Hawassa Diaspora Full Gospel Believers Church

You might also like

Download as pdf or txt
Download as pdf or txt
You are on page 1of 6

ሀዋሳ ዲያስፖራ ሙሉ ወንጌል አማኞች አጥቢያ ቤተ ክርስቲያን

Hawassa Diaspora Full Gospel Believers Church

እግዚአብሔርን ማምለክ ያስመልጣል፡፡

ኦሪት ዘጸአት 23፡25-27

By Cherinet Alemgena Kuri


06 የካቲት 2014 ዓ.ም

1|Page
ርእስ፡ እግዚአብሔርን ማምለክ ያስመልጣል!!!

 ዘጸአት 23፡25-27 ” አምላካችሁንም እግዚአብሔርን ታመልኩታላችሁ፣ እርሱም


እህልህንና ዉኃሀን ይባርካል፤በሽታንም ከመካከልህ አርቃለሁ፡፡ በምድርም መካን
ወይም የምትጨነግፍ አትሆነም፣ የዘመንህን ቁጥር እሞላለሁ፡፡ መፈራቴንም
በፊትህ እሰድዳለሁ፣የምትሄድበትንም ሕዝብ ሁሉ አስደነግጣቸዋለሁ፣ ጠላቶችህንም
ሁሉ በፊትህ ጀርባቸውን እንዲያዞሩ አደርጋለሁ፡፡”
መግቢያ፡
 አምስቱ የህግ /የኦሪት/ መጽሐፋት ..ኦሪት ዘፍጥረት፣ኦሪት ዘጸአት፣ኦሪት
ዘሌዋውያን፣ኦሪት ዘሁልቁና ኦሪት ዘዳግም በሙሴ እንደተጻፉ ይታመናል፡፡
 ኦሪት ዘጸአት በሙሴ እንደተጻፈ… ዘጻ 17፡14፣24፡ 4-7፣34፡27 ማግኝት ይቸላል፡፡
 ኦሪት ዘጸአት የተጻፈበት ዘመን ከ1440-1400 B.C
 ኦሪት ዘጸአት አጠቃላይ 40 ምእራፎች ሲኖሩት ( ከምእራፍ 1-14 የእስራኤል ሕዝብ
በፈሪኦን ባርነት ስረ ለ430 ዓመት የተሰቃዩበትን መከራ እግዚአብሔር እንደ
አየ፣እንደሰማ፣እንደወረደላቸው፣ የሙሴ መነሳትና እግዚአብሔር በሙሴ በኩል ከባሪነት
በግብጽ ምድር ላይ # መቅጸፍትን በማምጣት ነጻ እንደአወጣቸው፣በድንቅና ታአምእራት
የኤርትራን ባህር አካፍሎ ሕዝቡን በደረቅ ምድር በታላቅ ክንዱ አሻግሮ ፣ የፈሪኦንን
ክንድ መስበሩን/ የሚያሳይ ሲሆን፤

ከምእራፍ 15-37
የሚያሳየው ደግሞ እግዚአብሔር ህዝቡን እርሱን ቢቻ
እንዲያመልኩ፣እንዲታመኑ እንዲፈሩት እያሳሰባቸው ፣በድንቅና በታምራት ፣ መናን
እያበላቸው፣ መራራን ውኃ እያጣፈጠላቸው ፣ውኃን ከአለት እያፈለቀላቸው ፣በእሳትና በዳመና
እየመራቸው ፣በጠላቶቻቸው ላይ ድል እየሆነላቸው ፣ከእርሱ የተደነገገችውን አስርቱ ትእዛዛትን
እንዲጠብቁ ቢየዛቸውም ሕዝቡ ግን በእርሱ ላይ እንደተነሱ የሚያሳዩ ምእራፎች ናቸው፡፡
የመጨረሻ ሶስቱ መእራፎች ደግሞ ፤

ከምእራፍ 38-40 ለእግዚአብሔር የመገናኛ ድንኳን እንዲዘጋጅ ለሙሴ ትእዛዝ መስጠቱ፣


በእግዚአብሔር ትእዛዝ የመገናኛ ዲንኳን መዘጋጀቱ፣ ደመና የመገናኛ ዱንኳኑን መክደኑና
የእግዚአብሔር ክብር ማደሪያውን መሙላቱ እና እርሱም ልኡል እግዚአብሔር በቀን በደመናና
በሌሊት በእስት በመንገዳቸው እንደመራቸው / ያሳያል፡፡
#1) ውኃ ወደ ደም ተለወጠ (ዘጸ7፡20) 5) ከብቶቻቸው በሞት ተመቱ/ ዘጸ 9፡6/

