Masino

You might also like

Download as docx, pdf, or txt
Download as docx, pdf, or txt
You are on page 1of 7

የመስኖ ልማት ሞአዊ ሚክር ማኑዋል

1.መግቢያ

በሀገራችን የመስኖ ልማት የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ በግብርናው ዘርፍ ለአምራች የሰው ሀይል የስራ ዕድል ፈጥሮ

ገቢን በማሳደግ ረገድ የጀርባ አጥንት ሲሆን እያደገ ለመጣው የምርት ቅነሳ ስጋት አስተማማኝ መፍትሄ ይሰጣል፡፡

በሀገሪቱ መስኖ ዋነኛ ዘርፍ የሆነና በዘላቂነት የረጅም ጊዜ የምግብ እህል ምርት ዕቅድ ይኖረው ዘንድ ግንዛቤ የተወሰደበት

ሲሆን ውጤታማና ቁጥጥር ያለበት የውሃ ሀብት አጠቃቀምን እውን ያደረጋል፡፡ በአሁኑ ጊዜ አዲሱ አስተሳሰብም በውሃ

ሀብት ማኔጅመንት ማዕቀፍ የመስኖ ውሃ አስተዳደር ተግባራዊ እንዲሆን መሠረት ተጥሏል፡፡

በተጨማሪም የቴክኖሎጂ ፓኬጅ አቅርቦት ከአፈሩ ዓይነትና ከውሃው አቅርቦት የድርጊት መርሀ ግብር ጋር የተገናዘበ

ሲሆን ለአነስተኛ አርሶ አደሮች የሚሰጠው ተቋማዊ የሆነ የገበያ ድጋፍ ለመስኖ ሰብል ልማቱ መጨመር ወሳኝ ነው፡፡

የመስኖ ልማት ኤክስቴንሽን ትግበራ በፍላጎት ላይ የተመሠረተ ሲሆን የውሃ ተጠቃሚዎችን በማሳተፍ፣ የመስኖ ውሃ

ተጠቃሚ ማህበራትን በማጠናከር፣ የግብዓት አቅርቦትን በማሳደግ፣ የምርምር-ኤክስቴንሽን-አርሶ አደር ግንኙነትን

ባካተተ መልኩ ከተቋማት የድጋፍ አገልግሎት ጋር ያለውን ግንኙነት በማስተሳሰር የመስኖ አውታርን ውጤታማ ማድረግ

ያስፈልጋል፡፡ ይህም የሚያመላክተው አሳታፊ በሆነ የመስኖ ልማት ኤክስቴንሽን አቀራረብ ዘዴ የባለአነስተኛ ይዞታ አርሶ

አደሮችን በማሳመን የተሻሻሉ የግብርና ቴክኖሎጂዎችን ተቀብለው በሥራ ላይ እንዲያውሉ ማድረግ ነው፡፡

1.1 .ዓላማ

ይህ ማኑዋል ዓላማው የመስኖ ልማት አገልግሎትን በዘላቂነት ለማሳደግ ተግባራዊ የሚሆኑ መልዕክቶችንና ምክሮችን

በመስኖ ልማት ላይ ለተሰማሩ ተጠቃሚ አርሶ አደሮች በመስጠት፣ አሳታፊ በሆነ መልኩ በመስኖ ውሃ የማልማት

ተጠቃሚነታቸውን ከፍ በማድረግ ምርታማነታቸውን ለማሳደግ እና የተጠቀሚ ማህበረሰቡን ገቢ እንዲጨምር

ለማድረግ እንዲረዳ ነው፡፡


የመስኖ ልማት ሞአዊ ሚክር ማኑዋል

1.2 ተልዕኮ

የተሻሻሉ የግብርና ቴክኖሎጂዎችን ተቀብለው ዘመናዊ የመስኖ ግብርናን ለመተግበር፤ የአካባቢ ጥበቃን

መሰረት ያደረግ የሰብል ልማት አያያዝ በማጠናከር እና በሥራ ላይ እንዲያውሉ በማድረግ ለፍጆታ እና ለገበያ

የሚውሉ ምርቶችን ለማምረት እንዲያስችል የሚረዳ ነው፡፡ በመሆኑም የመስኖ ልማት ተልእኮ፡-

