Download as docx, pdf, or txt
Download as docx, pdf, or txt
You are on page 1of 6

ቁጥር፦______________________________________

ቀን፦____________________

ለስልጤ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት


ዉራቤ

ከሣሽ፡- አቶ ኑራድን ሁሴን አህመድ አድራሻ፦ አለም ገበያ ከተማ


ተከሣሽ፡- የአለም ገበያ ማዘጋጃ ቤት፟- ወኪል የአለም ገበያ ከተማ አስተዳዳር ዐ/ህግ አድራሻ፦ አለም
ገበያ ከተማ

ሀ. የክሱ መዝገብ ቁጥር 22690 ነው፡፡


ለ. ለክሱ መልስ የምሠጠው በ ወኪል የአለም ገበያ ከተማ አስተዳዳር ዐ/ህግ በኩል ነዉ ነው፡፡
ሐ. የመከላከያ መልስ ለማቅረብ የህግ ችሎታ አለኝ፡፡
መ. የመከላከያ መልሱ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 234 መሠረት ተሟልቶ የቀረበ ነው፡፡
ከሳሽ በቀን 14/09/2016 ዓ/ም በመዝገብ ቁጥር 22690 ፅፎ ባቀረበው አቤቱታ ላይ በተከሳሽ የቀረበ
የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ እና አማራጭ የመከላከያ መልስ ነው፡፡

ከሳሽ በተከሳሽ ላይ የቀረበው አቤቱታ በአጭሩ፡- ከሳሽ በቀን 14/09/2016 ዓ/ም ፅፎ ባቀረበው
በዓለም ገበያ ከተማ 01 ቀበሌ ውስጥ የሚገኝ ስፋቱ 4000 ካሬ ሜትር የሆነ እና አዋሰኙን በማጥቀስ በቀን
2/5/2007 ዓ.ም የሆቴል ኢንቨስትመንት አገልግሎት ለመስራት ባልተገደበ ግዜ የመሬት ኪራይ ውል ገብቼ
እና ይዞታ ማረጋገጫ ተሰጥቶኝ G+2 የሆቴል ህንፃ እና 11 ክፍል እንግዳ ማረፊያ ፔንሲዮን ቤቶች ሰርቼ
የያዝኩት 4000 ካሬ ሜትር ይዞታዬ ውስጥ ተከሳሽ ህግን ሳይከትል ከይዞታዬ ውስጥ ቀንሶ 2320 ካሬ
ሜተር እና በላዩ የተገናባ ግምቱ 3,200,000(ሶስት ሚሊዮን ሁለት መቶ ሺህ) ብር የሚሆን ግንባታ
ያለበትን ይዞታዬ እና ንብረት ተነጥቄያለው በሚል የሰጠው ህገ-ወጥ ውሳኔ ህገ-ወጥነቱ ተረጋግጦ ይዞታና
ንብረቱ ሊነጠቅ አይገባም በሚል የቀረበ ክስ ነው፡፡

የመልሱ ዝርዝር መግለጫ


ሀ. የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ
 ፍ/ቤቱ ነገሩን አይቶ ለመወሰን የሥረ-ነገር ሥልጣን የሌለዉ መሆኑ:- የሥረ ነገር ሥልጣን
በተለያየ ደረጃ ካሉት ፍርድ ቤቶች ጉዳዩ በየትኛዉ ፍርድ ቤት ይቀርባል የሚለዉን ነጥብ የሚመለከት
በመሆኑ መሰረት ከሚያደርገው ነገር ዉስጥ አንዱ ለክርክሩ ምክንያት/መነሻ የሆነውን ጉዳይ የገንዘብ
መጠን ነዉ፡፡ እንዲሁም የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የፍርድ ቤቶች አዋጅ ቁጥር: 01/2016 እስከ
3,000,000(ሶስት ሚሊዮን) ብር የሚገመት የገንዘብ መጠን ያላቸዉ ጉዳዮች የሥረ ነገር ሥልጣን
የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤቶች እንደሆነ ደንግጓል። ከሳሽ ክስ ያቀረበበት ጉዳይ የገንዘብ መጠን
ምንም እንኳን ከሳሽ 3,200,000(ሶስት ሚሊዮን ሁለት መቶ ሺህ) ብር የሚገመት የገንዘብ መጠን
ያላቸዉ ነው ብሎ ቢያቀርብም ግምታቸዉ በፍፁም ከሳሽ ያቀረበዉን የገንዘብ መጠን ግምት
የሚያወጡ አይደለም። እንዲሁም ከሳሽ አያይዞ ያቀረባቸዉ የሰነድ ማስረጃዎች መሬቱ ባዶ እና
ያለማ ያሚያሳይ ከመሆኑም በላይ መሬት በገንዘብ የማይተመን በመሆኑም ፍ/ቤቱ አስፈላጊዉን
ማጣራት አድርጎ የሥረ ነገር ሥልጣኑ የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ነዉ በማለት በፍ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 231(1)

