Download as pdf or txt
Download as pdf or txt
You are on page 1of 11

የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ

ፌደራል ነጋሪት ጋዜጣ


FEDERAL NEGARIT GAZETTE
OF THE FEDERAL DEMOCRATIC REPUBLIC OF ETHIOPIA

ሠላሳኛ ዓመት ቁጥር ፳፮ 30th Year No. 26


አዲስ አበባ ግንቦት ፲፭ ቀን ፪ሺ፲፮ ዓ.ም በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ADDIS ABABA, 23th May , 2024
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጠባቂነት የወጣ

ማውጫ Content
ደንብ ቁጥር ፭፻፵፭/፪ሺ፲፮ Regulation No. 545/2024

የአካባቢ ጥበቃ ባለሥልጣን አደረጃጀት፣ ሥልጣንና The Powers, Duties and Organization of the
ተግባርን ለመወሰን የወጣ የሚኒስትሮች ምክር ቤት Environmental Protection Authority Council of
ደንብ ….….…………..……….…...ገጽ ፲፭ሺ፭፻፹ Minister Regulation………………......Page 15580

ደንብ ቁጥር ፭፻፵፭/፪ሺ፲፮ REGULATION No.545/2024

THE POWERS, DUTIES AND ORGANIZATION OF


የአካባቢ ጥበቃ ባለሥልጣን አደረጃጀት፣ ሥልጣንና
THE ENVIRONMENTAL PROTECTION
ተግባር ለመወሰን የወጣ የሚኒስትሮች ምክር ቤት
AUTHORITY COUNCIL OF MINISTERS
ደንብ
This Regulation is issued by the Council of
የሚኒስትሮች ምክር ቤት የኢትዮጵያ ፌደራላዊ
Ministers pursuant to Article 59 (2) of the
ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የአስፈፃሚ አካላትን
Definition of Powers and Duties of Executive
ሥልጣንና ተግባር ለመወሰን በወጣው አዋጅ ቁጥር
Organs of the Federal Democratic Republic of
፩ሺ፪፻፷፫/፪ሺ፲፬ አንቀጽ ፶፱ (፪) መሠረት ይህንን
Ethiopia Proclamation No. 1263 /2021.
ደንብ አውጥቷል፡፡
1. Short Title
፩. አጭር ርዕስ
This Regulation may be cited as the “The
ይህ ደንብ “የአካባቢ ጥበቃ ባለሥልጣን አደረጃጀት፣
Powers, Duties and Organization of the
ስልጣንና ተግባርን ለመወሰን የወጣ የሚኒስትሮች
Environmental Protection Authority Council of
ምክር ቤት ደንብ ቁጥር ፭፻፵፭/፪ሺ፲፮” ተብሎ
Ministers Regulation No.545/2024.
ሊጠቀስ ይችላል፡፡

፪. ትርጓሜ 2. Definition
በዚህ ደንብ ውስጥ የቃሉ አገባብ ሌላ ትርጉም In this Regulation unless the context otherwise
የሚያሰጠው ካልሆነ በስተቀር፡- requires:
፩/‘‘ባለሥልጣን” ማለት በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ
1/ “Authority” means the Environmental
ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የአስፈጻሚ አካላትን Protection Authority established under Article
ሥልጣንና ተግባር ለመወሰን በወጣው አዋጅ 59 (1) of Proclamation No.1263/2021 on the
ቁጥር ፩ሺ፪፻፷፫/፪ሺ፲፬ አንቀፅ ፶፱ (፩) Definition of the Powers and Duties of the
መሠረት የተቋቋመው የአካባቢ ጥበቃ Executive orangs of the Federal Democratic
ባለሥልጣን መሥርያ ቤት ነው፤ Republic of Ethiopia;

ÃNÇ êU nU¶T Uz¤È ±.œ.q.Ü *¹þ1


Unit Price Negarit G. P.O.Box 80001
gA ፲፭ሺ፭፻፹፩ Ød‰L ነU¶T Uz¤È qÜ_R ፳፮ ግንቦት ፲፭ ቀን ፪ሺ፲፮ ›.M Federal Negarit Gazette No. 26, 23 th May, 2024….page 15581

፪/ “የአካባቢ ጥበቃ ” ማለት የሰው ልጅን ጨምሮ 2/ “Environmental Protection” means the
የማንኛውም አካል ሕይወት እና እድገት protection of land ,water, air, climate system
የሚወስኑ የመሬት፣ የውሃ፣ የአየር፣ የአየር and similar other environmental resources,

