Download as pdf or txt
Download as pdf or txt
You are on page 1of 6

የይርጋዓሇም ሰዎች

በመኩቲ

በቀዯም ላሉት በህሌሜ ይርጋሇም መናኸሪያ የሚባሇው ሰፈር ምን ሊዯርግ እንዯሄዴኩ አሊወቅኩም።
ይርጋሇም ነው ተወሌጄ ያዯግኩት 12ኛ ክፍሌ ዴረስ። በየዓመቱ እሄዴ ነበር።አሁን አራት ዓመት ሆነኝ
ከሄዴኩ። በሌጅነታችን መናኸሪያ የሚባሇው ሰፈር ከቤት ተሌኮ ካሌሆነ በቀር የታየ ሌጅ ወዯ ቤቱ
ሲመሇስ ጉዴ ይፈሊበት ነበር። እና መናኸሪያ ያገኘኋቸው ሰዎች. . .
ይርጋሇም ሁለም ሰው እርስ በርሱ ይተዋወቃሌ የኔ ቢጤው (በሌመና የሚተዲዯሩ) እነ እሰዬ-ሌመና
እንዯሙያ የምርጫ ጉዲይ ይመስሇኝ ነበር ሌጅ እያሇሁ ምክንያቱም አንዲንድቹ በር ሊይ መጥተው
“ስሇግዚያብሔር” ሲለ “ና እስቲ እንጀራ ሌጋግር ነው ይህቺን እንጨት ሸንሸን አርጋት” ሲባሌ ክምር
እንጨት ፈሌጦ የተሰጠውን እንጀራ እዚያው በሌቶ ይሄዴ ነበር። እሰዬ እንኳን ሸምገሌ ብል ጣሉያንኛ
ይናገር ነበር። ቱሚሊ የሚባሌ ሰው ነበረ- ቱሚሊ ዋና ገብስ ፈታጊና በርበሬ ዯሊዥ ሲሆን የራሱ የሥራ
ዘፈንም ነበረው፣ የሚሊሊኩ እነ አጋ (መስማት የተሳነው ነው)፣ በገንዘብ ተገዝተው ሰዎችን ያስፈራራለ
የሚባለት እነ ቆሌማሜ- አቤት የቆሌማሜ ቁመት ሁላ ከሚሇብሰው ቁምጣ ጋር እንዳት እንዯሚያስፈራ
“ሇቆሌማሜ ብር ሰጥቼ እንዲሊስጠፈጥፍሽ” የሚባባለ የተጣለ የሰፈር ሴቶችን መስማት የተሇመዯ ነበር።
ወዯ ወንዝ ወርዯው የሰዎችን ሌብሶች የሚያጥቡት ማን ነበር ስማቸው? ቆይ አንዳ ጓዯኛዬ ጋር ሌዯውሌ.
. .ሃል ሃይ ምግባር(አብሮ አዯጌ ነው ምግባር) ሰሊም ነው? እኔ የምሌህ ሥራ ካሌያዝክ ይርጋሇም ቆሌማሜ
አሇ እንዳ? “አዎ አሇ”። ሌብስ የሚያጥቡት ሰውዬ ማን ነበረ ስማቸው? “ጋሽ ባፋ እሳቸው ግን ሞቱኮ”. . .
