አሊ መስጅድ ምን ተፈጠረ

You might also like

Download as txt, pdf, or txt
Download as txt, pdf, or txt
You are on page 1of 1

አሊ መስጅድ ምን ተፈጠረ?

==== ⨳ === ⨳ ==== ⨳ =====ኑራው ኢሽቀኛው


*
ነገር በምሳሌ ይገባልና በምሳሌ ላስረዳ ... ቤተል ተቅዋ መስጅድ መፈንቅለ ኮሚቴ አስበሃል እንበል ... ከዛ ምን ታደርጋለህ
መሰለህ? .... የመስጅዱን ጀምአ ኻዲሞች የሚመስል ፒፕስ ታሰራለህ ... ከዛ ብዙ ጀምዐ የማይኖርበትን አሳቻ ሰዓት ትጠብቅና
መጥረጊያ ይዘህ ቤተል መስጂድ ትገባለህ ... ከዛ ቪዲዬ ስታንድ ባይ አድርገህ ታዘጋጃለህ ... የመስጂዱ ኻዲሞች መጥተው "ምን
እያደረግክ ነው?" ሲሉህ ... ሸሊላቱን እያቀለጥከው "እኛ ሙስሊሞች ነን ማፅዳት መብታች ነው " እያልክ ትፎክራለህ ... ረብሻ እና
ወከባ ታስነሳለህ ... "እዩን ልናፀዳ ከለከሉን" እያልክ ቀድመህ ባዘጋጀኸው ካሜራ ትቀርፃለህ ... ከዛ ትፈናከታለህ ... ከተመቸህ
በከተር እና ጩ-ቤ ተው ያለህን አህባብ ትወጋለህ ... ከዛ "ስናፀዳ ከልክለውን ነው" ብለህ ትከሳለህ ... የመጅሊሱን ሽፋን ተጠቅመህ
ጀምዐውን ታሳስራለህ ... ከዛ ቤተል መስጂድን ትረከባለህ ...
*
ዛሬ በአሊ መስጅዲ የሰሩት የሁከት ድራማ ይሄ ነው ... ባለፉት ቀናት የመስጂዱ ወጣቶች የደም ልገሳ እና የበጎ አድራጎት ስራዎችን
በማድረጋቸው የተበሳጨው እና መስጂድ ያከራዩት ሱቅ ይመስል አስረክቡን ብሎ የማጎፈላው ቡድን ... በደንብ ተዘጋጅቶ እና አቅዶበት
"እኔም መስጂዱን አፀዳለሁ" በሚል ሰበብ በፈጠረው አተካራ የወንድሞቻችን ደ ም አላግባብ ፈሷል ...
*
ጆን ኤፍ. ኬኔዲ አንዲት ገራሚ አባባል አለችው... "የእኔው የእኔ እና የእኔ ብቻ ነው ... የአንተውን ግን ልንከፋፈለው
(ልንደራደርበት) እንችላለን ከሚል ሰው ጋር እንዴትም መግባባት አይቻልም" የምትል... "You cannot negotiate with
people who say what's mine is mine and what's yours is negotiable." John F Kennedy.
... ፅ ዬ ናዊ ው መጅሊስም ገዢ መርሁ ይሄ ነው ... "የሰለፍያው መድረሳ እና መስጂድ የሰለፊያ ነው ... የሱፍያውን ግን
እንደፈለግን እናደርገዋለን " የሚል ዕቡይነት ....
*
አየርጤና መስጂድ መውሊድ ካላከበርኩኝ ብሎ ያስቸገረ የነብዩ ‫ ﷺ‬ሙሒብ ሰምተን አናውቅም... ቤተል ፖርላማ መስጅድ የተብሊግ ጀምዐ
እግሩ አይደርስም ... የተከበሩ የፖርላማው አባል ዲስኩር እንጂ በያንም ሆነ ኢዕላን... ከላመል ጁሉስም ሆነ ተርጊብ ተደርጎበት
አያውቅም... የሱፍያው መስጂዶች ወይንም ሱፍያው የሚበዛባቸው መስጂዶች ግን በሪፎርም ስም ከኢባዳ ቦታነት ወደ ሁከት ሜዳነት
ተቀይረዋል ... የአላህ ፍሪጅ ቅርብ ነው ... ያፈላ እና የፈላ መቀዝቀዙ አይቀርም ... እስከዛው ግን እንደራጅ! እንቀናጅ ! ብልጥ
እንሁን!ንቁ እንሁን!

You might also like