Download as pdf or txt
Download as pdf or txt
You are on page 1of 8

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ትምህርት

ፅፈት ቤት የ6ኛ ክፍል የ2 ኛው ወሰነ ትምህርት የአከባቢ ሳይንስ ሞዴል ፈተና

ግንቦት 2016 ዓ.ም

የጥያቄ ብዛት ፡- 40 የተፈቀደዉ ሰዓት ፡- 1:00 ሰዓት

አጠቃላይ ትዕዛዝ

ይህ አከባቢ ሳይንስ ፈተና ነዉ፡፡በዚህ ፈተና ዉስጥ 40 ጥያቄዎች ተካተዋል ፤ ለእያንዳንዱ


ጥያቄ ትክክለኛ መልስ የሆነዉን አማራጭ የያዘዉን ፊደል በመምረጥ መልስ መስጫ በተሰጠዉ
ወረቀት ላይ በማጥቆር መልስ ይሰጣለል፡፡በፈተና ላይ የተሰጡትን ትዕዛዞች በጥንቃቄ በማንበብ
ፈተናዉን መስራት ይጠበቅባችኋል ፡፡ መልስ የሚሰጠዉ ከፈተናዉ ጋር በተያያዘዉ የመልስ መስጫ
ወረቀት ላይ ነዉ ፤በመልስ መስጫ ላይ ትክክለኛዉ መልስ የሚጠቆረዉ በእርሳስ ብቻ ነዉ ፤
ትክክለኛዉን መልስ በማጥቆር ሲሰራ ለማጥቆር የተፈቀደዉ ቦታ በሙሉ በሚታይ መልኩ በደንብ
መጥቆር አለበት ፤የጠቆረዉን መልስ ለመቀየር ቢፈለግ በፊት ጠጠቆረዉን በደንብ በማጥፋት መፅዳት
አለበት ፡፡

ፈተናዉን ሰርቶ ለመጨረስ የተፈቀደዉ ሰዓት 1:00 ሰዓት ነዉ፡፡ ፈተናዉን ሰርቶ ለመጨረስ
የተሰጠዉ ሰዓት ሲያበቃ ለመስሪያነት የምጠቀምበትን የመፃፊያ እርሳስ ማስቀመጥ እና ፈተናዉን
መስራት ማቆም አለብን ፡፡ፈተናዉ እንዴት እደሚሰበሰብ በፈታኙ/ኟ እሰከሚነገር ድረስ በቦታችሁ
ተቀምጣችሁ መጠበቅ አለባችሁ፡፡

መኮረጅ ወይም በፈተና ሰዓት የፈተናዉን ህግ የማያከብር ተፈታኝ ፈተናዉ አይያዝለትም ፤


ፈተናዉን እንዳይፈተኑም ይደረጋል፡፡

ፈተናዉን መስራት ከመጀመራችሁ በፊት መልስ መስጫዉ ላይ መሙላት የሚገባዉን መረጃ ሁሉ


በጥንቃቄ መሞላት አለበት፡፡

ፈተናዉን መስራት ጀምሩ ሳይባል መጀመር ክልክል ነዉ


መመሪያ:-ከተራቁጥር 1-40 የሚገኙትን ጥያቄዎች በጥሞና ካነበባችሁ በኋላ ለእያንዳንዱ ጥያቄ
ከቀረቡት አራት አማራጮች መካከል በይበልጥ ተስማሚ የሆነውን መልስ በመምረጥ በመልስ
መስጫው ወረቀት ላይ አጥቁሩ።

1.ከሚከተሉት ውስጥ አንፃራዊ መገኛን የማይገልፀው የቱ ነው?

ሀ/ሰሜን ሐ/ምስራቅ

ለ/ደቡብ መ/ኬንትሮስ

2.በካርታ ወይም በሉል ላይ ከምድር ወገብ በስተሰሜን ስንት ትይዩ መስመሮች ይገኛሉ?

ሀ/ 90 ሐ/ 60

ለ/180 መ/360

3…………..የቀላል ማሽን አይነት ሲሆን አንድን ነገር ለሁለት ለመክፈል የሚረዳ ቀላል
የመኪና አይነት ነው፡፡

ሀ/ሽብልቅ ሐ/ሽክርክሪት

ለ/ዘንባይ ወለል መ/መፈንቅል

4.በተለመደው የወር አበባ የዑደት ህግ መሰረት አንዲት ሴት ታህሳስ 20 ቀን የወር አበባ


ብታይ የውፃት ቀኗ መቼ ይሆናል?

