Download as docx, pdf, or txt
Download as docx, pdf, or txt
You are on page 1of 13

የአጋእዝተ ዓለም ቅድስት ሥላሴ መዝሙራት

1:እንዘ ይብሉ

እንዘ ይብሉ ይዜምሩ በልሳን ዘኢያረምም፤

መንግሥተ ሥላሴ ዘለዓለም /2/።

ትርጉም:_ዝም በማይል እና በማያቋርጥ አንደበት የሥላሴ መንግሥት ዘላለማዊት


ናት እያሉ ይዘምራሉ ፤ ያመሰግናሉ።

2:ኃይልየ ሥላሴ

ኃይልየ ሥላሴ ወጸወንየ ሥላሴ፤

በስመ ሥላሴ /2/ እቀጠቅጥ ከይሴ/2/።

ትርጉም :- ኃይሌም መጠጊያዬም ሥላሴ ነው ፤ በሥላሴ ስም ከይሲ


/እባብን/ዲያብሎስን እቀጠቅጣለሁ።

3:ይረድአነ

ይረድአነ አምላክነ /2/ ወመድኃኒነ፤

አምላክነሰ አምላከ አድኅኖ ስብሐት ለአብ ስብሐት ለወልድ ስብሐት ለመንፈስ


ቅዱስ።

ትርጉም :-ይረዳናል አምላካችን /2/ መድኃኒታችን፤

አምላካችን የምሕረት አምላክ ነው ምስጋና ለአብ ምስጋና ለወልድ ምስጋና


ለመንፈስቅዱስ።

4:ወፅአ (ዘሐምሌ)

ወፅአ እምድረ ካራን ወቦአ ብሔረ ከነዓን

ተአመነ አብርሃም /2/ በእግዚአብሔር

5:(ዓዲ)

ወፅአ አብርሃም እምድረ ካራን፤


ወቦአ ብሔረ ከነዓን (2) አብርሃም እምድረ ካራን።

ትርጉም:-ከካራን ምድር ወጣ ወደ ከነአንም ገባ አብርሃም በእግዚአብሔር ታመነ።

6:ነአምን

ነአምን በአብ ወነአምን በወልድ/2/፤

ወነአምን /4/ ነአምን በመንፈስ ቅዱስ።

ትርጉም:- እናምናለን በአብ እናምናለን በወልድ/2/፣

እናምናለን /5/ በመንፈስቅዱስ።

7:ኵሎ ዘፈቀደ

ኵሎ ዘፈቀደ ገብረ እግዚአብሔር፤

በሰማይኒ ወበምድርኒ ወበባሕርኒ ወበኵሎ ቀላያት/4/።

ትርጉም :- እግዚአብሔር የፈቀደውን እና የወደደውን ሁሉ በሰማይ በምድር እና


በባሕር እንዲሁም ከውሃ በታች በጥልቁ ውስጥ ሠራ ።

8:ሥላሴ ትትረመም

ሥላሴ ትትረመም ወትትነከር፤

ሥላሴ ትትረመም ወትትነከር/2/።

ትርጉም :-ምሥጢረ ሥላሴን ከማድነቅ ወይም ዝም ከማለት በቀር የማይመረመር


ነው።

9.በስመ አብ ወወልድ

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ፤

ኃይለ መስቀሉ እትመረጐዝ /2/።

ትርጉም :-በአብ እና በወልድ በመንፈስቅዱስ ስም የመስቀሉን ኃይል እመረኮዛለሁ።

10፡የእግዚአብሔር አብ ሰላም
የእግዚአብሔር አብ ሰላም የእግዚአብሔር ወልድ ፍቅር የእግዚአብሔር መንፈስ
ቅዱስ ሃይማኖት ይደርባችሁ፤

