Download as pdf or txt
Download as pdf or txt
You are on page 1of 2

በአዋጁ በተጀመረው የቤት ኪራይ ውል አከራዮች ከፍተኛ ጭማሪ

እያደረጉ መሆኑ ተከራዮችን አስጨንቋል - ሪፖርተር - Ethiopian


Reporter
ethiopianreporter.com/130588

June 19, 2024

ማኅበራዊበአዋጁ በተጀመረው የቤት ኪራይ ውል አከራዮች ከፍተኛ ጭማሪ እያደረጉ መሆኑ ተከራዮችን
አስጨንቋል

በአዋጁ በተጀመረው የቤት ኪራይ ውል አከራዮች ከፍተኛ ጭማሪ እያደረጉ መሆኑ


ተከራዮችን አስጨንቋል

‹‹በተከራይና አከራይ መካከል ስምምነት ከሌለ አንመዘግብም››

የቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የቤት ኪራይ ውል ምዝገባ በሁሉም ወረዳዎች ማካሄድ ከጀመረ በኋላ፣ አከራዮች
ከፍተኛ የዋጋ ጭማሪ እያደደረጉ በመሆናቸው ተከራዮች ከአቅማቸው በላይ መሆኑንና መጨነቃቸውን እየገለጹ
ነው፡፡

መንግሥት የመኖሪያ ቤት የኪራይ ዋጋ መናርን ለማስተካከል በመጋቢት ወር 2016 ዓ.ም. ‹‹የመኖሪያ ቤት


ኪራይ ቁጥጥርና አስተዳደር›› አዋጅ ማፅደቁ ይታወሳል፡፡ አዋጁ የተመዘገበ የቤት ኪራይና ውል የተፈጸመበት
የኪራይ ዋጋ ለሁለት ዓመት ይፀናል ይላል፡፡

በአዋጁ መሠረት የከተማ አስተዳደሩ የውል ምዝገባ ማካሄድ የጀመረ ሲሆን፣ ምዝገባው በአንድ ወር ውስጥ
እንደሚጠናቀቅ ተመላክቷል፡፡ ይሁንና በርካታ አከራዮች ለሚቀጥሉት ሁለት ዓመታት የኪራይ ዋጋ መጨመር
አንችልም በማለት አሁን ከፍተኛ የኪራይ ዋጋ ጭማሪ እያደረጉ መሆናቸውን ቅሬታ አቅራቢዎች ይናገራሉ፡፡

ከቅሬታ አቅራቢዎች መካከል ላፍቶ አካባቢ የሚገኝ ኮንዶሚኒየም ተከራይታ የምትኖርና ስሟን መግለጽ
ያልፈለገች ተከራይ፣ የውል ምዝገባ ከተጀመረ በኋላ 20 ሺሕ ብር ትከፍልበት የነበረው ቤት 30 ሺሕ ብር
እንድትከፍል እንደተነገራት ገልጻለች፡፡

በተመሳሳይ በፊት ይከፍሉት ከነበረው የቤት ኪራይ ዋጋ በእጥፍ የተጨመረባቸው ሌላ ግለሰብ፣ ይህ የተፈጠረው
በሕጉ ላይ ባለው ክፍተት ምክንያት ነው ብለዋል፡፡ ‹‹አዋጁ የኪራይ ዋጋውን በካሬ ሜትር መክፈል እንዲቻል
ቢደነግግ ወይም የኪራይ ውሉን ስንፈራረም አንድ ተከራይ መጨመር ያበትን ዋጋ መጠን ቢያሳውቅ አሁን
የሚነሱ ቅሬታዎች አይቀርቡም፤›› ነበር ብለዋል፡፡ አሁን የተነሳው ቅሬታ ወደፊትም በአከራይና ተከራይ መካከል
አለመግባባት እንዲፈጠር ምክንያት ይሆናል ሲሉ ገልጸዋል፡፡

‹‹የመኖሪያ ቤት ኪራይ ቁጥጥርና አስተዳደር›› አዋጅን ተግባራዊ ለማድረግ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር
የመኖሪያ ቤት ኪራይ ቁጥጥርና አስተዳደር መመርያ ቁጥር 7/2016 አውጥቷል፡፡ የጽሕፈት ቤቱ ውል መዝጋቢ
ባለሙያ አከራይና ተከራይ ውሉን በፈቃዳቸው የሚዋዋሉ መሆኑን ማረጋገጥ እንደሚኖርበት በመመርያው
ተመላክቷል፡፡

1/2
በተጨማሪም አከራይና ተከራይ ለምዝገባ የሚያቀርቡት የመኖሪያ ቤት ኪራይ ውል የዋጋ ጭማሪ ካለው፣
የከተማ አስተዳደሩ የቤቶች ልማትና አስተዳዳር ቢሮ በሚያወጣው የዋጋ ጭማሪ ተመን መሠረት የተደረገ
መሆኑን የወረዳ ጽሕፈት ቤት እንደሚያረጋግጥ የተደነገገ ሲሆን፣ በተመዘገበው ውል ከሠፈረው የመኖሪያ ቤት
ኪራይ ዋጋ በላይ ክፍያ ሲፈጸምም ለወረዳው ጽሕፈት ቤት በአካል በመቅረብ፣ በስልክ ወይም በሌላ
በማናቸውም የመገናኛ ዘዴዎች ለተቆጣጣሪው አካል ቅሬታውን ሊያቀርብ እንደሚችል ተገልጿል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ የሕዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር ወ/ሮ የንጋትኮከብ
አባቡ፣ የውል ምዝገባው የሚካሄደው በአከራይና በተከራይ ስምምነት ብቻ መሆኑን ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡
‹‹ምዝገባው የሚካሄደው አከራይና ተከራይ በተስማሙበት ነው፣ ካልተስማሙ ምዘገባውን አናካሂድም፤››
ከማለት ባለፈ ቢሮው ሌላ መፍትሔ ይኑረው ወይም አይኑረው ያሉት ነገር የለም፡፡

ይመዝገቡ

2/2

You might also like