ስቅለት

You might also like

Download as doc, pdf, or txt
Download as doc, pdf, or txt
You are on page 1of 7

ተዋሕዶን እንወቅ።:

ሰግዳችሁ አረፍ በምትሉበት ሰዓት ይህንን ያንብቡ👇

#አንድ_አምላክ_በሚሆን_በአብ_በወልድ_በመንፈስ_ቅዱስ ስም አሜን

የመድኃኔዓለምን የሕማሙን የሞቱን ነገር መናገር እንጀምራለን፡፡ 13 ቱ ሕማማተ መስቀል እነማን ናቸው ቢሉ
ተዓሥሮ ድኅሪት (የፊጥኝ መታሰር)፣ ወዲቀ ዲበ ምድር (በመሬት ላይ መውደቅ)፣ ተከይዶ በእግረ አይሁድ (በአይሁድ
እግር መረገጡ)፣ ተስሕቦ በማዕከለ ዓምድ (ታንቆ መጎተት)፣ ተጸፍዖ መልታሕት (ፊትን መጥፊ መመታት)፣ ተኰርዖ
ርእስ (የራስ መገመስ)፣ አክሊለ ሦክ (የእሾህ አክሊል)፣ ተዐርቆተ ልብስ (ርቃን መቆም)፣ ተቀሥፎ ዘባን (ጀርባን
መገረፍ)፣ ፀዊረ መስቀል (መስቀል መሸከም)፣ ተቀንዎ በቅንዋት (በችንካር መቸንከር)፣ ተሰቅሎ በዕፅ (መሰቀል) እና
ሰሪበ ሐሞት (ሐሞት መጠጣት) ናቸው፡፡

13 ቱ ሕማማተ መስቀል የሚባሉት እነዚህ ናቸው፡፡ ምነውሳ ወሪቀ ምራቅ፣ ጽርፈተ አይሁድና ርግዘተ ገቦ ከእነዚህ
ውስጥ የማይቆጠሩ? ቢሉ እነዚህ ሦስቱ ከንዑሳን የሚቆጠሩ ናቸው እንጂ ከ 13 ቱ ገብተው አይቆጠሩም፡፡ ስለምን
አይቆጠሩም? ቢሉ ወሪቀ ምራቅ የምራቅ መተፋት ነው፡፡ አይሁድም ጌታችንን ርኩስ ምራቃቸውን ተፍተውበታል
ነገር ግን ሰውን ቢተፉበት ይጸየፈዋል እንጂ ምራቅ ሕማም ሆኖ አይገድልም፡፡ ስድብም ያናድዳል ያስቆጣል እንጂ
ሕማም ሆኖ አይገድልምና ጽርፈተ አይሁድ አይቆጠርም፡፡ ርግዘተ ገቦ ማለት የጌታችን ጎኑ በጦር መወጋቱ ነው፡፡
ሰውን ከሞተ በኋላ ቢወጉት ሕማሙ አይሰማውምና ርግዘተ ገቦ አይቆጠርም፡፡

13 ቱን ሕማማት እንዴት ነው የተፈጸሙ ቢሉ ክፉዎች አይሁድ መድኃኔዓለምን ሊይዙት የጦር መሣሪያቸውን


ሰብስበው የታጠቁ 300 ጭፍራዎችን አስከትለው ወደ ጌቴሴማኒ በመጡ ጊዜ ‹‹ማንን ትፈለጋላችሁ?›› ቢላቸው
‹‹የናዝሬቱን ኢየሱስን እንፈልጋለን›› ሲሉት ‹‹እኔ ነኝ›› ቢላቸው ከአንደበቱ የወጣውን መለኮታዊ ቃል ብቻ
መቋቋም አቅቷቸው መሬት ላይ ወድቀው ተዘርረዋል፡፡ ይህም ክስተት ለሦስት ጊዜ ያህል በተደጋጋሚ ተከስቷል፡፡ ዮሐ
18፡1-14፡፡ የጌታችን ሞቱ በፈቃዱ መሆኑንና የትዕግሥቱን ብዛት አይተን እናደንቅ ዘንድ ከመጻሕፍት ጠቅሰን
እንነግራችኋለን፡፡

አይሁድ ጌታችን አብርሃም ሳይወለድ በፊት እርሱ ከባሕርይ አባቱ ከአብ ከባሕርይ ሕይወቱ ከመንፈስ ቅዱስ ጋር
በአንድነት በሦስትነት የሚመሰገን አምላክ መሆኑን ቢነግራቸው ሊወግሩት ድንጋይ አነሡ፡፡ እሱ ግን ጊዜው ገና ነበርና
ተሰውሮአቸው በመካከላቸው አልፎ ሲሄድ በፍጹም አላዩትም ነበር፡፡

በቅዱስ ወንጌል ላይ እንዲህ ተብሎ እንደተጻፈ፡- ‹‹አባታችሁ አብርሃም ቀኔን ያይ ዘንድ ሐሤት አደረገ፥ አየም ደስም
አለው። አይሁድም:- ገና አምሳ ዓመት ያልሆነህ አብርሃምን አይተሃልን? አሉት። ኢየሱስም:- እውነት እውነት
እላችኋለሁ፥ አብርሃም ሳይወለድ እኔ አለሁ አላቸው። ስለዚህ ሊወግሩት ድንጋይ አነሡ፤ ኢየሱስ ግን ተሰወራቸው
ከመቅደስም ወጥቶ በመካከላቸው አልፎ ሄደ፡፡›› ዮሐ 8፡56-59፡፡

