Download as docx, pdf, or txt
Download as docx, pdf, or txt
You are on page 1of 26

የተዋህዶ የክህነት ማእረግ እና መጽሐፍ ቅዱስ

1.ክህነት በብሉይ ኪዳን

1.1 ክህነተ መልከጼዴቅ


መልከ ጼዴቅ የሳሌም ንጉስ እንደሆነ ይነገርለታል: በተዋህዶ አንዳንድ ትውፊቶች መሰረት ሳሌም የተባለች ኢትዮጵያ
ናት የሚል አመለካከት አለ: ነገር ግን የጥንት የእስራኤላውያን መጽሐፍ የሆነው መጽሐፈ ያሽር: የኢየሩሳሌም ንጉስ ነበር
ይለዋል መልከ ጼዴቅ በቅዱሳን መጻህፍት ልማድ መሰረት የተጻፈ የትውልድ ሃረግ የለውም: የዘመኑ ጥንት
አልተመዘገበም: ስለዚህ ማንነቱን ለማወቅ አንችልም: አንዳንድ ሰወች: አብርሐም አራቱን ነገስታት አሽንፎ በተለሰ ጊዜ
አስራት ስለሰጠው ራሱ ክርስቶስ ነው ይላሉ: አንዳንድ ሰወችም አይ የክርስቶስ ምሳሌ እንጅ ክርስቶስ አደለም ይላሉ::

በዘፍ 14:18 “የልኡል እግዚአብሔር ካህን ነበረ ይለዋል”

የዕብራውያን መጽሐፍ ጸሐፊም በ ም 7:3 ”አባትና እናት የሉትም: ለዘመኑም ጥንት ለሕይወቱም ፍጻሜ የለውም: ዳሩ
ግን በእግዚአብሔር ልጅ ተመስሎ ለዘላለም ካህን ሆኖ ይኖራል”

በማለት ክህነቱ በእግዚአብሔር ልጅ ምሳሌ ያደርገዋል: በቁጥር 4 ም አብርሐም ከ አስራቱ ስለሰጠው ይህ ሰው ምን


ያህል ትልቅ እንደነበር ይገልጻል: ይህን ካህን ሲያነሳ ግን ስለክህነቱ እንጅ አላማው ካህኑ መልከ ጼዴቅ አደለም::

የመልከ ጼዴቅ ክህነት በባህሪዋ: ለዘላለም የሆነች: (ዕብ 6:20፤ 7:3 :17 :20-21 ፤ መዝ 110:4) የሚሻል ስለሆነ
የሚሻለው አስራት የሚገባውየሆነ (ዕብ 7:4: 15-16) ናት::

1.1 የአሮን ክህነት


አሮን የሙሴ ወንድም የሆነ ዕብራዊ ነው የ 137 ከአመት እድሜ ባለጸጋው እንበረም ና ክዮካብድ(መጽሐፈ ያሽር
እድሜዋን 126 ያደርገዋል:: ) ከማርያም ቀጥሎ ከሙሴ ቀድሞ የተወለደ የቤተሰባቸው ሁለተኛ ልጅ ነው:: ይህ ለአሮን
የተሰጠው ክህነትን የማገዝ ስልጣን ለሌዊ ነገድ በሙሉ የደረሰው የአሮን ልጆች ናባድና አብድዩ በሲና ምድረ በዳ
እግዚአብሔር ካዘዘው እሳት ልዩ እሳት ባቀረቡ ጊዜ በሞት ስላለፉ ልጆችም ስላልነበራቸው: ከአሮን ልጆች ውጭ ያሉት
የሌዊ ነገድ ታጭቷል:: ለዚህ አገልግሎትም የሌዊ ልጆች አገልግሎት:- የማደሪያውን ስራ በመስራት: የመገናኛውን እቃ
ሁሉ በመጠበቅ: ለአገልግሎት ሁሉ የሚያስፈልገውን ሁሉ በመጠበቅ የአሮንን ልጆች ማገዝ ነው::

ካህን የሚለው የአማረኛ ቃል እና ኮህን የሚለው የእብራይስጥ ቃል ተመሳሳይ ድምጸት ያላቸው ናቸው: ካህናቱ ህዝቡን
ወክለው በመገናኛው ድንኳን የሚያገለግሉ ተራው ህዝብ የሌለው እግዚአብሔር ጋ የመገናኘት እድሉ ያላቸው ልኡካን
ናቸው:: እነዚህ ካህናት: በየቀኑ መስዋእት ያቀርባሉ: እጣን ያጥናሉ: መቅረዝ ያበራሉ: በየሳምንቱም አዲስ ዳቦ:
በመገናኛው ድንኳን የቆየውንም ይበላሉ::

1.1.1 ሌዋውያን

ከላይ ቀንጭበን እንዳየነው የመገናኛው ድንኳን ሰራተኞች በሁለት ይከፈላሉ: ካህናትና ካህናቱን የሚያግዙ
ሌዋውያን:: ሌዋውያን የሌዊ ነገዶች በሙሉ ሲሆኑ ካህናት ደግሞ ከዚሁ ከሌዊ ወገን የወጣው አሮንና ልጆቹ ለዚህ
ልዩ አገልግሎት በያህዌ ተመርጠዋል:: ስለዚህ: ካህናት ሁሉ ሌዋውያን ሲሆኑ ሌዋውያን ሁሉ ግን ካህናት አደሉም::

ሌዋውያን ካህናቱን ከሚያግዙበት አንድ ነገር ካህናቱ ብቻ መንካትና ማየት የሚፈቀድላቸውን የቅድስተ ቅዱሳን
እቃወችና የመገናኛውን ታቦት: በመጋረጃ ከጠቀለሉላቸው በሁዋላ ከቦታ ቦታ በመሽከም እና በማንቀሳቀስ ያግዛሉ
(ዘሁልቁ 3) ከእስራኤል ነገድ መካከልም የነርሱ ድርሻ ከካህናቱና ከእግዚአብሔር እንጅ ከሌላው እስራኤልጋ
ድርሻአ የላቸውም::(ዘዳ 18:1 : 17:9)

1.1.2 አስራት

የሌዊ ነገድና ሌዋውያን ካህናት ከሌሎች እስራኤላውያንጋ የሆነ ርስትና ድርሻ የላቸውም: ነገር ግን በህዝቡ አስራትና
ነው ሚተዳደሩት:: ዘኍልቍ 18:21-22
እግዚአብሔርም አሮንን አለው፦ በምድራቸው ርስት
በመካከላቸውም ድርሻ አይሆንልህም፤ በእስራኤል
ልጆች መካከል ድርሻህና ርስትህ እኔ ነኝ።
ለሌዊም ልጆች፥ እነሆ፥ በመገናኛው ድንኳን
አገልግሎት ስለሚያገለግሉ፥ የእስራኤልን ልጆች
አሥራት ርስት አድርጌ ሰጥቼአለሁ።

እነሱም: የአስራት አስራት ያቀርባሉ ይህም እንደ አስራትና ቁርባን ይቆጠርላቸዋል ይህም የማንሳት ቁርባን ይባላል:
(ዘኍልቍ 18:26-30)

ካህናትም: መባው: የእህል ቁርባን: የሃጢያት መስዋእት: የበደል መስዋእት ሁሉ ለእነርሱ


እንዲበሉት እግዚአብሔር ለአገልግሎታቸው ዋጋ ቀድሶላቸዋል: እንዲሁም የማንሳትና
የመወዝወዝ ቁርባንም ለካህናት: ና ለቤተሰቦቻቸው እንዲሆን እግዚአብሔር ሰጥቷቸዋል::
(ዘኍልቍ 18:8-20)

1.1.3 ልዩ የክህነት መጎናጸፊያ

የብሉይ ኪዳን ካህናት ከሌሎች ህዝቦች ይልቅ የተለየ የአለባበስ ስርአትም ነበራቸው:
ይህንም ልብስ ለመስራት እግዚአብሔር የጥበብ መንፈስ የሞላባቸው በልባቸው
ጥበበኞች የሆኑ ሰወች እንዲሰሩት ይደረግ ነበር:: ለካህናት ልብስ እንዲሆን:
1. የደረት ኪስ ኤፉድ
2. ቀሚስ
3. ዥንጉርጉር ሽሚዝ
4. መጠምጠሚያ
5. መታጠቂያ ለመስሪያ ያገለግላል::

1.1.3.1 የሊቀ ካህናቱ ልብስ ከላይ ወደታች::

ሊቀ ካህናቱ ከላይ መጠምጠሚያ ያደርጋል: ለክብርባ ለጌጥ ቆቦችን ያደርጋል: ከጥሩ ወርቅ
የተሰራ እንደ ማህተምም ቅድስና ለእግዚአብሔር የሚል ጽሁፍ የተቀረጸበት የቅጠል ቅርጽ
በሰማያዊ ፈትል አድርጎ በሊቀ ካህኑ ግንባር ላይ ይንጠለጠላል:: ሽሚዙም ዥጉርጉር ከሆነ ጥሩ
በፍታ ይሰራል: በሁለት የመረግድ ድንጋይ የ 12 ቱ የእስራኤል ነገድ ስም ስድስት ስድስት ተደርጎ
ይጻፍበታል: የወርቅ ፈርጥም ይደረግለትና በሊቀ ካህኑ ሁለት ትከሻወች ላይ ከሽሚዙ በላይ
ለእስራኤል ልጆች መታሰቢያ ያደርጋል:: በደረቱም ላይ ከኤፉዱም በላይ ኪስ ይሰራል: ኤፉዱ:
ከወርቅ: ሰማያዊ: ሐምራዊ: ና ቀይ ግምጃ ይሰራል:: በደረት ኪሱም ውስጥ ኡሪምና ቱሚም
ይደረጋል እነዚህም በሊቀ ካህናቱ ልብ ላይ ሲሆኑ: የእስራኤል ልጆችን ፍርድ የመሽከም
ምልክት ነው:: የወገብም መታጠቂይ በጥልፍ አሰራር ይሰራል:: የደረት ኪሱ አሰራር: እንደ
ኤፉድ አሰራር ሁኖ ርስመቱና ስፋቱ ስንዝር ሁኖ ከኤፉዱ ይደረባል:: ከላይ ወደታች በአራት
ተራ የከበሩ ድንጋዮች ይደረጋል በጎን በኩል ሶስት: በድምሩ አስራ ሁለት:: የመጀመሪያው ረድፍ
ላይ : ሰርድዮን: ቶጳዝዮን እና እንቁ ይደረግበታል፤ በሁለተኛው ረድፈ ላይ : በሉር: ሰንጴርና
አልማዝ ይደረጋል፤ በሶስተኛው ረድፍ ላይ ያክንት: ኩልቄዶን: አሜቴስጢኖስ ይደረግበታል፤
በአራተኛውም ላይ ተራ ቢረሌ መረግድ እና ኢያስጲድ በወርቅ ፈርጥ ይደረግበታል:: እነዚህም
እይንዳንዳቸው ላይ አንድ የእስራኤል ነገድ ስም እንደማህተም ይቀረጽበታል:: ከውስጥም እንደ
ፓንት ከወገባቸው እስከ ጭናቸው ሚደርስ የውስጥ ሱሪ ያደርጋሉ:: ከስር በቀሚሱ ዘርፍም:
የመአዛ ሽታ የሆነ የሮማን ፍሬና: ትናንሽ ደወል ያደርጋል(ዘጸ 28)(እያንዳንዱ የልብሱ ትርጉም
የክርስቶስ ጥላ ነውና ይህ ራሱን የቻለ ርእስ ነው)
1.1.3.2 የካህናት ልብስ::
ዝርዝሩና አሰራሩ ካላይ ስላለ ከጌጦቹ ውጭ ተራው ካህን ጥምጣም: መጎናጸፊያ የውስጥ ሱሪ እና የወገብ መታጠቂያ
ብቻ ያደርጋል::

1.1.4 ባርኮታቸው

ካህናት እስራኤልን ሲባርኩ እንኳ እንዲባርኩበት የተሰጠው በራሱ በእግዚአብሔር እንጅ እንደፈለጉ በራሳቸ
አያባርኩም ነበር:

ለአሮንና ለልጆቹ ንገራቸው፦ የእስራኤልን


ልጆች ዘኍልቍ 6:23-26
“ስትባርኩአቸው እንዲህ በሉአቸው፦
እግዚአብሔር ይባርክህ፥ ይጠብቅህም፤
እግዚአብሔር ፊቱን ያብራልህ፥ ይራራልህም፤
እግዚአብሔር ፊቱን ወደ አንተ ያንሣ፥
ሰላምንም ይስጥህ።
እንዲሁ ስሜን በእስራኤል ልጆች ላይ
ያደርጋሉ፤ እኔም እባርካቸዋለሁ።”

1.1.5 ቁርባን(መስዋእት)

መስዋእቶች አምስት አይነት ናቸው: በእነዚህ የመስዋእት አግልግሎቶች: ሌዋውያን: ካህናትና ሊቀካህኑ ሚና
ይወስዳሉ::

1.1.5.1 የሚቃጠል ቁርባን(ዘሌ 1: 6:8-13)

በሌሎች አራቱ መስዋእቶች ግማሹ ለካህናት ቀለብ ሲሆን በዚህ ግን መስዋእት አቅራቢው ሰው ለሰራው ሰው
ቤዛ ስለሆነ አንድም እንኳን ሳይቀር በመሰዊያው ላይ ይቃጠላል::

1.1.5.2 የእህል ቁርባን(ዘሌ : 6:14-23)

ይህ ከእህሉ ዘይት ጨምሮ የሚያቀርበው መስዋአወት ሲሆን ካህኑ ወስዶ ያቃጥለዋል የቀረውን ደግሞ ለራሱ
ቀለብ እነዲሆን ይወስደዋል:

1.1.5.3 የደህንነት ቁርባን (ዘሌ 3: 6:14-23)

ይህ መስዋእት ሶስት አይነት ነው: የምስጋና: የስእለት: እና የነጻ ፈቃድ መስዋእት ነው::

1.1.5.4 የሃጢያት ቁርባን(ዘሌ 4:1-5: 6:24-30)

ይህ መስዋእት ሚቀርበው ሰው ሳያውቅ ለሚሰራው ሃጢያት ነው:: በዚህ መስዋእት ላይ ካህኑም ተካፋይ
ይሆናል::

1.1.5.5 የበደል ቁርባን(ዘሌ 5:14-6:7)

የበደል መስዋእትና የሃጢያት መስዋእት ተመሳሳይነት ያላቸው ናቸው: ነገር ግን በበደል መስዋእት ሃጢያቱን
ባላወቀ ጊዜ እንደሃጢያት አይቆጠርበትም: ነገር ግን ሃጢያት መሆኑን ባስተዋለ ጊዜ ወዲያውኑ ሃጢያት
ይሆንበታልና መስዋእት ማቅረብ ይኖረበታል::
1.1.6 ልዩ ቁርባን

በጣም ብዙ አይነት ቁርባኖች ቢኖሩም ጽሁፉን ለማሳጠር ያክል ግን ሶስቱን ዋና ዋና ቁርባኖች


እንመለከታለን::

1.1.6.1 የጠዋትና የማታ ቁርባን(ዘጸ 28:38-39)

በዚህ ቁርባን ሁለት ነውር የሌለባቸው አንድ አመት ተባእት ጠቦቶች ይዘጋጃሉ አንደኛው በጠዋት
ሁለተኛውም በማታ የሚቃጠል መስዋእት ሁነው ይቀርባሉ::(ዘጸ 28:38-39፤ ዘዳ 28:1-8)

1.1.6.2 የፋሲካ ቁርባን (ዘጸ 12)

ይህኛው መስዋእት ለየት የሚያደርገው ጠቦቱን ካህናት ብቻ ሳይሆኑ ህዝቡ ሁሉ ቤተሰብ ቤተሰብ ሁነው
በየቤታቸው የሚመገበው ነው:: (ይህም ራሱን የቻለ ብዙ ሚጻፍበት ነው)

1.1.6.3 የታላቁ ሰንበት ቁርባን(ዘሌ 16)

በዚህ ቁርባን አንድ ወይፈን ለሃጢያት መስዋእትና ሁለት ፍየል ይቀርባል አንዱ ፍየል ወደበረሃ የሚለቀቅ
አንዱም ለሚቃጠል መስዋእት ይሆናል ይህም ለአሮንና ልጆቹ ማስተሰረያ ነው: ሌላ አነድ አውራ በግና ሁለት
ፍየል ለእስራኤል ልጆች ይቀርባል አንደኛው ለሃጢያት መስዋእት አንደ`ኛውም ፍየል የእስራኤልና ሃጢያት
ተሽክሞ በበረሃ የሚለቀቅ ይሆናል: ፍየሉን ተሽክሞ አንድ ሰው ወደበረሃ ይለቀውና ሲመለስ በውሃ ይታጠብና
ወደ ህዝቡ ይቀላቀላል::

2. ክህነት በአዲስ ኪዳን:

በብሉይ ኪዳን እንዳየነው የካህናት አገልግሎት ህዝቡን ወክሎ ወደ እግዚአብሔር መቅረብ መስዋእት ማቅረብ
ማጠን ሲሆን፤ እግዚአብሔርን ወክሎ ወደ ህዝቡ ደግሞ ሚመጡ ነብያት ነበሩ እግዚአብሔርን ወክለው ሚገዙም
ጥንቱን መሳፍንት በኋላም ነገስታት ናቸው::

የክህነት መሰረታዊ ሐሳብ በእግዚአብሔርና በሰው መካከለኛ መሆን ሰለነበር በአዲስ ኪዳን ይህ ስርአት በመስቀለ
ክርስቶስ አብቅቶለታል:: አሁን በአዲስ ኪዳን በሰው እና በእግዚአብሔር መካከል ያለ መካከለኛ ክርሰቶስ ኢየሱስ
በመሆኑ በአንድያችን ሊቀ ካህናት መካከለኛነት መክንያት እግዚአበሔርን በቀጥታ የመገናኘት እድሉን ስላገኘን
ከሰው የተለዩ ካህናት አስፈላጊወች አደሉም:: ክርስቶስ አንድ ጊዜ ራሱን በማቅረብ ላሃጢያት የሚቀርብን መስዋእት
ሁሉ ከንቱ አድርጎታል

ፊተኛይቱም ድንኳን በዚህ ገና


ቆማ ሳለች፥ ወደ ቅድስት
የሚወስደው መንገድ ገና
እንዳልተገለጠ መንፈስ ቅዱስ
ያሳያል።
ይህም ለአሁኑ ጊዜ ምሳሌ ነው፥ እንደዚህም መባና መስዋዕት
ይቀርባሉ፤ እነዚህም እስከ መታደስ ዘመን ድረስ የተደረጉ፥ ስለ
ምግብና ስለ መጠጥም ስለ ልዩ ልዩ መታጠብም የሚሆኑ የሥጋ
ሥርዓቶች ብቻ ናቸውና የሚያመልከውን በህሊና ፍጹም
ሊያደርጉት አይችሉም።
ነገር ግን ክርስቶስ ይመጣ ዘንድ ላለው መልካም ነገር ሊቀ
ካህናት ሆኖ፥ በምትበልጠውና በምትሻለው በእጆችም
ባልተሠራች ማለት ለዚህ ፍጥረት ባልሆነች ድንኳን፥
የዘላለምን ቤዛነት አግኝቶ አንድ ጊዜ ፈጽሞ ወደ ቅድስት በገዛ
ደሙ ገባ እንጂ በፍየሎችና በጥጆች ደም አይደለም።
የኮርማዎችና የፍየሎች ደም በረከሱትም ላይ የተረጨ የጊደር
አመድ ሥጋን ለማንጻት የሚቀድሱ ከሆኑ፥
ነውር የሌለው ሆኖ በዘላለም መንፈስ ራሱን ለእግዚአብሔር
ያቀረበ የክርስቶስ ደም እንዴት ይልቅ ሕያውን እግዚአብሔርን
ልታመልኩ ከሞተ ሥራ ሕሊናችሁን ያነጻ ይሆን? (ዕብ 9:8-14)
ስለዚህም ስለእኛ የሚቀርብ የሃጢያት መስዋእት ከሌለ ሰለ እኛ የሚቀርብ መስዋእት አቅራቢም አያስፈልገም: ልክ
እንደዚሁ ሁሉ ስለ እኛ የሚታይ በሰው እና በእግዚአብሔር መካከል የሚቆም ሊቀ ካህናትም አያስፈልግም ምክንያቱም
ሊቀ ካህናት እያለ ሌላ ሊቀ ካህናት አይተካም: ለእኛ ደግሞ የማይሞትና ለዘላለም የሆነ ስለእኛ ለዘላለም ሊያማልድልን
ወደ ሰማይ የራሱን አንድ ጊዜ ያቀረበውን ደም ይዞ የገባ የማይሞት ሞትን አሽንፎ የተነሳ ሊቀ ካህናት አለን:: (

“ክርስቶስ በእጅ ወደ ተሰራች፥ የእውነተኛይቱ ምሳሌ ወደ ምትሆን ቅድስት አልገባምና፥ ነገር


ግን በእግዚአብሔር ፊት ስለ እኛ አሁን ይታይ ዘንድ ወደ እርስዋ ወደ ሰማይ ገባ።” (ዕብ 9:24)

“እነርሱም እንዳይኖሩ ሞት ስለ ከለከላቸው ካህናት የሆኑት ብዙ ናቸው፤ እርሱ ግን ለዘላለም


የሚኖር ስለሆነ የማይለወጥ ክህነት አለው፤ ስለ እነርሱም ሊያማልድ ዘወትር በሕይወት
ይኖራልና ስለዚህ ደግሞ በእርሱ ወደ እግዚአብሔር የሚመጡትን ፈጽሞ ሊያድናቸው
ይችላል።” ዕብ 7:25