ወዯ ትምህርት ቤት ስንሄዴ ጋሽ ባፋ በአንሶሊ የታሰረ ትሌቅ የሌብስ ክምር ተሸክመው ወይ ወዯ ወንዝ
ሲወርደ ወይ ከወንዝ ሲመሇሱ ማየት የተሇመዯ ነበር። ሁሌ ጊዜ የሚሇብሱት ከአሮጌ ጂንስ ሱሪ ተቆርጦ
የተሰፋ ቁምጣና ቀሇም ከማጣቱ የተነሳ ዴርቅ ያሇ ማሰሪያ የላሇው የወታዯር ጫማ። ጋሽ ባፋ በየትኛውም
አቅጣጫ ቢሄደ ከወንዝ እየተመሇሱ ወይም ገና እየሄደ መሆኑን ማወቅ ቀሊሌ ነበር። እግራቸውን በማየት-
አመዴ ከመሰሇ እየተመሇሱ ነው።
አባቴ በናፍጣና በዘይት የቆሸሸ የሥራ ቱታውን “ይሄን ሇጋሽ ባፋ ስጠው” ብል ከ 1ብር ጋር ሲሰጠኝ
አብሮ የሚነግረኝ መሌዕክት “በቆሮቆንዲ አትሸው በሇው እንዲይቀዯዴ” የሚሌ ነበር። ቆሮቆንዲ በቆል
ተፈሌፍል የሚቀረው እንጨት መሰለ ነው።
በዚያ ጊዜ የፈሇገ የየቀበላው ነዋሪ ጓሮ ይሰጠኝ “አሇማሇሁ” ብል ቀበላውን ያስፈቅዴና ወዯ ወንዝ
አካባቢ ያሇ ሰፋፊ መሬት ይሰጠዋሌ። እዚያ መሬት ሊይ የጫካ ቡና፣የተሇያዩ የፍራፍሬ ዛፎች በተሇይ
ዘይቱን፣ሙዝ፣ ዋንዛ፣ ዝግባና ብሳና የመሳሰለት ዛፎች አለ። “አሇማሇሁ” ብሇው መሬቱን የሚወስደት
ሰዎች ግፋ ቢሌ በአመት አንዳ በቆል ቢዘሩ ነው እሱንም ጎበዝ ከሆኑ። ላልቹ ቡናው በዯረሰ ጊዜ
መሌቀም ብቻ ነው። ታዱያ መሬቶቹ የጋሽ ባፋ ጓሮ፣ የጋሽ በካል ጓሮ፣ የመምሬ አየሇ ጓሮ እየተባለ
ይጠራለ።
እኛና ከኛ ከፍ ከፍ የሚለት ሌጆች ዯህና ዯህና የዯረሱ የሸንኮራ አገዲዎች ወይም የበሰሇ ዘይቱን ያሇበትን
ጓሮ ሳናስፈቅዴ(ዘረፋ) እንገባና ሆዲችን እስኪወጠር በሌተንና የቻሌነውን ያህሌ ተሸክመን ወዯየቤታች
እንመጣሇን። የጋሽ በካል እና የጋሽ ባፋ ጓሮ በዘይቱን ምርቱና ጥራቱ የታወቀ ነበር። የቀሇሟ እናት ጓሮ
ዯግሞ በሸንኮራ አገዲውና ጥርት ባሇ የምንጭ ውሃው።
የአንዲንዴ ሰዎች ጓሮ ዯግሞ ጣሬ አሇው ተብል ይፈራ ነበር። ጣሬ በሲዲማ ባህሌና እምነት ሰዎች
ሰብልቻቸውን ከላባ የሚጠብቁበት የረቀቀ መሊ ነው። እንዳት? የዯረሰ እርሻ ያሇው ሰው ጣሬ የሚሰሩ
ሰዎች ጋር ይሄዴና በእራፊ ጨርቅ የተቋጠረች ዴግምት ነገር ትሰጠዋሇች። ያቺን እርሻው መሃከሌ በረጅም