የጌታችን ሞቱ በፍጹም ፈቃዱ ባይሆን ኖሮ በጌቴሴማኒ ሊይዙት የመጡት ክፉዎች አይሁድን እንደመጀመሪያው ሁሉ
በተሠወራቸው ነበር አሊያም ከአንደበቱ በሚወጣው አምላካዊ ቃሉ ብቻ በፊቱ እንዳይቆሙ አድርጎ ባጠፋቸው
ነበር፡፡ ጌታችን ግን ወደዚህች ምድር የመጣበትን ዓላማ ይፈጽም ዘንድ እንዲገድሉት በፈቃዱ ራሱን አሳልፎ
ቢሰጣቸው ያን ሁሉ እጅግ አሠቃቂ መከራ አደረሱበትና ለመስቀል ሞት አበቁት፡፡

ወዮ ለዚህ ለመድኃኒዓለም ፍጹም ትዕግስት አንክሮ ይገባል! ዓለምን በመዳፉ የያዘ አምላክ በአይሁድ እጅ እንደሌባ
ተያዘ፤ ሠራዊተ መላእክት ለምሥጋና በፊቱ የሚቆሙለት መድኃኔዓለም እርሱ ሊፈረድበት በፍርድ አደባባይ ቆመ፤
በእስራት ያሉትን የሚፈታ እርሱ በብረት ችንካር ተቸነከረ፤ ሰማይን በከዋክብት ምድርም በአበባ ያስጌጠ እርሱ ግን
የእሾህ አክሊል በራሱ ላይ ደፋ፤ ዓለሙን ሁሉ በቸርነቱ የሚመግብ እርሱ ተጠማሁ አለ፡፡ ወዮ የመድኃኔዓለም የማዳኑ
ምሥጢር ምንኛ ድንቅ ነው!!! ይህንን ከትውልዱ ማን አስተዋለ?

የሕማማቱን ነገር ወደመፈጸም እንመለስ፡፡ ጌታችን 300 የታጠቀ ሠራዊት አስከትለው ሊይዙት የመጡትን አይሁድን
በፊቱ ሦስት ጊዜ በጣላቸው ሰዓት በመጀመሪያው በልባቸው ጥሎ ገሃነመ እሳትን አሳይቷቸዋል፤ በሁለተኛው
በጀርባቸው ጥሎ መንግሥተ ሰማያትን አሳይቷቸዋል፡፡ በሦስተኛው ደግሞ ፈረስ በቅሎዎቻቸውን ከላይ አይሁድን
ከሥር አድርጎ ፊታቸውን ከኋላ ኋላቸውን ከፊት፣ ቀኛቸውን ግራ ግራቸውን ቀኝ አድርጎ በማሳየት ሁሉን ማድረግ
የሚችል የባሕርይ አምላክ መሆኑን በተግባር አሳይቷቸዋል፡፡

እነርሱ ግን አንድ ጊዜ ሰይጣን በልባቸው አድሯልና ወደ ህሊናቸው መመለስ አልቻሉም፡፡ እነርሱም ‹‹እኛ ታዘን ነውና
የመጣነው እባክህ ጌታ ሆይ! በፈቃድህ ተያዝልን›› ብለው ለመኑት፡፡ ሁሉ በእጁ የተያዘ አምላክ ጌታችን ኢየሱስ
ክርስቶስም ያንጊዜ ራሱን አሳለፎ ሰጣቸው፡፡

1 ኛ. #ተዓሥሮ_ድኅሪት፡- አይሁድም ከዚህ በኋላ የጌታችንን መጋፊያና መጋፊያው እስኪጋጠም ድረስ የፊጥኝ
ረግጠው ካሠሩት በኋላ አፍንጫውን 25 ጊዜ ቢመቱት ደሙ በመሬት ላይ እንደ ውኃ ፈሰሰ፡፡ አሥረውም ከቀያፋ ወደ
ሐና፣ ከሐና ወደ ቀያፈ ሲያመላልሱት አደሩ፡፡ ዮሐ 18፡12፡፡ ይህም ለአርአያ እና ለቤዛነት ነው፡፡ ቤዛነቱ አዳምንና
ሔዋንን አጋንንት ገሃነመ እሳት አውርደው በእሳት ሰንሰለት የፊጥኝና የግርግሪት አሥረው ሲያሠቃዩአቸው ነበርና
እነርሱንና የሰውን ልጅ በሙሉ ለማዳን ነው፡፡ አርአያነቱ በእኔ ምክንያት ያስሯችኋል ነገር ግን በፍቅሬ ታስራችሁ ኑሩ፣
መከራን ተቀበሉት እንጂ አተሰቀቁ ሲል ነው፡፡

