Download as doc, pdf, or txt
Download as doc, pdf, or txt
You are on page 1of 27

ለኦሮ/ብሄ/ዞን/ከፍይህፍ/ቤት

ከሚሴ

የፍ/መ/መ/ቁ 3129/2016

ቀን 26/5/2016

ዐ/ህግ/ወ/መዝ/ቁ ፦151/2016

የፖ/ጽ/መዝ/ቁጥር ፦269/2016

ከሳሽ ፦ የኦሮ/ብሄ/ዞን ዐ/ህግ

ተከሳሽ ፦አህመድ አብዱ ጣሂር እድሜ ፦17 ስራ ፦ አርሶ አደር ስልክ ቁጥር.....አድራሻ ወረዳ ፦አርጡማ ፉርሲ
ቀበሌ፦ጎልቦ አርባ ጎጥ፦ቡርቃ

ወንጀሉ

በ 1996 ዓ,ም የወጣውን የወንጀል ህግ አንቀጽ 539 (1)ሀ ስር የተደነገገውን በመተላለፍ

የወንጀሉ ዝርዝር

ተከሳሽ ሰው ለመግደል በማሰብ በቀን 27/01/2015 ዓ,ም ከቀኑ በግምት 6፡00 ሰአት ሲሆን በአርጡማ ፉርሲ
ወረዳ ጎልቦ ቀበሌ ጎጥ ቡርቃ ተብሎ በሚጠራበት ቦታ ልጅ መታ በሚል ምክንያት ሟች ሁሴን በሺር
የሚባለውን ቁጥሩ 17292 የሆነውን ክላሽ በሚባለው የጦር መሳሪያ በአንድ ጥይት ቀኝ እግሩ ፣ በአንዱ ጥይት
ልቡ ላይ እንዲሁም በአንድ ጥይት ግንባሩ ላይ በአጠቃላይ በሶስት(3) ጥይት በመምታት በጭካኔ ፣ አሰቃቂ ና
አደገኛ በሆነ ሁኔታ ከባድ የሆነ ጉዳት አድርሶበት ስለገደለው በከባድ የሰው ነፍስ ግድያ ወንጀል በመፈፀም
ተከሷል ።

ሀ.የሰው ማስረጃ

1 ኛ አብዱሶመድ ሁሴን በሺር አድራሻ፦ወረዳ አርጡማ ፉርሲ ቀበሌ ፦ ጎልቦ አርባ ስልክ....

2 ኛሀሊማ መሀመድ ጅብሪል አድራሻ፦ወረዳ አርጡማ ፉርሲ ቀበሌ፦ጎልቦ አርባ ስልክ 0960977079

ለ. የሰነድ ማስረጃ

> አልቀረበም

የዐቃቤ ህግ የማይነበብ ፊርማ አለበት ።

✍ ተርጓሚ ፦ መሀመድ ሀሰን የሰፍ


ለኦሮ/ብሄ/ዞን/ከፍ/ፍ/ቤት መ/ቁጥር፦0205655

ከሚሴ ቀን፦

አመልካች አህመድ አብዱ በቀረበብኝ ክስ ከፍ/ፍ/ቤቱ በቀን 5/06/2016 በዋለው ችሎት እንድከላከል ብይን
ሰጥቷል።በዚህም መሰረት መከላከያ ምስክሮቼን አንደሚከተለው አቀርባለሁ፦

1. መሀመድ አብዱ ጣሂር አድራሻ አርጡማ ፉርሲ ወረዳ ጎልቦ ቀበሌ

2. መሀመድ አሊይ ያሲን አድራሻ አርጡማ ፉርሲ ወረዳ ጎልቦ ቀበሌ 3………….አድራሻ
.......4. ......................አድራሻ ...............

ስለዚህ መከላከያ ምስክሮቼ እንዲቀቡልኝ መጥሪያ ወረቀት ይጻፍልኝ በማለት አመለክታለሁ ።

የአመልካች ስምና የማይነበብ ፊርማ አለበት

✍ ተርጓሚ ፦ መሀመድ ሀሰን የሱፍ

ቁጥር ፦529/2016
ለኦሮ/ብሄ/ዞን/ከፍ/ፍ/ቤት ቀን ፦ 29/06/2016

የዐ/ህግ/ወን/መዝ/ቁ ፦151/2016

የፍ/ቤቱ/ወን/መዝ/ቁ ፦0205655

ከሳሽ ፦የኦሮ/ብሄ/ዞን ዐ/ህግ

ተከሳሽ ፦አህመድ አብዱ ጣሂር

በወ/ስ/ስ/ህግ አንቀጽ 143/1 እና 2 መሠረት የቀረበ ማስረጃ

ተከሳሽ በሰው ግድያ ተከሶ ለፍ/ቤቱ ባቀረብነው መሰረት መዝገቡ ተከፍቶ ክርክር ላይ መሆናችን ይታወቃል:
ይሁን እንጂ ከሳሽ ዐ/ህግ ክሱን ሲያቀርብ ወንጀሉ የተፈጸመበትን መሳሪያ ኤግዚቢት ተደርጎ አልተጠቀሰም
።ስለዚህ የተከበረው ፍ/ቤት በወ/ስ/ስ/ህግ አንቀጽ 143/1 እና 2 መሠረት ይህ የተያዘው ኤግዚቢት

• ቁጥሩ 17292 የሆነውን የክላሽ መሳሪያ እና ሶስት ጥይት እንደ ኤግዚቢት እንዲያዝልን እንጠይቃለን ።

የማይነበብ የዐ/ህግ ስምና ፊርማ አለበት ።

✍ ተርጓሚ፦መሀመድ ሀሰን የሱፍ

የመ/ቁጥር ፦0205655

ቀን ፦26/05/201
ዳኞች

አምዴ ጋቢሳ

ሁሴን ሀሰን

መሀመድ አብደላ

ከሳሽ ፦ የኦሮ/ብሄ/ዞን ዐ/ህግ

ተከሳሽ/ተከሳሾች፦ 1, አህመድ አብዱ ጣሂር

የኦሮሞ ብሄረሰብ ዞን ፍትህ መምሪያ ዐ/ህግ በቁጥር 3129 በቀን 26/05/2015 በተጻፈው ተከሳሽ በከባድ የሰው
ነፍስ ግድያ ወንጀል ተከሷል በማለት የክስ ቻርጅ አቅርቧል ። ስለዚህ መዝገቡ ተከፍቶ ለችሎት ቀርቧል።

ትዕዛዝ

የኬሚሴ ከተማ ማረሚያ ቤት የዐ/ህግን ክስን እና የፍ/ቤቱን መጥሪያ ወረቀት ለተከሳሹ ሰጥቶት ተከሳሹንም
በቀን 05/04/2015 ዓ.ም ቀነ ቀጠሮ እንዲያቀርብ ሆኖ ተከሳሽም የክስ ተቃውሞ ካለው

