Download as docx, pdf, or txt
Download as docx, pdf, or txt
You are on page 1of 4

ሪል እስቴት አብሮ የማልማት ስምምነት ውል

ውል ሰጭዎች - xxxxxx
አድራሻ -አዲስ አበባ፤ xxxxxx ክ/ከ፤ ወረዳ xxxxxx ፤የቤ.ቁ.
xxxxxx (ከዚህ በኋላ ውል ሰጭ እየተባሉ የሚጠሩ ይሆናል)

ውል ተቀባይ… xxxxxxxxxx አድራሻ፡ xxxxxxxx ክ/ከ xxxxxxx የቤ.ቁ.xxxxx


(ከዚህ በኋላ ውል ተቀባይ እየተባሉ የሚጠሩ ይሆናል)
መካከል ሪል እስቴት አብሮ የማልማት ስምምነት ውል ዛሬ xxxxxx ፥ 2016 ዓ.ም. ተደርጓል።

አንቀጽ አንድ
የውሉ አላማ

1.1. ውል ሰጭ በአዲስ አበባ ከተማ፤ xxxxxx ክ/ከ፤ ወረዳ xxxxxx ፤ በይዞታ የምስክር ወረቀት ቁጥር xxxxxx ፥ ሴሪ.
ቁጥር xxxxxxx፥ በይዞታ ልዩ መለያ ቁጥር xxxxxx መሰረት በጠቅላላው xxxxxx ካሬ ሜትር መሬት በስሙ ተመዝግቦ
በይዞታው ስር የሚገኝ በመሆኑና ይህንንምይዞታ ውል ሰጭ ለውል ተቀባይ ለማስተላለፍ በመስማማቱ።

1.2. በጋራ በሚለማው በዚሁ የሪል እስቴት ልማት ውስጥም ውል ሰጭ ሪል እስቴቱን ለማልማት እንዲቻል አስፈላጊ
መሬት አሟልቶ ለልማት ዝግጁ የሚያደርግ በመሆኑ።

1.3. ውል ተቀባይ በበኩሉ ለዚህ አስፈላጊ የሪል እስቴት ፈቃድ፣ የሰው ኃይል፣ የኩባንያ አስተዳደርና ማኔጅመንት
እንዲሁም አስፈላጊ የፋይናንስ አቅምና ሌሎች ለግንባታው የሚያስፈልጉ ማናቸውም አቅሞች ያለው በመሆኑ።

1.4. ውል ተቀባይ በዚህ ውል ዝርዝር ድንጋጌዎች መሰረት የዲዛይንና የግንባታውን ስራ ሙሉ ወጪ ለመሸፈን የተስማማ
በመሆኑ።

1.5. በዚህ ውል ዝርዝር ስምምነት መሰረትም በጋራ ከሚለማው የሪል እስቴት ህንጻ [xxxxxx B+G+ xxxxxx] ውስጥ
ከመኪና ማቆሚያ ውጭ ካሉት xxxxxx ወለሎች ውስጥ፥ ለውል ሰጭ xxxxxx ወለል [xxxxxx ኛ]፥ ቀሪዎቹን xxxxxx
ወለሎችን ደግሞለውልተቀባይሊከፋፈሉ በመስማማታቸው።እያንዳንዱ
ወለልየጋራኮሪደር፥ደረጃ፥ሊፍትናተያያዥመጠቀሚያዎችን ጨምሮ በአማካኝ xxxxxx ካሬ ሜትር ይሆናል።

አንቀጽ ሁለት
የሪል ስቴት ልማቱ ዓይነት

2.1. የሪል እስቴት ልማቱ በሚሰራው ዲዛይን መጠን ልክ የሚጠናቀቅ ባለ xxxxxx ወለል (xxxxxx ቤዝመንት፣ 1 ምድር
እና xxxxxx ፎቆች) ሁለገብ አገልግሎት ያለው ህንጻ ነው። ይህ ህንጻ ተገንብቶ ሲያልቅ ለኪራይ፣ ለሽያጭ፣ ለመኖሪያ
ወይም ለሌላ ሕጋዊ አገልግሎት የሚል ይሆናል።