ንብረት ሥርዓት የመሳሰሉ ሌሎች የአካባቢ factors and conditions which affect the life and

ሀብቶች፣ ክስተቶችና ሁኔታዎች በመጠበቅ development of all organisms including


human beings with a view to safeguarding the
የአሁኑን ትውልድ ፍላጎት የማርካቱ ሂደት
interests of the present generations without
የመጪውን ትውልድ ዕድል ሳያሰናክል
compromising the opportunity for the future ;
እንዲሟላ ማስቻል ነው፤
3/ “Environmental Laws” means; environment
፫/“የአካባቢ ሕጎች” ማለት ከአካባቢ ጥበቃ ጋር
related Policies, Strategies, Proclamations,
ተያያዥነት ያላቸው በሥራ ላይ ያሉ እና
Regulations and Directives that are currently
ወደፊት የሚወጡ ፖሊሲዎች፣ ስትራቴጂዎች፣
under implementation and that will be
አዋጆች፣ ደንቦች እና መመሪያዎች ነው፤ promulgated in the future;
፬/ “መጤ ወራሪ ዝርያ” ማለት የስነ-ምህዳር 4/ “Invasive Alien Species” means a plant, an
ተወላጅ ያልሆነ እፅዋት፣ እንስሳት እና ደቂቅ animal or microbe that is non-native to an
ዘአካላትን የሚያጠቃልል ሲሆን፣ በአንድ አካባቢ ecosystem, which may cause economic or
በመዛመቱ ኢኮኖሚያዊ እና አካባቢያዊ ጉዳትን environmental harm or adversely affect human
ሊያስከትል ወይም በሰው እና በእንስሳት ጤና and animal health;
ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ ሊያሳድር የሚችል ነው፤
5/ “Ecosystem” means a complex natural or
፭/ “ሥርዓተ-ምህዳር” ማለት ህይወት ያላቸውንና
manmade system in which living and non-
የሌላቸው ነገሮችን እንደ ሙሉ አካል
living things interact;
የሚስተጋበሩበት ውስብስብ የሆነ የተፈጥሯዊ
ወይም የሰው ሰራሽ ሥርዓት ነው፤
6/“Climate Change” means a change of climate
፮/ “ የአየር ንብረት ለውጥ ” ማለት ከተፈጥሮ
which is attributed directly or indirectly to
የአየር ንብረት ተለዋዋጭነት ባሻገር በዋናነት
human activity that alters the composition of
በሰው ልጆች ቀጥተኛም ሆነ በተዘዋዋሪ ከሚደረግ
the global atmosphere and which is in
እንቅስቃሴ የተነሳ በረጅም አማካይ ወቅት addition to natural climate variability
በአየር ንብረት ላይ የሚከሰት የከባቢ አየር observed over comparable time periods;
ይዘት ለውጥ ነው፤

፯/ “የአየር ንብረት ለውጥ ማጣጣሚያ” ማለት በአየር 7/ “Climate Adaptation” means adjustments in
ንብረት ለውጥ ምክንያት ለተከሰቱ እና ecological, social, or economic systems in
እንደሚከሰቱ ለሚጠበቁ ተፅዕኖዎች በሥርዓተ- response to actual or expected climatic
ምህዳር፣ በማህበራዊ ወይም በኢኮኖሚያዊ stimuli and their effects or impacts;

ሥርዓቶች ላይ የሚደረጉ ማስተካከያዎች ነው፤


፲፭ሺ፭፻፹፪
gA Ød‰L ነU¶T Uz¤È qÜ_R ፳፮ ግንቦት ፲፭ ቀን ፪ሺ፲፮ ›.M Federal Negarit Gazette No. 26, 23 th May, 2024….page 15582

፰/“የአየር ንብረት ለውጥ ማስተሰርያ” ማለት 8/ “Climate Mitigation” means any efforts to
የሙቀት አማቂ ጋዞች ልቀትን ለመቀነስ ወይም reduce or prevent emission of greenhouse

ለመከላከል የሚደረግ ማንኛውም ድርጊት ነው፤ gases;

፱/ “የሙቀት አማቂ ጋዞች ” ማለት በከባቢ አየር 6/ “Greenhouse Gases” means those
ውስጥ በተፈጥሮ እና በሰው ሰራሽ የሚገኙ ጋዞች gaseous constituents of the atmosphere,
ሆነው የረዥም ሞገድ ጨረሮችን ለረጂም ጊዜ both natural and anthropogenic, that absorb

የሚይዙ እና መልሰው ወደ ምድረ ገጽ የሚለቁ and retain for a long period of time and re-

ጋዞች ናቸው፤ emit long wave radiation to the earth;