✍ ተርጓሚ፦መሀመድ ሀሰን የሱፍ

የመዝ/ቁጥር፦05655

ቀን 04/07/2015
ዳኞች

ፈጠነ

አምዴ ጋቢሳ

ሁሴን ሀሰን

ከሳሽ ፦የኦሮ/ብሄ/ዞን/ዐ/ህግ ዳኒኤል አሰፋ፡ቀረበ

ተከሳሽ፦ አህመድ አብዱ ጣሂር :ቀረበ

ተከሳሽ ጠበቃ ይዤ እንድቀርብ ቀጠሮ እንዲሰጠኝ በማለት አሳስቧል።

ትዕዛዝ

ተከሳሽ በግሉ ጠበቃ ይዞ ቢቀርብ ለመጠበቅ ቀጠሮ ለ 02/08/2015


ቀን 02/08/2015

ዳኞች

1, አሊ መሀመድ

2, ሁሴን ሀሰን

3. አምዴ ጋቢሳ

ከሳሽ ፦ የኦሮ/ብሄ/ዞን ዐ/ህግ ሁሴን አደም........ቀረበ

ተከሳሽ/ተከሳሾች፦ 1, አህመድ አብዱ ጣሂር ........ቀረበ

ተከላካይ ጠበቃ ፦ አሊ መሀመድ .............አልቀረበም

መዝገቡ ያደረው የተከሳሽ ጠበቃን ለመጠበቅ ነበር : ቀርቧል።ነገር ግን በጸጥታ ችግር ምክንያት
አልተሰራም።

✍ ተርጓሚ፦መሀመድ ሀሰን የሱፍ

ትዕዛዝ
ክሱን ለመስማት ቀጠሮ ለ 25/08/2015

መዝ/ቀጥር:05655

ቀን : 25/08/2015

ዳኞች

1.አሊ መሀመድ አደም

2.አምዴ ጋቢሳ

3.ሁሴን ሀሰን

ከሳሽ ፦ የኦሮ/ብሄ/ዞን ዐ/ህግ አህመዲን መሀመድ ........ቀረበ

ተከሳሽ፦ 1, አህመድ አብዱ ጣሂር ........ቀረበ

መዝገቡ ያደረው ተከሳሽ ጠበቃ ቢቀርብ ለመጠበቅ ነበር, አልቀረበም። መንግስት ጠበቃ ያቁምልኝ
በማለት አሳስቧል።

ተከላካይ ጠበቃ.፦አሚናት ኡመር : ፍ/ቤቱ ያቆመለት

°ተከሳሽ ፦ አህመድ አብዱ ጣሂር የሆነው አድራሻ አርጡማ ፉርሲ ወረዳ ጎልቦ አርባ ቀበሌ የሆነው ቀርቦ
የዐ/ህግ ክስ ተነቦለት ከተገነዘበ ቡሃላ ተከላካይ ጠበቃው የክስ ተቃውሞ የለንም ብሏል። ተከሳሽም ወንጀሉን
አልፈጸምኩም ጥፋተኛ አይደለሁም በማለት ክዶ ተከራክሯል። ዐ/ህግም ምስክሮች ስላሉን አቅርበን
እንድናሰማ ቀጠሮ ይሰጠን በማለት አሳስቧል።

✍ ተርጓሚ፦መሀመድ ሀሰን የሱፍ

ትዕዛዝ
የዐ/ህግ ምስክሮችን ለመጠበቅ ቀጠሮ 22/09/2015

ቀን 22/09/2015

ዳኛች

1, አሊ መሀመድ

2, ሁሴን ሀሰን

3, አምዴ ጋቢሳ

ከሳሽ ፦ የኦሮ/ብሄ/ዞን ዐ/ህግ ሁሴን አደም........ቀረበ

ተከሳሽ፦ አህመድ አብዱ ጣሂር ........አልቀረበም

ተከላካይ ጠበቃ፦አሚናት ኡመር .........ቀረበች

መዝገቡ ያደረው የዐ/ህግ ምስክሮችን ከቀረቡ ለመጠበቅ ነበር። አልቀረቡም

ዐ/ህግ አንድ ቀጠሮ ይሰጠን በማለት አሳስበዋል።

ትዕዛዝ

የዐ/ህግ ምስክሮችን ለመጠበቅ ቀጠሮ ለ 27/10/2015

ቀን 27/10/2015

ዳኛች

1.አሊ መሀመድ አደም

2.ሁሴን አደም

3.አምዴ ጋቢሳ

✍ ተርጓሚ፦መሀመድ ሀሰን የሱፍ

ከሳሽ ፦ የኦሮ/ብሄ/ዞን ዐ/ህግ ቀልቤሳ ዊርቱ........ቀረበ


ተከሳሽ፦ አህመድ አብዱ ጣሂር ........ቀረበ

ተከላካይ ጠበቃ፦አሚናት ኡመር .........ቀረበች

መዝገቡ ያደረው የዐ/ህግ ምስክሮችን ከቀረቡ ለመጠበቅ ነበር። አልቀረቡም

ዐ/ህግ ምስክሮቼን እንድናቀርብ ቀጠሮ ይሰጠን በማለት አሳስቧል ።

ትዕዛዝ

የዐ/ህግ ምስክሮችን ለመጠበቅ ቀጠሮ ለ 06/02/2016

መዝ/ቁጥር 05655

ቀን 06/02/2016

ዳኞች

1.አሊ መሀመድ አደም

2.ሁሴን ሀሰን

3.አምዴ ጋቢሳ

ከሳሽ ፦ የኦሮ/ብሄ/ዞን ዐ/ህግ ሁሴን አደም........ቀረበ

ተከሳሽ፦ አህመድ አብዱ ጣሂር ........ቀረበ

ተከላካይ ጠበቃ፦አሚናት ኡመር .........አልቀረበችም

መዝገቡ ያደረው የዐ/ህግ ምስክሮችን ከቀረቡ ለመጠበቅ ነበር። አልቀረቡም

ዐ/ህግ ምስክሮችን እንድናቀርብ ተለዋጭ ቀጠሮ ይሰጠን በማለት አሳስቧል።

✍ ተርጓሚ ፦ መሀመድ ሀሰን የሱፍ


ትዕዛዝ

የዐ/ህግ ምስክሮችን ለመጠበቅ ቀጠሮ ለ 05/03/2016

ቀን 05/03/2016

ዳኞች፦1, አሊ መሀመድ

2, ሁሴን ሀሰን

3, አምዴ ጋቢሳ

ከሳሽ፦ዐ/ህግ ቀልቤሳ ዊርቱ ......... ቀረበ

ተከሳሽ ፦አህመድ አብዱ ጣሂር......... ቀረበ

ተከላካይ ጠበቃ፦ አሚናት ኡመር ..........ቀረበች

መዝገቡ ያደረው የዐ/ሀግ ምስክሮች መቅረብ ለመጠበቅ ነበር በዚህም መሠረት ሁለት ሰዎች ቀርበው
የምስክርነት ቃላቸውን ሰጥተው ቃላቸው በቴፕ ተቀድቷል ።

ትዕዛዝ

የተከሳሽ መከላከያ ምስክሮች መቅረብን ለመጠበቅ ቀጠሮ ለ 11/04/2016

የመዝ/ቁጥር፦0205655

ቀን፦5/03/2016

ዳኞች፦1.አሊ መሃመድ

2.ሁሴን ሀሰን

3.አምዴ ጋቢሳ

✍ ተርጓሚ ፦ መሀመድ ሀሰን የሱፍ


ከሳሽ፦ዐ/ህግ ቀልቤሳ ዊርቱ ......... ቀረበ

ተከሳሽ ፦አህመድ አብዱ ጣሂር......... ቀረበ

ተከላካይ ጠበቃ፦ አሚናት ኡመር ..........ቀረበች

መዝገቡ ያደረው የዐ/ህግ ምስክሮችን ከቀረቡ ለመጠበቅ ነበር። ተሟልተው ቀርበዋል ።ዐ/ህግም ጭብጥ
ያስያዘው ምስክሮቻችን ለክሳችን እንዲመሰክሩልን በማለት ጭብጥ አስይዘዋል።

1 ኛ የዐ/ህግ ምስክር

ስም፦አብዱሶመድ ሁሴን እድሜ፦13 ስራ ፦ ተማሪ አድራሻ ወረዳ ፦ አርጡመሠ ፉርሲ ቀበሌ፦ጎልቦ አርባ ዛሬ
ምስክር ሁኜ ነው የመጣሁት ፡ ተከሳሽን አውቀዋለሁ ፡ አህመድ አብዱ ጣሂር ይባላል ፡ ዝምድናም ጠብም
አለን።

የዐ/ህግ ዋና ጥያቄ የምስክር መልስ

ተከሳሹ አባቴን ገድሎ ነው የተከሰሰው። የገደለውም በቀን 27/01/2015 ከቀኑ ከ 6:00 _ 7:00 ባለው ነው።
ቦታውም ጎልቦ አርባ ቀበሌ ጎጥ ቡርቃ ይባላል ። በዚህ ቀን የአባቴ ታላቅ የአምስት ልጆች አባት ጋር ሁነን
ከእርሻ ስንገባ ውሃ ቅዳልኝ ብሎኝ ከዚያም ቡሃላ እኛ ወደ ወንዝ ስንወርድ ተከሳሹ ድንጋይ ወደ ታች
ወረወረብን። እኛም ሸሽተን ገብተን ለአባቴ ተናገርን። አባቴም ይህንን ሰምቶ ከቤት ሲወጣ ሲመታው
አይቻለሁ። አባቴ ተመትቶ የሞተበት ቦታ ቡርቃ ይባላል። ተከሳሹ ከታላቅ ወንድሙ ጋር ነው ። ተከሳሹ
አባቴን በጥይት የመታው ቀኝ እግሩን፣ልቡ ላይ እንዲሁም ግንባሩ ላይ መትቶት ወደ ፊት ወጣ። እሱ ሲመታ
እኛ ወደ ታች ሮጥን ።ከዚያም እናቴ ወደ ታች ሩጣ ደርሳ እሱን አንስተው ወደ ላይ መለሱት። ይህ ተከሳሽ
አባቴን በክላሽ ጥይት መትቶት እኛ ወደ ታች ሄደን እሱጋ ስንደርስ ሞቷል ይህን አይቻለሁ።

