የእናቶች ጤና

You might also like

Download as docx, pdf, or txt
Download as docx, pdf, or txt
You are on page 1of 3

"ከወሊድ ቦሀላ ደሟ መፍሰስ የጀመረ እናት በሕይወት የምትቆየው ለሁለት ሰዓታት ብቻ ነው!

"

" " ተብሎ በዘመቻ መልክ የእናቶች ጤና ላይ አተኩሮ በተለያዩ መሪ ቃሎች


የጥር ወር በየአመቱ የጤናማ እናትነት ወር

ይከበራል። ዘንድሮም "መከላከል በምንችላቸው ምክንያቶች የሚሞቱ እናቶችን ሞት እንግታ" በሚል መሪ እየተከበረ
የሚገኝ ሲሆን የጤናማ እናቶች ወር በዓለማችን ለሰላሳአምስተኛ ጊዜ ፤ በሀገራችን ለአስራሰባተኛ ጊዜ እና በክልላችን
ደሞ ለአስራሶስተኛ ጊዜ በተለያዩ ክንውኖች እየተከበረ ይገኛል። በወላድ እናቶች ላይ ትኩረቱን አድርጎ የሚከበረው ይህ
የጤናማ እናቶች ወር ከዚህ ቀደም ሳይቀረፉ የቀሩ ውዝፍ ችግሮችን በዘመቻ መልክ ለመቅረፍ ታልሞ የሚሰራበት ወር
ነው እንጂ የእናቶች የጤና ጉዳይ ከዓመት እስከ ዓመት የሚሰራበት ወሳኝ የጤና ዘርፍ ነው።

የጥር ወር ከሌሎች ወራት በተለየ ባለድርሻ አካላትን ለማስተባበር ፤ ውሳኔ ሰጪ አካላትን ደሞ ለማስታወስ እና
ለማነቃቃት በልዩነት ታስቦ ይሰራበታል እንጂ የእናቶች የጤና ጉዳይ ተፈጥሯዊው የመዋለድ ስርዓት እስካለ ድረስ
የሚቀጥል ነው።

በዓለም አቀፍም ፣ በሀገራችንም ሆነ በክልላችን የእናቶችን ሕይወት በከፍተኛ ሁኔታ እየቀጠፉ ካሉ የጤና እክሎች
/ //
ግንባር ቀደሙ ከወሊድ ቦሀላ የሚከሰት ከፍተኛ የደም መፍሰስ አደጋ ነው። ሲ ር አዲስዘመን ጫኔ በአማራ ብ ክ መ

"
ጤና ቢሮ የእናቶች ጤና ፕሮግራም አስተባባሪ ሲሆኑ ይህ የጤና አደጋ የገጠማት አንዲት እናት በሕይወት የመቆየት

ዕድሏ ቢበዛ ለሁለት ሰዓታት ብቻ ነው " ይላሉ።

ከወሊድ ቦሀላ የሚከሰት መድማት በማንኛውም ወላድ እናት ላይ ሊፈጠር የሚችል እና በቀላሉ የሚገመት አጋጣሚ
/
አለመሆኑን የሚገልፁት ሲ ር አዲስዘመን ችግሩ ሊያጋጥማቸው የሚችሉ እናቶችንም በእርግጠኝነት መግለጽ
እንደማይቻል እና ለዚህ የጤና እክል መከሰት ብዙ ምክንያቶች ቢኖሩም በዋናነት ግን ከወሊድ ቦሀላ የማህፀን
በተፈጥሯዊ መንገድ ወደቀድሞ ቦታው
አለመመለስ ትልቁን ድርሻ እንደሚይዝ ነግረውናል።

ይህን የእናቶች የጤና ችግር ለመከላከል ዋናው መፍትሔ እናቶች በጤና ተቋማት እንዲወልዱ ማስቻል ነው የሚሉት
ባለሙያዋ እናቶች በጤና ተቋማት ፅንሳቸውን እንዲገላገሉ ለማስቻል ብዙ ስራዎች እየተሰሩ ይገኛሉ። ከእነዚህ ተግባራት
መካከል የእናቶች ኮንፍረስ አንዱ ነው። ይህንን ኮንፍረስ በየቀበሌው በየወሩ ለማከናወን እየተሰራ ሲሆን ነፍሰጡር
እናቶችን ፣ ባሎቻቸውን ፣ ታዋቂ ሰዎችን እና የሐይማኖት አባቶችን በአንድ መድረክ በማገናኘት እናቶች የቅድመ ወሊድ
፣ የወሊድ እና የድህረ ወሊድ የጤና አገልግሎትን ከጤና ተቋማት እንዲያገኙ ለማስቻል ከጤና ባለሙያዎች ጋር
የሚከናወን ምክክር ነው።

