Main Research Edited

You might also like

Download as pdf or txt
Download as pdf or txt
You are on page 1of 40

የጫት ወጪ ንግድ

ሎጅስቲክስና አገልግሎት አሰጣጥ ተግዳሮቶች የዳሰሳ ጥናት

በጉምሩክ ኮሚሽንና በትራንስፖርት ሚኒስቴር ትብብር የተዘጋጀ


አጥኝዎች፡-
1. አቶ ክብሩ ላቀው
2. አቶ ኤርጋና ቡቼ
3. አቶ አዲስ አየለ
4. ወ/ሮ ገነት አብርሃም
5. አቶ ወጋየሁ አዳሙ
6. አቶ መንግስቱ ተፈራ
7. አቶ እንዳሻው ተመስገን
8. አቶ ጌታቸው ምህረት

ጥቅምት/2014 ዓ.ም

አዲስ አበባ

ማውጫ

ርዕስ ገፅ
መግቢያ .....................................................................................................................................................1
1. የጥናቱ ዓላማ .....................................................................................................................................1
2. የጥናቱ አስፈላጊነት .............................................................................................................................2
3. የጥናቱ ወሰን ......................................................................................................................................5
4. የጥናቱ ዘዴ (Methodology) ...............................................................................................................5
5. የጥናቱ አወቃቀር ................................................................................................................................8
ክፍል ሁለት ................................................................................................................................................9
2. የጫት ወጪ ንግድ ነባራዊ ሁኔታ ዳሰሳ ...................................................................................................10
የጫት ምርት፣አቅርቦትና ግብይት ሁኔታ .............................................................................................11
የጫት ወጪ ንግድ የሰነዶች ዳሰሳ .......................................................................................................12
የጫት ወጪ ንግድ የገበያ ሁኔታና የመንግስት ሚና .............................................................................14
የጫት ወጪ ንግድ የሀገር ውስጥ መነሻ ቦታዎችና የመዳረሻ ሀገራት ......................................................15
2.2 የጫት ላኪዎች ሁኔታ ..................................................................................................................16
2.2.1 በማህበር የተደራጁ ላኪዎች ......................................................................................................18
2.2.2 የግለሰብ ጫት ላኪዎች .............................................................................................................19
2.3 የጫት ወጪ ንግድ ሥርዓት ሁኔታ ................................................................................................20
2.3.1 የጫት ወጪ ንግድ ፈቃድ አሰጣጥና እድሳት ..............................................................................22
የባንክ ፈቃድ አሰጣጥና የውጭ ምንዛሪ ግኝት ክትትል .........................................................................23
ኬላ ቁጥጥርና የጉምሩክ ዕቃ አወጣጥ ሥርዓት ...................................................................................24
የሎጅስቲክስ አገልግሎት አሰጣጥ ሁኔታ..............................................................................................25
2.4.1. የኢትዮጵያ አየር መንገድ .........................................................................................................26
የግል አየር መንገድ ............................................................................................................................27
2.4.3 የኢትዮጵያ ፖስታ የጫት ወጪ ንግድ አገልግሎት ........................................................................28
2.4.4 የጫት ሚዛን ልኬት..................................................................................................................29
የጭነት ተሸከርካሪ የውጪ ጫት ጭነት ውልና ክፍያ አፈጻጸም .............................................................30
የመጫኛና የመነሻ ቦታ ......................................................................................................................33
የጫት ላኪዎችና ተቀባዮች ሚና .........................................................................................................34
የጫት ላኪዎች ሚና ..........................................................................................................................35
የተቀባይ ሚና ...................................................................................................................................36
በተቀባይ ሀገር ያሉ የኢትዮጵያ ኤምባሲዎች ሚና ................................................................................37
2.5 የአወዳይ የጫት ንግድ እንቅስቃሴ ................................................................................................38
2.6 የኮንትሮባንድ ጫት የማጓጓዝበት ሁኔታ .......................................................................................39
2.6.1 የወጪ ጫት መተላላፊያ መስመር፣ መውጫ በር ሁኔታ..............................................................40
ክፍል ሦስት ..............................................................................................................................................41
3. የጫት የወጪ ንግድ መረጃ ትንተና.........................................................................................................41
ክፍል አራት ..............................................................................................................................................41
4. ማጠቃሊያና የመፍትሔ ሐሳብ ..............................................................................................................42

የሰንጠረዦችና የግራፎች ዝርዝር


ርዕስ ገፅ
ግራፍ 1፡- በአምስት አመት ወደ ውጪ የተላከ ጫት መጠን ........................................................................22
ሰንጠረዥ 1፡- በአምስት አመት ወደ ውጪ ከተላከ ጫት የተገኘ የውጪ ምንዛሬ በዶላር ...............................23
ግራፍ፡- 2 የግል ላኪዎች ሁኔታ በመዳረሻ ሀገር............................................................................................25
ግራፍ፡- 3 የማህበር ላኪዎች በመዳረሻ ሀገር ...............................................................................................27
ግራፍ፡-4 የጫት ወጪ ንግድ ሌሎች መዳረሻ ሀገራት ..................................................................................29
ሰነጠረዥ 2፡- የጫት ወጪ ንግድ መጠን እና የውጪ ምንዛሬ ግኝት ድርሻ በመዳረሻ ሀገር.............................33
ሰንጠረዥ፡-3 የወጪ ጫት የማጓጓዣ ዓይነት ..............................................................................................34
ግራፍ 5፡ የወጪ ጫት የማጓጓዣ ዓይነት በምስል .........................................................................................35
ቻርት 1፡- ከ2009 እስከ 2013 ዓ.ም ድረስ በኮንትሮባንድ ከሀገር ሲወጣ የተያዘ ጫት ድርሻ በጉምሩክ ቅ/ፅ/ቤቶች
...............................................................................................................................................................36
ሰንጠረዥ 4፡- የ1996 እና 2010 ዓ.ም የጫት ምርት የሚመረትበት መሬት በሄክታር እና ምርቱ በፍጥነት
ያደገባቸው ክልሎች...................................................................................................................................37
ክፍል አንድ

1. መግቢያ

1.1 መግቢያ
ኢትዮጵያ ጫት በብዛት ከሚመረትባቸው ሀገራት መካከል አንዷና በርካታ ዜጎቿ በዚሁ የምርት ስራ ላይ በመሰማራት የኑሮ
መሰረታቸው ያደረጉ ከመሆኑም በተጨማሪ ወደ ውጪ ተልኮ ከፍተኛ የውጪ ምንዛሬ ከሚያስገኙ ዋና ዋና የግብርና የወጪ
ንግድ ምርቶች አንዱ ነው፡፡ ባለፉት ዓመታት ኢትዮጵያ ወደ ውጪ ልካ ከፍተኛ የውጪ ምንዛሬ ካገኘችባቸው የወጪ ምርቶች
መካከል ጫት አንዱ ቢሆንም ካለው ሀገራዊ የምርት አቅምና እና የውጪ ገበያ እድል አንፃር የተገኘው የውጪ ምንዛሬ
የሚፈለገውን ያህል አለመሆኑን መገንዘብ ተችሏል፡፡

ለዚህም ከጫት ምርት እምቅ አቅም፤ የሀገር ውስጥ የጫት ግብይት ስርዓት እና የውጭ ሀገር የጫት ንግድ እድል፤ በዘርፉ ላይ
ተዋናይ የሆኑ አካላት እንዲሁም የጫት ምርት ከምርት አሰባሰብ ጀምሮ እስከ መዳረሻ ቦታው ድረስ ያለው የሎጀስቲክስ
አገልግሎት አሰጣጥ ላይ የሚስተዋሉ ክፍተቶች እና ለዚሁ ምክንያት የሆኑ ተግዳሮቶች በጥናት ላይ ተመስርቶ መፍታት
አስፈላጊ እና ጊዜ የሚሰጠው ጉዳይ አይደለም፡፡ በመሆኑም ከሎጀስቲክስ አገልግሎት አሰጣጥን ጋር በተያያዘ የጫት የወጪ
ንግድ ተግዳሮቶችን አጥንቶ የመፍትሔ ሐሳብ የሚያቀርብ የጥናት ቡድን ተቋቁሟል፡፡

ጫት ፈጣንና የተሳለጠ የሎጀስቲክስ ስርዓት ከሚፈልጉ የወጪ ምርቶች መካከል ዋነኛው በመሆኑ በጫት የወጪ ንግድ ስራ
ላይ የተሰማሩ ላኪዎች ያላቸው የጫት ንግድ እንቅስቃሴ፤ የኢትዮጵያ አየር መንገድና የግል አየር መንገድ ኦፕሬተሮች የወጪ
ጫት በማጓጓዝ ረገድ ያላቸው ሚና፤ የፌደራል፤ ኦሮሚያ ክልል የአወዳይ ከተማ እና የሶማሊ ክልል እንዲሁም የድሬዳዋ ከተማ
አስተዳደር የንግድ ቢሮዎች ዘርፉን ከመደገፍ አንፃር ያላቸው ሚና፤ የጉምሩክ ኮሚሽን የድሬዳዋና የጅግጅጋ የጉምሩክ
ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶችና በስራቸው የሚገኙ መቆጣጠሪያ ጣቢያዎች ከሌሎች የፀጥታ አካላት ጋር በመቀናጀት የጫት የወጪ
ንግድ አስፈላጊው የጉምሩክ አገልግሎት ከመስጠትና በህገ ወጥ መንገድ ከሀገር የሚወጣውን ጫት ከመቆጣጠር አንፃር በጥናቱ
ታይቷል፡፡

በመሆኑም የጫት ወጪ ንግዱ የሎጀስቲክስ አገልግሎት ከማሳለጥ አንፃር በጥናቱ የተዳሰሱ አካላትና ተያያዥ ጉዳዮች
የተስተዋለባቸው ተግዳሮቶች የመፍትሔ ሐሳቦች በዚህ ሰነድ ተካተው ቀርቧል፡፡

1.2 የጥናቱ ዓላማ

በጫት ወጪ ንግድ ሎጀስቲክስ አገልግሎት አሰጣጥና አሰራር ላይ የሚታዩ ችግሮች በጥናት በመለየት የመፍትሄ ሃሳብ
ማቅረብ ነው፡፡

1.3 የጥናቱ አስፈላጊነት

የሀገራችን የወጪ ንግድ በግብርና ምርት ውጤቶች ላይ የተመሰረተ በመሆኑ ከእነዚህ ምርቶች የሚገኝ የውጪ ምንዛሪ መጠን
በሚጠበቀው መልኩ እንዲሆን መንግስት ልዩ ክትትል እያደረገ የሚገኝ መሆኑ ይታወቃል፡፡ ልዩ ክትትል ከሚደረግባቸው
ምርቶች አንዱ የጫት ንግድ ሲሆን ይሄው ወጪ የጫት ንግድ በአሠራርና በቁጥጥር ሥርዓት፣በሎጅስቲክስና በቅንጅት
ሥራዎች ላይ ያሉ ተግዳሮቶች ሳቢያ ባለፉት ጊዜያት ከጫት ምርት የተገኘው የውጪ ምንዛሬ በሚፈለገው ደረጃ እያደገ
ባለመምጣቱ ይህንን ሁኔታ ለማስተካከል ጥናት ማድረግ አስፈልጓል፡፡

1.4 የጥናቱ ወሰን

ይህ ጥናት ትኩረት የሚያደርገው በጫት ወጪ ንግድ በሎጀስቲክስ፣ በአሠራርና አገልግሎት አሰጣጥና በዘርፉ የሚስተዋሉ
ችግሮችን ለይቶ ማውጣትና የመፍትሄ ሐሳብ ማመላከት ላይ ያጠነጥናል፡፡

1.5 የጥናቱ ዘዴ (Methodology)

ጥናቱን ለማካሄድ የጉምሩክ የጫት ወጪ ንግድ መረጃዎችን፣ የንግድ እና ኢንዱስተሪ ሚ/ር የጫት ወጪ ንግድ ሪፖርት፣
ከብሔራዊ ባንክ የጫት የወጪ ንግድን የሚመለከቱ የሰነድ ማስረጃዎችንና ሌሎች ተያያዥ ሰነዶችን በማሰባሰብ እንዲሁም
በክልልና ከተማ መስተዳድር ንግድ ቢሮዎች (በሱማሌ፣ በኦሮሚያ፣ በሐረሪ እና በድሬዳዋ)፣ በጉምሩክ ኬላዎች፣ በመንግስትና
በግል ባንኮች፣ በአየር፣ በየብስና ፖስታ ጥቅል አጓጓዦች፣ በዕቃና በጉምሩክ አስተላላፊዎች፣ በጫት አቅራቢዎች፣ በጫት ላኪ
ማህበራት፣ በጫት ላኪዎች እንዲሁም በኢትዮጵያ ሲቪል አቪየሽን ባለስልጣን ድረስ በአካል በመሄድ የመስክ ምልከታ እና
የአሠራር ስርዓት ቅኝት ተደርጓል፡፡

1.6 የጥናቱ አወቃቀር

ይህ ጥናት በውስጡ 4(አራት) ዋና ዋና ክፍሎች ያሉት ሲሆን በክፍል አንድ የጥናቱ መግቢያ፣ በክፍል 2(ሁለት) የወጪ
ጫት ንግድ አጠቃላይ የነባራዊ ሁኔታ ዳሰሳ፣ በክፍል 3(ሶስት) በወጪ ጫት ንግድ ላይ አጠቃላይ የመረጃ ትንተናና
የወጪ ጫት ንግድን አስመልክቶ የተገኙ ዋና ዋና የጥናት ግኝቶች እንዲሁም በክፍል 4(አራት) የወጪ ጫት ንግድ
የሎጀስቲክስ አሰራሩን ለማሳለጥ የሚያስችሉ ማጠቃለያና የመፍትሄ ሃሳቦች ይቀርባሉ

ክፍል ሁለት
2. የጫት ወጪ ንግድ ነባራዊ ሁኔታ ዳሰሳ
ሀገራችን ከቡና ቀጥሎ የውጪ ምንዛሪ የምታገኝበት የጫት ምርት ቢሆንም ከዘርፉ የሚገኘው የውጪ ምንዛሪ ካለው የጫት
ምርት አንፃር የሚፈለገውን ሆኖ አልተገኘም፡፡ የጫት ምርት ከምርት ቦታው ጀምሮ እስከ መዳረሻ ድረስ ሲጓጓዝ ያለውን
አጠቃላይ ሂደትና የሚስተዋሉ ተግዳሮቶችን ዋና ዋና ከሚባሉ ተዋንያን ማለትም በግለሰብና በማህበር ከተደራጁ ላኪዎች፣
ከኢትዮጵያ ሲቪል አቪየሽን ባለስልጣን፣ ከኢትዮጵያ አየር መንገድና የግል አየር መንገዶች፣ ከኢትዮጵያ ፖስታ አገልግሎት
ድርጅት፣ ከፌዴራልና ከክልል ንግድ ቢሮዎች፣ ከሚመለከታቸው የጉምሩክ ኮሚሽን ቅ/ጽ/ቤቶችና መቆጣጠሪያ ጣቢያዎች
ነባራዊ ሁኔታውን አስመልክቶ የተገኙ ግኝቶች እንደሚከተለው ቀርቧል፡፡

2.1 የጫት ወጪ ንግድ የሰነዶች ዳሰሳ

በኢትዮጵያ የጫት ወጪ ንግድ ረጅም ዘመናትን ያስቆጠረ በመሆኑ በጫት ምርት፣ ግብይትና ወጪ ንግድ ላይ በርካታ ጥናቶች
ተደርገዋል፡፡ በዚህ ጥናት የተወሰኑትን ለመዳሰስ ተሞክሯል፡፡ ባልዋልና ተሾመ በ2011 እ.ኤ.አ በጥናታቸው እንዳሰፈሩት
ጫት በመጀመሪያ ከሀረር የተገኘ ሲሆን በጊዜ ሂደት ደግሞ ወደ ኦሮሚያና ሌሎች ክልሎች የተስፋፋ መሆኑን በጽሑፋቸው ላይ
አመላክተዋል፡፡ በትራስፖርት አማራጭና መሠረተ ልማት እጦት ምክንያት በአገር ውስጥ ብቻ ጥቅም ላይ ይውል የነበረው
የጫት ምርት ቀይ ባህርን የሚያቋርጥ የአየር መንገድ በ1949 እ.አ.አ ሲጀመር የጫት ምርት ከኢትዮጵያ ወደ ኤደን ብቻ ይላክ
እንደነበረ በ2010 እ.አ.አ ፕሮፌሰር ገቢሣ በሳተመው የጥናት ሰነድ ላይ ገልጿል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ ፕሮፌሰር ገቢሣ
ከሁለተኛው ዓለም ጦርነት በኋላ እ.አ.አ በ1954 እና 1961 ዓ.ም. በሀረርጌ ሰፊ የእርሻ መሬት ለጫት ምርት ይውል
እንደነበረና የባቡርና የየብስ ትራንስፖርት መሠረተ ልማት ሲስፋፋ ወደ ጅቡቲና ሶማሊላንድ መላክ እንደተጀመረ አውስቷል፡፡

ጫት በኦሮሚያ ክልል ምስራቅና ምዕራብ ሀረርጌ በስፋት የሚመረት ምርት ሲሆን በአሁኑ ወቅት በሀገራችን የተለየዩ ክልሎች
ለምሳሌ፡- በአማራ፣ በቤንሻንጉል ጉሙዝ፣ በጋምቤላ፣ በሶማሊ፣ በሀረሪ፣ በድሬዳዋ እና በደቡብ ክልሎች በስፋት ይመረታል፡፡
ይሁን እንጂ በዋናነት ለወጪ ንግድ የሚውለው በኦሮሚያ ክልል ምስራቅና ምዕራብ ሀረርጌ የሚመረተው መሆኑን ጴጥሮስ
ተረፈ ቡልቻ በ2020 እ.አ.አ ባደረገው ጥናት ገልጿል፡፡ ጫት ኢትዮጵያን ጨምሮ በዓለምአቀፍ ደረጃ በኬንያ፣ በአረቢያን
ፔንሱላ፣ በደቡብ ምዕራብ ሳውድ አረቢያ፣ በየመንና መደጋስካር እንደሚመረት እ.አ.አ. በ2003 በታዬ ኃይሉ ፈይሣ እና ጆንስ
ቢ.ኦን የተጠናው ጥናት ያመለክታል፡፡ በጥናቱ መሠረት እንደ ኢትዮጵያ፣ ሶማሊያ፣ ጅቡቲ፣ ኡጋንዳ እና የመን ባሉ ሀገራት
ጫት መቃም በህብረተሰቡ ዘንድ ስር የሰደደ ማህበራዊና ባህላዊ ልማድ ሆኗል፡፡

እ.አ.አ. በ2017 የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ባወጣው የወጪ ንግድ ሪፖርት ኢትዮጵያ ከአጠቃላይ ከወጪ ንግድ ከምታገኘው
ገቢ አራት በመቶውን የሚሸፍነው የጫት ወጪ ንግድ መሆኑን ይገልፃል፡፡ ይህ አሃዝ በ2020/2021 ወይም 2013
እ.ኢ.ዘመን አቆጣጠር ወደ 11.7 በመቶ ማደጉን ከጉምሩክና ንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ድሬዳዋ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት
የተገኘውን መረጃ ያሳያል፡፡ ይህም ኢትዮጵያ በ2013 በጀት ዓመት ከዚህ ዘርፍ 350.92 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር ማገኘቷን
ያስረዳል፡፡

በ2020 እ.አ.አ ጴጥሮስ ተረፈ ቡልቻ ባጠኑት ጥናት መሰረት ጫት “Khat, Qat, Kat, Kus-es-Salahin, Mirra, Tohai,
Tschat, Catha, Quat, Abyssinian tea, African tea, and African salad” እየተባለ በተለያዩ አገራት በተለየዩ
ስሞች የሚጠራ መሆኑ ተገልፃል፡፡ ከጉምሩክ ዲክለራሲዮን መረዳት እንደሚቻለውም ከኢትዮጵያ ወደ ውጭ የሚላከው ጫት
በተላየዩ የጉምሩክ ታሪፍ ቁጥር ላይ እንደሚመደብና በተለይ ደረቅ ጫት ወደ ውጪ ሲላክ የተለያዩ ስሞች እየተሰጠው ከአገር
እንደሚወጣ ያመለክታል፡፡

እንደ ደቡብ አፍሪካ እና ኤርትራ ሀገራት ጫት ጥበቃ የሚደረግበት የተክል ዝርያ ሲሆን በአብዛኛው የአረቢያን ፔንሱላ አገራት፣
በሶማሊያ፣ ጅቡቲ፣ ኬንያ እና የመን ባሉ ሀገራት ያለምንም ክልከላ እየተመረተ ለፍጆታ ይውላል፡፡ በሌላ በኩል እንደ ዩናይትድ
ስቴትስ ኦፍ አሜሪካ (ሚሶሪ እና ካሊፎርኒያ ስቴትስ)፣ ቻይና፣ ኢንዶኔዥያ፣ ሳውድ አረቢያ፣ ማሌዥያ፣ ኖርዌይ፣ ስዊድን፣
ፈረንሳይ፣ ቤልጂየም፣ ስዊዘርላንድ፣ የተባበሩት አረብ ኢመሬትስ፣ እስራኤል፣ ፖላንድ፣ ጣሊያን፣ ሩዋንዳ፣ ታንዛንያ፣
ኔዘርላንድ፣ ካናዳ፣ ዩናይትድ ኪንግደም፣ ንዊዝላንድ፣ ዴንማርክ፣ ጀርመን፣ ፊንላንድ፣ አየርላንድ፣ ጆርዳን እና አውስትራሊያ
ያሉ ሀገራት ጫት ወደ አገራቸው እንዳይገባ ክልከላ ያደረጉ መሆኑን በሎጋን ኮችራንና ዴቪን ኦ”ሬጋን፣ 2016፣ እና ጴጥሮስ
ተረፈ ቶልቻ፣ 2020 የተደረገው ጥናት ያመለክታል፡፡

