Download as pdf or txt
Download as pdf or txt
You are on page 1of 11

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን

የደብረ ገሊላ ዐማኑኤል ካቴድራል


እግዚአብሔር ምስሌነ ሰንበት ትምህርት ቤት

የምስጢረ ንስሐ ሥርዓት አፈጻጸም በቤተክርስቲያን

በመምህር ሀብታሙ ይርጋ

ኅዳር ፳፻፲፮
አዲስ አበባ ኢትዮጵያ
የምስጢረ ንስሐ ሥርዓት አፈጻጸም በቤተክርስቲያን

የዚህ ጥናትና ምርምር ዋና ጹሑፍ የሚቀረበው


ለደብረ ገሊላ ዐማኑኤል ካቴድራል
እግዚአብሔር ምስሌነ ሰንበት ትምህርት ቤት ትምህርት ክፍል ነው

በመምህር ሀብታሙ ይርጋ

መስከረም ፳፻፲፮
አዲስ አበባ ኢትዮጵያ
ረቂቅ ሃሳብ (Abstract)
ንስሐ ማለት ነስሐ ተጸጸተ ካለው የግእዝ ቃል የተገኘ ሲሆን በሰሩት ኃጢአት መጸጸት፣ ማዘን ወደ እግዚአብሔር ለመመለስ
መወሰን እንዲሁም ከዘላለማዊው ፍርድ የሚያድን፣ ዘማዊዉን እንደ ድንግል፣ ሌባውን እንደ መጽዋች የሚያደርግ በፊት
ከተሰራው ኃጢአት ንጹሕ አድርጎ ከእግዚአብሔር ጋር አንድ የሚያደርግ ምስጢር ነው፡፡ በመሆኑም የዚህ ጥናት ዋና ዓላማ
የምስጢረ ንስሐ ሥርዓት በቤተክርስቲያን ውስጥ ያለውን አፈጻጸም መቃኘት ሲሆን የደብረ ገሊላ ዐማኑኤል ካቴድራል
ደግሞ ጥናቱ የሚሰራበት ቦታ ነው፡፡ እንዲሁም ይህ ጥናት ስድስት መሰረታዊ ዓላማዎች ሲኖሩት እነዚህም ምዕመናኑ
በሀገሪቱ ኢኮኖሚያዊ እና ማኅበራዊ ኩነቶች ምክንያት ከምሥጢረ ንስሐ የሥርዓትና የአፈጻጸም ድርሻቸው (ሱታፌያቸው)
ላይ ያለውን ተጽዕኖ መቃኘት፣ ድኅረ ዘመናዊነት (Post Modernism) በምሥጢረ ንስሐ አፈጻጸም ላይ ያለውን አሉታዊ
ተጽዕኖ መመርመር፣ በምሥጢረ ንስሐ ሥርዓት አፈጻጸም ዙርያ በቤተክርስቲያን መዋቅር ደረጃ ያሉት የባለድርሻ አካላት
ኃላፊነታቸውን መቃኘት እና ማሳወቅ፣ ከምሥጢሩ ጋር ቀጥተኛ ተሳትፎ ያላቸው ካህናት አባቶቻችን በሥርዓቱ ዙርያ
ሊኖራቸው የሚገባውን የእውቀትና የአፈጻጸም ሒደትን ማመላከት፣ በምዕመናኑ ዘንድ ያለ የተቃራኒ ጾታ ግንኙነቶች
በምሥጢረ ንስሐ ሥርዓት እና አፈጻጸም ዙርያ የሚኖረውን ተጽዕኖ ማሳየት እንዲሁም በአሁኑ ወቅት በምሥጢረ ንስሐ
ሥርዓትና አፈጻጸም ዙርያ የምዕመናኑ የግንዛቤ እና በምሥጢሩ ያላቸውን የተካፋይነትን መጠን ወይም ያሉበትን ሁኔታ
መቃኘት ናቸው፡፡ በተጨማሪም በዚህ ገላጭ ጥናት ወስጥ በጠቅላላው_______ ያህል ሰዎች(ምዕመናን) የተሳተፉ ሲሆን
መረጃዎችም በጥናቱ ላይ የተካተቱትን ሃሳቦችን ሊገልጥ(ገላጭ) በሆነ መልኩ ለማቅረብ የሚሞከርበት ነው፡፡ እንዲሁም
በጥናቱ የሚገኙ ውጤቶችንም ወደ ትርጉም ወዳለው አቀራረብ ለመቀየር የሚጠቀምበት መንገድ የቃላት እና የቁጥር
ድቅል(Both Qualitative and Quantitative Method) ነው፡፡ ብሎም ጥናቱ ገላጭ የጥናትና ምርምር ንድፈ ሃሳብ
(Research Design) ይጠቀማል እንዲሁም ለናሙና የተመረጡትም አካላት በጉዳዩ ላይ ቀጥተኛ ተሳታፊነት አላቸው
ተብለው በምዕመናኑ ዘንድ የሚታወቁትን በመጠቀም የተሰራ ከመሆኑም በተጨማሪ ጥናቱ ርዕቱና ኢ - ረቱዕ ብሎም የቡድን
ውይይትን እንደ መረጃ ምንጭነት የሚጠቀም ነው፡፡ በመጨረሻም ጥናቱ የማጠቃለያ እና የመደምደሚያ ሃሳቦችን የሚያነሳ
ሲሆን በተጨማሪም በአጥኚዎቹና በተለያዩ አካላት የተሰጡ የመፍትሔ ሃሳቦችንም በተገኘው የጥናቱ ውጤት ላይ
በመመስረት የተሰጠበት ነው፡፡ እነዚህም የመፍትሔ ሃሳቦች ከምዕመናኑ ወገንም ሆነ በጥናቱ ላይ ከተጠቀሱት የባለድርሻ
አካላት መሐከል የምስጢረ ንስሐ ሥርዓት አፈጻጸም በቤተክርስቲያን ውስጥ ካለበት ዝቅተኛ ደረጃ ከፍ ለማድረግ
በሚያስችል ሁኔታ በደብሩም ሆነ በሰንበት ት/ቤቱ አደረጃጀት በኩል አስፈላጊ ናቸው ተብለው የቀረቡትን የመፍትሔ
ሃሳቦችን ተግባራዊ ከማድረግ አንጻር አቅጣጫ የሚጠቁም ነው፡፡
ማውጫ
አርዕስት ገጽ
ረቂቅ ሃሳብ (Abstract)..............................................................................................................