ቀርከሃ ወይም ላሊ እንጨት ጫፍ እንዴትታይ አዴርጎ ይሰቅሊታሌ። ታዱያ በላቦችም በላሊውም ዘንዴ
ምን ተብል የታመናሌ? ጣሬ ካሇበት እርሻ ሰርቆ የበሊ ሰው “እሱ ይርጋሇም ቁጭ ብል ሆደ ብቻውን
እየተነፋ ሻሸመኔ ወይም አዱሳባ ይዯርሳሌ።” 300 ኪል ሜትር። እንዳት እንዯሚያስፈራ አስቡት። ዴርሽ
የሚሌ የሇም እዚያች ጓሮ። ከጦጣና ከዝንጀሮ ሇመጠበቅ ዯግሞ በቡቶቶ የተሰራ ሰው መሳይ ፈረንጆቹ ከኛ
ወስዯው “ስኬር ክሮው” የሚለት ዓይነት ይሰቀሊሌ። (በላሊ ጊዜ ስሇ ጣሬ እና አካኩ-ፍርዴ የሚሰጥበት
የእምነት ቦታ የተሻሇ እፅፋሇሁ)
እነ ታዯሇ ጫማ ሰፊው -ታዯሇ ጫማ ሰፊው ጋር ብዙ በኳስ የተገነጠለ ጫማዎቼን አሰፍቼአሇሁ ታዱያ
አንዴ ጊዜ የካራቴ ጫማ የሚባሌ ተገዝቶሌን በመጀመሪያው ቀን ትምህርት ቤት አዴርጌው ኳስ ተጫውቼ
ዙሪያው ሇቀቀ ማንም ሳያየኝ ወዯ ቤት ሄዴኩና ሽቦ ቀጥቅጬ መስፊያ ሰራሁና ታዯሇ ጋር ባየሁት መሠረት
ሰፍቼ ከቁጣ አመሇጥኩ።
እሌፍኝ ጠጅ፣ አብዬ ተሻሇ ቅመማ ቅመም ነጋዳው- 12ኛ ክፍሌ ሆኜ እንኳ እናቴ አብዬ ተሻሇ ጋር “ሮጥ
በሌና ጥቁር አዝሙዴ የስሙኒ፣ ኮረሪማ የ1 ብር ነጭ አዝሙዴ የ50 ሳንቲም ይዘህ ና ትሇኝ ነበር”
ቅመሞቹን ትሸጥ የነበረችው የአብዬ ተሻሇ ባሇቤት ፅጌ ሁሌ ጊዜ አፍንጫዋ እርጥብ ሆኖ ያስነጥሳት ነበር።
ሳይነስ መሆኑ ነው?. . .
ንጋቱ እብደ-የአዕምሮ ህመምተኛ ነው ንጋቱ ወዯ ይርጋሇም መጀመሪያ እነዯመጣ እጅና እግሩ በሰንሰሇት
የታሰረ ነበረ ኋሊ ተፈትቶ ዯህና ነበረ። አሌሽቴኪ- ይሄኛውም የአዕምሮ ህመምተኛ ሆኖ ማጅራቱ ሊይ
ተሸክሞት ይዞር የነበረ ትንሽ ወንዴ ሌጅ ነበረው። በኋሊ ይህ ሌጅ አዴጎ ሉስቲሮ ይሰራ ነበረ።
አባባ ገዯቡ- አባባ ገዯቡ የነ ቁምሊቸው ገዯቡ አባት ሁሌ ጊዜ ነጭ ተነፋነፍ ሱሪና ጋቢ ሇብሰው ከቀርከሃ
በተሰራ ወንበር ሊይ ከቤታቸው ዯጅ ይቀመጡ ነበረ። ታዱያ ሌጅ ሆኜ ሁሌ ጊዜ ማታ ማታ በረዯኝ
ስሇምሌ ቤተሰቦቼ ጋቢ ይሰጡኝና “አባባ ገዯቡ” እያለ ያበሽቁኝ ነበረ።
እነ ጋሽ ሳሉክ ታክሲ ነጂው -ሇመጀመሪያ ጊዜ ብቻዬን በታክሲ ተሳፍሬ ከአፖስቶ (ዘመዴ ቤት) ይርጋሇም