(ለ) እና 244(2)(ሀ) መሰረት አቤቱታውን በብይን ውድቅ እንዲያደርግልን በአክብሮት እንጠይቃለን፡፡


ፍ/ቤቱ ይህንን የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያችንን አያልፈዉም እንጂ ምናልባት የሚያልፈው ከሆነ ግን
በፍሬ ጉዳዩ ላይ የሚከተለውን አማራጭ መልሳችንን እናቀርባለን፡፡
ለ. በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 234 መሠረት የቀረበ አማራጭ የመከላከያ መልስ
1 ኛ. ከሳሽ በቀን 2/5/2007 ዓ.ም የሆቴል ኢንቨስትመንት አገልግሎት ለመስራት ባልተገደበ
ግዜ የመሬት ኪራይ ውል አግኝቼ የሚለውን በተማለከተ፡- ከሳሽ ከተከሳሽ ጋር በቀን 2/5/2005
ዓ.ም ውል የገባነው ይባል እንጅ ውል የገባነው 2007 ዓ/ም የሆቴል ኢንቨስትመንት አገልግሎት ለመስራት
ለልተወሳና ግዜ የመሬት ኪራይ ውል የወሰዳ ቢሆንም ከሳሽ ከተከሳሽ የገቡቱ ውል የሚተዳደራው አሁን
በስራ ላይ ባለዉ በኢ.ፌ.ዲ.ሪ የሊዝ አዋጅ ቁጥር 721/2011 እና ይህንን አዋጅ ለማስፈፀም በወጣው የደቡብ ክልል
ደንብና መመሪያ መሰረት በመሆኑ ከሳሽ ክርክር ያነሰበት ጉደይ አሁን ስራ ላይ በለው ህግ ብቻ በመሆኑ ባልተገደበ
ግዜ የመሬት ኪራይ ውል አግኝቼ ብሎ ያነሳው ተገቢነት ያሌለው ነው፡፡ በመሆኑም የተከበረው ፍ/ቤት
የከሳሽን አቤቱታ ውድቅ በማድረግ በነፃ እንዲያሰናብተን በአክብሮት እንጠይቃለን፡፡

