Download as doc, pdf, or txt
Download as doc, pdf, or txt
You are on page 1of 6

Company Name:

የባሕርዳር ጨርቃ ጨርቅ አክሲዩን ማኀበር Document No.


BAHIR DAR TEXTILE SHARE COMPANY OF/BDTSC/8-1-040

Title
Issue No. Page No.:
INTER OFFICIAL LETTER 1 Page 1 of 1

የደንበኞች እርካታ ግብረ መልስ ማጠቃለያ ሀሳብ


የዚህ የዳሰሳ ጥናት አላማ የባህር ዳር ጨርቃጨርቅ አክሲዮን ማህበር የሚያመርታቸውን ምርቶች ለሚገዙ
ደንበኞች የሚሰጠውን አገልግሎት ለመገምገም ደንበኞች ከባህር ዳር ጨርቃጨርቅ አ.ማህበር ጋር
በነበራቸው የስራ ግኑኝነት አክስዮን ማህበሩ ከሚሰጣቸው አገልግሎቶች አንፃር በተመረጡ መስፈርቶች
ከ 1 አስከ 5 ነጥብ እንዲሰጡ ተደርጓል፡፡ በዚሁም መሰረት ፤1 በጣም ዝቅተኛ፤ 2 ዝቅተኛ፣ 3 አጥጋቢ፣ 4
ከፍተኛ፣ እና 5 በጣም ከፍተኛ በማለት አስተያየታቸውነ እነዲገልጹ በተየቁት መሰረት መሰረት 15 ደንበኞች
ለ 12 ጥያቄዎች የሰጧቸው ምላሾች ከታች በሰንጠረዥ ተጠቃለው ቀርበዋል፡

Page 1 of 6
Company Name: Document No::
ባህር ዳር ጨርቃ ጨርቅ አክሲዮን ማህበር OF/BDTSC/5-1-008
BAHIR DAR TEXTILE SHARE COMPANY
Title
Issue No.: Page No.:
: CUSTOMER SATISFACTION EVALUATION SHEET 3 Page 1 of 6

የተሰጠ ምላሽ በቁጥር


መስፈርቶች በጣም ከፍተኛ አጥጋ ዝቅተ በጣም
ከፍተኛ ቢ ኛ ዝቅተ

1 የሚፈልጉትን ምርት በሚፈለገው ጊዜና መጠን 4 2 1 3 3
ይቀርብልዎታል?
2 የሚፈልጉትን ምርት በሚፈልጉት ጥራት ይቀርብልዎታል? 5 3 4 3 -
3 የሚፈልጉትን ምርት በሚፈልጉት ፍጥነት 4 1 3 3 3
ይቀርብልዎታል?
4 የሚፈልጉትን ምርት በሚፈልጉት ፍትነት 3 1 1 4 3
ይቀርብልዎታል?
5 የሚፈልጉትን ምርት ገበያውን መሰረት ባደረገ ዋጋ 2 6 5 1 -
ይቀርብልዎታል?
6 ለአዲስ የምርት ትእዛዝ ዋጋ በተገቢው ጊዜ ተሰርቶ 2 6 - 4 2
የሽያጭ አገልግሎት ያገኛሉ?
7 በተገቢው ወቅት ተገቢ ማስታወቂያ ይሰራል? - 6 1 3 2
8 ወኪሎችን የሚያበረታታ የዱቤ ሽያጭ ይደርጋል? 1 2 5 2 4
9 ወኪሎችን የሚየበረታታ የዋጋ ቅናሽ /Discount/ 1 2 5 2 4
ይደርጋል?
10 ሰራተኞች በአክብሮት አቀባበል ያደርጋሉ? 3 5 3 2 2
11 ሰራተኞች ግልጽና የተሟላ መረጃ ይሰጣሉ? 3 4 2 1 3
12 ሌላ አስተያየት ካለዎት ተብሎ ለተጠየቀው ጥያቄ የሚከተለው ተጨማሪ አስተያየት ተሰጥቷል፡፡
 የወቅቱን ዋጋ ባገናዘበ ሁኔታ ምርቱን ለነጋዴ ይቅረብ
 የምርት ጥራት የሸማቹን እና የደንበኛውን ፍላጎት መሰረት ያድርግ
 የምር አቀራረብ፣ የጭነት አገልግሎት አሰራር የተቀላጠፈ ይሁን
 የምርት አስተሻሸግ በተለያዩ ከለርና ሳይዝ ተደበላልቀው ይታቸጉ