2 ኛ. #ወዲቀ_ዲበ_ምድር፡- ክፉዎች አይሁድ ጌታችንን ካሠሩት በኋላ ከጌቴሴማኒ እስከ ሐና ቤት ድረስ 65 ጊዜ


በምድር ላይ ጥለውታል፡፡ የራስ ጠጉሩንም እየያዙ እያንጠለጠሉ 25 ጊዜ እያነሡ ጥለውታል፡፡

3 ኛ. #ተከይዶ_በእግረ_አይሁድ፡- አይሁድ አሥረው እየጎተቱ ሲወስዱት የፊተኞቹ ሲስቡት የኋለኞቹ ይለቁታል


ያንጊዜም በልቡ ሲወድቅ ከኋላ ያሉት ፈረሳቸውን በቅሏቸውን በላዩ ይነዱበታል፡፡ የኋለኞቹ ሲስቡት የፊተኞቹ
ይለቁታል በጀርባው ይወድቃል፡፡ ቀድመውት የሄዱትም ‹‹…ወዴት ሄደ? አመለጠን?...›› እያሉ በመዘበት
ተመልሰው በልቡ ላይ ይሄዱበታል፡፡ እንዲህ እያደረጉ 65 ጊዜ ከመሬት ጋር አጋጭተውታል፡፡ ሳውልም በዚያ ጊዜ
ከእነርሱ ጋር ነበርና ጌታችን ‹‹መመለስህ ላይቀር ለምን ትረግጠኛለህ?›› ቢለው ትንቢት ተናገረብኝ ብሎ ሳውል
440 ጊዜ አስገረፈው፡፡ ዳግመኛም በጅንፎ በትር 62 ጊዜ መቱት፤ በአለንጋ 62 ጊዜ ገረፉት፤ አፉንና አፍንጫውን ደሙ
እስኪወርድ ድረስ 40 ጊዜ መቱተ፤ የእጆቹ ጣቶች እስኪደቁ ድረስ 42 ጊዜ መቱት፡፡

4 ኛ. #ተስሕቦ_በማዕከለ_ዓምድ፡- ይኽም ጉሮሮን ታንቆ እንደውሻ መጎተት ማለት ነው፡፡ ጌታችንን አይሁድ
ጉሮሮውን በብረት ሰንሰለት አጥብቀው አሥረው ደም እስኪነስረው ዐይኑ ሊፈርጥ እስኪደርስ ድረስ 27 ጊዜ በጡጫ
መቱት፡፡ በሁለት ታላላቅ ግንዶች መሐል አግብተው አንገቱን የታሠረበት ከግንዶቹ ጋር በማሠር የፊተኞቹ ሲስቡት
የኋለኞቹ ይለቁታል በፊቱ ያለው ግንድ ልቡን ደረቱን ፊቱን ይመታዋል፤ የኋለኞቹ ሲስቡት የፊተኞቹ ይለቁታል
የኋላው ግንድ ወገቡን ራሱን ይመታዋል፡፡ እንዲህ እያደረጉ 62 ጊዜ ከግንዱ ጋር አጋጩት፡፡

5 ኛ. #ተጸፍዖ_መልታሕት፡- ሊቀ ካህናቱ ሐና ወደ ቀያፋ በላከው ጊዜ ቀያፋም ‹‹‹አምላክ ነኝ ከሰማይ ወርጃለሁ›


የምትል አንተ ነህን?...›› ብሎ ጠየቀው፡፡ ጌታችንም ‹‹አምላነቴን እኔ ብቻ የምናገረው አይደለም አንተም ደግሞ
ራስህ ተናገርኽ እንጂ›› አለው፡፡ ማቴ 27፡11፡፡ ቀያፋም ሎሌዎቹን ‹‹ተቀምጣችሁ አታሰድቡኝ›› ብሎ በመቆጣት
ልብሱን ቀደደ፡፡ እነርሱም ይህን ጊዜ ጌታችንን ፊቱን በጥፊ መቱት፡፡ ዮሐ 18፡22፡፡ እጃቸውን ቢደክማቸው ድንጋይ
ጨብጠው አጥንቱ እስኪደቅ ድረስ በድንጋይ ጥፊ 120 ጊዜ ፊቱን ጸፉት፡፡

6 ኛ. #ተኰርዖ_ርእስ፡- አይሁድ ጌታችንን ‹‹ኃላፊያቱን መጻኢያቱን አውቃለሁ ትላለህ…›› እያሉ በመዘበት ፊቱን
እየመቱ ራሱን እየገመሱ ‹‹የመታህ ማነው?›› ይሉት ነበር፡፡ ማቴ 26፡67፣ ሉቃ 22፡63፡፡ ዳግመኛም አክሊለ ሦኩን
ለማድረግ እንዲያመቻቸው የራስ ፀጉሩን 25 ጊዜ ነጩት፡፡

