Wel Kaza 2 - T

You might also like

Download as pdf or txt
Download as pdf or txt
You are on page 1of 8

ሪል እስቴት አብሮ የማልማት ስምምነት ውል

ውል ስጪ፤ አድራሻ፤ አዲስአበባ፤ ክ/ከ ፤ ወረዳ ፤ የቤ/ቁ ፤ (ከዚህ በኋላ ውል ሰጭ እየተባሉ የሚጠራ)

ውል ተቀባይ፤ ፤፤ አድራሻ፤ አዲስአበባ ክ/ከ፤ ፤ ወረዳ የቤ/ቁ፣ .

ከዚህ በኋላ ውል ተቀባይ እየተባለ የሚጠራ) መካከል ሪል እስቴት አብሮ የማልማት ስምምነት ውል ዛሬ ሚያዚያ ፤

2016 ዓ.ም. ተደርጓል።

አንቀጽ አንድ
የውሉ አላማ

1.1. ውል ሰጭ በአዲስ አበባ ከተማ፤ ክ/ከ፤ ወረዳ ፤ በይዞታ የምስክር ወረቅት ቁጥር ፤ ሴሪ ቁጥር
እንዲሁም የምዝገባ ቁጥር መሰረት በጠቅላላው ( ) ካሬ ሜትር መሬት
በስማቸው ተመዝግቦ የሚገኝ ይዞታ ላይ ውል ሰጪና ውል ተቀባይ በጋራ ሪል እስቴት ለማልማት የተስማሙ ሲሆን ውል
ተቀባይም ሙሉ በሙሉ የግንባታውን ወጪ ሙሉ ገንዘብ በመሸፈን በዚህ ይዞታ ላይ ከመሬት በላይ ወለል፤
የመሬት ወለል እና ቤዝመንት ያለው አፓርታማ እንዲገነባና በዚህ ውል በተመለከቱት ሁኔታዎች
የሚገነቡትን አፓርትመንት ቤቶችን ለመከፋፈል በማሰብ የተደረገ ውል ነው፡፡

1.2. በጋራ በሚለማው በዚህ የሪል እስቴት ልማት ውስጥም ውል ሰጭ ሪል እስቴቱን ለማልማት እንዲቻል አስፈላጊ
መሬትና ቅድመ ሁኔታዎችን አሟልቶ ለልማት ዝግጁ የሚያደርግ በመሆኑ፤

1.3. ውል ተቀባይ በበኩሉ ለዚህ በጋራ ለሚለማው የሪል እስቴት ቤቶች አስፈላጊ የሪል እስቴት ፈቃድ፤ የሰው ኃይል፤
የኩባንያ አስተአደርና ማኔጅመንት እንዲሁም አስፈላጊ የፋይናንስ አቅምና ለሎች ለግንባታው የሚያስፈልጉ ማናቸውም
አቅሞች ያለው በመሆኑ፤

1.4. ውል ተቀባይ በዚህ ውል ዝርዝር ድንጋጌዎች መሰረት የዲዛይንና የግንባታውን ስራ ሙሉ ወጪ ለመሸፈን የተስማማ
በመሆኑ፤

አንቀጽ ሁለት
የሪልስቴት ልማቱ ዓይነት

2.1. የሪል እስቴቱ ህንጻ ግንባታ ጠቅላላ ወለል ስፋት እንደ ፕላን ስመምነቱ እና እንደሚፀድቀው ግንባታ ፈቃድ ካሬ
ሜትር ገደማ ላይ የሚያርፍ ይሆናል፡፡

2.2. የሪል እስቴት ልማቱ በሚሰራው ዲዛይን መጠን ልክ ባለ ወለል ( ቤዝመንት፤ ምድር እና ፎቆች)
ሁለገብ አገልግሎት ያለው ህንፃ ነው። ይህ ህንፃ ተገንብቶ ሲያልቅ ለኪራይ፤ ለሽያጭ፤ ለመኖሪያ ወይም ለሌላ ህጋዊ
አገልግሎት የሚውል ይሆናል።