 አካባቢ ጥበቃን መሰረት ያደረገ የመስኖ አጠቃቀም ማለትም ብክለትን እና የአፈር መሸርሸርን

ለማቀነስ፣

 የግብዓት ተጠቃሚነት ቅልጥፍናን፣

 የውሃ

 የጉልበት እና ሀብት አጠቃቀምን ለማሰደግ፤

 በመስኖ አገልግሎት የሚመጡ ስጋቶችን እና ቢዝነስ ኪሳራን ለማቀነስ፡

 ተሳትፎአዊ እና ዘለቄታዊ የመስኖ ልማት ግልጋሎትን ለማጎልበት፡፡

1.3.ግብ

የመስኖ ምርትና ምረታማነትን በማሳደግ የአርሶ አደሩን ማህበራዊና ኢኮኖሚዊ ችግር በዘላቂነት በመፍታት የሃገርን

እድገት ማፋጠን ሲሆን የመስኖ ልማት ኤክስቴንሽን የማስተማር/ ማሰልጠን ጥረት የመጨረሻ ውጤት በመስኖ ግብርና

በሂደት ለሚታዩ ችግሮች መፍትሄ በመፍጠር የአርሶ አደሩን ችግር በራሱ እንዲፈታና አዲስ ችሎታ ወይም ሌሎች የባህሪ

ለውጦችን እንዲፈጥር በማስቻስል ነው፡፡

1.4. የመስኖ ልማት አገልግሎት ጥቅም

የተሻሻሉ የግብርና ቴክኖሎጂዎችን ተቀብለው ዘመናዊ የመስኖ ግብርናን ለመተግበር፤ የአካባቢ ጥበቃን መሰረት ያደረግ

የሰብል ልማት አያያዝ በማጠናከር እና በሥራ ላይ እንዲያውሉ በማድረግ ለፍጆታ እና ለገበያ የሚውሉ ምርቶችን

ለማምረት እንዲያስችል የሚረዳ ነው፡፡

በመሆኑም የመስኖ ልማት ኤክስቴንሽን ጥቅሙ፡-

 — የምርት እድገትን ይጨምራል


የመስኖ ልማት ሞአዊ ሚክር ማኑዋል

 — አካባቢ ጥበቃን መሰረት ያደረገ የመስኖ አጠቃቀም ማለትም ብክለትን እና የአፈር መሸርሸርን ይቀንሳል

 — የግብዓት ተጠቃሚነት ቅልጥፍናን፣ የውሃ ፣የጉልበት እና ሀብት አጠቃቀምን ያሳድጋል

 — በመስኖ አገልግሎት የሚመጡ ስጋቶችን እና ቢዝነስ ኪሳራን ይቀንሳል

 — ተሳትፎአዊ እና ዘለቄታዊ የመስኖ ልማት ግልጋሎትን ያጎለብታል፡፡

2. የመስኖ ቴክኖሎጂ አመራረጥ አገልግሎት እና መሠረታዊ ባህሪያት


የመስኖ ልማት አሰራር ዘዴ የመስኖ ውሃ ተጠቃሚዎችን ማህበርና አነስተኛ የመስኖ ተጠቃሚ አባውራ/እማወራ አርሶ

አደሮች የተሻሻሉ የመስኖ መረጃዎችን በመጠቀም፣ የመስኖ ቴክኖሎጂዎችንና አሰራሮችን በመለማመድ ተግባር ላይ

በማዋል ምርትና ምርታማነታቸውን እንዲያሳድጉ መደገፍ የሚያስችል ውጤታማ የሆነ አሰራር ወይም ዘዴ ነው፡፡

2.1 .የመስኖ ቴክኖሎጂ መረጣ

የመስኖ ቴክኖሎጂ መረጣ የአርሶ አደሩን ነባራዊ ሁኔታዎች እና አካባቢውን ያገናዘበ ሊሆን ይገባል፡፡ በመሆኑም የተወሰኑ

የመስኖ ቴክኖሎጂ ዓይነቶች በሚመረጡበት ጊዜ የአርሶ አደሩን የመተግበር አቅምና ጥንካሬ ባገናዘበ መልኩ ሆኖ

ሁለንተናዊ የአያያዝና የጥገና መስፈርቶችን ማሟላት ይኖርበታል፡፡ ይህን እውን በማድረግ ረገድ ግድፈቶች

ከመፈጠራቸው በፊት ቀድሞ አርሶ አደሮቹን ቀርቦ ማማከር ተገቢ ነው፡፡ የቴክኖሎጂ ምርጫ ለአርሶ አደሮች እና