7 ኛ. #አክሊለ_ሦክ፡- እነሆ ክፉዎች አይሁድ ሰይጣን በልባቸው ነግሦ ክፋትን ብቻ እንዲያስቡ አድርጓቸዋልና ስቁረት
ያለበት እንደ ወረንጦና እንደ ወስፌ እንደ መርፌም ያለ 300 እሾህ ያለው ስረወጽ አድርገው የብረት አክሊል ሠርተው
ከፍላት አግብተው በጉጠት አንሥተው ‹‹ኢየሱስ ናዝራዊ ንጉሥ ነህ ዘውድ ይገባሃል› ብለው ያ ሁሉ እስኪገባ ድረስ
በራሱ ላይ መቱበት፡፡ ለአክሊለ ሦኩም 73 ስቁረት ነበረው፡፡ ዳግመኛም እራሳቸው እንደ መሮ፣ ወርዳቸው እንደ
ሞረድ 4 ማዕዘን አሠርተው ቁመታቸውን ክንድ ከስንዝር፣ ስለታቸውን እንደ ወስፌ እንደ መርፌ አድርገው 73
ችንካር ሠርተው በዚያ በአክሊሉ 73 ስቁረት አግብተው ያ ሁሉ እስኪገባ ድረስ በራሱ ላይ ቢመቱበት ሥጋ ለሥጋ
ገብቶ በአንገቱ ወርዶ መሐል ልቡን ወጋው፡፡ አክሊሉንም እንዳሸከሙት ጲላጦስ እንዲመረምረው ከቤት ወደ አደባባይ
3 ጊዜ አመላለሱት፡፡ በ 4 ኛው ከአደባባይ አኑረው ‹‹ንጉሥ ሆይ!...›› እያሉ ርኩስ ምራቃቸውን እየተፉበት
ተዘባበቱበት፡፡ እየሰገዱ ሲነሡ በፊቱ ተፍተውበት ይነሣሉ፡፡ ጀርባውንም በዘንግ ይመቱት ነበር፡፡

8 ኛ. #ተዐርቆተ_ልብስ፡- አይሁድ ‹‹ስቃዩን አበዛነው አሁን ደግሞ አፍሮ ደንግጦ ይሞታል›› ብለው በሰው ሁሉ
መካከል ራቁቱን አቁመውታል፡፡

9 ኛ. #ተቀሥፎ_ዘባን፡- አይሁድ ጲላጦስን ‹‹…ኃይለኛ በደለኛ ሰው ይዘናል ጉባኤ ሥራልን›› አሉት፡፡ ጲላጦስም
በጠዋት ጉባኤ ሠራላቸው፡፡ ክፉዎች አይሁድም ጌታችንን ‹‹በቃሉ ሐሰት በሰውነቱ ክፋት የለበትምና ጲላጦስ ይህን
ተመራምሮ በነፃ ቢለቀውና ባይፈርድነበት ሀዘናችን ይበዛል በኋላ እንዳይቆጨን›› ብለው አስቀድመው 305 ጊዜ
በሽመል ደበደቡት፡፡ በባሕርይ አምላክነቱ ቻለው እንጂ አንዱ ብቻ በገደለው ነበር፡፡

እያዳፉም ወስደው ጲላጦስ ፊት ካቆሙት በኋላ ‹‹ኃይለኛ በደለኛ ነውና ስቀለው›› አሉት፡፡ ጲላጦስም ‹‹በምን
በደሉ ልስቀለው? በደሉን ንገሩኝ?›. አላቸው፡፡ አይሁድም ‹‹ሰንበትን ሻረ፣ የሰሎሞንን ቤተ መቅደስ አፈርሱት በ 3 ኛ
ቀን እሠራዋለሁ አለ፣ ራሱን አምላክ አደረገ›› የሚሉ ሦስት ክሶችን አቀረቡ፡፡ ዮሐ 9፡16፣ 13፡29፣ 18፡30፣ ኩፋ 34፡
13፣ ሉቃ 23፡1-10፣ ማር 15፡3፣ 19፡10፡፡ የአይሁድን ክፋት ማሸነፍ የማይሆንለት ሆኖ ነው እንጂ ጲላጦስ ጌታችንን
ለማዳን ብዙ ለፍቶ ነበር፡፡ በሕጋቸው መሠረት የሚሰቀል አይገረፍም፣ የሚገረፍም አይሰቀልም ነበርና ጲላጦስ
‹‹ገርፋችሁ ልቀቁት›› አላቸው፡፡

አይሁድንም ዳግመኛ ‹‹ሕጋችሁ ስንት ይገረፍ ትላለች?›› ቢላቸው እነርሱም ‹‹…41 ይገረፍ ይላል ነገር ግን
ለእርሱ አይበቃውም›› አሉት፡፡ ጲላጦስም ‹‹ለእርሱ ስትሉ ሕጋችሁን ትተላለፋላችሁን? በሉ እንደሕጋችሁ ብቻ
ገርፋችሁ ልቀቁት፣ ከቁጥር አብልጣችሁ ብትገርፉት ግን ከደሙ ንጹሕ ነኝ›› ብሎ በፊታቸው ታጠበ፡፡ አይሁድም
‹‹ደሙ በእኛና በልጆቻችን ላይ ይሁን›› በማለት በራሳቸው ላይ ርግማን ስላወጁ ዛሬም ድረስ ወንድ ቢወልዱ ልጁ
ደም ጨብጦ ይወለዳል፣ ሴት ቢወልዱ ልጅቱ ያለድንግልና ትወለዳለች፡፡

