከሩትንም ምክር አልተቀበለም፡፡
በመጨረሻም ‹‹መልአኩ›› ለዚህ አባት በሕይወቱ እያለ እንደ ኤልያስ ወደ ሰማይ እንደሚወሰድ ነገረው፡፡ ይህ
ምስኪን መነኩሴም ወንድሞቹ መነኮሳትን ሊሰናበት ሔደ፡፡ ነገሩ ከዲያቢሎስ ቢሉትም አልሰማቸውም፡፡ መልአክ ነኝ
ባዩም ይህንን አባት ወደ ተራራ ይዞት ወጣ፡፡ እንዲዘልልም ነገረው ፤ ይህ አባትም በተባለው አምኖ ሲዘልል ወድቆ
ተከስክሶ ሞተ፡፡ አበምኔቱ ይህ መነኩሴ ራሱን እንዳጠፋ በመቁጠር ጸሎተ ፍትሐት እንዲደረግለት እንኳን
አልፈቀደም፡፡

ሌላ መልአክ ነኝ ባይ ደግሞ ለሌላ መነኩሴ ለሦስት ዓመታት ተገለጠለት፡፡ በዚህ መልአክ ብርሃን ይህ አባት የሚኖርባት
በአቱ ታበራ ነበርና ሻማዎችን ማብራት አያስፈልገውም ነበር፡፡ ከሦስት ዓመታት በኋላ ይህ በራእይ በ‹‹ገነት››
አይሁዳውያን በአብርሃም እቅፍ ሆነው ክርስቲያኖች ደግሞ በሲኦል ሲሰቃዩ አስመስሎ አሳየው፡፡ ይህ መነኩሴ
ክርስትናን ትቶ አይሁዳዊ ሆነ፡፡

በሰይጣን የማይታለሉ ጥበበኛ የሆኑ መነኮሳትም ነበሩ፡፡

ለአንዱ መነኩሴ ‹‹ገብርኤል›› ነኝ ባይ ጋኔን ከእግዚአብሔር ተልኬ መጣሁ አለው፡፡ መነኩሴውም ‹‹የመጣኸው ወደ
ትክክለኛው በአት አይደለም ፤ እኔ ገና ራእይ ለማየት የማይገባኝ ኃጢአተኛ ነኝ! ከዚህ ቀጥሎ ያለው መነኩሴ ግን
ጻድቅ ሰው ነው›› ሲል መለሰለት፡፡ ገብርኤል ነኝ ባዩም እንደ ጢስ ተነነ!

ለሌላ አባት ደግሞ ዲያቢሎስ ‹ክርስቶስ ነኝ› ብሎ ተገለጠለትና የአምልኮት ስግደት እንዲያቀርብለት ነገረው፡፡ ይህ
አባት ግን ‹‹እኔ ክርስቶስን በሰማይ እንጂ በምድር ላይ ለማየት አልፈልግም !›› አለው፡፡ ይህም ክርስቶስ ነኝ ባይ እንደ
ጢስ ተንኖ ጠፋ፡፡

እነዚህ ነገሮች ከዘመናት በፊት በመነኮሳት ላይ የተፈጸሙ ናቸው፡፡ ነገር ግን ዲያቢሎስ ዛሬም ይህንኑ ስልት
እየተጠቀመ እና እየተሳካለት ነው፡፡

ከዓመታት በፊት ነው ፤ አንድ አገልጋይ ወደ ቤተ ክርስቲያን መምጣት እንዳቆመና ለረዥም ጊዜም ሥጋ ወደሙ
መቀበል እንደተወ ተረዳሁ፡፡ መጠየቅ እንደሚገባኝ በማመን ወደ እርሱ ሔጄ ምክንያቱን ልጠይቀው ሞከርሁ፡፡ ቀለል
አድርጎ መለሰልኝ ፡- ‹‹እሑድ እሑድ አቡነ ቄርሎስ ይገለጡልኛል ፤ ሥጋ ወደሙም ያቀብሉኛል !›› ከሌላ ቦታ
የመጣ አንድ አገልጋይ ደግሞ ወደ እኔ መጥቶ ኅሊናውን የሚረብሸው ነገር እንዳለ ነገረኝ፡፡ እኔም የንስሐ አባቱ
ባለመሆኔ የንስሐ አባቱን እንዲያናግርና እንዲናዘዝ መከርሁት፡፡ በማግሥቱ ጠዋት መጥቶ ጠራኝና በሕልሙ ‹‹አቡነ
ቄርሎስ››

መጥተው ተናዘዝ እንዳሉትና ጸሎተ ንስሐ እንዳደረጉለት ነገረኝ፡፡ ከዚያም ይህ ይበቃው እንደሆነ ጠየቀኝ ፤ እኔ ግን
አሁንም ወደ ንስሐ አባቱ ሔዶ እንዲናዘዝና ስላየው ሕልምም እንዲነግራቸው ነገርሁት፡፡

ትክክለኛ ገንዘብ አለ ፤ የሐሰት ገንዘብ ደግሞ አለ፡፡ እንዲሁም እውነተኛ መገለጥ አለ ፣ የሐሰትም መገለጥ አለ፡፡
ሕልሞችን ፣ ራእዮችና መገለጦችን ለማስተናገድ ትክክለኛው መንገድ የንስሐ አባትን ማማከር ነው፡፡ መንፈሳዊ ሰው
ሁልጊዜም ራሱን ሕልም ራእይ ለማየት የማይገባው አድርጎ ማየት ይገባዋል፡፡ በተለይ ሕልሞች በዲያቢሎስ ሙሉ
ቁጥጥር ሥር ናቸው ማለት ይቀላል፡፡ እግዚአብሔር ለአንዳንድ ሰዎች ጋር በሕልም ተናግሯል፡፡ ሆኖም እነዚህ በጣት
የሚቆጠሩ ሲሆኑ እነርሱም ነቢያትና ቅዱሳን ነበሩ እንጂ እንደ እኛ ኃጢአተኞች አልነበሩም፡፡ ለሕልሞችም ይህን
ያህል ክብደት መስጠት የለብንም፡፡

አንድ ጊዜ ቅዱስ እንጦንስ እንዲህ ብሏል፡-


‹‹በሕልሞች የሚያምን የዲያቢሎስ መጫወቻ ነው››

ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ


ሚያዝያ 26 2012 ዓ ም
(ተግባራዊ ክርስትና ከተሰኘው መጽሐፍ የተወሰደ
አቡነ አትናስዮስ እስክንድር እንደጻፉት
ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ እንደተረጎመው
የቴሌግራም ቻናሌ መቀላቀል ለምትሹ
https://t.me/tsid

+++ ልብስህን ማን ወሰደው? +++


❖❖❖❖
በአንድ ወቅት አባ ሰራብዮን ወደ እስክንድርያ በሄደ ጊዜ በገበያም ስፍራ አንድ ከልብስ የተራቆተ ነዳይ አገኘ፡፡ ለራሱም
"ይህ ደሃ ሰው ታርዞ መነኩሴ የተባልኩ እኔ እንዴት ለብሼ እታያለሁ ? በእውነት ይህ 'ታርዤ አልብሳችሁኛልና' ብሎ
የተናገረው ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ አይደለምን? በዚህ ብርድ እየተሰቃየ እንዴት አልፌው እሄዳለኹ?" ብሎ ፈጥኖ
ልብሱን በማውለቅ ይለብሰው ዘንድ ለዚያ ደሃ ሰጠው፡፡ ከዚያም በእጁ ያለውን መጽሐፍ ቅዱስ እንደ ያዘ እርቃኑን
በጎዳናው ዳር ተቀመጠ፡፡ እርሱን የሚያውቀው አንድ የከተማው ባለጠጋ ሰው አባ ሰራብዮን ባለበት ሥፍራ ሲያልፍ
ተመልክቶት ወደ እርሱ ቀረበና ‹አባ ሰራብዮን ሆይ ልብስህን ማን ወሰደው?› ሲል ጠየቀው፡፡ ቅዱሱም በእጁ ወደ
ያዘው መጽሐፍ ቅዱስ እየጠቆመ ‹ልብሴን የወሰደው ይህ ነው!› አለው፡፡ ያም ባለጠጋ አዲስ ልብስ ገዝቶ አለበሰው።

ከዚህም በኋላ አባ ሰራብዮን ከእርሱ እንደ ተለየ በመንገድ ሲሄድ ዕዳውን መክፈል ባለመቻሉ እያንገላቱ ወደ ወኅኒ ቤት
የሚወስዱትን አንድ ምስኪን ሰው ተመለከተ፡፡ እርሱም የያዘውን መጽሐፍ ቅዱስ ፈጥኖ በመሸጥ የዚያን ሰው ዕዳ
ከፍሎ ነጻ አደረገው፡፡ ይህንንም አድርጎ ጉዞውን ሲጀምር እንደ ገና ሌላ የታረዘ ነዳይ ሲለምን ተመለከተ። አባ
ሰራብዮንም እንደ ቀድሞው የለበሰውን ልብስ አውልቆ ለነዳዩ በመስጠት እርሱ እርቃኑን ወደ በአቱ ተመለሰ፡፡ ደቀ
መዛሙርቱም መምህራቸውን እርቃኑን ባዩት ጊዜ ደንግጠው ‹መምህር! ልብስህ ወዴት አለ?› ብለው ጠየቁት፡፡
እርሱም ‹መጸወትኩት› አላቸው፡፡ ደቀ መዛሙርቱም መልሰው ‹እኛን የምታጽናናበት መጽሐፍ ቅዱስህስ
አባታችን?› ሲሉ ደግመው ጠየቁት፡፡ አባ ሰራብዮንም ‹በእጄ የነበረው መጽሐፍ ቅዱስ ሁል ጊዜ ‹ሂድ ያለህን ሽጠህ
ለድሆች ስጥ› ይለኛል፤ ስለዚህ ያለኝ እርሱ ነበር እርሱንም ሸጥኩት› አላቸው፡፡

ኢትዮጵያዊው ቄርሎስ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ እንደሚናገረው ምጽዋት የፊት መብራት ናት፡፡ አንድ ሰው በጨለማ
ሲጓዝ ከኋላው መብራት ቢያበሩለትም እንኳ ከፊቱ የሚቀድመው የገዛ የአካሉ ጥላ እንቅፋት እየሆነበት ይጥለዋል፡፡
ወደ ፊት ያለውን መንገድ አጥርቶ እያየ ያለ ስጋት ለመሄድ እንዲችል የግድ የፊት መብራት ያስፈልገዋል፡፡ ጾም
፣ጸሎት እና ሌሎች መንፈሳዊ ትሩፋት እንደ ኋላ መብራት ናቸው፡፡ የፊት መብራት የተሰኘች ምጽዋት
ካልታከለችባቸው እነዚህ ብቻቸውን ዋጋን አያሰጡንም፡፡ የምጽዋትን ታላቅነት ልንረዳ ይገባል፡፡ ዓለም ሁሉ
ከወደቀበት የሕግ እርግማን የዳነው ቸር እረኛ በሆነው በመድኃኔ ዓለም በአካሉ ምጽዋትነት (በሥጋው በደሙ
መሰጠት) ነውና!!!

ለሌሎች ሼር በማድረግ እንድታደርሱ በፍቅር እጠይቃለሁ!


የቴሌግራም ቻናሌ መቀላቀል ለምትሹ
https://t.me/tsidq

+++ ዝምተኛው ፓትርያርክ +++

ከእለታት በአንዱ ቀን በግብጽ መንበረ ፓትርያርክ ሕንፃ እንግዳ መቀበያ ክፍል ውስጥ አረጋዊ ጳጳስ ቆመው ሳሉ አንድ
ሰው ወደ ውስጥ ሲገባ ‹‹ብዙ ልጆች ያሉህ፣ ሸክምህ የከበደብህ ልጄ ሆይ ና!›› ሲሉ ጠሩት፡፡ ሰውየውም ግራ
እየተጋባ ‹‹ማን? እኔን ነው አባቴ? እኔ እኮ አንድ ልጅ ብቻ ነው ያለኝ›› አላቸው፡፡ ጳጳሱም ‹‹ልጄ ሆይ፣
አልተረዳህም እንጂ ሸክምህ ከባድ ልጆችህም ብዙ ናቸው›› አሉት፡፡ እርሱ ግን ‹‹እመኑኝ አንድ ልጅ ብቻ ነው
ያለኝ›› እያለ ተከራከራቸው፡፡ በዚህም ጊዜ አረጋዊው ‹‹ልጄ፣ እንግዲያውስ ነገ ትረዳዋለህ›› ብለው ጥለውት ሄዱ፡፡
ይህ በሆነ በማግስቱ ሰባት ልጆች የነበሩት የዚህ ሰው ወንድም ድንገት በአደጋ ምክንያት ሞተ፡፡ ታዲያ የወንድሙን
ሰባት ልጆች የማሳደግ ኃላፊነት በእርሱ ላይ ወደቀ፡፡ ትናንትና አንዲት ሴት ልጅ ብቻ የነበረው ዛሬ ግን የ 8 ልጆች
አባት ሆነ። ይህም ሰው ነገሩን ቀድመው ወደ ነገሩት እኚህ አባት ሄዶ የሆነውን ሲያብራራላቸው ‹‹ልጄ፣ ሸክምህ
የከበደና ብዙ ልጆች ያለህ እንደ ሆንህ ስነግርህ እኮ አላመንከኝም?!›› አሉት፡፡ ለመሆኑ እኚህ አባት ማን ይሆኑ?

እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር በ 1950 ዎቹ መጀመሪያ የግብጽ ቤተ ክርስቲያን በሙስና የተጥለቀለቀችበትና ትልቅ
አስተዳደራዊ ችግር ውስጥ የገባችበት አሳዛኝ ጊዜ ነበር፡፡ በኋላም የሕዝቡ ቁጣ ገንፍሎ ፓትርያርኩን አግቶ እስከ
መውሰድና ‹‹ሥልጣኔን በፈቃዴ ለቅቄያለሁ›› የሚል ደብዳቤ ላይ ተገድደው እንዲፈርሙ እስከ ማድረግ ደርሶ ነበር፡፡
ይሁን እንጂ በዚህ ግርግር መሐል የጸጥታ አስከባሪ ፖሊሶች ደርሰው ፓትርያርኩን ከዚህ እገታ በማዳን ወደ
መንበራቸው እንዲመለሱ አድርገዋል፡፡ ይህ ከሆነም ከአንድ ዓመት በኋላ የቤተ ክርስቲያኗ ቅዱስ ሲኖዶስ ባደረገው
ጉባዔ ፓትርያርኩ ዮሳብ (ዳግማይ ዮሴፍ) ከኃላፊነታቸው እንዲነሡና በግብጽ ካሉ ገዳማት በአንዱ ገዳም እንዲኖሩ
በአንድ ድምጽ ወሰነ፡፡ የግብጽ ቤተ ክርስቲያንም ከሦስት ዓመት በላይ ያለ ፓትርያርክ ቆየች፡፡ ይህም የቅብጥ ቤተ
ክርስቲያንን መንፈስ ያወከና በጉልበቷ ያንበረከከ አሳዛኝና የማይረሳ ጥቁር ትውስታ ሆነ፡፡

እንደ ጎልያድ ክንዱን አፈርጥሞ ይገዳደራት የነበረን የሙስና እና የብልሹነትን መንፈስ አንገቱን ቆርጠው የሚጥሉ
እንደ ዳዊት ያሉ አባት ለግብጽ ቤተ ክርስቲያን ተገኙላት፡፡ እኚህም የከተማው መናኝ ፓትርያርኩ አቡነ ቄርሎስ
ናቸው፡፡ አቡነ ቄርሎስ በሙስና እና በብልሹ አስተዳደር ምክንያት የምታነባ እና በልጆቿ ተወግታ እየደማች ያለች ቤተ
ክርስቲያንን ቢረከቡም፣ በአሥራ ሁለት ዓመት (1959-71) ውስጥ ግን ይህ ሁሉ ተቀይሮ የቅብጧ ቤተ ክርስቲያን
እንደ አዲስ ያንጸባረቀችበትና ያበራችበት ጊዜ ሆኗል፡፡ ይህ ወቅት የቅዱስ ማርቆስ አጽም ወደ ግብጽ የመጣበት፣
የቅብጥ ቤተ ክርስቲያን ወደ ዓለም መስፋፋት የጀመረችበት ወርቃማ ጊዜ ነው።

የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን የራሷ ፓትርያርክ እንዲኖራት ይደረግ በነበረው የንጉሡና የእኛ ሊቃውንት እንቅስቃሴም
ላይ እርሳቸውም ጉዳዩ የራሳቸው እስኪመስል ድረስ ትልቅ ጥረትና ትግል አድርገዋል፡፡ በዚህም ድርጊታቸው የቅብጧ
ቤተ ክርስቲያን ኢትዮጵያን በተመለከተ አቅሌስያዊ አትሕቶን (Ecclesial kenosis) እንድትላበስ አድርገዋታል፡፡

አቡነ ቄርሎስ ለፓትርያርክነት ሲታጩ የታቃወሙ ነበሩ፡፡ ከእነዚህ ተቃዋሚዎች አንዱ በኋላ የቅዱሱ ቅርብ ወዳጅ
የሆነው ናዝሚ ቡትሮስ የተባለው ጠበቃ ነበር፡፡ ይህም ጠበቃ ምንም የዚያን ጊዜውን አባ ሚናስን በአካል
ባያውቃቸውም፣ ስለ እርሳቸው ሲወራ በሰማው አሉባልታ ግን የእርሳቸውን ለፓትርያርክነት እጩ መሆን በኃይል
ተቃውሞ ጋዜጣ ላይ ጽፎባቸው ነበር፡፡ አባ ሚናስም ‹‹አቡነ ቄርሎስ›› ተብለው ከተሾሙ በኋላ ‹‹እንኳን ደስ
አልዎት›› ለማለት ወደ እስክንድርያ መጣ፡፡ ፓትርያርኩም ደስ ብሏቸው ተቀበሉት፡፡ እርሱም ፊታቸው ላይ ያለውን
የደስታ ስሜት ሲመለከት ‹‹እርሳቸውን ተቃውሞ ጋዜጣ ላይ የጻፈው ሰው እኔ መሆኔን ባያውቁ ነው›› ብሎ አሰበ፡፡
ቁጭ ብለው ግን ሲጨዋወቱ ‹አንዳንዶች ግን ስለ እኔ ይህንንም ያንንም ሲሉ ነበር…› ብለው እርሱ የጻፈባቸውን
ክስ የሚመለከት ነገር ነገሩት፡፡ በዚህ ጊዜ ያ ጠበቃ እያፈረ ‹‹ቅዱስነትዎ፣ እባክዎ ይቅር ይበሉኝ፡፡ እርሶን በሚገባ
ባለማወቄ ነው፡፡›› አላቸው፡፡ አቡነ ቄርሎስም ፈገግ እያሉ ‹‹አይዞህ፣ ለዓለሙ ሙት የነበረውን ባሕታዊው አባ
ሚናስን እንጂ እኔን አላጠቃህም፡፡ አሁን እኔ ቄርሎስ የሁሉ አባት ነኝ›› አሉት፡፡ ይህም ጠበቃ እውነተኛ ፍቅራቸውንና
ይቅር ባይ ልባቸውን አይቶ የልብ ወዳጃቸው ሆኖ ቀረ፡፡

በ St. Vladmir Seminary press የታተመው የ‹‹A Silent Patriarch›› የተሰኘው መጽሐፍ ጸሐፊ ዶ/ር ዳንኤል
ፋኑስ እንደሚናገረው የአቡነ ቄርሎስን የግል ሕይወት በተመለከተ የሚታወቁት በጣም ጥቂት ነገሮች ናቸው። የቅርብ
አገልጋያቸው የነበረ ሰው እንኳን ስለኖሩት(የግል) ሕይወት ብዙ አያውቅም፡፡ በእርግጥም ዝምታ እንደ ጸጋ
የሆነላቸው፣ የጸጥታን ሕይወት የመሩ፣ መላ የአገልግሎት ዘመናቸውን በቅዳሴና በጸሎት ያሳለፉ አባትን የተሰወረ
ሕይወት እንዴት በቀላሉ መርምረን ማወቅ እንችላለን? ቅዱስነታቸው በኃዘናቸውም ቢሆን በሰዎች ከመከበብ ይልቅ
መሸሸጊያና መጽናኛ ያደርጉት የነበረው ብቸኛው ቦታ ከመሠዊያው ታቦት ስር ሄዶ መውደቅ ነበር፡፡

አቡነ ቄርሎስ የግብጽን ቤተ ክርስቲያን አሥራ ሁለት ዓመት በቅድስና እና በጸሎት መርተው ክፋውን ዘመን ያሻገሩ
ጻድቅ አባት ናቸው። ችግሮች ሁሉ የድርሻን ከመወጣት ጋር በጸሎት ይፈታሉ ብለው የሚያምኑ፣ "አባ ይህ ችግር
አጋጠመን?" ሲሏቸው "እንጸልይበታለን" የሚለው መልስ ከአፋቸው የማይጠፋ በጸሎት ኃይል የሚተማመኑ ቅዱስ
ነበሩ። የግብጽ ቤተ ክርስቲያን አቡነ ቄርሎስ ካረፉ ከ 42 ዓመታት በኋላ በ 2013 ዓ.እ. ባደረገችው የቅዱስ ሲኖዶስ
ጉባኤ ቅድስናቸውን በግልጽ ለልጆቿ አሳውቃለች፡፡

ቅዱስነታቸው በሕይወት እያሉም ሆነ ካረፉ በኋላ በእርሳቸው ምልጃና ጸሎት የተፈጸሙ ተአምራትን የያዙ ወደ
አሥራ ስምንት የሚሆኑ ተከታታይ ቅጽ ያሏቸው መጻሕፍትም ታትመዋል፡፡ አቡነ ቄርሎስ በግብጽ በጣም የሚወደዱ
አባት ናቸው፡፡ በመላዋ ግብጽ ከሚኖሩ የክርስቲያን ቤቶች ውስጥ የእርሳቸው ፎቶዎች ያልተሰቀሉበት ቤት ማግኘት
በጨለማ መርፌ የመፈለግ ያህል ከባድ ነው፡፡

