Download as pdf or txt
Download as pdf or txt
You are on page 1of 39

13 ዓመት q$_R 4 bdb#B B/@éC½ B/@rsïCÂ ?

ZïC KLል
hêú ሚያዚያ 3 qN 1999 ዓ/ም›.M Mክር b@T -ÆqEnT ywÈ አዋጅ

ydb#B B/@éC½ B/@rsïCÂ ?ZïC KLላዊ መንግሥት የከተሞች


አደረጃጀትና የአስተዳደር ስርዓት ደንብ ቁጥር 58/1999

ከተሞች የአገርን ማህበራዊ ኢኮኖሚያዊ ዕድገት በማፋጠን የልማት እንቅስቃሴን በማጎልበት


ረገድ የሚጫወቱት ሚና ጉልህ መሆኑን በመገንዘብ ተሻሽሎ የወጣውን የከተሞች አዋጅ ቁጥር
103/1999 ተግባራዊ ለማድረግ ዝርዝር ጉዳዮችን በመወሰን የአፈፃፀም ደንብ ማውጣት
በማስፈለጉ፣

የከተሞች አደረጃጀትን፣ አስተዳደርና አመራር አካላትን ከዲሞክራሲ መርሆዎችና ከመልካም


አስተዳደር ስርዓት ጋር እና ከወቅታዊ የዕድገት አቅጣጫና የከተማ ልማት ፖሊሲ አንፃር
በማጣጣም እንደገና ለማደራጀት በሥራ ላይ የቆዩትን የከተሞች አደረጃጀትና አስተዳደር ስርዓት
ደንብ ቁጥር 6/1995 እና የከተማ ሽግግር አስተዳደር ማቋቋሚያ ደንብ ቁጥር 7/1995 ማሻሻል
በማስፈለጉ፣

የደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልላዊ መንግሥት መስተዳድር ምክር ቤት አዲስ


ተሻሽሎ በፀደቀው የክልሉ ከተሞች አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 103/1999 አንቀጽ ፶፮ ንዑስ
አንቀጽ 1 በተሰጠው ስልጣን መሠረት ይህን ደንብ አወጥቷል፡፡

ክፍል አንድ
ጠቅላላ
1. አጭር ርዕስ
ይህ ደንብ የደቡብ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ክልላዊ መንግሥት የከተሞች አደረጃጀትና
የአስተዳደር ስርዓት ደንብ ቁጥር 58/1999 ተብሎ ሊጠቀስ ይችላል፡፡

1
2. ትርጓሜ
በአዋጁ ውስጥ በአንቀጽ ፪ ትርጓሜ የተሰጣቸው ጉዳዮች እንደተጠበቁ ሆነው በዚህ ደንብ
ውስጥ በግልጽ ሌላ ትርጓሜ ካልተሰጣቸው በስተቀር፡-
1. «አዋጅ» ማለት የከተሞች አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 103/99 ማለት ነው፡፡
2. «ቢሮ» ማለት አግባብ ባለው የክልሉ ሕግ መሠረት የተቋቋመ የሥራና ከተማ ልማት
ቢሮና በሥሩ ያሉ የበታች መዋቅር ያካትታል፡፡
3. «ክፍለ ከተማ» ማለት የደቡብ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል መንግሥት
በከተማች አስተዳደር የከተማው ሁለተኛ የአስተዳደር እርከን ነው፡፡
4. «የቀበሌ አስተዳደር» ማለት የከተማ አስተዳደር ታችኛው የአስተዳደር እርከን ነው፡፡
5. መሪ ከተማ አስተዳደር ማለት በክልሉ ውስጥ የተሻለ እና የመሪነት ሚና የሚጫወት
የሕዝብ ብዛት ከ100 000 በላይ የሆነ ከተማ ነው፡፡
6. ከፍተኛ ከተማ አስተዳደር ማለት በኢኮኖሚና ማህበራዊ እንቅስቃሴ የላቀ ደረጃ የደረሰ፣
የህዝብ ብዛት ከ60000 – 100000 የሆነ ከተማ ነው፡፡
7. መካከለኛ ከተማ አስተዳደር ማለት የተሻለ የኢኮኖሚና ማህበራዊ እንቅስቃሴ ያለው፣
የህዝብ ብዛቱ ከ30000 እስከ 60000 የሚደርስ ከተማ ነው፡፡
8. ታዳጊ ከተማ አስተዳደር ማለት የነዋሪው ሕዝብ ብዛት ከ10000 እስከ 30000 የሆነ
የተደራጀ የከተማ አስተዳደር ነው፡፡

3. የፆታ አገላለጽ
በዚህ ደንብ ውስጥ ለወንድ ፆታ የተደነገገው የሴቷንም ፆታ ያካትታል፡፡

4. የተፈፃሚነት ወሰን
ይህ ደንብ በአዋጁ መሠረት በተቋቋሙ የክልል የከተማ አስተዳደር ከተሞች እና የማዘጋጃ
ቤት ከተሞች ሁሉ ተፈፃሚ ይሆናል፡፡

ክፍል ሁለት
በከተማነት ስለመቋቋም
5. በከተማነት ለመቋቋም የሚያበቁ ሁኔታዎች
በከተማነት ለመቋቋም በአዋጁ አንቀጽ ፰ ንዑስ አንቀጽ ፪ እና ፫ የተደነገገው አጠቃላይ
ድንጋጌ እንደተጠበቀ ሆኖ የከተማነት እውቅና በቢሮው አነሳሽነት በሚደረግ ጥናት ወይም
በማህበረሰቡ ጥያቄ ሊከናወን ይችላል፡፡

2
1. በቢሮው አነሳሽነት የሚሰጥ የከተማ እውቅና
1.1. ቢሮው በሚያደርገው ጥናት የከተማነት እውቅና መስጠት የሚቻለው መሠረታዊ
መስፈርቶችን የሚቀይር የአዋጅ ወይም ሌሎች ሕጐች በሚያስከትሉት ለውጥ
ብቻ ነው፡፡
1.2. ከላይ በቁጥር 1.1 የተጠቀሰው እንደተጠበቀ ሆኖ ቢሮው የከተማ እውቅና
እንዲያገኘ የተመረጠው ከተማ በዞኑ አስተዳደር አማካኝነት ጥያቄውን ላቀረበው
ማህበረሰብ ቀርቦ ስምምነት ላይ መደረስ ይኖርበታል፡፡
2. በሕዝቡ ጥያቄ ስለሚሰጥ የከተማነት እውቅና
2.1. አንድ ማህበረሰብ የከተማነት እውቅና እንዲሰጠውና እንዲተዳደር መጠየቅ
ይችላል፡፡
2.2. በማህበረሰቡ የሚቀርብ የከተማነት ጥያቄ በተወካዮቹ የሚቀርብ ሆኖ በዚህ ደንብ
አንቀጽ ፮ እና ፯ በተደነገገው መሠረት ተፈፃሚ ይሆናል፡፡

6. በከተማነት ለመቋቋም ስለሚቀርብ ማመልከቻ


በአዋጁ አንቀጽ ፰ ንዑስ አንቀጽ 3 የተደነገገው እንደተጠበቀ ሆኖ፣
1. የተወካዮች አመራረጥ
የከተማነት ደረጃ ለማግኘት የሚፈልግ ማህበረሰብ ለቢሮው ማመልከቻ የሚያቀርበው
ከዚህ በታች በተዘረዘሩት ሶስት አባላት ባሉት ተወካዮች አማካኝነት ይሆናል፡፡
ውክልናቸውም በወረዳ ወይም ልዩ ወረዳ ምክር ቤት በተፃፈ ደብዳቤ መረጋገጥ
ይኖርባታል፡፡
1.1. ማህበረሰቡ ከሚያቅፋቸው ቀበሌዎች አንድ የቀበሌ ምክር ቤት ተመራጭ፣
1.2. በማህበረሰቡ የሚወከል አንድ የሀገር ሽማግሌ /ታዋቂ ግለሰብ/
1.3. ማህበረሰቡ ከሚኖርበት አካባቢ ካሉ መንግሥታዊ ተቋማት/የትምህርት፣ የጤና
ወዘተ/ አንድ ተወካይ፣
2. የማመለከቻው ይዘት
የከተማነት ደረጃ ለማግኘት ለቢሮው ከሚቀርቡ ማመልከቻ ጋር የሚከተሉት
ማስረጃዎች ተያይዘው መቅረብ አለባቸው፡፡
2.1. በማህበረሰቡ ከታቀፈው መራጭ ህዝብ ከ10 ከመቶ በላይ የሚሆነው ጥያቄውን
በመደገፍ ያረጋገጡበት የድጋፍ ፊርማ ሠነድ፣
2.2. የከተማ ዳር ድንበር በግልጽ የተወሰነበት ማስረጃ

3
2.3. የዳር ድንበሩን ማስረጃ በተመለከተ ማህበረሰቡ ከታቀፈበት የወረዳ/ልዩ ወረዳ
አስተዳደር ምክር ቤት የተሰጠ የድጋፍ ደብዳቤ፡፡

7. ከማመልከቻ ጋር ስለሚቀርብ ሠነድ


በአዋጅ አንቀጽ ፰ ንዑስ አንቀጽ 3.2 በተደነገገው መሠረት ከማመልከቻ ጋር የሚቀርበው
ደጋፊ ሠነድ የሚከተሉትን ያካተተ መሆን አለበት፣
1. ማህበረሰቡ የሚኖርበት ስፍራ ዳር ድንበር የሚከተሉት አካላት በሚያደርጉት የጋራ
ስብሰባ የሚወሰንና በተሰብሣቢዎቹ በሚፈረም ቃለ ጉባዔ የሚረጋገጥ ይሆናል፡፡
1.1. ማበረሰቡ ከታቀፈበት ወረዳ ምክር ቤት አንድ ተወካይ - ሰብሣቢ
1.2. ማበረሰቡ ከታቀፈበት ወረዳ የገጠር ልማት ጽ/ቤት አንድ ተወካይ - አባል
1.3. ከማህበረሰቡ አዋሳኝ ቀበሌ ገበሬ ማህበራት አንዳንድ ተወካይ - አባላት
1.4. ማህበረሰቡ የሚገኝበት ቀበሌዎች ጽ/ቤት/ቤቶች ማህበራት አንዳንድ ተወካይ -አባላት
1.5. ማህበረሰቡ የሚገኝበት ቀበሌዎች ሁለት ታዋቂ ግለሰቦች - አባላት
1.6. ጉዳዩ የሚመለከተው መምሪያ አንድ ተወካይ አባለና ፀሐፊ

2. ቃለ ጉባዔው የወሰኖችን ምልክቶች በግልጽ የሚያመላክት እና የሚመለከተው የወረዳ ወይም ልዩ


ወረዳ አስተዳደር ምክር ቤት በሚሰጠው የድጋፍ ማረጋገጫ ደብዳቤ የተረጋገጠ መሆን አለበት፡፡

8. በቢሮ ስለሚቀርብ ጥናት ሠነድ


የጥናት ሠነዱ በዞን መምሪያዎች የሚቀርብ ሆኖ የሚከተሉትን ማካተት ይኖርበታል
8.1. ማህበረሰቡ በከተማነት ለመቋቋም የሚያስፈልጉ ማህበራዊ ኢኮኖሚያዊ ሁኔታዎች
የሚያሟላ መሆኑን በማረጋገጥ በመምሪያው ወይም በወረዳው የተዘጋጀ የጥናት
ሠነድና የሶስት ዓመት የልማትና የመልካም አስተዳደር እቅድ፣
8.2. ከማህበረሰቡ የሶስት ተከታታይ ዓመት አማካይ ገቢ ውስጥ ቢያንስ 75% ለታዳጊ
የማዘጋጃ ቤት ከተሞች የሚያስፈልገውን ሰው ሀይል ደመወዝ ለመሸፈን የሚበቃ
መሆኑን የሚያሳይ ማረጋገጫ፣
8.3. ማህበረሰቡ በከተማነት ቢቋቋም ሊኖረው የሚችለው የገቢ አቋም፣
8.4. የማህበረሰቡን የመሠረተ ልማትና የማህበራዊ አገልግሎት ገጽታ እንዲሁም
የአካባቢውን የመሬት አቀማመጥ ለልማት አመቺነት የሚያመላክት ጥናት፣
8.5. የማህበረሰቡ የህዝብ ብዛት ከ2000 በላይ መሆኑን የሚያረጋግጥ ሠነድ መሆን
አለበት፣

4
9. የከተማነት ዕውቅና ስለማግኘት
1. ከአዋጁ በፊት እውቅና ስላላቸው ከተሞች
1.1. አዋጁ እስከወጣበት ጊዜ ቀደም ሲል በነበረው ህግ መሠረት በክልሉ መስተዳድር
ምክር ቤት የከተማነት እውቀና የተሰጣቸው ከተሞች በዚህ ደንብ የከተማነት
እውቅና ለማግኘት የተመለከቱ ድንጋጌዎች መፈፀም ሳያስፈልጋቸው በአዋጁ
አንቀጽ 5 በተመለከተው መሠረት እንደ ህዝብ ብዛታቸው እየታዩ በየፈርጅ
ይመደባሉ፡፡
1.2. በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ አንድ መሠረት በየፈርጁ የተመደቡ ከተሞች ዝርዝር
መስተዳድር ምክር ቤቱ በሚያወጣው የህግ ክፍል ማስታወቂያ ይገለፃል፡፡
2. ከአዋጁ በፊት እውቅና ስለሌላቸው ከተሞች
2.1. አዋጁ እስከወጣበት ቀን ድረስ የከተማነት ዕውቅና ካላገኘ ከማንኛውም
ማህበረሰብ የሚቀርብ ጥያቄ በአዋጁና በዚህ ደንብ በከተማነት ለመቋቋም
የሚበቁ ሁኔታዎችና መመዘኛዎች በተመለከተ የተደነገጉ ድንጋጌዎች ተፈፃሚ
ይሆናሉ፡፡
2.2. በአዋጁ አንቀጽ ፰ ንዑስ አንቀጽ 6 መሠረት እያንዳንዱ የከተማነት ደረጃ
የተሰጠው ማህበረሰብ የከተማነት ህጋዊ እውቅና ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት
ይሰጠዋል፡፡

0. ከህጋዊ አካልነት ስለመሰረዝ


1. አንድ ከተማ ከህጋዊ አካልነት እንዲሰረዝ ቢሮው አስተያየት ሲያቀርብ የከተማውን
የኦዲት ውጤት፣ ከተማው ባለበት ደረጃ የያዛቸው መብቶችና ግዴታዎች በዝርዝር
የሚያሳይና በከተማነት ለመቀጠል ከሚያስፈልጉት መመዘኛዎች ያጓደለውን መመዘኛ
በግልጽ የሚያመላክት ጥናት መቅረብ አለበት፡፡
2. አንድ ከተማ ከህጋዊ አካልነት ሲሰረዝ የከተማው መብቶችና ግዴታዎች ከተማው
ለሚገኝበት የወረዳ/ልዩ ወረዳ አስተዳደር ምክር ቤት ይተላለፋሉ፡፡
3. ከላይ በንዑስ አንቀጽ 1 እና 2 የተጠቀሱት እንደተጠበቁ ሆነው፡-
በህጋዊ አካልነት ለመቋቋም የሚያበቃውን መመዘኛ ያጓደለ ከተማ መመዘኛውን
ያጓደለው በአፈፃፀም ችግር ምክንያት ብቻ የሆነ እንደሆነ ከህጋዊ አካልነት ከመሰረዙ
አስቀድሞ በቢሮው ልዩ ክትትልና ድጋፍ እየተደረገለት ለአንድ ሙሉ የበጀት ዓመት
እንዲታይ ይደረጋል፣ በዚህ ጊዜ ውስጥ ያጓደለውን መመዘኛ ማሟላት ካልቻለ
ከከተማነት ይሰረዛል፡፡

