Download as docx, pdf, or txt
Download as docx, pdf, or txt
You are on page 1of 6

መግቢያ

የኢትዮጵያ መንግሰት ግብርና መር የእድገት አቅጣጫ ቀይሶ በግብርናው ዘርፍ እድገት ለማስመዝገብ ያላሳለሰ ጥረት
እያደረገ ነው፡፡ በተለይ ዘርፉን ውጤታማ ለማድረግ ምርትና ምርታነማነትን ለማሳደግ የመስኖ ልማትን በአገርአቀፍ
ደረጃ ለማጎልበት የተለያዩ እንቅስቃሴዎች እየተደረገ መሆኑ የሚታወቅ ነው፡፡ የአዲስ አበባ ከተማ መስተዳደር ከዚሁ
ከአገሪቱ ራዕይ በመጋራት የከተማ ግብርና እንቅስቃሴዎችን በማከናወን ላይ ነው፡፡ ከነዚህ የግብርና ኤክስቴንሽን
አገልግሎቶች ውሰጥ አንዱ በአነስተኛ ቦታ ምረታማነታቸው ከፍ ያለና የገበያ አማራጫቸው ሰፋ ያሉ የእፅዋት
ምርቶችን በማምረት አነስተኛ ገቢ ያላቸውን የከተማውን ነዋሪዎችን በዘርፉ በማሰማራት የገቢ አማረጭ ለመፍጠርና
የከተማውን የአትክልትና ፈረፍሬ ፍላጎት በቅርብ ለማሟላት የሚደረግ ጥረት ነው፡፡ ይህም ጥረት ውጤታማ እንዲሆን
የመስኖ ልማት የሚያደርገው አስተዋፅዖ አሌ የማይባል ነው፡፡ በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ የአርሶአዳርና ከተማ
ግብርና ጽ/ቤት በእጽዋት ቡድን የመስኖ አግሮኖሚ ዘርፍ የሚገኘው በመስኖ የሚለሙ የሥራ እንቅስቃሴዎችን
በመከታተል ለተገልጋዩ የሙያና የቴክኒክ ድጋፍ እንዲሁም የአትክልት ዘር ግብዓትን በማቅረብ በሙያው
የሚደረገውን እንቀቅስቃሴ በመደገፍ ላይ ይገኛል፡፡ የመስኖ ልማቱን በሳይሳዊ መንገድ ለማስኬድ ይህንን
አስመልክቶ ትምህርታዊ ጽሁፍ ማዘጋጀት አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ ከዚህ ቀጥሎ አነስተኛ መስኖ ልማት በሚል
መነሻ ሃሳብ ጽሑፉን ለማዘጋጀት ተሞክሯል፡፡ ስለዚህ ይህንን ትምህርታዊ ጽሑፍ መነሻ በማድረግና ሌሎች
ወቅታዊ ኢነፎረሜሽኖችን በመጠቀም አነስተኛ የመስኖ ልማት በማስፋፋት የክፍለ ከተማውን ና የከተማውን
የከተማ ግብርና ራዕይና ተልዕኮ ከግብ ለማድረስ ሁላችንም በአንድነት እንድንነሳ በማስገንዘብ ወደ ዝርዝር ጉዳዩ
እንገባለን፡፡

አነስተኛ የመስኖ ልማት


 ትርጉም
መስኖ የሚለው ቃል በተለያዩ ፀሓፊያን የተለያ ትርጉም የተሰጠው ሲሆን ለዚህ ፅሑፍ ይስማማል
የሚለውን ትርጉም የሚከተለው ነው፡፡ መስኖ ማለት ውሃን ከተፈጥሮ ዝናብ ውጪ ለተክል በማጠጣት
የምግብ ሰብልን ማለትም አዝዕርት፣ አትክልትና ፍራርሬ እንዲሁም የመኖ ዘርን ለእንስሳት ምግብነትና
የተለያዩ አካባቢን የሚያሳምሩና የሚጠብቁ ተክሎችን ማምረት ና ማልማት ማለታችን ነው፡፡