የተሳፈርኩት በጋሽ ሳሉኩ ታክሲ ነው አዯራ ተብል ያን ቀን ሜርሰዱስ ታክሲው ውስጥ አዱስ የወጣው
የአረጋኸኝ ዘፈን “እስኪ ዘሇሌ ዘሇሌ. . .” ተከፍቶ ነበር።
ጋሽ መኮንን የሚባለ ፔጆ ታክሲ የነበራቸው ሰውዬ ነበሩ። ታክሲዋ እየተበሊሸች ከማስቸገሯ የተነሳ
ከትምህርት ቤታችን አጠገብ በነበረው ሰፊ ግቢያቸው ውስጥ ጉዴጓዴ አስቆፍረው ዯንበኛ ጋራዥ
ነበራቸው። ይህች ታክሲ ክሊክስ ስሊሌነበራት ጋሽ መኮንን በግራ እጃቸው ረጅም አሇንጋ ይዘው ነበር
የሚሾፍሩት በመንጋዲቸው የገባን እግረኛ “ዞር አትሌም አንተ” እያለ ያንን አሇንጋ ይሰነዝሩ ነበር።
ጋሽ ቀቀቦ ጋራጅ- ጋሽ ቀቀቦ “የአውሮፕሊን ካምቢዮ ሳይቀር እጠግናሇሁ” ይሊሌ እያለ ይሳሳቃለ ።
አባባ እሳቱ ገራዡ(ወንዴ ሌጆችን የሚገርዙ) “ከእነ እንትና ቤት 4 ከነእንትና 3 ከነእንትና ቤት የ7ቱንም
የቆረጠው አብዬ ነው” ሲሌ ሰምቸዋሇሁ ሌጃቸው እንዲሇ እሳቱ የሶሪያ እሳቱ ወንዴም። እስቲ አንዳ
እንዲሇ ጋር ሇዯውሌ. . .ሃል እንደ መኩቲ ነኝ እንዳት ነህ? “ውይ ሞኪዬ እንዳት ነህ ጌታዬ ጠፋህብኝኮ
በቀዯም እንዯውም ይርጋሇም ሄጄ (አዋሳ ነው የሚኖረው) ትዝ ብሇኸኝ ነበር ምነው ጠያቂዬ ዘጋኸኝ?”
ስንፍና ነው እንደ ይቅርታ አዴርግሌኝ። እኔ የምሌህ ሶሪያ ዯህና ነው? ዯህና ነው ሞኪዬ አሁንማ ሶሪያ
ጡረታ ወጥቶ ቤት ቁጭ ብል ነው ያሇው ያቺ ስኳሯም አጣፍጣው. . .ኪኪኪ. . .” እሺ እንደ ጤንነትህ
ዯህና ነው አይዯሌ? የሚመጣው ሳምንት ውስጥ እዯውሌሌሃሇው ቻዎ። የይጋሇም ሰው መቼም በራሱ
መቀሇዴ የሚወዴ ኮሚክ ነው “ስኳሯ አጣፍጣው”. . . በተሇይ የነእንዲሇ ቤተሰብ። ደሮ ይርጋሇም ስኳር
ያዘው የሚባሌ ሰው ሰምቼ አሊውቅም ነበር። ሶሪያ እሳቱ ግን የሚገርም ስም እኮ ነው። ትንቢት።
ጋሽ ስጦታ የ 06 ቀበላ እዴር ጥሩንባ ነፊ ነበሩ ሇመጀመሪያ ጊዜ “ጥንዲሻም” የሚሇውን ስዴብ የሰማሁት
ከርሳቸው ነው በ1980። ይኮሊተፉ ነበር “ጥ ጥ ጥ ጥ. . . ጥንዲሻም!”።
እነ ጋሽ ካሳ ባሇሱቁ (ዘመዴ ናቸው)፣ጋሽ ኩማ መካኒኩ( አባቴ ነው) እነ ዘሪሁን አጂፕ፣እማማ ቆል፣ ዘሪቱ
ቴላ፣ አበዙ ቀበላ፥ ሇታይ አንባሻ፣ታዯሰ ቡዋንቧ፣ንግስት ታይፒስቷ፣ እነ ቦጋሇ ፖሉሱ፣ክፍልም ትራፊኩ፣
