Professional Documents
Culture Documents
በገንዘብ ማገልገል
በገንዘብ ማገልገል
በገንዘብ ማገልገል
በገንዘብ ማገልገል
ክለሣ
ገንዘብ መገልገያ ነው ብለናል
የተሣሣተ እይታ እና አያያዝ ካለ ግን ከጌታ ጋር ያለንን ግንኙነት የሚያበላሽ አደገኛ ሁኔታ ውስጥ
የሚያስገባን ነገር ነው
~ ከወደድነው የሐጥያት ሁሉ ምንጭ ነው
~ የእግዚአብሔርን ቦታ የሚተካ ጌታ
~ አታላይ ነው
~ በመንግስተ ሰማየት መንገድ ላይ ያለ ወጥመድ ነው
በገንዘብ ማገልገል ማለት
~ ከአጠቃቀሞ ጠናማነት ጀሞ ለሌሎች መቆረስን የሚያካትት ነው
~ በወንጌል አገልግሎ ላይ በቀጥታም በሌላም አስዋጽዖ ማድረግ ማለት ነው
~ ከትርፍ / ሲተርፉ መስጠት ሳይሆን ከልብ ትዳርን አስከ መጣል በሚመስል መስጠት መስጠት ማለት
ነው።
በገንዘብ የምናገለግልባቸው 6 መንገዶች አሉ ብለን 3 አይተን ነበር
~ መባ
~ በኵራት
~ ስጦታ
ዛሬ የተቀሩትን 3 ቱን እናያለን
4. በበጎ አድራጎት ስራ ላይ በማዋል ነው
በጎ ማድረግ ለተቸገሩት እና እርዳታችንን ለሚፈልጉ መዘርጋት በፍላጎት የሚደረግ ጉዳይ ሳይሆን
የክርስቲያናዊ ግዳታ ነዉ
በጎ ማድረግ እግዚአቢሔር ደስ ከሚሰኝበት አገልግሎታችን መካከል አንዱ ነው
ሐዋርያት የአገልግሎትቸው አንድ አካል እንዲያደርጉ አደራ የተባሉበት ጉዳይ ነው
የክርስቶስ ፍቅር እና ርህራሄ ያለን መሆኑ የሚያሳይ ጉዳይ ነዉ
“ንጹሕ የሆነ ነውርም የሌለበት አምልኮ በእግዚአብሔር አብ ዘንድ ይህ ነው፤ ወላጆች የሌላቸውን
ልጆች ባልቴቶችንም በመከራቸው መጠየቅ፥ ....።” — ያዕቆብ 1፥27
“ነገር ግን መልካም ማድረግን ለሌሎችም ማካፈልን አትርሱ፤ እንዲህ ያለው መሥዋዕት
እግዚአብሔርን ደስ ያሰኘዋልና።”— ዕብ 13፥16
ገላትያ 2
⁹ ደግሞ የተሰጠኝን ጸጋ አውቀው፥ አዕማድ መስለው የሚታዩ ያዕቆብና ኬፋ ዮሐንስም እኛ ወደ
አሕዛብ እነርሱም ወደ ተገረዙት ይሄዱ ዘንድ ለእኔና ለበርናባስ ቀኝ እጃቸውን ሰጡን፤
¹⁰ ድሆችን እናስብ ዘንድ ብቻ ለመኑን፥ ይህንም ደግሞ ላደርግ ተጋሁ።
“ነገር ግን የዚህ ዓለም ገንዘብ ያለው፥ ወንድሙም የሚያስፈልገው ሲያጣ አይቶ ያልራራለት
ማንም ቢሆን፥ የእግዚአብሔር ፍቅር በእርሱ እንዴት ይኖራል?” — 1 ኛ ዮሐንስ 3፥17
“አምላክህ እግዚአብሔር በሰጠህ በአገርህ ደጅ ውስጥ ከሚኖሩ ከወንድሞችህ አንዱ ቢደኸይ፥
ልብህን አታጽና፥ በድሀው ወንድምህ ላይ እጅህን አትጨብጥ።” — ዘዳግም 15፥7
5. አስራትን በመክፈል
አስራትን በተመለከተ እንደዚች ቤ/ክ ሰፊ ክፍተት አለ
ይህ ትምህርት እንዲዘጋጅ የተፈለገውም ከዚህ በመነሳት ነው
ያለው ችግር ምንድን ነዉ?