ምዕራፍ አንድ

፩. መግቢያ (Introduction)....................................................................................
፩.፩ የጥናትና ምርምሩ ዳራ (Background of the Study)..............................................

፩.፪ የችግሩ ምንነት (Statement of the problem).......................................................

፩.፫ የጥናትና ምርምሩ ቁልፍ ጥያቄዎች (Basic research question)............................

፩.፬ የጥናትና ምርምሩ ዓላማ (Objective of the study).................................................

፩.፬.፩ ዓብይ ዓላማ (General Objective)...............................................................

፩.፬.፪ ንዑስ ዓላማ (Specific Objective)...............................................................

፩.፭ የጥናትና ምርምሩ ጠቀሜታ (Significance of the study).......................................

፩.፮ ጥናትና ምርምሩ ውስን ያልሆነበት (Delimitation of the study)..............................

፩.፯ የጥናትና ምርምሩ ውስንነት (Limitation of the study)............................................

፩.፰ የቃላት ትርጉም (Definition of term).....................................................................

፩.፱ የጥናትና ምርምሩ ሥነ - ዘዴ (Research Design and Methodology)...................

፩.፲ በጥናትና ምርምሩ ሽፋን ያገኘው ቦታ (Specific area of the study)........................

፩.፲፩ የጥናትና ምርምሩ ንድፈ ሃሳብ (Research Design).....................................

፩.፲፪ በጥናቱ የሚካተቱ የሕዝብ ስብጥር (Target Population)...............................

፩.፲፫ የጥናቱ የናሙና መጠን (Sample size)........................................................

፩.፲፬ የናሙና አወሳሰድ ዘዴ (Sampling Techniques)...........................................

፩.፲፭ ጥናቱ የተጠቀመባቸው የመረጃ አይነቶች (Types of data)............................

፩.፲፮ ጥናቱ የሚጠቀመው የመረጃ አሰባሰብ ዘዴ (Data Collection Method)...........

፩.፲፯ የጥናቱ የመረጃ አተናተን ዘዴ (Data Analysis Method)...............................

፩.፲፰ የጥናቱ የወረቀት መዋቅር (Organization of the study)..............................


ምዕራፍ ኹለት

፪. የተዛማጅ ጹሑፍ ዳሰሳ (Literature Review)........................................


፪.፩ ጽንሰ ሐሳባዊ የተዛማጅ ጹሑፍ ዳሰሳ (Theoretical Literature Review)...................

ዋቢ መጽሐፍት (Reference)................................................................................
ምዕራፍ አንድ
፩. መግቢያ (INTRODUCTION)
፩.፩ የጥናትና ምርምሩ ዳራ (Background of the Study)
ምሥጢረ ንስሐ በምሥራቅ አብያተ ክርስቲያናት ሰባቱ ምሥጢራተ ቤተ ክርስቲያን ተብለው በሥርዓት በቀኖና
ከሚነገሩት ምሥጢራት አንዱ ነው፡፡ በቤተ ክርስቲያናችን ግን ምሥጢራት ተብለው የሚነገሩት አምስት ናቸው፡፡

ንስሐ ከሁሉም ምስጢራተ ቤተክርስቲያን በፊት የሚከናወን ነው። ምክንያቱም ምስጢራትን ሁሉ ለመፈጸም የሚያበቃው
የመንፈስ ቅዱስ ጸጋ እንዲሁም በረከት የሚገኘው በንስሐ ስለሆነ ነው። ይህንንም ለማጠየቅ በሉቃስ ወንጌል ላይ
የተመዘገበውን የጠፋውን ልጅ ታሪክ ስንመለከት ወደ አባቱ ቤት መግባት የቻለው የንስሐ ሒደትን ከአከናወነ በኋላ መሆኑን
እንረዳለን። (ሉቃ.፲፭, አቡነ ሺኖዳ ፫ኛ, ፴፪) ነገር ግን ከዚህ ሰፋ ባለ መንገድ ለማየት የተፈለገ እንደሆነ ከቀደመ ክፋት
አመጽ ተጸጽቶ መመለስ ፣ ኃጢአትን እርኩሰትን እርም ማለት ሁለተኛ ከአስከፊ ግብር እና መንገድ ላይ ላለመገኘት በቁርጥ
ሕሊና መወሰን እና ቃል መግባት ማለት ነው፡፡ (eotcssd.org/dogma-ethiopian orthodox tewahido
church.)