እስኪ እኛም ለበረከት እንዲሆነን ከዕረፍታቸው በፊትና በኋላ ከአደረጓቸው ተአምራት ሦስቱን አንሥተን
እንሰነባበት።

+++ "ለምን አልደወልሽም?" +++

የሴቶች ገዳም እመምኔት የነበረች አንዲት መነኩሲት አቡነ ቄርሎስን በስልክ ማናገር ስለፈለገች ወደ በቢሯቸው ሄዳ
በግል የሚጠቀሙበትን የስልክ ቁጥር እንዲሰጧት ጠየቀች። በጊዜው እርሳቸው በሕመም ላይ ስለ ነበሩ የቢሮው
ሠራተኞቹ ሲሻላቸው በአካል ታገኛቸዋለሽ ብለው ከለከሏት። ቅዱስነታቸው ግን በዚያው ቀን ሌሊት ለመነኩሲቷ
በሕልሟ ተገልጠው አጽናንተው የስልክ ቁጥራቸውን ነገሯት። እርሷ ግን ነገሩን ችላ ብላ ሳትደውል ቀረች። ይህ ከሆነ
ከጥቂት ጊዜ በኋላ እመምኔቷ ከአቡነ ቄርሎስ ጋር በአካል ስትገናኝ "የግል ቁጥሬን ሰጥቼሽ አልነበር? ለምን
አልደወልሽም?" ሲሉ ጠየቋት። እርሷም በነገሩ ስለተደናገጠች አፏ ተሳሰረ። የምትመልሰውም አጥታ ዝም አለች።

+++ "ቁርሷን በልታለች" +++

ቅዱስነታቸው ቅዳሴ ቀድሰው በሚያቆርቡበት ጊዜ አንዲት እናት ሴት ልጇን እንዲያቆርብላት ዲያቆኑ ሳሊብን
ጠየቀችው። እርሱም ሕፃኗን ታቅፎ ወደ አቡነ ቄርሎስ ሲያመጣት "ይህችን ልጅ መልሳት። ቁርሷን የባቄላ ቅቤ በልታ
ነው የመጣችው" አሉት። ዲያቆኑም ልጅቷን ወደ እናቷ መልሶ "ቁርሷን በልታለች?" ብሎ ቢጠይቃት፣ "አዎ፤ ትንሽ
ዳቦ በባቄላ ቅቤ በልታ ነው የመጣነው" አለችው። ዲያቆኑም በልቶ መቁረብ እንደማይቻል ለእናትየው ካስረዳ በኋላ፣
በአቡነ ቄርሎስ ይህን ማወቅ ግን እየተገረመ ወደ ቅዳሴው ተመለሰ።

(ከዕረፍታቸው በኋላ)

+++ "ማንም አይናደድም" +++


በእስክንድርያ የምትኖር አንዲት ሴት ልጅ የነበረቻት እመቤት፣ ለልጇ ወንድም የሚሆን ልጅ እንዲሰጧት ወደ አቡነ
ቄርሎስ ጸለየች፡፡ ጸሎቷን ሰምተው ወንድ ልጅ ከሰጧትም ስሙን ‹ቄርሎስ› ብላ እንደምትጠራው ተሳለች፡፡ ያቺም
ሴት ልመናዋ ተሰምቶ ጸነሰች፡፡ ባለቤቷም ‹‹የሚወለደው ወንድ ልጅ ከሆነ ለአባቴ መታሰቢያ እንዲሆን በእርሱ ስም
ዛኪ ብዬ መጥራት እፈልጋለሁ›› አላት፡፡ እርሷም ወንድ ከሆነ ስሙን ‹ቄርሎስ› ልትለው ስእለት እንደ ገባች
ብትነግረውም ባለቤቷ ግን በሞተው አባቴ ስም ካልተጠራ አይሆንም ብሎ ተቃወማት፡፡ እመቤቲቱም ነገሩን
ለእግዚአብሔር እንዲያስተካክለው ተወችው፡፡ የመውለጃዋ ሰዓት በደረሰ ጊዜም መንታ ወንድ ልጆችን ተገላገለች፡፡
ለልጆቿም ስም ስታወጣ አንዱን እንደ ስእለቷ ቄርሎስ አለችው። ለሌላኛውን ደግሞ እንደ ባለቤቷ ፈቃድ ዛኪ ብለው
ጠሩት፡፡ አቡነ ቄርሎስም በሆስፒታሉ ውስጥ ሳለች ወደ እርሷ መጥተው ‹‹አንቺ ሴት አሁን ደስ አለሽ? በዚህ መንገድ
ከሆነ ማንም አይናደድም›› አሏት፡፡

ዲያቆን አቤል ካሳሁን


አዲስ አበባ
የቴሌግራም ቻናሌ መቀላቀል ለምትሹ
https://t.me/tsidq

የዐቢይ ጾም የመጀመሪያ ሳምንት

ዘወረደ

በዚህ ሳምንት የቃል ርደት፣ የወልድ ልደት፣ የአዳም ድኅነት ቢነገርም እርሱ ኢየሱስ ክርስቶስ ግን ከሰማይ የወረደ
ሰማያዊ፣ በክብር ያረገ በኩረ ትንሣኤ መሆኑ አይዘነጋም፡። ለዚህም ወንጌላዊው ቅዱስ ዮሐንስ “እውነት እውነት
እልሃለሁ፥ የምናውቀውን እንናገራለን፤ ያየነውንም እንመሰክራለን፥ ነገር ግን ምስክርነታችንንም አትቀበሉትም።
በምድር ያለውን ስንነግራችሁ ካላመናችሁኝ፥ በሰማይ ያለውን ብነግራችሁ እንዴት ታምኑኛላችሁ? ከሰማይ
ከወረደው የሰው ልጅ በቀር ወደ ሰማይ የወጣ የለም፥ እርሱም በሰማይ የሚኖረው ነው። ሙሴ በምድረ በዳ እባቡን
እንደ ሰቀለው የሰው ልጅ እንዲሁ ይሰቀል ዘንድ አለው፡፡ያመነበት ሁሉ ለዘለዓለም ሕያው ሆኖ እንዲኖር እንጂ
እንዳይጠፋ፣ በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘለዓለም ሕይወትን እንዲያገኝ እንጂ እንዳይጠፋ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን
ቤዛ አድርጎ እስኪሰጥ ድረስ ዓለሙን እንዲሁ ወዶታልና” እንዳለ እርሱ ምድራዊ ያይደለ ሰማያዊ ነው።
(ዮሐ.፫፥፲፩-፲፮) “ተጠምቀ ሰማያዊ በእደ መሬታዊ” ስለ ፍቅሩ በፈጠረው የተጠመቀ ሰማያዊ ነው።

ጾመ ድጓው የሚጀምረውም እንዲህ በማለት ነው፤ “ዘወረደ እምላዕሉ፣ አይሁድ ሰቀሉ…. እግዚአ ኩሉ ዘየሐዩ
በቃሉ፤ ….በቃሉ የሚያድነውን ከላይ የወረደውን የሁሉን ጌታ አይሁድ ሰቀሉት…”

ዘወረደ የዐቢይ ጾም የመጀመሪያ ሳምንት ነው። ስያሜውም የቅዱስ ያሬድ ነው። ትርጉሙም “ከሰማያት የወረደ”
ማለት ነው። ቅድመ ዓለም ከአባቱ ከአብ የተወለደ ፣ድኅረ ዓለም ከድንግል ማርያም የተወለደ ነው። ስም አጠራሩ
ያለና የነበረ፣ እግዚአብሔር፣ በፈቃዱ ዓለምን ለማዳን የመምጣቱን ምሥጢር የምንረዳበት ሳምንት ነው። ይህ
የመጀመሪያው ሳምንት ‹ጾመ ሕርቃል› እየተባለም ይጠራል፡፡ ሕርቃል (ኤራቅሊዮስ) በ፮፻፲፬ ዓ.ም የነበረ
የቤዛንታይን ንጉሥ ነው፡፡ለክርስቲያኖች ባደረገው ርዳታ ምክንያት አንድ ሳምንት ጾመውለት ነበር፡፡ ዛሬም ድረስ ጾመ
ሕርቃል እየተባለ ይጠራል፡፡ ሙሉ ታሪኩ በፍትሐ ነገሥት ትርጓሜ አንቀጽ ፲፭ ላይ ይገኛል፡፡

በዚህ ሳምንት ቤተ ክርስቲያን ስለ ጾም ጥቅምና እንዴት መጾም እንዳለብን ታስተምረናለች፡፡ቅዱስ ያሬድ በጾመ
ድጓው “አከለክሙ መዋዕል ዘኃለፈ ዘተቀነይክሙ ለግዕዘ ሥጋክሙ፤ ለሥጋቸሁ ፈቃድ የተገዛችሁበት ያለፈው ዘመን
ይበቃችኋል፤ ከአሁን በኋላ ግን ጹሙ፣ ጸልዩ ለእግዚአብሔር ተገዙ” እያለ የጾም አዋጅ ያውጃል። ጾም ፈቃደ ሥጋን
ለፈቃደ ነፍስ፣ ፈቃደ ነፍስን ለፈቃደ እግዚአብሔር የምናስገዛበት መንፈሳዊ መሣሪያ ነው፡፡
ጾሙ በሚጀመርበት ሰንበት በሚሰበከው ምስባክ እንዲህ ብሎ ያሳስበናል፤ “ለእግዚአብሔር በፍርሃት ተገዙ፣
በረዓድም ደስ ይበላችሁ” ጾም ከምግብና ከመጠጥ እንዲሁም ከሌሎች ምቾቶችና ደስታዎች ከመከልከል ያለፈ
ጥልቅ ትርጉም ያለው ተግባር ነው። (መዝ.፪፥፲፩-፲፪) “ንጹም ጾመ ወናፍቅር ቢጸነ ከመ ያብርህ ብርሃነ ስብሐቲሁ
በላዕሌነ፤ (የእግዚአብሔር) የክብሩ ብርሃን በላያችን ላይ ያበራ ዘንድ ጾምን እንጹም፤ወንድማችንንም እንውደድ”
እንዲል። (ጾመ ድጓ)

በዘወረደ እሑድ የሚነበቡት ምንባባትም ይህንን የጾምን ጸጋ የያዙ ናቸው።

“ነገር ግን ፈጣሪያችን የምትበልጠውን ጸጋ ይሰጣል፤ ስለዚህም “እግዚአብሔር ትዕቢተኞችን ይቃወማል፤


ለትሑታን ግን ጸጋን ይሰጣል” ይላል፡፡ እንግዲህ እግዚአብሔርን እሺ በሉት፤ ሰይጣንን ግን እንቢ በሉት፤ ከእናንተም
ይሸሻል፡፡ እግዚአብሔርን ቅረቡት፤ ይቀርባችሁማል፤ እናንተ ኃጥኣን እጆቻችሁን አንጹ፤ ሁለት አሳብም ያላችሁ
እናንተ ልባችሁን አጥሩ፡፡ እዘኑና አልቅሱ፤ ሳቃችሁን ወደ ልቅሶ ÷ ደስታችሁንም ወደ ኀዘን መልሱ፡፡ በእግዚአብሔር
ፊት ራሳችሁን ዝቅ አድርጉ፤ እርሱም ከፍ ከፍ ያደርጋችኋል፡፡” (ያዕ.፬፥፮-፲)

“በውኑ እንግዲህ በስሙ እናምን ዘንድ የከንፈሮቻችን ፍሬ የሚሆን የምስጋና መሥዋዕትን በየጊዜው ለእግዚአብሔር
ልናቀርብ አይገባንምን? ነገር ግን ለድሆች መራራትን፥ ከእነርሱም ጋር መተባበርን አትርሱ፤ እንዲህ ያለው መሥዋዕት
እግዚአብሔርን ደስ ያሰኘዋልና፡፡” (ዕብ.፲፫፥፲፭-፲፮)

በጾም የተጠቀሙ ቅዱሳንን እያሰብን ለጾም እንድንተጋም ወደ እነርሱ እንድንመለከት ቤተ ክርስቲያን


ታስተምራለች፡፡“ ልባችሁ በመብል ያይደለ በጸጋ ቢጸና ይበልጣልና፤ በዚያ ይሄዱ የነበሩ እነዚያ አልተጠቀሙምና።”
(ዕብ.፲፫፥፱) ሳምንቱ በሚጀምርበት ሳምንት የሚነበበው የቅዱስ ጳውሎስ መልእክት እንዲህ ይላል፡፡ ጾመ ድጓው
አባቶቻችን ያገኙትን በረከት እንደምናገኝበት ሲገልጽ “የእግዚአብሔር የክብሩ ብርሃን በላያችን ላይ ያበራ ዘንድ
ጾምን እንጹም፤ ወንድሞቻችንም እንውደድ፤ ኤልያስ በጾም ወደ ሰማይ አርጓልና፤ዳንኤልም ከአናብስት አፍ
ድኗልና፡፡”

ጾም ፈቃደ ነፍስን በፈቃደ ሥጋ ለማሠልጠን የአጋንንት ኃይል ለመቋቋም የሚያስችል የክርስቲያኖች ጋሻ በመሆኑ
በሃይማኖት ለሚመሩ ምእመናን እጅግ አስፈላጊና ከምንም በላይ የሕይወታቸው መርሕ መሆን እንደሚገባ ቅዱስ
ጳውሎስ በመልእክቱ እንዲህ በማለት ያስተምራል፡፡ ” አሁንም ወንድሞቻችን በዚህ በሥጋችን ሳለን ፈቃደ
ሥጋችንን ልንሠራ አይገባም፤ ፈቃደ ሥጋቸውን የሚሠሩ ሰዎች በወዲያኛው ዓለም ምውታን ናቸውና፡፡ የሥጋችሁን
ፈቃድ በነፍሳችሁ ፈቃድ ድል ከነሣችሁት ለዘለዓለም ሕያዋን ትሆናላችሁ፡፡ የነፍሳቸውን ፈቃድ የሚሠሩ ሰዎች ሁሉ
የእግዚአብሔር ልጆች ናቸውና፡፡" (ሮሜ ፰፥፲፪-፲፬)

ጾም አበው ቅዱሳን ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን በጊዜ ቀምረው፣ በበታ ወስነው፣ በሁኔታ ገድበው ... ባስቀመጡልን
ወቅት ከእህልና ከውኃ በመከልከልና ሰውነትን በማድከም ብቻ ሳይሆን ለስሕተት ከሚዳርጉ ነገሮችና ቦታዎች ተቆጥቦ
በጸሎት መትጋትም እጅጉን አስፈላጊ ነው፡፡ ልበ አምላክ ቅዱስ ዳዊትም ይህንን እውነታ በተመለከተ እንዲህ ይላል፡፡
“እኔ ግን እዘንልን፤ ለምንልን ባሉኝ ጊዜ ማቅ ምንጣፍ ለብሼ አዘንኩላቸው፤ ሰውነቴን በጾም አደከምኩዋት፤
ልመናዬም እኔም ወደመጥቀም ተመለሰችልኝ፡፡” (መዝ. ፴፬/፴፭፥፲፫)

ጾም ከሥነ ምግባራት ሕግ አንዱ በመሆኑ እንኳንስ ያልተፈቀደውን የተፈቀደውም ቢሆን የማይጠቅም ከሆነ ፈጽሞ
በመተው ለእግዚአብሔር ያለንን ፍጹም ፍቅር የምናስመሰክርበት ምሥጢር ነው፡፡

ጾም ከመብልና ከመጠጥ ጋር የተያያዘም በመሆኑ መብል ጊዜያዊ ስለሆነ ማለትም በዚህ ዓለም እስካለን ብቻ
የምንገለገልበት እንጂ ዘለዓለማዊ ስላይደለ ለጊዜያዊ መብልና መጠጥ ምክንያት ከሃይማኖት ሥነ ምግባር እንዳንወጣ
ቅዱሳን አባቶቻችን ሐዋርያት ሲመክሩ “መብል በእግዚአብሔር ዘንድ ግዳጅ አይፈጽምልንም ወደ እግዚአብሔር
አያቀርበንም፤ ብንበላም አይረባንም፤ አይጠቅመንም፤ ብንተወውም አይጎዳንም” በማለት ሲመክሩን ቅዱስ
ጳውሎስም የመብልና የሆድ ጊዜያዊነት አስመልክቶ እንዲህ በማለት አስተምሯል፡፡ (፩ኛቆሮ.፰፥፰)

“ሁሉ ነገር ተፈቅዶልኛል፤ ሁሉ ግን አይጠቅመኝም፡፡ ሁሉ ተፈቅዶልኛል በእኔ ላይ ግን አንድ ነገር እንኳን


አይሠለጥንብኝም፡፡ መብል ለሆድ ነው ሆድም ለመብል ነው፡፡ እግዚአብሔር ግን ሁለቱንም ያሳልፋቸዋል”፤
(፩ኛቆሮ.፮፥፲፪-፲፫) “ለሚጠፋ ምግብ አትሥሩ፤ ይልቅስ የሰው ልጅ ለሚሰጣችሁ የዘለዓለም ሕይወት ስለሚሆን
ምግብ ሥሩ” እንደ ተባለ (ዮሐ. ፮፥፳፯) ካለን ጊዜ ለመንፈሳዊ ሕይወታችን ጊዜ በመስጠት ቢበሉት
የማያስርበውን፣ ቢጠጡት የማያስጠማውን፣ የዘለዓለም ሕይወት የምናገኝበትን ሥጋ እና ደሙን ተቀብለን
መንግሥቱን እንድንወርስ ቅዱስ ፈቃዱ ይሁንልን።

የሰማይ ወፎችን ተመልከቱ

| ጃንደረባው ሚድያ | መጋቢት 2016 ዓ.ም.|

✍🏽 ሊቀ ሊቃውንት ስምዐ ኮነ እንደጻፉት

ክፍል ፩

ለስም አጠራሩ ክብር ይግባውና ጌታችንና አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመጀመሪያው ጉባኤ
ካስተማረን ትምህርት አንዱ ይህ ነው − የሰማይ ወፎችን ተመልከቱ አለ። የሰው ልጅ በክርስትና የኑሮ ለውጥ ማድረግ
ይገባዋል። ክርስቲያን ስትሆን በሕይወትህ ውስጥ ልትሠራው የሚገባህን ብቻ ሠርተህ ልትሠራው የማትችለውን
ለእግዚአብሔር መተው እንዳለብህ የሚያስተምርህ የወፎችን አኗኗር ማየት ስትችል ነው። በእኛ ሕይወት ውስጥ
ሠራተኞች እኛ ብቻ አይደለንም፤ እግዚአብሔርም በሕይወታችን የሚሠራቸው ሥራዎች አሉት። የሰማይ ወፎች
የተጠቀሱትም ለዚህ ነው። ወፎች አይዘሩም፣ አያጭዱም፣ በጎተራም አይሰበስቡም፤ ነገር ግን የሰማዩ አምላክ
ይመግባቸዋል ማቴ. 6፥26። የተፈጠሩት እንዲበሩ እንጅ እንዲዘሩ አይደለምና። “ከምድር በላይ ከሰማይ ጠፈር
በታች ይብረሩ” ዘፍ 1፥20 ተብለዋልና። መዝራት ማጨድና መሰብሰብ የተፈጠሩለት ዓላማ ስላልሆነ
አላደረጉትም። ከታዘዙት ግን አንዳች ሳያጎድሉ በሰማይ ላይ ሲበሩ ይታያሉ።

የሰው ልጅ የሆነ እንደሆነ ለብዙ ነገሮች ራሱን እያዘጋጀ በአባቱ እና በእናቱ ቤት ያድጋል። ቀለም ያጠናል፤ የአባቱን
ሙያ ይለማመዳል፤ ለራሱ ቢሆንለት የሚመኘውን ነገር ሁሉ መላልሶ ለመያዝ ይሞክራል። የተፈጠረለት ዓላማ
እንዲሁ ነውና። “በምድር ላይ ገና የሚሠራባት ሰው አልነበረምና” ዘፍ 2፥5 የሚለው ትምህርት በምድር ላይ
ብቻውን ሠራተኛ ሆኖ የተፈጠረ ፍጥረት ሰው ስለመሆኑ የሚናገር ነው። በአምሳለ እግዚአብሔር ለመፈጠራችንም
አንዱ ማስረጃ ሠራተኝነታችን ነው። የሰማይን ወፎች ግን ከጠፈረ ሰማይ በታች እንዲበሩ እንጅ እንዲሠሩ
ስላላዘዛቸው በሕይወት መኖር ከጀመሩባት ጊዜ ጀምሮ ልምምዳቸው ለመብረር እንጅ እንደ ሰው ልጅ ቀለም
አጥንተው ሙያ ለምደው ለመኖር አይደለም። “የሰማይ ወፎችን ተመልከቱ” የሚያሰኝበት ምክንያት ከዚህ
ይጀምራል። ለተፈጠሩለት ዐላማ ራስን ማዘጋጀት የመጀመሪያው ጉዳይ ነው። የመጀመሪያው ፍላጎታቸው መብረር
መቻል ነው። “ይብረሩ” የሚል መለኮታዊ ትዕዛዝ አላቸውና።

ከሁሉም አስቀድመህ ከእግዚአብሔር ዘንድ የታዘዘልህን ነገር መርምረህ ድረስበት። እግዚአብሔር በቃል
ያልተናገራቸው ፍጥረታት እንዲህ ከታዘዙት በቃሉ የነገረህ አንተ ከዚህ በላይ ልትገዛለት ይገባልና። ጥንቱንም ሰው
በሕይወት የኖረው በእግዚአብሔር ትእዛዝ ውስጥ በኖረበት ጊዜ ብቻ ነው። ለሰማይ ወፎች ምግባቸውና በሕይወት
የመኖራቸው ምክንያት በታዘዙት መሠረት ጸንተው መኖራቸው ከሆነ እኛም በታዘዝነው መሠረት ብንኖር
እግዚአብሔር የዕለት ምግባችንን የዓመት ልብሳችንን የሚሰጠን አይደለምን? አንዳንዶቻችን የእግዚአብሔርን
ትዕዛዛት መፈጸም ለነፍሳችን ብቻ ጥቅም ሊመስለን ይችል ይሆናል፤ ነገሩ ግን እንደዚያ አይደለም። ለሁለንተናዊ
ሕይወታችን የእግዚአብሔርን ትዕዛዛት ያስፈልጉናል። ሰዶምና ገሞራ የሚጠቀሱት ስለመጽደቅና አለመጽደቃቸው
አይደለም በምድር ላይ በሕይወት ስላለመኖራቸው ነው።

እግዚአብሔር ቃሉን የሚጠብቁትን በሰማይ ላለው ተስፋ ብቻ የሚያዘጋጃቸው አይምሰላችሁ። በዚህም ዓለም ሳሉ
“አማልክት ዘበ ምድር” እስኪባሉ ድረስ በሰዎች ዘንድ ክብር እንዲኖራቸው ያደርጋቸዋል እንጅ አይተዋቸውም።
በሰማርያ በነበረው የሦስት ዓመት ተኩል ዘመነ ረሀብ ጥቂቷን አብዝቶ የተመገበው እንደ እግዚአብሔር ቃል ሲኖር
የነበረው ኤልያስ መሆኑን ልብ በሉ። የአንድ ቀኑን ምግብ ለሦስት ዓመት ተኩል እንዲበቃ አድርጎ ያበዛለት ቃሉን
የጠበቀለት እግዚአብሔር ነው 1 ነገ 17፥15።