የሰላም አምላክ /2/ አይለያችሁ።

11፡ስብሐት ለሥላሴ

ስብሐት ለሥላሴ ለፈጣሬ ኵሉ ዓለም፤

በመላእክቲሁ ስቡሕ (እኩት) ዘለዓለም/2/።

ትርጉም :_ምስጋና ለሥላሴ ለዓለሙ ሁሉ ፈጣሪ፤

በመላእክቱ ነውና ሲመሰገን ኗሪ /2/።

12፡ጸግዉኒ

ጸግዉኒ አጋእዝትየ ንዋየ ገጽ ትፍሥሕተ፤

ወዲበ አሠርቱ አህጉር ሀቡኒ ሢመተ (2)።

ትርጉም ፦ሥሉስ ቅዱስ ሆይ ከባሕርየ ገጽታችሁ ደስ የሚያሰኝ ፈገግታ


የተመላበትን ንዋየ ገጽ ስጡኝ፤ ለቅዱሳንም በተዘጋጁ በአሥሩ አህጉር ላይም
ሥልጣን ሰጥታችሁ ሹሙኝ።(መልክዐ ሥላሴ)

13፦ወበዐይኑ

ወበዐይኑ ይኔጽር፤
ይኔጽር ቀላያተ፡፡
ትርጉም፦በኪሩቤል ጀርባ ላይ ጸንቶ የሚኖር ውቂያኖሶችንም በዐይኑ የሚመለከት
ነውና ፍጥረት ሁሉ ለሥላሴ ይሰግዳል፡፡

14፦አጋእዝትየ

አጋእዝትየ (4)

ሀቡኒ ሢመተ(4)አጋእዝትየ ሀቡኒ ሲመተ

ትርጉም ፦ነጻ የምታወጡኝ ቅድስት ሥላሴ ሹመትን ስጡኝ(ጸግውኒ ወረቡን


ተመልከት)
የሥላሴ መንበር

የሥላሴን መንበር ቅዱሳን ከበውት

ኪሩቤል በደመና ዙፋኑን ይዘውት

ድንግልን ከመሐል ሚካኤልን ከፊት

አዕላፍ መላእክት ሲሰግዱ በፍርሃት

እዩት ተመልከቱት የሰማዩን ድምቀት

እዩት ተመልከቱት የሰማዩን አባት

የሥላሴን መንበር ቅዱሳን ከበውት

እያሸበሸቡ የሰማይ መላእክት

ካህናተ ሰማይ ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ ሲሉ

ይህን ታላቅ ክብር ሊያዩ የታደሉ

በጽድቅ ሥራቸው ደምቀው ይታያሉ /2/

አዝ...

የቅዱሳን ኅብረት የቅዱሳን ሀገር

ሲያወድስ ይኖራል የሥላሴን ክብር

ፍቅርና ርኅራኄ የተሞላ ሰማይ

እግዚአብሔር ያድለን በትንሣኤ እንድናይ/ 2/

ዘማሪ፦ ሊቀ መዘምራን ይልማ ኃይሉ


ሥላሴን አመስግኑ

ሥላሴን አመስግኑ( 2)