2 ኛ. ከሳሽ ይዞታውን ካገኘሁኝ ግዜ ጀምሮ የታለመለትን አላማ ለመሰራት ምንም አይነት


የመሰረተ ልማት አገልግሎት ሳይኖረው የእርሻ ማሳ በነበረ ይዞታ ላይ G+2 የሆቴል ህንፃ እና
11 ክፍል እንግዳ ማረፊያ ፔንሲዮን ቤቶች ሰርቼ በማጠናቀቅ ምቹ ባደርግም ምንም
አይነት ተጠቃሚ ባለመገኘቱ ከፍተኛ ኪሳራ የደረሰብኝ በመሆኑ ለቢሮ እና ለኦሞ ባንክ
አከራይቶ እያተጠቀመበት ያለ መሆኑን በመግለፅ ያቀራባውን በተማለከተ፡- የከሳሽ ይዞታ
ያለባት ቦታ ከተማ መሀል ቦታው የአስፋልት መንገድ የውሀ የቴሌ እና የመብራት እንዲሁም የመንገድ ዳር
መብራት ጨምሮ የመሰረተ-ልማት አቅርቦት ችግር በሌለበት ለታለመለት አላማ መስረት ሲገባው ከሳሽ
የገባውን ውል ወዳ ጎን በመተው ባይዞታው በሰሜናዊ ምዕራብ ጠርዝ ላይ 264 ካ/ሜ ቦታ ላይ ያረፈ
ተጀምሮ ያልተጠናቀቀ ደረጀውን የልጠበቀ(የ 1 ኛው ወለል (G+0)ተጠናቆ ውሉ ለሆቴል ንግድ አገልግሎት
ሆኖ እያለ ለኦሞ ባንክ ተከራይቶ፣ 1 ኛ ወለል ኮለን የቆመለት እና የ 2 ተኛ ወለል የተወሰኑ ኮለኖች
የተጀመረ) ሆኖ እያለ ከሳሽ G+2 የሆቴል ህንፃ ገንብቻለው የሚለው ሀሰት ነው፡፡ ሌላው በደቡባዊ
ምስራቅ ጠርዝ 320 ካ/ሜ ላይ ያረፈ 11 ክፍሎች ያካተተ ተጠናቆ ለቢሮ አከራይቶወል፡፡ ከሳሽ ውል ገብቶ
ከወሰደው በ 9(ዘጠኝ) አመት ውስጥ አንድም ቀን ለሆቴል አገልግሎት ምቹ በላደረገባት ከሳሽ ከፍተኛ
ኪሳራ ደረሰብኝ የሚለው ሀሰት ነው፡፡ ከሳሽ ለታለመለት አላማ መዋል እንደለበት ህጉ በግልፅ ይዳነግጋል፡፡
እንደደነገጋውም የፌዴራል የከተማ ቦታን በሊዝ ስለመያዝ የወጣዉን አዋጅ ቁ 721/2004 አንቀፅ 21(1)
የከተማ ቦታ ሊዝ ባለይዞታ በሊዝ ውሉ ውስጥ በተማለከተው የጊዜ ገደብ ውስጥ ቦታውን ለተፈቀደለት
አገልግሎት ጥቅም ላይ ማዋል እንዳለበት እና በዚሁ አዋጅ ቁ 721/2004 አንቀፅ 25(1)(ሀ) ለተፈቀደለት
አገልግሎት ጥቅም ላይ ከለዋለ ውሉ እንደሚቋረጥ ህጉ በግልፅ ይደነግጋል፡፡ ከሳሽ ይህ ክስ ያቀረበበት
አግባብ ህግን መሰረት ያለደረገ በመሆኑ የተከበረው ፍ/ቤት የከሳሽን አቤቱታ ውድቅ በማድረግ በነፃ
እንዲያሰናብተን በአክብሮት እንጠይቃለን፡፡

3 ኛ. ከሳሽ ለሆቴሉ ውበት የሚሆኑ በቁጥር 600(ስድስት መቶ) የሚሆን ግምቱ አንድ መቶ ሺ ብር
የሚሆን የተለያዩ ዛፎች እና ፍራፍሬዎችን በመትከል የለማዋቻውን እና የሻዋር እና ሽንት ቤት እና
የተለያዩ ሰርቪስ ቤቶች ግምታቸው ሶስት ሚሊዮን አንድ መቶ ሺ ብር የሚሆን ያላለቀ
ግንባታ ያለበት ሳያነሱ እያወደሙብኝ ይገኛሉ በማለት ያነሱትን በተማለከ፦ ከሳሽ የክስ አቤቱታ
የተነሳበትን ቦታ በ 2007 ዓ/ም በተደረገ ዉል ለሆቴል ኢንቨስትመንት አገልግሎት በሚል የወሰደ ቢሆንም
ለተባለለት አላማ እና አገልግሎት ከማዋል ይልቅ ቦታዉ ከተማ ማሀል እና አስፓልት ደር እንደመሆኑ
ለቦታዉከከሳሽ በተወሰደው መሬት ላይ ምንም አይነት ያለማ ነገር ዬለበትም፡፡ ከሳሽ ተወሰደብኝ የሚሉት
በውሉ መሰረት ደረጃውን ያልጠበቀ እና ግንባታ ፈቃድ ሳይወስዱ 180 ካ/ሜ ላይ ያረፈ 6 ክፍሎች
የመሰረት ግንባታ ስገነቡ ማዘገጀ ቤቱ ያስቆመው ህገ-ወጥ ግንበታ እንጅ ከሳሽ እንዳሉት ሶስት ሚሊዮን
አንድ መቶ ሺ ብር የሚሆን ግምት ያለዉ አይደለም። ሌላዉ ከሳሽ በተወሰደዉ መሬት ላይ የተለያዩ ግራር
እና ዛፎች የነበሩትን ከሳሽ በራሱ ወጪ ማንሳት እያለበት ተከሳሽ በራሱ ወጪ አንስቶ በቀሪዉ የከሳሽ
ይዞታ ላይ አስቀምጧል። ሊላዉ ከሳሽ እንዳለዉ 600(ስድስት መቶ) ዛፎች እና ፍራፍሬዎች የሌሉ እና
የዋጋ ግመታቸዉም አንድ መቶ ሺ ብር የሚያወጣ አይደለም የወደመም ምንም አይነት ነገር ዬለም።
ባአጠቃላይ በተወሰደዉ መሬት ምንም አይነት የለማ ንብረት ወይም በገንዘብ የሚተመን ንብረት የሌለበት
በመሆኑ የተከበረው ፍ/ቤት ከሳሽ ያቀረቡት አቤቱታ እዉነታዉን ሀቁን የካደ በመሆኑ የከሳሽን አቤቱታ ውድቅ
በማድረግ በነፃ እንዲያሰናብተን በአክብሮት እንጠይቃለን፡፡