እግዚአብሔር አድርጉ ያለንን እያደረግን ብንኖር አንዳች ነገር በማጣት አንቸገርም ነበር። ከሰማይ ወፎች
የምንማረው አንዱ ይህ ነው። የሰማይ ወፎች የራሳቸው የሆነ አገር፣ ምድር፣ ርስት፣ ጉልት የላቸውም፤ ነገር ግን
የሚመገቡትን እግዚአብሔር ይሰጣቸዋል። የዕለቱን መመገባቸውን እንጅ እንደ ገብረ ጉንዳን የዓመቱን
ባለመሰብሰባቸውም አያዝኑም የዕለቱን እንጅ የዓመቱን እንዲሰበስቡ አልታዘዙምና። የዕለት ቀለብ እንጅ የዓመት
ባለመሰብሰባቸውም ከገብረ ጉንዳን የማነስ ስሜት የለባቸውም ተፈጥሮ እንደፈቀደችላቸው እንዲሁ ይኖራሉ።
መሬት እስኪጠባቸው ሀብት ካልሰበሰቡ፤ በሰዎች እጅ ያሉ መዛግብትን ሁሉ የግላቸው አድርገው ካልዘገቡ ሲጨነቁ
ውለው የሚያድሩ ሰዎችን ኢየሱስ ክርስቶስ የሰማይ ወፎችን ተመልከቱ ብሏል በሏቸው።

እንደ ወፎቹ መብረራችንን አናቆምም እንጅ በመዝገባችን ያለውን ጥቂት ነገር አይተን አንጨነቅም። “እጅግ
ለለቀመ አልተረፈውም፤ ጥቂት ለለቀመመ አልጎደለበትም” ተብሎ ተጽፏልና ዘፀ 16፥18 የሰማይ ወፎችን
መመልከት የጭንቀት መድኃኒት ነው።

ሌላው አስደናቂ ነገር፦ ወፎች ምግባቸውን በምድር ላይ ቢያገኙም እንኳን መብረራቸውን አይተዉም። በምድር ላይ
ከሚርመሰመሱ ፍጥረታት ለይቶ የሚበሩበትን ክንፍ ከሰጣቸው በምድር ላይ የሚበሉትን የሚጠጡትን ማግኘታቸው
ከመብረር ለምን ያስቀራቸዋል። ምግባቸውን ለማግኘታውም ምክንያቱ መብረራቸው ነው ስለዚህም በምንም ሁኔታ
ውስጥ ቢሆንም መብረራቸውን አያቆሙም።

የሚበሉትን በልተው የሚጠጡትን ጠጥተው መብረራቸውን ይቀጥላሉ። እኛም በምድር ላይ ምንም እንኳን የተመቸ
ሕይወት ቢያጋጥመንም ኅሊናችንን ወደ ሰማይ ከመብረር ልንገታው አይገባንም። ወደ ሰማይ መመለሳችንን
የሚያስረሳ አጋጣሚ በየትኛውም ጊዜ ሊኖር አይገባውም። በምድር ላይ ባሉ ፍጥረታት ሁሉ ላይ ለመሠልጠናችን
ምክንያቱ በእግዚአብሔር መልክ መፈጠራችን መሆኑን መዘንጋት የለብንም። እሱን አስመስሎ ወደ ፈጠረን ወደ
ፈጣሪያችን ስለመመለሳችን እያሰብን እንኖራለን እንጅ እሱን መስለን በመፈጠራችን ምክንያት በተገዛልን ዓለም
ውስጥ ልባችንን ቀብረን አንኖርም።

የሰማይ ወፎችን ተመልከቱ!

ማስታወሻ :- ሊቀ ሊቃውንት ስምዐ ኮነ መልአክ የአራቱ ጉባኤያት መምህርና የባሕር ዳር ሀገረ ስብከት የሊቃውንት
ጉባኤ ሰብሳቢ ሲሆን የመጻሕፍት ደራሲም ናቸው:: ሊቅ ሊቃውንት የጃንደረባው ሚዲያ ዐምደኛ ሲሆኑ
ጽሑፎቻቸው ዘወትር ሰኞ የሚነበቡ ይሆናል::

እስኪ የአባቶቼን የአንደበት ፍሬ ላካፍላችሁ።

‹‹እግዚአብሔር ሆይ አፈርና ትቢያ ሆኜ ሳለ ጻድቅ አድርገው ከሚቆጥሩኝ ሰዎች አድነኝ›› ..............አባ እንጦንስ

‹‹ፍጡራንን መርምሮ ማወቅ ካልተቻልን ሁሉን የፈጠረ እርሱን መርምሮ ማወቅ እንደምን ይቻልናል››
.................................ቅዱስ አትናቴዎስ

‹‹ወርቅ በእሳት እንደሚፈተን ሁሉ የክርስቶስንም ፀጋና ክብር ሳይፈተኑ ማግኘት አይቻልም የዚህ ዓለም ፈተናና
እሳት ቶሎ ያልፋል ይጠፋል ኃጢያተኞች የሚገቡበት የገሀነም እሳት ግን ለዘላለም እንደ ነደደ ይኖራል››
.......................................ቅዱስ ሚናስ

‹‹በማንም ላይ ክፋትን አትስሩ አትፍርዱ ይህንን ከጠበቃችሁ ርስቱን ትወርሳላችሁና››


..................................ታላቁ አባ መቃርስ

‹‹ብዙ ጊዜ ብዙ እናገራለሁ በመናገሬም አዝናለሁ በዝምታዬ ግን ያዘንኩበት ጊዜ የለም››


.................................ቅዱስ አርሳንዮስ

‹‹ቤተክርስትያን መጠጊያችን ነች ቤተክርስትያን የኖኅ መርክብ ነች በውስጧ እንጠለላልን ከውጭዋ ግን ማዕበልና


ቀላያት ተከፍተዋል››
....................................ቅዱስ እንድርያስ

‹‹ልባችንን ጠፊና በስባሽ ከኾነው ከምድራዊው ምኞት አርቀን ከበደል በንስሐ ነጹሕ ካደረግነው በጸጋ መንፈስቅዱስ
የተሞላን እንሆናለን››
...................አባ አብርሃም መፍቀሬ ነዳያን

‹‹ሥጋዊ ፍላጎቶችን ማሸነፍ ለአክሊለ ሕይወት የሚያበቃ ሰማዕትነት ነው››


...................ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ ካልዕ

‹‹የቤተክርስቲያን ሕይወት በመስቀል ላይ ስለሆነ ፈተና ይበዛበታል ስለዚህ ከግል ሕይወታችሁ ይልቅ
የቤተክርስቲያናችሁን አቋም አጠንክሩ››
....................ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ ካልዕ ·
‹‹ከመኝታህ በፊት የምታደርገውን ፀሎት ትተህ እንድትተኛ መንፈስህ ሲገፋፋህ እሺ ብለህ አትቀበለው፡፡
እንዲያውም መዝሙረ ዳዊትን ጨምርና ሌሊቱን በሙሉ ስትጸልይ እደር››
............................ቅዱስ ይስሐቅ ሶርያዊ

‹‹ኃጢያታችንን እኛ እያሰብን የምንፀፀት ከሆነ እግዚአብሔር ይረሳልናል ኃጢያታችንን እኛ እረስትን የምንፅናና


ከሆነ እግዚአብሔር ያስብብናል››
......................................ቅዱስ እንጦስ
https://t.me/tsidq

#ተስፋ_መቁረጥና_ስንፍና

ተስፋ መቁረጥና ስንፍና እጅግ ክፉዎች ናቸውና ከእነዚህ እንራቅ፡፡

“ክፋታቸውስ እንደምን ያለ ነው?” ያልከኝ እንደ ኾነም እንዲህ ብዬ እመልስልሃለሁ፡- ተስፋ መቁረጥ የወደቀው
ሰው እንደ ገና እንዲነሣ አይፈቅድለትም፤ ስንፍናም የቆመው ሰው እንዲወድቅ ያደርጓል፡፡ ስንፍና ገንዘብ
ያደረግናቸውን መልካም ነገሮች ከማሳጣቱም በላይ ሊመጡ ካሉ ክፉ ነገሮች እንዳንጠበቅ ያደርገናል፡፡ ስንፍና
ከሰማያትም ቢኾን ይጥለናል፤ ቀቢጸ ተስፋም ወደ ክፋት ዐዘቅት እንድንሰጥም ያደርገናል፡፡ በእውነት በቀቢጸ ተስፋ
ካልተያዝን ከጽኑ ክፋት መመለስ ይቻለናል፡፡
እነዚህ ኹለቱ ምን ያህል ኃይል እንዳላቸው ይበልጥ ታውቅ ትረዳ ዘንድ ምሳሌ ጠቅሼ ልንገርህን ? መልካም!
ዲያብሎስ መጀመሪያ ላይ መልካም ነበር፤ ከስንፍናና ከቀቢጸ ተስፋ የተነሣ ግን እንደ ገና የማይነሣ ኾኖ ወደ ክፋት
ወደቀ፡፡ ዲያብሎስ ጥንቱ መልካም እንደ ነበረ ሲናገር መጽሐፍ ቅዱስ እንዲህ ያለውን አድምጥ፡- “ሰይጣን እንደ
መብረቅ ከሰማይ ሲወድቅ አየሁ” (ሉቃ.10፡18)፡፡ መብረቅ የሚለው አገላለጽ ዲያብሎስ ከመውደቁ በፊት ምን
ያህል ብሩህ ሕይወት እንደ ነበረውና በምን ያህል ቅጽበት እንደ ወደቀ የሚያመለክት ነው፡፡ ቅዱስ ጳውሎስ ደግሞ
ተሳዳቢ፣ አሳዳጅና ነውርን የማያውቅ ሰው ነበር (1 ኛ ጢሞ.1፡13)፡፡ ነገር ግን ቀናተኛ ስለ ነበርና ተስፋ ስላልቈረጠ
ተነሥቶ መላእክትን የሚተካከል ኾነ፡፡ ይሁዳ ሐዋርያ ነበር፤ ነገር ግን በስንፍና ምክንያት ጌታውን አሳልፎ ሰጠ፡፡
ፈያታዊ ዘየማን ደግሞ እንደዚያ እጅግ ክፉ የነበረ ሰው ቢኾንም ቅሉ ተስፋ ስላልቈረጠ ኹሉንም ቀድሞ ገነት ገባ፡፡
ፈሪሳዊው ሰው ራሱን ከፍ ከፍ ያደርግ ስለ ነበር ከምግባር ማማ ላይ ወደቀ፡፡ ቀራጩ ግን ተስፋ ስላልቈረጠ
ከፈሪሳዊውም በልጦ ወደ ምግባር ሰገነት ወጣ፡፡
ስለዚህ ይህን ዐውቀን ዘወትር ከስንፍናና ተስፋ ከመቁረጥ እንራቅ!

#ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ
የቴሌግራም ቻናሌ መቀላቀል ለምትሹ
https://t.me/tsidq
የቲክቶክ ገፄ መቀላቀል ለምትሹ
https://vm.tiktok.com/ZMYmbwUKA/

አንዳንድ ቤት ግን ሲጨንቅ! የሆነ በቁሙ የሞተ! ግድንግድ ሶፋ ፣ ውድ ቲቪ በሸክላ ሰሀን የተሞላ ቡፌ ፣ ውድ መጋረጃ
ለመርገጥ የሚያስፈራ ምንጣፍ .... ስልክ ቁጥር ለመፃፍ ቁራጭ ወረቀት ብትጠይቁ ግን የወረቀት ዘር በቤቱ የለም!
መፅሐፍማ እርሱት! "ወይ እዚህ ጋ ትፅፈው?" ብለው ናብኪን ያመጡላችኋል! እና እዚህ መቃብር ውስጥ ልጆች
ያድጋሉ! እናንተ በቤት እቃ የተገነዛችሁ ሰዎች እባካችሁ ልጆቻችሁን እንኳን ከእናተ የቁም ሞት አትርፏቸው !
ለናሙና እቤታችሁ የሚነበብ ነገር ለልጆቻችሁ አስቀምጡ! ወረቀት ሲንኮሻኮሽ ይስሙ! ያንብቡ በእድሚያቸው ልክ
መፅሐፍት ግዙላቸው! ምን አይነት ጨካኝ ወላጆች ብትሆኑ ነው ግን? ይሄን ኮተት እንደትልቅ ነገር አትቁጠሩት!
ልጆቻችሁ ያንብቡ ማለት የመፅሐፍ ሻጭ ተራ ማስታወቂያ አይደለም! ነገ ልጀ እንዲህ ሆን እንደዛ እያላችሁ
ከመነፋረቅ ያድናችኋል! ልጆቻችሁ ነገ ወደዚች አለም የእናተን ሶፋና ምንጣፍ ተሸክመው አይሄዱም! ባዶ ልጆች
ለዓለም አታዋጡ!

Alex Abreham

ቅትለተ መነኮሳት ከዝቋላ ወደ ደቡብ አፍሪቃ

አባ ተክለ ሃይማኖት (አባ ተክላ) ደቡብ አፍሪቃ ገጠር ውስጥ የሚያገለግሉ መነኩሴ ነበሩ :: ወላጆቻቸው
ለኢትዮጵያዊው ጻድቅ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ምልጃቸውን በመማጸን ተስለው ስለወለዱአቸው ስማቸውን በጻድቁ
ስም ሰይመዋቸዋል:: ከባለጸጋ ቤተሰብ የተወለዱትና የሚተዳደሩበት የራሳቸው መርከብ የነበራቸው እኚህ ወጣት
የእንጦንስ የመቃርስን መንገድ ተከትለው ሀብታቸውን ሸጠው ለድኆች ሠጥተው የቀረውን ለገዳም አውርሰው
መነኮሱ:: ከዓመታት በፊት በገዳማቸው ተገኝቼ በረከት በተቀበልሁበት ወቅት እንዴት እንደመነኮሱ ፣ ለአቡነ ተክለ
ሃይማኖት ያላቸውን ፍቅርና አንዳንድ ነገሮችን አጫውተውኝ ነበር:: ለእኔም ያሳዩት ስስትና ፍቅር ከሕሊናዬ
የማይጠፋ ነው:: ዛሬ በግፍ ሰማዕትነትን እንደተቀበሉ ቢቢሲ ዘግቦ አየሁ :: ሰይጣን የእውነተኛይቱን ቤተ ክርስቲያን
አድራሻ መቼም አይሳሳትም::

በግብፃዊው ጻድቅ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ስም በተሰየመ ገዳም የመነኮሱ ኢትዮጵያውያን ሰማዕታት በሆኑ
በሳምንቱ በኢትዮጵያዊው ጻድቅ ተክለ ሃይማኖት ስም የተሰየሙ መነኩሴ ከወንድሞቻቸው ጋር ሰማዕትነት
ተቀበሉ:: ሰይጣን ከሃይማኖታችን እንጂ ከዘራችን ጠብ የለውም::

“በዚያን ጊዜ ለመከራ አሳልፈው ይሰጡአችኋል ይገድሉአችሁማል፥ ስለ ስሜም በአሕዛብ ሁሉ የተጠላችሁ


ትሆናላችሁ" ማቴ. 24:9

#መልካምነት

አንድ ሰው ሶሰት ጓደኞች ነበሩት በጣም ነው የሚወዳቸው ብዙ ነገር ያደርግላቸዋል ያደርጉለታልም፡፡ አንድ ቀን አባቱ
"ልጄ ጓደኞች አሉህ" አሉት "አዎ ሶስት ጓደኞች አሉኝ በጣም የሚወዱኝ የምወዳቸው" አላቸው፡፡ እርሳቸውም
"ከእነዚህ ውሰጥ የልብ ጓደኛህ ማነው?" አሉት "ሁሉም" አለ "እርግጠኛ ነህ ልጄ" ሲሉት "አዎ" አለ፡፡ "እንደዚያ ከሆነ
የሆነ ነገር እንፍጠርና እውነተኛ መሆናቸውን እናረጋግጥ" ይሉታና ጓደኞቹን እንዲፈትን ያደርጉታ፡፡ ልጁም አባቱ
ባለው መሰረት ለአንዱ ጓደኛው ይደውልና "ያለጥፋቴ ሰው ገድለሃል ተብዪ ፍርድ ቤት ነኝ ድርሰልኝ " ይለዋል
ጓደኛውም "አዝናለሁ አልችልም" ይለዋል፡፡ አሁንም ለሁለተኛው ይደውላል ሁለተኛ ጓደኛውም "ችግር የለውም
እመጣለው እርዳታየም ካሰፈለገህ የምችለውን ሁሉ አደርግልሀለው ፍርድ ቤት ግን አብሬህ አልገባም አዝናለው "
ይለዋል አሁንም ለሶሰተኛው ይደውላል ሶሰተኛውም "እንዴ ኧረ ችግር የለውም ደሞ ለአንተ አይደለም ፍርድ ቤት
ሌላም ቦታ እመጣልሃለሁ" አለ፡፡ በዚህ ጊዜ ይህ ልጅ በአባቱ ምክር እውነተኛ የህይወት ጓደኛው ማን እንደሆነ
አረጋገጠ ።

#ፍርድ_ቤት_የተባለው_የሰው_ልጅ_ይችን_ዓለም_ተሰናብቶ_የሚኖርባት_የዘላለም_ቤቱ_ሲሆን

❶- #የመጀመሪያው_አልችልም_ያለው_ገንዘብ ነው መቸም የሰው ልጅ በዚች ምድር ሲኖር ምን ያህል ሀብት


ቢኖረው ከሞት አያሰጥለውም በሞት ጊዜ ተከትሎን አይመጣም ።

❷- #ሁለተኛው_ፍርድ_ቤቱ_እመጣለሁ እረዳሃለሁ እንጅ አልገባም ያለው ዘመድ ወይም ጓደኛ ነው፡፡ በአጠቃላይ
ሰው ምን ያህል ቢወድህ ያለቅሳል ያዝናል እንጂ ወደ ቀብር ቦታህ አብሮህ ይመጣል እንጅ መቸም አንተ ሞተሀልና
ልሙት አይልም።

❸- #ሶሰተኛው_እሰከ_መጨረሻው_ከአንተ_ጋር_ነኝ ያለው በዚች አለም ሰትኖር የሰራናቸው ጥሩና መልካም


ሰራዎች ናቸው፡፡ በዚህ ምድር ላይ የምንሰራቸው ጥሩ ሰራወች የዘላለም ሰንቃችን ናቸው እስከ መጨረሻው ከአኛ
ጋር ይከተሉናል፡፡
መልካምነት ለራስ ነውና
መልካም እንሁን መልካም እንስራ
ሌሎች ያነቡት ዘንድ ያጋሩ
የቴሌግራም ቻናሌ መቀላቀል ለምትሹ
https://t.me/tsidq

"እነዚህን 3 ቱን ነገሮች ካላቆምናቸው የኢትዮጵያ መከራ ይቆማል ብላችሁ አታስቡ‼

#1 ኛ ዝሙት ጭፈራ ሰማይን በጡጫ ምድርን በእርግጫ ገደብ የሌለው ፍላጎት ሰርቶ የማይጠግብ አይቶ
የማይጠግብ 24 ሰዓት የሚዘሙት የእግዚአብሔርን ተአምር አድርጎ ሊያስብ አይቻልም

#2 ኛ ስርዓተ ቤተክርስቲያንን ማጓደል

ሰላማችን የጎደለው ስርዓት እያጎደልን ነው ስትነገሩ ትቆጣላችሁ ሴቶች ሱሪ አትልበሱ ስትባሉ ትከፋላችሁ ስርዓት
የሌላት ቤተክርስቲያን በረት ናት። የሚሻለን መሰባሰብ መሳሪያ መዝረፍ መፎከር አይደለም መጀመሪያ እራሳችንን
እናፅዳ ቤት ሲጠረግ ከውስጥ ወደ ውጭ እንጅ ከውጭ ወደ ውስጥ አይደለም ።

#3 ኛ የእግዚአብሔር የሆነውን መቀማት

የእግዚአብሔር የሆነውን መቀማት ማለት አስራታችን ብቻ እንዳይመስላችሁ ቀኑ የእሱ ነው ሌሊቱም የእሱ ነው ቀን


ሳይፀልይ የሚውል ቀኑ የእግዚአብሔር ስለሆነ ከእግዚአብሔር ስላላስፈቀደ ይህን ቀን ሰርቋል ማለት ነው
ሌሊቱንም ሳይፀልይ ቢተኛ ሌሊት ተነስቶ ከፀለየ እንዳድር ፍቀድልኝ ማለት ነው ይህን የማያደርግ ሰው ሌባ ነው

እራስን መስረቅ ሌብነት ✅ነው፦

አይን የእግዚአብሔር ገንዘብ ነው መልካም የማይመለከትበት ሰው ሌባ ነው።


እግር የእግዚአብሔር ገንዘብ ነው የማይሰግድበት ሰው ሌባ ነው።
ሆድ የእግዚአብሔር ገንዘብ ነው የማይፆምበት ሰው ሌባ ነው
አንዱን ስንቀንስ አንዱን ስንቀንስ ሰላማችን ተቀንሶ አለቀ።

የቅዱሳን አምላክ ልቦና ማስተዋልን ያድለን አሜን

ቴሌግራም ቻናሌ ይቀላቀሉ


https://t.me/tsidq

📌 ተስፋ መቁረጥና ስንፍና

➯ ተስፋ መቁረጥና ስንፍና እጅግ ክፉዎች ናቸውና ከእነዚህ እንራቅ “ክፋታቸውስ እንደምን ያለ ነው?” ያልከኝ
እንደ ኾነም እንዲህ ብዬ እመልስልሃለሁ፤ ተስፋ መቁረጥ የወደቀው ሰው እንደ ገና እንዲነሣ አይፈቅድለትም፤
ስንፍናም የቆመው ሰው እንዲወድቅ ያደርጓል፤ ስንፍና ገንዘብ ያደረግናቸውን መልካም ነገሮች ከማሳጣቱም በላይ
ሊመጡ ካሉ ክፉ ነገሮች እንዳንጠበቅ ያደርገናል፤ ስንፍና ከሰማያትም ቢኾን ይጥለናል፤ ቀቢጸ ተስፋም ወደ ክፋት
ዐዘቅት እንድንሰጥም ያደርገናል፤ በእውነት በቀቢጸ ተስፋ ካልተያዝን ከጽኑ ክፋት መመለስ ይቻለናል፡፡

