Download as docx, pdf, or txt
Download as docx, pdf, or txt
You are on page 1of 8

ካሚሎስ ሪል እስቴት

የአፓርትመንት መኖሪያ ቤት ሽያጭ ውል

የደንበኛው ሙሉ ስም፡…………………………………..

የውል ቁጥር፡………………………..

ስልክ ቁጥር፡…………………………

የአፓርትመንት መኖሪያ ቤት ሽያጭ ውል

አንቀፅ 1
ተዋዋይ ወገኖች
ይህ ውል ከዚህ በኋላ “ሻጭ” እየተባለ በሚጠራው ካሚሎስ
ሪል እስቴት አድራሻ በአዲስ አበባ ከተማ ፣ ልደታ ክፍለ ከተማ፣ ወረዳ ፣የቤት ቁጥር ፣ የስልክ
ቁጥር ፤ ሞባይል የፋክስ ቁጥር ፤ የፓ.ሣ. ቁ ፤ Email / በሆነው፣ እና
ከዚህ በኋላ “ገዥ” እየተባለ በሚጠሩት አቶ/ወ/ሮ/ወ/ሪት…………………………………. ዜግነት…………………………
አድራሻው:…………………….ከተማ፣………………… ክ/ከተማ፣ ወረዳ………….፣የቤት ቁጥር ……የስልክ
ቁጥር………………………..፣ኢሜይል……………………………፣የመታወቂያ/ፓስፖርት ቁጥር……………………..፣ በሆነው
መካከል የአፓርትመንት መኖሪያ ቤት ሽያጭ ውል መመስረቱን የሚያረጋግጥ ውል ነው፡፡
አንቀፅ
2
የውሉ ዓላማ

ሻጭ በስሙ በካርታ ቁጥር በተመዘገበው እና አድራሻው በአዲስ አበባ ከተማ፣ልደታ ክ /ከተማ፣ ወረዳ
፣ የቤት ቁጥር በሆነው ይዞታው ላይ የአፓርትመንት መኖሪያ ቤት በመገንባት ለመሸጥ ስለፈለገ ገዥም መለያው በዚህ
ውል አንቀፅ 3 ላይ የተመለከተውን የአፓርትመንት የመኖሪያ ቤት መግዛት ስለፈለጉ ይህ ውል ሊመሰረት ችሏል፡፡
አንቀፅ 3
የሚሸጠው የአፓርትመንት መኖሪያ ቤት መለያና ይዘት
1
ሻጭ በዚህ ውል ለገዥ ለማስተላለፍ እና ገዥም ለመግዛት የፈለገው የአፓርትመንት የመኖሪያ ቤት መለያ እንደሚከተለው
ተዘርዝሯል፡፡

የአፓርትመንት መኖሪያ ቤቱ ስፋት………..ሜ/ካ፤ የአፓርትመንት መኖሪያ ቤቱ የሚገኝበት የሕንጻ ወለል……(ፎቅ) እና


ታይፕ….....ሲሆን የቤቱ መለያ ቁጥር………………………. ነው፡፡ - የቤቱ ጠቅላላ ክፍሎች አይነት እና ብዛት
የአፖርትመንት መኖሪያ ቤት ብዛት
የክፍሎቹ አይነት (በቁጥር)
ሳሎን