፲/ “ ካርበን ” ማለት ሕይወት ባላቸው እንዲሁም 7/ “Carbon” means a chemical element found
በሌላቸው አካላት ውስጥ የሚገኝ ከኦክስጅን ጋር in living and non-living things that creates a
ሲዋሃድ ሙቀት የማመቅ ባህሪይ ያለው ጋዝ gas with a nature of heat absorption when
የሚፈጥርና በከባቢ አየር ውስጥ ያለው mixed with oxygen; that results warming;
ተፈጥሮአዊ ክምችት በሰው ሰራሽ ምክንያቶች
ሲጨምር የምድር ሙቀት መጨመርን
የሚያስከትል ንጥረ-ነገር ነው፤
፲፩/ “ የካርበን ንግድ ” ማለት ወደ ከባቢ አየር 8/ “Carbon Trade” means a carbon market
ሊለቀቅ የሚችል የካርበን መጠንን መቀነስ ወይም system in which payment is made for carbon
ማስወገድ ወይም የተለቀቀውን የካርበን ልቀት emissions reduced, removed, or avoided;

መጠን በመቀነስ ክፍያ የሚፈፀምበት የግብይት


ሥርዓት ነው፤
፲፪/“የሚመለከታቸው ተቋማት” ማለት የአካባቢ 9/ “Relevant Institution” means any Federal
ጥበቃን በተመለከተ በህግ ሥልጣን የተሰጣቸው or Regional Government organ entrusted by

የፌደራል ወይም የክልል መንግሥት ተቋማትን law with a responsibility related to the
subject specified in the provisions where the
ያጠቃልላል፤
term is used;

፲፫/ “ሰው” ማለት የተፈጥሮ ሰው ወይም በሕግ 10/ “Person” means natural or legal person;
የሰውነት መብት የተሰጠው አካል ነው፤
፲፬/ ማንኛውም በወንድ ፆታ የተገለፀው አገላለፅ 14/ Any expression in the masculine gender

ሴትንም ይጨምራል፡፡ includes the feminine.

፫. ዋና መሥሪያ ቤት 3. Head Office


The Authority shall have its head office in
የባለሥልጣኑ ዋና መስሪያ ቤት በአዲስ አበባ ሆኖ
Addis Ababa and may have branch offices
በሀገሪቱ ውስጥ በተለያዩ ቦታዎች ቅርንጫፍ ሊኖሩት
elsewhere, as may be necessary.
ይችላል፡፡
፲፭ሺ፭፻፹፫
gA Ød‰L ነU¶T Uz¤È qÜ_R ፳፮ ግንቦት ፲፭ ቀን ፪ሺ፲፮ ›.M Federal Negarit Gazette No. 26, 23 th May, 2024….page 15583

፬. የባለሥልጣኑ ዓላማ 4. Objective of the Authority


የባለሥልጣኑ ዓላማ ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ The objective of the Authority is to issue

የልማት እንቅስቃሴዎች የሰዎችን እና የአካባቢ environmental standards and licenses for


activities that require environmental licensing
ደህንነትን በዘላቂነት ሊያራምዱ እና ሊያጎለብቱ
which foster social and economic
የሚያስችሉ የአካባቢ ደረጃዎችን የማውጣትና
development in a manner that enhance the
በወጣው ደረጃ መሠረት መተግበሩን ማረጋገጥ እና
welfare of humans and the safety of the
ፍቃድ በሚያስፈልጋቸው አካባቢያዊ ጉዳዮች ላይ
environment, and regulate their
ፍቃድ መስጠት እና መቆጣጠር ነው፡፡
implementation.

፭. የባለሥልጣኑ ሥልጣንና ተግባር 5. Powers and Duties of the Authority

ባለሥልጣኑ የሚከተሉት ሥልጣንና ተግባራት The Authority shall have the powers and duties
to:
ይኖሩታል፡-
1/ Propose recommendations to relevant
፩/ የአካባቢ ጥበቃ ጉዳዮች ፖሊሲዎችን፣ ስልቶችንና
institutions on environment related policies,
ሕጎችን አስመልክቶ ምክረ ሐሳብ ለሚመለከተው
strategies, laws and upon approval, regulate
አካል ያቀርባል፣ ሲፀድቁም በሥራ ላይ their implementation;
መዋላቸውን ይቆጣጠራል፤