2) ምድራቸው በጓጉንቸር/ በእንቁራሪት/ ተሸፈነ/ዘጸ8፡6/ 6) በቁስል ተመቱ /ዘጸ 9፡10/

3) በቅማል መታቸው/ ዘጸ 8፡17/ 7) በበረዶ ተመቱ /ዘጸ 9፡25/

4) በዝንብ መንጋ መታቸው/ ዘጸ8፡24/ 8) በአንበጣ መንጋ ተመቱ /ዘጸ 10፡13/

9) በጽኑ ጨለማ ጠመቱ /ዘጸ 10፡22/ 10) በኩራቸው ሁሉ በሞት ተመቱ /ዘጸ 12፡29)

2|Page
 አምልኮ ምንድን ነው? በእውነትና በመንፈስ፣አንደበትን በመግታት፣በንጹ ህልና ወይም ያለሽንገላ
እግዚአብሔርን መውደድ፣ማክበር፣ የባላይ አድርጎ መሾም ነው ፡፡ (2 ጢሞ 3፡5፣ዮሐ 4፡23-
24፣ያዕ 1፡26-27

 እግዚአብሔር አምላክን እንደት ነው የምናመልከው?


 ዋና ዋና ስድስት ነጥቦች፡
1) በስግደት፣ ዮሐ 4፡23-24…”ነገር ግን በእውነት የሚሰግዱ ፣ ለአብ በመንፈስና በእውነት
የሚሰግዱበት ጊዜ ይመጣል አሁንም ሆኖአል፣ አብ ሊሰግዱለት እንደ እነዚህ ያሉትን ይሻል፡፡
እግዚአብሔር መንፈስ ነው ፣የሚሰግዱለትም በመንፈስና በእውነት ሊሰግዱለት ያስፈልጋቸዋል፡፡”
 በሳሚራዊት ሴት እና በኢየሱስ ክርስቶስ መካከል የተደረገው ንግግር…
 ዘሬ እኛ ለመን እየሰገድን ነው? በእውነትና በመንፈስ ነው የምንሰግደው?
2) በዜማ፡/በምስጋና/ ሐዋ/ስራ 16፡25-26 ”በመንፈቀ ለሊት ግን ጳውሎስና ሲላስ እየጸለዩ
፣እግዚአብሔርን በዜማ ያመሰግኑ ነበር፣ እስረኞቹም ያዳምጡአቸው ነበር፡፡ ድንገትም የወህኑ
መሰረት እስክናወጥ ድረስ ታላቅ የምድር መንቀጥቀጥ ሆነ፣በዚያን ጊዜም ደጆቹ ሁሉ
ተከፈቱ፣የሁሉም እስራት ተፈታ፡፡”
 ሐዋሪያው ጳውሎስና ሲላስ በማይመች ሁኔታ ውስጥ ሁኖ እግዚአብሔርን በዜማ
አመለኩ/አመሰገኑ/….እኛስ? ወደ ምስጋና ህይወት እንመለስ!!
3) በጸሎት /በልመና/
ዳንኤል 6፡10….” ዳንኤልም ጽሕፈቱ እንደ ተፃፈ ባወቀ ጊዜ ወደ ቤቱ ገባ የእልፈኙም
መስኮቶች ወደ ኢየሩሳሌም አንጻር ከፊተው ነበር፣ቀድሞ ያደረግ እንደ ነበር በየእለቱ
ሶስት ጊዜ በጉለበቱ ተንበርክኮ በአምላኩ ፊት ጸለየ አመሰገነም፡፡”
ማቴ 7፡7 ”ለምኑ የሰጣችሁማል፣ፈልጉ ታገኙማላችሁ፣መዝጊያን አንኳኩ
ይከፈትላችሁማል፡፡”
 እነ ዳንኤል አዋጅ በታወጀበት ጊዜ እንኳን ወደ እግዝአብሔር መጸለይ አላቆሙም….እኛስ?
ወደጸሎት እንመለስ፣ የጸሎት ሀይል ይሰጠን!
4) የተቸገሩትን በመርዳት (በመጠየቅ)
ያዕቆ 1፡27 ”ንጹሕ የሆነ፣ ነውርም የሌለበት አምልኮ በእግዚአብሔር አብ ዘንድ ይህ
ነው፣ወላጆች የሌላቸውን ልጆች፣ባልቴቶችንም በመከራቸው መጠየቅ (መርዳት)፡፡”
ማቴ 25፡36-40.. ”ታምሜ ጠይቃችሁኛልና፣ታስሬ ወደ እኔ
መጥታችሁልና…..ቁ40..ንጉሡም መልሶ እውነት እላችሀለሁ ከሁሉ ከሚያንሱ ከእነዚህ
ወንድሞች ለአንዱ እንኳን ስላደረጋችሁት ለእኔ እደረጋችሁት ነው ይላቸዋል..”
 እኛስ ዛሬ ንጉሱ ብጠይቀን መልሳችን ምንድ ነው? እኛ ዛሬ እያረዳን ነው?
5) በመስጠት
ሚልክ 3፡10 ” በቤቴ ውስጥ መብል እንዲሆን አስራቱን፣ሁሉ ወደ ጎተራ
አግቡ፣የሰማይን መስኮት ባልከፍትላችሁ ፣በረከትም አትረፍርፌ ባላፈስላችሁ፣በዚህ
ፈትኑኝ ይላል የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር፡፡”
2ኛ ቆሮ 9፡7-9 ” እግዚአብሔር በደስታ የሚሰጠውን ይወዳልና፣እያንዳንዱ በልቡ
እንዳሰበ ይስጥ፣በሀዘን ወይም በግድ አይደለም፡፡”
 ለወንጌል ስራ መባ፣አስራት፣ስጦታችንን እየሰጠን ነው? ምን እያደረግን ነው?