APPROVAL: NAME: SIGNATURE: DATE:


Company Name: Document No::
ባህር ዳር ጨርቃ ጨርቅ አክሲዮን ማህበር OF/BDTSC/5-1-008
BAHIR DAR TEXTILE SHARE COMPANY
Title
Issue No.: Page No.:
: CUSTOMER SATISFACTION EVALUATION SHEET 3 Page 1 of 6

 የቦንዳዎች ክብደት ለሸክም እንዲያመች ክብደቱ ቢቀነስ


 ወቅቱን የጠበቀ የዲዛይን ማሻሻያ ቢደረግ
 በቦንዳው የታሸገ ምርት ቁጥር ጉድለትና ብልሽት ይሻሻል
 የተለያዩ ምርቶች ሲሸጡ ርክክብ በአዲስ አበባ ቢፈፀም
 የአስተሻሸግ፤ ሌቭል ማድረግ እና የብራንዲንግ ስራ ቢጠናከር
 የማስታወቂያ ስራ ይሰራ

መጠየቁን ከሞሉት አስራ አምስት ቀጥተኛ ተጠቃሚዎች ውስጥ በተራ ቁጥር አንድ ከተጠየቀው ደንበኛው
የሚፈልገውን ምርት በሚፈለገው ጊዜና መጠን ማቅረቡን በተመለከት ለተጠየቁት ጥያቄ 53.85% መላሾች ከአጥጋቢ
በላይ ነው ያሉ ቢሆንም ከ 46.15% በላይ መልስ ሰጭዎች ከአጥጋቢ በታች መሆኑን ገልጸዋል:: የአንድ ፋብሪካ ህልውና
የሚወሰነው የተለያዩ የምርት አይነቶችን በማምረት ለሁሉም ደንበኞች በተገቢው ጊዜ ማድረስ በመሆኑ የሚፈልገውን
ምርት በሚፈለገው ጊዜና መጠን የማቅረብ ተግባራችንን ማሻሻል ላይ ትኩረት ሰጥቶ መስራት ይገባል፡፡
ለመቆየት ለጥራት የሚሰጠው ትኩረት ከደነበኞች ፍላጎት አኳያ እንዲሆን ጠንካራ ስራ መስራት ያስፈልጋል፡፡

2/ የሚፈልገውን ምርት በምንፈልገው ጥራት ማቅረቡን በተመለከተ ደንበኞች ለተጠየቁት ጥያቄ 80.00% መላሾች
ከአጥጋቢ በላይ ነው ያሉ ሲሆን 20.00% በላይ መልስ ሰጭዎች ከአጥጋቢ በታች መሆኑን ገልጸዋል:: ከዚህ መገንዘብ
የሚቻለው ፋብሪካው የሚያመርተው ምርት ከደንበኞች ከሚነሳ የጥራት መስፈርት አኳያ አጥጋቢ አይደለም፡፡ አሁንም
ቢሆን ፋብሪካው ያለውን ስም ጠብቆ ለመቆየት ለጥራት የሚሰጠው ትኩረት ከደነበኞች ፍላጎት አኳያ እንዲሆን ጠንካራ
ስራ መስራት ያስፈልጋል፡፡

3/ ፋብሪካው የሚፈልገውን ምርት በሚፈልገበት ቦታ ያቀርባል? ተብለው ደንበኞች ለተጠየቁት ጥያቄ 57.14 % መላሾች
ከአጥጋቢ በላይ ነው ያሉ ሲሆን 42.86% በላይ መልስ ሰጭዎች ከአጥጋቢ በታች መሆኑን ገልጸዋል:: ከዚህ አንጻር
ፋብሪካው ምርቶችን ተደራሽ የሚያደርግባቸው አማራጭ ስልቶችን በመንደፍ መስራት ይጠበቅበታል፡፡ ደንበኞች በርቀት
ሆነው ግብይትን ከማካሄድ በቅርብና ፊት ለፊት የንግድ ልውውጥ ማድረግ ምቾት የሚሰጣቸው በመሆኑ ከዚህ አኳያ
በተለይም የሀገሪቱ የንግድ ማዕከል በሆነው አዲስ አበባና መርካቶ አካባቢ መጋዘን በማደራጀት የፋብሪካውን ምርቶች
ተደራሽ ማድረግ ለነገ የማይባል ተግባር ባለመሆኑ አቅም ሲፈቅድ ፈጣን ውሳኔ በመስጠት ተግባራዊ ማድረግ ይገባል፡፡