የቀድሞው ክህነት እንኳን የተሰራው ለአሁኑ የክርስቶስ ክህነት ምሳሌ ነው::(ዕብ 9:9) ይህም
ክህነት በክርስቶስ ፍጻሜውን አግኝቷል ስለዚህ ከዚህ በኋላ ሃጢያትን ብንሰራ የሚቀርልን
የሃጢያት መስዋእት የለም በዚያው ስርየትን ስንቀበል እንኖራለን: የብሉይ ሊቀ ካህናት
በየጊዜው መስዋእት እያቀረበ ያማልድ የነበረ ቢሆንም የአዲስ ኪዳኑ ሊቀ ካህናት ኢየሱስ ግን
አነድ ጊዜ ብቻ መስዋእት በማቅረብ ያንን ይዞ በመግባት በሰማይ አሁን ያማልደናል(ሮሜ 8:34)

ከዛ ባለፈ ግን አማኞች ሁሉ በሊቀ ካህኑ በኢየሱስ ስር ያሉ ካህናት ናቸው: ስለዚህም ወደ


እግዚአብሔር ለመግባት ቀጥተኛ የሆነ መንገድ በክርስቶስ በኩል ስለተከፈተልን ያለማንም
ከልካያ ራሳችን አንገባለንና ልዩ ልኡክ ካህናት አያስፈልጉንም::

“እንግዲህ፥ ወንድሞች ሆይ፥ በመረቀልን በአዲስና በሕያው መንገድ ወደ ቅድስት በኢየሱስ


ደም በመጋረጃው ማለት በሥጋው በኩል እንድንገባ ድፍረት ስላለን፥ እንግዲህ፥ ወንድሞች
ሆይ፥ በመረቀልን በአዲስና በሕያው መንገድ ወደ ቅድስት በኢየሱስ ደም በመጋረጃው ማለት
በሥጋው በኩል እንድንገባ ድፍረት ስላለን፥”(ዕብ 10:19-21)

ይህም ወደ ቅድስት የመግባት ድፍረታችን ሁላችን ካህናት የመሆናችንን ነገር ያስረዳል::

እንግዲህ፥ ወንድሞች ሆይ፥ በመረቀልን በአዲስና በሕያው መንገድ ወደ ቅድስት በኢየሱስ ደም


በመጋረጃው ማለት በሥጋው በኩል እንድንገባ ድፍረት ስላለን፥(1 ጴጥ 2:9)
ጴጥሮስ በዚህ ሁሉንም አማኞች ካህናት ብሎ በመጥራቱ: እያንዳንዳችን መካናናችንን እንጅ እንደ ኦርቶደዶክሶች
የተሻረውን የብሉዩን ስርአት ይዞ የተለዩ ካህናት ሚባሉ የተለየ ልብስ ሚለብሱ: በተለየ ሚባርኩ: ቁርባን ሚያቀርቡ:
ካህናት አለመኖራቸውን ያሳያል::

በተጨማረሪም በዮሐንስ ራእይ ላይ

መንግሥትም ለአምላኩና ለአባቱም ካህናት እንድንሆን ላደረገ፥ ለእርሱ ከዘላለም እስከ


ዘላለም ድረስ ክብርና ኃይል ይሁን፤ አሜን።(ራእይ 1:6)
በማለት የአማኞችን አለማቀፋዊ ካህናትነት ይገልጻል:: ስለዚህም ለአባቱ ካህናትና ያደረገን ጌታ ምስጋና ለእርሱ ይሁን:
ነገር ግን ይህን በእርሱ በኩል ያገኘነውን መቀራረብ በክህነት ብቻ የቀረ ሳይሆን የአባትና የልጅም ስለሆነ: ልጅ አባቱን
ሂዶ ለማቀፍ በሰው አማላጆች በኩል እንደማይቀርብ ሁሉ በክርስቶስ በኩል ነውና ልጅነታችንን የተቀበልን እርሱ ብቻ
ካልሆነ በቀር ከእርሱ በላይ ሁኖ ከእኛም ልጀነት በልጦ አቀራራቢ ይሆን ዘንድም ቁርባን አቅራቢ ይሆን ዘንድም
የሚሾም ሌላ ቄስም ቢሆን: መልአክም ቢሆን ሰውም ቢሆን ማርያምም ብትሆን(ኦርቶዶከሶች ስለሚያመልኳት እንጅ
በተለየ ሁኔታ ለመጠቀስ ሚያበቃ ልዩ ማንነት የላትም) መካከለኛ የለም:: ስለዚህ ልጆች ስለሆንን እንደፈቃዱ አንዳች
ብንለምነው እኛኑ ራሳችንን ለመስማት ሁሌም ጆሮወቹ ወደኛ ናቸው(1 ዮሐ 5:4)

የክህነት አገልግሎት አንዱ መስዋእት ማቅረብ በመሆኑ: በእኛ የክህነት አገልግሎት ታዲያ የምናቀርበው መስዋእት
አለን? ብንል በድፍረት አወ አለ: ልንል እንችላለን:: ነገር ግን የሃጢያት መስዋእት አናቀርብም ምክንያቱም ይህ መስዋእት
አንዴ በክርስቶስ የተፈጸመ ነውና እና ለሃጢያታችን ስርየት አንዴ ጌታ ኢየሱስን በማመን ሊቀ ካህናቱ የሚጨርስልን
ጉዳይ እንጅ እኛ ምንጨነቅበት ጉዳይ አደለም(ዕብ 7:24-25) እርሱም በመስቀል ላይ አንዴ “ተፈጸመ” በማለት የዚህን
መስዋእት ጉዳይ አጠናቆታል(ዮሐ 19:30)

2.1 የአዲስ ኪዳን ካህናት መስዋእቶች

የካህናት አገልግሎት መካከል መስዋእት ማቅረብና ማጠን የአገልግሎታቸው ዋና እንደመሆኑ መጠን አማኞች
ሁላችንም እንደ ካህንነታችን የአዲስ ኪዳን ካህናትም ለእግዚአብሔር የምናቀርበው መስዋእት እና ዕጣን አለ::
ይሄውም:

2.1.1 የተሰበረ መንፈስ(ንስሃ)

“የእግዚአብሔር መሥዋዕት የተሰበረ መንፈስ ነው፥ የተሰበርውንና የተዋረደውን ልብ


እግዚአብሔር አይንቅም።” (መዝ 51:17)

“እግዚአብሔር ልባቸው ለተሰበረ ቅርብ ነው፥ መንፈሳቸው የተሰበረውንም ያድናቸዋል።”


(መዝ 34:18)

ለዘላለም የሚኖር ስሙም ቅዱስ የሆነ፥ ከፍ ያለው ልዑል እንዲህ ይላል፦ የተዋረዱትን ሰዎች
መንፈስ ሕያው አደርግ ዘንድ፥ የተቀጠቀጠውንም ልብ ሕያው አደርግ ዘንድ፥ የተቀጠቀጠና
የተዋረደ መንፈስ ካለው ጋር በከፍታና በተቀደሰ ስፍራ እቀመጣለሁ።(ኢሳ 57:15)

የጌታ የእግዚአብሔር መንፈስ በእኔ ላይ ነው፥ ለድሆች የምሥራችን እሰብክ ዘንድ


እግዚአብሔር ቀብቶኛልና፤ ልባቸው የተሰበረውን እጠግን ዘንድ፥ ለተማረኩትም ነጻነትን
ለታሰሩትም መፈታትን እናገር ዘንድ ልኮኛል።(ኢሳ 61:1 ሉቃ 4:17-19)

በመንፈስ ድሆች የሆኑ ብፁዓን ናቸው፥ መንግሥተ ሰማያት የእነርሱ ናትና።(ማቴ 5:3)

“እንዲህ ሲል፦ ሁለት ሰዎች ሊጸልዩ ወደ መቅደስ ወጡ፥ አንዱ ፈሪሳዊ ሁለተኛውም ቀራጭ።
ፈሪሳዊም ቆሞ በልቡ ይህን ሲጸልይ፦ እግዚአብሔር ሆይ፥ እንደ ሌላ ሰው ሁሉ፥ ቀማኞችና
ዓመፀኞች አመንዝሮችም፥ ወይም እንደዚህ ቀራጭ ስላልሆንሁ አመሰግንሃለሁ፤ በየሳምንቱ
ሁለት ጊዜ እጦማለሁ፥ ከማገኘውም ሁሉ አሥራት አወጣለሁ አለ። ቀራጩ ግን በሩቅ ቆሞ
ዓይኖቹን ወደ ሰማይ ሊያነሣ እንኳ አልወደደም፥ ነገር ግን፦ አምላክ ሆይ፥ እኔን ኃጢአተኛውን
ማረኝ እያለ ደረቱን ይደቃ ነበር። እላችኋለሁ፥ ከዚያ ይልቅ ይህ ጻድቅ ሆኖ ወደ ቤቱ ተመለሰ፤
ራሱን ከፍ የሚያደርግ ሁሉ ይዋረዳልና፥ ራሱን ግን የሚያዋርድ ከፍ ይላል።” (ሉቃ 18:19)
“የእግዚአብሔር መስዋእት የተሰበረ ልብ ነው: “ ተብሎ ተጽፎ እንዴት እንዴት ለአምላክ እጣን ላቀርብለት እችላለሁ?
በእውነት ትሁት ልብ መስዋእትም: ማራኪ ሽታ: እና አበባም ነው ለእግዚአብሔር“ ቅዱስ ቀለሜንጦስ ዘአሌክሳንድርያ
(2:293) (እነዚህ አባቶችን ስጠቅስ ከመጽሐፍ ቅዱስጋ ተስማሚ ሁነው ስላገኘኋቸው እንጅ ለእምነት መሰረት
የሚጠቀስ ሰው የለም: ሐዋርያት እንኳ ሌላ ጽሁፍ ጽፈው መንፈስ ቅዱስ ከገለጠላቸው ቅዱስ ቃሉ ካልተስማሙ
ተቀባይነት የላቸውም::)

2.1.2 የከንፈር ፍሬ(ምስጋና: አምልኮ)

ምስጋና የሚሠዋ ያከብረኛል፤ የእግዚአብሔርን ማዳን ለእርሱ የማሳይበት መንገድ ከዚያ


አለ።(መዝ 50:23)

እንግዲህ ዘወትር ለእግዚአብሔር የምስጋናን መሥዋዕት፥ ማለት ለስሙ የሚመሰክሩ


የከንፈሮችን ፍሬ፥ በእርሱ እናቅርብለት።(ዕብ 13:15)

እግዚአብሔርን ሁልጊዜ እባርከዋለሁ፥ ምስጋናውንም ዘወትር በአፌ ነው። (መዝ 34:1)

ማናቸውን ነገር ብታደርጉ ሁሉን ለእግዚአብሔር ክብር አድርጉት። (1 ቆሮ 10:31)

“የቤተክረስቲያን መስዋእት: ከነፍስ የሚወጣ የቃል እታን ነው:... በቅድስና ምትኖር ነፍስ ቅዱስ መሰዊያ እጣኑም ከእርሷ
የሚወጣ ጸሎት ነው ስንል ኤአምኑም” ቅዱስ ቀለሜንጦስ ዘአሌክሳንድርያ (2:531)

2.1.3 ፀሎት (እንደ ዕጣን)

የብሉይ ኪዳን ካህናት ከአገልግሎታቸው መካከል አንዱ ዕጣን ማጠን ነበር


አሮንም የጣፋጭ ሽቱ እጣን
ይጠንበት፤ በማለዳ በማለዳ
መብራቶቹን ሲያዘጋጅ ይጠነው።
ይህን በእግዚአብሔር ፊት ለልጅ ልጃችሁ የዘወትር
ዕጣን ይሆን ዘንድ አሮን በማታ ጊዜ መብራቶቹን
ሲያበራ ያጥነዋል። (ዘጸ 30:7-8)

ልክ እንደዚሁ የአዲስ ኪዳን ካህናት ምእመናንም የምናጥነው የዘወትር ልማዳችን የሆነው


እግዚአብሔር ደስ እያለው የሚምገው እጣናችን ከመንፈስ ቅዱስ ምልጃ የሚመጣው
ጽሎታችን ነው:: እንደ ኦርቶዶክሶች ሰው የጻፈውን ይዞ ማነብነብ ሳይሆን መንፈስ ቅዱስ
በየጊዜው ከእኛ የሚያፈልቀው የሆነ ጸሎት እንጅ (ሮሜ 8:26፤ ማቴ 6:7፤ ኤፌ 6:18፤ ይሁዳ
1:20 )

“ጸሎቴን በፊትህ እንደ ዕጣን ተቀበልልኝ፥ እጅ መንሣቴም እንደ ሠርክ መሥዋዕት ትሁን::”
መዝ 141:2

“መጽሐፉንም በወሰደ ጊዜ አራቱ እንስሶችና ሀያ አራቱ ሽማግሌዎች በበጉ ፊት ወደቁ፥


እያንዳንዳቸውም በገናንና የቅዱሳን ጸሎት የሆነ ዕጣን የሞላበትን የወርቅ ዕቃ ያዙ።” ራእ 5:8
ኢራኒየስ የተባለው የሁለተኛ ክፍለ ዘመን የቤ ተክርስቲያን አባት:
“በሚልኪያስ 1:11-14 የተጠቀሰው ዕጣን ቅዱስ ዮሐንስ በራእዩ እንደነገረን እጣን ማለት የቅዱሳን ጸሎት ነው::” ቅዱስ
ኢራኒየስ (1:574)
በማለት የአዲስ ኪዳን ምእመናን በትንቢት ጸሎታቸው እጣን ሁኖ እንደሚቀርብ ተናግሯል::

2.1.3 ወንጌልን መስክሮ ነፍሳትን ወደ መንግስቱ መጨመር

“ነገር ግን አሕዛብ በመንፈስ ቅዱስ ተቀድሰው የተወደደ መሥዋዕት ሊሆኑ፥ ለእግዚአብሔር


ወንጌል እንደ ካህን እያገለገልሁ” (ሮሜ 15:15)

“በዚያን ቀንም በኢየሩሳሌም ባለች ቤተ ክርስቲያን ላይ ታላቅ ስደት ሆነ፤ ሁሉም


ከሐዋርያትም በቀር ወደ ይሁዳና ወደ ሰማርያ አገሮች ተበተኑ።...
የተበተኑትም ቃሉን እየሰበኩ ዞሩ።” (ሐዋ 8:1-4)
2.1.4 ማንነትን ሙሉ ለሙሉ ማቅረብ::

“ብልቶቻችሁንም የዓመፃ የጦር ዕቃ አድርጋችሁ ለኃጢአት አታቅርቡ፥ ነገር ግን ከሙታን


ተለይታችሁ በሕይወት እንደምትኖሩ ራሳችሁን ለእግዚአብሔር አቅርቡ፥ ብልቶቻችሁንም
የጽድቅ የጦር ዕቃ አድርጋችሁ ለእግዚአብሔር አቅርቡ።” (ሮሜ 6:13)

“እንግዲህ፥ ወንድሞች ሆይ፥ ሰውነታችሁን እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝና ሕያው ቅዱስም


መሥዋዕት አድርጋችሁ ታቀርቡ ዘንድ በእግዚአብሔር ርኅራኄ እለምናችኋለሁ፥ እርሱም
ለአእምሮ የሚመች አገልግሎታችሁ ነው።” (ሮሜ 12:1)

“ገንዘብ የሚገዛውን የእጣን ፍሬ አልሰዋለትም: ይልቁንም ነገር ግን ሰውነቴን በመቀደስ: ያልተበከለች ነፍሴን: ቅዱሰም
መንፈሴን አቀርብለታለሁ” ጠርጡሊያን (3:42)

“እግዚአብሔር በእጣን: ሰውነትን በመጉዳት: እና በውድ ስጦታወች አይደሰትም: ነገር ግን በአምሮ በመታደሳችን ይደሰታል
እንጅ” ቅዱስ ላቅጣኒየስ (7:277)

2.2 መስዋእቱን የማቅረቢያ ስፍራ::

በብሉዩ ስርአት እንዳየነው የመስዋእት ማቅረቢያው ቀድሞ በበረሃ በመገናኛው ድንኳን ኋላም በቅዱስ ዳዊት
ታስቦ በሰሎሞን በተሰራው ቤተ መቅደስ ነበር: ኋላ ግን እግዚአብሔር ራሱ መጋረጃውን ቀዶ በነቅረብ በእኛ
መካከል በመሆኑ መቅደሱ ሰውነታችን በመሆኑ ልኡል በሰው እጅ በሰራው አያድርም ይልቁንም: ካህናቱ
እኛው: መስዋእት እኛው: መቅደስም እኛው ሁነን እንገለግለዋለን እንጅ::

“ኢየሱስም እንዲህ አላት፦ አንቺ ሴት፥ እመኚኝ፥ በዚህ ተራራ ወይም በኢየሩሳሌም ለአብ
የማትሰግዱበት ጊዜ ይመጣል። ገር ግን በእውነት የሚሰግዱ ለአብ በመንፈስና በእውነት
የሚሰግዱበት ጊዜ ይመጣል አሁንም ሆኖአል፤ አብ ሊሰግዱለት እንደ እነዚህ ያሉትን ይሻልና፤
እግዚአብሔር መንፈስ ነው፥ የሚሰግዱለትም በመንፈስና በእውነት ሊሰግዱለት
ያስፈልጋቸዋል።” (ዮሐ 4:21-24)

‘’ ነገር ግን ነቢዩ፦ ሰማይ ዙፋኔ ነው ምድርም የእግሬ መረገጫ ናት፤ ለእኔ ምን ዓይነት ቤት
ትሠራላችሁ? ይላል ጌታ፥ ወይስ የማርፍበት ስፍራ ምንድር ነው? ይህንስ ሁሉ እጄ የሠራችው
አይደለምን? እንዳለ፥ ልዑል የሰው እጅ በሠራችው አይኖርም።”(ሐዋ 7:48-50)

“ዓለሙንና በእርሱ ያለውን ሁሉ የፈጠረ አምላክ እርሱ የሰማይና የምድር ጌታ ነውና እጅ


በሠራው መቅደስ አይኖርም፤” (ሐዋ 17:24)
“ወይስ ሥጋችሁ ከእግዚአብሔር የተቀበላችሁት በእናንተ የሚኖረው የመንፈስ ቅዱስ ቤተ
መቅደስ እንደ ሆነ አታውቁምን? በዋጋ ተገዝታችኋልና ለራሳችሁ አይደላችሁም፤ ስለዚህ
በሥጋችሁ እግዚአብሔርን አክብሩ።” (|1 ቆሮ 6:19-20)

“እርሱም ዓለም የማያየውና የማያውቀው ስለ ሆነ ሊቀበለው የማይቻለው የእውነት መንፈስ


ነው፤ ነገር ግን ከእናንተ ዘንድ ስለሚኖር በውሥጣችሁም ስለሚሆን እናንተ ታውቃላችሁ።”
(ዮሐ 14:17)

“የሚወደኝ ቢኖር ቃሌን ይጠብቃል፤ አባቴም ይወደዋል ወደ እርሱም እንመጣለን በእርሱም


ዘንድ መኖሪያ እናደርጋለን።” (ዮሐ 14:23)

2.3 የሚለበሰው ልብስ::

በብሉይ ኪዳን ካህናት ለአገልግሎት የሚለብሱት ልብስ እንደነበረው ሁሉ በአዲስ ኪዳንም ካህናት የሆኑ
አማኞች ሁሉ የሚለብሱት ልብስ አለ:: እርሱም ጠቢባን የሚሰሩት ጨርቅ ሳይሆን እግዚአብሔር ራሱ
ያዘጋጀው ወደምድርም የላከው ጽድቃችን የሆነው ራሱ ክርስቶስ ነው::

“አቤቱ፥ ወደ ዕረፍትህ ተነሥ፥ አንተና የመቅደስህ ታቦት። ካህናቶችህ ጽድቅን ይልበሱ፥


ቅዱሳንህም ደስ ይበላቸው።” መዝ 132:8-9)

“ነገር ግን ጌታን ኢየሱስ ክርስቶስን ልበሱት፤ ምኞቱንም እንዲፈጽም ለሥጋ አታስቡ።” (ሮሜ
13:14)

“ለእውነትም በሚሆኑ ጽድቅና ቅድስና እንደ እግዚአብሔር ምሳሌ የተፈጠረውን አዲሱን ሰው


ልበሱ።” (ኤፌ 4:24)

“እንግዲህ እንደ እግዚአብሔር ምርጦች ቅዱሳን ሆናችሁ የተወደዳችሁም ሆናችሁ፥


ምሕረትን፥ ርኅራኄን፥ ቸርነትን፥ ትህትናን፥ የዋህነትን፥ ትዕግሥትን ልበሱ፤” (ቆላ 3:12)

በዚህ ክፍላችን ላይ ጌታ ረድቶን በብሉይ ኪዳን የካህናትን አገልግሎትና ስርአት ካየን በኋላ የሊቀ ካህናቱ አገልግሎት
በኢየሱስ መተካቱን: የካህናትም አገልግሎት አማኞች ካህናት በመደረጋቸው መተካቱን በቅዱስ መጽሐፍ አስደግፈን
አይተናል በቀጣይ ጌታ በጸጋው ከረዳን ደግሞ የተዋህዶወችን የብሉይ አይነት የተሻረ የክህነት ስርአት ወደ አዲስ ኪዳን
እንዴት ጎትተው ለማምጣት እንደሞከሩ አይተን ከመጽሐፍ ቅዱሱጋ ፈጽሞ ተቃርነው ምን ያህል ርቀት መሔዳቸውን
እናያለን::