ስለዚህ ንስሐ ኃጢአትን ለመደምሰስ በክርስቲያኖች ሕይወት ውሰጥ እጅግ አስፈላጊ እና ዓይነተኛ የመፍትሔ መሣሪያ ነው፡፡
በመጽሐፍ ቅዱስም " ኃጢያታችሁ ይደመሰስ ዘንድ ንስሐ ግቡ ተመለሱም" በማለት መጻፉም ይኽንኑን ሐሳብ የሚያጸና
ሆኖ እናገኘዋለን (ሐዋ. ፫ ÷፲፱)፡፡ ንስሐ መናዘዝ ፣ ኑዛዜ ማድረግ ወይም ኃጢያትን ለአበ ነፍስ (ለካህን) መናገርና ራስን
መግለጽ ነው ፡፡

ንስሐ በአፈጻጸሙ ረገድ ሲታሰብ ምሥጢራዊ ጠባይ ይኑረው እንጂ በትምህርታዊ ገጽታው በዚህ መልክ አይነገርም፡፡
ይሁንና ጉዳዩ ይህን ያህል አከራካሪ ምክንያት ስለማያስከትልና የምሥራቃውያኑም አባባል በእኛ ይትበሃል ውስጥ
እየተለመደ ስለመጣ አሁን ለተነሳንበት መሠረተ ሐሳብ አርእስት አድርገን ተጠቅመንበታል፡፡ ንስሐ በአዲስ ኪዳን ትምህርት
ውስጥ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወደዚህ ዓለም ስለመምጣቱና ሰው ስለመሆኑ፤ ሥጋም ስለመልበሱ ከሚነገሩት ዓበይት
ምክንያቶች አንዱ ምክንያት መሆኑ ይታወቃል፡፡ ስለሆነም “እኔ ኃጢአተኞችን ወደ ንስሐ ልጠራ ነዉ እንጂ ጻድቃንን ልጠራ
አልመጣሁም” የሚል ተጽፎ ማንበባችን ለዚህ ማሳያ ነው (ማቴ. ፱÷፲፫)፡፡

ስለዚህ ንስሐ ከዓሠርቱ ትእዛዛት አንዱ ሁኖ በሕግ ወይም በትእዛዝ መልክ ባይጻፍም እግዚአብሔር ለሰው ልጆች ምሕረቱን
ርኀራኄውንና ትዕግሥቱን በአጠቃላይ ልግስናውን የገለጸበትና የሚገልጽበት ታላቅ ሥርዓት ነው፡፡ በአርእስቱም ከፍ ብሎ
እንደ ተገለጸው ጥልቅና ረቅቅ ምሥጢራዊነቱ በጥቂቱም ቢሆን ሊያነጋግር የሚችል ነው፡፡ በዓለማዊ ሕግ በደለኛ ስለሠራው
በደል በሚሰጠው ፍርድ “የቅጣት ማቃለያ”የፍርድ ማሻሻያ የሚባሉ አንቀጾች ቢኖሩም ከቅጣት ነፃ የሆነ ትምህርት የለም፡፡
አልፎ አልፎ ምሕረት የሚል ድምጽ ቢሰማም በደለኛው ለተወሰኑ ጊዜያት በቅጣት ላይ ከቆየ በኋላ ይሆናል፡፡ የእግዚአብሔር
ምሕረት ግን ፍጹም ይቅርታ ስለሆነ ፈጽሞ ከዚህ ይለያል፡፡ ኃጢአተኛው በኃጢአቱ ምክንያት ያጣውን ሁሉ ያገኛል፡፡ ወደ
ቀደመ ክብሩና ወደ ቀደመ ሕይወቱ ይመለሳል፡፡ ያለፈው ኃጢአቱና በደሉ ሁሉ ይሠረይለታል፡፡

የሰው ልጅ በጥምቀት ከሥላሴ ተወልዶ በሜሮን የከበረ በክርስቶስ ደም የተዋጀ የመንፈስ ቅዱስ ቤተ መቅደስ ቢሆንም
በደካማ አእምሮ እና ሰውነት ኃጢአትን ሊያደርግ ይችላል፡፡ ስለዚህም ንስሐ ከሰሩት ኃጢአት የሚጸዱበት መንፈሳዊ የነፍስ
መድኃኒት በመሆኑ ዕለት ዕለት የሚፈጸምም ምስጢር ነው፡፡ ይሁን እንጂ ንስሐ በቤተክርስቲያናችን ውስጥ ካሉት ሰባቱ
ምሥጢራተ ቤተክርስቲያን መካከል የሚመደብ ዐብይ ሥርዓት ቢሆንም ከጊዜ ወዲህ ግን በአፈጻጸሙ ዙርያ ብዙ ክፍተቶች
እየተስተዋሉ ይገኛሉ፡፡ በመሆኑም ይኽ ጥናት ለሰው ልጆች ከወደቁበት በማንሳትና ታላቅ የመዳን ተስፋ የሚሰጠዉ ይህ
ምስጢር በንስሐ አባቶች እና ተነሳሒዎች (ልጆች) መካከል ባለ የዕውቀት ክፍተትና በሌሎች ተዛማጅ ችግሮች ምክንያት
የሚፈጠሩ ተግዳሮቶችን ለመቀነስ ብሎም ለማጥፋት በመሻት ላይ የተመሠረተ ተምኔት ያለው እና የንስሐ ሥርዓት አፈጻጸም
በቤተክርስቲያን ምን መምሰልና መሆን እንዳለበት ለማመላከት ነው፡፡ ጥናቱም ከተፈጸመ በኀላ በአጥኚዎች አስፈላጊ እና
መሠረታዊ ናቸው ተብለው የሚታሰቡትን የመፍትሔ ሃሳቦች የሚሰጡበት ሲሆን እነዚህም በጥናቱ የሚገኙ ችግሮች ላይ
መሠረት ያደረጉ ይሆናሉ፡፡
፩.፪ የችግሩ ምንነት (Statement of the problem)
ንስሐ ለተጠመቁ ሰዎች ከጥምቀት በኋላ የተሰጠች ሀብት ፣ በጥምቀት ከእግዚአብሔር የምትገኝ የልጅነት ሁለተኛ ማዕረግ
፣ በሃይማኖት ገንዘብ ያደረግነው የመንግሥተ ሰማያት አራቦን ፣ ለሚሿት ሰዎች የተከፈተች የይቅርታ በር ናት ፡፡ ስለሆነም
በንስሐ በርነት ከፈጣሪ ወደሚገኝ ቸርነት እንቀርባለን። በአጠቃላይ ምሥጢረ ንስሐ አንድ ሰው ከጥምቀት በኋላ
የፈጸመውን ጥፋት አውቆ ሁለተኛ ጥፋቱን ላለመድገም ወስኖ በእግዚአብሔርና በካህኑ ፊት ተንበርክኮ ከልቡ ተጸጽቶ
ኃጢአቱን በመናዘዝ ከኃጢአቱ እስራት የሚፈታበትና ከእግዚአብሔር ይቅርታን የሚያገኝበት ታላቅ የይቅርታ ምሥጢር
ነው። (https://t.me/s/mahtotetonetor before 59)