የተከሳሽ ጠበቃ መስቀለኛ ጥያቄ የምስክር መልስ

አባቴን ተከሳሹ ሲመታው ከበትር ውጪ አንድም ነገር በእጁ አልያዘም ነበር። አባቴ ከቤት ወጥቶ በመንገድ ላይ
ወደ ታች ሲሄድ ነው ተከሳሹ የመታው ፡ ቤታችን እና የተከሳሹ ቤትም አይራራቅም። ተከሳሹ አባቴን
ሲመታውም ከቤቴ ሁኜ ነው ያየሁት፡ እንዲሁም ጥይቱም ሲተኮስ እኔ ከቤት ወጥቼ እናቴ ወደዛ እየሮጠች
ነበር። ከቦታው ስደርስ አባቴ ሞቷል። ተከሳሹን ደግሞ ሰዎች ይዘውት ወደ ቤት እየመለሱት ነበር።

✍ ተርጓሚ ፦ መሀመድ ሀሰን የሱፍ


የዐ/ህግ ድጋሜ ጥያቄ የምስክር መልስ

ተከሳሹ አባቴን ሲመታው ቤታችን እና የተከሳሹ ቤት ስለሚቀራረብ አይቻለሁ ።

የፍ/ቤቱ ማጣሪያ ጥያቄ የምስክር መልስ

ተከሳሹ አባቴ ላይ ተኩሶ ሲገለው በአይኔ አይቻለሁ።

2 ኛ የዐ/ህግ ምስክር

ስም፦ሀሊማ መሀመድ ጅብሪል እድሜ፦40 ስራ፦የቤት እመቤት አድራሻ፦ አርጡማ ፉርሲ ወረዳ ጎልቦ
አርባ ቀበሌ

ዛሬ ምስክር ሁኜ ነው የመጣሁት፡ተከሳሽን አውቀዋለሁ አህመድ አብዱ ጣሂር ይባላል። ዝምድና አለን


ባለቤቴ እና የተከሳሹ አባት የአጎትማማች ልጆች ናቸው። እሱ የተያዘው ባለቤቴን ገድሎት ነው። ሲገለውም
አይቻለሁ፡የሞተውም ሁሴን በሺር ይባላል ።

የዐ/ህግ ዋና ጥያቄ የምስክር መልስ

በቀን 27/01/2015 ከቀኑ 6:30 ነው። በአርጡማ ፉርሲ ወረዳ ጎልቦ አርባ ቀበሌ የሞተበት ጎጥ ቡርቃ ይባላል።
የመታውም ምክንያቱ ከዚህ በፊት ወንድሙ መሀመድ አብዱ ጣሂር የሚባል የአምስት ልጆች አባት ነው
ከባለቤቴ ጋር ያጣላቸው። ባለቤቴ ደግሞ ጤና አጥቶ ነበር: እኔ ነኝ የምንከባከበው ከዘመዶቼ ጋር : የዚህን ጤና
የሌለውን ሰው ልጆች አባረው ውሃ ቅዱልን አላቸው። ትንሹ ልጄ አጥር ስር ቆሞ ነበር: ትልቁ ልጄ ደግሞ እኔ
የትምህርት ስኣት እየረፈደብኝ ኘው እኔ ውሃ አልቀዳም ሲለው ድንጋይ ወርውሮበት ትልቁን ልጅ ወደ ወንዝ
እንዲሄድ አደረገ ትንሹ ልጅ መጥቶ በሺር የት አለ ሲባል መሀመድ አብዱ ወደ ወንዝ አባሮታል አለኝ ለምን
ስለው ውሃ ቅዱልኝ ብሎን ነው።ባለቤቴ ጤና የለውም ተኝቶ ነበር : ተንስቶ ባዶ እጁን ሰይዲ የሚባለው ወደ
መስጂድ ሲሄድ አይቶት እሱን በእጁ ይዞ እነሱን ለቆ ወደኔ ቤት እየተመለሰ ነበር። ሊመለስ ሲል ሰይድ
የሚባለው ለሌላው ደወለለት ይህኛው ወደ ቤት ሲመለስ ተከሳሹ ደግሞ በስተጀርባ መጥቶ በስተጀርባው
በመሳሪያ ተኩሶ መታው። ምንድነው ብዬ ቆርቆሮ ተመታ እንዴ ብዬ በስተጀርባ ዙሬ ሳይ ባለቤቴ ወድቋል። እኔ
ስጮህ ሰዎች ተሰባሰቡ።በስተጀርባው ተመቶ በልቡ ላይ ወጣ ከሜዳ እየገባን ነው ጥፋት ምንም የለም።
ጎረቤትም ሩጠው እሱጋ ሲደርሱ እሱ ሞቷል። ተከሳሹን ይዘውት ወደ ቤቱ መለሱት።

✍ ተርጓሚ ፦ መሀመድ ሀሰን የሱፍ


0205655

የተከሳሽ ጠበቃ መስቀለኛ ጥያቄ የምስክር መልስ

መሳሪያው ሲተኮስ እኔ ቤት ነበርኩ የመንገዱ እርቀትም በመንገዱ መሀል አጥር አለ። ሁለታቸውንም አያለሁ ፣
እሱ ሲተኩስም አይቻለሁ፣ እንዲሁም መሳሪያ ይዞ ወደ ላይ ሲመለስ አይቻለሁ ። እነሱ ከቤት ሶስት አላቸው ፡
መሳሪያው ሲተኮስ የወንድሙንም ሚስት

አይቻታለሁ ፡ እሷ ጩሃ ተከሳሹ በጉልበት ከሷ ላይ ሲነጥቅ አይቻለሁ ፣ እንዲሁም አህመድ ባለቤቴን


ሲመታው አይቻለሁ። ለአህመድ አብዱ ሰይዲ ነው የደወለለት እንደደወለለት ያየሁት ቤት መጥቶ እሱን
አንስቶ ውጣ አለው እንጂ ሲደውል አላየሁም። አህመድ አብዱ እና ሁሴን በሺር ተጣልተዋል፡ በጀርባ መሬት
ከሱ ላይ አለን፡የሁሴን በሺርን ትልቁን ቤት እንካፈላለን ከዚህ ላይ እጠር አለን። ይህንን ትተው ለሁሴን በሺር
አጥር እኔና ባለቤቴ አንድ ቀን ሙሉ አይደርቄ/አጉሎ ተከልን። ይህ መሀመድ የሚባለው እርቅ አውርዶ ነበር እሱ
አሁን ሳውዲ ነው ያለው።

የዐ/ህግ በድጋሜ ጥያቄ የምስክር መልስ

በዛን ቀን ተከሳሹ እና ባለቤቴ ሊጋደሉ የቻሉት ያኛው ሲደውልለት ይህኛው ጠብቆ በመምታት፡ ጤና
የሌለውን ሰው እና መሳሪያ ከእጁ የሌለውን በልጅ ምክንያት ነው የገደሉት።

የፍ/ቤቱ ማጣሪያ ጥያቄ የምስክር መልስ

ከሰፈሬ ሟች አንስተው ቀብረው እኔ የተከሳሹን ቀብር አልሄድኩም በማለት መስክራ ተመልሳለች።

ትዕዛዝ

መዝገቡን መርምረን ተከሳሹ ይህንን ወንጀል አልፈጸምኩም ጥፋተኛ አይደለሁም በማለት ክዶ ቢከራከርም
የዐ/ህግ ምስክሮች በክሱ መሠረት ስለመሰከሩበት በወ/ስ/ስ ህግ አንቀጽ 142 መሰረት እንዲከላከል በሙሉ
ድምጽ ብይን ሰጥተናል።

የተከሳሽን መከላከያ ምስክሮችን ለመጠበቅ ቀጠሮ ለ 11/04/2016

✍ ተርጓሚ ፦ መሀመድ ሀሰን የሱፍ


መዝ/ቁጥር፦05655

ቀን፦11/04/2016

ዳኞች፦አሊ መሀመድ ፣ አምዴ ጋቢሳ ፣ ሂንዲያ ሱልጣን

ከሳሽ፦ዐ/ህግ ቶማስ መገርሳ ......... ቀረበ

ተከሳሽ ፦አህመድ አብዱ ጣሂር......... ቀረበ

ተከላካይ ጠበቃ፦ አሚናት ኡመር ..........ቀረበች

መዝገቡ ያደረው የተከሳሽን መከላከያ ምስክር ለመጠበቅ ነበር በዚሁ መሠረት ቀርበዋል። ነገር ግን በስራ
ብዛት ምክንያት አልተሰራም።