 የመስኖ አስፈላጊነት
 ውሃ ለተክል አስፈላጊ ከሆኑ ነገሮች ዋናው ነው፡፡ የተክሉን የውሃ ፍላጎት ለማሟላት በቂ ዝናብ
ባለባቸው አካባቢዎች የተፈጥሮ ዝናብ በመጠቀም የሚሟላ ሲሆን ዝናብ አጠር አካባቢዎች
የተፈጥሮ ዝናብ ተክሉ ለምርተ እስኪበቃ በቂ ስለማይሆን ተጨማሪ የውሃ ምንጭ አስፈላጊ ነው፡፡
ለዚህም ችግር አይነተኛ አማራጭ መስኖ መጠቀም ይሆናል፤
 ሙሉ ለሙሉ ዝናብ አጠር አካባቢዎች የመስኖ ቴክኖሎጂ መጠቀም አማራጭ የሌለው መፍትሄ ነው፤
 ወጥ የሆነ የዝናብ ስርጭት የሌለባቸው አካባቢዎችም መስኖ በተጨማሪ መጠቀም የኖርባቸዋል፤
 በማደግ ላይ ያለውን የሕዝብ ብዛት የምግብ ፍላጎት ለማሟላት በቂ ዝናብ የሚያገኙ አካባቢዎችም
የመስኖ አማራጭ በመጠቀም ጥረት ሲያደርጉ ይታያል በዚህም ጥረት ውጤታማ ለመሆን ችለዋል፤
 ለገበያ የሚውሉ ሰብሎችንም በመስኖ ማልማት ከምርት ማደግ ና ከጥራት አኳያ ተወዳዳሪ የለውም፤
 በአመት ሁለትና ሦሥት ጊዜ በማምረት ምርትና ምርታማነትን ለማሰደግ በመስኖ መጠቀም
አስፈላጊ ነው፤
 ውድ የሆነውን የውሃ ሀብታችንን በአግባቡ ለመጠቀምና ለመቆጣጠር መስኖ መጠቀም ታላቅ
ጠቀሜታ አለው፡፡

 ታሪካዊ አመጣጡ
የሰው ልጅ በመስኖ በመጠቀም የልማት ስራ ከጀመረ ብዙ ሺ ዓመታት እንደተቆጠሩ የሚታወቅ ነው፡፡
ለምሳሌ ያህል በጥቂቱ ከዚህ በታች ተዘርዝሯል፡-
 ከ 5000 ዓመታት በፊት ጀምሮ ህንድና የሩቅ ምስራቅ አገሮች ሩዝን በመስኖ ያመርቱ ነበር፤
 ከ 4000 ዓመታት በፊት የአባይ መዳረሻአገሮች ግብፅና ትግሪስና ኤፍራትስ ወንዝ ሜዳማ
ቦታዎች ኢራቅን ጨምሮ መስኖ ይጠቀሙ ነበረ፤
 በአሁኑ ጊዜ ከ 200 ሚሊዮን ሄክታር በላይ መሬት በ 5 አገሮች በመስኖ በመልማት ላይ ይገኛል፤
 በአፍሪካ በ 1952 ዓ.ም 4.2 ሚሊዮን ሄክታር የነበረው የመስኖ ልማት አድጎ ወደ 6.6 ሚሊዮን
ደርሶ ነበር፡፡ ሆኖም በያዝነው አስርት ዓመታት ይህ ቁጥር ከፍ እያለ መምጣቱ አንዳንድ
መረጃዎች ያመላክታሉ፤
 የመስኖ ልማት በኢትዮጵያ ስንምለከት እንደ FAO(1995) በ 1994 መሠረታዊ መረጃ
ኢትዮጵያ በአጠቃላይ 110 ሚሊዮን ሄክታር መሬት አላት፡፡ ከዚህ ውስጥ 13.2 ሚሊዮን (12%
ቱ ከአጠቃላይ መሬት) ሊታረስ ወይም ሊለማ የሚችል ሲሆን 6 ሚለዮን ሄክታር (45%)
ሊታረስ የሚችል መሬት ነው፡፡ ከዚህ ውስጥ 190,000 ሄክታር በመስኖ የለማ ነው፡፡ የመስኖ
ልማት በኢትዮጵያ የቆየ ታሪክ አለው፡፡ አሰራሩም በባህላዊ መንገድ ወንዝ በመጥለፍ ይከናወን
ነበር፡፡ ሰፋፊና ዘመናዊ የመስኖ ልማት እ.ኤ.አ በ 1960 መጀመሪያ ላይ አዋሽ ወንዝን ተከትሎ
በግል ኢንቨስተር የሸንኮራ አገዳ፣ አትክልትና ፍራፍሬ ና የጥጥ ተክልን ለማልመት
ተጀመረ፡፡ እንደ FAO መረጃ አጠቃላይ አነስተኛ መስኖ በኢትዮጵያ 63,581 ሄክታር ሲሆን
በዚህ ተግባር የተሰማሩ ገበሬዎች ቁጥርም 359,000 ነበሩ፡፡ በኢትዮጵያ በመስኖ ይለማል
ተብሎ የሚገመት የመሬት መጠን 1.8 – 3.7 ሚሊዮን ሄክታር ነው፡፡ ሰኔ ወር 2002
በኢትዮጵያ አቆጣጠር ከግብርናና ገጠር ልማት ሚኒሰቴር ህዝብ ግንኙነት በወጣ ዘገባ 1.1
ሚለዮን ሄክታር መሬት በመስኖ የለማ መሆኑን ለማወቅ ተችሏል፡፡