1 ኛ ሰዉ አስራት አይከፍልም የመድረክ አገልጋዮችም ጭምር
2 ኛ የሚከፈለውም በትክክለኛ ጊዜ ኣይከፍልም አብዛኛው ሰው ደስ ባለው ጊዜ ነው የሚከፍልው
3 ኛ በዚህም ጊዜ ቢሆን ትክክለኛ መጠን አይከፍልም ጥቁት ሰው ብቻ በዚህ ልክ ተጠንቅቆ ይከፍላል
።
ለምን? ያለማወቅ ነው? አደለም ታደያስ? በአመት አንድ ጊዜ ት/ት ይሰጣል
1 ኛ: እግዚአብሔርን ያለማመን ጉዳይ ነዉ
ሰዉ አስራት በመክፈሉ የሚጎድልበት ይመስለዋል
እግዚአብሔር ሰጪ ነዉ ብሎ ያለማመን ጉዳይ ነዉ
እግዚአብሔር ግን ስጡኝ እና ፍትኑኝ የሚጎድልባችሁ ስትሰጡ ሳይሆን ሳትሰጡ ስትቀሩ ነዉ
“በቤቴ ውስጥ መብል እንዲሆን አሥራቱን ሁሉ ወደ ጎተራ አግቡ የሰማይንም መስኮት
ባልከፍትላችሁ፥ በረከትንም አትረፍርፌ ባላፈስስላችሁ በዚህ ፈትኑኝ፥ ይላል የሠራዊት ጌታ
እግዚአብሔር።”
— ሚልክያስ 3፥10
በአዲስ ኪዳን አገልግሎቱን መደገፉን ስቶ መቀበል ዘርቶ ማጨድ ይለዋል ፍሊ 4:15 -17
2 ኛ፡ የእራስ ወዳድነት ጉዳይ ነዉ
ገንዘቡ ለቤ/ክ ይልቅ እኔን ያስፈልገኛል ብሎ ማሰብ ነው
መክፈል እንዳለበት እያወቀ ብሰራበት ብጠቀምበት በሚል ሀሳብ በመያዝ ሌላ ጊዜ ለመስጠት
ያቆየዋል
ሌላ ጊዜ ሌላ ፈተና መጥቶ ሀሳብ ይቀየራል ወይም ገንዘቡ ያሣሣው እና መከፈሉ ይቀራል
ኣሚል 3 ሁል ጊዜ መብል እንዲኖር
በጊዜው መስጠት ይኖርበታል በሣምነት በወር እና ለጥቂቶች በ 3 ወር
3 ኛ፡ በታማኝነት አለመክፈል
በአዲስ ኪዳን አስራት 1/10 ኛ አይደለም ሁለንተናን /እራስን እስከ መስጠት ነው
ቢያንስ ግን ሰዉ 10 ኛውን መስጠት ይኖርበታል። ነገር ግን 10 ኛውን እራሱ ሰዉ አይከፍልም
2 ኛ ቆሮ 9
⁶ ይህንም እላለሁ፦ በጥቂት የሚዘራ በጥቂት ደግሞ ያጭዳል፥ በበረከትም የሚዘራ በበረከት ደግሞ
ያጭዳል።
⁷ እግዚአብሔር በደስታ የሚሰጠውን ይወዳልና እያንዳንዱ በልቡ እንዳሰበ ይስጥ፥ በኀዘን ወይም በግድ
አይደለም።
ስለ አስራት አንዳንድ ነገሮችን እናንሣ
አስራትን ማን ነው መክፈል ያለበት
ለዚህ ጥያቄ መልስ ለማግኘት ለመጀመሪያ ጊዜ በመሃላ ሊስጥ ቃል የገባው ያዕቆብን ሊስጥ
የተነሣበትን ሀሳብ ማየት ጥሩ ነው።
ያዕቆብ በራሱ ጊዜ ተነሣስቶ አስራቱን ሊሰጥ ቃል የገባ ሰው ነው
ምክንያቱ ደግሞ እግዚአብሔር የሚባለውን የሚጠጣውን እና የሚለብሰውን እግዚአብሔር
ስላላሣጣው ነው
ዘፍጥረት 28
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
²⁰ ያዕቆብም እንዲህ ብሎ ስእለት ተሳለ፦ እግዚአብሔር ከእኔ ጋር ቢሆን፥ በምሄድባትም በዚች
መንገድ ቢጠብቀኝ፥ የምበላውንም እንጀራ የምለብሰውንም ልብስ ቢሰጠኝ፥
²¹ ወደ አባቴ ቤትም በጤና ብመለስ፥ እግዚአብሔር አምላኬ ይሆንልኛል፤
²² ለሐውልት የተከልሁት ይህም ድንጋይ የእግዚአብሔር ቤት ይሆናል፤ ከሰጠኸኝም ሁሉ ለአንተ
ከአሥር እጅ አንዱን እሰጥሃለሁ።
ስለዚህ አስራትን መክፈል የሚገባው እግዚአቢሔር የሚያስፈልገውን የሰጠው ሰዉ ነዉ
የበረከቱ ምንጭ እራሱ እግዚአብሔር መሆኑን የሚያምን ሁሉ ነው
የተረፈው ብዙ ያለው አገልጋዮች የፈለጋ አይደለም
የሚያስፈለገውን እግዚአብሔር የሰጠው ሰዉ ሁሉ ነው
ለምንድን ነው መክፈል ያለበት?