ሀ/ታህሳስ 30 ሐ/ታህሳስ 28

ለ/ጥር 4 መ/ ጥር 14

5.ከሚከተሉት የልብ ክፍሎች ውስጥ በኦክስጅን የበለፀገ ደም ከሳንባ ከፑልመናሪ ቬይን


አማካኝነት የሚቀበለው የትኛው ነው?

ሀ/ ቀኝ ተቀባይ ልበ ገንዳ ሐ/ቀኝ አቀባይ ልበ ገንዳ

ለ/ግራ ተቀባይ ልበ ገንዳ መ/ግራ አቀባይ ልበ ገንዳ


6.ኢትዮጵያን በስተሰሜን በኩል የሚያዋስናት የምስራቅ አፍሪካ ሀገር ማን ይባላል?

ሀ/ኬንያ ሐ/ኤርትራ

ለ/ጂቡቲ መ/ሶማሊያ

7.ከሚከተሉት ሀገራት መካከል የባህር በር ያለው ሀገር የቱ ነው?

ሀ/ማላዊ ሐ/ሩዋንዳ

ለ/ኢትዮጵያ መ/ማዳጋስካር

ከተራ.ቁ 8-9 ያሉትን ጥያቄዎች ከታች ያለውን ምስል በመመልከት መልሱ፡፡

50° 40° 30° 20° 10° 0° 10° 20° 30° 40° 50°

40°

•ሐ 30°

20°

•መ 10°

10°

•ለ •ሀ 20°

30°

40°

8. 20° ደቡብ ኬክሮስ እና 10° ምዕራብ ኬንትሮስ የሚያሳየው ፊደል የቱ ነው?

ሀ.-ለ- ሐ.-ሐ-

ለ. -መ- መ.-ሀ-
9.ፊደል -መ- የሚያመለክተው ቦታ ፊጹማዊ መገኛ በዲግሪ ከተቀመጠው ትክክል የሆነው የቱ
ነው?

ሀ.10° ደቡብ ኬንትሮስና 10° ምስራቅ ኬክሮስ

ለ. 10° ሰሜን ኬንትሮስ እና 10° ምዕራብ ኬክሮስ

ሐ.10° ሰሜን ኬክሮስ እና 10° ምስራቅ ኬንትሮስ

መ.10° ሰሜን ኬክሮስ እና 10 ምዕራብ ኬንትሮስ

10.ዓለም አቀፋዊ የመረጃ ሥርዓት መገኛ ቴክኖሎጂ (ጂፒኤስ) ለምን ይጠቅማል?

ሀ/አንድን ነገር አቅጣጫ ለማወቅ ሐ/የአንድን ሥፍራ መገኛ ለማወቅ

ለ/ፍጥነት ለመቆጣጠር መ/ሁሉም መልስ ናቸው።

11.ከሚከተሉት የጉልበት ምንጮች ውስጥ አንዱ ታዳሽ ያልሆነ የጉልበት ምንጭ የቱ ነው?

ሀ/የውሃ ጉልበት ሐ/የንፋስ ጉልበት

ለ/የፀሐይ ጉልበት መ/የተፈጥሮ ነዳጅ

12.የሟሙ ጠጣሮችን ከአሟሚው ፈሳሽ የምንለይበት የድብልቅ መለያ ዘዴ የቱ ነው?

ሀ/ንጥረት ሐ/ጥሊያ

ለ/ትነት መ/ቀረራ

13.የድንቅነሽ (ሉሲ) ቅሪት አካል የተገኘበት የምስራቅ አፍሪካ ሀገር የትኛው ነው?

ሀ/ኤርትራ ሐ/ጂቡቲ

ለ/ኢትዮጵያ መ/ኬንያ
14.ከሚከተሉት መተግበሪያዎች መካከል የአንድን አከባቢ የገበያ ትስስር ለመፈለግ
የምንጠቀምበት መተግበሪያ የቱ ነው?

