!

You might also like

Download as doc, pdf, or txt
Download as doc, pdf, or txt
You are on page 1of 5

ቢዝነስ ፕላን 1

የህንጻ መሳሪያ መሸጫ ሱቅ አዋጭነት አጭር ጥናት!

 መግቢያ
መዲናችን አዲስ አበባ በተለይም ከጥቂት ዓመታት ወዲህ በበርካታ ግንባታዎች የምትታወቅ

ከተማ ሆናለች፡፡ በመንግስት ብሎም በግል ባለሀብቶች በርካታ አዳዲስ ግንባታወች እየተከናወኑ

ይገኛሉ፡፡ በከተማው መሀል ካሉ የመንግስትና የግለሰብ ግንባታዎች ባሻገርም ከከተማ ወጣ

ብሎ በሚገኙ ስፍራዎችም የተለያዩ ሪልስቴቶች እና የግለሰብ መኖሪያ ቤቶች እንደዚሁም

ኮንዶሚኒየም ቤቶች እየተገነቡ ይገኛሉ፡፡ በተለይ ለግለሰቦች ከመንግስት የሚሰጡ

ኮንዶሚኒየም ቤቶች ግንባታቸው ሳይጠናቀቁ ለእድለኞች የሚተላለፉ በመሆናቸው ግለሰቦች

እጣው ከደረሳቸው ብኋላ የፊኒሽንግ ስራ ለመስራት ስለሚገደዱ በዋናነት በአካባቢያቸው

ከሚያስፈልጋቸው ግብአቶች አንዱና ዋነኛው የተለያዩ የግንባታ እቃዎች እና የፊኒሽንግ

ግብአቶች ናቸው፡፡ በመሆኑም በተለይ ከከተማ ወጣ ብለው በሚገኙ ኮንዶሚኒየም ያሉባቸው

አካባቢዎች የህንጻ መሳሪያ መክፈት አዋጭ የቢዝነስ ስራ ነው፡፡ በተለይ የትራንስፖርት

አገልግሎቱ የተዘጋጋና ውድ በሆነባት አዲስ አበባ መሀል ከተማ በመምጣትና እንደ መርካቶ ባሉ

ገበያዎች በመሄድ የህንጻ መሳሪያ መግዛት ተመራጭ ስለማይሆን ሰዎች ባካባቢያቸው

ወደሚገኙ የህንጻ መሳሪያ በመሄድ ግአቶችን መግዛት ተመራጭ በማድረጋቸው ይህ ቢዝነስ

አዋጭ እንዲሆን እና የማይቋረጥ ገበያ እንዲኖረው አድርጎታል፡፡

ለህንጻ መሳሪያው ጠበብ ያለ ሱቅ የሚያስፈልገው ሲሆን ግበአቶቹ ለረጅም ጊዜ ሳይበላሹ

መቆየታቸው ቢዝነሱ ለኪሳራ እንዳይጋለጥ ያደርገዋል፡፡ ይህ የቢዝነስ አማራጭ አዋጭ

መሆኑን መርካቶ ከሚገኙ አከፋፋዮች፣ የህንጻ መሳሪያ ሱቅ ከፍተው ከሚሰሩ ነጋዴዎች

እንዲሁም የፊኒሽንግ ስራ ላይ ተሰማርተው ከሚሰሩ አካላት ዳሰሳ ለማድረግ የሞከርን ሲሆን

እኛም በምንኖርበት የኮንዶሚኒየም ቤት አካባቢ ያለውን ተፈላጊነት ማየት ችለናል፡፡

የሚታደሱና የፊኒሽንግ ስራ የሚሰሩላቸው ቤቶች በርካታ ከመሆናቸው አንጻር ፍላጎቱ


ቢኖርም ያሉት የህንጻ መሳሪያ ሱቆች እራቅ ያሉ ሰፈሮች በመሆናቸው ገዥዎች የትንሽ

ርቀትም ቢሆን ትራንስፖርት እንዲጠቀሙ ሲገደዱ ይስተዋላል፡፡ በመሆኑም እዚሁ

