Download as docx, pdf, or txt
Download as docx, pdf, or txt
You are on page 1of 2

ለገቢዎች ሚኒስቴር

መካከለኛ ግብር ከፋዮች ቅ/ጽ/ቤት


አዲስ አበባ

ጉዳዩ፡-የጠየቅነው ክሊራንስ እንዲሰጠን መጠየቅን ይመለከታል፤


ድርጅታችን ኤ.ቢ.ኤ.ዋይ.ኤስ ትሬዲንግ ኃላ/የተ/የግል/ማህበር በግብር ከፋይ መለያ ቁጥር 0052975307 ተመዝግቦ

ምርቶቹን በሀገር ውስጥ እና ከሀገር ውጪም ደረጃውን የጠበቀ ምርት ለገበያ በማቅረብ USD 7,3 ሚሊዮን በላይ ያስገኘ

ድርጅት ሲሆን 800 (ከስምንት መቶ) በላይ ለሆኑ ሠራተኞች የስራ እድል የፈጠረ፣ ምርቶቹን በአሜሪካ እና በካናዳ ገበያ

በማቅርብ በየአመቱ ከፍተኛ የሆነ የዉጭ ምንዛሬ በማሰገባት ለሀገራችን እድገት የበኩሉን አሰተዋፆ በማድርግ ላይ

የሚገኝ ሀገር በቀል ድርጅት ነው።

ነገር ግን ድርጅታችን ኤ.ቢ.ኤ.ዋይ.ኤስ ትሬዲንግ ኃላ.የተ.የግ.ማ የሞተር ቁጥር PSAAH0110DY1G4054503

የሻንሲ ቁጥር YARVFAHKHGZ108380 የድርጅታችንን ሞተር ሽያጭ አከናውነን ክፈሉ የተባልነውን የተ.እ.ታ

422,701.35 (አራት መቶ ሃያ ሁለት ሺህ ሰባት መቶ አንድ ብር ከ 35/100) ከፍለን ደረሰኝ ያቀረብን እና ጥር 22 ቀን

2016 ዓ.ም ክሊራንስ እንዲሰጠን የጠየቅን ቢሆንም በሚኒስትር መስሪያ ቤታችሁ በተጻፈ የእዳ መካካሻ በቀን

28/06/2016 ዓ.ም በደብዳቤ ቁ.ገ/ሚ/መ/25/10675/16 ብር 496,836.11 (አራት መቶ ዘጠና ስድስት ሺህ ስምንት መቶ

ሠላሳ ስድስት ብር ከ 11/100 )ተመላሽ እያለን በሲስተም ላይ የሚታይ ዕዳ አለባችሁ በሚል የጠየቅነው ከሊራንስ

ሳይሰጠን እስካሁን በመንገላታት ላይ እንገኛለን ስለዚህም ቅርንጫፍ መስረያ ቤታችሁ ይህን ተገንዝቦ ክሊራንስ

እንዲሰጠን እንጠይቃለን ለሚደረግልን የሥራ ትብብር በቅድሚያ እናመሰግናለን።

ከሠላምታ ጋር

ይበልጣል ጌታቸው
ዋና ስራ አስኪያጅ
ግልባጭ
 ለፋይል
ለገቢዎች ሚኒስቴር
መካከለኛ ግብር ከፋዮች ቅ/ጽ/ቤት
አዲስ አበባ

ጉዳዩ፡-ለታክስ ተመላሽ ክፍል በቀን 5/07/2016 በቁጥር ገ/ማ/መ/2.5/105/5/16 የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመላሽ
ላይ የተሰጠን ውሳኔን ይመለከታል

ድርጅታችን ኤ.ቢ.ኤ.ዋይ.ኤስ ትሬዲንግ ኃላ/የተ/የግል/ማህበር በግብር ከፋይ መለያ ቁጥር 0052975307 ተመዝግቦ
ምርቶቹን በሀገር ውስጥ እና ከሀገር ውጪም ደረጃውን የጠበቀ ምርት ለገበያ በማቅረብ USD 7,3 ሚሊዮን በላይ
ያስገኘ ድርጅት ሲሆን ከስድስት መቶ በላይ ለሆኑ ሠራተኞች የስራ እድል የፈጠረ፣ ምርቶቹን በአሜሪካ እና በካናዳ ገበያ
በማቅርብ በየአመቱ ከፍተኛ የሆነ የዉጭ ምንዛሬ በማሰገባት ለሀገራችን እድገት የበኩሉን አሰተዋፆ በማድርግ ላይ
የሚገኝ ሀገር በቀል ድርጅት ነው።

ነገር ግን ድርጅታችን ቀድሞ ከነበረበት ከአነስተኛ ግብር ከፋዮች ምዕራብ ቅርንጫፍ ወደ እናንተ ከተዘዋወርን ጊዜ
ጀምሮ ወደ በሚኒስቴር መስሪያ ቤታችሁ መካከለኛ ግብር ከፋዮች ቀ/ጽ/ቤት ቀድሞ የተወሰነልንን የቫት ተመለሽ
ከመስከረም ወር ጀምሮ በመመላለስ በብዙ ውጣ ውረድ የካቲት 27 ቀን 2016 ዓ.ም ወሳኔ ያገኘን ቢሆንም የ 2015
ዓ.ም ህዳር 4,2016 ዓ.ም የተ.እ.ታ ተመላሽ ጠይቀን ምላሽ ባናገኝም የ 2014 ዓ.ም የውሳኔ ደበዳቤ ላይ በደብዳቤ ቁጥር
ገ/ሚመ/2.5/10643/16 በቀን 27/006/2016 ከሐምሌ /2014 እስከ ሰኔ 2015 ዓ.ም ያለው በአጠቃላይ ኦዲት እንዲታይ
ተወስኖ ደብዳቤ የደረሰን በሆንም ኦዲቱ ተደርጎ ምላሽ እየተጠባበቅን እያለን ምንም ሰነድ ባልታየበት ሁኔታ የ 2015
የቫት ተመላሽ ጥያቄያቸን መቋረጡን የሚገልጽ ደብዳቤ መጋቢት 5/ቀን 2016 ዓ.ም በቁ.ገሚመ/205/105/5/16
የደረሰን ሲሆን ወሳኔው አግባብነት የሌለው በመሆኑ ወሳኔው ታየቶ ኦዲት ተደርጎ ምላሽ እንዲሰጠን እንጠይቃለን
ለሚደረግልን የሥራ ትብብር በቅድሚያ እናመሰግናለን ።

ከሠላምታ ጋር

ይበልጣል ጌታቸው
ዋና ስራ አስኪያጅ

ግልባጭ
 ለፋይል

You might also like