/
ነፍሰጡር እናቶች ወደ ጤና ተቋማት ሄደው ፅንሳቸውን እንዲገላገሉ ለማስቻል እየተከናወኑ ስላሉት ጉዳዮች ሲ ር

አዲስዘመን እንዲህ ይላሉ:- "እንደሚታወቀው ከጥቂት ወራት አስቀድሞ በክልላችን በነበረው ጦርነት አብዛኞቹ
የጤና ተቋማት አምቡላንሶች ተሰርቀዋል። የተቀሩት ደሞ ከፍተኛ ጉዳት ደርሶባቸዋል። ይህ ችግር ለመጓጓዣ ፈታኝ
ከሆነው ከክልሉ አስቸጋሪ መልክዓ ምድር ጋር ተደምሮ ነፍሰጡር እናቶችን ምጣቸው በተከሰተበት ወቅት በአፋጣኝ ወደ
ጤና ተቋማት ለማድረስ የሚደረገውን እርብርብ በእጅጉ ወደ ሁዋላ እየጎተተው ይገኛል። ይህንን ከግምት ውስጥ
በማስገባት እናቶች የመውለጃ ጊዜያቸው ሲቃረብ ቢበዛ ሁለት ሳምንት ሲቀራቸው ከሚኖሩበት አከባቢ በጥንቃቄ ወደ
ጤና ተቋማት በመምጣት አስፈላጊው እንክብካቤ እና የጤና ክትትል ሊደረግላቸው የሚያስችሉ በጤና ተቋማት ውስጥ
"
የሚገኙ የእናቶች ማረፊያ " የተሰኘ በሀገርአቀፍ ሆነ በክልሉ ደረጃ እናቶች እስከሚወልዱበት ቀን ድረስ የሚቆዩበት
ስፍራ ለማዘጋጀት እየተሰራ ነው።"

//
እንደ አማራ ብ ክ መ ጤና ቢሮው ሳይንሳዊ ግምት ከሆነ በሕዝብ ብዛት ረገድ በሀገራችን ካሉ ክልሎች ውስጥ
በሁለተኛ ደረጃ በሚቀመጠው በአማራ ክልል በዚህ ዓመት ወደ ስምንት መቶ ሺ የሚጠጉ እናቶች ይወልዳሉ ተብሎ
ይጠበቃል። እነዚህ እናቶች በጤና ተቋማት እንዲገላገሉ ለማስቻል በሚሰራው ስራ ላይ ብዙ አካላት የድርሻቸውን
ይወጡ ዘንድ ይጠበቃል።
ነገር ግን ይህ የእናቶች የጤና ዘርፍ የታሰበውን ያህል አመርቂ ውጤት እንዳያመጣ ብዙ እንቅፋቶች እየተፈታተኑት
እንደሚገኝ ባለሙያዋ ይናገራሉ። እንደሳቸው ማብራሪያም ከፈተናዎቹም መሐከል በእናቶች እና ፅንስ እንዲሁም ተያያዥ
የሕክምና ዓይነቶች የሰለጠነ የባለሙያ እጥረት ፤ እንደ መብራት ፣ ውሃ ፣ መንገድ ፣ አምቡላንስ ፣ የጤና ተቋሙ ሕንፃ
እና መሠል የጤና ተቋማቱ የመሠረተ ልማቶች እጦት ፤ በማህበረሰቡ ዘንድ የተለመደው ከወሊድ ቦሀላ እናቶች የደም
መፍሰስ ችግር ሲገጥማቸው የሚደረጉ እንደ ብረትምጣድ መቀጥቀጥ እና ጥይት መተኮስ ያሉ ጎጂ ባህላዊ ልማዶች እና
የደም እጦት ተጠቃሾቹ ናቸው።

/ "
በመጨረሻም ሲ ር አዲስዓለም ሀሳባቸውን ሲያጠቃልሉ እንደሚታወቀው የክልሉ የጤና ዘርፍ በገጠመው ተደራራቢ
ወቅታዊ ችግሮች ብዙ ክፍተቶች ተፈጥረዋል። እነዚህ ችግሮች ደሞ በመንግሥት ብቻ ሊቀረፉ የሚችሉ አይደሉም።
በመሆኑም የወደሙ የጤና መገልገያ መሳሪያዎችን እና ተቋማትን መልሶ ለመገንባት ባለሐብቶች እና ረጂ አካላት
የድርሻቸውን ሊወጡ ይገባል። በተጨማሪም እስከዛሬ ድረስ በማህበረሰባችን ውስጥ ያለውን ከእናቶች ጤና ጋር
የተያያዘ ጎጂ ባህላዊ ልማዶች ለመቀየር የመገናኛ ብዙሃን እና የጥበብ ባለሙያዎች እንዲሁ በስፋት መስራት
ይጠበቅባቸዋል። በተጨማሪም የዚህ ሁሉ ስራ ባለቤት ማህበረሰቡ ነውና እሱም በባለቤትነት ጉዳዮን ሊከታተል
ይገባል። ነፍሰጡር እናቶችም በጤና ተቋማት ለመውለድ ማመንታት እንደሌለባቸው እና በተለምዶ በሀገራችን በአንዲት
ነፍሰጡር እናት ላይ የመወሰን ድርሻ ያላቸው ባሎች ፣ ወላጅ እናቶች እና ሌሎች የቅርብ አካላት ነፍሰጡር እናቶች የወር
አበባቸው ከተቋረጠበት ጊዜ ጀምሮ አስፈላጊውን የጤና ክትትል እንዲያደርጉ ሊያበረታቱ እና ሊደግፉ ይገባል። ይህም
የደም መፍሰሱ እንዳይከሰት እና ከተከሰተም አስፈላጊው መፍትሔ በባለሙያዎች እንዲሰጥ ያደርጋል " ብለዋል።

በፍራኦል ወርቅነህ

You might also like