➯ እነዚህ ኹለቱ ምን ያህል ኃይል እንዳላቸው ይበልጥ ታውቅ ትረዳ ዘንድ ምሳሌ ጠቅሼ ልንገርህን? መልካም!
ዲያብሎስ መጀመሪያ ላይ መልካም ነበር፤ ከስንፍናና ከቀቢጸ ተስፋ የተነሣ ግን እንደ ገና የማይነሣ ኾኖ ወደ ክፋት
ወደቀ፤ ዲያብሎስ ጥንቱ መልካም እንደ ነበረ ሲናገር መጽሐፍ ቅዱስ እንዲህ ያለውን አድምጥ
✍️
“ሰይጣን እንደ መብረቅ ከሰማይ ሲወድቅ አየሁ”
📖ሉቃ 10፥18

➯ መብረቅ የሚለው አገላለጽ ዲያብሎስ ከመውደቁ በፊት ምን ያህል ብሩህ ሕይወት እንደ ነበረውና በምን ያህል
ቅጽበት እንደ ወደቀ የሚያመለክት ነው፡፡

➯ ቅዱስ ጳውሎስ ደግሞ ተሳዳቢ፣ አሳዳጅና ነውርን የማያውቅ ሰው ነበር፤ ነገር ግን ቀናተኛ ስለ ነበርና ተስፋ
ስላልቆረጠ ተነሥቶ መላእክትን የሚተካከል ኾነ፤ ይሁዳ ሐዋርያ ነበር፤ ነገር ግን በስንፍና ምክንያት ጌታውን አሳልፎ
ሰጠ፤ ፈያታዊ ዘየማን ደግሞ እንደዚያ እጅግ ክፉ የነበረ ሰው ቢኾንም ቅሉ ተስፋ ስላልቆረጠ ኹሉንም ቀድሞ ገነት
ገባ፤ ፈሪሳዊው ሰው ራሱን ከፍ ከፍ ያደርግ ስለ ነበር ከምግባር ማማ ላይ ወደቀ፤ ቀራጩ ግን ተስፋ ስላልቈረጠ
ከፈሪሳዊውም በልጦ ወደ ምግባር ሰገነት ወጣ፤ ስለዚህ ይህን ዐውቀን ዘወትር ከስንፍናና ተስፋ ከመቁረጥ እንራቅ!
📌 ምንጭ
✍ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ

+ አቤቱ ቅጣኝ ነገር ግን እንዳታዋርደኝ! +

እግዚአብሔር ፍቅር ነው ፣ መሐሪ ነው ፣ ይቅር ባይ ነው፡፡ ፍቅር ይቆጣል ወይ? ይቅር ባይስ ይቀጣል ወይ?
ብዙዎቻችን ስለ ክርስቶስ ሲነገረን መሐሪነቱና ፍቅሩ ብቻ ቢነገረን አንጠላም፡፡ ጨርሶ የማንፈራው እግዚአብሔር
እንፈልጋለን፡፡ እንዲህ አታድርግ! የሚለን ሲመጣ ‘አትፍረድ’ እንላለን ፤ ቆይተን ግን የሰማዩን ዳኝም አትፍረድ
ማለት ይቃጣናል፡፡ ቅጣት የሌለበት ክርስትና እንሻለን፡፡

ይህ ዓይነቱን ክርስትና ‘ጣፋጭ ክርስትና’ {የስኳር ክርስትና ይሉታል} ምንም ምሬት የሌለበት ሁሌም ማር ማር
የሚል ሕይወት አድርገው ክርስትናን የሚሰብኩም ብዙ ናቸው፡፡ ‘አይዞህ ብትታመም ትፈወሳለህ ፣ ቤትህ ይሞላል ፣
ቀዳዳህ ይደፈናል ፣ ብትበድልም አትቀጣም’ ብቻ የሚሉ ስብከቶች የስኳር ክርስትና ስብከቶች ናቸው፡፡ ይህንን ብቻ
የሚያጮሁ ሰዎች ክርስቶስ ‘የምድር ጨው ናችሁ’ ያለውን ትተው የምድር ስኳር ለመሆንና ዓለምን ለማስደሰት
የሚፈልጉ ናቸው፡፡
በእርግጥ እግዚአብሔር ይቆጣል ወይ? አዎን ይቆጣል! እንዲህ ይላል መጽሐፉ

‘እግዚአብሔር ቀናተኛና ተበቃይ አምላክ ነው እግዚአብሔር ተበቃይና መዓትን የተሞላ ነው እግዚአብሔር


ተቃዋሚዎቹን ይበቀላል፥ ለጠላቶቹም ቍጣውን ይጠብቃል። በቍጣው ፊት የሚቆም ማን ነው ? የቍጣውንም
ትኵሳት ማን ይታገሣል? መዓቱ እንደ እሳት ይፈስሳል፥ ከእርሱም የተነሣ ዓለቶች ተሰነጠቁ’ ናሆ 1፡1፣6
‘‘ከቍጣው የተነሣ ምድር ትንቀጠቀጣለች አሕዛብም መዓቱን አይችሉም’’ ኤር 10፡10
‘‘እኛ በቍጣህ አልቀናልና፥ በመዓትህም ደንግጠናልና’’ መዝ. 90፡7

እግዚአብሔር በተቆጣ ጊዜ የሚመልሰው የለም፡፡ ቅዱሳን የቁጣውን መጠን ስለሚያውቁ በትሕትና ይለምኑታል፡፡

ይሁንና መጽሐፍ ቅዱስ ስለ እግዚአብሔር ቁጣ ደጋግሞ ቢነግረንም አንድ ሌላ ደስ የሚያሰኝ ነገርም ነግሮናል፡፡
የእግዚአብሔር ቁጣው ለዘላለም አይደለም፡፡ "ምሕረቱ ለዘላለም ነውና" ይላል እንጂ "ቁጣው ለዘላለም ነውና"
አይልም:: የእግዚአብሔር ቁጣ ጊዜያዊ ነው፡፡

‘መሐሪ ነኝና ለዘላለም አልቆጣም’ ኤር 3፡12


‘ቁጣው ለጥቂት ጊዜ ሞገሱ ግን ለሕይወት ዘመን ነው’ መዝ 29፡5
‘ጌታ ለዘላለም አይጥልም ቢያሳዝንም እንደ ምሕረቱ ብዛት ይራራል ፤ የሰው ልጆችን ከልቡ አያስጨንቅም
አያሳዝንምም’ ሰ.ኤር 3፡31

የፈጣሪን የነነደ የቁጣ እሳት ማጥፋት የሚቻለን በዕንባ ነው፡፡ በደላችንን አምነን ቅጣት ይገባናል ነገር ግን መሐሪ ነህና
ማረን ማለት ይገባል፡፡ ንጉሥ ዳዊት ‘አቤቱ በቁጣህ አትቅሠፈኝ በመዓትህም አትገሥፀኝ’ ብሎ የፈጣሪን ቁጣ
አበረደ፡፡ /መዝ 38፡1/ ነቢዩ ኤርያስም ‘አቤቱ ቅጣኝ ነገር ግን እንዳታዋርደኝ በመጠን ይሁን እንጂ በቁጣ አይሁን’
ብሎ ተለማመጠ፡፡ ኤር 10፡24

አንድ ሠዓሊ በጣም ብዙ ደክሞ የተጠበበትን ሥዕሉን የፈለገ ቢበሳጭ ለረዥም ጊዜ ያንን ሥዕል ለመሳል የተጠበበትን
ጥበብ አስቦ ሥዕሉን ወደ እሳት አይጨምረውም፡፡ አባ ጊዮርጊስ እንዲህ ሲል ይለምናል ‘ሠዓሊ ሥዕሉን ያጠፋል
ወይ? [ጌታ ሆይ እኔን ስትፈጥር የተጠበብክበትን] የቀደመ ጥበብህን አስብ እንጂ! አስበህም ማረኝ! [ያጠፋዖኑ
ለሥዕሉ ሠዓሊ ፤ ኪነተከ ዘትካት ኀሊ]
ይቅርታውን በንስሓ ለሚለምኑ ሁሉ ምሕረቱ ቅርብ ነው፡፡ በቀኝና በግራው ወንበዴዎች በተሰቀሉበት በዕለተ አርብ
የግራው ወንበዴ ሲሰድበው ጌታ መልስ አልሠጠም፡፡ የቀኙ ወንበዴ ማረኝ ሲለው ግን ከአፉ ተቀብሎ በገነት ትሆናለህ
አለው፡፡ ቁጣው የራቀ ምሕረቱ የበዛ እርሱ የራበው ሰው ለምግብ የሚቸኩለውን ያህል ይቅር ለማለት ይቸኩላል፡፡
‘ምሕረትን ይወድዳልና ቁጣውንም ለዘላለም አይጠብቅም ተመልሶ ይምረናል ፤ ክፋታችንንም ይጠቀጥቃል ፤
ኃጢአታችንንንም በባሕሩ ጥልቅ ይጥለዋል’ ሚክ 7፡18

ልጆች ሳለን ጥፋት ስናጠፋ ከወላጆቻችን እንደበቃለን፡፡በተደበቅንበት ሰዓት ውስጣችን በፍርሃት ይርዳል፡፡ ‘ዛሬ
ገደለኝ’ ‘ዛሬ መሞቴ ነው’ ብለን እንጨነቃለን፡፡ የሚደርስብንን ቅጣት እጅግ አጋንነን ከመፍራታችን የተነሣ
መሬት ተሰንጥቃ ብትውጠን አንጠላም፡፡ በዚያ ሁሉ ጭንቀት ውስጥ ግን ወላጆቻችንም እስኪያገኙን ይጨንነቃሉ፡፡
እግዚአብሔርም እንዲህ ነው፡፡ አጥፍቶ በገነት ዛፎች መካከል የተሸሸገ አዳምን ወዴት ነህ ብሎ የፈለገ እርሱ እኛንም
ይፈልገናል፡፡ አዳም ከገነት ሳይባረር ገነት ውስጥ እንደጠፋ ፈጣሪ ሳያባርረን ራሳችንን በኃጢአት ተሸማቅቀን ያባረርን
እኛን ይፈልገናል፡፡ እርሱ ስለመጥፋትህ ይጨነቃል አንተ ‘ዛሬስ አይምረኝም’ ትላለህ፡፡

የሚገርመው በጥፋታችን ከተደበቅንበት ወላጆቻችን ካገኙን በኋላ ሁለተኛው ዙር ጭንቀታችን ‘ምን አጥፍተህ
ነው የተደበቅከው’ መባል ነው፡፡ ጥፋታችንን ሲያውጣጡን እንንቀጠቀጣለን፡፡ ያጠፋነውን ስለምናውቀው ስንት
እንደሚያስገርፈንም እናውቀዋለን፡፡ ‘ብትናገር ይሻላል? ግዴለህም!’ ብለው አግባብተውም አስፈራርተውም
ወላጆቻችን ጥፋታችንን ያውጣጡናል፡፡ እየፈራን ያጠፋነውን ጥፋት ስንናዘዝ ግን ወላጆቻችን በጥፋታችን ቅጥል
ብለው ‘አልመታህም ተናገር’ ያሉንን ረስተው የዱላ ዝናም ያዘንቡብናል፡፡ እግዚአብሔር ግን ጥፋትህን
ስትነግረው ቁጣው የሚገነፍል አባት አይደለም፡፡
’’ኃጢአታችንን ብንናዘዝ ኃጢአታችንን ይቅር ሊለን ከዓመፃም ሁሉ ሊያነፃን የታመነና ጻድቅ ነው’ 1 ዮሐ 1፡9

ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ

+ ከአፍ የሚወጣ እሳት +

"አፌ ይለፈልፋል እንጂ ውስጤ እኮ ንጹሕ ነው"


አለች አባ ፊት ቀርባ - በክፉ ንግግርዋ ብዙ ሰው ያስቀየመች ሴት::

አባ መለሱላት :-
ልክ ነሽ ልጄ እባብም እኮ መርዙን ከተፋ በኁዋላ ውስጡ ንጹሕ ነው!

ምላስ አጥንት የለውም ነገር ግን አጥንት ይሰብራል:: እግዚአብሔር ምላስን እንደጆሮ ክፍት አላደረገም:: በከንፈርና
በጥርስ ሸፍኖታል:: ትንሽ አሰብ አድርገን እንድናወራ ነው:: "ሰው ለመናገር የዘገየ ለመስማት የፈጠነ ይሁን" የሚለው
ቅዱስ ያዕቆብ ስለ አንደበት ሲናገር "ትንሽ እሳት እንዴት ያለ ትልቅ ጫካ ያቃጥላል" እንዳለ የምላስ ኃይል እጅግ
ከባድ ነው:: ከአፍ የሚወጣ እሳት ብዙ ጉዳት ሊያደርስ ይችላል::

ሰው በዱላ ቢደበደብ ታክሞ ቁስሉ ያገግማል:: ክፉ ንግግር የሚያቆስለው ቁስል ግን በቀላሉ አይሽርም:: ዱላ
የሚያርፈው ሥጋ ላይ ሲሆን መጥፎ ንግግር ግን ነፍስ ላይ ነው:: ክፉ ንግግሮች ሰውን ለጊዜው ብቻ ሳይሆን ለዘላለም
ሊያመርሩት ይችላሉ::

(ሌላ ነገርዋን ትተነው) ሚሼል ኦባማ በአንድ ቃለ መጠይቅ ላይ በጣም ልብ የሚነካ ነገር ስትናገር ሰማሁ::
ስለወረደባት ስድብ ስታስታውስ "አንዳንድ ክፉ ቃላት የነፍስን ቅርፅ ይቀይራሉ" ብላ ነበር::

እውነት ነው በመራር ቃላት የነፍሳቸው ቅርፅ ከተቀየረ ስንቶች ናቸው :: የማይዘነጉት ንግግር እድሜ ልክ
የሚያቆስላቸው : የአንድ ሰው ከባድ ስድብ በራስ መተማመናቸውን የነጠቃቸው : የአንድ ሰው "አትችልም" የሚል
ድምፅ እጅና እግራቸውን ያሰራቸው እጅግ ብዙ ናቸው:: ሰው ለማሳቅ ተብለው የተሰነዘሩ "ትረባዎች"ና አጥንት
ሰባሪ ቀልዶች ቂመኛ ያደረጉዋቸው ሰውን ሁሉ ያስጠሉአቸው ስንት ናቸው? በስድብ ብቻ የፈረሱ ቤቶች አሉ::
ስለተሰደቡ ብቻ በሕዝብ ላይ የሚፈርዱ ዘር እስከማጥፋት የተነሡ አሉ :: ተናጋሪው በጥፋታቸው ውስጥ ትልቅ ድርሻ
እና ተጠያቂነት እንዳለው ግን ይዘነጋል::

እግዚአብሔርም "እንደ ዋዛ ለተናገራችሁት ቃል በፍርድ ቀን መልስ ትሠጡበታላችሁ" ብሎአልና ለሰዎች


የምንሰነዝረው እያንዳንዱ ቃል ያስጠይቀናል::

በተቃራኒው ለሰዎች ጥሩ ቃል መናገርን ብዙ ዋጋ አንሠጠውም:: ለስድብ የማናቅማማ ሰዎች ለምስጋና ሲሆን ግን


እንሽኮረመማለን::
ፊት ለፊት አሳምረን የምንሳደብ ሰዎች ለማመስገን ሲሆን "በፊትህ ማመስገን እንዳይሆንብኝ" እንላለን::

ሆኖም ብናወጣው ሰዎች የሚነገራቸው ጥቂት በጎ ቃል ሰብእናቸውን ይገነባል :: ፈጣሪ "ብርሃን ይሁን" ብሎ በቃሉ
እንዳበራው ማድረግ ባይቻልህ እንኩዋን በጥቂት በጎ ቃላት የአንድን ሰው ቀን ማብራት ትችላለህ::
ከምንም ሥጦታ በላይ መልካም የምስጋና ቃላት በሰው ልብ የሚቀር ውድ ሥጦታ ነው::

ባል ለሚስቱ ከሚገዛው ሥጦታ በላይ "ባልዋም ያመሰግናታል" የሚለውን ቃል ቢፈጽምላት ደስታ ይሆንላታል::
ልጆች ከብዙ ሥጦታዎች በላይ ከወላጆቻቸው የሚሰሙት የፍቅር ቃል ይሠራቸዋል::

የእስክንድርያው ፊሎ ለልጅ አባትና እናቱ ከሀገሪቱ ንጉሥና ንግሥት በላይ ናቸው ይላል :: የንጉሥ ቃል የሹመት ቃል
ነውና ልጆች በወላጆቻቸው የሚሰሙት "ጎሽ" የሚል ቃል ከፍ ያደርጋቸዋል::

"ልጅሽ ትምህርት የማይገባው ደደብ ስለሆነ ትምህርት ቤት አትላኪው" የሚልን ደብዳቤ "ልጅሽ በጣም ጎበዝ ስለሆነ
እሱን ማስተማር ስለማንችል በቤት አስተምሪው" ብላ ያነበበች እናት ትልቅ ሳይንቲስት አፍርታለች::

ብርሃን ይሁን ! ምድር ታብቅል! ብሎ የፈጠረን አምላክ በአርኣያው ፈጥሮናልና በቃላችን የምናሳምም ሳይሆን
የምንፈውስ እንሁን::

መድኃኔ ዓለም ክርስቶስ "ወንድሙን የሚሰድብ ነፍሰ ገዳይ ነው" ብሎአል:: ስድብ ከመግደል እኩል ነው ሲል ነገሩን
ለማግነን የተጠቀመው አገላለጽ ሳይሆን በእርግጥም መሳደብ ከመግደል ብዙም ስለማይለይ ነው :: ሀገራችን ላይ
ያንዣበበው የዘር ጭፍጨፋ ብዙዎቻችንን ያሳስበናል:: እንደ ሩዋንዳ ልንሆን ነው? እንላለን:: ወዳጄ የሩዋንዳ የዘር
ማጥፋት መነሻው እኮ የሚዲያ የጥላቻ ንግግር ነበር:: እውነት ለመናገር ዘር ነክ ስድቦችና በቀልድ መልክ የሚነገሩ
የንቀት ንግግሮች ሁሉ የዘር ማጥፋት ዋዜማ ናቸው:: የጥላቻ ንግግር (hate speech) የዘር ማጥፋት እጅግ ወሳኙ
መቆስቆሻ ነው:: ስለዚህ "በለው በለው" ብለህ በምትጽፈው comment ወንድሙን ከገደለው እኩል በፈጣሪ ፊት
ትጠየቃለህ:: ቅዱሱ እንዲህ ይላል
"እኔ ግን እላችኋለሁ፥ በወንድሙ ላይ የሚቆጣ ሁሉ ፍርድ ይገባዋል፤
ወንድሙንም ጨርቃም የሚለው ሁሉ የሸንጎ ፍርድ ይገባዋል፤ ደንቆሮ የሚለውም ሁሉ የገሃነመ እሳት ፍርድ
ይገባዋል" ማቴ 5:22

ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ


ሰኔ 11 2012 ዓ ም

ለተጨነቀች ነፍስ ዕረፍት የሆነው የእግዚአብሔር ቃል ለሁሉ ይዳረስ ዘንድ :: እኔም ለእናንተ ከሰበክሁ በኁዋላ
የተጣልሁ እንዳልሆን ስለ እኔ ዘንድ ጸልዩ!
https://t.me/tsidq

የሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅ መጋቤ ሐዲስ ነቅዐጥበብ አባቡ (ቀሲስ) በወቅታዊ የቤተ ክርስቲያን
ፈተና እና ችግር በተመለከተ የሰጡት ሙሉ መግለጫ እንደሚከተለው ቀርቧል።

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!!!