3. የተዋህዶ ክህነት::
በተዋህዶ ቤት የክህነት አጀማመር ትውፊታቸው እርስ በርስ ስምምነት የሌለው የተምታታበት ነው:: አቡነ ገብርኤል
“ትምህርተ ሐይማኖት ኦርቶዶክሳዊት” ብለው በ 1991 በጻፉት መጣጥፋቸው ላይ የክህነት አጀማመርን ሲያነሱ: “ክህነት
የተጀመረው በሰማይ. በ 24 ቱ ካህናተ ሰማይ ነው::” ብለው አስፍረዋል:: ሊቀ ስልጣናት አባ ሃብተ ማርያም በኋላም
አቡነ መልከ ጼዴቅ “የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን እምነትና ትምህርት” በተባለው መጽሐፋቸው ገጽ
283 ላይ “ይህን ታላቅ ስልጣን የመሰረተው በኋላም ለሐዋርያት የሰጠው ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው ይላሉ::
እንዲሁም አቡነ ሽኖዳ በጻፉትና ቀሲስ ተስፋ እንዳለ እና ዲያቆን ማለደ ዋሲሁን በተረጎሙት “ግብረስዶማዊነትና
የሴቶች “ክህነት በቤተ ክርስቲያን እይታ” በተባለው መጽሐፍ ገጽ 14 የሐዲስ ኪዳንን ብለው ቢገልጹም ክህነትን
የመሰረተው ኢየሱስ ክርስቶስ ነው ይላሉ “ሊቀ ካህናት” ክንፈ ገብርኤል ደግሞ “ስርአተ ቤተ ክርሰቲያን” በተባለው
መጽሐፍ ገጽ 95 ላይ ክህነት የተጀመረው በአዳም ነው ይላሉ: እንዲሁም “ሁለቱቱ ኪዳናት የተባለው: የማህበረ ቅዱሳን
መጽሐፍ “ክህነት አጀማመሩን ስንመለከት ከመጀመሪያው ሰው አዳም ጀምሮ እንደሆነ እንገነዘባለን”(ገጽ 109) ይላል::
ይህ ሁሉ የተዋህዶ ዝብርቅርቅ ትውፊት ስለክህነት ከመሰረቱ ወጥ እና መሰረታዊ አረዳድ እንደሌለ ሚያሳይ ነው:
ስለዚህ መጽሐፍ ቅዱሳዊ የክህነት አረዳድም መጠበቅ መሰረቱ ከተበላሽ ቤት ደህነኛ ጽናት እንደመጠበቅ ተማምኖም
እንደማንቀላፋት ነው::

በተዋህዶ መሰረት ባሪያወች ለክህነት አይሾሙም:: (ፍትሐ ነገስት 9:277) እንዲሁም ባሪያን ያገባ ሰው ክህነት ሊሰጠው
አይገባም:: (ፍትሐ ነገስት 87:281) ይህም ቅዱሱ መጽሐፍ “አይሁዳዊ ወይም የግሪክ.ሰው የለም: ባርያ ወይም ጨዋ
ሰው የለም: ወንድም ሴትም የለም: ሁላችሁ በክርስቶሰ አንድ ሰው ናችሁ” ገላ 3:21 የሚለውን ቅዱሱን ቃል የናቀ
ያጣጣለ ነው:: ክርስቲያኖች ሰውን እንደሰውነቱ ያያሉ: ማስበለጥም እንኳ ቢያስፈልግ ክርሰቲያንነቱን ያስበልጣሉ እንጅ
ያለበት ምድራዊ ሁኔታ በክርሰትናው ላይ ተጽእኖ የሚፈጥርበት አልነበረም::

ልክ እንደዚሁ አንድ ካህን አንዲት ሴት በወር አበባዋ ጊዜ ቤተ ክርሰቲያን ቢያስገባት ወይም የጌታን ራት ቢያቀብላት
ከክህነቱ ይሻር ይላል:: እንዲህ አይነት ሴት ልጅ በወር አበባዋ ትረክሳለች የሚል የብሉይ ኪዳን አስተሳሰብ ያለው
የኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ምን ያህል የክርሰቶስ ደምን እንደናቀች ማሳያ ነው:: ጌታ ኢየሱስ ራሱ ስለእኛ እርግማን
ሁኖ(ገላ 3:13) ከህግ እርግማን የዋጀን ሁኖ እያለ የክርስቶስ ስጋ ና ደም ነው ሚሉትን እነኳን የሚሰጥን “ካህን” ከነሱ
የስልጣን እርካብ ያስወግዱታል:: ጌታችን ኢየሱስ ግን እንዲህ ያለ ነገር ሊጸየፍ ይቅርና: 112 አመት ደም ይፈሳት የነበረች
ሴት የልብሱን ጫፍ ዳሳ ስትፈወስ: ልብሴን ልቀይር ላስወግደው አላለም: እሷንም አልተቆጣም ነገር ግን በፍቅር ቃል
ልጀ ሆይ እምነትሽ አድኖሻል አላት::(ሉቃ 8:47) ተዋህዶ ግን ኢየሱስን ሚጸየፍ ያልሞተልን ስለመርገም ዋጋ
ያልከፈለልን በማስመሰል እሷም እንደታገባበት ሌሎችም እንዳይገቡ የመንግስተ ሰማይን በር ትዘጋለች::

በተጨማሪም ወይንን መጠጣት የተከለከለ ነው ብሎ ሚያስተምር ይቅርና ሚያስብ ካህን እንኳን ካለ በተዋህዶ ከክህነቱ
ይሻር በማለት (ፍትሐ ነገስት 97:319) ይደነግጋል:: ነገር ግን በዘሌ 10:9 የብሉይ ኪዳን ካህናት እንኳን ወይን ከጠጡ
እንዲሞቱ ይናገራል:: ወይን መጠጣት ቁም ነገር ሁኖ ክርሰቲያናዊ ስልጣንህን ሚከለክልት ተዋህዶ በውነቱ አሳፋሪ ናት::

በተዋህዶ ስለዲያቆናት ያላቸው ድንጋጌ ውስጥ አንዱ “ሲሾሙ ያለሴት ሊኖሩ ቢሳሉ: ከተሾሙ በኋላ ቢያገቡ ይሻሩ”
ይላል: አንድ ሰው ጌታን ብቻ ለማገልገል ብሎ ላለማግባት ቢወስን ደግ አደረገ ነገር ግን እንዲሳልና ይህና ጫና አድርጎ
ማቅረብ ግን ፍጹም ኢ-መጽሐፍ ቅዱሳዊ ግኖስቲካዊነት ነው:: ያገባ መልካም አደረገ ማለት ሲገባቸው ወደ ሽረት
መግባት ተዋህዶ ምን ይህል የግኖስቲካዊነት ውጤት መሆኗን ያሳያል(1 ጢሞ 4:3)

እንዲሁም በዚሁ በዲያቆናት አገልግሎት መርሃቸው ላይ የተምታታ አቋም አላቸው: ይህም የማስተማር
አግልግሎታቸው ላይ ፍትሐ ነገስት 79:249 ላይ ዲያቆናት እንዳያስተምሩ ይከለክላል:: “የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ
ቤተ ክርስቲያን መሰረተ ሐይማኖትና የካህናት ተልእኮ” በሚል ርእስ በሰይፈ ስላሴ ዮሐንስ የተዘጋጀው መጽሐፍ ደግሞ
በገጽ 42 ላይ “ዲያቆን ምስጢራትን መፈጸም አይችልም ነገር ግን ማንበብ :ማስተማር: መስበክ ለ ዲያቆን ይፈቀዳል
ይላል::

በጳጳሳት ላይም የግብጿ ኦርቶዶክስ በጋብቻ የነበሩትን ስትሾም: የእኛዋ ተዋህዶ ግን ድንግል ካልሆኑ ብላ ገግማለች::
ይህን ነገር አቶ ዘቤ ለማ “መጽሐፈ አሚን ወስርአት” ብሎ በጻፈው መጽሐፉ ገጽ 69 ላይ “በመጽሐፍ ቅዱስ ህግና
በጥንት የቤተ ክርስቲያን ስርአት ጳጳሳት የአንዲት ሚስት ባል የሆኑ ይሾሙ ነበር” በማለት ድርጅቷ ከመጽሃፍ ቅዱስ
ያፈነገጠች መሆኗን ለመሽሽግ አልቻሉም::

3.1 ልብሶቻቸው

በ 1983 “ስርአተ ቤተ ክርሰቲያን” በሚል ርእስ በትነሳኤ ማሳተሚያ ድርጀት አታሚነት “በሊቀ ካህናት” ክንፈ ገብርኤል
አልታየ በተዘጋጀው መጽሐፍ ላይ የተዋህዶ ካህናትን አለባበስ ምን መሆን እንዳለበት: “መቀደሻ አልባሳት” በሚል ርእ
ስር :-

“ሰ. ካህናት የሚደርቡት ካባ ላንቃ 5 መንዲል(ከልጅ) ያለው እንዲሆን ታዟል: መንዲል ወይም ከልጅ ማለት ለምድ
ነው::

ቀ. ካህናት በቀደሱ ጊዜ የሚለብሱት እስከተረከዛቸው የሚደርስ መሆን አለበት(ፍት ነገ 12)::

በ. ካህኑ ልብሰ ተክህኖ ከመልበሱ በፊት ልኩ የሚሆነውን መርጦ ይለብሳል ልብሰ ተክህኖ ከለበሰ በኋላ ማውለቅ
አይገባውም ቀሚሱ ከረዘመበት በዝናር ይታጠቀዋል(ፍት ነገ አንቀጽ 12)

ተ. የሚቀድሱ ካህናት ሲቀድሱ ነጭ ልብስ እንዲለብሱ ታዟል የሚቆርቡ ምእመናንም ንጹህ ነጭ ልብስ ለብሰው
መቁረብ ይገባቸዋል :: ‘ወአልባሰ ቅዳሴ እለ ይቄድሱ ቦቶን ይኩና ጸአድወ በከመ ይደሉ ለካህናት ወአኮ ህብራት’
እንዲል ፍትሐ ነገስት 12 በዶስ 47: በስ 96
ሀ ካህኑ ልብሰ ተክህኖወ ከመለበሱ በፊት ጳጳስ ካለ ጳጳስ አስባርኮ ይለብሳል ከሌለ ራሱ ባርኮ ይለብሳል” በማለት በ
93 ኛው ገጽ ላይ የአለባበስ ስርአቱን ያስቀምጣሉ:: በእውነቱ ተዋህዶ ይህን ፍልስፍናዋን ከየት እያመጣች ድሪቶዋን ይህ
በድህነት የነቀዘ ህዝብ ላይ አምሮውን በፈራ ስራ አዳብሮ እንዳያድግ ባልሆነ ትርኪ ምርኪ ስርአት አምሮውን አሳስራ
ይህችን አገር ወደ ኋላ እንዳስቀረች ሳስብ: እንዳጀማመራችን ኢትዮጵያ ያለ ተዋህዶ የት በደረሰች ነበር እያልኩ
እቆጫለሁ:: ይህን እንድለ ያደረገኝ ራሷን ከብሉይ ካህናትጋ ላማመሰሳሰል መንፈሳዊውን አምልኮ ስርአት ትታ የአለባበስ
የቦታና የንጽህና ጉዳይ አድርጋው እግዚአብሔር ያልሰጠውን ስርአት ህዝቤ ላይ በማሽከም ህዝቤ ነጻ ሁኖ አምላኩን
በመንፈስ እያመለከ በነጻ አምሮ ስንት መስራት ሲችል በዚህ የሰው ስርአት የሆነ የመበለቶች ስርአት የሆነ እግዚአብሔር
ያልሰጠውን ስርአት እንዲሽከም ማድረጓ ነው:: ለመሆኑ እግዚአብሔር በአዲስ ኪዳን እንዲህ አይነት መስጠት
ቢያስፈልገው በውኑ ቦታ ነው ጊዜ ጠቦት ነው ይህን ወሳኝ ነገር መናገር ያቃተው? ነው ወይንስ በብሉይ ደክሞት
በአዲስ ኪዳን ሳይናገር ቀረ? ይልቁንም ክርስቶስን ለብሰን በእግዚአብሔር ፊት ራቁታችንን እንኳን ብንቀርብ የሚያየው
የለበስነውን ክርስቶስን እንጅ የእኛ አለባበስ ቁመቱ እስከተረከዝ መሆን አለመሆኑን: ቀለሙን ቸክ ሲያደርግ ሚውልበት
ጊዜም የለውም:: መንፈስ በውስጣችን ነውና የክረስቲያን አምልኮና ቅዳሴ በማንኛውም ሰአት በየትኛውም ስፍራ
በማነኛውም ሁኔታ ነው::

“ክህነት በአዲስ ኪዳን” በሚለው ክፍል እንዳየነው በአዲስ ኪዳን እንድንለብስ የታዘዝነው ራሱን ክርሰቶስን እንጅ
የምድራዊ ጥበብና ሽማ አደለም:: ናባድና አብድዩ እግዚአብሔር ካዘዘው እሳት ሳይሆን ራሳቸው በመረጡት እሳት
ለማገልገል ሲጣጣሩ እንደሞቱት: የቆሬ ልጆች የክህነት ሳይመረጡ የአሮን ልጆች ብቻ ያላቸውን የክህነት አገልግሎት
ሊወርሱ ስለመረጡ እንደተቀሰፉት እንደዛው: ተዋህዶም እግዚአብሔር እንድንለብስ ያዘጋከጀልንን ሽማ ክረስረቶስን
ምእመናኖቿን ከማልበስ ይልቅ ሰው ሰራሽ ድሪቶ ህዝቡ ላይ በመጫን ክርስቶስን አስረስታ ህዝቡን ከጽድቅ ጎዳና
አውጥታ እየነዳችው ትገኛለች::

ጌታችን “የሰውም ሥርዓት የሆነ ትምህርት እያስተማሩ በከንቱ ያመልኩኛል ተብሎ እንደ
ተጻፈ በእውነት ትንቢት ተናገረ።” (ማር 7:7፤ 13) ብሎ እንደተናገረ እግዚአብሔር ያልሰጠውን የሰው ስርአት
እየፈለሰፈች: በከንፈሩ ሚያመልክ ልቡ ግን አመጸኛ የሆነ: በስጋው የጾመ ሚመስል በልቡ ግን ከሃጢያት አለም ያልወጣ
ጾም እንዳለቀች ወደ ዳንኪራውና ዝሙቱ ሚፈጥን: “ታቦት” ብላ የተሽከመችወን እንጨት በዘፈን የሚያጅብ: ከዛን
ቀጥሎ ወደድራፍቱ ሚሮጥ: አመጸኛ ግብዝ ትውልድ ፈጥራለች::

3.2 ተዋህዶ የአማኞችን ክህነት መካዷ


“ክህነት ለሁሉ አይሰጥም በምእመናን ለተመረጡት ብቻ ነው” (ስርአተ ቤተ ክርሰቲያን ገጽ 97)
“ክህነት ልዩ አገልግሎት በመሆኑ ለሁሉ አይሰጥም” (ሁለቱ ኪዳናት ገጽ 156)
“ክህነት ለሰው ሁሉ የሚያድሉት ወይም በተፈጥሮ እንደ ንጹህ አየር ማንም የሚያገኘ ነገር አይደለም”(ሁለቱ
ኪዳናት ገጽ 109)
“ስልጣነ ክህነት ለተመረጡት ብቻ ይሰጣል ስልጣነ ክህነት ለሁሉም አይሰጥም” (ሊቀ ጉባኤ አባ አበራ፤
ትምህርተ ሃይማኖትና ክርሰቲያናዊ ህይወት፤ ገጽ 260)

ክህነት በአዲስ ኪዳን በሚለው ክፍል ላይ አማኞች ሁሉ ካህናት መሆናቸውን: የአማኞች ጌታ ኢየሱስም ሊቀ ካህናት
መሆኑን: ስላየን እዚህ መድገሙ አስፈላጊ ስላልሆነ ተመልሶ ማየት ይቻላል:: ተዋህዶ ግን ይህን የአማኞች
ከእግዚአብሔርጋ መቀራረብ: ስላላስደሰታትና ሰይጣን ለአላማው ይጠቀምባት ዘንድ አማኞች ክህነታቸውን ረስተው
እግዚአብሔር አባታቸው መሆኑን ረስተው የሩቅ መስሏቸው: ተስፋ የመቁረጥ እነዲሁም: ቀጥታ አላገኘውም ብለው
በትካዜ እነዲኖሩ በማድረግ: ከፈጣሪያቸው ለመራቅና ተስፋ ቢስ በሃጢያት የተጨማለቀ: እግዚአብሔርን በላይ
ባለባበሱ ለመደለል የመሚሞክር ጠዋት ነጭ ለብሶ ስለሄደ ስለ ቀረ ሚጠላው የሚመስለው ትውልድን አፍርታለች::
ይህም ደግሞ ከሁሉም በላይ በውስጣችን ያለው መንፈስ ቅዱስን እንደሌለ በማድረግ እኛ ካህናት ብቻ ሳንሆን ቤተ
መቅደሱ እንኳን መሆናችንን ልታስረሳ የተነሳች ተቋም ናት::

3.3 በተዋህዶ ካህናት የሚፈጽሙት ተግባር


በተዋህዶ ካህናት ጥቂተቾች ብቻ እንደመሆናቸው መጠን ለነሱ ብቻ ብላ ለነዚሁ ጥቂት ሰወች የምተሰጣቸው
አገልግሎቶች አሉ:: ከነዚህም አገልግሎቶች መካከል: ክርስቲያናዊና መጽሐፍ ቅዱሳዊ የሆኑ ግን ማንም ምእመን
መፈጸም ሚችለው: እንዲሁም ፈጽሞ ክርስትና የሌለው የአረማውያን የጣኦታውያን የምውታን መንፈስ ሳቢወች
ተግባር የሆነ እንዲሁም በብሉይ ኪዳን የቀረ አዲስ ኪዳን የመንፈስ አገልግሎት መሆኑን ዘንግታ ከብሉይ
የተዋሰችው ስጋዊ ስርአቶች አሉበት:: የተወሰኑትን ለማየት ያክል::

3.3.1 በእግዚአብሔርና በሰው መካከል መካከለኛ መሆን


“ከረሀረነት መንፈሳዊ አገልግለሎት ነው ሰውን ወደ እግዚአብሔር መንግስት የሚያቀርብ ከእግዚአብሄር
የተገኘ ስጦታና ስልጣን ነው” (ሁለቱ ኪዳናት፤ ገጽ 109)

ተዋህዶ እንግዲ ድፍረቷ በመጽሐፍ ቅዱስ የሌለ ትምህርት በማስገባት የሷ ካህናት የመንግሰተ ሰማያት
የሚያቀርቡ ተደርገው ቀርበዋል ነገር ግን:: እንግዲ የክርስቶስን ስራ ለፍጡራን ጣኦታቶቿ ለሙታኖቿና
በቁማቸው ለሞቱ ሙታኖቿ አከፋፍላ አልበቃት ያለው: ህዝቧን ፈጽሞ ከክርስቶስ ለመንቀል ነው:: ይህ
የኑፋቄ ትምህርቷ ፈጽሞ በመጽሐፍ ቅዱስ የሌለ መሆኑ ብቻ ሳይሆን የክርስቶስን ተግባር: ደሙን
አክፋፍታ መስቀሉ ላይ ተፍታ የራሷን ፍጡሮች ግን አዳኞች የመንግስተ ሰማይ አቅራቢወች አድርጋ
ታቀርባለች:: ሲጀመር ወደ መንግስተ ሰማይ አቅራቢ ማን ነው ብለን ብንጠይቅ:-
“አሁን ግን እናንተ በፊት ርቃችሁ የነበራችሁ በክርስቶስ ኢየሱስ ሆናችሁ በክርስቶስ ደም
ቀርባችኋል።” (ኤፌ 2:13)
“እናንተንም ነውርና ነቀፋ የሌላችሁና ቅዱሳን አድርጎ በእርሱ ፊት ያቀርባችሁ ዘንድ፥ በፊት
የተለያችሁትን ክፉ ሥራችሁንም በማድረግ በአሳባችሁ ጠላቶች የነበራችሁትን አሁን
በሥጋው ሰውነት በሞቱ በኩል አስታረቃችሁ።” (ቆላ 1:21-22)
ሚል መልስ እናገኛለን እንጅ ፈጽሞ ፈጽሞ ካህናት አቀራራቢ ናቸው ሚል አናገኝም:: ለመሆኑ እንደ ተዋህዶ ቅዠት
“ካህናት” ሚባሉ መካከለኞች ቢኖሩ እንዴት ይህን ያህል በተዋህዶ ቤት አንገብጋቢ የሆነው ነገር ሐዋርያት ረሱት?
ለዚህ መልሱ ቀላል ነው:: ሐዋርያት ተዋህዶን አያውቋትም: ተዋህዶም ሐዋርያትን አታውቃቸውም:: እንጅ በድፍረት
የፍጡራን መካከለኞች ባላመጣች ነበር:: መጽሐፍ ቅዱስ ስለመካከለኛው ሲናገር::

“አንድ እግዚአብሔር አለና፥ በእግዚአብሔርና በሰውም መካከል ያለው መካከለኛው ደግሞ


አንድ አለ፥ እርሱም ሰው የሆነ ክርስቶስ ኢየሱስ ነው” (1 ጢሞ 2:5)

“ስለዚህም የፊተኛው ኪዳን ሲጸና ሕግን የተላለፉትን የሚቤዥ ሞት ስለ ሆነ፥ የተጠሩት


የዘላለምን ርስት የተስፋ ቃል እንዲቀበሉ እርሱ የአዲስ ኪዳን መካከለኛ ነው።” (ዕብ 9:15)