ርጉማን አይሁድ ጌታችንን ከጲላጦስ ተረክበው ከወሰዱት በኋላ አዝማሪ አስመጥተው ጌታችንን እያሰደቡት 80 ጊዜ
ፂሙን ነጭተውታል፡፡ መከራውን ሲያጸኑበት አድረዋልና ደሙ እንደ ውሃ ጎርፍ ፈሷል፣ ሥጋው እየተላጠ መሬት ላይ
ወድቋል፡፡ ክፉዎች አይሁድ ‹‹አሠቃቂ ግርፋትን ሲገረፍ ያየነው እንደሆነ ልባችን ሊራራ ይችላል›› ብለው ሰንጠረዥ
ገበጣ ሠርተው ሲጫወቱ አንዱ ተነሥቶ 50 እና 60 ድረስ ይገርፍና ሲደክመው ‹‹ቆጠራችሁን?›› ብሎ ይጠይቃል፡፡

ሌሎቹም ‹‹አልቆጠርንም›› ሲሉት ከድካሙ የተነሣ ‹‹እኔው ልግረፍ እንደገና እኔው ልቁጠር›› ብሎ ትቶት
ሲቀመጥ ሌላኛው ይነሣና እንደመጀመሪያው ገራፊ ሁሉ በተራው እንደገና አንድ ብሎ ጀምሮ 50 እና 60 ይገርፈዋል፡፡
ሁሉም እንዲህ እያሳሳቱ የራሳቸውን ሕግ እየተላለፉ አይሁድ ጌታችንን ሥጋው አልቆ አጥንቱ እንደበረዶ ነጭ ሆኖ
እስኪታይ ድረስ 6666 ጊዜ ጽኑ ግርፋትን ገረፉት፡፡ በእነዚህ ሁሉ ግርፋቱ ወቅት 366 ጊዜ ሥጋው ተቆርሶ መሬት ላይ
ወድቋል፡፡ ሥጋው እየተቆረሰ ከምድር የወደቀው 76 ነው፡፡ ያበጠውና የበለዘው ግን የሚቆጠር አይደለም፡፡ ስፍር
ቁጥርም የለውም፡፡
10 ኛ. #ፀዊረ_መስቀል፡- ጌታችንን አይሁድ የዕንጨት መስቀል አሸክመው ከሊቶስጥራ እስከ ቀራኒዮ ድረስ እያዳፉ
ሲወስዱት 136 ጊዜ በምድር ላይ ጥለውታል፡፡ ከኋላ ያሉት ‹‹ፍጠን›› እያሉ ገፍትረው ይጥሉታል፣ ከፊት ያሉት
ደግሞ ‹‹ምን ያስቸኩልሃል?›› እያሉ መልሰው ገፍትረው ይጥሉታል፡፡ እንዲህ እያደረጉ መስቀል አሸክመው እያዳፉ
ቀራንዮ አድርሰውታል፡፡

11 ኛ. #ተቀንዎ_በቅንዋት፡- ቀራንዮ ካደረሱት በኋላ አይሁድ ቁመታቸው ክንድ ከስንዝር፣ ስለታቸው እንደ ወስፌ
እንደ መርፌ ያሉ፣ ወርዳቸው እንደሞረድ የሆኑ፣ 4 ማዕዘን የሆኑ ራሳቸው እንደ መሮ ያሉ 5 ታላላቅ ችንካሮችን
ሠርተው ሳዶር በሚባለው ችንካር ቀኝ እጁን፣ በአላዶር ግራ እጁን፣ በዳናት ሁለት እግሮቹን፣ በአዴራ መሐል ልቡንና
በሮዳስ ደረቱን ቸንክረው የአዳም ራስ ቅል ባለበት ቀራኒዮ አደባባይ ላይ ሰቅለውታል፡፡

12 ኛ. #ተሰቅሎ_በዕፅ፡- መስቀሉን በሥሩ ተክለው ጊዜ ቀትር ሲሆን ጌታችንን ቢሰቅሉት ሥጋው በግርፋት አልቆ
ነበርና የጎኑ አጥንት ተተረተረ፡፡ አይሁድም ‹‹የጎኑ አጥንት ስንት ነው? እስኪ ቁጠሩት…›› እያሉ ተዘባበቱበት፡፡
ይኽም በነቢዩ ቅዱስ ዳዊት ‹‹አጥንቶቼ ሁሉ ተቆጠሩ›› (መዝ 21፡17) ተብሎ የተነገረው ትንቢት ይፈጸም ዘንድ
ነው፡፡ ጌታችን ከምድር ከፍ ከሰማይ ዝቅ ብሎ በ 7 ክንድ ከስንዝር መስቀል ላይ በጊዜ ቀትር ተሰቅሎ 7 ቱን
መስተፃርራን አስታረቃቸው፡፡ እነዚህም 7 መስተፃርራን እግዚአብሔርና ሰው፣ ሰውና መላእክት፣ ነፍሥና ሥጋ፣
ሰማይና ምድር፣ ሕዝብና አሕዛብ ናቸው፡፡

