SBD Goods FA Section

You might also like

Download as doc, pdf, or txt
Download as doc, pdf, or txt
You are on page 1of 6

ምዕራፍ :1 ¡õM 3 : ¾Ú[ታ ´`´` S[Í c”Ö[»

ክፍል 3

የጨረታዎች የግምገማ ዘዴና መስፈርቶች

ማውጫ

1. ፕሮፌሽናል፣ ቴክኒካልና ፋይናንሻል የብቃት መስፈርቶች........................................................................IV


2. አሸናፊ ጨረታን ስለመወሰን............................................................................................................V
3. ልዩ አስተያየት..........................................................................................................................VII
4. የበርካታ ግዥዎች ግምገማ.........................................................................................................VIII
5. አማራጭ ጨረታዎች................................................................................................................VIII

የማእቀፍ ስምምነት - ለዕቃዎችና ተያያዥ አግልግሎቶች - በገ/ኢ/ል/ቢሮ የተዘጋጀ (ቅጂ-2፣/2009)

ክፍል 3 III/IX
ምዕራፍ :1 ¡õM 3 : ¾Ú[ታ ´`´` S[Í c”Ö[»
[ማስታወሻ ግዥ ፈፃሚው አካል፤ ከዚህ በታች የተዘረዘሩት መስፈርቶች ለብቻቸው ተጫራቾችን ለመምረጥ
እንደመጨረሻ ተደርገው መቆጠር የለባቸውም]

¡õM 3 -የጨረታዎች ግምገማ ዘዴና መስፈርቶች


ይህ ክፍል የተጫራቾች መመሪያ ከሚለው ክፍል 1 እና የጨረታ ዝርዝር መረጃ ሠንጠረዥ ከሚለው ክፍል
2 ጋር ተጣምሮ ሲነበብ ግዥ ፈፃሚው አካል አንድ ተጫራች ተፈላጊዎቹ ብቃቶች ያሉት ስለመሆኑ
ለመገምገምና ለመወሰን መጠቀም ያለበትን ሁሉንም ነጥቦች፣ ዘዴዎችና መስፈርቶችን ይይዛል፡፡ ሌሎች
ማናቸውም ነጥቦች፣ ዘዴዎች ወይም መስፈርቶች ጥቅም ላይ አይውሉም፡፡

1. ፕሮፌሽናል፣ ቴክኒካልና ፋይናንሻል የብቃት መስፈርቶች


የሚከተሉት የብቃት መስፈርቶች በሁሉም ተጫራቾች ተፈፃሚ ይሆናሉ፡፡ ጨረታው የቀረበው በጊዜያዊ
ማህበር ከሆነ እነዚህ የብቃት መስፈርቶች በጊዜያዊ ማህበሩ በአጠቃላይ ተፈፃሚ ይሆናል፡፡ [ተስማሚ
በሆነው ፊደል ምልክት ይደረግ]
የተጫራች ፕሮፌሽናል ብቃትና አቅም (የተጫራቾች መመሪያ አንቀጽ 14)
(ለዚህ ጨረታ ተግባራዊ አይደረግም)
(ሀ)  ተጫራቹ በአሁኑ ወቅት ቢያንስ ቁልፍ ሠራተኞች ያሉት [አስፈላጊው ቁጥር ይግባ]
(ለ)  ከላይ በ“ሀ” ለተጠቀሱት ቁልፍ ሠራተኞች መካከል ቢያንሰ___ (የሙያቸውን
ዓይነት፤ ደረጃ፤ ወዘተ ይጠቀስ).
(ሐ)  ተጨማሪ መስፈርት ካለ ይጠቀስ
የተጫራቹ ቴክኒካል ብቃት፣ ክህሎትና የሥራ ልምድ (የተጫራቾች መመሪያ አንቀጽ 16)
(ሀ)  ተጫራቹ ባለፉት ሁለት (2) ዓመታት ቢያንስ ይህንን ጨረታ የሚመጥን 1 (አንድ)
ኮንትራቶች ማከናወኑን
(ለ)  ተጨማሪ መስፈርት ካለ ይጠቀስ
 ተጫራቹ የግብር ምዝገባ ቁጥር ወይም የግብር ከፋዩ መለያ ቁጥር ምዝገባ ምስክር ወረቀት
 ተጫራቹ አግባብነት ያለው የንግድ ዘርፉን የሚያመላክት የዘመኑን ግብር የከፈሉበት ንግድ ፍቃድ፡፡
ለሎት 1 እና ሎት 2 በዘርፉ ተለይቶ መምጣት ይኖርበታል
 ተጫራቹ በአቅራቢዎች ዝርዝር የተመዘገቡ መሆኑን የሚያመላክት የምስክር ወረቀት
 ተጫራቹ የተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዘገበበተ ሠርተፍኬት