“የአዲስም ኪዳን መካከለኛ ወደሚሆን ወደ ኢየሱስ፥ ከአቤልም ደም ይልቅ የሚሻለውን


ወደሚናገር ወደ መርጨት ደም ደርሳችኋል።” (ዕብ 12:24)
መጽሐፍ ቅዱስ እንዲህ ቁልጭ ብልጭ ባለ መንገድ መካከለኛው አንድ እንደሆነ ቢገልጽም ቅሉ ተ ዋህዶ ፈጽሞ
ፍጡራኖቿን ከማምለክ ትመለስ ዘንድ ተስኗታልና ቃሉን ንቃ አናንቃ ክርስቶስን አውርዳ ፍጡራኖቿን በመካከለኛነት
ስፍራ ሹማቸዋለች:: ቅዱስ ቃሉንም ለመስማት ፈጽመሞ አልሻችም:: በእግዚእብሄር ላይ ማመጽ የተዋህዶ ፍጹም
ተግባር ሁኗል:: ስለዚህ አሁንም ተዋህዶ እነዚህን ፍጡራን ቀድሰው ወጠው የእመበለቶችን ጓዳ በርብረው: በየሰው ቤት
እየዞሩ ገንዘብ ሚሰበስቡ ቤመንገዱ ሚለምኑ “ካህናት” ተብየወች አሽቀንጥራ ጥላ: ወደ አንዱ መካከለኛ ትመለስ ዘንድ
ባ e ርሱ ብቻ ስለስሙ የሚሰጠውን የሃጢያት ስርየት ብትሰብክ ለራሷም ለምእመናኖቿም ታተርፋለች: ጣኦታቶቿ
ከጥፋት ውጭ የክርስቶስን ወደ መንግስቱ የማቅረብ ስራ: በም`ኞት ትቃጠል ይሆናል የሰይጣን ፈረስ ሁና ትቀጥል
ይሆናል እንጅ እንደ ምኞቷ አቀራራቢ ሊሆኑ ቀርቶ ፈጽሞ የጥፋቷ ምንጮች ናቸው::

3.3.2 ማጥመቅ
“ዲያቆን ያስተመምርና ያጠምቅ ዘንድ: ወይም ይቀድስና ህዝቡን ይባርክ ዘንድ ስልጣን የለውም” (ፍትሐ
ነገስት 79:249)
ተዋህዶ ሌላው ፍልስፍናዋ አንድ ሰው ሲያምን ማጥመቅ ሚችል “ካህን” ብቻ ነው ትላለች: ያው በእሷ
ቤት አማኞች ሁሉ ካህናት አደሉም ለማለት ነው እንግዲህ:: ይህ ሲሆን እንግዲ ለዚህ ፍልስፍናዋ አንዴት
ኬት እንዳገኘችው እንኳን እኔ አንድ ትንሽ ልጅ ይቅርና እሷ ራሱ አስካሁን ስታምነው ከየት አመጣሽው
ብትባል መልስ አይኖራትም::

ነገር ግን በክረስትና ስንመጣ ከተዋህዶ አስተምህሮ በተቃራኒ ነው: እንደ ክርስትና ከሆነ ማንኛውም
ክርስቲያን በክርስቶስ አሳምኖ ማጥመቅ እንደሚችል በመጽሐፍ ቅዱስ እናነባለን:: ለምሳሌ ኢትዮጵያዊው
ጃንደረባ: የተጠመቀው በፊሊጶስ ነው ፊሊጶስ ደግሞ ዲያቆን እንጅ የተዋህዶወች ካህን አልነበረም::(ሐዋ
6:5፤ 8:1፤ 8:38) ወንጌልን ለአህዛብ እስከ ምድር ዳርች ይዞ የሄደው ሐዋርያው ጳውሎስ እንኳን
የተጠመወው በአንድ ተራ ሰው:: መጽሐፍ ቅዱስ “አንድ ሰው” ብች ብሎ የጠራው በቤተ ክርስቲያን
ምንም አይነት ማእረግ የሌለው ሰው ነው:: (ሐዋ 9:10-18) እንደ ተዋህዶ ማጥመቅ የካህናት ስራ ነው
ከተባለኮ ኢየሱስ ማንንም አላጠመቀም (ዮሐ 4:2) ሐዋርያው ጳውሎስ ለማጥመቅ እንኳን ቸልተኛ ነበር
እንጅ ተልእኮየ ነው ባላደርገው ወዮልኝ አላለም(1 ቆሮ 1:17)

አንዳንድ ኦርቶዶክስ ቃላቸውን እንሰማለን ምትላቸው የድሮ የቤተ ክርስቲያን አባቶች ውስጥ እንኳን
እንደ ጎርጎሪወስ ዘእንዚናዙ “ማንም ሰው ማጥመቅ ይችላል፤ ያንዱ ሂወት ከሌላው የተሻለ ሊሆን ቢችልም
የጥምቀት ጸጋ ግን ያው ነው” (40th Oration, 26, p. 715) ብሏል::

Rials, Kerby. The Three Great Churches: Comparing the beliefs of Catholics, Protestants
and Orthodox (p. 207). Looking Glass River Publishing. Kindle Edition.

ታዲያ ተዋህዶ ከየት ባመጣችው ፍልስፍና ነው አማኞች ማጥመቅ አ አይችሉም ማጥመቅ የካህናት
ተልእኮ ነው እያለች ራሷ ተወዛግባ ህዝቧን ምታወዛገበው? እስከመቸስ በዚ ውዝግቧ ትቀጥላለች?

3.3.3 ሃጢያት ማስተሰረይ(ማናዘዝ)


“ስለዚህ የሐዋርያት ስልጣነ ክህነት ፍጹም ነወ እነሱ የፈቱት የተፈታ: ያሰሩት የታሰረ ነውና ክህነታቸው
ፍጹም የሃጢያት ይቅርታ የሚያሰጥም ነው:: ካህናቱም በሃጢያት(ጥንተ አብሶ) ያልታሰሩ ክህነቱም
ሁሉንም ሃጢያተት የሚያስተሰርይ ምሉእና ፍጹም ነው:: ካህናት ሰወች እንደ መሆናቸው መጠን ሃጢያት
የሚሰሩ ቢሆኑም እለት እለት እየተናዘዙ የሚነጹ ስለሆነና: እነርሱ ፍጹማን ባይሆኑም ካሃጢያት በንስሃ
ይድኑበት ዘንድ የተሰጠ ስልጣን ላይ ድካምና ህጸጽን ሊያመጣ ስለማይችል ክህነቱ ፍጹምና ምሉእ ነው”
(ሁለቱ ኪዳናት ገጽ 154)
“የክህነተ ሐዋርያት ስልጣን ፍጹምነት ሃጢያተ ምእመናንን ለማስተሰረይ ብቻ ሳይሆን የእርሱን ቅዱስ
ስጋና ክቡር ደም እየፈተቱ ለምእመናን ማቁረብ ነው:: (ሁለቱ ኪዳናት፤ ገጽ 154)
“”ምእመናን ንስሃ እንዲገቡ ሃጢያታቸውን እንዲናዘዙ በማድረግ የማንጻት ተግባሩን ካህኑ ሊፈጽም
ይችላል” (ሊቀ ስልጣናት ሃብተ ማርያም ወርቅነህ፤ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት እና ትምህርት፤
ገጽ 286)

በመጀመሪያ ደረጃ መጽሐፍ ቅዱስ በአደባባይ ሃጢያትን ስለመናዘዝ እንጅ በድብቅ “ካህን” ለተባለ ሰው ስለመናዘዝ
አንድም ቦታ አያስተምርም::
“ኃጢአታቸውንም እየተናዘዙ በዮርዳኖስ ወንዝ ከእርሱ ይጠመቁ ነበር።” (ማቴ 3:6)

“የይሁዳም አገር ሁሉ የኢየሩሳሌምም ሰዎች ሁሉ ወደ እርሱ ይወጡ ነበር፥ ኃጢአታቸውንም


እየተናዘዙ በዮርዳኖስ ወንዝ ከእርሱ ይጠመቁ ነበር።” (ማር 1:4-5)

“አምነውም ከነበሩት እጅግ ሰዎች ያደረጉትን እየተናዘዙና እየተናገሩ ይመጡ ነበር።” (ሐዋ
19:18)

ሲቀጥል ለሃጢያታችን ምህረትን ከራሱ ከእግዚአብሔር እንድንለምን እንጅ “ካህናት” ወደ


ሚባሉ እንድንሔድ አልታዘዝንም::

“እንግዲህ እናንተስ እንዲህ ጸልዩ፦ በሰማያት የምትኖር አባታችን ሆይ፥... እኛም ደግሞ
የበደሉንን ይቅር እንደምንል በደላችንን ይቅር በለን” (ማቴ 6:9-12)
“እንግዲህ ስለዚህ ክፋትህ ንሰሐ ግባ፥ ምናልባትም የልብህን አሳብ ይቅር ይልህ እንደ ሆነ ወደ
እግዚአብሔር ለምን፤” (ሐዋ 8:22)

“ቀራጩ ግን በሩቅ ቆሞ ዓይኖቹን ወደ ሰማይ ሊያነሣ እንኳ አልወደደም፥ ነገር ግን፦ አምላክ
ሆይ፥ እኔን ኃጢአተኛውን ማረኝ እያለ ደረቱን ይደቃ ነበር። እላችኋለሁ፥ ከዚያ ይልቅ ይህ
ጻድቅ ሆኖ ወደ ቤቱ ተመለሰ፤ ራሱን ከፍ የሚያደርግ ሁሉ ይዋረዳልና፥ ራሱን ግን የሚያዋርድ
ከፍ ይላል።” (ሉቃ 18:13-14)
እንግዲህ በዚህ በሉቃ 18 ባለው ታሪክ: እንደምናነበው: ፈሪሳዊው እንደ ተዋህዶወች እግዚአብሔርን ያከበረ መስሎት
ስራወቹን ሲቆጥር ቀራጩ ግን ሚመካበት አንዳች የለውም: ሚተማመነውም ጌታን ብቻ ነውና በእምነቱ ብቻ ጻድቅ
ሁኖ ተመለሰ:: እንደተዋህዶ ከእግዚአብሔር ከማመን በተጨማሪ ደግሞ ስራየ ይቆጠርልኛል ያለው ፈሪሳዊ ሳይጸድቅ
ቀረ:: ከዚህ ምንረዳው ሃጢያትን ሚምር ራሱ እግዚአብሔር ነው: እንኳን አሁን ቅዱስ መንፈሱን ሰጦን ልጆቹ ሁነን
ይቅርና በብሉይ ኪዳን በዘመነ ኩነኔ እንኳን ቀራጩ በቀጥታ ወደ እግዚአብሔር ንስሃ ገብቶ ጸድቋል::

በዚህ ረገድ ልዩ የክህነት ስርአት የነበራቸው አይሁድ እንኳን አልሳቱም”

“ከአንዱ ከእግዚአብሔር በቀር ኃጢአት ሊያስተሰርይ ማን ይችላል? ብለው አሰቡ።”( ማር 2:7)


ተመልከቱ እንግዲ ዋህዶ እንኳን የተሰወረባን እውነት አይሁድ ግን በቅዱሳት መጻህፍት መሰረት ያውቁታል:: ተዋህዶ
አንድ ሚምታታባት ነገር ቢኖር: አንዴ “ካህናት” መካከለኞች ናቸው ብላ ሃጢያት የሚያሰጡ ናቸው ትላለች አንዴ ደሞ
ሾጥ ሲያደርጋት ካህናት ራሳቸውን ሃጢያትን ይቅር የሚሉ. ታደርጋለች: ደግሞ መልሰው ይቅር የሚባሉት ሲጾሙ
ሲሰግዱ ነው: ብላ መጽሐፍ ቅዱስ አንድም ቦታ ያላስተማረውን ስለጾሙ ስለሰገዱ ስለጸለዩ ነው ይቅር ሚባሉ ብላ:
ሃጢያት ይቅር ማለታቸውን ረስተውት ካህናቶቿ “ይህን ያህል ስገድ: ያን ያህህል ስገድ፤ ይህን ያህል ቀን ጹም” እያሉ
ቀኖና ሚባል ኢ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ስርአት ይደረድራሉ::

ለመሆኑ መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ሃጢያት ስርየት ምን ይላል? “ካህናት” ሚባልንስ ለሃጢያት ስርየት ተጠቀሙባቸው
ይላልን? ብለን ብንጠይቅ መጽሐፍ ቅዱስ ያለምንም ማወላዳት በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ በማመን በደሙ መሆኑን
በግልጽ ያስረዳል እንጅ ፈጽሞ ካህናት ሚባሉ ሰወችንም አያነሳም::

“በእርሱ የሚያምን ሁሉ በስሙ የኃጢአቱን ስርየት እንዲቀበል ነቢያት ሁሉ


ይመሰክሩለታል።” (ሐዋ 10:43) ጴጥሮስ እንግዲ ለቆርኔሌወስ ቤተሰብ እኔ ካህን ነኝ የሃጢያት ስርየት እሰጣኋለሁ:
አላለም:: ይልቁንም በስሙ በማመን የሚገኝን ስርየት ሰበከላቸው እንጅ::
“የኃጢአትንም ስርየት በእኔም በማመን በተቀደሱት መካከል ርስትን ያገኙ ዘንድ፥ ከጨለማ
ወደ ብርሃን ከሰይጣንም ሥልጣን ወደ እግዚአብሔር ዘወር እንዲሉ ዓይናቸውን ትከፍት ዘንድ፥
ከሕዝቡና ወደ እነርሱ ከምልክህ ከአሕዛብ አድንሃለሁ።” (ሐዋ 26:17-18) በዚህ ክፍል ጌታችን ኢየየሱስ
ጳውሎስን “ሃጢያታቸውን አንተ ታስተሰርያለህ” አላለውም ይልቁንስ “የሃጢያትንም ስርየት በእኔ በማመን” አለው
እንጅ “አንተን ካህን አደርግሃለሁ መካከለኛ አማላጅ አስታራቂ አደርግሃለሁ፤ ሃጢያት ታስተሰርያለህ፤ ቀኖና ሰጠህ ጾም
ጸሎት ስግደታቸው ሃጢያታቸውን ያስተሰርይላቸዋል::” ሚል እንደተዋህዶ የተምታታበት ተልእኮ አልሰጠውም::

“በውድ ልጁም፥ እንደ ጸጋው ባለ ጠግነት መጠን፥ በደሙ የተደረገ ቤዛነታችንን አገኘን እርሱም
የበደላችን ስርየት።” (ኤፌ 1:7)
“እንደ ሕጉም ከጥቂቶች በቀር ነገር ሁሉ በደም ይነጻል፥ ደምም ሳይፈስ ስርየት የለም።” (ዕብ
9:22)

“የልጁም የኢየሱስ ክርስቶስ ደም ከኃጢአት ሁሉ ያነጻናል።” (1 ዮሐ 1:7)

“ለወደደን ከኃጢአታችንም በደሙ ላጠበን” (ራዕ 1:5)

“እነዚህ ከታላቁ መከራ የመጡ ናቸው፥ ልብሳቸውንም አጥበው በበጉ ደም አነጹ።” (ራእይ 7:14)
መጽሐፍ የሚናገረው እና የሚያስተምረው ይህ ሆኖ ሳለ ግን ተዋህዶ ደሙን አክፋፍታ: አሳንሳና ገፍታ “ካህናት
ለሚባሉ በሃጢያት የተጨማለቁ እነሱ ራሳቸው እንኳን በደሙ ስርየት ለሚያስፈልጋቸው: በመስቀል ላይ ቀርቶ በሰፈር
ትንንሽ ነገሮች እንኳን የማይደርሱልንን ሰወች የአምላክን ብቻ የአምላክነት ስልጣን ሰጠዋቸዋል::

ተዋህዶ ለዚህ ኑፋቄዋ የምታቀርበው ከመጽሐፍ ቅዱስ ለመጠቃቀስ የሞከረቻቸው ጥቅሶች የሉም ማለት ግን አደለም:
የተወሰኑ ይደግፉኛል ያለቻቸውን ጥቅሶች ከሙሉ የመጽሐፍ ቅዱስ መልእክትና ከአውዱ ነጥላ ለማቅረብ ሞክራለች::
መጽሐፍ ቅዱስን ለመረዳት:- በዘመኑ የነበረውን ታሪካዊ ሁኔታ: የተጻፈላቸውን ሰወች አና የጻፊወችን ባህል:
የመጽሐፉን የመልእክት አላማ እና በምን ምክንያት እንደተጻፈ: መቸ እንደተጻፈ: አውዱን: ከዛም ሙሉ ምእራፉን
መጽሐፉን ከዛም ከሙሉ የመጽሐፍ ቅዱስ መልእክትጋ ማሰተያየት ግድ ይላል:: ተዋህዶ ግን ከዚህ ፈጽሞ በራቀ መልኩ
ለሷ የኑፋቄ ትምህርት ይስማማ እንጅ ማንም እንደገዛ ሃሳቡ እንዲተረጉም እና እንዲያጨማልቅላት በሯን ክፍት አድርጋ
ትጠብቀለች: ለመጽሐፍ ቅዱስ አተረጓጎም ስልትም ግድ የላትም: ማንም ደብተራየተረጎመላትን አባ እከሌ እንደተናገረው
እያለች የመለኮትን ሐሳብ በነ አባ ደብተተራ ትለውጣለች እንጅ::

ተዋህዶ ለትምህርቴ ያዋጣኛል ይመጥነኛል ስትል የምትጠቅሳቸው ጥቅሶች መካከል:-


“እውነት እላችኋለሁ፥ በምድር የምታስሩት ሁሉ በሰማይ የታሰረ ይሆናል፥ በምድርም
የምትፈቱት ሁሉ በሰማይ የተፈታ ይሆናል።” (ማቴ 18:18)

ይህ እንግዲ መጽሐፉን በጥንቃቄ ካለማንበብ የሚመጣ ስህተት ነው:: በመጀመሪያ ደረጃ


መሐፉን በጥንቃቄ ስናነበው ከ ቁ 15 ጀምሮ እንዲህ ይላል:-

“ወንድምህም ቢበድልህ፥ ሄደህ አንተና እርሱ ብቻችሁን ሆናችሁ ውቀሰው። ቢሰማህ፥


ወንድምህን ገንዘብ አደረግኸው፤ ባይሰማህ ግን፥ በሁለት ወይም በሦስት ምስክር አፍ ነገር ሁሉ
እንዲጸና፥ ዳግመኛ አንድ ወይም ሁለት ከአንተ ጋር ውሰድ፤ እነርሱንም ባይሰማ፥ ለቤተ
ክርስቲያን ንገራት፤ ደግሞም ቤተ ክርስቲያንን ባይሰማት፥ እንደ አረመኔና እንደ ቀራጭ
ይሁንልህ።”

ይህን ካለ በኋላ ነው እንግዲ “በምድር ያሰራችሁት በሰማይ የታሰረ ይሆናል...” ያለው:: ይህ


ክፍል የሚናገረው ወንድሜ በእኔ ላይ የሚሰራውን ሃጢያት ይቅር ማለትን እንጅ
በእግዚአብሔር ላይ የሚሰራውን ሃጢያት ወይም በሌላ ሰው ላይ የሚሰራውን ሃጢያት ይቅር
ስለማለት አደለም:: ተዋህዶ ግን ለካህናቶቿ የሰጠችው “ስልጣን” ለእግዚአብሔር ብቻ
ያለውን የትኛውንም ሃጢያት ይቅር ማለትን ነውና ይህ ጥቅስ አውዱን ስናነበው
እንደሚናገረው ከተዋህዶ በተቃራኒ ለማነኛውም ሰው የተሰጠ፤ በራሳችን ላይ የሚሰራን በደል
እኛ በምድር ላይ ይቅር በማለት: በመምከር አንደምንፈታው ሚያሳይ ነው::

“ኃጢአታቸውን ይቅር ያላችኋቸው ሁሉ ይቀርላቸዋል፤ የያዛችሁባቸው ተይዞባቸዋል


አላቸው።” (ዮሐ 20:23)
ተዋህዶ ይህን በመጥቀስ ኢየሱስ በዚህ ስፍራ “ለካህናት ስልጣነ ክህነትን መስጠቱ ነው” ትላለች:: በመጀመሪያ ደረጃ
ይህ ክፍል ተዋህዶ እንደምትለው የማይሆንበት ብዙ መንገድ አለ:: በመጀመሪያ ደረጃ ቶማስ በዚህ ስፍራ አልነበረም:
ታዲያ ተዋህዶወች እንደሚሉት ጌታ ኢየሱስ “የክህነት ስልጣን” ከሆነ የሰጠው ታዲያ ቶማስ በንፍአት የተሰጠውን
ክህነት አልተቀበለም ማለት ነው? በመቀጠል በዚህ ስፍራ ላይ መረዳት ያለብን ነገር በማቴ 18:18 ቃል የተገባልን ነገር
ተፈጻሚ ይሆን ዘንድ ቤተ ክርስቲያን በይፋ በደሙ መመስረቷን የሚያሳይ ነው:: ለዚህ ነው በ ኤፌ 4:32 ላይ “እርስ
በርሳችሁም ቸሮችና ርኅሩኆች ሁኑ፥ እግዚአብሔርም ደግሞ በክርስቶስ ይቅር እንዳላችሁ
ይቅር ተባባሉ።” ያለው: እንግዲህ እኔ ወንደሜ ቢበድለኝ እና ይቅር ብለው ይቀርለታልና: ማለት ነው:: ለዚህ ነው
ጌታ ኢየሱስ “ለሰዎች ኃጢአታቸውን ይቅር ብትሉ፥ የሰማዩ አባታችሁ እናንተን ደግሞ ይቅር
ይላችኋልና” (ማቴ 6:15) በማለት ሃጢያታቸውን ይቅር እንድንል ያስተማረን:: ስለዚህ በሰማይ የእኛንም ሆነ የሰውን
ሃጢያት ይቅር ይባልልን ዘንድ እርስ በራሳችን በምህረትና በፍቀር መተያየት አንዳለብን ካስተማረ በኋላ ይህን
እንድናደርግ ደግሞ በዮሐ ወንጌል ነገረን::