በቀራንዮ አደባባይ ላይ በገበያ ቀን በተሰቀለም ጊዜ አይሁድ ሲያልፉ ሲያገድሙ ‹‹…ከወንበዴዎች ጋር የተሰቀለው ያ


‹አምላክ ነኝ ከሰማይ ወርጃለሁ› ብሎ ይናገር የነበረው አይደለምን? ታዲያ ምነው ተሰቀለ!?…›› ብለው ስቀው
አንገታቸውን ነቅንቀው ያልፋሉ፡፡ ቅዱስ ዳዊት ‹‹እኔም በእነርሱ ዘንድ ለነውር ሆንኩ፣ ባዩኝ ጊዜ ራሳቸውን ነቀነቁ››
ብሎ ትንቢት እንደተናገረ፡፡ መዝ 108፡25፡፡ ነገር ግን ‹‹የጌታችን ርቃን አናሳይም›› ብለው ፀሐይ ጨለመች፣
ጨረቃም ደም ሆነች፣ ከዋክብትም ረገፉ፡፡

13 ኛ. #ሰሪበ_ሐሞት፡- ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ 12 ቱን ሕማማተ መስቀል ሲቀበል ውሎ ዘጠኝ


ሰዓት በሆነ ጊዜ ‹‹ተጠማሁ›› አለ፡፡ ዮሐ 19፡26፡፡ አይሁድም ‹‹ይህ ዕብራዊ ‹ውሃ ጠማኝ› አለ፣ ጲላጦስ
ተመራምሮ ሳያድነው በቶሎ የሚገድል ነገር እናጠጣው ብለው ከመከሩ በኋላ ጉሮሮ ቆርጦ የሚጥል አንጀት የሚበጥስ
ከብዙ ነገር የተደባለቀ እጅግ መራራ አጠጡት፡፡ ጌታችንም ቀምሶ ተፋው እንጂ አልዋጠውም፡፡ በዚኽም ነቢዩ ቅዱስ
ዳዊት ‹‹ለመብሌ ሐሞት ሰጡኝ፣ ለጥማቴም ሆምጣጤ አጠጡኝ›› ብሎ የተናገረው ትንቢት ተፈጸመ፡፡ መዝ 68፡
21፡፡ ጌታችን ከዚህ በኋላ 7 ቱን ቃላት በመስቀል ላይ ተናግሮ ራሱን ወደቀኝ ዘንበል አድርጎ ቅድስት ነፍሱን በገዛ
ሥልጣኑ ለየ፡፡ ዮሐ 10፡15፣ 19፡30፡፡

የመድኃኔዓለም ቸርነቱ የድንግል እናቱ ምልጃና ጸሎት ከሁላችን ጋር ይሁን! አሜን!!

ዕለተ ዓርብ፣ ዕለተ ስቅለት፣ መልካሙ ዓርብ

በዚህች ዕለት ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዕፀ መስቀል የተሰቀለባት ዕለት ናትና “ዕለተ ስቅለት”፣
የእግዚአብሔር መልካምነት ለሰው ልጅ ድኅነት በፈቃዱ ራሱን አሳልፎ ለሞት በመስጠቱ የተገለጠባት ናትና
“መልካሙ ዓርብ” ይባላል።

ዓርብ ነግህ (ሲነጋ)

በዚህች ዕለት በነጋ ጊዜ የአይሁድ ሊቃነ ካህናት ኢየሱስን ወደ ፍርድ አደባባይ ሊያወጡት፣ ለጲላጦስ አሳልፈው
ይሰጡት ዘንድ እንዲሁም በፍርድ አደባባይ ይሰቅሉት ዘንድ የተማከሩበት ዕለት ነው። “ሲነጋም ጊዜ የካህናት
አለቆችና የሕዝቡ ሽማግሎች ሁሉ ጌታችን ኢየሱስን ሊገድሉት ተማከሩ፤ አስረውም ወሰዱት፥ ለገዢው
ለጰንጤናዊው ጲላጦስም አሳልፈው ሰጡት” እንዲል። (ማቴ.፳፯፥፩-፪)

ዓርብ ሦስት ሰዓት

በዚህች ሰዓት ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ወደ ጲላጦስ ፍርድ ወስደው አቁመውታል፤ ጲላጦስም
በርባንን ፈትቶ ጌታችንን ገርፎት እንዲሰቅሉት አሳልፎ ሰጥቷቸዋል፣ ጌታችንንም ይዘውት ሊሰቅሉት ወስደውታል።
“በየበዓሉም ከእስረኞች የመረጡትን አንዱን ይፈታላቸው ነበር። ከክፉ አድራጊዎችና ከነፍሰ ገዳዮች ጋር የታሰረ
በርባን የሚባል አንድ ሰው ነበረ። ሕዝቡም ወጥተው እንደ አስለመደ ያደርግላቸው ዘንድ እየጮኹ ለመኑ። ጲላጦስም
መልሶ፥ “የአይሁድን ንጉሥ እፈታላችሁ ዘንድ ትወዳላችሁን?” አላቸው። የካህናት አለቆች በቅንዓት አሳልፈው
እንደ ሰጡት ያውቅ ነበርና። የካህናት አለቆች ግን በርባንን እንዲፈታላቸው ይለምኑት ዘንድ ሕዝቡን አነሣሡአቸው።
ጲላጦስም መልሶ፥ “እንግዲህ የአይሁድ ንጉሥ የተባለውን ምን ላደርገው ትወዳላችሁ?” አላቸው። እነርሱም
እንደገና ‘ስቀለው’ እያሉ ጮኹ።” (ማር.፲፭÷፮-፲፫)

አምስቱ ቅንዋተ መስቀል (ችንካሮች) የሚባሉት እነማን ናቸው?