2/ In consultation with relevant institutions, set


፪/የአካባቢ ደረጃዎችን አዘጋጅቶ ለኢትዮጵያ
environmental standards and regulate
ደረጃዎች ምክር ቤት እንዲጸድቅ ያቀርባል፣
compliance with those standards;
በጸደቀው መሠረት መከበራቸውንም
ይቆጣጠራል፤
3/ Regulate the implementation of
፫/ የአካባቢ ጥበቃ ሕጎችን አተገባበር ይከታተላል፤
environmental laws ;
ይቆጣጠራል፤
4/ Where projects are subject to federal
፬/ የሥራ ፈቃድ የመስጠት፣ የመተግበር ወይም
licensing, execution or supervision or where
ክትትል የማድረግ ሥልጣን የፌደራል they are likely to entail inter- regional
መንግሥት የሆነባቸው ወይም ክልል ተሻጋሪ impacts, review environmental impact study
የአካባቢ ተፅዕኖ ሊያስከትሉ የሚችሉ reports of such projects and notify its
ፕሮጀክቶችን የአካባቢ ተፅዕኖ ጥናት ዘገባ decision to the concerned licensing agency
ይገመግማል፣ ለፈቃድ ሰጪው አካል ውሳኔውን and, as may be appropriate, audit and
ያሳውቃል፤ እንደተገቢነቱም የትግበራው regulate their implementation in accordance

ይሁንታ ሲሰጥ በተመለከቱ ግዴታዎች መሠረት with the conditions set out during

ፕሮጀክቶቹ መተግበራቸውን ያረጋግጣል፣ authorization;

ይቆጣጠራል፤ 5/ Issue certificate of competence to any


person seeking to engage in consultancy
፭/ በአካባቢና ማህበራዊ ተፅዕኖ ግምገማ እና በአካባቢ
services in the areas of environment and
ኦዲት ዘርፍ በማማከር አገልግሎት ለመሰማራት
social impact assessment, environmental
ለሚፈልግ ሰው ወይም ተቋማት የብቃት
audit and regulate the same;
ማረጋገጫ ይሰጣል፣ ይቆጣጠራል፤
gA ፲፭ሺ፭፻፹፬ Ød‰L ነU¶T Uz¤È qÜ_R ፳፮ ግንቦት ፲፭ ቀን ፪ሺ፲፮ ›.M Federal Negarit Gazette No. 26, 23 th May, 2024….page 15584

፮/ በደንብ ቁጥር ፭፻፯/፪ሺ፲፬ ለቴክኖሎጂ ባለስልጣን 6/ Notwithstanding powers and duties

የተሰጠው ሥልጣንና ተግባር እንደተጠበቀ ሆኖ designated to Energy Authority in


accordance with Regulations No 507/2024
የኢንዱስትሪ ኬሚካል ወደ ሀገር ውስጥ ማስገባት፣
issue certificate of competence to a person
ወደ ውጭ በመላክ እንዲሁም ማከፋፈል ሥራ
seeking to engage in the importation,
ለመሰማራት ለሚፈልግ ሰው የብቃት ማረጋገጫ
exportation, transportation and storage of
ምስክር ወረቀት ይሰጣል፣ ይቆጣጠራል፤
industrial chemicals and regulate the same;

7/ Issue license to any person seeking to


፯/ አደገኛ ቆሻሻ መሰብሰብ፣ ማጓጓዝ፣ ማከማቸት፣
engage in the collection, transportation,
በድጋሚ ጥቅም ላይ ማዋል፣ መልሶ ጥቅም ላይ
storage, reuse, recycling, disposal and trans-
ማዋል፣ አወጋገድ እና ድንበር ዘለል የአደገኛ
boundary movement of hazardous waste
ቆሻሻ እንቅስቃሴ ለመሰማራት ለሚፈልግ
and regulate the same;
ማንኛውም ሰው ፈቃድ ይሰጣል፣ ይቆጣጠራል፤
8/ Issue license to any person seeking to
፰/ ልውጥ ሕያው መስራት ወይም ለዝግ
engage in any making or use of any
አጠቃቀም፣ወደ አካባቢ ለመልቀቅ፣ ወደ ሀገር
modified organism for contained use,
ውስጥ ለማስገባት፣ ወደ ወጭ መላክ፣ ትራንዚት፣ release into the environment, import,
ማጓጓዝ እና ማከማቸት ለሚፈልግ ማንኛውም export, transit, transportation and storage
ሰው ፈቃድ ይሰጣል፣ ይቆጣጠራል፤ and regulate the same;
9/ In collaboration with relevant institutions,
፱/ ከሚመለከታቸው ተቋማት ጋር በመቀናጀት የመጤ
regulate, monitor and verify the expansion
ወራሪ ዝርያዎች መስፋፋት እና ቅነሳ ላይ
and reduction of invasive alien species;
ክትትል፣ ቁጥጥር እና የማረጋገጥ ሥራ ይሰራል፤