ስለሆነም ዲያብሎስ ከሚዋጋባቸው የድኅነት መንገዶች ውስጥ ንስሐን የሚያክል የለም፡፡ ምክንያቱም ንስሐ ጠላት ዲያብሎስ
የክርስቲያኖችን ሕይወት ለማጥፋት የገነባውን የኃጢአት ሕንፃ ሁሉ በእግዚአብሔር ቸርነት እንዳልነበረ በማድረግ
ስለሚያፈርስበት ነው፡፡ ከዚህ የተነሳ የሰው ልጅ ንስሐ እንዳይገባ ቢገባም ቶሎ እንዳይሆን የተቻለውን ከማድረግ ፈጽሞ
አያርፍም፡፡(አቡነ ሺኖዳ ፫ኛ, ፴፫)

እንደሚታወቀው በከተማችን በሚገኙ በአብዛኛዎቹ አብያተ ክርስቲያናት ውስጥ የምስጢረ ንስሐ ሥርዓት አፈጻጸም ከጊዜ
ወደ ጊዜ በምዕመናኑ ዘንድ ያለው ሱታፌ እየቀነሰ ከመምጣቱ ጋር ተያይዞ በተለይም የወጣቶች ድርሻ (ሱታፌ) እጅግ በጣም
ሊባል በሚችል ደረጃ እየተዳከመ መምጣቱን ጥቂት የማይባሉ ጥናቶች ያረጋገጡት እውነታ ከሆነ ውሎ አድሮዋል፡፡

ስለዚህ በምስጢረ ንስሐ ሥርዓት አፈጻጸም ላይ ጥናት ለማድረግ በአጥኚዎቹ ታምኖበታል፡፡ ሆኖም በዚህ ጥናት አጥኚዎች
የችግሮቹን መንስኤ ሙሉ በሙሉ ለመለየት እና መፍትሔ ሰጥቶ ማለፍ ባይቻልም አቅም በፈቀደና በተቻለ መጠን በዋነኛነት
ለችግሩ መንስኤ ይሆናሉ ተብለው በምዕመናኑ ዘንድ ለቀረቡት ተግዳሮቶች የመፍትሔ ሃሳብ ሰጥቶ ማለፍ ነው፡፡ በመሆኑም
ይህ የጥናትና ምርምር ጹሑፍ ለመቃኘት የሚሞክረው በአሁኑ ሰዓት የምስጢረ ንስሐ ሥርዓት አፈጻጸም ምን ይመስላል
እንዲሁም በአፈጻጸሙ ዙሪያ ያሉበትን ተግዳሮቶች ምንድን ናቸው የሚለውን በመለየት መቆጣጠር የሚቻልበትን መንገድ
ጥልቅ በሆነ ቅኝታዊ አትኩሮት በመጠቀም የመፍትሔ ሃሳብ ለመስጠት የሚሞከርበት ነው፡፡

፩.፫ የጥናትና ምርምሩ ቁልፍ ጥያቄዎች (Basic research question)


➢ የሀገሪቱ ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ ኩነቶች ምዕመኑ በምሥጢሩ ዙሪያ ያለውን ሱታፌ ቀንሶታል ወይም
ይቀንሰዋል ማለት ይቻላል ?

➢ ድኅረ ዘመናዊነት (Post Modernism) በምሥጢረ ንስሐ አፈጻጸም ዙሪያ አሉታዊ ተጽዕኖ አሳርፎዋል ማለት
ይቻላል ?

➢ ምሥጢረ ንስሐ ለሌሎች ምሥጢራተ ቤተክርስቲያን በር ከፋች እንደ መሆኑ መጠን አስፈላጊውን አትኩሮት
በመዋቅር ደረጃ ካሉት የባለድርሻ አካላት አግኝቶዋል ማለት ይቻላል ?

➢ ካህናት በምሥጢረ ንስሐ ዙሪያ ያላቸው የእውቀትና የአፈጻጸም ሒደት አግባብነት ያለው ነው ማለት ይቻላል?

➢ የተቃራኒ ጾታ ግንኙነት በምሥጢረ ንስሐ አፈጻጸም ዙሪያ አሉታዊ ተጽዕኖ አለው ተብሎ ይታመናል ?

➢ በአሁኑ ወቅት በምዕመናኑ ዘንድ በምሥጢረ ንስሐ ሥርዓትም ሆነ በአፈጻጸሙ ዙርያ የግንዛቤ ወይም የእውቀት
ችግር አለ ማለት ይቻላል?