 u}Ý^‹ }ð`V SG}w ¾}Å[Ñuƒ ¾Ú[ታ መልስ መስጫ ክፍል አራት (4) ሰነድ
 በተጫራች }ð`V SG}w ¾}Å[Ñuƒ ተጫራች የተወዳደረባቸው እቃዎች እና አገልግሎት ክፍል 6 ዝርዝር
የመወዳደሪያ ሀሳብ
 ካታሎግ
 ¾Ú[ታ ማስከበሪያ (CPO) ለሎት አንድ(01) እና ሎት ሁለት (02)
የተጫራቹ የፋይናንስ አቅም (የተጫራቾች መመሪያ አንቀጽ 15) (ለዚህ ጨረታ ተግባራዊ አይደረግም)

የማእቀፍ ስምምነት - ለዕቃዎችና ተያያዥ አግልግሎቶች - በገ/ኢ/ል/ቢሮ የተዘጋጀ (ቅጂ-2፣/2009)

ሰነድ: የጨረታዎች የግምገማ ዘዴና መስፈርቶች ክፍል-3 IV/5


ምዕራፍ :1 ¡õM 3 : ¾Ú[ታ ´`´` S[Í c”Ö[»

(ሀ)  ተጫራቹ ባለፉት ዓመታት [የአመታት ብዛት ይግባ] የነበረው አማካይ የተረጋገጠ
ዓመታዊ ገቢ ቢያንስ ለዚህ ጨረታ ከቀረበው የፋይናንስ መወዳደሪያ ሀሳብ ጊዜ
[አስፈላጊው ጊዜ ይግባ] የሚበልጥ መሆን አለበት፡፡ (ለዚህ ጨረታ ተግባራዊ አይደረግም)
(ለ)  ተጨማሪ መስፈርት ካለ ይጠቀስ

1. አሸናፊ ጨረታን ስለመወሰን

በመንግሥት ግዥ አዋጅና መመሪያ መሠረት የግዥ ፈፃሚው አካል ከሚከተሉት ሁለት መሰረታዊ
መምረጫ ዘዴዎች መካከል አንዱን በመጠቀም አሸናፊው ተጫራች የሚመርጠው፤ [ተስማሚ በሆነው
TKKl¾W œ_N §Y "X" ፊደል ምልክት ይደረግ]

(ሀ)በአንድ ኢንቨሎፕ እንዲቀርብ የተጠየቀ ለጨረታው ተቀባይነት ያለው ሕጋዊነት፣ ፕሮፌሽናል፣


ቴክኒካልና ፋይናንሻል ብቃቱ ተገምግሞ በጨረታ ሰነዱ የፍላጎት መግለጫ ዝርዝሩ የሚጠይቀውን መሠረታዊ
መመዘኛዎችን ካሟሉት ተጫራቾች መካከል አነስተኛ ዋጋ ያቀረበ ተጫራች በመምረጥ ይሆናል::
(ለ) በሁለት ኢንቨሎፕ እንዲቀርብ የተጠየቀ ለጨረታው ተቀባይነት ያለው ሙያዊ ቴክኒካዊ እና
ፋይናንሺያል ቴክኒካል መመዘኛው የፍላጎት መግለጫ ዝርዝሩ የሚጠይቀውን ካሟሉት ተጫራቾች
ግዥው የሚኖረውን ጠቀሜታ ወይንም ኢኮኖሚያዊ እሴት ሊወስኑ የሚችሉ መስፈርቶችን እና እያንዳንዱ
መስፈርት የሚኖረውን አንፃራዊ ክብደት በግልፅ በጨረታ ሰነዱ በተቀመጠው መስፈርቶች በመመስረት
ተገምግሞ በሚገኝ አጠቃላይ ድምር ውጤት ከፍተኛ ነጥብ ያገኘውን ተጫራች በመምረጥ ይሆናል::