መኝታ ቤት

የቤት ውስጥ ረዳት ማደሪያ

መፀዳጃ ቤት

ምግብ ማብሰያ

የመኪና ማቆሚያ

አንቀፅ
4
የሚሸጠው አፓርትመንት መገለጫና የጋራ መጠቀሚያዎች

4.1 ይህ መኖሪያ አፓርታማ ቤት ሙሉ ለሙሉ እራሱን የሚችል ሲሆን በተጨማሪ ከሌሎቹ የመኖሪያ ቤቶች ጋር በጋራ
የሚጠቀምባቸው መጠቀሚያዎች ከዚህ በታች በአንፅ 4.2 የተገለፀ ሲሆን እነዚህን የጋራ መጠቀሚያዎች ከሌሎች
ነዋሪዎች ጋር በጋራና በኃላፊነት የመጠቀም መብትና ግዴታም ጭምር እንዳለበት ከወዲሁ ወዶና ፈቅዶ ተስማምቷል፡፡
4.2 በዚህ ውል አንቀፅ 3 ላይ የተመለከተው የአፓርትመንት መኖሪያ ቤት ሙሉ ለሙሉ ግንባታው ሲጠናቀቅ የተሟላ
የመብራትና የውሃ አገልግሎት፣ደረጃ፣ኮሪደር፣የእንግዳ መቀበያ፣ አሳንሰር፣የቆሻሻ መጣያ፣የህንጻው ጣሪያ (ሩፍ ቶፕ)
ላይ የሚገኝ የጋራ መጠቀሚያ፣የዘበኛ (ጥበቃ) ቤት፣የጋራ የውሃ ማጠራቀሚያ (ታንከር) እና የጋራ መኪና ማቆሚያ
ይኖሩታል፡፡
4.3 ገዢ የጋራ መጠቀሚያዎችን (Communal Space) በተመለከተ የህንጻው ባለቤቶች በጋራ በሚያወጡት
መተዳደሪያ ደንብ መሰረት ከሌሎች ገዢዎች ጋር በጋራና በኃላፊነት የመጠቀም መብትና ግዴታም ጭምር እንዳለበት
ከወዲሁ ወዶና ፈቅዶ ተስማምቷል፡፡ ገዥው በጋራ መጠቀሚያዎች በአግባቡ መገልገል አለበት፣የጋራ መጠቀሚያው
ለቤቱ ባለቤቶች አይከፋፈልም፣አይታጠርም፣አይሸጥም።
አንቀፅ 5
የሽያጭ ዋጋ

5.1. በዚህ ውል አንቀጽ 3 የተጠቀሰው የአፓርትመንት መኖሪያ ቤት ጠቅላላ መሸጫ ዋጋ


$..................................................... ( የአሜሪካን ዶላር…………………………………..) 15
(አስራ አምስት ከመቶ) የቫት (ተ.እ.ታክስ) ክፍያን ጨምሮ እንዲሆን ሻጭና ገዢ ተስማምተዋል፡፡

2
5.2. በዚህ ውል የተጠቀሰው ቤት በግንባታ ወቅት በሚያጋጥሙ የተለያዩ ምክንያቶች የወለል ስፋቱ ከ 3% በላይ
ቢጨምር ወይም ቢቀንስ የቤቱ የመሸጫ ዋጋ በቤቱ በካሬ ዋጋ ስሌት መሰረት ማስተካከያ ይደረግለታል፡፡

አንቀፅ 6
የአከፋፈል ሁኔታ
6.1 ገዥ የመጀመሪያ ክፍያ ከቤቱ ጠቅላላ የመሸጫ ዋጋ ውስጥ 15% $..........................
(የአሜሪካን ዶላር ………………………………………………………………………..) ሲሆን ይህ ዋጋ እ.ኤ.አ በዲሴምበር
02,2023 ባለው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የመሸጫ የአሜሪካን ዶላር ምንዛሬ ሲሰላ በኢትዮጵያ ብር
………………………..(ብር ……………………………………………………………………) በቅድሚያ ከፍለዋል፡፡
6.2 ቀሪ ክፍያው የሚከናወነው በኢትዮጵያ ብር ሆኖ የክፍያው መጠን የሚሰላዉ ክፍያዉ በሚፈጸምበት እለት ባለው
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የመሸጫ የአሜሪካን ዶላር ምንዛሬ መሰረት ይሆናል፡፡ገዢ ቀሪውን ክፍያ እንደሚከተለው
ከፍሎ ለመጨረስ ተስማምቷል፡፡

ተ.ቁ ከጠቅላላው የቤት ዋጋ ክፍያ በመቶኛ የሚከፈልበት ጊዜ

2 ኛ ክፍያ ከቤቱ ጠቅላላ የመሸጫ ዋጋ ላይ 20% የህንጻው ጠቅላላ የስትራክቸር ስራ ከወለል በላይ ስድስተኛ ፎቅ
ስላብ ተሞልቶ ሲጠናቀቅ