2.3. በዚህ ውል ዝርዝር ስምምነት መሰረትም በጋራ ከሚለማው የሪል እስቴት ህንጻ ውስጥ ፣ ለመኪና ማቆሚያ
የሚውል ሲሆን ከቀሩት ወለሎች ውስጥ፤
2.3.1. ለውል ሰጪ ከምድር ወለል በላይ የ ኛ እና ወለሎች ባለቤት ይሆናሉ። ለውል ሰጪ በይዞታቸው ላይ
ከተገነባው ግንባታ ጠቅላላ ስፋት ውስጥ የጋራ መጠቀሚያዎችንና የተከፋፈሉበትንም ግድግዳ ጨምሮ 20 % የሆነ
ጠቅላላ ስፋት ባለቤት የሆናሉ፡፡ ይህም 20% ቤት የሚገኘው ከምድር ወለል በላይ በ 3 ተኛ እና በ 4 ተኛ
ወለሎች ላይ ይሆናል፡፡

2.3.2. ለውል ሰጪ ብቻ አገልግሎት የሚሆን በፓርኪንግ ወለል ላይ የሚጠቃለል ስፋቱ ካሬ ሜትር የሆነ የመኪና
ማቆሚያ የሚሆን ስፍራ ገንብቶ ለመስጠት ተስማምተዋል፡፡

2.3.3. ለውል ሰጪ የሚሰጡት ወለሎች ላይ በከፊል የተጠናቀቁ (Semi Finished) አፓርትመንቶች የሚሆን ሲሆን ለዚህም
ግንባታ የሚያስፈልገውን ወጪ ሙሉ በሙሉ በውል ተቀባይ የሚሸፈን ይሆናል።

2.3.4. ውል ተቀባይም ቀሪዎቹን ወለሎች ድርሻውን ሊወስድ ውል ሰጪ እናውል ተቀባይ ተስማምተዋል።

2.4. በአንቀጽ 2.3 ስር በተዘረዘሩት ንኡስ አንቀፆች ላይ በተገለጸው መሰረት የውል ሰጪ ደርሻ በሚፀድቀው ዲዛይን
መሰረት ይሆናል።

2.5. በዲዛይኑ እና ግንባታ ውስጥ የሚካተቱ ፡ የጄኔሬተር ክፍል፤ የኤሌክትሪክእና የሳኒተሪ ደክት፤ የጥበቃ ክፍል፤ የውሃ
ማጠራቀሚያ (Reservoirs system)፤ ዘምናዊ አሳንሰር/ሮች ፤ የእሳት ጊዜ መውጫ እና የቆሻሻ ማስወግጃ (Garbage
Chute) ይኖረዋል።

አንቀጽ ሶስት

ዝርዝር ስምምነቶች

3.1. ውል ሰጭ መሬቱን/ካርታውን/ ለውል ተቀባይ በጋራ የማልማት ስራ እንዲውል ያለምንም የገንዘብ ክፍያ
የሚያዛውርላቸው ሲሆን፣ ውል ተቀባይም የቦታውን ክፍያ በአይነት ሚሰጣቸው ማለትም በአንቀጽ 2.3 ስር በተዘረዘሩት
ንኡስ አንቀፆች ላይ በተጠቀሰው የውል ሰጪ ድርሻ አፓርትመንቶች አልምቶ የይዞታ ባለቤትነት እስኪያስተላልፍ ድረስ
ከዚህ ውል ጋር በተያያዘ በኢትዮጵያ የንግድ ህግ፣ የፍትሃ ብሄር ህግና ሌሎች ህጎች ላይ የተቀመጡት መብትና ጥቅሙ
እንደተጠበቀ ሆኖ ውል ስጪ የመስሪያ ቦታውን ከነ ሙሉ ጥቅሙና ግዴታው ጋር ለውል ተቀባይ ያዛውራል።