ትዕዛዝ

የተከሳሽ መከላከያ ምስክሮችን ለመስማት ቀጠር ለ 05/06/2016

ቀን፦05/06/2016

ዳኞች፦አሊ መሀመድ

ሁሴን ሀሰን

መሀመድ አብደላ

ከሳሽ፦ዐ/ህግ ቶማስ መገርሳ ......... ቀረበ

ተከሳሽ ፦አህመድ አብዱ ጣሂር......... ቀረበ

ተከላካይ ጠበቃ፦ አሚናት ኡመር ..........ቀረበች

መዝገቡ ያደረው የተከሳሽን መከላከያ ምስክር መቅረብን ለመጠበቅ መከላከያ ምስክሮቹ ሁለት ሰዎች
ቀርበው የምስክርነት ቃላቸውን ሰጥተው ቃላቸው በቴፕ ተቀድቷል።
✍ ተርጓሚ፦ መሀመድ ሀሰን የሱፍ

ትዕዛዝ

መዝገቡን መርምረን ውሳኔ ለመስጠት ቀጠሮ ለ 22/06/2016

መዝገ/ቁጥር/0205655

ቀን፦22/06/2016

ዳኞች፦አሊ መሀመድ አደም ፣ ሁሴን ሀሰን ፣ መሀመድ አብደላ


ከሳሽ ፦ዐ/ህግ አህመዲን መሀመድ ........ቀረበ

ተከሳሽ፦ አህመድ አብዱ ጣሂር ........ቀረበ

ተከላካይ ጠበቃ፦አሚናት ኡመር .........ቀረበች

መዝገቡ ያደረው መርምረን ውሳኔ ለመስጠት ነበር ፡ ነገር ግን መዝገቡ የተጻፈ የመከላከያ ምስክሮችን
መልስ ስለሌለው አልተመረመረም።

ትዕዛዝ

የመከላከያ ምስክሮች መልስ ተጽፎ መዝገቡ ውስጥ ተካቶ ይከፈት።

መዝገቡን መርምረን ውሳኔ ለመስጠት ቀጠሮ ለ 06/07/2016

ቀን፦06/07/2016

ዳኞች፦አሊ መሀመድ አደም

ሁሴን ሀሰን

መሀመድ አብደላ

ከሳሽ ፦ዐ/ህግ አህመዲን መሀመድ ........ቀረበ

ተከሳሽ፦ አህመድ አብዱ ጣሂር ........ቀረበ

ተከላካይ ጠበቃ፦አሚናት ኡመር .........ቀረበች


መዝገቡ ያደረው መርምረን ውሳኔ ለመስጠት ነበር ባደረው መሠረት አልተመረመረም። ምክንያቱም
የመከላከያ ምስክሮች ቃል ኮፒ ተደርጎ አልተያያዘም።

✍ ተርጓሚ ፦መሀመድ ሀሰን የሱፍ

ትዕዛዝ 0205655

የመከላከያ ምስክሮች ቃል ኮፒ ተደርጎ ከመዝገቡ ጋር ይያያዝ።

መዝገቡን መርምረን ውሳኔ ለመስጠት ቀጠሮ ለ 20/07/2016

ቀን፦ 05/06/2016

ዳኞች፦አሊ መሀመድ

ሁሴን ሀሰን

መሀመድ አብደላ

ከሳሽ፦ዐ/ህግ ቶማስ መገርሳ ......... ቀረበ

ተከሳሽ ፦አህመድ አብዱ ጣሂር ከማረሚያ ቤት......... ቀረበ

ተከላካይ ጠበቃ፦ አሚናት ኡመር ..........ቀረበች

መዝገቡ ያደረው የተከሳሽ መከላከያ ምስክርን ለመስማት ነበር ፡ ባደረው መሰረት ተሟልተው ቀርበዋል።
የተከሳሽ ጠበቃም ጭብጥ ያስዘው ምስክሮቻችን የሚመሰክሩልን ተከሳሽ በቀን 27/01/2015 ሟች ሁሴን
በሺርን ገድሏል፡ነገር ግን ተከሳሽ የገደለው ሟች እሱን ሊመታው ሲመጣ ራሱን ለመከላከል በመሆኑ፡ሟች
ብረት ይዞ ይህንን ተከሳሽ ሲመታው ብረቱን ለመከላከል ብሎ መሳሪያ ይዞ ነበር ተከሳሹ ላይ መሳሪያውን
ሲይዝ በዚህ ምክንያት እዚህ መሀል ላይ መሳሪያ ተተኩሶ ሟች ህይወቱ ያለፈ መሆኑን በማለት
እንዲመሰክሩልን በማለት የጉዳዩን ጭብጥ አስይዛለችች።

✍ ተርጓሚ ፦መሀመድ ሀሰን የሱፍ


0205655

1 ኛየተከሳሽ መከላከያ ምስክር

ስም..................መሀመድ አልይ

እድሜ ................45

ስራ......................አርሶ አደር

አድራሻ .......ወረዳ ፦ አርጡማ ፉርሲ ቀበሌ ፦ ጎልቦ አርባ ዛሬ ለምን እንደመጣሁ አውቃለሁ የተከሳሽ
መከላከያ ምስክር ሁኜ ነው የመጣሁት ተከሳሽን አውቀዋለሁ አህመድ አብዱ ይባላል። ከእርሱ ጋር ዝምድናም
ሆነ ጠብ የለንም መታሰሩን አውቃለሁ። መታሰሩን አውቃለሁ ሁሴን በሺርን ገድሏል ተብሎ ነው። ሲገለው
አላየሁም።

የተከሳሽ ጠበቃ ዋና ጥያቄ የምስክር መልስ

ይህ ተከሳሽ የተያዘው ሰው ገድለሃል ተብሎ ነው ለራሱም ተመቷል።

በቀን 27/1/2015 ዓ.ም 6፡00 ሰኣት ላይ በአርጡማ ፉርሲ ወረዳ በጎልቦ አርባ ቀበሌ በሚባለው አህመድ አብዱ
ጣሂር እጁን ተመቷል ሁሴን በሺር ደግሞ ሞቷል።እኛ ወደ መስጅድ እየሄድን ነበር መሳሪያ መተኮሱን ሰማን
እንጂ በአይናችን አላየንም። መሳሪያው ሲተኮስ ወደዛ ሮጥን ሰዎችም እየወጡ ነው እነሱ ጋር ስንደርስ።
የተመታው ወንድሙ ሰይድ ይባላል እዛው ነበር ፡ መትቶ አልፏል ይህኛውንጉሥ አልፎታል። ሁሴን በሺር
የሚባለው እብድ ነው የራሱን ቤት አቃጥሏል። ጸብ እንዳላቸው አላውቅም። አብዱሶመድ ሁሴን በሺር ወደዛ
መጥቶ እዛው ነበር። ይህ ሟች ወይም ይህ ሁሴን በሺር በእጁ ገጀራ ይዟል፡ተከሳሽን በገጀራ መታው። ይህ
ሁሴን በሺር የተመታውም ከአህመድ ቤት በር አጠገብ ነው። ወንድሙንም መትቶ አህመድ አብዱንም
ለመምታት ወደ ቤቱ ሄደ እሱ አያቱ ጋር ተቀምጦ ነበር።

✍ ተርጓሚ ፦መሀመድ ሀሰን የሱፍ


0205655

የዐ/ህግ መስቀለኛ ጥያቄ የምስክር መልስ

በቀን 27/1/2015 6:00 ሰኣት ላይ ነው በአርጡማ ፉርሲ ወረዳ ጎርቦ አርባ ቀበሌ ይባላል ቦታውም ከአያቱ ቤት
ፊት ለፊት ጸብ የላቸውም እሱ እብድ ነው። እብድ መሆኑ የታወቀው ሰውንም ቤቱንም አቃጥሏል። እሪታ
ሲሰማ ሩጠን ለሱ ቤት ሰራንለት። ይህ ሟች ሲሞት እኔ እዛው ሰፈር ነበርኩ ለጁሙኣ ወደ መስጅድ እየሄድኩ
ነበር ሌላ ሰው አልነበረም መሀመድ ጋር ሄድን ፡ ተከሳሹ ግራ እጁን ተመቶ ነበር፡ደም አይቻለሁ ፡ ይህ የሚጎላው
በክላሽ ነው የተመታው። ሁለት ጥይት ሲተኮስ እኔ እና መሀመድ ሩጠን ከቦታው ስደረስን ተከሳሹ ተመትቶ
ቆሟል ሟችም ሞቷል። ሟች ፊቱ ላይ ተመቷልብ ሌላ ቦታ አላስተዋልኩም ፡ አላየሁምም አጠገቡ ቆሜ ነበር
ደንግጫለሁ። እነሱ ሲመታቱ እኔ አላየሁም፡ ሟች ገጀራ ይዟል ጩቤ ወገቡ ላይ አለ አላወጣም ቀደም ብሎ
አውጥቶ መልሶት እንደሆነ አላውቅም እጂ ግን ከወገቡ ላይ ታጥቋል። የተመታበት ቦታው የተከሳሹ ነው ፡
ሟችና ተከሳሹ ጎረቤት አይደሉም ይራራቃል። የተመታቱበትን ምክንያት አላውቅም ድሮውንም እብድ ነው
ይባላል። እኛ እዛው ስንደርስ ሌላ ሰው አላየንም ተከሳሱ የጦር መሳሪያ መሬት ላይ ጥሎ ሸሸ እኛ መሳሪያውን
አነሳን።አስታውሳለሁ ተከሳሹ የለበሰው ነጭ በርበራ ነው ጫማውን አላስታውስም ወደ ታች ሸሸ። እኛ
ከሰዎች ጋር ሟችን ይዘን መስጅድ አደረስን። ስናነሳው ሁለተኛው ምስክር ጋር አብረን ነበርን በዚያው ቀን
11:00 ላይ ተቀበረ።