APPROVAL: NAME: SIGNATURE: DATE:


Company Name: Document No::
ባህር ዳር ጨርቃ ጨርቅ አክሲዮን ማህበር OF/BDTSC/5-1-008
BAHIR DAR TEXTILE SHARE COMPANY
Title
Issue No.: Page No.:
: CUSTOMER SATISFACTION EVALUATION SHEET 3 Page 1 of 6

4/ የሚፈልገው ምርት በሚፈለገው ፍጥነት ይቀርባል? ተብለው ደንበኞች ለተጠየቁት ጥያቄ 41.67% መላሾች ከአጥጋቢ
በላይ ነው ያሉ ሲሆን 58.33 % በላይ መልስ ሰጭዎች ከአጥጋቢ በታች መሆኑን ገልጸዋል:: በገበያ ባህሪ ዛሬ የተፈለገ ምርት
ነገ የሚኖረው ተፈላጊነት ተለዋዋጭ ስለሆነ የምርት ትዕዛዝ ተቀብሎ በሚፈለገው ፍጥነት ለደንበኛው ማድረስ ከሁሉም
ተግባሮች በላይ ጥረት የሚጠይቅ ሲሆን ይህን በማድረግ የሚገኘው ጥቅም ሆነ ጉዳት እጅግ ከፍተኛ በመሆኑ ምርትን
በሚፈለገው ፍጥነት ለደንበኛው ማቅረብ አለመቻል የሚያስከትለው ጉዳት ከፍተኛ በመሆኑ በዚህ ረገድ ከምርት እስከ
ደንበኛ መጋዘን ያለውን ቅብብሎሽ እና የሽያጭ አገልግሎት ፈጣን እና ቀልጣፋ ማድረግ ያስፈልጋል፡፡

5/ የሚፈለገውን ምርት ገበያውን መሰረት ባደረገ ዋጋ ይቀርባል? ተብለው ደንበኞች ለተጠየቁት ጥያቄ 92.86% መላሾች
ከአጥጋቢ በላይ ነው ያሉ ሲሆን 7.14% በላይ መልስ ሰጭዎች ከአጥጋቢ በታች መሆኑን ገልጸዋል::ዋጋ ለሀገራች ገበያ
ማለትም ዝቅተኛ ገቢ ላለው ህብረተሰብ ወሳኝ ጉዳይ በመሆኑ የምርት ጥራትን የደንበኞች ፍላጎትን መነሻን በማድረግ
ከጥራት እስታንዳርድ በመነሳት ለጥራት የሚወጣን ወጭ ሚዛን በመጠበቅ ተመጣጣኝና ለሸማቹ አቅም የሚሆን ዋጋን
መሰረት ያደረገ ምርት ማምረትና የስርጭት አውታርን አጭር በማድረግ የምርት መሸጫ ዋጋን ገበያውን በመከተል
ማስተካከል ይገባል፡፡4

6/ ለአዲስ የምርት ትእዛዝ ዋጋ በተገቢው ጊዜ ተስርቶ የሽያጭ አገልግሎት ይሰጣል ? ተብለው ደንበኞች ለተጠየቁት ጥያቄ
57.14% መላሾች ከአጥጋቢ በላይ ነው ያሉ ሲሆን 42.86% በላይ መልስ ሰጭዎች ከአጥጋቢ በታች መሆኑን
ገልጸዋል::በመሆኑም የነበረን ምርት ሲታዘዝም ሆነ አዲስ ምርት ሲታዘዝ ከማምረቻ ወጭና ከገበያ ሁኔታ ጋር የተገናዘበ
ዋጋ በመስራት ለደንበኞች ተገቢውን አገልግሎት መስጠት አስፈላጊነት በመገንዘብ በዚህ ስራ ላይ የሚሰሩ የኮሚቴ አባላት
ገበያን መሰረት ያደረገ የመሻጫ ዋጋ ለመተመን በትጋትና በቁርጠኝነት ሊሰሩ ይገባል፡፡
7/ በተገቢው ወቅት ተገቢ ማስታወቂያ ይሰራል? ተብለው ደንበኞች ለተጠየቁት ጥያቄ 58.33% መላሾች ከአጥጋቢ በላይ
ነው ያሉ ሲሆን 41.7% በላይ መልስ ሰጭዎች ከአጥጋቢ በታች መሆኑን ገልጸዋል:: ቀደም ብሎ የተሰራ ማስታወቂያ
በ 40.0% መላሾች በአዎንታ መታየቱ የተወሰነ ማስታወቂያ መስራት በሸማቹና በደበኞች ላይ የሚፈጥረው ተጽዕኖ ያሳያል፡፡
በመሆኑም በተገቢው ጊዜና ቦታ ማስታወቂያ መስራት አዳዲስ አከፋፋዮችን ወደ ስራ ለማስገባት፣ የፋብሪካው ምርቶች
በብዛትለመሸጥ፣ የገበያ ግለቱን ለመጨር እና ሸማቹ ህብረተሰብ ለባህርዳር ጨርቃ ጨርቅ አ.ማ ምርቶች ያለውን መረጃ ለማደስ ያለው
አስታዎጾዎ ከፈተኛ በመሆኑ በተገቢው ወቅት ተገቢ ማስታወቂያ መስራት ያስፈልጋ፡፡