3.2. ውል ተቀባይ የግንባታውን ዲዛይን በራሱ ወጪ አማካሪ በመቅጠር አዘጋጅቶ በሚመለከተው መንግስታዊ አካል
ያጸድቃል፣ በተጨማሪም የግንባታ ፈቃድና የግንባታ ማስጀመሪያ ፈቃድም በራሱ ወጪ ከሚመለከተው አካል ፈቃድ
ያወጣል። ውል ሰጪ የመስሪያ ቦታውን ከነሙሉ ጥቅሙና ግዴታው ለውል ተቀባይ ያዛውራል። በምትኩም ውል ተቀባይ
ግንባታውን ሲያጠናቅቅ 2 ወለሎችን ለውል ሰጪ በአንቀጽ 2.3 ስር በተዘረዘሩት ንኡስ አንቀፆች ላይ በተዘረዘሩት መሰረት
ለመስጠት ተስማምቷል።

3.3. ውል ሰጭ ከሚገነባው የሪል እስቴት ህንጻ ውስጥ በአንቀጽ 2.3 ስር በተዘረዘሩት ንኡስ አንቀፆች ላይ በተዘረዘሩት
መሰረት የ ወለል ባለሃብት ይሆናል። በዚህም መሰረት ውል ሰጪ ያለውን የመስሪያ ቦታ በተገመተበት ማለትም በ
( ብር) ብር ዋጋ ለውል ተቀባይ በጋራ የማልማት ስራ እንዲውል በአይነት ለማስተላለፍ ተስማምተዋል።
እንዲሁም የስም ዝውውር ለማከናወን እንዲረዳ በውልና ማስረጃ የሽያጭ ውል ስምምነት ለውል ሰጪ ምንም አይነት
የገንዝብ ክፍያ ሳይፈጸም ለማከናወን ተስማምተዋል፤ ውል ተቀባይም የሪል እስቴት ልማቱን የሚመለከቱ ግዴታዎችን
በሙሉ በራሱ ወጪ አሟልቶ ወደ ስራ ለመግባት ተስማምተዋል፣ ውል ተቀባይም መሬቱ ከተላለፈለት በኋላ የንግድ
ስያሜንም ሆነ አርማውን የመቀየር መብት አለው፤ የትኛውም ለውጥ ግን ውል ሰጪ በዚህ ውል ያለውን ማንኛውንም
መብት የሚያስጠብቅ እንጂ የሚያስቀር መሆን አይኖርበትም።

3.4. ውል ተቀባይ በፍትሃ ብሄር ህግ አንቀጽ 1793 ስር የተዘረዘሩት ከአቅም በላይ የሆኑ ሁኔታዎች ካላጋጠሙ በስተቀር
ሌሎች ማናቸውም ዓይነት ሁኔታዎች ከግምት ውስጥ ሳይገቡ በዚህ ውል መሰረት የቤት ሽያጭ ውል ከሚፈራረሙበትና
የኮንስትራክሽን ስራው ከሚጀመርበት ቀን ጀመሮ የውል ሰጭን ድርሻ በ 36 ወራቶች ውስጥ በጥራትና በብርቱ ጥንቃቄ
በከፊል የተጠናቀቁ ቤቶችን ለማስረከብ ተስማምተዋል፡፡

አንቀጽ አራት
ዋስትናን በተመለከተ

4.1. ውል ተቀባይ የአርክቴክቸራል ዲዛይኑ እንዳለቀ በአንቀጽ 3.2 መሰረት የገባውን ግዴታ እንደሚፈጽም ለውል ሰጭ
ዋስትና እንዲሆነው ውል ተቀባይ ለእያንዳንዱ ቤት የመያዣ ዋስትና ውል ይፈርማል። ተዋዋይ ወገኖች በጋራ በመሆን
የቦታውን ካርታና ሌሎች ማናቸውንም የውል ሰነዶችን ህጋዊነት ለማረጋገጥ ከሚመለከታቸው የመንግስት ተቋማትና
አካላት ያረጋግጣሉ።

4.2. ውል ተቀባይ በተዋዋይ ወገኖች የጋራ የዋጋ ጥናት እና ስምምነት መሠረት የሚወሥኑትን የይዞታው የገበያ ዋጋ
የሚሸፍን ዋስትና የኢንሹራንስ ከለላ ቦንድ ለውል ሰጪ ተስማሚዎች ዋስትና ይሆንላቸው ዘንድ ይሠጣል፡፡