በራኬሽ ብልዋልና ሀሰን ተሾመ በ2010 እ.አ.አ በተጠና ጥናት አርሶ አደሩ ጫቱን በስፋት ማሳው ድረስ ለሚሄዱ ደላሎች
ወይም ኮሚሽን ኤጀንቶች ወይም በአከባቢው ቋንቋ ቀቀቢ ለሚባሉት እንደሚሸጥና እነዚህ ደላሎችም ከአርሶ አደሩ ኮሚሽን
እንደሚቀበሉ ይገልፃል፡፡ ልምድ ያለቸው ጥቂት አርሶ አደሮች ግን በቀጥታ ዋጋውን ከላኪው ጋር በመደራደር ለላኪው
የሚሸጡበት ሁኔታ መኖሩንም ጥናቱ አመላክቷል፡፡ የወጪ ንግድ ጫት በዋናነት ከአወዳይ፣ በዴሳ፣ ጋራ ሙልአታ፣ ኮምቦልቻ
እና ጭሮ አከባቢዎች በኮሚሽን ኤጀንቶች፣ አቅራቢዎች እና አርሶ አደሮች ተሰብስበው ለላኪው እንደሚቀርቡ ጥናቱ ገልጿል፡፡
በተጨማሪም የብልዋልና ተሾመ ጥናት በክልሎች በየቦታው የዕዳት ተብሎ የሚሰበሰበው የመዘጋጃ ክፍያ፣ የኤክስፖርት ጫት
መሸጫ ዋጋ በየወቅቱ የገቢያ ሁኔታ እየተፈተሸ አለመሻሻሉ፣ የጫት ደረጃ የሚወሰንበት ግልፅ የሆነ አሠራርና ስታንዳርድ
አለመኖሩ፣ የተቀባይ ሀገራት ገዥዎች በሞኖፖሊ ወይም በብቸኝነት ገቢያውን መቆጣጠራቸውና ለመቆጣጠር የሚያደርጉት
እንቅስቃሴ፣ ለምርቱ ወጪ ንግድ እንደሌሎች ምርቶች በቂ የመንግስት ድጋፍ አለመደረጉና ማበረታቻ ለዘርፉ አለመሰጠቱ
የጫት ወጪ ንግዱ እንዳያድግ እያደረጉ ካሉት ችግሮች ዋና ዋና መሆናቸውን ተለይቷል፡፡

2.1 የጫት ምርት አቅርቦትና ግብይት ሁኔታ


2.1.1 የጫት ወጪ ንግድ የገበያ ሁኔታና የመንግስት ሚና

በኢትዮጵያና ኬንያ መካከል ያለውን የጫት የወጪ ንግድ ሁኔታ ጋር በተያያዘ ካነጋገርናቸው አካላት ያገኘነው መረጃ
እንደሚያመላክተው ኢትዮጵያና ኬንያ ጫት አምራች ሀገራት ቢሆኑም የሚልኩበት የጫት መዳረሻ ቦታ አንድ አይነት ስለሆነ
ውድድሩም እጅግ ከፍተኛ ነው፡፡ በኬንያ በኩል የጫት ሽያጭን ከማበረታታት አንፃር ማለትም ከዋጋ ወቅታዊነት፣
ትራንስፖርት ከማመቻቸት፣ ከላኪ እስከ ተቀባይ ድረስ ያለውን ግንኙነት የተሳለጠ እንዲሆን በማድረግ በኩል የተለያዩ
ማበረታቻዎችን በማመቻቸትና አምራችና ላኪዎች ተጠቃሚ እንዲሆኑ በማስቻል በኩል የመንግስት ሚና የተሻለ እንደሆነ
መረዳት ተችሏል፡፡

በኢትዮጵያ በኩል የጫት ምርት የተሻለ የውጪ ምንዛሪ የሚያስገኝ እንደሆነ ቢታወቅም ከጫት አላላክ ጀምሮ በተቀባይና
በላኪ በኩል ያለውን ግንኙነት በመደገፍ፣ የትራንስፖርት አቅርቦትንና ሌሎች መሰረተ ልማቶችን በማመቻቸት፣ በየጊዜው
ወቅቱን የጠበቀ የዋጋ ማስተካከያ በማድረግ፣ የጫት ምርት በግብርና ኤክስቴንሽን በመደገፍ፣ ከተቀባይ ሀገር ጋር ጠንካራ
የኢኮኖሚ ዲፖሎማሲ ድጋፍ በማድረግ በኩል የመንግስት ሚና በሚፈለገው ደረጃ አለመሆኑና የጫት አላላኩ በጥቂት
ነጋዴዎች ብቻ የተያዘና ኮታ ላይ የተመሰረተ እንዲሆን ያደረገ ስለሆነ አምራቹም እንደ ሀገርም ከምርቱ የሚጠበቀውን ጥቅም
ማግኘት እንዳልተቻለ መገንዘብ ተችሏል፡፡

2.1.2 የጫት ወጪ ንግድ የሀገር ውስጥ መነሻ ቦታዎችና የመዳረሻ ሀገራት

የጫት ወጪ ንግድ የመነሻ ቦታዎች በአብዛኛው በምስራቁ የሀገራችን ክፍል ማለትም በድሬዳዋ፣ አወዳይ፣ እና ጅግጅጋ ሲሆን
በነዚህ ቦታዎች ላይ በመዘዋወር አካላዊ ምልከታ ተደርጓል፡፡ የመዳረሻ ሀገራትን በተመለከተ በዋነኛነት ጅቡቲ፣ ሞቃዲሾ፣
ሃርጌሳ፣ ፑንት ላንድ፣ እስራዔል እንዲሁም ሌሎች በርካታ የአለም ሀገራት መሆናቸውን መገንዘብ የተቻለ ሲሆን በተለይም ወደ
ጅቡቲና ሶማልያ የሚላከው የጫት ምርት ላኪና ተቀባይ ባላቸው የዝምድናና የጥቅም ትስስር ምክንያት የጫት ዋጋ የሚወሰነው
በገበያ ሁኔታ ሳይሆን በተቀባዩ መልካም ፈቃደኝነት ላይ የተመሰረተ መሆኑን ከተገኙ የሰነድና የሰው ማስረጃዎች ማረጋገጥ
ተችሏል፡፡

ከተወሰኑ ዓመታት በፊት የጫት ምርት ወደ ውጪ የሚላክባቸው በርካታ ሀገራት የነበሩ ሲሆን እ.ኤ.አ ከ2012 ጀምሮ ግን
እንደ ሳውዲአረበያ፣ ኒውዝላንድ፣ ጀርመን፣ አውስትራልያ፣ ጆርዳን፣ ኖርዌይ፣ ስዊድን፣ ፈረንሳይ፣ ዴንማርክ፣ ፊንላንድ፣
አሜሪካ፣ አየርላንድ፣ ታንዛንያ፣ ዩናይትድ አረብ ኢሚሬትስ፣ ስዊዘርላንድ፣ ካናዳ፣ ቤልጅየም፣ ፖላንድ፣ ጣሊያን፣ እስራኤል፣
ሩዋንዳ፣ ኔዘርላንድ፣ ቻይናና ዩናይትድ ኪንግደም ያሉ ሀገራት ምርቱ ወደ ሀገራቸው እንዳይገባ ክልከላ ማድረጋቸውን በ2016
በLOgan Cochrane እና በDavin O. Regan ከተደረገ ጥናት መረዳት ተችሏል፡፡

2.2 የጫት ላኪዎች ሁኔታ


2.2.1 በማህበር የተደራጁ ላኪዎች

በአብዛኛው በጫት ወጪ ንግድ ዘርፍ ከተሰማሩት ውስጥ ከፍተኛውን የመላክ ድርሻ የሚይዙት ውስንና ጥቂት
ግለሰቦች/ድርጅቶች ሲሆኑ እነዚህም ድርጅቶች ከጫት ተቀባዩ ጋር የተለየ የዝምድና ግንኙነት ያላቸው ማለትም ከኢትዮጵያ
የሚልከውና በሶማሊያ የሚቀበለው ግለሰብ/ድርጅት አንድ መሆን (የሁለቱ ሀገራት መታወቂያና ፓስፖርት ያላቸው ነጋዴዎች
መኖራቸው) በጫት ወጪ ንግዱ ውስጥ አዳዲስ ላኪዎች እንዳይሳተፉ፣ በስራው ላይ ያሉትም ተወዳዳሪ እንዳይሆኑ፣ የጫት
ዋጋ በነፃ ገበያ ውድድር እንዳይወሰንና የጫት ወጪ ንግድ ሥርዓቱ ግልጽነት የጎደለው እንዲሆን ከማድረጉም በተጨማሪ
የውጪ ምንዛሬው ወደ ሀገር እንዳይገባ በማድረግ በሀገር የውጪ ምንዛሬ ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ላይ ከፍተኛ አሉታዊ
ተፅዕኖ እየፈጠረ መሆኑን ከተለያዩ የግል አውሮፕላን ኦፕሬተሮች፣ የጫት ላኪዎችና ሌሎች አካላት ላይ በተደረገ ጥናት
ለመገንዘብ ተችሏል፡፡ እንደማሳያ ቢፍቱ ባሃ ኦሮሚያ የተባለ የጫት ላኪ ማህበር ቀደም ሲል ወደ ሶማሊያ ጫት መላክ
ሲጀምር በአንድ ጊዜ እስከ 40,000 ኪ.ግ ለአንድ ኪ/ግ 10 የአሜሪካን ዶላር የጫት ሽያጭ ያከናወነ ሲሆን በዚህም የተነሳ
ሌሎች ላኪዎች ከሶማሊያ ተቀባይ ጋር ያልተገባ የጥቅም ትስስር በመፍጠር የሚላከው የጫት መጠን ወደ 4,000 ኪ/ግ
በዋጋም ደረጃ በኪ.ግ ወደ 5 ዶላር እንዲቀንስ በማድረግ ሀገር ከዘርፉ የምታገኘው ጥቅም እንድታጣ የተደረገ መሆኑን
የሚያመልከት የባንክ ፈቃድ ከጥናት ሰነዱ ጋር በአባሪነት ተያይዟል፡፡

ጫት ነጋዴዎች ከሶማሊያ ወደ ኢትዮጵያ መጥተው በጫት ንግድ ውስጥ ተሳትፎ የሌላቸውን ግለሰቦች በመመልመል የጫት
ላኪ አስመስለው በስማቸው ንግድ ፈቃድ በማውጣት የጫቱ ተቀባይ ራሳቸው ከመሆናቸው አንፃር በፈቀዱት ዋጋ ልክ ጫት
የሚላክበት፤ ከፍተኛ የውጪ ምንዛሬ በዚያው እንዲቀር በማድረግ ከዚህ ሲያልፍም ዋጋ በማሳነስ ዕቃን ወደ አገር ውስጥ
በማስገባት የዋጋ ንረትን በማባባስና በሀገር ውስጥ የሚከፈለው ግብር በማሳነስ ተያያዥ የኢኮኖሚ አሉታዊ ተጽእኖ
እንዲፈጠር ምክንያት መሆን፤ የሚገኘውም አነስተኛ የውጪ ምንዛሬ በማስመጣት ስራ ላይ ለተሰማሩ ነጋዴዎች በመሸጥ የዋጋ
ንረቱ እንዳይረጋጋ የማድረግ ተፅእኖ እየፈጠረ በመሆኑ የንግድ ፈቃድ አሰጣጥ ሂደቱ በአግባቡ ሊፈተሽ እንደሚገባ በዘርፉ
የተሰማሩ አካላት በሰፊው አንስተዋል፡፡

በጅግጅጋ ያነጋገርናቸው የጫት ላኪ ተወካዮች የጫት ላኪነት ፈቃድ ያላቸውና ወደ ውጪ የሚላከውን ጫት ከገበሬ ማሳ
በመግዛት፣ ምርቱን በመጋዘን በማዘጋጀት ህጋዊ ሂደቱን ተከትሎ ከሀገር እስከሚወጣ ድረስ ያለውን አጠቃላይ ሂደት
የሚያከናውኑና ወደ ውጪ ከሚላከው ጫት ለሀገር የውጪ ምንዛሬ በጉምሩክ ዲክለራሲዮን ላይ በሚገለፁት ላኪዎች ስም
የሚያስገቡ ቢሆንም በራሳቸው ስምና የንግድ ፈቃድ ጫቱን ኤክስፖርት ለማድረግ መቸገራቸውን በሰፊው አንስተዋል፡፡ ከዚህ
በመነሳት በወካዩና በተወካዩ መካከል ያለው ግንኙነት ከህጋዊ ንግድ ሥርዓቱ አንፃር ጤናማ አለመሆኑን የጥናት ቡድኑ
ተገንዝቧል፡፡ እነዚህ የጫት ላኪ ተወካዮች የወከላቸውን የጫት ላኪውን በአካል አይተው እንደማያውቁም ገልፀዋል፡፡

ከሶማሊ ክልል የንግድን ኢንዱስትሪ ቢሮ የስራ ኃላፊዎች ከተገኘው መረጃ ለማወቅ እንደተቻለው ተቀማጭነታቸው በክልሉ
የሆኑ ከ15 በላይ የጫት ላዎች ያሉና እነዚህ ላኪዎች ከዓመታት በፊት በስማቸው ህጋዊ ሂደቱን ጠብቀው ጫት ወደ ሶማሊ
ላንድ በመላክ በህጋዊ የውጪ ንግድ ስርዓቱ ተጠቃሚ የነበሩ ቢሆንም ከጥቂት ዓመታት ወዲህ ግን በአካል የወጪ የጫት
ንግድ ውስጥ የሌሉ አካላት የጫት መላክ ፈቃድ በመውሰድ ከዚህ ቀደም ጫት በስማቸው ሲልኩ የነበሩና ሌሎች በጫት ስራ
ላይ የተሰማሩ ነጋዴዎችን ውክልና በመስጠት እነዚህ ነጋዴዎች ጫቱን ለኤክስፖርት በማዘጋጀት ከኤክስፖርቱ ጋር ተያያዥነት
ያላቸው ወጪዎች በሙሉ በመሸፈን ጫቱን ትክክለኛው የጫት ንግድ ውስጥ በሌለው ላኪ ድርጅት ስም ጫቱን ወደ ሶማሊ
ላንድ የሚልኩ ሲሆን ሂደቱም እንደሚከተለው መሆኑን አስረድተዋል፡፡

1) ተቀማጭነታቸው ሶማሌ ክልል የሆኑ በስማቸው የላኪነት ፈቃድ ያላቸው እና ሌሎች በዘርፉ የተሰማሩ ነጋዴዎች
በጉምሩክ ዲክላራሲዮን ላይ በስም ከሚታወቀው የጫት ወጪ ንግድ ፈቃድ ካለው ድርጅት/ግለሰብ ላኪ ውክልና
በመውሰድ ጫቱን ከአቅራቢ ከመረከብ ጀምሮ አጠቃላይ ያሉት ሂደቶችን በማጠናቀቅ ጫቱን ሶማሌ ላንድ ላለው
ተቀባይ መላክ፤

2) በጉምሩክ ዲክላራሲዮን ላይ በተመዘገበው ላኪ ውክልና የተሰጠው ወኪል ሶማሌ ላንድ ውስጥ ባለው ወኪል
አማካኝነት ጫቱን በመረከብ በኢትዮጵያ ብር፣ በሶሚሊ ሺሊንግ፣ በአሜሪካ ዶላር እንዲሁም በሌሎች የውጪ
ምንዛሬ በመሸጥ ገንዘቡን ሶማሌ ላንድ ላይ ባለው የምንዛሬ ተመን ወደ ዶላር መመንዘር፤
3) የጉምሩክ ዲክላራሲዮን ላይ ያለው ላኪ (በሰነድ ላይ ብቻ የሚታወቀው አካል) ተጠቃሎ ወደ ዶላር የተቀየረው
ገንዘብ ቀደም ሲል በስሙ ጫት ወደ ሶማሌ ላንድ እንዲልክለት ከወከለው አካል ዶላሩን ሶማሌ ላንድ ባለው የምንዛሬ
መጠን በመግዛት ዶላሩ በስሙ ወደ አገር ውስጥ እንዲገባ ማድረግ፤

4) የጉምሩክ ዲክላራሲዮን ላይ ያለው ላኪ( በሰነድ ላይ ብቻ የሚታወቀው አካል) በስሙ የውጪ ምንዛሬ የገባለት
በመሆኑ የገባለትን የውጪ ምንዛሬ ጫት ለመላክ በቅድሚያ እንደተከፈለው በማስመሰል የባንክ ፈቃድ (export
bank permit) በስሙ በማሰራት ጫት በውክልና ለመላክ እንዲያስችለው ለወኪሉ ማስተላለፍ፤

5) ተቀማጭነታቸው ሶማሌ ክልል የሆኑ በስማቸው የላኪነት ፈቃድ ያላቸው እና ሌሎች በዘርፉ የተሰማሩ ነጋዴዎች
በጉምሩክ ዲክላራሲዮን ላይ በስም ከሚታወቀው የጫት ወጪ ንግድ ፈቃድ ካለው ድርጅት/ግለሰብ በግዥ ያገኙትን
የባንክ ፈቃድ በመጠቀም ሂደቱን በሙሉ በማጠናቀቅ በወከላቸው ስም ጫት መላክና በዚሁ መሰረት ከላይ ከተራ
ቁጥር 1 እስከ 4 በተገለፀው መሰረት ይህ አሰራር ስርዓት ሆኖ መቀጠል፤

ይህ በውክልና ጫት የመላክ ሂደት በስሙ ጫት የሚላክለት አካል በአብዛኛው በዕቃ አስመጪነት ዘርፍ የተሰማራ በመሆኑ
የውጭ ምንዛሪ ለማግኘት ዓላማው ያደረገ ሲሆን ውክልና በመውሰድ ጫት የሚልከው አካል ደግሞ ቀጣዩን ጫት ወደ ሶማሌ
ላንድ መላክ እንዲችል የባንክ ፈቃድ የሚፈልግ እና በሶማሌ ላንድ የጫት ገበያ ላይ በኢትዮጵያ ብር እና በሶማሊያ ሺልንግ
የሸጠውን ገንዘብ ሶማሌ ላንድ ባለው የምንዛሬ መጠን ዶላር ገዝቶ ወደ ኢትዮጵያ ማስገባት ያለበት ከመሆኑ አንፃር ዶላሩ
ሶማሌ ላንድ ከገዛበትና ወደ ኢትዮጵያ ልኮ ከባንክ ተመንዝሮ በሚሰጠው መካከል በማነስ የምንዛሬ ልዩነት ያለ በመሆኑ ይህንን
ልዩነት ለማካካስና ጫት የመላክ የባንክ ፈቃድ ለማግኘት በዲሀብሽን ወይም በአካል ሶማሌ ላንድ ቶጎ ውጫሌ ድረስ
በመምጣት ለጉምሩክ ካስመዘገበ በኋላ ከጉምሩክ የተሞላውን ፎርም ማረጋገጫ በመውሰድ በጉምሩክ ዲክላራሲዮን ላይ
በላኪነት በተመዘገበው አካል ስም ዶላሩን ለባንክ የማስገባት ውስብስብ ሂደቶች ያሉ መሆኑን የጥናት ቡድኑ ከመረጃ
አቅራቢዎች መገንዘብ ችሏል፡፡

ከእርሻው ጀምሮ የጫት ምርቱን ከማጓጓዝ ጋር በተያያዘ በተለያዩ ቦታዎች በክልሎች የተቋቋሙ የቁጥጥር ኬላዎች
ከመብዛታቸውም በላይ የክፍያ ጥያቄያቸው ወጥነት የሌለውና በዘፈቀደ የሚቀርብ መሆኑ በጫት ንግዱ ላይ መጓተትንና
እንግልትን የፈጠረ ስለመሆኑ በከፍተኛ ቅሬታ የላኪ ተወካዮች አንስተዋል፡፡ በማሳያነትም አወዳይ ላይ ለአንድ መኪና እስከ
10000 ድረስ የሚከፍሉበት ሁኔታ መኖሩን፣ ቦምባስ ላይ መኪናው የሚቆምበትና ቆሻሻ የሚጥልበት ሁኔታ ባይኖርም
በመኪና 1000 ብር ድረስ የሚከፈል መሆኑ፣ ጅግጅጋ ላይ በኪሎ 1.50 ብር የሚከፈል መሆኑ፣ ቶጎጫሌ ላይ በመኪና
ከ800 እስከ 1000 የሚከፈል መሆኑን መረዳት ተችሏል፡፡