፲/ በአካባቢ ሕጎች መሠረት የአካባቢ ጥበቃ 10/ In accordance with environmental laws,

ግዴታዎች መከበራቸውን ለማረጋገጥ ወደ enter any land, premise or any other place,
inspect anything and take samples as
ማናቸውም መሬት፣ ቅጥር ግቢ ወይም ሌላ ቦታ
deemed necessary with a view to
ሊገባ ይችላል፣ ኃላፊነቱን ለመወጣት ተገቢ
discharging its duty and ascertaining
በሆነው ልክ ፍተሻዎችን ያደርጋል፣ ናሙናዎችን
compliance with environmental protection
ይወስዳል፤ ይህን ተግባር የሚፈጽም ባለሞያ
requirements; a professional who performs
ሥራውን እንዲሰራ ስለመታዘዙ ደብዳቤ የማቅረብ
this mandate is obliged to submit a letter
እና ማንነቱን የሚገልጽ መታወቂያ የማሳየት
about being instructed to do so and to show
ግዴታ አለበት፣ an identity card.
፲፩/ የዘርፍ መሥሪያ ቤቶች እና ሌሎች ባለድርሻ 11/ Monitor and regulate the proper
አካላት የአካባቢ ጥበቃ ጉዳዮችን በአግባቡ implementation of environmental protection
መተግበራቸውን ይቆጣጠራል፤ issues by relevant institutions and other
stakeholders;
፲፭ሺ፭፻፹፭
gA Ød‰L ነU¶T Uz¤È qÜ_R ፳፮ ግንቦት ፲፭ ቀን ፪ሺ፲፮ ›.M Federal Negarit Gazette No. 26, 23 th May, 2024….page 15585

፲፪/ የአካባቢ ጥበቃ ጉዳዮችን በሚመለከት በዓለም 12/ Take part in the negotiations of
አቀፍ እና በሌሎች መድረኮች ላይ ኢትዮጵያን international environmental agreements;

ወክሎ ይሳተፋል፣ እንዲሁም ዓለም አቀፋዊ monitor and regulate the implementation of
international environmental agreements;
የአካባቢ ጥበቃ ግዴታዎች በአግባቡ
መተግበራቸውን ይከታተላል፣ ይቆጣጠራል፤

፲፫/ ከሚመለከታቸው ተቋማት ጋር በመቀናጀት 13/ In collaboration with relevant institutions,


establish a system for payment for
ሀገራዊ የአካባቢ አገልግሎት ክፍያ ወይም
environmental services or payment for
የሥርዓተ-ምህዳር አገልግሎት ክፍያ የአሰራር
ecosystem services, and monitor and
ሥርዓት ይዘረጋል፣ አተገባበሩን ይከታተላል፣
regulate its implementation;
ይቆጣጠራል፤
፲፬/ በልማት እቅዶችና በኢንቨስትመንት መርሐ 14/ In cooperation with relevant institutions,
prepare or cause the preparation of
ግብሮች ውስጥ የሚካተቱ የአካባቢ የአዋጭነት
environmental cost benefit analysis
ማስሊያ ቀመሮችንና የስሌት ሥርዓትን
formulate an accounting system to be used
ከሚመለከታቸው ተቋማት ጋር በመተባበር
in development plans and investment
ያዘጋጃል ወይም እንዲዘጋጁ ያደርጋል፣
programs and, as the case may be, monitor
እንደሁኔታው በጥቅም ላይ የመዋላቸውን ሂደት
and regulate their application;
ይከታተላል፣ ይቆጣጠራል፤
15/ In consultation with relevant institutions,
፲፭/ዘላቂነት የጎደለው የተፈጥሮ ሀብቶች አጠቃቀምንና
regulate disincentive measures are taken to
ልምድን፣ የአካባቢ ጉስቁልና ወይም ብክለትን
discourage practices that may hamper the
ለመከላከል የሚያስችሉ የመግቻ እርምጃዎች
sustainable use of natural resources or the
መወሰዳቸውን ይቆጣጠራል፤
prevention of environmental degradation or
pollution;
፲፮/ በልዩ ልዩ መንገድ ወደ አየር የሚለቀቁ በካይ
16/ Shall follow-up and monitor relevant
ጋዞች በማህበረሰቡ እና በአካባቢ ላይ ጉዳት
institutions whether they properly function
አለማድረሳቸውን በሚመለከታቸው ተቋማት to ensure that polluting gases released into
በአግባቡ መተግበሩን ይከታተላል፣ the air in various ways do not harm the
ይቆጣጠራል፣ አስፈላጊውን እርምጃ ይወስዳል፤ community and the environment and take
necessary measures;