4.3 ውል ሰጪ በሰነዶች ማረጋገጫ ኦጀንሲ ቀርቦ የሽያጭ ውል ከመዋዋሉ በፊት ከላይ ለተጠቀሱት 2 ወለሎች
ተገንብተው እንደሚረከብ ዋስትና ይሆነው ዘንድ በ ኢንሹራንስ በውል ተቀባይ እና በውል ሰጪ መካከል
የሶስትዮሽውል በመዋዋል የገንባታ ሳይቱን ማለትም ይዞታውን በመያዣነት በማስያዝ የኢንሹራንስ ከለላ ዋስትና
ይይዛል፡፡ ኢንሹራንሱም ዋስትናውን ይዞ ከለላውን ከሰጠ በኋላ መያዣነቱ እንደተጠበቀ ሆኖ የስም ዝውውር ወደ
አልሚው ቢደረግ የማይቃወም መሆኑን የሚገልፅደብዳቤ ለውል ተቀባይ ይሰጣል፡፡ እናም የኢንሹራንስ ከለላው
ግንባታው እስከሚጠናቀቅ ጊዜ የፀና ይሆናል፡፡

4.4. ውል ተቀባይ በዚህ ውል መሰረት ከውል ሰጭ በሚረከበው ይዞታ ላይ ለሚገነባቸው ቤቶች የውል ሰጪ ድርሻን
ሳያካትት በባንክ በማስያዝ መበደር ይችላል። የሚበደረውንም ገንዘብ ወይም ማንኛውም ብድር በዚህ ስምምነት
ለተጠቀሰው አፓርታማ ግንባታ ማልሚያ ብቻ እንዲውል ግዴታ ገብቷል። ሆኖም ውል ተቀባይ በዚህ ውል መሰረት የውል
ስጭ ድርሻ በአንቀጽ 2.3 ስር በተዘረዘሩት ንኡስ አንቀፆች ላይ የተዘረዘሩትን ቤቶች በምንም መልኩ በዋስትናነት ማስያዝ
አይችልም።

4.5. ውል ተቀባይ በአንቅጽ 4.4 መሰረት ብድር መበደር በሚፈልግበት ወቅት፤ ለውል ሰጪ በቅድሚያ ማሳወቅ
ይኖርበታል።

4.6. ውል ተቀባይ ከዚህ ውል ቀደም ብሎ በገባው ማንኛውም ግዴታ መሰረት የሚመነጭ የባንክም ሆነ የኢንሹራንስ
ዋስትና ይህንን ከውል ሰጭ የሚተላለፍለትን ይዞታ የማይመለከት መሆኑን በዚህ ውል ግዴታ ገብቷል።

፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡
አንቀጽ አምስት
የተዋዋዮች መብትና ግዴታ

5.1. በዚህ ውል ስምምነት መሰረት ውል ተቀባይ ግዴታውን ተወጥቶ ለውል ሰጭ ባስተላለፉት የመሬት ዋጋ መሰረት እና
በዚህ ውል ስምምነት መሰረት የእያንዳንዱ የቤት ዋስትና ውል በመፈራረም የወለል ፕላንም (Floor Plan)
ለእያንዳንዳቸው ቤቶች ለውል ሰጪ ያስረክባሉ፡፡ ካስረከቡ በኋላ በውል ተቀባይና በውል ሰጭ መካከል ያለው ግንኙነት
የሪል እስቴት ቤት ሻጭና ገዥ ግንኙነት ይሆናል።

5.2. ውል ሰጪ ለውል ተቀባይ የሚያስተላልፈው ቦታ ምንም አይነት ዕዳ እንዲሁም ያልተከፈል የሊዝና ተያያዥ ክፍያ ካለ
ሙሉ በሙሉ የመክፈል ግዴታው የውል ሰጭ ይሆናል። ነገር ግን ስም በሚዞርበት ወቅት ከነባር ይዞታ ወደ ሊዝ መደብ
ሲዞር የሊዝ ክፍያው በውል ተቀባይ የሚሸፈን ይሆናል።

5.3. ውል ሰጭ በውል ተቀባይ በሚቀርበው የህንጻው ዲዛይን ላይ የኮንስትራክሽን ስራ ከመጀመሩ በፊት የራሱን ሃሳብ
ወይም አስተያየት የመስጠት መብት አለው። ሆኖም በውል ተቀባይ ተቀባይነትን ሲያገኝ ብቻ ይተገበራል፡፡