4 ኛ. ተከሳሽ ለከሳሽ በስተላለፈልኝ ውል ላይ በ 4000 ካ.ሜ በሙሉ ላይ ግንባታ እንድገነባ


የሚያስገድድ የውል ድንጋጌ በሌላበት በሚመጠን ሁኔታ በ 2000 ካ.ሜ ያህሉ ግንባታ
ገንብቼ ያሚለውን በተማለከተ፡- ከሳሽ በውል ላይ በ 4000 ካ.ሜ መሬት የሆቴል ኢንቨስትመንት
አገልግሎት ወይም ለታለመለት አላማ ለመዋል ቢወስድም ከሳሽ ይዞታው ላይ ግንባታ ያሰረፈበት ቦታ
በሰሜናዊ ምዕራብ ጠርዝ ላይ 264 ካ/ሜ ቦታ ላይ ያረፈ ተጀምሮ ያልተጠናቀቀ (G+0 GROUND ወለል
ያለቀ 1 ኛ ወለል ኮለን የቆመለት እና የ 2 ተኛ ወለል የተወሰኑ ኮለኖች የተጀመረ)፤ በደቡባዊ ምስራቅ
ጠርዝ 320 ካ/ሜ ላይ ያረፈ 11 ክፍሎች ያገነበ ሲሆን አሁን ግንባታው ያረፈበት ቦታ 584 ካሬ ሜትር
እንደማይበልጥ አፈፃፀሙም በፐርሰንት 22.5 ብቻ ነው፡፡ ይህንንም ካሳሽ ቅሬታ ያቀረበለት የስልጤ ዞን
ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ልማት መምሪያ የመሬት ልማት እና ማኔጅመንት ባለሙያዎች ከዞን
አስተዳደር በተወከለ ባለሙያ ቦታውን ድረስ ተንቀሳቅሰው ከሳሽ በተገኙበት የይዞታ ልኬትና ቴክኒካል
ቡድን በተገኙበት እና ጥሬ መረጃዎች በመሰብሰብ እንዲሁም በቢሮ የሚገኙ በይዞታ ማህደራቸው
በተያያዙ ማስረጃዎች አረገግጦዋል፡፡ ከሳሽ ለሆቴል ኢንቨስትመንት አገልግሎት ምቹ ባለደረገበት በ 2000
ካ.ሜ ያህሉ ግንባታ ገንብቻለው ብሎ ያነሱት ክርክር ሀሰት በመሆኑ የተከበረው ፍ/ቤት የከሳሽን አቤቱታ
ውድቅ በማድረግ በነፃ እንዲያሰናብተን በአክብሮት እንጠይቃለን፡፡