የጅቡቲ የጫት ንግድ ከረጅም ዓመት በፊት በኢትዮጵያና በጅቡቲ መንግስታት መካከል በተደረሰ ውል ወደ ጅቡቲ የሚላከው
የጫት ምርት ብዛት (ኮታ) እና ዋጋ የተወሰነ ሲሆን በዚህም መሰረት የጅቡቲ መንግስት በተለይ ለግለሰብ ላኪዎች በአጠቃላይ
እስከ 25,000 ኪ.ግ በየቀኑ እየደለደለ በኢንባሲ በኩል ለንግድ ቢሮ በመላክ በዚሁ መሰረት ግለሰብ ላኪዎች ጫት ወደ ጅቡቲ
በመላክ የውጪ ምንዛሬውም በባንክ በኩል እንደሚገባ የጥናት ቡድኑ ተገንዝቧል፡፡
ወደ ጅቡቲ ለሚላከው ጫት ተቀባዩ በብቸኝነት ሶጂክ በሚባል ድርጅት ሲሆን ግዥውን የሚፈፅመው ኮታን መሠረት ባደረገ
መልኩ ከስድስት የኢትዮጵያ ጫት ላኪ ማህበራት እና ከ65 እስከ 70 ከሚደርሱ ግለሰቦች መሆኑ በአሰራር ደረጃ በተወሰነ
መልኩ የንግድ ስርዓቱን የጠበቀ እንደሆነ የጥናት ቡድኑ ተገንዛቧል፡፡

በማህበር የተደራጁ ጫት ላኪዎች ያለምንም ኮታ የአንደኛ ደረጃ ጫት በ8 ዶላር እና ሁለተኛ ደረጃ ጫት በስድስት(6)
የአሜሪካን ዶላር ወደ ጅቡቲ መላክ እንደሚችሉ ገልፀው በወቅቱ የወጪ ንግድ ሚኒስቴር በቁጥር ወ2-ው311/3/15 ግንቦት
28 ቀን 1984ዓ.ም ለላኪዎች በተፃፈ ደብዳቤ የመላኪያ ዋጋ ካለው የጫት አቅርቦት ዋጋ፤ የትራንስፖርት ወጪ እና ሌሎች
ተዛማጅ ወጪዎች እንዲሁም በተቀባይ ሀገር ካለ የጫት ወቅታዊ የመሸጫ ዋጋ አንፃር በየጊዜው እየተፈተሸ መከለስ ሲገባው
ላለፉት 30 ዓመታት በነበረበት የቆየ በመሆኑ በጫት አምራቾች፣ ላኪዎችና በሀገሪቱ የውጭ ምንዛሪ ግኝት ላይ ከፍተኛ የሆነ
አሉታዊ ተፅዕኖ እንዳሳደረ ለመረዳት ተችሏል፡፡

ከኢትዮጵያ ወደ ሶማሊያ የሚላከው የጫት ንግድ እየጨመረ የመጣው ከኬንያ ወደ ሶማሊያ የሚገባው ጫት ከአንድ ዓመት
በፊት በመቋረጡ ምክንያት ሲሆን ይህ ገበያ በዓለም አቀፍ የንግድ ስርዓት የማይመራና ገበያውን ጫና ውስጥ በሚከቱ ግለሰብ
ነጋዴዎች እና የመንግስት መዋቅር ውስጥ ያሉ ተባባሪዎች ጭምር ተፅእኖ ውስጥ የወደቀ ነው፡፡ ይህም በመሆኑ ገበያው
እንደተከፈተ ጫት ወደ ውጪ ይላክበት ከነበረው አሥራ አምስት(15) የአሜሪካ ዶላር በአሁኑ ወቅት ወደ አምስት(5)
የአሜሪካን ዶላር ወርዷል፡፡ ይህ ጤነኛ ያልሆነ የንግድ ሂደት ማስተካከያ እስካልተደረገበት ድረስ የዋጋ መቀነሱ ከዚህም በታች
መውረዱ ብቻ ሳይሆን የኬንያ እና የሶማሊያ የጫት ንግድ ገበያ ወደነበረበት ሲመለስ ሙሉ ለሙሉ ከኢትዮያ ወደ ሶማሊያ
የሚላክ ጫት እና የሚገኘው የውጭ ምንዛሬ ላይ ከባድ ፈተና ሊገጥመው እንደሚችል በዘርፉ የተሰማሩ አካላት ገልፀዋል፡፡

ፑንት ላንድ በአውሮፕላን ጫት እንዲልክ የተፈቀደለት ሬድ ስታር ሲሆን አጓጓዥ ኦፕሬተሩ ደግሞ የኢትዮጵያ አየር መንገድ
ብቻ መሆኑና የሞቃዲሾ የማረፊያ ፈቃድ ደግሞ ለላኪዎች ወይም በአለም አቀፍ ሲቪል አቪየሽን ህግ በሀገራት መካከል ባለው
የፍቃድ አሰጣጥ ስርዓት በረራው ለሚነሳበት ሀገር ሲቪል አቪየሽን መሰጠት ሲገባው ለተቀባይ የሚሰጥ በመሆኑ ምክንያት
ሌሎች የጫት ላኪዎች ተወዳድረው ገበያውን ማግኘት እንዳይችሉ ያደረገ መሆኑን መገንዘብ ተችሏል፡፡ ይህም ክፍተት በሁለቱ
ሀገራት ያሉ አንዳንድ የመንግስት አካላት ንግዱን በብቸኝነት ከተቆጣጠሩት አካላት ጋር አላስፈላጊ ግንኙነት በመፍጠራቸው
ምክንያት መሆኑን መረጃውን ከሰጡ አካላት መገንዘብ ተችሏል፡፡

2.2.2 የግለሰብ ጫት ላኪዎች

የግለሰብ ጫት ላኪዎች የሚልኩት ጫት የሚዘጋጀው በዋናነት አወዳይ ላይ ነው፡፡ በግለሰብ ደረጃ የሚልኩ እስከ 70
የሚደርሱ የግል ላኪዎች ያሉ ሲሆን ጅቡቲ ባለ ጫት ተቀባይ በሚወሰነው የኮታ መጠን መሰረት ጫቱን ወደ ጅቡቲ ይልካሉ፡፡
ነገር ግን የኮታ ገደብ ኖሮም የግለሰብ ላኪዎች በኪ.ግ ስምንት (8) ዶላር የሚያስገቡ ሲሆን ማህበራት ደግሞ በኪ.ግ 6 ዶላር
ያስገባሉ፡፡ በዚህም ምክንያት የግለሰብ ላኪዎች የተሻለ ዶላር እያስገቡ በኮታ መገደቡ ላይ ቅሬታ እንዳላቸው አስረድተዋል፡፡

2.3 የጫት ወጪ ንግድ ሥርዓት ሁኔታ


2.3.1 የጫት ወጪ ንግድ ፈቃድ አሰጣጥና እድሳት
የጫት ወጪ ንግድ ፈቃድ አሰጣጥን በሚመለከት ማንኛውም አካል በአካባቢው ባለው ንግድ ቢሮ ቀርቦ በቀላሉ ፈቃድ
ማግኘት የሚችልበት ምቹ ሁኔታ ያለ ሲሆን ፈቃድ ፈላጊው አካል መታወቂያ፣ ቲን ቁጥር እና ንግድ ፈቃድ ይዞ ሲቀርብ በ30
ደቂቃ ውስጥ ፈቃድ ማግኝት የሚችልበት አሰራር መኖሩን ድሬዳዋ ያለው የንግድ ሚኒስቴር ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ተገልጿል፡፡
ሆኖም ግን የፌዴራል ንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የኦንላይን የንግድ ፈቃድ አሰጣጥና ፈቃድ እድሳት ስርዓት እስከዘረጋ
ድረስ ለክልሎችና ሌሎች የከተማ አስተዳደር ውክልና በመስጠት በቀላሉ ተደራሽ ማድረግ የሚቻልበት ሁኔታ መመቻቸት
እንደሚገባው አስተያየት ተሰጥቷል፡፡ ከዙህ ንግድ ፈቃድ አሰጣጥ ጋር በተያያዘ የጎረቤት ሀገር ተወላጅ ሆኖ በአካባቢው 6
ወርና ከዛ በላይ ኖሯል በሚል መታወቂያ በመስጠት የጫት ላኪነት ፈቃድ በማውጣት ወደ ጫት ንግድ ስራ በመሰማራት
በንግዱ ላይ አሉታዊ ጫና ያሳደሩ መሆኑ በቅሬታ መልክ ቀርቧል፡፡

2.3.2 የባንክ ፈቃድ አሰጣጥና የውጭ ምንዛሪ ግኝት ክትትል

በድሬዳዋና በጅግጅጋ በኩል ወደ ጅቡቲ የሚላክ ጫት የውጪ ምንዛሪ ክፍያ ስርዓቱ በሌተር ኦፍ ክሬዲት (Letter of
Credit, LC) ወይም በቅድመ ክፍያ ቴሌግራፊክ ትራንስፈር (Telegraphic Transfer, TT) መሰረት የሚፈፀም ነው፡፡ ነገር
ግን የባንክ ለባንክ ግንኙነት በሌለበት አካባቢ የጫት ላኪና ተቀባይ የግዥና ሽያጭ ግንኙነት በቅድመ ክፍያ ቴሌግራፊክ
ትራንስፈር (Telegraphic Transfer, TT) ቀድመው ዶላሩን በቶጎጫሌ በኩል እጅ በእጅ ወይም በካሽ እና በሶማሌ የባንክ
አገልግሎት የሚሰጠው ደሃብሺል በኤክስፖርተሩ ስም ወደ ኢትዮጵያ ንግድ ባንኮች በማስገባት የኤክስፖርት ባንክ ፈቃድ
እንዲገኝ ይደረጋል፡፡

በቶጎጫሌ የጠረፍ ከተማ የቆዳ ስፋቱ አነስተኛ ቢሆንም ከከተማዋ አቅም በላይ 15 የሚሆኑ የግል ባንኮችና 2 የኢትዮጵያ
ንግድ ባንክ ቅርንጫፎች መኖራቸው ከፍተኛ የሆነ የውጪ ምንዛሪ መኖሩን ያሳያል፡፡ በቶጎውጫሌ ወደ ሀገር የሚገባው ዶላር
ከመንግስት ባንክ ይልቅ በግል ባንኮች የሚደረግ ሲሆን ለዚህም ማሳያው ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቶጎውጫሌ ቅርንጫፍ ጋር
ያለው ግብይት በጣም ዝቅተኛ መሆኑና በስድስት ወር ጊዜ ውስጥ አንድም የዶላር ገቢ ጥያቄ ያልቀረበ መሆኑ ነው፡፡ ይህም
ሁኔታ በቶጎውጫሌ ከተማ ውስጥ ያለው የውጭ ምንዛሪ ዝውውር በጥልቀት መፈተሽ እንደሚገባው አስተያየት
ተሰጥቶበታል፡፡ የግል ባንክ ስራ አስኪያጆች በስራው የሚያገኙት ደመወዝና ያላቸው የገንዘብ መጠን ተገማች ቢሆንም
በስማቸው በግል ባንኮችና በንግድ ባንክ አካውንት በመክፈት RTGS በሚባል የባንክ አሠራር በርካታ መጠን ያለው ገንዘብ
ወደ ሌላ ባንክ የሚያስተላልፉ መሆናቸው የተስተዋለ ሲሆን ከዚህም በተጨማሪ ባንኮች ደንበኛው የአሜሪካን ዶላር ይዞ
ሲቀርብ ከየት ዶላሩ ከየት እንደመጣ የማይጠይቁ መሆናቸው ከጉምሩክ ተመዝግቦ ያለፈበትን ደብዳቤ ብቻ የሚጠቀም መሆኑ
ከቶጎጫሌ መቆጣጠሪያ ጣቢያ፣ ከባንኮች ከተገኙ መረጃዎች እንዲሁም ከክልሉ ንግድ ቢሮ ጋር በተደረገ ውይይት ለመገንዘብ
ተችሏል፡፡

ከዚህም በተጨማሪ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክንና የአቢሲንያ ንግድ ባንክ ቅ/ጽ/ቤቶች የስራ ኃላፊዎችን በመጠየቅ የተሰበሰበው
መረጃ የሚከተሉትን ዋና ዋና ጉዳዮች አካቷል፡-
ዶላሩን ከሶማሌ ላንድ የተለያዩ ምንጮች በማሰባሰብ ወደ ባንክ የሚያስገባው የጫት ላኪ ወይም ወኪሉ መሆኑና ወደ ባንክ
ገቢ የሚደረግ ቢሆም ይሄው ዶላር ከመሀል ሀገር በጥቁር ገበያ ተመንዝሮ የመጣ ሊሆን እንደሚችል አንዳንድ ጠቋሚ
መረጃዎችና ሪፖርቶች ያመለክታሉ፡፡

2.3.3 ኬላ ቁጥጥርና የጉምሩክ ዕቃ አወጣጥ ሥርዓት

በህጋዊ መንገድ ወደ ውጪ የሚላክ ጫት በዋናነት በድሬዳዋ ፤ ጅግጅጋ፣አዲስ አበባ ኤርፖርትጉምሩክና በኢትዮጵያ ፖስታ
ቤት በኩል ከባንክ የውጪ ምንዛሬ ፈቃድ ቀርቦና ተመዝግቦ እንደ ማንኛውም የውጪ ንግድ የጉምሩክ ስርዓት ተፈጽሞበት
ከሀገር እንዲወጣ ይደረጋል፡፡ አልፎ አልፎ ላኪው በባንክ ፈቃድ ከተመዘገበው መጠን ባላይ ትርፍ ጫት ለማውጣት የሚደረግ
ሙከራ መኖሩ ከተሰበሰበው መረጃ መረዳት ተችሏል፡፡ ከዚህ ጋር በተያየዘ ቀደም ሲል በትርፍነት የሚያዘውን ጫት
በማቃጠል የሚወገድበት ሁኔታ የነበረ ሲሆን አሁን ላይ በመመሪያ ቁጥር 112/2008 መሠረት ጫቱን ማስቆምና ማቃጠል
ሳያስፈልግ ጫቱ ወደ ውጪ እንዲላክ ተደርጎ በቀጣይ አስተዳደራዊ እርምጃ የሚወሰድበት ሥርዓት ተፈጥሯል፡፡

በተለይ በድሬዳዋ በኩል በተሽከርካሪ ወደ ጅቡቲ የሚላከው ጫት ከ90 እስከ 95 በመቶ በመካከለኛ የስጋት ደረጃ
ይስተናገዳሉ፡፡ ይህም ማለት የቀረበውን ሰነድ ብቻ በማጣራት ምንም ዓይነት አካላዊ ፍተሻ ወይም የሚዛን ልኬት ማስረጃ
ሳያስፈልግ የሚስተናገድ መሆኑ ለመገንዘብ ተችሏል፡፡ ከዚህ አንፃር ሁለት ጉዳዮች አስታርቆ መሄድ እንደሚያስፈልግ በዘርፉ
የተሰማሩ አካላት ያነሳሉ፡፡ ይህም ጫት በባህሪው ቶሎ የሚበላሽ በመሆኑ ፈጣን የጉምሩክ አገልግሎት ካልተሰጠው ጫቱ ወደ
ውጪ ሀገር ሳይላክ የሚቀርበት ሁኔታ በመፍጠር ከወጪ ንግዱ የሚገኘውን የውጪ ምንዛሬ ሊያሳጣ እንደሚችል በውይይቱ
ወቅት ተነስቷል፡፡ በሌላ በኩል የጫት የወጪ ንግድ አብዛኛው ግብይት እየተከናወነ ያለው ቤተሰባዊ ትስስር ባላቸው ወገኖች
መካከል በመሆኑ ከ90 እስከ 95 በመቶ የሚሆነው ጫት በጉምሩክ አካላዊ ፍተሻ ያለመታየቱ ዋነኛው የስጋት ምንጭ
ስለመሆኑ የአጥኚ ቡድኑ ግንዛቤ የወሰደ ሲሆን በጉምሩክ በኩል ወደ ውጪ የሚላከው ጫት ባለው የስጋት ደረጃ መሰረት
የማይመዘን ቢሆንም በጅቡቲ ጉምሩክ ተወካይ፣ በሶጂክ ተወካይ እና በሌሎች አካላት ምዘና የሚከናወንበት ሁኔታ ስለመኖሩ
ታይቷል፡፡

ወደ ጅቡቲ በተሸከርካሪ የሚላከው ጫት የሚመዘነው በሁለት መልኩ ሲሆን አንደኛው የተለያዩ ማህበራት የሚልኩትን ጫት
ከሌሊቱ 7 ሰዓት ጀምሮ ለዚሁ በተዘጋጀ በለገሀር መጋዘን ላይ በመሰብሰብ የጅቡቲ ጫት ተቀባይ እና የጅቡቲ ጉምሩክ
ተወካይ እንዲሁም የጉምሩክ አስተላላፊ በተገኙበት በማንዋል ሚዛን ተመዝኖ የጉምሩክ ባለሙያ በፕሎምፕ አሽጎ የመንገድ
ወረቀት ተዘጋጅቶለት በለሊት ወደ ጅቡቲ እንዲወጣ ይደረጋል፡፡ ሁለተኛው በግለሰብ ቀድሞ በተወሰነ ኮታ መሰረት የሚላክ
ጫት ሲሆን እዚህ ላይ በተመሳሳይ ከላይ የተገለፁት አካላት ተገኝተው በዲጂታል ሚዛን ከተመዘነ በኋላ ለላኪዎቹ ከተሰጠ
ኮታ ተጨማሪ ጫት ቢገኝ የጅቡቲ ተቀባዩ ወኪል ወዲያው እንዲመለስ የሚያደርግበት ሂደት እንዳለ በአካል በተደረገ ምልከታ
ለማረጋገጥ ተችሏል፡፡

ወደ ሶማሊያ (ከሶሚሊ ላንድ ውጪ) ጫት የሚላከው በአውሮፕላን በድሬዳዋ ኤርፖር በኩል ሲሆን የላኪው ወኪል፤
የጉምሩክ ፍተሻ ባለሙያ፤ የደህንነት ሰራተኞች እና የኤርፖርት ሰራተኞች በተገኙበት በዲጂታል ሚዛን በመመዘን በኢትዮጵያ
አየር መንገድና በተለያዩ ኦፕሬተር አውሮፕላኖች ተጭነው ይላካል፡፡ በዚህ ሂደት ከአጓጓዡ የሚገኝ የጭነት ማኒፌስት መረጃ
የጫቱ ክብደት ቀደም ሲል በዲጂታል ሚዛን ከተመዘነው በማነስ ለጉምሩክ የማቅረብ ሁኔታ የሚገጥም መሆኑ በአካል
በተደረገው እይታ ለማረጋገጥ የተቻለ ሲሆን ይህ በሚያጋጥምበት ወቅት በጉምሩክ በኩል በቀድሞው መረጃ መሰረት
በመመዝገብ ሰነድ የሚዘጋጅ መሆኑ ለመገንዘብ ተችሏል፡፡

ጠረፍ አካባቢ ለሚገኙ ወረዳዎች የተፈቀደው የጫት ኮታ የህዝብ ቁጥር መጨመርን ከግምት ባስገባ መልኩ የኮታ መጠን
መሻሻል ሊደረግበት ሲገባ ለረጅም ጊዜያት የቆየ በመሆኑ በአካባቢው ነዋሪዎች እና ህግ አስከባሪ አካላት ላይ ቅሬታ እየፈጠረ
በመምጣቱ ከአሁን ቀደም የጫት ኮንትሮባንድ መከላከል ላይ ይተባበሩ የነበሩ የሚልሻ አባላትና ነዋሪዎች በአሁኑ ጊዜ ወጪ
የጫት ኮንትሮባንድ በጉምሩክ መቆጣጠሪያ ጣቢያዎች በሚያዝበት ወቅት ከፍተኛ አስተዳደራዊና ማህበራዊ ጫና በመፍጠር
የተያዘውን ጫት ሚያስለቅቁበት ሁኔታ መኖሩን ያነጋገርናቸው የጉምሩክ መቆጣጠሪያ ጣቢያዎች ገልጸዋል፡፡ ከላይ ከተገለጸው
በተጨማሪ ጠረፍ አካባቢ ለሚኖሩ ነዋሪዎች ፍጆታ የሚውል በሚል ሽፋን ብዛት ያለው ጫት በኮንትሮባንድ በሰው ሸክም፣
በእንስሳ ጀርባ፣ በባጃጅ እንዲሁም በተለያዩ ማጓጓዣዎች በመጠቀም ወደ ድንበር በመጠጋት በአካባቢው ሚላሻም ጭምር
ድጋፍ በህጋዊ መንገድ ከሚወጣ በላይ በህገ ወጥ መንገድ ወደ ጅቡቲ እና ሶማሊ ላንድ የሚወጣ ስለመሆኑ ለመገንዘብ
ተችሏል፡፡