ስለወቅታዊ ሁኔታ አስመልክቶ ከሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከት የተሰጠ መግለጫ።

እግዚኦ ቦኡ አሕዛብ ውስተ ርስትከ ወአርኰሱ ጽርሐ መቅደስከ ወረሰይዋ ለኢየሩሳሌም ከመ ልገተ ዓቃቤ ቀምሕ ፤
አቤቱ አሕዛብ ወደ ርስትህ ገቡ የቅድስናህንም መቅደስ አረከሱ ኢየሩሳሌምንም እንደ መደብ አደረጓት መዝ 78:1

ጥንታዊት ፣ ታሪካዊት ፤ ሐዋርያዊት ፣ ዓለም አቀፋዊት እና ኢትዮጵያዊት ፊተኛዪቱ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ


ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ለቅድስት ሀገራችን ኢትዮጵያ የሀገረ መንግሥት ግንባታ በታሪክ ፣ በትምህርት ፣ በኪነ ሕንጻ
እና በመሳሰሉት ሁለተናዊ ቁልፍ ጉዳዮች ያበረከተችው በጎ አስተዋጽኦ ማንም ሊክደው የማይችል ዓለም ያወቀው
ፀሐይ የሞቀው የአደባባይ ምሥጢር ነው።

ይሁን እንጂ ከጥቂት ዓመታት ወዲህ ታላቋ ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን ለሀገር ክብር ለሕዝቦቿ አንድነት የዋለችው
ውለታ ተዘንግቶ ክብሯን በሚነካና መብቷን በሚጋፋ ሁኔታ ላም ባልዋለበት ኩበት ለቀማ እንዲሉ አበው ያለ ስሟ
ስም በመስጠት በቤተ ክርስቲያናችን ላይ ፣ በአገልጋይ ካህናት ላይ እና በምእመናን ልጆቿ ላይ በርካታ አሳዛኝ እና ልበ
ሰባሪ ድርጊቶች ተፈጽመዋል ፣ አሁንም ባላሰለሰ ሁኔታ እየተፈጸሙ ይገኛሉ።

በዚህም መሠረት በሀገረ ስብከታችን ባለፉት ጥቂት ዓመታት በርካታ አብያተ ክርስቲያናት ቅጥራቸው ተደፍሮ
ፈርሰዋል ንዋያተ ቅድሳቶቻቸው ተቃጥለዋል ካህናት አገልጋዮቿ ተገለዋል ምእመናን ልጆቿ ሞተዋል ከሞቀ ቀያቸው
ከደመቀ ቤታቸው ተፈናቅለው ለከፋ የሕይወት እንግልት ተዳርገዋል።

ችግሩ ከነገ ዛሬ ይቀላል በማለት በትዕግሥት ለማለፍ በአባቶቻችን መንገድ እና ጥበብ ለማለፍ ብንሞክርም ችግሩ ግን
ከዕለት ወደ ዕለት እየተባባሰ በመምጣቱ በጣም አዝነናል ልባችንም በእጅጉ ተሰብሯል።

አሁን እንኳን በዚህ ታላቅ ጾም ተረጋግተን ፊታችንን ወደ እግዚአብሔር በፍጹም ንስሐ መልሰን ስለሀገራችን ስለ ቤተ
ክርስቲያናችን እና ስለሕዝባችን ሰላም በምናለቅስበት ሰዓት ሁልጊዜ የመከራ ገፈት ቀማሽ በሆነው የይፋት ቀጠና
ከዚህ በፊት የተቃጠሉብንን አብያተ ክርስቲያናት መልሰን ሠርተን ለማክበር ጫፍ ስንደርስ እያፈረሱብን በሀዘን ላይ
ሀዘን እየተጨመረብን ይገኛል።

አሁንም በዚህ ወቅት በኤፍራታ እና ግድም ወረዳ ቤተ ክህነት የካሬ ቆሬ ደብረ ከዋክብት አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ
ቤተ ክርስቲያን በድጋሚ ወድሟል የሞላሌ ቅዱስ መድኃኔ ዓለም ቤተ ክርስቲያን ተጎድቷል።

በተመሳሳይ በቀወት ወረዳ ቤተ ክህነት የኩሪብሪ ቅዱስ ሚካኤል እና የዋጮ ቅዱስ በዓለ ወልድ አብያተ ክርስቲያናት
መጎዳታቸውን እና የየለን ቅድስት ማርያም ንዋያተ ቅድሳት መዘረፉ ሀዘናችንን እጽፍ ድርብ አድርጎታል።

ስለዚህ፦
1.ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን የሰላም ቤት የአንድነት ተምሳሌት የሀገር ባለውለታ ያለ ቋንቋ ፣ ያለዘር እና ያለከለር
ልዩነት ለሁሉም በእኩልነት መንፈሳዊ አገልግሎቷን ተደራሽ አድራጊ መሆኗ ታውቆ በቤተ ክርስቲያናችን ላይ
የሚደረገውን ግፍ እና አስነዋሪ ነገር ሁሉ በፅኑዕ እንቃወማለን የሚመለከተው አካልም በቤተ ክርስቲያናችን ላይ
የሚፈጸውን ድፍረት የተሞላበት በደል እና ነውር ያስቆምልን ዘንድ በአጽንኦንት እንጠይቃለን።

2.የዜጎችን ሰላም እና ደኅንነት ማረጋገጥ የሚገባው አካል የምእመናን ልጆቻችንን በሰላም ወጥቶ በሰላም የመግባት
ሰላም እና ደኅንነት በማረጋገጥ ከአካባቢያቸው ተፈናቅለው በችግር ውስጥ ያሉ ወገኖቻችን ወደ ቤት ቀያቸው
እንዲመለሱ አስፈላጊው ሁሉ ይደረግልን ዘንድ በቤተ ክርስቲያናችን ስም እናሳስባለን።

3.ለወገን ደራሽ ወገን በመሆኑ በይፋት ቀጠና እና በምንጃር ወረዳ ቤተ ክህነት ከአውራ ጎዳና አካባቢ ከቤታቸው እና
ከቀያቸው ተፈናቅለው ላሉ ወገናቻችን ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውን በሙሉ የድጋፍ እጃችሁን
ትዘረጉልን ዘንድ በጸሎታችሁም ታስቡን ዘንድ በትህትና እናሳስባለን።

@አቡቀለምሲስ ሚዲያ

+ እግዚአብሔርን ለምን - አልለምንም! +

‘እነሆ ድንግል ትጸንሳለች’ የሚለው ትንቢት ከመነገሩ አስቀድሞ ምክን ያት የሆነ አንድ ክስተት ይህ ነበር፡፡
የይሁዳ ንጉሥ አካዝ ዙሪያውን በጠላቶች ተከብቦ ነበር፡፡ ሁለት ነገሥታት ሊወጉትና ኢየሩሳሌምን ሊወርሯት
አሰፍስፈው እየጠበቁ ነው፡፡ የጦር ምክራቸውም ‘ወደ ይሁዳ እንውጣ እናስጨንቀው እንስበረው በላዩ ላይም ሌላ
ንጉሥ እናንግሥበት’ የሚል ነበር፡፡ ይህን ምክራቸውን አስቀድሞ ይነግረው ዘንድ እግዚአብሔር ነቢዩ ኢሳይያስን
ወደ ንጉሥ አካዝ ላከው፡፡ ኢሳይያስም የሚመጣበትን የጠላት ከበባና መጻኢ ፈተናውን ነገረው፡፡

እንደመፍትሔም እንዲህ አለው ‘ከጥልቁም ወይም ከከፍታውም ከእግዚአብሔር ምልክትን ለምን’ የሚል ምክር
ነበር፡፡ እግዚአብሔር ወይ ከሰማይ ወይ ከምድር አንዳች ተአምር አድርጎ ከዚህ ጭንቅ እንዲያወጣህ ፈጣሪህን ለምን
ብሎ የነገረው ከእግዚአብሔር በቀጥታ የተላከው ነቢይ ነበር፡፡ ‘’ለምነኝ አሕዛብን ለርስትህ እሰጥሃለሁ’
እንደማለት ያለ ዕድል ቀርቦለት ነበር፡፡
ንጉሥ አካዝ ግን ግልጽ እና አጭር ምላሽ ሠጠ ፦ አልለምንም ፤ እግዚአብሔርንም አልፈታተንም! /ኢሳ 7፡13/

እርግጥ ነው በኦሪት ጌታ አምላክህን አትፈታተነው ተብሎ ተጽፎአል፡፡ ራሱ እግዚአብሔር ነቢዩን ልኮ ለምነኝ ተአምር
ልፈጽምልህ እያለህ ‘አልለምንም እግዚአብሔርን አልፈታተንም’ ማለት ግን በራሱ እግዚአብሔርን መፈታተን
ነው፡፡

ንጉሥ አካዝ እንዲህ በጠላት ተከብቦ እያለ ‘ወደ ፈጣሪ ለምን’ ሲባል እምቢ ያለው እርሱ እንዳለው
እግዚአብሔርን ላለመፈታተን አልነበረም፡፡ በዚያ ጦርነት እንዲረዳው ወደ አሶር ንጉሥ ቴልጌልቴልፌልሶር መልእክተኛ
ልኮበት ስለነበር ነው፡፡ በታላላቅ ተአምራት ሕዝቡን የታደገ እግዚአብሔርን እንዲለምን ጥሪ እየቀረበለት አካዝ ግን
ከፈጣሪ ይልቅ በአሶር ንጉሥ እርዳታ ተስፋ አድርጎ ነበር፡፡ ኢሳይያስም ጸልይ ሲለው የልቡን ሃሳብ ደብቆ ፣ ከፈጣሪ
ይልቅ በሰው ለመመካቱም መንፈሳዊ ካባን አልብሶ ‘ፈጣሪን አልፈታተንም’ ብሎ ተናገረ፡፡

አካዝ ይረዳኛል ብሎ የተማመነበት በመጽሐፍ ቅዱስ በስሙ ርዝመት ሁለተኛ የሆነው ቴልጌልቴልፌልሶር
በጥያቄው መሠረት ወደ ይሁዳ ቢመጣም እንኳን አስጨነቀው እንጂ አልረዳውም፡፡ ይረዳኛል ብሎ ከቤተ መንግሥቱ ፣
ከመኳንንቱ ግማሹን አሳልፎ ለአሶር ንጉሥ እስከመሥጠት ቢደርስም ቴልጌልቴልፌልሶር ግን እንደ ስሙ የተንዛዛ
ቆይታ ቆይቶ በዘበዘው፡፡ ችግር በመፍታት ፈንታ ችግር ሆነበት ፤ አካዝም በዚህ ተበሳጭቶ ‘ለምነኝ‘ ብሎ
ሲጠይቀው አልፈልግም ያለውን እግዚአብሔርን መንቀፍ ጀመረ፡፡ ጭራሽ ጠላቶቼ እኔን ድል ያደረጉት
አማልክቶቻቸው ከእኔ አምላክ ቢበልጡ ነው ብሎ ለጠላቶቹ አማልክት መሥዋዕት አቀረበ፡፡ መጨረሻውም እጅግ
የከፋ ሆነ፡፡ /2 ዜና 28፡20/
‘’አልለምንም እግዚአብሔርን አልፈታተንም’’ ብዙ ጊዜ የእምነታችንን ማነስ የምንደብቅባት ሽፋን ናት፡፡
ሀገር ሲታመስ ፣ መከራ ሲጸና ፣ ነገሮች ድብልቅልቅ ሲሉ ፣ ጠላት ከግራና ቀኝ ሲበዛ ምንድን ነው መፍትሔው ?
አካዝን ለምነኝ ያለ አምላክ ለእኛም ‘‘በመከራህ ቀን ጥራኝ እኔም አድንሃለሁ አንተም ታከብረኛለህ’’ ብሏል፡፡
/መዝ 49፡15/ በደስታችን ቀን ትዝ ብሎን የማያውቀው ፈጣሪያችን ግድ የለም በመከራህ ቀን ጥራኝ ብሎ ለሁላችን
ጥሪ አቅርቧል፡፡ ምንም ዓይነት ፈተና በግላችን ፣ በሀገራችንና በቤተ ክርስቲያናችን ላይ ሲመጣ ቅድስት ቤተ
ክርስቲያን መፍትሔዋ ከጥልቁ ወይም ከከፍታው ምልክትን ከእግዚአብሔር መለመን ነው፡፡ ቤተ ክርስቲያን ዕንባዋን
ትረጫለች ፤ የኃያላን ኃያል ፣ ብርቱዎችን ከዙፋናቸው የሚያዋርድ ፣ ትዕቢተኞችን የሚሰብር አምላክ እንዲደርስላት
እንደ ኢሳይያስ የፈጣሪ አንደበት የሆነች ቤተ ክርስቲያን ጸልዩ ትላለች፡፡

ይህን ጊዜ አካዞች እንበሳጫለን ‘አልለምንም ፣ እግዚአብሔርንም አልፈታተንም’ እንላለን ቤተክርስቲያንን የላካት


ኢሳይያስን የላከው አምላክ መሆኑን አናስተውልም፡፡ የጾም ፣ ጸሎት ፣ ስግደት ፣ ምሕላ ጥቅም አይታየንም፡፡ ሌላ
መፍትሔ መፈለግ ነው እንጂ ዝም ብሎ ወደ ሰማይ በማንጋጠጥ ጊዜ ማጥፋት የለብንም እንላለን በሆዳችን፡፡ አፋችን
ግን ለታዛቢ ይጠነቀቃል ስለዚህ ‘ዝም ብሎ መጸለይማ እግዚአብሔርን መፈታተን ነው’ እንላለን፡፡ እነ እገሌ
ቢረዱን ብለን የምናስባቸው ቴልጌልቴልፌልሶሮች ብዙ ናቸው፡፡ ማናቸውም ግን መጥተው ያስጨንቁናል እንጂ
አይረዱንም፡፡ ሰውን ተስፋ ከማድረግ ከጥልቁ ወይም ከከፍታው ምልክትን ብንለምን ጥሩ ነው፡፡

እኛ ባንለምንም ግን እግዚአብሔር ከእኛ ጋር እንደሚሆን እንዲህ ብሎ ተጽፎአል፦

ጌታ ራሱ ምልክትን ይሠጣችኋል ፤ እነሆ ድንግል ትጸንሳለች ወንድ ልጅንም ትወልዳለች ስሙንም አማኑኤል ይሉታል
/ኢሳ 7፡14/

ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ


ታኅሣሥ 24 2012 ዓ ም
ሐዋሳ ፤ ኢትዮጵያ

በውጊያ ላይ የቆሰለ ወታደር ቁስሉ ይድንለት ዘንድ ለሐኪም ማሳየትን አያፍርም፡፡ ንጉሡም ቢሆን ከቁስሉ የዳነን
ወታደር ወደ ሰራዊቱ መልሶ ይቆጥረዋል እንጂ አይተወውም፡፡ እንደዚሁ ሁሉ ጠላታችን ሰይጣን ያገኘው፣ በኃጢአት
የጣለው ሰውም ኃጢአቱን በመናዘዝ የንስሐን መድኃኒት ተቀብሎ መዳንን ማፈር የለበትም፡፡

ቆስሎ ቁስሉን መናገር ያፈረና በቶሎ መድኃኒት ያልተደረገለት ወታደር ቁስሉ ወደ ካንሰር ይለወጥና አመርቅዞ መላ
ሰውነቱን በመምታት ይጎዳዋል፡፡ ጉዳቱን ቶሎ የተናገረ ታማሚ ግን ታክሞ በመዳን ወደ ጦር ሜዳው ይመለሳል፡፡
ቁስሉን ባለመታከሙ ወደ ካንሰር የተለወጠበትና ያመረቀዘበት ሰው ግን ሊድን አይችልምና ወደ ጦር ሜዳው ሊመለስ
አይችልም፡፡

እንደዚሁ ሁሉ በተጋድሎ ውስጥ ያለ ሰው እንደ ወታደር ነው። በተጋድሎ ውስጥ ያለ ሰው በኃጢአት ወድቆ
"በኃጢአት ወድቄአለሁ" ብሎ የተናዘዘ የንስሓን መድኃኒት ያገኛል፡፡ ኃጢአቱን የደበቀ ግን ሊድን አይችልም፡፡
ምክንያቱም ታማሚው መድኃኒት አግኝቶ ከቍስሉ ሁሉ ይድን ዘንድ በሽታውን ሁለት ዲናር ወስዶ ለሚያክመው ባለ
መድኃኒት አልተናገረምና።"

(ቅዱስ አፍርሐት ዘሶርያ - በእንተ ንስሐ ገጽ 52)

የጽሙና ጊዜ አለህ?

| ጃንደረባው ሚድያ | መጋቢት 2016 ዓ.ም.|


✍🏽 ዲያቆን አቤል ካሣሁን እንደ ጻፈው

በጸሎት ጊዜ ሐሳቡ እየተበተነበት የተቸገር አንድ ደቀ መዝሙር ወደ አረጋዊ አባት ሄዶ ስለሆነው ነገር ይነግራቸዋል።
እኛም አረጋዊ ልጁን በምሳሌ ሊያስተምሩት ስለ ፈለጉ ከፊቱ ውኃ አመጡ። ከዚያም በውኃው ላይ ጠጠር
በመወርወር ልክ የሚርገበገብ ሞገድ ሲፈጠር ያን ደቀ መዝሙር ፊቱን በውኃው ውስጥ እንዲያይ ጠየቁት።
ተማሪውም በውኃው ውስጥ ጥላ የሚመስል ነገር እንጂ መልኩን ማየት እንዳልቻለ ነገራቸው። ቀጥለውም አረጋዊው
ውኃው እስኪረጋጋ ጠብቀው "አሁንም መልሰህ ተመልከት?" አሉት። አየ፤ "አሁን ልክ እንደ መስታወት ውኃው ፊቴን
እያሳየኝ ነው" አላቸው። አረጋዊውም "ልጄ ሆይ፣ አንተም እንዲሁ ሂድና ራስህን አረጋጋ። ያን ጊዜ በጸሎትህ ውስጥ
መጽናናትን ታገኛለህ" አሉት። (Paradise of the holy fathers)

የቆርቆሮና የብረት ጩኸት ጋጋታ ባለበት ውብና ለስላሳ የሆነውን የዋሽንት ድምጽ መስማት የሚቻለው ማን ነው?
ሁከትና ረብሻ በሚነግስበት፣ የማይቋረጥ ግፊያና አለመረጋጋት ባለበት የሰዎች ግርግር ውስጥ ሆነህ እንዴት የመንፈስ
ቅዱስን ድምጽ ልትሰማ ትችላለህ? የእግዚአብሔርን ድምጽ በአውሎ ነፋስ ፋጨት፣ በምድር መናወጥ፣
በሚያስገመግም የእሳት ድምጽ ውስጥ አታገኘውም። እርሱ የሚናገረው ከእነዚህ ሁሉ በኋላ በሚሆነው "ትንሽ
የዝምታ" ጊዜ ነው።(1 ኛ ነገ 19፥12)

ልክ የመድኃታችንን የልብሱን ጫፍ በስውር ነክታ ከቁስሏ እንደ ተፈወሰችው ሴት፣ አንተም የነፍስህን ቁስል
ለማድረቅ በመቅደሱ የሞላውን የጌታን የልብሱን ዘርፍ በምሥጢር የምትዳስስበት የብቻ ጊዜ ያስፈልግሃል?

ከእሾህ ወይን ከኩርንችትም በለስ እንደማትለቅም፣ ራስህን ከዚህ ዓለም ሁከት የምትለይበት ጊዜ ሳይኖርህ እውነተኛ
የነፍስ መጽናናትን ልታገኝ አትችልም። ለዚህም ነው ጌታችን በወንጌል "ስትጸልይ ወደ እልፍኝህ ግባ፤ መዝጊያህንም
ዘግተህ በስውር ላለው አባትህ ጸልይ" በማለት ያስተማረን። ላዘነችው ነፍስህ መጽናናትን፣ ለልቡናህ ዕረፍትን
ትፈልጋለህ? ስለ ኃጢአትህ የምታፈሰው የንስሐን እንባስ ትሻለህ? እንግዲያውስ ከሰው ርቀህ በርረህ ወደ ፈጣሪ
የምትሄድበት የጽሙና ጊዜ ይኑርህ።

የእስራኤል ልጆች የመላእክትን እንጀራ የተመገቡት ቆነጃጅቱ በሚዘፍኑበት እና ለጣዖት የሚቀርብ ዳንኪራ በነገሠበት
ግብጽ አይደለም። ሰማያዊውን መና ያገኙት ግብጽን ጥለው ከወጡ በኋላ በበረሃ ሳሉ ነው። አብርሃም ታላቅ ሕዝብ
የሚሆንበትን ጽኑዕ ቃልኪዳን የተቀበለው ያደገበትን አገር እና የአባቱን ቤት ጥሎ በመውጣቱ ነው። አንተስ እንደ
እስራኤል ልጆች መላእክት እንዲመግቡህ፣ እንደ አባታችን አብርሃምስ ታላቅ ሕዝብ መሆን ትፈልጋለህ ?
እንግዲያውስ ዛሬውኑ ከግብጽ የምትሸሽበትን ዕቅድ ያዝ። የአባትህን ቤት ትተህ ለጥቂት ጊዜ ፈቀቅ የምትልበትንም
ገዳም አስስ።

ጌታን ያጠመቀውና ለብዙዎች በብርሃኑ ደስ የሚያሰኝ "የሚነድ መብራት" የነበረው ቅዱስ ዮሐንስ ከዚህ ሁሉ በፊት
ብቻውን ከአምላኩ ጋር በበረሃ ነበር። የሐዲስ ኪዳኑ ባለ ራእይ ቅዱስ ዮሐንስ እነዚያን ሁሉ ሰማያዊ ምሥጢራት
የተመለከተው ብቻውን በፍጥሞ ደሴት ሆኖ ነው። ስሙን በአሕዛብ፣ በነገሥታቱና በእስራኤል ልጆች ሁሉ ፊት
ይሸከም ዘንድ የተመረጠው ቅዱስ ጳውሎስ፣ ከሁሉ አስቀድሞ ግን የመረጠው አምላኩ መንፈሳዊውን ኃይል
ያስታጥቀው ዘንድ የገዛ ድክመቶቹን ተሸክሞ ብቻውን ወደ አረብ በረሃ ገስግሶ ነበር።

ያንተስ እንደ ቅዱስ ዮሐንስ መጥምቅ በመንፈስ የምትጎለምስበት በረሃህ ፣ እንደ ወንጌላዊው ዮሐንስ ጣዕመ
መንግስተ ሰማያትን የምትዘከርበት ፍጥሞ ደሴትህ፣ እንደ ሐዋርያው ጳውሎስ በነፍስ ታድሰህ የምትወጣበት አረባዊ
ገዳምህ የት ነው? መቼ መቼስ ወደዚያ ትወርዳለህ?

+ በራስህ ክፉ ነገር አታድርግ +


ይድረስ ለተከፋኸው ወንድሜ
መኖር ለደከመህ ፣ ሕይወት ለታከተህ ፣ የሚሰማህ ላጣኸው ፣ የሚረዳህ ሰው ላላገኘኸው መከረኛው ወዳጄ!

ከሞት ውጪ ሌላ መፍትሔ አልታይ ካለህ የአንተ ቢጤ መከረኞቹ ጳውሎስና ሲላስ እስር ቤት ውስጥ ሆነው እንዲህ
ይሉሃል::

"በራስህ ክፉ ነገር አታድርግ" ሐዋ. 16:28

አውቃለሁ ዙሪያው ገደል ሆኖብሃል:: ምነው ባልተፈጠርሁ እስክትል ድረስ ተጨንቀሃል::


ግን ይህ ስሜት በአንተ አልተጀመረም:: ሰው ሆኖ ተፈጥሮ ኑሮ ያልመረረው ማን አለ? መሞት ያልተመኘስ ማን አለ?

ሞት ያማረህ አንተን ብቻ መሰለህ?