እነ ጋሽ ነጋሽ ባሇ ወፍጮው፣ድክተር አብረሃም ፈሇቀ-ድክተር አብረሃም የታወቀ የቀድ ጥገና ሐኪም ነበረ
ስሇርሱ ሇመፃፍ አቅሜ አይፈቅዴም። እነ ጋሽ ሻኪር ባሇዲቦ ቤቱ (የየሺ እመቤት ዘፈን ትዝ አሇኝ “ሻኪር
ባሇዲቦው አይ ዯስ ሲሌ አዋሳ ቤት ሰርቶ. . .” እያሌን እንዘፍን ነበር። ምን የመሰሇ አሁን ኬክ የሚለት
ዓይነት ዲቦ 10 ሳንቲም። እነ ጋሽ አስፋው ሌብስ ሰፊው፣ ጋሽ ሇገሠ ሉቀመንበሩ፣ ጋሽ መንገሻ ፋርማሲው-
እዚያው ፋርማሲ ውስጥ የክሉኒክ አግሌግልትም ነበረ ስንት መርፌ ጠጥቼያሇሁ። ጋሽ መንገሻ ግዙፍ
ነው። የሆነ ነገር ታመን እዚያ ስንሄዴ የክሉኒኩ ጓዲ ከገባን መርፌ አይቀርም ሽታውና ንፅሕናው ግን ዯስ
ይሇኝ ነበር ዓይናችንን ገሇጥ ገሇጥ አርጎ ያይና መርፌ ይወጋናሌ። ሇመጀመሪያ ጊዜ ሱቅ የተሊክሁት አበበ
ሱቅ ነው። የጋሽ አበበ ሱቅ ዘይትና አቧራ ተዯባሌቆ እንዯ ጭቃ የተሇጠፈበት የቆየ የሱቅ መዯርዯሪያ በሊዩ
ሊይ የተቀመጠውን ሚዛን አጣብቆ ይዞት ትዝ ይሇኛሌ።
ታዯሰ ሪድ የሚባሌ ግዙፍ ሰው አሇ ዯግሞ ደሮ የዜሮ አምስት ቀበላ ኳስ ቡዴን ተገዲጋጅ (ተከሊካይ)
ነበር። (አሁን የቀበላ የኳስ ቡዴን ቀርቷሌ አይዯሌ?-የሃገራችን አካሄዴ ሇምን እንዯ ማይክሌ ጃክሰን ዲንስ
እንዯሚያምታታን አሊውቅም ወዯ ፊት ነው ወዯ ኋሊ?) ታዱያ ሪድን (ታዯሰ ሪድን ሰዎች ሪድ ብሇው ነው
የሚጠሩት) አሌፎ ጎሌ ማስቆጠር ዘበት ነበር። ታዯሰ የመብራት ሃይሌ መስሪያ ቤት የጥበቃ ባሌዯረባ ሆኖ
ሰፈር ውስጥ ዯግሞ ዋና የኤላክትሪክ ሠራተኛ ነው።

ይርጋሇም ሰዎች ወይ በሙያቸው ወይ በላሊ የቀሌዴ ቅጽሌ ሥም ነበር የሚጠሩት። ዘርና ሃይማኖት
የሚጠይቅ የሇም። በየነ ሾፌሩ- በየነ 7 ዓመት ሆኖኝ ጥርሴን የነቀሇሌኝ ጎረቤታችን ነው። “በዯንብ
ተነቃንቆ ሲበስሌ በጠዋት ና” ይሇኝና ጥርሶቼ በተነቃነቁ ጊዜ ጠዋት ጠዋት እቤቱ እሄዴና በክር እያሰረ
ይነቅሌሌኝ ነበረ የአብተው ከበዯ ዘፈን “ሳውንዴ ትራክ” ፣ ኮሌት ኮሚኩ. . .አሌታዬ ክትፎ፣ ታዯሠ ወርቅ
ሠሪው. . .ሞገስ አስተማሪው- ሞገስ ሇእኔ እንዯ አባት ነው ከ6ኛ ክፍሌ ጀምሮ ያስጠናኝ ነበረ እሱ የሃይ