በመቀጠል ይህን ክፍል ሰዋሰዋዊ አረዳዱንም መረዳት ያስፈልጋል:: የሚለው “ይቅር ያላችኋቸው ይቀርላቸዋል ሳይሆን:
ቀርቶላቸዋል:” “የያዛችሁባቸውም ተይዞባቸዋል” ይላል:: በቀጥታ ከግሪኩ ለሚያነብ ሰው: የሚሰጠው ትርጉም: ይቅር
የተባሉትን እንደሚሉ: የተያዘባቸውን እንደሚይዙ ነው:: ምክንያቱም “ቀርቶላቸዋል” እና “ተይዞባቸዋል ሚሉት የሃላፊ
ጊዜን አመልካች ሲሆኑ “ይቅር ያላችኋቸው” እና “የያዛችሁባቸው” አሁንን ሚያሳይ ነው::

እንደተዋህዶ አመክንዮ ብንሔድና ይህ ቦታ እነሱ እንዳሉት ነው ብንል: ካህናቶቻቸው ይቅር ያሉት ሃጢያት ሁሉ ይቅር
ሚባል ከሆነ:: እግዚአብሔር ሃጢያቱን ይዞ እነሱ ይቅር ቢሉት እነሱ ከእግዚአብሔር ይልቅ መሃሪ ሁነው የማሩትን
እግዚአብሔር ይቅር ሊለው ነውን? ለምሳሌ እንበልና ልጁን የደፈረ አባት ቢኖር: አንድ የተዋህዶ ካህን ሂዶ: ይቅር
ብየሃለሁ ስላለው ይቅር ይባላል ማለት ነው? አንድን ሰውስ እግዚአብሔር ሃጢያአቱን ይቅር ያለውን አንድ የተዋህዶ
ካህን ሂዶ ሃጢያትህን ይቅር አልልህም ቢለው እግዚአብሔር መልሶ ሊይዝበት ነው ሃጢያቱን? ከሁለቱ አንዱም ካልሆነ
ታዲያ ይህ የጌታ የሚሰራውና የተነገረው በእኛ ላይ የሚሰራውን ሃጢያት ይቅር ስለማለትና ስላለማለት እንጅ
የእግዚአብሔር ብቻ ስልጣን ስለሆነው ስለ ሁሉ ሃጢያት የሚያወራ አደለም:: አይ እግዚአብሔር ይቅር ያለውም ላይ
ቢይዙ ይያዝባቸዋል: እግዚአብሔር የያዘበትን ይቅር ቢሉ ደግሞ ይቀርለታል:: ከተባለ ደግሞ እነሱ ከእግዚአብ`ሄር
በለጡ ማለት ነው:: ለዚህ ነው ጴጥሮስን
“እግዚአብሔር ያነጻውን አንተ አታርክሰው” ሐዋ 10:15 የሚል ቃል የመጣለት:: ጴጥሮስ እንግዲ እግዚአብሔር
የፈታውን እሱ የማሰር ስልጣን ቢኖረው ኑሮ ቆርነሌወስ ወደ ክርስተና ባልመጣ ነበር:: የኢየሩሳሌም ወንድሞችም
ያልተገረዙ አህዛብን አስረዋልና: ሐዋ 11:1 ቆርነሌወስና ቤተሰቡ የሃጢያትን ስርየት በስሙ በማመን ባልተቀበሉም ነበር
(ሐዋ 10:43) እንዲሁም ጴጥሮስ እግዚአብሄር ያሰረውን ለመፍታት ስልጣን ቢኖረው ኖሮ: በሐዋ 819 ሲሞን እጅ
በመጫን መንፈስ ቅዱስ እንደሚሰጥ ባየ ጊዜ መንፈስ ቅዱስን በገንዘብ ሊገዛ ስለፈለገ በረገመው ጊዜ: ላሃጢያቱ ግን
ምህረት እንዲያገኝ ያለው “የልብህን አሳብ ይቅር ይልህ እንደሆነ ወደ እግዚአብሔር ለምን” አለው እንጅ በተሰጠኝ
ክህነት ይቅር እልሃለሁና ተናዘዝ አላለውም:: ስለዚህ የእግዚአብሔርን ቃል ስናነብ ከሙሉ የቅዱስ መጽሐፍጋ
አስተያይተን እንጅ እንዲት ጥቅስ ብቻ አይተን የእኛን አሳብ መትደግፍ ሲመስለን ከሙሉ የእግዚአብሔር ቃል ነጥለን
አውጥተን ጥቅስ መበደል አይገባንም:: ይህ ደግሞ ተዋህዶና መምህራኖቿ የተካኑበት የኑፋቄ ማርሻቸውና መርሃቸው
ነው::

“ከእናንተ የታመመ ማንም ቢኖር የቤተ ክርስቲያንን ሽምግሌዎች ወደ እርሱ ይጥራ፤ በጌታም
ስም እርሱን ዘይት ቀብተው ይጸልዩለት። የእምነትም ጸሎት ድውዩን ያድናል ጌታም
ያስነሣዋል፤ ኃጢአትንም ሠርቶ እንደ ሆነ ይሰረይለታል።” ( ያዕ 5:14-15)
በመጀመሪያ ደረጃ ይህ ክፍል የሚለው የቤተ ክርሰትቲያን ሽማግሌወችን ይጥራ እንጅ ካህናትን ይጥራ አደለም:: ካህን
ሚለው ቃልና ሽማግሌ ሚለው ቃል ፈጽሞ በአገልግሎትም በስያሜም የተለያዩ ናቸው ካህን ማለት በግሪክ
“ሔርየሰስ”(ἱερεὺς) ሲሆን ይህ ቃል ግን ሚለው ፕሪስባይትሮስ(πρεσβυτέρους) ነው:: ካህን
የሚለውን ቃል በአዲስ ኪዳን ለምእመናን ሁሉ ለሚውል ነው እንጅ የተጠቀመው ለሽማግሌወች ብቻ አንድም ቦታ
አልተጠቀመውም(ካህን በአዲሰ ኪዳን በሚል የጻፍኩትን መመልከት ይቻላል::)

ሲቀጥል እዚህጋ “እርስ በእርሳችሁ” ተናዘዙ እንጅ ለሽማግሌው ብቻ እንድንናዘዝም አያዝም:: ይህ Ppublic
confession ደግሞ ዛሬ በፕሮቴስታንት አብያተ ክርስቲያናት ሚፈጸመው አይነት እንጅ ለማናዘዝ የተሾመ አለ እንደ
ምትለው ተዋህዶ አደለም:: ተዋህዶ እንዲህ ያለ ነገር አንድም ቦታ እንኳን ከእግዚአብሔር ቃል አታመጣም:: ከሚሳሳቱ
ና ተራ ሰወችና ደብተራወቿ እንጅ:: የሃጢያቱ ስርየትም ካየነው ጌታ ሲፈውስ ሃጢያትን ይቅር ብሎ መሆኑን ሚያሳየው
ምክንያቱም ጌታ ሲፈውስ ሃጢያት ይቅር ብሎ ነውና::(ጌታ በማርቆስ ወንጌል 2:5 ላይ ሽባውን ሲፈውሰው ሃጢያትህ
ተሰረየችልህ ማለቱን ልብ ይሏል:: ሰውየውም የቤተ ክርስቲያን ሽማግሌወችን ሲጠራ በበደሉ ተተጽቶ ነውና በዚህ
በንስሃው የተነሳ እንጅ ካህን አስተሰርዮለት ነው አይልም::

3.3.4 መስዋእት ማቅረብ(ማቁረብ፤ እጣን)

“ዛሬ በዚች ቀን በፍቅርና በትህትና ግሩም በመትሆን ምስጢር ፊት እቆማለሁ: በዚህ ማዕድና መስዋእት ፊት”
(ቅዳሴ ማርያም ዘአባ ህርያቆስ)

“የክህነተ ሐዋርያት ስልጣን ፍጹምነት ሃጢያተ ምእመናንን ለማስተሰረይ ብቻ ሳይሆን የእርሱን ቅዱስ ስጋና ክቡር
ደም እየፈተቱ ለምእመናን ማቁረብ ነው:: (ሁለቱ ኪዳናት፤ ገጽ 154)

“ከእለታት በአንዱ ቀን ፍሬምናጦስ እንበረምን እንዲህ አለው የኢትዮጵያ ሰወችን ባህል አደንቃለሁ አለው::
ትገረዛላችሁ በክርስቶስም ታምናላችሁ: ነገር ግን ጥምቀት አትጠመቁም ስጋወደሙን አትቀበሉም አለው:: እንበረምም
ፍሬምናጦስን እንዲህ አለው: ግዝረትን አባቶቼ ሌዋውያን አመጡልን: ሃይማኖትንም የህንደኬ ባለሟል አመጣልን::”
(ገድለ ተክለ ሃይማኖት 4:11-17)

“አርድእትና ጠባቂወች ደሙን ማቀበል አይገባቸውም::” (ፍትሐ ነገስት 85:268)

“በቅዳሴ ጊዜ እርገተ እጣን አይቀርም: የሚደረገውም ዕርገተ እጣን 5 ጊዜ ነው. ማእጠንት(ጥና)


የመሚይዝና የሚያጥን ቄስ ነው እንጅ ዲያቆን በእጁ ጥና ይዞ አያጥንም ኤጲስ ቆጶስ መሰዋእቱን ካጠነ
በኋላ ህዝቡና ካህናቱን ቤተ ክሰርቲያኑን እየዞረ እንዲያጥን ጥናውን ለቄስ ይሰጣል(ድስቅልያ
12:23:38)”(ስርአተ ቤተክርስቲያን: ገጸ 58)
መስዋእት ማቅረብ ሌላው የተዋህዶ “ካህናት” የስራ ዘርፍ ነው:: ስለዚህም ቁርባን “መስዋእት” ብለው ይጠሩታል
በመሰቱ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ስለ ህብስቱና ወይኑ ሲያወራ::

“የምንባርከው የበረከት ጽዋ ከክርስቶስ ደም ጋር ኅብረት ያለው አይደለምን? የምንቆርሰውስ


እንጀራ ከክርስቶስ ሥጋ ጋር ኅብረት ያለው አይደለምን?” 1 ቆሮ 10: 16 በማለት ነው እዚህጋ
ልናስተውለው የሚገባን ነገር ጽዋ እና እንጀራ እንጅ ቁርባን ብሎ አለመጥራቱን ነው:: ሌላው ደግሞ ምናስተውለው
ነገር ጽዋውን ከጌታ ደምጋ ህብረት ያለው እንጅ የጌታ ደም ብሎ አይጠራውም እንጀራውንም ከክርስቶስ ስጋጋ ህብረት
ያለው ብሎ ይጠራዋል እንጅ የክርስቶስ ስጋ ብሎ አይጠራውም:: ቅዱስ ጳውሎስ ለጋንንት ሚቀርብ መስዋእት እያለ
ይጠቀማል ነገር ግን ስለ ህብስቱና ጽዋው ሲመጣ መስዋእት ብሎ አይጠራውም:: ስለዚህ ህብረቱ የክርስቶስን ደም
የሚያስታውሰን የመታሰቢያ ጽዋና ህብስት መሆኑ እንጅ ሌላ አደለም ሐዋርያው እንዳለው:: ሕብረት አለው እንጅ ነው
ልንለው አንችልም:: አደለምም ስለዚህ የጌታ ራት መስዋእት አለመሆኑን በተዋህዶ ቤት የታወቅ ይሁን::

ታዲያ የጌታን ራት መስዋእት(ቁርባን) ነው ነገር ምን ነው ብለን ብንጠይቅ: ዳቦው ተለውጦ በቀጥታ የጌታ ስጋ: ወይኑም
በቀጥታ ተለውጦ የጌታ ደም ይሆናል ብለው ማመናቸው ነው::(እኔ በግሌ ስቆርብ ነው ያደኩት: ወይኑም ያው ወይን
ወይን ነው ሚል ዳቦውም ያው ዳቦ ዳቦ ነው ሚል)

“በካህኑ እጅ ሆኖ ህብስቱን በጻህል ወይኑን በጽዋ አድርጎ በጽሎተ ቅዳሴ አሐዱ አብ ቅዱስ: አሐዱ ወልድ ቅዱስ:
አሐዱ ውእቱ መንፈስ ቅዱስ ብሎ በባረከው ጊዜ: ህብስቱ ተለውጦ ስጋ መለኮት ወይኑም ተለውጦ ደመ መለኮት
ይሆንና ምእመናን በክብር በባለሟልነት ወደ እግዚአብሔር ለመቅረብ የሚቀበሉት ነው” ( ያዕቆብ ሰንደቁ፤ መስዋእተ
ወንጌል፤ ገጽ 8)\

ታዲያ “ሰይጣንም ለተንኮሉ ይጠቅሳል” እንዲሉ አበው፤ ምንም እንኳ “እንጀራው ስጋ: ወይኑም ደመ መለኮት ይሆናል”
ሚል በመጽሐፍ ቅ u ስ አንድም ቦታ ባይገኝም፤ ተዋህዶዋውያን እንጀራውን የጌታ ስጋ ወይኑን የጌታ ደም ይሆናል
ለማለት ያበቃቸው: አንዳንድ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎችም. የሉም ማለት አደለምና: ኑፋቄያቸውን ያጠጋጉበት አንዳንድ
ክፍሎችም አይጠፉም እና እንያቸው::

1 ኛ. “ሲበሉም ኢየሱስ እንጀራን አንሥቶ ባረከ ቈርሶም ለደቀ መዛሙርቱ ሰጠና፦ እንካችሁ፥
ብሉ ይህ ሥጋዬ ነው አለ። ጽዋንም አንሥቶ አመስግኖም ሰጣቸው እንዲህም አለ፦ ሁላችሁ
ከእርሱ ጠጡ፤ ስለ ብዙዎች ለኃጢአት ይቅርታ የሚፈስ የአዲስ ኪዳን ደሜ ይህ ነው።” (ማቴ
26: 26-28)

ይህን የኢየሱስ ቃል በግርድፉ ላየነው እና ቃሉን በሙላት ለማይረዱ ቆርጦ ቀጥል ተዋህዶወች የሚያወዛግብ ቢሆን
ፈጽሞ የሚገርም አይሆንም: እኛ ግን ይህን: ለመረዳት ቅዱሳት መጻህፍትን ከቅዱሳት መጻህፍት አነጻጽረን አንድ ላይ
ሚሰጡትን መልእክት እንጅ : እንደ ቷአህዶወች አንዲትን ጥቅስ ከሙሉ የእግዚአብሔር ሐሳብ ነጥለን ሳንሮጥ ለማንበብ
ይህን ክፍል ሐዋርያው ጳውሎስ ባብራራበት ክፍሉ: (1 ኛ ቆሮንቶስ 11:25-26) እንዲሁም ጌታ ኢየሱስ ይህን ክፍል
ሲናገር ማቴወስን ግልጽ አድርጎ የሚነገረንን የሉቃስን (ሉቃ 22:20) አብረን እንይ::

“እንደዚሁም ከእራት በኋላ ጽዋውን ደግሞ አንሥቶ፦ ይህ ጽዋ በደሜ የሚሆን አዲስ ኪዳን
ነው፤ በጠጣችሁት ጊዜ ሁሉ ይህን ለመታሰቢያዬ አድርጉት አለ። ይህን እንጀራ በበላችሁ ጊዜ
ሁሉ፥ ይህንም ጽዋ በጠጣችሁ ጊዜ ሁሉ ጌታ እስኪመጣ ድረስ ሞቱን ትናገራላችሁና።”(1 ቆሮ
11:25-26)

“እንዲሁም ከእራት በኋላ ጽዋውን አንሥቶ እንዲህ አለ፦ ይህ ጽዋ ስለ እናንተ በሚፈሰው


በደሜ የሚሆን አዲስ ኪዳን ነው።” (ሉቃ 22:20)
በዚህ ንግግሩ ጌታ ኢየሱስ ክልኤ ምስለ ንግርት(double figurative speech) ነው የተናገረው: በዚህ ንግግሩ ስለ
ጽዋው እና ስለ ደሙ ነው ስለ ተናገረ: እናስተውል ስለ ወይኑ ብቻ አልተናገረም ወይኑ ስለሚቀመጥበት ጽዋ ጭምር
አንጅ:: ስለ ጽዋው ሲናገር እንዲህ አለ “ይህ ጽዋ ስለ እናንተ በሚፈሰው በደሜ የሚሆን አዲስ ኪዳን ነው::” እንግዲ
ተዋህዶወች ይህንንም ቀጥታ ወስደው አዲስ ኪዳን ማለት ጽዋው ነው ሊሉን ነው ማለት ነው:: እኛ በዘመነ አዲስ ኪዳን
ውስጥ ነው ምንኖር ስንልም፤ እኛ በጽዋ ውስጥ ነው ምንኖረው ሊሉን ነው ማለት ነው? ችግሩ መናፍቃን አንዱን ጥሎ
አንዱን አንጠልጥሎ ባህሪያቸው ስለሆነ ይህም አንዱ መገለጫቸው ነውና: በተመሳሳይ ክፍል ላይ የተነሳውን:
“እንጀራውን ስጋየ ነው ብሏልና ስጋው ነው” እንደሚሉት፤ ጽዋውን አዲስ ኪዳን ነው ብሏልና አዲስ ኪዳን ነው
አይሉም:: በዚህ ክፍል እንዳውም ጌታ ኢየሱስ ከተዋህዶወች በተቃራኒ ወይኑም ወይን ሁኖ እንደቀጠለ እንመለከታለን::
“እላችኋለሁና፥ የእግዚአብሔር መንግሥት እስክትመጣ ድረስ ከአሁን ጀምሮ ከወይኑ ፍሬ
አልጠጣም አለ።” (ሉቃ 22:18
ተመልከቱ ተዋህዶወች “ወይኑ ከዛ በኋላ ወይን አደለም ስጋ መለኮት ነው፤ ፍጹም ተለውጧል” ቢሉም ጌታ ኢየሱስ ግን
አሁንም ወይን እያለ ይጠራዋል:: እንደዚህ ክፍል አገላለጽም ከሆነ እንገዲግ የእግዚአብሔር መንግስት ስትመጣስ ጌታ
የራሱን ደም ይጠጣል ይቆርባል ሊሉን ይሆን ተዋህዶወች? ምን ሊያደርግለት? ሌላው ማስተዋል ሚገባን ነገር
ተዋህዶወች የጌታን ራት “መስዋእት ነው” ሲሉ ያላስተዋሉት ነገር ቢኖር ጌታ ኢየሱስ ይህን የተናገረውም ሆነ የሰጣቸው
ከመሰቀሉ በፊት ነው:: ይህም ማለት ገና ራሱን መስዋእት አድርጎ አላቀረበም ነበር ማለት ነው:: ይህ ራሱ የጌታ ራት
መስዋእት አለመሆኑን ያሳያል፤ መቸስ ያልቀረበ መስዋእት ሆነ አይሉንም የኑፋቄ ስር የሆኑት የተዋህዶ ቅርንጫፎች::
ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስም በተመሳሳይ፤

“ስለዚህ ሳይገባው ይህን እንጀራ የበላ ወይም የጌታን ጽዋ የጠጣ ሁሉ የጌታ ሥጋና ደም ዕዳ
አለበት። ስለዚህ ሳይገባው ይህን እንጀራ የበላ ወይም የጌታን ጽዋ የጠጣ ሁሉ የጌታ ሥጋና
ደም ዕዳ አለበት።” (1 ቆሮ 11:27-29) በማለት ወይኑም እንዳልተወጠ እንጀራውም እንዳልተለወጠ በየስማቸው
ይጠራቸዋል እንጅ “የጌታን ስጋ የበላ፤ የጌታን ደም የጠጣ እያለ አይናገርም:: ስለዚህ ይህ እንጀራ ከጌታ ስጋጋ ህብረት
ያለው እንጀራ: ይህም ወይን ከጌታ ደምጋ ህብረት ያለው ወይን እንጅ ተዋህዶ እንደምትለው ተለውጦ ስጋ ተለውጦ
ደም አይሆንም:: ይሄ በቀጥታ ስጋ ና ደም ይሆናል ሚለው አመለካከት የአረማውያን በላኤ-ሰብነት(cannibalism) እንጅ
ሌላ ምንም ሊሆን አይችልም:: ነገር ግን ይህ ስርአት ለእርሱ መታሰቢያ የሚሆን ስርአት እንጅ ሌላ ከዛ ያለፈ ትርጉም
ሊሰጠው አይችልም::(1 ቆሮ 11:25) የጌታ “ለመታሰቢያየ አድርጉት” የሚለው ቃል በራሱ ወደራሱ ስጋ ሚለወጥ
አለመሆኑን ሚያሳየው: ስጋው ቢሆን ኑሮ ይህ ክርስቶስ ነውና: እሱ እዛው እያለ ሊታሰብ መታሰቢያ ሊባል ስለማይችል:
ይህን ማለት ባላስፈለገውም ነበር:: ለምሳሌ የወዳጆቻችንን: የዘመዶቻችንን: የቤተሰባችንን ፎቶ በኪሳችን: በዋሌታችን:
በቦርሳችን ለመታሰቢያ እንይዛለን:: ለሰውም ስናሳይ: ይህ ፍቅረኛየ ነው: ይህች ባለቤቴ ነች፤ ይህ ወንድሜ ነው: እያልን
ወደ ፎቶው እናሳያለን ይህ ማለት ታዲያ ፎቶው ራሱ: ፍቅረኛችን: ባለቤታችን: ወንድማችን ነው ማለት አደለም: የነሱ
መታሰቢያ በነሱ ስለጠራ እንጅ:: ጌታ ኢየሱስም የተናገረበት ንግግር ከዚህ የተለየ አለመሆኑን ለመታሰቢያየ አድርጉት
ማለቱ ማሳያ ነው::