አንቀጽ ሶስት
ዝርዝር
ስምምነቶች

3.1. ውል ሰጭ መሬቱን/ካርታውን/ለውልተቀባይ በሽያጭ እስኪያስተላልፍ ድረስ ከዚህ ውል ጋር በተያያዘበኢትዮጵያ


የንግድ ሕግ፥የፍትሐብሔርህግናሌሎችከሽያጭጋርየተያያዙህጎችላይየተቀመጡት መብትና ጥቅሙ እንደተጠበቁ
ይቆያሉ።

3.2. ውል ተቀባይ የሪል እስቴቱን የግንባታ ዲዛይን በራሱ ወጪ አማካሪበመቅጠርአዘጋጅቶና በሚመለከተው መንግስታዊ
አካል ያጸድቃል፤ በተጨማሪም የግንባታ ፈቃድና የግንባታ ማስጀመሪያ ፈቃድም በራሱ ወጪ ከሚመለከተው አካል
ፈቃድ ያወጣል። በውል ሰጭ የመስሪያ ቦታውን ከነሙሉ ጥቅሙና ግዴታው ለውል ተቀባይ ያዛውራል። በምትኩም ውል
ተቀባይ ግምባታውን ሲያጠናቅቅ xxxxxx ወለል የሚሆነውን ቤት ወይም ክፍል ለውል ሰጭ በአንቀጽ 1.5 የተዘረዘሩትን
ወለሎች ለመስጠት ተስማምቷል።

3.3. ውል ሰጭ ከሚገነባው የሪል እስቴት ሕንጻ ውስጥ በአንቀጽ 1.5 በተዘረዘሩት መሰረት የ xxxxxx ወለል ባለሃብት
ይሆናል። በዚሁም መሰረት ውል ሰጭ ያለውን የመስሪያ ቦታ በተገመተበት ማለትም በ xxxxxx (xxxxxx) ብር ዋጋ
ለውል ተቀባይ በሽያጭ ለማስተላለፍ ተስማምተዋል፤ ውል ተቀባይም የሪል እስቴት ልማቱን የሚመለከቱ ግዴታዎችን
በሙሉ በራሱ ወጭ አሟልቶ ወደ ስራ ለመግባት ተስማምተዋል፤ ውል ተቀባይ መሬቱ ከተላለፈለት በኋላ የንግድ
ስያሜንም ሆነ አርማውን የመቀየር መብት አላው፤ የትኛውም ለውጥ ግን ውል ሰጭ በዚህ ውል ያለውን ማንኛውንም
መብት የሚያስጠብቅ እንጂ የሚያስቀር መሆን አይኖርበትም።

3.4.ውልተቀባይበፍትሐብሔርሕግአንቀጽ 1793 ስርየተዘረዘሩትከአቅምበላይየሆኑሁኔታዎችካላጋጠሙበስተቀርሌሎች


ማናቸውም ዓይነት ሁኔታዎች ከግምት ውስጥ ሳይገቡ በዚህ ውል መሰረት የቤት ሽያጭ ውል ከሚፈራረሙበትና
የግንባታ ስራው ከሚጀምርበት ቀን ጀምሮ የውል ሰጭን ድርሻ በ xxxxxx ወራቶች ውስጥ በከፍተኛ ጥራትና
(በሚዘጋጀው Bill of Quantities and Specifications መሰረት) በብርቱ ጥንቃቄ ሙሉ በሙሉ በአንቀጽ 3.2
በተጠቀሰው የስራ ዝርዝር መሰረት ስራውን አጠናቆ የውል ሰጭን ድርሻ በአንቀጽ 1.5 የተዘረዘሩትን ወለሎች
በሸጡላቸው ቦታ ዋጋ ልክ ለማስረከብ ተስማምቷል፤ ይህ ግዴታም ከውል ሰጭ ጋር በሚደረገው የቤት ሽያጭ ውል
ውስጥ እንዲካተት ይደረጋል።

አንቀጽ አራት
ዋስትናን
በተመለከተ

4.1. ውል ተቀባይ የአርክቴክቸራል ዲዛይኑእናዳለቀ በአንቀጽ 3.4 መሰረት የገባውን ግዴታ እንደሚፈጽም ለውል ሰጭ
ዋስትና እንዲሆነው ውል ተቀባይ ለእያንዳንዱ ቤት የሽያጭ ውል ይፈርማል፥ የገንዘብ ዋስትና ውልና ቼክ ይሰጣል።
ተዋዋይ ወገኖች በጋራ በመሆን የቦታውን ካርታና ሌሎችማናቸውንም የውል ሰጭ ሰነዶችን ሕጋዊነት ለማረጋገጥ
ከሚመለከታቸው የመንግስት ተቛማትና አካላት ያረጋግጣሉ።

4.2. ውል ሰጭ ለሚደርሰውእያንዳንዱቤትየገንዘብዋስትናውል እንደተፈራረመ የይዞታ ካርታውን ወደ ውል ተቀባይ


ለማዛዎር ተስማምቷል።

4.3. ውል ተቀባይ በዚህ ውል መሰረት ከውል ሰጭዎች የሚረከበውን ይዞታ በባንክ በማስያዝ የሚበደረው ገንዘብ ካለ
ማንኛውም ብድር ለዚህ ሪል እስቴት ማልሚያ ግንባታ ብቻ እንዲውል ግዴታ ገብቷል።