አካባቢውን በማይጎዳ መልኩ ተስማሚ እንዲሆን የሚከተሉትን መስፈርቶች ግምት ውስጥ ያስገባ መሆን ይኖርበታል፡፡

 የአርሶ አደሩን የመስኖ ቴክኖሎጂ መግዣ ፋይናንስ አቅም ያገናዘበ መሆኑን፣

 አርሶ አደሩ ያወጣውን የኢንቨስትመንት ወጭ የመስኖ ቴክኖሎጂው ሊመልስለት የሚችል መሆኑን፣

 አርሶ አደሩ የሚያለማበት በቂ ማሳ መኖሩ፣

 አርሶ አደሩ የሚያለማቸው የሰብል ዓይነቶች መለየታቸው፣

 ቴክኖሎጂው የሚፈለገውን ያህል የሰው ኃይል/ጉልበት አቅም መኖሩ፣

 የጥገና አገልግሎትና መለዋወጫ ዕቃዎች መገኘት፣

 የቴክኖሎጂዎቹ ዘላቂነት/ለረጅም ጊዜ የሚያገለግል መሆን፣

 ቴክኖሎጂው ሥራ ላይ በሚውልበት ወቅት ያለው አከባቢያዊና ማህበራዊ ገጽታ

2.2. የተሻሻሉ አነስተኛ መስኖ ቴክኖሎጂዎች


የመስኖ ልማት ሞአዊ ሚክር ማኑዋል

አድካሚ ያልሆኑ ቀላልና አነስተኛ የውሃ መውረጃ ቦዮች/ቱቦዎች/መስመሮች፣ በሞተር ፓምፕ የሚሰሩ የውሃ
መሳቢያዎች፣ የመስኖ መሬት መደልደያ ማሽኖች፣ የርጭት መስኖ እና የጠብታ መስኖ በዘመናዊ መቆጣጠሪያ
መሳሪያዎች የሚመሩ ቴክኖሎጂዎች ናቸው፡፡

በሀገራችን ለአነስተኛና ሰፋፊ መስኖ ተጠቃሚ አርሶ አደሮች ተስማሚና የተሻሻሉ የአነስተኛ መስኖ ቴክኖሎጂዎች
የሚከተሉት ናቸው፡፡

 የቧንቧ ማሰራጫ ሲስተም -- (ለገፀ-ምድርና ከርሰ-ምድር መስኖ)፣


 የፔዳል/ትሪድል/ ሮፕና ወሸር እና የሞተር ፓምፕ -- (ውሃ ከመሬት ውስጥ የጠብታ፣ ለማውጣት)፣
 ዝቅተኛ ዋጋ ያላቸው የፕላስቲክ የውሃ ታንከሮች -- (በዝናብ ወቅት ውሃ ለማሰባሰብ)፣
 በመኖሪያ ቤት አካባቢ ውሃ ማከማቻዎች -- (የዝናብ ውሃ ለማሰባሰብ)፣
 ባልዲና በርሚል የመሳሰሉ ቁሳቁሶች፣
 ቦሮቦሮችን በመገደብ SSD (Soil storage dum constructed on Gully)

 በፀሃይ ኃይል የሚሠራ የውሃ መሳቢያ(Solar Pump)


 የውሃ መሄጃ ቆርቆሮን፣ የርጭትና የግፊት ቱቦን መጠቀም፣
 በእጅ የሚነቀነቅ ውሃ መሳቢያ፣
 ባህላዊ እና ዘመናዊ የወንዝ ጠለፋ
 ምንጭ በማጎልበት እና ነባር ምንጭ ጠለፋ
 የውሃ ቦዮችን ከስርገት በመከላከል(Lined) በማድረግ ውሃን በአግባቡ በመጠቀም የሚለማ መሬት በማስፋት
 የቤተሰብ ኩሬ እና የህብረተሰብ ኩሬ በመገንባት የዝናብ ውሃን ማሰባሰብ፤(Family & community pond

2.3 .የአፈር ክለትን መቀነስ የሚችል የመስኖ ውሃ አጠቃቀም

የመስኖ መሬት ውስጥ ከመሬቱ አቀማመጥ እና ከውሃ አጠቃቀም የተነሳ የመስኖ መሬቱ በአፈር ክለት

እንዲጎዳ እና ከአገልግሎት ውጭ ሊሆን ይችላል፡፡ በመሆኑም ተዳፋትነት ባላቸው የመስኖ መሬት ላይ ተገቢው

የአፈር ክለት ማገጃ ዘዴዎችን በመጠቀም እንዲሁም በአፈሩ ላይ አደጋ ሊያደርስ የሚችል የውሃ አጠቃቀም
የመስኖ ልማት ሞአዊ ሚክር ማኑዋል