፲፯/ ከሚመለከታቸው ተቋማት ጋር በመቀናጀት 17/ In collaboration with relevant institutions it


በልዩ ልዩ የልማት እንቀስቃሴዎች ምክንያት shall identify and control environmental,

የአካባቢ፣ ሥነ-ምህዳር እና የማህበረሰብ ecological and social vulnerability and


damage caused by various development
ተጋላጭነትንና እያደረሰ ያለውን ጉዳት
initiatives, and ensure necessary legal
በመለየት ቁጥጥር ያደርጋል አስፈላጊውን
measures are taken.
ህጋዊ እርምጃ እንዲወሰድ ያደርጋል፤
፲፭ሺ፭፻፹፮
gA Ød‰L ነU¶T Uz¤È qÜ_R ፳፮ ግንቦት ፲፭ ቀን ፪ሺ፲፮ ›.M Federal Negarit Gazette No. 26, 23 th May, 2024….page 15586

፲፰/ የሙቀት አማቂ ጋዞችን የልኬት ሥራዎችን 18/ Perform verification by carrying out
measurements of greenhouse gases; approve
በማካሄድ የማረጋገጥ ሥራ ያከናውናል ፣
and control the measurements made by
በሌሎች የተደረጉ የሙቀት አማቂ ጋዞች
others. And submit report to the concerned
ልኬቶችን ያረጋግጣል፣ ይቆጣጠራል፡፡
body.
ለሚመለከተው አካል ሪፖርት ያቀርባል፣

፲፱/ ከሚመለከታቸው ተቋማት ጋር በመቀናጀት 19/ In coordination with relevant institutions,


monitor and regulate technologies that
ለአየር ንብረት ለውጥ ማጣጣሚያ እና
contribute for climate change adaptation
ማስተሳሰሪያ አስተዋፅኦ የሚያደርጉ
and mitigation are environmentally friendly
ቴክኖሎጂዎች ከአካባቢ ጋር
and free from any environmental impacts;
መጣጣማቸውንና ከአካባቢ ተፅዕኖ ነፃ
መሆናቸውን ያረጋግጣል፣ ይቆጣጣራል፤ ‹

20/ Regulate the amount of carbon stored in the


፳/ በስነ-ምህዳር ውስጥ የሚከማች የካርበን መጠን
ecosystem, assure its inclusion in the
ላይ ቁጥጥር ያደርጋል፣ የስነ-ምህዳር
ecosystem service payment structure, and
አገልግሎት ክፍያ ስርዓት ውስጥ እንዲካተት
monitor its proper implementation;
ያደርጋል፣ በአግባቡ መፈጸሙን ይከታተላል፣
21/ In coordination with relevant institutions,
፳፩/ ከሚመለከታቸው ተቋማት ጋር በመቀናጀት
cause the establishment of a system for the
የውሀ አዘል መሬቶች ጥበቃ እና ዘላቂ
protection and sustainable management of
አያያዝ ሥርዓት እንዲዘረጋ ያደረጋል፣ wetlands;
ይቆጣጠራል፤
22/ In consultation with relevant institutions,
፳፪/ ከሚመለከታቸው ተቋማት ጋር በመመካከር
work to establish environmental tribunals
ከአካባቢ ጥበቃ ጋር የተያያዙ የፍትሐ- and courts that hear environment related
ብሔርና የወንጀል ጉዳይ የሚስተናገድበት civil and criminal case;
ችሎት እንዲሁም የአካባቢ አስተዳደር
ፍርድ ቤት እንዲቋቋም ይሰራል፤
23/ Establish an environmental information
፳፫/ የአካባቢና የተፈጥሮ መረጃ አሰባሰብን፣
system that promotes efficiency in
አደረጃጀትን እና አጠቃቀምን የሚያቀላጥፍ
environmental data collection, management
የመረጃ ሥርአትን ይዘረጋል፤ and use;
፳፬/ የሀገሪቱን የአካባቢ ሁኔታ ዘገባ በየወቅቱ
24/ Prepare and avail to relevant institutions a
ያዘጋጃል፣ ለሚመለከታቸው አካላት ተደራሽ
periodic report on the state of the
ያደርጋል፤
environment of the country;
፳፭/ ከሚመለከታቸው ተቋማት ጋር በመተባበር 25/ In collaboration with relevant institutions,
መደበኛና መደበኛ ያልሆኑ የአካባቢና expand formal and informal environment
የአየር ንብረት ለውጥ ትምህርት መርሀ and climate change education programs and
ግብሮች እንዲስፋፉ ያደርጋል፣ እንዲሁም coordinate the integration of environmental