4.4. ውል ተቀባይ ከዚህ ውል ቀደም ብሎ በገባው ማንኛውም ግዴታ መሰረት የሚመነጭ የባንክም ሆነ የኢንሹራንስ
ዋስትና ይህንን ከውል ሰጭ የሚተላለፍለትን ይዞታ የማይመለከት መሆኑን በዚህ ውል ግዴታ ገብቷል።

አንቀጽ አምስት
የተዋዋዮች መብትና
ግዴታ

5.1. በዚህ ውል መሰረት ውል ተቀባይ ግዴታውን ተወጥቶ ለውል ሰጭ ባስተላለፉት የመሬት ዋጋ ልክ የቤት ሽያጭ ውል
በመፈራረም እና የወለል ፕላንም /Floor Plan/ ለእያንዳንዳቸው ቤቶች ካስረከቡ በኋላ በውል ተቀባይና በውል ሰጭ
መካከል ያለው ግንኙነት የሪል እስቴት ቤት ሻጭና ገዥ ግንኙነት ይሆናል። ውል ሰጭ በዚህ ውል መሰረት ያሉትን የቤት
ድርሻዎች በከፊልም ሆነ በሙሉ ለውል ተቀባይ በጽሁፍ ሲያሳውቅና የጋራ ስምምነት ሲኖር ለሶስተኛ ወገን የሪል እስቴት
ህግና ደምብ መሰረት ማስተላለፍ ወይም መተካት ይችላል።

5.2. የውል ሰጭ ለሚደርሰው የመኖሪያ ቤቶች ድርሻ ለመኪና ማቆሚያ (ፓርኪንግ) እንዲሆናቸው ለእያንዳንዱ የመኖሪያ
ቤት የአንድ መኪና ማቆሚያ ቦታ ይሰጣቸዋል።

5.3. ውል ተቀባይ ከቦታ ዝውውሩ ጋር በተያያዘ ከውል ሰጭም ሆነ ከውል ተቀባይ ከተለያዩ የመንግስት ተቛማትና አካላት
የሚጠበቅ ማናቸውንም ዓይነት ወጪ በየራሳቸው ለመሸፈን ተስማምተዋል። እንዲሁም ውል ተቀባይ ለውል ሰጭ የቤት
ድርሻ የቤት ሽያጭ ውልን ተከትሎ የሚመጡ ማናቸውንም ወጭዎች እንዲሁም ውል ተቀባይና ውል ሰጭ
የሚጠበቅባቸውን ወጭ በየራሳቸው ለመሸፈን ተስማምተዋል። ሆኖም፥ ውል ሰጭ ለውል ተቀባይ የሚያሰተላልፈው
ቦታ ምንም አይነት ዕዳ እንዲሁም ያልተከፈለ የሊዝና ተያያዥ ክፍያ ካለ ሙሉ በሙሉ የመክፈል ግዴታው የውል ሰጭ
ይሆናል።

Page 2 of 4

5.4. ውል ሰጭ በውል ተቀባይ በሚቀርበው የሕንጻው ዲዛይን ላይ የኮንስትራክሽን ስራ ከመጀመሩ በፊት የራሱን ሀሳብ
ወይም አስተያየት የመስጠት መብት አለው።
5.5. የውል ሰጭ ባላው የመሬት ይዞታ፣ የይዞታ ማረጋገጫ ካርታና የተያያዙ ሰነዶች ጋር በተያያዘ እንዲሁም የውል ሰጪ
ንብረትን በተመለከተ ወይም ማናቸውም የሕጋዊነት ጥያቄቢነሳ ወይም ይገባኛል የሚል ጥያቄ ከሶስተኛ ወገን ቢነሳ
ኃላፊነቱን ይወስዳል።

5.6. ይህ ውል ከመፈጸሙ በፊት በነባር ይዞታው ላይ ለሚመጣ ማናቸውም የወንጀልም ሆነ የፍታብሔር ተጠያቂነት ውል
ሰጭ ኃላፊነቱን ይወስዳል።

5.7. በዚህውል መሰረትየግንባታው ስራ ሲካሄድ በሀገራችን የሚሰራባቸውየኮንስትራክሽንናየሪል እስቴትህጎች፥


መመሪያዎች እና ደምቦች ተፈጻሚ ይሆናሉ።

5.8. በዚህ ውል መሰረት ውል ሰጭዎች በሚኖራቸው የቤት ድርሻ ላይ መብታቸውንና ግዴታቸውን በጋራም ሆነ በተናጠል
መተግበር ይችላል።