3 ኛ ክፍያ ከቤቱ ጠቅላላ የመሸጫ ዋጋ ላይ 25% የህንጻው ጠቅላላ የስትራክቸር ስራ የመጨረሻ ፎቅ ስላብ
ተሞልቶ ሲጠናቀቅ

4 ኛ ክፍያ ከቤቱ ጠቅላላ የመሸጫ ዋጋ ላይ 25% የህንጻው የብሎኬት ድርድር፣የልስን፣የኤሌትሪክ


መስመር፣የሳኒተሪ መስመር ዝርጋታ ሲጠናቀቅ

5 ኛ ክፍያ የህንጻው የውጫዊ እና የጋራ መገልገያዎች ፊኒሺንግ ሲጀመር


ከቤቱ ጠቅላላ የመሸጫ ዋጋ ላይ 10%
6 ኛ ክፍያ ከቤቱ ጠቅላላ የመሸጫ ዋጋ ላይ 5% ርክክብ ሲፈጸም እና የይዞታ ማረጋገጫ (ካርታ) ሲቀበሉ

6.3 ገዢ በአንቀጽ 5 እና በአንቀጽ 6 መሰረት መክፈል የሚገባውን ክፍያ ከሻጭ የክፍያ መጠየቂያ በቀረበለት በ 15 ቀናት

ውስጥ መክፈል አለበት፡፡ ይህ ካልተፈጸመ ሻጭ ለገዢ ክፍያውን እንዲፈጽም የ 30 ቀናት የክፍያ ጊዜ ገደብ

ማስጠንቀቂያ በጽሁፍ ይሰጠዋል፡፡ በ 30 ቀናት የማስጠንቀቂያ ጊዜ ውስጥ ክፍያ ካልፈጸመ ሻጭ ውሉን በመሰረዝ

ለሌላ 3 ኛ ወገን የመሸጥ ሙሉ መብት እንዲኖረው ግራ ቀኛችን ተስማምተን ግዴታ ገብተናል፡፡ ይህም ሲሆን ሻጭ
ለገዥ መመለስ ያለበት የገንዘብ መጠን ቫትን እና ለሽያጭ ባለሙያዎች የተከፈለ ኮሚሽን ከገዥ ከተቀበለው ክፍያ ላይ
በመቀነስ ይሆናል፡፡

3
6.4 ገዢ በዚህ ውል የተመለከቱትን ማናቸውም ክፍያዎች በድርጅቱ ሀልቡላሎ ሪል እስቴት አክስዮን ማህበር ስም
በተከፈቱ የተለያዩ ባንኮች ሂሳብ ቁጥሮች ውስጥ በማስገባት ወይም በሲ.ፒ.ኦ.(C.P.O) ለመክፈል ተስማምቷል፡፡

አንቀፅ 7
ሌሎች ክፍያዎች

7.1. ሻጭ የአፓርትመንት መኖሪያ ቤቶቹን የተናጠል ካርታ በስሙ ለማውጣት የሚያስችለውን ማንኛውንም ክፍያ
ይፈጽማል፡፡
7.2. ገዥ የቤት ባለቤትነት በስሙ እንዲዛወር ሻጭ የተናጠል ካርታ በስሙ ካወጣ በኋላ በተጨማሪነት በኢፌዲሪ ፍትህ
ሚኒስቴር የሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ ኤጀንሲ ቀርቦ ከሻጭ ጋር ህጋዊ ውል በመፈጸም ንብረቱን በስሙ
ያዛውራል፡፡ ገዢ ቤቱን በስሙ
ለማዞር የሚከፈል የስም ማዛወሪያ አሹራ ክፍያ ይከፍላል ፡፡
አንቀፅ
8
የመኖሪያ አፓርታማ ቤቱ ማጠናቀቂያ ጊዜ እና የቤቱ ርክክብ