5
01. በነጋሪት ጋዜጣ በይፋ ስለማሳወቅ
አንድ ማህበረሰብ በከተማነት በመቋቋም ህጋዊ ሰውነት ሲያገኝ ወይም ከከተማነት
በመሰረዙ ምክንያት ህጋዊ ሰውነቱን ሲያጣ ይኸው በደቡብ ነጋሪት ጋዜጣ በሚታተም
የህግ ክፍል ማስታወቂያ ይፋ ይደረጋል፡፡

ክፍል ሶስት
የከተማ አስተዳደር ከተሞች አመሠራረት እና አካላት
ምዕራፍ አንድ
አመሠራረት
፲፩ የከተማ አስተዳደር የሚቋቋምባቸው ከተሞች አወሳሰን
1. መመዘኛ መስፈርቶች
1.1. የከተማ ዕውቅና የተሰጣቸውና የከተማ አገልግሎቶችን በመስጠት ላይ
የሚገኝ፣
1.2. የነዋሪው ሕዝብ ብዛት ከ10 ሺህ በላይ የሆነ፣
1.3. በአካባቢው ከሚገኙ ከተሞች በኢኮኖሚ እንቅስቃሴው የተሻለ ደረጃ ላይ
የሚገኝ፣ ከከተሞችና ከገጠሩ ጋር ተሳስሮ በማደግ አካባቢውን ይዞ
ለመልማት ዕድሉ ከፍተኛ የሆነ፣
1.4. በከተማው የመሠረተ ልማት እና ማህበራዊ አገልግሎቶች የተስፋፋበት እና
ገቢ የመሰብሰብ አቅሙ ከፍተኛ የሆነ፣
1.5. የፖለቲካ እና አስተዳደር ማዕከል የሆነ፣
1.6. ሁለት እና ከዚያ በላይ የቀበሌ አስተዳደሮችና ምክር ቤቶች ያሉት፣
2. ውሣኔ ሰጪ አካል
2.1. አንድ ከተማ የከተማ አስተዳደር ሊዋቀርለት የሚችለው ከላይ በንዑስ
አንቀጽ 1 መሠረትና ሌሎች ቴክኒካዊ መስፈርቶችን መሠረት አድርጎ ቢሮው
ለሚያደርገው ጥናት መነሻነት የክልሉ መስተዳድር ምክር ቤት በሚሰጠው
ውሣኔ ነው፡፡
2.2. ከላይ በቁጥር 2.1 የተጠቀሰው እንደተጠበቀ ሆኖ የከተማ አስተዳደር
እንዲዋቀር በቢሮው የሚደረግ ጥናት ቢያንስ በየ3 ዓመቱ መሆን
ይኖርበታል፡፡

6
03. በሪፎርም ፕሮግራም የታቀፉ ከተሞች
በከተማች አስተዳደር አዋጁ ቁጥር 103/99 በአንቀጽ 6/2 በተደነገገው መሠረት የከተማ
አስተዳደር ከተሞች ሆነው የሚቋቋሙ ከተሞች በሪፎርም ፕሮግራም የታቀፉ ከተሞች
ይሆናሉ፡፡

ምዕራፍ ሁለት
የከተማ አስተዳደር አካላትና አሰያየም
04. የከተማ አስተዳደር አካላት
የከተማ አስተዳደር ከተሞች የሚከተሉት የአስተዳደር አካላት ይኖራቸዋል፡፡
1. የከተማ ምክር ቤትና አፈጉባዔ እንዲሁም እንደአስፈላጊነቱ ምክትል አፈጉባዔ፣
2. ከንቲባ እንደአስፈላጊነቱ ምክትል ከንቲባ
3. የከንቲባ ኮሚቴ
4. የማዘጋጃ ቤት አገልግሎቶች ሥራ አስኪያጅ እንዲሁም እንደአስፈላጊነቱ ምክትል
ሥራ አስኪያጅ
5. የከተማ ነክ ጉዳዮች ፍርድ ቤቶች
6. በዚህ ደንብ አንቀጽ ፲፮ መሠረት የሚቋቋሙ ሌሎች አስፈፃሚ መስሪያ ቤቶች
የሚመሩ ኃላፊዎች፡፡

05. ስለ ከንቲባ አሰያየምና ተጠሪነት


1. አሰያየም
1.1. አብላጫ ወንበር ከያዘው ፖለቲካ ፓርቲ አቅራቢነት በም/ቤቱ ይሰየማል፡፡
1.2. የእያንዳንዱ ከተማ ከንቲባ ከየከተማው አይነትና ደረጃ አንፃር ሊኖረው
የሚችለውን የትምህርት፣ የሥራ ልምድ፣ የማስፈፀምና የፖለቲካ አመራር
ብቃትና ችሎታ መሠረት ያደረገ መሆን ይኖርበታል፡፡
1.3. ከከተማው ምክር ቤት መቀመጫ የተወሰነ ቁጥር ለአካባቢው ብሔረሰብ/ቦች
እንዲሆን በክልሉ መስተዳድር ምክር ቤት ሲወሰን ከንቲባው በከተማው
አካባቢ ወይም በዞኑ ወይም ከልዩ ወረዳው ከሚገኙ ብሔር ብሔረሰቦች
ከሚወክሉት የምክር ቤት አባላት መካከል ይሆናል፡፡

2. የከንቲባው ተጠሪነት
7
2.1. ከንቲባው በሁሉም ጉዳዮች ለከተማው ምክር ቤት ተጠሪ ይሆናል፡፡
2.2. ከላይ በንዑስ አንቀጽ 1 የተመለከው እንደተጠበቀ ሆኖ የፌዴራልና የክልል
ህጎች፣ ፖሊሲዎችና ደረጃዎች አፈፃፀም፣ ከመንግሥት ለከተማ የተላለፉትን
ተግባራት ክንውንና የገንዘብ አጠቃቀምን በሚመለከቱ ጉዳዩች፣
ሀ. የመሪ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ተጠሪነቱ ለክልሉ ርዕስ መስተዳድር፣
ለ. የከፍተኛና መካከለኛ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ለሚመለከተው ዞን ዋና
አስተዳዳሪ፣
ሐ. የዞን አስተዳደር መቀመጫ የሆነ ታዳጊ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ለዞን
ዋና አስተዳዳሪ፣
መ. በልዩ ወረዳዎች ውስጥ የሚገኝ በማንኛውም ደረጃ የሚገኝ ከተማ ከንቲባ
ለልዩ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ ተጠሪ ይሆናሉ፡፡

2. ቃለ መሀላ
የከንቲባው ምርጫ በከተማው ምክር ቤት ከፀደቀ በኋላ ከንቲባው ሥራውን
ከመጀመሩ በፊት በከተማው ምክር ቤት ፊት የሚከተሉትን መሀላ ይፈጽማል፡፡
እኔ በዛሬው ዕለት የ ከተማ ከንቲባ
በመሆን ሥራዬን ስጀምር በሕዝቡና በም/ቤቱ የተጣለብኝን ከፍተኛ ኃላፊነት በብቃት
በመረዳት ለከተማው ልማት መረጋገጥ መልካም አስተዳደር መስፈን ኃላፊነቴን
በትጋት እና በታማኝነት ለመወጣት ቃል እገባለሁ፡፡

06. ስለ ከንቲባ ኮሚቴ


1. መቋቋም
የከተማ አስተዳደር በተቋቋመባቸው የክልሉ ከተሞች
1.1. በአዋጁ አንቀጽ ፳፬ በተደነገገው መሠረት የከንቲባ ኮሚቴ ይቋቋማል፡፡
1.2. የከንቲባ ኮሚቴ አባላት በከንቲባው አቅራቢነት በከተማው ም/ቤት
ይሰየማሉ፡፡
1.3. በማንኛውም ደረጃ የተቋቋመ የከንቲባ ኮሚቴ አባላት ከአስፈፃሚ አካላት
የተውጣጡ ኃላፊዎች ይሆናል፡፡
1.4. ከከንቲባው በስተቀር የከንቲባ ኮሚቴ አባላት ከከተማ ምክር ቤት አባላት
ወይም ከም/ቤት አባላት ውጭ ሊሆኑ ይችላሉ፡፡
1.5. የከንቲባ ኮሚቴ አባላት በከተማ አስተዳደር ስልጣናቸው በጋራ
ለሚያሳልፉት ውሣኔና ለሚፈጽሙት ተግባር የጋራ ኃላፊነት አለባቸው፡፡
8
2. ስለ ከንቲባ ኮሚቴ አባላት
1. የከንቲባ ኮሚቴ አባላት የሚከተሉት ይሆናሉ
2.1. የከተማ ከንቲባ እና ምክትል ከንቲባ
2.2. በዚህ ደንብ አንቀጽ ፲፯ መሠረት ለከንቲባ ተጠሪ ሆነው የተቋቋሙትን
አስፈፃሚ አካላት የሚመሩ ኃላፊዎች
ሀ/ በመሪ ከተማ አስተዳደር 7 የመምሪያ ኃላፊዎች
ለ/ በከፍተኛና መካከለኛ ከተማ አስተዳደር 6 የጽ/ቤት ኃላፊዎች
ሐ/ በታዳጊ ከተማ አስተዳደር 5 የጽ/ቤት ኃላፊዎች
2.3. የማዘጋጃ ቤት ሥራ አስኪያጅ - ድምጽ የማይሰጥ - አባል

ምዕራፍ ሦስት
የከተማ አስተዳደር አስፈፃሚ አካላት ስልጣንና ተግባር
07. አስፈፃሚ አካላት ስለመቋቋም
በአዋጁ አንቀጽ ፳፬ ንዑስ አንቀጽ 3 መሠረት በእያንዳንዱ የክልሉ የከተማ አስተዳደር
ከተሞች ለከንቲባው ተጠሪ የሆኑ የሚከተሉት አስፈፃሚ አካላት ተቋቁመዋል፡፡
1. የመሪ ከተማ አስተዳደር አስፈፃሚ አካላት
1.1. የከንቲባው ጽ/ቤት
1.2. የፋይናንስ ኢኮኖሚ ልማት መምሪያ
1.3. የትምህርትና አቅም ግንባታ መምሪያ
1.4. ጤናና የአካባብ ንጽህና መምሪያ
1.5. የንግድና ኢንዱስትሪ መምሪያ
1.6. ወጣቶች፣ ስፖርትና አካባቢ ልማት መምሪያ
1.7. ሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ መምሪያ
1.8. የፍትህ፣ ፀጥታና ደንብ ማስከበር መምሪያ
2. የከፍተኛና መካከለኛ ከተማ አስተዳደር፣ አስፈፃሚ አካላት፣
2.1. የከንቲባው ጽ/ቤት
2.2. የፋይናንስ ኢኮኖሚ ልማት ጽ/በት
2.3. ማህበራዊ አገልግሎትና አቅም ግንባታ ጽ/ቤት
2.4. የንግድና ኢንዲስትሪ ጽ/ቤት

9
2.5. ወጣቶች ስፖርትና አካባቢ ልማት ጽ/ቤት
2.6. ሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ጽ/ቤት
2.7. የፍትህ፣ ፀጥታና፣ ደንብ ማስከበር ዋና ጽ/ቤት
3. የታዳጊ ከተማ አስተዳደር አስፈፃሚ አካላት፣
3.1. የከንቲባው ጽ/ቤት
3.2. የፋይናንስ ኢኮኖሚ ልማት ጽ/ቤት
3.3. ማህበራዊ አገልግሎትና አቅም ግንባታ ጽ/ቤት
3.4. የሴቶች፣ ወጣቶች እና አከባቢ ልማት ጽ/ቤት
3.5. የንግድና ኢንዲስትሪ ልማት ጽ/ቤት
3.6. የፍትህ፣ ፀጥታና፣ ደንብ ማስከበር ጽ/ቤት

08. የወል ስልጣንና ተግባር


የከተማ አስተዳደር አስፈፃሚ አካላት የሚከተሉት የወል ስልጣን ይኖራቸዋል፣
1. የከተማው የወደፊት ራይና አቅጣጫን የሚያመላክት ስትራቴጂያዊ እቅድ
ለተፈፃሚነቱ አርአያ መሆን፣
2. ህገወጥነትን በመከላከል የከተማውን ሰላምና ፀጥታ ማረጋገጥ፣
3. ህብረተሰቡ የሚፈልገው አገልግሎት ቀልጣፋ በሆነ መንገድ መቅረቡን ማረጋገጥ፣
4. በመልካም አስተዳደርና ልማት የመንግሥትን፣ የህብረተሰቡንና የባለሀብቱን አቅም
አሟጦ መጠቀምና ለዚህም ቅንጅቶችን ማስተባበርና ማጠናከር፣
5. በከተማው የመሠረተ ልማትና የአገልግሎት ግንባታዎች እንደጠቀሜታቸው በቅደም
ተከተል እንዲከናወኑ ማድረግ፣ የኢኮኖሚና ማህበራዊ አገልግሎቶችን ማስፋፋት፣
6. ለኢንቨስትመንት መስፋፋት በተለይ የጥቃቅንና አነስተኛ ንግድ ኢንዱስትሪ
እንዲስፋፋ ሁሉ አቀፍ ድጋፍ ማድረግ፣
7. ዘርፈ ብዙ ድጋፍ በማፈላለግ የከተማውን አስተዳደር፣ የህብረተሰቡንና የግሉን ዘርፍ
አቅም መገንባት፣
8. በፌዴራልና በክልል መንግሥት የወጡ ፖሊሲዎችና ሕጎች በሥራ ላይ መዋላቸውን
ማረጋገጥ፣
9. የሲቪል ሰርቪስ ማሻሻያ ፕሮግራምን ማስፈፀምና የአቅም ግንባታ ሥራዎችን
ማከናወን፣
10. አግባብ ካላቸው አካላት የከተማው ነዋሪዎች ጋር በአጋርነት ለመስራት የሚያስችሉ
ስልቶች በመቀየስ ተግባራዊ ማድረግ፣