፩.፬ የጥናትና ምርምሩ ዓላማ (Objective of the Study)


፩.፬.፩ ዐብይ ዓላማ (General objective)

በቤተክርስቲያናችን ውስጥ ምሥጢራተ ቤተክርስቲያን ብለን ከምንማራቸው እና ከምንፈጽማቸው ምሥጢራት መሐከል


ምሥጢረ ንስሐ አንዱ ነው፡፡ እንዲሁም የንስሐን ሥርዓትና አፈጻጸም ደረጃን ከፍ ከማድረግ አንጻር ከፍተኛ አትኩሮት
የሚፈልግ የምሥጢራተ ቤተክርስቲያን አይነት ነው፡፡ በመሆኑም የዚህ ጥናት ዐብይ ዓላማም በአሁኑ ሰዓት የምሥጢረ
ንስሐ ሥርዓት አፈጻጸም በቤተክርስቲያን ምን እንደሚመስል መቃኘት ነው፡፡

፩.፬.፪ ንዑስ (ዝርዝር) ዓላማ (Specific objective)

❖ ምዕመናኑ በሀገሪቱ ኢኮኖሚያዊ እና ማኅበራዊ ኩነቶች ምክንያት ከምሥጢረ ንስሐ የሥርዓትና የአፈጻጸም
ድርሻቸው (ሱታፌያቸው) ላይ ያለውን ተጽዕኖ መቃኘት

❖ ድኅረ ዘመናዊነት (Post Modernism) በምሥጢረ ንስሐ አፈጻጸም ላይ ያለውን አሉታዊ ተጽዕኖ መመርመር

❖ በምሥጢረ ንስሐ ሥርዓት አፈጻጸም ዙርያ በቤተክርስቲያን መዋቅር ደረጃ ያሉት የባለድርሻ አካላት
ኃላፊነታቸውን መቃኘት እና ማሳወቅ

❖ ከምሥጢሩ ጋር ቀጥተኛ ተሳትፎ ያላቸው ካህናት አባቶቻችን በሥርዓቱ ዙርያ ሊኖራቸው የሚገባውን የእውቀትና
የአፈጻጸም ሒደትን ማመላከት

❖ በምዕመናኑ ዘንድ ያለ የተቃራኒ ጾታ ግንኙነቶች በምሥጢረ ንስሐ ሥርዓት እና አፈጻጸም ዙርያ የሚኖረውን
ተጽዕኖ ማሳየት

❖ በአሁኑ ወቅት በምሥጢረ ንስሐ ሥርዓትና አፈጻጸም ዙርያ የምዕመናኑየግንዛቤ እና በምሥጢሩ ያላቸውን
የተካፋይነትን መጠን ወይም ያሉበትን ሁኔታ መቃኘት

፩.፭ የጥናትና ምርምሩ ጠቀሜታ (Significance of the study)


✓ ምሥጢረ ንስሐ ማለት አንድ ሰው ከጥምቀት በኋላ የፈጸመውን ጥፋት አውቆ ሁለተኛ ጥፋቱን ላለመድገም ወስኖ
በእግዚአብሔርና በካህኑ ፊት ተንበርክኮ ከልቡ ተጸጽቶ ኃጢአቱን በመናዘዝ ከኃጢአቱ እስራት የሚፈታበትና
ከእግዚአብሔር ይቅርታን የሚያገኝበትታላቅ የይቅርታ ምሥጢር ነው። በመሆኑም ጥናቱ የሚያበረክተው
ጠቀሜታ ከዚህ አንደሚከተለው በሚቀርቡ ሃሳቦች ላይ የተመሰረተ ነው፡፡

✓ ጥናቱ በምሥጢረ ንስሐ ሥርዓትና አፈጻጸም ረገድ የሚስተዋሉ ተግዳሮቶችን በማሳየት ጥናቱ ትኩረት ሰጥቶ
የሚሰራባቸው የባለድርሻ አካላት መውሰድ ስለሚኖርባቸው የመፍትሔ እርምጃዎችን ከመጠቆም አንጻር
ጠቀሜታ ይኖረዋል፡፡

✓ በዚህ ጥናት የሚገኙ ውጤቶች በጥናቱ ትኩረት ያገኙትን አካላት ማለትም ካህናት አባቶች እና የምዕመናኑን
የግንዛቤ መጠን ከማሳደግ አንጻር ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያለው ከመሆኑም በላይ በምሥጢረ ንስሐ ሥርዓት አፈጻጸም
ዙርያ ያሉ ተግዳሮቶች በምን ያህል ደረጃ የድኅነት መንገድ በሆነዉ የንስሐ ሕይወት ላይ ያለውን አሉታዊ ተጽዕኖ
ከማሳየት አንጻር ጠቀሜታ ይኖረዋል፡፡

✓ ዘመን አመጣሽ የሆኑ አስተሳሰቦችን (Post Modernization Thinking) ከጥንታዊው የቤተክርስቲያን


አስተምህሮት አንጻር ያላቸውን የተቀባይነት መጠን ከማሳየት በዘለለ የሚያስከትሉትን አሉታዊ ተጽዕኖ ከመግለጽ
አንጻር ጠቀሜታ አለው፡፡

✓ በኢኮኖሚያዊ ችግሮች እና በማህበራዊ ትስስሮች አማካኝነት የሚፈጠሩ አፈ ታሪካዊ መረዳ (Mythological


understanding) በምሥጢረ ንስሐ ሥርዓትና አፈጻጸም ዙርያ የሚያሳጡትን በቁዔት ከመግለጥ አንጻር
ጠቀሜታ ይኖረዋል ተብሎ ይታመናል፡፡