5.4. ይህ ውል ከተፈረመበት ቀን ጀምሮ በሚታሰብ ውል ተቀባይ በተወሰኑ ወራቶች ውስጥ አስፈላጊውን የግንባታ
ዝግጅቶች፤ ማለትም የህንጻ ዲዛይን፣ ፈቃድ እንዲሁም አስፈላጊ የቴክኒክ ዝግጅቶችን ያከናውናል፤ በተጨማሪም የግንባታ
ፈቃድና የግንባታ ማስጀመሪያ ደብዳቤ ከሚመለከተው የመንግስት አካል ከተሰጠው በኋላ በ ስድስት ወራት ውስጥ
ግንባታ የሚጀምር ይሆናል።

5.5. ውል ተቀባይ በዚህ ውል በገቡት ግዴታ መሰረት ከአቅም በላይ የሆኑ ነገሮች ካላጋጠሙት በስተቀር የውል ሰጭን
የቤት ድርሻ በ36 (በሰላሳ ስድስት) ወራቶች ውስጥ ማስረከብ ካልቻለ በአልሚው ምክንያት ከተራዘመ ደንበኛው
የክፈለበትን የውል ሰጭን የቤት ድርሻ ዋጋ አምስት 5% እስኪደርስ ድረስ ውል ተቀባይ ግንባታውን ላጓተተበት
እያንዳንዱ ወር 0.20% አልሚው ለደንበኛው መቀጫ የመክፈል ግዴታ ይኖርበታል፡፡

5.6. ውል ተቀባይ በአንቀጽ 5.6 መሰረት የገቡትን የቤት ኪራይ የመክፈል ግዴታ ባይፈጽሙ የውል ሰጭ በአንቀጽ 4
በተጠቀሰው መሰረት በመያዣነት ከውል ተቀባዮች የሚሰጣቸውን ዋስትና መሰረት በማድረግ እንዲሁም በዚህ ውል እና
በቤት ሽያጭ ውሉ መሰረት የሚኖራቸውን ማናቸውንም መብት በህግ አግባብ ለማስከበር ህጋዊ እርምጃ የመውሰድ
መብት አላቸው።

5.7. ይህ ውል ከተደረገ በኋላ፣

5.7.1. ተዋዋይ ወገኖቹ ይህንን ውል ከመፈራረማቸው በፊት ይዞታውን በተመለከተ ከ3ኛ ወገን የሚነሳ ማናቸውም
ዓይነት የይገባኛል ጥያቄ እና ዕዳ፣ ከመንግሥት ወይም ከ3ኛ ወገን የመጣ እገዳ ወይም ጥያቄ ቢኖር ሁሉንም የመሸፈን
ኃላፊነት የባለይዞታዎቹ (የውል ሰጭ) ነው፡፡ ውል ሰጪ ሀላፊነቱ የራሱ ሆኖ ጉዳዩን በህግ ተከላክሎ ፍጻሜ የማድረስ ግዴታ
አለበት።

5.7.2. ውል ተቀባይ የህንጻው ዲዛይንና አስርቶ በሚጸድቅበት ወቅት የህንጻው ዲዛይንና የህንጻው ከፍታ ይዘት ላይ ልዮነት
ቢፈጠር በዚህ ውል መሰረት የውል ሰጪ መብት የፕሮጀክቱ 20% ብቻ ይሆናል፡፡

5.8. ይህ ውል ከመፈጸሙ በፊት በነባር ይዞታው ላይ ለሚመጣ ማናቸውም የወንጀልም ሆነ የፍትሃ ብሄር ተጠያቂነት
ውል ሰጭ ኃላፊነቱን ይወስዳል።
5.9. በዚህ ውል መሰረት የግንባታው ስራ ሲካሄድ በሃገራችን የሚሰራባቸው የኮንስትራክሽን ህጎች፤ መመሪያዎች እና
ደምቦች ተፈጻሚ ይሆናሉ።