10
11. ስለሥራው አፈፃፀም በየወቅቱ ተጠሪ ለሆነበት አካል በየወቅቱ ሪፖርት ማቅረብ፣

09. የፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት መምሪያ ሥልጣንና ተግባራት


1. የተቀናጀ የማህበራዊ ኢኮኖሚያዊ ልማት ለማምጣት የሚያስችል የከተሞች ፕላን
ዝግጅትና ትግበራን ያስተባብራል፣ ይመራል፡፡
2. የከተማ ልማት ለመምራት ለማስፈፀምና ለመደገፈ የሚረዱ የፖሊሲ ሃሳቦችን
ማመንጨት፣ የበጀት ድልድል አዘጋጅቶ ያቀርባል፣ ሲፈቀድም ተግባራዊ ያደርጋል፣
3. በክልል መስተዳድር ምክር ቤት ሲፈቀድ ከሀገር ውስጥና ከውጪ ምንጮች ብድሮችን
ከተማውን ወክሎ ይበድራል፡፡
4. የከተማውን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ መረጃ የማደራጀት፣ ማቀነባበር፣ ለአገልግሎት
ሲጠየቅም ለሚመለከተው አካል ያስተላልፋል፡፡
5. ማናቸውም የከተማውን የፋይናንስ ንብረት ኢንስፔክሽን ሥራ ያከናውናል፡፡

፳ የትምህርትና አቅም ግንባታ መመሪያ ሥልጣንና ተግባራት


1. በከተማው የአቅም ግንባታ ፕሮግራሞች ስራዎችን በበላይነት ያስተባብራል፣
አፈፃፀሙንም ይከታተላል፡፡
2. የሲቪል ሰርቪስ ሪፎርም ፕሮግራም በተሟላ ሁኔታ ተግባራዊ መሆኑን ይከታተላል፡
3. የከተማውን የሰለጠነ የሰው ሀይል አስተዳደር፣ አደረጃጀትና አሠራር ተግባራዊ ማድረግ
የሚያስችል ስልት ይቀይሳል፣ ሲፈቀድም ተግባራዊ ያደርጋል፣
4. የመንግሥት የአቅም ግንባታ ፖሊሲና ፕሮጀክቶች አፈፃፀማቸውን የከታተላል፣
ያስተባብራል፣
5. በከተማው የአንደኛና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርትን እንዲስፋፋ ያደርጋል፣
6. የቴክኒክና የሙያ ተቋማት እንዲስፋፉና እንዲጠናሩ ያደርጋል፣
7. የከተማውን አስፈፃሚ አካላት ድርጅቶችን፣ ጽ/ቤቶችንና ተቋማትን፣ ኮሚሽንና ቦርዶችን
እንዲሁም ሌሎች ተመሳሳይ አካላት አቅምን የሚገነባበትን ሁኔታ ያመቻቻል፣

፳፩ የንግድና እንዱስትሪ መምሪያ ሥልጣንና ተግባራት


1. በከተማ ውስጥ ሰፊ የሥራ ዕድል እንዲፈጠር ጥቃቅንና አነስተኛ የንግድ ተቋማት
እንዲስፋፉ ያደርጋል፣ ድጋፎችንም ያስተባብራል፡፡
2. ንግድ ኢንዲስትሪና እደ ጥበብ በከተማ ውስጥ እንዲስፋፋ ያደርጋል፣ የሀገር ውስጥ
ባለሀብቶች በከተማ ውስጥ በንግድ ኢንዱስትሪ ስራ ላይ በሰፊው እንዲሰማሩ
ያበረታታል፣ የቴክኒክ የምክር አገልግሎቶችን ይሰጣል፣ የንግድ ቁጥጥር ሥራ
ይሰራል፣
11
3. አግባብ ካላቸው አካላት ጋር በመተባበር የከተማውን የቱሪስት መስህቦች
ይመዘግባል፣ እንዲደራጁ እንዲስፋፉና እንዲጠበቁ ሁኔታዎችን ያመቻቻል፣
የቱሪዝም እንቅስቃሴዎች እንዲስፋፉ ድጋፍ ይሰጣል፣
4. በከተማ ውስጥ የግብርና ምርት በጥራት የሚመረትበትና ለገበያ የሚቀርብበትን
እንዲሁም የግብርና ልማትን የሚያሻሽልበት፣ ስልት ይቀይሳል፣ ሲፀድቅም
ተግባራዊ መሆኑን ያረጋግጣል፣
5. የከተማውን የኢንቨስትመንት እንቅስቃሴዎችን ያስተባብራል፣ ያስፋፋል፣
ያበረታታል፣ ምክርና የቴክኒክ ድጋፍ ይሰጣል፣
6. የከተማ ትራንስፖርት እንዲስፋፋ፣ እንዲጠናከር፣ እና ህብረተሰቡም ዘመናዊ
የትራንስፖርት አገልግሎት እንዲያገኝ ስልት ይቀይሣል፣

፳፪ ሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ መምሪያ ሥልጣንና ተግባራት


1. የማህበራዊ ፖሊሲ ተግባራዊነት የሚረዱ እቅድ ያወጣል፣
2. በከተማ ውስጥ ማህበራዊ ችግሮችና ጠንቆች ሊወገዱ የሚችሉባቸውን ህብረተሰቡን
የሚያሳትፉ ስልቶች ይቀይሣል፣ ሲፀድቁም ተግባራዊ መሆናቸውን ያረጋግጣል፣
3. ለሲቪልና ማህበራዊ ጉዳዮች መንግሥታዊ ባልሆኑ ድርጅቶች በኩል ማህበራዊ
ደህንነትን በሚመለከት ለሚካሄዱ ሥራዎች ድጋፍ ይሰጣል፣
4. የሴቶችን ኢኮኖሚያዊ ማህበራዊ ፖለቲካዊ ሁኔታዎችን ለማሻሻል፣ ለፆታ እኩልነት
እንቅፋት የሚሆኑ በሥራ ላይ ያሉ ህጎች፣ መመሪያዎች፣ ደንቦችና አሠራሮችን፣
እንዲጠኑ በማድረግ እንዲሻሻሉ ሃሣብ ያቀርባል፣ በአዲስ መልክ ወይም ተሻሽለው
የሚወጡ ማናቸውም ዓይነት ህጎች፣ መመሪያዎችና ደንቦች የሴቶች ሁለንተናዊ መብት
የሚያስጠብቁ መሆናቸውን ያረጋግጣል፣
5. ለሲቪልና ማህበራዊ ጉዳዮች መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች የሚያቀርቧቸውን
ፕሮጀክቶች አግባብነት በማረጋገጥ ስምምነቶችን ይመሰርታል፣ አፈፃፀማቸውን
ይከታተላል፣
6. በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ለሚገኙ ህፃናትና ለአረጋውያን፣ ለአካል ጉዳተኞች፣
ማህበረሰብ አቀፍ የተሀድሶ አገልግሎት ስርዓት የሚስፋፋበት ሁኔታ ያጠናል፣ ተስማሚ
ስልቶችን ይቀይሳል፣ ሲፀድቅም ተግባራዊነታቸውን ያረጋግጣል፣

፳፫ ወጣቶች ስፖርትና አከባቢ ልማት መምሪያ ሥልጣንና ተግባራት

12
1. ህብረተሰቡ እራሱን በልዩ ልዩ ማህበራት እያደራጀ በልማት ሥራው ተሳታፊ
የሚሆንበትን ሁኔታ ያመቻቻል፣ የህብረተሰቡ ተሳትፎ በስርዓት የሚመራበት ስልት
ይቀይሣል፣ ማህበራት የእርስ በእርስ ተሞክሮ ልውውጥና መደጋገፍ እንዲያደርጉ
በቅንጀት እንዲንቀሳቀሱ ተገቢውን ጥረት ያደርጋል፣ ያበረታታል፣
2. የከተማው ወጣቶች በኢኮኖሚ፣ በማህበራዊና ፖለቲካው እንቅስቃሴ ውስጥ የነቃ
ተሳትፎ እንዲያደርጉ ያበረታታል፡፡
3. ወጣቱ ከአጉልና ጎጂ ድርጊቶች እንዲቆጠብና ጥሩ ዜጋ እንዲሆን ከተለያዩ አካላት ጋር
ይንቀሳቀሳል፡፡
4. በከተማው ወጣት ተኮር አካባቢ ልማት እንዲስፋፋ ጥረቶችን ያስተባብራል፣
ፕሮጀክቶችን ይቀርፃል፣ ሲፀድቅም ተግባራዊ ያደርጋል፡፡
5. የክልሉ አጠቃላይ ጨዋታዎች /ውድድሮች/ በከተማው ክልል በሚዘጋጅበት ወቅት
ከክልሉ ስፖርት ኮሚሽን ጋር በመተባበር ያዘጋጃል፣ በተከማውም የስፖርት ምክር ቤት
እንዲቋቋም ያደርጋል፣

፳፬ የጤናና አካባቢ ንጽሕና መመሪያ ሥልጣንና ተግባራት


1. አካባቢ እንዳይበክል የመከላከያ ስልት ይቀይሳል፣ የሚመለከታቸውን አካላት በአካባቢ
ንጽሕና ጉዳይ ያስተባብራል፣

2. ስለ አካባቢ ንጽሕና በመገናኛ ብዙሃን ትምህርት እንዲሰጥ ያደርጋል፣


3. የኢንዱስትሪ ዝቃጭ ተረፈ ምርትና ቆሻሻ በህግ መሠረት መወገዱን ይከታተላል፣
ይቆጣጠራል፣

4. የአካባቢ ንጽሕና ህጎች መሠረት በማድረግ የማምረቻና የአልግሎት መስጫ ተቋማት


የብቃት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት ይሰጣል፣

5. የክልሉን የጤና ፖሊሲና ደረጃ በማገናዘብ የከተማውን የጤና አገልግሎት ደረጃ


ተግባራዊነቱን ያረጋግጣል፣ በጤና ጉዳዮች ላይ የግንዛቤ ማስጨበጫ ትምህርት
ለከተማው ነዋሪ አመቺ በሆነ ዘዴ ይሰጣል፣

6. በከተማው አስተዳደር ባለቤትነት ስር ያሉ የጤና ተቋማት በህጉ መሠረት


ያስተዳድራል፣

7. መከላከልን መሠረት ያደረገ የጤና ጥበቃ እንቅስቃሴ ማድረግ እና ኤች.አይ.ቪ


ኤድስን በተቀናጀ መልኩ ለመከላከል ጥረት ያደርጋል፣

13
፳፭ የፍትህ፣ ፀጥታና ደንብ ማስከበር ዋና ጽ/ቤት ሥልጣንና ተግባራት
1. ቀልጣፋ ፍትህና የነዋሪዎች ሰላምና ደህንነት በከተማች እንዲሰፍን ያደርጋል፣
2. በከተማው አስተዳደር ስር የሚወድቁ የፍትህና ፀጥታ ጉዳዮችን ያስከብራል፣
3. በከተማው የፍትህ ስርዓት ማሻሻያ ፕሮግራም ተግባራዊ ያደርጋል፣
4. የከተማውን ነዋሪ ንቃተ ህግ ለማዳበር ከሚመለከታቸው የክልሉ አካላት ጋር
በመቀናጀት የህግ ትምህርት ይሰጣል፣
5. በህግ ጉዳዮች የከተማው አስተዳዳር ዋና አማካሪ ሆኖ ይሰራል፣ በሌሎች አካልም
ሲጠየቅ የህግ ምክር ይሰጣል፣
6. በህገ ወጥነት ላይ በህጉ መሠረት ተገቢውን እርምጃ ይወስዳል፣
7. የአስተዳደሩንና የነዋሪዎችን መብትና ጥቅም ለማስከበር አስፈላጊ ሆነው ሲያገኛቸው
በፍርድ ቤትና በማንኛውም ዳኝነት ስም ክስ ይመሰርታል፣ ክስ እንዲመሰረት ያደርጋል፣
ወይም ጠበቃ በመግዛት ይከራከራል፣
8. ህጎችና ደንቦች በሥራ ላይ መዋላቸውን ያረጋግጣል፣
9. የውል ማስረጃ ምዝገባዎችን ያከናውናል፣
10.የጽዳት መጓደል፣ ህገ ወጥ ንግድ ፣ ህገ ወጥ ግንባታና ሌሎች ደንብ መተላለፉን
ይቆጣጠራል፣ በህጉ መሠረት ተገብውን እርምጃ ይወስዳል፣ ወይም እንዲወሰድባቸው
ያደርጋል፣

፳፮ የከፍተኛና መካከለኛ ከተማ አስተዳደሮች የሚቋቋሙ አካላት ስልጣንና


ተግባር
1. የፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ጽ/ቤት፣ የንግድና ኢንዲስትሪ ጽ/ቤት፣ ሴቶችና ማህበራዊ
ጉዳይ ጽ/ቤት፣ ወጣቶች ስፖርትና አከባቢ ልማት ጽ/ቤት፣ የፍትህ፣ ፀጥታና ደንብ
ማስከበሪ ጽ/ቤት ከላይ በአንቀጽ ፲፱፣፳፩፣ ፳፪፣ ፳፫ እና ፳፭ የተጠቀሱት ስልጣንና
ተግባር በቅደም ተከተል ይኖራቸዋል፡፡
2. የማህበራዊ አገልግሎትና አቅም ግንባታ ጽ/ቤት ከላይ በአንቀጽ ፳ እና ፳፬ የተጠቀሱት
ስልጣንና ተግባር ይኖረዋል፡፡

፳፯ በታዳጊ የከተማ አስተዳደሮች የሚቋቋሙ አካላት ስልጣንና ተግባር


ከላይ በአንቀጽ ፳፮ የተጠቀሰው እንደተጠበቀ ሆኖ የሴቶች፣ ወጣቶች፣ ስፖርት እና
አካባቢ ልማት ጽ/ቤት በአንቀጽ ፳፪ እና ፳፫ የተጠቀሱት ስልጣንና ተግባራት
ይኖሩታል፡፡

14
፳፰ የገቢዎችና ታክስ አስተዳደር ስለመቋቋም
1. ተጠሪነቱ ለከተማው ከንቲባ የሆነ የገቢዎችና ታክስ አስተዳደር ጽ/ቤት በከተማ
አስተዳደር ከተሞች ተቋቁሟል፡፡
2. የጽ/ቤት ስልጣንና ተግባር የሚከተለው ይሆናል፡፡
2.1. የገቢ አወሳሰንና የሂሣብ አያያዝ በተሳለጠና ብቃት ባለው መልኩ ለማከናወን
የሚያስችሉ የአሠራር ዘዴዎች ይቀይሳል፡፡
2.2. አዲስ የገቢ ምንጮች እያጠና በሥራ ላይ ያውላል፣ ይከታተላል፡፡
2.3. በክልሉ ምክር ቤት በፀደቀው የፋይናንስ ደንብ መሠረት የከተማውን ገቢ
ማስተዳደር፣ ግብር፣ ቀረጥ፣ የአገልግሎት ክፍያና ሌሎች ገቢዎች
ይሰበስባል፣ እንዲሰበሰቡ ያደርጋል፡፡
2.4. ግብር ከፋዮችን ለይቶ ለማወቅና ለመመዝገብ የሚያስችሉ አሠራሮችን
ተግባራዊ ያደርጋል፡፡
2.5. በከተማው የሚሰበሰቡ ገቢዎችን ይወስናል፣ የግብር ውሣኔዎችን ለግብር
ከፋዮች በጽሑፍ ያስታውቃል፣ ይሰበስባል፡፡
2.6. በክፍለ ከተማ የተሰበሰቡ ገቢዎች በወቅቱ ፈሰስ መደረጋቸውን ያረጋግጣል፡፡
2.7. ግብር ከፋዮች ሕጎችን አውቀው መብትና ግዴታቸውን እንዲወጡ
ይቀሰቅሳል፣ ግዴታቸውን መወጣታቸውን ያረጋግጣል፡፡