 የመስኖ ልማት ዋናዋና ጥቅሞች


 የምግብ እህል ምርትነ በማሳደግ የምግብ ፍላጎት ለማሟላት፣
 የገበያ ሰብል ና አትክልትን ለማምረት፣
 የቤተሰብን ገቢ ለማሳደግ፣
 የተፈጥሮ ሀብትን ከመጠበቅ ከሚከሰቱ የተፈጥሮ አደጋዎች ለመታደግ፣
 የመሬትን ምርታማነትና ዋጋ ያሳድጋል፣
 የኤሌትሪክ ኃይል ለማመንጨትና መስኖን በጋራ መጠቀም ለማስቻል፣
 የውሃ ፍላጎትን ለቤተሰብ ፣ለቤት እንስሳትና ለኢንደስትሪ ለማሟላት፣
 ለትራንስፖርት አገልግሎት፣
 በመስኖ ቦይ ዳር ዳር የደን ዛፍ ለማልማት፣
 የከርሰ ምድር ውሃ መጠን ለመጨመር፣
 ለእርሻሥራ መስፋፋት፣ ወ.ዘ.ተ ናቸው፡፡
 የመስኖ አማራጮች
1. ሰፋፊ የመስኖ ልማት
2. አነስተኛ የመስኖ ልማት

ሰፋፊ የመስኖ ልማት


- ከፍተኛ የሆነ ኢንቨስትመንት የሚጠይቅ ቢሆንም በርከት ያሉ ሄክታር መሬቶችን
ለማልማት ይረዳል፤
- ከፍተኛ ካፒታልና የተማረ የሰው ኃይል የሚጠይቅ በመሆኑ አብዛኛውን የህብረተሰብ
ክፍል የያዘውን አነስተኛና መለስተኛ የመስኖ ተጠቃሚዎችን ለማቀፍ አያስችልም፤
- በመሆኑም አነስተኛ ይዞታ ያላቸውንናበከተማ ክልል የሚገኙ መሬታቸው ውሱን የሆኑ
የመስኖ ተጠቃሚዎችን ሊጠቀሙበት አያስችልም፤
- በመንግስትና መንግስታዊ ባልሆኑ ድርጅቶች ይህ ዓይነቱ ተሮጀክት በተግባር መዋል
የሚችል ሲሆን ለአገራችንና ለህዘቡ የምግብ ፍላጎት መሟላትነ ኢኮኖሚ ማደግ
የሚያደርገው አስተዋፀዖ ቀላል አይባልም፤

አነስተኛ የመስኖ ልማት


- በቀላሉ በተግባር ሊተገበር የሚችል የመስኖ ልማት ነው፤
- የግንባታ ወጪ በጣም ዝቅተኛ ነው፡፡
- ግንባታውን ለማከናወን በአካባቢ በሚገኝ እውቀት፣ ከአካባቢ ከሚገኝ የግንባታ እቃዎች
ሊሰራ ይችላል ጥገናውም እንዲሁ በቀላሉ ከሚገኝ የአካባቢ እቃዎች ሊከናወን
ይችላል፤
- ሥራውን ለማካሄድ፤ለመቆጣጠርና ለመንከባከብ በአነስተኛ የእውቀት ደረጃና
በአካበቢው ከሚገኝ የሰው ኃይል መከናወን ይችላል፤
- ይህ የመስኖ ልማት የተጠቃሚዎችን በጋራ የመስራት ፍላጎት ያነሳሳል ያጠናክራል፤
- ከዚህ ቀለል ያለ ባህሪው አንፃር አብዛኛውን የህብረተሰብ ክፍል ማሰተፍ ተጠቃሚ
ያደርጋል፡፡