2.4 የሎጅስቲክስ አገልግሎት አሰጣጥ ሁኔታ

የጫት ወጪ ንግድ ፈጣንና ቀልጣፋ የሎጀስቲክስ አገልግሎት ከሚፈልጉ የግብርና ምርቶች መካከል አንዱ በመሆኑ በዚህ
ክፍል የጫት ወጪ ንገድ የሎጀስቲክስ ሁኔታን በሚገባ ለመፈተሸ ተሞክሯል፡፡ በሎጀስቲክሱ ረገድ ያለውን ተግዳሮት
በአግባቡ ለመረዳት እንዲያስችል ከኢትዮጵያ አየር መንገድ፣ ከግል የአውሮፕላን ኦፕሬተሮች፣ከኢትዮጵያ ፖስታ አገልግሎት
ድርጅት፣ ከክልል ንግድና ትራንስፖርት ቢሮዎች፣ ከጫት ላኪዎች እና ከጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤቶችና መቆጣጠሪያ ጣቢያዎች
የተሰበሰቡ መረጃዎችን በመተንተተን እንደሚከተለው ቀርቧል፡፡

2.4.1. የኢትዮጵያ አየር መንገድ

ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ጋር በተደረገው ውይይት የጫት ተቀባይ ሀገራት ከጊዜ ወደ ጊዜ ብዛታቸው በአንዳንድ ሀገራት
ክልከላ ምክንያት እየቀነሰ የመጣ ሲሆን ይህም በአውሮፕላን ወደ ውጪ በሚላከው የጫት ምርት መጠን ላይ የመቀነስ
አዝማሚያ እየታየ ስለመሆኑ እና በሀገራችን የውጪ ምንዛሬ ግኝት ላይ የራሱን አሉታዊ ተጽዕኖ ስለማሳረፉ ለመረዳት
ተችሏል፡፡ አየር መንገዱ ቅድሚያ ከሚሰጣቸው የሀገር ውስጥ የግብርና ምርቶች መካከል ጫት አንዱ ስለመሆኑ እና ከፍተኛ
የገቢ ምንጭ ለአየር መንገዱ የሚያስገኝ ስለሆነ ከፍተኛ ትኩረት ስለሚሰጠው በሎጀስቲክስ በኩል ችግር የማይገጥም መሆኑ
ግንዛቤ ተወስዷል ፡፡

በርካታ ጫት ላኪዎች ጫት ወደ ተለያዩ ሀገራት ለመላክ ፍላጎት እንዳላቸው ሲያሳውቁ አየር መንገዱ በቅድሚያ በየሀገራቱ
ባሉት ወኪሎቹ አማካኝነት ጫት ሀገራቱ ጫት እንዲገባ የሚፈቅዱ ወይም የሚከለክሉ ስለመሆኑ ቅድሚያ የማጣራት ስራ
የሚያከናውን ስለመሆኑ አስረድቷል፡፡ በዚሀም ሒደት በርካታ ሀገራት እንደ ናይጄሪያ፣ እንግሊዝ፣ ኮሪያ፣ ቱርክ፣ ሆንግ ኮንግ፣
ቻይና እና የመሳሰሉት ሀገራት ጫት ወደ ሀገራቸው እንዳይገባ የሚከለክሉ በመሆናቸው ምክንያት የሀገራትን ህግ መጠበቅ
ስለሚገባ አየር መንገዱ ማጓጓዝ የማይችልበት ሁኔታ መኖሩ ግንዛቤ ተወስዷል፡፡
አየር መንገዱ ወደ ወጪ ለሚያጓጉዘው የጫት ምርት የማጓጓዣ ክፍያ የሚቀበለው በኢትዮጵያ ብር ሲሆን ሌሎች የግል
ኦፕሬተሮች ግን ለሰጡት የትራንስፖርት አገልግሎት ለማጓጓዣ የሚያስከፍሉት በውጪ ምንዛሬ ስለመሆኑ ለመረዳት
ተችሏል፡፡ ይህም እንደ ሀገር ከትራንስፖርት አገልግሎት መገኘት ያለበት የውጪ ምንዛሬ ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ አሳድሯል፡፡

2.4.2 የግል አየር መንገድ

ጅቡቲ እና ሶማሊያ ከፍተኛ ፍላጎት እና የንግድ ፍሰት ያለ ቢሆንም ለዚሁ ስራ የሚመቹ አውሮፕላን ያሏቸው በተለይም የግል
ኦፕሬተሮች ውስን መሆናቸው እንደ ክፍተት የታየ ሲሆን ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ በኢትዮጵያ ሲቪል አቪዮሽን ባለስልጣን
በተወሰዱ ልዩ ውሳኔዎች የተወሰኑ ኦፕሬተሮች እንዲሳተፉ ተደርጓል፡፡ ነገር ግን በሶማሊያ ሲቪል አቪየሽን በኩል የማረፊያ
ፈቃድ ለአየር መንገዱ ሳይሆን ለጫት ተቀባይ ስም ተጠቅሶ የሚሰጥ በመሆኑ ይህም በግል ኦፕሬተሮች ተወዳዳሪና ተሳታፊ
እንዳይሆኑ ክልከላ ማድረግ ብቻ ሳይሆን ጫት ገበያው በሚፈልገው መጠን ከሀገር እንዳይወጣና ሀገሪቱ ከዘርፉ በምታገኘው
ጥቅም ላይ ከፍተኛ ተግዳሮት እየፈጠረ እንደሚገኝ ግንዛቤ ተወስዷል፡፡

የግል ኦፕሬተሮች በሲቪል አቪየሽን ልዩ ውሳኔ በጫት ማጓጓዝ የተሳማሩ ቢሆንም በህጉ መሰረት እነዚህ ኦፕሬተሮች ለሀገር
ውስጥ በረራ ብቻ መስራት ያለባቸው መሆኑ የተደነገገ በመሆኑ ስራው ዘላቂና አስተማማኝ እንዳይሆን ተፅእኖ እንዳይፈጥር
ስጋት ፈጥሯል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም በበረራ ስራ መሰማራት የሚችለው አውሮፕላን ከ25 ዓመት በላይ አገልግሎት የሰጠ
አውሮፕላን በንግድ ስራ ውስጥ እንዳይሰማራ የሲቪል አቪየሽን ህግ የሚከለክል በመሆኑ አዳዲስ አውሮፕላን ለመግዛት
የአቅምና የውጪ ምንዛሪ አቅርቦት ውስንነት ትልቅ ማነቆ እንደሆነ ተመላከቷል፡፡ በሌላ በኩል በኬንያ በዚሁ ስራ የተሰማሩ
የግል ኦፕሬተሮች ይህ አይነት ችግር እንዳይገጥማቸውና መንግስት ለዘርፉ በሰጠው ልዩ ትኩረት ምክንያት የተለያዩ ድጋፎችን
የሚሰጥ መሆኑን በዘርፉ ከተሰማሩ ባለሙያዎች ገለፃ መረዳት ተችሏል፡፡

የግል ኦፕሬተሮች የማጓጓዣ አገልግሎት ለሰጡበት የማስጫኛ ክፍያ (ፍሬት) ከኬንያ ለተከራዩት ካምፓኒ በባንክ በኩል
በቀጥታ መክፈል ሲገባቸው በሀገር ውስጥ ዶላር የማግኘት ችግር በመኖሩና የተመቻቸ የባንክ አገልግሎት የማይሰጥ በመሆኑ
የአውሮፕላን በረራ አገልግሎት ደግሞ ፍጥነትንና ቅልጥፍናን የሚጠይቅ ስለሆነ የማስጫኛ ክፍያው በተቀባዩ በማራገፊያ ቦታ
በቀጥታ እንዲፈፀም አስገዳጅ ሁኔታ በመፈጠሩ በዚህም ሂደት በውጪ ሀገር የሚከፈለው ዶላር መጠን ማስጫኛው
ሰማኒያ(80%) ሀገር እየቀረ ቀሪው ሃያ(20%) በመቶ ብቻ ወደ ሀገር ውስጥ እንደሚገባ ከተደረገው ማብራሪያ መገንዘብ
ተችሏል፡፡ የግል ኦፕሬተሮቻችን ከኪራይ ነፃ የሆነ የራሳቸው አውሮፕላን ቢኖራቸው በጫት ትራንስፖርት አገልግሎት በውጭ
ምንዛሪ የሚገኘው የጭነት ክፍያ ሙሉ በሙሉ ወደ ሀገር ውስጥ ሊገባ እንደሚችል የጥናት ቡድኑ መገንዘብ ችሏል፡፡

2.4.3 የኢትዮጵያ ፖስታ የጫት ወጪ ንግድ አገልግሎት


ከፖስታ ጥቅል የጫት ወጪ ንገድ ጋር ተያይ የኢትዮጵ ፖስታ ድርጅት ከጫት ላኪዎች ፈትሾና መዝኖ በመረከብ ጫት ላኪዎች
አ/አ ኤርፖርት ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት ቀርበው የጉምሩክ ሥነ-ሥርዓት በመፈጸም መልቀቂያ ሲሰጣቸው ለፖስታ ድርጅት
በማቅረብ ወደ መዳረሻው አገር በአየር ትራንስፖርት እንዲላክበት የሚደረግበት አሠራር ተግባራዊ ሲያደርግ ቆይቷል፡፡
በተመሳሳይ በድሬዳዋ ፖስታ ቤት ቅ/ጽ/ቤት እና በድሬዳዋ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት ተመሳሳይ አገልግሎት ሲሰጥ ቆይቷል፡ የከጥር
1 ቀን 2013 ዓ.ም ጀምሮ የጫት ወጪ ንግድ ተያይዞ ከተከሰቱ የማጭበርበር ድርጊቶች በኢትዮጵያ ፖስታ ላይ ተጠያቂነትና
የውጭ ምንዛሪ ባለዕዳ በመደረጉ አገልግሎቱ ሙሉ በሙሉ እንዲቆም መደረጉ መረዳት ተችሏል፡፡ ከጫት ወጪ ንገድ አሠራር
ጋር ጫት ወደ ከለከሉ አገሮች በእስራኤል በኩል ወደ አሜሪካና ሌሎች አገሮች የፖስታ አላላክ ስህተት ነው በሚል ስተካክሎ
(Redirecte) እንዲተላለፍና ለተቀባይ ተደራሽ የተደረገበት የአገልግሎት ክፍያ ኢትዮጵያን ተጠያቂ እያደረገ መሆኑ
አስረድተዋል፡፡ ከዓለም አቀፍ የፖስታ ህብረት ድርጅት ጫት የሚከለክሉ አገሮች መረጃ ከጊዜ ወደ ጊዜ አየጨመሩ
መምጣታቸው( አሜሪካ፣ካናዳ፣ናይጄሪያ ወዘተ) የተገለጸ ሲሆን ከዚሁ ጋር በተያያዘ በፖስታ ጥቅል ወደ ውጭ አገር በተላከ
ጫት ምክንያት የኢትዮጵያ አየር መንገድ ማስጠንቀቂያ የደረሰው በመሆኑ የፖስታ አገልግሎት ሥራ ላይ ችግር እንደተፈጠረ
ከኃላፊዎች መረዳት ትችሏል፡፡ በሌላ መልኩ ከዚሁ የጫት ወጪ ንግድ ጋር ተያይዞ የሥነ ምግባር ችግሮች
ማጋጠማቸው፣አንዳንድ ጫት ላኪዎች የጫት ዓይነት መግለጫ ተቀይሮና ሽፋን በማግኘት እንዲላክላቸው
መፈለጋቸው፣የፖስታ ቤት ሰራተኞች ከጫት ላኪዎች ጋር በመመሳጠር የጫት መግለጫ፣ አድራሻና መዳረሻ መረጃ በማዛባት
ሲልኩ መገኘታቸውን የፖስታ ድርጅቱ አስረድቷል፡፡ ጫት ወደ ከለከሉ አገሮች በፖስታ ጥቅል ጫት ሊላክ ሲል የአየር መንገድ
ሴኩሪቲ በተደጋጋሚ ችግሮች በመከሰታቸው የኢትየጵያ ፖስታ ድርጅት በጫት አድራሻ እርማት እና የማድረስ አገልግሎት
ሽፋን የውጭ ምንዛሪ ክፍያ ተጠያቂነት ትርፋማነቱ ላይ የተፈጠረውን አደጋ እንዲቆም ማድረግ ግድ ያለበት ደረጃ ላይ
በመደረሱ የጫት ወጪ ንገድ የፖስታ ቤት አገልግሎት እንዲቋረጥ መደረጉን መረዳት ተችሏል፡፡

2.4.4 የጫት ሚዛን ልኬት

በየብስም ሆነ በአየር ወደ ውጪ የሚላከው የጫት ምርት የክብደት መጠኑን የማረጋገጥ ሂደቱ በማኑዋልና በዲጂታል ሚዛኖች
የሚከናወን መሆኑን መገንዘብ ተችሏል፡፡ በተለይም በዚህ ሂደት በዲጂታል ሚዛን የሚሰጠው አገልግሎት በማኑዋል
ከሚሰጠው የሚዛን አገልግሎት ጋር ሲነፃፀር አስተማማኝነቱ የተሸለ መሆኑን የጥናት ቡድኑ መረዳት ችሏል፡፡ ነገር ግን
የዲጅታል ሚዛኑም ቢሆን በሁሉም ቦታ የራሱ ደረሰኝ ያለውና መረጃውን በሲስተም መዝግቦ በመያዝ በኩል ውስንነት ያለበት
መሆኑን መለየት ተችሏል፡፡

2.4.5 የጭነት ተሸከርካሪ የውጪ ጫት ጭነት ውልና ክፍያ አፈጻጸም

የጫት ላኪዎች የራሳቸው የጭነት ተሸከርካሪ ያላቸው እንዳሉ ሁሉ በርካታ ላኪዎች ጫት ወደ ውጪ ለመላክ ተሸከርካሪዎችን
በኪራይ እንደሚጠቀሙና ለዚህም በቀን ለአንድ ጉዞ እስከ 15000 (አስራ አምስት ሽህ ብር) እንደሚከፈልና የጉዞው መጠንም
እንደየሁኔታው አንድ ላኪ በቀን ከአንድ እስከ ሶስት መኪና እንደሚከራይ የዳሰሳ ጥናቱ አመላክቷል፡፡ ከዚህ ጋር ተያይዞ
ላኪዎች የትራንስፖርት ወጪ የሚከፍሉትን ክፍያ ብር ለማዳንና የጫት ወጪ ንግድ ትራንስፖርትን ለማሳለጥ የራሳቸውን
መኪና ለመግዛት ጥያቄ አቅርበው ያልተፈቀደላቸው መሆኑን በሉላ ጎን ደግሞ የውጪ ምንዛሪ ለማያስገቡ ሌሎች
የኢንቨስትመንት ሴክተሮች እስከ አራት መኪና መግዛት እንዲችሉ ፈቃድ እንደሚሰጣቸው በመግለፅ ያላቸውን ቅሬታ ያነሳሉ፡፡

2.4.6 የመጫኛና የመነሻ ቦታ

የመጫኛ ቦታን በተመለከተ በቦሌ ኤርፖርትም ሆነ በድሬዳዋ ኤርፖርት በአካል በመገኘት በተደረገው ምልከታና በተገኘው
መረጃ መሰረት ጫት በላኪው አማካኝነት በአይሱዙ ተጭኖ ኤርፖርት ከደረሰ በኋላ በዕቃ አስተላላፊው በኩል የጫት ምርት
ወደ ውጪ እንዲላክ የጉምሩክ ስነ-ስርዓት የተፈጸመበት ሰነድ ቀርቦ የላኪው ተወካይ፣ የሲቪል አቪየሽን ተወካይ፣ የጉምሩክ
ተወካይ፣ የአየር መንገድ ተወካይ እና በላኪው የተዘጋጀው የሰው ኃይል በጋራ በመሆን ጫቱን ካቀረበው አጓጓዥ ጋር በምድር
ድጂታል ሚዛን እንዲመዘን በማድረግ ክብደቱና የጥቅሉ ብዛት ተመዝግቦ ወደ ኤክስሬይ ማሽን እንደሚተላለፍና መረጃውም
በጉምሩክ የፍተሻ ውጤት መግለጫ ላይ ሰፍሮ ዕቃው በአውሮፕላን እንዲጫን እንደሚደረግ የጥናት ቡድኑ ተገንዝቧል፡፡

2.4.7 የጫት ላኪዎችና ተቀባዮች ሚና

የጥናት ቡድኑ በጫት ወጪ ንግድ የሚሳተፉ የጫት ላኪዎችና ተቀባዮችን ሚና ለመለየት ከጫት ላኪዎች ጋር ባደረገው
ውይይት ሚናቸው የሚከተሉት መሆናቸውን መረዳት ችሏል፡-

2.4.7.1 የጫት ላኪዎች ሚና


o ከጫት ወጪ ንግድ ጋር ተያይዞ ላኪው ህጋዊና ተቀባይነት ያለው የንግድ ውሎችን (Sales Contrat) ማዘጋጀት
o በንግድ ውሉ መሰረት የኤልሲ (Letter of Credit) ወይም ሌላ የሽያጭና ግዥ ስርዓት ማጠናቀቅ
o በተጠናቀቀው የሽያጭና ግዥ ስርዓት መሰረት የባንክ ፈቃድ ማውጣት
o በንግድ ውሉ ላይ የተጠቀሰውን የማጓጓዣ አይነት ማዘጋጀት ወይም እንዲዘጋጅ ማድረግ
o ለወጪ ንግድ የሚዘጋጀውን የጫት ምርት ደረጃውን ጠብቆ እንዲቀርብ ማዘጋጀት
o ከተመረተበት ቦታ ወደሚጫንበት ቦታ ማጓጓዝ
o የጉምሩክ ፎርማሊቲ እዲጠናቀቅ አስፈላጊውን ሰነድ አዘጋጅቶ ፎርማሊቲውን ለማጠናቀቅ ሰነዱን ለጉምሩክ
አስተላላፊ ማስረከብና
o ዕቃው እንዲቀርብ አድርጎ በጉምሩክ አስፈትሾ ለዕቃው ተቀባይ መላክ ዋና ዋናዎቹ ናቸው፡፡
2.4.7.2 የተቀባይ ሚና
o ከጫት ወጪ ንግድ ጋር ተያይዞ ተቀባዩ ህጋዊና ተቀባይነት ያለው የንግድ ውሎችን (Sales Contrat) ማዘጋጀት
o በንግድ ውሉ መሰረት የኤልሲ (Letter of Credit) ወይም ሌላ የሽያጭና ግዥ ስርዓት ማጠናቀቅ
o በተጠናቀቀው የሽያጭና ግዥ ስርዓት መሰረት የባንክ ፈቃድ ማውጣት
o በንግድ ውሉ ላይ የተጠቀሰውን የማጓጓዣ አይነት ማዘጋጀት ወይም እንዲዘጋጅ ማድረግና
o ጭነቱ እንዲከናወን ትዕዛዝ መስጠት ይጠቀሳሉ፡፡

ከዚህ በተጨማሪ ከጫት ወጪ ንግድ ጋር ተያይዞ ባለው ነባራዊ ሁኔታ ተቀባዩ የንግድ ውሎችን (Sales Contrat)
የሚያዘጋጀው በራሱ መልካም ፈቃድና በሞኖፖሊ ከመሆኑም በላይ ላኪዎችንም ሆነ አጓጓዥ ድርጅቶችን መምረጥ፣
የማራገፊያ ቦታ (Landing Certificate) ማግኘትን፣ የግዢ ዋጋ መወሰንን የሚያካትት ወደ አንድ ጎን ያጋደለ እና ሰፊ ሚና
እየተጫወተ እንደሚገኝ የጥናት ቡድኑ ከተደረገለት ማብራሪያ መረዳት ችሏል፡፡

2.4.8 በተቀባይ ሀገር ያሉ የኢትዮጵያ ኤምባሲዎች ሚና

በጫት ተቀባይ ሀገር የሚገኙ የኢትዮጵያ ኤምባሲዎች ከጫት ንግድ ጋር በተያያዘ የሚታዩ ችግሮች ሲከሰቱ ብቻ ሳይሆን
ከመከሰታቸውም በፊት የንግድ ስርዓቱ የተሳለጠ እንዲሆን ምቹ ሁኔታ መፍጠር ይጠበቅባቸዋል፡፡ ነገር ግን የጥናት ቡድኑ
ባደረገው የዳሰሳ ጥናት መሰረት በሶማሊያ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ከኢትዮጵያ ላኪዎች በኩል የሚቀርብለትን
የተቀባይና የላኪ ግንኙነት ችግር በመፍታት ረገድ ክፍተቶች የሚስተዋሉበት ሲሆን እንደማሳያም ኤምባሲው የኢትዮያ
ላኪዎችን በእኩል አለማስተናገድና በተቀባይ ሀገር ካሉ የጫት ተረካቢዎች መካከል ለተወሰኑት ብቻ በመወገን እና ተገቢ
ባልሆነ አግባብ ድጋፍ በማድረግ የጫት ወጪ ንግዱ ከትክክለኛው መስመር እንዲወጣ ያደረገ ሚና ተጫውቷል የሚል ከፍተኛ
ቅሬታ በላኪዎች በኩል ቀርቧል፡፡ በተጨማሪም ከሶማሊያ አቪየሽን ባለስልጣን የአውሮፕላን ማረፊያ ፈቃድ አሰጣጥ ጋር
በተያያዘ ያሉ ችግሮች፣ ከወቅታዊ የዋጋ ጥናት እንዲሁም ፍትሐዊ የገበያ ማፈላለግና ትስስር ከመፍጠር አንፃር አስገላጊው
ድጋፍ እየተሰጠ እንዳልሆነ ግንዛቤ ተወስዷል፡፡