፳፱ ስለውሃ አገልግሎት ድርጅት ስለመቋቋም


1. በአዋጅ ቁጥር 40/1994 በተደነገገው መሠረት የከተማ አስተዳደር በተቋቋመባቸው
ከተሞች የውሃ አገልግሎት ድርጅት ተቋቁሞአል፡፡
2. በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ 1 የተጠቀሰውን አዋጅ ለማሻሻል በወጣው አዋጀ ቁጥር
71/96 አንቀጽ 2 ንዑስ አንቀጽ 4 በተደነገገው መሠረት የውሃ አገልግሎት ድርጅት
ሥራ አመራር ቦርድ አባላት የሚከተሉት ናቸው፡፡
1. የከተማው ከንቲባ ሰብሣቢ
2. የከተማው ማዘጋጃ ቤት ሥራ አስኪያጅ አባል
3. የንግድና ኢንዲስትሪ መምሪያ/ጽ/ቤት አባል
4. የጤናና አካባቢ ንጽህና መምሪያ ጽ/ቤት አባል
5. የፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት መም/ጽ/ቤት አባል
6. ከተጠቃሚው ህብረተሰብ የሚወከል አባል
15
7. ከነጋዴው ህብረተሰብ የሚወከል አባል
8. ከድርጅቱ የሚወከሉ ሁለት ሠራተኞች አባል
9. የድርጅቱ ሥራ አስኪያጅ አስረጂ
3. የድርጅቱ ተጠሪነት ለቦርዱ ሆኖ በአዋጅ ቁጥር 40/1994 አንቀጽ 11 የተመለከተው
ሥልጣንና ኃላፊነት ይኖረዋል፡፡

፴ ስለከተማ ነክ ፍ/ቤቶች መቋቋም


በአዋጁ ከአንቀጽ ፳፰ እስከ አንቀጽ ፴፩ በዝርዝር የተቀመጠው ተፈፃሚነት
እንደተጠበቀ ሆኖ፡-
1. የከተማ አስተዳደር በተቋቋመባቸው 22 ከተሞች በአዋጁ አንቀጽ ፳፱ መሠረት
የከተማ ፍ/ቤቶች ይቋቋማሉ፡፡
2. በሌሎች የማዘጋጃ ቤት ከተሞች በአቅራቢያቸው ከሚገኙ የከተማ አስተዳደር
ከተሞች ጋር በሚደረግ ስምምነት የከተማ ነክ ጉዳዮችን በጋራ ፍ/ቤቶች
መጠቀም ይችላሉ፡፡ ዝርዝር አፈፃፀሙ የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት በሚያወጣው
መመሪያ ይወሰናል፡፡
3. ከላይ በንዑስ አንቀጽ 2 የተጠቀሰው እንደተጠበቀ ሆኖ ማንኛውም የማዘጋጃ ቤት
ጉዳዮችን ባለው የክርክር ጉዳዮች ስፋትና ወጪን በመሸፈን አቅም መነሻነት
በከተማው የከተማ ነክ ጉዳዮች ፍ/ቤትን ለማቋቋም ጥያቄ አቅርቦ ይኸው
ሲፈቀድ ሊያቋቁም ይችላል፡፡

ክፍል አራት
ስለ ማዘጋጃ ቤት አገልግሎቶች እና የማዘጋጃ ቤት ከተሞች
ምዕራፍ አንድ
የከተማ አስተዳደር በተቋቋመባቸው ከተሞች የማዘጋጃ ቤት አገልግሎቶች
፴፩ የማዘጋጃ ቤት አገልግሎቶች አስፈፃሚ አካላት መቋቋም
የሚከተሉት ለማዘጋጃ ቤት አገልግሎቶች ሥራ አስኪያጅ ተጠሪ የሆኑ አስፈፃሚ አካላት
ተቋቁመዋል፣
1. በመሪ ከተማ አስተዳደር
1.1. የመሠረተ ልማት እና ምህንድስና ኤጀንሲ

16
1.2. የመሬት ዝግጅትና ልማት ኤጀንሲ
1.3. የመሬት አስተዳደር እና አቅርቦት ኤጀንሲ
1.4. የቤቶች ኤጀንሲ
1.5. የገቢዎች ኤጄንሲ
2. በከፍተኛ ደረጃ የከተማ አስተዳደር
2.1. የመሬት ልማትና ምህንድስና ኤጀንሲ
2.2. የመሬት አቅርቦትና አስተዳደር ኤጀንሲ
2.3. የገቢዎች ኤጀንሲ
2.4. የቤቶች ኤጀንሲ
3. በመካከለኛ እና ታዳጊ ከተማ አስተዳደር
3.1. የመሬት ዝግጅት፣ አቅርቦትና ምህንድስና ኤጀንሲ

፴፪ የማዘጋጃ ቤት አገልግሎቶች አስፈፃሚ አካላት ስልጣንና ተግባር፣


1. የመሠረተ ልማት እና ምህንድስና ኤጀንሲ ስልጣንና ተግባር
1.1. በማዘጋጃ ቤቱ ለሚካሄዱ ግንባታ ነክ ፕሮጀክቶች ጥናትና የኮንትራት ውል
እንዲዘጋጅ ያደርጋል ለፕሮጀክቱ አጠቃላይ የአፈፃፀም ስልቶችና የድርጊት
መርሃ ግብር ተነድፎ የጊዜ ሰሌዳዎችን ጠብቀው እንዲፈፀሙ ይከታተላል፡፡
1.2. የከተማውን መሠረታዊ አውታሮች የሕዝብ መፀዳጃ፣ የቆሻሻ መሰብሰቢያ፣
የመንገድ ንጣፎችን፣ ሕንፃዎችንና አደባባዮችን፣ የመንገድ መተላለፊያዎችን፣
መናኸሪያዎችን የከተማ ውበትን የጠበቀ ዲዛይን እንዲወጣ ያደርጋል፡
በዲዛይኑ መሠረት የከተማ ግንባታዎችን ይመራል፣ ይከታተላል፡፡
1.3. ከማ/ቤቱ ሕንፃዎች ወይም የከተማ የመሠረተ አውታሮች ግንባታ እድሳት
ይመራል ይከታተላል፡፡
1.4. በከተማው ክልል የሚተከሉና በከተማው ክልል ባሉ ሕንፃዎች የሚለጠፉ
የማስታወቂያ ሰሌዳዎች አግባብነት ይመረምራል፣ ይቆጣጠራል፣ ተገቢውን
ክፍያ ያስፈፅማል፡፡
1.5. ማዘጋጃ ቤቱ ከኮንትራክተሮች ጋር ሊያደርግ ያሰበውን ውል ይመረምራል፣
የቴክኒክና የዋጋ ዝርዝሮች ያወጣል፡፡ በሚደረጉ ድርድሮችና ውዝግቦች
በባለቤትነት ይሳተፋል ለማዘጋጃ ቤቱ ምክር ይሰጣል፡፡

17
1.6. የከተማው የመሠረተ ልማት ሥራዎች የተቀናጀና ደጃውን የጠበቀ የመሠረተ
ልማት ኔት ወርክ ዲዛይን ጥናት ያካሂዳል፣ በዚህ ዲዛይን መሠረት
የመሠረተ ልማት ገንቢዎች ሥራቸውን አቀናጅተው እንዲሠሩ ያደርጋል፡፡
1.7. የመሠረተ ልማት ግንባታ ሥራዎች የወጣውን ዲዛይንና ስታንደርድ
ጠብቀው መፈፀማቸውን ይከታተላል፡፡
1.8. ማዘጋጃ ቤቱ ለመስራት የሚያቅዳቸውን የመኖሪያ ቤቶችና ሕንፃዎች
በከተማው ማስተር ፕላን የተመለከተው የሕንፃ ዓይነትና ደረጃ ተጠብቆ
ግንባታዎች በተዘጋጀው ዲዛይን ሥራ ዝርዝር መሠረት መሠራታቸውን
ይከታተላል፣ ይቆጣጠራል፡፡
1.9. ማዘጋጃ ቤቱ በኮንትራክተር ለሚያሠራቸው ግንባታዎች አማራጭ የጨረታ
ሠነድ በማዘጋጀት ጨረታው ተገምግሞ ሲፀድቅ ውል እንዲዘጋጅ ያደርጋል
በውሉም መሠረት አፈፃፀሙን እየተከታተለ የግንባታው ሥራ እስከሚጠናቀቅ
ድረስ በውልና በሥራ ዝርዝሩ መሠረት ዲዛይኑን ጠብቄ ለመሠራቱ
ይከታተላል ያረጋግጣል፣ ይቆጣጠራል፡፡
1.10. ከሚመለከታቸው ጋር በመቀናጀት ለከተማው የመንገድ፣ የውሃና ፍሳሽ፣
የስልክና የኤሌክትሪክ እንዲሁም የጎርፍ መስመሮች ውህደት ካርታ
እንዲዘጋጅ ያደርጋል፣ በዚህም ካርታ መሠረት አዳዲስ ሥራዎች
እንዲከናወኑ ያደርጋል፡፡
1.11. የተፈቀዱ የሥራ ፕሮግራሞች በተግባር ለመተርጎም የሠራተኛ፣ የፋይናንስ፣
የማሣሪያዎችና ዕቃ አቅርቦችን ወጪዎች በተመለከተ የድርጊት መርሃ ግብር
እንዲዘጋጅና እንዲቀርብ በማድረግ ተግባራዊነቱን ይከታተላል፡፡
1.12. በከተማው ውስጥ ለተለያዩ ግንባታዎች ፈቃድ ይሰጣል፣ በዚሁ ፈቃድ
መሠረት ብቻ ግንባታ መከናወኑን፣ የፍርድ ቤት ትዕዛዝ፣ የቀበሌ ቤት
እድሳት፣ የስምና ንብረት ዝውውር እና የመሳሰሉትን የምህንድስና የግምት
ስራዎች ቁጥጥር ያደርጋል፣ በከተማው ውስጥ የሚገነቡ መሠረተ ልማቶች
መረጃ ተመዝግቦ እንዲያዝ ያደርጋል በየጊዜውም ወቅታዊ እንዲሆን
ያደርጋል፡፡
2. የመሬት ልማትና ዝግጅት ኤጀንሲ ስልጣንና ተግባት
2.1. ከተማው ዝርዝር ፕላን በመሪ ፕላኑ መሰረት እንዲዘጋጅ፣ የከተማ ፕላን
ህግጋት እንዲከበሩ፣ የከተማ ፕላን የመረጃ ጥናት ያደርጋል፣ ይከታተላል፣

18
2.2. ከተማ ቦታ በደረጃና በንዑስ ደረጃ በመመደብ የኢንቨስትመንት ፖቴንሻል
ጥናቶችን ያደርጋል፣ የቦታዎቹን ጋይድ ማፕ ያዘጋጃል፣ የቦታዎቹ ምደባ
መሠረት በቦታው ላይ መከናወን ያለበት የኢንቨስትመንት ፕሮጀክት በቅደም
ተከተል በመዘርዘር ለመሬት አስተዳደርና ቅርቦት መምሪያ ያስረክባል፣
2.3. የከተማውን ድርጊት ፕላንና ዝርዝር ፕላን ሥራዎችን በመሪ ፕላኑ
መሰረት ያዘጋጃል፣ ይመራል፣ ይቆጣጠራል፣ አፈጻፀሙን ይከታተላል፣
2.4. የከተማውን የክለሳና የዞኒንግ ጥናት ስራዎች ያጠናል፣ ሲፈቀድም ተግባራዊ
ያደርጋል፣
2.5. የከተማውን እድገት ተከትሎ ለሚመጡ የኢንቨስትመንት ጥያቄዎች የቦታ
ክለሳ ጥናት ያደርጋል፣ ያዘጋጃል፣ ለቦታ አስተዳደር መምሪያ ያስረክባል፡፡
2.6. የከተማው ውበት የተጠበቀ እንዲሆን የአረንጓዴ ስፍራዎች እንዲለሙ
ጥናቶችን እያደረገ ከሚመለከታቸው ጋር በመወያየት ገቢራዊ ያደርጋል፣
2.7. በከተማው መሬት የመሠረተ ልማት አውታሮች ማለትም የስልክ፣ መብራት
፣የውሃ፣ የመንገድ፣ ወዘተ.. ፊዚካል ፕላኖች ለከተማው እድገት ቀጣይነት
በሚኖረው መልኩ እንዲዘረጉ ለሚመለከታቸው ሁኔታዎችን ያመቻቻል፣
2.8. የከተማው ስትራቴጂክ ፕላን መሰረት የከተማው ድንበር እንዲካለል
ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በሚደረገው ውይይት ይሳተፋል፣ ሲወሰንም
ያስፈጽማል፣
2.9. በከተማው ውስጥ መንግስት ቦታዎችን ለልማት በመፈለጉ ሳቢያ
ለሚፈናቀሉ ባለይዞታዎች በካሣ አዋጅ፣ ደንብና መመሪያ መሠረት
ክፍያዎች ያጠናል፤ የውሳኔ ሃሳብ ለስራ አስኪያጁ ያቀርባል
2.10. በከተማው ውስጥ ለተለያዩ አገልግሎቶች የሚዘጋጁ ቦታዎች የፕላን
ምደባዎች መሠረት አድርገው እንዲዘጋጁ ያደርጋል፣ ይሸነሽናል፣ ተዘጋጅቶ
ለሚመለከተው አካል ያስረክባል፣
3. የመሬት አስተዳደርና አቅርቦት ኤጀንሲ ስልጣንና ተግባር
3.1. የከተማ ቦታ ለተለያዩ የልማት ስራዎች እንዲውሉ የቦታ እደላ መሰረታዊ
የሆነ ጥናት በማድረግ ያከናውናል፣
3.2. ለጥቃቅንና አነስተኛ ንግድ ተቋማት እንዲሰጥ የተዘጋጁ ቦታዎች በተቀላጠፈ
መልኩ እንዲሰጡ የአሠራር ስልቶች ይቀይሳል፣