2 ኛ. “ሥጋዬን የሚበላ ደሜንም የሚጠጣ የዘላለም ሕይወት አለው፥ እኔም በመጨረሻው ቀን


አስነሣዋለሁ። ሥጋዬ እውነተኛ መብል ደሜም እውነተኛ መጠጥ ነውና። ሥጋዬን የሚበላ
ደሜንም የሚጠጣ በእኔ ይኖራል እኔም በእርሱ እኖራለሁ።” (ዮሐ 6:54-56)
ጌታ ኢየሱስ በዚህ ክፍል እየተናገረ ያለው ቃሉን ሰምቶ ማመንን እምነትን በስጋው: በደሙ መስሎ እንጅ ተዋህዶወች
እንደሚሉት በቀጥታ ስለስጋው በቀጥታ ስለደሙ እየተናገረም አደለምም አልነበረምም:: ተዋህዶ ለዚህ ስህተቷ ይህን
ጥቅስ እንደማስረጃ ማቅረቧ ራሱ ከዚህ ሁለ “አራት አይናወቿ”(መጽሐፈ መነኮሳት ሚባል ተረት ሲቀነስ ሁለት
ይሆናል) መካከል አንዱማ አለምየቱ አይን ቢኖርም ከታወረ እንደማይጠቅም ማሳያ ነው::

በዚህ ክፍል ላይ ቁጥር 26 ጀምረን ስናነበው: ጌታ ኢየሱስ 5 ገበያ ህዝብ ከመገበ በኋላ: ሊያነግሱሰት ሲመኙ
ሲሰወርባቸው: እሱን አፈላልገው የመጡትን ሰወች:-

“ኢየሱስም መልሶ፦ እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ የምትፈልጉኝ እንጀራን ስለ በላችሁና ስለ


ጠገባችሁ ነው እንጂ ምልክቶችን ስላያችሁ አይደለም። ለሚጠፋ መብል አትሥሩ፤ ነገር ግን
ለዘላለም ሕይወት ለሚኖር መብል የሰው ልጅ ለሚሰጣችሁ ሥሩ፤ እርሱን እግዚአብሔር አብ
አትሞታልና።”(ቁ 27) በማለት አንድ የማይጠፋ መብል እንዳለ ይነግራቸዋል: እነሱም ይህን
የማይጠፋ መብል ለማግኘት በመመኘት “እንግዲህ፦ የእግዚአብሔርን ሥራ እንድንሠራ ምን
እናድርግ? አሉት።” (ቁ 28) ብለው በጉጉት ሲጠይቁት፤ እንግዲህ ይህን ምግብ ጌታ ኢየሱስ
አስረግጦ ሲነግራቸው:: “ኢየሱስ መልሶ፦ ይህ የእግዚአብሔር ሥራ እርሱ በላከው እንድታምኑ
ነው አላቸው።” በማለት ይህ መብል ማለት በእርሱ ማመን መሆኑን አስረዳቸው:: እንግዲ ተዋህዶወች ጌታ ኢየሱስ
እርሱ ስጋየን መብላት ደሜን መጠጣት ብሎ የጠራው ቃሉን ሰምቶ ማመን መሆኑን በዚህ ተናግሮ የነበር ቢሆንም:
ቆርጦ ቀጥል: የመጽ`ሀፍ ቅዱስ አተረጓጎም ስልት የሌላቸው “መጽሐፍ ቅዱስን እንደፈለክ ተረጉም” የሚል መርህ
የሚከተሉት:: ተዋህዶወች ግን ዘለው ሂደው ከአውዱ ነጥለው ቁጥር 54 ላይ ሂደው ባልተነገረበት መልኩ በመናገር ሌላ
ርእስ ላይ ገብተዋል:: እንግዲህ እነሱም እርሱን በማመን መንፈሳዊ ምግብ ሳይሆን የፈለጉት ልክ እንደተዋህዶወች ስጋዊ
ሚታኘክ ሚዋጥ ነውና: እርሱ ሚሰጣቸው ምግብ እምነት መሆኑ አላረካቸውምና፤ “እንግዲህ፦ እንኪያ አይተን
እንድናምንህ አንተ ምን ምልክት ታደርጋለህ? ምንስ ትሠራለህ?”( ቁ 30) በማለት ይበሉ ዘንድ መናን
ሰጣቸው ተብሏል ምናምን ብለው ተዋህዶወች ቅዱሳን እንዲህ አደረጉልን እያሉ እንደሚያመልኳቸው ሙሴ እንዳደረገ
ሲናገሩ፤ ጌታ ኢየሱስ እንጀራ የሰጣችሁ አባቴ እንጅ ሙሴ አይደለም ብሎ የሰወችን አምልኮት ከተቃወመ በኋላ::
“የእግዚአብሔር እንጀራ ከሰማይ የሚወርድ ለአለምም ህይወትን የሚሰጥ ነውና” አላቸው:: እንግዲህ ተመልከቱ
ተዋህዶዋውያን ከሰማይ የወረደ ሳይሆን ከጓሮ የበቀለ ስንዴና እና ወይን እየበሉ እየጠጡ ነው እንግዲ ኢየሱስ
እየተናገረለት ስላለ ከሰማይ ሚወርድ(ኢየሱስ ከሰማይ የመጣ የህይወት ቃል አለው) ነገርጋ ለማመሳሰል ሚሞክሩት::
ጌታ ኢየሱስ ይህን ካለ በኋላ በቁጥር 35 “ኢየሱስም እንዲህ አላቸው፦ የሕይወት እንጀራ እኔ ነኝ፤ ወደ
እኔ የሚመጣ ከቶ አይራብም በእኔ የሚያምንም ሁልጊዜ ከቶ አይጠማም።” በማለት ደግሞ መልሶ
በእረሱ ማመንን በመጠጥ ይመስለዋል:: አንግዲህ ይህን ካለ በኋላ ነው ጌታ ኢየሱስ በቁጥር 53: “ስለዚህ ኢየሱስ
እንዲህ አላቸው፦ እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ የሰውን ልጅ ሥጋ ካልበላችሁ ደሙንም
ካልጠጣችሁ በራሳችሁ ሕይወት የላችሁም።” ያላቸው:: ከላይ ቃሉን ሰምቶ ማመንን በእንጀራ ና መጠጥ
ከመሰለላቸው በኋላ ነውና ይህን ያለው አንድ ላይ መረዳት ያለብን ነገር ቢኖር ስጋና ደሜ ያለው ቃሉን ሰምቶ በእርሱ
ማመንን ነው:: ነገሩ ተዋህዶዋውያን በስጋዊ ጆሮዋቸው ሰምተው መሰናከላቸው የሚገርም አደለም: ሐዋርያቱም
የመልእክቱን አውድ ባለመረዳት “ስጋየን ብሉ” ሚለውን ብቻ አንደ ተዋህዶወች አንጠልጥለው በመሔድ “
“ከደቀ መዛሙርቱም ብዙዎች በሰሙ ጊዜ፦ ይህ የሚያስጨንቅ ንግግር ነው፤ ማን ሊሰማው
ይችላል? አሉ።” (ቁ 60) በማለት ስጋውን ሊያበላን ነው የሚል ስጋት አድሮባቸው አንጎራጉረው ነበር:: ጌታ
ኢየሱስ ግን “እንዳንጐራጐሩ በልቡ አውቆ አላቸው፦ ይህ ያሰናክላችኋልን? እንግዲህ የሰው ልጅ
አስቀድሞ ወደ ነበረበት ሲወጣ ብታዩ እንዴት ይሆናል? ሕይወትን የሚሰጥ መንፈስ ነው፤ ሥጋ
ምንም አይጠቅምም፤ እኔ የነገርኋችሁ ቃል መንፈስ ነው ሕይወትም ነው።” (ቁ 61) በማለት
ህይወትን ሚያገኙት ቃሉን ሰምተወ በእርሱ በማመን እንጅ ስጋውን በመብላት ስላልሆ ሚጠቀሙት ስጋየን ይዠው
አርጋለሁና እንድትበሉት አልሰጣችሁም ብሎ አርሟቸዋል::

እንደወ በአውዱ እንረዳው ብየ እንጅማ ጌታ ኢየሱስ እንዲህ ራሱን በተለያየ መንገድ እየመሰለ መናገሩ ቤ o ሐንስ
ወንጌል ተደጋግሞ የተጻፈ ነውና ይህ አዲስ ነገር አደለም:: ስለዚህ ይህን ክፍል ራሱ በቀጥታ እንውሰድ
ከተባለ ሌሎች ምሳያዊ ንግግሮችም በቀጥታ መውሰድ አስፈለጊ ሊሆን ነው ማለት ነው::
ለምሳሌ ከዚህ ክፍል ሁለት ምእራፍ ብቻ ከፍ ብለን ምእራፍ 3 ላይ ጌታ ኢየሱስ ሳምራዊቷን
ሴት “ኢየሱስም መልሶ፦ ከዚህ ውኃ የሚጠጣ ሁሉ እንደ ገና ይጠማል፤ እኔ ከምሰጠው ውኃ
የሚጠጣ ሁሉ ግን ለዘላለም አይጠማም፥ እኔ የምሰጠው ውኃ በእርሱ ውስጥ ለዘላለም
ሕይወት የሚፈልቅ የውኃ ምንጭ ይሆናል እንጂ አላት።”(ዮሐ 4:140) ታዲያ ተዋህዶወች ይህን ቀጥታ
ወስደው ኢየሱስ ውሃ ይሰጣል ከክርስቲያኖች ውስጥም ምንጭ አለ ውሃ ይፈልቃል ሊሉን ይሆን?

በተመሳሳ ይ መንገድ እንዲሁ በ ዮሐ 10: 7 ላይ “በሩ እኔ ነኝ” ስላለ ኢየሱስን በቀጥታ በር ነው ሊሉት ነው? ነው
ወይንስ ልክ መስዋእት እንደ ሚያዘጋጁት ሁሉ በር ሰርተው ይህ ወደ ኢየሱስ ይቀየራል ብለው በዚህ በር ግቡ ውጡ
ሊሉን ይሆን? ነው ወይንስ በዮ 15:5 ላይ “እኔ የወይን ግንድ ነኝ እናንተም ቅርንጫፎች ናችሁ። ያለ እኔ
ምንም ልታደርጉ አትችሉምና በእኔ የሚኖር እኔም በእርሱ፥ እርሱ ብዙ ፍሬ ያፈራል።” ስላለ
ኢየሱስን በቀጥታ የወይን ግንድ ነው ሊሉት ይሆን ወይንስ ለጌታ ራት የሚሆነውን ወይን ሚያመጡበት የወይን ግንድ
ወደ ኢየሱስነት ተቀይሯል ለዛ ነው ወይኑን የጌታ ደም ነው የምንለው ሊሉን ነው? ወይንስ በ ዮሐ 14:14-15
“መልካም እረኛ እኔ ነኝ፥ አብም እንደሚያውቀኝ እኔም አብን እንደማውቀው የራሴን በጎች
አውቃለሁ የራሴም በጎች ያውቁኛል፤ ነፍሴንም ስለ በጎች አኖራለሁ።” ስላለ በቀጥታ ወስደው
ኢየሱስ በእረኝነት ተቀጥሮ ሚሰራ ዋሽንት ሚነፋ ጎረምሳ መስሎ ይታያቸው ይሆን? እኛስ ወደ በግነት ተቀይረናል ሰው
እንምሰል እንጅ ወደ በግነት እንቀየራለን ይሉ ይሆን? ነው ወይንስ እንደ ማቴ 5:13 አገላለጽ “እናንተ የምድር
ጨው ናችሁ፤ ጨው አልጫ ቢሆን ግን በምን ይጣፍጣል? ወደ ውጭ ተጥሎ በሰው ከመረገጥ
በቀር ወደ ፊት ለምንም አይጠቅምም።” ስለሚል ወደ ጨውነት ነው ምንቀየረው? ነው ወይንስ ወደ በግ
ጨውነት ነው ምንቀየረው? አንግዲ ተዋህዶወች በምሳሌ የተነገረውን ሁሉ ቀጥታ ከወሰዱ ሁሉንም ነው መውሰድ
ያለባቸው:: ነገሩ የመናፍቅ ባህሪ አንዱን ጥሎ አንዱን አንጠልጥሎ ነውና ይህና ባታደርግ የሚገርም አይሆንም ይህች
የመናፍቅ ድርጅት::

“በቅዳሴ ጊዜ እጣን አይቀርም...” ብላለች ተዋህዶ ስርአተ ቤተ ክርስቲያን በተባለው መጽሐፏ:: ለመሆኑ እጣኑ ለማን
ነው? እኔ ሚገርመኝ ተዋህዶ ከአረማውያንና ጥላና ምሳሌ ሁነው ካለፉ ለአይሁድ ብቻ ተሰጥተው ከነበሩ ስርአቶች
አምጥቶ: ለክርስትና ማዋል እንደው የቅዠት ሁሉ ቅዠት ካልሆነ ከቶ ምን ልንለው እንችላለን? ሲጀመር የብሉዩ
የመቅድስ ሰርአትን ለማመሳሰል ከሆነ የተዋህዶ ከአረማውያን መቅደሶችጋ ቢመሳሰል እንጅ ከብሉዩ የመቅደስ ስርአት
አይመሳሰልም:: ሲቀጥል በአዲስ ኪዳን መቅደስ እኛ ክርስቲያኖች እንጅ የሰው እጅ የሰራው የድንጋይ ክምር አደለም::
ጌታ ኢየሱስስን ሐዋርያት የመቅደሱን ውበት ሲያሳዩት በመቅደሱ ውበት አልተማረከም:: ይልቁን ተጸይፎት ድንጋይ
በደንጋይ ላይ ሳይወድቅ አይቀርም በማለት የድንጋይ ክምር ፈጽሞ እንደማይስበው ተናግሯል:: እንጅ የድሮው የመቅደስ
ስርአት በብሉይ አልቀጠለም:: ሲሰልስ የመቅደሱ ስርአቶች ለእስራኤል ዘስጋ የተሰጠ ስርአት እንጅ ለአዲስ ኪዳን
አማኞች ይህ ስርአት ተሽሯል አይሰራም::
“እነርሱ እስራኤላውያን ናቸውና፥ ልጅነትና ክብር ኪዳንም የሕግም መሰጠት የመቅደስም
ሥርዓት የተስፋውም ቃላት ለእነርሱ ናቸውና” (ሮሜ 9:4)

3.3.5 ለሙታን መጸለይ


“ለሙታን ወገኖቻችን የመታሰቢያ ጸሎት ለሃጢያታቸው ስርየት የሚያሰጥ ጸሎት ካረፉበት እለት አንስቶ
መጸለይ እንዳለበት ከቤተ ክርስቲያን አገልግሎት አንዱና ዋነኛው ነው::” ((ሊቀ ስልጣናት ሃብተ ማርያም
ወርቅነህ፤ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት እና ትምህርት፤ ገጽ 237)

ተዋህዶወች ሌላው አሰቂኙና የሞኝ ስራቸው ይህ ነው አንዴ ወደእግዚአብሔር ፍርድ የገባን ሰው


እግዚአብሔርን በሃብታቸው በገንዘባቸው በመደለል: “ካህናት” ተብየወች ተሰብስበው በግእዘኛ
ስለተንጫጩና ስለጮሁ እና የ “ካህናቱን” ሆድ ሳልስት: ሰባት: አርባ ሰማኒያ እያሉ ስለሞሉ ሰውየው
ከስሳት ወጥቶ የሚድን የሚመስላቸው ጅሎች ናቸው::
መጽሐፈ ግንዘት ገጽ 215 ላይ ስለዚህ የሞኝ አሰራር አመሰራረት ሲናገር አንድ ጨካኝ ባለጸጋ ሰው ነበር
በሂወቱ በክፋት ሲኖር ኤጲስ ቆጶስ የሆነ ልጁ ቢመክረው አልሰማ አለ በመጨረሻ ሰውየው ሞተ: በዚህ
ጊዜ ኤጲስ ቆጶሱ ሲያዝን እግዚአብሔር የአባቱን ሁኔታ ሲያሳየው በጣም በማዘን በስሙ መዘከር ጀመረ:
በዚህ ጊዜ በሶስተኛው ቀን እሳቱ ቀንሶለት አየ እንዲሁ በሰባተኛው ቀን እሳቱ ቀነሰለት እንዲህ እንዲህ
እያለ ሰውየው: በሰባተኛው አመት ከእሳት ወጣ:: ብሎ ይተርካል ያው ተረቴን መለስሱ አፌን በዳቦ አብሱ
ብሎ ግን አያጠናቅቅም::

ያረጋል አበጋዝ የተባለ ዝም ብሎ የተረት መጽሐፍ ቢጽፍ ማይደክመው ሰው ደግሞ በአስቂኝ መጽሐፉ: መድሎተ
ጽድቅ ቅጽ 1 ገጽ 461 ላይ “ኦርቶዶክሳዊት ተዋህዶ ቤተ ክርሰቲያን ከሞት በኋላ ንስሃ ወይም ደግሞ መካነ
ንስሐ(purgatory) አለ ብላ አታምንም: አታስተምርም:: ይህ አይነቱ ባህል የካቶሎሊክ ቤተ ክርስቲያን ካመጣችው
የፈጠራ ትምህርት አንዱ ነው:: እኛ ምናምነው እግዚአብሔር ባወቀ ይቅር ይላቸውና ቸርነቱን ያበዛላቸው ዘንድ ላረፉት
ወገኖቻችን እንጸልያለን” ብሎ ጭራሽ ያወሳስበዋል:: እንደው ለመሆኑ ይህ አይነት ነገር በመጽሐፍ ቅዱስ:
በእግዚአብሔር ቃልም: በሐዋርያት ስራም እንዲህ ሲደረግ አላየንም እንጅ: ቢሆን እንኳን ከኦርቶዶክሱስ የካቶሊኩ
ሳይሻልም የሚቀር አይደለም:: ለመሆኑ አቶ ያረጋል አስተውሎ ከሆነ እኮ ካለ ንስሃ ወጣ ከማለት በንስሃ ወጣ ማለት:
ከሃጢያተኞች መካከል አንዱ ከሌሎች እኩል: ምናልባትም በባሰ መልኩ ሃጡያት ሲሰራ ኑሮ በምድር ያሉ ሚያውቁት
ሰወች ስለጸለዩለት: ዘመዶቹ: ምግብ የቄስና የሰው ሆድ ሰብስበው ስላበሉለት: ጠላ ስላጠጡለት: ስላሰከሩለት: ብቻ
ተለይቶ ከሃጥአን መካከል ወጣ ከማለት ማለት: በምድር መንፈሳዊ ኑሮ ስለነበረው: የጥፋቱን ያክል ሚቀጣበት
የመንጻት ስፍራ(purgatory) ስላለ እዛ ገባ ሚለው ሚዛን ይደፋ ነበር:: ይህ ሰው ይህን ይበል እንጅ Meyendorff
የተባለ የኦርቶዶክስ ስነ-መለኮታዊ ከሞት በኋላ የንስሃ እድል ሊኖር እንደሚችል “Man’s freedom is not destroyed
even by physical death; thus, there is the possibility of continuous change and mutual intercession.”
(Byzantine Theology, p. 222) በማለት ተናግሯል:: አንግዲህ ከሁለቱ የቱ ትክክለኛ የተዋህዶ ትምህርት ነው ብንል
ተዋህዶወች የተመቻቸውን መርጠው የተመቻቸውን የመውሰድ ባህላቸውን እዚጋ ያውሉታል::