5 ኛ. ከሳሽ ያላለቀ ሽንት ቤት እና ሰርቪሶች ግንባታ ያለበት እና የተለያዩ ዛፎች በመ ትከል


እያለመሁኝ ያለሁባትን ማሬት በህገ ወጥ መንገድ ከመሀል በመቁረጥ 2320 ካሜ ተከሳሽ
ቀንሶ ወሰደብኝ የሚለውን በተመለከተ፡- ለከሳሽ ለሆቴል ኢንቨስትመንት አገልግሎት ተብሎ
በ 2007 ዓ/ም 4000 ካሜ መሬት ተላልፎለታል። ይህም መሬት በልኬት ሲራጋገጥ 4320 ካሬ ሜትር የሆነ
ነገር ግን መሬቱ በተወሰደው ልክ ያለማ በመሆኑ እና ለተፈለገው አገልግሎት ያልዋለ መሆኑን እና ጥቅም
የልሰጠ መሆኑን ተረገግጦዋል፡፡ በዚህም ከጠቅላለው መሬት ማለትም 4000 ካሬ ሜትር ላይ ያለመውን
በኩል 2000 ካሬ ሜትር እንድሁም ሲለካ በትርፍ የተገኛውን የማዘገጀ ቤት መሬት 320 ካሬ ሜትር
ጨምሮ በድምሩ 2320 ከሬ ሜትር መሬት ተቀንሶ ወደ መሬት ባንክ መግበት እንደለበት ተወስኖዋል፡፡
ይህም ውሳኔ በቀን 24/09/2016 ዓ/ም የተቋሙ የማኔጅመንት ኮሚቴ በተያዘው ቃለ ጉባኤ ለተፈለገው
አገልግሎት ያልዋለ መሬት ወደ መሬት ባንክ መግበት እንደለበት ተወያይተዉ ለከንቲባ ኮሚቴ አቅርበው
በቀን 28/08/2016 ዓ/ም የከንቲባ ኮሚቴ አፅድቀው እንድሁም በዓለም ገባያ ከተማ አሰተባበሪዎች ተይቶ
የተሰጣ ውሳኔ ነው፡፡ ይህም ውሳኔ የደቡብ ክልል የከተማ መሬት በሊዝ ስለመፍቀድ የወጣዉን ደንብ ቁጥር
123/2007 ለማስፈፀም ተሻሽሎ የወጣዉን መመሪያ ቁጥር 8/2007 አንቀጽ 55(2)(ረ) የግንባታ
ማጠናቀቂያ ጊዜ ስላለፈባቸው ይዞታዎች መሬትን ለልማት በምደባ በጨረታ አና በሌሎች ሁኔታዎች
ወሰዶ ያላለሙ ወይም በወቅቱ ግንባታ ያልጀመሩ በመመሪያዉ መሰረት የዉል ጊዜ ያለፈባቸዉና ግንባታ
ያላጠናቀቁ ግለሰቦችን ድርጅቶችን ወይም ተቋማትን የመሬት ልማትና ማኔጅመንት ጽ/ቤት በየ ሩብ
ዓመቱ በጥናት በመለየት በጽ/ቤቱ ማነጅመንት በመገምገም የዉሳኔ ሀሳብ ለከተማ አስተዳደሩ በማቅረብ
ያጸድቃሉ፣ በዉሰኔዉ መሰረት ከማስጠንቀቂያ እሰከ ይዞታ መቀማትና የካርታ ማምከን እርምጃ በመዉሰድ
መሬቱን ወደ መሬት ባንክ የመመለስ ተግባር እንደሚያከናውን በግልጽ ደንግጓል፡፡ ከሳሽም ይህን ውሳኔ ቅር
በመሰኘት ዞን ለሚመለከተው አካል ቅሬተ ቢያቀርቡም በቀን 12/9/2016 ዓ/ም በመ/ቁ 2970/16 ዓ/ም
በፃፉት ደብዳቤ ተቋሙ የሰጠዉ ውሳኔ የህግ ማዕቀፎችን የማይጻረር ከመሬት አሰራር አንጻር ተገቢነት
ያለው እና ፍትሀዊ መሆኑን ያረጋገጠ እንድሁም ከሳሽ ያላጠናቀቁትን እንድያጠነቁ ጭምር መስጠነቀቅያ
ተሰጥቶዋቻው ውሳኔው ተገቢ ነው ብለዋል፡፡ ሌላው ከከሳሽ በተወሰደው መሬት ላይ ምንም አይነት የለማ
ነገር ዬለበትም፡፡ ከሳሽ ተወሰደብኝ የሚሉት በውሉ መሰረት ደረጃውን ያልጠበቀ እና ግንባታ ፈቃድ
ሳይወስዱ 180 ካ/ሜ ላይ ያረፈ 6 ክፍሎች የመሰረት ግንባታ ሲገነቡ ማዘገጀ ቤቱ ያስቆመው ህገ-ወጥ
ግንበታ እንጅ የነበሩ ዘፎች ተቆርጠው ለከሳሽ በታተወለት 2000 ካሜ መሬት ላይ ይገኘሉ ሌላ ምንም
አይነት የለማ ነገር ዬለም፡፡ ይህ ውሳኔ የፌዴራል የከተማ ቦታን በሊዝ ስለመያዝ የወጣዉን አዋጅ ቁ
721/2004 አንቀፅ 21(1)እና 25(1)(ሀ) እና የደቡብ ክልል የከተማ መሬት በሊዝ ስለመፍቀድ የወጣዉን
ደንብ ቁጥር 123/2007 ለማስፈፀም ተሻሽሎ የወጣዉን መመሪያ ቁጥር 8/2007 አንቀጽ 54(2)
እንዳሚደነግገውም ይህ የሊዝ መመሪያ ከመጽደቁ በፊት በሊዝ አግባብ ቦታ ወስደው ግንባታ ጀምረው
ያላጠናቀቁ ይዞታዎች እንደ ግንባታቸው ደረጃ ከሁለት እስከ አራት አመት የሚደርስ የግንባታ ማጠናቀቂያ
ጊዜ ሊሰጣቸው እንደሚችል ይደነግጋል፡፡ ከሳሽ ግን ከ 2007 ጀምሮ 09( ዘጠኝ )አመት ሙሉ ይዞታውን
ለተፈቀደለት አገልግሎት ጥቅም ላይ ሰያዉሉ ቀርቶ በተደጋጋሚ ማስጠቀቂያ ተሰጥቶት ማልመት
በለመቻሉ ህግ መሰረት አድርጎ የተወሰደ ነው እንጅ ከሳሽ እንደለው በህገ ወጥ መንገድ አይደለም፡፡
ስለሆነም የተከበረው ፍ/ቤት የከሳሽን አቤቱታ ውድቅ በማድረግ በነፃ እንዲያሰናብተን በአክብሮት እንጠይቃለን፡፡