✓ በቤተክርስቲያናችን ሥርዓትና ትውፊት መሰረት የተቃራኒ ጾታ ግንኙነት እንዴት ሊመሰረት እንደሚገባው እና


በውስጡም ለሚፈጠሩ ችግሮች መፍትሔ የመስጠት አቅማችንና አቅጣጫችን ምን መሆን እንዳለበት ከማመላከት
ረገድ ራሱን የቻለ በቁዔት ይኖረዋል ተብሎ ይታመናል፡፡
✓ ጥናቱ በአጠቃላይ በምዕመናኑ ዘንድ ያለውን የግንዛቤ እና የአፈጻጸም ሒደትን በማጎልበት ምሥጢረ ንስሐ ለሰው
ልጆች የሚሰጠውን የድኅነት ተስፋን ከማመልከት አንጻር ፋይዳ ይኖረዋል ተብሎ ይታመናል፡፡

✓ ጥናቱ በምሥጢረ ንስሐ ሥርዓት አፈጻጸም ዙርያ ያለውን የአትኩሮት ደረጃን ከመጨመር አንጻር ጠቀሜታ
ይኖረዋል፡፡

✓ በጥናቱ የሚገኙ ውጤቶችን በማሳወቅ በቀጣይ በርዕሰ ጉዳዩ ላይ ከዚህ ሰፋ ባለ መልኩ ጥናት ለመስራት ለሚነሱ
አጥኚዎች ጉልህ ጠቀሜታ ይኖረዋል በሚል ጽኑ ተስፋ የሚሰራ የጥናትና የምርምር ጹሑፍ ነው፡፡

፩.፮ የጥናትና ምርምሩ ወሰን (Scope or Delimitation of the study)


እንደሚታወቀው በአሁን ሰዓት በአዲስ አበባ ከተማ ብቻ ከ ፻፵ በላይ አድባራትና ገዳማት መኖራቸውን መረጃዎች
ያመለክታሉ (https://addisababa.eotc.org.et). ሆኖም በሁሉም አድባራትና ገዳማት ዞሮ ጥናት ለማድረግ
የገንዘብና የጊዜ እጥረት ከመኖሩም በላይ በአሁኑ ወቅት የኮሮና ቫይረስ (Covid 19) በሀገራችን ላይ እክል በመፍጠሩ
ምክንያት በጥናቱ ወሰን ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ ፈጥሮዋል፡፡ ስለዚህ ይህ ጥናት በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን
የደብረ ገሊላ ዐማኑኤል ካቴድራል ላይ ብቻ የሚሰራ ሲሆን በተጨማሪም ጥናቱ በቤተክርስቲያን ውስጥ ካሉት የክህነት
ደረጃዎች ውስጥ በካህናት ላይ የሚሰራ ሆኖ በምዕመናኑም በኩል ወጣቶች ላይ በዋነኛነት ሽፋን ሰጥቶ የሚሰራባቸው አካላት
ናቸው፡፡ ብሎም ይህ ጥናት በርዕሰ ጉዳዩ ላይ በተመለከተ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ዶግማና ሥርዓት
መሰረት የተዘጋጁትን መረጃዎችን ብቻ እንደ አጋዥነት የሚጠቀም ነው፡፡

፩.፯ የርዕሰ ጉዳዩ የቃል በቃል ትርጉም (Operational, Definition of term)


ምሥጢር:- ምሥጢር ማለት ቃሉ የግሪክ ቋንቋ ሆኖ ቃሉ ከግእዝና ከአማርኛ በቀጥታ የተወረሰ ሲሆን ትርጉሙም ድብቅ
፣ ስውር፣ ሽሽግ፣ ረቂቅ ፣ ለቅርብ ዘመድ ካልሆነ በቀር የማይገለጥ ማለት ነው (https://addisababa.eotc.org.et).

ንስሐ:- ንስሐ ቃሉ የግእዝ ሲሆን ትርጉሙም በሰሩት ኃጢያት መጸጸት ምነው ባልሰራሁት ባላደረኩት ብሎ ማልቀስ ወደ
ኃጢያት ላለመመለስ መወሰን፣ በሕጉ ጸንቶ ለመኖር ቃል መግባት ማለት ነው (https://addisababa.eotc.org.et).

ሥርዓት:- ሥርዓት “ሠርዐ” ሠራ ከሚለው የግዕዝ ቃል የወጣ ሲሆን ትርጉሙም ደንብ፣ አሠራር፣ መርሐ ግብር ማለት ነው
((https://addisababa.eotc.org.et).

አፈጻጸም:- አፈጻጸም ማለት አተገባበር ወይም በጽንሰ ሐሳብ ደረጃ የሚታወቀውን እውቀት ወደ ተጨባጭነትና ተፈጻሚነት
የምንቀይርበት ሥርዓት ነው፡፡

ቤተክርስቲያን:- ቤተክርስቲያን እንደ ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን አመሥጥሮ ቤተ ክርስቲያን ማለት “እግዚአብሔር ግዕዛን
ካላቸው ፍጥረታት ጋር ያለው ግንኙነት ነው ይላሉ አንድም ቤተክርስቲያን ማለት የክርስቲያን ወገን ማለት ነው ክርስቲያን
የሆነ ሁሉ (የምእመናን አንድነት ጉባኤ) የሚጠራበት ስም ቤተክርስቲያን ነው፡፡ ይህም ስብስቡን ብቻ ሳይሆን በዋናነት
በመካከላችን ያለውን ፍቅር ትስስር ህብረት አንድነት ነው የሚመለከተው፡፡ቤተ ክርስቲያን በክርስቶስ ራስነት አንድ አካል
የሆኑ የምእመናን አንድነት ናት (https://astemhro.com/).