አነስተኛ መስኖ ልማት አብዛኛውን የህብረተሰብ ክፍል ተጠቃሚ ከማድረጉም ባሻገር አነስተኛይዞታ ያላቸው
የገጠርና የከተማ ነዋሪዎች በልማቱ ማሳተፍ ስለሚያስችል የዚህ ፅሑፍ ትኩረት በዚህ ላይ ያመዘነ ይሆናል፡፡

 የመስኖ አይነት
ሁለት የመስኖ አይነቶች አሉ እነርሱም፡-

1. የመሬት ስበት ኃይልን በመጠቀም የእርሻ ማሣ የማጠጣት ዘዴ


2. ከዝቅተኛ ቦታ ውሃን በተለያዩ ዘዴዎች በመሳብ ውሃን የማጠጣት ዘዴ ናቸው፡፡

1. የመሬት ስበት ኃይልን በመጠቀም የእርሻ ማሣ የማጠጣት ዘዴ፡- የመሬት ስበት ኃይልን በመጠቀም
የእርሻ ማሣ የማጠጣት ዘዴ ለመስኖ ተግባር የሚፈለገውና የተገኘው ውሃ ከሚገኝበት የውሃ ከፍታ
ወደ ማሳው በመሬት ስበት ኃይል ውሃውን በማስተላለፍ የእርሻ ማሳን የማጠጣት ዘዴ ነው፡፡
 የመስኖ ዓይነትነ መሰረት በማድርግ በቁጥር አንድ የተጠቀሰውየመስኖ ዓይነት እዲሁ
እነደሚከተለው መክፈል ይቻላል፡፡ እነርሱም፡-
ሀ/ ቋሚ መስኖ
ለ/ ኢነንዴሽን/በጎርፍ ውሃ የእርሻ መሬትን ማርጠብ/

ሀ/ ቋሚ መስኖ፡- ለሰብል የሚያስፈልገው የመስኖ ውሃ በቋሚነት የሰብሉ የእድገት ደረጃ እሰኪጠናቀቅ


በመስኖ ማጠጣት ማለት ሲሆን ለዚህ አገልግሎት የሚውለው የመስኖ ውሃ በከፍተኛ ጎርፍ ወቅት
አንድም በግድብ ወይም ወንዝ በመጥለፍ የተጠራቀመ ውሃሆኖ ለሰብል በሚፈለግበት ጊዜ በመስኖ
መልክ ለማጠጣት የሚያስችል ነው፡፡
- ቋሚ መስኖ እነዲሁ እነደሚከተለው ይከፈላል
o ቀጥታ መስኖ
o ውሃን በማጠራቀም መስኖ
o ሁለቱን የማዋሃድ መስኖ ተብለው ይከፈላሉ፡፡

o ቀጥታ መስኖ፡- በቀጥታ መስኖ ጊዜ በቀጥታ ወንዝን በመጥለፍ የሰብል ማሳን በመስኖ
ማጠጣት ማለታችን ነው፡፡ በዚህ ዘዴ ውሃን ማጠራቀም አስፈላጊ አይደለም፡፡
o ውሃን በማጠራቀም መስኖ፡- ውሃን በማጠራቀም ለመስኖ የመጠቀም ዘዴ ስንል ወንዝን
በመገደብ ውሃውን በማጠራቀም ሰው ሰራሽ ሀይቅ በመስራት የተጠራቀመውን ውሀ በዋና
ቦይ ከተጠራቀመበት ግድብ ውሃውን ወደ ማሳ በመውሰድ ለመስኖ አገልግሎት ማዋል ነው፡፡
o ሁለቱን የማዋሃድ መስኖ፡- ወንዝን በመገደብ ውሃን በማጠራቀም እንዲሁም ከተጠራቀመው
ውሃ በዋና ቦይ የመስኖ ውሃ በመውሰድ ማሳን ከማጠጣት በተጨማሪ ከግድቡ የሚተረፈውን
የወንዝ ውሃ በመጥለፍ በቀጥታ መስኖ ለተጨማሪ የመስኖ አገልግሎት ማዋል ነው፡፡
ለ/ ኢነንዴሽን/በጎርፍ ውሃ የእርሻ መሬትን ማርጠብ/፡- ኢነንዴሽን/በጎርፍ ውሃ የእርሻ መሬትን
ማርጠብ/ ስንል በከፍተኛ ጎርፍ መሬቱ እነዲርስ ከሆነ በኋላ ጎርፉ ከሰብል ዘር ወቅት በፊት
ሲንጠፈጠፍ ያን መሬት በሰብል በመሸፈን ለሰብል ምርት አገልግሎት ስንጠቀም ማለታችን ነው፡፡