APPROVAL: NAME: SIGNATURE: DATE:


Company Name: Document No::
ባህር ዳር ጨርቃ ጨርቅ አክሲዮን ማህበር OF/BDTSC/5-1-008
BAHIR DAR TEXTILE SHARE COMPANY
Title
Issue No.: Page No.:
: CUSTOMER SATISFACTION EVALUATION SHEET 3 Page 1 of 6

8/ ወኪሎችን የሚያበረታታ የዱቤ ሽያጭ ይደርጋል? ተብለው ደንበኞች ለተጠየቁት ጥያቄ 57.14.00% መላሾች ከአጥጋቢ
በላይ ነው ያሉ ሲሆን 42.86% በላይ መልስ ሰጭዎች ከአጥጋቢ በታች መሆኑን ገልጸዋል:: ይህም ማለት የምርት
ተደራሽነትን እና ተወዳዳሪ ሆኖ ገበያ ላይ ለመቆየት ከሚሰሩ ስራዎች የዱቤ ሽያጭ አንዱ ስልት በመሆኑ ለተመረጡ
ደንበኞች የተጀመረውን የዱቤ ሽያጭ አገልግሎት አጠናክሮ መቀጠል ይገባል፡፡

9/ ወኪሎችን የሚያበረታታ የዋጋ ቅናሽ /Discount/ ይደርጋል? ተብለው ለደንበኞች ለቀረበው ጥያቄ 57.14.00% መላሾች
ከአጥጋቢ በላይ ነው ያሉ ሲሆን 42.86% በላይ መልስ ሰጭዎች ከአጥጋቢ በታች መሆኑን ገልጸዋል:: በመሆኑም ብዙ ምርት
ሊገዙ ደነበኞች የዋጋ ቅናሽ ማድረግ ምርት የማንሳት አቅምን የሚያበረታታ እና የገበያና ስርጭት ወጭንም የሚቀንስ
በመሆኑ እና በሽያጭ መመሪያ ላይም የተፈቀደ በመሆኑ አክስዮን ማህበሩ በብዛት ለሚገዙ ደንበኞች የዋጋ ቅናሽ አሰራርን
ተግባራዊ ሊያደርግ ይገባል፡፡

10/ ሰራተኞች ለደንበኞች በአክብሮት አቀባበል ያደርጋሉ? ተብለው ደንበኞች ለተጠየቁት ጥያቄ 73.33% መላሾች ከአጥጋቢ
በላይ ነው ያሉ ሲሆን 26.67% በላይ መልስ ሰጭዎች ከአጥጋቢ በታች መሆኑን ገልጸዋል:: ይህ ምላሽ ከወገንተኝነት በጸዳ
ሁኔታ የተሰጠ ነው ተብሎ ቢወሰድ እንኳ በተለይ የሽያጭ ስራ በመልካም ስነምግባርና መስተንግዶ ማከናወን መሰረታዊ
የገበያ መርህ በመሆኑ ማናቸውም የማህበሩ ሰራተኞች ደንበኛ ንጉስ ነው የሚለውን መርህ በመከተል እና በጥብቅ የስራ
ዲስፕሊን አገልግሎት በመስጠት የደንበኞችን እርካታ 100 ፐርሰንት ለማድረስ ሁሉም አገልግሎት ሰጭዎች በቅንነትና
ትሀትና ደንበኞችን ማስተናገድ ይጠበቅባቸዋል፡፡