የተከሳሽ ጠበቃ ተጨማሪ ጥያቄ የምስክር መልስ

ሟች ሳንጃ/ጩቤ ወገቡ ላይ ታጥቋል ገጀራው ደግሞ እዛው ተቀምጧል ሚስማር መንቀያውም እዛው ነው
ተከሳሹ እና ሟች ከዚህ በፊት ጸብ እንዳላቸው አላውቅም።

የፍ/ቤቱ ማጣሪያ ጥያቄ የምስክር መልስ፦ የለንም

2 ኛየተከሳሽ መከላከያ ምስክር

ስም፦መሀመድ አብዱ ጣሂር እድሜ፦35 ስራ፦አርሶአደር አድራሻ፦አርጡማ ፉርሲ ወረዳ ጎርቦ አርባ ቀበሌ

ዛሬ የመጣሁበትን አውቃለሁ ፡ የመከላከያ ምስክር ሁኜ ነው የመጣሁት፡ተከሳሽን አውቀዋለሁ አህመድ አብዱ


ጣሂር ይባላል ። ከእሱ ጋር ዝምድና አለን ወንድሜ ነው። መታሰሩን አውቃለሁ ሁሴን በሺር የሚባለውን ሰው
ገድሏል ተብሎ ነው እኔ ገድሏል ነው የምለው።
✍ ተርጓሚ ፦ መሀመድ ሀሰን የሱፍ

የተከሳሽ ጠበቃ ዋና ጥያቄ የምስክር መልስ

ይህ ተከሳሽ የተያዘው ሰው ገድለሃል ተብሎ ነው ለራሱም ተመቷል።

በቀን 27/1/2015 6:00 ሰኣት ላይ በአረርጡማ ፉርሲ ወረዳ ጎርቦ አርባ ቀበሌ ቡርቃ ጎጥ ይባላል እኔ መስጅድ
እየሄድኩ ነበር ያየሁት መጀመሪያ ሁሴን በሺር የአህመድን ወንድም ሰይድ የሚባለውን በብረት መትቶት ሄደ
እኛ ደግሞ ከመስጂድ እየወጣን ነበር ከዛም ሁሴን በሺር ከአህመድ ቤት ሄዶ ከአህመድ ጋር ተያይዘው ሲመታቱ
አይቻለሁ። አህመድ መሳሪያ ይዟል ተያይዘው የኮሰውን አላውቅም መሳሪያው ተተኩሶ ስዞር አህመድ ሄዷል።
ሁሴን በሺር ወድቋል ሁሴን በሺር እብድ ነው ቤቱን አፍርሷል እኛ ደግሞ ሰራንለት አብዶ ታስሮ ይቀመጣል
ሰውን ያሯሩጣል ይህንን አይቻለሁ ሁሴን በሺር አጠገብ ብረት ነበር ይህንን አይቻለሁ ሌላ ነገር አላየሁም።

የዐ/ህግ መስቀለኛ ጥያቄ የምስክር መልስ

ተከሳ እና ሟች ከዚህ በፊት ጸብ የላየውም ዝምድና አላቸው። እኔ ወንጀሉ ሲፈጸም እኔ ከመስጅድ እያወጣሁ
ነው እኔና መሀመድ አሊ አብረን ነን ርቀት የለውም ማዶ ናት ማዶ ይተያያል 6:00 ሰኣት ላይ ለሶላት መስጂድ
እየሄድን ነበር ሲያያዙ እና ሲሯሯጡ አይቻለሁ ነገር ግን የተኮሰውን አላውቅም። ሁሴን ከፍ አህመድ ቤት ሄዶ
ተያያዙ ተከሳሹ መሳሪያ ይዟል ግን መመታታቸውን አላየሁም ሟች ረጅም የብረት በትር ይዟል ግን ተከሳሹ
ሲመታ አላየሁም። ሟች እና ተከሳሽ ተያያዙ የተያያዙት ደግሞ በክላሽ ሰደፍ ነው ሁለት ጥይት ተተኮሰ ሟች
እግሩ ላይ ተመትቶ ወደቀ። ተከሳሹ መሳሪያው መሬት ጥሎ ሄደ የት እንደሄደ ግን አላየሁም የለበሰውን ልብስ
አላየሁም ራቅ ብሏል የለበሰውን ልብስ አላየሁም።ተከሳሹ ደግሞ ሽርጥ አሸርጧል። ተከሳሹ ግራ እጁን ነው
የተመታው ፡ እነሱጋ ስንሄድ እኔና ከኔ ጋር የመጣው ምስክር አለ። ይህ ሰው ጋር ደግሞ እነ አህመድ
አደም፣ሰይዱ የሱፍ፣አህመድ ሰይድ፣ እብራሂም ብዙ ሰዎች ነበሩ፣የተቀበረበት ቦታ እኔ ሄጃለሁ ምሽትልቅ
12:00 ሰኣት ነበር አንደኛ ምስክሩም ከኔ ጋር ሄዷል። ሟች መጀመሪያ ሰይዲን ነው የመታው። ከመስጂድ
ሲወጣ እብድ ስለሆነ እንዲሁ መታው። ሀኪም ቤት ሄዷል ግን ምን እንደተሰጠው አላውቅም ።

የተከሳሽ ጠበቃ ደጋሚ ጥያቄ የምስክር መልስ

ወንጀሉ የተፈጸመበት ቦታ ከኛ በፊት ሌላ ሰው የለም፡ እኛ መጀመሪያ በሩጫ ከቦታው ደርሰን ከዚያም ቡሃላ
ሌሎች ሰዎች ተሰባሰቡ። ተከሳሹ ሟችን ገድሎ እኔ ቀብር የሄድኩት እነሱ ዝምድና ስላላቸው እና ሟች ደግሞ
እብድ ስለሆነ ነው። ስለዚህ ካሁን በፊት ጸብ የላቸውም፡ ካሁን በፊት ከቤት ሸሽተን ነበር አሁን ግን
ተመልሰናል። ሟቹ ወንድም የለውም የበሰለ ነገርና የሚያስፈልገውን ነገር እኛው ነን የምናደርግለት ቤተሰብ
ስለሆንን ።
✍ ተርጓሚ ፦ መሀመድ ሀሰን የሱፍ