ሀ/ጂፒኤስ ሐ/ጎግል ካርታ

ለ/ጎግል ኧርዝ መ/ኮምፓስ

15.ከሚከተሉት የደም ህዋሶች መካከል ኦክስጅንን ለመሸከም የሚያስችል ሄሞግሎቢን የሚባል


ሃመልሚል ያላቸው የትኞቹ ናቸው?

ሀ/ቀይ የደም ህዋሶች ሐ/ፕሌትሌትስ

ለ/ነጭ የደም ህዋሶች መ/ፕላዝማ

16.ኦክስጅንና አልሚ ምግቦች ለሰውነታችን ህዋሶች የሚያሰራጩበት ሂደት ምን ይባላል?

ሀ/ሥርዓተ ልመት ሐ/የደም ዑደት

ለ/ሥርዓተ ትንፈሳ መ/ሁሉም

17.ከሚከተሉት ልዩ ቁሶች መካከል ድብልቅ የሆነው የትኛው ነው?

ሀ/ውሃ ሐ/ጨው

ለ/ስኳር መ/ወተት

18.ከሚከተሉት የሥርዓተ ትንፈሳ ክፍሎች ውስጥ ቅርፁን በመቀያየር ሳንባችን በትክክል


እንዲተነፍሱ የሚያስችለው የቱ ነው?

ሀ/ሰርን ሐ/ድልሺ

ለ/የአፍ ወና መ/ትንከረት

19. .ከምድር ወገብ በስተ ደቡብ የሚገኙት የምሥራቅ አፍሪካ ሀገራት ዝናብ
ሚያገኙት ከ……………… ባሉትወራትነው፡፡
ሀ. ሰኔ እስከ መስከረም ሐ. ከህዳር እስከ መጋቢት
ለ. ታኅሣሥ እስከ የካቲት መ. ጥር እስከ መጋቢት
20.ዓመታዊ አማካይ የዝናብ መጠናቸው ከ250ሚ.ሜ በታች የሆኑ ቦታዎች ……..ተብለው
ይጠራሉ፡፡

ሀ.የሣር ምድር ሞቃታማ የአየር ንብረት ክልል


ለ.የበረሃ አየር ንብረት ክልል
ሐ.የሐሩር ሞቃታማ የባሕር ዳርቻዎች
መ.የደጋ የአየር ንብረት ክልል

21.በምስራቅ አፍሪካ ወርቅ፣ብር፣ብረት፣የድንጋይ ከሰል፣ጨው፣እምነ-በረድ፣ሶዳአሽ፣


ሸክላአፈር ማዕድናት የምትታወቀው የምስራቅ አፍሪካ ሀገር ማን ናት?
ሀ.ኢትዮጲያ ሐ.ኤርትራ
ለ.ሶማሊያ መ. ኬንያ

22. ካምቢሶል እና ላቪሶል የአፈር አይነት የሚገኝበት ሀገር?


ሀ.ኢትዮጲያ ለ.ሶማሊያ
ሐ.ኤርትራ መ.ኬንያ

23.የአፈር መሸርሸር መከላከያ ዘዴ የሆነው የቱ ነው?


ሀ.ድነና ለ.ዳግምድነና
ሐ.የእርከንስራ መ.ሁሉም

24..ወደ ህንድ ውቅያኖስ የማይገባው የምስራቅ አፍሪካ ወንዝ የቱ ነው?


ሀ. ሩቩማ ለ. ታና
ሐ. ናይል መ. ገናሌ

25.የምስራቅ አፍራካ ተገቢ ያልሆነ የማዕድናት አጠቃቀም ላይ የሚያስከትለው


አሉታዊ ተፅዕኖ ያልሆነው የቱ ነው?
ሀ.ለአፈር እና ውሀ ጥበቃ ይመቻል
ለ.የአየር እና የውሀ መበከል ያስከትላል
ሐ.የመሬት አቀማመጥን ያበላሻል
መ.የግብርና ምርት እንዲቀንስ ያደርጋል

26.በምስራቅ አፍሪካ የማዕድናት አጠቃቀም ተግዳሮት ያልሆነው የቱ ነው?