6 ኛ. ከሳሽ ተከሳሽን ቦታዉን ለመንጠቅ የሚያስችል አንድም ቀን ማስጠንቀቂያ ሳይሰጠኝ የተሰጠው


ውሳኔ ህግን ያልተከተለ ነው የሚለውን በተመለከተ:- ከሳሽ ቀድሞ ዉል የገባዉ ባአካባቢዉ በሚጠራበት
ስም ኑርታታ ሁሴን በሚል ስም ቢሆንም ሁለተኛ ዙር በመምጣት የመታወቂያ እና የፓስፖርት ስሜ
ኑረዲን ሁሴን ነዉ በማለት የዉሉን ስም እንዲቀየር አድርጓል በመሆኑም ለማስጠንቀቂያ ደብዳቤ ቀድሞ
ዉል የገባበትን ኑርታታ ሁሴን በሚል ተጠቅመናል። የማስጠንቀቂያ ደብዳቤ በህጉ መሰረት 2 ዙር
ተሰጥቶት በ 3 ተኛው ዙር የመንጠቅ እርምጃ እንዲወሰድ የሚያስገድድ ቢሆንም ተከሳሽ ከ 4 ዙር በላይ
የማስጠንቀቂያ ደብዳቤ ለከሳሽ ባአድራሻዉ ፅፎ ሰጥቷል ይህም (የመጀመሪያው ማስጠንቀቂያ 1 ኛዉ ዙር
በቀን 22/11/2007 ዓ/ም፣ 2 ኛዉ ዙር በቀን 16/02/2008 ዓ/ም፣ 3 ኛዉ ዙር በቀን 05/10/2010 ዓ/ም፣
4 ኛዉ ዙር በቀን 07/12/2012 ዓ/ም፣ 5 ኛዉ ዙር በቀን 19/01/2014 ዓ/ም፣ 6 ኛዉ ዙር በቀን 17/09/2014
ዓ/ም፣ 7 ኛዉ ዙር እና በቀን 03/01/2016 ዓ/ም) በተለያዩ ጊዚያት በማዘጋጃ ኃላፊዎች የተሰጠዉ በመሆኑ
ከህጉ በላይ ዕድል ተሰጥቶት ያልተጠቀመበት እና በህግ አግባብ የተወሰደበት እንዲሁም ከሳሽ በገባዉ ዉል
መሰረት ባለመፈፀሙ እንጂ ከሳሽ እንዳለዉ በህገ ወጥ መንገድ ተነጥቆ አይደለም። ስለሆነም የተከበረው
ፍ/ቤት ከሳሽ ያቀረቡት አቤቱታ እዉነታዉን ሀቁን የካደ በመሆኑ የከሳሽን አቤቱታ ውድቅ በማድረግ በነፃ
እንዲያሰናብተን በአክብሮት እንጠይቃለን፡፡