የምድር ፍጥረታት ዘምሩ እልል በሉ

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ

ምስጋና ይገባል ከምንም በፊት

ዓለማትን ሁሉ ለፈጠረ ጌታ

ምስጋና ይገባል ጠዋትና ማታ

ኪሩቤል ሱራፌል የሚያመሰግኑት

መላእክት በሰማይ የሚዘምሩለት

እኛም የአዳም ልጆች እንዘምራለን

በሰማይም በምድር እንጠራሃለን

ብራብ በሥላሴ እጠግባለሁኝ

ብጠማም በአምላኬ እረካለሁኝ

ሥላሴ አምባዬ ክብሬ ናቸውና

ሁሌ ይመሩኛል በሕይወት ጎዳና

ዘማሪ፦ ቀሲስ ምንዳዬ ብርሃኑ

እኔስ እዘምራለሁ
እኔስ እዘምራለሁ ለሥላሴ/ 2/

ፈጥሮኛል እና በሥጋ በነፍሴ

እኔስ እዘምራለሁ ለሥላሴ

ሥሉስ ቅዱስ ተብለህ የምትመሰገን

ሰውን ከመከራ ከሞት የምታድን

ነፍሴ ትገዛልህ ትንበርከክልህ

ቅዱስ ፈጣሪዬን አንተን ታምልክህ

በመሓሪነትህ ጠብቀህ ያኖርከኝ

በማዳን ችሎታህ ለዚህ ያደረስከኝ

ለአንተ ለአምላኬ ምስጋና አቀርባለሁ

ስምህን ለዘለዓለም ሁሌም እጠራለሁ

አብርሃም ለአምላኩ በቀና ቢታዘዝ

ሥላሴ ገቡና ቤቱን ባረኩለት

ሣራንም ጎበኟት በእርጅናዋ ጊዜ

ይሥሐቅን ሰጧት ዘለዓለም ሥላሴ

ዘማሪ፦ ቀሲስ ምንዳዬ ብርሃኑ

ኃይሌ ብርታቴ
ኃይሌ ብርታቴ ክብሬ ሞገሴ(2)

የዘለዓለሙ ለአብርሃሙ ሥላሴ(2)

ተመረጠች ነፍሴ አንተን ለማወደስ

ከላይ ከአርያም ከሥላሴ መቅደስ

በአንድነት ሦስትነት በዙፋኑ ሞልቶ

የሚሳነው የለም ለሥላሴ ከቶ

ከመንገድ ዳር ልቁም የወደቀ ላንሳ

የተራበ ላብላ የታመመ አልርሳ

እንደ አብርሃም አድርገኝ እንደ ደጉ አባት

ቤቴ እንዲሞላ በአንተ በረከት

ጠፈሩን በውኃ በጥበብ የሠራ

እኔስ ይገርመኛል የሥላሴ ሥራ

ኑ እና ተመልከቱ ተአምራት ሲሠራ

ሰዎች እልል በሉ ወላድ ሆነች ሣራ

አብ አንድያ ልጁን እስኪሰጥ ወዶናል

ወልድም በተዋሕዶ እኛኑ መስሎናል

ኃይሉ ተገለጠ የመንፈስ ቅዱስ

በቅዱሳን አድሮ ሲያድን ሲፈውስ


ዘማሪ፦ ጸሐፌ ትእዛዝ ታዴዎስ ግርማ

ይለመነናል

ይለመነናል አምላከ አብርሃም

ይታደገናል መድኃኔዓለም (2)

ለፍጥረት ሁሉ እጁን የዘረጋ

ቸር እረኛ ነው አልፋ እና ኦሜጋ (2)

አብርሃም ይሥሐቅን ያዕቆብን አስበህ

የማልክላቸውን ቃል ኪዳን አስታውሰህ

ደካማ ለሆንነው ሥጋ ሠልጥኖብን

አትመልስ ጌታ የምሕረት ዐይንህን

ከሰማየ ሰማይ ይድረስ ጩኸታችን

እንዘን እናልቅስ ስለበደላችን(2)

ባይመለከተን አምላከ አብርሃም

በምሕረት ዐይኖቹ መድኃኔዓለም

ባይዘረጋልን አምላከ አብርሃም

የፍቅር እጆቹ መድኃኔዓለም

ሕዝበ እግዚአብሔር ሁሉ ለአምላክ ዘምሩ


አድኖናል እና በሚያስደንቅ ፍቅሩ(2)

ምንም እንኳን ክህደት ቅጥፈት ቢበረታ

ስለ አብርሃም ብለህ አልተውከንም ጌታ

ለቅዱሳን ያለህ ቃል ኪዳን ሲጸና

ቀስተ ደመናህን ዐይተነዋልና

የእስራኤል አምላክ የማታንቀላፋ

በፍቅርህ ታደገን በሞት ሳንጠፋ(2)

ቃል ኪዳንህ ግሩም አምላከ አብርሃም

ምሕረትህ የበዛ መድኃኔዓለም

ርስት ጉልታችን አምላከ አብርሃም

የሕይወታችን ቤዛ መድኃኔዓለም

ሳይጸየፍ ጌታ ያደፈ ኃጢአቴን

ከማጥ ውስጥ አወጣኝ ታደጋት ሕይወቴን (2)