3|Page
6) በመመለስ/በንህሳ/

ኢዩ 2፡ 12-13 … ”አሁንስ ይላል እግዚአብሔር ፣በፍጹም ልባችሁ፣በጾምም በለቅሶና በዋይታ ወደ እኔ


ተመለሱ፣ ልባችሁን እንጂ ልብሳችሁን አትቅደዱ…”

2 ዜና 7፡ 13-14.. ዝናብ እንዳይወርድ ሰማያቱን ብዘጋ፥ ወይም ምድሪቱን ይበላ ዘንድ አንበጣን
ባዝዘው፥ ወይም በሕዝብ ላይ ቸነፈር ብሰድድ፥ በስሜ የተጠሩት ሕዝቤ ሰውነታቸውን አዋርደው
ቢጸልዩ፥ ፊቴንም ቢፈልጉ፥ ከክፉ መንገዳቸውም ቢመለሱ፥ በሰማይ ሆኜ እሰማለሁ፥ ኃጢአታቸውንም
ይቅር እላለሁ፥ ምድራቸውንም እፈውሳለሁ።

 እኛም ዛሬ በፍጹም ልባችን ወደ እግዚአብሔር እንመለስ?

የአምልኮ ጥቅሞች፣ በዚህ መእራፍ እንደተገለጸው እግዚአብሔር አምላክን ስናመልክ፡


1) እህልና ውኀችንን ይባርካል፣
ዘጸ 23፡25…”እርሱም እህልህንና ዉኃሀን ይባርካል…”
 ኢዩ 2፡24…” አውድማችሁም በእህል ይሞላል፣ ምጥመቂያዋችሁም የወይን ጠጅና ዘይትን
አትረፈርፈው ያፈሳሉ፡፡”

 1ኛ ነገስት 17፡14.. ”የእስራኤልም አምላክ እግዚአብሔር እንድ ይላልና፣በምድር ላይ እግዚአብሔር


ዝናብ እስከሚሰጥበት ቀን ድረስ ዱቄት ከማድጋ አይጨረስም፣ዘይቱም ከማሰረው አይጎድልም፡፡”
 እግዚአብሔርን ስናመልክ ከብክነት፣ከማጣት፣ከድህነት፣ከጉስቁልና…. ያስመልጠናል፡፡

2) በሽታንም ከኛላይ ያርቃል፣ (መንፈሳዊ በሽታና ስጋዊ በሽታ/

ዘጸ 23፡25…፤በሽታንም ከመካከልህ አርቃለሁ…”

 በሽታ የሰውን ሁለንተና (ነፍስ፣ስጋና መንፈስን/ ልነካ ይችላል!