ከፍርድ ቤቱ የምጠይቀዉ ዳኝነት


1 ኛ. ከዚህ በላይ ያቀረብኩት የመከላከያ መልሴን ፍ/ቤቱ ተገቢ ነዉ በማለት ከሳሽ ያቀረበብኝን ክስ ዉድቅ
እንዲያደርግልኝ እና በነፃ እንዲያሰናብተኝ በአክብሮት እጠይቃለሁ፡፡
2 ኛ. ለዚህ ክስ ያወጣሁት ወጭ እና ኪሣራም ታስቦ እንዲከፍለኝ እንዲወሰንልኝ እያመለከትኩ ማስረጃዬን

በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 223 መሠረት አያይዣለሁ፡፡


መልሱ እውነት ለመሆኑም በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 92 መሠረት አረጋግጣለሁ፡፡
የተከሣሽ ወኪል፦______________________________________ፊርማ፦______________________________________

ቁጥር፦______________________________________
ቀን፦____________________

ለስልጤ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት


ዉራቤ

ከሣሽ፡- አቶ ኑራድን ሁሴን አህመድ አድራሻ፦ አለም ገበያ ከተማ


ተከሣሽ፡- የአለም ገበያ ማዘጋጃ ቤት፟- ወኪል የአለም ገበያ ከተማ አስተዳዳር ዐ/ህግ አድራሻ፦ አለም
ገበያ ከተማ
በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 223 መሠረት ተሟልቶ የቀረበ የማስረጃ ዝርዝር
ሀ) የሰዉ ማስረጃ
1. አቶ ሱልጣን መሀመድኑር አልዬ አድራሻ፦ አለም ገበያ ከተማ አስተዳደር 01 ቀበሌ
2. አቶ ራመቶ ሹክሬ ሰይድ አድራሻ፦ አለም ገበያ ከተማ አስተዳደር 01 ቀበሌ
3. አቶ ኢልማ ሳኒ አድራሻ፦ አለም ገበያ ከተማ አስተዳደር 01 ቀበሌ
4. ወ/ሮ አብድረሂም የሱፍ አድራሻ፦ አለም ገበያ ከተማ አስተዳደር 01 ቀበሌ
5. አቶ ከማል ሞላ ፎሬ አድራሻ፦ አለም ገበያ ከተማ አስተዳደር 01 ቀበሌ
6. አቶ በህረዲን ኑሪ አሊ አድራሻ፦ አለም ገበያ ከተማ አስተዳደር 01 ቀበሌ
7. አቶ መሀመድኑር ራህመቶ አድራሻ፦ ወራቤ ከተማ አስተዳደር 01 ቀበሌቀበሌ
8. አቶ ሙስባህ አምዳላ አድራሻ፦ ወራቤ ከተማ አስተዳደር 01 ቀበሌ
ለ) የሰነድ ማስረጃ
1. በቀን 24/08/2007 ዓ/ም ከሳሽ ከተከሳሽ የገቡት የዉል ሰነድ 03 ገጽ፤
2. በቀን 24/08/2016 ዓ/ም በአለም ገበያ ከተማ ማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት ጽ/ቤት ማኔጅመንት ለተፈለገለት አገልግሎት ያልዋለ
መሬትን ወደ መሬት ባንክ እንዲገባ ዉሳኔ ያስተላለፈበት ቃለ ጉባኤ 04 ገጽ፤
3. በቀን 28/08/2016 ዓ/ም ያአለም ገበያ ከተማ ከንቲባ ኮሚቴ የማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት ጽ/ቤት ማኔጅመንት ዉሳኔ ያፀደቀበት
ቃለ ጉባኤ 03 ገጽ፤
4. በቀን 27/08/2016 ዓ/ም ያአለም ገበያ ከተማ አስተባባሪዎች/ካቢኒዎች የማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት ጽ/ቤት ማኔጅመንት ዉሳኔ