ሀ. ዝቅተኛ ዋጋ የቀረበበት ጨረታ


1.1. በተጫራቾች መመሪያ አንቀጽ 23 መሠረት የጨረታው ሰነድ የሚጠይቃቸውን የሰነድ
ማስረጃዎች መሟላታቸው መመርመር አለበት፡፡
1.2. አስገዳጅ የሰነድ ማስረጃዎች በተገቢው መንገድ መሟላታቸው ከተረጋገጠ በኋላ የግዥ ፈፃሚው
አካል በጨረታ ሰነዱ ውስጥ ከተጠየቁት የፕሮፌሽን፣ የሕግ፣ የቴክኒክና የፋይናንሻል ተቀባይነት
ፍላጐቶች ጋር በማገናዘብ ጨረታው የተሟላ ወይም ያልተሟላ መሆኑ ይወሰናል፡፡
1.3. በመቀጠልም የግዥ ፈፃሚው አካል ጨረታው የተጠየቀውን የቴክኒክ ዝርዝር ፍላጐት ማሟላት
አለማሟላቱን ከመረመረ በኋላ ከቴክኒክ አንፃር ጨረታው ብቁ ነው ወይም አይደለም የሚለውን
ይወስናል፡፡
1.4. የግዥ ፈፃሚው አካል ጨረታው ውስጥ ያለመጣጣሞችና ግድፈቶች እንዳይኖሩ በመገምገም
ለተጠየቁት ፍላጐቶች መሠረታዊ መልስ የሚሰጥ ስለመሆኑ የማጣራት ሂደቱን ይቀጥላል፡፡
1.5. የግዥ ፈፃሚው አካል ጨረታው ከቁጥር እና ስሌት ስህተቶች የፀዳ መሆኑን ያጣራል፣ የቁጥርና
የስሌት ስህተቶች ካሉም ለተጫራቹ የታረመውን ስህተት በማሳወቅ እርማቶችን እና ጥቃቅን
ግድፈቶች ስለመቀበሉ በሦሰት የስራ ቀናት (3) ውስጥ እንዲያሳውቅ ይጠይቃል፡፡
1.6. በመጨረሻም የጨረታው ሕጋዊነት፣ ፕሮፌሽናል፣ ቴክኒካልና ፋይናንሻል ግምገማ ከተካሄደ በኋላ
የግዥ ፈፃሚው አካል በጨረታ ሰነዱ የተጠየቁትን ፍላጐቶች በመሠረታዊነት የሚያሟላና
በዋጋም ዝቅተኛ ሆኖ የተገኘን ጨረታ አሸናፊ እንዲሆን ያደርጋል፡፡

የማእቀፍ ስምምነት - ለዕቃዎችና ተያያዥ አግልግሎቶች - በገ/ኢ/ል/ቢሮ የተዘጋጀ (ቅጂ-2፣/2009)

ሰነድ: የጨረታዎች የግምገማ ዘዴና መስፈርቶች ክፍል-3 V/5


ምዕራፍ :1 ¡õM 3 : ¾Ú[ታ ´`´` S[Í c”Ö[»

ለ. ከፍተኛ ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ ውይም እሴት ሊወስኑ በሚችሉ መመዘኛዎች አነስተኛ የተገመገመ
ጨረታ ሰነድ በነጥብ አሰጣጥ ዘዴ ስለመወሰን
1.7. የተቴክኒካል የጨረታ ማወዳደሪያ ሐሳብን መገምገም
ጨረታው አስገዳጅ የሆኑትን የህግ፣ የፕሮፌሽን፣ የቴክኒክና የፋይናንስ መገምገሚያዎች ማሟላቱን ከተረጋገጠ
በኋላ የሁለት ደረጃ የግምገማና የነጥብ አሰጣጥ ዘዴ ይከናወናል፡፡ በተጫራቾች መመሪያ ንዑስ አንቀጽ 38.4
(ረ) አንቀጽ 38.5 መሠረት የግዥ ፈፃሚው አካል ጨረታዎችን በሚገመግምበት ጊዜ ከአነስተኛ ጨረታ ዋጋ
በተጨማሪ የሚከተሉትን የግምገማ መስፈርቶች በጠቀሜታ ቅደም ተከተል መሠረት ነጥብ በመስጠት
ጨረታውን ይመዝናል፡፡
(ሀ) ተጨማሪ የመገምገሚያ መስፈርቶችና ለእያንዳንዱ የተቀመጠው የምዘና ነጥብ እንደሚከተለው
ተቀምጧል፡፡