ሀ.ማዕድናት ከከርሰ ምድር ለማውጣት በቂ የሆነ መሰረተ ልማት አለመኖር
ለ.የማዕድን ቁፋሮ የቴክኖሎጂ እጥረት
ሐ.አነስተኛ የሀገር ውስጥ ፍላጎት
መ.መልሱ አልተሰጠም
27.ተገቢ ያልሆነ የተፈጥሮ ሀብት አጠቃቀም የሆነው የቱ ነው?
ሀ. በወንዞች አካባቢ ዛፍ መትከል
ለ. ባዮ ጋዝ መጠቀም
ሐ.በቤት ውስጥ ውሀን በአግባቡ መጠቀም
መ. የተፈጥሮ ሀብቶችን ያለገደብ መጠቀም

28 .ከምስራቅ አፍሪካ ሀይቆች በጥልቀቱ የመጀመሪያው የቱ ነው?


ሀ. ኬቩ ለ. ማላዊ
ሐ.ታንጋኒካ መ.ኤድዋርድ

29.በምስራቅ አፍሪካ አነስተኛ የህዝብ ቁጥር ያላት ሀገር ማን ናት


ሀ.ኢትዮጲያ ለ.ሞሪሽየስ
ሐ.ሲሸልስ መ.ሪዩኒየን

30.ከሚከተለት ውስጥ የማዕድን ጠቀሜታ ያልሆነው የቱ ነው?


ሀ. የውጭ ምንዛሬ መጨመር ለ.ገቢ መቀነስ
ሐ.የሥራ አጥ ቁጥር መቀነስ መ.የገቢ ምኝጭ መሆን Commented [A1]:

31 .የኩሽ መንግስት የመጀመሪያ ከተማ ማን ይባላል?


ሀ. ናፓታ ለ.አክሱም
ሐ .ሜሮይ መ.ሁለም

32. ከሚከተለት ውስጥ መንፈሳዊ ቅርስ የሆነው የቱ ነው?


ሀ. የሀዘን ስርዓት ለ.በሀይማኖት ስፍራ የሚታዩ ትርኢቶች
ሐ. ክብረ በዓላት መ. ሁለም

33. ከሚከተለት ውስጥ በርዝመቱ ትልቁ የአለማችን ንፁህ ሀይቅ የቱነው


ሀ.ማሊዊ ለ.ቪክቶራያ
ሐ.ታንጋኒካ መ. ጣና

34. በምስራቅ አፍሪካ ሁለተኛው ስልጣኔ የ……………. ስልጣኔ በመባል ይታወቃል፡፡


ሀ. የኑቢያስልጣኔ ለ.የኩሽስልጣኔ
ሐ. የአክሱምስልጣኔ መ. ሁሉም

35. የቪክቶርያፏፏቴ በ ……………ወንዝ የተፈጠረ የአፍሪካ ትልቁ ፏፏቴ ነው፡፡


ሀ.ሩቩማ ለ.ናይል
ሐ.ታና መ.በዛምቤዚ
36.ከቦታ ቦታ በሚዘዋወሩ የዱር እንሰሳት የሚታወቀው የምስራቅ አፍሪካ ስነ-ምህዳር የቱ ነው?
ሀ. የደንከልበረሀ ሐ. የቫሩንጋተራራ
ለ.ማሣይማራፓርክ መ. የሰሜንተራሮችብሄራዊፓርክ

37. ከሚከተሉት ሀገራት መካከል ከደንከል በረሀ ጋር የማይዋሰነው ሀገር የቱ ነው?


ሀ.ሱዳን ለ.ጀቡቲ
ሐ. ኢትዮጵያ መ.ኤርትራ

38.ኤችአይቪ ኤድስ የሚያጠቃው የደም ህዋስ የቱ ነው?


ሀ.ቀይ የደም ህዋስ ለ.ነጭ የደም ህዋስ
ሐ.ፕላትሌቶች መ.መልሱ አልተሰጠም

39.በ አልኮል ውስጥ የሚገኝ ኬሚካል ምን ይባላል?


ሀ.ኒኮቲን ለ.ሞርፊን
ሐ.ካቴኒን መ.ኢታኖል

40.ለድርቅ ተጋላጭ የሆነ የምስራቅ አፍሪካ ሀገር የቱ ነው?


ሀ.ኢትዮጲያ ለ.ሶማሊያ
ሐ.ጅቡቲ መ.ሁሉም

You might also like