19
3.3. ሕጋዊ ለሆኑ ባለይዞታዎች የይዞታ ማረጋገጫ ተዘጋጅቶ ስለሚሰጥበት
ሁኔታ ያመቻቻል፣
3.4. የከተማው ቤትና የቦታ ግብር አፈፃፀም ከሌሎች ከሚመለከታቸው
የማዘጋጃ ቤቱ አገልግሎት ጋር በመሆን ማሻሻያ ሃሳብ ለበላይ ኃላፊው
ያቀርባል፣
3.5. የተለያዩ የቤትና የንብረት ይዞታ የማስተላለፍ ውልና የስም ዝውውር
ሥራዎች በህጋዊ መንገድ ተግባራዊ እንዲሆኑ ያደርጋል፣ ያረጋግጣል፣
3.6. በባንክና በግለሰቦች መካል በሚደረገው ብድር ውል ስምምነት ወቅት
ለዋስትና የቀረቡ ቤትና ድርጅት ይዞታ ከማኛውም ዕዳ ነጻ ስለመሆናቸው
ማረጋገጫ ይሰጣል፣
3.7. በሊዝ ደንብ መሠረት ስለሚሰጡት ቦታዎች ያመቻቻል፣ መረጃ ይይዛል፣
ለባለሀብቶች መረጃ ይሰጣል፣
3.8. በሊዝ በተለያዩ ስልቶች ለሚሰጡ ቦታዎች የፕሮሞሽን ሥራዎች
ለሚሠሩበት ሁኔታ ያመቻቻል፣
3.9. የተጠናከረ የካዳስተር ሥርዓት በከተማው እንዲኖር ያደርጋል፣
3.10. የሊዝ ገቢ ያጠናል፣ ስለአጠቃቀሙ የውሳኔ ሃሳብ ያቀርባል፣
3.11. ስለሊዝ ዓመታዊ እቅድ፣ የሊዝ ጨረታ ሰነድ ያዘጋጃል፣ የሊዝ ውል
ያዘጋጃል፣ የክፍያ አሰባሰብና አወሳሰን የውሳኔ ሃሳብ ያቀርባል፣
3.12. ለግንባታ ፈቃድ የሚቀርቡ ዲዛይኖች አርክቴክቸራል፣ ስትራክቸራል፣
ኤሌክትሪካል፣ ሳንቴሪ ፕላኖች ከቦታ ስፋት አንጻር መሆናቸውን
ያረጋግጣል፣ የቦታዎችን አስተዳደር በሚመለከት የማሻሻያ ጥናት
ያደርጋል፣
4. የቤቶች ኤጀንሲ ስልጣንና ተግባር
4.1. ስለ ውርስ የመንግሥት ቤቶች የወጡ ህጎች ተግባራዊነታቸውን ይከታተላል፤
4.2. በከተማው ውስጥ የመኖሪያ ቤት ችግር ለመቅረፍ ሊረዱ የሚችሉ ልዩ ልዩ
ጥናቶችን ያደርጋል፣ የግል ባለሀብቶች፣ መንግሥታዊ ያልሆኑ
ድርጅቶችንና ማህበራት በመስኩ እንዲሳተፉ አስፈላጊውን ድጋፍ ይሰጣል፣
4.3. በከተማ የመኖሪያ ቤት ፍላጎትና አቅርቦት በማጥናት የመፍትሄ አቅጣጫ
ያስቀምጣል፣ የተቀናጀ የቤቶች ልማት ፕሮግራም በማይተገበርበት ከተማ

20
የቤት ችግር ለመቅረፍ በማዘጋጃ ቤቱ ገቢ የቁጠባ ቤቶች እንዲገነቡ
ያደርጋል፣
4.4. በከተማ ውስጥ የተጎሳቆሉና ያረጁ ውርስ የመንግሥት ቤቶችን በማጥናት
ለኢንቨስትመንት እንዲውሉ ያደርጋል፣ የሚታደሱበት ሁኔታ ያመቻቻል፣
4.5. ስለ ቤት ካሣ አከፋፈል፣ ስለ አበል አከፋፈል ስለመካካሻና አዲስ ቤት
አስተዳደር የወጡ መመሪያዎችን በሥራ ላይ እንዲውሉ ያደርጋል፣
አፈፃፀማቸውን ይከታተላል፣
4.6. በክፍለ ከተማ የሚተዳደሩ የውርስ የመንግሥት ቤቶችን አስተዳደር
ይከታተላል፣ ለኢንቨስትመንት እንዲውሉ ሲወሰን ቤቱን የተከራዩ ሰዎች
አስፈላጊ ሁኔታዎችን በማመቻቸት እንዲለቁ ያደርጋል፣
4.7. የከተማ ነዋሪዎችን የቤትን ችግር ለመቅረፍ ለመኖሪያ ቤቶች የህብረት
ሥራ ማህበራት ድጋፍ ያደርጋል፣ ይመዘግባል፣ ለሚመለከተው
ያስተላፋል፣
4.8. አነስተኛ ገቢ ላላቸው ግለሰቦች የመኖሪያ ቤት ግንባታ በቀላሉ ለማስኬድ
የሚያስችላቸው የገንዘብ ምንጭ /ብድር ወይም እርዳታ/ የሚገኝበትን
መንገድ ያጠናል፣
4.9. ውርስ የመንግሥት ቤቶች /የቁጠባ ቤቶች/ የኪራይ ዋጋ በማጥናት
በአካባቢው ገበያ ዋጋ የሚሻሻልበትን ሁኔታ በማጥናት ለበላይ ኃላፊ
ያቀርባል፣ ሲፈቀድም ተግባራዊ ያደርጋል፣
4.10. ከመንግሥት ውርስ ቤቶች የሚሰበሰበውን ኪራይ በወቅቱ ገቢ መደረጉን
ይከታተላል፡፡

5. ገቢዎች ኤጀንሲ

5.1. የገቢ ፖቴንሻል ጥናትና የገቢ ትንተና ሥራዎችን ያካሂዳል፡፡


5.2. የከተማው ማዘጋጃ ቤት የገቢ መሠረቶችን ለማስፋት የሚያስችል ጥናት
ያካሄዳል አዳዲስ አርዕስቶች ለቢሮው ያስተላልፋል፣ የገቢ ማሻሻያ ጥናት
ያካሂዳል፣ የተዘጋጀ የተመን መስመሮች ላይ በጥናት እንዲሻሻል የውሳኔ
ሃሳብ ያቀርባል፡፡

21
5.3. የማዘጋጃ ቤቱ ገቢ አሰባሰብ በዘመናዊ ዕቅድ የሚመራና ከብክነት የፀዳና
ውጤት ተኮር እንዲሆን ስልት ይነድፋል በዋና ሥራ አስኪያጅ ተቀባይነት
ሲያገኝ ተግባራዊ ያደርጋል፡፡
5.4. በተለያየ የገቢ ርዕሶች የሚሰበሰቡ ገቢዎች ወቅታቸውን ጠብቀው
እንዲሰበሰቡ ያደርጋል አፈፃፀሙን በየወቅቱ እየገመገመ እንዲሻሻል
ያደርጋል፡፡
5.5. የተሰበሰቡ ገቢዎች በወቅቱ በተቀመጠው ሥርዓት ገቢ እንዲደረጉ
ያደርጋል፣
5.6. የግብርና ታሪፍ ከፋዮች ዝርዝር በመረጃ እንዲያዝ ይደረጋል፣ ወቅቱን
ጠብቀው ይካተታል፣ ውዝፍ የሚሰበሰብበትን ስልት ይነድፋል፣ ሲፈቀድም
ተግባራዊ ያደርጋል፣
5.7. ኃላፊነታቸውን በማይወጡ ማናቸውም አካላት ላይ አስፈላጊው የማስተካከያ
እርምጃ እንዲወሰድ ለሚመለከተው ክፍል ያስተላልፋል፡፡

6. በከፍተኛ ከተማ አስተዳደር ለሚቋቋሙ ኤጄንሲዎች ከላይ በዚህ አንቀጽ የተዘረዘረው


ስልጣንና ተግባር እንደተጠበቀው ሆኖ የመሬት ልማትና ምህንድስና ኤጀንሲ በንዑስ
አንቀጽ 1 እና 2 የተጠቀሱት ስልጣንና ተግባር ይኖሩታል፡፡

7. በመካከለኛና ታዳጊ ከተማ አስተዳደሮች የመሬት ዝግጅት፣ አቅርቦትና ምህንድስና ኤጀንሲ


በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ 1፣2፣እና 3 የተጠቀሱት ስልጣንና ተግባር ይኖሩታል፡፡

ምዕራፍ ሁለት

ስለማዘጋጃ ቤት ከተሞች

፴፫ ስለ እጩ ከተማ ማዘጋጃ ቤት ከተሞች

1. ለዕጩ ከተማ ማዘጋጃ ቤት ከተማነት የሚያበቁ መመዘኛዎች


1.1. ማንኛውም ማህበረሰብ በከተማነት ለመቋቋም የሚያስፈልጉ ህጋዊ ሁኔታዎችን
እሲኪያሟላ ድረስ በቢሮ ስር ሆኖ እንዲለማመድ ሊወሰንለት የሚችለው፣
ሀ. የህዝብ ብዛት ከ1500-2000 የሆነ እንደሆነ፣
ለ. አብዛኛው ነዋሪ ከግብርና ውጪ በሆነ ስራ የሚተዳደር የሆነ እንደሆነ

22
ሐ. የዳር ድንበሩ ክልል የተወሰነ ስፍራ ያለው እንደሆነ፣
መ. ቢሮ በሚያወጣው መመሪያ በግልጽ የሚደነገጉ ሌሎች መመዘኛዎችን
የሚያሟላ እንደሆነ ነው፡፡
1.2. ዕጩ ማዘጋጃነት የሚሰጠው በቢሮው ሆኖ የሚከተሉትን ተግባር ያስፈጽማል፡፡
ሀ. የእጩ ከተማውን የአስተዳደርና የአደረጃጀት ስርዓት ይወስናል፣
ለ. የእጩ ከተማ ፕላን አዘገጃጀትና የአፈፃፀም እንዲሁም የታሪፍ የግብር
አወሳሰን መመሪያዎችን ያወጣል፣
ሐ. በእጩ ከተማው የሚቀርቡ አገልግሎቶችን ዓይነትና ደረጃ ይወስናል፣
መ. የእጩ ከተማውን የልምድ ሂደት ይገመግማል፣ በውጤቱም መሠረት
ሀ. በከተማነት ለመቋቋም የሚያስችለውን መመዘኛ አሟልቶ ሲገኝ
በከተማነት እንዲቋቋም ለመስተዳደር ምክር ቤት አስተያያት ያቀርባል፣
ለ. በእጩ ከተማነት ለመቆየት የሚያስፈልጉትን መመዘኛዎች አጓድሎ ሲገን
ይሰርዛል፡፡
፴፬ . ቋሚ ያልሆነ የከንቲባ ኮሚቴ
1. አሰያየም
1.1. የከተማ አስተዳደር ባልተቋቋመባቸው ማዘጋጃ ቤት ከተሞች ከቀበሌ ምክር ቤት
አባላት፣ በጎ ፈቃድ ከንቲባና የከንቲባ ኮሚቴ ይሰየማሉ፡፡
1.2. የከንቲባ ኮሚቴ አባልነት የበጎ ፈቃድ ከንቲባው የሚያቀርባቸው ዕጩዎች
ዝርዝር መነሻነት በምክር ቤት ይወሰናል፡፡
1.3. በማዘጋጃ ቤት ከተሞች የሚቋቋመው ቋሚ ያልሆነ የከንቲባ ኮሚቴ ከንቲባውን
እና እሱ የሚመርጣቸውን 5 አባላት የያዘ ይሆናል፡፡
2. የኮሚቴ አባልት የስራ ድርሻ

እያንዳንዱ ቋሚ ያልሆነ የከንቲባ ኮሚቴ አባል ከዚህ በታች በተጠቀሰው መሰረት


የሚያስተባብረው የልማትና የመልካም አስተዳደር ሥራዎች ሲኖሩት በስሩ ቁጥራቸው
5 የሆኑ አባላት ያሉት ኮሚቴ ይሰበስባል፡፡
2.1. የፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ጉዳዮች አስተባባሪ
2.2. የማህበራዊ አገልግሎትና አቅም ግንባታ ጉዳዮች አስተባባሪ
2.3. የህብረተሰብ ተሳትፎና አካባቢ ልማት አስተባባሪ
2.4. የጥቃቅንና አነስተኛ የደንብ ማስከበር ጉዳዮች አስተባባሪ
2.5. የፍትህ ፀጥታና የደንብ ማስከበር ጉዳዮች አስተባባሪ

23
3. የቀበሌ አስተዳደር ጽ/ቤት ተቀጣሪ ሠራተኛ

የቀበሌ አስተዳደር ጽ/ቤት የተለያዩ የጽ/ቤቱን ሥራዎች የሚያከናውንና የጽህፈት ቤት


ኃላፊ የሆነ አንድ ተቀጣሪ ሠራተኞች ይኖረዋል፡፡
፴፭ ቋሚ ያልሆነ የከንቲባ ኮሚቴ ስልጣንና ተግባር

ቋሚ ያልሆነ የከንቲባ ኮሚቴ የሚከተሉት ስልጣንና ተግባራት ይኖሩታል፡፡

1. የከተማውን የማዘጋጃ ቤት አገልግሎቶች ስራ አስኪያጅ ይቀጥራል፣ ያሰናብታል፡፡


2. የከተማው ነዋሪ በኢኮኖሚና ማህበራዊ ጉዳዮች ላይ ሰፊ ንቅናቄ እንዲያደርግ ያደርጋል፡፡
3. የከተማ ቦታ በህጉ መሰረት መተዳደሩን ያረጋግጣል፡፡
4. የማዘጋጃ ቤት አገልግሎት አቅርቦቶችን መጀመር ወይም መቋረጥ ያጠናል፤ የውሳኔ
ሀሳብ ለምክር ቤት ያቀርባል፡፡
5. የስራ ሁኔታዎችን እያጠና ለምክር ቤት ለውሳኔ ውሳኔ ያቀርባል፡፡
6. በአካባቢ ልማት የነዋሪውን ተሳትፎ ለማጎልበትና አቅም አሟጦ ለመጠቀም የሚያስችሉ
ሁኔታዎችን ያስተባብራል፣ ያቀናጀል፡፡

፴፮. ቋሚ ያልሆነ የከንቲባ ኮሚቴ የአሰራር ስርዓት

1. ኮሚቴው በወር አንድ ጊዜ ስብሰባ ያደርጋል፣ ሆኖም በ2/3ኛ የኮሚቴ አባላት ሲጠየቅ
ወይም በከንቲባ አነሳሽነት አስቸኳይ ስብሰባ ሊያደርግ ይችላል፡፡
2. በማንኛውም ስብሰባ ኮሚቴው አባላት ከግማሽ በላይ በስብሰባ ከተገኙ ምልአተ ጉባኤ
ይሆናል፡፡
3. የኮሚቴው ውሳኔ የሚተላለፈው ምልአተ ጉባኤው በሚያቋቁሙት አባላት አብላጫ
ድምጽ ይሆናል፣ ድምጽ እኩል በሆነ ጊዜ ሰብሳቢው የደገፈው ሀሳብ ይጸናል፣

ክፍል አምስት
ስለ ምርጫ

፴፯ የከተማ ምክር ቤት አባላት ምርጫ

1. በአዋጁና በዚህ ደንብ መሰረት የከተማ ምክር ቤት አባላት ምርጫ በየአምስት ዓመቱ
የሚካድ ሲሆን ምርጫው የሚካሄድበት ጊዜ በክልሉ ምክር ቤት የሚሰጠውን ውሳኔ
ሃሳብ መሰረት በማድረግ በብሄራዊ የምርጫ ቦርድ ይወሰናል፡፡

