የጤፍ ሽያጭ እና የግዢ ውል ስምምነት ሰነድ

You might also like

Download as docx, pdf, or txt
Download as docx, pdf, or txt
You are on page 1of 3

ቀን 30/12/2014 ዓ.

የጤፍ ሽያጭ እና የግዢ ውል ስምምነት ሰነድ

 ውል ሰጪ የኩዩ ሀረሰዴን ኃ/የተ/የገበሬዎች ዩኒዬን ድርጅት

አድራሻ፡- ኦሮሚያ ሰሜን ሸዋ ዞን ኩዩ ወረዳ ቦንዴ ጊዳቦ ቀበሌ ገበሬ ማህበር

 ውል ተቀባይ ኤ.ቢ.ኤ.ዋይ.ኤስ ትሬዲንግ ስራ ኃ/የተ/የግ/ማ

አድራሻ፡- አ/አ ከተማ አራዳ ክ/ከተማ ወረዳ 07 የቤት ቁጥር 576 ስልክ +251923666611/0910071223

 ውሉ በፍትሐ-ብሔር ሕግ አንቀፅ 1731/2005 መሰረት በውል ሰጪ እና በውል ተቀባይ መካከል የተደረገ


ውል ነው፡፡
 የውሉ ዝርዝር እንደሚከተለው ይሆናል፡፡

አንቀፅ አንድ
የወሉ አላማ
 ሻጭ ወይም ውል ሰጪ ያለውን ነጭ ጤፍ እና ቀይ ጤፍ ምርት በወቅቱ ገበያ ሁኔታ ትርፍ ለማግኘት
ለተቋቋመው ውል ተቀባይ ድርጅት በሽያጭ ለማቅርብ ውል ተቀባይም ለመግዛት የተደረገ ውል ነው፡፡
አንቀፅ ሁለት
የወሉ ዘመን
1. ይህ ውል ከነሀሴ 30 ቀን 2014 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ነሀሴ 30 ቀን 2015 ዓ.ም ድረስ የፀና ይሆናል፡፡
2. ውሉ ለማደስ ሁለቱ ወገኖች ሲስማሙና አዲስ ውል በፅሁፍ ሲዋዋሉ ይህ ውል ቀሪ ይሆናል፡፡
አንቀፅ ሶስት
የሻጭ መብትና ግዴታ
1. ውል ሰጪው ወይም ሻጭ በውል ተቀባይ በተጠየቀ ጊዜ የእህል ዓይነት ነጭ ጤፍ እና ቀይ ጤፍ
በአንድ ዓመት ውስጥ ደረጃውን የጠበቀ ንፁህ ጤፍ ባዕድ ነገር ያልተቀላቀለበት 8100(ስምንት ሺህ
አንድ መቶ) ኩንታል ከነሀሴ 30/12/2014 ዓ.ም እስከ ነሀሴ 30/12/2015 ዓ.ም ድረስ በውል ተቀባይ
በተጠየቀ ጊዜ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ የማቅረብ ግዴታ አለበት፡፡
2. የውል ተቀባይ ዋና መስሪያ ቤት አ/አ ሲሆን ውል ሰጪም በሽያጭ ለማቅረብ የተዋዋለውን ጤፍ
በየግዜው በተፈለገው መጠን ልክ በራሱ ትራንስፖርት ወጪ አጓጉዞ ውል ተቀባይ ባለበት አዲስ አበባ
ወይም የውል ተቀባይ ፋብሪካ ያለበት ሱሉልታ ከተማ የማስረከብ ግዴታ አለበት፡፡
3. ሻጭ በስራ ሂደቱ ላይ የሚከሰቱ ማናቸውም ጉድለቶች እና የሚፈጠሩ ብልሽቶች ለምሳሌ ምርቱ
ከማሳ በሚሰበሰብት ጊዜ የዝናብ ውሀ ነክቶት የእህሉ ቃና የተቀየረ ከሆነ እና ባዕድ ነገሮች አፈርና
ሌሎች ነገሮች የተቀላቀለበት ከሆነ ውል ተቀባዩ የማይቀበለው መሆኑን በማወቅ ያቀረበውን ምርት
መልሶ በመውሰድ በምትኩ በውሉ መሰረት ጥራት ያለው እህል ብቻ የማቅረብ ግዴታ አለበት፡፡
4. ሻጭ በሽያጭ ላቀረበው እህል ባቀረበው መጠን ልክ የወቅቱን ገበያ ያማከለ የሽያጭ ዋጋ ምርቱን
ለግዥ ከአቀረበበት ግዜ ጀምሮ በምቀጥሉት ተከታታይ 10 ቀናት ባለው ግዜ ውስጥ ክፍያ የማግኘት
መብት አለው፡፡