የጥናት ቡድኑም ይሄንን ጉዳይ ኤምባሲን በግንባር አግኝቶ ማነጋገር ባለመቻሉ እውነታነቱ በውጪ ጉዳይ ሚ/ር በኩል
ተጣርቶ መፍትሄ መስጠት እንደሚያስፈልግ የዳሰሳ ጥናቱ ያመላክታል፡፡

2.5 የአወዳይ የጫት ንግድ እንቅስቃሴ

የጫት የወጪ ንግድ ሁኔታን ለማጣራት የጥናት ቡድኑ 24/1/2014 ዓ.ም የጫት የወጪ ንግድ እቅስቃሴ ወደሚደረግበት
አወዳይ የጫት ማዕከል ድረስ በመንቀሳቀስ በጫት ንግድ ላይ የተሳተፉትን ላኪዎችን፣ አቅራቢዎችን፣ ገበሬዎችንና የጫት ንግድ
የሚካሄድበትን መጋዘን በአካል በመገኘት ጉብኝት አድርጓል፡፡በጉብኝቱ ወቅትም የጥናት ቡድኑ የሚከተሉትን ዝርዝር
ሁኔታዎች መገንዘብ ችሏል፡-

 ከአወዳይ የሚመረተው ጫት ተዘጋጅቶ ወደ ሁለት የተለያዩ አቅጣጫዎች ማለትም ወደ ሶማልያና ጅቡቲ


እንደሚላክና ይሄንን ጫት ወደ ጅቡቲ በመላክ የሚሳተፉ ድርጅቶች 6 ሲሆኑ ወደ ሶማልያ ደግሞ አስር ድርጅቶች
ጫት እንደሚልኩ ተገልጸዋል፡፡

 በአካባቢው ጫት በአመት ውስጥ ከ2 እስከ 3 ጊዜ የሚመረት ሲሆን ተመርተው የሚላኩ የጫት አይነቶችም 3
አይነት ናቸው፡፡ ስማቸውም ሃዳር ጫት፣ ኡረታ ጫትና ሃርቡላ ጫት ይባላሉ፡፡
 እነዚህም ጫቶች እንደአይነታቸው ዋጋቸውም የሚለያይ ሲሆን ሃዳር ከ400 ብር ጀምሮ እስከ 2500 ብር ድረስ
ይሸጣል፡፡ ቡረታ ጫት ከ1500 ብር እስከ 7000 ብር ይሸጣል፡፡ ሌሎች የጫት አይነቶች ደግሞ 1500 እስከ 3000
ብር የሚሸጡ ሲሆን ጥቂት የጫት አይነቶች እስከ 20000 ብር ድረስ ይሸጣሉ ነገር ግን አልፎ አልፎ የሚገኙ
ናቸው፡፡

 ይህ ከላይ የተጠቀሰው የጫት ዋጋ በክረምትና በበጋ የሚለዋወጥ መሆኑን

 በተደረገው ምልከታ የጫት ማዘጋጃ ቦታ ዕጥረት መኖሩና ቦገኝም ከግለሰቦች ላይ በውድ ዋጋ የሚከራዩ ሲሆን ከዚህ
ጋር ተያይዞ ከቤቶች የጥራት ችግር ጋር ተያይዞ በምርቱ ጥራት ላይም አሉታዊ ተፅዕኖ እያሳደረ እንደሚገኝ መገንዘብ
ተችሏል፡፡

 በጫት ዋጋ አወሳሰን ላይ ገዥዎቹ አስቀድመው ተነጋግረው እንደሚመጡና ገበሬው በነፃ ገበያ ስርዓት መሰረት
እንዳይገበያይ በማድረግ አማራጭ እያሳጡዋቸው እንደሚገኙና እነሱ በሚወስኑላቸው ዋጋ ብቻ ለመሸጥ እየተገደዱ
መሆናቸው

 ከአወዳይና አካባባው በቀን 253000 ኪ፣ግ የሚጠጋ የጫት ምርት ወደ ገበያ እንደሚገባና ከዚህ ውስጥ 160000
ለሀገር ውስጥ ፍጆታና ቀሪው93200 ለውጪ ንግድ እንደሚቀርብ፤
 የምርት አቅርቦት ሠንሰለቱ በአርሶ አደሩ እና በላኪው መካከል ቀጥተኛ ግንኙነት የሌለ ሲሆን የአቅርቦት ሰንሰለቱም
በተለያየ ደረጃ ባሉ ደላሎች የተያዘ ነው፡፡ይህም፡-
o አርሶ አደሩ ቆኜ(ደላላ) ሰፈራ( አቅራቢ) ላኪ ሲሆን፡
▪ ቆኜ(ደላላ) አርሶ አደሩን እና አቅራቢውን የማገናኘት ሚና የሚጫወት ሲሆን ከአርሶ አደሩ
ሽያጭ ላይ የ10 በመቶ ድርሻ የሚወስድ ስለመሆኑ ለመረዳት ተችሏል፡፡

 የሀገር ውስጥ ነጋዴዎች ቁጥር 234 ሲሆን ወደ ውጪ የሚልኩት ነጋዴዎች ግን 57 መሆናቸውና እነዚህ ነጋዲዎች
በወጪ ንግድ በተሰማሩ 15 ላኪዎች ስር ተሰማርተው የሚንቀሳቀሱ መሆናቸውና ከመጨረሻ ጫት ተቀባዮች ጋር
ግንኙነት እንደሌላቸው
 የጫት ዋጋ የሚወሰነው በአርሶ አደሩ ሳይሆን በምርት ሰንሰለቱ ባሉ ደላሎች እና ላኪዎች የሚወሰን ስለመሆኑ
ለመረዳት ተችሏል፡፡
 ገበሬው የጫት ምርቱን ለገዥው የሚሸጠው በውል ሳይሆን በካሽ ሲሆን ልኬቱም የጫቱ መጠን በሚዛን የሚለካ
ሳይሆን በእስር(በአንድ እቅፍ) ነው፡፡ ነገር ግን እብደ አንድ ኪሎ ግራም ተቆጥሮ የሚሸጠው አንድ እስር ጫት
ክብደቱ በግምት ከ4-5 ኪሎ ግራም መሆኑንና በሸጫ ውጋው ደግሞ እንደ ጫቱ አይነት ከ400 ብር እስከ 2500 ብር
ይሆናል፡፡
 አርሶ አደሩ ከዚህ ቀደም ሽያጩ ሙሉ ለሙሉ በዱቤ የነበረና በወቅቱ ክፍያ የማያገኝ በመሆኑ ለኪሳራ የዳረገ ነበር፡፡
ይህም በአብዛኛው ለምርቱ አቅርቦት ከፍተኛ አሉታዊ ተጽዕኖ ያሳደረ የነበረ ሲሆን በአሁኑ ወቅት ከፍተኛ መሻሻል
ያለበት እና የእጅ በእጅ ሽያጭ እየተከናወነ የሚገኝ ቢሆንም አሁንም የዱቤ ሽያጩ ሙሉ ለሙሉ ያልቀረና የእጅ
በእጅ ሽያጩም አርሶ አደሩ ገንዘቡን እያገኘ ያለው በቀጣይ ቀን ሌላ ምርት ሲያቀርብ ስለመሆኑ ታይቷል፡፡
 በጫት ንግድ እንቅስቃሴ ላይ ገበሬውን ቨተጠቃሚ የሚያደርግ የህግ ማዕቀፍ የሌለ መሆኑና ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ግን
በኦሮሚያ ክልል ጫትን አስመልክቶ ገበሬውን ከጫት ገበያ ጋር የሚያስተሳስር ህግ ማውጣቱ፤

 ገበሬወውን በጫት ንግድ እንቅስቃሴ ውስጥ ሊደግፉ የሚችሉ ፋሲሊቲዎችም ሆነ ሴክተር መስሪያ ቤቶች
በአቅራቢያ የሌሉና ውክልናም ያልተሰጣቸው መሆኑ፤

 አልፎ አልፎ ጥቂት ሻጮችና ገዢዎች በዱቤ የጫት ቅብብሎሹን ካከናወኑ በኋላ ከገዢው ጫቱ የተገዛበት ብር
ለገበሬው የማይከፈለው ሲሆን በተለይ ደግሞ ከገበሬው ላይ የሚገዡ አቅራቢዎች በዚህ ሂደት ተጎጂዎች
መሆናቸው፤

 ገበሬው ከማሳው ምርቱን ወደ ገበያ ለማቅረብ የትራንስፖርትና የመሰረተ ልማት ችግር ያለበት መሆኑና አወዳይ
ከፍተኛ የጫት አቅራቢ ሆና እያለ የራሱ የሆነ መናህሪያና በቂ የትራንስፖርት ቅርቦትና ስምሪት የሌለ መሆኑ፤

 በአወዳይ የጫት ንግድ እንቅስቃሴን ለማሳለጥ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የጫት
ምርት የገቢያ ማዕከል ግንባታ መጀመሩን የጥናት ቡድኑ የተመለከተ መሆኑ

ጅግጅጋ

 ቡድኑ ምልከታውን በመቀጠል በ25/01/2014 ዓ.ም ለመስክ ምልከታ ወደ ጅግጅጋ አቅንቶ የጅግጅጋ
ቅ/ፅ/ቤትንና የሶማሌ ንግድና ኢንዱስትሪ ቢሮን በማነጋገር በጫት ወጪ ንግድ ዙሪያ የሚከተሉትን ጭብጦች
መገንዘብ ተችሏል፡፡

 በጅግጅጋና አካባቢው በርካታ የክልል ፍተሻ ኬላዎች እንዳሉና በየኬላዎቹ ላይ የፅዳት እየተባለ ከ3 ብር- 6 ብር
በኪሎ እንደሚከፈልና ከኬላ ኬላ የክፍያ መጠኑ እንደሚለያይ ይህም በጫት ላኪዎች ላይ ቅሬታና እንግልት
እንደፈጠረ ተነስቷል፡፡

 የጫት እንቅስቃሴው የሚካሄደው በጫት ላኪው ሳይሆን በተወካዮ አማካኝነት እንደሚከናወንና አሰራሩም ከቀኑ
10፡00 ጀምሮ እሰከ ምሽቱ 4፡00 እንደሚቀጥል ተገጿል፡፡

 የአሰራር ሂደቱን በተመለከተ የጫት ላኪው ወይም ተወካዩ አስፈላጊውን የጉምሩክ መብት ማስፈፀሚያ ሰነዶች
ማለትም የንግድ ፈቃድ፣ ተወካይ ከሆነ ውክልና፣ የጉምሩክ አስተላላፊ ውክልና ስምምነት፣ ፓኪንግ ሊስት፣
ኢንቮይስ፣ ባንክ ፐርሚት፣ ከጉምሩክ ዲክላሬሽን ጋር ሲያቀርብ ኢኤክስ-8 ዲክላሬሽን ተዘጋጅቶ ጫት የጫነ መኪና
ሲመጣ መጀመሪያ ባዶውን ተመዝኖ ክብደቱ ተይዞ መኪናው እንደገና ጫቱን ጭኖ ተመዝኖ የክብደት መጠኑ
ይታወቅና ባዶውን የተመዘነው መኪና ያለው ክብደት ከተቀነሰ በኋላ የሚመያው የተጣራ ክብደት የጫቱ ክብደት
እንደሆነ ተወስዶ ለመኪናው ቲ-1 ተዘጋጅቶለት ከመጀመሪያው ኢኤክስ-8 እየተቀናነሰ ጭነቱ ከሀገር እንዲወጣ
እንደሚደረግና ይህ ሂደት ላኪ በባንክ ፐርሚት ላይ ያስመዘገበው የጫት መጠን እስኪጠናቀቅ ድረስ የሚሰራ መሆኑ
ግንዛቤ ተወስዷል፡፡

2.6 የኮንትሮባንድ ጫት የሚጓጓዝበት ሁኔታ

የኮንትሮባንድ ጭነት የሚጓጓዝባቸው ማጓጓዣዎች በተመለከተ በአካባቢው ያሉ ማንኛውንም የማጓጓዣ ዘዴ


እንደሚጠቀሙ በተለይም ግመል፣ አህያ፣ በሰው ሸክም ከፍ ሲልም ባጃጅና 4WD ተሸከርካሪዎች እዲሁም በመስመር
የሚንቀሳቀሱ ሰውንም ሆነ ዕቃ የሚያጓጉዙ የጭነት ተሸከርካሪዎች የተሰማሩበት መሆኑን ማወቅ ተችሏል፡፡ በእንስሳ፣
በሰውና በተለያየ ተሸከርካሪ ከድሬዳዋ ተነስቶ ቢያቆቤቤ ከመድረሱ በፊት በግራና በቀኝ በኩል እንዲሁም ደወሌ
ከመድረስ በፊት በቀኝ በኩል ከጥቁር አስፋልት በመውጣት ኮንትሮባንድ ጫት ከሀገር እንደሚወጣ፣ በጅግጅጋ መስመር
ደግሞ መነሻውን ጭናቅሰን አድረጎ በመረር ቀበሌ ኤሌማሃል ቀበሌ፣ መካኒሳ ኦሮም፣ ዳሮናጅ/አዎበሬ፣ በሮማ፣ በቶጎጫሌ
አድርጎ ወደ ሀርጌሳ፣ አወዳይ መነሻ በማድረግ ጫት በባቢሌ በኩል በፊቅ መስመር አድረጎ የጎዴን ዞን በማለፍ ወደ ሶማሌ
ላንድ እንዲሁም በበዴሳ፣ በመቻራ መስመር ወደ ጎዴ ዘን በመሻገር ወደ ሶማሌ ላንድ ይወጣል፡፡ በዚህ የማጓጓዝ ሂደት
ውስጥ አጓጓዦች እስከ አንድ ሽህ ብር ድረስ እየተከፈላቸው ህገ ወጥ ጫትን እንዲያሳልፉ የሚያደርጉ በመሆኑ
የኮንትሮባንድ ንግድ እየናረ እንዲሄድ እድል ፈጥሯል፡፡ ኮንትሮባንድን በሀገር ውስጥ ሽያጭ ብዙ ግብር የሚከፈልበት
በመሆኑ የጫት ምርት ወደ ውጪ እንዲላክ የነጋዴዎች ከፍተኛ ፍላጎት ነው፡፡ ወደ ውጪ የሚላከው ጫት በህጋዊ
መንገድና በኮንትሮባንድ ወደ ውጪ እንደሚወጣ መረጃዎች እንደሚከተለው ያመላክታሉ፡-

 በተለይም ለጠረፍ አካባቢ ህብረተሰብ ከሚፈቀደው ጫት ጋር ኮንትሮባድ ጫት የሚወጣ ስለመኖሩ፤

 በአካባቢው ስራው የሚራው ዋና ላኪው ቀርቦ ሳይሆን በተወካዮቻቸው አማካኝነት መሆኑን፤

 ከጅግጅጋ ተነስቶ ወደ ሶማሌ ላንድም ወደ ጅቡቲም ለሚወጣ ጫት በተለያዩ ቦታዎች (በከተማ መስተዳድር፣ በዞን፣
በወረዳ) የማዘጋጃ ቤት ፅዳት እየተባለ ፍፍያ የሚጠየቅ መሆኑ፤

 በባንክ ፐርሚት የተፈቀደ የጫት መጠን በአንዴ ወደ ውጪ የማይላክ በመሆኑ በጉምሩክ በኩል የማቀናነስ ስራ
አስቸጋሪ እየሆነ መምጣቱን፤

 የማቀናነስ አሰራሩ እያንዳንዱን የሚመጣ ጭነት መዝኖ የሚዛኑን መጠን በመለየት ሰነድ ላይ በማስፈር ጭነቱን ወጪ
ማድረግ ጊዜ ወሳጅ መሆኑንና ይሄንን ለማስቀረት ጫረቱ ከመነሻው ተመዝኖና ክብደቱ ታውቆ ሰነድ ተዘጋጅቶለት
እንዲመጣ በተደጋጋሚ የተገለፀ ቢሆንም ተግባራዊ ሊሆን አለመቻሉንና አሰራሩ በባህላዊ ደረጃ የሚገኝ መሆኑን፤

 በጫት ንግዱ ሰንሰለት ቅንጅት አለመኖሩን በዚህም የተነሳ ሙሉ ቀን ጫት ይመጣል እየተባለ ሲጠበቅ እንደሚውልና
ይህም ከፍተኛ የሃብት ብክነት ያስከተለ መሆኑን፤
 የጫት የወጪ ንግድን በሚመለከት አንድም ጊዜ የባለድርሻ አካላት የጋራ መድረክ ተዘጋጅቶና ግንኙነት ተፈጥሮ
እንደማያውቅና በዘርፉ ላይ ያሉ ችግሮች ተለይተው መፍትሄ ስለሚፈለግበት ሁኔታ ውይይት ተደርጎ እንደማያውቅ፤

 የጫት የወጪ ንግድ በየመንገዱ ችግሮች ሲያጋጥሙ ችግሩ እዲፈታ በኃላፊነትና በባለቤትነስ ስሜት የሚጠየቅ አካል
አለመኖሩና በጉምሩክ በኩል ወደተለያዩ ቢሮዎች ስልክ በመደወልና በተደጋጋሚ ውትወታ ችግሩ እንዲፈታ
እንደሚደረግ ቡድኑ ከጉምሩክ ቅ/ፅ/ቤቱ መረዳት ችሏል፡፡

ከዚህ ጉዳይ ጋር በተያያዘ የጥናት ቡድኑ የሶማሌ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ንግድ ቢሮ በመሄድ የቢሮ ኃላፊውንና
ምክትል ቢሮ ኃላፊውን አነጋግሯል፡፡ በዚህም መሰረት የሚከተሉት ጭብጦች ከኃላፊዎች ማብራሪያ ተሰጥቶባቸዋል፡፡

 አካባቢ በጣም ሰፊ አካባቢ በመሆኑ ምክንያት ከጎረቤት ሀገራት ጋር በጣም ሰፊና ከ1000 ኪ.ሜ በላይ ድንበር
ያለ በመሆኑና ድንበሩ ሜዳማ እና ለቁጥጥር አስቸጋሪ በመሆኑ ከወጪ ጫት ንግድ ጋር ተያይዞ የኮንትሮባንድ
ችግር እንደሚስተዋል፤

 በጫት እንቅስቃሴ ውስጥ የሚታዩት በሰነዱ ላይ የሚታዩ ላኪዎች ሳይሆኑ በርካታ የተለያዩ ተወካዮች
መሆናቸው የጫት የወጪ ንግድ ቁጥጥርን አስቸጋሪ እንዳደረገው፤

 ይሄን ችግር ለመፍታትም ክልሉ ህጋዊ ነጋዴዎች እንዲበረታቱ ለማድረግ ከሚመለከተው አካል ጋር ግንኙነት
መፈጠሩን እና ጉዳዩን ወደ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በመውሰድ ከፍ ባለ ሁኔታ እየተነጋገሩበት እንደሚገኝ፤

 ጫት በኮንትሮባንድ ይወጣባቸዋል ተብሎ የሚታሰቡ ቦታዎች ለይተን ጉምሩክ መቆጣጠሪያ ጣቢያ


እንዲሰራባቸው ዝርዝሩን ለማስተላለፍ ጥናት እየተደረገ መሆኑን፤

 በክልላችን የጫት ንግድ ፈቃድ ያወጡ ነጋዴዎች በባንኮች በኩል ስማቸው ስለሌለ ገንዘብ በስማቸው
እየመጣላቸው እንዳልሆነ ባደረግነው ማጣራት ተገንዝበን ይህ ጉዳይ መፍትሄ ካልተሰጠው በነጋዴዎችና
በክልሉ ገቢ ላይ አሉታዊ ተፅእኖ ሊያሳድር እንደሚችል ተገንዝበን ችግሩ እንዲፈታ ከባንኮች ጋር ስርዓት
ለመዘርጋት ጥረት እየተደረገ መሆኑን፤

 የኢምፖርት ኤክስፖርት ፈቃድ በክልሉ ሳይሆን የሚሰጠው ድሬዳዋ እየሄዱ የሚያወጡ እንደሆነ፤

 የጫት የወጪ ንግድ በከፍተኛ ሁኔታ እንደጨመረ እንደሆነና ነገር ግን አብዛኛው በኮንትሮባንድ የሚወጣ
ስለመሆኑ መረጃ እንዳላቸው፤

 የጫት ኤክስፖርት እንቅስቃሴን ለማገዝ የክልሉ ንግድና ኢንዱስትሪ ቢሮ ተጨማሪ አገልግሎት ሰጪ ቢሮዎችን
ማደራጀቱን፤
 የጫት ለወጪ ንግድ የሚያስፈልገውን ፎርማሊቲ አሟልቶና በፕሎም ታሽጎ ከድሬዳዋና ከጅግጅጋ እንደሚመጣና
ፖሎምፑ ያልተበጠሰ መሆኑ ተጣርቶና ከሰነዱ ጋር ተገነባዝቦ ወደ ውጪ የሚላክ መሆኑን፤