 መንፈሳዊ በሽታ በጌታ በኢየሱስ ደም ከእኛላይ ይወገዳል!!

ኢሳይያስ 5፡4 -5… በእውነት ደዌያችንን ተቀበለ ሕመማችንንም ተሸክሞአል፤ እኛ ግን እንደ ተመታ
በእግዚአብሔርም እንደ ተቀሠፈ እንደ ተቸገረም ቈጠርነው። እርሱ ግን ስለ መተላለፋችን ቈሰለ፥ ስለ
በደላችንም ደቀቀ፤ የደኅንነታችንም ተግሣጽ በእርሱ ላይ ነበረ፥ በእርሱም ቍስል እኛ ተፈወስን።

1ኛ ጴጥሮስ 2፥24 “ለኃጢአት ሞተን ለጽድቅ እንድንኖር፥ እርሱ ራሱ በሥጋው ኃጢአታችንን


በእንጨት ላይ ተሸከመ፤ በመገረፉ ቁስል ተፈወሳችሁ።”

 እግዚአበሔርን ስናመልክ ማንኛውም በሽታ ከእኛ ላይ ይርቃል፡፡ በህይወታችን ላይ ስልጣን


የለውም!!

4|Page
3) መካንነት እና ጭንገፋን ከእኛ ያርቃል፣

ዘጸ 23፡26……” በምድርም መካን ወይም የምትጨነግፍ አትሆነም፣…”

 ስጋዊ መካንነት የስወግዳል፡


 ዘፍ 21፡1-2…እግዚአብሔርም እንደ ተናገረው ሣራን አሰበ፣እግዚአብሔርም እንደ ተናገረው
ለሣራ አደረገላት
ቁ2…ሣራም ፀነሰች፣እግዚአብሔርም በተናገረው ወራት ለአብርሃም በእርጅናው ወንድ ልጅን
ወለደችለት፡፡
 1ኛ ሳሙ 1፡19-20…በእግዚአብሔር ፊት ሰገዱ፣ተመልሰውም ወደ አርማቴም ወደ
ቤታቸው መጡ፣ ሕልቃናም ሚስቱን ሐናን አወቃት እግዚአብሔርም አሰባት፡፡”
 ሉቃ 1፡24-25..ከዚሀም ወራት በኋላ ሚስቱ ኤልሳቤጥ ፀነሰች ነቀፌታዬን ከሰው መካከል
ያስወግድልኝ ዘንድ ጌታ በተመለከተበት ወራት እንዲሁ አድርጎልኛል ስትል ራስዋን አምስት
ወር ሰወረች፡፡
 መንፈሳዊ መካንነት ያስወግዳል፡
 ኤርም 17፡7-8፡ … በእግዚአብሔር የታመነ እምነቱም እግዚአብሔር የሆነ ሰው ብሩክ
ነው፡፡ በውኃ አጠገብ እንደ ተተከለ፣ በወንዝም ዳር ሥሩን እንደሚዘረጋ ሙቀትም
ስመጣ እንደማይፈራ ቅጠሉም እንደሚለመልም፣ በድርቅ ዓመታትም እንደማይሰጋ
ፍሬውንም እንደማያቋርጥ ዛፍ ይሆናል፡፡……
 ገላቲ 5፡22
 በኢየሱስ ስም፡ የመንፈስ ፍሬያችሁ…ፍቅር፣ደስታ፣ሰላም፣ትእግስት፣ቸርነት፣በጎነት፣
እምነት፣ የውሀነት፣ራስን መግዛት….ከእናንተ አይታጣ!!!
 ስጋዊ እና መንፈሳዊ ጭንገፋ አይሆንም፡

2ኛ ነገሥት 2፡21-22 .. ” ውኀው ወዳለበት ምንጭ ወጥቶ ጨው ጣለበትና እግዚአብሔር እንዲህ


ይላል ይህን ውሀ ፈውሼዋለሁ፣ከዚህም በኋላ ሞትና ጭንገፋ አይሆንበትም አለ፡፡” ኤልሳዕም
እንደተናገረው ነገር ውኀው እስከ ዘሬ ድረስ ተፈውሶአል፡፡

 ስለዚህ ዛሬ እግዚአብሔር ከመካንነትና ከጭንገፋ ያስመልጠናል፡፡

4) የዘመናችንን ቁጥር ይሞላዋል!

