Download as pdf or txt
Download as pdf or txt
You are on page 1of 3

Amhara Revenue Bureau

facebook.com/AmraNews/posts/pfbid036KEnWTaBKcXUoUxf3WRCxKHRbUPpAD3XTi4LyAbjB4fnCzJw6yUdNS3KH
vXCvEGDl

የሽያጭ መመዝገቢያ መሣሪያ ግዥ ለመፈፀም መሟላት ያለባቸው ቅድመ-ሁኔታዎች እና የተጠቃሚዎች


ግዴታ፣

1. ቅድመ-ሁኔታዎች

የንግድ ምዝገባ ፈቀድና በዘመኑ የታደሰ የንግድ ሥራ ፈቃድ፣

የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ሰርተፊኬት፤

ድርጅቱ ለተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዘገበ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ ሠርተፊኬት፤

የቀበሌ ነዋሪነት መታወቂያ፣

በተወካይ የሚያሰራ ከሆነ የፍርድ ቤት ውክልና፣

የሽያጭ መመዝገቢያ መሳሪያ መግዛት እያለባቸው ለመግዛት ፈቃደኛ ያልሆኑ ግብር ከፋዮች የግብር ክሊራንስ
መጠየቅ ወይም የታክስ ሪፖርት ማቅረብ አይችሉም፡፡

2. የተጠቃሚዎች ግዴታ፣

 መሳሪያና ሶፍትዌር እንዲገዛ በገቢ ተቋሙ ሲታዘዝ ዕውቅና ከተሰጠው አቅራቢ ሰድርጅት ገዝቶ የመጠቀም፣

 ስልጠና ሣይወስዱ መሳሪያውን ጥቅም ላይ አለማዋል፤

 መሣሪያው በጥገና ላይ ባለበት ጊዜ ወይም በሌላ በቂ ምክንያት ካልሆነ በስተቀር በሽያጭ መመዝገቢያ
መሣሪያ ከታተመ ደረሰኝ ውጪ ያለደረሰኝ ወይም በሌላ ማናቸውም ዓይነት ደ ረሰኝ ግብይት አለማከናወን፣

 በሽያጭ መመዝገቢያ መሣሪያ ወይም የፊስካል ማስታወሻ ላይ ጉዳት አለማድረስ ወይም የፊስካል
ማስታወሻ አለመቀየር ወይም እንዲቀየር ሙከራ አለማድረግ፣

 የታክስ ሠራተኛ የሽያጭ መመዝገቢያ መሣሪያን ሥርዓት ኦዲት እንዳያደርግ መሰናክል አለመፍጠር፣

 በመሣሪያው ላይ በዓመት አንድ ጊዜ በአገልግሎት ማዕከል የቴክኒክ ምርመራ ማስደረግ፣

 የመሳሪያ ብልሽት ሲገጥም በሁለት ሰዓት ውስጥ ለገቢ ተቋሙ በማስታወቅ ወደ አገልግሎት ማዕከል
በመውሰድ በወቅቱ አስጠግኖ የመረከብ ፤

 በንግድ ሥራው ለሚጠቀምበት የሽያጭ መመዝገቢያ መሣሪያ ከአገልግሎት ማዕከል ጋር ውል መፈጸም

 የሽያጭ መመዝገቢያ መሣሪያውን ከተርሚናል ጋር በማያያዝ የተጠቀም፣

 የሽያጭ መመዝገቢያ መሣሪያው የምርመራ መዝገብ ከመሣሪያው ጎን ማስቀመጥ

1/3
 በሽያጭ መመዝገቢያ የተመዘገቡ ዕቃዎች ተመላሽ መደረጋቸው ወይም ደንበኛው የተመላሽ ጥያቄ ማቅረቡ
በተመላሽ መዝገብ ላይ በትክክል መመዝገቡ ሳይረጋገጥ የተመላሽ ደረሰኝ አለመስጠት፣

 የሽያጭ መመዝገቢያ መሣሪያው በስርቆት ወይም ከአቅም በላይ በሆነ ምክንያት ጉዳት የደረሰበት በመሆኑ
አገልግሎት መስጠት ሲያቋርጥ በሦስት ቀናት ጊዜ ውስጥ ወይም በሌላ ማናቸውም ምክንያት የሽያጭ
መመዝገቢያ መሣሪያው ብልሽት ባጋጠመው በአራት ሰዓት ውስጥ ለአገልግሎት ማዕከሉ እና ለገቢ ተቋሙ
የማስታወቅ፣

 የሽያጭ መመዝገቢያ መሣሪያ የሚቀመጥበትን የንግድ ቦታ ትክክለኛ አድራሻ ለገቢ ተቋሙ የማስታወቅ፣

 የአድራሻ ወይም የስም ለውጥ ሲያደርግ ወይም የንግድ ሥራውን የሚያቋርጥ ሲሆን ከሦስት ቀናት
አስቀድሞ ለአገልግሎት ማዕከሉ እና ለገቢ ተቋሙ፣ የማስታወቅ፣

 የሽያጭ መመዝገቢያ መሣሪያው ጥቅም ላይ በሚውልበት የንግድ ሥራ ቦታ የሚከተሉትን መረጃዎች የያዘ


ማስታወቂያ አዘጋጅቶ መለጠፍ፣

 የተጠቃሚውን ስም፣ የንግድ ስም፣ የንግዱ ሥራ የሚካሄድበትን አድራሻ፣ የታክስ ከፋዩን መለያ ቁጥር፣
የሽያጭ መመዝገቢያ መሣሪያውን የዕውቅና እና መጠቀሚያ ፈቃድ ቁጥር፣

 “የሽያጭ ሠራተኞች መሣሪያው የተበላሸ ከሆነ በገቢ ተቋሙ ፈቃድ የታተመ ተከታታይ ቁጥር ያለው ደረሰኝ
ለደንበኞች የመስጠት ግዴታ አለበት” የሚል ማስታወቂያ፣ እና

 “ደረሰኝ የማይሰጥ ከሆነ አይክፈሉ” የሚል ጽሑፍ ያለበት ማስታወቂያ፣ በግልጽና በሚታይ ቦታ መለጠፍ፣

ሥራ ላይ የዋለውን የሽያጭ ነቁጣ ሶፍትዌር ገቢ ተቋሙ ዕውቅና ባልተሰጠው ድርጅት/ሰው እንዲቀየር ወይም
እንዲሻሻል አለማድረግ፣

2/3
3/3

You might also like