ለቤ/ክ አገልግሎት እና ለአገልጋዮች አስፈላጊውን ነገር ለማድርግ ነው
የተቸገሩትን ደካሞችን ለመርዳት ነው
ዘዳግም 14
²² ከእርሻህ በየዓመቱ ከምታገኘው ከዘርህ ፍሬ ሁሉ አሥራት ታወጣለህ።
…
²⁷ ድርሻና ርስት ከአንተ ጋር ስለሌለው በአገርህ ደጅ ውስጥ ያለውን ሌዋዊ ቸል አትበል።
²⁸ በየሦስተኛው ዓመት መጨረሻ በዚያ ዓመት የፍሬህን አሥራት ሁሉ አምጥተህ በአገርህ ደጅ ውስጥ ታኖረዋለህ፤
²⁹ ሌዋዊውም፥ ከአንተ ጋር ክፍልና ርስት የለውምና፥ በአገርህም ደጅ ያለ መጻተኛ ድሀ አደግም መበለትም
መጥተው ይበላሉ ይጠግባሉም፤ ይኸውም አምላክህ እግዚአብሔር በምታደርገው በእጅህ ሥራ ሁሉ ይባርክህ ዘንድ
ነው።
እንዴት ነው የሚሰጠው
ገብቶን እና ደስ እያለን እንጂ ግድ ሆኖብን መስጠት የለብንም
የሚሰጥ በልግስና እንጂ ብድራት ፍለጋ መሆን የለበትም
እኛ እራሱ የጌታ መሆናችን ተረድተን የእኛ የሆነው ሁሉ የእርሱ መሆኑን በማመን ልንሰጥ ይገባል። አስራት
የቸርነት ጉዳይ ሳይሆን የመታመን ጉዳይ ነው። ስራቃችሁኛል!
6. ገንዘባችን ከክፉ ዓላማ በመጠበቅ
ገንዘብ አቅም ነው። ገንዘብ ያለዉ ብዙ ነገር የማድረግ አቅም አለው።
ገንዘባችን ከእግዚአብሔር መንግስት ሀሳብ ጋር ተቃራኒ ለቆመ ነገር ሀይል መሆን የለበትም።
“ኢየሱስ ግን አሳባቸውን አውቆ እንዲህ አላቸው፦ እርስ በርስዋ የምትለያይ መንግሥት ሁላ
ትጠፋለች፥ እርስ በርሱ የሚለያይ ከተማም ሁሉ ወይም ቤት አይቆምም።” — ማቴዎስ 12፥25
ልናፈርሰው የተሰማራንበትን የሰይጣንን መንግስት የሚገነባ ነገር ልናደርግ አይገባንም
በፀሎታችን በትምህርቶችን በህይወታችን አንድ አይነት አቌም ከሌለን ለጠላት ምቹ እድል ነው
የሚፈጥረው
ልጆቻችን በሱስ እንዳይያዙ እየፀለይን እየመከረን በገንዘባችን በዚህ ተቃራኒ ብንቶም አይሆንም
እዚህ ጋር የሰሞኑን የቤ/ክ መመሪያ ላንሣ