24
2. የከተማው ምክር ቤት አባላት ምርጫ አፈፃፀም የከተማውን ቀበሌዎች መሰረት
በማድረግ ይሆናል፡፡
3. የከተማው ምርጫ የሚካሄድበት ቀበሌዎች ዝርዝር የከተማውን ደረጃ መሰረት
በማድረግ ቢሮው አጥንቶ በሚያቀርበው ሀሳብ ላይ በመመስረት የክልሉ መስተዳድር
ምክ/ቤት በሚያወጣው የህግ ክፍል ማስታወቂያ ይገልፃል፡፡
4. ከእያንዳንዱ ቀበሌ ለከተማ ምክ/ቤት መቀመጫዎች የሚመረጡ ተወካዮች ብዛት
የከተማውን ደረጃና የህዝብ ብዛት መሰረት በማድረግ መስተዳድር ምክር ቤት
በሚያወጣው የህግ ክፍል ማስታወቂያ ይወሰናል፡፡
5. ከመሪ ከተማ ውጪ ባሉ ከተሞች ለከተማ ምክር ቤት ምርጫ ከከተማ ዙሪያ
የሚካተቱ የገጠር ቀበሌዎች ብዛትና የተወካዮች ቁጥር የክልሉ መስተዳድር ምክር ቤት
ከተማው ከሚገኝበት ልዩ ወረዳ ወይም ዞን አስተዳደር ጋር በመመካከር ሲወስን
ተፈጻሚ ይሆናል፡፡

፴፷. የማዘጋጃ ቤት ከተሞች ምክር ቤት አመሰራረት

1. የከተማነት እውቅና ያላቸው በአንድ ቀበሌ የተደራጁ የማዘጋጃ ቤት ከተሞች ለከተማ


አስተዳደር ከተሞች የተቀመጠውን ተፈላጊ መስፈርቶች አሟልተው የከተማ አስተዳደር
ደረጃ እስኪያገኙ ድረስ የከተማ ምክር ቤት ተወካዮች ምርጫ አይኖራቸውም፡፡
2. በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ 1 ስር የተደነገገውን ድንጋጌ እንደተጠበቀ ሆኖ የማዘጋጃ
ከተማ በተቋቋመበት ስፍራ የሚገኝ የቀበሌ ም/ቤት የከተማው ምክር ቤት ሆኖ
ያገለግላል፡፡

፴፱. ስለ ምርጫ ሂደት

በአዋጁ እና በዚህ ደንብ ተለይተው ባልተገለጹ የምርጫ ጉዳዮች ላይ የኢትዮጵያ


ብሄራዊ የምርጫ ቦርድ በሚሰራባቸው ብሄራዊ የምርጫ ህግጋት የተመለከቱ አግባብ
ያላቸው ድንጋጌዎች ተፈጻሚ ይሆናል፡፡

፵. የከተማ ምክር ቤት መቀመጫ ለከተማው አካባቢ ብሄረሰብ/ቦች ስለሚቀመጥበት ስርዓት

1. በአዋጁ አንቀፅ ፲፯ ንዑስ አንቀጽ 3(1) በተደነገገው መሰረት በእያዳንዱ ከተማ ውስጥ
የሚኖረውን የአካባቢ ብሄረሰቦች ተወላጆች ቁጥር መሰረት በማድረግ ተለይቶ

25
የሚቀመጠው ተጨማሪ የከተማ ምክር ቤት መቀመጫ ብዛት መስተዳድር ምክር ቤት
በሚያወጣው በህግ ክፍል ማስታወቂያ ይገለጻል፡፡
2. ለከተማው የአካባቢ ብሄረሰብ/ቦች የሚቀመጡ ተጨማሪ የከተማ ምክር ቤት
መቀመጫዎች ብሄረሰቡን/ቦቹን ከሚወክለው ከከተማው አካባቢ ገጠር ቀበሌዎች
በሚደረገው ምርጫ በሚወከሉ አባላት የሚያዝ ይሆናል፡፡
3. ከከተማው ምክር ቤት መቀመጫዎች የተወሰነው ቁጥር እንዲመደብላቸው የተወሰነው
የአካባቢ ብሄረሰቦች ቁጥር ከአንድ በላይ የሆነ እንደሆነ ለአካባቢ ብሄረሰቦች ተለይቶ
የሚቀመጠውን መቀመጫ የሚይዙ አባላት ብዛት የብሄረሰቦቹን ተዋፅኦ በማገናዘብ
የሚወሰን ይሆናል፡፡
4. በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ 2 ና 3 ሥር የተመለከቱ ድንጋጌዎች የክልሉ መስተዳድር
ምክር ቤት ከተማው ከሚገኝበት ልዩ ወረዳ ወይም ዞን አስተዳደር ምክር ቤት ጋር
በመመካከር በሚወስነው መሰረት የሚፈፀም ይሆናል፡፡

፵፩ . ልዩ መብት

ማንኛውም የከተማ ምክር ቤት አባል በምክር ቤቱ ውስጥ በሚሰጠው ድምጽ ወይም


አስተያየት ምክንያት አይከሰስም፣ አስተዳደራዊ እርምጃም አይወሰድበትም፡፡

፵፪. አመኔታ ማጣት

ማንኛውም የከተማ ምክር ቤት አባል በመራጩ አመኔታ ባጣ ጊዜ የክልል ምክር ቤት፣


የልዩ ወረዳ ወይም ቀበሌ ምክር ቤት አባላት በመራጫቸው አመኔታ በሚያጡበት ጊዜ
ለሚወስድ እርምጃ በወጣው አዋጅ ለምክር ቤት አባል ተፈጻሚ የሚሆነው ስርዓት
ተፈፃሚ ይነበታል፡፡

ክፍል ስድስት
የክፍለ ከተሞች አደረጃጀትና አስፈጻሚ አካላት
፵፫. ስለ ክፍለ ከተሞች መቋቋም

በአዋጁ አንቀጽ ፳፮ (8) ሥር የተደነገገውን መሰረት በማድረግ በተወሰኑ የክልሉ


ከተሞች የክፍለ ከተማ አስተዳደር ይቋቋማል፡፡ ዝርዝሩ መስተዳድር ምክር ቤት
በሚያወጣው የህግ ክፍል ማስታወቂያ ይወሰናል፡፡

26
፵፬. የክፍለ ከተሞች ተጠሪነት

በዚህ ደንብ አንቀጽ ፵፫ ሥር በሰፈረው መሰረት በክልሉ ከተሞች የተቋቋሙ ክፍለ


ከተሞት ተጠሪነት ለሚመለከተው የከተማ አስተዳደር ይሆናል፡፡

፵፭. የክፍለ ከተሞች አስተዳደር አካላት


እያንዳንዱ ክፍለ ከተማ የሚከተሉት ስልጣንና ተግባር ይኖሩታል፣
1. የክፍለ ከተማ ዋና አስፈጻሚ
2. የክፍለ ከተማ አስተዳደር ኮሚቴ
3. የክፍለ ከተማ ስራ አስኪያጅ

፵፮. የክፍለ ከተማ አስተዳደር ስልጣንና ተግባራት


እያንዳንዱ ክፍለ ከተማ የሚከተሉት ስልጣንና ተግባር ይኖሩታል፣

1. የክፍለ ከተማውን አጠቃላይ እቅዶች፣ መርሀ ግብሮችና ፕሮጀክቶች ያዘጋጃል፣ በስራ


ላይ እንዲውሉ ያደርጋል፣ አፈጻጸማቸውን ይከታተላል፣ ይቆጣጠራል፤
2. ፖሊሲዎች፣ ህጎች ደረጃዎችና የአስተዳደሩ የበላይ አካላት ውሳኔዎችን በክፍለ ከተማው
ተግባራዊ መሆነቸውንና የክፍለ ከተማው ጸጥታ መጠበቁን ያረጋግጣል፣
3. የተደለደለለትን በጀት በስራ ላይ ያውላል፣ አፈፃፀሙን በፋይናንስ ህግ መሰረት መሆኑን
ይከታተላል፣ በሚወጣ መመሪያ መሰረት የማዘጋጃ ቤት አገልግሎት ክፍያዎችን
ይሰበስባል፣ የክፍለ ከተማ ገቢ የሚያድግበት ሁኔታ በማፈላለግ በህግ መሰረት
ተግባራዊ ያደርጋል፣
4. የክፍለ ከተማውን የመንግስት አስተዳደር ሰራተኞች በሲቪል ሰርቪስ ህጎች መሰረት
ያስተዳድራል፣
5. በክፍለ ከተማው ውስጥ የህዝብ ተሳትፎ ለማሳደግ እንዲረዳ የብዙሃን ማህበራት
ብቃት ለማሳደግ የሙያና የአቅም ግንባት ድጋፍ እንዲያገኙ ያደርጋል፣
6. አነስተኛ ነጋዴዎችን፣ የእደጥበብ ባለሙያዎችን እና የመሳሰሉትን ማህበራት
እንዲደራጁ ድጋፍ ይሰጣል፣ አሰራራቸውን ይቆጣጠራል፣
7. በክፍለ ከተማው የሚገኙ ቦታዎችን ያስተዳድራል፣ ህገ ወጥ ግንባታዎችን ይከላከላል፣
ያስወግዳል፣ በከተማው ባለቤትነት ስር ያሉ ቤቶችን ያስተዳድራል፣ ይቆጣጠራል፣
8. በክፍለ ከተማው የሚገኙ ቀበሌዎች ያስተባብራል፣ በአቅም ግንባታ ይደግፋል፣

27
9. የክፍለ ከተማ አስፈጻሚና የማዘጋጃ ቤት አገልግሎት ሥራዎችን ይመራል፣
ያስተባብራል፣
10.የአገልግሎት አሰጣጥ ቀልጣፋ፣ ግልጽና ተጠያቂነት ያለበት እንዲሆን ያደርጋል፡፡
የሚሻሻልበትን ሁኔታ ያመቻቻል፣

፵፯ ስለ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ኮሚቴ አባላት


የክፍለ ከተማ አስተዳደር ኮሚቴ አባላት የሚከተሉት ይሆናሉ

1. የክፍለ ከተማው ዋና አስፈጸሚ


2. በዚህ ደንብ አንቀፅ ፵፰ የተቋቋሙበት ጽ/ቤትን የሚመሩ ኃላፊዎች፣
3. የክፍለ ከተማ ስራ አስኪያጅ

፵፰. ስለ ክፍለ ከተማ አስፈጻሚ አካላት መቋቋም

በእያንዳንዱ ክፍለ ከተማ ለሥራ አስፈጻሚ ተጠሪ የሆኑ የሚከተሉት ጽ/ቤቶች


ተቋቁመዋል፣

1. የጥቃቅን እና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ልማት ጽ/ቤት


2. ነዋሪ ደህንነትና ደንብ ማስከበር አገልግሎ ጽ/ቤት
3. የገቢዎች አስተዳደር ጽ/ቤት
4. ወጣቶች፣ ስፖርትና የአካባቢ ልማት፣ ጽ/ቤት
5. ሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳይ ጽ/ቤት
6. የማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎቶች ጽ/ቤት

፵፱. የክፍለ ከተማ ሥራ አስፈፀሚ አካላት ስልጣንና ተግባራት

በዚህ ደንብ አንቀጽ ፵፰ መሠሰረት የተቋቋመ እያንዳንዱ ጽ/ቤት የሚከተሉት ስልጣንና


ተግባር ይኖሩታል፣

1. የጥቃቅን አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ልማት ጽ/ቤት

1.1. በክፍለ ከተማ ውስጥ የተለያዩ የንግድ ማህበራት እንዲቋቋሙ በማድረግ


የጥቃቅን አነስተኛ ተቋማት እንዲስፋፉ ያደርጋል፣
1.2. የንግድ ፈቃድ ይሰጣል፣ ያድሳል፣ ይመዘግባል፣

28
1.3. በክፍለ ከተማው ውስጥ ከመንግስታዊና መንግስታዊ ካልሆኑ ድርጅቶች ጋር
ግንኙነት በመፍጠር የጥቃቅን አነስተኛ የንግድ ስራ ማህበራት ድጋፍ
እንዲያገኙ ሁኔታዎችን ያመቻቻል፣ በተለይም የማምረቻና መሸጫ ቦታዎች፣
የፋይናንስ የብድር አገልግሎቶች፣ የጥሬ እቃና የማምረቻ መሳሪያዎች
በአንድ ማዕከል የሚያገኙበትን ሁኔታ ያመቻቻል፡፡
1.4. የጥቃቅን አነስተኛ ንግድ ስራዎች ማሰልጠኛ ማእከላት እንዲቋቋሙ
ሁኔታዎችን ያመቻቻል፣ በዘርፉ ለተሰማሩ የህብረተሰብ ክፍሎች ስልጠናዎች
እንዲዘጋጅ ያደርጋል፣ ያስተባብራል፣
1.5. በክፍለ ከተማ ውስጥ የሚገኙትን ስራ አጥ የሆኑ ወጣቶችና ሴቶች አምራች
ዜጋ ሊያደርጉ የሚችሉ፣ የጥቃቅንና አነስተኛ የንግድ ስራ ፕሮጀክቶች
እንዲጠኑ ያደርጋል፣ ተግባራዊነቱን ይከታተላል፣
1.6. መረጃና ምክር ለተጠቃሚዎች የሚሰጥበትን ስርዓት ይዘረጋል፣

2. የነዋሪ ደህንነትና ደንብ ማስከበር አገልግሎት ጽ/ቤት

2.1. በክፍለ ከተማው ውስጥ ህግና ስርዓትን መከበሩንና የህብረተሰቡ ሰላምና


ደህንነት መጠበቁን ያረጋግጣል ይከታተላል፣
2.2. የህዝብ ደህንነትና ጸጥታ ስራዎችን የሚያመላክቱ መረጃዎችን ያሰባስባል፣
ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ግንኙነት ያደርጋል፣
2.3. ስለህዝቡ ሰላምና ደህንነት ከከተማ አስተዳደር ፖሊስና ሌሎቸ አካላት ጋር
በቅንጅት ይሰራል፣
2.4. የወጡ ህጎችና ደንቦች በስራ ላይ እንዲውሉ ያደርጋል፣ ህገወጥነትና ደንብ
መተላለፍን ይቆጣጠራል፣
2.5. የጽዳት መጉደልን፣ ህገወጥ ንግድንና ህገወጥ ግንባታን ይቆጣጠራል
2.6. በደንብ መተላለፍ ዙሪያ በህግ መሰረት ተገቢው እርምጃ እንዲወሰድ
ያደርጋል፣
2.7. የክፍለ ከተማውን ደንብ አስከባሪ ሀይል ይመራል ያዛል ይቆጣጠራል፣
3. የገቢዎች አስተዳደር ጽ/ቤት
3.1. ከክፍለ ከተማ የተሰበሰቡ ገቢዎችን ለከተማው ገቢዎችና ታክስ አስተዳደር
ጽ/ቤት በወቅቱ ገቢ ያደርጋል፣