ስኩሌ መምህር ሆኖ። ስዴስተኛ ክፍሌ ሆኜ የወሇዯው ሌጅ የክርስትና አባት እኔ ነኝ። አሁን ያ ሌጅ
በጎንዯር ዩኒቨርሲቲ የሶስተኛ ዓመት የህክምና ተማሪ ነው።
እነዚህ ሁለ እርስ በርሳቸው የሚተዋወቁ አብረው ሇብዙ ዘመናት ከተሇያዩ ቦታዎች መጥተው ቤተሰብ
መስርተው፣ ተዋዯው፣ ተሳስበው፣ እዴር መስርተውና እቁብ ተጣጥሇው የሚኖሩ የይርጋሇም ሰዎች
ናቸው። ከይርጋሇም ጋር ያሊቸው ትስስር እንዱህ በቀሊለ የሚገሇፅ አይዯሇም። ሇምሳላ ጋሽ ካሣ አዋሳ
እንቅሌፍ አይወስዲቸውም። ምን ቢመሽባቸው ይርጋሇም መጥተው ያዴራለ እንጂ።
በህሌሜ ይርጋሇም መናኸሪያ ሰፈር ቆሌማሜ፣ አጋ እና ላልች ተሰብስበው ካቴናው የወሇቀ ብስክላት
እየጠገኑ ነበረ። እኔ ዯግሞ መናኸሪያ መሃሌ በመገኘቴ ግራ ተጋብቼ መሃሊቸው ቆሜያሇሁ። ብንን አሌኩና
በምናቤ ወዯ ሌጅነቴ ምዴር ይርጋሇም በሃሳብ ነጎዴኩ። አንዲንዳ ህሌምና እውኑ ይምታታለ።
እኛ ቤት ያኔ የመኪና ባትሪዎችን ቻርጅ የሚያዯርግ ማሽን ነበረ እና የባትሪ አሲዴም ከአዱስ አበባ
እየተጫነ ይሸጥ ነበረ። ታዱያ አንዴ ቀን (ሌጅ እያሇሁ ነው) ቆሌማሜ እንዯ ጀሪካን ነገር ይዞ አሲዴ
ሽጡሌኝ ብል መጣ እኔ ነበርኩ በር የከፈትኩሇት። ዯግነቱ አባቴ በዯንብ አስረዴቶናሌ “አሲዴ ሇማንም
ሰው በዕቃ አይሸጥም ባትሪ ውስጥ ብቻ ይጨመራሌ እንጂ”። ይሄንኑ ነግሬ መሇስኩት። ኋሊ እዚህ አዱስ
አበባ በአሲዴ ምን እንዯተዯረገ ስሰማ ከቆሌማሜ አጉሌ ስምና አስፈሪነት ጋር ምን እንዲሰብኩ ገምቱ።
ባትሪ ቤት ገባ ብሇን የወጣን እንዯሆነ የሇበስነው ሌብስ ከጥጥ የተሰራ እንዯሆነ ቡጭቅ ቡጭቅ እያሇብን
አባቴ “ሇምን እሱን ሇብሰህ ገባህ” እያሇ ይቆጣን ነበረ።
ከአዱስ አበባ ወዯ ይርጋሇም ስሄዴ እየተቃረብኩ መሆኔን የማውቀው በመንገደ ዲር እና ዲር ሊይ
በማያቸው የተክሌ ዓይነቶች ነው። እንዱያውም አንዴ ሲቀጠፍ ወተት ዓይነት ፈሳሽ የሚወጣው ቀይ
ቅጠሌ ያሇው ቁጥቋጦ ዋናው ምሌክቴ ነው። ከተሇያዩ ሃገራት የመጡ የአፈር ናሙናዎች ቢሰጡኝ
የይርጋሇምን አፈር አይቼም አሽትቼም እሇየዋሇሁ።. . .እንባ!?