 በመቅረጫ ጣቢያው ለማጣሪያነት ጥቅም ላይ የዋሉ ሰነዶች የላኪው ወይም የወኪሉ ዶላር ማስገቢያ ጥያቄ ወኪሉ
የተወከለበት ህጋዊ ሰነድ፣ የወኪሉ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ፣ በቀረበው ጥያቄ መሰረት ዶላሩ ለባንክ ገቢ እንዲደረግ የተፃፈ
ደብዳቤ፣ ወኪሉ በላኪው ስም ዶላር ወደ ባንክ ገቢ ስለማድረጉ የማረጋገጫ የባንክ ክሬዲት ኖት፣ ከባንክ የተሰጠ
የባንክ ፈቃድ፣ ዕቃው የጉምሩክ ክሊራንስ ተጠናቆለት ስለመውጣቱ የሚያሳይ የጉምሩክ ቲ-1 መሆናቸውን፤

 ውጪ ምንዛሪ ጋር ተያይዞ ዶላር ከሀገር እንዳይወቀጣ ቁጥጥርና ክትትል የሚያደርጉ ባለሙያዎች ተገቢው ከለላ
እየተሰጣቸው አለመሆኑና ከዚህም የተነሳ የቁጥጥሩ ሁኔታ እየላላ መምጣቱን፤

 የጫት መግዣና መሸጫ ዋጋ መካከል ከፍተኛ ልዩነት የሚታይ መሆኑንና መሸጫ ዋጋው እስከ 25000 ብር
የሚደርስ መሆኑን፤

 ለቶጎውጫሌ አካባቢ ህብረተሰብ ፍጆታ የሚላከው ጫት በአግባቡ ኮታ ያልተሰጠው በመሆኑ ኮንትሮባንድም አብሮ
ተጭኖ ሊመጣ የሚችልበት አጋጣሚ መኖሩ፤

 በዚህ መልኩ የመጣው ትርፍ ጫት በቶጎ ውጫሌ ወንዝ በኩል በኮንትሮባንድ የመኪወጣ መሆኑንና በአካባቢው
በጉምሩክ ቁጥጥር ለማድረግ የሚያስችል ከመስተዳደሩ ጋር የተደረገ ስምምነት የሌለ መሆኑን፤

 በኮንትሮባንድ ቁጥጥሩ ጊዜ በጥሬ ገንዘብ ሲያዝ ገንዘቡ ለመንግስት ገቢ እንዳይደረግ በአካባቢው በኩል
በባለሙያዎች ላይ ከፍተኛ ጫና የሚደረግ መሆኑንና በጫናው ውስጥ ከፍተኛ የሆነ የፖለቲካ አካላት ጭምር
የሚሳተፉበት መሆኑ፤

2.6.1 የወጪ ጫት መተላላፊያ መስመርና መውጫ በር ሁኔታ

የጫት ወጪ ንግድ ከአወዳይ ጀምሮ ድሬዳዋ፣ ዱሬ፣ ቢዮቆቤ እና ደወሌ እንዲሁም ከምዕራብ ሐረርጌ በዴሳ እና ከምሥራቅ
ሐረርጌ ደደር፣ ቆቦ፣ ጨለንቆ፣ አወዳይ፣ ሐረር፣ ጅግጅጋና ቶጎጫሌ መተላለፊያ መስመሮች ተከትሎ ከአገር ይወጣል፡፡ በመስክ
ምልከታው ወቅት ከመውጫ በር የጉምሩክ ጣቢያ ያሉ የስራ ኃላፊዎች ጋር በተደረገ ውይይት የተነሱ ዋና ዋና ጉዳዮች መካከል
ከመነሻ ቦታ የጉምሩክ ሥነ-ሥርዓት ተፈጽሞበት ከሀገር የሚወጣ ጫት መውጫ በር ላይ ሲደርስ አልፎ አልፎ በናሙና ፍተሻ
በመቶ ኪ/ግ ሚዛን የመመዘን ስራ የሚከናወን ሲሆን በሌላ መልኩ ከኢንተለጀንስ መረጃ ሲደርሳቸውም መረጃውን መሠረት
በማድረግ የሚሰራበት ሁኔታ ያለ ሲሆን በግኝት ደረጃ ከሰነድ ከተጠቀሰው በላይ ትርፍ ጭነት የሚገኝበት መሆኑን መረዳት
ተችሏል፡፡ በሚዛን ፍተሻ የተገኘው ትርፍ ጭነት በተለይ 6፣300፣310 እና 600 ኪ.ግ ድረስ መሆኑን አስረድተዋል፡፡ ይህ
የምዘና ስራ በተካሄደባቸው ጊዜያት ትርፍ ጭነት ካልተገኘባቸው መጠን ይልቅ ትርፍ መጠን የተገኘባቸው ጊዜያት የሚበልጥ
መሆኑን የኬላ ኃላፊዎች አረጋግጠዋል፡፡ የተገኘው ትርፍ ጭነት ቀደም ሲል በነበረው አሰራር ስርዓት መሰረት ትርፉ በተገኘበት
መቆ/ጣቢያ ይቃጠል እንደነበር የተገለጸ ሲሆን በኋላ ላይ በተሰጣቸው አቅጣጫ መሰረት በትርፍ የተገኘው ጫት መጠን
ተገልፆ ለድሬዳዋ ቅ/ፅ/ቤት ሪፖርት እየተደረገ የትርፍ ጭነቱ መጠን ተመዝግቦ ተቀባዩን ወይም ወኪሉን በማስፈረም
በመመሪያ ቁጥር 112 መሰረት ቅጣት እየተፈጸመ ተጨማሪ የውጪ ምንዛሪ እንዲያስገባ ተደርጎ ለተቀባይ እየተለቀቀ እንዳለ
ተገልጸዋል፡፡ የምዘና ስርዓቱ እጅግ አስቸጋሪ እና ስጋትን በሚፈጥር ሁኔታ የሚካሄድ ሲሆን ምዘና የሚደረግበት ሚዛን ጥራት
በመጠንም ሆነ በአይነት ለፍተሻ ጣቢያው የሚመጥን አለመሆኑን የጥናት ቡድኑ ተገንዝቧል፡፡

ከዚህ በተጨማሪ በደወሌ ወረዳ ሥር የሚገኙ አራት ቀበሌዎች መካከል ቢያጉርጉር፣ኤሌሄሌና ሲንቺፍና ደያህ ለሚኖር
ህብረተሰብ በየቀኑ በኮታ የሚላከው ጫት በቢያቆቤቤ የጉምሩክ መቆጣጠሪያ ጣቢያ በሚዘን እየተጋገጠ ማለፍ ሲገባው
መቆጣጣሪያ ጣቢያው ከመድረሱ በፊት በኬላው ግራና ቀኝ አቋርጠው በማለፍ ከተፈቀደው ኮታ በላይ ጫት በኮንትሮባንድ
ጫት ሊወጣ እዲሚችል ከፍተኛ ጥርጣሬ መኖሩን አስረድተዋል፡፡

የጥናት ቡድኑ ከጣቢያው አስረጅዎች ጋር ስለኮንትሮባንድ እንቅስቃሴ የተወያየ ሲሆን የኮንትሮባንድ እንቅስቃሴ የራሱን
የኮንትሮባንድ መስመርና የጭነት መኪናዎችን ሳይቀር የሚጠቀም መሆኑን በአካል ቦታው ድረስ በመሄድ የጥናት ቡድኑ
የተመለከተ ሲሆን መቆጣጠሪያ ጣቢዎች ያላቸውን ውስን የሰው ኃይልና አቅም ተጠቅመው የኮንትሮባንድ እንቅስቃሴዎች
ይካሄድባቸዋል ወደሚባሉ መስመሮች በመንቀሳቀስ በኮንትሮባንድ ይመላለሱ የነበሩ የጫት ምርት መያዝና መቆጣጠር
መቻላቸውን መረዳት የተቻለ ቢሆንም ከዚህ የቁጥጥር ስራ ጋር ተያይዞ ከክልል ሚሊሻና የመስተዳደር አካላት የተለያዩ
ጫናዎች እየተደረጉባቸው ጫቱ እንዲለቀቅ የሚደረገው ግፊት እየበዛባቸው ሲመጣ የቁጥጥር ስራውን የሚያደርጉ
ባለሙያዎች ስጋት እያደረባቸው መምጣቱን፤ በቢዮቆቤ ከ2013 ዓ.ም ጀምሮ የጫት ንግድን ለመቆጣጠር በሚደረገው ጥረት
በተፈጠረ ረብሻ የአንድ ሰው ህይወት ካለፈ በኋላ ቁጥጥሩ እጅግ እየላላ መምጣቱን የጥናት ቡድኑ ተገንዝቧል፡፡ ከዚህ ጋር
ተያይዞ ከክልል አካላት፣ ከሚሊሻ፣ ከፌዴራል ፖሊስ እና ከመከላከያ ተገቢው ድጋፍ እየተደረገላቸው አለመሆኑን፣
የአካባቢውን ተጨባጭ ሁኔታ ያገናዘበ የትራንስፖርትና የሎጀስቲክስ እንዲሁም ለባለሙያዎች የሚሰጥ የጥቅማ ጥቅም
ሁኔታዎች ያልተሟሉ መሆናቸው የኮንትሮባንድ ቁጥጥር ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ እየፈጠሩ መሆኑን፣ የህግ የበላይነት በተግባር ላይ
ለማዋል በአካባቢው ባለው የፖለቲካ ሁኔታ ምክንያት ያልተቻለ መሆኑን አስረጂ አካላት ለጥናት ቡድኑ አስረድተዋል፡፡
ክፍል ሦስት
3. የጫት የወጪ ንግድ መረጃ ትንተና

3.1 የወጪ ጫት መጠን

ግራፍ 1፡- ከ2016/2017 እስከ 2020/2021 እ.ኤ.አ ድረስ ወደ ውጪ የተላከ የጫት መጠን በኪሎ ግራም
የተላከው የጫት መጠን በኪሎ ግራም

271,945,587

46,914,814 52,949,025 57,050,605 71,087,467


(6.76%) (12.86%) (7.75%) (24.6%)
43,943,676

2016/2017 2017/2018 2018/2019 2019/2020 2020/2021 ድምር

ምንጭ፡ የጉምሩክ ኮሚሽን የአምስ ዓመት የጫት የወጪ ንግድ መረጃ

ከላይ በግራፍ 1 ላይ መረዳት እንደሚቻለው ወደ ውጪ የተላከው የጫት መጠን እ.ኤ.አ ከ2016/2017 ወደ 2017/2018
በ6.76 በመቶ ፤ ከ2017/2018 ወደ 2018/2019 በ12.86 በመቶ፤ ከ2018/2019 ወደ 2019/2020 በ7.75 በመቶ
እና ከ2019/2020/ ወደ 2020/2021 በ24.60 በመቶ እድገት ያለው ሲሆን ባለፉት አራት አመት በአማካይ በ13 በመቶ
እድገት አሳይቷል፡፡ በተለይ እ.ኤ.አ በ2020/2021 ከባለፉት አራት አመታት አንፃር በተሻለ በ24 በመቶ እድገት ማሳየቱ
እ.ኤ.አ ከጥቅምት 2020 ጀምሮ ኬንያ ለሶማሊያ የምትልከው ጫት የተቋረጠ በመሆኑ በተፈጠረ የገበያ እድል ምክንያት
መሆኑ መገንዘብ ይቻላል፡፡ የጥናት ቡድኑ ባደረገው የመስክ ምልከታ እንዲሁም በዘርፉ ከተሰማሩ ላኪዎች ፤ የአየር መንገድ
ኦፕሬተሮች፤ የፌደራልና የክልል ንግድ ቢሮዎች እና ሌሎች ከጫት ንግድ ጋር ቀረቤታ ያላቸው አካላት ጋር የተደረገው
ውይይት ይህንኑ የሚያረጋግጥ ሆኖ ተገኝቷል፡፡

3.2 የተገኘ የውጭ ምንዛሬ

ሰንጠረዥ 1፡- በአምስት አመት ወደ ውጪ ከተላከ ጫት የተገኘ የውጪ ምንዛሬ በዶላር


የተላከበት ዓ.ም. እድገት በመቶኛ
የውጭ ምንዛሪ መጠን በአሜሪካ ዶላር
2016/2017 247,526,786.76 -
2017/2018 264,790,108.10 6.97
2018/2019 301,455,052.70 13.85
2019/2020 323,310,364.09 7.25
2020/2021 400,502,561.82 23.88
ድምር 1,537,584,873.47
ምንጭ፡ የጉምሩክ ኮሚሽን የአምስ ዓመት የጫት የወጪ ንግድ መረጃ
ከላይ በሰንጠረዥ 1 ላይ ከወጪ ጫት ንግድ የተገኘው የውጪ ምንዛሪ መጠን በአማካይ 13 በመቶ እያደገ የመጣ መሆኑ
መገንዘብ ይቻላል፡፡ በተለይ እ.ኤ.አ በ2020/2021 የተገኘው የውጪ ምንዛሬ ከባለፉት አራት ዓመታት አንፃር ሲታይ
77,192,197.73 የአሜሪካ ዶላር (23.88 በመቶ) እድገት ያስመዝገበ መሆኑ ያሳያል፡፡ ይህም ኬንያ ለሶማሊያ የምትልከው
ጫት እ.ኤ.አ ከጥቅምት 2020 ጀምሮ በመቋረጡ በተፈጠረው ተጨማሪ የገበያ እድል የመጣ እድገት ለሆን እንደሚችል
ይታመናል፡፡ በመሆኑም ዘርፉ ልዩ ትኩረት ከተሰጠውና በህገ ወጥ መንገድ ከሀገር የሚወጣውን ጫት መቆጣጠር ከተቻለ
ለሀገር የተሻለ የውጪ ምንዛሬ የሚያመነጭ የግብርና ምርት መሆኑ ለማየት ተችሏል፡፡

3.3 የላኪዎች ሁኔታ


ግራፍ፡- 2 የግል ላኪዎች ሁኔታ በመዳረሻ ሀገር
300
250
200
150
100
50
0
2016/2017 2017/2018 2018/2019 2019/2020 2020/2021
ወደ ሶማሊያ የላኩ ግለሰቦች 40 71 139 186 272
ወደ ጅቡቲ የላኩ ግለሰቦች 87 92 91 102 120
ወደ ሌሎች አገራት የላኩ ግለሰቦች 40 35 44 71 77

ምንጭ፡ የጉምሩክ ኮሚሽን የአምስ ዓመት የጫት የወጪ ንግድ መረጃ

ከላይ በግራፍ 2 ላይ መረዳት እንደሚቻለው ወደተለያዩ ሀገራት ጫት የሚልኩ ግለሰብ ነጋዴዎች ቁጥራቸው ከጊዜ ወደ ጊዜ
እየጨመረ የመጣ ሲሆን በተለይ ወደ ሶማሊያ የሚልኩ ላኪዎች ቁጥር እጅግ ከፍተኛ መሆኑንና የአጨማመር ፍጥነቱም
ከዓመት ወደ ዓመት ማለት 2017 ወደ 2018 በ78 በመቶ ፤ 2018 ወደ 2019 በ96 በመቶ ፤ 2019 ወደ 2020 በ41 እና
2020 ወደ 2021 በ46 በመቶ የጨመረ መሆኑ መገንዘብ ይቻላል፡፡ በተለይ ወደ ሶማሊያ በግለሰብ ላኪዎች የሚላከው
የጫት የወጪ ንግድ ተቀባይነት እያገኘ የመጣ መሆኑና አገር ውስጥ ያለው የአሰራር ስርዓት ይበልጥ ከተሻሻለ በቀጣይነትም
ይህ ፍላጎት እየጨመረ ሊሄድ የሚችል መሆኑ አመላካች እንደሆነ ማየት ይቻላል፡፡ ከሶስቱ መዳረሻ ቦታዎች የጅቡቲና
የሶማሊያ የጫት ንግድ ፍላጎት ከፍተኛ ድርሻ ያላቸው ሲሆን በተለይ የሶማያ ከጅቡቲ ጋር ሲነፃፀር በ2021 ላይ 127 በመቶ
ብልጫ ያለው ሲሆን ንግዱ ግለቱን ጠብቆ እንዲቀጥል በሎጂስቲክስ ሰንሰለት ያሉት ተግዳሮቶች ትኩረት ተሰጥቶባቸው
እንዲፈቱ ማድረግ የሚጠበቅ መሆኑ ያመለክታል፡፡

ግራፍ፡- 3 የማህበር ላኪዎች በመዳረሻ ሀገር


6
5
4
3
2
1
0
2016/2017 2017/2018 2018/2019 2019/2020 2020/2021
ወደ ሶማሊያ የላኩ ማህበራት 0 0 0 0 1
ወደ ጅቡቲ የላኩ ማህበራት 4 4 4 5 5
ወደ ሌሎች አገራት የላኩ ማህበራት 0 0 0 0 0

ምንጭ፡ የጉምሩክ ኮሚሽን የአምስ ዓመት የጫት የወጪ ንግድ መረጃ

ከላይ በግራፍ 3 ላይ መረዳት እንደሚቻለው የማህበራት ላኪዎች ቁጥር ባለፉት አምስት ዓመታት ከነበረበት አራት ወደ
አምስት ያደገ ቢሆንም እነዚህ ማህበራት በስራቸው በርካታ ገበሬዎችን በማቀፍ ተጠቃሚ የሚያደርጉ እና በአሰራር ደረጃም
ከግለሰብ ላኪው ይልቅ የተደራጁና ግልፅነት ያላቸው ከመሆኑ አንፃር የሚጠበቀው ድጋፍ በማድረግ ቁጥራቸው እንዲጨምር
አለመደረጉ የሚያሳይ ስለሆነ በቀጣይ ትኩረት በመስጠት መስራት አስፈላጊ መሆኑ ያሳያል፡፡

ግራፍ፡-4 የጫት ወጪ ንግድ ሌሎች መዳረሻ ሀገራት

99 95

73 72

40

2016/2017 2017/2018 2018/2019 2019/2020 2020/2021

ምንጭ፡ የጉምሩክ ኮሚሽን የአምስ ዓመት የጫት የወጪ ንግድ መረጃ

ከላይ ከተመለከተው ግራፍ እንደሚታየው ከሶማሊያ እና ጅቡቲ ውጪ ያሉ ጫት ተቀባይ ሀገራት ብዛት በተለይ እ.ኤ.አ 2018
ጀምሮ እየቀነሰ መምጣቱንና በ2021 ላይ 2018 አንፃር 148 በመቶ ያሽቆለቆለና ለዚህ ዋነኛ ምክንያ ከጊዜ ወደ ጊዜ የጫት
ምርት ወደሀገራቸው እንዳይገባ የሚከለክሉ ሀገራት ብዛት ቁጥር እየጨመረ መምጣቱ ሲሆን በቀጣይም ይህ ክልከላ ሊቀጥል
እንደሚችል ስጋት ያለ መሆኑ ያመላክታል፡፡ ስለዚህ የጫት ምርትን በቋሚነት የሚቀበሉና የሚጠቀሙ ሀገራት ፍላጎት
በየወቅቱ እየተጠና ተገቢው ሁኔታ እየተመቻቸ ቀጣይነቱ ማረጋገጥ የሚያስፈልግ መሆኑን ያስገንዝባል፡፡

ሰነጠረዥ 2፡- የጫት ወጪ ንግድ መጠን እና የውጪ ምንዛሬ ግኝት ድርሻ በመዳረሻ ሀገር
ወደ ሶማሊያ የተላከ ወደ ጅቡቲ የተላከ ወደ ሌሎች 97 አገራት የተላከ

ከተገኘው የውጭ ምንዛሬ ያለው


ጠቅላላ አጠቃላይ

የውጭ ምንዛሬ ያለው ድርሻ


አጠቃላይ ከተላከው ያለው
የተላከው የተገኘ

ድርሻ በመቶኛ
የውጭ
ኪ.ግ የውጭ ኪ.ግ ውጭ

ከተገኘው
ጫት የተላከበትና ምንዛሬ መጠን ኪ.ግ የውጭ

ድርሻ
ምንዛሬ ግኝት ምንዛሬ ግኝት ኪ.ግ በሺህ
የውጪ ምንዛሬ በሚሊዮን በሚሊዮን ግኝት በሚሊዮን ምንዛሬ
በሚሊዮን በሚሊዮን
በሚሊዮን
የተገኘበት ድምር
ዓ.ም. በሚሊዮን
35.71 178.17 72 7.93 59.49 24 296.76 9.86 4 43.94 247.52
2016/2017
38.45 191.74 72.4 8.10 60.78 23 352.17 12.26 4.6 46.91 264.79
2017/2018
42.89 214.06 71 9.59 71.26 24 460.98 16.12 5.35 52.94 301.45
2018/2019
46.85 234.58 73 9.71 71.74 22 484.86 16.97 5 57.05 323.31
2019/2020
59.34 302.40 75.5 10.36 75.90 19 1,377.11 22.18 5.5 71.08 400.50
2020/2021
ድምር 223.25 1,120.98 72.78 45.72 339.18 22.33 2,971.90 77.41 4.89 271.94 1,537.58
ምንጭ፡ የጉምሩክ ኮሚሽን የአምስ ዓመት የጫት የወጪ ንግድ መረጃ