" ስለ ምን ከማኅፀን አወጣኸኝ? ዓይን ሳያየኝ ምነው በሞትሁ" ያለውን ጻድቅ ኢዮብ አልሰማህም? (ኢዮ. 10:18)

"ከአባቶቼ አልበልጥምና ነፍሴን ውሰድ" ብሎ እንዲሞት የለመነውን ኤልያስን አላየኸውም? 1 ነገሥ. 19:4

ዮናስንስ "አሁንም፥ አቤቱ፥ ከሕይወት ሞት ይሻለኛልና እባክህ፥ ነፍሴን ከእኔ ውሰድ፡ አለው" ሲል አልሰማኸውም?
(ዮናስ 4:3)

ወንድሜ እመነኝ ምክንያቱ ምንም ይሁን ምን መኖር ያላስጠላው ሰው በታሪክ ፈልገህ አታገኝም::

ሞት ሞት የሸተተው ልቡ የተሰበረ ብዙ ነው:: አንተ ላይ ብቻ የደረሰ ልዩ ፈተና የለም:: "ለሰው ሁሉ ከሚሆነው


በቀር ምንም ፈተና አልደረሰባችሁም፤ ነገር ግን ከሚቻላችሁ መጠን ይልቅ ትፈተኑ ዘንድ የማይፈቅድ እግዚአብሔር
የታመነ ነው፥ ትታገሡም ዘንድ እንድትችሉ ከፈተናው ጋር መውጫውን ደግሞ ያደርግላችኋል" ይላል መጽሐፍ::
1 ኛ ቆሮ. 10:13

ምናልባት የልብህን መሰበር የኀዘንህን ጥልቀት አይቶ ምቹ ጊዜ አገኘሁ ብሎ ራስህን እንድትጎዳ ሰይጣን ሊገፋፋህ
ይችላል:: እንዴት እንዲህ ዓይነት ሃሳብ በልቤ ሊመጣ ቻለ ብለህ አትረበሽ:: ሰይጣን ይህንን ክፉ ሃሳብ ላንተ ብቻ
ሳይሆን ለክርስቶስም አቅርቦለታል::

"የእግዚአብሔር ልጅስ ከሆንህ፥ ወደ ታች ራስህን ወርውር" ብሎ ክርስቶስን እንኳን [ማንነቱን ሳያውቅ] ራሱን
እንዲወረውር ሊገፋፋው የሞከረ ደፋር ነው:: የእግዚአብሔር ልጅ የሆነ ሰው ግን ራሱን አይጎዳም:: "ጌታ አምላክህን
አትፈታተነው" "ሒድ አንተ ሰይጣን" ብለህ ሰይጣንን ገሠፀው::

ሰይጣን ክርስቶስን "ከሕንፃ ጫፍ በመወርወር የእግዚአብሔር ልጅ መሆንህን አሳይ" ሲለው ክርስቶስ ሰይጣንን
ሒድልኝ ብሎ በመገሠጹ በክብር ወደ ሰማይ ዐርጎ በእግዚአብሔር ቀኝ ተቀመጠ::
ወንድሜ ሆይ አንተም ሰይጣንን አትስማው ሃሳቡ ራስህን ጎድተህ ከፈጣሪህ እንድትጣላ ሊያደርግህ ነው :: ሰይጣንን
ከገሠጽከው በእግዚአብሔር ቀኝ ከበጎቹ ጋር ትቆማለህ::

አሁን ያለህበት ችግር ያልፋል:: የሚሰማህ ክፉ ስሜት መቼም የማይለወጥ አይምሰልህ:: ኀዘኑም ፣ ብቸኝነቱም ፣
ተስፋ ቢስነቱም ያልፋል:: ጨለማው ይነጋል:: የተዘጋው በር ይከፈታል:: ችግሩ ሲፈታ አንተ ከሌለህ ግን ትርጉም
የለውም::
ስለዚህ ለሚፈታ ችግር የማይቀለበስ ውሳኔ አትወስን:: ራስን ማጥፋት ከጊዜያዊ ችግር ለመሸሽ ሲሉ ዘላቂ ችግር
ውስጥ መግባት ነው:: ጊዜያዊ ሕመምን ለማስታገስ የዘላለም ሕመምን ለምን ትመርጣለህ? "የሞተ ተገላገለ" ሲሉ
ሰምተህ እንዳትታለል ሞት ዕረፍት የሚሆነው ራሱ እግዚአብሔር ሲጠራህ ብቻ ነው::
"እናንተ ደካሞች ሸክማችሁ የከበደ ወደ እኔ ኑ እኔም አሳርፋችኋለሁ " ያለው ጌታ ሳይጠራህ ራስን ማጥፋት የዘላለም
ስቃይ ያመጣል::

ወዳጄ "በራስህ አንዳች ክፉ አታድርግ"

የሕይወትህን ዋጋ ታውቅ ይሆን? አንተ እኮ የእግዚአብሔር ልጅ ለአንተ ሲል የሞተልህ ነህ:: ሊፈውስህ የቆሰለ ፣
ሊያከብርህ የተዋረደ ፣ ሊያረካህ የተጠማ ፣ ሊያለብስህ የተራቆተ ለአንተ እኮ ነው::
ክርስቶስ ስለ አንተ ሞቶአል:: አንተን ግን የጠየቀህ እንድትሞትለት ሳይሆን እንድትኖርለት ነው::
ለሞተልህ አምላክ እንዴት መኖር ያቅትሃል?

ወዳጄ ሆይ ሰውነትህ በአምላክ ደም የተገዛ ክቡር ሰውነት ነው:: አካልህ "አንተ" እንጂ "ያንተ" አይደለም:: "በዋጋ
ተገዝታችኋልና ለራሳችሁ አይደላችሁም፤ ስለዚህ በሥጋችሁ እግዚአብሔርን አክብሩ" ይላል

ስለዚህ በከበረ የእግዚአብሔር ልጅ ደም የተገዛ ሰውነትህን ለሰይጣን በርካሽ አትሽጠው:: አትግደል የሚለው ሕግ
ራስህንም ይጨምራል:: ቤተ መቅደስ የሆነ ሰውነትህን ለማፍረስ አታስብ::
"ማንም የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስ ቢያፈርስ እግዚአብሔር እርሱን ያፈርሰዋል፤ የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ
ቅዱስ ነውና፥ ያውም እናንተ ናችሁ" 1 ኛ ቆሮ. 3:17

ሰዎች አስቀይመውህ ይሆን?

"አሳያቸዋለሁ ፤ ስሞት የእኔን ነገር ይገባቸዋል" ብለህ በሰዎች ተቀይመህ ራስህን አትጉዳ:: እመነኝ ብትሞት ሰዎች
ከሳምንት በላይ አያስታውሱህም:: ለሕይወትህ ዋጋ ያልሠጡ ሰዎች ለሞትህ ዋጋ አይሠጡም :: ፈጥነውም
ይረሱሃል:: ለሚረሱህ ሰዎች ብለህ የማይረሳህን አምላክ አታሳዝን:: ሰው ስለ አንተ ግድ የለውም እግዚአብሔር ግን
የራስህን ጸጉር ሳይቀር በቁጥር ያውቀዋል :: እንኳንስ ራስህን ልትጎዳ አንዲት ጸጉር እንኳን ከአንተ እንድትወድቅ
አይፈልግም::

እግዚአብሔርን በኃጢአት ብታሳዝነው እንኳን ኖረህ ንስሓ እንድትገባ እንጂ እንድትሞት አይፈልግም:: አባትህ ነውና
ከእርሱ ጋር ባትሆንም እንድትኖር ይፈልጋል:: በምሳሌ ልንገርህ :-

ሁለት ሴቶች አንድን ሕፃን "የኔ ልጄ ነው" ብለው እየተከራከሩ ጠቢቡ ሰሎሞን ፊት ቀረቡ:: ጠቢቡ ሰሎሞን ሰይፍ
አመጣና "ልጁን ቆርጬ ለሁለት ላካፍላችሁ" አላቸው:: አንደኛዋ ሴት "እሺ እንካፈል" ስትል እውነተኛዋ እናት ግን
"ልጄ ከሚሞት እርስዋ ትውሰደው" አለች:: እናት መሆንዋም በዚህ ታወቀ::

ወዳጄ ያንተም ኑሮህ ከእግዚአብሔር ጋር ላይሆን ይችላል:: ዓለም የራስዋ አድርጋህም ይሆናል:: በሱስ ውስጥ
ትዘፍቀህ ፣ እንደ ሶምሶን በደሊላ እቅፍ ፣ እንደ ዴማስ በተሰሎንቄ ውበት ተማርከህ ይሆናል :: እግዚአብሔር ግን
አባትህ ነውና ሞትህን አይፈልግም::

"ልጄ ከሚሞት እርስዋ ትውሰደው" እንዳለችው እናት ፈጣሪህ ከነኃጢአትህም ቢሆን እንድትሞት አይፈልግም::
ከእርሱ ጋር ባትኖርም መኖርህን ይፈልጋል:: "የሟቹን ሞት አልፈቅድምና፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር፤ ስለዚህ
ተመለሱና በሕይወት ኑሩ" ሕዝ. 18:32
የይሁዳ ኃጢአቱ ጌታውን መሸጡ አልነበረም:: ራሱን መግደሉ ነው:: እግዚአብሔር የሚያዝነው ከበደልህ በላይ
በእርሱ ተስፋ ቆርጠህ ራስህን ስትጎዳ ነው::

ወዳጄ የአንተን መኖር የሚፈልጉ ብዙ ናቸው:: ፈጣሪ ወደዚህች ዓለም ያለ ምክንያት አላመጣህም:: በአንተ
አለመኖርም የሚጎድል ነገር አለ:: አንተን የሚመስል ሌላ ሰው አልፈጠረምና ለዚህ ዓለም አንተን የሚተካ የለም ::
በክብር ወደዚህ ዓለም ያመጣህ አምላክ በክብር ወደራሱ እስኪወስድህ ድረስ "በራስህ ላይ ክፉ ነገር አታድርግ"

"የወኅኒውም ጠባቂ ከእንቅልፉ ነቅቶ የወኅኒው ደጆች ተከፍተው ባየ ጊዜ፥ እስረኞቹ ያመለጡ መስሎት ራሱን
ይገድል ዘንድ አስቦ ሰይፉን መዘዘ።
ጳውሎስ ግን በታላቅ ድምፅ፦ ሁላችን ከዚህ አለንና በራስህ ክፉ ነገር አታድርግ፡ ብሎ ጮኸ" ሐዋ. 16:27-28

ይህ ሰው እስረኛ ያመለጠ መስሎት ራሱን ሊያጠፋ ሲል ጳውሎስ "ሁላችን ከዚህ አለንና በራስህ ክፉ ነገር አታድርግ "
አለው::

ወዳጄ አንተስ ተስፋ የቆረጥኸው ምን ያመለጠ መስሎህ ነው?

የትምህርት ዕድል ያመለጠህ መስሎህ ነው? ገና ሺህ የትምህርት ዕድሎች አሉህ:: ዕድሜህ ያመለጠህ መስሎህ ነው?
ነገ የሚጠብቁህ ብሩሕ ዘመናት እኮ ቁጭ ብለው አሉ? የሚረዳኝ ሰው የሚያስብልኝ ሰው አጥቼያለሁ? ብለህ
ከሆነም ካልሰሙህ ጥቂቶች በላይ ልንሰማህ የምንሻ "ሁላችን ከዚህ አለንና በራስህ ክፉ ነገር አታድርግ"

መከራ ጸናብኝ ኑሮ ጨለመብኝ የሀገሪቱ ሁኔታ ተስፋ አሳጣኝ ብለህ ይሆን? እኛስ አብረንህ አይደልንም? አብረን
ከገባንበት ችግር አብረን ብንወጣ አይሻልም? ከአንተ በባሰ ሁኔታ የታሰርንና የተገረፍን ጳውሎሶችና ሲላሶች "ሁላችን
በዚህ አለንና በራስህ ክፉ አታድርግ" ስንልህ ስማን::

ይልቅ አንተም እንደ ወኅኒው ጠባቂ "እድን ዘንድ ምን ላድርግ ብለህ?"ነፍስህን የምታድንበትን መንገድ ወደ መቅደሱ
ቀርበህ ጠይቅ::

ወዳጄ ይህንን ጽሑፍ ያነበብኸውም በሕይወት ስላለህ ነው:: የአንተን ዓይን የሚጠብቁ ብዙ ጽሑፎች ፣ የአንተን ጆሮ
የሚፈልጉ ብዙ ድምፆች ፣ የአንተን መሐረብ የሚፈልጉ ብዙ ዕንባዎች ፣ የአንተን ሳቅ የሚፈልጉ ብዙ ቀልዶች ... ገና
ብዙ ብዙ አሉ::

ስለዚህ ሰይጣንን አሳፍረው:: እንዲህ በለው :-

"ጠላቴ ሆይ፥ ብወድቅ እነሣለሁና፥ በጨለማም ብቀመጥ እግዚአብሔር ብርሃን ይሆንልኛልና በእኔ ላይ ደስ አይበልሽ "
ሚክ. 7:8

ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ


ጥቅምት 2016 ዓ.ም.
ሜልበርን አውስትራሊያ

ለተጨነቀች ነፍስ ዕረፍት የሆነው የእግዚአብሔር ቃል ለሁሉ ይዳረስ ዘንድ :: እኔም ለእናንተ ከሰበክሁ በኁዋላ
የተጣልሁ እንዳልሆን አጥብቃችሁ ስለ እኔ ጸልዩልኝ!
በኮሜንት መስጫው ሥር "ለሚሰሙት ጸጋን ይሰጥ ዘንድ፥ እንደሚያስፈልግ ለማነጽ የሚጠቅም ማናቸውም በጎ
ቃል እንጂ ክፉ ቃል ከአፋችሁ ከቶ አይውጣ" (ኤፌ 4:29)
እየጦሙ አለመጦም

ተወዳጆች ሆይ ! እየጦሙ የጦምን ፍሬ ጻማ የማያገኙበት ሁኔታ እንዳለ ታውቁ ዘንድ እወዳለሁ

ይህስ እንደ ምን ነው ያላችሁኝ እንደሆነም :-

💠ከምግበ ሥጋ ተከልክለው ሳለ ከምግበ ኃጢአት ያልተከለከልን እንደሆነ

💠ከጥሉላት ርቀን ሳለ ነዳያንን ያልጎበኘን እንደ ሆነ

💠ወይን ከመጠጣት ታቅበን ሳለ በክፋ መሻት ከመስከር ያልራቅን እንደ ሆነ

💠ጀምበር እስክትጠልቅ ድረስ ከእህል ከውኃ ርቀን ሳለ በዓይናችን መልካም ያልሆኑ ትእይንቶችን ከማየት ያልጦምን
እንደ ሆነ ነው ብዬ በእውነት ያለ ሐሰት እነግራችኋለሁ ።

ስለዚህምእየጦሙ አለመጦምእንዳለ እወቁ : ተረዱም።


ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቂ

+ ኢየሱስ ሆይ ከሀገራችን ሒድልን +

ሰዎች ኢየሱስን በብዙ ምክንያት ለምነውታል:: "ማረኝ" "ዓይኔን አብራልኝ" "ልጄን ፈውስልኝ" "ሙት አስነሣልኝ" ብለው
የጮኹ ብዙዎችናቸው:: የጌርጌሴኖን ሰዎችግን ጌታን በአንድ ላይ ተሰብስበው "ከሀገራቸው እንዲሔድላቸው ለመኑት" ማቴ. 8:34

"ኢየሱስ ሆይ ውጣልን ! : ኢየሱስ ሆይ ሒድልን : ኢየሱስ ሆይ አትድረስብን : ኢየሱስ ሆይ አትምጣብን ! " የሚል
ድምፅ እያሰሙ ተረባረቡበት::

ውጣልን ያሰኛቸው ሁለት ጋኔን የያዛቸውን ሰዎች ከላያቸው አጋንንቱን አውጥቶ ወደ አሳማ መንጋ እንዲገቡ በፈቀደ ጊዜ አጋንንቱ
አሳማዎቹን ወደ ገደል እንዲገቡ ስላደረጉ ነበር::

ጌታችን አጋንንቱ ወደ አሳማ መንጋ እንዲገቡና ገደልም እንዲሰዱአቸው በመተዉ ትልቅ መልእክትን ለሰው ልጅ
አስተላልፎ ነበር::

አጋንንቱ ወደ አሳማው ከመሔዳቸው በፊት ሁለት ሰዎች ላይ ነበሩ :: እነዚያን ሰዎች ላይ ቢቆዩም ግን ሰዎቹን ወደ ገደል
አልከተቱአቸውም:: ልክ አሳማዎቹ ላይ እንደሰፈሩ ግን ወደ ገደል ጨመሩአቸው:: ክርስቶስ በዚህ ያስረዳን "እኔ በቸርነቴ
ባልከለክለው ሰይጣን በእያንዳንዳችሁ ላይ ያለው ዕቅድ በቅጽበት ወደ ገደል እስከ መጨመር የጨከነ ነው " የሚል ነው::
ሰዎቹን ገደል እንዳይሰድ የከለከለው እሱ ነበር:: ዛሬም እኛን ከአፋፉ ላይ ሆነን ወደ ገደል ያልወረድነው "ያልጠፋነው
ከእግዚአብሔር ምሕረት የተነሣ ነው" በተጨማሪም ሰይጣንም እንኳን በሰው ልጅ ላይ ቀርቶ በአሳማ ላይ እንኳን
እንደፈለገ የመስፈር ሥልጣን እንደሌለውም በዚህ ታሪክ ተረዳን::

የጌርጌሴኖን ሰዎች ግማሾቹ ጌታችንን ስለኃይሉ በትሕትና ፈርተውት ግማሾቹ ደግሞ በአሳማዎቹ መሞት ተበሳጭተው ክርስቶስን
ውጣልን አሉት:: ክርስቶስ የሰው ልጅ ከሚሰቃይ ጊዜያዊው ንብረት ቢጠፋ ይሻላል ብሎ ቅድሚያ ሲሠጥ ሰዎቹ ደግሞ ንብረታችን
ከሚወድምሁለቱ ሰዎችጋኔን ቢጫወትባቸው እንመርጣለን ብለው ውጣልን አሉት::

አሣማ ቆሻሻ እንስሳ ነው:: በግእዝ ሕሱምሐሳማማለት አስቀያሚማለት ነው:: ቆሻሻ ወዳዱ ሰይጣን ወደ ማደሪያው ገብቶ
ሕዝቡንም በጌታ ላይ አሳመፀ:: ሕዝቡም ኢየሱስ ሆይ ሒድልን አሉት::
ጌታ ሆይ ከእኛ ጋር እደር ጌታ ሆይ ቶሎ ና ተብሎ ለሚዘመርለት ጌታ ሒድልንን አዜሙለት::

አፍ አውጥተን አንበለው እንጂ እኛም ጌታችንን ብዙ ጊዜ "ሒድልን" ብለነው እናውቃለን::

ወዳጄ አንተስ “ክርስትና በአፍንጫዬ ይውጣ" ብለህ አታውቅም? ያምባይሆን መንፈሳዊ ነገር ማሰብ ወይምመዝሙር መስማት
የማትፈልግበት ቀን ወይም ቃሉን ማዳመጥ የምትሸሽበት ቀን የለም? ዛሬስ ይቅርብኝ ብለህ ከልብህ ሀገር ኢየሱስን
እንዲሔድልህ የለመንክበት ቀን : በቂም በቀል ልብህ ቆስሎ አኩርፈህ የይቅር ባዩን ጌታ ስሙን መስማት የጠላህበት ዕለት
የለም?

ነጋዴው ከንግዱ ላይ ኢየሱስ ዘወር ቢልለት አይጠላም:: ኢየሱስ ከመጣ ገደል የሚጨምራቸው ብዙ ቆሻሻ ሥራዎች
ያሉበት ሰው ጌታን ከሥራው ቦታ ዞር በልልኝይለዋል:: ሌብነት ማሟረት ጥንቆላ ዝሙት ሙስና የሚባሉ አሳማዎችን ገደል እንዳይገቡ
ለመንከባከብ ስንል የናዝሬቱን መድኃኒት ዘወር በልልን ብለን የተማጸንን ብዙዎችነን::

እንደፈለግን ለመኖር ከቆሸሸ አሳማ ጋር ለመዋል መርጠን በሀገራችን ላይ አጋንንት ሲጨፍሩ ሳያስከፋን የጌታችንን መምጣት ግን
ያልፈለግን ብዙዎችነን:: ከእኛ መካከል እንደ አሳማየከፋ ልማዱ እና ሱሱ ወደ ጥልቅ እንዳይወረወርበት ፈርቶ የሚሸሽስንት አለ?
የጌታችንን ቃል ለመስማት የማንፈልግ መንፈሳዊ ነገር ስንሰማ ጆሮአችንን የምንደፍን "ሒድልን እባክህ" ብለን የምንለምን ስንቶች
ነን::

ጌታ ሆይ ክፋትን መርጠን ከሀገራችን ሒድልን ከቀዬያችን ውጣልን ስላልንህ አትቀየመን :: በሽተኛ ሲነጫነጭ ክፉ
የሚያናግረው በሽታው ነው እንደሚባለው ክፉ የሚያናግረን ኃጢአታችን ነውና አትቀየመን:: የኃጢአት ፍቅር እንደ አሣማ ፍቅር
ከባድ ነው:: ሽታው ቢከረፋም እኛ ግን ለምደነዋልና በቀላሉ መላቀቅ አቅቶናል::

አንተ ግን ሒድልን ብንልህም አትስማን:: አሳማ ኃጢአታችንን ከሚፈትኑን አጋንንት ጋር ወደ ጥልቁ ጣልልን:: ያን ጊዜ
ነቢዩ የተናገረው ቃል ይፈጸማል:-

"ተመልሶ ይምረናል፤ ክፋታችንንም ይጠቀጥቃል፥ ኃጢአታችንንም በባሕሩ ጥልቅ ይጥለዋል"


ሚክ 7:19
ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
መጋቢት 20 2013 ዓ ም

ለተጨነቀች ነፍስ ዕረፍት የሆነው የእግዚአብሔር ቃል ለሁሉ ይዳረስ ዘንድ :: እኔም ለእናንተ ከሰበክሁ በኁዋላ
የተጣልሁ እንዳልሆን ስለ እኔ ጸልዩ! በኮሜንት መስጫው ሥር "ለሚሰሙት ጸጋን ይሰጥ ዘንድ፥ እንደሚያስፈልግ
ለማነጽ የሚጠቅም ማናቸውም በጎ ቃል እንጂ ክፉ ቃል ከአፋችሁ ከቶ አይውጣ" (ኤፌ 4:29)

######
ፈረስ የሚጋልብ ሰው ልጓሙን በአግባቡ ካልያዘው በቀር ፈረሱም ጋላቢውም ይጎዳሉ፡፡ አንድ እባብ የነደፈው ሰው
ባለመድኃኒቶችን አግኝቶ መርዙ ወደ ሰውነቱ ኹሉ እንዳይሰራጭ ካላደረገ በቀር ወደ ሞት ሊደርስ ይችላል፡፡
በተመሳሳይ መልኩ አንድ ትንሽ ቁስል በጊዜው ጊዜ ካልታከሙት በቀር ሰፍቶና ተስፋፍቶ ትልቅ ቁስል ወደ መኾን ያድጋል፡፡

በእኛ በክርስቲያኖች ዘንድም እንደዚህ ነው፡ ፡ የኃጢአት ቁስል የሚሰፋው ችላ ሲባል ነው፡ ፡ ገና ትንሽ ነው በሚባልበት ደረጃ
ካላራቅነው በቀር ነገ ከነገ ወዲያ ትልቅ ቁስለ ነፍስ ይኾናል፡ ፡

ተመልከቱ! ዛሬ ላለመቈጣት የሚታገል ሰው ነገ ሰዎችን የሚጎዳበት ዘዴን አይዘይድም፡፡ ሰዎችን የሚጎዳበት ዘዴ


ካልዘየደም ብዙ ባልንጀሮች ይኖሩታል፡ ፡ ብዙ ባልንጀሮች ካሉት የሚጠላቸውም የሚጠሉትም ሰዎች አይኖሩም፡ ፡
ባልንጀራ እንጂ ጠላት የሌለው ሰውም የምግባር ኹሉ ፍጻሜ የኾነውን ፍቅር ገንዘብ ያደርጋል፡፡

ስለዚህ ተወዳጅ ሆይ! ወደዚህ ምግባር ታድግ ዘንድ ወደዚህ እንዳታድግ የሚያደርጉህን ጥቃቅን ኃጢአቶችን ከአንተ
አርቅ፡ ፡ ሰፍቶተስፋፍቶነገ እንዳይቸግርህ ዛሬ በእንጭጩ እያለ ችላ አትበለው፡ ፡