29
3.2. ግብር ከፋዮች ህጎችን አውቀው መብትና ግዴታቸውን እንዲወጡ
ይቀሰቅሳል፣ ግብር የመክፈል ግዴታቸውን በህግ መሰረት እንዲፈጽሙ
ያደርጋል፣
3.3. የክፍለ ከተማው ገቢ የሚያድግበትን ያጠናል፣ የገቢ አሰባሰብ ህጎችና ደንቦች
በስራ ላይ እንዲውሉ ያደርጋል፣
3.4. ግብር ከፋዮች ለይቶ ለማወቅና ለመመዝገብ የሚያስችሉ አሰራሮችን
ተግባራዊ ያደርጋል፣
3.5. የክፍለ ከተማው ሌሎች ገቢዎች በወቅቱ እንዲሰባሰቡ ያደርጋል፣
3.6. የገቢና አወሳሰንና የሂሳብ አያያዝ ብቃት ባለው መልኩ ለማከናወን
የሚያስችሉ የአሰራር ዘዴዎችን ይቀይሳል፣ ተግባራዊነታቸውን ይከታተላል፣
4. ወጣቶች፣ ስፖርትና የአካባቢ ልማት ጽ/ቤት
4.1. የከተማው ወጣቶች በልማትና በዲሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ሊሳተፉ
የሚችሉበትን እንዲሁም ወጣቶች በመልካም ስነ-ምግባር እንዲታነጹና
እውቀት ለመቅሰም የሚያስችላቸውን አገልግሎቶች ማግኘት የሚችሉበት
ሁኔታ ያመቻቻል፣
4.2. ስፖርት የሚሻሻልበትና የሚያድግበት ስልት ይቀይሳል፣ የስፖርት
ማዘውተሪያ ስፍራዎች በአግባቡ እንዲያዙና እንዲጠበቁ ያደርጋል፣ አግባብ
ካላቸው ድርጅቶችና ባለሀብቶች ጋር በመተባበር የስፖርት ትጥቅና
መሳሪያዎች በክፍለ ከተማ ውስጥ እንዲመረቱ ያበረታታል፣ በእርዳታና
በግዥ የሚገኙበትን ሁኔታ ያመቻቻል፣
4.3. ለጎርፉ የተጋለጡ የከተማውን ክፍሎች በተመለከተ ነዋሪዎችንና ሌሎች
ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመተባበር የጎርፍ መከላከያ ግንባታ
ያከናውናል ወይም እንዲከናወን ያደርጋል፡፡
4.4. በከተማው የሚገኙ የመዝናኛ ሥፍራዎችና ፓርኮች ያደራጃል፣ ይመራል፣
የሚለሙበት ስልት እየቀየሰ ያስተባብራል፣
4.5. በክፍለ ከተሞች መካከል የሚካሄዱ የአካባቢ ልማት ስራዎች የተጣጣሙና
የተደጋገፉ እንዲሆኑ ያስተባራል፡፡

5. ሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ጽ/ቤት


5.1. ህብረተሰቡ እራሱን በልዩ ልዩ ማህበራት እያደራጀ በልማት ስራው ተሳታፊ
የሚሆንበትን ሁኔታ ያመቻቻል፣ የህብረተሰቡ ተሳትፎ በስርዓት የሚመራበት

30
ስልት ይቀይሳል፣ ማህበራት የእርስ በእርስ ተሞክሮ ልውውጥና መደጋገፍ
እንዲያደርጉ በቅንጅት እንዲንቀሳቀሱ ተገቢውን ጥረት ያደርጋል፣
ያበረታታል፣
5.2. በከተማ ውስጥ ማህበራዊ ችግሮችና ጠንቆች ሊወገዱ የሚችሉባቸውን
ህብረተሰቡን የሚያሳትፍ ስልቶች ይቀይሳል፣ ሲፀድቁም ተግባራዊ
መሆናቸውን ያረጋግጣል፣
5.3. መንግስታዊ ባልሆኑ ድርጅቶች በኩል ማህበራዊ ደህንነት በሚመለከት
ለሚካሄዱ ስራዎች ደጋፍ ይሰጣል፣
5.4. ማህበራትን በህብረተሰብ ውስጥ የማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ግንኙነት ተሳትፎ
እንዲያደርጉ ድጋፍ ይሰጣል፡፡
5.5. የሴቶችን አቅም የሚያጎለብቱ ትምህርታዊ፣ ሙያዊ ፣ የተጨማሪ ክህሎት
ስልጠናዎችን ያመቻቻል፣ ሴቶችን ተጠቃሚ የሚያደርጉ ፕሮጀክቶችን
ያፈላልጋል፣
5.6. አግባብ ካላቸው አካላት ጋር በመተባበር ሴቶችን በማህበራት እንዲደራጁ
የብድርና የቁጠባ አገልግሎቶች እንዲያገኙ ሁኔታዎችን ያመቻቻል፣
5.7. በሴቶች ላይ የሚደርሱ ጥቃቶችን ይከላከላል፣
5.8. በኤች አይቪ ኤድስ ላይ ለህብረተሰቡ ግንዛቤ የሚሰጡ ተቋማትን
ያስተባብራል፣ የተጠቁትን አካላት እንክብካቤ የሚያገኙበት ሁኔታ
ያመቻቻል፣
6. የክፍለ ከተማ ማዘጋጃ ቤት ስራ አስኪያጅ
6.1. መናፈሻዎችን፣ መካነ መቃብርና የጋራ መጸዳጃ ቤቶችን ያስተዳድራል፣
ያስፋፋል፣
6.2. መናፈሻዎች ለተለያዩ ማህበራዊ ጉዳዮች እንዲያገለግሉ ያደርጋል፣
መዝናኛዎችን አዘጋጅቶ ያቀርባል፣
6.3. ኅብረተሰቡን በመናፈሻዎች ልማትና እንክብካቤ ያሳትፋል፣
6.4. የደረቅ ቆሻሻ አወጋገድ በተመለከተ የግል ባለሀብቶችና ሌሎች የኅብረተሰብ
ክፍሎች እንዲሳተፉ ያደርጋል፣
6.5. ደረቅ ቆሻሻ እንደገና በስራ ላይ የሚውልበትንና ጠቃሚ ውጤት
የሚያስገኝበትን ስልት በማጥናት ተግባራዊ የሚሆንበትን ሁኔታ
ያመቻቻል፣

31
6.6. በክፍለ ከተማው ባለቤትነት ሥር ያሉ ቤቶችን ይመዘግባል፣ ያስተዳድራል ፣
ቤቶችን በመሻሻል ወደ ግል ባለቤትነት የሚዛወሩበትን ሁኔታ አጥንቶ
ያቀርባል፣
6.7. ቤቶች በሚሰሩበት አካባቢ መሰረተ ልማቶችና ማህበራዊ አገልግሎቶች
የሚሟሉበት ሁኔታ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመሆኑ ያመቻቻል፣
6.8. በቤት ስራ ማህበራትና መንግስታዊ ባልሆኑ ድርጅቶች የመኖሪያ ቤት
ግንባታ እንዲካሄድ ያበረታታል የቴክኒክ ድጋፍ ይሰጣል፣
6.9. እንዲለሙ የሚፈለጉ ቦታዎችን በማጥናት ያዘጋጃል፣
6.10. የመሬት ልማት ሥራ ለማከናወን ፍላጎት ካላቸው አልሚዎች ጋር በጋራ
በመስራት የልማት ስራው የሚካሄድበትን ሁኔታ ያመቻቻል አፈጻጸሙን
ይከታተላል፣
6.11. በካሳ ክፍያ አፈፃፀም መመሪያ መሰረት ተመጣጣኝ ካሳ መከፈሉን
ያረጋግጣል፣
6.12. የግንባታ ህጎች ተግባራዊ መሆናቸውን ያረጋግጣል፣
6.13. የመብራት ሀይል፣ የስልክ፣ የውሃና የመሳሰሉት የመሰረተ ልማት
ግንባታዎች በተቀናጀ ዲዛይን ተጣጥመው እንዲካሄዱ ያስተባብራል፣
6.14. በመሰረተ ልማት ስራዎች ህብረተሰቡ እንዲሳተፍ ሁኔታዎችን ያመቻቻል፣
6.15. ለጎርፍ የተጋለጡ የከተማውን ክፍሎች በተመለከተ የጎርፍ መከላከያ ጥናት
በማድረግ ሲጸድቅም ደረጃ በደረጃ ተግባራዊ መሆኑን ያረጋግጣ፣
6.16. ልደት፣ ሞት፣ ጋብቻ፣ ፍቺ ይመዘግባል፣ የምስክር ወረቀት ይሰጣል፣
6.17. ለነዋሪዎች የነዋሪነት መታወቂያ ወረቀት የሚሰጥበት ሁኔታ ያመቻቻል፣
6.18. በከተማው ተወስኖ ከሚሰጥ የገቢ ምንጮች የማዘጋጃ ቤት ገቢ ያሰበስባል፡፡

ክፍል ሰባት

ስለ ከተማ ቀበሌ አስተዳደር አካላት

፶ . ስለቀበሌ አስተዳደር መቋቋም

1. በእያንዳንዱ ከተማ አስተዳደር ከተሞች እንደየከተማው የህዝብ ብዛት ቁጥራቸው


የሚለያይ ቀበሌ አስተዳደሮች ይቋቋማሉ፣

32
2. በእያንዳንዱ የከተማ አስተዳደር የሚኖሩ የቀበሌ አስተዳደሮች ዝርዝር የክልሉ
መስተዳድር ምክር ቤት በህግ ክፍል ማስታወቂያ ይገለጻል፣

፶፩ . ስለከተማ ቀበሌ አስተዳደር አካላት


1. እያንዳንዱ የከተማ ቀበሌ ምክር ቤት አፈጉባኤ፣ የቀበሌ ሊቀመንበር፣ የቀበሌ
ኮሚቴና ማህበራዊ ሸንጎ ይኖሩታል፡፡
2. ስለቀበሌ አስተዳደር የውስጥ አደረጃጀትና አሰራር ስርዓት በከተማው ምክር ቤት
በሚወስነው መሰረት ይፈጸማል፡፡
3. ከላይ በንዑስ አንቀጽ 2 የተመለከተው እንደተጠበቀ ሆኖ የቀበሌ ኮሚቴ
ሊቀመንበሩን ጨምሮ 6 አባላት የያዘ ይሆናል፡፡
4. የቀበሌ አስተዳደር ኮሚቴ አባላትና የስራ ድርሻ በዚህ ደንብ አንቀጽ 34/2
በተመለከተው መሰረት የሚፈጸም ይሆናል፡፡

፶፪ . ስለ ከተማ ቀበሌ ምክር ቤት

1. በአንድ ቀበሌ ብቻ በመዋቀራቸው ምክንያት በከተማ ንዑስ አስተዳደር ክፍሎች


መከፋፈል ከማይችሉ ከተሞች በቀር እያንዳንዱ ከተማ በስሩ በአንድ ላይ የከተማ
ቀበሌ ምክር ቤቶች ይኖሩታል፡፡
2. የከተማ ቀበሌ ምክር ቤቶች አባላት የከተማ ቀበሌው በሚያቅፈው ህዝብ ነጻና
ቀጥተኛ ምርጫ ይመረጣሉ፣
3. የየእርከኑን ምክር ቤት ተወካዮች ብዛት ለመወሰን በክልል ምክር ቤት በወጣው
አዋጅ ቁጥር …./1999 አንቀጽ 3 ንዑስ አንቀጽ 6 በተደነገገው መሰረት የእያንዳንዱ
ከተማ ቀበሌ ምክር ቤት አባላት ብዛት 200 ይሆናል፡፡

፶፫. የቀበሌ ምክር ቤት ስልጣንና ተግባር

እያንዳንዱ የቀበሌ ምክር ቤት የሚከተሉት ስልጣንና ተግባራት ይኖሩታል፣


1. በቀበሌው እቅድ ላይ በመምከር ለክፍለ ከተማው ምክር ቤት እንዲቀርብ
ያደርጋል፣
2. የቀበሌው ነዋሪ በየአካባቢው በልማትና በመልካም አስተዳደር የሚያደርገው
ተሳትፎ ከፍ እንዲል ያደርጋል፣
3. የምክር ቤቱን አፈ ጉባኤና ቀበሌ ሊቀመንበር ከምክር ቤቱ አባላት መካከል
ይመርጣል፤

33
4. በቀበሌ ሊቀመንበር አቅራቢነት የቀበሌውን ኮሚቴ አባላትና ማህበራዊ ሸንጎ
ዳኖች ሹመት ያጸድቃል፣
5. የቀበሌ ምክር ቤት ኮሚቴዎችን ያቋቁማል፣
6. በቀበሌው ሊቀ መንበር የሚቀርቡ ዓመታዊና ወቅታዊ ሪፖርት መርምሮ ውሳኔ
ይሰጣል፣

፶፬. የአፈጉባኤ ስልጣንና ተግባር፣

ከምክር ቤቱ አባላት የሚመረጥ ሆኖ፣

1. የምክር ቤቱን ስብሰባዎች ይመራል፣ የመወያያ አጀንዳዎችን ያዘጋጃል፣


2. የምክር ቤቱን ኮሚቴ ያስተባብራል፣
3. ምክር ቤቱ በአባላት ላይ የሚወስዳቸውን የስነ-ስርዓት ርምጃዎች ያስፈጽማል፣
4. በምክር ቤቱ ስለሚወስኑ ውሳኔዎች ወቅታዊ መግለጫ ለቀበሌ ነዋሪዎች ይሰጣል፣
ለሚመለከታቸው አካላት ያሳውቃል፣
5. የምክር ቤቱ አባላት አቅም ግንባታ ስራ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመቀናጀት
ያስፈጽማል፣
6. ሶስተኛ ወገኖች ጋር በሚደረግ ግንኙነት ምክር ቤቱን ይወክላል፣
7. በምክር ቤቱ የሚሰጡትን ሌሎች ተግባሮች ያከናውናል፣

፶፭. የቀበሌ ሊቀመንበር

በጎ ፈቃድ የቀበሌ ሊቀመንበር ተጠሪነቱ ለቀበሌው ምክር ቤት ሆኖ የሚከተሉት


ስልጣንና ተግባራት ይኖሩታል፣

1. በከተማው የቀበሌ ምክር ቤት የሚወሰኑ የቀበሌ ተግባራትንና የውስጥ አደረጃጀት


ያስፈጽማል፣ ይመራል፣
2. የቀበሌ ኮሚቴ አባላትን ከምክር ቤት አባላትና የምክር ቤት አባላት ካልሆኑት
መካከል መርጦ ለቀበሌው ምክር ቤት በማቅረብ ሹመታቸውን ያጸድቃል፣
3. ከቀበሌ ኮሚቴ ጋር የቀበሌውን አመታዊ እቅድ በማዘጋጀት ለቀበሌ ምክር ቤት
ያቀርባል፣ የቀበሌ ኮሚቴ ይመራል፣ በቀበሌ ህግና ስርዓት ያስከብራል፣
4. በአካባቢ ልማት የህብረተሰቡን ተሳትፎ ያስተባብራል የተለያዩ ኮሚቴዎች
እንዲቋቋሙ ያደርጋል፣
34
5. በብሄራዊና በህዝብ በአላት ስነ-ስርዓቶች ላይ እንደአስፈላጊነቱ ቀበሌውን ይወክላል
6. ዓመታዊና ወቅታዊ ሪፖርት ለክፍለ ከተማ ስራ አስፈጻሚና ለቀበሌው ምክር ቤት
ያቀርባል፣
7. በቀበሌው ምክር ቤትና በክፍለ ከተማው ስራ አስፈጻሚ የሚወጡትን ሌሎች
ተግባራት ያከናውናል፣