እንዳይኖር የመስኖ ልማት ኤክስቴንሽን ባለሙያው ምክር ያስፈልጋል፤ ተገልጋዩም ህብረተሰብ መተባበር

ይገባዋል፡፡

2.4.በመስኖ መሬቶች ላይ ከመጠን በላይ የመስኖ ውሃ እንዲተኛ አለማድረግ

የመስኖ ውሃ ተገኘ ተብሎ በተለይ ደግሞ ምንም የተዳፋትነት መጠን በሌለባቸው አካባቢዎች እና አፈሩ ባህሪ

ውሃን ወደታች የማስረግ አቅም በሌላቸው አካባቢ በማጥለቅለቅ እና ከመጠን በላይ የመስኖ ውሃን በማሳ

ውስጥ መጠቀም ውሃው እንዲተኛ ወይም ረግረግ እንዲሆን ያደርጋል፣ እንዲሁም በማሳ ላይ የበቀሉ ሰብሎች

ላይ የተለያዩ በሽታዎች እንዲፈጠሩ መነሻ ይሆናል፡፡ ስለሆነም ተጠቃሚው ህብረተሰብ የመስኖ ልማት

ባለሙያው በሚሰጠው የመስኖ ውሃ አጠቃቀም መመሪያና ተረፈ-መስኖ ውሃ የሚወገድበት የተለያዩ

ማስወገጃ ስራዎች በመገንባት አላስፈላጊ ውሃ ማስወገድ እንዲሁም ከመጠን በላይ ውሃ ማሳ ውስጥ

እንዳይተኛ ጥንቃቄ ማድረግ ይገባዋል፡፡

3.ክትትልና ድጋፍ ማድረግ

የክትትልና ድጋፍ ሥራ ለማካሄድ በመጀመሪያ ደረጃ ቼክሊስትና መጠይቅ ማዘጋጀት፣በተዘጋጀው ቼክሊስትና

መጠይቅ መሰረት አስፈላጊውን ክትትልና ድጋፍ በማድግ የሚታዩ ጠንካራ ጎኖችንና ምርጥ ተሞክሮዎችን

በማበረታታት በድክመትና በክፍተት ለሚለዩት ችግሮች ሙያዊ ድጋፍ/ግብ-መልስ መስጠት


የመስኖ ልማት ሞአዊ ሚክር ማኑዋል

የመስኖ ልማት ውጤታማ የሚሆነው አርሶ አደሩን በማሳተፍ፣ አካባቢያዊ ሁኔታዎችን በማገናዘብና የመስኖ

ግብዓቶች ተደራሽነት መሠረት አድርጎ ተስማሚ ቴክኖሎጂዎችን የማስተዋወቅና የማላመድ ሥራ ሲተገበር

ነው፡፡

ለምሳሌ፡- በክትትልና ድጋፍ ወቅት አርሶ አደሩ ባመላከታቸው

 የመስኖ መሬት ዝግጅት

 የቦይ ጠረጋ

 የመስኖ ችግኝ ዝግጅት

 የመስኖ ውሃ ማጠጫ ዘዴዎች

 መስኖ ሰብል ዘር መረጣ ቴክኒክ

 የመስኖ ማደበሪያ አጠቃቀም

 የመስኖ ሰብል አሰባሰብና ድህረ ምርት አያያዝ

 የውሃ ተጠቃሚዎች ቴክኖሎጂን ተቀብሎ ሥራ ላይ ለማዋል፣

 ለውሃ ተጠቃሚዎች የቴክኒክ ድጋፍ መድረግ

ዕዝል 1. በተመረጡ ሰብሎች የእሴት ሰንሰለት ላይ ያሉ ጠቃሚ አሠራሮች

ሰብል በእሴት ሰንሰለት ስራ ዝርዝር


ቦታ መረጣና ችግኝ ከፍታ፡-

ዝግጅት፣ማሳ ዝተከላ አፈር፡-


ዝርያ መረጣ፡-
የመስኖ ልማት ሞአዊ ሚክር ማኑዋል

ግጅት፣አያያዝ፣ተባይና

መሽታ ወረርሽኝ የዘር መደብ፡- 1.20 x 5 – 10

ቁጥጥር፣ማምረት ሜ
ርቀት እና መዝራት
አያያዝ፡ -ውሃ ማጠጣት

ማረም፣ ከጀርም ነጸ ማድረግ


ከተከላ በፊት፡- መስመር

ማውጣት እና በቅድሚያ ውሃ

ማጠጣት
ውሃ ማጠጣት፡- የሰብሉን

ውሃ ፍላጎት መሠረት

በማድረግ

You might also like