8.1 ሻጭ በዚህ ውል ግዴታ የገባበትን ቤት ይህ ውል በተፈረመ በ 24 ወር (ሁለት አመት) ውስጥ 80% ሰርቶ ለማጠናቀቅ
የተስማማ ሲሆን ይሁን እና በተለያዩ ችግሮች ምክንያት በተባለው ጊዜ ማጠናቀቅ ባይቻል በተጨማሪ 6(ስድስት)
ወራት የማጠናቀቂያ ጊዜው ሊራዘም ይችላል፡፡
8.2 ገዥ በዚህ ውል አንቀፅ 5.1 ላይ የተመለከተውን የሽያጭ ዋጋ በአንቀጽ 6.1 እና 6.2 በተጠቀሰው መሰረት እስከ
4 ኛው ክፍያ ድረስ ያለውን አጠቃሎ እንደከፈለ ሻጭ የመኖሪያ አፓርታማ ቤቱን 80% ገንብቶ ማለትም የውጭ በርና
መስኮት፣ የጅብሰም ቻክ፣ የኤሌክትሪክ ገመድ ዝርጋታ እና የሳኒታሪ የመስመር ዝርጋታ ሰርቶ ገንብቶ በውሉ አንቀፅ
8.1 በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥ ግንባታውን ያጠናቅቃል፡፡ይሁንና ሻጭ ይህንን ቤት ለገዥ የሚያስረክበው ሻጭ ቀሪውን
የፊኒሺንግ ስራ ካጠናቀቀ በኋላ ነው፡፡
8.3 ገዥ በ 80% ስራ ውስጥ ያልተካከቱ የፊኒሺንግ እቃዎቹን እራሱ ገዝቶ ለማቅረብ የተስማማ ሲሆን
የሚያቀርባቸውም የፊኒሺንግ እቃዎች ሴራሚክ፣ የኤሌክትሪካል እና የሳኒታሪ እቃዎች (ፊክስቸርስ) በሙሉ፣ የቤት
ውስጥ ቀለም፣ የውስጥ በሮች፣ ቁምሳጥን እና ኪችን ካቢኔት ናቸው፡፡ የፊኒሺንግ ስራውም በሻጭ ባለሙያዎች
የሚሰራ ሲሆን በዚህ ውል አንቀፅ 5.1 ላይ ያለው ጠቅላላ ክፍያም የባለሙያውን ክፍያ (የእጅ ዋጋ) የማያጠቃልል
ነው፡፡
8.4 ገዥ በአንቀፅ 8.3 የተጠቀሱትን የፊኒሺንግ እቃዎች የሚያቀርብበት ጊዜም ቤቱ 80 ከመቶ ተገንብቶ ከመጠናቀቁ ከ
4 (አራት) ወራት በፊት ይሆናል፤ ይህም በአንቀፅ 1 በተጠቀሰው የገዥ አድራሻ በአንደኛው የመገናኛ መንገድ በሻጭ
በተጠየቀ በ 1 (አንድ) ወር ባልበለጠ ጊዜ ውስጥ ለማቅረብ ተስማምቷል፡፡
8.5 ሻጭ በአንቀፅ 8.1 መሰረት 80% ግንባታውን ባጠናቀቀ በ 6(ስድስት) ወራት ውስጥ ከገዥ በአንቀፅ 8.3 በተረከበው
የፊኒሺንግ እቃዎች የፊኒሺንግ ስራውን አጠናቆ ለገዥ ቤቱን ለማስረከብ ተስማምቷል፡፡
8.6 ገዥ በአንቀፅ 8.3 የተጠቀሱትን የፊኒሺንግ እቃዎች ማቅረብ ካልቻለ ወይም ካልፈለገ ሻጭ እቃውን
እንዲያቀርብለትና በጊዜው ባለው የእቃው የገበያ ዋጋ እና የእቃውን ዋጋ 40% ተጨማሪ ክፍያ ለሻጭ ለመክፈል
ሊስማማ ይችላል፡፡ ይህንንም ስምምነት በዛሬው እለት ወይም ገዥ የፊኒሺንግ እቃዎቹን ማቅረብ ካለበት ጊዜ (አንቀፅ
8.4) በፊት ለሻጭ በፅሁፍ ማሳወቅ ይኖርበታል፡፡