ከሰንጠረዥ 2 ላይ መገንዘብ እንደሚቻለው ባለፉት አምስት አመታት 271.94 ሚሊዮን ኪሎ ግራም ወይም 1,537.58
ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር ዋጋ ያለው ጫት ከኢትዮጵያ ወደ ውጪ የተላከ ሲሆን ሶማሊያ፤ ጅቡቲ እና ሌሎች ሀገራት ናቸው፡፡
ለእነዚህ ሀገራት የሚላከው ጫት እንደቅድመተከተላቸው 72.78 በመቶ፤ 22.33 በመቶ እና 4.89 በመቶ ጫት የመቀበል
ድርሻ ያላቸው መሆኑ ያስረዳል፡፡ ወደ ሶማሊያ የሚላከው የጫት መጠንና የሚገኘው የውጪ ምንዛሬ ባለፉት አምስት
ዓመታት በአማካይ 14.43 በመቶ እያደገ የመጣና ዋነኛ የኢትዮጵያ የወጪ ጫት ንግድ መዳረሻ ሀገር መሆኗን ያመለክታል፡፡
በአንፃሩ ለጅቡቲ የሚላከው የጫት መጠን በኮታ የተገደበ በመሆኑ ከዘርፉ የሚገኘው የውጪ ምንዛሬ ከአመት ወደ አመት
እምብዛም እድገት የማይታይበት መሆኑን ያመለክታል፡፡ ይሁን እንጂ ከፍተኛ መጠን ያለው ጫት በህገ ወጥ መንገድ ወደ
ጅቡቲ እንደሚሄድ ከተሰበሰበው መረጃ ለመረዳት ተችሏል፡፡ ከሶማሊያ እና ጅቡቲ በተጨማሪ ጫት ወደ 97 ሀገራት የሚላክ
ሲሆን ከሚላከው አጠቃላይ የጫት የወጪ ንግድ 4.89 በመቶ ድርሻ ይይዛል፡፡ ስለሆነም ሶማሊያ እና ጅቡቲ የሚላከው
የወጪ የጫት መጠን ከፍተኛ ድርሻ የሚይዝ በመሆኑ በእነዚህ ሀገራት ገበያ ላይ ትኩረት ሰጥቶ መስራ እንደሚያስፈልግ
ያመለክታል፡፡

3.4 የማጓጓዣ ዓይነት

ሰንጠረዥ፡-3 የወጪ ጫት የማጓጓዣ ዓይነት

የተላከ መጠን በማጓጓዣ ዓይነት እና በኪሎግራም ድምር


በየብስ በአየር በፖስታ
ዓ.ም.
ኪ.ግ በሺህ የውጭ ምንዛሪ ዋጋ ኪ.ግ በሺህ የውጭ ኪ.ግ የውጭ ኪ.ግ በሺህ የውጭ ምንዛሪ
በሚሊን ምንዛሪ በሺህ ምንዛሪ በሚሊዮን
በሚሊዮን በሚሊዮን
2016/2017 3,654.868 237.88 208.55 6.839 80.27 2.81 43,943.67 247.57
2017/2018 46,568.74 252.89 323.40 11.11 22.66 0.79 46,914.81 264.79
2018/2019 52,432.786 28.48 473.27 14.48 42.97 1.492 52,949.02 301.456
2019/2020 56,416.53 305.59 628.18 17.52 5.89 0.21 57,050.60 323.31
2020/2021 64,513.80 348.88 6,572.42 51.57 1.25 0.44 71,087.46 400.50
ድምር 263,586.73 1,430.72 8,205.82 101.52 153.03 5.37 271,945.60 1,537.58

ድርሻ 96.93% 93.05% 3.02% 6.6% 0.05% 0.35%


ምንጭ፡ የጉምሩክ ኮሚሽን የአምስ ዓመት የጫት የወጪ ንግድ መረጃ

ግራፍ 5፡- የወጪ ጫት የማጓጓዣ ዓይነት በግራፍ

70,000,000.00

60,000,000.00

50,000,000.00

40,000,000.00

30,000,000.00

20,000,000.00

10,000,000.00

0.00
2016/2017 2017/2018 2018/2019 2019/2020 2020/2021
በየብስ የተላከ ጫት መጠን በኪ.ግ 3,654,868.70 46,568,747.1252,432,786.3156,416,533.2064,513,800.88
በአየር የተላከ ጫት መጠን በኪ.ግ 208,550.73 323,403.20 473,271.88 628,181.85 6,572,415.25
በፖስታ የተላከ ጫት መጠን በኪ.ግ 80,256.87 22,663.93 42,966.68 5,889.99 1,250.82

ከላይ በሰንጠረዥ 3 እና በግራፍ 5 ላይ እንደተመለከተው በአምስት አመት ጊዜ ውስጥ ከሀገር ውስጥ ወደ ውጪ ሀገር
ከሚላከው ጫት 97 በመቶው በየብስ የተጓጓዘ ሲሆን ቀሪው 3 በመቶ በአየር ትራንስፖርት የተጓጓዘ መሆኑ መገንዘብ
ይቻላል፡፡ ከላይ በክፍል ሁለት እንደተብራራው የየብስ ትራንስፖርት ብዙ ተግዳሮቶች እያሉበትም በዚህ መጠን ማጓጓዝ
መቻሉ ዘርፉ ተገቢው ድጋፍና ትብብር ቢደረግለት ከዚህ በበለጠ የወጪ የጫት ንግድ ለማጓጓዝ የሚያስችል አቅም እንዳለው
ያመላክታል፡፡ ከአሰራር ጥራት አኳያ የአየር ትራንስፖርት የተሻለ መሆኑ ግምት ውስጥ ገብቶ አሁን የሚታየው የወጪ ጫት
ንግድ የማጓጓዝ መጠን ከፍ እንዲል በተቀባይ ሀገራት በኩል የሚታዩ ማነቆዎች እንዲስተካሉ ማድረግ ቁልፍ ጉዳይ መሆኑ
ይታመናል፡፡

3.5 የጫት ወጪ ኮንትሮባንድ መረጃ


ግራፍ 6፡- የጫት ወጪ ኮንትሮባንድ መረጃ በኪሎ ግራም እና በአሜሪካ ዶላር

77,276,456

32,730,834

16,581,527
9,874,815 11,390,461
6,698,819
21,004 12,910 13,718 16,741 26,250 90,623

ብዛት ጠ/ዋጋ ብዛት ጠ/ዋጋ ብዛት ጠ/ዋጋ ብዛት ጠ/ዋጋ ብዛት ጠ/ዋጋ ብዛት ጠ/ዋጋ
በኪ.ግ በብር በኪ.ግ በብር በኪ.ግ በብር በኪ.ግ በብር በኪ.ግ በብር በኪ.ግ በብር
2009 2010 2011 2012 2013 ጠቅላላ

ምንጭ፡- የጉምሩክ ኮሚሽን የኮንትሮባንድ መከላከል አፈፃፀም ሪፖርት ከ2009 ዓ.ም እስከ 2013 ዓ.ም

ከላይ በግራፍ 6 እንደተመለከተው በ2009 ዓ.ም 9.87 ሚሊዮን ብር ወይም 219 ሺህ ዶላር የሚገመት የጫት ምርት ከሀገር
ሲወጣ ተይዟል፡፡ በ2010 ዓ.ም 6.7 ሚሊዮን ብር ወይም 149 ሺህ ዶላር የሚገመት የጫት ምርት የተያዘ ሲሆን በምስራቁ
የሀገራችን ክልል በወቅቱ በነበረው የፀጥታ ችግር ምክንያት የተያዘው የጫት ምርት በ32 በመቶ ቅናሽ አሳይቶ ነበረ፡፡ በ2011
የተያዘው የጫት ምርት 11.4 ሚሊዮን ብር ወይም 253 ሺህ ዶላር የሚገመት ሲሆን ከ2010 ዓ.ም ጋር ሲነፃፀር የ70 በመቶ
ከፍተኛ ጭማሪ አሳይቷል፡፡ በተመሳሳይ መልኩ በ2012 በጀት ዓመት 16.58 ሚሊዮን ብር ወይም 368 ሺህ ዶላር የሚገመት
ጫት በኮንትሮባንድ ሲወጣ የተያዘ ሲሆን ከ2011 በጀት ዓመት ጋር ሲነፃፀር የ45.6 በመቶ ጭማሪ ተመዝግቧል፡፡ በ2013
በጀት ዓመት 32.73 ሚሊዮን ወይም 727 ሺህ ዶላር የሚገመት የጫት ምርት በኮንትሮባንድ ሲወጣ የተያዘ ሲሆን ከ2012
በጀት ዓመት ጋር ሲነፃፀር በ97.4 በመቶ ጭማሪ አሳይቷል፡፡ በዚህም መነሻነት የጫት ኮንትሮባንድ በየዓመቱ ከፍተኛ ጭማሬ
እያሳየ እንደሆነና ይህ ደግሞ በህጋዊ የጫት ወጪ ንግድ ላይ ከፍተኛ የሆነ አሉታዊ ታፅእኖ እያሳደረ እንደሆነ መገንዘብ
ይቻላል፡፡ ስለዚህ ይህ ከፍተኛ የሆነ የውጪ ምንዛሬ እንዳይባክን የኮንትሮባንድ እንቅስቃሴ ላይ የሚደረገው ክትትልና ቁጥጥር
ሁለንተናዊ ሆኖ በዚህ ዘርፍ የተሰማሩ የክትትላ ቁጥጥር ባለሙያዎች ተገቢው የህግ ከለላ፤ አስፈላጊው ሎጂስቲክስ ድጋፍ እና
ማበረታቻ ስርዓት እንዲኖር ማድረግ አስፈላጊ መሆኑን መረጃው ያመላክታል፡፡

ቻርት 1፡- ከ2009 እስከ 2013 ዓ.ም ድረስ በኮንትሮባንድ ከሀገር ሲወጣ የተያዘ ጫት ድርሻ በጉምሩክ ቅ/ፅ/ቤቶች
ጅግጅጋ
0%
ጅማ
0% ጋላፊ
22%
አ.አ ኤርፖርት
6%

ሃዋሳ
5%
መቀሌ
ድሬዳዋ 0%
47%
ሞያሌ
20%

ምንጭ፡- የጉምሩክ ኮሚሽን የኮንትሮባንድ መከላከል አፈፃፀም ሪፖርት ከ2009 ዓ.ም እስከ 2013 ዓ.ም

ከላይ በቀረበው ቻርት እንደምንረዳው ከ2009 ዓ.ም ጀምሮ እስከ 2013 ዓ.ም ድረስ ባሉት አምስት ዓመታት በተለያዩ
የድንበር መውጫ በሮች በህገ ወጥ መንገድ ሲወጡ ከተያዙ የጫት ምርቶች ውስጥ 47 በመቶ የሚሆነው የጫት ምርት
በድሬዳዋና አካባቢው በሚገኙ የድንበር መውጫ በሮች የተያዘ ነው፡፡ በዚህም በንፅፅር በድሬዳዋና አካባቢው ከፍተኛ መጠን
ያለው ጫት ምርት በኮንትሮባንድ ሲንቀሳቀስ እንደተያዘ መገንዘብ ይቻላል፡፡ 22 በመቶ የሚሆነው የጫት ምርት የተያዘው
በጋላፊና አካባቢው ሲሆን በዚህ አካባቢ ያሉ መውጫ በሮችና የኮንትሮባንድ መተላለፊያ መስመሮች በቀጥታ በድሬዳዋ
አካባቢ ካሉ የኮንትሮባንድ መተላለፊያ መስመሮች ጋር ግንኙነት ያላቸውና ተመጋጋቢ ናቸው፡፡ 20 በመቶ የሚሆነው የጫት
ምርት የተያዘው በሞያሌ አካባቢ ሲሆን ከምስራቁ የሀገራችን ክፍል ተነስቶ የተለያዩ መተላለፊያ መስመሮችን በመጠቀም
በሞያሌ በኩል ከሀገር ሲወጣ የተያዘ ሲሆን በ3ኛ ደረጃ ከፍተኛውን ድርሻ ይዞ ይገኛል፡፡ 6 በመቶ የሚሆነው የጫት ምርት
በአዲስ አበባ ኤርፖርት በኩል ሲወጣ የተያዘ ሲሆን 5 በመቶ የሚሆነው የጫት ምርት የተለያዩ የኮንትሮባንድ መተላለፊዎችን
በመጠቀም አቆራርጦ ለመውጣት ሲሞክር መሀል ላይ በበሀዋሳ አካባቢ በሚገኙ መቆጣጠሪያ ጣቢዎች በቁጥጥር ስር ውሏል፡፡
በሌሎች አካባቢዎች ማለትም በጅግጅጋ፣ በመቀሌና በጅማ አካባቢዎች የተያዘው የጫት ምርት ጥቂት ሲሆን በተለይ በጅግጅጋ
አካባቢ በአካባቢው ካለው ከፍተኛ የጫት ምርት እንቅስቃሴ አንፃር ከህብረተሰቡ ጀምሮ በመንግስት መዋቅር ውስጥ እስካሉ
አመራሮች ድረስ በምርቱ ላይ አስፈላጊው ቁጥጥር ተደርጎ እርምጃ እንዳይወሰድ ጫናዎች የሚደረጉ በመሆናቸው ምክንያት
ምንም እንኳን ከፍተኛ የሆነ የጫት የኮንትሮባንድ እንቅስቃሴ በአካባቢው ቢኖርም ምርቱን ይዞ አስፈላጊውን ህጋዊ እርምጃ
ለመውሰድ ግን ፈታኝ እንደሆነ ከተገኙት መረጃዎች መገንዘብ ተችሏል፡፡
3.6 የሀገር ውስጥ የጫት ምርት ሽፋን በክልል ደረጃ

ሰንጠረዥ 5፡- የ1996 እና 2010 ዓ.ም የጫት ምርት የሚመረትበት መሬት በሄክታር እና ምርቱ በፍጥነት ያደገባቸው
ክልሎች

ጫት የሚመረትበት የመሬት
ዕድገት የጫት ምርት መጠን በኩንታል ዕድገት
ክልል ስፋት በሄክታር
በመቶኛ በመቶኛ
1996 2010 1996 2010
አማራ 2,718 11,260.18 314.28 13,566 72,103.44 430.5
ቤንሻንጉል ጉሙዝ 46 813.24 1,667.9 457 14,796.96 3,137.85
ድሬዳዋ 713 1,159.74 62.66 2,409.94 3,072.59 27.5
ሀረሪ 39 6,364.75 212.3 33,363 135,696.57 306.73
ኦሮሚያ 2,038 162,184.94 115.68 543,737 1,305,332.93 140.07
ደቡብ 75,196 65,549.20 190.4 238,109 649,682.24 172.85
ሶማሊ 22,570 3.33 -20.3 104,138 21,175.58 -79.67
ድምር 80,750 247,332.05 831,642 2,180,684.73
ምንጭ:- ከጴጥሮስ ተረፈ ቶልቻ 2020 እ.አ.አ ጥናት ላይ የተወሰደ

ከላይ ከሰንጠረዡ ማየት እንደሚቻለው በ2010 ዓ.ም አጠቃላይ የአገር ውስጥ የጫት ምርት 218,068,473 ኪ.ግ ሲሆን
በዚሁ ተመሳሳይ ዓመት ወደ ውጪ የተላከው የጫት መጠን 46,914,810 ኪ.ግ ወይም 22 በመቶ ብቻ ነው፡፡ በቀጣይ
ዓመታትም ቢሆን የሀገር ውስጥ የጫት ምርት እየጨመረ የሚመጣ መሆኑ ታሳቢ ተደርጎ ከሀገር ውስጥ ፍጆታ ተጨማሪ 22
በመቶ እንኳ ወደ ውጪ መላክ ቢቻል ሊገኝ የሚችለው የውጪ ምንዛሬ መጠን በ2013 ከተገኘው ከፍተኛ እድገት ሊኖረው
እንደሚችል ታሳቢ ማድረግ ተገቢ ነው፡፡

ክፍል አራት
4. ማጠቃለያና የመፍትሔ ሐሳብ
4.1. ማጠቃለያ

የጫት ምርት በኢትዮጵያ በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ መምጣቱን በጥናቱ ውስጥ ከተካተተው መረጃ መረዳት ይቻላል፡፡
ኢትዮጵያ ከጫት ምርት የምታገኘው የውጭ ምንዛሬ ባለው የምርት መጠን ልክ አለመሆኑን መረጃዎች ያሳያሉ፡፡ በዚህ ረገድ
ወደ ውጭ ተልከው ለሀገሪቷ የውጭ ምንዛሪ ከሚያስገኙ የግብርና ምርቶች መካካል ከቡና ቀጥሎ ጫት በሁለተኛ ደረጃ ላይ
ይገኛል፡፡ ይሁን እንጂ ኢትዮጵያ ከምታመርተው የምርት መጠን አንፃር ከዘርፉ የምታገኘው የውጭ ምንዛሪ አነስተኛ ነው
ሊባል ይችላል፡፡ ይህም ሊሆን የቻለው ዘርፉ በብዙ ውስብስብ ችግሮች የተጠላለፈ በመሆኑ ነው፡፡

በአጠቃላይ የጫት ወጪ ንግዱ የመንግስት ቢሮክራሲ በከፍተኛ ሁኔታ የተጫነው፣ አልፎም አንዳንድ የመንግስት መዋቅር
ውስጥ ያሉ ግለሰቦች ወደ ሶማሊያ ከሚልኩት ላኪዎች መካከል ለተወሰኑት ብቻ በማድላት ሶማሊያ ከሚገኘው የኢትዮጵያ
ኢምባሲ ጋር በመመሳጠር ለአንዱ ጫት ላኪ ብቻ የገበያ ሁኔታ በማመቻቸት እንዲሁም በሶማሊያ ሲቪል አቪየሽን
ባለሥልጣንና ተቀባዩ ጋር በመሆን የበረራና የማረፊያ ፈቃድ እንዲሰጥ የሚደረግበት ሁኔታ ያለ ሲሆን ለአብነትም በአንድ
ድርጅት አርባ ሺህ /40,000/ ኪሎግራም በአስር /10/ የአሜሪካን ዶላር ይላክ ከነበረበት ወደ ሶስት ሺህ /3,000/
ኪሎግራም እና መላኪያ ዋጋውም ወደ አምስት /5/ የአማሪካን ዶላር እንዲወርድ የሚያደርጉበት፣ በመንግስት በኩል ድጋፍ
የማይደረግለት፣ ማበረታቻም የማይሰጠው፣ ጫት ወደ ውጭ የሚለካበት በቂ የትራንስፖርት አማራጭ የሌለው፣ በጥቂት
ዝምድና ባላቸው ግለሰቦች የተያዘ፣ ራቅ ሲልም የሌላ ሀገር ተወላጆች በኢትዮጵያ ውስጥ ስድስት /6/ ወር ኖረዋል ተብለው
መታወቂያ አውጥተው ንግዱ ውስጥ በቀጥታ የተሰማሩበት፣ የጫት ደረጃ በመላኪያ ዋጋ ላይ ከፍተኛ ተዕፅኖ የሚያሳድር
ቢሆንም የጫት የጥራት ደረጃ የሚወሰንበት ግልፅ የሆነ አሰራርና ስታንዳርድ ያልተበጀለትና በገዥው አገር ተቀባይና ላኪው
ስምምነት በዘልማድ የሚወሰንበት፣ የወጪ ንግድ ጫት ዋጋውም በነፃ ገበያ የማይወሰንና ማሻሻያ የማይደረግበት፣ የገንዘብ
ዝውውሩም የባንክና ዓለምአቀፍ ንግድ ሥርዓትን የማይከተል እና የአመዛዘን ሥርዓቱም ወጥነት የጎደለው መሆኑን ለመረዳት
ተችሏል፡፡

ስለሆነም መንግስት የጫት ወጪ ንግድ ለኢትዮጵያ የውጭ ምንዛሪ በማስገኘት ረገድ ከፍተኛ ድርሻ ያለውና ለዘርፉም በቂ
ትኩረት ከተሰጠው የሀገሪቷን የውጭ ምንዛሪ ግኝት በከፍተኛ ሁኔታ የማሻሻል አቅም ያለው መሆኑን ተገንዝቦ ለጫት ወጪ
ንግዱ ከፍተኛ ትኩረት በመስጠት በዘርፉ ላይ የሚስተዋሉ ውስብስብና ጥልፍልፍ ችግሮችን መቅረፍ ይጠበቅበታል፡፡

4.2. የመፍትሔ ሐሳብ

የጫት ወጪ ንግድ ሎጅስቲክስና አገልግሎት አሰጣጥ ሂደትን በመፈተሽ በዘርፉ የሚስተዋሉ ተግዳሮቶችን በጥናት ለመለየት
የጉምሩክ፣ የንግድ እና ኢንዱስተሪ ሚ/ር፣ የብሔራዊ ባንክ፣ የኢትዮጵያ ሲቪል አቪየሽን ባለስልጣን፣ የመንግስትና የግል አየር
መንገዶች፣ የኢትዮጵያ ፖስታ አገልግሎት ድርጅት፣ የፌዴራልና የክልል ንግድ ቢሮዎች፣ላኪዎች እንዲሁም ከሌሎች ጉዳዩ
ከሚመለከታቸው አካላት የተገኙ መረጃዎችና የጫት ወጪ ንግድን የተመለከቱ የሰነድ ማስረጃዎችን በመሰብሰብ፣
በማደራጀትና በመተንተን፣ በአካል ምልከታ በማድረግ፣ እንዲሁም ከመንግስት የስራ ኃላፊዎችና ከላኪዎች ጋር ውይይት
በማድረግ በጫት ወጪ ንግድ ላይ የሚስተዋሉ ችግሮች በጥናት የተለዩ ሲሆን ችግሮችን በመፍታት ከጫት ወጪ ንግድ
የሚገኘውን የውጭ ምንዛሬ ማሳደግ እንዲቻል የሚከተሉት የመፍትሔ ሐሳቦች ቀርበዋል፡-