5.10. ውል ሰጭ የውል ተቀባይን መብቶች፤ ውል ተቀባይም የውል ሰጭን መብቶች የማክበር ግዴታ አለባቸው።

5.11. ውል ተቀባይ በዚህ ውል በተመለከተው መሠረት ከሚገነባው አፓርመንት ላይ የውል ሰጭ ድርሻ እንደሆኑ በዚህ
ውል የተመለከቱትን ቤቶች ሠርቶ ማስረከብ ግዴታ አለበት፡፡

5.12. ውል ተቀባይ ለውል ሰጭ በዚህ ውል የተዘረዘሩትን ቤቶች ስመ ሀብት በሚያስተላልፍበት ጊዜ ውል ሰጭ ለውል


ተቀባይ ምንም ዓይነት ክፍያ አይከፍሉም፡፡

5.13. ውል ሰጭ በአንቀጽ 2.3 በተመለከቱት ቤቶች ባለቤቶች የሚሆኑ ሲሆን በተጨማሪ በአፓርትመንቱ በአጠቃላይ
የጋራ መጠቀሚያ ቦታዎች እና መተላለፊያዎች ላይ በንጽጽር መብት እና ጥቅም ይኖራቸዋል፡፡

5.14. ውል ተቀባይ ግንባታውን ከገነባና ለእያንዳንዱ የአፓርትመንት ቤቶች ራሱን የቻለ ካርታ በማውጣትና አሰፈላጊውን
ነገሮች ሁሉ በማሙዋላት ውል ሰጭ የሚደርሳቸውን ቤቶች ስመ ሀብት እንዲዞር የማስቻል ግዴታ አለበት፡፡

5.15. ውል ተቀባይ የባለይዞታዎችን ቤቶች (የውል ሰጭ ቤቶችን) የሚያስረክበው በከፊል የተጠናቀቀ (semi finished)
አፓርትመንቶችን ይሆናል፡፡

5.16. ከዚህ ቀጥሎ የተመለከቱትን ወጪዎች የመሸፈን ግዴታ የውል ተቀባይ ይሆናል

5.16.1. ለግንባታ ፈቃድ ለማውጣት የሚወጣ ወጪ

5.16.2. ለግንባታው የሚደረግ የአፈር ምርመራ፣ ለፕላን ዲዛይን ጥናት (አርክቴክቸራል፣ ስትራክቸራል፣ ሜካኒካል፣
ኤሌክትሪካል ፋየር ስትራቴጂ) ግንባታ ወጪዎችን፣

5.16.3. በዚህ ውል አንቀጽ መሠረት የይዞታ ማረጋገጫ ሰርተፍኬት/ካርታ/ ለማውጣት እና ስም ለማዞር የሚከፈሉ
አስተዳደራዊ ክፍያዎችን

5.16.4. ቀሪ የሊዝ ክፍያዎችን ለአያንዳንዱ ባለ ቤት ይከፋፈላል፡፡

5.16.5. ግንባታው በሚከናወንበት ቦታ ላይ የነበሩ ግንባታዎችን ለማፍረስ እንዲሁም ቦታውን ለግንባታ ለማዘጋጀት እና
ምቹ ለማድረግ የሚወጡ ወጪዎችን ሙሉ በሙሉ ገንቢው(ውል ተቀባይ ) ይከፍላል፡፡

5.17. ውል ተቀባይ ለሚገነባው አፓርትመንት ግንባታው ከተጠናቀቀ በኋላ የ1 አመት የግንባታ ጥራት ዋስትና ለውል
ሰጭ መስጠት አለበት፡፡ ውል ሰጭ ቤቶቹን ከተረከቡ በኋላ በራሳቸው ኃላፊነት ለሚደርስ ጉዳት ካልሆነ በስተቀር ሕንጻው
ላይ ከግንባታ ጥራት ጋር በተያያዘ ለሚደርስ ጉዳት 1 አመት ገንቢው ኃላፊነት ይወስዳል፡፡

፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡

፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡
አንቀጽ ስድስት
ውሉ ጽኑ ስለመሆኑ

6.1. ይህ የውል ስምምነት በሁለታችንም ተዋዋይ ወገኖች መካከል በንጹህ ህሊና ወደን እና ፈቅደን የውሉን ውጤት
በመረዳት እና በመፈለግ በመሬት ይዞታችን ላይ ህንጻ እንዲገነባ በውሉ ላይ በተጠቀሰው መሰረት ክፍፍል ለማድረግ
በፍትሀ ብሄር ህግ ቁጥር 1675፣ 1731 እና 2005 መሰረት ተፍራርመናል።

6.2. ይህ ውል ከመፈረሙ ብፊት በይዞታው ላይ የሚነሳን የመብት ጥያቄ የውል ሰጪ ወገን ሲሆን የይዞታ ባለቤትነት
መብት ከዞረ እና ግንባታው ከተጀመር በኋላ በይዞታው ላይ ለሚነሳ ማንኛውም ጥያቄዎችን በተመለከተ የውል ተቀባይ
ሃላፊነት ይሆናል።

6.3. በአንቀጽ 8 ስር የተቀመጡት ሁኔታዎች እንደተጠበቁ ሆነው ይህንን ውል ያፈረሰ ወይም ለማፍረስ የሞከረ ወገን
ውሉን ለአከበረ ወገን ብር 1,000,000.00 (አንድ ሚሊየን) በ/ፍ/ህ/ቁ/1889/1890 መሰረት መቀጮ ከፍሎ ውሉ የጸና
ይሆናል።

አንቀጽ ሰባት .
ውሉ የሚሻሻልበት ሁኔታ

7.1. ማንኛውም የዚህ ውል ይዘት ወይም የውሉ ስምምነት ማሻሻል ካስፈለገ በሁለቱም ወገኖች ስምምነት በጽሁፍ ብቻ
ሲደረግ የሚጸና ይሆናሉ።

7.2. ተዋዋይ ወገኖች ከዚህ ውል በተጨማሪ ሌሎች ውሎችን በማናቸውም ጊዜ ሊዋዋሉ ይችላሉ። ውሎቹም የዚህ ውል
አካል ይሆናሉ።

አንቀጽ ስምንት
ከአቅም በላይ የሆኑ ሁኔታዎች
8.1 በዚህ ውል ስምምነት መሰረት ውል ተቀባይ ግዴታውን ለመወጣት ከአቅም በላይ የሆኑ ሀኔታዎች ማለትም ለዚህ ው
ተፈፃሚነት መሰናክል ሊሆኑ የሚችሉ ከአቅም በላይ የሆኑ ፣ ምክኒያታዊ እና ከውል ተቀባይ ቁጥጥር ውጪ የሆኑ
ሀኔታዎች ካጋጠሙት፣ ውል ተቀባይ ግዴታውን ሙሉ በሙሉም ሆነ በከፊል እንዳይወጣ እንቅፋት ወይም መሰናክል
የሚሆኑ ከተፈጥሮ ከመንግስትም ሆነ ከግለሰብ የሚመነጩ ሁኔታዋች ማለት ነው፡፡
8.1.1. ከተፈጥሮ ጋር የተያያዙ አደጋዋች፣ የመሬት መንቀጥቀጥ፣ ፍንዳታ፣የእሳት አደጋ፣የጎርፍ፣ የመብረቅ እና
የመሳሰሉት የአየር ፀባዮች
8.1.2. የፖለቲካ፣ የአለም አቀፍ ወይም የአገር ውስጥ ጦርነት ወይም ሰላም ማጣት ፣ የማንኛውም አይነት የመንግስት
አካል ጣልቃ ገብነት
8.1.3. ሌሎች በህገ መንግስቱ ላይ ከአቅም በላይ ተብለው የተጠቀሱ ሁኔታዎች
::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::
::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::
::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::
::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::
::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::
አንቀጽ ዘጠኝ
ውሉ የሚሰረዝበት ሁኔታ

9.1. በዚህ ውል ጠቅላላ ድንጋጌ በተመለከተው አግባብ የዚህ ውል ዓላማ በሙሉም ሆን በከፊል ከመጠናቀቁ በፊት
በማናቸውም ጊዜ ሁለቱም ተዋዋይ ወገኖች ውሉን ለማቋረጥ ከተስማሙና ስምምነታቸውንም በጽሁፍ ካረጋገጡ ውሉ
ይቋረጣል።