ነገሩ የካቶሊኩም የኦርቶዶክሱም ግን ከመጽሐፍ የወጣ የተጣላ ከንቱ የፍጡር ፈጠራና የምኞት እንጅ የእግዚአብሔር
ሃሳብም አደለም በቃሉም የለም:: ነገሩ ያረጋል አሰቂኝነቱ የቀረው: በዚህ መጽሐፉ ገጽ 455 ይህን ምናደርገው
እግዚአብሔር ቸር ስለለሆነ ነው የሚል ማመካኛ ማምጣቱ ነው:: ለመሆኑ እግዚአብሔር ቸር ስለሆነ እያለ ቢዘሙት
ቢደፍር ይሆናልን? የእግዚአብሔር ቸርነት መጻህፍት ከተናገሩት ለመራቅ ፈጠራን ለማስገባት ለመጠቀም ካሰብክ
እንግዲያው ሃዋርያው ጳውሎስ:
“እንግዲህ የእግዚአብሔርን ቸርነትና ጭከና ተመልከት፤ ጭከናው በወደቁት ላይ ነው፥
በቸርነቱ ግን ጸንተህ ብትኖር የእግዚአብሔር ቸርነት በአንተ ላይ ነው፤ ያለዚያ አንተ ደግሞ
ትቆረጣለህ።” (ሮሜ 11:12) በወደቁት ላይ ጨካኝ እንጅ ቸር አይደለም ይለዋል:: ይህ ሰው ግን ቃሉን ትቶ የተረት
ትምህርቱን ያጸደቀ መስሎት በቸርነቱ ተሽሽገ:: ነገሩ ይህ ትምህርት የእግዚእብሔርን ቸርነት ሚያሳይ ሳይሆን
ከእግዚአብሔር ይልቅ የሰው ልጆችን ቸር አድርጎ ሚያቀርብ የአጋንንት ትምህርት ነው:: ምክንያቱም እግዚአብሔር
ልጁን እንኳን የከፈለላትን ነፍስ መንግሰተ ሰማይ አይገባትም ብሎ ጥሏት እያለ፤ ከእሱ ይልቅ ግን ፍጡራን ራርተውና
ሳስተው ወደ ከሲኦል በጸሎታቸው እግዚአብሔርን አሽንፈው ሃሳባቸውን አስቀየሩ አንደማለት ነው ነገሩ እንዲህ ያለ
ነገር በተዋህዶ ቤት የተለመደ ነው:: ለምሳሌ ያክል መንገደ ሰማይ በተባለች ትንሼ ክታብ: አንዲት ነፍስ አጋንንት
እያሰቃዩ ሲወስዷት አግንንቱን እንዲያሳርፏት ትማጸናቸዋለች:: እንዲህ ይላል ክታቡ “ስለተሰቀለው መድኃኔ ዓለም
ብላችሁ ጥቂት አሳርፉኝ ትላቸዋለች መድኃኔ ዓለምን ማወቅ ቀድሞ ነበር፤ ዛሬ ደርሰሽ ከኛ ስትመጭ ነው
ማወቅሽ? ቀድሞ ዝክሩን መዘከር በዓሉን ማክበር ነበር እንጂ ዛሬደርሰሽ እንዲህ ብትይ ይሆናልን ይልቁንስ
በሏት ቀጥቅጧት በማለት መከራውን በእጥፍ ድርብ ያጸኑባታል።” (መንገደ ሰማይ 1:46) በዚህ ክፍል
የመድሃኒያለምን ስም ስለጠራች እንኳን ልታርፍ እንደወም መከራው ይጸናባታል: ቀጥሎም ይህች ነፍስ “በእነ
እግዝእትነ ማርያም ጥቂት አሳርፉኝ ትላቸዋለች እግዝእትነ ማርያምን ዛሬ ደርሰሽ ከኛ ስትመጭ ነው
ማወቅሽ? ቀድሞ ዝክሯን መዘከር በዓሏን ማክበር ነበር እንጂ ዛሬ ደርሰሽ እንዲህ ብትይ ይሆናልን ይልቁንስ
በሏት ቀጥቅጧት በሚሉበት ጊዜ እግዝእትነ ማርያም ስሟን ሲጠሯት ፈጥና ደራሽ ናትና ሄዳ ከልጅዋ እግር
ወድቃ መሐር ወልድየ ወተዘከር ኪዳንየ ልጄ ሆይ የሰጠኸኝን ቃል ኪዳን አስበህ ይህቺን ነፍስ ማርልኝ
ትለዋለች። እሱም እናቴ ሆይ እኔን የከዳች አንችን የበደለች ነፍሰ ገዳይ ወምበዴ ነፍስ ናት በምን ምግባሯ
ልማርልሽ ይላታል ለዘጸውዓ ስመኪ ወለዘገብረ ተዝካረኪ እምሕር ለኪ ብለኸኝ የለምን የሰጠኸኝ ቃል ኪዳን
ይታበላልን? እነሆ በሲኦል ሁና ስሜን ትጠራለችና ትለዋለች። እርሱም የናት ልመና ፊት አያስመልስ አንገት
አያስቀልስምና ጥቂት ጊዜ ስለናቴ ብላችሁ አስርፏት ይላቸዋል።” (መንገደ ሰማይ 1:47-49) በማለት ይተርካል
ተመልከቱ የጌታን የኢየሱስን ስም መጥራት መከራን ሚያብስ የማርያምን ስም መጥራት ግን ረፍት ሚሰጥ: ጌታ የጌታን
ስም የሚጠራ መከራው ሚብስበት: የማርያምን ስም የሚጠራ ግን የሚድን የሚያርፍ: እሷ ቸር እሱ ግን ልቡ ማይራራ
ደንዳና:: አድርገው በማቅረብ ሰውን ከክርስቶስ የሚያርቅ ሰይጣናዊ አሰራርን ምታስፋፋ ሃይማኖት ናትና ፍጡራን
ከክርስቶስ ይልቅ ቸሮች አድርጋ ማቅረቧ በተዋህዶ ብዙም ሚፈረድ አደለም:: የአጋንንት አሰራር ላይ ጽድቅን መጠበቅ
እንዴት ይቻላል?

የዚህን አጋንንታዊ ትምህርተ ምንጩን ለመመርመር ወደ ኋላ ብንመለስ: የጣኦታውያን የአረማውያን ሁኖ እናገኘዋለን


እንጅ ሐዋርያት በአንድም ስፍራ ይህን አይነት ስርአት ይፈጽሙ እንዳልነበር: እስጢፋኖስን ሲቀብሩት እንዲህ ያለ
ስርአት አለመፈጸማቸውን በማንበብ እነረረዳለን:: (ሐዋ 8:2) ለመሆኑ መለቀሱን እንኳ ያስጻፈለን መንፈስ ቅዱስ
ስርአተ ፍትሐትን ረስቶተ ሳያስጽፈው ቀረን??

ይልቁንም ይህ አሰራር ከምንጩ ለፈተሽ በጥናታዊ ስልጣኔወች ለምውታን ወደ አማልክቶቻቸው ይጸልዩ አንደነበር
እንዲሁም ለምውታን የመዳን ተስፋ እንዳለም ያምኑ እንደነበር ይረዳል:: በፊሎሶፊ ሚታወቀው ፕላቶ “አንዳንዶች
ከሞቱ በኋላ የሚገባቸውን ያህል ቅጣት ወደሚያገኙበት ይወሰዳሉ ከዛ ወደ መልካም ስፍራ ይወሰዳሉ ፤ ሌሎቹ ደግሞ
ልክ በህይወት ይወሰዳሉ::” (pluto Phaedrus page 249)

በጥንት ግብጻውያን አረማውያን አንዱ ስርአት የነበረው: የጣኦት ካህናት ለምውታን ስርአተ ፍትሐት መፈጸም ነበር::
ይህን ስርአት ለመፈጸም ልክ እንደ አሁን ተዋህዶወች ለካህናቱ ገንዘብ መክፈልና ሆዳቸውን መሙላት እንደ ግዴታ
ይታይ ነበር:: ያለ ካህኑ ፍትሃት ካልሆነ ሟቹ ቅጣቱ አያቆምም ብለው ያምኑ ነበር:: ልክ እንደ ተዋህዶ ካህናት ሁሉ
ተረት እየተከተሉ ወሬ የሚወዱትን የመለቶችን መቀነት እየፈቱ ኪሳቸውን ያደልባሉ ሆዳቸውንም በዝክር ስም
ይሞላሉ:: በአማራና ትግሬ ዛሬ ድረስ የፍትሃት ዝክር ያላበላ ልክ እንደ እብድ ውሻ ነው ሁሉም ሚያገላቸው
ሚጠቋቆምባቸው::

መጽሐፍ ቅዱስ ግን ፈጽሞ ሙታን ከሲኦል ወደ ገነት የሚሄዱበት እድል አለ ብሎ ፈጽሞ አያስተምርም እንዳውም
በተቃራኒው እንጅ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስም ስለ ባለጸጋውና እና ስለ አልአዛር ባስተማረበት ክፍል::

“ከዚህም ሁሉ ጋር ከዚህ ወደ እናንተ ሊያልፉ የሚፈልጉ እንዳይችሉ፥ ወዲያ ያሉ ደግሞ ወደ


እኛ እንዳይሻገሩ በእኛና በእናንተ መካከል ታላቅ ገደል ተደርጎአል አለ።” (ሉቃ 16:26) በማለት
ሃጢያተኞች ወደ ጻድቃን ጻድቃንም ወደ ሃጢያተኞች አለም ሚሽጋገሩነት እድል ፈጽሞ አንደሌለ ነው አስረግጦ
የተናገረው:: እንጅ እንደ ተዋህዶወች በዘመዶችህ ገንዘብና ጠላ ይሽጋገራሉ አታስብ ዘመዶችህ ዝክርህን ያውጡ
መጽሐፈ ግንዘትን ይተግብሩ አላለውም:: ሃብታሙም አንዲያስ ከሆነ ወንድሞቸ እንዳይመጡ ልሂድና ልንገራቸው
ቢለውም አሁን አርፍዷል: የሙሴና የነብያትን ቅዱሳት መጻህፍት ያንብቡ እንሱ ሁሉን ይንግሯቸዋል አለ እንጅ::
እንደው ትውፊቱንም መጽሐፈ ጤፉቱንም አውተፍትፈው ይዳኑ አላለውም:: እንዲሁም በመጽሐፈ መክብብ ጠቢቡ
ሰሎሞን::
“የጭንቀት ቀን ሳይመጣ በጕብዝናህ ወራት ፈጣሪህን አስብ፤ ደስ አያሰኙም የምትላቸውም
ዓመታት ሳይደርሱ፤ ፀሐይና ብርሃን ጨረቃና ከዋክብትም ሳይጨልሙ፥ ደመናትም ከዝናብ
በኋላ ሳይመለሱ፤ ቤት ጠባቆች በሚንቀጠቀጡበት፥ ኃያላን ሰዎችም በሚጎብጡበት፥
ጥቂቶች ሆነዋልና ፈጭታዎች ሥራ በሚፈቱበት፥ በመስኮትም ሆነው የሚመለከቱ
በሚጨልሙበት፥ በአደባባይም ደጆቹ በሚዘጉበት ቀን፤ ወፍጮ ድምፅ ሲላሽ፥ ከወፍ ድምፅ
የተነሣ ሰው ሲነሣ፥ ዜማም የሚጮኹ ሴቶች ልጆች ሁሉ ዝግ ሲሉ፤ ከፍ ያለውን ደግሞ
ሲፈሩ፥ ድንጋጤም በመንገድ ላይ ሲሆን፤ ለውዝም ሲያብብ፥ አንበጣም እንደ ሸክም
ሲከብድ፥ ፈቃድም ሲጠፋ፤ ሰው ወደ ዘላለም ቤት ሲሄድ፥ አልቃሾችም በአደባባይ ሲዞሩ፤
የብር ድሪ ሳይበጠስ፥ የወርቅም ኵስኵስት ሳይሰበር፥ ማድጋውም በምንጭ አጠገብ
ሳይከሰከስ፥ መንኰራኵሩም በጕድጓድ ላይ ሳይሰበር፥ አፈርም ወደ ነበረበት ምድር ሳይመለስ፥
ነፍስም ወደ ሰጠው ወደ እግዚአብሔር ሳይመለስ ፈጣሪህን አስብ።” (መክብብ 12:1-7) በማለት
ቀድሞ ነበር እንጅ አስቀድሞ መ’ቀ’ደ’ስ አሁን ምን ያደርጋል ሲኦል ገብቶ ማልቀስ ይልቅ ይሻለናል ተዋህዶን ማደስ
እመቢ ካለች ማፍረስ:: እንድንል ያደርገናል ምክንያቱም መጽሐፍ ቀድሞ ሳይረፍድ ተስፋ ሳይሟጠጥ ነው ወደ እርሱ
መቅረብ እያለ:: ተዋህዶ ግን ህዝቡን ወደ እግዚአብሔር እንዳይቀርብ ችግር የለም ሲኦል ገብቶም መውጣት አለ እያለች
ህዝቡን ወደ ሲኦል ትነዳዋለችና:: ይህን ያረፈደ ለቅሶ ዋጋ ቢስነት ጌታ ኢየሱስ ሲያስመለክት::

“በጠበበው በር ለመግባት ተጋደሉ፤ እላችኋለሁና፥ ብዙዎች ሊገቡ ይፈልጋሉ አይችሉምም።


ባለቤቱ ተነሥቶ በሩን ከቈለፈ በኋላ፥ እናንተ በውጭ ቆማችሁ፦ ጌታ ሆይ፥ ጌታ ሆይ፥
ክፈትልን እያላችሁ በሩን ልታንኳኩ ትጀምራላችሁ እርሱም መልሶ፦ ከወዴት እንደ ሆናችሁ
አላውቃችሁም ይላችኋል። በዚያን ጊዜም፦ በፊትህ በላን ጠጣንም በአደባባያችንም
አስተማርህ ልትሉ ትጀምራላችሁ፤ እርሱም፦ እላችኋለሁ፥ ከወዴት እንደ ሆናችሁ
አላውቃችሁም፤ ሁላችሁ ዓመፀኞች፥ ከእኔ ራቁ ይላችኋል።” (ሉቃ 13:24-27) በማለት ጌታ ኢየሱስ
አንዴ ከረፈደና ሞት መጥቶ የሂወት ምእራፍ ከተዘጋ በኋላ ማንም ምንም አይነት ውለታ ቢዘረዝር አደለም ተሰብስቦ
ተዝካር በመብላት በመጠጣት አንዴ ከረፈደ የኪዳኑ ህዝብ መሆን እንኳን አያድንም: ሚከፈት መንግስተ ሰማያትም
የለም:: ይህን ጌታችን ርግጥ አድርጎ ተናግሮታል:: እንዲሁም፤

“ከዚያ በኋላ እንኳ በረከቱን ሊወርስ በወደደ ጊዜ እንደ ተጣለ ታውቃላችሁና፤ በእንባ ተግቶ
ምንም ቢፈልገው ለንስሐ ስፍራ አላገኘምና።” (ዕብ 12:17) በማለት ማንም አንዴ ጌታ የሰጠውን እድል
አልጠቀም ብሎ ካለፈ በኋላ የንስሃ እድል እንደማይሰጠው ያሳያል:: ያለንስሃ ደግሞ መዳን ዘበት ነው:: እግዚአብሔር
በሂወት ዘመናችን ነው የንስሃ እድልን ሚሰጠን(ራዕ 2:21፤ ሉቃ 19 44) ከዛ በኋላ ግን አንድ ጊዜ ሞት ከዛን በኋላ ፍርድ
ነው የተመደበው እንጅ መዳን ወይንም ንስሃ አደለም:: “ለሰዎችም አንድ ጊዜ መሞት ከእርሱ በኋላም
ፍርድ እንደ ተመደበባቸው፥” (ዕብ 9:27) መጽሐፍ ቅዱሳችንና ጌታ ኢየሱስ ሰው አንዴ በሃጢያት ሲኦል
ተጥሎ ከዛ በኋላ ወደ መንግስተ ሰማያት መምጣት አንደሚችል ቁልጭ አድርጎ እያስተማረ ልበ ደንዳናዋ የኑፋቄ ቤተ
መደብር ተዋህዶ ግግ የአግዚዘብሔር ቃል ተሳስቷል ብላ ጸንታለች:: ከመጽሐፍ ቅዱስ አንድ ተጨማሪ ጌታ ኢየሱስ
ሃጢያተኞች ከሞቱ በኋላ ሊድኑ አንደማይችሉ የተናገረበትን ላሳያችሁ እና እናብቃ::
“በኃጢአታችሁም ትሞታላችሁ እኔ ወደምሄድበት እናንተ ልትመጡ አትችሉም አላቸው።”
ዮሐ 8:21 ከዚህ በላይ ምን እንፈልጋለን እንግዲህ?

“ሃጢያታችንን የመናዘዝ እድሉ እያለን አሁን እንጠቀምበት: በሲኦል እድሉ የለንምና” (ኢግናጢየስ፤ Epistle of
Ignatius to the Smyrnaeans, chap.)

“በሲኦል ያሉት አሁን ለመመለስ አይችሉም ረፍዶባቸዋል (ዮስጦስ ሰማእት Justin’s Hortatory Address to the
Greeks,)

“የትኛዋም ነፍስ በስጋ እያለች ካልሆነ በቀር ለመዳን በጭራሽ እድል የላትም፤ በህይወት በአጸደ ስጋ መሆናችን ብቻ ነው
የመዳን እድል ያለን::” (ጠርጡሊያን፤ On the resurrection of flesh, chap. 8, Ante-Nicene Fathers, c. 210 A.D.)

3.4 ባርኮታቸው
“የቅዳሴ ቡራኪያት 42 ናቸው: እነዚህም 21 የአፍአ 21 የውስጥ ቡራኬያት ናቸው የአፍአ ቡራኪያት ለካህኑና
ለህዝቡ ነው::“(ስርአተ ቤተ ክርሰቲያን ገጽ 58)

ተዋህዶ በረከትን ሰው ሚቀበለው በካህን በቅዳሴ እንደሆነ የምታስተምር ሲሆን እኒሁ ቡታኪያት 21 እንደሆኑ
እንዲሁም በግል: በመስቀል በኩል እንደሚባርክ ትናገራለች ነገር ግን መጽሐፍ ቅዱስ የበረከታችንን ምንጭ
ሲናገር:-

“በጎ ስጦታ ሁሉ ፍጹምም በረከት ሁሉ ከላይ ናቸው፥ መለወጥም በእርሱ ዘንድ ከሌለ
በመዞርም የተደረገ ጥላ በእርሱ ዘንድ ከሌለ ከብርሃናት አባት ይወርዳሉ።” (ያዕ 1:17) ይላል እንጅ
ከአካህኑ በረከትን ልትቀበሉ ሂዱና አስቀድሱ አይልም:: ደግሞም ከ 42 ቡራኬያት 21 ዱን ብቻ አጉድሎ ሳይሆን ፍጹም
የሆነ በረከት ከሰማይ አባት መባረካችንን ነው ቅዱሰ መጽሐፍ ሚነግረን እንጅ ቅዳሴ አባ ህርያቆስ ብሎ “ጎሳ ልብየ: ጎሳ
ልብየ..ልቦናየ በጎ ነገርን አወጣ እኔስ የድንግልን ውዳሴዋን እናገራለሁ በማብዛት አይደለም በማሳነስ ነው እንጅ...” እያለ
የአምላክን ምስጋና ለፍጡር ስለሰጠ የምንባረክብት ምንም አይነት አግባብ የለም::

ተዋህዶ በካህን በ”ቤተ መቅደስ እንባረካለን” በማለት የብሉይ አይነት ስርአት ትጎትታለች ነገር ግን መጽሐፍ ቅዱስ
ስለምንባረክበት ሳይሆን አንዴ ለዘላለም ስለተባረክንበት ስፍራ ነው ሚናገረው እንዲሁም በማን እንደተባረክን ሲናገር:-

“በክርስቶስ በሰማያዊ ስፍራ በመንፈሳዊ በረከት ሁሉ የባረከን የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ


አምላክና አባት ይባረክ።”(ኤፌ 1:3)
አለ እንጅ እንደ ተዋህዶ ካህናት በሚባሉ ሰወች በምድር ባለ ልኡል በማይኖርበት የሰው እጅ
በሰራው: በየጊዜው 21 ቡራኬያት ትባረካላችሁ አይልም::

3.5 የሐዋርያት ተዋረድ(Apostolic succession)

“ስልጣነ ክህነት ለሐዋርያት ብቻ ተሰጥቶ በዚያው አልቀረም” ትምህረተ ሃይማኖትና ክርሰቲያናዊ ህይወት ገጽ 259

እስካሁን ባለኝ መረጃ የሃይማኖቷ አስተምህሮ ማወቅ ባልችልም: አማኞቿ(እኔም ተዋህዶ እያለሁ እለው
የነበረው)፤ “ጳጳስ ከሌለ ካህን የለም ካህን ከሌለ ቤተ ክርስቲያን የለችም” ይላሉ:: ይህን Apostolic succession
ይሉታል:: አንድ ሰው የስልጣን ተዋረዱ ከሐዋርያት ሲወርድ ሲዋረድ የመጣ ካልሆነ ማስተማርም ማገልገልም
አይችልም አይካንም ማለታደው:: እንግዲ በዚ አይነት ምን ያህል እርግጠኛ ሁነው ቆጥረው የአንድ ካህን ወደ
ሐዋርያት እንደደረሰ እያረጋገጡ ለአገልግሎት እንደሚቀጥሩት አላውቅም:: የ”ክህነታቸው” carbon dating”
አላቸው ይሆን? “የሐዋርያት ተዋረድን” የግሪክ ኦርቶዶክስ: የሮማ ካቶሊክ: አንግሊካን: ሉተራን Claim ያደርጋሉ:
እንግዲ የትኛው ነው ትክክለኛ ተዋረድ ያለው? እንግዲ ሁሉም ከሰማይ ከምድር የተራራቀ አስተምህሮ ይዘው
ሁሉም ልክ አይሆኑምና ለዚህ carbon dating ካላቸው ከነዚህ ሁሉ አንዳቸው እስኪ ያረጋግጡልን:: መቸም የኔ
ነው በሚል ገገማ ንግርት አይሆንምና በማስረጃ ሊያሳዩ ግድ ይላል::

ይህ ትምህርት ፈጽሞ በመጽሐፍ ቅዱስ የማይገኝ ነው:: ሆኖም ተዋህዶን መጽሐፍ ቅዱስ ላይ አለ የለም እያሉ
መወያየት አህያን “የተሽከምሽው ማር ይጥማል አይጥምም?” እያሉ እንደማነጋገር አንደማወያየት ነውና: መጽሐፍ
ቅዱስ ለተዋህዶ እንግዳ ስለሚሆንባት: የተሽከመችውን መጽሐፍ ቀምሳ ስለማታጣጥመው: ለአህያ ሰርዶ:
ተረትንም ለተዋህዶ: ብሎ ማለፍ ይቀላል:: እንዲህ ያለ ተረት ለመፈልሰፍ ያበቃት ተረታተረቷ ነውና ተዋህዶን
ነጻ ሚያወጣት: ኢየሱስ ነውና ኢየሱስጋ እንድትተዋወቅ እንጸልይላት:: የሆነው ሆኖ ይህ ትምህርት ከቅዱስ ቃሉ
አንድም ቦታ የሌለ ተረታተረት ነው:: ከላይ እንዳልኩት ከሐዋርያትጋ ቀጥታ ግንኙነት አለው ምትለው እንግዲ
የሌለው “ካህን” የሰበካቸው: ያጠመቃቸው ካሉ ምንም እንኳ በኢየሱስ: ቢያምኑ እሱ ያሳመነው ያቆረበው ሁሉ
አልዳነም ሲኦል ይጣላሉ ማለት ነው:: ታዲያ ይህ ሰው በተዋህዶ ቤት አልተካነምና ጌታ “በአኔ ያመነ የዘላለም
ህይወት አለው” ያለውን ጥሎ በእኔ ያመነ ከሃዋርያት ተዋረድ የመጣ ካህን ስላላሳመነው አይድንም ማለት ነው?