ለመስፈርቱ የተሰጠው ነጥብ መቶኛ


በቅደምተከ አንፃራዊ ክብደት
የመስፈርት መጠሪያ
ተል
%
1. መስፈርት I
2. መስፈርት II
3. መስፈርት III
4. መስፈርት IV
አጠቃሊይ ተጨማሪ መስፇርት (1+2+3+4)
I
II የጨረታ ዋጋ
III ጠቅሊሊ ዴምር (I+II) 100

ማሳሰብያ፤ለቴክኒክ የተሰጠው ነጥብ ወደ 100% የሚቀየር ሲሆን 70% እና ከዚያ በላይ ያገኙ ተጫራቾች ለፋይናንሻል
ውድድር ያልፋሉ፤አሸናፊ የሚለየው የቴክኒካል ከፍተኛውን ውጤት ከ 50% በመቀየር እና የፋይናንስ ግምገማውን
ዝቅተኛ ዋጋ የቀረበውን 50% ድምር ከፍተኛ ውጤት ያገኘ ነው።
(ለ) የግዥ ፈፃሚው አካል ማንኛውም ተጨማሪ መስፈርት የሚገመግመው በሚከተለው የነጥብ ምዘና መሠረት
ነው፡፡
ምዘና መግለጫ
1ዐ እጅግ በጣም ከተጠየቀው መሥፈርት በላይ የሆነ፣ በጣም ጠቃሚና በጣም አስፈላጊ
ጥሩ የሆነ
9 በጣም ጥሩ ከመስፈርት በላይ የሆነ፣ ለፍላጐታችን ጠቃሚ የሆነ
7-8 ጥሩ መስፈርቶችን በሙሉ ያሟላ
5-6 አጥጋቢ አብዛኛዎቹ መስፈርቶችን በተሻለ አኳኋን ያሟላ፣ የተወሰኑ ወሳኝ
ያልሆኑ መስፈርቶችን ያላሟላ ሊሆን ይችላል
3-4 ደካማ የተጠየቁትን መስፈርቶች በዝቅተኛ ደረጃ የሚያሟላ
1-2 በጣም ደካማ ሁሉም ሳይሆን የተወሰኑትን መስፈርቶች ብቻ ያሟላ ወይም ወሳኝ
የሆኑትን መስፈርቶች ያላሟላ

የማእቀፍ ስምምነት - ለዕቃዎችና ተያያዥ አግልግሎቶች - በገ/ኢ/ል/ቢሮ የተዘጋጀ (ቅጂ-2፣/2009)

ሰነድ: የጨረታዎች የግምገማ ዘዴና መስፈርቶች ክፍል-3 VI/5


ምዕራፍ :1 ¡õM 3 : ¾Ú[ታ ´`´` S[Í c”Ö[»
0 የማያሟላ በማንኛውም መንገድ የተጠየቁትን መስፈርቶች ያላሟላ

የእያንዳንዱ የቴክኒክ መስፈርት ከላይ በተቀመጠው መሠረት የምዘና ነጥብ ይሰጣቸዋል፡፡ የምዘና ውጤት
የሚሰላው የምዘና ነጥቡን ከእያንዳንዱ መስፈርት ጋር በማባዛት ነው፡፡ በዚሁ የአሠራር መንገድ መሠረት
የሚገኘው ውጤት የጨረታዎችን ደረጃ ለማውጣት ያገለግላል፡፡

ሁለት ተጫራቾች እኩል ነጥብ በሚያገኙበት ጊዜ የሀገር ውስጥ ምርቶችን ወይም አገልግሎቶች ለሚያቀርብ
ተጫራች ቅድሚያ ይሰጣል፡፡
የግዥ ፈፃሚው አካል ተጫራቾች እኩል የግምገማ ውጤት በሚያገኙበት ጊዜ ለመለየት እንዲቻል በተወሰኑ
ነጥቦች ላይ የመወዳደሪያ ሀሳብ እንዲያቀርቡ መጠየቅ ይቻላል፡፡

ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሀሳብ እንዲያቀርቡ ተጠይቀው ሳያቀርቡ ቢቀሩ ወይም በድጋሚ ባቀረቡት
የመወዳደሪያ ሀሳብ አሁንም እኩል የግምገማ ነጥብ ቢያገኙና አሸናፊውን ተጫራች መለየት ሳይቻል ሲቀር
እስከተቻለ ድረስ ተጫራቾቹ በተገኙበት አሸናፊው ተጫራች በዕጣ የሚለይ ይሆናል፡፡

2. ልዩ አስተያየት

የግዥ ፈፃሚው አካል በተጫራቾች መመሪያ አንቀጽ 35 መሠረት በኢትዮጵያ ለሚመረቱ ምርቶች ልዩ
አስተያየት እንዲደረግ የፈቀደ ከሆነ ለጨረታዎች ውድድር ዓላማ ሲባል ብቁ ጨረታዎች በሚከተሉት መልክ
ይመደባሉ፡፡

(ሀ) ምድብ “ሀ” - በተጫራቾች መመሪያ አንቀጽ 35.3 መሰረት በሀገር ውስጥ ለተመረቱ ዕቃዎች
የቀረቡ ጨረታዎች
(ለ) ምድብ “ለ” - ሌሎች ጨረታዎች
በአንቀጽ 35.3 መሠረት ምድብ “ለ” ተብለው በተለዩት ተጫራቾች ዋጋ ላይ 15% ይጨመራል፡፡

3. የበርካታ ግዥዎች ግምገማ

በተጫራቾች መመሪያ ንዑስ አንቀጽ 38.6 መሠረት ግዥ ፈፃሚው አካል አንድ ወይም ከአንድ በላይ የሆኑ
ኮንትራቶችን ለተጫራቾች መስጠት ይችላል፡፡ አፈፃፀሙም እንደሚከተለው ይሆናል፡፡

(ሀ) በተጫራቾች ንዑሰ አንቀጽ 12.10 መሠረት ቢያንስ ተፈላጊውን መቶኛ ፍላጐትና መጠን ያሟሉትን
ኮንትራቶች ወይም የሎት (lot) ግዥዎችን መገምገም፣
(ለ) ግምት ውስጥ የሚገቡ፣
የመገምገሚያ መስፈርቶችን በማሟላት ዝቅተኛ ዋጋ የቀረበበት እያንዳንዱ ሎት (lot) ግዥ፣
በእያንዳንዱ የብዙ ምድብ (lot) ግዥ የቀረበው የዋጋ ቅናሽና የአፈፃፀም ዘዴዎች፣
በአቅርቦትና አፈፃፀም አቅም ዙሪያ ሊኖሩ የሚችሉትን ውስንነቶችና ችግሮች ግምት ውስጥ በማስገባት
የሚኖረው የተሻለና ከፍተኛ ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ፡፡

4. . አማራጭ ጨረታዎች

የማእቀፍ ስምምነት - ለዕቃዎችና ተያያዥ አግልግሎቶች - በገ/ኢ/ል/ቢሮ የተዘጋጀ (ቅጂ-2፣/2009)

ሰነድ: የጨረታዎች የግምገማ ዘዴና መስፈርቶች ክፍል-3 VII/5


ምዕራፍ :1 ¡õM 3 : ¾Ú[ታ ´`´` S[Í c”Ö[»
በጨረታ ዝርዝር መረጃ ሠንጠረዥ 20.1 መሠረት አማራጭ ጨረታዎች የተፈቀዱ ከሆነ የሚገመገሙት
እንደሚከተለው ይሆናል

የማእቀፍ ስምምነት - ለዕቃዎችና ተያያዥ አግልግሎቶች - በገ/ኢ/ል/ቢሮ የተዘጋጀ (ቅጂ-2፣/2009)

ሰነድ: የጨረታዎች የግምገማ ዘዴና መስፈርቶች ክፍል-3 VIII/5

You might also like