በመደበኛ ሥርዓተ ትምህርት ውስጥ protection concerns in the regular


educational curricula;
እንዲካተት ያስተባብራል፤
፲፭ሺ፭፻፹፯
gA Ød‰L ነU¶T Uz¤È qÜ_R ፳፮ ግንቦት ፲፭ ቀን ፪ሺ፲፮ ›.M Federal Negarit Gazette No. 26, 23 th May, 2024….page 15587

፳፮/የአካባቢ ጥበቃ የድርጊት ዕቅዶችንና 26/ Promote or assist in the formulation of

ፕሮጀክቶችን ዝግጅት ያበረታታል ወይም environmental protection action plans and


projects and solicit support for such action
ያግዛል፣ ለድርጊት ዕቅዶቹና ፕሮጀክቶቹ
plans and projects;
ማስፈፀሚያ የሚውሉ እገዛዎችን ያፋልጋል፤
አተገባበሩን ይከታተላል፤
፳፯/ የንብረት ባለቤት ይሆናል፣ ውል ይዋዋላል፣ 27/ Own property, enter into contracts and sue
and be sued; and
በራሱ ስም ይከሳል፣ይከሰሳል፤
28/ Carry out such other activities as are
፳፰/ ዓላማውን ለማስፈጸም የሚረዱ ሌሎች ሕጋዊ
necessary for the fulfillment of its
ተግባሮችን ያከናውናል፡፡
objectives.

፮. የባለሥልጣኑ አቋም 6. Organization of the Institute


ባለሥልጣኑ፡- The Authority shall have:

፩/ ዋና ዳይሬክተር 1/ A Director General


፪/እንደአስፈላጊነቱ ምክትል ዋና ዳይሬክተሮች፤ 2/ Deputy Director Generals as may be
እና necessary ; and

፫/ አስፈላጊው ሰራተኞች ይኖሩታል፡፡ 3/ The necessary staff.


፯. የዋናው ዳይሬክተር ሥልጣንና ተግባር 7. Powers and Duties of the Director General

፩/ዋና ዳይሬክተሩ የባለሥልጣኑ ዋና ሥራ 1/The Director General shall be the chief


executive officer of the Authority and shall,
አስፈጻሚ በመሆን የባለስልጣኑን ሥራዎች
subject to the general direction of the
ይመራል፣ ያስተዳድራል፡፡
Ministry, direct and administer the activities
፪/ የዚህ አንቀፅ ንዑስ አንቀፅ (፩) አጠቃላይ of the Authority.

አገላለጽ እንደተጠበቀ ሆኖ ዋና ዳይሬክተሩ፡- 2/ Without limiting the generality of sub-


article (1) of this Article, the Director
General shall:
ሀ) በዚህ ደንብ አንቀጽ (፭) የተመለከቱትን
a) Exercise the powers and duties of the
የባለሥልጣኑን ሥልጣንና ተግባራት በሥራ
Authority specified under Article 5 of
ላይ ያውላል፤
this Regulation;
ለ) የባለሥልጣኑን ሠራተኞችን በፌዴራል b) Employ and administer employees of
ሲቪል ሰርቪስ ሕጎች መሠረት ይቀጥራል the Authority in accordance with the
ያስተዳድራል፤ Federal Civil Service laws;

ሐ) የባለሥልጣኑን የሥራ ፕሮግራምና በጀት c) Prepare the work program and budget
of the Authority and implement same
አዘጋጅቶ ለሚመለከተው የመንግሥት አካል
upon approval;
ያቀርባል፤ ሲጸድቅም ተግባራዊ ያደርጋል፤
d) Effect expenditure in accordance with
መ) ለባለሥልጣኑ በተፈቀደው በጀትና የሥራ the budget and work program approval
ፕሮግራም መሠረት ክፍያዎችን ይፈጽማል፤ for the Authority;
፲፭ሺ፭፻፹፰
gA Ød‰L ነU¶T Uz¤È qÜ_R ፳፮ ግንቦት ፲፭ ቀን ፪ሺ፲፮ ›.M Federal Negarit Gazette No. 26, 23 th May, 2024….page 15588

ሠ) ከሦስተኛ ወገን ጋር በሚደረግ ግንኙነት e) Represent the Authority in its dealings

ባለሥልጣኑን ይወክላል፤ with third parties


f) Prepare and submit to the Ministry the
ረ) የባለሥልጣኑን የሥራ አፈፃፀምና የሂሳብ
performance and financial reports of
ሪፖርቶች አዘጋጅቶ ለሚመለከተው
the Authority.
የመንግሥት አካል ያቀርባል፡፡