9.2. ውል ተቀባይ ስመ ሀብቱ ከዞረለት በኋላ የህንጻ ዲዛይን፣ ፈቃድና የግንባታ ፈቃድ እና የግንባታ ማስጀመሪያ ፈቃዶችን
ተቀብሎ በስድስት ወራት ውስጥ ምንም አይነት ግንባታ ያልጀመረ ክሆነ ውል ሰጪ የውሉን የግንባታ ጊዜ 60 ወራቶችን
መጠበቅ ሳያስፈልገው ውሉን የማቋረጥ መብት አለው፣ እንዲሁም ውል ተቀባይ የይዞታውን ስመ ሀብት ወደ ውል ሰጪ
በራሱ ወጪ የማዞር ኋላፊነት አለበት።

፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡

፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡

አንቀጽ አስር
አለመግባባት ስለሚፈታበትሁኔታ

10.1. ተዋዋይ ወገኖች በመካከላቸው ለፈጠር የሚችልን አለመግባባት በቅድሚያ በመመካከር የመፍታት ግዴታ
አለባቸው።

10.2. ተዋዋይ ወገኖች አለመግባባትን በመመካከር ሊፈቱ ካልቻሉ እያንዳንዳቸው በሚመርጡት አንድ አንድ የግልግል
ዳኛና ሁለቱ የግልግል ዳኞች በጋራ በሚመርጡት ሶስተኛ ገላጋይ ዳኛ ውሳኔ ይሰጣል። በሁለቱም ገላጋይ ዳኞች የተመረጠው
ገለልተኛ ገላጋይ ዳኛ ሰብሳቢ ገላጋይ ዳኛ ይሆናል።

10.3. ከተዋዋይ ወገኖች አንዱ የግልግል ዳኛ ለመምረጥ ፈቃደኛ ካልሆነ ወይም ሁለት ዳኞች በ15 ቀን ውስጥ ሶስተኛ
ገለልተኛ ገላጋይ ዳኛ ካልመረጡ ፍ/ቤት እንዲመርጥ ይደረጋል።

10.4. ገላጋይ ዳኞች በሚሰጡት ውሳኔ ካልተስማሙ በመደበኛ ፍርድ ቤት ጉዳያቸውን በማቅረብ መብታቸውን ማስከበር
ይችላሉ።

10.5. ሆኖም የፍትሀ ብሄር ስነስርዓት ህጉ በሚፈቅደው መሰረት በገላጋይ ዳኞች ላይ ቅር የተሰኘ ተዋዋይ ወገን ስልጣን
ላለው መደበኛ ፍ/ቤት ይግባኝ ማለት ይችላል።

10.6. ለገላጋይ ዳኞች የሚወጣ ማንኛውንም ወጭ ጉዳዩ በግልግል ዳኝነት ሲጠናቀቅ በዳኝነት የተፈረደበት ወገን
እንዲከፍል ተስማምተዋል።

፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡

፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡

፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡
አንቀጽ አስራ አንድ
ውሉ የተፈረመበት ቦታ እና ቀን

ይህ ውል በተዋዋይ ወገኖች መካከል ዛሬ ቀን ወር ዓ.ም. በ አዲስ አበባ ከተማ


በምስክሮች ፊት ከተፈረመበት ቀን ጅምሮ የጸና ነው፡፡

ስለ ደንበኛ ስለ አልሚ

ስም_________________________________ _________ ስም_____________ _____ _______

ፊርማ_____________________________ _____________ ፊርማ___________ _______ _______

ቀን___________________________________ _______ ቀን______________ ____ _______

የምስክሮች ፊርማ
እኛ እማኞች ይህ ውል በተዋዋይ ወገኖች መካከል ያለምንም ተጽዕኖ በተዋዋይ ወገኖች ሙሉ ፍላጎትና ፍቃድ ሲፈረም
መመልከታችንን በፊርማችን አናረጋግጣለን፡፡

ስም ፊርማ ቀን

1 .................................................................................. ........................................................ ..................................................

2 .................................................................................. ........................................................ ..................................................

3 .................................................................................. ........................................................ ..................................................

You might also like