4
8.7 ገዥም በአንቀጽ 8.4 መሰረት እቃውን ማቅረብ ባይችል ሻጭ የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ ሰጥቶ በተጨማሪ በ 15 ቀን
ጊዜ ውስጥ እንዲያቀርብ ይጠይቃል፡፡ ሆኖም ግን አሁንም በተጨማሪው 15 ቀን ጊዜ እቃውን ማቅረብ ባይችል ሻጭ
እቃውን ከገበያ ላይ በገበያ ዋጋ ገዝቶ አቅርቦ ስራውን የሚሰራ ሲሆን ገዥም የእቃውን ዋጋ እና የእቃውን ዋጋ 50%
እቃው በተገዛ በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ የመክፈል ግዴታ አለበት፡፡ ይህ ሳይሆን ቢቀር በአንቀፅ 6.3 ላይ የተገለፅው
ተፈፃሚ ይሆናል።

አንቀፅ 9
የሻጭ ግዴታዎች

9.1 ሻጭ ከአቅም በላይ ተብለው የሚታመኑ ችግሮች ካላጋጠሙት በስተቀር በዚህ ውል የተጠቀሰውን የቤት ግንባታ
በዚህ ውል ውስጥ በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥ የማጠናቀቅ ግዴታ አለበት፡፡
9.2 ከዚህ የአፓርትመንት መኖሪያ ቤት ሽያጭ ጋር ተያይዞ ሻጭን የሚመለከት የቤት ባለቤትነት ጥያቄ ክርክር ቢነሳ ሻጭ
በራሱ ወጪ ተከራክሮ ቤቱን ከክርክሩ ነፃ በማድረግ ለገዢ ያስረክባል፡፡
9.3 የአፓርትመንት ህንጻው ባለቤቶች (ገዢዎች) በማህበር የሚደራጁበትን ሁኔታ በማመቻቸት የሚተዳደሩበትን
የመተዳደሪያ ደንብ እና ውስጠ ደንብ በማርቀቅ ሂደት እና የአፓርትመንት ህንጻው ባለቤቶች (ገዢዎች) የጋራ
አፓርትመንት ህንጻ ማህበር እንዲያቋቁሙ ተገቢውን ድጋፍ እና እገዛ ያደርጋል፡፡
9.4 በዚህ የአፓርትመንት ሕንፃ ውስጥ ያሉ ቤቶች ተሽጠው ሙሉ በሙሉ ለገዢዎች እስኪተላለፉ ድረስ ወይም
የአፓርትመንት ህንጻው ባለቤቶች (ገዢዎች) የራሳቸውን የጋራ አፓርትመንት ህንጻ ማህበር አቋቁመው በጋራ
ህንጻውን ማስተዳደር እስኪችሉ ድረስ በዚህ ውል ውስጥ የተመለከተውን የነዋሪዎች የጋራ መጠቀሚያ ቦታዎችን ሻጭ
የመጠበቅ እና አጠቃቀማቸውን የመወሰን እንዲሁም የመከታተል ኃላፊነት አለበት፡፡
9.5 ከዚህ የመኖሪያ አፓርታማ ቤት ጋር ተያይዞ ቤቱ በሽያጭ ከመተላለፉ በፊት የሚነሳ ማንኛውንም የዕዳ እና የዕገዳ
ጥያቄዎች ቢኖር ሻጭ ኃላፊነቱን ወስዶ ቤቱን ከዚህ ዕዳ እና ዕገዳ ነፃ የማድረግ ኃላፊነት አለበት፡፡
9.6 ሻጭ ለገዥ መኖሪያ አፓርታማ ቤቱን ከማስረከቡ በፊት በቤቱ ላይ ለሚደርስ ማናቸውም ጉዳት ኃላፊነት አለበት፡፡
9.7 አፓርትመንቱ የሚገነባበትን መሬት የሊዝ ክፍያ በሙሉ ሻጭ ይከፍላል፡፡
9.8 የይዞታ ምዝገባ ዋስትና ፈንድ ክፍያን ሻጭ ይከፍላል፡፡