የምንኖርበት አካባቢ ይህን አይነት ቢዝነስ ከፍቶ የሚሰራ ባለመኖሩ ይህን ቢዝነስ ከፍተን

ብንሰራ ካለው የገበያ ፍላጎት አንጻር አዋጭ ይሆናል፡፡

ከዚህም በተጨማሪ ቢዝነሱን በብዛት ግንባታ በሚከናወንባቸው ስፍራዎች መክፈት አዋጭ

ነው፡፡ በብዛት የኮንስትራክሽን ስራ የሚከናወንባቸው ቦታዎች በርካታ ሲሆኑ ከማሀል ከተማ

ወጣ ብለው የሚገኙ ግንባታ በስፋት ያለባቸው ቦታወች እና የሪሊስቴት ግንባታ ያለባቸው

እንዲሁም የግል ቪላ መኖሪያ ቤት የሚገኙባቸው አካባቢዎች ለቢዝነሱ ተመራጭ ናቸው፡፡

 የቢዝነሱ አላማ

 የተሻለ ገቢ ማግኘትና ትርፋማ መሆን

 ወጣቶች የስራ እድል መፍጠር

 ከቢዝነሱ የሚያስገኘው ገቢ በአማካይ

ይህ የቢዝነስ አይነት የእለት ገቢ ቢኖረውም ትርፍና ኪሳራ የሚሰላው በየወሩ ነው፡፡ በዚህም መሰረት ባደረግነው ዳሰሳ

በአማካይ በወር እስከ 50.000 (ሀምሳ ሽህ) ብር ትርፍ እንደሚገኝበት ነው፡፡

 ቢዝነሱን ለመጀመር መሟላት ያለባቸው ህጋዊ መስፈርቶች

 ንግድ ፍቃድ ማውጣት፣


 የተሻለ ገበያ ያለበትን ቦታ በመምረጥ ሱቅ መከራየት እና ለፍቃድ ሰጭዎች ማስመዝገብ፡፡

 ቢዝነሱን ለመጀመር የሚያስፈልጉ ጉዳዮች

 ከመርካቶና ከተለያዩ አከፋፋዮች የህንጻ መሳሪያዎችን መረከብ፡፡ ለምሳሌ ሲሚንቶ ከአምራቾች በቀጥታ

መረከብ፡፡ ብረትና ፓይፖችም ከዋና አከፋፋዮች በተመጣጣኝ ዋጋ መረከብ፡፡ ሌሎች ቀለምን ጨምሮ

አስፈላጊ ግብአቶችን ከመርካቶ አከፋፋዮች ተረክቦ ወደ ሱቅ ማስገባት፡፡

 አንድ የጉልበት እና አንድ የሽያጭ ሰራተኛ መቅጠር፡፡

 ግብአቶቹን በቋሚነት ለማመላለስ የጭነት መኪና ደንበኛ ማነጋገርና መያዝ፡፡

 ቢዝነሱን ለመጀመር የሚያስፈልጉ ወጭዎች

 ወርሀዊ የሱቅ ኪራይ በአማካይ ከ 10.000 እስከ 15.000 ብር፡፡

 የሰራተኛ ደመወዝ በወር 6000 ብር

 የትራንስፖርት ወርሀዊ ወጭ በሳምንት አንዴ ለማመላለስ 4000 ብር

 ቢዝነሱን ለመጀመር የሚያስፈልገው ካፒታል

ቢዝነሱን ለመጀመር እንደ ሲሚንቶ፣ ብረት፣ ፓይፕ፣ ጂብሰም፣ ቀለምና ሌሎችን የህን መሳሪያዎችን እና የፊኒሽንግ

ማቴሪያሎችን ለማሟላት የሚያስፈልገውን ካፒታል በሁለት ከፍለን እንመለከታለን፡፡

አማራጭ አንድ፡- አነስ ያለ የህንጻ መሳሪያ ሱቅ ለመክፈት ባደረግነው ዳሰሳ መሰረት እስከ 1.5 ሚሊዮን የሚወስድ

ይሆናል፡፡

አማራጭ ሁለት፡- መካከለኛ የህንጻ መሳሪያ ሱቅ ለመክፈት ከ 2 እስከ 2.5 ሚሊዮን ብር የሚወስድ ይሆናል፡፡
 ማጠቃለያ

You might also like