፫/ ዋና ዳይሬክተሩ ለሥራ ቅልጥፍና ሲባል 3/ The Director General may delegate part of

ሥልጣንና ተግባሩን በከፊል ለሌሎች his powers and duties to the Deputy
Director Generals and employees of the
ኃላፊዎችና ሠራተኞች በውክልና ሊሰጥ
Authority to the extent necessary for
ይችላል፡፡
efficient performance of the activities of
the Authority
፰. የምክትል ዋና ዳይሬክተሩ ሥልጣንና ተግባራት
8. Powers and Duties of Deputy Director
General
፩/ ምክትል ዋና ዳይሬክተሩ ከዋና ዳይሬክተሩ
1/ The Deputy Director General shall:
በሚሰጥ መመሪያ መሠረት፡-
a) Assist the Director General in planning,
ሀ) የባለሥልጣኑን ተግባሮች በማቀድ፣
organizing, directing and coordinating
በማደራጀት፣በመምራትና በማስተባበር ዋና the activities of the Authority; and
ዳይሬክተሩን ይረዳል፤
b) Lead the division that he is assigned;
ለ) የሚመደብበትን የሥራ ዘርፍ ይመራል፤
c) Perform other activities specifically

ሐ) በዋና ዳይሬክተሩ የሚሰጡትን ሌሎች assigned to them by the Director


General.
ሥራዎች ያከናውናል፡፡
2/ In the absence of the Director General, the
፪/ ዋና ዳይሬክተሩ በማይኖርበት ጊዜ ምክትል
Deputy Director General shall, act on his
ዋና ዳይሬክተሩ ተክቶ ይሰራል፤ ከአንድ
behalf; where there are more than one
በላይ ምክትል ዋና ዳይሬክተሮች ካሉና ዋና Deputy Director Generals and no specific
ዳይሬክተሩ በተለይ ካልወከለ በሹመት delegation has been given by the Director
ቅድሚያ ያለው ምክትል ዋና ዳይሬክተር General, the Deputy Director who is senior
ተክቶ ይሰራል፡፡ by appointment shall act on behalf of the
Minster.
፱. በጀት
9. Budget
የባለሥልጣኑ በጀት በመንግሥት ይመደባል፡፡ The budget of the Authority shall be
allocated by the Government.
gA ፲፭ሺ፭፻፹፱ Ød‰L ነU¶T Uz¤È qÜ_R ፳፮ ግንቦት ፲፭ ቀን ፪ሺ፲፮ ›.M Federal Negarit Gazette No. 26, 23 th May, 2024….page 15589

10. Book of Accounts


፲. የሒሳብ መዛግብት
1/ The Authority shall keep complete and
፩/ ባለሥልጣኑ የተሟሉና ትክክለኛ የሆኑ ሒሳብ
accurate books of accounts.
መዛግብት ይይዛል፡፡
2/ The books accounts and financial
፪/ የባለሥልጣኑ የሒሳብ መዛግብትና ገንዘብ ነክ
documents of the Authority shall be
ሰነዶች በዋናው ኦዲተር ወይም እርሱ
audited annually by the Auditor General
በሚሰይመው ኦዲተር በየዓመቱ or by an auditor assigned by him.
ይመረመራሉ፡፡

፲፩. ተፈጻሚነት የማይኖራቸው ሕጎች 11. Inapplicable Provisions

ከዚህ ደንብ ጋር የሚቃረን ማንኛውም ደንብ፣ Any Regulation or Custom contrary to this
Regulation shall not apply to the matters
መመሪያ እና ልማዳዊ አሠራር በዚህ ደንብ
covered under this Regulation.
ውስጥ በተመለከቱ ጉዳዮች ላይ ተፈጻሚነት
አይኖራቸውም፡፡
፲፪. ደንቡ የሚጸናበት ጊዜ 12. Effective Date
ይህ ደንብ በፌደራል ነጋሪት ጋዜጣ ታትሞ This Regulation shall enter into force on the
ከወጣበት ቀን ጀምሮ የጸና ይሆናል፡፡ date of their publication in the Federal
Negarit Gazzette.

አዲስ አበባ ግንቦት ፲፭ ቀን ፪ሺ፲፮ ዓ.ም Done at Addis Ababa, On this Day of
May 23th, 2024.

አብይ አህመድ (ዶ/ር)


ABIY AHMED (Dr.)

የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ PRIME MINISTER OF THE FEDERAL

ሪፐብሊክ ጠቅላይ ሚኒስትር DEMOCRATIC REPUBLIC OF ETHIOPIA


gA Ød‰L ነU¶T Uz¤È qÜ_R ፳፮ ግንቦት ፲፭ ቀን ፪ሺ፲፮ ›.M Federal Negarit Gazette No. 26, 23 th May, 2024….page 15590

You might also like