ሴቶች

You might also like

Download as doc, pdf, or txt
Download as doc, pdf, or txt
You are on page 1of 2

ምርጥ መላ፤ ባሎቻቸውን መግደል ለሚፈልጉ ሚስቶች

============================
በአንድ ወቅት አንዲት ቆንጆ ልጅ የትዳር ህይወቷ ሰልችቷት የትዳር ጓደኛዋን ለመግደል ፈለገች። አንድ ቀን ጠዋት
ወደ እናቷ ሮጣ "እናቴ ሆይ የባለቤቴን ከንቱ ንግግር መቋቋም ፤ ከእሱ ጋር መኖር አልችልም። ልገድለው እፈልጋለው
ግን የአገሪቱ ህግ ተጠያቂ እንዳያደርኝ እፈራለሁ፣ እባክሽ እናቴ፤ እርጂኝ" አለቻት፡፡

እናትየዋ መለሰች፡- - አዎ ልጄ ልረዳሽ እችላለሁ፣ ግን፣ ቀድመሽ መሥራት ያለብሽ ትንሽ ስራ አለ ፤ አለቻት።

ልጅቷ "ምን አይነት ስራ ነው? እሱ እንዳቃጠለኝ፣ ሬሣውን ከቤቴ ለማስወጣት ከሆነ ማንኛውንም ስራ ለመስራት
ፈቃደኛ እና ዝግጁ ነኝ" እባክሽ ምን ላድርግ? ስትል ጠየቀች፤

እናት፦ እሺ፤ የሚከተሉትን ነገሮች በጥንቃቄ አድርጊ አለቻት፤

1 ኛ. እሱ ሲሞት ማንም በግድያ እንዳይጠራጠርሽ አስቀድመሽ ከዚህ በፊት በነበረሽ ቅራኔ ላይ ይቅርታ ጠይቀሽ
መታረቅ አለብሽ፤

2 ኛ ከመሞቱ በፊት ለሌሎች ስለአንቺ መልካምነት እንዲያወራ ወጣት እና ማራኪ ለመምሰል እራስሽን ማስዋብ
ይኖርብሻል፤

3 ኛ እሱን በደንብ መንከባከብ ፣ ባደረገው ነገር ሁሉ እሱን አመስጋኝ መሆን አለብሽ፤

4 ኛ ምንም የሚያስቆጣ ነገር ቢያደርግ፣ አፀፋ ከመመለስ ይልቅ፤ ታጋሽ ፣ አፍቃሪ፣ ከምቀኝነት የፀዳ ልብ፣ ብዙ
ከመናገር ይልቅ አድማጭ ፤ ሀሳቡን የበለጠ አክባሪ እና ታዛዥ መሆን አለብሽ፤

5 ኛ. ያለሽን ገንዘብ ወጭ አርጊለት እናም እሱ ምንም ገንዘብ ባይሰጥሽም እንዳትቆጪበት፤

6 ኛ መሞቱ ስለማይቀር እስከ እለቱ ድረስ በፍፁም እንዳትጠረጠሪ ንግግርሽን ሁሉ ሰላምና ፍቅርን እንጂ
በተቃውሞ ድምፅ አታሰሚ። ይህን ሁሉ ማድረግ ትችያለሽ ? እናትየው ጠየቀቻት።

ልጅቷ፦ አዎ እችላለሁ፡ብላ መለሰች፤

እሺ አለች እናትየው። እንግዲያውስ የነገርኩሽን ሁሉ እያደረግሽ ይህንን ዱቄት ወስደሽ በየቀኑ ምግቡ ውስጥ ትንሽ
ትንሹን ጨምሪ፤ ቀስ ብሎ ይገድለዋል አለቻት፡፡

ከ 30 ቀን በኋላ ልጅቷ ወደ እናቷ ተመልሳ መጥታ እንዲህ አለች። እናቴ፣ አሁን ላይ ባለቤቴን የመግደል ሐሳብ
በፍፁም የለኝም። አሁን እሱ ሙሉ በሙሉ ስለተለወጠ ካሰብኩት በላይ በጣም ጣፋጭና ምቹ ባል እየሆነ መጥቷል።

ጉድ ሆኛለሁ፤ የሰጠሽኝን የመርዝ ዱቄት ከምግብ ጋር እያበላሁት ነበር፤ ቀስ ብሎ እንደሚገድል ነግረሽኝ ስለነበር
የመሞቱን ነገር ሳስብ ፡"ምነው ሞቱ ለእኔ በሆነ" እያልኩ መጨነቅ ጀምረአለሁ፡፡ መርዙ እንዳይገድለው ምን ማድረግ
አለብኝ? እባክሽ እናቴ እርጂኝ ስትል በሀዘን ስሜት ተማጸነች።

እናትየው መለሰች; ልጄ፣ በፍፁም አትጨነቂ፤ የሰጠሁሽ የምግብ ቅመም ዱቄት ነው፤ ለጤንነቱም እጅግ ጠቃሚ
እንደሆነ አውቃለሁ፤ በፍጹም አይገድለውም።
አሁን እውኔታውን ስለተረዳሽ እነግርሻለሁ ፤ ባለፈው ጊዜ ነግሬሽ ቢሆን ላትሰሚኝ ትችዪ ነበር፤ ባልሽን በውጥረት
እና በጭንቀት ስሜት ቀስ በቀስ እየገደልሽ የነበርሺው መርዝ አንቺው ነሽ።

አየሽ ልጄ፤ አሁን እሱን መውደድ፣ ማክበር እና መንከባከብ ስትጀምሪ ጥሩ እና ጣፋጭ ባል ሆኖ ሲቀየር አየሺው።
ወንዶች በእውነቱ ክፉዎች አይደሉም፣ ነገር ግን ከእነሱ ጋር የምንኖርበት የህይወት ሥርዓትና መንገድ ፣ ለእኛ
ያላቸውን ምላሽ እና ስሜታቸውን ይወስናል።

ሴቶች ለባሎቻቸው አክብሮትን፣ ራስን መስጠትን፣ ፍቅርን፣ እንክብካቤን እና ቁርጠኝነትን ብቻ ማሳየት ከቻሉ
100% ለሚስቶቻቸው ምቹ መሆን ይችላ፤ ይህ ነው የጤናማ ትዳር የህይወት ሥርዓት በማለት ልጇንና ትዳሯን
አከመችላት፡፡

በ Ewere Okonta ተፅፎ በተስፋዬ ገደቾ ተተረጎመ፡፡

You might also like