ይሁዳ ገና የገንዘብ ፍቅር ደረጃ ላይ እያለ ራሱን ቢመረምርና ይህን ለማራቅ ቢጥር ኖሮ በኋላ ከተሰበሰበው ገንዘብ ወደ መስረቅ ባላደገ
ነበር፡ ፡ ገና ከመጀመሪያው ደረጃ እያለ ችላ ባይል ኖሮ የኃጢአት ኹሉ ራስ የኾነው ኃጢአት ወደ መፈጸምባልደረሰ ነበር፡ ፡

ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስም እንደዚህ ልናደርግ እንደሚገባን ሲያስተምረን ከዝሙት ብቻ እንድርቅ
ሳይኾን የእርሱ ሥር የኾነውንና አይቶ መመኘትን ችላ ልንለው እንደማይገባን ነገረን (ማቴ.5፡28)፡፡ ኃጢአት ሥር ሰዳና ሰፍታ
ከመቸገራችን በፊት በችግኝ ደረጃ ላይ እያለች ነቅለን መጣል ቀላል ነውና፡፡

#ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ
##################

ሳሙኤል ተመስገን ዘመሰረተ ተዋህዶ ሰ/ት/ቤት:


ሴቲቱ በዮሴፍ ላይ ብዙ ያልተሳካ ሙከራ ካደረገች በኋላ አንድ ቀን ግን ዮሴፍን ሰው በሌለበት መኝታ ቤት አገኘችው።
"ዛሬስ አልለቅህም" ብላ ያዘችው። ዮሴፍ ግን በእሷ እጅ አልወደቀም። ልብሱን ጥሎላት ሸሸ ፣ ወደ ውጪ ወጣ።
የጲጥፋራ ሚስት ዮሴፍ

ን ይዤ አስቀራለሁ ብላ ስትፎክር ልብሱን ብቻ ታቅፋ ቀረች። እፍረቷን መሸከምስላቃታት ዮሴፍ ጥሏት እንደሸሸ ሳይሆን ታማኝነቱን
ትቶእንዳስቸገራት አድርጋ የሐሰት ወሬ ነዛች።

ምስኪኑ ዮሴፍ ከዚህ በኋላ ወደ እስር ቤት ወረደ። በዚያምሳለ ሁለት ጓደኞችአፈራ። ለሁለቱ ጓደኞቹ ሕልምፈቺ ሆነ። አንደኛው
ወደ ሞት ሌላኛው ወደ ሕይወት እንደሚሔዱም እዚያው እያሉ ነገራቸው። ዮሴፍ ጸጋ ነበረውና ያለው ነገር
ተፈጸመ። ይህ ሕልም የመፍታት ጸጋውም ዮሴፍን በግብጽ ከፈርዖን ቀጥሎ እንዲሾም አደረገው። የንጉሥን ሕልም
ፈትቶ ዮሴፍ የራሱን ሕልም እውን አደረገ ፣ ታላቅ ባለ ሥልጣን ሆነ። የግብጽን እህል አከማችቶም ዓለም ሲራብ
እነሱን አጠገበ። ግብፃውያን ዮሴፍን "ጸፍናት ፐዕናህ" (የሕይወት እንጀራ) ብለው ሰየሙት።

አሁን ደግሞ የዮሴፍን ነገር ትተን "የሕይወት እንጀራ እኔ ነኝ" ስላለው ክርስቶስ ወደ መናገር እንመለስ። አብረውት ከታሰሩት
ጓደኞቹ አንዱን "አንተ በሕይወት ትኖራለህ" ብሎ ወደ ቤተ መንግሥት ከላከው ዮሴፍ ይልቅ አብረውት ከተሰቀሉት ሁለት
ወንበዴዎች አንዱን "ዛሬ ከእኔ ጋር በገነት ትሆናለህ" ብሎ ስለተናገረው ጌታ ብንናገር አይሻለንም?

ዮሴፍን የጲጥፋራ ሚስት ልትጥለው ስትታገል እንደኖረች ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስንም ሞት ሊያሸንፈው ብዙ
ታግሎ ነበር። ሞት በክርስቶስ ላይ ዓይኑን የጣለችበት ገና ሲወለድ ነበር። እርሱን ለመጣል በሔሮድስ በኩል ሞት
ስትታገል ብዙ ሕጻናትን ፈጀች ፣ መሲሑን ግን አላገኘችውም። ዲያቢሎስም ክርስቶስ በሞት እንዲሸነፍ በግልጽ አባብሎታል።
"የእግዚአብሔር ልጅስ ከሆንህ፥ ወደ ታችራስህን ወርውር አለው።" (ማቴ 4:6) ግን አልተቀበለውም።

ሞት ጌታችንን ለማሸነፍ ከጲጥፋራ ሚስት በላይ ብዙ ታገለች። ወንጌሉ እንዲህ ይላል:

" ስለዚህ ሊወግሩት ድንጋይ አነሡ፤ ኢየሱስ ግን ተሰወራቸው ከመቅደስምወጥቶበመካከላቸው አልፎ ሄደ።" (ዮሐ. 8:59)

" አይሁድ ሊወግሩት ደግመው ድንጋይ አነሡ።" (ዮሐ 10:31)

የጲጥፋራ ሚስት ዮሴፍን በመኝታ ክፍል እስክታገኘው ድረስ ልትይዘው እንኳን እንዳልተቻላት ሞትም ክርስቶስን ልትይዘው
አልተቻላትምነበር ፣ አንድ ቀን ግን በመኝታ አገኘችው። የምን መኝታ?

ወደ ሌላ ጥቅስ እንሒድ ፣ በትንሣኤ ዕለት የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን የምትሰብከውን የመዝሙረ ዳዊት ምስባክ
እናስታውስ። "እግዚአብሔር ከእንቅልፍ እንደሚነቃ ተነሣ ..." (ወተንሥአ እግዚአብሔር ከመ ዘንቃህ እም ንዋም) ብሎ
ይጀምራል። (መዝ 77) የክርስቶስ ሞት በእንቅልፍ ተመስሏል ማለት ነው። ደራሲውም "ከመ አንበሳ ተንሣእከ እምክቡድ ንዋምከ"
(ከከባድ እንቅልፍህ እንደ አንበሳ ተነሣህ) ይላል። በመጽሐፍ ቅዱስ ሞት እንቅልፍ ለመባሉ "ወዳጃችን አልዓዛር ተኝቷል"
"ከአባቶቹ ጋር አንቀላፋ" "አንቀላፍተው ስላሉት እንዳታዝኑ" "አያሌዎች አንቀላፍተዋል" የሚሉ ብዙ ጥቅሶችን ማስረጃ
ማድረግ ይቻላል። የጌታችን ሞት እንቅልፍ ከተባለ መቃብር ምንድር ነው??? .... አዎን መኝታ ቤት ነው።

የጲጥፋራ ሚስት ልትይዘው ያልቻለችውን ዮሴፍ በመኝታ ቤት እንደያዘችው ጌታን ለመያዝ ብዙ የሞከረችው ሞትም በመጨረሻ
በመኝታ ቤት በሚመሰል መቃብር አገኘችው። የጲጥፋራ ሚስት ዮሴፍን አገኘሁህ ብላ እዚያው ይዛ ልታስቀረው ስትደሰት ልብሱን
ጥሎላት ሸሸ ፣ ወደ ውጪምወጣ።

መድኃኒታችንም ሞት ይዛ እንድታስቀረው እጁን አልሰጣትም። የመግነዙን ልብስ ጥሎላት ከመቃብሩ ወጣ። ሞት እንደ ጲጥፋራ
ሚስት ጨርቅ ታቅፋ ውርደት ተከናነበች። እኛም "ሞት ሆይ መውጊያህ የታለ?" እያልን በሞት ላይ ተዘባበትን። ቅዱስ
ኤፍሬም እንዳለው "ዮሴፍ በባልና ሚስቱ እልፍኝ ውስጥ የኃጢአትን ኃይል እንደበጣጠሰ የነፍሳችን መድኃኒት ጌታችንም በክንዱ
የሞትን ኃይል አጠፋ"

ከእፍረቷ በኋላ የሐሰት ወሬ አስወርታ የዮሴፍን ስምልታጠፋ እንደሞከረችው ሴት ሞትንምጌታ ድል አድርጓት በሥልጣኑ መግነዙን
ትቶ ሲነሣ "ሐዋርያት ሰርቀውት ነው ፣ ደብቀውታል ፣ ሌባ ወስዶታል ፣ አውሬ በልቶታል " እያለችትንሣኤውን ልትሸሽግ ሞከረች፣
የትንሣኤው ብርሃን ግን ለሁላችን አበራ።

ዮሴፍ በግብጽ ከተሾመ በኋላ ወንድሞቹ ምግብ ሊገዙ ወደ እርሱ መጡ። ማንነቱን ግን አላወቁም። አልፈው ተርፈው
ስለ ቤተሰባቸው ሲጠይቃቸው "ዮሴፍ የሚባል ወንድማችን ነበር ፣ ሞቷል" ብለው ነግረውት አረፉ። ለቀባሪው ሳይሆን
ለሟቹ አረዱት። እሱ ግን ቢረሱትም አልረሳቸውም። ቀስ ብሎ ማንነቱን ገለጸላቸው። ወንድማችሁ ነኝ ብሎ እጁን
ዘረጋላቸው። ከብበው አዩት ፣ እርሱም በይቅርታ ተቀበላቸው። ይህ ክስተት ደግሞ ወደ ኤማሁስ መንገደኞች
ይመራናል።

ጌታችን በተነሣበት በዕለተ እሑድ ተስፋ ቆርጠው ሁለት አርድእት ወደ ኤማሁስ መንደር ጉዞ ጀምረው ነበር።
ጌታችን አብሯቸው ሲሔድ ግን አላወቁትም። "እየጠወለጋችሁ ስትሔዱ የምትነጋገሩት ምንድር ነው?" አላቸው።
እነርሱም "በኢየሩሳሌምእንግዳ ነህን?" ብለው ወግ ጀመሩ። የጌታችንን ተሰቅሎ መሞት ለራሱ ለጌታችን ነገሩት። (ሉቃ 24)

እርሱ ግን አልተቆጣም አንድ በአንድ ገለጸላቸው። እንደ ዮሴፍ ሁሉንም ደቀ መዛሙርቱን በፍቅር ተቀበላቸው። "ወደ እኔ ኑ ፣
በችንካሬ ውስጥ እጃችሁን አግቡ" አላቸው። (Fr Athanasius Iskander : Christ in the old testament)
ዮሴፍ ወንድሞቹን እንዳልወቀሳቸው ጌታም ጥለውት የተበተኑትን ሐዋርያት አልወቀሳቸውም። እኛንም እንዲሁ
አይቀየመንም ፣ ዮሴፍ ተቆጥቶ ከተናገረ በኋላ ለሞት እንዳልሰጣቸው ራሱም ወደ ጓዳ ሔዶ ያለቅስ እንደነበር
መድኃኔዓለም ክርስቶስም በቁጣው ውስጥ ርኅራኄ አለ። " መገሠጽስ እግዚአብሔር ገሠጸኝ፤ ለሞት ግን አልሰጠኝም።" (መዝ
118:18)

ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ

"ከቶ ወልዳ ላልሳመቻቸው ልጆቿ ራሔል የምታለቅስ ከኾነ እንደ ሰው አቅፋ ለተሸከመችው( ላሳደገችው ) ልጇ ድንግል እንዴት
አታለቅስ?" ላሐ ማርያም
######
ሳሙኤል ተመስገን ዘመሰረተ ተዋህዶ ሰ/ት/ቤት:
+ ወደ ኖኅ መርከብ ለመጨረሻ ጊዜ የገባችው እንስሳ +

የኖኅ መርከብ ጉዳይ በጣም አስገራሚ ከሚሆኑብኝ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች አንዱ ነው:: በዓለማችን አሁን ያሉ
እንስሳት ሁሉ "ከነ ባለቤትዎ" እንዲገኙልን እንደሚባልበት ሰርግ ጥንድ ጥንድ ሆነው የገቡባት ትልቅ መርከብ ታሪክ :
ዳግም ለሰው ልጆች ወላጆች ለመሆን የተመረጡ አራት ወንዶችና አራት ሴቶች ብቻ የተሳፈሩባት ትልቅ መርከብ
ሁኔታ ትኩር ብሎ ላየው አስገራሚ እውነቶችን ያዘለ ነው::

ከሁሉም በላይ ግን መርከቢቱ የቤተ ክርስቲያን ምሳሌ መሆንዋ ብዙ ነገር እንድናስብ ያግዘናል:: ቅዱስ ዮሐንስ
አፈወርቅ "ወደ ኖኅ መርከብ ተኩላ ገብቶ ሲወጣም ተኩላ ሆኖ ይወጣል:: ወደ ቤተክርስቲያን ግን ተኩላ ሆነው
ገብተው በግ ሆነው የወጡ ብዙዎች ናቸው" ብሎአል::

እውነትም ቤተ ክርስቲያን ወደ እርስዋ የገቡትን መለወጥ የምትችል መርከብ ናት :: ወደ ቤተ ክርስቲያን እንደ ጅብ


ሆዳም ሆነው ገብተው ጾመኞች ሆነው የወጡ አሉ :: እንደ የሌሊት ወፍ በቀን መኖር አቅቶአቸው ሌሊቱን የልባቸው
ዓይን ታውሮ በኃጢአት ጨለማ ሲደናበሩ የኖሩ ሰዎች ወደ መርከቢቱ ገብተው እንደ ንስር አርቀው አጥርተው ቀኑን
የሚያዩ ሆነዋል:: ቤተ ክርስቲያን ወደ እርስዋ የገቡትን የምትለውጥ መርከብ ናት:: ውኃ ወደ እርስዋ ሲገባ ጠበል
ይሆናል:: አፈር ወደ እርስዋ ሲገባ እምነት (እመት) ይሆናል:: ዘይት ወደ እርስዋ ሲገባ ቅዱስ ቅባት ይሆናል:: ኅብስትና
ወይን ወደ እርስዋ ሲገባ ወደ ቅዱስ ቁርባን ይለወጣል::

ወደ ቤተ ክርስቲያን ገብቶ ያልተለወጠ ሰው ግን ሲገባም ጅብ ሲወጣም ጅብ ሆኖአል:: ኖኅ ከመርከብ መልእክት ልኮት


የቀረው የቁራ ነገርስ? ከቤተ ክርስቲያን ወጥተው ስንቶች በዚያው ቀርተዋል? ለዓለም ጨው እንዲሆኑ ተልከው
በዚያው ሟሙተው የቀሩ ስንት አሉ:: ርግብ ግን ማረፊያ ስታጣ ተመልሳ ነበር:: ከመርከቢቱ የራቅን ሁላችን "ልባችን
በእግዚአብሔር እስካላረፈ ድረስ ዕረፍት የለውም" እንዳለ ሊቁ ወደ መርከቢቱ ፈጥነን መመለስ አለብን::

ሰሞኑን ደግሞ አንድ ጥያቄ በአእምሮዬ ተመላለሰብኝ:: "ወደ ኖኅ መርከብ ለመጨረሻ ጊዜ የገባው እንስሳ ማን ሊሆን
ይችላል?" የሚል:: ይህን ጥያቄ በግልም በጉባኤ ላይም ሰዎችን ጠይቄ ነበር:: መቼም ለዚህ ጥቅስ አያስፈልገውም::
ኖኅ ቆሞ እንስሳቱ እስኪገቡ ድረስ እንደጠበቀና ማንንም እንስሳ ጥሎ እንዳልገባ የታወቀ ነው::
በዚህ ምክንያት እንስሳቱ ወደ መርከቢቱ የሚገቡት እንደደረሱበት ቅደም ተከተል ነው:: ክንፍ ያላቸው በርረው
ቀድመው ይገባሉ:: እንደ ጥንቸል እንደ ካንጋሮ እንደ ሚዳቁዋ ያሉትም እየዘለሉ ፈጥነው ይገባሉ::

ወደ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ነፍሳቸውን ለማዳን ፈጥነው በርረው የገቡ እንደ ሚዳቋ ዘልለው የደረሱ ብርቱዎች
አሉ:: እንደ ፒኮክ ያሉ ባለ ውብ ክንፎች : እንደ ቀጭኔ ያሉ ባለ ረዥም አንገቶች እንደ ጃርት ያሉ ሌላው ላይ
የሚሰኩት እሾኽ የለበሱ እንስሳት ወደ መርከብዋ ገብተዋል :: በቤተክርስቲያን እንደ ፒኮክ አምሮ መታየት መዘባነን
የሚወዱ ለታይታ የሚገዙ ብዙዎች ገብተዋል:: እንደ ቀጭኔ አንገታቸውን ከፍ አድርገው ሰውን ቁልቁል
የሚመለከቱና "አንገታቸውን እንደሚያገዝፉ የዕብራውያን ሴቶች" ዓይነት ሕይወት ያላቸውም ገብተዋል:: እንደ
ጃርት በክፉ ንግግር የሰው ልብ ላይ የሚሰኩት ጥላቻ የተላበሱ ሰዎችም ገብተዋል:: የኖኅ መርከብ ያልያዘችው እንስሳ
እንደሌለ ቤተ ክርስቲያንም ያልተሸከመችው ዓይነት ሰው የለም::

ወደ ጥያቄው ስመለስ በእኔ ግምት ወደ መርከቡ በጣም ዘግይታ የገባችው ኤሊ ነበረች :: በላይዋ ድንጋይ የተጫናት
እጅግ ቀርፋፋዋ ኤሊን የማይቀድም እንስሳ መቼም አይኖርም:: ምንም ብትዘገይም ኖኅ እስከመጨረሻው ጠብቆ
አስገብቶ ለዘር አትርፎአታል:: የኤሊ ዘሮችም "ኖኅ ዘርን ባያስቀርልን ኖሮ እንደ ዳይኖሰር በጠፋን ነበር" ብለው ኖኅን
ማመስገናቸው አይቀርም:: እግዚአብሔር ምንም ብትዘገይ ኤሊ ሳትገባ መርከቡን አልዘጋውም::

የኤሊ በመርከቡ መትረፍ በቤተ ክርስቲያን ልንተርፍ ተስፋ ለምናደርግ ለእኛ ትልቅ መጽናኛችን ነው::

ወዳጄ ወደ ቤተ ክርስቲያን ለመምጣት እንደ ወፍ ትበርራለህ? እንደ ሚዳቋ ትዘልላለህ? ወይንስ እንደ ኤሊ
ትጎተታለህ? እግሮችህ ለመንፈሳዊ ነገር ሲሆን አቅም እያጡ አልተቸገርህም?
ልብህ ቢፈልግም እንደ ኤሊዋ የተጫነህ የኃጢአት ድንጋይ አላንቀሳቅስ ብሎህ አልዘገየህም?

እንዲህ ከሆነ አትጨነቅ መርከብዋ ቤተ ክርስቲያን አንተን ሳትይዝ ጥላህ ወዴትም አትሔድም :: ጉዞህን እስካላቆምህ
ድረስ ትጠብቅሃለች:: እየተጎተትህም እየተሳብህም ቢሆን አንተ ብቻ ወደ ደጁ ገስግስ::
አንተ ብቻ መንገድ ጀምር እንጂ ፈጣሪ በሩን የሚዘጋው አንተ እስክትገባ ጠብቆ ነው::

ከቅዱስ ኤፍሬም ጋር እንዲህ ብለህ ለምነው :-


"ብበድልህም እንኳን አሁንም በርህን እያንኳኳሁ ነው:: እየተጎተትሁም ቢሆን አሁንም የምጉዋዘው ወደ አንተ
ለመምጣት ነው"

ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ


ሚያዝያ 5 2013 ዓ ም

ለተጨነቀች ነፍስ ዕረፍት የሆነው የእግዚአብሔር ቃል ለሁሉ ይዳረስ ዘንድ :: እኔም ለእናንተ ከሰበክሁ በኁዋላ
የተጣልሁ እንዳልሆን አጥብቃችሁ ስለ እኔ ጸልዩልኝ!
በኮሜንት መስጫው ሥር "ለሚሰሙት ጸጋን ይሰጥ ዘንድ፥ እንደሚያስፈልግ ለማነጽ የሚጠቅም ማናቸውም በጎ ቃል እንጂ ዋጋን
በምድር የሚያስቀር ውዳሴምሆነ ሌላ ክፉ ቃል ከአፋችሁ ከቶአይውጣ" (ኤፌ 4:29)

ይህንን የመሰለ ሕንፃ ቤተ መቅደስ 👇


• መቅደስ ቢኖረውምይጎበኛል እንጂ አይቀደስበትም
• አሁን ምዩዚዬም ነው
• ሁሉ ተሟልቶየተሠራለት ቢሆንምአምልኮ አይፈጸምበትም
• መጠመቂያ ቢኖረውምየሚጠመቅበት የለም
ምክንያቱም የሀገሩ ሰዎች ሃይማኖታቸውን ትተዋል ሃይማኖት አልባ ሆነዋል ....ከሃይማኖት ባዶ መሆናቸውን በኩራት
ያስጎበኛሉ...የካቴድራሉን ሕንጻ ከአገልግሎት ባዶ መሆኑን በኩራት ይናገራሉ!!!!
እኛምይህንን አይተን ጎብኝተን ስለ ራሳችን
• ሀገር
• ሃይማኖት
• ቤተ ክርስቲያን
• ባህል ...ተነጋግረን ከመቅደሱ ወጣን
እኔምይህንን ቃል አስቤ አዘንኩ 👇
ማቴዎስ 23
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
³⁸ እነሆ፥ ቤታችሁ የተፈታ ሆኖ ይቀርላችኋል።
³⁹ እላችኋለሁና፥ በጌታ ስምየሚመጣ የተባረከ ነው እስክትሉ ድረስ ከእንግዲህ ወዲህ አታዩኝም።"

👉እንደ አማኝና አገልጋይ ሁሌምየሚሰማኝይህ ነው !

ወደፊት የሚመጣው ትውልድ ቤተክርስቲያኗን ከነሥርዓቷ በምን ያህል መጠን ይረከባታል?

እኛ ስለ ዘርና ስለ ብሔር ስለ ሥልጣንና ሢመት ስለ ገንዘብና ኑሮ ስናስብ ትውልዱን ከእጃችን እየተቀማን ቤተ ክርስቲያንን ዝቅ
አድርገን የኛን ልዕልና ብቻለማሳየት እየተጋን የት እንደርስ ይሆን?....

የቤተ ክርስቲያን አምላክ ትውልዳችንን በሃይማኖት ያጽናልን ይጠብቅልን


ተረካቢ አያሳጣን!!!!