0205655

የፍርድ ቤቱ ማጣሪያ ጥያቄ የምስክር መልስ

እነሱ ሲጋደሉ እለቱ ጁሙኣ ነው እኛ ደግሞ ወደ መስጂድ እየሄድን ነው በዚያው ቀን ተቀበረ በማለት መስክሮ
ተመልሷል።

የተከሳሽ ጠበቃ ማሳሰቢያ

የቀረቡት ምስክሮች በቂ ስለሆኑ ተከሳሹ ሟችን አስቦበት አልገደለውም ማለት ነው ፡ የቀረበው የዐ/ህግ
ምስክርም በተከሳሹ እና በሟች መካከል ምንም ጸብ እንደሌለ፣ ከዚህ በፊት ሟች የአዕምሮ ህመምተኛ ስለሆነ
ማስረጃ መቅረቡን በተጨማሪ በሰው ምስክር የተጣራ በመሆኑ ፡ እንዲሁም ሟች ከተከሳሹ ቤት ሄዶ
ሊመታው ሲል የተመመታ በመሆኑ ፡ አሁን በተከሰሰበት ወንጀል ጥፋተኛ ሊያስብለው ስለማይችል፡ተከሳሹ
ጥፋተኛ ነው ቢባልም እንኳ ራስን መከላከል በማለፍ ተብሎ በህጉ አንቀጽ 541 መሰረት ጥፋተኛ እንዲባልልን
እና ተከሳሹ ወንጀሉን የፈጸመው ራስን መከላከል በማለፍ፣ እና የ ከዚህ በፊቱ ተከሳሽ ሰይድ አብዱ ጣሂር
የሚባለው የአህመድ አብዱ ጣሂር ወንድምን ባለፈው አመት ሟቹ መትቶት እስካሁን ከመሬት ላይ ያልተነሳ፡
ፓራላይዝ/ሽባ ሁኖ ለምስክርነት መምጣት እንኳ የማይችል መሆኑን አጣርተናል። በዚህ ምክንያት ከዚያ ቀን
ጀምሮ የአህመድ አብዱ ጣሂር ወንድም ከቤት ወጥቶ አያውቅም ሟች አዕምሮው ትክክል ባለመሆኑ ምክንያት
ስለሆነ ጥፋትን የፈጸመው ፡ ፍርድ ቤቱ ይህንን ከግምት ውስጥ በማስገባት የመሰለ ውሳኔ እንዲሰጥልን
ብላለች።

የዓቃቤ ህግ ማሳሰቢያ

ፍርድ ቤቱ የተከሳሽ መከላከያ ምስክሮችን ሰምቷል፡ በተሰሙት ምስክሮች መሰረት አስፈላጊውን ውሳኔ
እንዲሰጥልን በዚሁ መፍትሄ እንዲሰጠን እንጠይቃለን።

✍ ተርጓሚ ፦ መሀመድ ሀሰን የሱፍ


0205655

ትዕዛዝ

መዝገቡን መርምረን ውሳኔ ለመስጠት ቀጠሮ ለ 22/6/2016

የመ/ቁጥር ፦ 0205655

ቀን፦ 20/07/2016

ዳኞች አሊ መሀመድ አደም

ሁሴን ሀሰን

መሀመድ አብደላ

ከሳሽ፦ዐ/ህግ ቶማስ መገርሳ ......... ቀረበ

ተከሳሽ ፦አህመድ አብዱ ጣሂር ከማረሚያ ቤት......... ቀረበ

ተከላካይ ጠበቃ፦ አሚናት ኡመር ..........ቀረበች

✍ ተርጓሚ ፦ መሀመድ ሀሰን የሱፍ

መዝገቡ ያደረው ተመርምሮ ውሳኔ ለመስጠት ነበር ባደረው መሰረት በመከላከያ ምስክሮች የምስክርነት ቃል
ምክንያት ተያይዞ አልተመረመረም

ትዕዛዝ

መዝገቡን መርምረን ውሳኔ ለመስጠት ቀጠሮ ለ 11/08/2016


የማይነበብ የሶስት ዳኞች ፊርማ አለበት፧

0205655

ቀን፦11/08/2016

ዳኞች አሊ መሀመድ አደም

ሁሴን ሀሰን

መሀመድ አብደላ

ከሳሽ፦ዐ/ህግ ቶማስ መገርሳ ......... ቀረበ

ተከሳሽ ፦አህመድ አብዱ ጣሂር ከማረሚያ ቤት......... ቀረበ

ተከላካይ ጠበቃ፦ አሚናት ኡመር ..........ቀረበች

መዝገቡ ያደረው ለመመርመር ነበር ነገር ግን በስራ ብዛት ምክንያት ምርመራው አልተጠናቀቀም።

ትዕዛዝ

መዝገቡን መርምረን ውሳኔ ለመስጠት ቀጠሮ ለ 24/08/2016

ማረሚያ ቤቱ ተከሳሽን እንዲያቀርብ ይጻፍ።

የማይነበብ የሶስት ዳኞች ፊርማ አለበት

✍ ተርጓሚ ፦ መሀመድ ሀሰን የሱፍ


መዝገ/ቁጥር፦0205655

ቀን፦ 24/08/2016

ዳኞች፦

አሊ መሀመድ አደም

ሁሴን ሀሰን

መሀመድ አብደላ

ከሳሽ፦ዐ/ህግ ቶማስ መገርሳ ......... ቀረበ

ተከሳሽ ፦አህመድ አብዱ ጣሂር ከማረሚያ ቤት......... ቀረበ

ተከላካይ ጠበቃ፦ አሚናት ኡመር ..........ቀረበች

መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ውሳኔ ሰጥተናል

ውሳኔ

መዝገቡ ተከፍቶ ሊቀርብ የቻለው ዓቃቤ ህግ በቁጥር ፍ/መ 3129/2015 በቀን 26/05/2015 ተጽፎ በቀረበ ክስ
ሲሆን የክሱ ዝርዝርም ተከሳሽ የወንጀል ህግ አንቀጽ 539 (1)ሀ ስር የተደነገገውን በመተላለፍ ተከሳሽ ሰው
ለመግደል በማሰብ በቀን 27/01/2015 ዓ,ም ከቀኑ በግምት 6፡00 ሰአት ሲሆን በአርጡማ ፉርሲ ወረዳ ጎልቦ
ቀበሌ ልዩ ቦታው ቡርቃ ተብሎ በሚጠራበት ቦታ ልጅ መታ በሚል ምክንያት ሟች ሁሴን በሺር የሚባለውን
ይዞ በነበረው ቁጥሩ 17292 የሆነውን ክላሽ በሚባለው የጦር መሳሪያ በአንድ ጥይት ቀኝ እግሩ ፣ በአንዱ ጥይት
ልቡ ላይ እንዲሁም በአንድ ጥይት ግንባሩ ላይ መትቶ በማቁሰል ከባድ የሰው ነፍስ ግድያ ወንጀል ፈጽሟል ።
ተከሳሹም ለችሎት ቀርቦ ማንነቱ ከተረጋገጠ ቡሃላ ክሱ ተነቦለት ከተገነዘበ ቡሃላ በተከላካይ ጠበቃው ታግዞ
የተከሳሽ ተከላካይ ጠበቃም የክስ ተቃውሞ የለንም ሲል ተከሳሹ ወንጀሉን አልፈጸምኩም ጥፋት የለኝም
ብሎ ክዶ ተከራክሯል።

ዓቃቤ ህግም ምስክሮች እንዳሉት እና እንደቀረቡ በመግለፅ ይሰሙልን በማለት አሳስቦ ምስክሮቻችንም
ለክሳችን እንዲመሰክሩልን በማለት የጉዳዩን ጭብጥ አስይዟል።

✍ ተርጓሚ ፦ መሀመድ ሀሰን የሱፍ

1 ኛ የዐ/ህግ ምስክር፦ የሟች ልጅ ሲሆን ተከሳሽን እንደሚያውቀው ስሙን በመግለፅ ከተከሳሽ ጋር


ጸብም ዝምድናም እንዳላቸው፡የተከሰሰውም አባቱ የሆነውን ሟች ሁሴን በሺርን ገድሏል ተብሎ እንደሆነ፡
ሲገድለውም በአይኑ እንዳየ ገልጾ ፡ ተከሳሹ ወንጀሉን የፈጸመበት ቦታ፣ቀን እና ሰኣት ክሱ ላይ እንደተገለጸው
መሆኑ፡የግድያውም ምክንያት እሱ ከወንዝ ወደ ቤት ሲገባ ተከሳሽ መንገድ ላይ ጠብቆ ተመለስና ውሃ
በሀይላንድ ቅዳና አምጣ ብሎ እንዳዘዘው፡እሱም ተቀብሎት ወደ ወንዝ ሲመለስ ተከሳሹ በስተኋላው በድንጋይ
እንዳሯሯጠው በዚህ ሰኣት እሱም አምልጦ ወደ ቤቱ ገብቶ ለሟች አባቱ ተናግሮ ፡ በዚህ ሰኣት ሟችም በትር
ይዞ ከቤት ወጥቶ መንገዱ ላይ ሲደርስ ግራ እግሩን፣ልቡን እና ግንባሩን መትቶ እንደጣለው እያየሁ እንደነበረ
እና ሟች አጠገብ ስደርስ ነፍሱ እንደወጣች ፣ ሩጠው የመጡትም ሰዎች ተከሳሽን ይዘው ወደ ቤቱ
እንዳስገቡት በመግለጽ መስክሯል።