ለመሆኑ “ካህን ከሌለ ቤተ ክርስቲያን የለችም” ሚሉትና “ያለሐዋርያት ተዋረድ ማንም መስበክ :ማስተማር
:ማገልገል አይችልም” ሚሉት Apostolic Succession መጽሐፍ ቅዱሳዊ ነውን ሚለውን እንመልከት::

ቤተ ክርስቲያን ማለትም በግሪኩ ኤቅሌሲያ:- ስብስብ፤ ጉባኤ ማለት ነው:: በዚህም ክርስቶስ ራሷ ነውና ይገኝላታል::
ጌታ ኢየሱስ ደግሞ “ሁለት ወይም ሦስት በስሜ በሚሰበሰቡበት በዚያ በመካከላቸው እሆናለሁና።”
(ማቴ 18:20) በማለት ሁለት ሰው እንኳ ባለበት እንደሚገኝ ተናግሯልና: ያ ቤተ ክርስቲያን ይባላል:: እንደው for the
sake of argument እንደ ኦርቶዶክሶች አስተሳብ እንሂድ ብለን እንጅ እነሱ እንዳሉት: ካህን የሌላት ቤተ ክርስቲያን:
ቤተ ክርስቲያን ልትባል አይገባም ሚለውን አስተሳሰብ አንቀበል ብንል እንኳ: አማኞች ሁሉ ካህናት ስለሆኑና: ከምንም
በላይ ደግሞ ሊቀ ካህናት የሆነው ኢየሱስ ስላለ: ቤተ ክርሰቲያን አትባልም ሚለው ሙገታቸው አፈር ከድሜ በልቶ
ላይነሳ ይቀበራል:: እንዲሁም ሐዋርያ ጳውሎስ (ሮሜ 16:5) በማለት የእያንዳንዳችን ቤተሰብ ክርስቲያን መሆኑን
አሳይቷል ታዲያ በየ ቤታችን “ካህናት” ሚባሉ ቀዳሾችን እንቅጠር ይሉ ይሆን ተዋህዶወች?

ያለ ሐዋርያት ተዋረድ ማስተማርና መስበክ መካን አይቻልም ሚለው ፈጽሞ የተሳሳተ መሆኑን መጽሐፍ ቅዱስ በግልጽ
አስቀምጧል::(ነገሩን አርቀን እንውሰደው ብለን እንጅ ይህ ሙግታቸውም ከላይ ከቀረበው ማቴ 18:20 ላይ ፈርሷል)
ነገር ግን አሁንም for the sake of argument እንቀጥል እና መጽሐፍ ማን ከማን ይማራል? ምንስ ያስተምራል
ሚለውን እንመልከት:: በመጀመሪያ ደረጃ ሰው የሚማረው ከእግዚአብሔር እንጅ ከሰው አደለም:: “ሁሉም
ከእግዚአብሔር የተማሩ ይሆናሉ ተብሎ በነቢያት ተጽፎአል፤ እንግዲህ ከአብ የሰማ የተማረም
ሁሉ ወደ እኔ ይመጣል።” (ዮሐ 6:45)
“እናንተስ ከእርሱ የተቀበላችሁት ቅባት በእናንተ ይኖራል፥ ማንም ሊያስተምራችሁ
አያስፈልጋችሁም፤ ነገር ግን የእርሱ ቅባት ስለ ሁሉ እንደሚያስተምራችሁ፥ እውነተኛም እንደ
ሆነ ውሸትም እንዳልሆነ፥ እናንተንም እንዳስተማራችሁ፥ በእርሱ ኑሩ።” (1 ዮሐ 2:27) ከሰው
ሚጠበቀው ከእግዚአብሔር(በቅዱሳት መጻህፍት የተጻፉትን ያመነውን) ማብራራት እንጅ ማስተማር(መግለጥ)
አደለም፤ መግለጥ የእግዚአብሔር ስራ ነውና:: በመቀጠል ለማስተማር ከእግዚአብሔር መማር እንጅ የሐዋርያት ተዋረድ
አያስፈልግም ጳውሎስ ራሱ:: ጌታ ኢየሱስ ለአገልግሎት የተለየው ገና በእናቱ ማህጸን እንጅ በሐዋርያት አደለም:: ጌታ
ተገልጦ ለአገልግሎት በጠራው ጊዜ ወደ አረቢያ ምድር ሄደ እንጅ ወደ ስጋ ወደ ሆኑ ሐዋርያት ሊያማክራቸው
አልመጣም፤ ከሶስተ አመት በኋላ ሲመጣም የኢየሱስን ወንድም ያዕቆብን ብቻ እንጅ ሌላ ሐዋርያትን አላገኘም::
እንደውም ከ 15 አመት በኋላ እንኳን ሲያገኘው ጴጥሮስን ከስህተቱ በማረም ነው የጀመረው::
“ኢየሱስ ክርስቶስ ገልጦልኛል እንጂ እኔ ከሰው አልተቀበልሁትም አልተማርሁትምም።...ነገር
ግን በእናቴ ማኅፀን ሳለሁ የለየኝ በጸጋውም የጠራኝ እግዚአብሔር በአሕዛብ መካከል ስለ እርሱ
ወንጌልን እሰብክ ዘንድ ልጁን በእኔ ሁኔታ ሊገልጥ በወደደ ጊዜ፥ ወዲያው ከሥጋና ከደም ጋር
አልተማከርሁም፥ ከእኔም በፊት ሐዋርያት ወደ ነበሩት ወደ ኢየሩሳሌም አልወጣሁም፥ ነገር
ግን ወደ ዓረብ አገር ሄድሁ እንደ ገናም ወደ ደማስቆ ተመለስሁ።” (ገላ 1: 12-16)

“ነገር ግን እንደ ወንጌል እውነት በቅንነት እንዳልሄዱ ባየሁ ጊዜ በሁሉ ፊት ኬፋን፦ አንተ
አይሁዳዊ ሳለህ በአይሁድ ኑሮ ያይደለ በአሕዛብ ኑሮ ብትኖር፥ አሕዛብ በአይሁድ ኑሮ ሊኖሩ
እንዴት ግድ አልሃቸው? አልሁት።” (ገላ 2:14)
ሐዋርያው ጳውሎስ የአገልግሎት ጸጋውን ያገኘው ከእግዚአብሔር ከራሱ እንጅ ከሰው እንዳልተቀበለ: ከተናገረ የቤተ
ክርስቲያን ሐላፊነት እውቅና መስጠት ነው:: እግዚአብሔር የጠራውን ደግሞ እውቅና መስጠት ሚያስፈልገው ስልጣን
ለመስጠት ሳይሆን አብሮ ሰራተኛ ለመሆን ነው:: ይህ ሐላፊነት ደግሞ የሙሉ ቤተ ክርስቲያን እንጅ እንደ Apostolic
succession theory በጳጳሳት ወይ በሐዋርያት ሚደረግ አደለም:: ሐዋርያው ጳውሎስ ለአገልግሎት ሲለይ

“በአንጾኪያም ባለችው ቤተ ክርስቲያን ነቢያትና መምህራን ነበሩ፤ እነርሱም በርናባስ፥ ኔጌር


የተባለው ስምዖንም፥ የቀሬናው ሉክዮስም፥ የአራተኛው ክፍል ገዥ የሄሮድስም ባለምዋል
ምናሔ፥ ሳውልም ነበሩ። እነዚህም ጌታን ሲያመልኩና ሲጦሙ መንፈስ ቅዱስ፦ በርናባስንና
ሳውልን ለጠራኋቸው ሥራ ለዩልኝ አለ።” (ሐዋ 13:2) እንግዲ በዚህ ስፍራ ነብያትና መምህራን እንጅ
ሐዋርያትም ሆኑ ጳጳሳትን አናገኝም::

ጌታ ኢየሱስ ራሱ ሐዋርያዊ ተዋረድን አፈ ታሪክን በግልጽ ተቃውሟል:: ከሐዋርያት መካከል አንዱ


“ዮሐንስ መልሶ፦ መምህር ሆይ፥ አንድ ሰው በስምህ አጋንንትን ሲያወጣ አየነው፥
ስለማይከተለንም ከለከልነው አለው። ኢየሱስ ግን አለ፦ በስሜ ተአምር ሠርቶ በቶሎ በእኔ ላይ
ክፉ መናገር የሚችል ማንም የለምና አትከልክሉት፤ የማይቃወመን እርሱ ከእኛ ጋር ነውና።”
(ማር 9:38-40) በማለት ኢየሱስን ሚሰብክን ሰው መቃወሙን አውግዞታል:: ይህም ሚያሳየው ማንም በእግዚአብሔር
ሲመረጥ በቀጥታ ማገልገል ሚችል መሆኑን ነው:: ቤተ ክርስቲያን ጸጋውን አይታ እውቅና ትሰጣለች እንጅ እንጅ
ሐዋርያዊ ተዋረድ ከሌለህ አታስተምርም ብላ አትከለክልም:: አትችልምም:: እውቅና ባትሰጥም እግዚአብሔር እውቅና
የሰጠውን መከልከል ስለማትችል ሐዋርያዊ ተዋረድ ሚባል አፈ ታሪክ አይሰራም::

ሲጀመር ተዋህዶ የሳተችው ነገር የክህነት አገልግሎት በእግዚአብሔር የሚሰጥ እንጅ ተዋህዶ እንደምታደርገው ማንም
ግዕዝ ተምሮና: ድጓ: ጾመ ድጓ: ቅኔ: ዝማሜ: ቅዳሴ: ተምሮ ብድግ አድርጎ ሚወስደው ነገር አደለም:: “እንደ አሮንም
በእግዚአብሔር ከተጠራ በቀር ማንም ክብሩን ለራሱ የሚወስድ የለም።” (ዕብ 5:4) ተዋህዶ ግን ዛሬ
“ክህነቷን” ምትሰጠው ካህን ልሁን እስኪ ብሎ እግዚአብሔር ሳይሆን ራሷ ያወጣችውን መስፈርት ሲያሟሉላት ብቻ
ነው:: ይህም ደግሞ ሚያሳየው ድርጅቷ ራሴን ከእግዚአብሔር በላይ ነኝ በማለት አንደሾመችና ከወንጌል ተለይታ
የተጣለች መሆኗን ያሳያል::

አሁንም for the sake of argument ይህን “የሐዋርያት ተዋረድ” ኑፋቄዋን እንያዝላትና የኢትዮጵያን ኦርቶዶክስ
ህልውና እንገምግም::

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተረክ የክርስትናን ወደ ሃገራችን እንደሚያስረዳው “የክረስትና ሃይማኖት ወደ ኢትዮጵያ የገባው
ወይም ኢትዮጵያና ክርስትና የተዋወቁት መጽሐፍ ቅዱስ እንደሚለው ፊልጶስ ጃንደረባውን ባጠመቀው ጊዜ ነው”
(ብጹእ አቡነ ጎርጎርዮስ: የኢትዮጵያ ቤተ ክረስቲያን ታሪክ፤ ገጽ 20) በማለት ነው:: እንግዲ በኢትዮጵያ ክርስትና
ሃይማኖት ከመጀመሪያው ክፍለ ዘመን ጀምሮ ነበር ይሉናል::
በገድለ ትክለ ሃይማኖትም “እንበረምም ፍሬምናጦስን እንዲህ አለው: ግዝረትን አባቶቼ ሌዋውያን አመጡልን:
ሃይማኖትንም የህንደኬ ባለሟል አመጣልን::” (ገድለ ተክለ ሃይማኖት 4:11-17) በማለት የክርስትና ሃይማኖት ወይም
እንደነሱ አባባል ተዋህዶ በመጀመሪያው ክፍለ ዘመን ገብቶላቸው ነበር:: ይህ ከሆነ ደግሞ ካህን የሃይማኖት ኖረ
እያሉን ነው ለመሆኑ ያለ ቤተ ክርስቲያን እንዴት የክርስትና ሃይማኖት ይኖራል? የክርስትና ሃይማኖተ ካለ አማኞች
አሉ ማለት ነው ቤተ ክርስቲያን ማለት የአማኞች ስብስብ መሆኑን ከላይ እንዳየነው ደግሞ ደግሞ ቤተ ክርስቲያን
አለች ማለት ነው:: ስለዚህ እነሱ ራሳቸው ያለ ካህን ቤተ ክርስቲያን አለች እያሉን ነው ወይ ደግሞ ክርስትና የለምና
ውሽት ነው እያሉን ነው ማለት ነው::

እንግዲ የኢትዮጵያ ተዋህዶ እንደነሱ አባባል “የሐዋርያት ተዋረድ” ብዙ ጊዜ ይቋረጥባት ነበር “ኢትዮጵያ ከግብጽ
ጳጳሳትን ታስመጣ ስለነበር... በእስላሞች ገዥወች ዘንድ ተወዳጅነትን ለማትረፍ ከክርስትና ይልቅ እስልምናን
ለማስፋፋት ለማስፋፋት ይጥሩ እንደነበር ተመልክተናል:: ስለዚህ የግብጽ ሱልጣኖች ካልፈቀዱ ስለማይመጡ ብዙ
ጊዜ መምጣታቸው ይቋረጥ ነበር ::” (ብጹእ አቡነ ጎርጎርዮስ: የኢትዮጵያ ቤተ ክረስቲያን ታሪክ ገጽ 44-45)
ስለዚህ በነዚህ ጊዚያት የኢትዮጵያ ተዋህዶ በነዚህ ጊዚያት ሁሉ ጠፍታለች ሙታለች ማለት ነው ስለዚህ
ያ i ትዮጵያ ተዋህዶ የለችም ማለት ነው:: ምክንያቱም “የሐዋርያት ተዋረዷ” ጠፍቷልና::

የኢትዮጵያ ተዋህዶን አንዳንዴ ራሳቸው ግብጾች አንዳንዴም ደግሞ ሙስሊሞች እየሽወዱ ጳጳስ ነን ብለው
በመምጣት መስጊድ ይተክላሉ: ሙሰሊሞችን ያስፋፋሉ: ወርቅ ብር ይገበርላቸዋል: የኢትዮጵያን ደሃ ገበሬ ገንዘብ
ምግብ ሃብት ይበዘብዛሉ፤ ኢትዮጵያንም ሃብቷን ይዘርፋሉ: ለዚህ ደግሙ ድርጅቷ ዋነኛ ሚና ተጫዋች ነበረች(አይ
ተዋህዶኮ ግፏ?)

“አባ ቄርሎስ ወደ ኢትዮጵታ ልከሃል ተብለው ወህኒ ገብተው ሰልነበር የኦትዮጵያ መልእክተኞች ጳጳስ አላገኙም ::
በዚህ መሃል አብዱም የሚባል ግብጻዊ እስላም የሐሰት ደብዳቤ ይዞ ወደ ኢትዮጵያ መጥቶ አባ ቄርሎስ ነኝ አለ ::
የጵጵስና አቀባበልም ተደረገለት” (ብጹእ አቡነ ጎርጎሬወስ፤ የኢትዮጵያ ቤተ ከርስቲያን ታሪክ: ገጸ 47)

ለ 40 አመታት የጉዲት ዘመን “ጳጳስ ስላልነበር የህዝቡ ተወካዮች ወርቅና ብራቸውን ጭነው ጳጳስ ለማምጣት
እንደተለመደው ሄዱ... ምርጫ ተደረገና አቡነ ጴጥሮስ የተባሉት ለኢትዮጵያ ጳጳስ እንዲሆኑ ተመረጡ:: ወደ
ኢትዮጵያ ሲገቡም በእስላሞች ጭከናና በአክሱም መንግስት ላይ በወረደው አደጋ ለብዙ ዘመን የጳጳስ መምጣት
ቋርጦ ስለነበር...” (ብጹእ አቡነ ጎረጎሪዮስ፤ የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን ታሪክ፤ ገጽ 33)

ተመልከቱ እንግዲ የተዋህዶ በነዚህ ጊዚያትም እስላም በሚመጣባት ጊዜ: እንዲሁም በጠንካራዋ የኢትዮጵያ ንግስት
በይሁዲት የንግስና ዘመን: ሁሉ በተዋህዶ “የሐዋርያት ተዋረድ” ሚባል የለም:: ስለዚህ ድርጅቷ የለችም ማለት ነው::
በነዚህ ጊዜ አምነው የተጠመቁ ቢኖሩ ክርሰቲያን አደሉም አረመኔ: ከሃዲ: እስላም ናቸው ማለት ነው: በነሱ አመክንዮ
መሰረት::

ሌላው ቀርቶ በገድለ ተክሌ ላይ “ንሳእ መንፈስ ቅዱስ ብሎ የሹመት ሃብት አሳደረበት በምድር ያሰርከው በሰማይ
የታሰረ ይሁን: በምድር የፈታሃው በሰማይ የተፈታ ይሁን...” (ገድለ ተክለ ሃይማኖት 21:67) ሚል ንባብ እናገኛለን
ይህም አባ ተክሌን ጌታ ቀጥታ ክህነት በንፍሃት እንደሾመው ሚያሳይ ነው ይህ ራሱ ከሃዋርያት ተዋረድ የመጣ
ሚለውን አፍርሶ ጌታ ራሱ ይሾማል አንጅ የ “ሐዋርያት ተዋረድ” ሚባለውን ነገር ሚያፈርስ ነው::
ልክ አንዲሁ ተዋህዶ የኔ ነው በምትላቸው መጻህፍት መሰረት ተዋህዶ የ “ሐዋርያት ተዋረድ” ን ያልጠበቀች ውጉዝ
ትሆናለች:: ግብጻውያን ይህን “የሐዋርያት ተዋረድ” ሚለውን ኑፋቄ ተጠቅመው ኢትዮጵያንና የተዋህዶን ድርጅት
ቀጥቅጠው ገዝተዋል:: ለዚህ ደግሞ ድርጅቷ ከነሱ “የሐዋርያትን ተዋረድ” ስትጠባበቅ እግዚአብሔርን ሳይሆን
የግብጻውያንን ሹመት ስትጠባበቅ የራሷን ጳጳሳት ሳትሾም ኑራለች:: ህዝቡንም ካህን ከንጉስ ይበልጣል እያለች
የግብጻ ጳጳሳዊ ነገስታት እያስመጣች በራሳችን የገበሬ ወታደሮች በድርጅቷ ተቋምነት ግብጽ ሃገራችንን “በፍትሐ
ነገስቱ” ህግ እያወጣች “በስንክሳሩ” ህዝቡንና ካህናቱን እንዳይሰሩ እያስተኛች በአላት እያባዛች: አምሯአችን የዛገ
ታሪካችን የደም እንዲሆን አድርጋለች::

“ኒቂያ 42:: የኢትዮጵያ ሰወች ከአዋቂወቻቸው ወገን በራሳቸው ፈቃድ ሊቀ ጳጳሳትን ለራሳቸው አይሹሙ::
ጳጳሳቸው ከእስክንድርያ ባእለ መንበር፤ ስልጣን በታች ነውና” (ፍትሃ ነገስት 30: 50)

“በሚያዝያ 10 በሚነበበው ስንክሳራችን ግን ይህንኑ ሲተርክ ይህን ብሔራዊና ሃይማኖታዊ ስሜት ያለው ቅዱስ
ንጉስ:- ስሙን እንኳ ሳይጠራ ኢትዮጵያውያን”- ኤጲስ ቆጶሳት ይሹሙልኝ ማለቱን እንደ ሃጢያት ፤ የግብፁን ሊቀ
ጳጳስ አባ ገብርኤል እንደ ገባሬ ተአምር በመቁጠር:- ንጉሱ ኢትዮጵያውያን ኤጲስ o ጶሳት እንዲሾሙ በመጠየቁ
እግዚአብሔር ተቆጥቶ በአገሩ በኢትዮጵያ ላይ መቅሰፍት አወረደበት ይላል” (ብጹእ አቡነ ጎርጎርዮስ፣ የኢትዮጵያ
ቤተ ክርስቲያን ታሪክ፣ ገጽ 40)

እንግዲ በዚህ መሰረት “የሐዋርያት ተዋረድ” የሚለው ተረቷ ኢትዮጵያውያንን እና ኢትዮጵያዊነትን ያስናቀ
ያስደፈረ:: ለቅኝ ግዛት ያስገዛ: ድርጅቷንም ህልውና ሳይኖራት ለዘመናት እንድትኖር አድርጎ የኖረ ኢትዮጵያን
የበደለ:: ሐገር ያጠፋ:: ራሷን ድርጇትንም ያከሰረ ለእስላም ያስገዛ ነው:: እንግዲ በዛ እስላም ስንቱ ካህን ተሹሞ
ይሆን? ያስ ካህን ስንቱን አጥምቆ ይሆን? በሃላስ ያጠመቀው ሰው ቀስሶ ይሆን ከነሱስ ሲዋረድ የመጣ ዛሬ የጰጰሰ
የለም ይሆን? ታዲይ በ “ሐዋርያት ተዋረድ” ኑፋቄ ከሔድን አሁን ቤተ ክርስቲያኒቱ አለች ማለት ይቻላል? የስንቱ
ጳጳስስ በርግጠንነት ስልጣኑ ወደላይ ወደ ሐዋርያት ይደርሳል?

ለማነኛውም እንዳየነው የተዋህዶ የኑፋቄ ክህነት አደገኛነቱ: ለቤተ ክርስቲያንም: ለሰው ህይወትም: ለሃገርም ነውና
ፈጽሞ የተወገዘ የተለየ እንዲሆን ባለኝ የክህነት ከምንም በሚበልጠው ስልጣን በልጅነቴ አውግዣለሁ:: በተዋህዶ
ክህነት የሚያምን ፈጽሞ የተወገዘ የተለየ ይሁን::

አስጀምሮ ያስፈጸመኝ አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ የተመሰገነ ይሁን::

ተፈጸመ

ቶማስ መንፈስ ቅዱስን ተቀበሉ ብሎ ጌታ ሲናገር አልነበሩምና የህንድ ቤተ ክርስቲያን የለችም ልንል ነውን?
4 ለቤተ ክርስቲያን የተሰጡ መንፈሳዊ የአገልግሎት ስጦታወች::

You might also like