11/ ሰራተኞች ግልፅና የተሟላ መረጃ ይሰጣሉ? ተብለው ደንበኞች ለተጠየቁት ጥያቄ 69.23% መላሾች ከአጥጋቢ በላይ ነው
ያሉ ሲሆን 30.77% በላይ መልስ ሰጭዎች ከአጥጋቢ በታች መሆኑን ገልጸዋል:: ደንበኞች ሊያሟሏቸው የሚገቡ ቅድመ
ሁኔታዎች፣ የምርት አቅርቦት፣ የመሸጫ ዋጋና ሌሎች አገልግሎቶች ሲጠየቁ መረጃን ሳያንጠባጥቡ መስጠት ደንበኛውን
ከምልልስ እና ከተለያዩ ወጭዎች ያድናል፡፡ በሌላ በኩል ከደንበኛው የሚፈለግ መረጃን ለአብነትም የሽያጭ ውል፤ የምርት
ትዕዛዝ፤ የክፍያ ሰነድ፤ ውክልና እና የመሳሰሉ ቅድመ ሁኔታዎች በተቆራረጠ ጊዜ ሲጠየቁ የደንበኛን ስሜትና ምቾት የሚነሱ
መሆኑን ተገንዝቦ የተሟላ መረጃ ስራን ማዕከል ባደረገ ሁኔታ ከተገቢው ቦታ የሚሰጥበት አሰራር ሊጠናከር ይገባል፡፡

APPROVAL: NAME: SIGNATURE: DATE:


Company Name: Document No::
ባህር ዳር ጨርቃ ጨርቅ አክሲዮን ማህበር OF/BDTSC/5-1-008
BAHIR DAR TEXTILE SHARE COMPANY
Title
Issue No.: Page No.:
: CUSTOMER SATISFACTION EVALUATION SHEET 3 Page 1 of 6

በአጠቃላይ 15 መልስ ሰጭዎች ለ 11 ጥየቄዎች የሰጡት አሀዛዊ መረጃ እንደሚያሳየው የሁሉም አገልግሎቶች አሰጣጥ
ደረጃ ውጤት በአማካኝ 36.00% ከአጥጋቢ በታች ሲሆን 64.00% ብቻ ከአጥጋቢ በላይ ሆኗል፡፡ በመሆኑም የአገልግሎት
አሰጣጣችንን ለማሻሻል ከታች ደንበኞች ለሰጧቸው የመፍትሄ ሀሳቦች ትኩረት መስጠት ያስፈልጋል፡፡
1. ምርት የወቅቱን ዋጋ ባገናዘበ ሁኔታ ይቅረብ፣
2. የምርት ጥራት ችግር በደንበኛው ፍላጎት መሰረት ይስተካከል፣
3. አገልግሎት አሰጣጡ ይሻሻል፤ በተለይም በምርት ሽያጭ፣ መረከብና መጫን ሂደት ያሉ እንቅፋቶች ይስተካከሉ፤
4. የምርት አስተሻሸግ ላይ ጥናት በማድረግ በአስተሻሸግ፤ሌብል በማድረግ እና በሚታሸጉ ምርቶች ክብደት ላይ
ማስተካከያ ይደረግ፤
5. የቦንዳዎች ክብደት ለሰው ሸክም በሚሆንበት መጠን ይስተካከል፤
6. የዲዛይን ማሻሻያ ይደረግ፤ የፋብሪካው ስም ምርቱ ላይ ታትሞ ይወጣ ወይም ታግ ይጨመርበት፤
7. በቦንዳ የሚታሸጉ ምርቶች ጉድለት አንዳይኖር ተገቢ ጥንቃቄ ቢደረግ፤ ለብልሽትም እንዳይጋለጡ ሆኖ ይታሸጉ፣
8. ምርቶች ሲሸጡ በወኪል በኩል ርክክብ ለመፈጸም የሚደረገው አሰራር ቀልጣፋ ይሁን፣
9. የፋበሪካው ምርት አቅርቦት አዲስ አበባ ላይ ጭምር ይሁን
10. የማስታወቂያ ስራ ይሰራ፡፡

APPROVAL: NAME: SIGNATURE: DATE:

You might also like