ዘጸ 23፡26…” የዘመንህን ቁጥር እሞላለሁ…”

መዝ 91፡15-16.. ” ይጠራኛል እመልስለትማለሁ፣ በመከራውም ጊዜ ከእርሱ ጋር እሆናለሁ፣


አድነዋለሁ፣ከብረውማለሁ፣ ረጅመን ዕድሜ አጠግበዋለሁ፣ማዳኔንም አሳየዋለሁ፡፡”

 ስለዚህ ዛሬ እግዚአብሔር ካለ ጊዜ ሞት እንዲሁም ከመንፈሳዊ ሞት ያስመልጠናል፡፡


5) ጠላቶቻችንን ያዋርዳቸዋል፣
 ዘጸ 23፡27…” መፈራቴንም በፊትህ እሰድዳለሁ፣የምትሄድበትንም ሕዝብ ሁሉ
አስደነግጣቸዋለሁ፣ ጠላቶችህንም ሁሉ በፊትህ ጀርባቸውን እንዲያዞሩ አደርጋለሁ…”
 ዘጸ 23፡22…” አንተ ግን ቃሉን ብትሰማ ፣ያልሁንም ብታደርግ፣ ጠላቶችህን
እጥላቸዋለሁ፣የሚያስጨንቁህንም አስጨንቃቸዋለሁ…”

5|Page
 መዝ 91፡7. ” …በአጠገብህ ሺህ በቀኝ አስር ሺህ ይወድቃሉ፣ ወደ አንተ ግን
አይቀርቡም፡፡”
 መዝ 108፡13…በእግዝአብሔር ሀይል እናደርጋለን፣ እርሱም የሚያስጨንቁንን
ያዋርዳቸዋል፡፡

 ስለዚህ ዛሬ እግዚአብሔር ከጠላቶቻችን እጅ ያስመልጠናል፡፡

ማጠቃለያ፡ 1ጴጥ 1፡19 ፣ 1፡23 ፣ 2፡10 ፣ 1 ዮሐ 1፡7…እኛም ዛሬ በክርስቶስ ኢየሱስ ደም


የተዋጀን፣ ከሞትና ከሀጢአት ባሪነት ነጻ የወጣን፣ ወዳጆቹ የሆን፣ ከማይጠፋ ዘር ደግመኛ
የተወለድን ፣ በእውነትና በመንፈስ እርሱን ማምለክ አለብን!!

 ዮሐ 4፡23-24…”ነገር ግን በእውነት የሚሰግዱ ፣ ለአብ በመንፈስና በእውነት የሚሰግዱበት ጊዜ


ይመጣል አሁንም ሆኖአል፣ አብ ሊሰግዱለት እንደ እነዚህ ያሉትን ይሻል፡፡ እግዚአብር መንፈስ ነው
፣የሚሰግዱለትም በመንፈስና በእውነት ሊሰግዱለት ያስፈልጋቸዋል፡፡”

ትንቢታዊ አዋጅ ፤
 ዛሬ/አሁን/ ፣በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም !!!

 የአምልኮ መንፈስ /ሀይል/ በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ይጨመሪላችሁ!!


 በረከታችሁን የበላ ፣አንበጣና ደጎብያ፣ኩብኩባና ተምች ፣በጌታ
በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ይሰበር/ይነሳ፡፡
 ማንኛውም በሽታ ከእናንተ ላይ ፣በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም
ይነሳ/ይሰበር/፡፡
 ማንኛውም መንፈሳዊና ሲጋዊ መካንነት፣ጭንገፋ ፣በጌታ በኢየሱስ
ክርስቶስ ስም ይነሳ/ይሰበር፡፡
 የዘመናችሁ ቁጥር ፣በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ይሙላ፡፡
 ማንኛውም ጭንቀት ከህይወታችሁ ላይ፣በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም
ይነሳ/ይሰበር፡፡
 በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ጠላታችሁ ይዋረድ፡፡
ጥሪ፡
ለአዲስ ሰዋች….ጌታን ላልተቀበላችሁት…ኑ ወደ ጌታችን ኢየሱስ
ክርስቶስ…እርሱ በቃሉ ወደ አንተ/አንቺ መጧል!! ንሲሃ መግባት
የምትፈልጉም ኑ ወደ ጌታ!

ጌታ ይባረክ!! 06 የካቲት፣ 2014 ዓ.ም

6|Page

You might also like