ያፀደቀበት ቃለ ጉባኤ 04 ገጽ፤
5. በቀን 22/11/2007 ዓ/ም ያአለም ገበያ ከተማ ማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት ጽ/ቤት ለከሳሽ ግንባታ ገንብተዉ እንዲያጠናቅቁ የተሰጠ
ማስጠንቀቂያ 01 ገጽ፤
6. በቀን 16/02/2008 ዓ/ም ያአለም ገበያ ከተማ ማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት ጽ/ቤት ለከሳሽ ግንባታ ገንብተዉ እንዲያጠናቅቁ የተሰጠ
ማስጠንቀቂያ 01 ገጽ፤
7. በቀን 05/10/2010 ዓ/ም ያአለም ገበያ ከተማ ማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት ጽ/ቤት ለከሳሽ ግንባታ ገንብተዉ እንዲያጠናቅቁ የተሰጠ
ማስጠንቀቂያ 01 ገጽ፤
8. በቀን 07/12/2012 ዓ/ም ያአለም ገበያ ከተማ ማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት ጽ/ቤት ለከሳሽ ግንባታ ገንብተዉ እንዲያጠናቅቁ የተሰጠ
ማስጠንቀቂያ 01 ገጽ፤
9. በቀን 19/01/2014 ዓ/ም ያአለም ገበያ ከተማ ማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት ጽ/ቤት ለከሳሽ ግንባታ ገንብተዉ እንዲያጠናቅቁ የተሰጠ
ማስጠንቀቂያ 01 ገጽ፤
10. በቀን 17/09/2014 ዓ/ም ያአለም ገበያ ከተማ ማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት ጽ/ቤት ለከሳሽ ግንባታ ገንብተዉ እንዲያጠናቅቁ የተሰጠ
ማስጠንቀቂያ 01 ገጽ፤
11. በቀን 03/01/2016 ዓ/ም ያአለም ገበያ ከተማ ማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት ጽ/ቤት ለከሳሽ ግንባታ ገንብተዉ እንዲያጠናቅቁ የተሰጠ
ማስጠንቀቂያ 01 ገጽ፤
12. በቀን12/09/2016 ዓ/ም የስልጤ ዞን ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን መምሪያ ያአለም ገበያ ከተማ ማዘጋጃ ቤታዊ
አገልግሎት ጽ/ቤት የሰጠዉ ዉሳኔ ትክክል መሆኑን የገለፀበት ደብዳቤ 06 ገጽ፤
13. በቀን 28/08/2016 ዓ/ም ያአለም ገበያ ከተማ ማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት ጽ/ቤት ማኔጅመንት ለከንቲባ ኮሚቴ አቅርቦ
ከፀደቀ በኋላ ወደ መሬት ባንክ እንዲገባ የመጨረሻ ዉሳኔ የሰጠበት ደብዳቤ 01 ገጽ፤ በድምሩ 29 ገጽ የማስረጃ ዝርዝር
አቅርብያለሁ።
ያቀረብኩት የማስረጃ ዝርዝር እዉነት መሆኑን በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 92 መሠረት አረጋግጣለሁ፡፡

የተከሣሽ ወኪል፦______________________________________ፊርማ፦______________________________________

You might also like