ሳሩ ቅጠለ ዛፉ ዴንጋዩ ሁለም ሇእኔ ሌዩ ናቸው። ያኔ ይርጋሇም አንደ የኔ ወይም የወንዴሜ ጓዯኛ
ከቤተሰቡ ያኮርፍና እኛ ቤት ይገባሌ ከኔና ከወንዴሜ ጋር ይተኛሌ። እኛ ቤት ምግብ የምንመገበው
ሁሊችንም አንዴ ሊይ ነው በአንዴ ትሪ አባቴ፣ እናቴ፣ እኔ፣ታናሽ ወንዴሜ፣ ትንሿ እህቴ እንዱሁም ከቤቱ
አኩርፎ የመጣው። ይርጋሇም ሁለም እንዱሁ ነበር። ባሌ እና ሚስት እንኳ ሲጋጩ ሚስት ካኮረፈች
ዘመዴም እያሊት ጎረቤት ነው የምትሄዴ። እኔም ባኮርፍ። ያ ሌጅ በበነጋው ወዯ ትምህርት ቤት የኔን
ወይም የወንዴሜን ጃኬት ወይም ሱሪ ሇብሶ ሉሄዴ ይችሊሌ። በሶስተኛው ወይም በአራተኛው ቀን አባቴ
ወይም እናቴ ይዘውት ወዯ ቤቱ ይሄደና ከቤተሰቡ ያስታርቁታሌ።
ሰዎች እርስ በርሳቸው እጅግ የተቀራረቡ፣ ጎረቤታሞች ቤቶቻቸውን እስከ መሶብ ዴረስ የሚተዋወቁ አንደ
ቤት በርበሬ የተፈጨ እንዯሆነ ይሸታቸዋሌ ተብል በጎዴጓዲ ሰሃን ወዯ ላልቹ ቤቶች ይሊክ ነበረ። ድሮ
ወጥ ተሰርቶም እንዯሆነ እንዯዚሁ። በጓሮው እሸት ወይም ፍራ ፍሬ የዯረሰ ከሆነም ሇየጎረቤቱ ይሰጥ
ነበረ።
ከጎረቤት አንዶ እርጉዝ የሆነች እንዯሆን መውሇጃዋ ሲዯርስ ላልች የጎረቤት ሴቶች እናቴን ጨምሮ እንዯ
እቁብ ነገር ይጣጣለና ሇነፍሰ-ጡሯ መታረሻ የሚሆን የገንፎ እና የአጥሚት እህሌ አስፈጭተው ቤቷ
ይዘውሊት ሄዯው (የሙከራ) ገንፎ ይበለ ነበረ። ዛሬ ፈረንጆቹ “ቤቢ ሻወር” የሚለትን ከ እኛ ነው
የወሰደት ማሇት ነው። እንዯ ቁንጮ፣ “ባሊቶሉ” እና ንቅሳት. . .ምን ያሌወሰደብን አሇ. . . ኪኪኪ
ይርጋሇም ምዴረገነት የሚባሌ ሆቴሌ አሇ ወዯ ትምህርት ቤት ስንሄዴና ስንመሇስ ከዯጃፉ ሊይ ኮርኪ
እንሇቅም ነበረ። ኮርኪ እንኳን የደሮ ይሻሊሌኮ ጎበዝ በውስጡ የተሇጠፈው ፕሊስቲክ በቀሊለ ይወጣና
ሇትምህርት ቤት የእጅ ሥራ ቀበቶ እንሰራበት ነበር። የአሁን ኮርኪ እጣ እያሇው እንኳ በላሊ ሹሌ ነገር
ይፋቅ እንዯሁ እንጂ መች ይሊጣሌ።
ይርጋሇም መቼስ የላሇ የፍራፍሬ ዓይነት አሌነበረም። ሙዝ እንኳን በትንሹ ሦስት ዓይነት አሇ። የፈረንጅ
ሙዝ የምትባሇው ሌክ እዚህ አዱስ አበባ የምናውቀው ዓይነት ቢጫ ሆና አጫጭርና በጣም ጣፋጭ፣
የሃበሻ ሙዝ የምንሇው ዯግሞ አሇ ሁሇት ዓይነት ነው እሱ ሁሇቱም ከበሰለም በኋሊ ወዯ አረንጓዳ
የሚያመዝን ቀሇም ያሇው ሌጣጭ ነው ያሊቸው። መዓዛቸውም እዚህ ከምናውቀው የተሇየ በጣም