5..9 ውል ሰጭ የውል ተቀባይን መብቶች፤ ውል ተቀባይም የውል ሰጭን መብቶች የማክበር ግዴታ አለባቸው።

5.10.ተዋዋይ ወገኖች ይህን ውል እንደተፈራረሙ፥ ውል ተቀባይ ለውል ሰጭዎች ዋስትና ይሆናቸው ዘንድ የገንዘብ
ዋስትና ውል ከተፈራረመና የዋስትና ቼክ እንደሰጠ ውል ሰጭ ወዲያውኑ የመሬት ይዞታ ካርታውን በፌደራል የሰነዶች
ማረጋገጫና ምዝገባ በመቅረብበሸያጭለውልተቀባይያስተላልፋል።

አንቀጽ ስድስት
ውሉ ጸንቶ የሚቆይበት
ጊዜ

6.1. በዚህ ውል ጠቅላላ ድንጋጌ በተመለከተው አግባብ የዚህ ውል ዓላማ በሙሉም ሆነ በከፊል ከመጠናቀቁ በፊት
በማናቸውም ጊዜ ሁለቱም ተዋናይ ወገኖች ውሉን ለማቋረጥ ከተስማሙና ስምምነታቸውንም በጽሁፍ ካረጋገጡ ውሉ
ይቋረጣል።

6.2. ተዋዋይ ወገኖች ከዚህ ውል በተጨማሪ ሌሎች ውሎችን በማናቸውም ጊዜ ሊዋዋሉ ይችላሉ፤ ውሎቹም የዚህ
ውልአካል ይሆናሉ።

አንቀጽ ሰባት
ስለ ቅጣት

7.1. ይህንን ውል ያፈረሰ የትኛውም ተዋዋይ ወገን xxxxxx ብር መቀጮ ለሌላኛው ተዋዋይ ወገን ከፍሎ ውሉ የጸና
ይሆናል።

Page 3 of 4
አንቀጽ ስምንት
አለመግባባት ስለሚፈታበት
ሁኔታ

8.1. ተዋዋይ ወገኖች በመካከላቸው ሊፈጠር የሚችልን አለመግባባት በቅድሚያ በመመካከር የመፍታት ግዴታ አለባቸው።

8.2. ተዋዋይ ወገኖች አለመግባባትን በመመካከር ሊፈቱ ካልቻሉ እያንዳንዳቸው በሚመርጡት አንድ አንድ የግልግል ዳኛና
ሁለቱ የግልግል ዳኞች በጋራ በሚመርጡት ሶስተኛ ገላጋይ ዳኛ ውሳኔ ይሰጣል፡፡ በሁለቱ ገላጋይ ዳኞች
የተመረጠውገለልተኛ ገላጋይ ዳኛ ሰብሳቢ ገላጋይ ዳኛ ይሆናል።

8.3. ከተዋዋይ ወገኖች አንዱ የግልግል ዳኛ ለመምረጥ ፈቃደኛ ካልሆነ ወይም ሁለቱ ዳኞች በ 15 ቀን ውስጥ ሶስተኛ
ገለልተኛ ገላጋይ ዳኛ ካልመረጡ ፍ/ቤት እንዲመርጥ ይደረጋል።
8.4. ገላጋይ ዳኞች በሚሰጡት ውሳኔ ካልተስማሙ በመደበኛ ፍርድ ቤት ጉዳያቸውን በማቅረብ መብታቸውን ማስከበር
ይችላሉ።

8.5. ሆኖም የፍትሐብሔር ስነ ስርዓት ሕጉ በሚፈቅደው መሰረት በገላጋይ ዳኞች ውሳኔ ላይ ቅር የተሰኘ ተዋዋይ ወገን
ስልጣን ላለው መደበኛው ፍ/ቤት ይግባኝ ማለት ይቻላል።

8.6. ለገላጋይ ዳኞች የሚወጣ ማንኛውንም ወጭ ጉዳዩ በግልግል ዳኝነት ሲጠናቀቅ በዳኝነቱ የተፈረደበት ወገን
እንዲከፍል ተስማምተዋል።

ይህ ውል ዛሬ xxxxxx ፥ 2016 ዓ.ም. በአዲስ አበባ ከተማ ተደረገ።

ተዋዋዮች
ስለ ውል ሰጭ ስለ ውል ተቀባይ

ምስክሮች
እኛ ስማችን ከዚህ በታች የተጠቀሰው ምስክሮች ተዋዋይ ወገኖቹ በዚህ የውል ሰነድ በተጻፈው የውል ቃል መሰረት
ተስማምተው ውሉን ሲፈርሙ ያየንና የሰማን መሆናችንን በፊርማችን እናረጋግጣለን።

ስም አድራሻ ፊርማ

1. ___________________ ______________________________
______________________ ___________
________ ______________________________
___________________
2. ___________ ______________________________
______________________
________ ___________________
___________
3.
______________________
________

Page 4 of 4

You might also like