2 ኛ የዐ/ህግ ምስክር፦ የሟች ባለቤት እንደሆነች በመግለፅ ተከሳሽን እንደምታውቀው ስሙን


በመግለፅ፡የተከሰሰውም ባለቤቷ የሆነውን ሟች ሁሴን በሺርን ገድሏል ተብሎ እንደሆነ፡ሲገድለውም በአይኗ
እንዳየች ገልጻ ፡ ተከሳሹ ወንጀሉን የፈጸመበት ቦታ፣ቀን እና ሰኣት ክሱ ላይ እንደተገለጸው መሆኑን ገልጻ፡
ተከሳሽ ይህንን ወንጀል የፈጸመው ከዚህ በፊት የተከሳሽ እና የሟች ወንድሞች ጠበኞች ስለሆኑ ይህንን
ወንጀል ሊፈጽም ሲል ደግሞ ልጆቿ(የሟች ልጆች)ከወንዝ ወደ ቤት ሲገቡ ተከሳሽ መንገድ ላይ አይቷቸው
ውሃ ቅዱልኝ እንዳላቸው፣አነሱን በድንጋይ እንዳባረራቸው፣ትንሹ ልጅ አምልጦ ወደ ቤቱ እንደተመለሰ ፣
አንደኛው ልጅ ደግሞ ወደ ወንዙ እንደተመለሰ ወደ ቤቱ አምልጦ የመጣው ልጅ እንደነገራት ፣ በዚህ ሰአት
ሟች ባዶ እጁን ታሞ ከተኛበት ቦታ ተነስቶ ከቤት ወጥቶ ወደ ወንዝ የተመለሰውን ልጁን አይቶ ለመመለስ
መንገድ ላይ ሲወጣ ተከሳሽ በስተኋላው መጥቶ እግሩ ላይ ወገቡ ላይ እና ግንባሩ ላይ መሳሪያ ተኩሶበት
እንደመታው፣ከቤት ወጥታ ስታይ ሟቹ ባለቤቷ ተመቶ እንደወደቀ አይታ ጮህች በዚህ ስኣት ሰዎች
ተሰብስበው ተከሳሽን ወደ ቤቱ እንዳስገቡት፣የተከሳሽ አባት እና ሟች የአጎትማማች ልጆች እንደሆኑ፣ተከሳሽ
የሟችን የቀብር ስነ-ስርዓት እንዳልተገኘ በመግለፅ መስክራለች።

ዓቃቤ ህግም በዚሁ የሰው ምስክር ማሰማቱን እንዳጠናቀቀ በመግለጽ መፍትሔ እንዲሰጠው አሳስቧል።
ፍ/ቤቱም መዝገቡን መርምሮ አይቶ ተከሳሽ የተከሰሰበትን ወንጀል እንደፈጸመ ዓቃቤ ህግ አቅርቦ ባሰማው
የሰው ምስክር እንዳረጋገጠበት ገልጾ እንዲከላከል በማለት ብይን ሰጥቷል።

ተከሳሽም በቀ 0 05/06/2016 ዓ.ም በጻፈው ማመልከቻ የመከላከያ ምስክሮች እንዳሉት በመግለፅ በዝርዝር
አቅርቦ ከመዝገቡ ጋር አያይዟል።
በቀጠሮው ቀንም መከላከያ ምስክሮቹ ቀርበው፡ተከሳሽም መከላከያ ምስክሮቼ የሚመሰክሩልኝ እኔ ሟችን
መትቼ እንደገደልኩት እና ግን የገደልኩት ሟች እኔን ለመምታት ብረት ይዞ ከቤቱ ተነስቶ ከቤቴ ሲመጣ እኔም
ራሴን ለመከላከል ብዬ ሟች መሳሪያዬን ሲይዝብኝ ከመካከላችን ጥይት ተተኩሶ ሟችን መታው በማለት
የጉዳዩን ጭብጥ አስይዟል።

✍ ተርጓሚ ፦ መሀመድ ሀሰን የሱፍ

1 ኛ የመከላከያ ምስክር

ተከሳሽንም ሟችንም እንደሚያውቃቸው ገልጾ የተከሰሰውም ሟች ሁሴን በሺርን ገድሏል ተብሎ እንደሆነ፡
ሲገድለውም በአይኑ እንዳላየ ገልጾ ፡ ተከሳሹ ወንጀሉን የፈጸመበት ቦታ፣ቀን እና ሰኣት ክሱ ላይ እንደተገለጸው
መሆኑን በመግለፅ፡ተከሳ ወንጀሉን ፈጸመ የተባለው እሱ ሁለተኛው መከላከያ ምስክር ጋር ለጁሙኣ ሶላት ወደ
መስጂድ ሲሄዱ የመሳሪያ ተኩስ እንደሰሙ፡የመሳሪያ ድምጽ ወደ ሰሙበት ቦታ ተሯሩጠው ሲሄዱ ሟች
በመሳሪያ ተመትቶ ወድቆ እንደሞተ እና ተከሳሽም እጁ ላይ በገጀራ ተመትቶ ገጀራውን ሟች አጠገብ እንዳየ
እና ጩቤ/ሳንጃም ታጥቆ እንዳየ የተከሳሽም መሳሪያ እዛው መሬት ላይ ወድቆ እንዳዩ፣ተከሳሹም ከቦታው ወደ
ታች ሸሽት እንደነበረ፣ሟችንም ከወደቀበት አንስተው ወደ መስጂድ እንዳደረሱት፣ተከሳሹ እና ሟቹ ጉርብትና
እንደሌላቸው እና ቤታቸው እንደሚራራቅ፣ሟችም እብድ/የአዕምሮ ህመምተኛ እንደሆነና ሰፈር ውሰጥ
ሰዎችን በማሯሯጥ እንደሚታወቅ በመግለፅ መስክሯል።

2 ኛ የመከላከያ ምስክር

1 ኛው የመከላከያ ምስክር ገልጾ በመሰከረው መልክ በመመስከር ልዩነቱም ሟች መጀመሪያ ሰይድ የሚባለውን
የተከሳሽ ወንድምን በብረት መትቶ ተመልሶ ወደ ተከሳሽ ቤት ሄዶ ከተከሳሹ ጋር በእጅ እንደተያያዙ በርቀት
እንዳየ ፣ ሟች እና ተከሳሹ የተያያዙበት ቦታ አይቶ ከተከሳሹ በር ላይ እንደሆነ፣የመሳሪያ ድምጽ ሰምተው
ወደ ተጣሉበት ቦታ ሲሄዱ ሟች ተመትቶ ወድቆ እንዳየው ፣ እረጅም የብረት በትር አጠገቡ እንዳለ እና ሌላ
ነገር እንዳልያዘና፣ ተከሳሽም ሟች ከተመታ ቡሃላ የጦር መሳሪያውን ጥሎ እንደሄደ እና ወደየት እንደሄደ
እንዳላየ እና መሳሪያ የተኮሰውን ሰው እንደማያውቅ በመግለፅ መስክሯል።

እንግዲህ ክሱ እና የዐቃቤ ህግ ምስክርነት ቃል እንዲሁም የመከላከያ ምስክርነት ቃል ከዚህ በላይ እንደተገለጸው


ሲሆን እኛም መዝገቡን መርምረናል።

በ ምርመራችንም 1 ኛ የተከሳሽ የመከላከያ ምስክሮች የዐቃቤ ህግን የምስክርነት ቃልን አስተባብለዋል ወይንስ
አላስተባበሉም? 2 ኛ አላስተባበሉም የሚባል ከሆነ ተከሳሽ የፈጸመው የሰው ግድያ ወንጀል ዓቃቤ ህግ
በከሰሰበት አንቀጽ ስር የሚወድቅ ነው ወይንስ የማይወድቅ? የሚለው ሊጣራ የሚገባ ነጥብ ሁኖ አይተናል።