አንቀፅ አራት
የገዢ መብትና ግዴታዎች
1. የእህሉ ዋጋ በተመለከተ በገበያ ሁኔታ እና በወቅቱ ምክንያት አንዴ ከፍ ሌላ ግዜ ደግሞ ዝቅ በማለት
የዋጋ መቀያየር የሚከሰት በመሆኑ ውል ተቀባይ ባለው የገበያ ጥናት ባለሙያዎች ገበያውን አጥንቶ
የአንድ ኩንታል ጤፍ ዋጋ ተጣርቶ ባቀረበው ኩንታል ብዛት ልክ ክፍያ ለመፈፀም ግዴታ ገብቼ ይህንን
ውል ተፈራርመናል፡፡
2. ውል ተቀባዩ የቀረበለትን እህል በወቅቱ ገበያ ሁኔታ የሽያጩን ዋጋ እህሉ በውል ተቀባይ ዋና መስሪያ
ቤት አ/አ ካቀረበበት ግዜ ጀምሮ በሚቀጥሉት 10 ቀናት ውስጥ ለውል ሰጪው ክፍያ ለመፈፀም ግዴታ
አለበት፡፡
3. ውል ተቀባይ ወይም ገዢው በውል ሰጪው ደረጃውን እና ጥራቱን የጠበቀ እህል ቀርቦለት አልቀበልም
ለማለት አይችልም፡፡
አንቀፅ አምስት
የውሉ አስገዳጅነት
 ይህ ውል በፍትሐ-ብሔር ህግ አንቀፅ 1675፣1771 እና 2005 ድንጋጌ መሰረት በተዋዋዮች መካከል ውል
ሆኖ በፍትሐ-ብሔር ህግ አንቀፅ 1731 ድንጋጌ መሰረት ህግ ሆኖ ተዋዋዮችን የሚገዛ መሆኑን
ተስማምተን ተዋውለናል፡፡
አንቀፅ ስድስት
ህግን ማክበር
1. ውል ተቀባዩ ለትርፍ የተቋቋመ ድርጅት በመሆኑ በዚህ ውል መሰረት ውል ሰጪም የጤፍ ምርቱን
በሽያጭ ማቅረቡን የሚያቋረጥ ከሆነ በድርጅቱ ላይ ኪሳራ የሚደርስ በመሆኑ ውል ተቀባይ ላይ
ለሚደርሰው ኪሳራ ውል ሰጪው ያለአንዳች ምክንያት በፍትሐ-ብሔር ህግ አንቀፅ 1790 ድንጋጌ
መሰረት ኪሳራውን የመክፈል ግዴታ አለበት፡፡
2. ውል ተቀባይ በውሉ መሰረት የቀረበለትን የጤፍ እህል ያለ በቂ ምክንያት ካልወሰደና ወይም ወሰዶ
በውሉ ውስጥ በተጠቀሰው ግዜ ገደብ ውስጥ ክፍያ የማይፈፅም ከሆነ በውል ሰጪው ላይ ለሚደርሰው
እንግልት ብር 50,000.00 (ሀምሳ ሺህ) ክፍሎ ውሉ በህግ ፊት የፀና ይሆናል፡፡
 በውል ሰጪ በውል ተቀባይ መካከል በዚህ ውል አፈፃፀም ጋር በተያያዘ አለመግባባት ግጭት ወይም
ቅራኔ ቢፈጠር ሁለቱም ወገኞች በመመካከር ለመፍታት ተስማምተናል፡፡ ነገር ግን አለመግባባታችን
በመመካከር ለመፍታት ካልቻልን ጉዳዩን ለማየት ስልጣን ባለው ፍ/ቤት ለመውሰድ ተስማምተናል፡፡
ስለመስማማታችንም በውሉ ሰነድ ላይ ፈርመናል፡፡
 ይህ ውል በፍ/ብ/ሕ/ቁ 1731 2005 መሰረት በህግ ፊት የፀና ነው፡፡
 ይህ ውል ዛሬ ነሀሴ 30 ቀን 2014 ዓ.ም በአ/አ ከተማ ተፈፀመ፡፡ የውሉም ኮፒ በውል ተቀባይ እጅ
ይገኛል፡፡
ገዢ ስምና ፊርማ ሻጭ
ስም፡- ኤ.ቢ.ኤ.ዋይ.ኤስ ትሬዲንግ ስም፡- የኩዩ ወረዳ ሀረሰደን ኃ/የተ/የግ/ማ
ኃ/የተ/የግ/ማ ዩኒየን ድርጅት

ፊርማ ………………………….. ፊርማ …………………………..

ምስክሮች

ስም ………………………………. ስም ……………………………….

ፊርማ ……………………………. ፊርማ …………………………….

ስም ………………………………. ስም ……………………………….

ፊርማ ……………………………. ፊርማ …………………………….

እኛም ምስሮች ውል ሰጪው እና ውል ተቀባዩ ሲስማሙና ሲዋዋሉ አይተን በውሉ ሰነድ ላይም
ፈርመናል፡፡

You might also like