መጋቤ ሐዲስ ነቅዐጥበብ ከፍያለው

ከ ኖርዌይ ትሮንዳሂም
ግንቦት 5 /2016 ዓ.ም
##########
ሳሙኤል ተመስገን ዘመሰረተ ተዋህዶ ሰ/ት/ቤት:
ከእለታት አንድ ቀን አንድ አባት ወደ አባታችን አባ መቃርዮስ በኣት ሄደና "አባቴ ሆይ ድኅነትን አገኝ ዘንድ ምን ላድርግ?" ሲል
ጥያቄ አቀረበላቸው። አባታችንምእንዲህ በማለት አሉት።
"ወደ መቃብር ሂድና ሙታንን ሰድበሃቸው ና" አሉት። ይህ አባትም የተባለውን አድርጎ ተመለሰ። አባታችንም "ምን
አሉህ?" ሲሉ ጠየቁት። ሰውየዉም "ምንም አልመለሱልኝም" ሲል መለሰ። አባ መቃርዮስም "አሁን ደግሞ ሂድና
ሙታንን አመስግናቸው" አሉት። ሄዶም አመሰገናቸው። "አሁንስ ምን አሉህ" ሲል በድጋሚ ጠየቁት። ሰውዬም
"ምንም አልመለሱልኝም" ሲል መለሰ። አባታችን አባ መቃርዮስም: "ስትሰድባቸው ፤ስታመሰግናቸው እና ስታወድሳቸው
ምንም አልመለሱም፤ አንተም ለነፍስህ ድህነትን ከፈለግህ እንደሞተ ሰው ሆነህ ኑር። ሰዎች ክፉ ቢያደርጉብህም፣ ቢያመሰግኑህም
ምንምአይሰማህ" አሉት።

+ ወደ ኖኅ መርከብ ለመጨረሻ ጊዜ የገባችው እንስሳ +

የኖኅ መርከብ ጉዳይ በጣም አስገራሚ ከሚሆኑብኝ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች አንዱ ነው:: በዓለማችን አሁን ያሉ
እንስሳት ሁሉ "ከነ ባለቤትዎ" እንዲገኙልን እንደሚባልበት ሰርግ ጥንድ ጥንድ ሆነው የገቡባት ትልቅ መርከብ ታሪክ :
ዳግም ለሰው ልጆች ወላጆች ለመሆን የተመረጡ አራት ወንዶችና አራት ሴቶች ብቻ የተሳፈሩባት ትልቅ መርከብ
ሁኔታ ትኩር ብሎ ላየው አስገራሚ እውነቶችን ያዘለ ነው::

ከሁሉም በላይ ግን መርከቢቱ የቤተ ክርስቲያን ምሳሌ መሆንዋ ብዙ ነገር እንድናስብ ያግዘናል:: ቅዱስ ዮሐንስ
አፈወርቅ "ወደ ኖኅ መርከብ ተኩላ ገብቶ ሲወጣም ተኩላ ሆኖ ይወጣል:: ወደ ቤተክርስቲያን ግን ተኩላ ሆነው
ገብተው በግ ሆነው የወጡ ብዙዎች ናቸው" ብሎአል::

እውነትም ቤተ ክርስቲያን ወደ እርስዋ የገቡትን መለወጥ የምትችል መርከብ ናት :: ወደ ቤተ ክርስቲያን እንደ ጅብ


ሆዳም ሆነው ገብተው ጾመኞች ሆነው የወጡ አሉ :: እንደ የሌሊት ወፍ በቀን መኖር አቅቶአቸው ሌሊቱን የልባቸው
ዓይን ታውሮ በኃጢአት ጨለማ ሲደናበሩ የኖሩ ሰዎች ወደ መርከቢቱ ገብተው እንደ ንስር አርቀው አጥርተው ቀኑን
የሚያዩ ሆነዋል:: ቤተ ክርስቲያን ወደ እርስዋ የገቡትን የምትለውጥ መርከብ ናት:: ውኃ ወደ እርስዋ ሲገባ ጠበል
ይሆናል:: አፈር ወደ እርስዋ ሲገባ እምነት (እመት) ይሆናል:: ዘይት ወደ እርስዋ ሲገባ ቅዱስ ቅባት ይሆናል:: ኅብስትና
ወይን ወደ እርስዋ ሲገባ ወደ ቅዱስ ቁርባን ይለወጣል::

ወደ ቤተ ክርስቲያን ገብቶ ያልተለወጠ ሰው ግን ሲገባም ጅብ ሲወጣም ጅብ ሆኖአል:: ኖኅ ከመርከብ መልእክት ልኮት


የቀረው የቁራ ነገርስ? ከቤተ ክርስቲያን ወጥተው ስንቶች በዚያው ቀርተዋል? ለዓለም ጨው እንዲሆኑ ተልከው
በዚያው ሟሙተው የቀሩ ስንት አሉ:: ርግብ ግን ማረፊያ ስታጣ ተመልሳ ነበር:: ከመርከቢቱ የራቅን ሁላችን "ልባችን
በእግዚአብሔር እስካላረፈ ድረስ ዕረፍት የለውም" እንዳለ ሊቁ ወደ መርከቢቱ ፈጥነን መመለስ አለብን::

ሰሞኑን ደግሞ አንድ ጥያቄ በአእምሮዬ ተመላለሰብኝ:: "ወደ ኖኅ መርከብ ለመጨረሻ ጊዜ የገባው እንስሳ ማን ሊሆን
ይችላል?" የሚል:: ይህን ጥያቄ በግልም በጉባኤ ላይም ሰዎችን ጠይቄ ነበር:: መቼም ለዚህ ጥቅስ አያስፈልገውም::
ኖኅ ቆሞ እንስሳቱ እስኪገቡ ድረስ እንደጠበቀና ማንንም እንስሳ ጥሎ እንዳልገባ የታወቀ ነው::
በዚህ ምክንያት እንስሳቱ ወደ መርከቢቱ የሚገቡት እንደደረሱበት ቅደም ተከተል ነው:: ክንፍ ያላቸው በርረው
ቀድመው ይገባሉ:: እንደ ጥንቸል እንደ ካንጋሮ እንደ ሚዳቁዋ ያሉትም እየዘለሉ ፈጥነው ይገባሉ::

ወደ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ነፍሳቸውን ለማዳን ፈጥነው በርረው የገቡ እንደ ሚዳቋ ዘልለው የደረሱ ብርቱዎች
አሉ:: እንደ ፒኮክ ያሉ ባለ ውብ ክንፎች : እንደ ቀጭኔ ያሉ ባለ ረዥም አንገቶች እንደ ጃርት ያሉ ሌላው ላይ
የሚሰኩት እሾኽ የለበሱ እንስሳት ወደ መርከብዋ ገብተዋል :: በቤተክርስቲያን እንደ ፒኮክ አምሮ መታየት መዘባነን
የሚወዱ ለታይታ የሚገዙ ብዙዎች ገብተዋል:: እንደ ቀጭኔ አንገታቸውን ከፍ አድርገው ሰውን ቁልቁል
የሚመለከቱና "አንገታቸውን እንደሚያገዝፉ የዕብራውያን ሴቶች" ዓይነት ሕይወት ያላቸውም ገብተዋል:: እንደ
ጃርት በክፉ ንግግር የሰው ልብ ላይ የሚሰኩት ጥላቻ የተላበሱ ሰዎችም ገብተዋል:: የኖኅ መርከብ ያልያዘችው እንስሳ
እንደሌለ ቤተ ክርስቲያንም ያልተሸከመችው ዓይነት ሰው የለም::

ወደ ጥያቄው ስመለስ በእኔ ግምት ወደ መርከቡ በጣም ዘግይታ የገባችው ኤሊ ነበረች :: በላይዋ ድንጋይ የተጫናት
እጅግ ቀርፋፋዋ ኤሊን የማይቀድም እንስሳ መቼም አይኖርም:: ምንም ብትዘገይም ኖኅ እስከመጨረሻው ጠብቆ
አስገብቶ ለዘር አትርፎአታል:: የኤሊ ዘሮችም "ኖኅ ዘርን ባያስቀርልን ኖሮ እንደ ዳይኖሰር በጠፋን ነበር" ብለው ኖኅን
ማመስገናቸው አይቀርም:: እግዚአብሔር ምንም ብትዘገይ ኤሊ ሳትገባ መርከቡን አልዘጋውም::

የኤሊ በመርከቡ መትረፍ በቤተ ክርስቲያን ልንተርፍ ተስፋ ለምናደርግ ለእኛ ትልቅ መጽናኛችን ነው::

ወዳጄ ወደ ቤተ ክርስቲያን ለመምጣት እንደ ወፍ ትበርራለህ? እንደ ሚዳቋ ትዘልላለህ? ወይንስ እንደ ኤሊ
ትጎተታለህ? እግሮችህ ለመንፈሳዊ ነገር ሲሆን አቅም እያጡ አልተቸገርህም?
ልብህ ቢፈልግም እንደ ኤሊዋ የተጫነህ የኃጢአት ድንጋይ አላንቀሳቅስ ብሎህ አልዘገየህም?

እንዲህ ከሆነ አትጨነቅ መርከብዋ ቤተ ክርስቲያን አንተን ሳትይዝ ጥላህ ወዴትም አትሔድም :: ጉዞህን እስካላቆምህ
ድረስ ትጠብቅሃለች:: እየተጎተትህም እየተሳብህም ቢሆን አንተ ብቻ ወደ ደጁ ገስግስ::
አንተ ብቻ መንገድ ጀምር እንጂ ፈጣሪ በሩን የሚዘጋው አንተ እስክትገባ ጠብቆ ነው::

ከቅዱስ ኤፍሬም ጋር እንዲህ ብለህ ለምነው :-


"ብበድልህም እንኳን አሁንም በርህን እያንኳኳሁ ነው:: እየተጎተትሁም ቢሆን አሁንም የምጉዋዘው ወደ አንተ
ለመምጣት ነው"

ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ


ሚያዝያ 5 2013 ዓ ም
ለተጨነቀች ነፍስ ዕረፍት የሆነው የእግዚአብሔር ቃል ለሁሉ ይዳረስ ዘንድ :: እኔም ለእናንተ ከሰበክሁ በኁዋላ
የተጣልሁ እንዳልሆን አጥብቃችሁ ስለ እኔ ጸልዩልኝ!
በኮሜንት መስጫው ሥር "ለሚሰሙት ጸጋን ይሰጥ ዘንድ፥ እንደሚያስፈልግ ለማነጽ የሚጠቅም ማናቸውም በጎ ቃል እንጂ ዋጋን
በምድር የሚያስቀር ውዳሴምሆነ ሌላ ክፉ ቃል ከአፋችሁ ከቶአይውጣ" (ኤፌ 4:29)

ይህንን የመሰለ ሕንፃ ቤተ መቅደስ 👇


• መቅደስ ቢኖረውምይጎበኛል እንጂ አይቀደስበትም
• አሁን ምዩዚዬም ነው
• ሁሉ ተሟልቶየተሠራለት ቢሆንምአምልኮ አይፈጸምበትም
• መጠመቂያ ቢኖረውምየሚጠመቅበት የለም
ምክንያቱም የሀገሩ ሰዎች ሃይማኖታቸውን ትተዋል ሃይማኖት አልባ ሆነዋል ....ከሃይማኖት ባዶ መሆናቸውን በኩራት
ያስጎበኛሉ...የካቴድራሉን ሕንጻ ከአገልግሎት ባዶ መሆኑን በኩራት ይናገራሉ!!!!
እኛምይህንን አይተን ጎብኝተን ስለ ራሳችን
• ሀገር
• ሃይማኖት
• ቤተ ክርስቲያን
• ባህል ...ተነጋግረን ከመቅደሱ ወጣን
እኔምይህንን ቃል አስቤ አዘንኩ 👇
ማቴዎስ 23
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
³⁸ እነሆ፥ ቤታችሁ የተፈታ ሆኖ ይቀርላችኋል።
³⁹ እላችኋለሁና፥ በጌታ ስምየሚመጣ የተባረከ ነው እስክትሉ ድረስ ከእንግዲህ ወዲህ አታዩኝም።"

👉እንደ አማኝና አገልጋይ ሁሌምየሚሰማኝይህ ነው !

ወደፊት የሚመጣው ትውልድ ቤተክርስቲያኗን ከነሥርዓቷ በምን ያህል መጠን ይረከባታል?

እኛ ስለ ዘርና ስለ ብሔር ስለ ሥልጣንና ሢመት ስለ ገንዘብና ኑሮ ስናስብ ትውልዱን ከእጃችን እየተቀማን ቤተ ክርስቲያንን ዝቅ
አድርገን የኛን ልዕልና ብቻለማሳየት እየተጋን የት እንደርስ ይሆን?....

የቤተ ክርስቲያን አምላክ ትውልዳችንን በሃይማኖት ያጽናልን ይጠብቅልን


ተረካቢ አያሳጣን!!!!

መጋቤ ሐዲስ ነቅዐጥበብ ከፍያለው

ከ ኖርዌይ ትሮንዳሂም
ግንቦት 5 /2016 ዓ.ም

በቦታህ መምህር፤ ያለቦታህ ደግሞተማሪ ሁን››

መጋቤ ሐዲስ እሸቱ


...
በወጣትነት ሁሉምነገር ትክክል ነው ከሚል መመሪያ
ውጣ፤ ሁሉንምካላየሁ አላምንምአትበል። ሰምቶማመን፣ ከተጎዱት መማር አስተዋይነት መሆኑን አትርሳ። የሰማንያ ዓመት ዕውቀትን
ለመገብየት ግድ ሰማንያ ዓመት መኖርየለብህም። ሰማንያ ዓመት ከኖሩት በትሕትና መጠየቅ ይገባሃል።

ምክርን ብትሰማ በነጻ ትማራለህ። ምክርን አልሰማ ብትል ግን በዋጋ እንደምትማር እወቀው። በዋጋ መማር ግን አድካሚ ደግሞም
የሚያስመርር ነው። ብልህ ከሆንህ በሰው ከደረሰው ትማራለህ፣ ሞኝከሆንህ ግን በራስህ ሲደርስ ትማራለህ።
---
የታየህን አሳይ፣ ያልታየህን አጥራው። በደንብ
ያልተረዳኸውን አታስተምረው። ያልቀመስከውን ለሰው
አትጋብዝ። የሰማኸውን ሁሉ አትመን። ያየኸውን ሁሉ
ስጡኝ፣ የተናገርከውን ሁሉ ፈፅሙ አትበል። የሰጠኸውን እርሳ እንጂ አታውራ። ፍፃሜውን ሳታይ ምስጋና አታብዛ። ቀኑ ሳይመሽቀኑ
ጥሩ ነው አትበል።

ገንዘብ የሚመልሰው የገንዘብን ጥያቄ ብቻ ነውና ሁሉንም


ነገር ገንዘብ ያስገኝልኛል ብለህ አታስብ። ላለው አትሩጥ፣
መልካምምክር ብትሰማሕይወት ቀላል
የቴሌግራም ቻናሌ መቀላቀል ለምትሹ
https://t.me/tsidq

+ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ እንዲህ አለ +

"በምሰብክበት ጊዜ ስታጨበጭቡልኝ ሰው እንደመሆኔ በዚያ ቅጽበት ደስታና መደነቅ ይሰማኛል :: ወደ ቤቴ ሔጄ ያጨበጨቡልኝ


ሰዎች ምንም ጥቅም እንዳላገኙ ሳስብ ግን ንግግሬ ሁሉ በከንቱ እንደቀረ ይሰማኛል :: ስለዚህ ማጨብጨባችሁን የሚከለክልና ዝም
ብላችሁ እንድትሰሙኝብቻየሚያደርግ ሕግ ስለማስቀመጥ አስባለሁ"
(On His Message 80)

“ቤት ውስጥ የእንግዳ ማረፊያ ቤት ይኑርህ:: አልጋ አዘጋጅ:: ጠረጴዛና መቅረዝምይኑረው:: ክርስቶስ ሊመጣና ሊያርፍበት
የሚችልበት ክፍል አዘጋጅና "ይህ የክርስቶስ ክፍል ነው" በል:: ምድር ቤት ያለ ትንሽ ክፍልምቢሆን እሱ አይንቀውም:: ዕርቃኑን
የሆነው እንግዳ የሚፈልገው መጠለያ ብቻ ነው"
(On Acts Homily 40.2)

“ለሞቱት ብቻአናልቅስ:: በቆሙት ብቻምአንደሰት::


ታዲያ ምን እናድርግ? ለኃጢአተኞች በሞቱ ጊዜ ብቻ ሳይሆን በቁማቸውም እናልቅስ:: ስለ ጻድቃን ደግሞ በቁማቸው ብቻ
ሳይሆን በሞቱም ጊዜ ደስ ይበለን::
ምክንያቱምኃጢአተኞችቆመውምሞተዋል:: ጻድቃን ግን ሞተውም ሕያዋን ናቸው::
(On Phil. 3)

"ጴጥሮስ አለቀሰ:: ማልቀስ ብቻ ሳይሆን ምርር ብሎ አለቀሰ:: ከዓይኑ በፈሰሰው ዕንባ ድጋሚ ተጠመቀ:: አምርሮ በማልቀሱም
በዕንባው ኃጢአቱን አጠበ:: አንተም እንዲሁ አድርግ" (Paent 3.4)

“ንብ ከሌሎችእንስሳት ሁሉ ትከበራለች:: የምትከበረው ታታሪ ሠራተኛ በመሆንዋ ሳይሆን የምትሠራው ለሌሎችበመትረፉ ነው"
##################
¹⁴ ስለዚህምስለ ሆነው ነገር ሁሉ እርስ በርሳቸው ይነጋገሩ ነበር።
¹⁵ ሲነጋገሩና ሲመራመሩም፥ ኢየሱስ ራሱ ቀርቦ ከእነርሱ ጋር ይሄድ ነበር፤
¹⁶ ነገር ግን እንዳያውቁት ዓይናቸው ተይዞ ነበር።
¹⁷ እርሱም፦ እየጠወለጋችሁ ስትሄዱ፥ እርስ በርሳችሁ የምትነጋገሩአቸው እነዚህ ነገሮችምንድር ናቸው? አላቸው።
¹⁸ ቀለዮጳ የሚባልም አንዱ መልሶ፦ አንተ በኢየሩሳሌም እንግዳ ሆነህ ለብቻህ ትኖራለህን? በእነዚህ ቀኖች በዚያ የሆነውን ነገር
አታውቅምን? አለው።
¹⁹ እርሱም፦ ይህ ምንድር ነው? አላቸው። እነርሱም እንዲህ አሉት፦ በእግዚአብሔርና በሕዝቡ ሁሉ ፊት በሥራና በቃል
ብርቱ ነቢይ ስለ ነበረው ስለ ናዝሬቱ ስለ ኢየሱስ፤
²⁰ እርሱንምየካህናት አለቆችና መኳንንቶቻችን ለሞት ፍርድ እንዴት አሳልፈው እንደ ሰጡትና እንደ ሰቀሉት ነው።
²¹ እኛ ግን እስራኤልን እንዲቤዥያለው እርሱ እንደ ሆነ ተስፋ አድርገን ነበር፤ ደግሞምከዚህ ሁሉ ጋር ይህ ከሆነ ዛሬ ሦስተኛው ቀን
ነው።
²² ደግሞምከእኛ ውስጥ ማልደው ከመቃብሩ ዘንድ የነበሩት አንዳንድ ሴቶችአስገረሙን፤
²³ ሥጋውንም ባጡ ጊዜ፦ ሕያው ነው የሚሉ የመላእክትን ራእይ ደግሞ አየን ሲሉ መጥተው ነበር።
²⁴ ከእኛምጋር ከነበሩት ወደ መቃብር ሄደው ሴቶችእንደ ተናገሩት ሆኖ አገኙት፥ እርሱን ግን አላዩትም።
²⁵ እርሱም፦ እናንተ የማታስተውሉ፥ ነቢያትምየተናገሩትን ሁሉ ልባችሁ ከማመን የዘገየ፤
²⁶ ክርስቶስ ይህን መከራ ይቀበል ዘንድና ወደ ክብሩ ይገባ ዘንድ ይገባው የለምን? አላቸው።
²⁷ ከሙሴና ከነቢያት ሁሉ ጀምሮ ስለ እርሱ በመጻሕፍት ሁሉ የተጻፈውን ተረጐመላቸው።
²⁸ ወደሚሄዱበትም መንደር ቀረቡ፥ እርሱም ሩቅ የሚሄድ መሰላቸው።
²⁹ እነርሱ፦ ከእኛ ጋር እደር፥ ማታ ቀርቦአልና ቀኑምሊመሽጀምሮአል ብለው ግድ አሉት፤ ከእነርሱምጋር ሊያድር ገባ።
³⁰ ከእነርሱምጋር በማዕድ ተቀምጦ ሳለ እንጀራውን አንሥቶባረከው፥ ቈርሶምሰጣቸው፤
³¹ ዓይናቸውምተከፈተ፥ አወቁትም፤ እርሱምከእነርሱ ተሰወረ።
³² እርስ በርሳቸውም፦ በመንገድ ሲናገረን መጻሕፍትንምሲከፍትልን ልባችን ይቃጠልብን አልነበረምን? ተባባሉ።

ቅዳሴ ዲዮስቆሮስ

ለግሪክ ሰዎችና ላልተማሩም፥ ለጥበበኞችና ለማያስተውሉምዕዳ አለብኝ፤


በወንጌል አላፍርምና፤ አስቀድሞለአይሁዳዊ ደግሞምለግሪክ ሰው፥ ለሚያምኑ ሁሉ የእግዚአብሔር ኃይል ለማዳን ነውና።
ጻድቅ በእምነት ይኖራል ተብሎ እንደ ተጻፈ የእግዚአብሔር ጽድቅ ከእምነት ወደ እምነት በእርሱ ይገለጣልና። ሮሜ
1÷14

እግዚአብሔር ሆይ የሚሳንህ ነገር የለምና የራቀውን አቅርበህ የረቀቀውን አጉልተህ እየሰማነው ካለነው መርዶና ሰቀቀን ዕረፍተ ሥጋንና
ዕረፍተ ነፍስን አትንሣን

ጸልዩ በእንተ ሰላም


ስለ ሰላምእንጸልይ
በጭንቅ በመከራ ስላሉት እንጸልይ
በረሀብ በስደት ስላሉት እንጸልይ
ስለ ሀገራችን እንጸልይ
ስለ ቤተ ክርስቲያን እንጸልይ
በጽኑ ሕመምተይዘው ስለሚሰቃዩት እንጸልይ
የሰላምየምህረት የቸርነት ባለቤት እግዚአብሔር ሰላሙን ምህረቱን ቸርነቱን አይንሳን

አባ አትናቴዎስ ወልደ ጎርጎርዮስ


ዘዝዋይ ገዳም

You might also like