2. ከዝቅተኛ ቦታ ውሃን በተለያዩ ዘዴዎች በመሳብ ውሃን የማጠጣት ዘዴ


ከዝቅተኛ ቦታ ውሃን በተለያዩ ዘዴዎች በመሳብ ውሃን የማጠጣት ዘዴን የምንጠቀምበት ጊዜ መቼ
ነው? የሚለውን ጥያቄ ስናነሳ የውሃው ምንጭ ከምናጠጣው ማሳ ዝቅ ብሎ ሲገኝና በመሬት ስበት
ኃይል ውሃውን ወደ ማሳ ማፍሰስ ሳንችል ሰንቀር ነው የሚል መልስ እናገኛለን፡፡ ስለዚህ የመስኖውን
ዓላማ ለማሳካት የግድ በተለያዩ ዘዴዎች የመስኖውን ውሃ ከምንጩ መሳብ አስፈላጊ ይሆናል፡፡
ለዚህም ምሳሌ የሚሆነን የጉድጓድ ውሃ መስኖ ነው፡፡

 የመስኖ ቅድመ ሁኔታዎች፡- ወደ መስኖ ስራ ከመግባታችን በፊት ማየት የሚገባንና በመስኖ ስራው
ላይ የጎላ ተፅዕኖ ሊያሳድሩ የሚችሉ ዋና ዋና ነገሮችን ለይተን ማወቅ ይጠበቅብናል፡፡ እነዚህንም
ከዚህ እንደሚከተለው እንመለከታለን፡-
 የአየር ሁኔታ (የዝናብ መጠን፣የሙቀት መጠን፣የትነት ሁኔታ፣የእርጥበት መጠን)
 የአፈሩ ሁኔታ ( ሸክላ፣ሲልት፣ሎምና አሸዋማ)
 የመሬት አቀማመጥ( ሜዳማ፣ወጣ ገባ፣ተራራማ)
 የውሃ ምንጭ ( መጠን )
 የተክሉ ዓይነት
 የሰው ኃይል ( የተማረ ና የሰው ጉልበት )
 ህጋዊነት ( ህጋዊ ፈቃድ ) የመሳሰሉት ናቸው፡፡

ስለ መስኖ ከላይ ባለው መልኩ ግንዛቤ ከጨበጥን ስለ አነስተኛ መስኖ ዝርዝር ተግባራት ከዚህ በታች ባለው
ዋናና ንዑስ እርዕስ ለመመለከት እንሞክራለን፡፡

1. የአፈርን እርጥበት በመቆጠብ መስኖን መጠቀም


 የጎርፍ ውሃን ማገድ፡- በዘቅዛቀማ ስፍራ በዝናብ ወቅት የሚፈጠረውን የጎርፍ ውሃ አነስተኛ
ማገጃ ደልዳላ ና ወደ ደልዳላነት የሚቀርብ ቦይ በመስራት የጎርፉን ውሃ በማገድ ውሃውን
ወደመሬት እነዲሰርግ በማድረግ በአፈሩ እርጥበት ሰብልን ማምረት መቻል ነው፡፡ ይህ መስኖ
በተጨማሪ አፈርን ከመከላት ለመከላከል ያስችላል፡፡
 በጎርፍ ውሃ እርሻ፡- ከከፍተኛ ቦታ የሚጎርፈውን የጎርፍ ውሃ ወደ ማሳ በመውሰድ ሰብልን
ማምረት መቻል ማለታችን ነው፡፡ ይህ መስኖ ለበረሃማ ና ወንዝ ለሌለባቸው

You might also like