አንቀፅ 10
የገዥ ግዴታዎች

10.1. ገዢ የስም ማዛወሪያ አሹራ ወይም ማንኛውንም ከስም ዝውውር ጋር የተያያዘ ክፍያ
ይከፍላል፡፡
10.2. ገዢ ይህን የሽያጭ ውል ለማስመዝገብ በኢፌዲሪ ፍትህ ሚኒስቴር የሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ ኤጀንሲ
የሚዘጋጀውን ውል ቀርቦ የመፈረም ግዴታ ገብቷል፡፡የንብረት ምዝገባው እና የስም ዝውውሩ በሚመለከተው
መ/ቤት ቀርቦ በራሱ ያስፈጽማል፡፡
10.3. ሆኖም ግን ገዥ በአንቀፅ 10.2 የተጠቀሰውን ግዴታው ለመወጣት ተገቢውን ጥረት በወቅቱ ሳያደርግ ቢቀር ይህ
ተግባር የሚፈፀመው ለሻጭ አመቺ በሆነ ግዜ ይሆናል፡፡
10.4. ገዢ በሚቋቋመው የጋራ አፓርትመንት ህንጻ ማህበር ውስጥ በአባልነት የመመዝገብ እና የአባልነት ግዴታውን
በመወጣት ከሌሎች የአፓርትመንት ህንጻው ባለቤቶች (ገዢዎች) ጋር በስምምነት እና በመከባበር የመኖር ግዴታ
አለበት፡፡

5
10.5. ገዢ የጋራ መጠቀሚያዎችን በአግባቡ የመጠቀም እና በጋራ አፓርትመንት ህንጻ ማህበር መተዳደሪያ ደንብ
ድንጋጌዎች መሰረት የመገዛት ግዴታ አለበት፡፡ ከነዚህ መመሪያዎችና ደንቦች ውስጥ አንዱ ለአብነት ያህል
የተገዛውን ቤት ለማንኛውም የመጠጥ ቤት/ግሮሰሪ፣ ጫት መቃሚያ/መሸጫ፣አደንዛዥ እጽ መጠቀሚያ ወይም
ሌሎች ከሞራል ተቃራኒ የሆኑ ንግዶችን/አገልግሎቶች መጠቀም ማካሄድ አይችልም።
10.6. ገዢ ቤቱን ከተረከበበት ጊዜ ጀምሮ ለሚነሱ ማንኛውም ክርክሮች፣ ክፍያዎች ወይም ጥያቄዎች ኃላፊነቱን
ይወስዳል፡፡
10.7 ሻጭ ለስም ዝውውር የሚያስፈልጉ ሰነዶችን ለሚመለከተው መንግስታዊ መ/ቤት ካስረከበ በኃላ የባለቤትነት
ማረጋገጫ ሰነዱን ተከታትሎ የማግኘት ግዴታ የገዥ ነው።
10.8 በግንባታ ላይ ያለውን ቤት ገዥ ከመረከቡ በፊት ለሶስተኛ ወገን ማስተላለፍ ከፈለገ ተጨማሪ 30% በመቶ
የአገልግሎት ክፍያ ይከፍላል። ይህ የሚሰላው በሽያጭ ጊዜ (ውል በተፈራረሙበት ጊዜ) ያለው የአፓርትመንት
ቤቱ የብር ጠቅላላ ዋጋ ላይ ይሆናል፡፡

አንቀፅ 11
ውሉ ስለሚፀናበት ጊዜ ሁኔታ

11.1 ይህ ውል በተዋዋይ ወገኖች እና በእማኞች ፊት ከተፈረመበት ጊዜ ጀምሮ የፀና ይሆናል፡፡ 11.2 በዚሁ ውል መነሻነት
ሻጭ እና ገዢ ያደረጓቸው ሌሎች ተጨማሪ ስምምነቶችም ሆነ በመጨረሻም በኢፌዲሪ ፍትህ ሚኒስቴር የሰነዶች
ማረጋገጫና ምዝገባ ኤጀንሲ ቀርበው የሚፈርሙት የንብረት ማስተላለፍ ውል ስምምነት የዚህ ሽያጭ ውል አካል ሆነው
ይቆጠራሉ፡፡ አንቀፅ 12
አለመግባባት ስለሚፈታበት ሁኔታ