፩.፰ የጥናትና ምርምሩ ሥነ - ዘዴና አካሄድ (Methodology of the study)


፩.፰.፩ የጥናትና ምርምሩ ንድፈ ሃሳብ (Research Design)

ይህ ጥናትና ምርምር የሚከተለው የጥናት ንድፈ ሃሳብ (Research design) አይነት ገላጭ የጥናትና ምርምር ንድፈ ሃሳብ
(Descriptive research design) የሚባለውን ሲሆን ይህም የተመረጠበት ምክንያት ንድፈ ሃሳቡ የአንድን ሁኔታ
ትክክለኛ ገጽታ ለማወቅ ወይም በትክክል ለመግለጽ ሲባል መረጃዎችን ከመጽሐፍትና ከሌሎችም ጥናታዊ የጽሑፍ
ምንጮች በማሰባሰብና የምልከታ መረጃዎችን በማጠናቀር ትንተና በማድረግ የሚያጠና በመሆኑ ነው፡፡
፩.፰.፪ የጥናትና ምርምሩ የሕዝብ ስብጥር (Target or study population)

በዚህ የጥናትና ምርምር ሥራ ውስጥ መረጃዎች ከደብረ ገሊላ ዐማኑኤል ካቴድራል ቤተክርስቲያን ውስጥና ዉጪ ካሉ
አካላት የሚሰበሰብ ሲሆን የጥናቱ አጠቃላይ የሕዝብ ስብጥርን ስንመለከት በደብሩ ውስጥና ውጪ የሚገኙ ካህናት አባቶች፣
በሰንበት ትምህርት ቤት አደረጃጀት ውስጥ የሚገኙ ተማሪዎች(አባላት)፣ በሰንበት ትምህርት ቤት አደረጃጀት ውስጥ የሚገኙ
መንፈሳዊ ማህበራት ውስጥ የሚገኙ ምዕመናን እንዲሁም ከላይ ከተጠቀሱት አደረጃጀቶች ውጪ የሆኑ የአጥቢያ ምዕመናንን
ጨምሮ በጥናቱ እንደ አጠቃላይ የሕዝብ ስብጥር የሚታሰቡ ሲሆኑ ቁጥራቸውም_____________ ያህል ነው፡፡

፩.፰.፫ የጥናትና ምርምሩ የናሙና መጠን (Sample size)

ጥናቱ የናሙና መጠንን (Sample size) እና ከአጠቃላይ የሕዝብ ስብጥር ውስጥ ተወካዮችን ለመለየትና ለማስላት
የሚጠቀመዉ በዶ/ር የማነ በ፲፱፻፷ ዓ.ም የፈጠረውን የስታትስቲክስ (ቁጥራዊ) መተግበሪያ መምሪያን ( Statistical
Instrument Formula) ነው፡፡ ምክንያቱም ጥናቱ ከፍተኛ የሆነ የሕዝብ ስብጥር ባለበት ቦታ ላይ ስለሚሰራ ይህንን
የናሙና መጠን አሰላል መንገድን ተግባራዊ በማድረግ ረገድ በአጥኚዎቹ ተመራጭ እና ምክንያታዊ ሆኖ ስለተገኘ ነው፡፡

መምሪያውም (Formula)

n= N n = የናሙና መጠን

1+ N(e)2 N = አጠቃላይ የሕዝብ ስብጥር

e = በጥናቱ ከግምት የገባው የፉረት መጠን

በዚህ መሰረት_________ የሚሆኑ ለናሙና የሚመረጡ አካላትን ከአጠቃላይ የሕዝብ ስብጥር ማለትም_____
ከሚሆኑት ማግኘት ችለናል ስለዚህ በጥናትና ምርምሩ ለናሙና የተመረጡ አካላት ብዛት _____ መሆኑም በአጥኚዎቹ
ዘንድ አግባብነት እንዳለው ተመልክቷል፡፡

፩.፰.፬ የጥናትና ምርምሩ የናሙና አወሳሰድ ስልት (Sampling Technique)

ጥናቱ የሚጠቀመው የናሙና አወሳሰድ ዘዴን ስንመለከት ግምት በማይሰጥ የናሙና አወሳሰድ (non probability
sampling) ከሚባሉት ውስጥ የታለመ ናሙና የሚባለውን (Purposive sampling) ዘዴን የሚጠቀም ነው፡፡
ምክንያቱም ጥናቱ ያቅፋቸዋል ተብለው ከሚገመቱ ሰዎች ወይም ሁኔታዎች መካከል በይበልጥ ለተመረጠው ርዕስ
ይስማማሉ ብሎ የሚገምታቸውን ለይቶ በመውሰድ የሚጠቀምበት የናሙና አመራረጥ ስልት በመሆኑ በአጥኚዎቹ
የተመረጠ ነው፡፡

፩.፰.፭ ጥናቱ የሚጠቀምባቸው የመረጃ ምንጭ አይነቶች ( Source of data)

ጥናቱ በመረጃ ምንጭነት የሚጠቀመው ሁለቱንም የመረጃ ምንጮችን ሲሆን እነርሱም ርቱዕ ምንጭ / Primary source/
ኢርቱዕ ምንጭ /Secondary source/ በመባል የሚታወቁትን ነው፡፡ ርቱዕ የመረጃ ምንጭ / primary source/
ለጥናትና ምርምር ሥራ ተፈላጊ የሆነ ጥሬ መረጃ በጽሁፍ መጠይቅ፣ በቃል መጠይቅ፣ በመስክ ምልከታ ወዘተ… አማካኝነት
በቀጥታ የሚገኝ ነው፡፡ ኢርቱዕ የመረጃ ምንጭ (Socondary Source) ደግሞ አንዳንድ መጽሐፍት፣ መጽሔቶችና
የመሳሰሉት በጽሑፍ መልክ የሚገኙ ዶክመንቶች ከኢርቱዕ የመረጃ ምንጮች የሚመደቡበት ነው፡፡ እነዚህ ምንጮች የብዙ
ምሁራንና የምርምር ባለሙያዎችን ጥናታዊ ሪፖርቶች ፍሬ ነገር በማሰባሰብና በመጭመቅ የተዘጋጁ በመሆናቸው ለጥናትና
ምርምር ሥራ ከፍተኛ እገዛ ያደርጋሉ ብሎ በማመን ነው፡፡