#ሳዶር ፦ኢየሱስ ክርስቶስ የቀኝ እጁን የተቸነከረበት ችንካር ነው፤


#አላዶር ፦ኢየሱስ ክርስቶስ የግራ እጁን የተቸነከረበት ችንካር ነው፤
#ዳናት ፦ኢየሱስ ክርስቶስ ሁለት እግሮቹ የተቸነከሩበት ችንካር ነው፤
#አዴራ ፦ኢየሱስ ክርስቶስ መሐል ልቡን የተቸነከረበት ችንካር ነው፤
#ሮዳስ ፦ኢየሱስ ክርስቶስ ደረቱን የቸነከሩበት ችንካር ነው።

ዓርብ ስድስት ሰዓት

በዚህች ዕለት በዚህች ሰዓት ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን አይሁድ መስቀል አሸክመው፣ ከለሜዳ
አልብሰው፣ ምራቅ እየተፉ ከተዘባበቱበት በኋላ ከለሜዳውን ገፍፈው፣ ልብሱን አልብሰው፣ እየገፉ፣ እያዳፉ ቀራንዮ
አደባባይ አደረሱት፤ ልብሱንም ገፍፈው ራቁቱን በሁለት ወንበዴዎች መካከል በመስቀል ላይ ሰቀሉት።

“ከዚህም በኋላ የመስፍኑ ጭፍሮች ጌታችን ኢየሱስን ተቀብለው ወደ ፍርድ ሸንጎ ወሰዱት፤ ጭፍራውንም ሁሉ ወደ
እርሱ ሰበሰቡ። ልብሱንም ገፈው ቀይ ልብስ አለበሱት። የእሾህም አክሊል ጎንጉነው በራሱ ላይ አቀዳጁት፤ በቀኝ
እጁም ዘንግ አሲያዙት፤ በፊቱም ተንበርክከው፥ “የአይሁድ ንጉሥ ሆይ፥ ሰላም ለአንተ ይሁን” እያሉ ተዘባበቱበት፤
በላዩም ተፉበት፤ ዘንጉንም ነጥቀው ራሱን መቱት። ከተዘባበቱበትም በኋላ ቀዩን ልብስ ገፍፈው ልብሱንም
አለበሱት፤ ሊሰቅሉትም ወሰዱት።” (ማቴ ፳፯÷፳፯-፴)
“በወሰዱትም ጊዜ የቀሬና ሰው ስምዖንን ከዱር ሲመለስ ያዙት ከጌታችን ከኢየሱስ በስተኋላ መስቀሉን
አሸከሙት።” (ሉቃ.፳፫÷፳፮)

“ከዚህ በኋላ ሊሰቅሉት አሳልፎ ሰጣቸው፤ ጌታችን ኢየሱስንም ተቀብለው ወሰዱት። መስቀሉንም ተሸክሞ
በዕብራይስጥ ጎልጎታ ወደ ተባለው ቀራንዮ ወደሚባል ቦታ ወጣ። በዚያም ሰቀሉት፥ ከእርሱም ጋር አንዱን በቀኝ፥
አንዱንም በግራ አድርገው ሌሎች ሁለት ወንበዴዎችን ሰቀሉ፤ ኢየሱስንም በመካከላቸው ሰቀሉ። ጲላጦስም
ጽሕፈት ጽፎ በመስቀሉ ላይ አኖረ፤ ጽሕፈቱም። ‘የአይሁድ ንጉሥ የናዝሬቱ ኢየሱስ’ የሚል ነበር።”
(ዮሐ.፲፱÷፲፮-፲፱)

#ዓርብ_ስድስት_ሰዓት_የሚነበብ (የስምዖን ዐምዳዊ ጸሎት)


ጌታዬ፡ ኢየሱስ፡ ክርስቶስ፡ ሆይ፡ በዕንጨት መስቀል፡ ላይ፡ ራቁትህን፡ የሆንክ፡ ጨለማን ከለበሰና፡ ስሕተትን፡ ከሚያመጣ፡
ሰይጣን መንፈስ፡ ለየኝ።

በኃይልህ፡ እታደስ፡ ዘንድ፡ በጥበብህም፡ እመገብ፡ ዘንድ፡ የሕይወት፡ ሐር፡ ልብስን፡ አልብሰኝ።

ጌታዬ፡ ኢየሱስ፡ ክርስቶስ፡ ሆይ፡ መላእክትን፡ የብርሃን፡ መጐናጸፊያ፡

የምታጐናጽፋቸው ኃይልንም የምታስታጥቃቸው በመስቀል፣ ላይ፡ ራቁትህን፡ ቆምክ።

ልቡናዬን፡ ከፍጹም፡ ድንቁርና፡ ጨለማ፡ አርቅ፣ (አንፃ)፣ በልቤና፡ በሕዋሳቴ፡ ውስጥም፡ የጌትነትህን፡ ብርሃን፡ አብራ፤
ከምድራዊ፡ ሀሳብና፡ ጠባይ፡ ተለውጠው፡ ከሰማያውያን መላእክት፡ ጋራ፡ ያመሰግኑህ፡ ዘንድ።