12.1 ተዋዋይ ወገኖች በመካከላቸው አለመግባባት ቢፈጠር አለመግባባታቸውን በተቻለ መጠን በስምምነት ለመፍታት
ተገቢውን ጥረት ያደርጋሉ፡፡ ሆኖም ግን ተዋዋይ ወገኖች አለመግባባታቸውን በስምምነት መፍታት ካልቻሉ ጉዳዩን ሥልጣን
ላለው የህግ አካል ማቅረብና ውሳኔ ማግኘት ይችላሉ፡፡

አንቀፅ
13
ከአቅም በላይ የሆነ ችግር

13.1 ሻጭ በውሉ ላይ በተመለከተው የጊዜ ሰሌዳ መሰረት የአፓርትመንት መኖሪያ ቤቶቹን ግንባታ ከአቅም በላይ በሆነ
ምክንያት አጋጥሞት በተቀመጠው የጊዜ ሰሌዳ መሰረት ባያጠናቅቅ ከአቅም በላይ የሆነውን ችግር በመግለጽ ለገዢ
ችግሩ በተፈጠረ በ 15 ቀናት ውስጥ በጽሁፍ፣ በኢሜል፣ በስልክ በሌሎች አማራጭ የግንኙነት መንገዶች ያሳውቃል፡፡

13.2 ሻጭ በገባው የውል ግዴታ መሰረት ለመፈጸም ያልቻለው ከአቅም በላይ በሆነ ችግር ምክንያት ከሆነ በገዢ ላይ
ለሚደርስ ማንኛውም ኪሳራ ተጠያቂ አይሆንም፡፡ ነገር ግን ሻጭ ተፈጠረ በማለት የገለጸው ችግር በተቀመጠው የጊዜ
ሰሌዳ መሰረት የአፓርትመንት መኖሪያ ቤቶቹን ለማጠናቀቅ የሚያስችለው እንደነበር በገለልተኛ አካል ከተረጋገጠ
ለገዢ በአንቀፅ 5.1 የተገለፀውን የአፓርትመንት መኖሪያ ቤት ጠቅላላ መሸጫ ዋጋ 0.5% በየወሩ የውሉ ዋጋ 5%
የመጨረሻ የክፍያ ጣሪያ እስኪደርስ ድረስ ኪሳራ የሚከፍል ይሆናል፣ከዚህ በኃላ አልሚው በተራዘመው የጊዜ ገደብ

6
ውስጥ ቤቱን አጠናቆ ማስረከብ ካልቻለ ገዥ 5% መቀጫ እንዲከፈለው የመጠየቅ መብቱ እንደተጠበቀ ሆኖ በገዥ
ምርጫ የተሰራውን ቤት ገዥ ግምት ከፍሎ ውሉን በማቋረጥ ቤቱን ተረክቦ በሌላ ዘዴ ግንባታውን ሊጨርስ ይችላል፡፡

አንቀፅ 14 ውሉ
ስለማፍረስ
14.1 ሁለቱም ወገኖች በጋራ በሚደርሱበት ስምምነት ይህን ውል በስምምነት ማፍረስ ይችላሉ፡፡

14.2 ይህ ውል በስምምነት በሚፈርስበት ጊዜ ሁለቱም ወገኖች ውሉን ለማፍረስ በሚደርሱበት ስምምነት መሰረት
የተከፈለ ክፍያ ካለ ተመላሽ ይደረጋል፡፡
14.3 በገዢ ተነሳሽነት ወይም በገዢ የውል ግዴታን ባለመወጣት የውል ማፍረስ ሲፈጸም በተከፈለ ክፍያ ላይ ለመንግስት
የተከፈለን ታክስ እና ለሽያጭ ባለሙያዎች የተከፈለ ኮሚሽንን ሻጭ ተመላሽ እንዲያደርግ አይገደድም፡፡
14.4 ገዢ በዚህ ውል በአንቀፅ 5 የተጠቀሰውን የቤቱን ዋጋ በአንቀፅ 6 ዝርዝር መሠረት አሟልቶና በጊዜው ካልከፈለ ሻጭ
በአንቀፅ 6.3 በተገለጸው መሠረት ውሉን የማፍረስ መብት አለው፡፡
14.5 ከላይ በንዑስ አንቀፅ 14.4 የተመለከተው እንደተጠበቀው ሆኖ ገዢ ለቤቱ ግዢ የተወሰነ ክፍያ ከፍሎ በቀሪ ክፍያ
ላይ የውል ግዴታውን ባይወጣ ሻጭ ውሉን በማፍረስ ገዢ ገዝቶ የነበረውን ቤት ለሌላ ቤት ገዢ መሸጥ ይችላል፡፡
አስቀድሞ ገዢ የከፈለው ክፍያ ተመላሽ የሚደረገው ቤቱ ለሌላ ገዢ መሸጥ ሲችል ብቻ ይሆናል፡፡ የሚመለሰውም
ገንዘብ መጠን በዚህ ውል በአንቀጽ 14.3 በተቀመጠው መሰረት ይሆናል፡፡