ክፍል ስምንት
ስለ ማህበራዊ ሸንጎና ደንብ አስከባሪ አካል

፶፮. ማህበራዊ ሸንጎ ስለመቋቋም

1. በአዋጁ አንቀጽ ፲፭ ንዑስ አንቀጽ 2 እና አንቀጽ ፳፯ ንዑስ አንቀጽ 5 በተደነገገው


መሰረት በእያንዳንዱ የከተማ ቀበሊያት በሚፈጸሙ የደንብ መተላለፍና በስነ-ስርዓት
ማጉደል የሚቀርቡ ክሶችን የሚዳኝ የማህበራዊ ሸንጎ ፍርድ ቤት ይቋቋማል፣
2. የቀበሌ ማበራዊ ሸንጎ ተጠሪነቱ ለቀበሌ ምክር ቤት ይሆናል

፶፯ . የማህበራዊ ሸንጎ ስልጣን

የቀበሌ ማበራዊ ፍርድ ቤቶችን እንደገና ለማቋቋም በወጣው አዋጅ ቁጥር 65/95
የተደነገገው የማህበራዊ ፍርድ ቤት የዳኝነት ስልጣን እንደተጠበቀ ሆኖ በሚከተሉት
ጉዳዮች ስልጣንና የተሟላ ዳኝነት ይኖረዋል፣

1. ህገወጥ ግንባታ፣ መሬት አጠቃቀም፣ እንዲሁም በይዞታ ካርታ ፕላን አተገባበር


በጽዳት መጓደል፣ ሀይጂንና ሳኒቴሽን ጉዳይን፣ የህዝብ አገልግሎቶችን እና ክፍት
ቦታዎችን አጠቃቀም በተመለከተ፣
2. ሕገወጥ እርድ፣ ሕገወጥ ንግድ፣ ደረጃቸውን ያልጠበቁ የታሸጉ ምግቦችንና ሸቀጦችን
በተመለከተ፣
3. የቤት እንሰሳትና የአካባቢ ብክለት በተመለከተ፣
4. የነዋሪውን ደህንነትና ሰላም እንዲሁም ክብርና ጥቅም የሚጎዱ ሌሎች የከተማ ስነ-
ስርዓት እና ደንብ መተላለፍ የተመለከቱ ጉዳዮች፣

፶፷ . ስለማበራዊ ሸንጎ ዳኞች አሿሿም

1. የከተማ ቀበሌ ማህበራዊ ሸንጎ ፍርድ ቤት ሶስት ዳኞች ይኖሩታል፣

35
2. የማህበራዊ ሸንጎ ፍርድ ቤት ዳኞች በቀበሌው ሊቀመንበር አቅራቢነት በቀበሌው ምክር
ቤት ይሾማሉ፣

፶፱. ደንብ አስከባሪ አካል ስለማቋቋም

1. በአዋጁ አንቀጽ ፳፯ ንዑስ አንቀጽ 6 በተደነገገው መሰረት እያንዳንዱ የከተማ ቀበሌ


ቁጥራቸው እንደሁኔታው የሚለያይ ስነ-ስርዓትና ደንብ አስከባሪ ግብረ ሀይል
ይኖረዋል፡፡
2. በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ 1 መሰረት የሚቋቋም የቀበሌ ስነስርዓትና ደንብ አስከባሪ
ሀይል በቀበሌ ሊቀመንበር አቅራቢነት በምክር ቤቱ የሚሾም አስተባባሪ
እንደአስፈላጊነቱ ረዳት አስተባባሪ ይኖረዋል፡፡
3. የቀበሌ ስነስርዓትና ደንብ አስከባሪ ሀይል አስተባባሪ ተጠሪነቱ ለምክር ቤቱና ለቀበሌ
ሊቀመንበር ይሆናል፡፡
4. የቀበሌ ስነስርዓት ደንብ አስከባሪ አባላት ብዛት ምልመላና ሌሎች አስተዳደራዊ
የአሰራር ስርዓቶች በከተማው አስተዳደር ተጠንቶ በከተማው ምክር ቤት በሚወስነው
መሰረት የሚፈጸም ይሆናል፡፡

ክፍል ዘጠኝ
ስለግንኙነትና የሪፖርት ስርዓት
፷. የከተማና የመንግስት ግንኙነት

1. ማንኛውም የክልሉ ከተማ አስተዳደር ወይም የማዘጋጃ ቤት ከተማ በከተማው ክልል


ውስጥ በሚንቀሳቀሱ የክልልና የፌዴራል መንግስት ተቋማት ወይም ከሌሎች ድርጅቶች
ጋር የከተማውን ዓላማ ለማሳካት የሚረዱ ግንኙነት መፍጠር ይቻላል፡፡
2. በማናቸውም ደረጃ የሚገኝ ከተማ በመንግስት የወጡ ፖሊሲዎችን፣ ህጎችንና ደንቦችን፣
ደረጃዎችን የማስፈጸም ተጠሪ ለሆነለት የመንግስት አካል ወቅታዊ ሪፖርት የማቅረብና
የፈጸማቸውን ተግባራት አስመልክቶ ተገቢውን መግለጫና መረጃ የመስጠት ግዴታ
አለበት፣ የሚመለከተውም የበላይ አካልም የመከታተል ግዴታና ሀላፊነት ይኖርበታል፣

36
፷፩. ሕጎችን ደንቦችንና ደረጃዎችን ስለማስፈጸም፣

1. ማንኛውም ከተማ በመንግስት የሚወጡ ፖሊሲዎች፣ ህጎችን፣ ደንቦችን፣ ደረጃዎች


የማስፈፀምና የመፈጸም ግዴታ አለበት፣
2. ከተማው ተጠሪ ለሆነለት የመንግስት አካል የሚያቀርበው ሪፖርት ይህ ግዴታ
ስለመፈፀሙ የሚያረጋግጥ መግለጫ ያካተተ ሊሆን ይገባል፣
3. ከተማው ተጠሪ የሆነለት የመንግስት አካል ወይም ቢሮው ወቅታዊ ኢንስፔክሽን
ኦዲትና ግምገማ በማድረግ በመንግስት የወጡ ህጎች፣ ደንቦችና ደረጃዎች በከተማች
ተግባራዊ መሆናቸውን ያረጋግጣል፣

፷፪. በከተማ የመንግሥት ተቋማት ተጠሪነት

1. በከተማ ደረጃ የሚቋቋመው መንግሥታዊ ተቋማት ተጠሪነት ለከተማው አስተዳደር


ከንቲባና እንደ ከተማው ደረጃና ተጠሪነት ለክልል ቢሮ ወይም ለዞን መምሪያ
ይሆናል፡፡
2. በክፍለ ከተማ ደረጃ የሚቋቋሙ መንግስታዊ ተቋማት ተጠሪነት ለክፍለ ከተማው
ዋና አስፈጻሚ እና ለከተማው መምሪያ ወይም ጽ/ቤት ይሆናል፡፡

፷፫. ሪፖርት የማቅረብ ግዴታ

እያንዳንዱ ከተማ የስራ እና የገንዘብ አጠቃቀም ሪፖርቶች በየሩብ ዓመቱ እንዲሁም


የኦዲት ሪፖርት በየዓመቱ ተጠሪ ለሆነለት የመንግስት አካል ያቀርባል፣ የሪፖርቱ
ግልባጭ ለቢሮው እንዲደርስ ያደርጋል፣

፷፬. የሥራ አፈጸጸም ሪፖርቱ ይዘት

1. በከተማች የሚቀርበው የስራ አፈፃፀም ሪፖርት ሰነድ የቀረበበት ወቅት


የሚያመለክት ሆኖ በዋነኝነት የሚከተሉትን ያካተተ መሆን አለበት፣
1.1. የታቀዱ ተግባራት ዝርዝር
1.2. የተከናወኑ ተግባራት
1.3. የተገኘውን ውጤት
1.4. ከሌሎች አካላት ጋር የተደረገውን ግንኙነትና የስራ ደረጃ፣
1.5. ያጋጠሙ ችግሮችና የተወሰዱ የመፍትሄ እርምጃ

37
1.6. ለሚቀጥለው ወቅት የታቀዱ ተግባራት
1.7. እቅዶችን ለመፈጸም የሚያስፈልጉ ግብአቶች፣ ከመንግስት የሚያስፈልገው
ትብብርና ድጋፍ፣
2. የገንዘብ አጠቃቀም ሪፖርት በዋነኝነት የሚከተሉትን ማካተት አለበት፣
2.1. የገንዘብ አጠቃቀም እቅድ
2.2. በወቅቱ የተገኘው ገቢ
2.3. በወቅቱ የወጣውን ወጪ
2.4. ለሚቀጥለው ወቅት የተዘጋጀውን የገንዘብ አጠቃቀም እቅድ
2.5. እቅዶችን ለመፈጸም ከመንግስት የሚያስፈልገውን ትብብርና ድጋፍ፣
3. የስራ አፈፃፀም ሪፖርቱም ሆነ የገንዘብ አጠቃቀም ሪፖርቱ አስፈላጊ የሆኑ የድጋፍ
ሰነዶች/መረጃዎች/ ያካተተ ይሆናል፣

፷፭. በሪፖርቱና በክትትል ግምገማዎች መነሻነት ስለሚወሰዱ ርምጃዎች፣

ከተማው ተጠሪ የሆነለት መንግስታዊ አካል በሚቀርብለት ሪፖርትና በሚያደርገው


ክትትል ላይ በመመስረት የሚከተሉትን እርምጃዎች በቅደም ተከተል ሊወስድ ይችላል፣

1. ከተማው ሪፖርቱን በወቅቱ ሳያቀርብ የቀረ እንደሆነ ወይም ሪፖርቱ የከተማውን


ትክክለኛና እውነተኛ ሁኔታ የማያሳይ የሆነ እንደሆነ ወይም የኦዲት ኢንስፔክሸን
ወይም የግምገማ ውጤት የአስተዳደር ብቃት የሚያንስ መሆኑን የሚያመላክት
ሲሆን ወይም ተገቢ ደጋፊ ሰነድ ከሪፖርቱ ጋር ያልተያያዘ እንደሆነ በጉዳዩ ላይ
ተገቢው ማብራሪያ እንዲቀርብ ወይም አስፈላጊው ደጋፊ ሰነድ እንዲያዝ መጠየቅ
ስልጣን አለው፣
2. የቀረበው ጥያቄ በተገቢው ጊዜ ሳይፈጸም ወይም ምላሽ ሳያገኝ የቀረ እንደሆነ
ከከተማው ምክር ቤት ጋር የጋራ ስብሰባ እንዲደረግ ሃሳብ ያቀርባል፣
3. የጋራ ስብሰባ ዓላማና ግብ የችግሩን ትክክለኛ ገጽታ መረዳትና የከተማውን የእቅድ
አፈፃፀምና ሪፖርት አቀራረብ አቅም ማጎልበት ይሆናል፣
4. የጋራ ስብሰባ የተፈለገውን ውጤት ሳያስገኝ የቀረ እንደሆነ ከቢሮው ጋር በመመካከር
ጉዳዩን ለከተማው ህዝብ አጠቃላይ ስብሰባ የሚያቀርብበት ሁኔታ ይመቻቻል፣
5. ሁኔታዎች ሲያስገድዱ ለቢሮውና ለሚመለከታቸው መንግስታዊ አካላት ተጨማሪ
አስተያየት ሊያቀርብ ይችላል፣

38
6. ሁኔታው ከተማው ምክር ቤት መፍረስ የሚያመለክት ከሆነ ውሳኔው በአዋጁ
አንቀጽ 19 በተመለከተው መሰረት በክልሉ መስተዳድር ምክር ቤት የሚሰጥ
ይሆናል፣

ክፍል አሥር
ልዩ ልዩ ድንጋጌዎች
፷፮. የመሸጋገሪያ ድንጋጌ

1. የከተሞች ሽግግር አስተዳደር እና የከተማ አስተዳደር ኮሚቴ የከተማ ምርጫ እስከ


ሚደረግ ብቻ ያገለግላል፣
2. በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ 1 ስር የተመለከተው እንደተጠበቀ ሆኖ የከተማ ምክር
ቤት አባላት ምርጫ በተከናወነ በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ የከተማ ሽግግር አስተዳደርና
የከተማ አስተዳደር ኮሚቴ ስልጣኑን ለተመረጠው የከተማ ምክር ቤት ያስረክባል፣
መብትና ግዴታውም ለከተማ ምክር ቤት ይተላለፋል፣

፷፯. ስለተሻሩና ተፈጻሚነት ስለማይኖራቸው ህጎች


የሚከተሉት በዚህ ደንብ ተሸረዋል፡፡
1. የከተሞች አደረጃጀትና አስተዳደር ስርዓት እንዲኖር ለማስቻልና አዋጅ ቁጥር 51/94
ለማስፈፀም የወጣው የከተሞች አደረጃጀትና አስተዳደር ስርዓት ደንብ ቁጥር6/1995
2. የከተሞች ምክር ቤት እስኪቋቋም ድረስ የሽግግር አስተዳደር ሂደቱን የሚመራ የከተሞች
አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 51/94 የሚያስፈጽም የከተሞች ሽግግር አስተዳደር ለማቋቋም
የወጣው ደንብ ቁጥር 7/1995
3. በሌላ ሁኔታ በግልጽ ካልተደነገገ በስተቀር ይህ ደንብ ከመውጣቱ በፊት ሲሰራባቸው የቆዩና
ከዚህ ደንብ የማይጣጣሙ ወይም የሚቃረኑ ማናቸውም ደንቦችና መመሪያዎች በዚህ ደንብ
በተመለከቱ ጉዳዮች ላይ ተፈጻሚነት አይኖራቸውም፡፡

፷፰. መመሪያ የማውጣት ሥልጣን


ቢሮው ደንቡን በመከተል ለደንቡ መተግበር አስፈላጊ የሆነውን መመሪያ ያወጣል፡፡

፷፱. ደንቡ የሚጸናበት ጊዜ


ይህ ደንብ ከዛሬ ሚያዚያ 3 ቀን 1999 ዓ.ም ጀምሮ የፀና ይሆናል
ሽፈራው ሽጉጤ
የደቡብ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል መንግሥት
ርዕሰ መስተዳድር
አዋሳ

39

You might also like