የመጀመሪያውን ነጥብ አስመልክቶ ተከሳሽ የተጠየቀውን የእምነት እና የክህደት ቃሉን ሲሰጥም ወንጀሉን
አልፈጸምኩም ብሎ ክዶ ተከራክሮ የዐቃቤ ህግ ምስክሮችም ተሰምተው እንዲከላከልም ብይን ተሰጥቶት
የመከላከያ ምስክሮቹን አቅርቦ የመከላከያ ምስክሮቹም ይመስክሩልኝ ብሎ ጭብጥ ያስያዘው ሟች እሱን
ሊመታው ብረት ይዞ ከቤቱ መጥቶ መሳሪያ ሲይዝበት መሀከላቸው ላይ ጥይት ተተኩሶ እንደተመታ በማለት
የጉዳዩን ጭብጥ ያስያዘ መሆኑ የተከሰሰበትን ወንጀል እንደፈጸመ የሚያመለክት ነው። ቀርበው የተሰሙት
የመከላከያ ምስክሮችም ሟች እና ተከሳሽ ተጣልተው በእጅ እንደተያያዙ ተከሳሽ ይዞት የነበረው መሳሪያ
ድንገት መካከላቸው ላይ ተተኩሶ ሟችን መትቶ የገደለው መሆኑን ፣ ቦታው ላይ እንዳልነበሩ እና መሳሪያው
ተተኩሶ ሟችን መትቶ ከገደለው ቡሃላ ተሯሩጠው መሄዳቸውን ያረጋገጡት እንጂ ተከሳሽ እንዴት ይህንን
ግድያ ሊፈጽመው እንደቻለ የጉዳዩን ጭብጥ አስይዘው እንዳላረጋገጡ ተገንዝበናል።ይህም ተከሳሽ
የተከሰሰበትን ወንጀል ሲፈጽም እነዚህ መከላከያ ምስክሮች በቦታው እንደሌሉና በሀሰት ተደራጅተው ቀርበው
የምስክርነት ቃላቸውን የሰጡ የሚያረጋግጥ መሆኑን ማወቅ ችለናል።

✍ ተርጓሚ ፦ መሀመድ ሀሰን የሱፍ

0205655

በሌላ መንገድ 1 ኛው የመከላከያ ምስክር ከ 2 ኛው መከላከያ ምስክር ጋር ሟች የሞተበት ቦታ ሲደርስ ሟች


ገጀራ ይዞ እንደነበር እና ሟች አጠገብ መሬት ላይም ወድቆ ያየ መሆኑን፣ ሟች አጠገብም ሳንጃ ወድቆ
እንዳየ፣ሟች ወደ ተገደለበት ቦታ ሊሄዱ የቻሉት የመሳሪያ ተኩስ ሰምተው እንደሆነ ሲገልጽ 2 ኛው
የመከላከያ ምስክር የመከላከያ ምስክርነት ቃሉን ሲሰጥ ከመጀመሪያው ጋር በሚጻረር እና በሚያፈርስ መልኩ
ሟች ከተገደለበት ቦታ 1 ኛ መከላከያ ምስክር ጋር ተሯሩጠው ሲሄዱ እረጅም የብረት በትር ሟች ከወደቀበት
ቦታ ላይ እንዳለና ሌላ ነገር ሟች እንዳልያዘ፣ሟች ወደ ተገደለበት ቦታ ተሯሩጠው ሊሄዱ የቻሉት ተከሳሹ እና
ሟች ተጣልተው በእጅ ተያይዘው ከርቀት አይተው እንደሆነና የመሳሪያ ተኩሱን ኋላ ላይ እንደሰሙ በመግለፅ
የመሰከሩ መሆኑን ተረድተናል።

የመከላከያ ምስክሮች የምስክርነት ቃላቸው እርስበርስ በሚጻረር መልኩ መገለጹ ምስክርነታቸው ተከሳሽ
የተከሰሰበትን ወንጀል ሟች ላይ ሲፈጽም በቦታው እንደሌሉ ፣ እንዳላዩ እና በሀሰት ተደራጅተው ቀርበው
የመሰከሩ መሆኑን የሚያረጋግጥ ነው። ስለዚህ ከዚህ በላይ ከገለጽነው ላይ በመነሳት የመከላከያ ምስክሮችን
ቃል ስንመዝን በበቂ መልኩ የዐቃቤ ህግ ምስክሮችን ቃል ስለማያስተባብሉ ውድቅ አድርገናል።

2 ኛውን ነጥብ አስመልክቶ ተከሳሽ ሟችን በአንድ ጥይት መትቶ መግደሉን እንጂ ቂም በመያዝ ወይንም
የወንጀሉን በአሰቃቂ እና ጭካኔ በተሞላበት መንገድ መፈጸሙን የዐቃቤ ህግ ምስክሮች ያረጋገጡት ነገር የለም
ስለዚህ ተከሳሽ የፈጸመው የግድያ ወንጀል በወንጀል ህግ አንቀጽ 539 /1/ሀ ስር የማያስከስሰው ስለሆነ
በወ/ስ/ስ/ህ ቁጥር 113/2/ መሠረት የተከሰሰበትን አንቀጽ ወደ ወንጀል ህግ አንቀጽ 540 በመቀየር ወይንም
በማሻሻል ተከሳሽ በተሻሻለው አንቀፅ ስር ያለውን በመተላለፍ ተከሳሽ ተራ የግድያ ወንጀልን ሟች ሁሴን
በሺር ላይ ፈጽሟል። የፈጸመውም የወንጀል ድርጊት ተሻሽሎ በተቀየረው አንቀጽ መመረት ጥፋት ነው
በማለት በወ/ስ/ስ/ህግ ቁጥር 149/1/ መሰረት በሙሉ ድምፅ የጥፋተኝነት ውሳኔ ወስነናል።

የዐቃቤ ህግ የቅጣት አስተያየት ፦ ተከሳሽ ጥፋተኛ ነው የተባለበት አንቀጽ በቅጣት አወሳሰን መርህ
መሠረት ደረጃ እና እርከን የወጣለት በመሆኑ የወንጀሉ ደረጃ 6 ኛ እንዲሁም የእስራት ቅጣት እርከን 33 ኛ
ላይ ተደርጎልን አስተማሪ የሆነ ቅጣት ይወሰንልን በማለት አሳስቧል።
የተከላካይ ጠበቃዋ የቅጣት አስተያየት ፦ ተከሳሽ የወንጀል ሪከርድ የለበትም፣መሀይም እና ያልተማረ
ነው እንዲሁም በእርሻ ስራ አምስት (5) የቤተሰቦቹን አባል በማገዝ የሚያስተዳድር ስለሆነ ይህ ከግምት ውስጥ
ገብቶ ቅጣቱን በማቅለል እንዲወሰንልን በማለት አሳስባለች።

ቅጣት

ተከሳሽ የሰው ግድያ ወንጀል ፈጽሟል ተብሎ የጥፋተኝነት ውሳኔ የተወሰነበት አንቀጽ የወ/ህ/አንቀጽ 540
ሲሆን፡ይህንን አንቀጽ በመተላለፍ ወንጀልን የፈጸመ ሰው የጥፋተኝነት ውሳኔ ተወስኖበት ከ 5 አመት እስከ 20
አመት በሚደርስ ከባድ የእስር ቅጣት ሊቀጣ እንደሚችል ይደነግጋል።

✍ ተርጓሚ ፦ መሀመድ ሀሰን የሱፍ

0205655

ድንጋጌውም በቅጣት አወሳሰን መሰረት ደረጃ እና እርከን የወጣለት በመሆኑ የወንጀሉ ደረጃ 6 ኛ እንዲሁም
የእስራት ቅጣት እርከን 33 ኛ ላይ ይወድቃል። በዐቃቤ ህግ በኩል የቀረበ የቅጣት ማክበጃ ምክንያት የለም
በተከሳሽ በኩል ሶስት(3) የቅጣት ማቅለያ ምክንያቶች ቀርበው ተይዘውለታል ይህም በወ/ህ/አንቀጽ 82/1/ሀ
መሰረት የወንጀል ሪከርድ እንደሌለው እና ያልተማረ መሃይም እንደሆነ ነው እንዲሁም በወ/ህ/አንቀጽ 86
መሠረት በግብርና ስራ 5 ቤተሰቦቹን የሚያስተዳድር መሆኑ ነው ይህም 3 የቅጣት እርከን ይቀንስለታል
የእስራት ቅጣት እርከን 30 ኛ ይሆንለታል ማለት ነው።

እርከኑም ከአስራ አንድ አመት(11) እስከ አስራ ሶስት አመት ከሁለት ወር(13.2) በእስራት ሊያስቀጣ
እንደሚችል ይደነግጋል። ስለዚህ ተከሳሽ ከተያዘበት ቀን 27/01/2015 ዓ.ም ጀምሮ የሚታሰብለት ሁኖ በአስራ
ሁለት አመት ከስድስት ወር /12.6/ ጽኑ እስራት እንዲቀጣ በማለት የቅጣት ውሳኔ ተወስኖበታል።

ትዕዛዝ

የኦሮሞ/ብሄ/ዞን ማረሚያ ቤት ተከሳሽ ላይ የተወሰነውን የእስር ቅጣት ተከታትሎ እንዲያስፈጽም ኦራንት


ይጻፍ በማለት መዝገቡን ዘግተን ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ ብለናል።

የማይነበብ የሶስት ዳኞች ፊርማ አለበት


✍ ተርጓሚ ፦ መሀመድ ሀሰን የሱፍ

You might also like