አንቀፅ 15
ውሉ የተፈረመበት ቦታና ቀን እና የውሉ ተፈጻሚነት

15.1 ይህ ውል በተዋዋይ ወገኖች መካከል ዛሬ -------/--------/------- (ቀን/ወር/ዓ.ም.) በአዲስ አበባ ከተማ


በምስክሮች ፊት ተፈረመ፡፡

15.2. ይህ ውል የቅድመ ክፍያ ተከፍሎ ውሉ ከተዋዋይ ወገኖች ከተፈረመበት ቀን ጀምሮ የጸና ይሆናል።

15.3. በሻጭ በኩል ከስራ አስኪያጁ በተጨማሪ የቦርድ የባንክ ፈራሚ ከሆኑት አንዱ አብሮ ካልፈረመ ተፈጻሚ አይሆንም።

15.4. የዚህ ውል ግዴታዎች በተዋዋይ ወገኖች ወራሾች፣ትራስቶች(trustee) እና መብት ተቀባዮች ላይ ተፈጻሚነት


ይኖራቸዋል።

አንቀጽ

16

የዋናው ውል አካል ወይም ተያያዥ የሆኑ ሰነዶች

16.1. የአፓርትመንት ቤቱን የወለል ፕላን፣ንድፍና ሌሎች ተጓዳኝ መግለጫዎች

16.2. የቦታው የይዞታ ማረጋገጫ (ካርታ)

7
16.3. በሻጭ ካሚሎስ ሪልስቴት አስተዳደር ክፍል እና/ወይም በሚቋቋመው የቤት ባለንብረቶች ማህበር የሚወጡ ህገ
ደንብና መተዳደሪያዎች የዚህ ውል አካል ናቸው፣ በዚህ ረገድ ይህን ውልም የማስፈጸም መብትና ግዴታ ተሰጥቷቸዋል።

የሻጭ ወኪሎች
ስምና ፊርማ

እኛ የሻጭ ኩባንያ ስራ አስኪያጅ እና የሽያጭ ወኪል ድርጅት ስራ አስኪሂጅ የሆነው ይህንን የሽያጭ ውል ለመፈራረም
ስልጣን ያለን መሆኑን አረጋግጠን ሻጭን በመወከል ፈርመናል፡፡

1. የሥራ አስኪያጅ ሥም_______________________ ፊርማ__________________

2. የሽያጭ ወኪል ስራ አስኪሂያጅ ሥም ______________________ ፊርማ____________________

የገዥ ስምና ፊርማ

እኔ ገዥ/የገዥ ህጋዊ ወኪል/ ከዚህ ውል ጋር በተያያዘው መታወቂያ/ህጋዊ ውክልና/ መሰረት ገዢ/የገዥ ተወካይ/ መሆኔን
አረጋግጬ ፈርሜያለሁ፡፡

ሥም________________________________ ፊርማ______________________
የምስክሮች ፊርማ

እኛ ምስክሮች ይህ ውል በተዋዋይ ወገኖች መካከል ያለምንም ተፅእኖ በተዋዋይ ወገኖች ሙሉ ፍላጎትና ፍቃድ ሲፈረም
መመልከታችንን በፊርማችን እናረጋግጣለን፡፡

ስም አድራሻ ፊርማ ስ.ቁ

1. _____________________ክ/ከ_____ ወረዳ____ የቤ/ቁጥር____ ________ _______

2. _____________________ክ/ከ_____ ወረዳ____ የቤ/ቁጥር____ _______ _______

You might also like