1. በኢትዮጵያና በሶማሊያ (ሶማሌ ላንድ፣ ሞቃዲሾ፣ ፑንት ላንድ) መካከል ግልፅ የሆነ የሲቪል አቪዬሽን የሁለትዮሽ
ስምምነት ባለመኖሩ የሶማሊያ ሲቪል አቬሽን ባለሥልጣን ለግል ኦፕሬተሮችና ጫት ተቀባይ ለሆኑ የሶማሊያ ዜጎችና
ጥምር ዜግነት ላላቸው በተለየ ሁኔታ ፈቃድ የሚሰጥበትን መንገድ በማመቻቸት ረገድ በሶማሊያ የሚገኘው
የኢትዮጵያ ኤምባሲ ያሉ አንዳንድ የስራ ኃላፊዎች፣ የኦሮሚያ ክልል ግብርና ቢሮ ያሉ አንዳንድ ከፍተኛ አመራሮችና
ሌሎች የመንግስት አካላት ጣልቃ ገብነት የጫት ወጪ ንግዱ በጥቂት ግለሰቦች እንዲያዝና ፍትሃዊነት የጎደለው
እንዲሆን ያደረገ መሆኑ በሰፊው ተነስቷል፡፡ ስለሆነም የኢትዮጵያ መንግስት ከሶማሊያ መንግስት ጋር በመነጋገርና
ስምምነት በመፈራረም የአውሮፕላን በረራና ማረፊያ ፈቃድ አሰጣጥ ከጫት ተቀባይ ወይም ከአንዳንድ ባለስልጣናት
እጅ ወጥቶ እንደ ሀገር ለኢትዮጵያ መንግስት ሲቪል አቪዬሽን እንዲሰጥ በማድረግ ሁሉም ላኪዎች ያለ ምንም አድሎ
በፍትሃዊነት የሚገለገሉበት ግልጽ ሥርዓት እንዲዘረጋ ቢደረግ፤

2. በስራ ላይ ያሉት ጥቂት የግል አይሮፕላኖች ከኬንያ በኪራይ የተሸፈኑ በመሆናቸው የአይሮፕላን ኪራይ ክፍያ
በኢትዮጵያ ባንክ ሥርዓት ሳያልፍ በቀጥታ ከሶማሊያ ወደ ኬንያ የሚተላለፍበት መንገድ በሀገራችን የውጭ ምንዛሬ
ግኝት ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ አሳድሯል፡፡ በመሆኑም ይህንን ችግር ለማቃለል የባንክ የውጭ ምንዘሬ አቅርቦት
እንዲሻሻል፣ የአይሮፕላን ትራንስፖርት አማራጭ በአገር ውስጥ እንዲኖር ድጋፍ እንዲመቻች፣ የግል አይሮፕላን ግዥ
የእድሜ ገደብ ህግ እንዲሻሻል፣ የብድርና ልዩ ማበረታቻ ድጋፍ እንዲመቻች፣ በአለም አቀፍ የንግድ ስምምነት(
Incoterms) መሰረት ወጥነት ባለው መልኩ ለጭነት የሚከፈል የውጭ ምንዛሬ ወደ ሀገር እንዲገባ የሚያስችል
ስርዓት እንዲዘረጋ፣ ለሀገር ውስጥ ኦፕሬተሮች በልዩ ሁኔታ ወደ ሶማሊያ እንዲበሩ በሲቪል አቪዬሽን የተፈቀደው
ዘላቂና አስተማማኝ ባለመሆኑ ቀጣይ የህግ ማሻሻያ ቢደረግ፡፡ በድሬዳዋ ያለው አለም አቀፍ ኤርፖርት ለመንገደኞችና
ለወጪ ጫት ጭነት አይሮፕላኖች መነሻና ማረፊያ ቦታ የመያዝ አቅሙ 5(አምስት) ሲሆን ተሸጋሽጎ እስከ 9(ዘጠኝ)
አይሮፕላኖች ለመያዝ ቢችልም ከፍተኛ የቦታ ጥበት በመፈጠሩ በቀጣይ ለሚጨመሩት ለጫት ማጓጓዣ
አይሮፕላኖች ማነቆ ሊሆን ስለሚችል ቀጣይ የመሰረተ ልማት ማስፋፊያ እና ሌሎች በሀገር ውስጥ ያሉ ለምሳሌ፡-
ባህር ዳር፣ ጅግጅጋና አርባ ምንጭ ኤርፖርቶችን እንደ አማራጭ መጠቀም የሚቻልበትን የማስተካከያ እርምጃ
ቢወሰድ፤

3. የኢትዮጵያ ፖስታ አገልግሎት ድርጅት በጫት ወጪ ንግድ የፖስታ ጥቅል አላላክ ላይ የጫት ስያሜና መግለጫ፣
የተቀባይ ሀገርና ተረካቢ አድራሻ አመዘጋገብ መረጃ በማዛበት በአለም አቀፍ የፖስት ህብረት ድርጅት አሠራር
የአድራሻ ማስተካከያ እየተደረገ ጫት ክልከላ ወደ አደረጉ ሀገራት እንዲሄድ በመደረጉ የፖስታ ድርጅቱ ለተጨማሪ
የውጭ ምንዛሬ ዕዳና የኢትዮጵያ አየር መንገድ ጫት በከለከሉ ሀገራት ማስጠንቀቂያ እንዲደርሰው በመደረጉ
በአመራሩ ውሳኔ የፖስታ ጥቅል የጫት ወጪ ንግድ እንዲቋረጥ መወሰኑ ከችግር የተነሳ የተወሰደ እርምጃ ቢሆንም
በህጋዊ የጫት ወጪ ንግድ፣ በውጭ ምንዛሪ ግኝትና በፖስታ ድርጅቱ ጥቅም ላይ አሉታዊ ተጽእኖ እያሳደረ በመሆኑ
ግልጽ የሰነድ ርክክብ፣ የፍተሻ፣ የሚዛን ልኬት፣ የደረቅ ጫት የመጋዘን ቆይታ ጊዜ በማሳጠር እንዲሁም የጫት
ተቀባይ ሀገርና ተረካቢ አካል አድርሻ ምዝገባ ዘመናዊ አሠራር በመዘርጋትና ለጉምሩክም ሆነ ለሴኩሪቲ ቁጥጥር
የወጪ ጫት የፖስታ ጥቅል ለብቻው ተለይቶ እየታሸገ በድሬዳዋና በአዲስ አበባ ቦሌ ካርጎ ተርሚናል በአየር
የሚላክበት አገልግሎት እንዲቀጥል ቢደረግ፤

4. ጫት ከሚመረትበት ቦታ ወደሚዘጋጅበት ቦታ በማጓጓዝ ሂደት ከመንገድ መሰረተ ልማት ችግር፣ የተሽከርካሪ እጥረት
በጫት ወቅታዊ ተደራሽነትና ጥራት ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ ማሳደሩ፣ በተጨማሪም ጫት በብዛት የሚመረትባት
አወዳይ ከተማ የትራንስፖርት መናኸሪያ አለመኖሩ የትራንስፖርት ስምሪቱ የውል ስርዓትን እንዳይከተልና የማጓጓዣ
ዋጋ ላይም አሉታዊ ተፅዕኖ መፍጠሩ፣ የመጓጓዣ ትራንስፖርት አይነቱም አይሱዙ በመሆኑ በጫት አያያዝና ጥራት
ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ አሳድሯል፡፡ ስለሆነም በቀጣይ የመሰረተ ልማት ማሻሻያ ስራ ቢደረግ፣ የተሽከርካሪ ሰምሪትና
ቁጥጥር ተግባራዊ ማድረግ የሚያስችል ደረጃውን የጠበቀ መናኸሪያ ቢገነባ፣ በአይሲዙ የተገደበው የማጓጓዣ ዓይነት
ማቀዝቀዣ የተገጠመላቸው ቫን የጭነት ተሸከርካሪዎች ለጫት ወጪ ንግድ ማጓጓዣነት እንዲውሉ እና የጫት
ላኪዎች ተጨማሪ ተሸከርካሪዎችን ማስገባት የሚችሉበት የማበረታቻ ስርዓት መዘርጋት ቢቻል፡፡

5. አሁን ላይ ወደ ውጭ ሀገር የሚላክ ጫት የሚዘጋጅበት ቦታ በዘፈቀደ፣ በተበታተነና ደረጃውን ባልጠበቀ መልኩ


የሚካሄድ በመሆኑ የጫት ወጪ ንግድ ዘመናዊነትን ለማረጋገጥ እና የጫቱን ጥራት ለመጠበቅ ከማሳው የተነሳ ጫት
የሚዘጋጅበትና የሚስተናገድበት ደረጃውን የጠበቀና በሲስተም የተደገፈ ዲጂታል ሚዛን ያለው (በየብስና በአየር)፣
ማቀዝቀዣ የተገጠመለት፣ አንድ አለቅ የአገልግሎት ማዕከል ያለበትና ሌሎች አስፈላጊ የሆኑ መሰረተ ልማቶች
የተሟሉለት ሜጋ የገበያ ማዕከል እንዲገነባ ቢደረግ፤

6. በክልል ከተማ መስተዳደሮች፣ ዞኖችና ወረዳዎች በየቦታው ኬላ እያቋቋሙ ለፅዳት በሚል የማዘጋጃ ክፍያ
በተሸከርካሪ ወይም በኪሎ ግራም የሚከፈል ቁርጥ ክፍያ በተደጋጋሚ የሚሰበሰቡ መሆኑ በተሽከርካሪ ጉዞ ላይ
አላስፈላጊ መጓተት በመፍጠር በወጪ ጫት ንግድ ላይ አሉታዊ ተዕፅኖ ያሳደረ በመሆኑ የፌዴራል መንግስት ከክልል
መስተዳደሮች ጋር በመነጋገር ኬላዎች የሚወገዱበትን ሁኔታ እንዲያመቻችና የማዘጋጃ ቤት ፅዳት ክፍያ የጉምሩክ
ዲክለራሲዮን መሠረት በማድረግ በመነሻ ቦታ ላይ አንድ ጊዜ ብቻ እንዲሰበሰብና የክፍያ ማስረጃው በሁሉም
አካባቢዎችና የመንግስት አካላት ላይ ተቀባይነት እንዲኖረው ቢደረግ፡፡

7. የጫት ወጪ ንግድን ለመመዘን አገልግሎት እየሰጠ ያለው ሚዛን የመመዘን አቅም ውስንነት ያለበት፣ የጥራት
አይነቱም የተለያየ መሆኑ (ማኑዋልና ዲጂታል) እንዲሁም በየጊዜው ካሊብሬት ባለመደረጉ የጫት ልኬቱ
ትክክለኛነት ላይ መተማመን የማይፈጥርና በውጭ ምንዛሬ ግኝት ላይም ተፅዕኖ ሊኖረው ስለሚችል የወጪ ንግድ
ጫት በሚመዘንባቸው ቦታዎች ማለትም አወዳይ፣ ድሬዳዋ፣ ጅግጅጋ፣ ኤርፖርት፣ ድሬዳዋ ላጋር፣ ደወሌ፣ ቶጎጫሌ፣
እና ጫት ላኪዎች ማህበራት መጋዘኖች ላይ የመመዘን አቅሙ ከፍ ያለ፣ ደረጃውን የጠበቀ፣ ዲጂታል የሆነ፣ የህትመት
ደረሰኝ ያለውና በመረጃ ቴክኖሎጂ ሥርዓት የተደገፈ፣ በየጊዜው ካሊብሬት የሚደረግ ሚዛን እንዲሟላና ጉምሩክ
በስጋት ሥራ አመራር ሥርዓት መሰረት ሁሉም የጫት ወጪ ንገድ እየተመዘነ የሚያልፍበት ስርዓት ተግባራዊ
ቢደረግ፡፡

8. የወጪ ጫት መሸጫ ዋጋ እንደየደረጃው የሚለያይ ቢሆንም ግልፅ የሆነ የደረጃ አወሳሰን ስርዓት ባለመኖሩ በላኪውና
ተቀባይ መካከል በሚደረግ ስምምነት በዘልማድ የሚወሰን በመሆኑ የደረጃው ትክክለኝነት ላይ እርግጠኛ መሆን
ስለማያስችል ሀገራችን በዚህ ምክንያት ልታጣ የምትችለውን የውጭ ምንዛሬ ለማስቀረት የጫት ወጪ ንግድ ደረጃ
የሚወሰንበት ግልፅ የአሰራር ስርዓትና ስታንዳርድ በፌደራል ንግድ ሚኒስቴር ተቀርፆ ተግባራዊ ቢደረግ፣
9. የጫት ምርት ንግድ እንደሌሎች የግብርና ምርቶች ድጋፍ የማይደረግለትና ማበረታቻ የሌለው በመሆኑ መንግስት
ከዘርፉ የሚገኘውን የውጭ ምንዛሪ ለማሳደግ እንደሌሎች የግብርና ምርቶች የድጋፍና ማበረታቻ ሥርዓት ዘርግቶ
ተግባራዊ ቢያደርግ፤

10. የጫት ምርት የውጭ ምንዛሬ ምንጭ በመሆን ከሚያስገኘው ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ አኳያ ለረጅም ጊዜ በስራ ላይ
ያለው ቁርጥ የጫት ዋጋ ያልተከለሰና ያልተስተካከለ በመሆኑ የውጪ ምንዛሬ ግኝት ላይ ተፅዕኖ ፈጥሯል፡፡ ይህም
በተቀባይ ሀገር ከሚሸጥበት የጫት ዋጋ ጋር ሲነፃፀርም በጣም ዝቅተኛ ያደርገዋል፡፡ ለዚህም ማሳያ በቦሌ ኤርፖርት
በኩል ወደ ሌሎች መዳረሻ ሀገራት የሚላከው እርጥብም ሆነ ደረቅ ጫት በኪሎ ግራም 35 ዶላር መሆኑ ወደ
ጅቡቲና ወደ ሶማሊያ የሚላከው የጫት መሸጫ ዋጋ አነስተኛ መሆኑን የሚያመለክት በመሆኑ ወደ እነዚህ ሀገራት
የሚላከው ጫት መሸጫ ዋጋው ገበያውን መሠረት ባደረገ ሁኔታ በየወቅቱ እየተፈተሸ ማስተካከያ የሚደረግበት
ሥርዓት ቢዘረጋ፤

11. በጅግጅጋ ያነጋገርናቸው ግለሰቦች የላኪነት ንግድ ፈቃድ ያላቸው ሆነው ከሌላ የጫት ላኪ ፈቃድ ውክልና
በመውሰድ የሚሰሩ በመሆኑ ዶላሩን ወደ ራሳቸው አካውንት ገቢ አድርገው እቃን ለማስመጣት አለመቻላቸውን
ቢገልፁም ጫት በራሳቸው ገንዘብ ከአርሶ አደሩ ከመግዛት ጀምሮ አዘጋጅተው ወደ ውጭ እስከመላክ ያለውን
አጠቃላይ ሥራ በመስራት የውጭ ምንዛሪውን በራሳቸው ከጥቁር ገቢያ ገዝተው ወይም ከተቀባያቸው ሰብስበው
ውክልና ለሰጣቸው ጫት ላኪ አካውንት ላይ ያስገባሉ፡፡ ይህ የሚያሳየው በግለሰቦቹና በወካዮቻቸው መካከል ግልፅ
ያልሆነ የጥቅም ትስስር ከመኖሩም በላይ በራሳቸው ስምና ንግድ ፈቃድ ጫት ወደ ውጭ መላክ ሲቻል በውክልና
መስራታቸው ህገውጥ የዶላር ንግድ እያከናወኑ መሆኑን ፍንጭ ይሰጣል፡፡ ስለሆነም ይህን የንግድ ግንኙነት
በተለይም ዶላር በመሰብሰብ በሌላ ሰው ስም የማስገባተን ሁኔታ በጥልቀት በመፈተሽ የራሱን የላኪነት ፈቃድ
በመደብቅ በስውር የጥቅም ግንኙነት በመፍጠር ከግብር የሚሸሽበትን ዋሻ የሚያፈርስ የተሻለ ሥርዓት በኢትዮጵያ
ብሔራዊ ባንክ፣ በፌደራል ንግድ ሚኒስቴርና በክልል ንግድ ቢሮ እንዲዘረጋ እንዲሁም እንደ አዲስ ሁሉም የጫት
ላኪ የንግድ ምዝገባና እድሳት እንዲያደርግ በፌደራል ንግድ ሚኒስቴር የተዘረጋው የኦን ላይን አገልግሎት አሰጣጥ
መሠረት ለክልል ንግድ ቢሮ ውክልና የጫት ወጪ ንግድ ፈቃድ የማጥራት እርምጃ በመውሰድ ወደ ትክክለኛው
ሥርዓት እንዲገባ ቢደረግ፡፡

12. በኢትዮጵያና በሶማሊያ መካከል ያለው የንግድ ግንኙነት እንደ ሌሎች ሀገራት ህጋዊ የንግድ ስርዓትን፣ የግዥና ሽያጭ
የሰነድ ልውውጥን እንዲሁም የውጭ ምንዛሬ ክፍያ ስርዓትን ባልተከተለ መንገድ በቶጎጫሌ ድንበር በኩል ለጫት
ወጪ ንግድ ቅድሚያ ክፍያ ዶላር በሰው እጅ እንዲመጣ ከተደረገ በኋላ ለዚሁ በተዘጋጀው ቅፅ በጉምሩክ
እየተመዘገበ ወደ ግልና ንግድ ባንኮች ገቢ የሚደረግበት አግባብ እንደ መደበኛ አሠራር መለመዱ የጥቁር ገበያን
በሀገራችን በማስፋፋት ፍትሃዊ የንግድ ውድድር እንዳይኖር በማድረግ በሀገር ኢኮኖሚ ላይ ከፍተኛ አሉታዊ ጫና
እያሳደረ በመሆኑ በሀገር ደረጃ ከሶማሊያ ሁሉም የመንግስት አካላት ጋር በመወያየትና የሁለትዮሽ ስምምነት
በመፈራረም ህጋዊ የንግድ ግንኙነት፣ የሰነድ ለውውጥ እና የፋይናንስ ዝውውር ስርዓትን በተከተለ አግባብ
የሚፈጽምበት አሠራር እንዲዘረጋ ቢደረግ፡፡
13. በኮንትሮባንድ ከአገር የሚወጣው የጫት ምርት ከጊዜ ወደ ጊዜ መጨመር፣ የጫት ኮንትሮባንድ መተላለፊያ
መስመሮችም በየጊዜው መቀያየር እንዲሁም ለጠረፍ አካባቢ ነዋሪዎች ፍጆታ የተፈቀደው የጫት ኮታ በየጊዜው
እያደገ የሚመጣውን የህዝብ ቁጥር እንዲሸፍንና ወቅታዊ እንዲሆን አለመደረግ፣ ህብረተሰቡ የጫት ኮንትሮባንድን
በመከላከል ሂደት ተባባሪ ያለመሆን ዝንባሌ መፈጠሩና በአካባቢው ያሉ የመስተዳደርና የፀጥታ አካላት በቅንጅት
የጫት ኮንትሮባንድን ከመከላከል ይልቅ ለኮንትሮባንዲስቶች ተባባሪ መሆናቸው ከፍተኛ የጫት መጠን
በኮንትሮባንድ እንዲወጣ በማድረግ ህጋዊ የወጪ ጫት ንግድን እየተገዳደረና የውጭ ምንዛሬ ግኝት ላይም ከፍተኛ
እንቅፋት እየፈጠረ በመሆኑ የኮንትሮባንድ እንቅስቃሴ ላይ የሚደረገው ክትትልና ቁጥጥር በማጠናከር፣ በዚህ ዘርፍ
የተሰማሩ የክትትልና ቁጥጥር ባለሙያዎችና የፀጥታ አካላት ተገቢውን የህግ ከለላና የህይወት መድን ዋስትና
እንዲያገኙ ማድረግ ፣ ስትራቴጅክ የሆኑና የተመረጡ የጉምሩክ ኬላዎችን በድንበር አካባቢ መጨመርና በፓትሮል
ተሸከርካሪና ሰው ኃይል ማጠናከር ፣ በድንበር አካባቢ ካሉ ከአጎራባች ሀገሮች እና ከክልል መንግስት ጋር በመሆን
ቅንጅታዊ አሰራሩን ማጠናከርና ለዚሁ የሚሆኑ አስፈላጊ መሰረተ ልማቶችን ማሟላት፣ የአካባቢውን ህብረተሰብ
ግንዛቤ ማሳደግና አስፈላጊውን ሎጂስቲክስ በማሟላት የቁጥጥር ስራው በቴክኖሎጂ እንዲደገፍ ቢደረግ፡፡ 6

You might also like