ዘማሪ፦ ጸሐፌ ትእዛዝ ታዴዎስ ግርማ

የምስጋና መሥዋዕት

የምስጋና መሥዋዕት ማሕሌት ውዳሴ

ይገባል ለክብሩ ለቅድስት ሥላሴ


ሰውን የፈጠረ በአምሳሉ ሠርቶ

ሥጋን ያዘጋጀ አጥንትን ሰክቶ

ውብ አድርጎ ፈጠረን በከሀሊነቱ

እንዘምራለን ስለ ጌትነቱ(2)

ሰማይን የሠራ በታላቅ ጥበቡ

ምድርን ያዘጋጀ በቅዱስ ሐሳቡ

ይመለካል ዘወትር እርሱ በፍጥረቱ

ሰላም የመላ ነው ዘለዓለም መንግሥቱ(2)

ዐይኖች የመላ ነው ኪሩቤል መንበሩ

ጽንሐን ጨብጠዋል ሱራፌል ለክብሩ

በዕጣን ጢስ ሲመላ አስፈሪው እልፍኙ

መላእክት ዘመሩ ቅኔ እየተቀኙ(2)

እሳት አዳራሹ ውሃ ነው ጠፈሩ

ምድር መረገጫው ሰማይ ነው መንበሩ

ሲወደስ ይኖራል በሰማይ መዝሙር

ይገባል ለክብሩ ውዳሴ እና ክብር

በመምሬ አድባር ሥር (ሐምሌ 7)


በመምሬ አድባር ሥር አብርሃም ያገኘው

የሥላሴ ጸጋ ልዩ በረከት ነው

ልግስናው እና ቅንነቱን አይተው

ሥላሴ ባረኩት ከቤቱ ተገኝተው

ሥላሴ በአካል በሦስትነታቸው

አብርሃምን ቃኙት በፍቅር ተገኝተው

በአምሳለ እንግዳ ተገኝተው ከቤቱ

በረከትን ሰጡት ጣፈጠ ሕይወቱ

ፍቅር እና ርኅራኄ አብርሃም ስላለው

በግሩም ሕይወቱ ሥላሴን ጠራቸው

ደሀን በመውደዱ ሰይጣን ቢቀናበት

ከቤቱ ተገኝተው ሥላሴ ባረኩት

ለቅድስት ሥላሴ ድንኳን ቢያንስባቸው

የአብርሃም ደግነት እንግዳ አረጋቸው

የደግነት ፍሬ የመጨረሻው

የሥላሴ ወዳጅ ቅሩብ መሆን ነው

ሰይጣንን ድል ነስቶ ጽድቅን የናፈቀ


ፍጻሜው እንዲያምር በአብርሃም ታወቀ

ምስጋና አምልኮ ስግደት

ምስጋና አምልኮ ስግደት ውዳሴ

ይገባል በሉ ሰዎች ለቅድስት ሥላሴ

ዘለዓለም ዓለም ቅዱስ ነህ

አምሳያ ወደር የሌለህ

መተማመኛ ሆነኸኛል

ሥላሴ በአንተ ደስ ይለኛል

የታመነ ነው የተፈራ

የጽድቅን ፀሐይ የሚያበራ

ዓለሙ ጸንቷል በሥላሴ

ትዘምርለት ለእርሱ ነፍሴ

ዘመናት በእጁ በመዳፉ

ሁሌም የእርሱ ነው ድሉ ሰልፉ

የእሳት መድረኮች ያሉት ጌታ

የማያልፍ ነው የማይረታ
አብርሃም አምኖ ተሰደደ

በእርጅናው ወራት ልጅ ወለደ

የተስፋውን ቃል ፈጸመለት

ሥላሴ በሉ በቀን በሌሊት

ዘማሪት ጸዳለ ጎበዜ

You might also like