ጌታዬ፡ ኢየሱስ፡ ክርስቶስ፡ ሆይ፡ የከበሩ፡ እጆችህን፡ በዕንጨት፡ መስቀል፡ ላይ፡ የዘረጋህ፡ ፍቅርህ፡ በውስጡ፡ ያድርበት
ዘንድ፡ ልቡናዬን፡ እንዲከፈት፡ አድርገው።

ጌታዬ፡ ኢየሱስ፡ ክርስቶስ፡ ሆይ፡ መላእክትን ከእሳት፡ የፈጠርካቸው፡ ሰማይንም፡ እንደ ድንኳን፡ የዘረጋህ፡ የምድርንም፡
ስፋቷን ያበዛህ።

በበላይዋም፡ ዓለማተ፡ ሰማይን፡ እጅግ፡ ከፍ አድርገህ፡ የፈጠርክ፡ ከበታችዋም፡ እጅግ ጥልቅ ያደረግህ፡ ዙሪያዋንም፡
በባህር፡ የከበብህ ትእዛዝህም፡ ምድርን፡ በባሕር፡ ላይ፡ ጸንታ እንድትኖር፡ ያደረጋት፡ በውስጥዋ፡ ያለውንም ሁሉ።

በመስቀል፡ ላይ፡ እንዴት፡ እጅህን ዘረጋህ? እንዴትስ፡ በቀኖት፡ ተቸነከርክ፡ ወዴትስ ወረድክ? ለሞት፡ እስክትደርስ፡ ድረስ፡
የአዳምን፡ ማዳን፡ እንደምን፡ ወደድክ።

አፍና፡ አንደበት፡ ካላቸው፡ ለጌትነትህ፡ ምስጋና፡ ማቅረብ፡ የሚችል፡ ማን፡ ነው።

ጌታዬ፡ ኢየሱስ፡ ክርስቶስ፡ ሆይ፡ ፍቅርህን፡፡ በልቤ፡ ውስጥ፡ ቅረጽ፤ ከክፉ፡ ማሰሪያ፡ ፍታኝ፤ ለዘላለም፡ ጸንቶ፡ በሚኖር፡
ፍቅርህም፡ እሰረኝ።

ጌታዬ፡ ኢየሱስ፡ ክርስቶስ፡ ሆይ፡ ማሕየዊ፡ መስቀልህን፡ አቅፌ፡ ከእርሱ፡ የሕይወትና፡ የመድኃኒት፡ መዐዛ፣ አሸት፡ ዘንድ፡
ስጠኝ።

በልቡናዬም፡ ውስጥ፡ ንጹሕ፡ ደምህ፡ ይውረድ፤ ንጹሕ፡ መሠዊያ፡ ይሆን፡ ዘንድ፡ ልቡናዬን፡ ያክብረው፤ በውስጡም፡
የሕይወትን፡ መንፈስ፡ ያንቀሳቅስ፤ የሕይወት፡ መንፈስ፡ አንተን፡ ይቀበል።

ጌታዬ፡ ኢየሱስ፡ ክርስቶስ፡ ሆይ በመስቀል ላይ፡ መጻጻንና፡ ሐሞትን፡ የጠጣህ ከታላቁ፡ ንጹሕ፡ ፍቅርህ፡ አጠጣኝ፤
ከመራራው፡ ሞተ፡ ነፍስም፡ አድነኝ።

(#ግብረ_ሕማማት_ዘዓርብ)

"ሕማማተ መስቀል" ተብለው የሚዘከሩት አሥራ ሦስት ሲሆኑ እነዚህም፦

1. በብረት ሐብለ መጋፊያና መጋፊያው እስኪጋጠም ድረስ የኋሊት መታሰሩ


2. ከአፍንጫው ደም እስኪውጣ ድረስ 25 ጊዜ በጡጫ መመታቱ
3. 65 ጊዜ ከግንድ ማጋጨታቸው
4. 120 ጊዜ በድንጋይ ፊቱን መመታቱ

5. 365 ጊዜ በሽመል መደብደቡ


6. 80 ጊዜ ጽህሙን መነጨቱ
7. 6666 ጊዜ መገረፉ
8. አክሊለ ሦክ በራሱ ላይ መደፋቱ
9. 136 ጊዜ በምድር ላይ መውደቁ

10. ሳዶር፡ አላዶር፡ ኤዴራ፡ ዳናትና ሮዳስ በሚባሉ 5 ቱ ቅንዋተ መስቀልበችንካር መቸንከሩ
11. መራራ ሐሞትን መጠጣቱ
12. መስቀሉን ተሸክሞ መንገላታቱ
13. በመስቀል መሰቀሉ ናቸው።

You might also like