፩.፰.፮ ጥናቱ የሚጠቀምባቸው የመረጃ አሰባሰብ ስልት (Data Collection Method)


መረጃን ለመሰብሰብ ከምንጠቀምባቸው መንገዶች መሐከል ይህ ጥናት ትኩረት አድርጎ ከሚሰራባቸው ውስጥ
የመጀመሪያው የጹሑፍ መጠይቅ (Questionnaire) ሲሆን ይህም ክፍት እና ዝግ ይዘት ያላቸውን ጥያቄዎችን የሚጠቀም
ሲሆን በሁለተኛ ደረጃም ጥናቱ የቃል መጠይቅ (Oral Interview) እንዲሁም ጥናቱ የተመረጠ የቡድን
ዉይይትን(Focus Group Discussion) እንደ መረጃ አሰባሰብ ስልት የሚጠቀመዉ ነው፡፡

፩.፰.፯ የጥናቱ የመረጃ አተናተን ስልት (Data Analysis Method)

በዚህ ጥናት ውስጥ በጥናቱ ተግባራዊ እንቅስቃሴ የሚገኙትን መረጃዎች ገላጭ (ግልጥ) በሆነ መልኩ ለማቅረብ
የሚሞከርበት ከመሆኑ በተጨማሪ መረጃዎችን ለመተንተን የምንጠቀምበት መንገድ የቃላትና የቁጥር ድቅል (Both
Qualitative and Quantitative Method) የሚባለውን ሲሆን እያንዳንዱ የተገኘውን መረጃ ለመተንተን ከተሞከረ
በኋላ የመረጃዎቹ አቀራረብ ቀጥሎ የሚሰራ ወይም የሚተገበር ይሆናል፡፡ በተጨማሪም መረጃዎችንም ለማቅረብ
የሚሞከረው የተለያዩ የመረጃ አቀራረብ ዘዴዎችን በመጠቀም ሲሆን ይህም ሰንጠረዦችን፣ አማካይ
ውጤቶችን(Percentages) እንዲሁም የተለያዩ የግራፍ አይነቶችን በመጠቀም ይሆናል፡፡ እንዲሁም ጥናቱ ከተነሱት
ችግሮች ጋር ያለዉን ተያያዥነት ሊያሳይ በሚችል መልኩ እና የተተነተነው መረጃም ቀላል በሚባል መልኩ ወይም ለመረዳት
በማያስቸግር ሁኔታ የጥናቱ መደምደሚያ ሃሳብ ሊሆን በሚችል መልኩ የንስሐ ሥርዓት አፈጻጸም ላይ ተግዳሮት የሆኑትን
ሐሳቦች በማሳየት ላይ የተመሰረተ ነው፡፡

፩.፱ የጥናትና ምርምሩ የወረቀት መዋቅር (Organization of the study)


ይህ ጥናትና የምርምር ተግባር የሚከናወነው በአምስት ምዕራፎች ሲሆን የመጀመሪያው ምዕራፍ በውስጡ የያዛቸው ርዕሰ
ጉዳዮች የጥናትና ምርምሩ ዳራ፣ የችግሩ ምንነት፣ የጥናቱ ቁልፍ ጥያቄዎች፣ የጥናቱ ዓላማ፣ የጥናቱ ጠቀሜታ፣ የጥናቱ ወሰን፣
የጥናቱ ታሳቢ ክፍተቶች እንዲሁም የርዕሰ ጉዳዩ የቃላት ትርጉም ናቸው፡፡

በምዕራፍ ሁለት ደግሞ የተዛምዶ ጹሑፍ ዳሰሳ የሚካሄድበት ሲሆን ይህም ከርዕሰ ጉዳዩ ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት ያላቸው
ናቸው፡፡

በምዕራፍ ሦስትም የጥናትና ምርምሩ ሥነ - ዘዴ እና አካሄድ የሚገለጽበት ሲሆን በዉስጡም የጥናቱ ግልጻዊ የቦታ ሽፋን፣
የጥናቱ ንድፈ ሃሳብ (Research Design)፣ የጥናቱ አጠቃላይ የሕዝብ ስብጥር፣ የጥናቱ የናሙና መጠን፣ የጥናቱ የናሙና
አወሳሰድ ስልት፣ ጥናቱ የሚጠቀምባቸው የመረጃ አይነቶች፣ ጥናቱ የሚጠቀመዉ የመረጃ አሰባሰብ ዘዴ እና የጥናቱ የመረጃ
አተናተን ዘዴ የሚካተቱበት ሲሆን

በምዕራፍ አራትም የመረጃ አተናተን እና አቀራረብ ዘዴ የሚቀርብበት ሲሆን በውስጡም ለናሙና የተመረጡ አካላት ግላዊ
መረጃ እንዲሁም በጥናቱ የተገኙ ዐበይት ውጤቶች የሚቀርቡበት ነው፡፡

በመጨረሻም የማጠቃለያ፣ የመደምደሚያ እና የመፍትሔ ሐሳቦችን በምዕራፍ አምስት የሚቀርቡበት ይሆናል፡፡

You might also like