የሚጥምና ጉሌህ ነው። አንዯኛው ረጅም ላሊኛው አጭር ሆኖ ዴፉጭ ያሇ-ከአንዴ በሊይ ሇመብሊት ይሄ
ይመረጣሌ። ረጅሙን አንዴ እንኳ መጨረስ ከባዴ ነው።በጠረቂቾ የሚባሌ ፍሬ ያሇው ዛፍ ነበር የተፈጥሮ
ከረሜሊ ከነማሸጊያው ማሇት ነው። የበጠረቂቾ ዛፍ ትሌቅ ስሇነበር እሊይ ወጥቶ ፍሬዎቹን ያወርዴሌን
የነበረው ጠንካራው ያጎቴ ሌጅ ቴዱ (አሁን ድክተር) ነበር።
ዜሮ ሰባት የሚባሌ ቀበላ አሇ ከዋናው መንገዴ ዲርና ዲር በራሳቸው ጌዜ የበቀለ የአቮካድ (አቦካቶ ነበር
የምንሇው) ዛፎች ነበሩ እና ፍሬ ባፈሩ ቁጥር አስፋሌቱ ሊይ እየረገፉ መንገደን ያበሊሹ ስሇነበር ቀበላው
ያስሇቅምና በማዲበሪያ እየሞሊ ሇህዝቡ ይሸጥ ነበረ። ማዲበሪያ መሌስ 50 ሳንቲም ከነማዲበሪያው 1ብር።
ታዴያ አሁን ሳስበው የሚገርመኝ ከላሊው ጊዜ የበሇጠ አስፋሌቱ ይቆሽሽ የነበረው ያን ቀን ነበረ።
አቦካቶው የሚሸጥ ቀን።
ይርጋሇም ማን ሃይማኖቱ፣ዘሩ ወይም ብሔሩ ምን እንዯሆነ የሚጠይቅም የሚያውቅም አሌነበረም። እኔ
ራሴ አባቴ ከአቃቂ ሇሥራ ሄድ እዚያው የቀረ ኦሮሞ እንዯሆነ የተረዲሁት ዩኒቨርሲቲ ከገባሁ በኋሊ ሳይሆን
አይቀርም። ቅዴም እንዲሌኩት ሰዎች የሚተዲዯሩበትን ሙያ ነበር እንዯ አባት ስም የምንጠቀመው። ዛሬ
ግን እነ እገላ የእንትን ብሔር ሰዎች ናቸው ስሇዚህ እዚህ መኖር አይችለም እየተባሇ ነው አለ።. . .እንባ!

ላሊው ቀርቶ አሁን በቅርቡ እንኳ በተሇያዩ ላልች ክሌልች የብሔር ግጭቶች ተነሱ ሲባሌ ስሰማ
ይርጋሇምን አይመሇከትም ብዬ ነበረ የማስበው፤ ነገር ግን ይርጋሇምም እንዱሁ መሆኑን ሳውቅ የተሰማኝን
ስሜት በቃሊት መግሇፅ ይከብዯኛሌ። . . .እንባ!?
በበኩላ ግን ይህ ነገር አሁንም ቢሆን በሲዲማ ምዴር እኔን አይመሇከተኝም። በሲዲማ ምዴር በየትኛውም
ገጠር ከሰማይ ብወዴቅ የሲዲማ ህዝብ ተንከባክቦ የምወዯውን ዋሳ (ቡሪሳሜ) እና ወይራ በታጠነ ዕቃ
የረጋ እርጎ አጥግቦ እንዯሚሌከኝ ከእርግጠኛ በሊይ ነኝ። በየትኛውም የሃገራችን የገጠር ክፍሌ ይኸው
ነው። ከተማ ቀመሱ ሳይሆን አይቀርም የችግሩ ምንጭ። የጋሞ አባቶች ያዯረጉትን መመሌከት እንዯዚያ
ያለ ብርቅዬ ባህልቻችንን መኮትኮትና ማገዝ ከምንም በሊይ ተገቢና አስፈሊጊ ነው።
በተሇይ በዚህ የሇውጥ ወቅት ሰዎች ላልችን የመበዯሌ አዝማሚያ ሲሰማቸው ራሳቸውን በላልች ተጎጂ
ወገኖች ቦታ ኣዴርገው የመመሌከት ሌምዴ ቢዲብር መሌካም ነው እሊሇሁ።

You might also like